Barak Obama of The White House says no to US ground forces to combat Shabaab: “We don’t send our marines in to do the fighting. The Ethiopians are tough fighters.”በሶማሊያ ምድር በአልሸባብ ለተገደሉ ለተማረኩ ወታደሮች ቤተሰቦች እንኳን ካሳ ሊከፈል የጡረታ …

በደሃው ወታደር ደም የአሜሪካ ጥቅም የወያኔ ስልጣን ሊጠበቅ ነው ? እስከ መቼ ? Read more »

Addis Admass.com ኢህአዴግ፤ “ኒዮሊበራል” በማለት አሜሪካን መዝለፍ ያዘወትራል። ታዲያ እንዴት፣ ኦባማ “ድንገት” ተነስተው ዋና የኢህአዴግ አድናቂ ይሆናሉ? (ድንገተኛ አይደለም፡፡ አባማ ነባር ሃሳባቸውን ላለፉት 6 ዓመታት በተደጋጋሚ ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡) · የዲያስፖራ ፖለቲከኞች፤ ለኦባማ የምርጫ ዘመቻ ቀስቅሰዋል። ዛሬ ግን፣ የኦባማ ጉብኝት ድንገተኛ …

አሜሪካ፣ የኢህአዴግ “አድናቂ” ትሆናለች ብሎ ማን አሰበ! Read more »

• ‹‹ኦባማ ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው›› • ‹‹ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 …

ኢ/ር ይልቃል መንግስት ለፕሬዝደንት ኦባማ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ አስታወቁ:: Read more »

ለማነኛውም ጋዜጣዊ መግለጫ የሚመስለው ነገር አብቅቶዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ኦባማ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግሰት (እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ያለውን) በኃይለ ለመጣል የሚደረግ ሙከራን አይደግፉም፡፡ በሀይል ብንጥለው ግን ምን ያደርጉን ይሆን ብዬ በማሰብ ላይ ነኝ!!!! እግዚር ያክብራቸው ስለ ግብረ ሰዶም ለወንድም እና እህቶች ኬኒያ …

በዚህ ጉብኝት ኦባማ የሆነ ተዓምር ሊያመጡ ይችላሉ ብሎ የጠበቀ ከነበረ ቁርጡን የሰማ ይመስለኛል፡፡ Girma Seifu Maru Read more »

ምንሊክ ሳልሳዊ :- እናት ሃገሬ በናንተ ስም መጠራቷ ለኔ ይሁን ሃገሩን ለሚወድ ሁሉ ትልቅ እፍረት ነው:: ስለ ዲፕሎማሲ እና እንግዳ አቀባበል መማር ያስፈልጋል እንዳይባል አሊያም ትምህርት ቤት እንዳይከፈት ይህ ጉዳይ የተለመደ የፕሮቶኮል ጉዳይ እና በየሚዲያው የሚታይ ነገር ነው:: እንኳን ባለስልጣን …

የሰው መሳቂያ ሆናቹ አገራችንን የሰው መሳለቂያ አደረጋችሁ::የደህንነት ባለስልጣናቱ ተደብቀው ያዩ ነበር:: ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኦባማን ከናይሮቢ መንቀሳቀስ ተከትሎ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ተኮልኩለው የነበር የስርአቱ ታማኝ ጋዜጠኞች እቃችሁን ልንፈትሽ ነው ከተባሉ በኋላ ደጅ ራቅ ብለው እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ መግባት እንደተከለከሉ ተናግረዋል:: እናንተ በሌላቹበት እቃችሁን መፈተሽ እንፈልጋለን ከተባሉ በኋላ የወያኔ ደህንነቶች ፈትሸው …

የስርአቱ ታማኝ ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ተባረሩ:: Read more »

(ሀ) ፕሬዚደንት ኦባማ ነገ እሑድ አዲስ አበባ ይገባሉ። አንዱን ቀን- እንደደንቡ ሰኞ-በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ራት እንደሚኖር ይጠበቃል። የታሪክ ምጸቱን ከዚያ ጀምረን እናደንቃለን። ራቱ ምኒልክ በሠሩት፣ ዛሬም በስማቸው በሚጠራው ቤተ መንግሥት ይሆናልና፤ መቼም ለራት ሼራተን፣ አለዚያም መቀሌ-አዳማ- ባህርዳር-አዋሳ-አሳይታ— አይወስዷቸውም ብዬ ነው። …

ኦባማ ባዲሳባ፣ የሚጠበቁ ምጸቶች (ቸሩ ቸርችሩ) Read more »

ኦባማ ነገሩን ይበልጥ ግልጽ አድርገውታል። ዛሬ ከሰአት በሁዋላ ከኬኒያ ሲቪል ማህበራት ጋር በብዙ ጉዳዮች ላይ ወይይት ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ የኬንያውያን የውስጥ ችግሮች በኬንያውያን በራሳቸው ብቻ ነው የሚፈታው ብለዋል። ነገሩን ይበልጥ ግልጥ ሲያደርጉትም ” ከቀዝቃዛው ጦርነትና ከቅኝ ግዛት ማብቅያ በሁዋላ ሀያላን ሀገራት …

“የውስጥ ችግራችሁ በራሳችሁ የሚፈታ ነው።” ኦባማ የትነበርክ ታደለ Read more »

በደርግ ዘመነ መንግስት በከፍተኛ 1 ሊቀ መንበርና የቀይ ሽብር መሪ ተዋናይ በመሆን የንፁህ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ነፍስ ሲቀጥፍና አካላቸውን ሲያጎድል የነበረው እርገጤ መድበው ታዋቂውን የታሪክ ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ)ን በስም ማጥፋት ከሰሰ:: እርገጤ መድበው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያን የከሰሰው ኢ.ሀ.አ.ፓና ስፖርት በተሰኘው በቁጥር …

ገነነ መኩሪያ(ሊብሮ) በደርግ ዘመነ መንግስት በከፍተኛ 1 ሊቀ መንበርና የቀይ ሽብር መሪ ተዋናይ ተከሰሰ :: Read more »

ለውጥ የሚጠላ ማንኛውም ሰው የለም:; ለውጥ የማይፈልግ ካለ አንድም ከአምባገነን ስርአቶች የተዳቀለ አሊያም የጥቅሞችን ማግበስበስ የለመደ ስግብግብ የሕዝብ ጠላት ብቻ ነው::በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ያስፈልጋል;ይህ ደግሞ ሳይታለም የተፈታ ነው::በስልጣን ላይ ያለው አመራር አስተዳደሩ የተበላሸ ስለሆነ ለውጥ ለማምጣት የማይችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱም …

ትኩረት ለሚገባቸው ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ::መዘናጋት እና አቅጣጫ መሳት ይቁም:: Read more »

ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ውጤት ቢሰጥ በእስካሁኑ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው በንግግር (በወሬ) ደረጃ A በተግባር ግን D እንደሚሰጧቸው ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ፡፡ አፍሪካውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ምዕራባውያን ዕንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስረዱ፡፡ በአሜሪካ ድምጽ የStraight Talk Africa አዘጋጅ ሻካ ሳሊ የፕሬዚዳንት ባራክ …

“በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን” – ኦባማ፡ “በንግግር (ወሬ) A፣ በተግባር D” ኦባንግ ሜቶ – (ጎልጉል ድረገጽ) Read more »

ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ውስጥ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንደሚገኝ ለማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በጎንደር መምህራን ኮሌጅ የአይ ሲቲ መምህርና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሆነው መምህር አለላቸው አታለለ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም …

በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንዳለ አልታወቀም:: ‪ Read more »

[youtube http://www.youtube.com/watch?v=AQHJ5_7gONQ] In advance of President Obama’s historic trip to Ethiopia, I led discussion on the House Floor as the founder and co-chair of the Congressional Ethiopian American Caucus to speak on the importance of our nation’s relationship with Ethiopia. …

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ማይክ ሆንዳ ስለፕሬዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት ንግግር Read more »

ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው::-በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)​-የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማስታጠቅ እና በማደራጀት ዙሪያ በደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስባቸው መሆኑ …

ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው:: – በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው:: Read more »

የባራክ ኦባማ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ኬንያን እና ኢትዮጵያን መጎብኘት የሰሞነኛ አዲስ ዜና ሲሆን ባራክ ኦባማ የሃያላኗ አገር መሪ በመሆናቸው የጉዞው ዜና ሰፊ ሽፋን አግኝቶ አለምን እያስተጋባ ይገኛል::ባራክ ኦባማ በርግጥ ከአፍሪካዊ አባት መገኘታቸው እንዲሁም የሃያላኗ አሜሪካ የመጀመሪያው ጥቁር መሪ መሆናቸው ለየት …

ለእኛ የሚበጀን በትግላችን ነጻነታችንን ማረጋገጥ እንጂ የኦባማ መግባት እና መውጣት አይደለም:: ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

ምርጫ 97 ላይ ድምፅ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ የተያዘው፣ ከዛም የሌባ አይነ ደረቅ ሆኖ እኔ ነኝ አሸናፊ ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ የተቀየመውን ህዝብን ትኩረት ለማስቀየስ አንዳች ዘመቻ ያስፈልገው ነበር፡፡ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ሶማሊያ ውስጥ ቡራከረዩ ሲል የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ለህወሓት/ኢህአዴግ ጥሩ አጋጣሚ …

አሁንም አልሸባብ! – ጌታቸው ሽፈራው Read more »

የፀረ ሽብር ግብረሀይል ነኝ ብሎ የሚጠራው ቡድን አንድ ሰሞን የብሄር እና የፖርቲ ተዎፆ ያማከለ በሚመስል መልኩ ጠንካሪ የተባሉ የፖርቲ አመራርና ንፁሀን ሀሳብ ያላቸውን ግለሰቦች ከየአሉበት ሀገር ሆነ አዲስ አበባ ጨምሮ በገፍ ያስራል ህውሀት ። ይሄን የተመለከተ የአንድ ፖርቲ ብሄራዊ ም/ቤት …

“እንደ ሰው ካሰብክ ትፈለጋለህ ” ጥላዬ ታረቀኝ Read more »

ፍትህ ካለ ሰላም አለ::ፍትህ ካለ እድገት አለ:;ፍትህ ካለ እስር ቤቶች በንጹሃን አይሞሉም:: ፍትህ ካለ ነጻነት እና መብት አለ:; ፍትህ ካለ የሚሸማቀቅ አይኖርም::ፍትህ ከተረጋገጠ ሕጎች ሁሉ በበላይነት የሕዝብ ይሆናሉ::ይህ ሁሉ የሚረጋገጠው በኛ ለኛ ከኛ ነው::እኛ አዎ እኛ በአሁን ወቅት እና ጊዜ …

የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ካወቅን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ወገባችንን አጥብቀን እንታገል:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

የማንዴላን ፎቶ ሰቅሎ መብላትና መጠጣት ሆድ ከመሙላት የዘለለ ምንም ፋይዳ የለውም። ስንቱን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ በየእስር ቤቱ አጉረው እያሰቃዩና እየገረፍ፣ የተረፈውን ለስደትና ሞት እየዳረጉ የማንዴላ ቀን በድግስ ማክበር የቆመለት አላማ ምን እንደ ነበር መዘንጋት ብቻ ሳይሆን የለየለት አስመሳይነት ነው። ማንዴላ መስዋነትነት …

ህወሃቶች “የማንዴላን ቀን” ለማክበር ሽርጉድ ሲሉ አለማፈራቸው ባይገርምም ያሳዝናል። አበበ ገላው Read more »

የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝ እንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡ በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ …

በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ == ርዕዮት አለሙ Read more »

ህወሓት በጠመንጃና ዱላ ብቻ የተንጠለጠለ ስልጣ ይዛ እንድትቀር፣ በ2007 ዓ/ም ምርጫ ተሸንፎ ቅስሙ እንዲ ሰበር ያደረግነው የተሻለ ኣማራጭ ፓሊሲ፣ የበለጠ ዲሞክራሲያዊ ባህሪ፣ የነጠረ ሃገራዊ ራኢ፣ ህዝባዊነት የተላበሱና ከሂወት መስዋእትነት ጀምረው የኣካል መጉደል፣ የስራ መፈናቀል፣ የቤተሰብ መበተንና ከትዳር መፈናቀል፣ ከማህበራዊ ግንኝነቶች …

ህወሓት ዱላዋ ኣስቀምጣ ትግጠመን…! አምዶም ገ/ስላሴ Read more »

የኦነግ አባላትን ለማደን ጋራሙለታ የዘለቀው የሕወሓት የደሕንነት ሃይል የኦሕዴድ ካድሬዎችን ፈጃቸው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከባሌ ክፍለሃገር ተነስተው አዳዲስ ተዋጊ አባላትን ለመመልመል ወደ ሃረርጌ ጋላሙለታ ዘልቀዋል የተባሉትን የኦነግ አባላት በደረሰው መረጃ መሰረት አድኖ ለመያዝ አሊያም የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ በሚል …

የኦነግ አባላትን ለማደን ጋራሙለታ የዘለቀው የሕወሓት የደሕንነት ሃይል የኦሕዴድ ካድሬዎችን ፈጃቸው:: Read more »

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ …

የልደታ ፍርድ ቤት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ፡፡ … Read more »

ኢትዮጵያዊው የ 55 አመት አባት የቀድሞ ሚስታቸውና አራት ልጆቻቸው በ 1980 ዎቹ እንደፈረንጆቹ ወደእስራኤል ከተሰደዱ አይሁድ ኢትዮጵያዊያን ውስጥ ይገኙበታል፡፡ ቤተሰቡ ወደእስራኤል ከገባ በኋላ ሙሉ የእስራኤል ዜግነት ከማግኘቱ በተጨማሪም አራቱ ልጆች አድገው በእስራኤል ጦር ሀይል ውስጥ ብሄራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በቅተዋል፡፡ ይሁን …

አራት ልጆቻቸው በእስራኤል ጦር ውስጥ አገልግሎት የሰጡት ኢትዮጵያዊ አባት በሀገሬው ባለስልጣናት የመኖሪያ ፈቃድ መከልከላቸው ተዘገበ:: Read more »

መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ የቆዩት እነ ወይንሸት ሞላ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ከተፈረደላቸው በኋላ ሰኔ 22/2007 አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ነበር፡፡ ይሁንና የልደታ ፍርድ ቤት ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት …

በእነ ወይንሸት ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ Read more »

በእነ ዘላለም ወርቃገኘው የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው ተከሳሾቹ ሀምሌ 1/2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት …

በእነ ዘላለም ወርቃገኘው የክስ መዝገብ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ): የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች …

በሕወሓት የበላይነት የብአዴንና ኦሕዴድ አስረሽ ምችው – ፈንጠዝያ ባርነት እስከመቼ ? Read more »

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ህወሃት በሙስሊሙ ኮሚቴ ላይ የወሰነውን ፖለቲካዊ ብይን አንቀበልም በማለት የተካሄደ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ::Minilik Salsawi

ቃል ስንገባ በስሜታዊነት አይሁን! ቃል ስንገባ በአድር-ባይነት አይሁን! ቃል ስንገባ ለይስሙላ አይሁን! ቃል ስንገባ በእርግጥ አደርገዋለሁ ወይ? ብለን ከልባችን ጠይቀን፣ በአዎንታዊነት እራሳችንን አሳምነን፣ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ቃል የምንገባበትን ጉዳይ …

ለትግል ጽናት ቃላችንን እናጥብቅ::ከጉዳይ ሁሉ ቀዳሚው በራስ መተማመን አንድነትን ማጠንከር በጋራ መቆም ነው፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

