የ«አይ ኤስ» ግድያ እና የኢትዮጵያ አስተያየት

በሊቢያ እስላማዊ መንግሥት የተሰኘው አክራሪ ድርጅት 30 ኢትዮጵያውያንን በጥይትና በመቀላት የገደለበት የጭካኔ ተግባር ፣ እንዲሁም፣ በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ዜጎች አንፃር በቀጠለው ሁከት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው የኃይል ተግባር በኢትዮጵያ ተወገዘ።