በደህንነት ቢሮ ለሊቱን ያጋመሰ ግምገማ መካሄዱ ተሰማ::
አለመተማመኑ እና ክፍተቱ እየሰፋ መምጣቱን በገሃድ ያሳየ ግምገማ መሆኑ ታውቋል:: Minilik Salsawi
የሕወሓት የደህንነት አባላት በተለየ ሁኔታ አዳማጭ የሆኑበት ትላንትና የተጀመረው በአዲስ አበባ ውስጥ የተሰማሩ የፌዴራሉ ደህንነት አባላት ግምገማ እጅግ በተካረረ እሰጥ አገባ ለሊቱ አጋማሽ ድረስ ቢደረግም በማጉረምረም እና ባለመስማማት መበተኑ ታውቋል::በአንድ ብሄር የበላይነት የተከሄደው እና በተያያዘ የአንድን ብሄር በተለየ ሁኔታ ያልነካው ይህ ግምገማ በገዛ አገራችን እንደ እንጀራ ልጅ እና እንደ ባይታዋራ ነገሩን ሁሉ በሌሎች ላይ ለምን ይላከካል የሚል ጥያቄ አስነስቷል::

መገምገም ካለበት ትእዛዝ ከሚሰጡ የበላይ ሃላፊዎች ጀምሮ ነው እንጂ ሁሉም እኩል የሰራውን ስራ የትግራይ ተወላጆችን ለይቶ አስቀምጦ አዳምጭ አድርጎ እኛን ለይታችሁ የምትገመግሙበት ምክንያቱ ምንድነው? ሁላችንም አንድ የጋራ ስራ እስከሰራን ድረስ በጋራ ልንገመገም ይገባል ግደሉ ስንባል ገለናል ዝረፉ ስንባል ዘርፈናል ተካፈሉ ስንባል ተካፍለናል::ይህንንም ስራ የትግራይ ተወላጆች አብረውን ፈጽመዋል::ብሄር የለየ እና ያማከለ ግምገማ የዜግነት መብታችንን ይጋፋል እንዴት እንዲህ እንቀጥላለን::ሁሉም በጋራ ሊገመገም ይገባል::አንዱን የቤት ልጅ ሌላውን የጎዳና ዱርዬ አድርጎ መገምገሙ ለምን አስፈለገ የሚሉ አስተያየቶች የተደመጡ ሲሆን:ሃላፊዎቻችን በቡድን በቡድን አደራጅተው በግል ትእዛዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ስራዎችን መስራታችን እየታወቀ ከነሱ በወረደ ትእዛዝ ለሰራነው ስራ ልንጠየቅም ሆን ልንገመገም አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል::በየክልሉ እየተገደሉ የሚጣሉ ግለሰቦችንም ኖን የሚዘረፉ ንብረቶችን የሚጠየቁ ገንዘቦችን አስመልክቶ ሃላፊዎቻችን ወርደው ሊገመገሙ ሲገባ እንዲሁም በማናለብኝነት ለሚፈጸሙ ወንጀሎች የሕወሓት የደህንነት አባላት መጠየቅ ሲገባቸው እነሱን ከዚህ ሁሉ ድርጊቶች አግለሎ እኛን መኮነኑ የማያዋጣ የግምገማ ሂደት ስለሆነ ሊታረም ይገባል ሲሉ ተገምጋሚዎቹ በአንድ ድምጽ ተናግረዋል::

በግምገማው ላይ ከተነሱት ጉዳዮች ሌላው ትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶችን በአዲስ አበባ ዙሪያ ማእረግ እና ሃላፊነት በመስጠት በፖሊስ ሰራዊት እና በመከላከያ ቢሮ ውስጥ ሲመደቡ የሌላው ብሄር ተወላጆች ወደ በረሃ በመወርወር በተዘዋዋሪ እየበደሉ እነ በክትትል እያሰቃዩ እስከ ሞት የደረሱ እንዳሉ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ጉዳይ ሊታይ ይገባዋል::መልቀቂያ የጠየቁ የደህንነት አባላት የሚጠብቃቸው እስር መሆኑን እያየን ነው:: የተሰደዱ አባላት በርካቶች ናቸው::የመንግስትን ይሁን የፓርቲ መረጃ የሚሸጡት የሕወሓት አባላት የሆኑ ደህንነቶች መሆናቸው ይታወቃል:; እነሱን አትንኩብን ማለት ነገ ለሚፈጠረው ችግር ተተያቂው ማነው? በሚል ጉዳይ ዙሪይ ጥያቄዎች ቢነሱም በማያረኩ ምላሾች ጉዳዮቹ ሳይገመገሙ አልፈዋል::ለሊት አጋማሽ ድረስ የዘለቀው ግምገማ ቀጣይ ሁኔታዎች ተጠንተው ድጋሚ ሌላ ግምገማ ይጠራል በሚል የበላይ ሃላፊዎች የተረጋጋ አንደበት ስብሰባው መዘጋቱን ምንጮቹ የገለጹ ሲሆን በደህንነት ክፍሉ ውስጥ አለመተማመኑ እና ክፍተት እየሰፋ መምጣቱን የስርአቱን መበስበስ ያመለክታል::

Image

• ‹‹ቀድሞውንም እንዳያማ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው ነው›› አቶ ስለሽ ፈይሳ
Image
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹እንደገና አስተካክሎ ካልላከ ለማስተላለፍ እቸገራለሁ›› በሚል መመለሱን ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ አስታወቀ፡፡

ኢብኮ አላስተላልፍም ብሎ ለመመለሱ በዋነኛነት የጠቀሰው ምክንያት ‹‹ለማጀቢያነት ለተጠቀማችሁት ሙዚቃ የባለመብቶቹን ፈቃድ ስለመኖሩ ማረጋገጫ አላመጣችሁም›› የሚል ነው፡፡ ኢብኮ ሌሎች ጉድለቶችን ያልጠቀሰ ቢሆንም በጥቅሉ ‹‹የምርጫ ህጉን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ፣ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ህጎች ወይንም ማንኛውም ህግ የሚተላለፍ መሆኑን በቂ ምክንያት ካለው መልዕክቱን አላስተላልፍም የማለት መብት አለው….›› በሲል ፓርቲው የላከውን የቅስቀሳ መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሚቸገር ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል የፓርቲው የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበር አቶ ስለሽ ፈይሳ ገዥው ፓርቲ የግለሰብና የፓርቲ ስም እያጠፋ፣ የመደራጀት፣ ሀሰብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብትን በጣሰ መልኩ ቅስቀሳ እያደረገ እንደሆነ ገልጸው ሰማያዊ ፕሮግራሙ ላይ ያስቀመጣቸውን ሀሳቦች እንዲቀይር እየተጠየቀ መሆኑ ሚዲያዎቹ ለገዥው ፓርቲ ያላቸውን ወገንተኝነት በድጋሜ ያጋለጠ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

‹‹የመንግስት ሚዲያዎች ተግባር ቀድሞውንም እንዳያማ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ነው፡፡ ቢያንስ በዚህ ጊዜ እንኳን ፍትሓዊ መሆን ነበረባቸው›› ያሉት አቶ ስለሽ የመንግስት የሚባሉት ሚዲያዎች በወንጀል ሊያስከስስ የሚችለውን የኢህአዴግ ቅስቀሳ ያለ ምንም ምርመራ እያስተላለፉ ሰማያዊ ላይ ህገ ወጥ ቅድመ ምርመራቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ኤፍ ኤም 96.3 ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ በላከው መልዕክት ላይ በማጀቢያነት የተጠቀመበት ሙዚቃ የባለ መብቱን ፈቃድ አላገኘም በሚልና መልዕክቱ ላይ የተጠቃለሉትን የፓርቲው አቋሞች እንዲያስተካክል በሚል የቅስቀሳ መልዕክቱን መመለሱ ይታወሳል፡፡

የሚመጣውን ሁሉ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው፡፡ጉዳዩን የሚያቅ፤ የበሰለ፣ ባለገድልና ባለታሪክ ሰዋችንን አንናቅ፡፡ምክር መቀበልና ማክበር ይገባል፡፡ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችልን ነገር አስቀድሞ ማሰብ፣ ማውጠንጠንና መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ብዙ አደጋዎችን፣ ብዙ ችግሮችን፣ ብዙ ውጣ – ውረዶችን ያየችው አገራችን መከራዋን ትወጣው እንጂ አብዛኛዎቹ የተከሰቱት ምክር በማይሰሙ መሪዎች ነው፡፡ የተቋጠረውን እየፈታን፣ የተዘጋ የሚመስለውን እየከፈትን፣ አደባባዩን ምሽግ ያደረገውን እየደረመስን፣ ወመቴን ከአለሌ፣ ጨውን ከአሞሌ፣ ቱሪስቱን ከፒስኮር፣ ህንዱን ከባኒያን፣ ጭልፊቱን ከአሞራው፣ የፖለቲካ ነጋዴውን ከሀቀኛ መንገደኛው፤ ለይተንና አበጥረን መጓዝ ለሀገርና ለህዝብ የሚመች አጓጓዝ ነው፡፡

የታለፉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ አጋጣሚዎች ደግመን ማጣት ከእንግዲህ ብርቱ ዋጋ ያስከፍለናልና ጥንቅቅ ብለን ማሰብ ይገባናል፡፡ የድህነት ነገር ሆኖብን ሁሌ ሥራችንን በዘመቻ እንድንሠራ እንገደዳለን፡፡ አንድን ሥራ በነጥብ መብራት አተኩረን መሥራት ትልቅ ጉልበት በማከማቸት ግብ እንድንመታ ይረዳናል፡፡ ሆኖም ዘላቂና የኔነት ስሜት ያለው ሥራ እንድንሠራ በሙያዊ ብቃት፣ በሥራ ክፍፍልና በሙሉ ስሜት እንድንራመድ ካልሆነ ለብዙ ችግር እንጋለጣለን፡፡ ጦርነትም ቢሆን እንኳ በኃይል በኃይሉ፣ በክህሎት በክህሎቱ ሲሰደር ነው ለግብ ይበቃል የሚባለው፡፡ የጋራ ጥቅም ላይ ያነጣጠሩ መስሎ የግል ጥቅምን በጐን ማሳደድ ሊነቃበት የሚገባ ጨዋታ ነው፡፡

መቼም የሀገራችን ነገር አንዱ ሲወርድ አንዱ ሲወጣ ያለበት ነው፡፡ ከሥራውም ይልቅ ሰውዬውን ለሚያይ ዘላቂነት ያለውና ያለፈውን ስህተት ለማረም የቻለ ጉዞ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ የሠራተኛው፤ የፓርቲ አባሉ፣ የበታች ኃላፊው ሁሉ፣ ሁልጊዜ “እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ ነው” የሚልበት ዘመን ያከተመ ይመስላል፡፡ “ተሰናባች አይርገምህ፤ ተተኪው አይጥላህ” የሚለውን በጥንቃቄ ካዩት ትርጉም ያለው ቁምነገር ያስጨብጠናል። ተሰናባች በግፍ፣ በምቀኝነት ወይም በአድልዎ ተባሮ ከሆነ እርግማኑ ይደርስብኛል ብሎ ማሰብ የአባት ነው፡፡ ተተኪው በተንጋደደ ዐይን የሚያይ ከሆነና “ለዚያኛው ያልተኛ እኔን አይምረኝም” ብሎ ያሰበ ከሆነም ሲሰጉ መኖር ነው፡፡ ከዚህም ይሰውረን፡፡

የሚመጣውን ሁሉ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ያለ ነው፡፡ ጣር መጣ ጦር መጣ እያሉ በጣም ያስፈራሩት ጀግና፤ በዝግታ እየተዘጋጀ፤ “ይምጣ ከመጣ ሞቼ ልጠብቀው እንዴ ልዘጋጅ እንጂ!!” አለ የሚባለውንም አንዘንጋ፡፡ ጉዳዩን የሚያቅ፤ የበሰለ፣ ባለገድልና ባለታሪክ ሰዋችንን አንናቅ፡፡ ከየቦታው ሰብስበን ሥራ ላይ እንዲቀመጥ እናድርግ፡፡ ልታይ ልታይ የሚለውንና የአደባባይ ጌጥ የሆነውን ትተን፤ ከልቡ ለሀገር የሚያስበውን እናስተውል፡፡
“ሰዎች የአስቸኳይ ጥቅምና ፍላጐታቸው ተገዢ ከመሆናቸው የተነሳ አታላይና አጭበርባሪ ሰው ከመጣ ለመታለልና ለመጭበርበር ዝግጁ ናቸው” ማኪያቬሊ

Image

Facebook

Settings
Logout

Promote
This week

21,736Page Likes

361,488Post Reach

31Contact Us

Unread

99Notifications
245Messages

Recent
2015
2014
Started

See Your Ad Here
Mereja
ወገኔ በል ስማኝ አገሬ:#Ethiopia አንድነት ይበጀናል ዛሬ:: ብርሃኑ ተዘራ እና ጃኪ ጎሲ ግጥም ብርሃኑ ተዘራ – ዜማ ታማኝ በየነ Bir…
Like Page
Boost Post
PageMessages99+Notifications99InsightsPosts
Settings
Help
Cover Photo
Change Cover
Mereja
Update Profile Picture
Mereja
News/Media Website
Contact Us
Share
More options

