ኢትዮጵያዊው በተመድ የአለም የጤና ድርጅት ባለስልጣን በታይላንድ ኢትዮጵያዊቷን ሰራተኛውን ሲያስቃይ ተደረሰበት::

ኢትዮጵያዊው በተመድ የአለም የጤና ድርጅት ባለስልጣን በታይላንድ ኢትዮጵያዊቷን ሰራተኛውን ሲያስቃይ ተደረሰበት::

ኢትዮጵያዊቷን ለሁለት አመት አግተው በታይላንድ ሲያሰቃይዋት የነበሩት ኢትዮጵያውያን ናቸው::

ዶክተር ዮናስ ተገኝ የተባለ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የሚሰራ ግለሰብ ለኢትዮጵያዊቷ ስቃይ ተጠያቂ መሆኑ ተደርሶበታል::ባለፈው ሳምንት አለምነህ ዋሴ በአዋዜ ፕሮግራሙ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ በለቀቀው የአንዲት ኢትዮጵያዊት የታይላንድ ሰቆቃ (http://www.clickhabesh.com/?p=105552) አሰቃዮቿ ተብለው በሰራተኝነት ቀጥረው የወሰዷት በተባበሩት መንግስታት የአለም ጤና ድርጅት የታይላንድ ባለስልጣን ዶክተር ዮናስ ተገኝ እና የትዳር አጋራቸው ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋግጧል::

አለምነህ ዋሴ ኤ ኤፍ ፒን ዋቢ አድርጎ የገለጻት ኢትዮጵያዊ ከሃገር ቤት በቤት ሰራተኝነት ሊያሰሯት ከወሰዴት በኋላ ለአመታት ደሞዟን ሳይከፍሉ ከተዋት እስከ ማታ ደረቅ ሩዝ እንድትበላ በማድረግ ከውሻ ጋር ባንድ ክፍል እንድትተኛ በማድረግ ሲያሰቃይውት እንደነበር እና በስተመጨረሻ ራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሰው ደርሶላት አድኗት ለአንድ የሰብ አዊ መብት ድርጅት እንደሰጣት እና በአሁን ሰአት ጉዳዩን የታይላድ ፖሊስ እየተከታተለው እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል::

ኢትዮጵያዊቷን በቤት ሰራተኝነት አምጥቶ ሲያሰቃያት የነበረው ግለሰብ ራሱን ከወንጀሉ ነጻ በማድረግ ምንም ወንጀል እንዳልፈጸመ እና ትክክለኛ ሰው አድርጎ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በኢሜይል ሊያስተባብል ሞክሯል::(viewtopic.php?f=2&t=95181)በዘመናዊ ባርነት ላይ የተመሰረተ የመብት ገፈፋ ያካሄደው ግለሰም የ25 አመቷን እና ስሟ እስካሁን ያልተጠቀሰውን ኢትዮጵያዊት በ2000 ብር ክፍያ ከኢትዮጵያ አምጥቶ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ሲያሰራት እንደነበር የገለጸው ባንኮክ ፖስት ግለሰቡን ለማናገር ቢፈልግም ዶክተር ዮናስ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል::

እጅግ ያማል!! ደሞ ነገሩን በይቅርታ እነ በፍቅር መፍታት ሲገባው አለማፈሩ ለኤ ኤፍ ፒ ኢሜይል ያደርጋል::http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=95181
Image