ሰማያዊ ቀለም በኢህአዴግ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል

• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን አስገብቷል›› ምክትል ሳጅን መላኩ
• ‹‹አብዮት እየጠራ ያለው ኢህአዴግ ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
Image
በትናንትናው ዕለት ፖሊስ የጥምቀትን በዓል ለማስተባበር በቀጨኔ መድሃኒያለም የተሰበሰቡ የበዓሉ አስተባባሪዎችን ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን ስላስገባ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳትለብሱ›› ሲል ማስጠንቀቁን ተወካዮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለበስ ያስጠነቀቁት የቀጨኔ ማዘዣ የወረዳ 4 ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ሳጅን መላኩ የጥምቀት በዓልን ለማስተባበር በቀጨኔ መድሃኒያለም የተሰበሰቡትን 150 ያህል ወጣቶች ‹‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን አስገብቷል፣ ቲሸርቶቹ አዲሱ ገበያ አካባቢ እንደሚገኙ መረጃ አግኝተናል፡፡ ማንም ሰው ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለብስ፡፡ ትዕዛዙ ከበላይ አካል የመጣ ነው›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ተወካዮቹ ለጥምቀት ያዘጋጁዋቸው ቲሸርቶች ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸውና ከመልበስም እንደማይቆጠቡ በመግለጻቸው ጉዳዩ ባለመግባባት ተቋጭቷል፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ፍቅረማሪያም ፖሊሶቹንና የበዓሉን አስተባባሪዎች ለማስታረቅ ጥረት ቢያደርጉም ፖሊሶቹ ‹‹ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ በመሆኑ እኛ የምንወስነው ነገር የለም፡፡›› በማለታቸው ባለመግባባት ተጠናቅቋል፡፡ ከቲሸርት በተጨማሪ ሰማያዊ ዣንጥላም እንዳይያዝ ፖሊሶቹ መከልከላቸውን የበዓሉ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ስለ ሁኔታው ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ኢህአዴግ ህዝቡን ስለማያምነው የማያስደነግጠው ነገር የለም፡፡ በደነገጠ ቁጥር ህዝብን የሚከለክለው ለዚህ ነው፡፡ አብዮት እየጠራ ያለው ራሱ ኢህአዴግ ነው፡፡ ምን ያህል ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ በሩ ዝግ እንደሆነ፣ ይህንም ሰብሮ ለመውጣት የተዘጋጀ ኃይል እንዳለ፣ ከዛ ውስጥ ሰማያዊ አንዱ መሆኑን ያውቀዋል፡፡›› ሲሉ የኢህአዴግን የስጋት ምንጭ ከምን እንደመነጨ ገልጸውልናል፡፡ ኢህአዴግ ህዝቡን በሆነ ባልሆነው ለማሸማቀቅና ለመከልከል ቢሞክርም ለውጡ እንደማይቀር፣ ፓርቲያቸው ይህንን ለውጥ ለመምራት የተዘጋጀ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ እንዲህ ከሰጋም ‹‹አዲሱ ገበያን እንዳያቃጥለው እሰጋለሁ›› ብለዋል አቶ ዮናታን፡፡

በሌላ ዜና የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ንግድና ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ሰማያዊ ቲሸርት (የደንብ ልብስ) ተሰርቶ መጥቶላቸው የነበር ቢሆንም በቀለሙ ምክንያት እንዳይለበስ በመከልከሉ ቢጫ ቀለም ያለው ሌላ ቲሸርት እንደተሰራላቸው ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን›› ካሰራቸው ቲሸርቶች መካከል ሰማያዊ ቀለም ያላቸው እንዳይለበሱ መከልከሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

Image

ክርስቲያኖች ለሀገር መሪዎችና ለሰላም እንድንጸልይ ታዘናል።እርቅን፥መግባባትን ማወጅ ሃላፊነታችን ነው፤የሚያስተራርቁ ብጹአን ናቸው ተብሎ ተጽፏልና::

በቅርቡ በሀገራችን ምርጫ ይካሄዳል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፉክክር፥ክርክር፥ውድድር ይኖራሉ።አንዳንዴም በሌላውም ዓለም እንደሚታየው መረር ያሉና መስመር ሊያስለቅቁ የሚችሉ ሽኩቻ ስድብና በጥላቻ ላይ የተመሰረታ ዘመቻ ይታያል።ከዚህም በፊት በሀገራችን ብዙ ሰዎች የሞቱበት አሳዛኝ ሁኔታ ተከስቶ ነበር።ያ እንዲደገም አንፈልግም።ለሰላምና ለመግባባት እንጸልያለን።

ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ውድድር ማድረግ እንዲችሉ ሜዳውን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ማመቻቸት ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ፥ፍርድ ቤትና ሚዲያው ሁሉንም እኩል የሚያስተናግዱ ሊሆን ይገባል።ኢትዮጵያ የምታድገው የተለያዩ ሃሳቦች ተፋጭተው ከውድድር በሚገኝ የነጠረ አስተሳሰብ ነው።ተቃዋሚ ሲኖር ለገዢው ፓርቲ መስተዋት ይሆናሉ፤ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋሉ፤ሙስናን ሌሎች ህገወጥነትን ያጋልጣሉ።ተወዳድረው ከተመረጡ ደግሞ ሀገር የመምራት እድል ያገኛሉ።

የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እንግልትና እስራት በተለያዩ ባለስልጣኖች ይደርስባቸዋል።እነዚህ በአግባቡ ታይተው መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል።ወንጀል የሰሩና ያልሰሩ መለየት አለባቸው።ባልተጣራ ሁኔታና በግል ቂም በቀል ንጹህ ሰው በፍጹም መንገላታት የለበትም።

መንግስት ምንም አላደረገም ማለት አይቻልም።ሀገሪቷ ከቀደሙት መንግስታት የተሻለ የዲሞክራሲ ብልጭታ ታይቶባታል።ሆኖም ግን ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ ወንጀልና ሃጢያትም ነውና።

ሰሞኑን በአንዳንድ ፓርቲዎችና በምርጫ ቦርድ መካከል ያለው መቃቃር በሰላምና በመግባባት እንዲያልቅ እንጸልያለን።
እነዚህ ፓርቲዎች ክፍተኛ ዝግጅት አድርገው ለመወዳደር ተነስተዋል፤አንዳንድ ግድፈቶች አሉ ከተባለ በማለፍ በተቻለ መጠን ምርጫውን እንዲካፈሉ መንግስት መጣር አለበት።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመካከላቸው የሚነሱትን ልዩነቶች ብስለት በተሞላበት መንገድ በውይይት መፍታትና አንድነት መፍጠር ሀገራዊ ግዴታቸው መሆኑን በውሉ ሊያጤኑት ይገባል። በአንዳንዶች የምናየው ስር የሰደደ ጥላቻ፥ስድብ፥የሰውን ስብእና ማዋረድና ዘረኝነት መግባባትንና እርቅን ይጎዳልና በአስቸኳይ መቆም አለበት።

በሀገራችን የዲሞክራሲ ግንባታ ትልቅ ሚና የሚጫወቱና ባሁን ሰአት ካሉት ፓርቲዎች ሁሉ በተሻለ ደረጃ ላይ ካሉት ከአንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል። ምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።እነዚህም ፓርቲዎች በሰላማዊ ትግል ላይ ተስፋ ይቆርጣሉ።እነርሱ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት(Civil Disobedience) እንገባለን እያሉ ነው፤በዚህም ሀገሪቷ ወደ አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ የምትገባ ሲሆን ይህ ደግሞ የሚካሄዱትን የልማት ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያዳክም ይችላል።

ዛሬ በኢትዮጵያ አንዱ የጎደለው ነገር ቅንነት ነው።ቅንነት ከሌለ መጨቃጨቅ፥መካሰስ፥ፍርድ ቤት መንከራተት ብቻ ይሆናል።አንዱ አንዱን ለማጥቃት ሰበብና ምክንያት ብቻ ነው የሚፈልገው፤አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱትም አይነሳምና። ስለሆነም ችግሮች ሁሉ የሚፈቱት በመነጋገርና በመከባበር ነው።ያለፈውን በደል ይቅርታ በመጠያየቅ ህዝባችን ከድህነት የሚወጣበትን መንገድ ማፋጠን እንጂ እኛ ለስማችንና ለክብራችን ስንከራከር ህዝብ ማለቅ የለበትም።

እግዚአብሔርም ይሄን አይወድም፤ይቅር ተባባሉ፥ተከባበሩ፥ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አትሸነፉ ነው ያለው።ሌላ አማራጭ የለም። “እርስ በርስ መግባባት፥ሀገርን መገንባት” መርሃችን ይሁን።

አብያተ ክርስቲያናትና የሃይማኖት ተቋማት እውነትን በፍቅር የመናገር ሃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። ቅንነት ለኢትዮጵያ!
ፍቅርና ፍትህ ለኢትዮጵያ!