TimelineselectedAboutPhotosLikesMore

People
354,430 likes
Promote Your Page
Connect with more of the people who matter to you
Promote Page
About
MEREJA.COM
Promote
http://www.mereja.com/
Photos
‘የሕብረት ሱቅ ሸመታ እንደ ደርግ ጊዜ በመቀሌና በደሴ #Ethiopia #Photos #Dessie #Mekelle @[473395172745422:274:Millions of voices for freedom – UDJ] ዶር ቴዎድርሶ ዳኖችም ከፈረንጆች በልምና የተገነቡ አንዳንድ ፕርሮጀክቶችን እና አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ቱጃር የሆኑ ያሰሯቸውን ፎቆች በማሳየት “ብሩህ ዘመን ከኢሕአዴግ ጋር” ሲሉ ነበር የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ያተኮሩት። ሆኖም የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ በማስጠበቅ ሕዝብን ያላማከለ የተሳሳት የሕወሃት የኢኮኖሚ ፖሊሲ አገሪቷን ወደ ከፍተኛ የኑሮ ዉድነት ቀዉስ ዉስጥ እየከተታት ነው። ሕወሃት የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል ይልቅ ቅድሚያ የሰጠውና በርካታ ንዋይ እያፈሰሰ ያለው በማይረቡ ጉዳይ ነው። 1. ሕዝቡን የሚያሰጨንቁና የሚያሸበሩ እጅግ በጣም ሰፋፊ የስለለ መረብ ለመዘርጋት ሕወሃት ብዙ ገንዘብ ያወጣል። 2. የ2007 ምርጫ ቁም ነገር የሌለዉን እና የዉሸት ከንቱ የምርጫ ድራማ ነው። ለዚህ ቀልድድራማ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ይወጣል። 3. የብሄረሰቦች ቀን፣ የመከላከያ ቀን፣ የህወሃት ምስረታ ቀን ፣ ግንቦት ሃይ .. እያለ፣ ቁጭ ደርግ በመስከርም 2 ያደርግ እንደነበረ፣ ዳንኪራና ሰልፎች እያየን ነውልል ለነዚህ በዓሎች በመቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ወጭ ይሆናል። የአገራችን ህዝብ ግን በኑሮ ዉድነት በጣም እየማቀቀ ነው። ሲነግሩን የነበረው ሞሎች፣ ትላልክ ሱፐርማርኬቶች እየተገነቡ፣ አገራችን ትልቅ ደረጃ እየደረሰች እንደሆነ ነው። ሆኖም የሚገነቡት ዘመናዊ ሱፐር ማርኬቶች ፣ ብር ያላቸው ባለስልጣናት፣ የዉጭ አገር ዜጎች፣ የውጭ ድርጅት የሚሰሩ ብቻ የሚገቡበት እንጂ 99% በመቶ የሚሆነው ህዝብ ዝር የሚልባቸው አይደሉም። ሕዝቡ ዘይት ሆነ ሌሎች ለኑሪ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከቀበሌ ሕብረት ሱቅ ለመግዛት፣ በደርግ ጊዜ እንደነበረው አሁንም ለሰዓታት እየተሰለፈ ነው። በመቀሌና በደሴ የሕዝቡን ችግር የሚያመላክቱ ፎቶዎች ይመለከቱ !’
‘የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ (በጴጥሮስ አሸናፊ) አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ አኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው? የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር ። የበርካታ ወገኖቹን የብሶትና የግፍ መልዕክት ይዞ በስዊዝ አየር ላይ የሚያንዣብበው ሃይለመድህንም “ለጊዜው የምፈልገው የስዊዝ መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጠኝ ፣ ለኢትዮጵያ መንግስትም ተላልፌ እንዳልሰጥና አውሮፕላኑን ጄኔቫ ላይ በሰላም ማሳረፍ ነው” የምትል ቅልብጭ ያለች ቃል ነበረች። በሁለቱም በኩል የተለያዩ መረጃዎችን ከተለዋወጡ በዃላ አውሮፕኑን ማሳረፍ እንደሚችል የተፈቀደለት ሃይሌም በተካነው ልዩ የማብረር ችሎታ ካለምንም ኮሽታ አውሮፕላኑን ጄኔቫ ክዋንትራን አየር ማረፊያ 202 መንገደኞችንና የበረራ ሠራተኞችን እንደያዘ በሰላም አሳርፎ ፤ እሱም “ያልጠረጠረ” የምትለዋን ብሂል ቋጥሮ ይዟት ነበርና በመስኮት በኩል በገመድ በመውረድ ለስዊዝ የደህንነትና ፖሊስ አባላት እጁን በሰላም በመስጠትና ቃሉንም ለማስመዝገብ ወደሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት አመራ። ሃይለ መድህን የአውሮፕላኑን የበረራ ሃላፊነት በብቸኝነት ከተቆጣጠረ ጀምሮ ከስዊዝ ፖሊሶች ጋር በአካል አስገተገናኘበት ጊዜ ደረስ ያደረጋቸውን በሙሉ በአፅንኦት የተከታተሉ አንድ አሜሪካዊ የቀድሞ ፓይለትና አሁን ደግሞ የግል የበረራ ተቋም ባለቤትን እንዳስደመማቸው እንደገለፁለት ወዳጄ ጋዜጠኛ አበበ ገላው አጫውቶኛል። ከዚያስ ፧ ከዚያ በኳላማ የአለም ታላላቅና ታናናሽ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች ዋና ዜና ሃይለመድህንና የተጠለፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሆነ። የቴሌቪዥን መስኮቶች በሃይለመድን ምስሎች ተሞሉ ፣ ሬድዮኖች ደጋግመው ደጋግመው ስሙን ያነሳሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች እነ ፌስቡክና ትዊተር ስለ ሃይለመድህን በሚያወሱ ወሬዎች ኮሜንት ፣ ላይክ ፣ ሼር እና ሪትዊት ስራ በዝቶባቸው ነበር። በአራቱም መአዘን የሚገኙ የጦቢያ ልጆች ቀፏቸው እንደተነካባቸው ንቦች ተነሱ። ሃይለመድህን ነፃ ይሁን የሚሉ ድምፆች ማስተጋባት ጀመሩ። ” ነፃ ሃይለመድህን ” የሚል አለም አቀፍ አስተባባሪ ግብረ ሃይል ተቋቋመ ፣ ሰላማዊ ሰልፎች በመላው አለም በከፍተኛ ድምቀት ተካሄዱ ፣ በሃይለመድን ስም ድረ ገፅና የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ተከፈቱ ፣ “ሀይለመድህን ብሔራዊ ጀግናችን ነው” የወቅቱ መሪ መፈክርም ሆነ። አዎ! ሕወሓት በሚከተለው ዘረኝነትንና ጠባብነትን መርህ ባደረገው የፖለቲካ አመራሩ ምክንያት ሠርቶ መብላት ላልቻለው ፣ በስደት ምክንያት በበረሃ አውሬና በባህር አሣ ለሚበላው ፣ ከሐገር ቤት አልፎ የሌሎች ሐገራትን ወህኒ ቤቶችን ለሚያጨናንቀው፣ የእምነት ተቋሙ ተደፍሮ ሲኖዶስና መጅሊስ ለሚመረጥለት፣ የእምነት አባቶችም በአባይ ፀሐዬ በኩል ለሚሾምለት፣ በሃገር ቤት ለመኖር ለመረጠም በገዛ ሀገሩ የሁለተኛና ሦስተኛ ዜግነትን ተቀብሎ እንዲኖር ለሚገደደውና ከፈጣሪ የተሰጠውና በአለም አቀፍ ተቋማት የተደነገገውን ኢትዮጵያም የተቀበለቻቸውንና የፈረመችባቸውን ሰብአዊ መብቶቹን ለተገፈፈው ኢትዮጵያዊ እንደ ሀይለመድህን አይነት ብሶቱን በአለም አደባባይ የሚያሳይለትና የሚያጋልጥለት ሲያገኝ እንዴት ብሔራዊ ጀግናው አያደርገው! እንደ መንግታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ዋና መስሪያ ቤት (UNHCR) መረጃ በፈረንጆቹ 2013 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ብቻ ከአርባ ሁለት ሺህ (42,000) በላይ ኢትዮጵያውያን ስደት ጠይቀዋል ። በውጭ መንግተስታት ዘንድ በተለይም እርዳታ በሚለግሱት ምእራባውያን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት አክባሪ መስሎ ለመታየት የሚዳዳው የሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት የደረሰበትን ፖለቲካዊ ኪሳራ ሂሳብ ለማወራረድ “ሀይለ መድህን የአእምሮ በሽተኛ ነው” የሚል ዘመቻ ቢጀምርም ወንዝ ሊያሸጋግረው አልቻለም ። በመቀጠል ህወሓት የወሰደው ርምጃ የመንግሥት ባለስልጣናትን ወደ ስዊዝ በመላክ የስዊዝ ባለሥልጣናትን አግባብቶና አሳምኖ ሀይለመድህንን ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ መሞከር ነበር (የየመን መንግሥት በነፃነት ታጋዩ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ያደረገውን እዚህ ላይ ማስታወሱ ተገቢ ነው) የስዊዝ ባለሥልጣናት ግን በፍፁም አይሞከርም የሚለው ቃል መልሳቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ሕወሓት የስዊዝ መንግሥት ባለሥልጣናትን ለማስፈራራት ይመስላል አንድ ከፍተኛ የህወሓት አባልና የመንግሥት ባለሥልጣን በድጋሜ ወደ ስዊዝ ላከ። የተላኩትም ሰሞኑን ከአንዲት የ14 አመት በአውስትራሊያ ነዋሪ ከሆነች ትውልደ ኢትዮጵያዊት “በሽልማት ያገኘችውን ” 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ተረከብኩ ያሉት የፌስቡክና ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴድሮስ አድሐኖም ነበሩ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2014 ዓ/ም። ስዊዞቹም እንኳን አንተና ባለራእዩ መሪያችሁ አፈሩን አራግፎ ቢመጣም ወይ ፍንክች አሏቸው መሰለኝ የፌስቡክ ሚንስትሩ ወደመጡበት ለመመለስ ሻንጣቸውን ከሸከፉ፣ ጠባቂዎቻቸውና አጃቢዎቻቸውን በቦታቸው መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ ለመውጣት ሲዘጋጁ ከፕሮቶኮላቸው አንዱ ጠጋ ብሎ አንድ ነገር ሹክ አላቸው ። ቴድሮስ አድሐኖም የስዊዝ ባለሥልጣናትን ከሚያነጋግሩባት የስዊዝ የመንግሥት መቀመጫ በሆነችው በርን ከተማ ላይ ከሚገኘው መሥሪያ ቤት በቅርብ ርቀት ለጀግናው ሀይለመድህን ፍትህና ነፃነትን የሚጠይቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፈኞች ስላሉ ፣ ከመሥሪያ ቤቱ ሲወጡ እንዳያገኟቸው ጥንቃቄ እንዲደረግ ነበር የፕሮቶኮሉ መልእክት ። ሰኔና ሰኞ የተገጣጠሙባቸው የማርክ ዙከርበርግ ቋሚ ደንበኛ ( valued customer) ቴዲ በከፍተኛ አጀባና ጥንቃቄ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በሌሉበት አቅጣጫ አፈተለኩ። መቼም የፌስቡክ ደንበኛ ሆኖ መስራቹንና ባለቤቱን አሜሪካዊውን ማርክ ዙከርበርግን የማያውቅ የለም። ይኸው ለነ ቴድሮስ አድሐኖም ምስጋና ይግባና በያዝነው ሳምንት ፎርብስ መጽሔት ይፋ ባደረገው የአለማችን ሀብታሞች ደረጃ መሠረት ዙከርበርግ በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ሃያዎቹ ቱጃሮች ውስጥ በመግባት የአለማችን 16ኛው ሃብታም ለመሆን ሲችል የሀብቱም መጠን 33.4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ። ድሮስ የተሰጣቸውን ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ገፋ በማድረግ አብላጫ ጊዜያቸውን ፌስቡክ ላይ ፎቶ ሲለጥፉ የሚውሉና የሚያድሩ እንደ ቴድሮስ አይነት ደንበኞችን ይዞ እንዴት ገቢው አያድግ! የስዊዘርላንድ መንግሥት ተወካዮች ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር ስላደረጉት ተደጋጋሚ ውይይት ፣ ከኢትዮጵያውያንና ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች እንዲሁም ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሚደርሷቸው ጥያቄዎች ጠቅለል ያለ መልሰ ለመስጠት ያስችላቸው ዘንድ ሜይ 9 ቀን 2014 ዓ/ ም ለመንግሥት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። በመግለጫቸውም: የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ተላልፎ እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ፣ ወደፊትም ተላልፎ የሚሰጥበት ሁኔታ እንደማይኖር ፣ የፍርድ ሒደቱን በስዊዝ ፍርድ ቤቶች ችሎት እንደሚታይ፣ የስዊዝ መንግስትም የህግ ከለላ እንደሚያደርግለት፣ ያቀረበውም የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ከፍርድ ሂደቱ መጠናቀቅ በኋላ እንደሚታይና አዎንታዊ መልስም እንደሚኖረው ( በስዊዝ ረዘም ላለ ጊዜ ለመኖር የሚያስችለውን ፈቃድ እንደሚያገኝ) አስረግጠው ተናገሩ ። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የሀይለመድህን ጠበቆች ቡድን መሪ ዶ/ር ፊሊፕ ኩራ ( እሳቸው እንኳን ይችን ዶክተር መባል አይፈልጓትም የተገዛች ስላልሆነች ነው የተጠቀምኩባት) የስዊዝ መንግሥት ያሳለፈው ውሣኔ ተገቢ የሆነና ትክክለኛ መሆኑን ገልፀው አንድ ተከሳሽ በተመሳሳይ ክሶች በሁለት የተለያዩ ሃገሮች ችሎት ፊት ይቅረብ የሚል አለም አቀፍ ሕግም እንደሌለ ተናግረዋል ። በድፕሎማሲው መንገድ እንዳልተሳካላቸው የተረዱት እነ ጭር ሲል አልወድም አዲስ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል አሉ። ይሄኛውስ ምንድነው? ይሄኛውማ ሀይለመድህን ባይኖርም በሌለበት ( in absentia) ሞት፣ የእድሜ ልክ እስርና ሌሎችንም ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አለም አቀፍ ዝናን ባተረፈው ፍርድ ቤታችንና የፍትሕ ስርአታችን አቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበት እንዲያስፈርድበት እናደርጋለን የሚል ነበረ። ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ሁለት ሲሆን፤ የመጀመሪያው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 507/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡- ‹‹…በዋና አብራሪ ፓትዮዝ ባርቤሪ አማካኝነት ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል ወደ ጣሊያን ሀገር ሮም ከተማ መንገደኞችን ለማድረስ በማጓጓዝ ላይ እንዳለ ዋናው አብራሪው የበረራ መቆጣጠሪያውን ክፍል ከውስጥ በመቆለፍ፣ ያለፍቃድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ አውሮፕላኑን በቁጥጥር ሥር በማድረግ የአውሮፕላኑ የበረራ ቡድን አባላት በሩን እንዲከፍት ሲጠይቁት አርፋችሁ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ በማስፈራራት፤ እንዲሁም የአውሮፕላኑን የመዳረሻ አቅጣጫ ያለአግባብ በማስቀየር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈቃድ ውጭ ወደ ስዊዘርላንድ አየር ክልል ውስጥ በመግባት ተሳፋሪዎች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ሕይወት እና ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አድርጎ በመጨረሻ በጄነቭ ከተማ ውስጥ ያለመዳረሻው እንዲያርፍ በማድረጉ እና ተሳፋሪዎችን ለአደጋ በማጋለጡ በፈፀመው በሕገ-ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን መያዝ ወይም ማገት›› የተከሰሰ መሆኑን ያትታል፡፡ በሁለተኛነት ክስ ደግሞ በዚሁ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 508/1/ ላይ ያለውን መተላለፍ የሚል ሲሆን፤ ክሱም በአጭሩ እንዲህ ይላል፡- ‹‹…ያለፍቃድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ አውሮፕላኑን በቁጥጥር ሥር በማድረግ የአውሮፕላኑ የበረራ ቡድን አባላት በሩን እንዲከፍተው ሲጠይቁት አርፋችሁ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት በማስፈራራት አውሮፕላኑን በድንገት እና በፍጥነት ሁለት ጊዜ ከፍ እና ዝቅ (dive) በማድረግ በአውሮፕላኑ ውስጥ ያሉትን የመንገደኞች ምግብ ማቅረቢያ ቁሳቁሶች እንዲገለባበጡ በማድረግ፣ የአውሮፕላኑን የመዳረሻ አቅጣጫ ያለአግባብ በማስቀየር፣ ከአትዮጵያ አየር መንገድ ፈቃድና እውቅና ውጭ ስዊዘርላንድ አየር ክልል ውስጥ በመግባት ስዊዘርላንድ ከተማ ጀኔቭ በመግባት አየር ላይ በማንዣበብ ከቆየ በኋላ እንዲያርፍ በማድረግ በፈፀመው በሕገ-ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን አስጊ ሁኔታ ላይ መጣል ወንጀል ተከሷል፡፡›› ይላል ። በፌ/አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ ፊርማ ለፍርድ ቤቱ የቀረበው ማመልከቻ ከስ ቻርጁን ጨምሮ አስራ አንድ ገፅ ሲሆን፤ የዋና አብራሪው፣ የአምስት የበረራ አስተናጋጆች እና የአራት ሰዎች ስም ዝርዝር በመስክርነት ተገልፆአል፡፡ በሰነድ ማስረጃነት ደግሞ አየር መንገዱ በ27/6/06 ዓ.ም ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የጻፈው አራት ገጽ እና ሲቪል አቬየሽን በ21/6/06 ኃይለመድንን በተመለከተ የጻፈው ማብራሪያ ከነአባሪው ሁለት ገጽ ቀርቧል፡፡ የኃይለመድን አበራን የጤንነት ሁኔታ በተመለከተ አየር መንገዱ ለፌደራል ፖሊስ በላከው ደብዳቤ በስድስት ወር ውስጥ አምስት ጊዜ ያህል ለቀላል ሆድ ቁርጠት፣ ራስ-ምታት፣ ጉንፋንና ተቀምጥ ወደ ድርጅቱ ክሊንኪ ከመሄዱ ያለፈ ምን ችግር ያሌለበት ጠኔኛ እንደሆነ ገልፆአል፡፡ ሲቪል አቬሽንም በተመሳሳይ መልኩ በላከው ደብዳቤ አብራሪው አመታዊ የጤና ምርምራ አድርጎ እ.ኤ.አ. እስከ 22/12/2014 ዓ.ም ድረስ ጤነኛ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፍኬቱን አድሶ እንደሰጠው አስታውቋል፡፡ ( እዚህ ላይ በመጀመሪያ መንግሥት ኃይለመድህን የአእምሮ በሽተኛ ነው ብሎ እንደነበር ልብ ይሏል) አየር መንገዱ ከዚሁ ጋር አያይዞ ሁለት መቶ ሀምሳ ሶስት ሺህ፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከአራባ ሁለት ሳንቲም (253,336.42) ዩሮ ኪሳራ እንደደረሰበት እና በቀጣይም ተጨማሪ ክፍያዎች እንደሚኖሩበት አሳውቋል፡፡ ህወሓት/ ኢሕአዴግ ራሱ ከሣሽ ራሱ ፈራጅ ሆኖ በሚተውንበት የፍርድ ቴአትር ቤት መታየት የጀመረው ድራማ የተጠበቀውን ተመልካች ማግኘት ካለመቻሉም በላይ የክሱም ስክሪፕት በጥሩ ፀሀፈ ተውኔት ስላልተፃፈ ቴአትሩን ለማየት ለታደሙትም ታማኝና ጥቂት የስርአቱ ልማታዊ ደጋፊዎችና ጋዜጠኞች የእንቅልፍ መድኃኒት ሆነባቸው ፣ አለም አቀፍም፣ ሐገር አቀፍም፣ ልማት አቀፍም ትኩረት አጣ። አዲሱ ትኩረት መሳቢያ ቴአትር —————————————- ባሳለፍነው ሳምንት አውሮፕላን የተጠለፈበትን አንደኛ አመት ለማሰብም ይመስላል ሕወሓት አዲስ ዘዴ አግኝቻለሁ ይላል። አዲሱ ዘዴ የተባለው ምንድነው ቢሉ፣ ኢንተርፖል በሚባል የአለም አቀፍ ፖሊስ ተቋም በኩል “ሀይለመድህን አበራ የሚባል ረዳት አውሮፕላን አብራሪዬ ጠፍቶብኛልና እባካችሁ ያያችሁ” የሚል የተማፅኖ ጥሪ ማሰማት ነው። በዚያውም የኢንተርፖል አባል መሆኔን እወቁልኝ ነው። “የኢንተርፖል አባል መሆን ብርቅ ነው እንዴ? ” አለ አሉ ይህን የሰማው ኮንስታብል ዶክሌ። ወደው አይስቁ ! ለማንኛውም “ረዳት አብራሪዬን ያያችሁ” ለሚለው በኢንተርፖል በኩል ለተሰራጨው ቀይ ማዘዣ( Interpol red notice) የመጀመሪያውን መልስ የሰጠችው ስዊዝ ነች ” አዎ እኔ አይቻለሁ እንቁልልጬ አይነት መልስ ። ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 27 ቀን 2007 ዓ/ም በፈረንሳይኛ ቋንቋ ለሚታተመው “ለ ማታ” (Le Matin) ጋዜጣ አስተያየታቸውን የሰጡት የሀይለመድህንን ጉዳይ የሚያየው የኮንፌዴሬሽኑ አቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ጃኔት ባልመር “ለኢንተርፖል ተላልፎ ይሰጣል ወይ? ለሚለው ጥያቄ በፍፁም አይሆንም አይሞከርም ነው መልሴ ብለዋል ። ጃኔት ባልመር ይቀጥላሉ ” የ31 አመቱ ሀይለ መድህን በአሁን ጊዜ ስዊዝ ውስጥ በሕግ ጥላ ስር ይገኛል። በፍርድ ቤትም ጉዳዩ እየታየ ነው። በኢትዮጵያም ከአለም አቀፍ የሕግ ሂደት ባፈነገጠ ሁኔታና በስዊዝ ችሎት መቅረቡ እየታወቀ ክስ እንደተመሠረተበት ፣ እኛም አሳልፈን እንደማንሰጠው አሳውቀናል ። ኢንተርፖልም የቀይ መያዣ( ማሳሰቢያ) ጥሪውን ያስተላለፈው በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ መሆኑን አሳውቋል ። ” ይላሉ። የሀይለመድህን ጠበቃ ፊሊፕ ኩራም ለዚሁ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ” የኢትዮጵያ መንግሥት ሀይለመድህንን በይፋ ” ከሐዲ ” ብሎ ፈርጆታል ። በመሠረታዊውን የፍትህ ስርአት (fundamental rule of law) “አንድ ሰው በተመሳሳይ ክስ በሁለት የተለያዩ ችሎቶች መቆም የለበትም” የሚለውን በመፃረር ከኛም እውቅና ውጪ በሌለበት ለመክሰስ ወስኗል ። በምን አይነት መልኩ ነፃ በሆነ የፍርድ ሂደት ጉዳዩ እየታየ እንደሆነም እኔ በበኩሌ የማውቀው ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውጤት አልባ የማሰናከያ ቀመሮችን እየፈጠረ ነው ” ይላሉ ። የአቃቤ ሕጉ ቃል አቀባይ ጃኔት ባርመር “ለኢትዮጵያ መንግስት የአፀፋ መልስ የለንም። ለመንግስታችን የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ያቀረበው የሀይለመድህን አበራ የፍርድ እጣ እዚሁ በጥሩ ሁኔታ ይወሰናል ። በርግጥ የፍርድ ሂደቱ ብዙም አልገፋም። ክፍት ችሎቶች የሉም። ምርመራዎች እንደቀጠሉ ናቸው ። ጉዳዩ ገና በምርመራ ላይ ያለ ስለሆነ ከዚህ በላይ ብዙ መናገር አልችልም ” ብለዋል ። ጠበቃ ፊሊፕ ኩራም “ሀይለ መድህን በጣም ደህና ነው ። ስለ ፍርድ ሂደቱም መናገር የምችለው: እንዲህ መጓተቱ የተለመደ ባይሆንም ከንብረት ጋር የተያያዙ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ ሐገሮች ለማግኘት ስንሞክርና መልስ ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ መውሰዱ ነው። ልዩ ወደሆኑት ቴክኒካዊ መረጃዎች ስንመጣ ይህም ራሱን የቻለ የቴክኒክና የሳይንስ ምርመራ ይጠይቃል። በመጨረሻም የኮንፌዴሬሽኑ የህዝብ አቃቤ ሕግ በመርህ ደረጃ 202 መንገደኞችን በሙሉ የሚያነጋግር ሲሆን አሁንም ከተሳፋሪዎቹ ስለራሳቸው መረጃዎችን እየጠበቀ ይገኛል ። ” ብለዋል የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ጉዳይ ከፌብሩዋሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ የነበረውን የአንድ አመት ጉዞ ባጭሩ ይሄን ይመስላል። ሀይለመድህን አበራ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ኦገስት 30 ቀን 1983 ዓ /ም በጣና ሃይቅ ዳርቻ በምትገኘው ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ተወልዶ ያደገ ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በመጋቢት 28 ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ ባህርዳር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል። ከፍተኛ ትምህርቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል በመከታተል ላይ እያለና ለማጠናቀቅም አንድ ሴሚስተር ብቻ ሲቀረው በማቋረጥ ከልጅነት ጀምሮ ይመኘው የነበረውን የበረራ ትምህርት ለመከታተል የኢትዮጵያ አየር መንገድን የበረራ ት/ቤት ተቀላቅሏል። ፌብሩዋሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም አውሮፕላኑን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ እስካሳረፈበት ጊዜ ድረስ በአየር መንገዱ በረዳት አብራሪነት አገልግሏል። ከከጠለፋውም በኋላ የአየር መንገዱ የበረራ ክፍል ሃላፊ የነበሩት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ከሥራቸው መልቀቃቸው ይታወቃል ። በመጨረሻም በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር ሐይል አባላት የሆኑ መኮንኖችና የበረራ ቴክኒሺያኖች በተለያዩ አቅጣጫዎች ሥርአቱን እየከዱ በመጥፋት ላይ መሆናቸውን እያየን ነው። በተለይም ወደ ጎረቤት ሐገር የኮበለሉት አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው መሆኑንም ራሱ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎቹ አረጋግጦልናል ። ከ25 እስከ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ሄሊኮፕተር እና ለስልጠና ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰባቸውን የበረራ ባለሙያዎችን ያጣውና በማጣት ላይ ያለው ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይና አመራሮቹ ረዳት አብራሪ ሀይለ መድህን አበራ ብቻ ገበናቸውን የገለጠባቸው ለማስመሰል ወደ ምእራባውያን ሐገሮች ባለሥልጣናቱን መላክና ኢንተርፖልን ደጅ መጥናት ውሀ አያነሳላቸውም። ምነው ዶ/ር ቴድሮስ በነካ እጅዎ ወዳደጉባትና ወደተማሩባት ኣስመራ ጎራ ብለው የሄሊኮፕተሯንና የበረራ ባለሙያዎቿን ጉዳይንም ቢመክሩባትስ? ከስዊዝስ ኣስመራ አትቀርብዎትም?’
‘ምርጫ በኢትዮጵያ ምን ይመስላል? (ገለታው ዘለቀ) በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ የተጀመረው እንደ ኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ1957 በዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ሲሆን በ1955 የወጣውን ህገ -መንግስት መሰረት ያደረገ ንጉሱንና የላይኛውን ቤት ወይም ሴነቱን የማይመለከት ነገር ግን የተወካዮች ምክር ቤት ኣባላትን መምረጥ ተጀምሮ ነበር። እማኞች ሲነግሩን ምርጫውና ቆጠራው ግን ሃቀኛ ነበር ኣሉ። ታዲያ ንጉሱ በነበሩበት ዘመን የነበሩት ምርጫዎች ጅማሪያቸው መልካም ቢሆንም ዓለም በማህበራዊ ለውጥ ላይ በነበረችበት በመጨረሻው ሰዓት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወ

ወገኔ በል ስማኝ አገሬ:‪
አንድነት ይበጀናል ዛሬ::
ብርሃኑ ተዘራ እና ጃኪ ጎሲ
ግጥም ብርሃኑ ተዘራ – ዜማ ታማኝ በየነ
Birhanu Tezera ft. Jacky Gosee – ወገኔ (Wogennee)

Please wait, video is loading…

ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ

በአበበ ገላው@ አዲስ ቮይስ
Image
ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር። ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።

በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።

ፖሊሶች “ያልተፈቀደ ስብሰባ” ነው በለው በተኗቸው:: ‪
ይህ የምታዩት ቪዲዮ (መክስተ ምስል) ዛሬ የአድዋን በዓልን አያከበርን ባለበት ወቅት እድሜአቸው ከ10-16 የሚሆኑ ህፃናት እንደ አባቶቻችን ሽለላና ቀረርቶ እያሰሙ እያለ ፖሊሶች “ያልተፈቀደ ስብሰባ” ነው በለው በተኗቸው …ሰዉ ቢቃወምም በሃይል በተኑን…..ግን ለምን?? በአሉ የነሱስ አይደለም እንዴ????? እረ ምን ጉድ ነው::

Please wait, video is loading…

Image
እንኳን ለአንድ መቶ አስራ ዘጠነኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
ዋ!….ያቺ ዓድዋ
ዋ!….
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ….
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመሰዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና….
ዋ !
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስርዋ
የኢትዩጵያነት ምሰክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው -እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው-በለው-በለው-በለው !
ዋ !…ዓድዋ…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ ፥ በለው -በለው !
ዋ !….ዓድዋ….
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና ።
….ዋ!….ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የእለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…..
የካቲት – (፲ ፱ ፻ ፷ ፬- ዓድዋ )
እሳት-ወይ-አበባ
ከጸጋዬ-ገብረ-መድኅን


Minilik Salsawi – የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንከኖቻችን ጥቅል ውጤት ማስጨነቁና ማሳሰቡ የሀገርና የህዝብ ስሜት ላለው ሁሉ አይቀሬ ነው፡፡በሃገር ቤት ማናቸውንም የጥፋት ድርጊት የሚፈጽሙ ወገኖች ለሀገር እንደቆሙ፤ የህዝብ ልጆች እንደሆኑ አድርገው መጮሃቸውና ሀቀኛ መምሰላቸው፤ ሌላው እንዳይናገር በር ይዘጋል፡፡ በበፊት ስርአቶች የእጅእላፊ አሊያም ጉቦ እንዲሁም ብዝበዛ ይባል የነበረው የምዝበራና አገርን የማራቆት ተግባር፣ ዛሬ ሙስና የተባለውን ፤ በልማት እና ትራንስፍሮሜሽን ሲስተም ሃገር የሚያደማ እና የሚያቃጥል ሆኗል፡፡ አገር ትልቅ ለውጥ ላይ ናት፤ ከፍተኛ የትራንስፎርሜሽን ሂደት ላይ ነን እየተባለ፤ በተጭበረበረ የፖለቲካ እና በቅጥር ቁልል የኢኮኖሚ እድገት ፕሮፓጋንዳ እየማሉ በጐን የዝርፊያ የኮንትሮባንድ እና በአንድ ጀንበር ፎቅ ሠርቼ ልደር ዘመናዊ ምዝበራ ይታያል፡፡ ከፖለቲካ እና ፖለቲከኞች የተጠጋጉ ሁሉ በአንዴ ዘጋ/ዘጋች ዛሬ በኢትዮጵያ የተለመደ ቋንቋ ነው፡፡ እንደአንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች ዐይንያወጣ የቀን ተቀን ዘረፋ የሚመጣው ከላይ እስከታች እየተወሳሰበ ያለው ሙስና ፍፁም ወደፈጠጠ ደረጃ ሲደርስ ነው፡፡

አንድም ሙስናው በየአቅጣጫው መሆኑ፤ አንድም ደግሞ ቢሮክራሲያዊ መጠቅለያ መኖሩ እጅግ ሊፈታ በማይችልበት ደረጃ ውስብስብ አድርጎታል፡፡በዚህ ላይ የወያኔ ግለሰቦች አሻጥር ተደምሮበት፣ ከቁጥጥር ውጪ ወደሆነ ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ የኢትዮጵያውያን በሃስት ክስ በየእስር ቤቱ መታጎር፣ የመሬት አሰቃቂ አወሳሰድ፣ ከፍተኛ የኮሚሽንና የድለላ ሥራ፣ አደገኛ ወገናዊ አሠራር…በአስደንጋጭ የድህነት መቀመቅ ውስጥ ያለችውን አገር ከምትሸከመው በላይ ትከሻ አጉብጥ ሸክም ጭኖባታል፡፡ወያኔ ኢትዮጵያን እያቃጠለ ከኔ ጋር ብሩህ ተስፋ እያለ ያብዳል::በትንሹም በትልቁም ነገር ከማበድ ይሰውረን፡፡ የመሞቻ መሣሪያ ከማማረጥ ያድነን፡፡ያኔ በደርጉ ዘመን በሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የሕዝብ ገንዘብ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የሚለው የዜና ሐረግ ነበር ሬዲዮንና ቴሌቪዥን ያጣበበው፡፡ ዛሬ በወያኔው ስርአት ዳር እስከዳር በየሰው አፍ የሚወራ ነገር ሆኗል፡፡ ዝርፊያው ዓይነት በዓይነት ሆኗል፡፡ የአንድ ሰሞን ሕዝብ ማዘናጊያ እና ሆያሆዬ ዘገባ ተወርቶም በቀላሉ ይረሳል፡፡ለህዝብ የማይሳሳው የማይጨነቀው ወያኔ ለህብረተሰብ ቀጥተኛ መጥፊያ የሚሆኑ እንደመድሃኒት ያሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ባመቸው መንገድ ሁሉ ተበርዘው ከተባዙ፣ ምን ያህል አሰቃቂ የሆነ ዕልቂት እንደሚያስከትሉ መገመት አያዳግትም፡፡ የሚያስገኙት ገንዘብ የትየለሌ፣ የሚፈጁት ህዝብ የትየለሌ!!ይህንን ስርአት በማስወገድ ራሳችንን ነጻ አውጥተን ሃገርን እና ወገንን ማዳን የዜግነት ሃላፊነት መሆኑን ልናውቅ ይገባል::

ሃገራችን እና ወገናችን በጨለማ ውስጥ እየዳከረ ባለበት በዚህ የወያኔ አገዛዝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በመረባረብ የዜግነት ግዴታውን አውቆ ለህዝቦች መብት እና ነጻነት መታገል አለበን። ሃገሪቷ በዚህ አደጋ ውስጥ ባለችበት ሰአት ላይ ህዝብ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ለኑሮ ውድነት ለሞት ለስደት እየተዳረገ ኢትዮጵያዊነት እየተዋረደ ከመሆኑም ባሻገር ኢትዮጵያን እያቃጠለ ከኔ ጋር ብሩህ ተስፋ እያለ የሚያጭበረብረውን ወያኔን ከስሩ መንግሎ በመጣል በመቃብሩ ላይ የህዝብን ነጻነት ማረጋገጥ አሌ የማይባልበት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን በማወቅ ከትግሎ ጎን አቅማችን በሚችለው ሁሉ በመቆም ነጻነታችንን ማረጋገጥ ግድ ይለናል::

– ምርጫ በመጣ ቁጥር እንክብካቤው ሰልችቶናል::ህክምና አተን ስንገላታ መች ደረሳችሁልን::የአዊ ነዋሪዎች
– የመኢአድ አመራሮች ከወያኔ የምርጫ ሜዳ ራሳቸውን እያወጡ ነው::ድርጅቱ ምርጫውን ጥሎ ይወጣል::

‪#‎Miniliksalsawi‬ – በምእራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን በማዳበሪያ እዳ ምክንያት ፓሊስና የወረዳው አመራር ያለ ፍቤት ትእዛዝ ቤታቸውን እየፈተሸ ከብት ንብረታቸውን እየዘረፉ መሆኑን አንድ ወዳጀ አሁን አስታውቆኛል።አርሶ አደሮቹንም ወደ ማጎሪያ እስር ቤት እየከተቱዋቸው ነው።

ጉልበት ያለውም ቤተሰቦቹን ይዞ በመሰደድ ላይ ነው እንደ ታማኝ ምንጮች ገለፃ ህዝቡ በጣም ተማሯል::።ከ50 ሰዎች በላይ እንደታሰሩ ከአንድ ቀበሌ ብቻ “የርግን” ከምትባል ቀበሌ ለጊዜው ቁጥራቸው የማይታወቁ ሰዎች ሀገር ጥለው ሸሽተዋል::አንድ “ወገዳድ”በሚባል ቀበሌ የሚኖር ሰው እስር ቤት ክቆየ በሁአላ እንደወጣ በድብደባ ብዛት መሞቱ ታውቋል::
የታሳሪዎች ስም:-
1.አርሶ አደር ወርቄ
2. ” አዝመራው
3. ” ስለሽ

የመኢአድ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኢንጅነር ሽፈራዉ ከምርጫዉ ራሳቸዉን ያገለሉበትን ምክንያት አሳወቁ::
የሰሜን ቀጠና ሃላፊ የሆኑት ኢንጅነር ሽፈራዉ ሑሉንም ነገር ወያኔ በተቆጣጠረበት በምርጫ መሳተፍ ለአባገነንነቱ ሕጋዊ እዉቅና ከመስጠት ባሻገር ሰላማዊ ትግል እየተባለ ሕዝብን ከወዲሁ ዉጤቱ በታወቀ ላይ ማድከም እና ሌሎች የሰላማዊ ትግሎች ላይ እንዳያተኩር ማዘናጋት በመሆኑ ነው ብለዋል:: ኢንጅነር ሽፈራዉ ባለፈዉ ትብብሩ በጠራዉ ሰልፍ ላይ በማስተባበር ላይ እንዳሉ ለአንድ ሳንምንት በወያኔ ደህንነቶች ታፍነዉ ተወስደዉ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጠመባቸዉ ይታወቃል::ለጊዜው ስማቸው ይፋ ያልሆነ አመራሮች ራሳቸውን ከወያኔ የምርጫ ሜዳ ያገለሉ ሲሆን ድርጅቱ ይህን ተከትሎ ምርጫውን ጥሎ ይወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው::

በተያያዘ ዜና በአዊ ዞን ኮሶበር ከተማ መንግስት ምርጫውን ምክናያት በማድረግ እስካሁን ተኝተው ከርመው አዊ ዩኒቨርስቲን የመሰረት ድንጋዪ አስቀመጡ በተመሳሳይ የኮሶበር ሆስፒታልንም በቶሎ ቶሎ ድንጋይ አስቀምጠዋል::የካቲት አንድ ቀን ህብረተሰቡ ግን እስከዛሬ የት ነበራችሁ ልጆቻችን ተምረው ዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው እሩቅ ቦታ ሲመደቡ አቅም አንሶዋቸው እዚሁ እንደኛው ገበሬ ሆነው ሲቀሩ ልጆቻችንና ባልተበቶቻችን ህክምና አጥተው በመንገድ ሲቀሩ እንዲሁም ምራጫ በመጣ ቁጥር ቃል የገባችሁልን ከዚህ በፊት የት አሉ ብሎዋቸዋል::

ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል ሆነና ነገሩ ይህንን እንኩአን እዉነቱን ሊነግሩን አልፈለጉም:: በጎነት እና አስተዋይነትን ወደ ርካሽ ፖሎቲካ አዞሩትና እንዴት ብሎ መጠየቅ ልማዱ ላልሆነው ህዝብ “በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድራ 20 ሚልዮን የአውስትራልያ ዶላር ተሸለመች” ብለዉት እርፍ::
ቅሌት!