Minilik Salsawi በዛሬው እለት ከእስር ባልተፈቱ አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን በቦታው የጦማርያኑ ቤተሰቦች እና ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች በካንጋሮው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል::እንዲሁም በቅርቡ የተፈቱት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን ርእዮት አለሙን ጨምሮ በፍርድ ቤቱ …

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የልደታ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሎ ለ32ኛ ጊዜ ለሓምሌ 22 ተቀጠረ:: Read more »

በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን የሳንቲም እጥረት ለመሸፈን እየተደረጉ ያሉ ሙከራዎች ሁሉ ባለመሳካታቸው ከፍተኛ ውጥረት እንደፈጠረበት ታውቋል!ህዝበ ሙስሊሙ የመገበያያ ሳንቲሞችን ከገበያ በማስወጣት መንግስት ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደረበት የሚገኝ ሲሆን አሁንም ይኸው መርሀ ግብር እየተከናወነ በመሆኑንና መንግስት እየደረሰበት ላለው ችግር ምላሽ …

በኢትዮጵያ የተፈጠረው የሳንቲም እጥረት ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሯል::የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚውን በዜሮ ድምር ውስጥ ከቶታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን የሳንቲም እጥረት ለመሸፈን እየተደረጉ ያሉ ሙከራዎች ሁሉ ባለመሳካታቸው ከፍተኛ ውጥረት እንደፈጠረበት ታውቋል!ህዝበ ሙስሊሙ የመገበያያ ሳንቲሞችን ከገበያ በማስወጣት መንግስት ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደረበት የሚገኝ ሲሆን አሁንም ይኸው መርሀ ግብር እየተከናወነ በመሆኑንና መንግስት እየደረሰበት ላለው ችግር ምላሽ …

በኢትዮጵያ የተፈጠረው የሳንቲም እጥረት ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሯል:: የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚውን በዜሮ ድምር ውስጥ ከቶታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

አሜሪካ ከኃይለስላሴ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራት ቢሆንም ከአሁኑ አንጻር ሲታይ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች አዲስ አበባ ድረስ መጥተው እንዲጠበቅላቸው የሚፈልጉት እንቅልፍ የሚነሳ ስጋት ነበራቸው ለማለት ግን ይከብዳል፡፡ ያም ሆኖ ግን በወቅቱ ለጥቁር ምቹ ባልነበረችው አሜሪካ ለጥቁር ህዝብ ነፃ መውጣት ስትባዝን የነበረችው …

ኦባማ የሚመጣው ለማን ነው? ጌታቸው ሺፈራው Read more »

የሃይል ሚዛኑ ያጋደለለት የሃይል ሚዛኑ ያላጋደለለት በፕሮፓጋንዳ የተወጠረው በአጉል የፖለቲካ ድቀት የሚዋዥቀው በጡዘት የሚሾረውን ጨምሮ በሰከረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የማናየው የማንሰማው ጉድ የለም::እኔ አውቅልሃለሁ ካለኔ ታጋይ ላሳር እኔ ካሌለሁ ኢትዮጵያ አበቃላት ወዘተ የሚለውን አካቶ ከተሳዳቢ እና ዘርጣጭ ጥሬ የፖለቲካ ከበሮ …

ከገባን !!! ለትግሉ ስኬት በአንድነት ለመቆም አሁንም ጊዜው አረፈደም:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

ሽቅብ ቁልቁል፣ተራራ እና ሸለቆ፣ሽርክት እና ለስላሳ ከፍ የማለት እና የማዘቅዝቅ፣ በሆነው ረዥም የአመታት ጉዞ በሀዘን ግዜ፣ በደስታ ግዜ፣በመዝራት እና በማጨድ ወቅት፣ እንዲሁም በድህነት ወይም በሀብት ዘመን ፣ ኑሮ የሌሊት ሲሆን የመከራ አሊያም የቀን ሲሆን የድሎት … በሁሉም አይነት አቅጣጫ የህይወት …

ከዝንጀሮ ቆንጆ ቢመረጥ፥ወያኔ አስቀያሚ ነው ቢንያም ግዛው Read more »

ስለተፈናጠጡ ብቻ የነገሡ የሚመስላቸው አያሌ አይተናል፡፡ በተሰጣቸው ትርጓሜ – ነገር መሠረት ብቻ ጉዳዮችን እየተረጎሙ የሚጓዙ የዋሃንንም አስተውለናል፡፡ ግራ ቀኙን ሳያዩ በተሰመረው መስመር ላይ ብቻ የሚነጉዱ፣ ወቅት የሚለወጥ የማይመስላቸውና ወቅትም የማይለውጣቸው በርካታ መንገዶችን ታዝበናል፡ “ሳይማር ያስተማረንን ገበሬ አንረሳውም” ብለው ሲያበቁ ከተማ …

የኢኮኖሚ ብሶት ወደ ፖለቲካ ምሬት መለወጡና የፖለቲካ ጥያቄን መውለዱም ሁለንተናዊ ዕውነታ ነው – ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

በርግጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የስርዓቱን ብልሹ አሰራር የጠቆሙና የተቹ በርካታ ንፁሃን በግፍ እስር እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የእስሩ ሰለባ የሆኑት ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች የኃይማኖት አባቶችና ነፃነት ጠያቂዎች፣ የዩነቨርስቲ ተማሪዎችና አስተማሪዎች፤ኸረ እናት ከነልጇ እና ገበሬዎች ቤት ይቁጠረው፡፡ ባለፈው የግፍ እስር …

ሴቶችን በእስር የማብቃት የመንግሥት አዲሱ ዕቅድ ይሆን? – ብስራት ወልደሚካኤል Read more »

የበሃገራችን የተንሰራፋው የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት የፍትህ ስርአቱ እንዲቀበር እና በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲሞት በማድረግ ህዝቦች በፍትህ አካላት ላይያላቸው እምነት ተስፋ እንዲያጣ አድርጓል::የፍትህ አካላት ለሃገሪቱ ዜጎች ማገልገል ሲገባቸው ለጥቂት ባለስልጣናት እና ለጥቅማ ጥቅም በመገዛት ህጎች እንዲፋለሱ በማድረግ ላይ ይገኛሉ :;ሊሻሻል እና …

ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠው የፍትህ አካላቱ ፖለቲካዊ ንቅዘት – ምንሊክ ሳልሳዊ‬ Read more »

Minilik Salsawi – በየቦታው ትንንሽ ጦርነት የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ የኛ ቅስቀሳ በተሳካ ቁጥር የእነሱ ብስጭት ይግል ነበር፡፡ ካድሬው ለሆዱ፣ መንግስት ለስልጣኑ በሚገባ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይሄ አመላካች ነው፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን ካድሬው ሽጉጥ ታጥቆ፣ ጠመንጃ ይዞ እገባለሁ አትገባም የሚል ግብግብ እስከመፈጠር ደርሷል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መኪናዎቻችን እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገው ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ሳይቀሩ ተደብድበዋል፡፡ በአባላቶቻችን ላይ እስር፣ ድብደባና ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በዘንድሮ ምርጫም ኦሮምያ ላይ እናሸንፋለን ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