ዳንኤል ጣሰው

ከኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ

የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ይህን እድል ከመጠቀም እና በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በፅሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂብ አንጓች ሆኖዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊትን ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቀላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሶስተኛ ፊርማ አስባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፉ እየተጫወተ አንድነትን ከጫወታ ለማስወጣት ካለሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው፡፡
ይህ በማን አለብኝ ሰሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ ያለምንም ጠንካራ ተቀናቃኝ ብቻውን ሮጦ ብቻውን እንዲያሻንፍ የሚያደረግ ተቋማዊ ሴራ ቦርዱን በታሪክ ተጠያቂ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በዚህች ሀገር ዘላቂ ሰላም ላይ ለሚፈጠረው አደጋ ቦርዱ ከተጠያቂነት እንደማይድን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ህዝቡን የስልጣን ባለቤት የማድረግ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ሳምንታትም በመንግሰትና በቦርዱ ላይ ጫና ማሳደሩን እንደሚቀጥልበት እያረጋገጥን አንድነት ፓርቲ ወደ ህገወጥነት የሚወሰደውን “የጋራ ጉባዔ” አካሂዱ የሚለው የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የማንቀበለው መሆኑን ለመላው አባላትና ደጋፊውች ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ጥር 8/2007
ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/

Image
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ
በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም እንደፈጠረበት አስታውቋል፡፡የታሪኩ ስለ ሁኔታው የገለጸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡
ስምንት አንድን ሰው በደም እስኪታጠብ ድረስ በርግጫ፣ በጥፊና በሰደፍ መደብደብ፣ በእጁ ላይ የሚገኝውን ብርና መፃሀፍ መንጠቅ፣ ስልኩን መስበር…. ይህ ድርጊት በሌሊት አንድ ሰው ላይ በሌቦች የተፈፀመ ሳይሆን ትላንት ከረፋዱ በ 5 ሰዓት ላይ በዝዋይ እስር ቤት ግቢ ውስጥ በኔ ላይ የተፈፀመ ነው፤
ነገሩ እነዲህ ነው የሆነው፣ እንደልማዴ ዝዋይ የደረስኩት በማለዳ ነው፡፡ የያዝኩትን ስንቅ አስፈትሼ እንደጨረስኩ የሬዲዬ መገናኛ የያዘ መቶ አለቃ እንደሆነ የሚገልፅ ማዕረግ ያለው ወታደር እየገላመጠኝ “ለምን መጣህ?” አለኝ፤ “እዚህ የታሰረ ወንድም አለኝ እሱን ለመጠየቅ ነው” ስል መለስኩ፡፡ ቀጥ ብለህ ወጣ ተከተለ “አንተ ወንድምህን መጠየቅ አትችለም” ሲለኝ “ምክኒያቱ ይነገረኝ” ብዬ ብናገር ከጉዳይም አልቆጠረኝም “እሺ እኔ ባልገባ እንኳን ያመጣሁት ምግብን አድርሱልኝ” ብል ስሚ አጣሁ፡፡ አንገቴን ደፍቼ ልወጣ ስል መቶ አለቃው በሬዲዬ እያወራ አንድቆም በእጁ ምልክት ሲሰጠኝ ልገባ ነው ብዬ ደሰ አለኝ፡፡ መቶ አለቃው በፍጥነት ወደኔ በመምጣት ያዙት አለ፡፡ በዙሬያዬ ወደ ስምንት የሚጠጉ ወታደሮች ከበቡኝ፡፡ የመቶ አለቃው “የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ነህ?” አለኝ፡፡ የተመስገን ወንድም መሆኔን በአንገቴም በአፌም “አዎ ነኝ” ከማለቴ ጥፊ ጆሮዬ ላይ ጮኽ፡፡ ከዛም አንደኛው በከስክስ ጫማ ሌላኛው በሰደፍ ተቀባበሉኝ፡፡ ደምቼ መሬት እስክወድቅ ድረስ ደበደቡኝ….ደበደቡኝ፤ ወደኩኝ፡፡ ከነደሜ አነሱኝ የያዝኩትን ብርና መጽሐፍ ነጠቁኝ ያመጣሁትን ምግብ መሬት ላይ ደፉተው እየገፈታተሩ ከግቢው አስወጡኝ፡፡ እስር ቤቱ ፊት ለፊት አቧራው ላይ ተቀመጥኩኝ፡፡ ተሜን በዓይን ርቀት ያህል ብቀርበውም መጠየቅ ባለመቻሌ አለቀስኩኝ፤ ደሜን አፍስሼ ወንድሜን ሳላይ ተመልሻለሁ … ተሜ ለኔ አንተን አለማየት የማይቻል ሽክም ነው፡፡ ይሄንንስ እነዴት ልንገርህ?!

Image
ሬዲዩ ፋና፣ ‹‹አንድነት ከአሸባሪ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል›› በማለት ወነጀለ ::አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አያይዘው ገልፀዋል፡፡

አንድነት እየቀረበበት የሚገኘው ውንጀላ መሰረተ-ቢስ መሆኑን የገለፁት አመራሮቹ፣ ፓርቲው አሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስብ እና ለዚህም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የአንድነት ደጋፊዎች፣ በፓርቲው እውቅና ተሰጥቷቸው የድጋፍ ሰጪ ቻፕተር ማቋቋማቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹‹አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት ብቻ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ሰዎች ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ›› የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በበኩላቸው የፓርቲው የፋይናንስ አሰራር ግልፅነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ገልፀው፣ በየዓመቱም ኦዲት እንደሚደረግና ምርጫ ቦርድም ለተከታታይ ዓመታት የፓርቲውን የፋይናንስ አሰራር ግልፅነት የሚታይበት እንደሆነ ጠቅሶ ለፓርቲው ሰርተፍኬት መስጠቱን› አቶ ግርማ አውስተዋል፡፡ የራዲዮ ፋና ውንጀላም ከዚህ አንፃር ተገቢነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡ ይህን መሰሉን ውንጀላ የአንድነት አባል ነን የሚሉ ሰዎች ባሳለፍነው ሳምንት በሬዲዮ ፋና ላይ ቀርበው ያሰሙ ሲሆን የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኛ ነኝ የሚል ብሩክ ከበደ፣ የተባለ ግለሰብም ይህን መሰሉን ውንጀላ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዘደንት አቶ ግርማ ሰይፉ እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ በሬዲዮ ፋና “ሞጋች” በተባለ ፕሮግራም ላይ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም በቀረቡበት ወቅት የገዢው ቡድን ተጠሪ የሆነው ብሩክ ከበደ ፣ “አንድነት ፓርቲ በሽብር ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይሰበስባል” የሚል ውንጀላ ሲያቀርብ እንደነበር የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት አስረድተዋል፡፡

ገዢው ፓርቲ አሰርጎ ባስገባቸው ሰዎች “የደንብ ጥሰት አለ” የሚል ውንጀላ ሲቀርብበት የነበረው አንድነት ዛሬ ላይ ደግሞ ውንጀላው በህዝብ ስም በተቋቋሙት ሚዲያዎች አማካኝነት “በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል” በሚል ሌላ ውንጀላ እየቀረበበት ይገኛል፡፡
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ገዢው ቡድን “አንድነት ፓርቲ ከግንቦት ሰባት 1 ሚሊዮን ብር ተቀብሏል፡፡” የሚል ክስ በተላላኪዎቹ በኩል ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የሚያጋልጥ መረጃ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡

Image
• ፖሊሶች የደረጃ እድገት እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል
የአማራ ክልል መስተዳደር በግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ተከትሎ አመጽ ከተከሰተ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን ስልጠና ለክልሉ ፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊስ፣ ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እየሰጠ መሆኑን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ስልጠናውም፤ ለፖሊሶች በዞን እንዲሁም ለሚሊሻና ለፀጥታ ጉዳይ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ በቀጣዩ ምርጫ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚፈራውን አመጽ መቆጣጠር እንደሆነ የገለጹት የፖሊስ ምንጮች በተለይ ፖሊስና ፀጥታ ጉዳይ ከ‹‹ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ›› ጋር በመተባበር የደፈጣ ውጊያን ለመከላከል ‹‹የደፈጣ ውጊያ ስምሪት›› በሚል አጭር ስልጣና እየወሰዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ይህም አገር ውስጥ አመጽ ያነሳል ተብሎ ከሚፈራው ህዝብ በተጨማሪ መሳሪያ ያነሱ ተቃዋሚዎች በምርጫው ወቅት ጦርነት ይከፍታሉ የሚል ስጋት በመኖሩ ነው ሲሉ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ በደብረማርቆስ ውስጥ ስልጠናውን የሚወስዱት ሰልጣኞች ማታ ማታ የተኩስ ልምምድ እንደሚያደርጉ አንድ የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ምርጫውን ተከትሎ ይከሰታል ከተባለው አመጽና ታጣቂ ቡድኖች ያደርሱታል ተብሎ ከሚፈራው ጥቃት በተጨማሪ የጥምቀት በዓል ላይ አመጽ እንዳይነሳ መከላከል፣ ከተነሳም መቆጠጠር የስልጠናው የአጭር ጊዜ ግብ ነው ተብሏል፡፡