በሪቱን ለማናገር የማሰነው ቡድን ከጎሮቤትም ሆነ ከቅርብ ቤተዘመድ ያገኘዉት ምላሽ የ20 ሚሊዮን ዶላሩን ታሪክ እና በሪቱ አሸነፈች ስለተባለዉ አዋርድ የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ ነዉ:: ዛሬም ከአንድ ፖለቲከኛ አፍ የሚወጣውን ሁሉ ምንም ሳያጣራ ልክ ከላይ ከጸባዖት እንደመጣ ቃል ጋቢ አንጥፎ እየሰገደ በእልልታ የሚቀበል ምስኪን ሰው በዚህ በመረጃ ዘመን መኖሩ ያሳዝናል :: እዉነቱ ወዲህ ነዉ::

ነገሩን የመልቦርን ነዋሪ እና በሪቱ ጃለታን በቅርበት የምያዉቃት ጃራ ቦሩ (jaarraa boru) እንዲህ ይገልፀዋል::
ታሪኩ እንዲህ ነው᎗ ባሪቱ ጃለታ(ከመሃመድ አህመድ እና ከክሚያ የተወለደች: የምልኬሳ እና ዳሜሳ እህት:) ከምትኖርበት ሜልበርን ልዩ ስሙ ወራቢ (Werribee) ከምባል ከተማ ለእረፍት ከቤተሰቦችዋ ጋር ሃገር ቤት ሄዳ በነበረችበት ወቅት በመንግስት ምንም ትኩረት ያልተሰጠበትን የጋራ ሙለታን አከባቢ ትምህርት ቤቶች ለመጎብኘት እድሉን ታገኛለች:: ያንን ጉብኝት ካደረገች በኋላ መንፈሷ እረፍት ያጣል:: ነብሷ ትጨነቃለች:: ወደምትኖርበት ሜልበርን (ወራቢ) ስትመለስ በዚሁ ጉዳይ ትታመማለች:: ትምህርቷን መከታተል ይሳናታል:: በየሳይካያትሪስቱ ብትወሰድ ለመንፈሷ ጭንቀት ምንም መፍትሔ ታጣ:: በመጨረሻም በሽታውን ያልተናገረ መፍትሄ አያገኝም በምለው ፕሪንስፕል በመመራት ለትምህርት ቤቷ ፕሪንስፓል (ዳይሬክተር) “ኢትዮጵያ ያሉት ልጆች በሚያፈስ ቤት ውስጥ እንደዚያ አፈር ላይ ተቀምጠው በተጨናነቀ ሁኔታ ሲማሩ አይቼ ደስታ ራቀኝ፣ እንቅልፍ አጣሁ፤ ምግብ እንኳ መብላት አልቻልኩም::” ብላ ስታለቅስባቸው ጊዜ የተለያዩ ገንዘብ የማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ተካሂዶ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑድርጅቶች ተረባርበው የዚህችን ሲበዛ ሰብዓዊነት የተሞላባትን ታዳጊ ወጣት መንፈስ ለመታደግ ባሳዩት ርብርቦሽ አንድ ትምህርት ቤት ለመስራት የሚያስችል ፈንድ ይገኝላታል:: ታዲያ ዶክተሩ እንደዚያ በስንት እንባ፣ ህመም እና ደጅ መጥናት የተገኘውን ገንዘብ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ከውጭ ለሚጎበኛቸው እነኒያ በመንግስት ቸል የተባሉት ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ሰዉን እንደሚያስለቅሱ ላለማንሳት እና ፖለቲካቸውን ለማሳመር እንዲመቻቸው ነው የሃያ ሚልዮኑን ቲዎሪ ይዘው ከች ያሉት::
አቶ ቴዎድሮስ ድፍን የሜልበርን ህዝብ የሚያውቀውን ታሪክ መልኩን ስለምን ለመለወጥ ፈለጉ:: የሆነ ሆኖ ዶክተሩን ሳላመሰግናቸው ላልፍ የማልፈልገው ግን ፈንዱን ወደ ትግራይ ሳያዞሩ እንደታቀደው ወደ ጋራ ሙለታ እንዲላክ መወሰናቸውን ነው:: በሪቱን እንኳን ደስ ያለሽ ልንላት ይገባል:: ያበባ እቅፍ ቱላማሪን አየር ማረፊያ ይጠብቃታል:: ዶክተር እርስዎን ግን ታዘብናችሁ::
Dagim Ahunim

Image

የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል! ‪
‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› —– ረቡእ የካቲት 18/2007 – ድምፃችን ይሰማ
Image
መንግስት ህገ መንግስታዊ መብቶቻችንን በመጣስ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ በደል ሲፈጽምብን ቆይቷል፡፡ እኛም እንደህዝብ ድምጻችንን አዋሕደን እና በአንድነት ቆመን ሰላማዊ ትግል ስናካሂድ ቆይተናል፡፡ ትግላችን እስካሁን አንድም ከሰላማዊነት መርህ ዝንፍ ሳይል የቆጠለ ሲሆን መንግስት ትግሉን ለማስቆም የሚወስዳቸው ግልብ እና አገር አጥፊ እርምጃዎችም ከመርሃችን ሊያዛንፉን እንደማይችሉ በተደጋጋሚ በተግባር ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ሰሞኑን መንግስት በተለመደው ግፍ መር እርምጃው በርካታ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን በማሰር ዘመቻ ላይ ተጠምዷል፡፡ አንዳችም ጥፋት ያልፈጸሙ ወጣቶችንም የ28 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ በመጠየቅ ወደማጎሪያ ካምፖቹ አስገብቷል፡፡ ይህ ‹‹ሙስሊሞችን በማሰር ከትግላቸው አስቆማለሁ!›› ከሚል መናኛ ቀቢጸ ተስፋ እና ባዶ ምኞት የመነጨ ለመሆኑ እማኝ መጥራት አያሻም – ካሁን ቀደምም መንግስት ሲፈጽመው የቆየው፣ ግና ሊያሳካቸው ያልቻለው ህልሙ ነውና!

አዎን! ደጋግመን ስናሳይ እንደቆየነው ሁሉ ህዝብን ማንገላታት አንጂ ማሸነፍ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም! ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው! በአላህ ፈቃድ ያሸንፋልም! ይህን ህገወጥ እና ሊሳካ የማይችል እኩይ የመንግስት ምኞት በተለያዩ ስልቶች መታገል የነፍስ ወከፍ ሐላፊነታችን የሚሆነውም ለዚሁ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ በመሆኑም ከነገ ወዲያ አርብ የካቲት 20/2007 መላው አገሪቱን ያሳተፈ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል፡፡ የተቃውሞውን መርሃ ግብር አስመልክቶ በነገው እለት የምናሳውቅ በመሆኑ እስከዚያው መረጃውን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ ተዘጋጅተን እንጠብቅ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!

የባለስልጣኖች መክዳት የተቃዋሚዎች የትግል ውጤት አንዱ አካል ነው:: በኢትዮጵያ የፍትህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተባሳ ጥለው ሕዝብን አንገቱን በማስደፋት ለለቅሶ የዳረገው የቀድሞ ዳኛ የዛሬው ባለስልጣን አቶ ሽመልስ ከማል ወደ አሜሪካ በግል ተጉዞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቅ የሚሉ ጭምጭምታዎች መሰማት ከተጠያቂነት ለመዳን የሚደረግ ሩጫ ,,,, እርግጥ ለትግሉ መረጃ በማሰባሰብ ረገድ ሽመልስ ከማል ሊረዳ ይችል ይሆናል ሆኖም ጎን ለጎን የፍትህ ስርአቱን በማኮላቸት እና በማበላሸት በኮሚኒኬሽን ስራ በሃሰት ሕዝብን ለማዘናጋት በፕሮፓጋንዳ በማጭበርበር ተግባራቸው ከተተያቂነት አይድኑም:: አሜሪካ የምትባል አገር በፈቃዷ የቆሻሾች ማጠራቀሚያ ሆነች?

በእኔ እይታ የባለስልጣኖች መክዳት የተቃዋሚዎች የትግል ውጤት አንዱ አካል ነው::ተቃዋሚዎች የወያኔን አምባገነንነት በገሃድ ማጋለጣቸው ለስር አት መፍረክረክ አስታውጾ አለው::የአቶ ሽመልስ ከማል መክዳት እውነት ሆኖ ከተገኘ ለትግሉ የመረጃ ፍሰውት በጣም ጠቃሚ ነው::እንደ ብስራት አማረ ያሉ ሃገር ቤት የሚመላለሱ የወያኔ ሙቀኞች ወንጀል ሰርተው በወንጀል ታጥበው በአሜሪካ እየኖሩ ነው::ሽመልስ በስርአቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሕወሓት ምንጫቸውን ማወቅም አዛዦችንም መለየቱ ለማወቅ አስፈላጊ ሰው ነው::የባለስልጣናት መክዳት የስርአቱን መበስበስ ያመለክታል::ያም ሆነ ያም ዋናው ለትግሉ የሚጠቅሙ መረጃዎችን ማግኘት ነው::ስለዚህ ጉዳዩን በሰከነ መልኩ ማየት ነው:
Image

Image
በአዲስ አበባ ትላንት ለሊቱን በተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞችን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም በራሪ ወረቀቶች ተበትነው እና ተለጥፈው ማደራቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡
ወረቀቶቹ በመንገድ ጋር ግድግዳዎች ላይ፣ በመንገድ ምልክቶች ላይ፣ በመብራት ፖሎች ላይ የተለጠፉ ሲሆን በየመንገዱም መበተናቸው ታውቋል፡፡

ትላንት ሌሊቱን ፒያሳ አምፒር አካባቢ፣ በሜክሲኮ ቄራ መንገድ ላይ፣ በጦር ሃይሎች፣በቦሌ ፒኮክ እና ወሎ ሰፈር፣ በመገናኛ፣ በመካኒሳ፣በቤተል እና በሌሎች ቦታዎች ላይ ወረቀት ተበትነው ማደራቸው ታውቋል፡፡ከተበተኑት እና ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል እስራት ትግላችንን አያስቆመውም፣መስዋትነት የኢስላም መንገድ ነው፣ሺ ሰው ቢታሰር ሺ ሰው ይተካል፣ ለኢስላም መታሰር ክብር ነው፣ ትግላችን ከምረጫው ቡሃላም ይቀጥላል፣ ድምፃችን ይሰማ፣ትግላችን ይቀጥላል የሚሉና ሌሎች በርካታ መልዕክቶችን የያዙ ወረቀቶች በመተናቸው ተገልፆል፡፡

መንግስት በአዲስ አበባ ሙስሊሞች የማሰር ዘመቻውን አጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ህዝበ ሙስሊሙ እስራት መፍትሄ እንደማይሆን በተግባር ያረጋገጠ መልዕክት በትላንትናው ለሊት አስተላልፏል::

Minilik Salsawi የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን። አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi : በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ክልል ደቡባዊ አቅጣጫ ቶንጎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በታጣቂ ሃይሎች እና በወያኔ ወታደሮች መካከል ለሊቱን ከባድ ውጊያ መደረጉን ለታጣቂ ሃይሎቹ ቅርብ ነን ያሉ ምንጮች ከማላካል አስታውቀዋል::

ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ተነስተው በምእራብ የኢትዮጵያ ድንበር ከሚገኙት የወያኔ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙት ታጣቂ ሃይሎች በስርአቱ በደል ደርሶባቸው የሸፈቱ እንደሆነ ምንጮቹ ሲገልጹ ለሊቱን ከባድ ውጊያ ያካሄዱ ሲሆን ከታጣቂ ሃይሎቹ 26 ሰውች መሰዋቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::

በጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በስርአቱ ከባድ በደል እየደረሰባቸው ሲሆን ምንም አይነት የልማት መዋቅር ካለመዘርጋቱም በላይ ከየአከባቢያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጪ ባለሃብት እንዲሁም ከትግራይ መጥተው ለሰፈሩ አልሚዎች ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች እየተሰጣብቸው ለስደት ለስራ አጥነት እና ለድህነት ተዳርገዋል::እነዚህ የስርአቱ በደል አንገሽግሿቸው ደቡብ ሱዳን ጫካ በመግባት ራሳቸውን ያደራጁ ታጣቂ ሃይሎች የወያኔን ወታደሮች መዋጋታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል::የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነጻነቱ እና ለመብቱ በሚያደርገው ትግል በአንድነት መነሳት አለበት አለበት ያሉት ምንጮቹ ራሳችንን ክበደል እና ከብዝበዛ ለማዳን ጠንክረን ልንታገል ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል::
Image

Image
ትላንት መቀሌ ከተማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪውን ያለፍላጎቱ በማስገደድ እንዲሰለፍ በተሰጠው መመርያ መሰረት ሁሉም የተሰጠውን ችቦ በመያዝ ቀኑን ሁሉ ከትምህርት ገበታቸው ላይ ተስታጉለው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ያለፍላጎታቸው በማስገደድ በሚደረገው ሰልፍ ላይ የህ ወ ሀ ትን የምስረታ 40 ኛ ዐመት በዐል በሚል አላማ ተማሪዎቹ የሚተባበሩ እና የሚያከብሩ በማስመሰል ድራማ ሲያሰሩዋቸው ቆይተዋል።
ምርጫው በተቃረበበት በዚህ ወቅት ገዢው ብድን ወያኔ በተለያዩ መንግስታዊና የግል ተቋማት እንዲሁም የእምነት ቤቶች ውስጥ እጁን በማስገባት ያለ ህዝብ ፈቃድ ዜጎችን ማስፈረም እና በግዳጅ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ማድረጉን በይበልጥ አፋፍሞታል። በትላንትናው ውሎ በተለምዶ የተማሪዎቹ የካፌው አሰራር የቁርስ ግዜያችውን የሚያስተናግደው በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 2፡30 ሲሆን ይህን አሰራር በመቀየር እና በማን አለብኝነት ለሊቱ ወደማብቂያው ገደማ 9፡30 ተጅምሮ 10፡30 ድረስ ለቁርስ ያልተገኘ ተማሪ መመገብ ሳይችል እንደሚቀር ለህዳሴ ካፌው ከባለስልጣናቱ በተላለፈው ማስጠንቀቂያ መሰረት በለሊት ቁርሳቸውን እንዲበሉ ተገደዋል።
ይህም ተማሪዋች ወደ ግዳጅ ሰልፉ ማልደው በቶሎ እንዲዘጋጁ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን ሁሉም በዚህ ጥሪ ላይ የመሳተፍ ግዴታው እንደሆነ በማስጠንቀቂያ መልዕክቱ ተላልፏል። ተማሪው ሳይፈልግ እና የራስ ተነሳሽነት በጎደለው መልኩ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ወያኔዎቹ ይህንን የማን አለብኝነት ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ ሀገሬውን እንደፈለጉ በጠመንጃ አፈሙዝ ግድ እንደሚሉት ሁሉም ሊይውቀው ይገባል ።
እንዲህ የሚመሳስሉ መረን የለሽ ግፍ እየተፈጽመበት በአይነ ቁራኛ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በረዥም የጭቆና ሰንሰለት ተሸምቅቆ ከወያኔ ፍላጎት ውጪ በሚያደረገው እንቅስቃሴ ታላቅ አፈና እና ግድያ ፊትለፊቱ ተጋርጦበት የተባለውን ብቻ የሚፈጽም ተደርጓል ።
ስለዚህም በግፍ አገዛዙ በአለም ሁሉ የሚታወቀው አምባገነኑ ወያኔ በሃገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፋዊ ስርዐት እና ሃብትን ያለአግባብ መዝረፉን፣ ማስገደዱንም ፣ ግድያውንም በቃኝ ጠግቢያለሁ ስልማይል በተባበረ ህዝባዊ አመጽ በቃህ ሊባል ይገባዋል።
Image
Image
Image

Image
የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ትግል የሁላችንም ነውና በጋራ እንነሳ!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሠላማዊ ትግል ፕሮግራም ካደረገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተከሰቱትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመገምገም ሁለተኛ ዙር ፕሮግራሙን ነድፎ ለምርጫ ዕጩዎችን የማስመዝገብ ተግባር ጎን ለጎን ለተግባራዊነቱ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ የዚህ የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ማጠቃለያም የካቲት 15 /2007 በተመረጡ 15 የአገራችን ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ የሚደረጉ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በመነሳት የዛሬው መግለጫ ለየካቲት 15 የታቀደውን በ15 ከተሞች የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ወደ የካቲት 22/07 መተላለፉን ለማሳወቅና ትብብራችን እስከ ዛሬ ያደረገውን ሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት፣ወቅታዊነትና ትክክለኝነት በተጨባጭ በማረጋገጥ፣የተያያዝነውን ሰላማዊና ህዝባዊ ትግል እንዴት ማስቀጠልና ውጤታማ ማድረግ ስለሚቻልበት የገዢዎቻችንን ከግምት ያለፈ የፍርኃትና ስጋት ደረጃን ያገናዘበ ስልት መቀየሳችንን ፣ የቆምንበትን ህገመንግስታዊነትና ህጋዊነት እንዲሁም የትግሉን ትኩረት የሚመለከቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የደረስንበትን ጭብጥ ለህዝባችን በዝርዝርና በስፋት በማቅረብ ለቀጣዩ ትግል ጥሪያችንን ለማቅረብ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት የተደረሰባቸው ጭብጦች፡-
1.ገዢው ፓርቲ/መንግስት የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድ የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ በረቀቀ ስልት እንደሚቀጥል የሙስሊም ማኅበረሰቡ ታህሳስ 10/07 ዓ.ም በኑር መስጂድ፣ የካቲት 06/07 በአንዋር ካሰማውና የትግሉን ቀጣይነት ካረጋገጠበት ፍጹም ሠላማዊ በሆነና አንድም ጉዳት ባልደረሰበት የተሳካ የተቃውሞ ድምጽና ክንዋኔ ተረድተናል፤

2. በታህሳስ 10/2007 ዓ.ም ተመሳሳይ ዕለት የባህር ዳር ከተማ ህዝብ ሃይማኖት፣ ዘርና ሌሎች ልዩነቶችን ወደጎን አድርጎ ፣ገዢው ፓርቲ በዘረጋው የአንድ ለአምስት የደህንነት መዋቅር ሳይጠለፍና ሳይገታ፣ በአንድነት ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነትም አፈና የቱንም የህዝብ ጥያቄ የማፈን አቅም የሌለው መሆኑን ይልቁንም ትግሉን ወደ ግብታዊነት ሊመራ እንደሚችል ተገንዝበናል፤

3. ገዢው ፓርቲ/መንግስት በመንግስት መዋቅሮችም ሆነ በህዝቡ ማኅበራዊ ግንኙነት እያደረሰ ያለው ጭቆና/የመብት ረገጣው፣ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት…/ እና ከህዝብ የመሸከም አቅም በላይ የሆነው የኑሮ ውድነት፣የመከፋፈልና የጥላቻ ፖለቲካ … የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት እያሳደገው መምጣቱን ፣የተባበረና የተቀናጀ አመራር ካገኘ ህዝቡ ለለውጥ ያለውን ጥማትና ዝግጁነት አስገንዝቦናል፤

እነዚህ ሲጠቃለሉም-ገዢው ፓርቲ/መንግስት ስለመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው በመሆኑ ለዚህ የተቋቋመውን የዲሞክራሲ ተቋም -የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቁጥጥሩ ሥር በማዋል በጠንካራ ፓርቲዎች የውስጥ ጉዳይ በማስገባት ከመጪው ምርጫ ለማግለል ቆርጦ መነሳቱን ፣ ለዚህም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎችን በሚመለከት በቦርዱ የተላለፈው ፖለቲካዊ ውሳኔና ፍጻሜው ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ለቀጣዩ ምርጫ ዕጩዎችን ለማስመዝገብ በተንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ በተለይ በኦሮሚያ፣በአማራና በደቡብ ኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ያሉት ተመሳሳይ ህገወጥ ተግባራት ነገ ወደ ትብብራችን አባላትና ሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ በግልጽና በቀጥታ የማሸጋገር አቅጣጫ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ኢቢሲ ያቀረበው በህገመንግስታዊው የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካዊ ሥርዓት የተቀመጠውን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የመኖር ትርጉም ዋጋ የሚያሳጣው ‹‹መንግስትንና የመንግስት አስፈጻሚዎችን ከተቻችሁ፣ካላከበራችሁ ወይም ጸጥ ለጥ ብላችሁ የምርጫ አጃቢ ካልሆናችሁ እስከ 15 ዓመት ትታሰራላችሁ›› የሚል አንድምታ ያለው በ ‹‹ባለሙያዎች ትንታኔ ›› ሥም የተላከው የማስፈራሪያ መልዕክትና የሌሉ የፈጠራ ክሶችን ለመፈብረክ በአባል ፓርቲዎቻችን ላይ ‹‹የሞተ ጉዳዩን ከመቃብር በመቀስቀስ›› እና በአዲስ መልክ የተጀመረው የሚዲያ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻም በግልጽ ያስተላለፈው ይህንኑ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የትብብራችን አባል ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ወደ ምርጫው በአንድ ምልክት ለመወዳደር በዕጩነት በቀረቡበትና በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ ላይ በምርጫ ክልል ክስና ቅሬታ ባልቀረበበት ከምርጫ ጋር ከተያያዙ ህጎች፣መመሪያዎችና ደንቦች ውጪ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተፈጠረው ችግር፣እስከ ትናንት ማታ ድረስ ከዕጩዎች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የትብብራችንን አባል የሰማያዊ ፓርቲን ሥም ለመጥራት የፈሩበትና እስከዛሬ ትብብራችን የሚጠቀምበትን የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ለማስለቀቅ የተጀመረው የተቀነባበረ ሴራም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፡፡

በሌላ በኩል ገዢው ፓርቲ/መንግስት በመንግስት እና በ ‹‹ግልና ነጻ ሚዲያ ሥም ›› በተደራጁ መገናኛ ብዙሃን እያስተላለፈ ካለው ‹‹ማስፈራሪያ›› በተጨማሪ አምስቱን ዓመታት እየሰራ ያለውን የምርጫ ፕሮፖጋንዳ በማጠናከር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህወኃት ምስረታ 40ኛ ዓመት ጋር አያይዞ ደደቢትን በ‹‹ልማታዊያን›› እያስጎበኘ፣በኢህአዴግ ውስጥ የህወኃትን የበላይነት ጠቅላይ ሚኒስትሩንና አፈ ጉባኤውን ጨምሮ በባለሥልጣናቱ እያስመሰከረ፣እንዲሁም የመሰረተ ልማት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ እያስቀመጠ የምርጫ ቅስቀሳ አጠናክሮ በስፋት በቀጠለበትና በጠንካራ ፓርቲዎች ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ በተላለፈበትም ገዢው ፓርቲ ከጠበቀው ውጤት በተቃራኒ የትብብሩን ትግል ለማጠናከር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በተለይ የአንድነት አባላትን ከሰላማዊ ትግሉ ያላሸሻቸው ይልቁንም ወደ ትግሉ በተጠናከረ ሞራልና በላቀ ቁርጠኝነት ከትብብራችን አባል ሰማያዊ ፓርቲ መቀላቀላቸው የነጻነት ሰላማዊ ትግሉ በአጠቃላይ፣ የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ፕሮግራማችን በተለይ፣ በተለያየ ፓርቲ የነበሩትን በአጋርነት በማሰባሰብና ለውጡ የምመጣለትን ምልዐተ- ህዝብ ወደ ትብብራችን የበለጠ በመሳብ ለቀጣዩ የጋራ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ የዚህ በስፋት የመቀጠል ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ገዢው ፓርቲ/መንግስት /ለውጡ የሚመጣባቸው አምባገነኖች/ ላይ ድንገተኛ ከፍተኛ ፍርኃትና ሥጋት በማሳደሩ ህገመንግሥቱን በመጨፍለቅ በግልጽና በአደባባይ ህገወጥ ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን ለመውሰድ መገደዳቸው፣ ይህም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት በማሳደግ ህዝባዊውን ትግል ወደ ላቀ/ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገሩ የበለጠ ግልጽ ሆኗል፡፡

