“የውስጥ ችግራችሁ በራሳችሁ የሚፈታ ነው።” ኦባማ የትነበርክ ታደለ
ኦባማ ነገሩን ይበልጥ ግልጽ አድርገውታል። ዛሬ ከሰአት በሁዋላ ከኬኒያ ሲቪል ማህበራት ጋር በብዙ ጉዳዮች ላይ ወይይት ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ የኬንያውያን የውስጥ ችግሮች በኬንያውያን በራሳቸው ብቻ ነው የሚፈታው ብለዋል።
ነገሩን ይበልጥ ግልጥ ሲያደርጉትም ” ከቀዝቃዛው ጦርነትና ከቅኝ ግዛት ማብቅያ በሁዋላ ሀያላን ሀገራት አሜሪካንን ጨምሮ ማን በስልጣን ላይ ይቀመጥ በሚለው ሁሉ በታዳጊ ሀገሮች ላይ ስንወስን ቆይተናል። እውነቱን ለመናገር ግን ይህን ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ቀይረነዋል። አሁን አሜሪካ የምትሰራው የራስዋን ጥቅሞች በማስጠበቅና በሚመቻት መልኩ ነው።” ካሉ በኋላ ህዝቦች ለሚያነሱት ዴሞክራሲያዊና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍትሄውን ራሳቸው ማምጣት አለባቸው።” ብለዋል።
በቅርቡ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄዳቸው “መቶ በመቶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ወንበር የተቆጣጠረን መንግስት ዲሞክራሲያዊ ነው የሚል እውቅና እንደ መስጠት ነው።” ሲሉ ሲቃወሙ ለሰነበቱት ወገኖች በተዘዋዋሪ መልስ የሰጡ ይመስላል። ይህም ሱዛን ራስን ጨምሮ የተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ምርጫ መቶ ፐርሰንት ዴሞክራሲያዊ ነበረ ማለታቸው መነሻው ይህ እንደሆነ ለመገመት የፖለቲካ ተንታኝ መሆን አይጠበቅብንም።