በኦሮሚያ ብዙ አካባቢዎች ሰፋፊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂደናል፡፡ ባኮ፣ አምቦ፣ ጀልዱ፣ ጊንጪ የመሳሰሉት አካባቢዎች እኔ የተገኘሁባቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ተደርገዋል፡፡ በየስብሰባው ከ60ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ ነው ድጋፉን ሲገልፅልን የነበረው፡፡ በተለይ የወጣቱ ድጋፍ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡ “ከዚህ በኋላ የፀረ-ዲሞክራሲ አገዛዝ ይብቃን” የሚሉ ህብረ ዝማሬዎችን እያሰማ ነው ህዝቡ በየስብሰባው ላይ ሲታደም የነበረው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲታዩ ቅስቀሳው ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ክልሉን እያስተዳደረ ያለው ኦህዴድ፣ በዚህ መልኩ ወጣቱ ለኛ ድጋፍ ይሰጣል ብሎ የገመተ አይመስለንም። አሁን ታዲያ የድንጋጤ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሃረርጌ፣ በባሌ እና በሸዋ አካባቢዎች አባሎቻችንን ማሰር፣ መደብደብና ማዋከብ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የቅስቀሳ መኪናዎቻችንን መስተዋቶች በድንጋይ የመስበር፣ መኪኖችን በቡና ቤቶች አካባቢ ማሳደር እንዳንችል የማድረግ ሁኔታዎች በስፋት ተስተውለዋል፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖችና አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆነ አቀባበል ከህዝቡ አግኝተናል፡፡ በአጠቃላይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይ እና በአዲስ አበባ በምርጫው እንወዳደራለን፡፡ በሁሉም ላይ ቦታ ሰፊ አቀባበል ያገኘን ቢሆንም በተለይ ኦሮሚያ ላይ ኢህአዴግ ምርጫውን ካላጭበረበረ በቀር የሚያሸንፍበት መንገድ የለውም፡፡ እኛ ሁለት ነገር ነው የምንጠብቀው፡፡ አንደኛ ኢህአዴግ ካላጭበረበረ በቀር ኦሮሚያ ላይ አያሸንፈንም፣ ሁለተኛ ደግሞ ፖለቲካውን በሚገባ እንዳሸነፍን አሳይተናል፡፡ ሰፊ ድጋፍ እንዳለን አስመስክረናል፡፡ በየትኛውም ሚዛን ከኦህዴድ እንደምንሻል አሳይተናል፡፡ በዚህ ተደናግጠው እኔ በምወዳደርበት አካባቢ ኦህዴዶች ህዝቡን በሬ አርደው ማብላት ሁሉ ጀምረዋል፡፡ የክልሉ ካድሬዎች አሁን አምቦ ከትመዋል፡፡ ሥራ ላይ ናቸው ማለት ነው፡፡ ኦህዴድና ህዝቡ ከተለያየ ቆይቷል፡፡ ያው በኢህአዴግ ጃንጥላና ጠመንጃ ስር ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ እነሱም እንደማያሸንፉ ያውቃሉ። እኛ በ97 እኮ አሳይተናቸዋል፡፡ በወቅቱ እነ አባዱላን ያሸነፉት እኮ የ6ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ኦህዴድ በኦሮሚያ ሊሸነፍ እንደሚችል በ97 ምርጫ ነው ያረጋገጥነው፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

“መድረክ” አብላጫ ድምፅ ካገኘ ጥምር መንግስት ይመሰርታል:: እኛ በፕሮግራማችን ላይ በግልፅ አስቀምጠናል። በሽግግሩ ጊዜ ጥምር መንግስት ያስፈልጋል ብለናል። ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድና ለመሳሰሉት ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች መልክ ማስያዣ ይሆን ዘንድ የብሄራዊ አንድነት መንግስት ያስፈልጋል፡፡ ከማን ጋር ይመስረት የሚለው በድርድር የሚከናወን ይሆናል፤ ነገር ግን አግላይ ፖለቲካ ውስጥ አንገባም፡፡አንድ ፓርቲ ሌላውን አግልሎ ኢትዮጵያን መንግስተ ሰማያት ያደርሳል የሚሉ ካሉ ወይ የፖለቲካ ሳይንስ ያልገባቸው ወይም እስከቻልን ድረስ በፈላጭ ቆራጭነት ረግጠን እንግዛ የሚሉ ናቸው፡፡ በተረፈ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ለማምጣት መታለፍ ያለበት አንዱ ሂደት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ማቋቋም ነው። ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡

በአጭሩ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋግሞ እንዲያስብበት የምመክረው ምርጫውን እንዳያጭበረብር ነው፤ ውጤቱ የፈለገ ይሁን፡፡ ምርጫን አጭበርብሮ አሸንፌያለሁ የማለት ጊዜ ማብቃቱን ማወቅ አለበት። ያንን ካላደረገ ሃገሪቷንና ህዝቦቿን ለበለጠ ተስፋ መቁረጥ ነው የሚዳርገው፤ ይሄ በተግባር እየታየ ነው። ወጣቱ ከቀይ ባህር እስከ ሜዲትራኒያን ድረስ የባህር ሲሳይ የሚሆነውና በረሃ ውስጥ እንደዚያ የሚታረደው፣ ደቡብ አፍሪካ እንደዚያ የሚቃጠለው በሃገሩ ተስፋ ስላጣ ነው፡፡ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ እንኳ “የስደት ዘመን ይብቃ” ብሎ ከፖሊስ ጋር እንዴት እንደተጋጨ ተመልክተናል፡፡ አጥፍቶ የመጥፋት ፖለቲካ ይብቃ! የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደጋግመው ያስቡበት። ህዝቡንም ወጣቱንም ተስፋ ማስቆረጥ ለማንም አይጠቅምም፡፡ በተለይ ወጣቱ በሃገሬ የተሻለ ሥራ አገኛለሁ የሚል ተስፋ ሊያድርበት ይገባል፡፡ ይሄንን ወጣት ተስፋ ማስቆረጥ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡ – addisadmassnews.com

Image

Image

Minilik Salsawi የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው ስንታየሁ ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስዶዋል።

ስንታየሁ ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል በሚደረገው ትግል ላይ ትግል እራሱን ሰጥቶ ይታገል የነበረ ጠንካራና ለትግሉም በምንም የማይደለል ታማኝ ወጣት ታጋይ ነው።

Image

ፒያሳ አካባቢ ያየነው ትንሽ ለየት ይላል፡፡ መርካቶን አሊያም ከዛም አለፍ ያሉትን የአዲስ አበባ ክፍሎች በቁጥጥር ስራቸው አውለው ወደ አራት ኪሎ እየገሰገሱ የሚመስሉ ፈርጣማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፒያሳ ላይ ገዥ መሬት ይዘዋል፡፡ መኪና አይቀርባቸውም እንጅ መኪና መንገዱን ግማሹን እነሱ እየተንፈላሰሱበት ነው፡፡ ተቆጣጥረውታል! ደግሞ ኮዳና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሳቸውን ግጥም አድርገው ታጥቀዋል፡፡ አንድ ሁለት እርምጃ እንዳለፉ የሚተኩሱ በሚመስል ሁኔታ መሳሪያቸውን ዘቅዝቀው ይዘውታል፡፡ በተጠንቀቅ! በቃ ፒያሳን የጦር ቀጠና አስመስለዋታል፡፡

ከሶስቱ መካከል አንዱ የሁለቱን ደህንነት ለመጠበቅ በሚመስል መልኩ ወደኋላ ይቀራል፡፡ ሰውንም፣ ወርቅ ቤቶቹንም፣ መኪናዎችንም ዘወር ዘወር ብሎ ያያል፡፡ እንደገና ፈጠን ፈጠን ብሎ ይቀላቀላቸውና በአንድ ላይ ወደቀኝና ግራ እያማተሩ መሳሪያቸውን ዘቅዝቀው ይነጉዳሉ፡፡

ሌላ ሶስት አባላት ያሉት ‹‹ጋንታ›› ይከተላል፡፡ እነዚህም በተመሳሳይ ሶማሊያ አሊያም ኤርትራ ድንበር ያሉ ነው የሚመስሉት፡፡ ቀኝና ግራ፣ ወደኋና ወደፊት ይቅበዘበዛሉ፡፡ የቆሙ መኪናዎችን ጠጋ ብለው ያያሉ፡፡ አላፊ አግዳሚው ላይ ያፈጣሉ፡፡ ከእነሱ በኋላ ደግሞ ጯፉ እሳት የተቆሰቀሰበት የሚመስለውን ዱላ ከአጋማሹ ላይ የያዙ አራት ‹‹ተራ አስከባሪዎች›› (ካልሲ አባራሪዎች) ይከተሏቸዋል፡፡ ደጀን ጦር መሆናቸውን ነው፡፡
በዛሬው እለት Getachew Shiferaw አዲስ አበባን እንዲህ ቃኛት::
ማሳሰቢያ፡- አብረውኝ ከነበሩት ሁለት ጓደኞቼ ጋር ፎቶ የማንሳት ፅኑ ፍላጎት የነበረን ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ፎቶ ማንሳት ሳይቻለን ቀርቷል!
Image