ስለዚህ ከላይ በተገለጸው አገራዊ ተጨባጭ እውነታ ውስጥ የሚደረግ ሠላማዊና ህጋዊ ትግል በብልሃት/ጥበብና ዲስፕሊን የሚመራ፤ ቆራጥነትን የተላበሰ፣ የተቀናጀና ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያሳትፍ፣በጠራ ኃሳብ ላይ የቆመ መሆን እንደሚገባው፣ አመራሩም የትግሉን ህጋዊነትና ትኩረት ለይቶ ለህዝብ ግልጽ ማድረግ እንዳለበት ተረድተናል፡፡ ስለሆነም ቀጣዩ ትግላችን ፡-
በመጀመሪያ – ትብብራችን የተከተለው የጋራ ትግል ትናንት፣ዛሬም ሆነ እስከ መጨረሻው ፍጹም ህገ መንግስታዊ፣ ህጋዊና ሰላማዊ፣በአገራችንም ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የተለመደ ነው፡፡ በተለይም ለየካቲት 15 ቀን ስናቅድ ለምርጫ 2007 በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዕውቅና የማይጠየቅበት የፓርቲዎች የቅስቀሳ ወቅት ስለሆነ እንደነበር፣ አሁን በከለስነው ዕቅድም የከተማ አስተዳደሮች ዕውቅና ወይም እነርሱ እንደሚሉት ‹‹ፍቃድ›› የማይጠየቁበት ለገዢው ፓርቲ የማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳ የማይውልና ምልዐተ-ህዝቡ ሰልፉ ተፈቅዷል/አልተፈቀደም ከሚል ጥያቄ ነጻ መሆኑ፣፤
በመቀጠልም – የትግል ጥያቄኣችን ትኩረት ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻነትና ክብር መሆኑ ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሁላችን ፣ በትግላችን ስኬታማነት የሚጎዱ ቢኖሩ ከግል ጥቅማቸው የሚነቀሉ፣ በአገርና ህዝብ ላይ በሰሩት ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ ጥቂት አምባገነኖችና ህገወጥ የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ብቻና ብቻ ናቸው፡፡ ገዢዎቹ እንደሚሉትና እንደሚያስፈራሩበት እንኳን ከእኛ የተለየ የፖለቲካ እምነት ያለው ዜጋ፣ ተራው የህወኃት/ኢህአዴግ አባልና ካድሬ፣ የመንግስት ሠራተኛ፣የፖሊስና መከላከያ አባልም ሆነ የደህንነት ሠራተኛ በምንም መልኩ በሚጠበቀው ለውጥ ተጎጂ እንደማይሆን፤ ለጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት ለመራጩ ህዝብ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የእኛ-የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ እነዚህም በአጭር አገላለጽ፡- አንድም –ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብለን፣የአገራችን ሉዓላዊነት በጥያቄ ውስጥ ባለበት፣ የጭቆና ቀንበር ተሸክመን በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፤ ያሊያም– አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ/ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል፣ ናቸው፡፡
ለእኛ ሁለተኛው ሁሉንአቀፍ የነጻነትና ክብርን የማስመለስ ሰላማዊ ትግል ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡ግባችንም በህገመንግስታዊው የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለአገራችን ሉኣላዊነት፣ዘላቂ ሠላምና ልማት፣ ለነጻነት፣ የዜግነት ክብር፣ እኩልነትና እኩል ተጠቃሚነት መረጋገጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው በኃይል ጭቆናን በማክበድ አምባገነንነትን ለማስቀጠል የሚደረገው ሁሉ ለውጡን ያዘገየው፣መስዋዕትነቱንም ያከብደው እንደሆነ እንጂ እንደማያስቀረው ግልጽ በመሆኑ ፣ በውጤቱም ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ፤በተለይም የገዢው ፓርቲ ‹‹ልዩ ተጠቃሚዎች /አምባገነኖችና ጥቂት ጭፍሮቻቸው/ ›› ተጠያቂነታቸውን የሚያጠናክር፣ህዝባዊ ትግሉም ከማናችንም/ከእነሱም ከእኛም/ ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሠላምና መረጋጋት ከጥያቄ የሚያስገባ አላስፈላጊ ሁኔታ እንዳይከሰት የመከላከል ሚና ያለው ነው፡፡ማለትም ትግላችን ህገመንግስታዊ መብታችንን በመጠቀም በህግና በሥርዓት የሚመራ ነው፡፡ በመሆኑም፡-
1ኛ/ ምልዐተ ህዝቡ፡- የተባበረን ህዝባዊ ትግል አሸንፎ በሥልጣኑ የዘለቀ አምባገነናዊ ሥርዓት ያለመኖሩን፣ ነጻነት ነጻ ያለመሆኑን፣ የፖለቲካ ትግል በተጨባጩ ዓለም የሚቻለውን ማድረግ ነውና የሰላማዊ ትግሉና የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ በር ሙሉ በሙሉ እስኪዘጋ ባለው የንፋስ መግቢያ ቀዳዳ በመጠቀም የነጻነት ትግሉን እስከምንችለው ጫፍ ድረስ በጽናትና ቆራጥነት ለመምራት ዝግጁ መሆናችንን ተረድታችሁ፣ በገዢው ፓርቲ የ‹‹ከፋፍለህ ግዛ›› ፖሊሲ ሳትጠለፉ፣በማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳዎች ሳትሸማቀቁ ፣
2ኛ/ ‹‹ኢህአዴግነት ከዜግነት በላይ ›› ሆኖ የሥራ ዋስትናችሁ፣ዕድገትም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙያችሁ፣ በልምዳችሁ፣ ክህሎታችሁ፣ በጥቅሉም በሥራ ብቃታችሁ ሳይሆን በፓርቲ አባልነት በሚመዝን ሥርዓት የሚደርስባችሁ ሁሉ እንዲገታ፣ የተነጠቃችሁትን በራስ መተማመን መንፈስ ለማስመለስ የምትተጉ፤ ሲቪል የመንግስት ሠራተኞች፣
3ኛ/ የቴለቪዥንና ሬዲዮው ‹‹ሚሊዬነርነት›› ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ የህይወት ለውጥ ያላመጣላችሁ ‹ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ›› የሆነባችሁ፣ የግብርና ግብአቶች ማግኘት የዜግነት መብታችሁ ሆኖ ሳለ ‹‹የፖለቲካ ጉቦ›› የምትጠየቁ በየምክንያቱ ለመፈናቀልና ስደት የተዳረጋችሁና የተጋለጣችሁ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ወገኖች፣
4ኛ/ በአገራችሁ በነጻነት ሰርቶ የማደር መብታችሁን ተነጥቃችሁ ለአድሎኣዊ ውድድርና ለሙሰኞች የተጋለጣችሁ፣ በየትኛውም ጊዜ ከየትም አቅጣጫ ሊመጣ በሚችል ጥቃት በስጋት እየተሰቃያችሁ ያላችሁ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣
5ኛ/ የህወኃት/ኢህአዴግ ተራ አባላትና ካድሬዎች፤ የፖለቲካ ልዩነት የተለያየ አመለካከትና ኃሳብ ማራመድ ጤናማ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መገለጫ እንጂ እንደሚነገራችሁ ‹‹ጠላትነት›› ባለመሆኑ፣ትግላችንም ለሠላማዊና ህጋዊ የሥልጣን ሽግግር እንጂ እንደሚነገራችሁ በናንተ ‹‹መቃብር ›› ላይ አዲሱን ሥርዓት የማቆም፣ የነበረውን አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመርና እናንተን የማጥፋት ዓላማ እንደሌለው ተረድታችሁ፣ ተቃዋሚዎች እንደናንተው ኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ የሚጨነቁ መሆናቸውን በመረዳት ተቃዋሚዎችን እንደ‹‹ ጠላት›› ከመመልከት አስተሳሰብ ራሳችሁን ነጻ አውጥታችሁ፣
6ኛ/ የፖሊስ፣ መከላከያ ሠራዊትና ደህንነት አባላት፤ ህገመንግስቱና የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጁ (573/2000) አንቀጽ 58 ከፓርቲ አባልነት/ተጽዕኖ ነጻነታችሁን ስለሚያረጋግጡ፣በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችሁ ላይ ህገ- ወጥ ትዕዛዝ በመፈጸም ከሚደርስባችሁ ህጋዊና ህሊናዊ ተጠያቂነት ራሳችሁን ጠብቃችሁ፣እንዲሁም የትግላችን ውጤት እኩል ተጠቃሚ መሆናችሁን ተረድታችሁ፣ ራሳችሁን የሚጠበቀው የስርዓት ለውጥ ‹‹ለማኞች ያደርጋችኋል ›› ከሚለው ፕሮፖጋንዳ ሰለባነት ነጻ አውጥታችሁ፣ የአምባገነኖች መጠቀሚያ መሳሪያ ከመሆን እንድትታቀቡና ህዝባዊና ህገ መንግስታዊ ወገኝተኝነታችሁን በማረጋገጥ፤
7ኛ/ ወጣቶችና ሴቶች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች– ማኅበራት/ሊጎች፤በሥራ አጥነት፣ከአቅም በላይ የሆነው የኑሮ ውድነት … በስደት ህይወት ከሚደርስባችሁ ስቃይ ባሻገር በጥቅማ ጥቅም እንድትንበረከኩና የገዢው ፓርቲ አገልጋይ እንድትሆኑ የሚደረገውን ሁሉ በጥሳችሁ ፣በተለይ በመብታችሁ ትግል ስም የተደራጃችሁ የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች- የሚሰጣችሁ ጊዜያዊ ጥቅምና የሚገባላችሁ አማላይ ቃል ኪዳን የምርጫ ሰሞን ማባበያ መሆኑን በተደጋጋሚ ያያችሁት በመሆኑ፣ የሚደረግላችሁም በዜግነት መብታችሁ ማግኘት የሚገባችሁን እንጂ የገዢው ፓርቲ ሥጦታ ባለመሆኑ፤
8ኛ/ መምህራንና ተማሪዎች በተለይም የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፡-በአገራችን የለውጥ ኃይል ማዕከልና ግንባር ቀደም ተሰላፊ የሆናችሁበትን ታሪክ እንድታድሱና ዛሬም እንደ ትናንቱ አገራችሁና ህዝባችሁ ከናንተ ብዙ የሚጠብቁ መሆናችሁን ተረድታችሁ፣
9ኛ/ የእምነት ነጻነት መብት ጠያቂ የማኅበረሰብ አባላት፡- በተለያዩ እምነት ተከታዮች እየቀረቡ ያሉት የእምነት ነጻነት ጥያቄዎች ከሠላማዊውና ህጋዊው የሥርዓት ለውጥና የነጻነት ጥያቄኣችን የማይነጣጠሉ በመሆናቸው በተናጠል መልስ የማያገኙና መፍትሄውም የዘላቂው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል መሆኑን ተረድታችሁ፤
10ኛ/ ኢትዮጵያዊ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፡- በአገር ቤትና በውጪ የምትገኙ ነጻና የአገርና ህዝብ ወገንተኛ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ በተለይም በተሻለ ኃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት በተከበረበት የምትገኙት የህዝብ ጆሮና ዓይን በመሆን የምትሰጡትን አገልግሎት በማጠናከር የተያያዝነውን ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል አማራጭ ኃሳባችንና የትግል ጥሪያችንን ለህዝቡ በማቅረብ የዲሞክራሲ፣ የአገርና ሕዝብ ወገንተኝነታችሁን አጠናክራችሁ በመቀጠል፤
11ኛ/ የፍትህ አካላት፡- በትምህርት ያገነባችሁትና በልምድ ያዳበራችሁት ሙያዊ ቃልኪዳንና የሰብዐዊ ኅሊናችሁ ሚዛን የሚጥልባችሁ ኃላፊነት በጊዚያዊ- የሚያልፍ ጥቅም በአገራችሁና ወገናችሁ ላይ ፍትህን እንዳታጓድሉ ያስገድዳሉና የአምባገነኖች መጠቀሚያ መሳሪያ በመሆን ከመተባበር እንድትቆጠቡ፣
12ኛ/ ሌሎች ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች፡- በአምባገነን ሥርዓቱ በተናጠል የሚደርስብንን አፈና በጋራ ለመመከትና የመድብለ ፓርቲ ትግላችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣በሚያግባቡን የምርጫ ጉዳዮችና የብሄራዊ ውይይትና ዕርቅ ጉዳይ ላይ በአጋርነት በጋራ የመቆም አስፈላጊነት ለነገ የማይባል ነው ስለሆነ፣
13ኛ/ ፓርቲዎቻችሁን የተነጠቃችሁ የነጻነትና የዲሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች፡- እስካሁን ባለው ጊዜ አፋጣኝና ወሳኝ ፖለቲካዊ ውሳኔ በመስጠት ከትብብሩ አባል ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀላችሁትን እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን፣ ሌሎቻችሁም የትብብራችን አገራዊ የጋራ ዓላማ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር በማገናዘብ፣
14ኛ/ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵዊያን/ዲያስፖራዎች፡- በተያያዝነው ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል ያላችሁን ሚና በግልጽ ለይታችሁ፣ ተሳትፎኣችሁና ድጋፋችሁ ለትግላችን ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በመገንዘብ ለአገራችሁና ህዝባችሁ ባላችሁ የባለቤትነትና የወገናዊነት ኃላፊነት መሰረት፣
በምናደርገው አገራዊ፣ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት እንድትሰለፉ፤ የየካቲት 22/07 ቀጠሮኣችንም የማይቀርበት በመሆኑ በየከተሞቹ በቦታውና በሰዓቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን አበክረን እናቀርባለን፡፡
በተቀናጀ የጋራ አመራር የተባበረ ህዝባዊ ሠላማዊ ትግል በእኩልነት ላይ የተመሠረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንደምትገነባ አንጠራጠርም!

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

የካቲት 10/ 2007 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

Image

Minilik Salsawi በኢትዮጵያዊነቱ እና በሃገር ወዳድነቱ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ የነጻነት እና የመብት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በአምባገነን መዳፍ ስር ያለው ሕዝብ ነጻ እንዲወጣ ወያኔን ለመጣል በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ አፍዴራ ጋድሌ እና አርዱፍ በመዋሃድ የጋራ ግንባር መፍጠራቸው እየተካሄደ ላለው ትግል አንድ እርምጃ መራመድ ትልቅ አስታውጾ ያለው ተግባር ነው::

ፓርቲዎች ባለፉት ዘመናት በተናጠል በመታገል ምንም ውጤት እንዳላገኙ በገሃድ የታየ ጉዳይ ነው::እንዲሁም በሀገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ሊዋሃዱ አሊያም ግንባር ሊፈጥሩ በሚፈልጉበት ወቅት የወያኔ አምባገነን ገዢ ደህንነቶቹን አሰማርቶ ከፍተኛ ወከባ በመፍተር ሰርጎ ገቦችን በማስረግ ክፍተኛ መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል::በቅርቡ በአስመራ የተካሄደ ውህደት እና አሁንም በአፋር ድርጅቶች መካከል የተደረገው የግንባር ምስረታ ለትግሉ ታላቅ ግብ እና እመርታ ነው::

የግንባሩን መፈጠር ተከትሎ የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው፣ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል።አዲሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ ክፍተቱን መጠቀም እንዳለባቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል::Minilik Salsawi
ለ24 አመታት ያህል ሰራዊቱን እና የደህንነቱን ክፍል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር ያዋሉት የወያኔ ጁንታ አምባገነኖች መውደቂያቸው መድረሱን ተከትሎ በደህንነት አካላት መካከል ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱን የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ደህንነቶች ላይ እምነት ያጣው የወያነው አምባገነን አዳዲስ የደህንነት አባላት ለቁጥጥር መመደቡ ታውቋል::

በደህንነት ክፍል ውስጥ በመላው ሃገሪቱ የተመደቡ የደህንነት አባላት ላይ እምነት እንዳሌለው የሚናገረው ወያኔ በተለያየ ጊዜ ዝውውር ቢያደርግላቸውም በሃላፊዎች እና በደህንነት አባላቱ መካከል አለመግባባቶች እየሰፉ መነካከስ መቀጠሉን ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ አገላለጽ የደህንነት አባላቱ የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ቢደረግላቸውም ከሃላፊዎች ጋር አለመግባባቱ እንዲሁም በመካከላቸው ያለ መተማመን መናዱ በግልጽ እየታየ ነው ሲሉ ተናግረዋል::

ተቃዋሚዎች የወያኔን መፈረካከስ እና በሰራዊቱ እንዲሁም በደህንነቱ አካላት ዙሪያ የተነሳዉን ክፍተት ተጠቅመው በሰከነ እና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ለለውጥ በሚደረገው ትግል ጎን ለጎን ያለውን አለመግባባት ክፍተት በመጠቀም የወያኔን ውድቀት ማፋጠን አለባቸው ሲሉ ምንጮቹ አስተያየት ሰጥተዋል::

ሰሞኑን የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመላው ኢትዮጲያ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በቅድሚያ እንኳን ለአርባኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ ፡፡ በትጥቅ ትግሉም ወቅት ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ይህን ቀን ለማየት ሳይታደሉ ያለፉ ብዙዎች ናቸውና ምንም ይሁን ምን ለዚህ ቀን መብቃት ትልቅ ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ የምፅፈው በተወለድኩባት ባደኩባትና አሁንም እየኖርኩባት ባለችው ኢትዮጲያ ከተመሰረተ ድፍን 40 ዓመት ያስቆጠረ ጎልማሳ የፖለቲካ ድርጅት ላይ እንደአንድ ዜጋ ያለኝን ቅሬታ ለማሳወቅ ነው ፡፡

ሰሞኑን የድርጅቱን 40ኛ ዓመት በዓል በቴሌቪዥን በሬዲዮ እንዲሁም ከመሃበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስመለከት እንዲሁም አገሪቱ ላይ ያለውን ተጨባጭ ችግር ስታዘብ ሳልፈልገው አእምሮየ ታሪክ እየመዘዘ ይሞግተኛል ፡፡ ባጭሩ ይህ በዓል በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው ብየ ሳስብ ከግራና ቀኝ ከህዝቡ የሚሰነዘረውን ትችት አስተያየትና ምሬት ስመለከት በዓሉን ለብቻችሁ እያከበራችሁት ነው የሚል ስጋት ፈጥሮብኛል ፡፡

ምንም እንኳን የህወሃት የትጥቅ ትግል የዛሬው የህወሃት ቀንደኛ ጠላት ሻእቢያን ጨምሮ በከፈሉት መስዋእትነት ባደረጉት ተጋድሎ አገራችንን ከደርግ አሰቃቂ አገዛዝ የታደጋት መሆኑን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ቢያውቅም ከነፃነቱ በኋላ ግን ስርዓቱ በሚከተለው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስመር ከፍ ያለ ቅሬታ አለው ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ህዝቡ የትም ሂዱ የት ይማረራል … መቸም ይሄ ሁሉ ህዝብ የሚማረረው የኢትዮጲያ ህዝብ ምስጋና የማያውቅ ስለሆነ አይመስለኝም ፡፡ እንደውም ከእግዜር ጀምሮ እስከአምባገነን መሪወቹ ድረስ ራቱን በልቶ ባደረ ቁጥር ከእልፍ ችግሩ ጋር ተጠቅልሎ በሚተኛባት መደብ ‹‹ተመስገን›› ብሎ የሚያድር ህዝብ እንደኢትዮጲያ ህዝብ ያለ አይመስለኝም ፡፡ ግን …… ብሶት ህወሃትን እንደወለደ ሁሉ አሁንም ተማራሪ ህዝብ እየፈለፈለ ምድሩን እየሞላው ነው ፡፡ እናንተም ለህዝብ ብሶትና ጥያቄ ጅራትና ቀንድ እየቀጠላችሁ ተናጋሪውን ሁሉ ባልሆነ መንገድ በመፈረጅ ከማሳቀቃችሁም በላይ የዝሆን ጆሮ ይስጠን እንዳላችሁ ይሄው ድፍን 40 ዓመት ፡፡

በእርግጥ በቴሌቪዥንም ሆነ በአካል ለህዝብ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው … ከባዱ ከህዝብ ጋር መነጋገር ነው ፡፡ ይሁንና ንግግር ማድረግም ቢሆን ቀላልነቱ ለሚናገሩባት ቅፅበት እንጅ ሲቆይ ወደሰማይ እንደወረወሩት ድንጋይ ተመልሶ አናት ላይ መስፈሩ አይቀርም ፡፡አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው ፡፡ የተገባው ቃል ሁሉ ስንዝር አልተራመደም ፡፡ በርካታ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል መንገድ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ግንባታ ግድቦች ዩኒቨርስቲዎች እነዚህ ሁሉ እናተም በተደጋጋሚ እንዲነገርላችሁ የምትፈልጓቸው ስኬቶች ናቸው ፡፡ ይሁንና ህዝብ ያልተሟላለትን ነገር ሲናገር የተሰራለትን እንደካደ አድርጎ ማሰብ ትልቁ የአረዳድ ችግራችሁ ነው ፡፡ ሰው ኑሮ ተወደደብኝ ብሎ ሲያማርር ኑሮ የሚቃለልበት መንገድ ላይ መስራት ብቻ ነው መልሱ ሊሆን የሚችለው ! …‹‹ አይ ኑሮ ቢወደድብህም ዩኒቨርስቲ ግን ሰርተንልሃል›› የሚል ምላሽ መቸም ህዝብን ሊያረካ አይችልም !! አሁን እየሆነ ያለው ግን ይህ ነው ! ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ማስፈራሪያ ዛቻ እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎችን ከህዝቡ እየመዘዙ ለብዙሃኑ ችግረኛ እንቆቅልሽ ማለትና የህዝቡን ቅሬታ ማድበስበስ የተለመደ የገዥው ፓርቲ ስራ ሁኗል ፡፡

በተለይም ኢቲቪ (EBC) ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ›› በማለት የሚያቀርባቸው ሰዎች ግራ እያጋቡን ነው ! እስቲ ኑሮ ተወዶብናል ስንል እነዚህ ‹‹አንዳንዶች ›› ኑሮ አልተወደደም የሚል በደፈናው ይዘው ህዝቡን ማበሳጨት ምን ይጠቅማል ?ለማንስ ነው የሚመሰክሩት …መብራት ጠፋብን ስንል አንዳንዶቹ ‹‹ኧረ በጭራሽ›› ይሉናል ፡፡ አንዳንዶች ብዙሃኑን ‹‹ውሸታም ነህ ›› ይሉታል ፡፡ይሄ ህዝብን መናቅ ነው …እንደውም በኑሮ ውድነት ከሚሰቃየው ህዝብ በመሰረተ ልማት አውታሮች እጥረት ፍዳውን ከሚበላው ህዝብ የሚፈጠሩ ህፃናት ወደፊት

‹‹ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ›› ሲባሉ

‹‹ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን መሆን እንፈልጋለን ›› እንዳይሉ እሰጋለሁ ፡፡ ….በአሁኑ ሰዓት ያለምንም ምሬት በተድላ እንደሚኖሩና ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ እንደሆነ የሚመሰክሩ ኢትዮጲያዊያን ቢኖሩ እነዚሁ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች›› ብቻ ናቸውና ምኞቱ እንዲህ ቢሆን አይገርምም ፡፡ ብሄራዊ ቴሌቪዥናችን ‹‹ራበን ›› ብሎ ሰልፍ ለወጣው ህዝብ ‹‹ለምን ኬክ አይበሉም ›› እንዳለችው ልእልት ሁኖብናል ፡፡ ስራ አጣን ስንል ቴሌቪዥናችን ለምን ስራ አትፈጥሩም ይለናል …ኑሮ ለማሻሻል ተሰደድን ስንል …አይ ጥጋብ ፈንቅሏችሁ እንጅ አገራችን ማሩ ወተቱ ይለናል …እንኳን ማርና ወተት የግዜሩንም ውሃ በስንት ጉድ ጥበቃ እንደማንዳረስ ሁሉ !

ችግሩ ይሄ ብቻ አይደለም በመልካም አስተዳደር ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግር ውስጥ ነን ፡፡ ሙስና ቁጥር አንድ ጠላታችን ሁኗል …ሙስና ደግሞ በባህሪው ስልጣናቸውን ገንዘብ ላለው ሰው የሚያከራዩ ባለስልጣናትና የስራ ሃላፊዎች ዘንድ የሚፈጠር አደገኛ ተግባር ነው ፡፡ መንግስት ህዝቡን ጠቁም አትጠቁም ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ‹‹ደህንነት›› ተብሎ ለአገር ደህንነት ሲባል ጓዳ ጎድጓዳውን እሰልላለሁ እንደሚለው የመንግስት አካል በዚህም ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ‹‹የደህንነት አካል ›› ቢቋቋምና መዘረፋችን ባይቆም እንኳን አሟጠው እንዳይነጥቁን ሃይ ቢባሉ መልካም ነው ፡፡መቸም ሚስኪን ፀሃፊና ጋዜጠኞችን ከማሳደድ ይሄ የተሸለ ስራ ይመስለኛል ፡፡

ሌላው የህወሃት አስጊ ችግር በብሔሮች መሃል የፈጠረውና አሁንም እየፈጠረው ያለው ቁርሾ ነው ፡፡ በተለይ በትግራይ ህዝብና በሌላው ኢትዮጲያዊ መካከል …በተደጋጋሚ ህወሃት በጉድለቶቹ ሲወቀስ የራሱን ችግርና በድርጅቱ ላይ የሚሰነዘረውን ጥላቻም ይሁን ነቀፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እንደተሰነዘረ በማስመሰል የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው ጥረት በተደጋጋሚ የሚታይ የአደባባይ ሚስጥር ነው !! ይህ ነገር የትግራይን ህዝብ ከእህትና ወንድሞቹ ጋር እያቃቃረው ከስርአቱ ልዩ ተጠቃሚ የሆነ እያስመሰለው ይገኛል ፡፡ የትግራይ ህዝብ በህወሃት የስልጣን ዘመን ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚ ሁኗል አልሆነም የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ እንደሆነ አለ !!

