ለእኛ የሚበጀን በትግላችን ነጻነታችንን ማረጋገጥ እንጂ የኦባማ መግባት እና መውጣት አይደለም:: ምንሊክ ሳልሳዊ
የባራክ ኦባማ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ኬንያን እና ኢትዮጵያን መጎብኘት የሰሞነኛ አዲስ ዜና ሲሆን ባራክ ኦባማ የሃያላኗ አገር መሪ በመሆናቸው የጉዞው ዜና ሰፊ ሽፋን አግኝቶ አለምን እያስተጋባ ይገኛል::ባራክ ኦባማ በርግጥ ከአፍሪካዊ አባት መገኘታቸው እንዲሁም የሃያላኗ አሜሪካ የመጀመሪያው ጥቁር መሪ መሆናቸው ለየት ሊያደርጋቸው የሚችል ቢሆንም የሚከተሉት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ በተለይ አፍሪካን በተመለከት የሚያራምዱት አቋም አምባገነኖችን ፈልፍሎ ከማበረታታት ውጪ ምንም የፈየደው ነገር የለም::
ኦባማ ወደ ስልጣን ሲመጡ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ ለመመረጥ የሚያስችላቸውን ድምጽ ለማግነት አፍሪካን በተመለከተ ቃልኪዳኖችን በማሽጎድጎዳቸው በተለይ ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ምድር ለመመረጣቸው ስኬት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል::ኦባማ ግን ወደ ስልጣን ወንበሩ ከተዋሃዱ በኋላ የአፍሪካ አምባገነኖችን በነጩ ቤተመንግስታቸው ሰብስበው በከፍተኛ ማበረታታት የአሜሪካንን ጥቅም በልዩ መልኩ በሚጠብቅ ሁኔታ ደም መጣጭ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችን አጓጉል በማሞገስ ለአፍሪካውያን ትልቅ አደጋ የሆኑ ወንጀሎች እንዲሰሩ እና መንግስታዊ ሽብርተኝነት እንዲስፋፋ አድርገዋል::
በርግጥ ምእራባውያን አፍሪካ ውስጥ ለብሄራዊ ጥቅማቸው እንደሚሰሩ የታወቀ ነው:: የሃይል ሚዛንም ባለበት ሆነው ጥቅማቸው እስካልተነካ ድረስ አምባገነኖችን በመደገፍ እንደሚያበረታቱ ሃቅ ነው::ኦባማ የውጪ ፖሊሲያቸው እንደሚያሳየው የአሜሪካን ጥቅሞች እስካልተነኩ ድረስ ማንኛውም አፍሪካዊ መሪ በሃገሩ ውስጥ የሚፈጽመውን የፖለቲካ ግፍ እንደማይመለከታቸው እና ጣልቃ መግባት እንደማይፈልጉ በተለያዩ ጊዜያት አጋጣሚዎችን ተጠቅመው ተናግረዋል::ሕዝቦች በኑሮ ውድነት መግቢያ መውጫ እንዳጡ በርካታ ድሆች ጥቂት በሙስና የከበሩ ቱጃሮች እንዳሉ በገሃድ እየታየ በዋጋ ግሽበት እና በተለያዩ የኢኮኖሚ ውድቀቶች ሃገራት እየሞቱ እያዩ በሃሰት የቁጥር ቁልሎች የኢኮኖሚ እድገት እየታየ እንደሆነ በመጥቀስ ከባልደረቦቻቸው እና ተቋሞቻቸው ጋር እየተቀባበሉ ሲናገሩ ተሰምቷል::ለዚህም በሞት አፋፍ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ አገራችንን ገነት እያደረጉ በመሳል ስህተቶች ሲፈጥሩ ማየት የተለመደ ተግባር ነው::ወታደሮቹን በሽብርተኝነት መዋጋት ሰበብ እየሸተ የሚገነውን ወያኔ መራሹን መንግስት በማቆለጳጰስ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ኢትዮጵያን እንዲወር በሩን ከፍተዋል::