Image

ከኦባማ ቀጥሎ በአሜሪካ ከፍተኛው ደመወዝ ተከፋይ ነበሩ
ከ2ሺ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን አከናውነዋል
ወንድሞቻቸው፡- ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ኤሌክትሮን እና ፖሲትሮን ይባላሉ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኤሌክትሮን ክበበው፤ ለ33ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የ2015 “የዓመቱ የዓለማችን ልዩ ስም” ውድድር ላይ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በቀዳሚነት እየመሩ እንደሆነ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
በአለማቀፍ ደረጃ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ዘንድሮም የተለያዩ አገራት ዜጎችና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ 64 ግለሰቦች ያልተለመዱ ስሞች ለውድድር የቀረቡ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ኤልክትሮን ክበበው፤ በ1ሺህ 132 ድምጽ፣ በ89.6 በመቶ ውጤት በቀዳሚነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በኢሜልና በተለያዩ መንገዶች ከቀረቡለት በርካታ ለየት ያሉ ስሞች 64 ያህሉን በመምረጥ፣ ለአንድ ሳምንት ያህል በድረ ገጽ አማካይነት ድምጽ እንዲሰጥባቸው የሚያደርገው የውድድር ኮሚቴው፤ የመጨረሻውን ውጤት ከጥቂት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
የሰማይ እንሽላሊት፣ ጣፋጭ ቡና፣ ዳላስ፣ ቶክዮ፣ ቴኒስ እና የመሳሰሉ የአገር፣ የቦታ፣ የእቃ፣ የሰብል ወዘተ መጠሪያዎችን የያዙ የተለያዩ አገራት ዜጎች በዘንድሮው ውድድር እንደተሳተፉ አወዳዳሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
በዘንድሮው ውድድር ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት በመምራት ላይ ለሚገኙት የ47 አመቱ ዶ/ር ኤሌክትሮን ይህን ስም ያወጡላቸው፣ ኤሌክትሪካል ኢንጂነር የሆኑት ኢትዮጵያዊው አባታቸው አቶ ክበበው ነበሩ፡፡
ልጆቻቸው የእሳቸውን ፈለግ ተከትለው በሳይንሱ ዘርፍ ላይሰማሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ያደረባቸው አቶ ክበበው፤ በልጆቻቸው ልቦና ውስጥ ገና በለጋ እድሜያቸው የሳይንስን ስሜት ለማስረጽ በማሰብ ነው፣ ባልተለመደ ሁኔታ ለልጆቻቸው ከኤሌክትሪሲቲ ጋር የተያያዙ ስሞችን ያወጡት፡፡
አቶ ክበበው፤ ለአምስቱ ልጆቻቸው ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ዲዩትሮን፣ ኤሌክትሮን እና ፖሲትሮን የሚሉ ስሞችን አውጥተዋል፡፡ ዶ/ር ኤሌክትሮን በስማቸው ብቻ አይደለም የሚለዩት፡፡ ከስማቸው በላይ ብዙዎችን ያስገረመው፣ በህክምና ሙያቸው የአሜሪካ መንግስት የሚከፍላቸው ዳጎስ ያለ ደመወዝ ነው ይላል ድረ-ገጹ፡፡
ከአራት አመታት በፊት “ዊኪኦርግቻርትስ” የተባለ ተቋም “የአመቱ የአሜሪካ መንግስት 1000 ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋዮች” በሚል ባወጣው ዝርዝር ውስጥ፣ ዶ/ር ኤሌክትሮንን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ቀጥሎ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያገኙ የመንግስት ሰራተኛ በማለት በሁለተኛነት አስቀምጧቸዋል፡፡
በአዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የተማሩት ዶ/ር ኤሌክትሮን ክበበው፤ በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ ከሚገኘው ዪኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በህክምና የተመረቁ ሲሆን የአሜሪካን ቦርድ ኦፍ ሰርጀሪን የቀዶ ህክምና ሰርተፊኬትም አግኝተዋል፡፡
ላለፉት 20 አመታት በሳንፍራንሲስኮ በኢንዶክሪንና ታይሮይድ ካንሰር ዘርፍ የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ዶክተሩ፤ በአሜሪካ ብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት፣ የካንሰር ምርምር ማዕከል የኢንዶክራይን ኦንኮሎጂ ቅርንጫፍ ሃላፊ ሲሆኑ የካንሰር ጄኔቲክስ ክፍሉንም በበላይነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ዶክተሩ በእስካሁኑ የሙያ ዘመናቸው ከሁለት ሺህ በላይ የተሳኩ ቀዶ ህክምናዎችን ያከናወኑ ሲሆን ከ150 በላይ የጥናት ጽሁፎችንና መጽሃፍትን ለህትመት እንዳበቁ “ብሬኪንግጎቭ” የተሰኘ ድረገፅ አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያዊው በተመድ የአለም የጤና ድርጅት ባለስልጣን በታይላንድ ኢትዮጵያዊቷን ሰራተኛውን ሲያስቃይ ተደረሰበት::

ኢትዮጵያዊቷን ለሁለት አመት አግተው በታይላንድ ሲያሰቃይዋት የነበሩት ኢትዮጵያውያን ናቸው::

ዶክተር ዮናስ ተገኝ የተባለ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የሚሰራ ግለሰብ ለኢትዮጵያዊቷ ስቃይ ተጠያቂ መሆኑ ተደርሶበታል::ባለፈው ሳምንት አለምነህ ዋሴ በአዋዜ ፕሮግራሙ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ በለቀቀው የአንዲት ኢትዮጵያዊት የታይላንድ ሰቆቃ (http://www.clickhabesh.com/?p=105552) አሰቃዮቿ ተብለው በሰራተኝነት ቀጥረው የወሰዷት በተባበሩት መንግስታት የአለም ጤና ድርጅት የታይላንድ ባለስልጣን ዶክተር ዮናስ ተገኝ እና የትዳር አጋራቸው ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋግጧል::

አለምነህ ዋሴ ኤ ኤፍ ፒን ዋቢ አድርጎ የገለጻት ኢትዮጵያዊ ከሃገር ቤት በቤት ሰራተኝነት ሊያሰሯት ከወሰዴት በኋላ ለአመታት ደሞዟን ሳይከፍሉ ከተዋት እስከ ማታ ደረቅ ሩዝ እንድትበላ በማድረግ ከውሻ ጋር ባንድ ክፍል እንድትተኛ በማድረግ ሲያሰቃይውት እንደነበር እና በስተመጨረሻ ራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሰው ደርሶላት አድኗት ለአንድ የሰብ አዊ መብት ድርጅት እንደሰጣት እና በአሁን ሰአት ጉዳዩን የታይላድ ፖሊስ እየተከታተለው እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል::

ኢትዮጵያዊቷን በቤት ሰራተኝነት አምጥቶ ሲያሰቃያት የነበረው ግለሰብ ራሱን ከወንጀሉ ነጻ በማድረግ ምንም ወንጀል እንዳልፈጸመ እና ትክክለኛ ሰው አድርጎ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በኢሜይል ሊያስተባብል ሞክሯል::(viewtopic.php?f=2&t=95181)በዘመናዊ ባርነት ላይ የተመሰረተ የመብት ገፈፋ ያካሄደው ግለሰም የ25 አመቷን እና ስሟ እስካሁን ያልተጠቀሰውን ኢትዮጵያዊት በ2000 ብር ክፍያ ከኢትዮጵያ አምጥቶ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ሲያሰራት እንደነበር የገለጸው ባንኮክ ፖስት ግለሰቡን ለማናገር ቢፈልግም ዶክተር ዮናስ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል::