ይህን ያልኩበት ምክንያት ደግሞ ህወሃት እራሱ እንደሚለው ኢፈርት ወይም ትእምት እጅግ በጣም ግዙፍ እና በኢትዮጲያ ውስጥ( አንዳንዶች እንደውም በአፍሪካም ይላሉ) በሀብት የሚወዳደረው የሌለ የንግድ ተቋም ነው ፡፡ ባለቤትነቱ ደግሞ በተለይ እንደተቀመጠው የትግራይ ህዝብ ነው ! እንግዲህ ይህን የሚያክል ትልቅ ተቋም በስሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፋብሪካዎች የማእድን ማውጫወች የኮንስትራክሽን ተቋማት የትራንስፖርት ድርጅቶች የእርሻ ድርጅቶች ያሉት ባለፀጋ ድርጅት ባለቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው ከተባለና በትክክል ለትግራይ ህዝብ ገንዘቡ ከዋለ የትግራይ ህዝብ በደንብ ተጠቃሚ ነው ለማለት ያስደፍራል !! ይሁንና እዚሁ ፌስቡክ ላይ የኢፈርት ነገር ላም አለኝ በሰማይ ነው እንደሚሉን በርካታ የትግይ ወንድሞቻችን አባባል ከሆነ ግን የትግራይ ህዝብ በተለይ ከስልጣኑም ከበረከቱም የሌለበት ሚስኪን ነዋሪ ያው እንደሁሉም ኢትዮጲያዊ ነው !!

ዋናው ነገር ተጠቀሙም አልተጠቀሙም አሁን ባለው በርካታ ኢትዮጲያዊ አመለካከት በተለያየ መንገድ እንደምንሰማውም ህወሃትና የትግራይን ህዝብ አዳብሎ የማየት ነገር ጎልቶ ይታያል ፡፡ ህወሃትም ቢሆን የትግራይ ህዝብና ህወሃት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው አይነት ዳርዳርታ ማብዛቱ በቀሪው የኢትዮጲያ ህዝብ ልብ ውስጥ ጥሩ ነገር ይፈጥራል የሚል እምነት የለኝም ! ህወሃት የፖለቲካ ድርጅት ነው ሊጠላም ሊወደስም ይችላል፡፡ እራሱን ችሎ መቆምና ከህዝብ የሚሰነዘርበትን ጥላቻም ሙገሳም ህዝቦችን ሳያነካካ መቀበል ይኖርበታል ፡፡ መልካም አስተዳደር ያሰፈነ ገዥ ፓርቲ የዚህኛው ብሔር የዛንኛው ዘር ነው አይባልም ጥሩ ድርጅት የሚያስተዳድረው ሃገር ድርጅት ነው !! አምባገነን እና ፀረ ህዝብ መንግስት ግን ከማንም ይጠጋ በማንም ይጠለል ህዝባዊ አይደለምና ብሔር የለውም !! አዎ የመላውን የሰው ልጆች ነፃነት ሰበዓዊና ዲሞክራሲ መብት ገፋፊ ከሆነ አምባገነን ብሄር የለውም!!

ይሄ ህወሃትን የነካ የትግራይን ህዝብ ነካ ጨዋታ በ1993 እና 1997 ላይ በተለይ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ተቃውሞች ላይ ነህዝቦች መካከለል አስነስቶ የነበረውን ተገቢ ያልሆነ መዘዝ በማየት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መታዘብ ይቻላል ፡፡ ያ ጊዜ የዚህ የጥላቻ ዘር ውጤት ፈጦ የታየበት ነበር ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂው ህወሃት ነው !! ለምን ቢባል በህዝቦቹ መካከል ወንድማማችነትን ለማጎልበት በቂ ስራ አልሰራም … (ፍላጎቱም ያለው አይመስልም) በመንግስት ስራ ውስጥም ሆነ በሌሎች ስራዎች የተሰማሩ አንዳንድ የአካባቢው ተወላጆች የትጥቅ ትግሉን ታሪክ የግል ጀብዷቸው ብቻ አድርገው ሲደነፉና ስለታገሉ ብቻ ልዩ ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሲጠቅሱ መንግስት መስመር ለማስያዝ ያደረገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም !!

አንዳንዴ እኮ ተራ መጠጥ ቤት ውስጥ ሳይቀር በሚነሳ አምባጓሮ ‹‹ደሜን አፍስሸ ባቀናኋት አገር ›› የሚላችሁ እንጩጭ ብሔረተኛ ያጋጥማችኋል ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይ በፀያፍ ስድብ ታሪክና ታላላቅ ሰዎችን በማጠልሸት ከእኛ በላይ አዋቂ የለም በማለትና አሳዛኝ ድርጊቶችን በመፈፀም የሚታወቁትም ተመሳሳይ ሰዎች ናቸው !! ይህ ከተጋነነ እውቀት ላይ ሳይሆን ትእቢት ላይ ከተመረኮዘ መጥፎ በራስ መተማመን የሚፈጠር በሽታ ከእኔ በላይ ላሳር የሚያስብላቸው እነዚሁ ሰዎች ናቸው !!

ለዚች አገር መሳሪያ አንስቶ የተዋጋው ብቻ ሳይሆን ግንበኛውም ሃኪሙም አስተማሪውም ላቡን አፍስሶላታል !! አበቃ !! ማንም ስለታገለ ደሙን ስላፈሰሰ ለህዝብ ነፃነት በጎ ነገር እንዳደረገ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንደተወጣ ያስብ እንጅ ለፈሰሰ ደሙ ከኢትዮጲያ ህዝብ ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለው ወይም ልዩ ተጠቃሚ የሚደርገው የይለፍ ወረቀት እንደያዘ አድርጎ ማሰብ ነውርም አሳፋሪ አስተሳሰብም ነው !! ሚሊየኖች እየወደቁላት እዚህ የደረሰች አገር ለሟችም ለገዳይም ነፃነትን እንጅ ካሳን የከፈለችበት ዘመን የለም ! ደሜ ለፈሰሰበት ይከፈለኝ የሚል እሳቤ ያለው ዜጋ ቅጥረኛ ወታደር እንጅ በምንም መስፈርት ጀግና ሊባልና ሊሞካሽ አይገባም !! የመስዋእትነት ክፍያው ነፃነት ብቻ ነው !! ነፃነቱም ለሁሉም ህዝብ በእኩልነት !!

መንግስት ለምን የፃፉትን ሁሉ ያስራል .. ለምን በተናገሩት ቁጥር ያኮርፋል … ዜጎቹን አኩርፎ ከውጭ አገር ሽማግሌ እስኪመጣለት አለያም አስሮ የሚያሰቃያቸው ዜጎቹ ያውም በካርዳቸው ድምፃቸውን ሰጡኝ የሚላቸው …ይቅር በለን ብለው እግሩ ስር እስኪወድቁለት የሚጠብቅ ስርዓት ምን አይነት መንግስት ሊወጣው ይችላል …ሁልጊዜ ስለመንገድ አውሩ ሁልጊዜ ስለፋሲካ ብቻ አውሩ የሚል መንግስት እንዴት የህዝብ መንግስት ሊሆን ይችላል ! መፅሄት ላይ ኮሽ ሲል በህዝብ ላብ በህዝብ ግብር በተማሩ ወታደሮችና ደህንነቶች ዜጎቹን የሚያሳፍስ ዘመድ ወዳጅ እንዳይጎበኛቸው የሚከለክል መንግስት ማንን ነው የሚመራው ….

በዚች በአርባኛ አመት በዓል ላይ የሚታየው ሌላው አሳዛኝ ነገር ደግሞ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ በላይ ጀግና አድርጎ የማቅረቡ ነገር ነው …እውነታውን ማስቀመጥ ይኖርብናል … ደርግን ለመጣል የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ወገኖቹ በላይ መስዋእትነት ከፍሏል ይሄ የማይካድ ሃቅ ነው …. ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከሰማየ ሰማያት የተለየ ጀግንነት ስለተቸረው ሳይሆን የትጥቅ ትግሉ በወቅቱ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚመች መልኩ ስላልተደራጀ ነበር ፡፡ እንጅኮ ደርግ ሲወድቅ ከአስራ ስምንት በላይ ብረት ያነሱ ተፋላሚዎች በኢትዮጲያ ነበሩ ! ቀደም ብለን ካየነውም በርካታ ኢትዮጲያዊ ደርግ አፍንጫ ስር ቁሞ በመፋለም ለህወሃት ትጥቅ ትግል መንገድ ከፍቷል …ተማሪዎች ለነፃነት ደማቸውን አፍስሰውላታል … ግለሰቦች ጨካኙን ስርአት ፊት ለፊት ተቃውመው ተሰውተዋል ….

… ደግሞ በህወሃት የትጥቅ ትግል ውስጥ ‹‹አምስት ሁነው ትግሉን ጀመሩ›› የሚለው የታሪክ መነሻ አምስት ሁነው ትግሉን ጨረሱ ማለት አለመሆኑን ማወቅም ተገቢ ይመስለኛል !! ሁሉም ኢትዮጲያ አንጀቱ አሮ በየቤቱ በተቀመጠበት ሰአት እንኳን አምስት አንድ ሰውም ተከተሉኝ ቢል እልፍ ያኮበኮቡ ኢትዮጲያዊያን ስርዓቱን ለመፋለም ዝግጁ ነበሩ …. ነበሩ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት በፊት ብረት አንስተው ስርዓቱን እንቢ ያሌ ነበሩ ፡፡ ምሬት ፅዋዋ ሞልቶ ነበር ህዝብ አገዛዙን አክ እትፍ ብሎት ነበር … ህወሃት አሁን ቁጭ ብሎ ማሰብ ያለበት የሚመስለኝ አምስት ሁኖ የትጥቅ ትግሉን መጀመሩን ሳይሆን አሁን የኢትዮጲያ ህዝብ ባጠቃላይ አምስት የሚወዳቸው የሚምናቸው መሪዎች ህወሃት ውስጥ አሉ ወይ የሚለውን ነው !!

በነገራችን ላይ ህወሃት ባለፈበት ጎዳና ሁኑ መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ከጎኑ ነበር !! የትግራይ ህዝብ ብቻው ከኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ጀግና ሊሆን አይችልም!! …ከወንድሞቹና ከእህቶቹ በላይ ጀብዱ እንዳለውም ማሰብ አይኖርበትም !! ይሄ እጅግ የተጋነነና የተዛነፈ እሳቤ ነው በኋላ ያልሆኑትን አድርጎ የማይገፉት ተራራ ጋር የሚያጋጨው …ሩቅ ሳንሄድ ሻእቢያ ከእኔ በላይ ጦርነት አዋቂ ከኔ በላይ ተኳሽ ላሳር ብሎ በእብሪት ከወረረን እኮ ገና አስራ አምስት አመት አልሞላውም … ይሁንና የቱንም ያህል ራሱን ጀግና ያድርግ የቱንም ያህል ራሱን ብልህና ጥበበኛ አድርጎ ያስብ ከመላው ኢትዮጲያ እንደአሸዋ የተዘረገፈው ህዝብ ነበር የከፈለውን ያህል መስዋእትነት ከፍሎ አገርን የታደጋት !! እውነቱን እናውራ ከተባለ የሻእቢያን ወረራ የትግራይ ህዝብ ብቻውን ይቋቋመው ነበር ?

መንግስት በቀረው እድሜ ሁሉ በብሔሮች መሃል በሃይማኖቶች መሃል እንዲሁም በፖለቲካ ድርጅቶች መሃል ታየም አልታየም ታወቀበትም አልታወቀበትም ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ባይኖረው መልካም ነው ፡፡ የፈለገ ቢከፋፈል ቢለያይ ገዥውን የጋራ ጥላት ያደረገ ህዝብ በአንድ ላይ መቆሙና መልሶ ችግር መሆኑ አይቀርም ! ዛሬ 40ኛ አመት በዓሉ ሲከበርም ይሄንኑ ታሳቢ ማድረጉ የሚበጅ ይመስለኛል !

ጉዳየን ስቋጭ እራሱ የህወሃት 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይም ታሪካዊ ጥያቄ በማንሳት ነው …

1965 ዓ/ም የወሎ ህዝብ በእረሃብ ሲረግፍ ከታች ጀምሮ እስከላይ እስከንጉሱ ርሃቡን በመደበቅና በማድበስበስ ስለረሃቡ የተነፈሱትን ሁሉ በማሰር ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የ80ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ለማክበር አዲስ አበባን በከፍተኛ ወጭ እያሽቆጠቆጧት ነበር ..የዜና አውታሮችም አገር ጥጋብ እንደሆነ ምርትም እንደተትረፈረፈ እየዘገቡ ነበር (እንዳሁኑ EBC) በዓሉም ሃምሌ 1965 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ … ይሄንና ይሄ የታፈነ ግፍና ሌላም የህዝብ በደል ተዳምሮ ንጉሱን በብርሃን ፍጥነት ከነዙፋናቸው አንኮታኮተ ኢትዮጲያንም ለሰሚው ወደሚዘገንን ወታደረዋ አገዛዝና ደም መፋሰስ ዳረጋት !!

ደርግ …በተመሳሳይ በርካታ ኢትዮጲያዊያን በተራቡበትና በእርሃብ በሚረግፉበት ወቅት የፓርቲ ምስረታ ገለመሌ በዓሉን መላዋን አዲስ አበባ በመብራትና በመፎክር አንዎጥቁጦ ሲያከብር ነበር ! ደርግም በተመሳሳይ ‹‹ጠላቶቸ …ሻእቢያ ገንይ ምናምን ከማለት ውጭ ስለውስጥ ችግሩ ትንፍሽ ሳይል ፌሽታውን አከበረ ….ዛሬስ ምን እያደረግን ነው … የእውነት ህዝባችን ፌሽታችንን ህዝባችን በዓላችንን የሚጋራበት የተረጋጋ ኢኮኖሚ ሰላም እና ዲሞክራሲ ላይ ነው …..? እንደኔ እንደኔ አዎ አገራችን በርካታ የልማትና የሰላም እምርታዎችን አስመዝግባለች ግን …በአደገኛ ሁኔታዎች ያሽቆለቆለችባቸው ሁነቶች ይበዛሉ … ስደቱ አሳሳቢ ነው …ከአገር ውጭ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ክፍለሃገራት ወደአዲስ አበባ የሚፈልሰው ህዝብ ሲታይ ‹‹እድገቱ የፈጠረው›› እያልን ማላገጡ መፍትሄ አይመስለኝም !!

አሁን ያለው የህዝብ ብሶት ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም ግን ህወሃትን እንደአንድ ዜጋ የምጠይቀው …ቅን ብልህና ከቂምና በቀል የፀዳ ስርዓት ለመገንባት ይነሳ … በገፍ እየጓፈፈ በየምክንያቱ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ጋዜጠኞች ጦማሪያን ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት አባላትና የሃይማኖት ሰዎችን ይፍታ ! መንግስት እንኳን ውሃ ቀጠነ ብሎ ያሰራቸውን ንፁሃን ቀርቶ በብዙ ጥፋት ውስጥ ያለፉ የህግ ታራሚዎችን በምህረት መልቀቁ ህዝባዊነት ሰበአዊነት ነው !! አዎ ‹‹ 40ኛ አመት የምስረታ በዓሉ ግማሹን አስሮ ግማሹን አስጨፍሮ ›› ሊሆን አይገባም !! ከየትኛውም ድግስ ከየትኛውም ጭፈራና ንግግር በላይ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ከህወሃት ኢህአዴግ የሚጠብቀው መሰረታዊ የአገሪቱ ችግሮች ያለምንም ምክንያት ድርደራ እንዲፈቱለት እንዲሁም ሃሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ የተለያየ ስም ተለጥፎባቸው ያታሰሩ ልጆቹን ጓደኞቹን የስራ ባልደረቦቹንና ወንድምና እህቶቹን እንዲፈታለት ነው !!

ሰላም !!

Image

በየመን የሚኖሩ የቀድሞ ኦነግ አባላት በኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር እየተመለመሉ ነው::በኬንያ ድርድሩ ቀጥሏል::

Minilik Salsawi በኬንያ የተደረገው የምልመላ እና ስብሰባ ጥሪ ሳይሳካ በተቃውሞ ታጅቦ መሰረዙ ታውቋል::በየመን በስደት የሚኖሩ የቀድሞ የኦነግ አባላት በወያኔ አጋዥነት በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አስተባባሪነት በሌንጮ ባቲ መሪነት ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ እየተመለመሉ መሆኑን በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገለጹ::ከወያኔ ጋር በኬንያ ድርድር እያካሄደ ያለውና በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር በየመን በመሰረተው ቅርንጫፍ አማካኝነት በወያኔ የደህንነት ሃይሎች እየታገዘ በየመን ለሚመለምላቸው የቀድሞ የኦነግ አባላት ከወያኔ አስፈላጊዉን በጀት እንደተመደበላቸው ለማወቅ ተችሏል::

የወያኔ እና የኦዴግ ዋና ግብ የአንድነት ሃይሎችን አዳክሞ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስፋፋት እንዲሁም በውጪ ላሉ የጎሳ ድርጅቶች አስፈላጊዉን አሟልቶ ወደ ሃገር ቤት መመለስ ሲሆን የቀድሞ የኦነግ አባላትን አሰባስቦ ወደ ሃገር ቤት ማምጣት ሌላኛው አላማቸው ነው በዚህም መሰረት በአቶ ሌንጮ ባቲ የሚመራ ቡድን በየመን እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ሲታወቅ ወደሰላማዊ ትግል መመለስ እንጂ ወያኔን ከስልጣን የማውረድ ግብ እንዳሌለው ለተመልማዮች ባዘጋጀው ኦረንቴሽን ላይ ገልጿል::

እንዲሁም ላለፉት 40 አመታት የታገልነው የመገንጠል ጥያቄ ምንም ውጤት ስላላመጣ በጋራ ከሕወሓት ጋር በመሆን ኦሮሚያን ማስተዳደር እና በግዴታ የሚጫንን ኢትዮጵያዊነት መቃወም የሚሉ ንግግሮች ለተመልማይ ስደተኞች አስደምጠዋል::ከሕወሓት ጋር አስፈላጊዉን ድርድር እንዳደረጉና ተመልሰው ወደ ሃገር ቤት ለሚገቡ ስደተኞች አስፈላጊ የደህንነት ከለላ እና ስራም እንደሚሰጣቸው እየተሰበከ መሆኑን ከአከባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ሲጠቁሙ በኬንያ እየተደረገ ያለውን ድርድር/ንግግር ተከትሎ ለስደተኞች ሊደረግ የታሰበው ሰበካ በሁለቱም ወገን ሳይሳካ ቀርቷል::በኬንያ የቀጠለው ድርድር ከኦሮሞ ተወላጆች ተቃውሞ እየቀረበበት ሲሆን ቀጣዩ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ጉዞ አለየለትም የሚሉ ወገኖች ቢከሰቱም ወደ ሃገር ቤት ለመግባት አስፈላጊዉን ሁሉ ከመስማማቱም በላይ ወደ ሃገር ቤት ለሚመለሱም ወገኖች አስፈላጊዉን ክፍያ ለማድረግ ከወያኔ ገንዘብ እንደተቀበለ ለግንባሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል::

ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ

• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፓርቲው ከትግራይ፣ እስከ ሞያሌ ጫፍ ዕጩ ማቅረቡ ለገዥው ፓርቲ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ሆኖበታል ያሉት ኢ/ር ይልቃል በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚደረጉት ጫናዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ ሰይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ 23 ዕጩዎችን አቅርበናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ዕጩ ያቀረቡ ፓርቲዎች ሳይቀር በሚዲያ ሲነገርላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት በቴሊቪዥን ቀርበው ‹ሰማያዊ በተደጋጋሚ ብንነግረው አልሰማም፣ በመሆኑም ሰኞ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል› ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሰማያዊ በምርጫው እንዳይሳተፍ ችግር መፍጠር እንደሚፈልጉ ነው፡፡›› ሲሉ ፓርቲው ላይ እየተፈጠረበት ያለውን ጫና ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በዛሬው ዕለት በኢቢሲ ቀርበው ሰማያዊ ይቅርታ ባለመጠየቁና ማስጠንቀቂያዎችን ባለመቀበሉ ነገ ሰኞ ጥር 9/2007 ዓ.ም ውሳኔ ያስተላልፋል ብለዋል፡፡

ከሌሎች ፓርቲዎች ሰማያዊን በመቀላቀል በፓርቲው ምልክት ለመወዳደር የወሰኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሰረዙ መደረጉና በሌሎች ዕጩዎች ላይም ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

Minilik Salsawi – ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የካቲት 6/2007 ዓ.ም ‹‹የምርጫው ሂደት በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት ነው!›› በሚል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የገዥው ፓርቲና የምርጫ ቦርድ አስፈጻሚዎች በፈጠሩት እንቅፋት እና ወከባ ፓርቲው ያቀረባቸው በርካታ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የምዝገባ ጊዜው እንዲያልፋባቸው መደረጉንና ከተመዘገቡ በኋላ መሰረዛቸውን ተግለጾአል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ዕጩ ተመዝጋቢዎች የተወለዱበት ዞን መሆኑ እየታወቀ ምስክር አምጡ በሚል ምክንያት እንዳይመዘገቡ መደረጋቸው ተገልጾአል፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉት ሁሉም ወረዳዎች የምርጫ አስፈጻሚዎች ጽ/ቤቶችን ዘግተው በመጥፋታቸው ዕጩዎች ሆን ተብሎ የምዝገባ ጊዜው እንዲያልፋቸው መደረጉን፣ በሰማያዊ ስር ለመመዝገብ የፈለጉ የሌሎች ፓርቲ አባላት ‹‹መልቀቂያ አምጡ!›› እየተባሉ እንዳይመዘገቡ ምርጫ ቦርድና ገዥው ፓርቲ እንቅፋት እንደፈጠሩባቸው ተገልጾአል፡፡

በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ፣ በሲዳማ፣ በጋምቤላ፣ በጋሞጎፋ፣ በምስራቅና በምዕራብ ጎጃም፣ ዕጩ ተመዝጋቢዎች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ታጣቂዎች ማስፈራሪያ፣ በአካባቢው ሽማግሌዎችና በእምነት ሰዎች በማውገዝ ከዕጩነት እንዲገለሉ ግፊት ተደርጎባቸዋል ሲል ፓርቲው ገልጾአል፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ክልል የገዠው ፓርቲ ታጣቂ ኃይል ዕጩዎችን በማሰርና መመዝገቢያ ደብዳቤዎችን መነጠቃቸውን፤ በሰሜን ጎንደር፣ በሲዳማና ከምባታ ዞኖች የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው መግለጫው አትቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር በደቡብ ኦሞ ዞን ሁሉንም መመዘኛ አሟልተው የተመዘገቡ 24 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች በምርጫ ቦርድ ደብዳቤ እንዲሰረዙ ተደርጓል ተብሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ስለሽ ፈይሳ ችግር ቢፈጠር እንኳ ችግሩን የሚፈታው ወይንም መመዘኛውን አላሟሉም ሊል የሚችለው የየአካባቢዎቹ የምርጫ ጣቢያ ሆኖ እያለ ምርጫ ቦርድ ደቡብ ኦሞ የተመዘገቡትን ዕጩዎች እንዲሰረዙ በደብዳቤ ማዘዙ የፖለቲካ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡

የምርጫ ሂደቱ በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት ነው!

ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እስካሁን ከተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድና የመንግስት አስፈፃሚ ተቋማት በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩና የፖለቲካ ምህዳሩም ለሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ፍትኃዊ እሰኪሆን ድረስ የነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ ዘመቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች እጩ ተወዳዳሪዎችን ለማስመዝገብ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የምርጫ አካባቢዎች በዕጩ ተወዳዳሪዎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ አባላትና በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ እንግልትና እንቅፋት የተፈጠሩባቸው ሲሆን ለአብነት ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
1. በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እጩ ተመዝጋቢዎች የተወለዱበት ዞን መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን ምስክር አምጡ በማለት እንዳይመዘገቡ ተደርገዋል፡፡
2. በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች በሙሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ፅ/ቤቶችን ዘግተው በመጥፋታቸው ምክንያት መመዝገብ በተደጋጋሚ የሄዱ እጩ ተመዝጋቢዎች ሳይመዘገቡ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርገዋል፡፡
3. በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በምርጫ አዋጁ መሰረት 1 እጩ ተመዝጋቢ ቅሬታ እስካልወቀረበበት ድረስ የመመዝገብ መብት እንዳለው እየታወቀ ነገር ግን የምርጫ ፅ/ቤት ሃላፊዎች የሌላ ፓርቲ አባላት ናችሁ ከፓርቲያችሁ መልቀቂያ ካላመጣችሁ በሚል ምክንያት በርካታ የፓርቲያችን እጩዎች ሳይመዘግቡ መልሰዋል፡፡
4. በሰሜን ሸዋ፤ በሲዳማ፤ ጋምቤላ፤ ጋሞጎፋ፤ በምስራቅና በምእራብ ጎጃም አካባቢዎች እጩ ተመዝጋቢዎችን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ታጣቂዎች በማስፈራራት፤በአካባቢ ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች በማሰወገዝ ራሳቸውን ከእጩነት እንዲያገሉ ተፅእኖና ግፊት ተደርጎባቸዋል፡፡
5. በደቡብ ክልል የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች እጩዎችን ሊያስመዘግቡ የሄዱ ተወካዮችን በማሰርና በእጃቸው የሚገኘውን የእጩዎች ማስመዝገቢያ ደብዳቤዎች በመንጠቅ የምዝገባ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርጓል፡፡
6. በሰሜን ጎንደር፤ በሲዳማና በከምባታ ዞኖች የፓርቲው እጩ አባላት በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡
7. በደቡብ ኦሞ ዞን የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልተው የተመዘገቡ የፓርቲያችን እጩዎች በ05/06/07(ማለትም የምዝገባው ጊዜ ካለቀ በኋላ)በደ/ቁ-አ573/ፖአ/ጠ470 ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ 18 የክልል ምክር ቤትና 6የተወካዮች ምክር ቤት በድምሩ24 እጩዎች እንዲሰረዙ ተደርጓል፡፡
እነዚህና ሌሎችም ጥፋቶች የሚፈፀሙት ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ነጻና ፍትሀዊ በሆነ የምርጫ ሜዳ እንዳይሳተፉ በማድረግ የአምባገነናዊን መንግስት የስልጣን ዘመን ለማስረዘም በዕቅድ የተፈፀሙ ድርጊቶች መሆናቸውን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎችም በማለፍ ፓርቲያችን ለመንግስትነት የሚያበቃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እጩ ተወዳዳሪዎችን በመላ የሐገራችን ክፍሎች አስመዝግቧል፡፡

ገዥው ፓርቲ በስልጣን ለመቆየት እንደ ስልት የያዘው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሕዝብ ዘንድ እምነት እንዲያጡ በብቸኝነት በተቆጣጠራቸው የመንግስት የመገናኛ ዘዴዎች ሥም ማጉደፍና ሕዝብም በምርጫው እምነት እንዲያጣ በማድረግ ከራሱ ደጋፊዎች ውጭ ሌሎች ዜጎች በንቃት እንዳይሳተፉ ማድረግን ነው፡፡ በመሆኑም ሕዝቡ በገዥው ፓርቲ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሳይዘናጋ የፈለገውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ በንቃት እንዲሳተፍና የመራጭነት ካርዱንም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ከህገ ወጥ አሰራር እንዲቆጠቡ ፓርቲያችን በአፅንኦት እያሳሰበ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የመሰረተውን ትብብር በማጠናከርና በምርጫውም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ውጤት ለማምጣት ሰማያዊ ፓርቲ ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም

የመጅሊሱን ሹም ሽር በመቃወም ድንገተኛና ደማቅ የፊኛ መልቀቅ ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ ተካሄደ! ‹‹ሲፈልግ ሾማቸው ሲፈልግ ሻራቸው!!›› አርብ የካቲት 6/2007

Image
የመንግስት እጆች ዛሬም በመጅሊስ ውስጥ እንደተዘፈቁ ያረጋገጠውን በቅርቡ የተካሄደውን ህገወጥ የመጅሊስ ሹማምንት ሹም ሽር በመቃወም ደማቅ ድንገተኛ ተቃውሞ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ ተካሄደ፡፡ ተቃውሞው ‹‹ሲፈልግ ሾማቸው ሲፈልግ ሻራቸው!›› በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ነበር፡፡ ህብረተሰቡ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ፊኛዎችን እና መፈክሮችን በመጠቀም መሪ ቃሉን በደማቅ ሁኔታ አንፀባርቋል፡፡ ተቃውሞው በወኪሎቻችን አማካኝነት ለመንግስት ያቀረብነው የ‹‹ነፃ መጅሊስ›› ጥያቄ ዛሬም ህያው የማታገያ አጀንዳ እንደሆነና ከወኪሎቻችን ጋርም እስከ ድል አብረን እንደምንቀጥል ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው፡፡
Image
በከፍተኛ መስዋእትነት በወታደራዊው ደርግ ዘመን ያገኘነው ተቋማዊ መብታችንን (መጅሊስን) በኢህአዴግ መንግስት ከተነጠቅን ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በይበልጥም የሃይማኖት መሪዎችን ምርጫ ‹‹በቀበሌዬ ካልሆነ አይሞከርም›› በሚል አይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ካድሬዎችን የሾመበት አጋጣሚ ‹‹መንግስት በመጅሊስ ውስጥ ጣልቃ ገባ›› የሚያስብል ከመሆንም አልፎ ህዝብ ትንሽም ቢሆን በተቋሙ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ በሩን የዘጋበት ታሪካዊ ሁነት ነበር፡፡ በቅርቡ ደግሞ ሲፈልግ ከያሉበት ጠርቶ በፖለቲካዊ ስሌት የሾማቸውን የመጅሊስ ህገወጥ ሹማምንት አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ ከመቀየር ባልከበደ ሁኔታ ሲሽራቸው ከርሟል፡፡ የሹም ሽሩ ድራማ በደም የተገኘውን መጅሊሳችንን ክብር ያጎደፈ፣ መንግስት ዛሬም ከመጅሊስ ለመውጣት ትንሽም ፍላጎት እንደሌለው ያሳየ፣ በመንግስት ጉያ ተሸሽገው ከህዝብ ተቃራኒ የቆሙ ወገኖች የነገ እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል በተግባር ያሳየ፣ እንዲሁም በመጅሊስ እና በሌሎች የመንግስት የፖለቲካ መዋቅሮች ውስጥ የሚካሄዱ ሹምሽሮች ከተመሳሳይ ቦታ በተመሳሳይ ‹‹ህግ›› የሚከናወኑ መሆኑን ከምንግዜውም በላይ በተግባር ያሳየ ነበር፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ ተቋሙን ዛሬ ላይ እጁን ተጠምዝዞ ተቀምቶ ህገ ወጦች እንዲፈራረቁበት ቢደረግም በተቋሙ ላይ ያለው የባለቤትነት ስሜት ግን አሁንም ህያው ነው፡፡ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል ዳር ሲያደርስ መጅሊስን እውነተኛ የህዝብ ተቋም እንዲሆን አድርጎ ነፃ ማውጣትም ትልቁ ግቡ ነው፡፡ መንግስት እያካሄደ ያለው ሹምሽር ህገ ወጦችን በህገ ወጦች መተካት በመሆኑ በራሱ ህገወጥነት ነው፡፡ ህዝቡም ተግባራዊ ምላሽ መስጠትን ጨምሮ ጉዳዩን በዝምታ እንደማያልፈው መግለፁ ይታወሳል፡፡ የዚህ ህዝባዊ ምላሽ አንድ አካል የሆነው የዛሬው የጁሙዓ መርሃ ግብር በተሳካ መልኩ ተከናውኗል፤ አልሐምዱሊላህ!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Image

Image
ስለ ህወሓት ልንሸማቀቅ ይገባልጌታቸው ሺፈራውለአገር ግንባታ በርካቶች በወደቁበት፣ የውጭ አገር ወረራን ለመዋጋት እልፍ አልዓፍ ጀግኖች በተሰውበት፣ አድዋን የአዲስ አበባ ከንቲባ ተወካይ ለ10 ደቂቃ ንግግር አድርጎ ‹‹ተከበረ›› በሚባልበት፤ የዛሬዎቹ ገንጣዮች የዶለቱበት የመጀመሪያው ቀን በማይወዷት አገር ሀብት ለወራት ያህል እየተከበረ ነው፡፡ ገንጣዮቹ አሁንም ስማቸውን እንኳ ባልቀየሩበት ያደረጉት ጦርነት ‹‹የአገር ግንባታ፣ ለኢትዮጵያውያን ነጻነት….›› እየተባለ እየተሞካሸላቸው ነው፡፡ የህወሓትና የኢትዮጵያ እንቆቅልሽ ቀጥሏል! ህወሓት ከዓለም የተለየ ‹‹ገዥ›› ነው፡፡ እኛም በዓለም ልዩና አሳዛኝ ተገዥዎች ሆነናል፡፡
ደቡብ አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ኤሲያ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ታጣቂ ቡድኖች የተፈለፈሉባቸው አገራት ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ታጣቂ ቡድኖች ደግሞ አንድም ከጨቋኝ የአገራቸው መንግስት አሊያም ከቅኝ ገዥዎች ነጻ ለመውጣት የሚንቀሳቀሱ ነበሩ፡፡ በመሆኑም ከአላማቸውም ባሻገር ነጻ አውጭነታቸውን በስማቸውም ይገለጻሉ፡፡ ሆኖም አብዛኛዎቹ ‹‹ነጻነት፣ አርነት›› የሚል ስም ቢይዙም ነጻ የሚወጡት ከአውሮፓውያኑ ስለነበር ከአገራቸው ክብር ጋር የሚቃረን አልነበረም ወይም አይደለም፡፡ እንደ ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ገብተዋል የሚባሉ አገራት ይገኙ የነበሩት ፓርቲዎች ሳይቀር ይህን ተገንጣይ ስሞች ሳይሆን አገራዊ አንዳንዶቹ ደግሞ አህጉራዊ ስም ይዘው ነው የተዋጉት፡፡ የጥቂት ነጮች አገዛዝ ደቡብ አፍሪካዊያንን ነጭ፣ ህንዳዊ፣ ጥቁር ብሎ በተለያዩ ቡድኖች ከፋፍሎ በሚገዛበት ወቅት የእነ ማንዴላ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንገረንስ ነበር ነጻ አውጭው፡፡ ሆኖም በጥቁሮች አሊያም በተወሰኑ ጎሳዎች ስም ‹‹ነጻ አውጭ ነን!›› አላሉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ከደቡብ አፍሪካም አልፈው አህጉራዊ ስም ይዘው ነው የታገሉት፡፡
በተመሳሳይ በሞዛምቢክ፣ አንጎላ፣ ዚምባብዌ የነበሩ ታጣቂ ቡድኖችና ፓርቲዎች አገራዊ ከዚያም አልፎ አህጉራዊ ስሞችን ይዘው ነው የተነሱት፡፡ ነጻ አውጭዎች ቢሆኑም ከአገራቸው በላይ አፍሪካንም ነጻ ለማውጣት መነሳታቸውን የሚያሳይ ስም ነበራቸው/አላቸው፡፡ በሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ዩጋንዳ፣ ሱዳንና ኮንጎ የነበሩትና ያሉትም በተመሳሳይ አገራዊና አህጉራዊ የነጻ አውጭነት ሚናን የያዙ ስሞችን መጠሪያቸው አድርገዋል፡፡ ለአብነት ያህል በአሁኑ ወቅት ችግር ቢገጥመውም ደቡብ ሱዳንን ነጻ አገር ያደረገው የእነ ሳልቫኪር ፓርቲ ‹‹የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጭ ንቅናቄ›› ነው የሚባለው፡፡ ራሱን በደቡብ ሱዳን ብቻ እንኳ አላጠረም፡፡ አሊያም ከዚህ ወርዶ ራሱን ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ ጎሳዎች ስም አልጠራም፡፡
በዓለም ገዥ ፓርቲ ሆኖ ነጻ አውጭ ስም ያነገቡት ፓርቲዎች በእጅ የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል ቲሞር ውስጥ ለበርካታ ጊዜ ገዥ ፓርቲ የሆነው የምስራቅ ቲሞር ነጻነት አብዮታዊ ግንባር፣ የኢልሳቫዶሩ ፋራቡንዶ ማርቲ ብሄራዊ የነጻነት ግንባር፣ የዶሚኒካ ነጻነት ፓርቲ ይገኙበታል፡፡ የእነዚህ ፓርቲዎች ‹‹ነጻ አውጭነት›› አገራዊ እንጅ ወደ ጎጥ የወረደ አይደለም፡፡ የቲሞሩ ገዥ ፓርቲ መጀመሪያ እንደ ፓርቹጋል ካሉ ቅኝ ገዥዎች ጋር የተዋጋ ፓርቲ ነው፡፡ ይህ ፓርቲ በተለያዩ ጊዜያት በምርጫ ተሸንፎ ለተቃዋሚዎች ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ አስረክቧል፡፡ ለአብነት ያህል እ.አ.አ በ2007ና 2012 ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ አጥቷል፡፡ የኢልሳቫዶሩ ገዥ ፓርቲም ብቻውን ሳይሆን ከሌላኛው የአገሪቱ ፓርቲ ጋር ነው አብሮ እየሰራ የሚገኘው፡፡ ይህ ፓርቲ በአብዛኛው እያሸነፈ የሚገኘው ከ40ና ከ30 በታች ድምጽ ነው፡፡ የዶምኒካን ፓርቲ ማዕከላዊነቱና ሌሎች አንዳንድ ፖሊሲዎቹ ከኢህአዴግ ጋር የሚያመሳስሉት ቢሆኑም የጎሳ ነጻ አውጭ አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት ከህወሓት ውጭ በዓለም የጎሳ (ብሄር) ነጻ አውጭ ነኝ የሚል ‹‹ገዥ ፓርቲ›› አይገኝም፡፡
ሻዕቢያ ‹‹የኤርትራ ነጻ አውጭ›› ስሙን ጥሎ አገራዊ ስም ሲይዝ የቀድሞ አቋሙን በመቀየር ድል ሲቀናው ትግራይ ከኤርትራ በተሻለ ከኢትዮጵያ ጋር ታሪካዊ ትስስር አላት ብሎ ወደ ምኒሊክ ቤተ መንግስት ያቀናው የአሁኑ ገዥ ፓርቲ ነጻ አውጭነቱን እንደተሸከመ ነው፡፡ ይህ ነጻን ህዝብ ነጻ የማውጣት እንቆቅልሽ አሁንም እወክለዋለሁ የሚሉትን ህዝብ መያዧና ከሌላው ጋር የረባ ግንኙነትና አንድነት እንዳይኖረው ማጎሪያ መሆኑን የብዙዎቹ እምነት ነው፡፡
ከኢትዮጵያም በላይ የደህንነት ችግር ያለባቸው አገራት የሚገኙ ፓርቲዎች እንኳ ከህወሓት የተሻለ አገራዊ ስም ያላቸው መሆኔ የኢትዮጵያውን ‹‹ገዥ ፓርቲ›› ለመንግስት መንበር የማይበቃ መሆኑን እንረዳለን፡፡ እየተበጣበጠች በምትገኘው ደቡብ ሱዳን አንድም በጎሳ መሰረት ነጻ አውጭ ሆኖ የተቀመጠ ፓርቲ የለም፡፡ የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የተባበሩት ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ የደቡብ ሱዳን ዴሞክራሲያዊ መድረክ፣ የደቡብ ሱዳን ሌብራል ፓርቲ፣…… የመሳሰሉት ስሞች ነው ያላቸው ናቸው፡፡ የእርስ በእርስ ጦርነት በሚንጣት ሱዳንም ቢሆን ፓርቲዎች አገራዊ ስም የያዙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ሌብራል ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ ብሄራዊ ኮንግረንስ፣ የሱዳዝ ባዝ ፓርቲ፣ ዴሞክራሲያዊ የአንድነት ፓርቲ….. የመሳሰሉትን የሚይዝ ነው፡፡ ታጣቂ ቡድኖችም ጭምር ይህን ያህል ነጻ አውጭ ስም አልያዙም፡፡ ሰላም አስከባሪ የሚጠብቃት ላይቤሪያ ፓርቲዎች የአንድነት ፓርቲ፣ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ጥምረት ለሰላምና ዴሞክራሲ…. የመሳሰሉትን ስሞች የሚጠቀሙ ናቸው፡፡
ህወሓት ይህንን የገንጣይ ስም በስያሜነት ሲጠቀም ጥቁር አሜሪካውያን ስለ ነጻነታቸው የሚታገሉበት ወቅት ነበር፡፡ ፓርቲው ይህን ስም ይዞ ሲመሰረት እነ ማርቱን ሉተር ኪንግና ሌሎችም የጥቁሮቹ መሪዎች ጥቁር አሜሪካውያን ከነጮች ጋር አንድ ካፍቴሪያ፣ ትምህርት ቤት፣ አውቶቡስና አገር ውስጥ እኩል እንዲገለገሉ ጥያቄ ያቀርቡበት የነበር ወቅት ነው፡፡ በአንድ ወቅት በአንድ አውቶቡስ ከነጮች ጋር መሄድ የማይፈቀድላቸው አሜሪካውያን ጥቁሮች አሁን እኩልነታቸው ተረጋግጧል፡፡ በትምህርት ቤት፣ አውቶቡስና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች አድሎና ጭቆና ይደርስባቸው የነበሩት ጥቁሮ አሁን ከአብራካቸው የወጣው ኦባማን ከአለም ትልቁ የስልጣን ማማ ላይ አስቀምጠዋል፡፡ በእርግጥ በዚህ ወቅት ነጭ አሜሪካውያን እንደሰው የማይቆጥሯቸው የነበሩት ጥቁር አሜሪካውያን ነጻ አውጭ ስምም ሆነ አላማ አልነበራቸውም፡፡ አሁንም ቢሆን አድሎና መገለል ሙሉ በሙሉ ከአሜሪካ ባይጠፋም ጥቁር አሜሪካውያን ግን ነጻ አውጭ አላስፈለጋቸውም፡፡ ምክንያቱም አገራዊ አላማ ይዞ እንደመታገል ያለ ሞራላዊ ጉዳይ ስለሌለ ነው፡፡
ለአሜሪካውያን ጥቁሮች ነጸነት ሲታገሉ በሞቱበት ወቅት ስሙን ‹‹ህወሓት›› ብሎ የሰየመው በጥቁሮች ዘንድ ነጻ ተደርጋ የምትወሰደው የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ግን እነ ኦባማ ስልጣን ላይ በወጡበት በአሁኑ ወቅትም በገንጣይ ስሙ ቀጥሏል፡፡ ህወሓት ራሱ ስልጣን በያዘበት ህዝብን ከማን ነው ነጻ የሚያወጣው? ከ90 በላይ የመከላከያ ሰራዊቱ አባል፣ የደህንነት መስሪያ ቤትና ሌሎቹም ተቋማት በእሱው ታጋዮች በተሞሉበት ህዝብን ከማን ነጻ ያወጣል? ኢትዮጵያ ማለት የአቶ መለስ ዜናዊ ታሪክና ዝና በእያንዳንዱ ተቋም አልፎ ቤት ለቤት እንዲዘመርባት የምትደርግ አገር ነች፡፡ ስፖርት፣ ጎዳና፣ ትምህርት ቤት፣ ……..ሁሉም በሟቹ የህወሓት አመራር ስም ተሰይመዋል፡፡ የህወሓት ባለስልጣናት፣ ካድሬዎች፣ ደህንነቶች፣ የመከላከያ አባላት በመላው የአገሪቱ ክፍል አዲስ ፊውዳል ሆነዋል፡፡ ታዲያ ማንን ከማን ነው ነጸ የሚያወጣው? ህወሓት ገዥ ፓርቲ እንደመሆኑ በውጭ ጉዳይ፣ በመከላከያ፣ በደህንነቱ፣ በአጠቃላይ በአገሪቱ በሚገኙት ስልጣኖች የትግራይን ህዝብ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን እያገለገልኩ ነው እያለን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ብሎም መንግስትን በትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም መንግስት እየመራሁ ነው እያለን ነው፡፡ መሪው በሞቱ ወቅት ደግሞ መለስ ሶማሊም፣ አፋርም፣ አማራም፣ ወላይታም፣…….ብቻ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አባል፣ ወኪልም ናቸው ብለውናል፡፡

እንዲህም ብለው ግን አሁንም ገንጣዮች ናቸው፣ አሁንም ‹‹አገር ገንቢዎች!›› ናቸው፣ አሁንም ‹‹ለሀገር አሳቢዎች›› ናቸው፣ አሁንም ዘራፊዎች ናቸው፡፡ አሁንም ገዥዎች ናቸው፡፡ ይህ እንቆቅልሽ በኢትዮጵያ ካልሆነ በስተቀር በየትኛውም አገር የለም፡፡ በፖለቲካም ነውር ይመስለኛል፡፡

‹‹ቅኝ ገዥ ነች፡፡›› ባለት ኢትዮጵያ ውስጥ ገዥ የሆነው ህወሓት ቢገድል፣ ቢዘርፍ፣ ቢያወዛግበን የሚገርም አይደለም፡፡ እሱን ሳያስበው እጁ ላይ የገባው ስልጣን ሞኝ (ጅል) አድርጎታል፡፡ የዓለም መሳቂያ! በእርግጥ እሱ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ለዓለምም የማይመጥን ገንጣይ ‹‹ገዥ›› ተሸክመን የዘለቅነው አሳዛኝ ተገዥዎች ልንሸማቀቅ፣ አንገት ልንደፋና ልናፍር ይገባል፡፡ ደግሞም የሚገድለው፣ የሚያስረው፣ የሚዘርፈው እኛውኑ ቢሆንም ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት›› እየተባለ ነው፡፡ ጅል (ሞኝ ) ባያፍር በዚህ ኢትዮጵያም ዓለምም የማይመጥነውን ስርዓት በመሸከማችን ልና

የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደመጋዝ ሳይሆን እንደ አጋዥ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ለሃገር ስኬት እና እድገት ለህዝብ ነጻነት እና መብት መከበር ለዜጎች ከእስር እና ስደት መዳን የሚረዳ እና ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡እርግጥ በኢትዮጵያ ያለው ወያኔ መራሹ አምባገነን ቡድን ማግባባትን እና መስማማትን አሊያም መደራደርን የሚጠቀመው ለመበላላት ሃገር ወዳዶችን ለማቀጨጭ አሊያም ለማጥፋት በመሆኑ በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር በመፍጠሩ የሕዝብ ችግሮች አግጥጠው ከመውጣታቸውም በላይ ሃግሪቷን እርቃኗን አስቀርቷታል::

የወያኔ ሰራሹ አምባገነን መንግስት ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሔ ሳይሰጥ ወደ ውስብስብና ግዙፍ ችግርነት እንዲያድጉ በቸልተኝነት በመፍቀዱ ያለ ጥርጥር ወደ ፖለቲካዊ ችግርነት አድጓል ፡፡ የወሎ ረሃብ እንደተነናቀ ወደ አብታዊ ማዕበልነት ተለወጠ፡፡ የሚሊተሪ ዲክታተራዊ አገዛዝ መናጠጥ፣ የቢሮክራሲያዊ በደል ማጠጥ፣ የሥልጣን መባለግና ያላግባብ መበልፀግ የአማጽያንን መፈልፈልና የተቃዋሚን ቁርጠኝነት መውለዱን ወለደ፡፡በአሁኑ ወቅትን ከባለፈው በባሰ መልኩ ሕዝባዊ የለውጥ አብዮቶች በውስጥ እና በውጪ እየተቀጣጠሉ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው::ይህ የሕዝብን ጥያቄ አለመመለስ የወለደው ሌላ ጥያዌ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል::

ዛሬም የህዝብን ኑሮና የሀገርን ውስብስብ ችግሮች በወቅቱ የመፍታት ቅን ልቦና ከሌለ ስልጣንን ለህዝብ ለማስረከብ ፍዋደኝነት ካልታየ በሃገሪቱ የተዘጋው የፖለቲካ ምህዳር ህግን ጥላ ባደረገ መልኩ ካልተከፈተ የፍትህ አካላት ከአምባገነን ባለስልጣናት መዳፍ ስር ካልወጡ እና ተመሳሳይ የሆኑ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግሮች በኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ ካልተፈቱ ዕጣ- ፈንታ ወዳዘዘው ውድቀት ማምራት ግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ስልጣኑን ይዣለሁ የሚለው አካል ዋንኛ ትኩረት በጠበንጃ የመተማመን የበላይነቱን ድርሻ ይውሰድ እንጂ የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራትና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጐች ወዘተ የነገዋ አገራችን ዕጣ-ፈንታ ይመለከተናል ማለት ኤጭ የማይባል ነገር መሆኑን ልብ ማለት ደግ ነው!ገዢ ነኝ የሚለውም ወያኔ ሃገር ወዳዶችን ስለሃገራችን ያገባናል የሚሉ ዜጎችን ሁሉ ከማግለል ከማሰር እና ከማሳደድ የማይቆጠብ ከሆነ ከገባበት አጣብቂኝ መውጣት ካለመቻሉም በተጨማሪ ወደ ማይወጣው ጥልቅ ጉድጓድ እንደሚወረወር ማወቅ ግድ ይላል::

ዕጣ-ፈንታችንን አናመልጥም፡፡ የዕጣ-ፈንታችን አካል ነን፡፡ የምንለው፣ የምናቅደው፣ የምንራዕየው ሁሉ የእኛው አካል ነው፡፡ በተናገርነው እንነገርበታለን፡፡ በደነገግነው እንቀጣበታለን፡፡ በደሰኮርነው እናፍርበታለን ወይም እንኮራበታለን፡፡ በተለይ መንግስት ስንሆን ባወጣነው ህግ እከሌ ከእከሌ ሳንል፣ ወገናዊና ኢፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ መተዳደርና መቀጣት አለብን፡፡የመንግሥትነታችን ትልቅ ቁም ነገር የህዝብን ደህንነትና የሀገርን ህልውና መታደግ ነው፡፡ ይህ ዋና ኃላፊነት ነው፡፡ ህዝብ እንዳይሸበር፣ እንዳይጠራጠር፣ ዕምነት እንዳያጣ ማድረግ፤ በአገሩ፣ በመንግሥቱና በኃላፊዎቹ ላይ የመተማመን ስሜት እንዲያድርበት ያደርገዋል፡፡የአስተዳደር ብስለታችን፣ የዲፕሎማሲያችን ጥራት፣ ስለፓርቲና ስለ ሀገር ያለን ግንዛቤ፤ የምንመራውን ህዝብ አመኔታና ተቀባይነት የሚያስገኘው ቁልፍ ነገር መሆኑን መቼም ቢሆን መቼም እንወቅ፡፡ የህዝብን የልብ ትርታ፣ የሀገር ወዳዶችንና ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ድምጽ እንደመጋዝ ሳይሆን እንደ አጋዥ በማየት ማግባባት፣ ማስማማት፣ ለሃገር ስኬት እና እድገት ለህዝብ ነጻነት እና መብት መከበር ለዜጎች ከእስር እና ስደት መዳን የሚረዳ እና ከመሪ የሚጠበቅ የብልህ እርምጃ ነው፡፡

