አራት ልጆቻቸው በእስራኤል ጦር ውስጥ አገልግሎት የሰጡት ኢትዮጵያዊ አባት በሀገሬው ባለስልጣናት የመኖሪያ ፈቃድ መከልከላቸው ተዘገበ::
ኢትዮጵያዊው የ 55 አመት አባት የቀድሞ ሚስታቸውና አራት ልጆቻቸው በ 1980 ዎቹ እንደፈረንጆቹ ወደእስራኤል ከተሰደዱ አይሁድ ኢትዮጵያዊያን ውስጥ ይገኙበታል፡፡ ቤተሰቡ ወደእስራኤል ከገባ በኋላ ሙሉ የእስራኤል ዜግነት ከማግኘቱ በተጨማሪም አራቱ ልጆች አድገው በእስራኤል ጦር ሀይል ውስጥ ብሄራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በቅተዋል፡፡
ይሁን እንጂ እኒህን አራት ልጆች አፍርተው ለእስራኤል የሰጡት አባት ለረጅም ጊዜ በሀገራቸው ኢትዮጵያ ከቆዩ በኋላ በ2013 እአአ ላይ ወደቤተሰቦቻቸው ጋር መሄዳቸውና በዛው በእስራኤል ኑሮን መጀመራቸው ነው የተነገረው፡፡ ዘግይቶም ቢሆን ግለሰቡ የጊዜያዊ ቪዛቸው ቀነ ገደብ በማለቁ በእስራኤል ከቤተሰባቸው ጋር ለመኖር የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለማግኘት ጥረት መጀመራቸው ቢነገርም የእስራኤል ባለስልጣናት ግን ለግለሰቡ መኖሪያ ፈቃድ እንደከለከሏቸው ይባስ ብሎም በህገወጥ መንገድ ያለፈቃድ በእስራኤል ለመኖር ሞክረዋል በሚል መታሰራቸው ነው የተዘገበው፡፡
መላ ቤተሰባቸው እሰራኤላዊ ሆኖ ሳለ በእስራኤል ለመኖር የሚያስችል ፈቃድ የተነፈጉት የእኚህ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በርካታ የዘር መድሎ በኢትዮ-አይሁዳዊያን ላይ ያደርሳል ተብሎ የሚታማውን የእስራኤል መንግስትን በእጅጉ እያሳማው የሚገኝ ቢሆንም እንኳን ግለሰቡ በፍርድ ቤት ሙግትም ቢሆን ፈቃዱን ያገኛሉ የሚል ተስፋ መኖሩን አንዳንድ የወሬ ምንጮች ዘግበዋል፡፡
ይህ ምንም የዘር መድሎ የለበትም ። የአገሪቱን ህግ ማክበር ወይም አለማክበር ጉዳይ ነው ። የሰውየው 10 ልጆቹም አገልግሎት ይስጡ እንበል ። እነሱ ስላገለገሉ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ይችላል የሚል ህግ እስከሌለ ድረስ ሁለት የማይገናኝ ነገር አታገናኙ ። ህጉን አክብሮ ይኑር ሰውየው ። ካላከበረ ደሞ አይገባውም ።
እኔ በጣም የሚገርመን እነዚህ ፈላሻ የሚባሉ ሰዎች አገራቸውን ኢትዮጵያን ክደው ወደማያቁዋቸውና ወደማይፈልጉዋቸው ዘረኞች እስራኤል አገር መሄዳቸው ነው። እስራኤል አገር ውስጥ ያለው ዘረኝነት በጣም አስከፊ ነው። በተለይ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያለው ሰው እንደሰ ብዓዊ ፍጡር አይቆጠርም። እነዚህ ፈላሾች እንደ ማንኛውም የፖለቲካ ችግር እንዳለበት የአገራችን ሰው የፖለቲካ ጥገኝነትና የስደተኝነት መብት በሚሰጣቸው አገር መኖር ሲገባቸው ዘረኝነት የመንግስት መተዳዳሪያ በሆነበት አገር ዜግነት ወሰደው የባርነትና የወርደት ኑሮ አቸውን በፍቃዳቸው ተያይዘውታል። እስራኤል ጥሩ አገር ከሆነች ለምንድ ነው የፍልስጥኤምን ሕዝብ አፍና በማሰቃየት የምትገዛው? በመሆኑም ጥቁር እስከሆነ ድረስ ተራ ወታደርም ሆነ ጄኔራል ወይም ሚኒሴቴር የጽዮናዊነት ገፈት ቀማሽ ነው። ጽዮናዊነት ደግሞ ዘረኝነት ነው። ስለሆነም ፈላሾች ቁጭ ብላችሁ በእርጋታ አስባችሁ ወደ እናት አገራችሁ ወደ ኢትዮጵያዊነት መመለስ አለባቸሁ። የሚያዋርዳችሁንና የሚያስንቃችሁን የእስራኤል ዜግነት አሽቀንጥራችሁ ጣሉት።