እጅግ ያማል!! ደሞ ነገሩን በይቅርታ እነ በፍቅር መፍታት ሲገባው አለማፈሩ ለኤ ኤፍ ፒ ኢሜይል ያደርጋል::http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=95181
Image

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ባሳለፍነው ቀናት ጀምሮ በፌዴራል ፖሊሶች እና በአዲስ አበባ ፖሊሶች ላይ ጠንከር ያለ ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ሲታወቅ የፖሊሶቹ ሞባይል ስልኮች ሳይቀሩ ድንገት በደህንነት ሃይሎች እየተፈተሹ እና አላስፈላጊ የተባሉ እና ለወያኔ የማይመቹ የተጫኑ ዘፈኖች ፎቶዎች እና የተለያዩ ዶክመንቶች ሲሰረዙባቸው የነበረ ሲሆን በርካታ ፖሊሶች በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ሲደረግ የተወሰኑ ደሞ ክትትል እንዲደረግባቸው ታዟል:ከስራቸው የታገዱ እና የታሰሩ እንዳሉም ተጠቁሟል::

በአዲስ አበባ ለከተማው ፓሊስና ለፊደራል ፓሊስ ድንገት የተጀመረው ገምገማ እረፍት አንዳይወጡ በእረፍት ላይ ያሉት እንዲመጡ ተደርጎ በድንገት ሞባይል ተሰብስቦ በውስጡ የተለያዩ በመንግስትና በባለስልጣን የሚያላግጡ ቀልዶች የቴዲ አፍሮ ከሊፕ የተገኝበት የአማርኛና የኦሮምኛ ሀይለኛ ቀሰቃሽ ዘፈኖች የተገኘበት ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተላላኩት መልክቶች ተጎርጉረው የተገኙባቸው እንዳስፈላጊው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ሲገለጽ የታገዱ የታሰሩ ደሞዛቸውን የተቀጡ ሲኖሩ ወደፊት በድጋሚ ቢገኝባቸው ትልቅ ችግር ሊፈጠርባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል::

የለውጥ ሃይሎች በወታደሩ እና በፖሊስ ሃይሉ ዙሪያ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት የመረጃው አድራሾች ፖሊሶች የሚያቀናጅ ሃይል እና የሚያስተባብር ሃይል ማጣታቸው እንዲሁም እንደ ደርግ ሃይል ትበተናላችሁ ሌላ ስልጣኑን ቢይዝ በማለት የሚደረገው ማስፈራሪያ በወያኔ እየተደረገባቸው መሆኑ ስለሆነ ከለውጥ በኋላ በስራቸው እንደሚቀጥሉ እና ከለውጥ ሃይሎች ጎን ቆመው ይህንን አምባገነን ስር አት እንዲገረስሱ አስፈላጊ የሆነ የግንዛቧ ማስጨበጫ ስራዎች እንዲሰሩ አሳስበዋል::

Image

በጋሞ ጎፋ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ አልጌ ቀበሌ ፖሊስ በንፁሃን ላይ የጭካኔ እርምጃ መውሰዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በአባያ ሀይቅ ዙሪያ በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩት ነዋሪዎች መሬት ትንባሆ ለሚያለማ ባለሀብት እንደተሰጠባቸው መነገሩን ተከትሎ የአካባቢው ሽማግሌዎች ከሶስት ጊዜ በላይ ለክልሉ አስተዳደር ማመልከቻ ቢያስገቡም መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ አስተዳደር ምንም አይነት መልስ ባይሰጥም የዞኑ አስተዳደር ‹‹መሬቱ ትንባሆ ለሚያለማ ባለሀብት ተሰጥቷል፡፡›› የሚል ውሳኔ በማስተላለፉ ነዋሪዎቹ ይህን የዞኑን አስተዳደር ውሳኔ እየተቃወሙ ይገኛሉ፡፡ ይህን የህዝቡን ተቃውሞ ተከትሎም ፖሊስ በአባያ ነዋሪዎች ሰፈር እየመጣ እያስፈራራ እንደሚመለስ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

የካቲት 30/ 2007 እንደተለመደው ፖሊስ ነዋሪዎቹን ለማስፈራራት ወደ ሰፈር በሄደበት ወቅት ነዋሪዎቹ ፖሊሶቹን ‹‹ከሰፈራችን ውጡልን!›› እንዳሏቸው ተገልጾአል፡፡ ይሁንና ፖሊስ ከሰፈራቸው እንዲወጡለት የጠየቁትን አዛውንቶችን ጨምሮ ነዋሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸሙ ተገልጾአል፡፡ ፖሊስ አዛውንቶቹ ላይ ድብደባ መፈጸሙን የተቃወሙ ወጣቶች ላይ ጥይት በመተኮስ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል፡፡ በወቅቱም አንድ ሰው ሲሞት ከ8 ሰዎች በላይ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተገልጾአል፡፡

እስካሁን ድረስ በንጹሃኑ ላይ የጭካኔ እርምጃ የወሰዱት ፖሊሶች ምንም አይነት ህጋዊ እርምጃ እንዳልተወሰደባቸውና በስራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

Image

ጊዜው 1997 ነው። አብዛኛዎቻችን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፥ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም ተመርቀን ስራ አጥተን ሰፈር ውስጥ የምንውል ስራ አጦችና ( በኢህአዲግ አባባል አደገኛ ቦዘኔዎች) ወጣትነት ጉልበታችንን በስራ ለመፈተን እየተንቀሳቀስን የነበርን ወጣቶች ትኩስ ኋይሎች ነበርን።

በወቅቱ በተነሳው የለውጥ እንቅስቃሴ አንዳችንን ከአንዳችን ሳይለይ በጊዜው የነበርነውን ሁሉ ማርኮን አጥብቀን በመከታተል በሂደቱ በተለያየ መልኩ ተሳታፊ ሆነን አገኘነው። በከፍተኛ ሁኔታ በለውጡ ማዕበል ውስጥ ሁላችንም እየተናጥን ነበር።

ለውጥ!የዚህ ትውልድ አባላት የሆንን በወቅቱ ምንም አይነት ይሁን እንጂ ለውጥ እንፈልግ ነበር። ለውጡም በምንም መልኩ ይምጣ አጠቃላይ መንግስታዊ ለውጥ ተካሂዶ ከማየት ባሻገር በአገር
ግንባታ ውስጥ መሰረታዊ የነበሩትን ጥያቄዎች የሚመልስ ለመሆኑ እርግጠኞች ለመሆን በብዙም አልተጨነቅንም። የተካሄደው የፖለቲካው እንቅስቃሴ ለውጡ ለውጡ እንዲዳፈን የተደረገበት መንገድ ትውልዱን በደንብ አገሩን እንዲያስባት አድርጎታል። ለዚህም በአዲስ ነገር ጋዜጣ በመስፍን ነጋሽ በኩል ወደ አደባባይ የወጣው የትውልዱ የመጀመሪያ ጥያቄ የነበረው ይህቺ አገር የማን ናት የሚለው ነበር። ይሄንንም ጥያቄውን ሲያውጠነጥን አገሩ የጥቂቶች ሆና ነው ያገኛት ስለዚህም ትውልዱ የኔ የሚላት አገር እንድትኖረው ሻተ።

ምን አይነት ሀገር? የ1997 ምርጫ ትውልዱን ብዙ አስተምሮታል። በህዝብ ዘንድ የነበረው የስርዓት ለውጥ ፍላጎት እንዲዳፈን የሆነው እንደሀገር ምን ስላልነበረን ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በእጅጉ እንዲያብሰለስለው ሆኖዋል። ተብሰልስሎ ብቻ አልቀረም አልቀረም ለጠየቃቸው ጥያቄዎች ራሱ በመብሰልሰሉ ውስጥ መልሱን አግኝቶት ነበር። ይኸውም የነፃ ተቋማት ያለመኖር ችግር
የለውጡን ፍላጎት እንዳዳፈነው ተረድቶታል።