የደቡብ ምስራቅ እዝ ውስጥ የተነሳው ውጥረት እየተካረረ ነው::2 ኮሎኔሎች ታስረዋል::

Minilik Salsawi በሰራዊቱ ውስጥ የዘረኝነት ጥቃት እየተፈጸመ ነው::የሰራዊቱ ተቃውሞ እንዳይስፋፋ ወያኔ ሰግቷል::በምስራቅ ኢትዮጵያ የሰፈረው የደቡብ ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባልት ከአለቆቻቸው ጋር የፈጠሩት አለመግባባት እየተካረረ መምጣቱን በቦታው የሚገኙ ወታደራዊ ደህንነቶች ያደረሱት መረጃ ጠቅሷል::ከቀድሞ በተለየ ሁኔታ የመከላከያ ሰራዊቱን እየሰበሰቡ መገምገም ማሰር የቀጠለ ሲሆን ከመሃል አገር ተመድበው የመጡ አዳዲስ አባላት በሰራዊቱ መካከል ገብተው ውጥረቱን ለማርገብ እና ለማዘናጋት ቢያስተባብሩን እንዳልተሳካ ታውቋል::

በሕገመንግስቱ በማእረግ እድገት እንዲሁም በጥቅማጥቅሞች ዙሪያ የተነሳው ጥያቄ ከወር በፊት አራት ወታደራዊ መኮንኖች መታሰራቸው ሲታወስ ከሁለት ቀን በፊት በተደረገው ግምገማ ኮሎኔል አብደላ ጫልቺሳ እና ኮሎኔል ተከተላቸው በወጉ የተባሉ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ እስር ቤት መወርወራቸው ታውቋል::የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ሕገመንግስቱ መሰረት ያደረገ አስተዳደር በኢትዮጵያ የለም ሕዝቡ በፖለቲካ በኢኮኖሚ ተጎዳ የሚል ጉዳዮችን በውይይት መድረካቸው ጊዜ አንስተው ቢወያዩበትም ጉዳዩ ተስፋፍቶ ከውይይት መድረክ ወደ ክርክር እና ተቃውሞ የተቀየረ መሆኑን እና በእዙ ውስጥ ውጥረት እንዲነግስ ማድረጉን የጠቀሱት ምንጮች የማእረግ እድገትን በተመለከተ ለአንድ ብሄር ብቻ እንደሚሰጥ እና ሃገሪቱን በጋራ እስካገለገልን ድረስ የእንጀራ ልጅ የሚባል ነገር የለም አድልዎ እየተደረገ ነው የሚል ተቃውሞ የተፈጠረ ሲሆን በጥቅማ ጥቅም ዙሪያ እንዲሁ እንደ ማእረግ እድገቱ የዘረኝነት ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታ እያሰሙ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::መከላከያ ሰራዊቱ ያነሱት ጥያቄ/ተቃውሞ ወደ ሰሜን እና ምእራብ እዝ እንዳይስፋፋ በጥንቃቄ የተያዘ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::

Image

ተቃዋሚዎችን በጥላቻ የሚመለከተው ወያኔ አሁንም የክስ ዋራንት ለመቁረጥ አሰፍስፏል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተጭበረበረ ፖለቲካ አገር አስተዳድራለሁ የሚለው ወያኔ ተቃዋሚዎች በመንግስታዊ ተቋማት ላይ አፍራሽ ተልእኮ ያራምዳሉ በማለት ሊያጠቃቸው መነሳቱን በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ያለእፍረት እየተነፈሰ መሆኑ በመስማት ላይ ነን::በፍትህ እና በምርጫ ቦድ እንዲሁም በማስተዳድራቸው ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ዲሞክራሲ እንዳያብብ እንቅፋት እየሆኑ ነው ያለው ወያኔ ራሱን የዲሞክራሲ ተበቃ አድርጎ በመሳል በአፍራሾች ላይ ውርምጃ እውስዳለሁ ሲል ሰበብ እየፈጠረ መሆኑን አድበልብሎ የሰራቸው እና የፈጠራ ውጤቶቹ የሆኑ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚባሉትን ካድሬዎቹን ሲያስደሰኩር ሰምተናል::

በመፍረከስከስ ላይ መሆኑን የሚያሳብቅበት ወያኔ በአንድነት ፓርቲ ላይ ዬማፍረስ እንዲሁም መኢአድን የመበጥበጥ ስራ ከሰራ በኋላ ተበደልም የሚሉ የፍትህ ያለ በሚሉበት ሰአት በሌላ ወንጀል ሰማያዊን ለማሸግ ማሰፍሰፉን እርግጫው ይናገርበታል::በአገሪቱ እያደረገ ያለው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ከማህበራዊ ድቀት ጋር ተደምረው ለምርጫ ቢቀርብ እንደሚሸነፍ ያረጋገጠው እና አከርካሪው የተመታው ወያኔ ላለመሞት በሚያደርገው መፈራገጥ ያሸንፉኛል ያላቸውን ፓርቲዎች እና ግለሰቦችን ጠልፎ በመጣል በመሳሪያ ሃይሉ ተማምኖ ወደ እስር ቤት ለመወርወር ማሰፍሰፉ አምባገነንነቱ ምን ያህል አግጥጦ እንደወጣ ያሳያል::

ዲሞክራሲያዊ ተቄማት የሚባሉት እንደ ምርጫ ቦርድ እና የፍትህ አካላት ነጻ እና ገለልተኛ ባልሆኑበት አገር ነጻነትን እና መብትን ለማስከበር የሚታገሉ ድርጅቶችን ለመዋጥ ባሰፈሰፈ የፖለቲካ ዘንዶ ራሱ እንደሚዋጥ ያላሰበው ወያኔ ነጻ እፓርቲዎች እና ግለሰቦች ሊታዘዙልኝ አልቻሉም እንደኔ ሊያስቡ አልቻሉም በሚል በጥላቻ የተሞላው ወያኔ የፓርቲ አመራሮችን ሰብስቦ ለማሰር ማሰፍሰፉ በሃገሪቱ እየተስፋፋ ያለው ህገወጥ መንግስታዊ አሸባሪነት ሃገር ወዳዶችን እና ለውጥ ፈላጊዎች አጥፍቶ ለመጥፋት ምን ያህን እንደተነሳ በገሃድ ይመሰክራል::

የፍትህ አካላት እና ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ከነሚዲያ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር በዋሉበት አገር ዜጎች በሰበብ አይታሰሩም አይሰደዱም አይገደሉም ማለት ዘበት ነው::ኢሕአዴግ መሰሎቹን ይዞ ወደ ሚያጭበረብረው ምርጫ ለመዝለቅ እንዲያስችለው ጠንካሮችን ከጨዋታው ውጪ በማድረግ ግስጋሴውን ተያይዞታል::የአውሮፓ ህብረት የመሰሉ ሃገሮች ለውጥ አልባ በሆነ ምርጫ እስጥ በታዛቢነት አንሳተፍም በማለት እጃቸውን የሰበሰቡ ሲሆን ወያኔ እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ አጋሮቹን ይዞ ሆይሆይታውን በመቀጠል ንጹሃንን በማሰር ፓርቲዎችን በማፍረስ ላይ ነው::ይህንን የተቃወሙ የለውጥ ሃይሎችንም በአፍራሽነት በመፈረጅ ላይ መሆኑን የራሱ ሚዲያዎች እየተናገሩ ነው::

ህዝብን በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስክ ቁም ስቅሉን እያሳየው ነው:: የሃገሪቱ ህገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ እና ውጪ በፖለቲካ መስክ የአይናቸው ቀለም ያላማረ ተቃዋሚዎች ይደበደባሉ ይታሰራሉ ይገረፋሉ በፍርድ ቤት በሃሰት መረጃ ከህግ ትእዛዛት ውጭ የረዥም አመት እስር ይከናነባሉ:: እንደ መንግስት ባለስልጣናት ሳይሰርቁ ደፋ ቀና ብለው ያፈሩት ንብረት ይወረሳል::ከዛም አለፍ ካለ በአደባባይ ይረሸናሉ:: በደህንነት ሃይሎች ይገደላሉ:: ይህ የሚያሳየው የጸጥታ ሃይሎች ከህግ በላይ ሆነው ፍትህን መግደላቸው ነው:: የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳይንቀሳቀሱ የጸጥታ ሃይሎች እንቅፋት ከመሆን አልፈው ወደ አንድ ፓርቲ ያደላ ኮንትሮባንዳዊ ፖለቲካ እየፈጸሙ ነው::ሕዝቦች ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ አምባገነኖች የሚያደርሱት ጭቆና ትግሉን ያፋፍመዋል እንጂ አያዳክመውም:: በሃገር ውስጥ ይሁን በውጪ ሃገር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለወያኔ መውደቅ ከበፊቱ በበለጠ ለትግላችን ስኬት እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በመገስገስ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻነታችንን በማረጋገጥ የወያኔን አምባገነን ስርአት በመጣል የጋራ አገራችንን ለመገንባት የምንነሳበት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን ለማረጋገጥ እወዳለሁ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላትና 2 ፓይለቶች ጠፉ!!

ጥር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት ሳምንት በፊት 5 የአየር ሃይል የጥበቃ አባላት እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው እንዲሁም 2 ፓይለቶች ከድሬዳዋ አየር ሃይል ጠፍተዋል። የጥበቃ አባላቱም ሆነ ፓይለቶቹ ያሉበትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ይህንን ተከትሎ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከመቶ አለቃ ማእረግ በላይ ያላቸውን አየር ሃይል አባላት ሰብስበው ግምገማ አካሂደው ነበር።

ጄ/ል ሳሞራ “የአየር ሃይል አባላት ለምን ይከዳሉ? አሁን ያላችሁትስ ምን ታስባላችሁ?” የሚል ጥያቄ ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን፣ የአየር ሃይል አባላቱም ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር በደል እንደሚደርስባቸው፣ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ክፍያ እንደሚከፈላቸው፣ በመኖሪያ ቤት እጦት እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል። መኮንኖቹ በርካታ ችግሮችን ዘርዝረው ያቀረቡ ቢሆንም፣ ጄ/ል ሳሞራ ችግሮችን ከመስማት ውጭ ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ሄደዋል።

የአየር ሃይል አባላት ሞራል ( ስሜት) መዳከም ገዢው ፓርቲ በሩሲያ ቅጥር አብራሪዎች ላይ እምነቱን እንዲጥል አድርጎታል። የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ እና ቴክኒሻን ብርሃን ግደይ ከመቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ጋር በመሆን ስርአቱን አናገለግልም ብለው ሄሊኮፕተር ይዘው መጥፋታቸው፣ የህወሃትን የዘር ፖለቲካ መሰረት እንዳናጋው ምንጮች ይገልጻሉ። ለወትሮው ይታመኑ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የአየር ሃይል አባላት ሳይቀሩ የሚታመኑ ሆነው ባለመገኘታቸው፣ባለስልጣናቱ አይናቸውን የውጭ ቅጥረኞች ላይ እያዞሩ ነው።

ስርዓቱን አናገለግልም ብለው የጠፉት የአየር ሃይል አባላት የተቃዋሚ ድርጅቶችን ተቀላቅለው እየታገሉ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአፍሪካ መሪዎችም ሆነ የሌሎች አገራት መንግስታት ለስብሰባ ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ጊዜ ለደህንነት ስራም ሆነ ለልዩ ጥበቃ የሚመደቡት የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው በማለት የሌሎች ክልሎች የደህንነት አባላት ቅሬታ ማሰማታቸው ታውቋል።

የ24ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ከተካሄደ በሁዋላ ለግምገማ ከተጠሩት ምድብተኛ የደህንነት ሰራተኞችና የጸጥታ አካላት መካከል አንዳንዶች፣ ” ለመሪዎችና ለእንግዶች ደህንነት የሚመደቡት ጠባቂዎች የአንድ አካባቢ ተወላጆች ብቻ መሆናቸው፣ “ስርአቱ የእናንተ አይደለም፣ አናምናችሁም” የሚል መልክት አለው በማለት በድፍረት ለገምጋሚዎች ተናግረዋል።

“በብሄራችን ምክንያት ተበድለናል” ያሉት የደህንነት ሰራተኞችና ጠባቂዎች፣ ደረሱብን ያሉዋቸውን በርካታ ችግሮች ዘርዝረው አቅረበዋል። ” በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪዎች ራሳቸውን እያደራጁና መረባቸውን እየዘረጉ በመጡበት ሁኔታ የምናምነውን ሰው እንመድባለን” የሚል መልስ ግምገማውን ከሚመሩ መሪዎች የተሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች በተሰጠው መልስ ማዘናቸውን በግምገማው የተሳተፉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

Image

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ለ የካቲት 11 ተቀጠሩ፡፡ በ26/05/2007 ዓ.ም. የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ ይቀየሩልን ሲሉ በፅሁፍ ያቀረቡት አቤቱታ የግራና የቀኝ ደኛው ውድቅ ሲያደርጉት የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ በራሴ ፈቃድ ከችሎቱ እራሴን አንስቻለሁ ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ታዳሚ ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ሰባተኛ ተከሳሽ ጦማሪ አቤል ዋቤላ ትላንት ከፍርድ ቤት ወደ ማረሚያ ቤት በሚመለስበት ወቅት እጅህ በካቴና ለምን አልታሰረም ብለው የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች እጄን በውሻ ሰንሰለት አስረው አሳድረውኛል ብሎም ዛቻና ዘለፋ ደርሶብኛል እንደዲሁም ማአከላዊ ታስሬ እያለሁ በደረሰብኝ ድብደባ ጀሮዬ ላይ ጉዳት ስለደረሰ ለማደዳመጥ ጀሮዌ ላይ የማረገውን ድምፅ ማዳመጫ መሣሪያ በማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ተነጥቂያለሁ ሲል እንባ በተናነቀው ንግግር ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ለምን ይህ እንደተደረገ እና ያደረገውን ሰው በፅሁፍ እንዲያቀርብ ለየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም እንዲያቀርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ሦስቱ ጋዜጠኞች እና ስድስቱ ጦማሪያን ደኛው ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ አግባብ አይደለም ያለው ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 2519 መሠረት የ500 ብር ቅጣት ይቀጡ የነበረው በስሜታዊነት ነው በማለት መቀጫውን ውድቅ አድርጓል፡፡ በየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃል በአዲስ የመሀል ዳኛ መሠረት ይሰማል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : መጨውን የኢሕአዴግ የሞኖፖል ምርጫ ጥሪ ተቀብለው ወደ ምርጫ እንገባለን ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ያስመዘገቧቸውም እጩ ተወዳዳሪዎች አስፈላጊዉን ገንዘብ እና ጥቅማ ጥቅም በመስጠት የመደለል ስራ ሊጀመር ነው ሲሉ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ጠቆሙ::የተቃዋሚ ድርጅቶች እያቀረቡ ያሉትን እጩዎች ስም እና ሙሉ አድራሻ ለኢሕአዴግ ጽ/ቤት የሚያስተላልፈው የገዢው ፓርቲ አጋር ተቋም የሆነው የምርጫ ቦርድ በክልል ወኪሎቹ እጮዎችን ከደህንነት አባላት ጋር በመሆን የማግባባት ስራ እንዲሰራ እና ከኢሕአዴግ ጽ/ቤትም አስፈላጊው በጀት ተመድቦ በሰፊው አፋጣኝ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ተወስኗል::

አብዛኛዎች የብሄር ድርጅቶች ወደ ምክር ቤቱ እንዲገቡለት የሚፈጋው ኢሕአዴግ ለታማኝ ተቃዋሚው ኢዴፓ እና በመድረክ ፓርቲ ውስጥ ላሉ ተለጣጭ ወሬ አቀባይ ተለጣፊ አመራሮች ወንበር እንዳዘጋጀላቸው ታውቋል::የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ዲፕሎማቶች ወያኔ ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲወያይ እያደረጉ ያለው ጥረት አንድነትን በማፍረስ እና መኢአድን በመበጥበጥ ቀጣይ እኩይ ስራዎችን በመስራት ዲፕሎማቶቹ ያቀረቡትን ሃሳብ ለማጣመም ቢሰራም ወያኔ እንዳልተሳካለት ታውቋል::ወያኔ የሰራቸው ጸረ ተቃዋሚዎች እኩይ ተግባራት በዲፕሎማቶች ተቀባይነት አለማግኘቱ ታውቋል::

ሆዳሞችን እና አንሾካሻኪዎችን በዚህ በሰለጠነ ዘመን ላይ በመፍጠር የሚታወቀው የወያኔው ጉጀሌ ተጨማሪ አምስት አመታት በመግዛት ኢትዮጵያን ለመበታተን እና ሃግራዊ አንድነት እና ፍቅር ለማጥፋት ቢሰራም አልተሳካለትም:: እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው ወያኔ በአለም አቀፍ ደረጃ ወንጀሉ የታወቀለት እና በሕግ የሚፈለግ አሸባሪ ድርጅት መሆኑን የሚወጡ ዘገባዎች ሲያመለክቱ ኢትዮጵያውያን ሃገራችንን ከመንግስታዊ አሸባሪ ውድመት በጋራ ሁነን የመከላከል የዜግነት ግዴታ አለብን በማለት ለመናገር እወዳለሁ::

በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው

የአንድነት ፓርቲ አላማዎችና እሴቶች በገዢው ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ ህገወጥ ሴራ አይጠፋም!!! – ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ

ገዢው ፓርቲ ለጻፋቸው ህጎችም ሆነ ይህን እንዲተገብሩ ኃላፊነት የወሰዱትን ሰዎች ክብር በሚያዋርድ መንገድ፤ በየደረጃው ያሉ ምርጫ ቦርድ ኃላፊዎችም ለመዋረድ ፈቃደኛ ሆነው በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አባላት አንድ ድምፅ ለማግኘት ለተቸገረ፤ ነገር ግን ለገዢው ፓርቲ ለመላላክ ቁርጠኛ ለሆነ ግለሰብ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድነት ፓርቲ የተቋቋመበት መሰረት የምርጫ ቦርድ ዕውቅና ሳይሆን በእያንዳንዱ አባላት ዘንድ የሚቀጣጠለው የነፃነት ስሜት እና ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲን መንፈስ፣ አላማዎቸና እሴቶች በዚህ ዓይነት እኩይ ደባ ከአባላትና ደጋፊ አዕምሮ ማውጣት አይቻለም፡፡

የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በገዢው ፓርቲ ደህንነት የተደራጁ የፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ያልሆኑ ሰዎች ያካሄዱትን ህገወጥ ስብሰባ ጉባዔ ነው በማለት እውቅና ሰጥቻለሁ ሲል፤ የተሰበሰቡት ሰዎች የአንድነት አባላት መሆናቸውን እና የጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ መሆናቸውን አረጋግጣችኃል ወይ? ለሚል ቀላል የጋዜጠኛ ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡ ዕቅዱም አንድነትን እንደተቋም ማፍረስ ስለነበር ይህን ሊያስፈፅም ለሚችል ተላላኪ መስጠታቸውን በይፋ ከተናገሩ በኋላ በማግስቱም የፓርቲውን ፅ/ቤት በጠብመንጃ አፈሙዝ አስወርረው ለህገወጥ ቡድን በህገወጥ መንገድ አስረክበዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በዚህ ዓይነት ህገወጥ ድርጊት የሚፈርስ አይደለም፡፡ የአንድነት አባላት በየትም ቦታ የምትገኙ ሁሉ ይህን ህገወጥ እርምጃ በፅኑ እየተቃወማችሁ ለነፃነትና ለኢትዮጵያዊነት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመከፍል ዝግጁ መሆን ይኖርባቸኋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ስልት የሚያምን በመሆኑ ይህን ትግል በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል አበክሮ ይስራል፡፡ እያንዳንዱ አባልም አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ሳይደናገጥ ለሰላማዊ ትግል ያለውን ፅናት እንደሚያስቀጥል እምነታችን ነው። በአንድነት ስራ አስፈፃሚ እምነት አሁን ባለው ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ተቀበረዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል።

በመሆኑም ስርዓቱ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚመች የአስተሳሰብ ለውጥ እሰካላመጣ ድረስ ምርጫን በየአምሰት ዓመት የሚደረግ ክብረ በዓል አድርጎ ለማድመቅ እና የህዝብ ሀብት ለማባከን በሚደረግ ሂደት ተሳተፊ ለመሆን አዲስ ፓርቲ መመስረትም ሆኖ አሁን ካሉት ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ መታገል የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱም ልከ በአንድነት ላይ እንደተደረገው በሀይል እንዲፈርሱ የማይደረጉበት ምንም ዓይነት ዋስትና አለ ብለን ስለማናምን ነው። ከዚህ በኋላ በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው የሚል ፅኑ እምነት አለን፡፡ ነገር ግን አሁንም የፓርቲ ፖለቲካ አላበቃም ብለው የሚያምኑ የአንድነት አባላት ካሉ በራሳቸው ነፃ ውሳኔ ወደ ፈለጉት ፓርቲ ተቀላቅለው የመታግል መብታቸው የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ካለበት አምባገነናዊ ስርዓት ተላቆ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሸጋገር ለማድረግ ህዝቡ የትግሉ ባለቤት ሆኖ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ እኛም የበኩላችንን ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ቁርጠኞች ነን፡፡

ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡

‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
Image

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች በዛሬው እለት ካንጋሮ ፍርድ ቤት ቀርበዋል::
Image
– ጋዜጠኛ ኤዶም ጸጉሯን በመላጨት ኢፍትሃእኢነት እና ዘረኝነት መስፋፋቱን በይፋ ተቃውማለች::
– የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ዳኛ እንዲቀየርላቸው ማመልከቻ አቅርበዋል::
Minilik Salsawi
በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ዞን ዘጠኝ ጦማርያን ጋዜጠኞች እንዲሁም የዲብርሃን አዘጋጅ የሆነው ዘላለም ወርቃለማሁ እና ከጋምቤላ በአሸባሪነት የተፈረጁ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል::በኢትዮጵያ የሆላንድ ኤምባሲና ሌሎች ዲፕሎማቶች በፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመከታተል ተገኝተዋል::

በዛሬው እለት ጋዜጠኛ ኢዶም ጸጉሯን በመላጨት በወያኔ መንግስት እና በእስር ቤቱ ያለውን በፍርድ ቤቱ የሚታየውን አድልዎ የሚደርሰውን ኢፍትሃዊነት እና ዘረኝነት በመቃወም አሳይታለች::..ተከሳሽ ተብለው በወያኔ የተፈረጁት ወገኖቻችን ዳኛው እንዲቀየሩላቸው የተየቁበትን አቤቱታ ከታች ያንብቡት::
ImageImage

Image

በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ‹‹ፀረ- ሰላም ህፃናት››

አቶ ቀኖ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ በጥበቃነት ይሰራሉ፡፡ አቶ ቀኖና ጎረቤቶቻቸው ሰብሰብ ሲሉ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተለይ ኢህአዴግ ስለሚወስዳቸው ህገ ወጥ እርምጃዎች፣ ስለተቃዋሚዎች ጥንካሬና ድክመት… የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ያወራሉ፣ ይወያያሉ፣ በሚያከራክሯቸው ነገሮችም ይከራከራሉ፡፡ ይህ የእነ አቶ ቀኖ ሰፈር ሰዎች የውይይት መድረክ በእነሱ ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ ጉዳዩ በመደጋገሙ ህፃናት ልጆቻቸው ሳይቀር ‹‹ሰማያዊ፣ አንድነት፣ መድረክ፣ ኢህአዴግ…..›› እያሉ የአቅማቸውንና የገባቸውን ያህል ያወራሉ፡፡ ቤተሰቦቻቸው ሲከራከሩና ሲያወሩ ከሰሙት! በዚህ አቋማቸውም ህፃናቱ ‹‹ፀረ ሰላም›› ተብለው ታስረውበታል፣ ተደብድበውና ይቅርታ ጠይቀውም ተለቀዋል፡፡

ማክሰኞ ጥር 19/2007 ዓ.ም ነው፡፡ ከቀኑ 11፡30 አካባቢ አራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መስከረም 2 ት/ቤት ተማሪዎች የሆኑት 14 ያህል ህጻናት ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ ህፃናቱ እንደወትሯቸው ከት/ቤተ መልስ እየተጨዋወቱ፣ እየተቀላለዱ፣ እየተሯሯጡ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ መሃል ላይ ግን ቤተሰቦቻቸው በተደጋጋሚ የሚያነሱትን ጉዳይ አንስተው መከራከር ጀምረዋል፡፡ የ13 አመት እድሜ ያለውና የ6ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው የአቶ ቀኖ ልጅ ‹‹ኢህአዴግኮ ፈሪ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲን ይፈራዋል›› ይላል፡፡ ጓደኛው ደግሞ ‹‹ኢህአዴግማ የሚፈራው አንድነትን ነው፡፡›› ይላል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ‹‹መድረክ የሚባል ፓርቲምኮ አለ፡፡ እሱንም ይፈራዋል፡፡ ኢህአዴግ ፈሪ ነው!›› ይላል፡፡ ሌሎቹም ቤተሰቦቻቸው ውሃ፣ መብራትና ኔትዎርክ ሲጠፋ፣ ኑሮ ሲወደድ፣ ሙስና ሲያስመርራቸው በስርዓቱ ላይ ከሚያሰሙት ሮሮ መካከል የሚያስታውሱትን እየጠቀሱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይከራከራሉ፣ ያወራሉ፡፡ ይቀልዳሉ!