በስልጠናው ወቅት በተለይ ፖሊሶች ‹‹ልዩ ኃይልና ፌደራል ፖሊስ በስራችን ጣልቃ ስለሚገቡ ነጻነት የለንም፣ ፖሊስ የህዝብ ነው እየተባለ ህዝብ ግን ይጠላናል፣ በህገ መንግስቱ መሰረት የህዝብን ሰላም ማስጠበቅ ሲገባን እርምጃ እንድንወስድ ከበላይ አካል እንታዘዛለን፣ ከፖለቲካው ገለልተኛ አይደለንም›› የሚሉና ሌሎች ቅሬታዎችንና ጥያቄዎችንም አንስተዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፖሊሶች በቂ ደመወዝና ዩኒፎርም አይቀርብልንም የሚል ቅሬታ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በስልጠናው ወቅትም በተለይ ፖሊሶች ጠንካራ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን መሰንዘራቸው ተከትሎ ሁሉም የክልሉ የፖሊስ አባላት አንድ የደረጃ እድገት እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል ተብሏል፡፡ ጥር 12007 ዓ.ም የጀመረው የ‹‹ፀጥታ ኃይሎች›› ስልጠና ቅዳሜ ጥር 9/2007 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከጥር 7/- ጥር 11/2007 ዓ.ም ለሚሊሻዎች አመራሮች ተጨማሪ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጾአል፡፡

በታህሳስ ወር የታቦት ማደሪያው ለባለሀብት መሰጠት የለበትም በሚል የባህርዳር ከተማ የክርስትና እምነት ተከታዮች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማታቸው እንዲሁም በደብረማርቆስና በሌሎች የክልሉ ከተሞች ስልጠና ላይ የነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸው በ‹‹ፀጥታ ኃይሎች› ስልጠና ወቅት መወያያ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ሁለቱ ክስተቶች የአማራ ክልል አስተዳደር በዚህ አመት አመጽ ይነሳል የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆነዋል ተብሏል፡፡

በምድራችን ላይ የሚገኘው ሀብት ውስን (አላቂ) መሆን እና በአንፃሩ የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ አልባነት፣ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ነገር በፈለገበት ሰአት እና ቀን እንዳያገኝ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ለየትኛውም ግለሰብም ሆነ ሀገር ትልቁ ፈተና ከእጥረት ጋር የተያያዘ እንዲሆን አድርጓል፡፡ በሌላ በኩልም አንድ ሰው የፈለገውን ነገር በፈለገበት ሰአት እና ቀን አለማግኘቱ የተገደበ (ውስን የሆነውን) ገቢውን፣ ሰአቱን እና ሀብቱን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው መሰረታዊ ነገሮቹ እንዲያውል ይገደዳል፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት እንደ ሀገር ትልቁ የኢኮኖሚ ዳራ በዋነኛነት ከእጥረት ጋር የተገናኘ ቢሆንም፤ በአለም ላይ ያሉ ሀገራት የየራሳቸውን ባህል፣ ሀብት (ቁሳዊም ሆነ ሰዋዊ)፣ ታሪክ ወዘተ ያገናዘበ የኢኮኖሚ ስርአት በመከተል፤ ከእጥረት ጋር የተገናኘውን ኢኮኖሚያዊ ዳራ ለመወጣት እንደሞከሩ እና እንደሚሞክሩ የኢኮኖሚ ታሪክ ላይ ትኩረት ያደረጉ ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ኢኮኖሚስቶች አራት አይነት (ባህላዊ፣ የእዝ፣ የገበያ መር እና ድብልቅ) የኢኮኖሚ ስርአት እንዳለ ስምምነት ላይ ቢደርሱም፣ ከእጥረት ጋር በተገናኘ ያለውን የኢኮኖሚ ዳራ ከመፍታት እና ከመቀነስ አኳያ የትኛው የተሻለው ነው የሚለው ላይ አንድ አይነት አቋምም ሆነ ስምምነት የላቸውም፡፡ መንግስታት የህዝብን ኑሮ ለማሻሻል በሚል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ሊመጣ የሚችለው የሚፈሰው ሀገራዊ ሀብት በአንድ በኩል ከወቅታዊው የሀገሪቷ ህዝብ ችግር አኳያ፣ ከዘለቄታዊ ጥቅሙ አኳያ በሌላ በኩል ለመጪው ትውልድ ከሚያስረክበው ተራፊ ሀገራዊ ሀብት አኳያ ከተገናዘበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት የመምጣቱ ዋስትና በመንግስታዊ ስርአት ባህሪ ላይ የተንጠለጠለ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም በእኔ እምነት ኢህአዴግ የሚለፍፍለትን የኢኮኖሚ እድገት በአንድ በኩል የኢኮኖሚ እድገቱ ማሳያ ተብለው የሚቀርቡትን የልማት እንቅስቃሴዎች እንደ ህዝብ ካለብን ድህነት እና የምግብ ዋስትና ማጣት አንፃር፣ ድህነታችንን በመቅረፍ የምግብ አንፃር ያላቸውን ፋይዳ፣ ዘለቄታዊ ጥቅማቸውን የሚፈስባቸውን ሀገራዊ ሀብት ማእከል ባደረገ መልኩ፤ ኢህአዲጋዊውን የልማታዊ መንግስት ስርአት መፈተሸ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

በልማታዊ መንግስት ስርአት ውስጥ የህዝብ ሚና እስኬት ድረስ ነው?

የልማታዊ መንግስት ንድፈ ሀሳብ፣ በዋነኛነት ማእከል የሚያደርገው መንግስት በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ባለው የቁጥጥር እና የተሳታፊነት ስፋት መጠን ላይ ብቻ ነው፡፡ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቃት በኋላ የጃፓን እና የምስራቅ ኤሽያ ሀገራት መንግስታት በሀገራቸው ኢንደስትሪን ለማስፋፋት ኢኮኖሚ ስርአቱን ተከላካይ በሆነ መልኩ በመምራትም ሆነ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ተሳታፊ በመሆን የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1980 ዓ.ም የላቲን አሜሪካ ሀገራት የብድር ቀውስ እና ከ1997 ዓ.ም የምስራቅ ኤሽያ ሀገራት የገንዘብ ቀውስ፣

ከአለም- አቀፋዊነት መስፋፋት እንዲሁም ኢኮኖሚን ከማረጋጋት፣ ትምህርት፣ ጤና እና መሰረተ-ልማቶችን ከማስፋፋት አንፃር መንግስት የሚኖረውን ሚና በተመለከተ በዋሽንግተኑ መግባቢያ ሰነድ ላይ የርዕዮት አለም ልዩነት ከመፈጠሩ ጋር በተያያዘ የልማታዊ መንግስት ስርአት በ20ኛው ክፍለ ዘመን እውቅና አግኝቷል፡፡ በሌላ በኩል ከልማታዊ መንግስት ጋር አንድ አይነት የሆነ ስርአት፣ ሆላንድን የመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት በ 17ኛው እና በ18ኛው ክፍለ-ዘመን ስለመተግበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው ልማታዊ መንግስት በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ፣ አንዳንዶች እንደሚሉት እና እንደሚያምኑት የልማታዊ መንግስትን ንድፈ ሀሳብ ኢህአዴግ የፈጠረው አለመሆኑን ነው፡፡ ‘እከሌ የሚባለው ሀገር በልማታዊ መንግስት መርህ ነው ያደገው፣ እከሌ ኒዮ-ሊበራሊስት ነው እከሌ ልማታዊ ነው’ የሚለውን የአላዋቂ ክርክር ወደጎን ትተን፣ በልማታዊ መንግስት መርህ ኢኮኖሚያቸውን በጠንካራ መሰረት ላይ በመገንባት ህዝባቸውን ከድህነት ያወጡ ሀገራትን ታሪክ እነዚህ አገራት ባህላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ሀብታቸውን መነሻ በማድረግ እና የፖለቲካ ልዩነትን ወደጎን በመተው አሳታፊ የሆነ ፖሊሲ በመቅረጽ ስለተንቀሳቀሱ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዋነኝነት ግን ህዝባዊ ቅቡልነት ስለነበረው መሆኑ አይካድም፡፡

