በኢትዮጵያ የተፈጠረው የሳንቲም እጥረት ከፍተኛ ውጥረት ፈጥሯል::የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚውን በዜሮ ድምር ውስጥ ከቶታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ
በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን የሳንቲም እጥረት ለመሸፈን እየተደረጉ ያሉ ሙከራዎች ሁሉ ባለመሳካታቸው ከፍተኛ ውጥረት እንደፈጠረበት ታውቋል!ህዝበ ሙስሊሙ የመገበያያ ሳንቲሞችን ከገበያ በማስወጣት መንግስት ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደረበት የሚገኝ ሲሆን አሁንም ይኸው መርሀ ግብር እየተከናወነ በመሆኑንና መንግስት እየደረሰበት ላለው ችግር ምላሽ ለመስጠት እየሞከረባቸው የሚገኙ መንገዶች ባለመሳካታቸው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ ታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱዋ በተለይም በአዲስ አበባ ያለውን የዝርዝር ሳንቲም ፍላጎት በመንግስት በኩል እስከ 50% ያህል እንኳን መሸፈን እንዳልተቻለ የታወቀ ሲሆን ብሔራዊ ባንክ ዝርዝር ሳንቲሞችን በፍላጎት ልክ ሳይሆን ባስቀመጠው ገደብ ልክ ብቻ እየሰጠ እንደሚገኝና ይሄንንም ለማግኘት የበርካታ ቀነ ገደብ ወረፋ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ታውቋል። ይህንን እጥረት ለመሸፈን በዐሁኑ ወቅት መንግስት ያለው ብቸኛ አማራጭ ተጨማሪ ሳንቲሞችን ማሳተምና ወደ ገበያ ማስገባት ሲሆን ይህም ከፍተኛ የሆነ ወጪ ከእቅድ ውጪ የሚያስወጣውና ተጨማሪ ሳንቲሞችን አሳትሞ ወደገበያ በሚያስገባበት ወቅት ህዝበ ሙስሊሙም የሰበሰባቸውን ሳንቲሞች መልሶ ወደ ገበያ ስለሚያስገባቸው በዚህም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሳንቲም የመግዛት አቅም ስለሚወርድ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ስለሚደርስበት እጥረቱን ለመሸፈን በቀጣይነት የትኛው መፍትሄ ላይ እንደሚወስን ውጥረት ውስጥ መግባቱ
ታውቃል።
ይህ የተቃውሞ መንገድ የጊዜ ገደብ ስላልተቀመጠለትና አሁንም ህዝበ ሙስሊሙ እንዲሰራው ድምፃችን ይሰማ እያስታወሰው በመሆኑ በቀጣይነትም የዝርዝር ሳንቲም እጥረቱ በሀገሪቱ ተባብሶ እንደሚቀጥልና ለመንግስት በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሚሆንበት የሚጠበቅ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙም ከድምፃችን ይሰማ በተሰጠው ትዕዛዙን አጠናክሮ ተግባራዊ በማድረግ የመንግስትን ውጥረት እንደሚያባብሰው ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚያቸው ከተንኮታኮተባችው 14 አገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን የአለም ባንክን ሪፖርት ጠቁሟል:: በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የብድር እዳ እንዳለባት የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ አገራዊ ምርቷ 45 በመቶ የሚሆነው ከብድር የተገኘ ገንዘብ እንደሆነ ጠቁሞ፤ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ይህ አኃዝ ወደ 65 በመቶ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁሟል፡፡ ከለጋሽ ተቋማትና ሃገራት የሚገኝ ብድር ለአጠቃላይ አገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ ከ30 በመቶ በላይ ከሆነ ሀገራት ወደ ከፍተኛ የእዳ ቀውስ እያመሩ መሆኑን እንደሚያመለክት የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ኢትዮጵያም በዚህ የአደጋ ቀጠና በከፍተኛ ደረጃ ከገቡ 14 የአለም ሀገሮች መካከል ተጠቅሣለች። ከፍተኛ የውጭ እዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል የተባሉት 14 ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡታን፣ ኬፕ ቨርዲ፣ ዶሚኒካ፣ ጋና፣ ላኦስ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞንጐሊያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሣሞኣ፣ ሣኦቶሜ ፕሪንቼቤ፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል 24 የአለም ሀገሮች የውጭ እዳቸው በሚያሰጋ ደረጃ እየጨመረና ወደ አደጋው ቀጠናም እየተንደረደሩ ነው በሚል ተጠቅሰዋል፡፡ አንዳንድ በአስጊ ደረጃ እዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል የተባሉ ሀገራት፣ የተበደሩትን ገንዘብ ለተገቢው አላማ መጠቀም አለመቻላቸው ለቀውስ እንደዳረጋቸው በሪፖርቱ ተጽፏል::