ባራክ ኦባማ ለአሜሪካ እና ለአሜሪካውያን ምናልባት ጥሩ መሪ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል::እርሳቸው ወደ ስልጣን ክመጡ በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ግድያ እስር እና የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙ እንዲሁም አለምን ያስደመመ እና ያሳዘነ ስደት መከሰቱ እሙን ነው::እርግጥ ነጻነታችንን እና መብታችን የሚያስከብሩልን ኦባማ አይደሉም::እኛ ራሳችን መሆናችንን መዘንጋት የለብንም::የኦባማ የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት ለኛ ምም የሚጠቅመን ነገር የለም::ለሽፋን ጥቂት እስረኞች ቢፈቱ በርካቶች መታሰራቸው እና መገደላቸው ቀጥሏል::ይህንን ልንፈታ የምንችለው በጋራ ቆመን በመታገል በአንድነት ሃይላችንን አጠናክረን የወያኔን ማፊያ መንግስት ስንደመሥ ብቻ እና ብቻ ነው::ምናልባት ኦባማ እንደተለመደው ፍሪደም ኦፍ ምናም የሚል የአንደበት አየር ባየር ንግግሮች ቢናገሩም በዋናነት የሚመለከቱት ግን የሃይል ሚዛኑን እና የሃገራቸውን ጥቅም እንደሆነ ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል::ለኛ የሚበጀን በትግላችን ነጻነታችንን ማረጋገጥ እንጂ የኦባማ መግባት እና መውጣት አይደለም::ድል በሕዝብ ለሕዝብ የሕዝብ ነው::#ምንሊክሳልሳዊ
Ahnung min abesachachihu Obama hagerachin biimeta. Ethiopian rasuan weyane nech bilachihu hagerituan telachihuwat? Asafariwoch. Ye Isayas firifari lekakamowoch
All signs point to Eritrean regime’s plan to march the Tigrean People Democratic Movement (TPDM) into Ethiopia in the near future. So far, there is no action on the ground except hyper propaganda. But by all indications, Shabia is ready for action because it cannot sit idly by while the country withers away as Eritrean youth run for the border and the U.N. sanction takes its toll. The country’s economy and military is depleted by the mass migration of Eritrean youth out of the country. Eritrea is in a death spiral. Molla Asgedom to the rescue…ውሻ ጮኸ ተብሎ ድንጋይ አይወረወርም
July 22, 2015
ቹቸቤ ነኝ አማን ነው? የሰሞኑን ነገር ለመግለጥ የሚሆን መንደርደርያ ፍለጋ ስባጅ ቆየሁ። ዛሬ ሁሉም ተናጋሪ ቢሆንም የነገር ድግግሞሽ አታክቶናል። ገና የተተነፈሰው እንደሰሚው ተወላግዶ ወይም ጣፍጦ የበሬ ግንባር በምታክለው ፌስ ቡክ ይለጠፋል። ወሬ ብርቅ አይደለም። እንዲያውም በርካታ ተግባር አልባ የወሬ ቤቶች ተከፍተው ወሬ ሲወቁ ነገር ሲሰልቁ ቡና ቤት መለወጥ እንደሚወድ ጠጪ ከአንዱ ፓልቶክ ወደ ሌላው እየዞሩ በጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ የሚያደነቁሩን አውርቶ አደሮች በዝተውብናል። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከፈር ቀዳጅ ታጋዮቹ መንደር ነበርንና አንቱ በሉን የሚሉ እድሜ ጠገቦቹ ከተማሪ ረብሻ ወዲህ አርባ አመት ያስቆጥሩም ቢሆን ዛሬም እንኳ የአስተሳሰብ ጨቅላነታቸውን አለመጨረሳቸውና አሁንም በረብሻ መተዳደርን የመረጡ በሚያስመስል አፍራሽ ተግባር ተጠምደው ማየታችን ነው።