የአለም ሀገራት የኢኮኖሚ ታሪክ እንደሚያሳየን መንግስታዊ ስርአቱ አንባገነን መንግስት በኢኮኖሚው ላይ የሚያደርገው ጣልቃ-ገብነት፣ ውስን በሆነው ሀገራዊ ሀብት የሚከናወኑ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉት የመንግስቱን ባለሟሎች እና ከመንግስታዊው ስርአት ጋር ተለጣፊ የሆኑትን የግል ባለሀብቶችን ብቻ ይሆናል፡፡ የአንባገነኑ ሙጋቤን ሀገር ዚምባቡዌ እና የአንባገነኑ ፒኖቼ ሀገር ቺሊ (በፒኖቼ አመራር ስር በነበረችበት ወቅት) ተመክሮ ለዚህ በቂ ማሳያ ይመስለኛል፡፡ መንግስት፣ በኢኮኖሚው ውስጥ በሚሣተፍበት የልማታዊ መንግስት ስርዓት ስኬት እና ውድቀት፣ ልማታዊ መንግስቱ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓትም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሁም ነፃና ገለልተኛ ተቋማት እንዲኖሩ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ የፖለቲካ ስርአቱን ለኢኮኖሚ እድገት አጋዥ ለማድረግ፣ ለመድብለ ፖርቲም ሆነ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት፤ እንዲሁም ለነፃ እና ለገለልተኛ ተቋማት መኖር ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያደርግ የልማታዊ መንግስት ስርአት፤ በአስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ በፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡ የልማታዊ መንግስትን መርህ በሚከተሉ ፖርቲዎች አማካይነት አሁን ላሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ የበቁትን የሆላንድን እና የጃፓንን ታሪክ በማሳያነት ማቅረብ ይቻላል፡፡

ኢህአዴግአዊው ልማታዊ መንግስትስ ?

ኢሕአዴጋዊው ልማታዊ መንግስት፣ ድህነትን ለመቅረፍ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ረጅም የስልጣን ዘመን የግድ ነው የሚለውን ሀሳብ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ስርዓት ጋር በመግመድ ብልፅግናን አመጣለሁ የሚል ስርዓት ነው፡፡ በእንደእኛ አይነቱ ደሀ ሀገር ከላይ በጠቀስኩት መልኩ ልማታዊ መንግስትነትን ለአንድ ፖርቲ ብቻ ተለቆ ቢቀጥል የሚቀነሰው የህዝቡ ድህነት ነው ወይስ የባለስልጣኖቹ እና ሸሪኮቻቸው ድህነት ነው? የሚል ጥያቄ በማንሳት ማየት ተገቢ ነው፡፡

አፍሪካ በኒዮ-ሊበራሊዝም አስተሳሰብ ኢኮኖሚዋ ከማደግ ይልቅ አዙሪት ውስጥ መግባቱን በመተንተን ከዚህ አዙሪት ለመውጣት አፍሪካ የኒዮሊበራሊዝም አስተሳሰብን አሽቀንጥራ በመጣል፣ የልማታዊ መንግስን ስርአት መከተል እንዳለባት፣ ልማታዊ መንግስት ህዝቦችን ከድህነት በማውጣት እና በማነቃቃት ድህነት ቀራፊ ፖሊሲ የሚነድፍ እና የሚተገብር፣ ለረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ የሚቆይ ፓርቲ አስፈላጊ ስለመሆኑ በመግለፅ ይህ ለረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ የሚቆየው ፓርቲ ረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ ለመቆየት ዋስትናው በሀገሪቷ በየጊዜው የሚያስመዘግበው የኢኮኖሚ እድገት መሆኑን የኢህአዴግ ጭንቅላት የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ “African Development the dead ends and the new beginning” በሚለው የዶክትሬት ዲግሪ ሟሟያ ጥናታዊ ፅሁፋቸው ላይ ያትታሉ፡፡ አቶ መለስ፣ ኢህአዴግ ለሚከተላቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ዋነኛው ነዳፊ እንደመሆናቸው መጠን ከላይ የጠቀስኩት ጥናታቸው የስርዓቱን የልማታዊ መንግስት ትርጓሜና አፈፃፀም በግልጽ ያሣያል፡፡

እውቁን ኢኮኖሚስት ፕሮፌሰር ማርክ ኦንልሰን፣ አንባገነን መንግስታት ለልማት በሚል የሚያፈሱት ሀገራዊ ሀብት ቅድሚያ ስሌቱ የህዝቡን ኑሮ ማሻሻል ሳይሆን ለስርአቱ ከሚያስገኘው ገቢ እና ለህልውናው ካለው ፋይዳ (ወተትን ለማግኘት እንጂ ለላሚቷ በማሰብ ሳር ከማይሰጣት ግለሰብ ጋር በተመሳሰለ መልኩ) አንፃር በመሆኑ አንባገነን መንግስታት የብዙሀኑን ህዝብ ኑሮ የሚያሻሽል አስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጡ አይችሉም’ ይላል፡፡ ይህን የኦንልሰን ንድፈ ሀሳብ መነሻ በማድረግ የሀገራችን ግብርና ዘርፍ ልማታዊ ነኝ የሚለው ኢህአዴግ፤ ከሀያ ሶስት አመት በሁአላም በሀገራችን ዋነኛ የግብርና ምርታማነት ግብአት የሆነው ማዳበሪያ ብቸኛ አቅራቢ እራሱ መሆኑ፣ ለግብርና ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የሚመድበው በጀት ሲታይ፣ የሚከተለው የመሬት ፖሊሲ ከገበሬው ይልቅ ሹመኞችን መጥቀሙ ወዘተ የኢህአዴግ ልማታዊ መንግስትነት ፋይዳው ለማን እንደሆነ የሚያመላክት ይመስለኛል፡፡
ኢህአዴግ፤ ‘ልማታዊ መንግስትነኝ’ ከማለቱ ጋር በተገናኘ ልማት በሚል የዳቦ ስም ሀገሪቷ ላይ የሚፈሰው የሀገሪቷ ሀብት፣ ከሀገሪቷ ህዝብ ወቅታዊም ችግርም ሆነ ከዘለቄታዊ ጥቅም አኳያ የህዝብ የምግብ ዋስትና በመሆኑ፣ ለግብርና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ኢህአዴግ ለግብርና ትኩረት አለመስጠቱ ከላይ ከጠቀስኩት የግብርናችን ተግዳሮት በተጨማሪ የግብርና ምርቶች የዋጋ ንረት ማሳያ ይመስለኛል፡፡ ኢህአዴግ በሚመራዊ ኢኮኖሚ ስርአት ውስጥ የሚታየውን ፖሊሲ ከመሸጥ (ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለግለሰቦች ማሳወቅ) እስከ ፖሊሲን ለሸሪኮች ማመቻቸት፤ ኢኮኖሚያዊ ስርአቱን ለፓርቲው ሰዎች ብቻ ምቹ ማድረግን እንዲሁም መንግስታዊ ሌብነትን መነሻ በማድረግ ከግብርና ውጪ ባሉ የኢኮኖሚ ክፍሎች ላይም የሚፈሰውን ሀገራዊ ሀብት ለህዝቡ ከሚያስገኘው ዘለቄታዊ ጥቅም አንፃር ሲታይ መንግስት በኢኮኖሚያዊ እድገት የብዙሀኑን ህዝብ ኑሮ ከማሻሻል ይልቅ የሀገሪቷ ሀብት በጥቂት ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚዘውሩት የኢኮኖሚ ኢምፖየር እንዲገነባ አድርጓል፡፡

የሃገራችን ማህበረ-ፖለቲካዊ አውድ ከድሮ እስከ ዘንድሮ፣ ከግለሰባዊነት ይልቅ ማህበራዊነት ያጠላበት ነው፡፡ ብዙዎቻችን ስንወድ ስንጠላ፣ ስንደግፍ ስንቃወም የጀማውን አዝማሚያ አይተን ነው፡፡ በግላችን የምናቀርበው ክርክር በጀማው ዘንድ ተቀባይነት ካጣ፣ በግል እምነታችን ከመፅናት ይልቅ ተሸማቀን የምናፈገፍግበት ጊዜ ይበዛል፡፡ ትክክለኛነታችንን የምንለካው፣ በተከተለን መንጋ ብዛት እንጂ በአመክንዮአችን ጥንካሬ አይደለም፡፡