ይህኔ ነው አስገራሚው ነገር የተከሰተው፡፡ ፖሊስ 14ቱንም ህፃናት በ‹‹ፀረ ሰላም›› እንቅስቃሴያቸው ከእነ ሙሉ የትምህርት መሳሪያቸው በቁጥጥር ስራ ካዋላቸው በኋላ በጥፊና በእርግጫ እያለ ወደ ወረዳ 7 ፖሊስ ጣቢያ ይወስዳቸዋል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ከደረሱ በኋላም ‹‹ተንበርከክ!›› ተብለው ‹‹ማን ነው ሰማያዊ፣ አንድነት፣ መድረክ እያለ ሲያወራ የነበረው?›› እየተባሉ ህፃናት ላይ ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ድብድባ ይፈፀምባቸዋል፡፡ ህፃናቱ ‹‹ፀረ ሰላም›› ለተባለው እንቅስቃሴያቸው ቅጣትና ማስፈራሪያ ከተደረገባቸው በኋላ ‹‹ከአሁን በኋላ አይደግመንም›› ብለው ይቅርታ ጠይቀው በ‹‹ፖሊስ ሆደ ሰፊነት›› ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ ከእስር ተለቀዋል፡፡

እነዚህ ህጻናት ‹‹ዳግመኛ አይለምደንም!›› ብለው ይቅርታ ባይጠይቁ ኖሮ ታስረው ሊያድሩም ይችሉ ነበር፡፡ ምን አልባትም ፖሊስ ‹‹ያልተፈቀደ ቅስቀሳ አድርገዋል፣ ህገ መንግስቱን ለመናድ ጥረዋል፣ ህዝብን ለማናወፅና አመጽ ለመቀስቀስ ተደራጅተው ተንቀሳቅሰዋል፣ ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን እየሰሩ ነው….›› የሚል ክስ እንደማይመሰርት እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ እስካሁን ፖሊስ ሲያቀርባቸው ካየናቸው አስቂኝ የቀጠሮ ማራዘሚያ ‹‹ምክንያቶች›› አንጻር ‹‹አብረዋቸው የሚማሩት ሌሎች ግብረ አበሮቻቸው አልተያዙም፣ ቢወጡ አሁንም ተመሳሳይ ‹ፀረ ሰላም› ተግባር ይፈፅማሉ፣ መረጃ ይደብቁብኛል›› በሚል ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ ላለማለቱ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

ስርዓቱን ለመከላከል ሲባል እስሩ እዚህ ደርሷል!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
January 31,2015
የገዢውን ፓርቲና መንግስትን ሽፍትነት ያጋለጠው አንድነትን የማፍረስ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በኢትዮጵያዊን ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም!!!
ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል፡፡
ገዢው ፓርቲና መንግሰት በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲነበብ ያደረጉት የፖለቲካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከወረቀት አልፎ በተግባር እንዳይታይ ግብዓት መሬቱን ፈፅመዋል፡፡ በዚህ ፀያፍ ተግባር ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆኖ ተቋማት በታሪክ ተገቢው የውርደት ቦታ እንደሚይዙ እምነታችን ነው፡፡ ይህ ህገወጥ አካሄድ ህጋዊ መሰመር እንዲከተል የበኩላቸሁን ድርሻ የተወጣችሁ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በሀገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁሉ በተለይ በገዢው ፓርቲ እኩይ ሴራ በሀስት ተወንጅላችሁ በወህኒ ቤት ለምትማቅቁ ታጋዮች ታሪካችሁ በወርቅ ቀለም ተፅፎዋል፡፡ በቀጣይም ያለምንም መዘናጋት እና ተሰፋ መቁረጥ በምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሀገራችን ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት ትንሳኤ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡
የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በህገወጥ መንገድ ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት አንድነት ፓርቲ አባላት እና በአንድነት አባልነት በማይታወቁ የገዢው ፓርቲ ጥርቅሞች ለተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያነገብነው የነፃነት መንፈስ በምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ሰርተፊኬትና ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኝ ስለአልሆነ ለነፃነት የምናደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል የምንቀጥል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአንድነት መዋቅሮች እና የአንድነት አባላት ለዚህ ህገወጥ ቡድን በግልፅ እውቅና እንዲነሱ እንጠይቃለን፡፡
ፓርቲያችን በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ተፈትነው ለወደቁ ተቋማት እድል ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ወሰኖ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ጥር 22/ 2007 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የፓርቲያቸን ፅ/ቤት በፖሊስ ተወሮ የፓርቲው ንብረት ያለምን ህጋው ርክክብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎዋል፡፡ በአሰተዳደር የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ቤት የማሰለወጥ ህጋዊ ሰርዓት እንዳለ ቢታወቅም ህገወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔን በፖሊስ ወረራ ለማሰፈፀም የተሄደበት መስመር ገዢው ፓርቲና መንግሰት አሁንም ከጫካ አሰተሳሰብ ያለመውጣቸውን እና የአውራ ፓርቲ ፍልስፍናቸውን በማናለብኝነት ለመተግበር መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ትእዛዙን ያስተላለፈው ክፍል መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
ሰለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት እንዲጎለብት ፍላጎት ያለችሁ ሁሉ ይህን እኩይ ተግባር በማውገዝ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወሰዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!
ጥር 22/ 2007 ዓ.ም
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

Minilik Salsawi እየተፍረከረከ ያለውና የመተማመን መንፈስ የጠፋበት የወያኔው ጁንታ ባለፈው ወር ያደረገውን የደህንነት ሃላፊዎች ስብሰባ ውስኔን ተከትሎ ከትግራይ ክልል ብቻ የተመለመሉ 2800 ሰዎች ለደህንነት ስልጠና አዲስ አበባ ገብተው መጠቃለላቸው ተሰምቷል::በደህንነት ሃላፊዎቹ ውሳኔ መሰረት በሌላው ክልል ዜጎች ላይ ያለው እምነት የሞተ ስለሆነ በደህነንቱ ስራ ላይ ስልጠና እንደማይሰጣቸው ታውቋል::ከክልሎች የደህንነት ተቋሙን የሚቀላቀሉ ማንኛቸውም ዜጎች እድሉ እንደማይሰጣቸው እና ያሉትንም ከደረጃቸው ዝቅ ያሉ ቦታዎች በመመደብ ሃገራዊ እና መንግስታዊ የምስጢር መረጃዎችን እንዳያገኙ መከላከል ያስፈልጋል የሚሉት የደህንነት ሃላፊዎቹ የደህንነት ተቋሙ ውስጥ መተማመን እንዲስፋፋ አድርገዋል ሲሉ ከክልሎች የመጡ ደህንነቶችን ወንጅለዋል::

መረጃውን የሰጡኝ ለኢሚግሬሽን እና ደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንዳሉት አዳዲስ ስልጠና ተሰቷቸው የሚመደቡ ደህንነቶች አስፈላጊውን ጥቅማ ጥቅም እና በፈለጉበት አገር ላይ ለወደፊት ኑሮ የሚሆን መኖሪያ ቤት ሳይቀር እንደሚገነባላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል::በደህንነት ተቋም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አለመተማመን መንገሱን ያወሱት ምንጮቹ በገሃድ ከምናየው የባለስልጣናቱ ውንብድና በተጨማሪ የሃገር (የብሄራዊ ጥቅም)ምስጢር ሳይቀር ለውጪ ሃይሎች እየተሸጠ መሆኑን ገልጸዋል::እንዲሁም ህገመንግስቱን እና ተቃዋሚ ሃይሎችን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች የደህንነት ሃላፊዎቹ በደህንነት አባላቱ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲሸረሸር ያደረገ መሆኑን ሲናገሩ ራሳቸው ሃላፊዎቹ የሚፈጥሩት ጫና አለመተማመኑን አስፍቶት እያለ የትግራይ ተወላጆች ባልሆኑ ዜጎች ላይ መደፍደፉ እንደማያዋጣ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

የሕወሓት የደህነንት ተቋሙ የትግራይ ተወላጆችን መልምሎ ወደ አዲስ አበባ ያመጣበት ሌላው ምክንያት ከዚህ ቀደም የደህነንት ተቋሙ አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በጦር ሰራዊቱ እና በፖሊስ ሰራዊቱ ውስጥ ከተራ ወታደርነት እስከ መኮንንነት ማእረግ ተሰቷቸው ሰርገው እንዲገቡ የተደረገ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል::በተለይ በፖሊስ ሰራዊቱ ውስጥ የፖሊስ ሳይንስ ሙያ ሳያጠኑ በከፍተኛ የአመራር ቦታዎች ላይ እና በየፖሊስ ጣቢያ አዛዥነት ላይ የተመደቡ የደህንነት አባላቱ በዜጎች ላይ ከባድ የሆነ ሰቆቃ እየፈጸሙ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::

#‎Ethiopia‬ ፖሊስ የህዝብነው ያሉ አንደበቶች በሀይል በትር እንዲዘጉ ተደረገ የኢትዮጵያ ፖሊሶች ለተቀጠሩለት ህገ መንግስት ሳይሆን ለአዛዦቻቸው ታማኝነታቸውን ዳግም አረጋገጡ ከነፍሰጡር ሴት እስከ ሽማግሌና አሮጊት የበቀል እርምጃ መብቴን ያስከብርልኛል ባሉትና በተማመኑበት ፖሊስ ተወሰደባቸው ::

phpBB [video]

በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሃሰት ምስክርነት የሰጠው ግለሰብ ታወቀ:: Minilik Salsawi
Image
ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ወጣት ሄኖክ ተስፋዬ ይባላል፡፡ ሁልጊዜ አርብ በመስጊዶች እየተገኘ ንፁሀን የእስልምና እምነት ተከታዮችን በሀሰት ውንጀላ የሚያሳስር የወያኔ ጆሮ ጠቢ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችውን ወጣት ወይንሸት ሞላን የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለመከታተል በሄደችበት ወቅት ፀጉሯን ጨምድዶ ከፎቅ ላይ እየጎተተ በማውረድ ከፖሊሶች ጋር በመሆን ከፍተኛ ድብደባ አድርሶባታል፡፡

በወቅቱ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ለደረሰው ድብደባና ስቃይም ተጠያቂ የሆነ ሰው ነው፡፡ይህ ወጣት በብዙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ በሀሰት ምስክርነት በፍርድ ቤት የሰጠ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም መንግስት ሰማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ እየሰራው ባለው ሴራ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ነን በማለት ፓርቲው እንደተከፋፈለ ለማስመሰል ከባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እየወሰደ መሆኑ ታውቋል፡፡
Image

-ከመጭው የኑሮ ውድነት ጉዳት ለመዳን በጋራ ተነስተን ይህንን ወንበዴ መንግስት ማፍረስ ይጠበቅብናል::
Minilik Salsawi የወያኔው መንግስት ለግሉ ዘርፍ ያለው አመለካከት ደካማ መሆኑ እና ከፖለቲካ ባለስልጣናት ጋር ቁርኝት ያላቸው ነጋዴዎች ለመክበር የሚያደርጉት ሩጫ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጣራ እንዲነካ አድርገውታል::እንዲሁም የኢኮኖሚ ውንብድና በሃገሪቱ ላይ እየተፈጸመ ነው::የስራ አጦች ቁጥር መጨመር ሃገሪቱን የወንጀለኞች መናኸሪያ እያደረጋት ነው::በአገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና እንቅስቃሴ ዋነኛው የኢኮኖሚው ማነቆ ከመሆኑም በላይ የፍትህ እና የንግድ ስርኣቱ መላሸቅ የኢኮኖሚ ቁጥጥሩን ስላ ላላው ለዋጋ ንረቱ መንስኤ ናቸው::

በአላቂ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ይከሰታል በሃገር ውስጥ ምርቶች ላይም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በሚቀጥለው አንድ አመት ይመጣል የግሉ አምራች ዘርፍ ጥሬ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ የተወሰነ የቀረጥ ክፍያ አለመኖሩ እና የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሰኛቸው በየጊዜው እየቀያየሩ የህገር ውስጥ ምርቶች እንዲጎዱ የማኑፋክቸሪውም ዘርፍ እንዲዳከም በማድረግ ችግር እንዲፈጠር አድርገዋል::

የባንኮችን መዳከም የስራ አጥነትን የስደትን የፖለቲካ ተጽእኖን የህዝቡን ምሬት ለመረዳት ለማሻሻል ምንም የማይሰራው የወንበዴዎች ስብስብ ባለስልጣኑ በሞኖፖል ንግዱን ይዞታል የውጪ ዜጎች ህገወጥ የኢኮኖሚ ስርኣት ዘርግተዋል ከፍተኛ ብዝበዛ በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ እየተደረገ ነው::ሕዝቡ ዳግም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያዘገመ መሆኑን አውቆ በጋራ በመነሳት ይህንን ወንበዴ መንግስት መጣል ያለበት መሆኑን መገንዘብ ሲኖርበት ለመጭው ትውልድ ከወንበዴዎች የጸዳች ሃገር የማስረከብ የዜግነት ግዴታ አለብን::

የኢህአዴግ ሴራ ከሸፈ::
አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡

የኢህአዴግና የምርጫ ቦርድ ድራማ ተዋናይ እያጣ ነው::ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ጻፍኩለት ያለውን አየለ ስሜን አጥቷል :: ምርጫ ቦርድ ለአቶ አየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ደብዳቤ መስጠቱን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሀላፊ አቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ከዚህ ቀደም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ዛሬ በምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው የነበሩት አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ከእነ አቶ አየለ ቀደም ብለው የተወሰኑ ወጣቶች ከፓርቲው ውጪ ይሰበስቧቸው የነበሩ ሰዎችን የጥፋት ተልዕኮ በመረዳት መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡
በእኔ እምነት ከዚህ ቀደም በፓርቲው ውስጥ በተደረገ ምርጫ ለራሳቸው የሰጡትን ድምጽ ብቻ ያገኙት አቶ ትዕግስቱ አወሉ ብቻቸውን ከመቅረታቸው በፊት እነ አየለ ስሜን በመከተል ይቅርታ እንደሚጠይቁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
Image

የሃገሪቱን አንጡረ ሃብት ለስለላ በመመደብ ሕዝብ ላይ ሽብር ታውጇል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ኢሕአዴግ ውስጥ በተነሳው የብሩህ ተስፋ ክሽፈት የመጣ በባለስልጣናቱ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት አመራሮችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። ባለፉት 24 አመታት በህዝብ እና በሃገር ላይ የተደረገው ከፍተኛ የሆነ በደል እና ዘረፋ በሕዝቡ ዘንድ ጥርስ እንዳስነከሰባቸው እና መጪው ጊዜ ይጨልምብናል ብለው ከፍተኛ ስጋት ስላደረባቸው በአራት ቡድኖች የተከፋፈለ በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ እና በመላው ሃገሪቱ የተበተነ የድህንነት እና የስለላ ሃይል ማሰማራታቸው ታውቋል።

የለውጥ ሃይሎች እና የዲያስፖራው ህዝባዊ ተቃውሞ በርትቶ እና ገኖ መውጣት፣በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣የካድሬዎች እንቢተኝነት፣ የውጪ ሃይሎች ጫና፣ የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ የሃገሪቱን እና የሕዝቡን አንጡረ ሃብት ስድሳ ከመቶውን ካለምንም እውቅና በዘፈቀደኝነት ለደህንነት እና ለስለላ ተግባር የመደቡት ከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን እንደገና መዋቀሩን ታውቀዋል።በሕወሃት የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ዳግም የተዋቀረው በየአከባቢው ከመንደር እና ቀበሌ ጀምሮ እስከ ከተሞች የገጠር ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በወያኔ ላይ ደባ ይሰራሉ ይፈጸማሉ ይመከራሉ የተባሉ እያንዳንዱን የዜጎች እንቅስቃሴዎች ሪፖርቶችን በትጋት በመሰብሰብ ወደ መሃል አገር በመላክ መታፈን ያለባቸው መገደል ያለባቸው ደብዛቸው መጥፋት ያለባቸውን ሰዎች በተመለከተ ከበላይ በሚተላለፍለት ትእዛዝ መሰረት መፈጸም ዋናው ስራው ነው።

ወያኔ የሚጠራው መጪው ምርጫ ሕዝቡ በ1997 እንዳደረገው አሁንም እንዲሁ ቂሙን በካርድ ይገልጽብናል በማለት የሚሰጋው ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የሃይል እርምጃ በመጠቀም ለማክሸፍ የሚያስችለው በየትኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሊሆን እንደሚችል ስለላውን ተያይዞታል፤በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች የካድሬዎች እንቢተኝነት የውጪ ሃይሎች ጫና የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ ማጣፊያው አጥሮት የሃገሪቱን ግማሽ በጀት የሚሆነውን ለደህንነት እና ለስለላ ተግብር በማዋል ከፍተኛ የሆነ አደጋ በሃገር ላይ አውጆ ሕዝብን እያሸበረ ይገኛል።

Image

ተቃዋሚ ሃይሎች ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ሰብረው በመግባት ስርአቱን ማፍረስ ያለባቸው ወቅት ነው::
Minilik Salsawi : ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የፖለቲካ የምጣኔ ሃብት እና የማሕበራዊ ቀውስ እና ውጥረት ተከትሎ የባለስልጣናት አረመረጋጋት ታክሎበት በገዢው መደብ የተዋቀረው የደሕንነት ተቋም መናጋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ የላኩት መረጃ ጠቁሟል::እንደውስጥ አዋቂ ምንጮች ዘገባ ከሆነ የደህንነት አባላቱ ቡድን እና ብሄር በመለየት በሃላፊዎቻቸው ላይ ያላቸውን ጥላቻ እና ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን ለአንድ ብሄር ብቻ ተለይቶ የሚደረገው የበላይነት አድሎአዊ አሰራር ፍትሃዊነትን ሳይሆን የበታችነታችሁን ያሳብቅባቹሃል የሚሉ ጠንካራ ቡድኖች ከኢሚግሬሽን እና ደህንነት መምሪያ አከባቢ መከሰታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል::

የደህንነት አባላቱ በዜጎች መካከል በሚደረግ አድሏዊ አሰራር ለሃገር ይጠቅማሉ የተባሉ አባላትን በየክፍለ ሃገሩ በማዘዋወር ከችሎታቸው እና ከሰለጠኑት የደህንነት ሙያ ጋር የማይገናኝ ስራ ላይ በመመደብ መረጃ አምጡ ማለት የስርአቱን ዝቅጠት ከማሳየቱም በላይ በቀበሌ ካድሬዎች እና በመንደር ጆሮ ጤቢዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን አሜሪካ እና እስራኤል ሰልጥነው በመጡ የአማራ እኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል የደህንነት አባላት ማሰለል ስር አቱ ምን ያህል መዋቅሩን እንደሳተ እና በሰለጠኑ ዜጎች ላይ ሃገራዊ እምነት እንዳሌለው ያሳያል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል::

በውጭ አገር ሰልጥነው የመጡ የደህንነት አባላት ወደ ሃገራዊ የደህንነት መረጃ ሃይሎች እና ጉዳዮች እንዳይጠጉ የሚደረግ ሲሆን በቦታው ከዚህ ቀደም የተመደቡም ቢሆኑ በመረጃ መውር ውስጥ እንዳይሳተፉ ሲደረግ የአንድ ብሄር ተወላጆች በዚህ ላይ እንዲቀሳቀሱ መደረጉ ለስር አቱ ሰዎች አደጋ እና የመዋቅር መናጋት የፈጠረ ሲሆን አንዳንድ የሕወሓት አባላት አብረውን ውጪ አግር ሰልጥነው የመጡ አባሎቻችን የት ሄዱ ለምን አብረውን አይሰሩም በማለት በመዋቅሩ ውስጥ አደጋ ሆነው በመገኘት መናጋቱን እንዳጦዙት ታውቋል::

እንደ ምንጮቹ ከሆነ በአሁኑ ውቅት በሰራዊት ውስጥ እና በደህንነቱ ውስጥ የመዋቅር መናጋት አለመተማመን እና የእርስ በርስ ፍትጊያዎች በስፋት እየታዩ በመሆኑ በሃገር ውስጥ እና በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎች ይህንን ክፍተት እና የመዋቅር መናጋት እንዲሁም የውስጥ ሽኩቻን ተገን በማድረግ ሰርገው በመግባት ለስርአቱ መውደቅ ተጨማሪ ሃይል ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል::

Image

አለመተማመኑ እና ክፍፍሉ እየሰፋ መቷል::የእርስ በርስ መወነጃጀሉም ተጧጡፏል::Minilik Salsawi

ሕወሓት በራሱ መልክ እና ቅርጽ የፈጠረው የመከላከያ ሚኒስቴር ስር ካለው ከጦር ሃይሎች መኮንኖች የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው የወያኔ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እርስ በራሳቸው መወነጃጀላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ በመግባት በግምገማ እየተፋተጉ መሆኑን ታውቋል::በዘረፋ እና መረጃ በመሸጥ:አሳልፎ ለጠላት ወገን በማስተላለፍ ወንጀል መፈራረጅ የጀመሩት የጦር መኮንኖቹ አብዛኛዎቹ የመንደር ጎጥ ለይተው ሲጠቋቆሙ እና ሲመሰካከሩ የታየ ሲሆን ለእረፍት ከሃገር ውጪ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች በአስቸኳይ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ተጠይቋል::

በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ ከንፈራቸውን የነከሱ በርካታ ከኮሎኔል በታች ያሉ የጦር መኮንኖች በቀጥዩ ግምገማ ላይ በመንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ የሚገልጹበት መድረክ እንደሚዘጋጅ የተነገረ ሲሆን ላለፉት ሁለት ቀናት የተደረገው እና አሁንም በቀጣይነት በመኮንኖች ክበብ እና በተለያዩ የመምሪያ አደራሾች ውስጥ በከፍተኛ መኮንኖች እና የጦር መምሪያ ሃላፊዎች ላይ የቀጠለው ግምገማ ውጠቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የሆነው ሌ/ጄ. ሳሞራ የኑስ ዋናው አትኩሮ ሲናገር የነበረው በሙስና እና በመረጃ ንግድ ላይ የተሰማራችሁ የጦር መኮንኖች ምስጢራችንን አሳልፋችሁ ሸጣችኋል እና ብትጠነቀቁ መልካም ነው ካልሆነ እርምጃ እንወስዳለን ሲል የዛተ ሲሆን እርምጃ የሚወሰድባቸው ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ተናግሯል::

ከጦር ሰራዊቱ ውስጥ ከአስረአምስት ቢሊዮን ብር በላይ አላግባብ ባክኗል የተባለው የሙስና ግምገማ በመኮንኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የቃላት አተካሮ እና አለመግባባት እየፈጠረ መሆኑን ምንጮቹ ለምንልክ ሳልሳዊ ተናግረዋል:: ይህንን ተከትሎ አንዳንድ አደገኛ የተባሉ የጦር መኮንኖችን ለማባረር በጡረታ ለማሰናበት እና ለማሰር የታቀደ ሲሆን አትኩሮት የሚደረግባቸው በሰራዊቱ ውስጥ ተከስቶ ያለውን አለመተማመን እና ክፍፍል ተከትለው ከስርአቱ በተጻራሪ ወገን ቆመዋል ጥያቄ ያበዛሉ የተባሉ የመለየት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል ምንጮቹ አክለው::

ተጨማሪ መረጃ (EDIT) : የሃገሪቱን አንጡረ ሃብት ዘርፈው ሃገሪቱን በውጪ ብድር ዪመራሉ ብድሩም ከዘረፋ አልተረፈም:: የሚገርመው እያንዳንዱ የጦር መኮንን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከመዝረፉም ባሻገር ለውጪ ሃይሎች መረጃ በመሸጥ ወያኔንን እርቃኑን አስቀርቶታል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሰላም አስከባሪ ስም የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በሚሊዮቾች ዶላሮች በኢትዮጵያ የጦር አለቆች ተጭበርብሬአለሁ የሚል ስሞታ አሰምቷል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image

ቅዳሜ ጥር 9/2007አዲስ አበባ ዛሬ ሌሊት በትግሉ መፈክሮች አሸብርቃ አደረች! ተቃውሞውን እና ለትግሉ ያለውን ቁርጠኝነት በተለያዩ መንገዶች ሲገልፅ የቆየው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አሁንም በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እየገለፀ ይገኛል።

የግራፊቲ መፈክሮቹ በቦሌ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በመካኒሳ፣ በቺቺኒያ፣ በአየር ጤና፣ በጦር ሀይሎች በሚገኘው መጅሊስ ቢሮ አካባቢ፣ በላንቻና በጎተራ፣ እንዲሁም በሌሎች ሰፈሮች ተፅፈው ያደሩ ሲሆን የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎችም በሁኔታው መደናገጣቸውን ማወቅ ተችሏል።

በግራፊቲው ከተፃፉት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:–

«የጨለማ ፈራጆች!»
«ኮሚቴው የህዝብ ነው!»
«ሂጃብ መለያችን!»
«ትግሉ ይቀጥላል!»
«ፍትህ ለኮሚቴው!»

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!