በእድሜ ዘመናቸው አንድም ሚዛን የሚደፋ ቁምነገር ሰርተው አያውቁም። በተለይ ደግሞ ወያኔ ወደስልጣን ከመጣ በሁዋላ ከኛ በላይ የወያኔ ተቃዋሚ ለአሳር እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው የሚውረገረጉም ቢሆን የዚህን አረመኔ ወያኔ እድሜ የሚያረዝም እንጂ የሚያሳጥር ምንም ሰርተው አያውቁም። እንዲያውም ከእድር ለየት ባለ የፖለቲካ ቡድንነት የተሰባሰቡ መሆናችው ትዝ የሚላችውና ነገር ጣል ለማደረግ የሚባንኑት ሌላው ወገን የሰራው ነገር መኖሩን ሲሰሙ ነው። ያኔ አይናቸው ደም ይለብሳል እንደ ወያኔ ተለጣፊ ወይም ተመሳሳይ ነገር ሰርተው የተሰራውን ለማፍረስ ይጣደፋሉ። ገና አልባነነ ይሆናል እንጂ ጋዜጠኛውም ከፍርስራሾቹ አንዱን እየሆነ ነው። እንዲያውም ቆመጥ አድርገውት የራሱን ኢሳትን ይደበድቡበታል። እርሱም ዝናዬን ቀሙኝ ኩርፊያ የያዘ ይመስል አጓጉል መሄዱን መርጧል። ብቻ አጎቶቻችን ለማፍረስ ሲሆን እንደ ተኩላ ናቸው በጩኸት ይጠራራሉ ሳይነጋገሩ ይግባባሉ። ድርጅት በአይነት በአይነት ያቋቁሙና የመጥለፍ ጥማታቸውን ለጊዜውም ቢሆን ያረካሉ። የጀመሩትን ከምን እንዳደረሱት የሚጠይቅ ስለሌለ አዲስ ባቆሙት ላይ ያወራሉ። ትግል የሚለውን ቃል በግርድፉ እንዲያው ቃል በቃል ወስደው ነው መሰል አድማ እየመቱ ከሁሉም ሲታገሉና ሲያፈርሱ እድሜ ራሱ አፈራርሶ ሊጨርሳቸው ነው።
በመጨረሻ አንደርዳሪ ብልጥ ሃሳብ አገኘሁ እነሆ የብልህ ሰዎች ማህደር ከዊንስተን ቸርችል አባባል ላይ ወስዶ የለጠፈው ቃል ማረከኝ። “ውሻ በጮኸብህ ቁጥር ድንጋይ እያነሳህ የምትወረውር ከሆነ ካሰብክበት አትደርስም” የሚል ነው። አዎ ሩቅ ለመሄድ አልመው ድንጋይ ወርዋሪና ማዶ ለማዶ ቆሞ ተሳዳቢነትን የመረጡ ያሰቡበት አይደርሱም። ሰሞኑን የሚነፍሰው ንፋስ ግምኛ ነው ይሰነፍጣል። በርግጥ እነዚህ ሰዎች ነጻነትን ይፈልጋሉ ወይንስ እኛ ካላረግነው ሁሉም አፈር ይብላው የሚሉ ናቸው? እውን እነዚህ ሰዎች ለአፍራሽ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ፍርፋሪ ኖሮ ነው ወይንስ ኑሮአቸው ይኸው ግርግር የመፍጠር ሆኖ ነው? ያስብላል። በተለይ የተማሩትና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል እያሉ የሚጽፉት ምሁራኖች እነሱ ባሉብት መድረክ ላይ በጠንካራ ታጋዮችና መሪ ድርጅቶች ላይ ተራ ስድብ ሲደረደርና ትግሉን የሚጎዳ ግርድፍ ሀሳብ ሲዥጎዶጎድ በዝምታ ማለፋቸው ምን ይባላል? እኔን አንቱ እስካላችሁኝ ድረስ ሌላውን ድባቅ ብታስገቡትና ትግሉን ብትጎዱት እኔ ምን ገዶኝ ብለዋል ማለት ነው? ይሄ ከሆነ ስሌቱ ፍላጎታቸው መድረክ ላይ መኮፈስ እንጂ ሀገርን ማዳን አይደለም ብለን እኛም ለእንደዚህ አይነቶቹ የሚቸረውን አክብሮት እንሰጣቸዋለን።
በተግባራዊ ትግል የተጠመደው ወገን ደግሞ እነ ሰው ከንቱን ቁም ነገር አድርጎ አቧራ ማጨሱን ተወት አድርጎ ጊዜውን ተግባራዊው ትግል በሚፈልገው እንቅስቃሴ ላይ ቢያተርኩር ይሻላል። የእነኚህ አፍራሽ ወሬኞች ፋይል መዘጋት አለበት። እነርሱን ሰምቶ ከመንጫጫት ከግንቦት ሰባት አመራር ተምረን ለወሬኞች የምናባክነው ሰአት የለንም ብለን ወደተግባሩ እንመለስ። የግንቦት ሰባት አመራሮች ለርካሽና ተልካሻ ነገር መልስ ለመስጠት ደፋ ቀና ሲሉ አናያቸውም። ስራው ላይ በማተኮራቸው የእምነት ጽናትም በማሳየታቸው መሬት ላይ የሚታይ ስራ እየሰሩ ነው። ‘በርገር’ እየበሉ ግፋ በለው ብቻ እንደማይሉ ደግሞ በተግባርም እያሳዩ ነው። የሚበልጠው ለእናት ሀገር ለመዋደቅ የቆረጡ ወጣቶችንና አርበኞችን መደገፍና ትግሉን ማፋፋም ወይንስ የአሽሙር ጧፍ እያበሩ የእርግማን አዝማች ያለው የስድብ መዝሙር መዘመር?