ስለሆነም ነፃ የፍትህ ተቋማት፥ ነፃ ሚድያ፥ ነፃ የሲቪክ ተቋማት፥ ነፃ የመከላከያ ኋይል፥ ነፃ የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የደህንነት ኋይል የተገነባች ሁሉም ጥያቄዎች በጠረጴዛ ዙሪያ የሚፈቱባት
ሀገርን ሽቶዋል። ለመሻቱ ተግባራዊነት ደግሞ በዚህ ወታደራዊ ነፍጥ አንጋቢ አንባገነን ሁሉን ጨፍልቆ መውሰድ በሚፈልግ ስርዓት ውስጥ ሊተገበር እንደማይችል አረጋግጦዋል። የትውልዱ
ጥያቄ ሊመለስ የሚችለው አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ሲቻል ብቻ እንደሆነ ተረድቶዋል። ለውጡ እንዴት ይምጣ? ትውልዱ ባለፉት 10 አመታት በተለያዩ ወቅቶች እርስ በእርስ
በነበረው ግኑኝነት ለውጥ፥ ለውጥ ብሎ ደጋግሞ አንስቶዋል። ይህ ትውልድ አሁን ወጣትነቱ ወደ ማብቂያው እየሄደ ቤተሰብም አፍርቶ ወደ ጉልምስናው መጀመሪያ እየገባ ነው።

በወጣትነቱ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ የወጣትነት ዘመኑ መጨለም ሊጀምር እየዳመነ ነው። ትውልዱ የጥያቄዎቹ እንዲሁም የታሪኩ ባለዕዳ ነው። ያነሳቸውን ጥያቄዎችና የታሪክ ኋላፊነቱን የሚወጣበት ጊዜው አሁን ነው። ወጣትነቱ ከመጨለሙ በፊት ባለታሪክ የሚሆንበት ለነገው ትውልድ ለሱ ልጆች የታሪኩን የተፃፈ ገፅ የሚያነብበት የዕርጅናው ወራት ሲመጣ ለልጆቹ የሚተርከው የተፃፈ ገፅ እንዲኖረው አሁን ወደ አደባባዮቹ የመትመሚያው የመጨረሻው ጊዜ ላይ ነው።

ይህ እንዴት ይሆናል? ለውጡን በምን መልኩ ማካሄድ ይቻላል? ብሎ የደረሰበት መደምደሚያ ህዝባዊ እምቢተኝነትን በሀገሩ ላይ በመተግበር ወደ አደባባዮቹ መትመም ያንተ የጦርነት አውድማ
አሲንባ ወይም ደደቢት አይደለም በሀገርህ ላይ ያሉት አደባባዮችህ ናቸው። ሀገር እንዳይኖርህ ሀገር አልባ ያደረገህን ስርዕት ከስሩ መንግሎ ማፍረስ ነው። ይህ ሲሆን ያኔ ባለታሪክ ይሆናል ጥያቄዎቹም ይመለሳሉ። ያኔ ታድያ የታሪኩ ባዶ ገፅ እየተገለጠ በሚነበብ፥ በሚተረክ የተፃፈ ገፅ ይሞላል።በጉልምስናህም ዘመን ኩራት፥ ክብር የሰው ልጆች ፍላጎት የሆነው ይኖርሃል፥ በማሻውም እድሜህ ለልጆችህ
የታሪክህን ገፅ እየገለጥክ ያኔ እነሱ በማንነታቸው ኮርተው የኔ ብለው የሚኖሩባትን ሀገር ዲሞክራሲያዊት፥ ፍትሃዊት፥ የነፃ ህዝቦች መኖሪያን፥ የሀገር ባለቤትነትን ማረጋገጥ የቻልክ አባት መሆንህን ትተርክላቸዋለህ።

አርአያዎች ከየትም አትፈልግ የትውልድህ አባላት የሆኑት ያንተን የነፃነት ውልድ እያማጡ ያሉ አሉልህ። ተመልከት እነ አንዷለም አራጌን፥ ተመልከት እነ ሃብታሙን አያሌውን፥ ተመልከት እነርዕዮትን፥ ተመልከት ተመስገንን ያንተን ምጥ ሲያምጥ፥ ተመልከት እነ ማህሌትን፥ እነ ኤዶምን፥ እነበፍቄን፥እነ ናቲን፥ እነ ዘላለምን እን አቤልን. ……….ለአንተ ትውልድ ጥያቄዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። ምን ቤት አለህና ቤትህ ትገባለህ ያንተ ቤት አደባባዮችህ ናቸው። ለባርነት ማዶ አትመልከት ለነፃነትህ ወደ ራስህ ቤት ተመልከት።

እንደመደምደሚያ ይህ ትውልድ ብዙ ተብሎዋል በጫት የናወዘ፥ ከራሱ ባሻገር አገራዊ ራዕይ የሌለው ወኔ አልባ፥ አደገኛ ቦዘኔና ብዙ አልባሌነቱን የሚነግሩት ማንነት ተደርቦለታል። እሱ ግን እንደዚህ እንዳልሆነ የሚያስመሰክርበት አሁን ታሪክ 2007ን ሰጥቶታል። አብዮቱንት ተሸክመው የሚዞሩት እንኳን አልፈሩም ትውልዱስ ስለምን ይፈራል? እሱ ከትላንት አባቶቹ በምን ያንሳል? እንደ ቱኒዝያ፥
ግብፅ፥ ቡርኪና ፋሶ አቻዎቹ የለውጡ ባለቤት እንደሆነ ያረጋግጣል የሚል እምነት አለኝ አደባባዮቹም የሀገሩን ልጆች ወጣቶቹን ናፍቀዋል።

ወራዙት ይአቅቡከ (ያፈቅሩከ)

Image

Tekle Bekele – ለኔ እዉነተኛዉ የአንድነት ፓርቲ ትናንት በፍ/ቤት ዉሳኔ ተቀብሯል፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆን ቀድም ሲል አዉቀናል፡፡ዳኛ ብርቱኳንም ፍርህይወትም ዳግም አልተከሰቱም፡፡እንደ ኢህአዴጉ የምርጫ ዉጤት 99.6 ከመቶዉ አመራሩና አባላቱ በምርጫ ቦርድ እንዲበተኑ የተበየነበት እንዲሁም በደጋፊዎች የተገዛ ንብረት ያለፍ/ቤት ትእዛዝ በመንግስት ታጣቂ ፖሊሶች የተዘረፈበት አንድነት የፍትህ ተቋሙን ለመፈተሸ ም/ቦርዱን መክሰሱ ይታወቃል፡፡
ም/ቦርድን መክሰሳችን አግባብ እንዳልሆነ አንቀጽ ተጠቅሶ ከማስፈራሪያ ጋር ክሱ ዉድቅ ተደርጓል፡፡ መፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል፡፡ቀጣዩን በቀጣይ ሂደት የምናየዉ ይሆናል፤እንደሚፈልጉት ተበትነን አንቀርም፡፡አንድነቶች በያለንበት እንረጋጋ!!
ታላቋ ምእራብ አፍሪካዊት ሃገር ናይጀሪያ እዚህ የደረሰችዉ ዉድ ዋጋ ከፍላ ነዉ፡፡ከናይጀሪያም በላይ ዋጋ ብንከፈልም በልተዉ በማይጠግቡ በሎች ትግሉ እየተነጠቀ ዛሬም እዛዉ ላይ ነን፡፡ታላቅዋ የምስራቅ አፍሪካ ኮከብ ሀገረ ኢትዮጵያ በልማት ስም ክብሯ እንዲወርድ እየተደረገች ትገኛለች፡፡እናም በዲፕሎማሲ፤በዲሞክራሲ፤በኢኮኖሚም ይሁን በሁለንተናዊ ልማት የአለም ማህበረሰብ በአፍሪካ ትኩረት ናይጀሪያ ሆናለች፡፡ኢትዮጵያ የምትፈለገዉ ለክፍለአሁጉሩ የደህንነት አጋርነት ብቻ ነዉ፡፡
የናይጀሪያ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና(የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ትብብርና ዉህደት ያስከተለዉን ዉጤትም ልብ ይሏል) የተወዳዳሪ ግለሰቦች ሚና ቀላል ባይሆንም ለናይጀሪያ ተስፋ የሆናት ግን ህዝቡ ነዉ፡፡የኢትዮጵያችንም የለዉጥ ተስፋ ህዝቡ ነዉ፡፡በዚህ ወቅት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍም የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
Image