ይህ አንደህዝብ የምንጋራው በጎ ያልሆነ እሴታችን ነው፡፡ መንግስት ደግሞ የህዝብ ነፀብራቅ ነውና በተለያየ ወቅት ሃገራችንን የመሩ መንግስታትም ከዚህ የተዋጁ አይደሉም፡፡ ገዥዎቻችን፣ ብዙሃኑ ህዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ እየተገዛላቸው፣ ጥቂት የተለየ ሃሳብ ያነሱ ዜጎችን ከምድር በታች ካላደረጉ እንቅልፍግ የማይወስዳቸው ለዚህ ነው፡፡ ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሃገሬው “ስዩመ እግዚአብሄር” እያለ ይሰግድላቸው የነበሩት አፄ ኃ/ስላሴ፣ ገርማሜ ነዋይን የመሰለ ባለ አእምሮ የገመድ ራት ያደረጉት በዚህ አግባብ ነው፡፡ የነ ልጅ እያሱ፣ በላይ ዘለቀ፣ ጥላሁን ግዛው አሳዛኝ ፍፃሜ የዚሁ የንጉሱ በደቦ የመግዛት ፍላጎት ክፉ ውጤት ነው፡፡ ዱላ ተቀባዩ ወታደራዊው መንግስትም ኢትዮጵያ ትቅደም፣ የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም፣ የእድገት በህብረት የእውቀት እና የስራ ዘመቻ፣ ሁሉም ነገር ወደጦር ግምባር፣ የቀይ ኮኮብ ዘመቻ ወዘተ እያለ በየጊዜው የሚያመጣቸው ግን ደግሞ እርሱ እራሱ በቅጡ ያልተረዳቸውን ፍልስፍናዎች በደቦ ያልደገፈውን ሁሉ ደም ከማፍሰስ ወደኋላ አይልም ነበር፡፡ የዚህ አካሄዱ ማጀቢያም “ከእኛ ጋር ያልሆነ ከጠላታችን ጋር ነው” የሚል የደመ-ነፍስ መርህ ነበር፡፡

ተተኪው ኢህአዴግም መውደድ መጥላቱን፣ አድናቆት ውግዘቱን ከዘጠና ሚሊዮኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በደቦ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ ያፈነገጠን ሁሉ የዲያቢሎስ አምሳያ የሃገር ጠላት አድርጎ ያብጠለጥላል፡፡ ይህን የደቦ አባዜውን፣ ከሃገሬው ህዝብ አልፎ እስከ ባህርማዶ የምዕራባዊያን ግለሰቦች እና ተቋማት ድረስ ያዘልቀዋል፡፡ ከሚያስተዳድረው ህዝብ አልፎ ባዕዳንም በደቦ የወደደውን እንዲወዱ የጠላውን እንዲያወግዙ ይፈልጋል፡፡

የፍቅር ደቦ -1

በ1977 ዓ.ም በሃገራችን ተከስቶ በነበረው ረሃብ ሰበብ፣ የምዕራባዊኑን ዶላር ጣዕም የቀመሰው ህወሃት የምዕራባዊያኑ ንዋይ የህይወት መስመሩን የሚያረዝም መሆኑን የተረዳው ገና ጫካ እያለ ነበር፡፡ ሸማቂው ቡድን፣ “ቆምኩለት” በሚለው ድሃው የትግራይ ህዝብ ስም የመጣውን የእርዳታ ገንዘብ አያሌ ድርሻ፤ በአቶ መለስ ፊታውራሪነት ለማሌሊት መመስረቻ እና ማጠናከሪያ እንዲውል እንደተደረገ፣ አልፎ ተርፎም ሱዳን ላይ ለድርጅቱ ትላልቅ የእርሻ መሬት ተገዝቶ ሰሊጥ እያመረቱ ይቸበችቡ እንደነበር በወቅቱ የድርጅቱ በጅሮንድ የነበሩት አቶ ገ/መድህን አርአያ፤ በአንድ ወቅት ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል፡፡ይህ ተግባር አሳፋሪ ቢሆንም፣ በዚሁ መንገድ የመጣው ረብጣ ገንዘብ ሕወሓትን በወቅቱ ከነበሩ ሃብታም ሸማቂዎች መካከል እንዲመደብ አድርጎታል፡፡ ነገሩ ድርጅቱን ከምዕራባዊያኑ ጋር ከአንጀት ባይሆንም ከአንገት በላይ በሆነ ፍቅር እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም የሸማቂነቱ ዘመን አብቅቶ መንግስት ሲሆን የምዕራባዊያኑን ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፈለግ እንደሚከተል ይገልፅ ጀመር፡፡ በፖለቲካው ረገድ፣ በምዕራባዊያኑ ዲሞክራሲ ስም በመማል በመገዘት፣ በኢኮኖሚው በኩል ደግሞ “የምከተለው ነጭ ካፒታሊዝምን ነው” ሲል ያመሽ ያነጋ ነበር፡፡ ዓለም-አቀፍ የሰብዐዊ መብት አንቀፆችን የህገ-መንግስቱ አካል በማድረግ፣ ለምዕራባዊያኑ ሊብራሊዝም ፅንሰ-ሃሳብ እና አጠቃላይ ርዕዮተ-ዓለም ያለውን ታማኝነት ለማስመስከር ሞክሯል፡፡ የጣለውን የደርግ ስርዓት ያብጠለጥል የነበረውም የዜጎችን ሰብዐዊ መብት በመርገጥ እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማስፈን ባለመቻሉ ያጠፋቸውን ጥፋቶች በማነሳሳት ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የምዕራባዊያኑ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ፈለግ፣ በኢሕአዴግ ዘንድ ብቸኛ የድኅነት መንገድ ተደርጎ ይወሰድ ነበርና ከዚህ ሃሳብ መለየት ለማንም አልተፈቀደም ነበር፡፡ የተለየ ሃሳብ አለኝ የሚል ቢገኝ እንኳ መጠሪያው የደርግ ርዥራዥ፣ “የዲሞክራሲ ጠላት” የሚል ይሆናል፡፡

የፍቅር ደቦ -2

ሕወሓት ከውልደቱ ጀምሮ በሻዕብያ ፍቅር ክፉኛ የተመታ ነበር፡፡ ይህ ጣራ የነካ ፍቅር በሚገርም ሁኔታ እናት ሃገርን ቅኝ ገዥ አድርጎ እስከማሰብ እና ቀኝ ተገዥዎችን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት እናት ሃገርን እስከ መውጋት አድርሶታል፡፡ ህወሃት፤ ከሻዕብያ ጋር የወደቀበት ሃያል ፍቅር፣ ወዳጅ ጠላቱን ለመለየት ሳይቀር ዋና መለኪያው፣ ያ ወገን የኤርትራን ጉዳይ የሚረዳበትን መንገድ እስከ ማድረግ ደርሶ ነበር፡፡ ለምሳሌ ህወሃትን ከኢህአፓ ጋር ያቃቃረው፣ ኢህአፓ የኤርትራን ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ለማለት ባለመድፈሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም የህወሃት ፍቅር፣ ከራሳቸው ከኤርትራዊያኑ ታጋዮች የበለጠ ለኤርትራ ያገባኛል እንደማለት ስለሚሞክረው ለወሬ የማይመች የሚሆንበት ጊዜም ነበር፡፡ አቶ መለስ፣ ጫካ በነበሩበት ወቅት የትክክለኛ ኤርትራዊነትን መስፈርቶች እስከማውጣት ደርሰው እንደነበር የአስራት አብረሃም “ከሃገር በስተጀርባ” መፅሃፍ ያስረዳል፡፡ አቶ መለስ፣ በዚሁ መስፈርታቸው በኢትዮጵያዊነት ስር ሆኖ የኤርትራ ጥያቄ ይመለስ የሚሉ፣ ኢትዮጵያ የኤርትራ እናት ሃገር ነችና መገንጠሏን አንቀበልም የሚሉ፣ ከደርግ ጋር ተደራድረው ኤርትራን ለመገንጠል የሚደረገውን ትግል ለማስቆም የሚከጅሉ ኤርትራዊያን፤ ከኤርትራዊነት የጎደሉ እንደሆኑ አምርረው ይናገሩና ይፅፉ ነበር፡፡ በአቶ መለስ መስፈርቶች ከተሰፈሩ፣ አንድ ሁለት ጊዜ ከደርግ ጋር ለመደራደር መለስ ቀለስ ብለው የነበሩት ኢሳይያስ አፈወርቂ ራሳቸው ኤርትራዊነት የሚጎድላቸው ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚወዱት እውቁ ኤርትራዊ ምሁር ፕ/ር ተስፋፅዮን መዳኔ፣ ከኤርትራዊነት ፀዳል የጎደሉ እንደሆኑ አቶ መለስ “የኤርትራ ህዝብ ትግል የቁልቁሊት አይደፋም” የሚል መፅሃፍ እስከመፃፍ በደረሰ ሙግት ሲያስረዱ ነበር፡፡
ይህ ከጠዋቱ ህወሃትን የተጣባው የሻዕብያ ፍቅር፣ ሸማቂ ቡድኑ አድጎ ኢህአዴግ በሚል ሰፊ ድርጅታዊ ማዕቀፍ ውስጥ ገብቶም፣ የመንግስትነት ሰገነት ላይ ወጥቶም የሚብስ እንጅ የሚበርድ አልሆነም፡፡ ሸማቂ ቡድኑ፣ ወደ አዲስ አበባ በሚያደርገው ግስጋሴ ሁሉ ቆምኩለት ከሚለው ኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እና ፍላጎት ይልቅ የሻዕብያ አመራሮችን ፍላጎት ያስቀድም ነበር፡፡ አዲስ አበባ ገብቶ የታላቋን ሃገር የኢትዮጵያን እጣ-ፋንታ አንድ ደረጃ ሳያደርስ፣ የኤርትራን መገንጠል በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የተባበሩት መንግስታትን ሹማምንት እረፍት በነሳ ውትወታ ተጠምዶ ነበር፡፡ የመገንጠሉ ሂደት ሚጢጢዋን ኤርትራን ያለ አግባብ ባለ ሁለት ወደብ ሲያደርግ ኢህአዴግ ታገልኩላት የሚላትን ታላቋን ሃገራችንን ወደብ አልባ ማድረጉ፣ በኤርትራ ፍቅር አይነ-ልቦናው ለታወረው ህወሃት ነገሬ የሚባል ጉዳይ አልነበረም፡፡