ምርጫችንን ልናውቅ ልንበስልና ልንበቃ የሚገባን ጊዜ ላይ ነንና ከአመት አመት ራሳችንን እዚያው የነበርንበት ላይ ማግኘት ደካማ አቅማችንን ፀሀይ ማስሞቅ ይሆናል። ለዚህ ነው እነ ስም አይጠሬን ከቁም ነገር መድረክ ላይ ቆልለን በጮሁ መጠን ቃላት የምንወራወር ከሆነ መቼም ቢሆን ካሰብንበት አንደርስም ለማለት የወደድኩት። እንዲያውም ተጋብቶብን ቀንደኛ ተሳዳቢና አለክላኪ ተጓዥ ሆነን እርስበርስ የመነካከስ ባህርያትንም እየወረስን ነውና እነሱን ከመሆን ያድነን እንበልና ወደፊት እንገስግስ። ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚል መፈክር ትዝ የሚለው ማነው? አዎ ያኔ ያለቀ ቢሆን ዛሬን ባልዘመትን ነበር።
ድል የማይቀር እውነት ነውና ዱር ቤቴ ላሉት ደጀን መሆን ምርጫችን ይሁን!
Molla Asgedom, the next Meles Zenawi?
Post a reply
Postby elias » Yesterday, 04:53
All signs point to Eritrean regime’s plan to march the Tigrean People Democratic Movement (TPDM) into Ethiopia in the near future. So far, there is no action on the ground except hyper propaganda. But by all indications, Shabia is ready for action because it cannot sit idly by while the country withers away as Eritrean youth run for the border and the U.N. sanction takes its toll. The country’s economy and military are depleted by the mass migration of Eritrean youth out of the country. Eritrea is in a death spiral. Molla Asgedom to the rescue… [The full text to be published shortly]
ውሻ ጮኸ ተብሎ ድንጋይ አይወረወርም
July 22, 2015
ዛሬ ሁሉም ተናጋሪ ቢሆንም የነገር ድግግሞሽ አታክቶናል። ገና የተተነፈሰው እንደሰሚው ተወላግዶ ወይም ጣፍጦ የበሬ ግንባር በምታክለው ፌስ ቡክ ይለጠፋል። ወሬ ብርቅ አይደለም። እንዲያውም በርካታ ተግባር አልባ የወሬ ቤቶች ተከፍተው ወሬ ሲወቁ ነገር ሲሰልቁ ቡና ቤት መለወጥ እንደሚወድ ጠጪ ከአንዱ ፓልቶክ ወደ ሌላው እየዞሩ በጉንጭ አልፋ ፍሬከርስኪ የሚያደነቁሩን አውርቶ አደሮች በዝተውብናል። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ከፈር ቀዳጅ ታጋዮቹ መንደር ነበርንና አንቱ በሉን የሚሉ እድሜ ጠገቦቹ ከተማሪ ረብሻ ወዲህ አርባ አመት ያስቆጥሩም ቢሆን ዛሬም እንኳ የአስተሳሰብ ጨቅላነታቸውን አለመጨረሳቸውና አሁንም በረብሻ መተዳደርን የመረጡ በሚያስመስል አፍራሽ ተግባር ተጠምደው ማየታችን ነው።