Minilik Salsawi ትላንትና ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በኦሮሚያ ክልል አምቦ አከባቢ አንድ ከፍተኛ የወያኔ ወታደራዊ ባለስልጣን መገደሉ ታወቀ::አምቦ በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር ስር መውደቋ ተረጋግጧል::በአከባቢው የመብራት እና የስልክ አገልጎት ተቋርጦ ያደረ ሲሆን ይህንን የአከባቢው ነዋሪዎች ለሰይፈ ነበልባል ራዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ እዮብ ባይሳ በሰጡት ቃለመጠይቅ አረጋግጠዋል::

በቀበሌ 2 በተባለ አከባቢ ሲያልፍ የነበረውንየወያኔ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን የገደለው ማንነቱ ያልታወቀ ሲሆን አምቦ በከፍተኛ የደህንነት ቁጥጥር ስር ነች ያሉት ነዋሪዎቹ በጊዜው ጉዳዩን ያልተረዱና ከፍተኛ መደናገጥ እንደደረሰባቸው የተናገሩ ሲሆን ፖሊሶች እና ማንነታቸው የማይታወቁ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን እያስቆሙ እና እየፈተሹ እንደነበር ታውቋል::

ከአስረ አንድ ወራት በፊት ወያኔ የነደፈውን እና ገበሬዎችን የሚያፈናቅለውን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ከ27 00 በላይ የአምቦ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወተው የነበረ መሆኑ ሲታወስ የሕወሓት አግአዚ ሰራዊት ከ30 በላይ ያልታጠቁ ተማሪዎችን እና ነዋሪዎችን የገደለ እና የቤተሰባቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ በቦታው የነበሩ ዜጎች ሳይቀር ለሞት እና ለቁስለት መዳረጋቸው የታወቀ ሲሆን የዘጠኝ አመት ሕጻን ታዳጊ ሳይቀር በሕወሓቶች መገደሉ ይታወሳል : ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

http://ayyaantuu.com/horn-of-africa-new … mbo-today/

Image

azeb mesfinመውደቂያው የደረሰው ወያኔ እርስ በርሱ መበላላት ጀምሯል:ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ ነን:: የደህንነት ሹሙ ጌታቸው ማለት እንደ ወይዘሮ አዜብ አነጋገር “…ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ..” እንደሆነ ሲታወቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወይዘሮ አዜብ በቤተሰቦቻቸው ስም ያቋቋሙት ድርጅት እና ያፈሩት ሃብት እና ንብረት ላይ ክትትል እንዲደረግ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቡድናቸውን ማዘዛቻው ወይዘሮዋ በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ መጀመራቸው ታውቋል::ወዳጆቻቸውን ተገን በማድረግ በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገቡ ከባድ እና ቀላል መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ቀረጥ ስለማይከፈልባችው ጥያቄ በአዜብ መስፍን ላይ ቢያስነሳም ወይዘሮዋ ከተጠየቅን አብረን ነው መጠየቅ ያለብን ሲሉ ከዚህ ቀደም መልስ መስጠታቸው እና ከዘረፋ ጋር ጋር የተያያዘ ጥቄዎች ሲነሳባቸው በጄኔራሎች ካኪ ስር መደበቅ ተግባራቸው መሆኑ ለደህንነት ፈላጭ ቆራጮ እንዳልተዋጠላቸው ታውቋል::

ከዚህ ቀደም በቤተመንግስቱ የውስጥ ሽኩቻ ውስጥ ቂም በቀል እንዳለባቸው የሚነግርላቸው የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው ወይዘሮ አዜብን አጥምዶ የሰው መሳቂያ ለማድረግ ከማሴር አልተቆጠቡን ሲሉ የወይዘሮዋ የቅርብ ሰዎች በምሬት ይናገረሉ:: ወዳጅ መሳይ ተናዳፊ እባብ ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ ብላ አዜብ የምትጠራው ጌታቸው በዘመዶቿ ስም ያፈራችውን ንብረት የመውረስ እና ሸጦ ገንዘቡን በሌላው እንደለመደው ከሃገር የማሻገር እቅድ እንደያዘ የቅርብ ወዳጆቿ አክለው ገልጸዋል::በደህንነት ሰዉየውና በሴትየዋ መካከል ያለውን ቅራኔ ፈትቶ ጉዳዩን ለማረጋጋት አቶ በረከት ስምኦን እና ጄኔራል ሳሞራ ጥረት ላይ መሆናቸው ታውቋል::

በውጪና በውስጥ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ትልቅ ጫና የበዛበት ወያኔ ከሃገር እና ህዝብ ሃብት በተጨማሪ እርስ በርሱ መበላላት እና መዘራረፍ የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ ዘራፊ ስር አት ለማስወገድ በጋራ እና በአንድነት በመታገል የዜግነት ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን::

• የሶዶ ፖሊስ 8 የሰማያዊ ዕጩዎችን በማሰር ቅስቀሳውን አስተጓጉሏል

• የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተዘርፏል

• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ ሆን ተብሎ የተቀየሰ ስልት ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም›› ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት ‹‹ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ›› አድርጋችኋል በሚል ሌላ ክስ 8 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችንና ሌሎች አባላትን በማሰር ቅስቀሳውን እንዳደናቀፈ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ታደመ ፈቃዱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በባህርዳር ከተማ ፖሊስ ‹‹በሞንታርቮ ለመቀስቀስ ፈቃድ ስላላመጣችሁ መቀስቀስ አትችሉም፡፡›› በሚል ፓርቲው ሊያደርገው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ እንዳደናቀፈ የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ‹ለምን ትከለክሏቸዋላችሁ?› በሚል ህዝቡ ፖሊሶቹን በማፋጠጡ በድምፅ መቀስቀስ ባንችልም በህዝቡ ድጋፍ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማሰራጨት የተሳካ ቅስቀሳ አድርገናል›› ሲሉ አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ ምንም አይነት ፈቃድ እንደማያስፈልግ የገለፁት አቶ ስለሽ ፖሊስ የሚፈጥረው እንቅፋት ሆን ተብሎ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ የተቀየሰ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን በመሰረዝ ፓርቲው ምርጫው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥረዋል፡፡ ይህ አልበቃ ሲልም የቅስቀሳ መልዕክቶቻችን በተደጋጋሚ በሚዲያ እንዳይተላለፉ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ማስቆም ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡

በሌላ ዜና የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ባልታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በ02/07/07 ሁለት ሰዓት ላይ አራት ግለሰቦች ጽ/ቤቱን በመስበርና የጽ/ቤቱን ጥበቃ አስፈራርተው በማባረር ለቅስቀሳ የተላከ 6 ሺህ ኦሮምኛ በራሪ ወረቀት እንዲሁም 3 ሺህ አማርኛ በራሪ ወረቀት፣ አንድ የፎቶ ካሜራ፣ አንድ ባነር፣ ለሸካ ዞን ሊላክ የተዘጋጀ 5 ሺህ በራሪ ወረቀት፣ 50 ፖስተር፣ አንድ የእጅ ሜጋ ፎን፣ ሁለት ባነር፣ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲዘርፉ የጽ/ቤቱን ኮምፒውተርም ሰብረዋል›› ሲሉ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