ይህ ምንጩን ለማወቅ የሚያስቸግር ህወሃት የወደቀበት ሃያል ፍቅር፣ ወደ ሁሉም ኢትዮጵዊ በደቦ ሰርጎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኤርትራን ጉዳይ ቀዳሚ እንዲያደርግ የመፈለጉ ዝንባሌ ራሱ ከወደቀበት ፍቅር ብርታት የበለጠ የሚገርም ነበር፡፡በወቅቱ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃት የፈለገውን ያህል በኤርትራ ፍቅር ሊወድቅ ቀርቶ፣ የኤርትራን ሃገርነት ለመቀበልም እንኳ ዝግጁ አልነበረም፡፡ በተቃራኒው ህዝቡ ኤርትራ የተገነጠለችበትን ሪፈረንደም አግባብነት እና የኢትዮጵያ ሁለት ወደብ አስረክቦ ወደብ አልባ መሆን እያስቆጨው ነበር፡፡ ይህ የአብዛኛው ዜጋ እምነት ታዲያ ለህወሃት መሪዎች የደርግ ቅሪት፣ የነፍጠኛው ስርዓት ርዝራዥ፣ የነፃነት ጥያቄ የማይገባው ትምክህተኛ፣ የተስፋፊነት አባዜ የተጠናወተው፣ የጎረቤት ሃገር ሉአላዊነት የማይዋጥለት ጦረኛ …. የሚል መጠሪያ ይሰጠው ነበር፡፡ “ስለ ኤርትራ አንዳች ክፉ የሚናገር ቀድሞ የሚጣላው ከእኛ ጋር ነው” የሚለው የህወሃት አባባል፤ ሽርክናው ወደ መሸካከር ተቀይሮ፣ በሁለቱ ሃገራት መሃከል ከፍተኛ ደም መፋሰስ ከሆነ በኋላም የቀጠለ ነው፡፡

‘የኤርትራ መገንጠል የነፃነት ምልክት ነው ከተባለ ይሁንና የኤርትራ አካል ያልሆነው የአሰብ ወደብ እንኳን ለሃገራችን ይትረፍ’ ማለትም በህወሃት መንደር የሚያስቀስፍ ሃጢያት ነበር፡፡ የወደብ እጦቱ ድህነቱን ያባባሰበት የኢትዮጵያ ህዝብም የአሰብን ወደብ ያለአግባብ ለኤርትራ መሰጠቱን በደቦ እንዲቀበል አልፎ ተርፎም ህገ-መንግስቱ ያመጣው የነፃነት ትሩፋት ነው ብሎ እንዲያምን ይጠበቅበታል፡፡ ህወሃት፣ ኤርትራን በተመለከተ የያዘውን አስገራሚ አቋም እንዲይዝ ባደረገው ፍቅር የተለከፈበት በሚናገረውም ሆነ በማይናገረው የራሱ ምክንያት ሆኖ ሳለ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ያለ ምክንያት ተገቢ ያልሆነውን የሚቀበልበት እና ከህወሃት ጋር የፍቅር ደቦ ገብቶ ‘ከኤርትራ ያስቀድመኝ’ የሚልበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ ሆኖም ደቦ ወዳዱ ህወሃት፣ እርሱ በወደቀበት የኤርትራ ፍቅር የኢትዮጵያም ህዝብ እንዲወድቅ ይጠብቃልና የወደቡ አንሶ ቡናው፣ ጤፉ፣ ገብሱ፣ ስንዴው …. ወደ ኤርትራ ሲጋዝ ከልቡ ደስ እንዲለው ሲፈርድበት ኖሯል፡፡

የፍቅር ደቦ-3

የመገንጠል መብትን የህገ-መንግስቱ አካል ያደረገው ኢህአዴግ፣ ህገ-መንግስቱ በፀደቀ ማግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ በደቦ በመገንጠል ፍቅር እንዲወድቅ፣ የመለያየት መዝሙር እንዲዘምር፣ ከሃገራዊነት ይልቅ ወንዘኝነቱን እንዲያጠብቅ፣ መገንጠልን የነፃነት ቁንጮ አድርጎ እንዲያስብ መፈለጉ አልቀረም፡፡ በሌላ በኩል በዘውዳዊው ስርዓትም ሆነ በወታደራዊው መንግስት ዘመን ለተቆጠሩ ረዥም አመታት በጋብቻ፣ በጉርብትና እና መሰል ማህበራዊ መስተጋብሮች አንድነቱ ሲያጠብቅ ለኖረው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ይህ በቀላሉ የሚዋጥ አልነበረም፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከጠዋቱ የሃገር አንድነትን በነፍጠኛ አማሮች ብቻ የሚቀነቀን ክፉ አባዜ አድርጎ ይቆጥር ነበርና እርሱ በወደቀበት የመነጣጠል ፍቅር ያለመመታት፣ የትምክህተኝነት ምልክት ተደርጎ ይወገዛል፡፡ የሚገርመው ይህን የሚለው ኢህአዴግ መገንጠልን አልመው የሚንቀሳቀሱ የብሄር ፓርቲዎችንም በጠባብነት ይከሳል፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ አተያይ፣ የመገንጠል ጥያቄ የነፃነት ትግል የሚሆነውም የሚሳካውም ሻዕብያ ሲያነሳው ብቻ ነው፡፡ በተረፈ ስለመገንጠል ቀርቶ ስለአንድ ብሄር መብት ጥያቄ ማንሣት የጥበት ምልክት ነው፡፡ ይህን ግራ የተጋባ የገዥው ፓርቲ አቋም፣ በደቦ መከተል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ግዴታ ነው፤ ካልሆነ የተለመደው ውግዘት ይከተለዋል፡፡

የፍቅር ደቦ – 4

ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ‘ዲሞክራሲያዊነቱን ትቼ ልማታዊ ሆኛለሁ’ ያለው ኢህአዴግ፣ ይህን ሲል ወደስልጣን ከመጣ ጀምሮ እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ ሲዘምርለት የኖረውን የምዕራባዊያን ዲሞክራሲ በልማታዊ መንግስት ርዕዮት ተክቶ ነው፡፡ “ሩቅ አሳቢ” ሲል የጠራውን የልማታዊ መንግስት እሳቤ፣ ‘የእስያን ሃገሮች ኢኮኖሚ እንደ ነብር እንዲፈተለክ ያደረገ ብቸኛ መድህን ነው’ ሲል አወዳድሶ፤ ቀድሞ ሲያሞካሸው የነበረውን የምዕራባዊያኑን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የርዕዮት አለም ዘይቤ ደግሞ፡- “በአሸናፊነት መንፈስ አለቅጥ የሰከረ፣ ለአፍሪካ ፈፅሞ የማይበጅ” ሲል አጣጥሎ ነው፡፡ የኒዮ ሊብራል ቀሳውስት ዶግማ የሚለውን የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ዘይቤ በተለይ “የዘበኛ መንግስት የመመስረት ህልም ያለው” ሲል ያራክሰዋል፡፡

በዚህ ቅፅበትም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲዘምርለት የኖረውን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ህልም ወዲያው ረስቶ፣ ከኢህአዴግ ጋር በቻይና ፖለቲካዊ ርዕዮት ፍቅር እንዲወድቅ፣ ስለሱው እንዲዘምር፣ በአንድ አውራ ፓርቲ ስር መሆንን ፀዳል ድንቅነት እንደያወድስ፣ ስለሰብዐዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ አያያዝ ሁኔታ ትንፍሽ ሳይል ስለቁሳዊ እድገት እና እንዲሁ በደቦ የልማታዊ መንግስትን መስመር ተከትሎ ስለሱው ትሩፋቶች ብቻ እንዲነጋገር ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ የደቦ አስተሳሰብ የሚያፈነግጥ የልማት አደናቃፊ፣ የህዝብ ጠላት የሚሉ ተቀፅላዎች ይንጠለጠሉበትና ጉዞው ወደቃሊቲ ይሆናል፡፡

ከላይ ለማሳያነት የቀረቡት የኢህአዴግ የደቦ ጉዞ ፍላጎቶች፣ በምክንያታዊነት ለሚያምን እና የራሱ አተያይ ላለው ዜጋ ክፉ ፈተና የሚደቅን ነው፡፡ ሌላው የዚህ ከመንግስት በኩል የሚፈለገው የደቦ ጉዞ ችግር፣ ራሱ ለደቦ የሚጋብዝበትን ሃሳብ ይዞ የመሰንበት ዝንባሌው አናሳ መሆን ነው፡፡ ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደተሞከረው ገዥው ፓርቲ ትናንት በፍቅር ወድቆለት ሌት ተቀን ሲያነሳሳው ህዝቡንም ለደቦ አድናቆት ሲጋብዝበት የነበረውን ርዕዮተ አለምም ሆነ መመሪያ፣ ከመቅፅበት ቀይሮት ጠላት ሲያደርገው ይስተዋላል፡፡ የምዕራባዊያኑ የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እሳቤ፣ ከኤርትራ ጋር የነበረው ወዳጅነት፣ የመገንጠል ጥያቄን የሚያስተናግድበት ሁኔታ ወ.ዘ.ተ ለዚህ አባባል በማሣያነት ሊቀርቡ የሚችሉ አብነቶች ናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ የደቦ ጉዞውን ለመቀበል ለተዘጋጀ ሰውም ቢሆን የኢህአዴግ አካሄድ አስቸጋሪ እና ግራ አጋቢ መሆኑ አይቀርም፡፡ በዚህ ሁኔታ ለመያዝ ለመጨበጥ አስቸጋሪ የሆነው የኢህአዴግ አካሄድ አስቸጋሪ ሆኖ ሳለ፣ መንግስት ለፍቅሩ ብቻ ሳይሆን ለጠቡም ደቦ የመፈለጉ አካሄድ ደግሞ ሌላው ከባድ እና ግራ አጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

የኢህአዴግ የፍቅርም ሆነ የጠብ ደቦ ፍለጋ፣ የዜጎችን እጣፈንታ የሚወስን እየሆነ መምጣቱ ይብስ አሳሳቢው ጉዳይ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ኢህአዴግ የወደደውን መውደድ የጠላውን መጥላት ብቻ ሳይሆን አብሮ ማውገዝ ከሁሉም በመንግስቱ ጥላ ስር የሚኖር ዜጋ ግዴታ ወደመምሰሉ እየሄደ መጥቷል፡፡ በዚህ የማይስማማ እጣ-ፈንታው ሁለት ነው ወይ ቃሊቲ መውረድ ወይ መሰደድ፡፡ እለት እለት እየጨመረ የመጣው የተሰዳጅ እና የታሳሪ ቁጥርም በአመዛኙ ከዚሁ ከኢህአዴግ የልብ ሃሳብ ጋር የመመሳሰል እና ያለመመሳሰል ጉዳይ ነው፡፡ ለፍቅርም ሆነ ለጠብ ከመንግስት ጋር እኩል ማሰብ ደግሞ ተፈጥሯዊም አይደለምና ለዜጎች ትልቅ ፈተና ነው፡፡ የፈተናውን ክብደት የሚያሳዩ የኢህአዴግ የጠብ ደቦ ፍላጎቶችን ለማሳየት ሳምንት እመለሳለሁ፡፡

ምርጫ ቦርድ አንድነትና መኢአድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ውሳኔ አስተላለፈ

• ለሰማያዊ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የውስጥ ችግራቸውን መፍታት አልቻሉም በሚል በዛሬው ዕለት ውሳኔ እሰጣለሁ ብሎ የነበረው ምርጫ ቦርድ ሁለቱ ፓርቲዎች በሁለት ሳምንት ውስጥ የውስጥ ችግራቸውን ፈትተው ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ የመጨረሻ ጊዜ ሰጥቻቸዋለሁ ሲል ገልጾአል፡፡ ቦርዱ ዛሬ ከሰዓት በሰጠው መግለጫ በአንድነትና መኢአድ ስም የተለያዩ ጉባኤዎች በመደረጋቸው ሁለቱ ፓርቲዎች ጥር 3 ያደረጉትን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አለመገኘቱን፣ አንድነት የ2004 ዓ.ም እንዲሁም የመኢአድን የ2001 ዓ.ም ደንብን እንጅ ከዛ በኋላ ያሉትን የፓርቲውን ደንቦች እንደማያውቅ በመግለጽ በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ችግራቸውን እንዲፈቱ የመጨረሻ ጊዜ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል መድረክ ረግጦ በመውጣት፣ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲያድሙ በማድረግ፣ ቦርዱ የማያውቀው ትብብር በመመስረት በሚል በምርጫ ቦርድ ክስ የቀረበበትና ይቅርታ እንደማይጠይቅ በደብዳቤ ለገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡ ማስጠንቀቂያውን የማያከብር ከሆነም ቦርዱ ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡

የቦርዱ ባለስልጣናት ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን ህገ ወጥ ትብብር በመመስረት ስትከሱ ሌሎቹን የትብብሩን አባል ፓርቲዎች ለምን አልከሰሳችሁም?›› በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ‹‹ፓርቲዎቹ 9 መሆናቸውን የሰማሁት አሁን ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹እስካሁን ሌሎች ትብብሮችን ምርጫ ቦርድ አያውቃቸውም ብላችሁ ከሳችሁ አታውቁም›› በሚል የ9ኙን ፓርቲዎች ትብብር ህገ ወጥ ነው ካሉ ገዠው ፓርቲ ከአጋሮቹ ጋር ያለውን ግንኙነትን ለምን ህገ ወጥ ነው እንደማይሉ ለቀረበላቸው ጥያቄም ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ‹‹ኢህአዴግ እንደገዥ ፓርቲ አጋር ፓርቲዎች ሊኖሩት ይቻላል፡፡ እንደ ገዥ ፓርቲ ከአጋሮች ጋር መስራት ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ነገሮችን ቦርዱ አይመለከተውም›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

አንድነትና መኢአድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ችግራቸውን እንዲፈቱ ተጨማሪ ጊዜ ሰጥቻለሁ ያለው ምርጫ ቦርድ በሁለት ሳምንት ውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔውን ያሳውቃል ብሏል፡፡

አንድነት ፓርቲን ለማፍረስ የተወጠነው ሴራ በዶክመንተሪ ፊልም ተቀናበረ::
በነሀብታሙ አያሌው እና የአንድነት አባላት ላይ ለመመስከር ስምምነት ተደርሷል::

የኢህአዴግ ሰርጎገብ የሆኑትና አንድነትን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱት(በትግስቱ አወሉ የሚመሩት) አካላት በምርጫ ቦርድና ጽ/ቤት ለብሄራዊ ደህንነት አባላት በቪዲዮ በሰጡት የሃሰት ምስክርነት አንድነት ፓርቲ በግንቦት7 ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት እየሰራ ነው የሚል መረጃ መስጣታቸው ታወቀ፡፡ ሰርጎገቦቹ የአንድነት አባላት በሆኑትና አሁን በእስር ላይ በሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው ላይም የሀሰት ምስክርነት ለመስጠት ተስማምተዋል፡፡

ዳንኤል ሙላት፤ኤዶም ሰይፉ፤ደረጀ ጣሰው እና ገዛሀኝ ንጉሴ በነሀብታሙ አያሌው እና ዳንኤል ሺበሺ ላይ ለተመሰረተው ክስ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው ለመቅረብ የውል ስምምነት ፊርማቸውን በትላንትናው እለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ሊግ ቢሮ አኖሩ፡፡ፓርቲውም ለነሱ ተላልፎ እንደሚሰጣቸው አልያም ሊዘጋ እንደሚችል ቃል ተገብቶላቸዋል ፡፡

Image

ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው::

Minilik Salsawi ህዝብን ያዘናጋ እየመሰለው የተዘናጋው ህዝብን ያፋጀ እየመሰለው ያፋቀረው ወያኔ እንደት እንደሚሳካለት ባለማወቁ እየዳከረ ነው::ህዝባዊ ጥያቄዎች እየበረቱበት የመጣው ወያኔ መላወሻ በማጣቱ የሚያደርገውን እስካለማወቅ ደርሷል:: ከእነዚህም ድንብርብሮች አንዱ ከአባቱ ሻእቢያ እንደወረሰው የፈጠራ ወሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት ነው:: እንዲሁም የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ያስረሱልኛል ጭንቅላት ይሰርቃሉ የሚል እደምታ ያለውን ፈጣን ዘገባ ማሰራጨት ቅርሶችን እና የሃገር እና ሕዝብ አትኩሮት ይስባሉ የተባሉ ነገሮችን ማውደም የህዝብን አንግት ለመስበር እና ህዝብን ሃዘን ለማስቀመጥ ማለም ሃሳብን ሰርቆ አቅጣጫ በማስቀየር የማሰቢያ ጊዜ እንዲያገኝ መትጋት ስራዬ ብሎ ይዞታል::

ባለፉት 24 አመታት የአገዛዝ ዘመኑ ወያኔ ስልታዊ የሆኑ ያልሰለጠኑ እና ጫካዊ ብልሃቶችን ለመፍጠር እና ሲነቁበትም አለማቀፍ ሽብርን ይፈጥራሉ የሚለውን ወንጀል በዜጎች ላይ በመላከክ የትግል መሪ ሃሳቦችን ወደ አንድ አቅጣጫ ሊነዳቸው ይፈልጋል:: የህዝቦችን የመብት እና የነጻነት ጥያቄ መመለስ ያቃተው ወያኔ በሚፈጥራቸው የፈጠራ ወሬዎች ህዝቡን ለማደንዘዝ እና ለማዘናጋት እየዳከረ ይገኛል::የስርኣቱን ንዝህላልነት እና እየደከመ ለመውደቅ መንገዳገዱን እንዳያሳብቅበት ይመስላል የተለያየ ዘዴ በመፍጠር እና በማስወራት ራሱን ለትዝብት ዳርጓል:: ህዝብን አዘናጋለሁ ብሎ ራሱ በመዘናጋት በሽታ የተጠቃው ወያኔ ለህዝባዊ ጥያቄዎች መልስ ቢሰጥ የተሻለ ይሆናል:: የዛኔ ህዝብን ማዘናጋት ይቻላል::

የራሳቸው ደጋፊዎች እና ተቃዋሚ ዲያስፖራዎች በሃገር ውስጥ ያለው የሰብኣዊ መብት አያያዝ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች….. የኑሩ ውድነት የመዘዋወር መብት የሃይማኖት እና የህግ ጉዳይ ጥያቄዎችን አንግበው ተነስተውባታል ወያኔ ላይ:: በምንም ነገር ህዝብን በማዘናጋት ትግልን ለማሰልሰል የተደረጉ ሙከራዎች አይሳኩም ህዝባዊ ጥያቄዎች ሲመለሱ የዛን ጊዜ …የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ሲፈቱ ያን ሰአት …ህዝብ ጠግቦ ሲያድር…መልክም አስተዳደር ሲሰፍን ሰው በእውቀት ሲሰራ ጎሳ መቁጠር ሲቆም …ፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ በሃገሪቱ ሲሰፍን ጠላትነት እና የጎሳ ተኮር ፖለቲካ ሲወገድ የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ ሲኖር ፍርድ ቤቶች/ዳኞች ከመንግስት ባለስልጣናት መዳፍ ወተው በነጻነት ሲሰሩ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ሲመለሱ ህዝብ አርፎ ይቀመጣል::

የሙስሊሙ ሕብረተሰብ ጥያቄና የተቃውሞ ሰልፍ፣ የተቃዋሚወች ጫጫታ፣ የኢኮኖሚው ድቀት፣ የስራአጥነት ብዛት፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን እንዲአሰፋና የዜጎችን መብት እንዲጠብቅ በምእራቡ ዓለም የሚደረግበት ግፊትና ተጽእኖ ወዘት ከአቢዮታዊ ዴሞካራሲ ጋር በቀጥታ የሚላተምበት ስለሆነ ብዙ ቅራኔ ውስጥ መግባቱ አያጠራጠርም:: በሰላም ሊአስገዛው የሚችል አይሆንም:: ተቃውሞው በዓይነት በመጠንና በስፋት እየጨመረበት ይሄዳል:: የህዝብ ተቃውሞ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የመንግስት አፈናም እይተባባሰ ይሄዳል::ይሕም ወደ ሕዝብ አመጽ ይሸጋገራል::ህዝባዊ ጥያቄዎች ታዝለው ግን ረዥም ማንገድ መሄድ አደጋ ስላለው የተዘናጋው ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው::

‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ በአጥቂነት ቦታ ተሰልፎ እየተጫወተ ነው››የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር
ትብብሩ ምርጫ ቦርድ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን በር ለመዝጋት እየተጋ መሆኑን አስታወቀ
Image
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን በር ለመዝጋት እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል ቅሬታውን ገለጸ፡፡ ትብብሩ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ምርጫ ቦርድ ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ የፓርቲዎችን ትብብር ‹ህገ-ወጥ› በማለትና በአባል ፓርቲዎቹ መካከል ‹አሰባሳቢና ተሰባሳቢ› እንዳለ በማስመሰል አለመተማመን ለመፍጠር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል፡፡
ትብብሩ የትብብሩ አባል ፓርቲ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ‹‹ትብብር በሚል ማሰባሰብን›› እንደ ጥፋት ቆጥሮ ይቅርታ እንዲጠይቅ ደብዳቤ መጻፉ ተገቢነት የሌለውና ትብብሩ የሚያወግዘው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ቦርዱ በአደባባይ ‹‹ፓርቲዎችን በእኩል ዓይን ነው የምመለከተው፣ በሆደ ሰፊነት እያስተናገድኩ ነው›› ቢልም፣ በፓርቲዎች መካከል አድሎ እንደሚፈጽም በማስረጃ ማስረዳት እንደሚችል የገለጸው ትብብሩ፣ የሚከተሉትን ነጥቦች በዋቢነት አንስቷል፡፡
1. ገዥው ፓርቲ/መንግስት ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚለው ፕሮግራማችን ህገ-መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን የጠራናቸው የአደባባይ ስብሰባዎችና ሰልፍ በማፈን ህገ-ወጥ እርምጃ ሲወስድ ቦርዱ ‹‹ህገ ወጥና እኔ የማላውቀው ትብብር ነው›› በሚል ክስ ማቅረቡ፣
2. ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ የትብብሩን አባል ፓርቲዎች በማበላለጥ አሰባሳቢና ተሰብሳቢ፣ የሁከት ጠንሳሽና ጀሌ፣ በማለት ያለ መተማመን ስሜት በመፍጠር ለመከፋፈል ያደረገው ሙከራን መጥቀስ ይቻላል ብሏል በመግለጫው፡፡
ፓርቲዎች በትብብር የጋራ አቋም ለመውሰድም ሆነ የጋራ ተግባር ለመፈፀም የቦርዱ እውቅና እንደማያስፈልግ፣ ከዚህ በፊት ለበርካታ ጊዜያት ፓርቲዎች በጋራ የጠሯቸውን ሰላማዊ ሰልፎች፣ በህጋዊ ሰውነታቸው የመሰረቷቸውን ግንኙነቶች (የኢተፓዴኀ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ መኢአድ፣ ኦብኮ፣ ደቡብ ህብረት ኀብረትና አማራጭ የመሰረቱትን ‹ትዲኢ›› እና 33ቱ) አውቀው መርሳታቸው፣ ገዥው ፓርቲ አምስት ክልሎችን ከሚመሩ ፓርቲዎች ጋር አጋር በሚል የሚያደርገው ግንኙነት ከእኛ ትብብር ቀርቶ በግንባር ከተደራጁ ያለፈና የጠነከረ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ለዘመናት በዘለቀበትና አንድም ቀን ጥያቄ ባላነሳበት፤ ቦርዱ በአዋጅ ባልተሰጠው ሥልጣን ለገዥው ፓርቲ ‹አጋር መልማይ› ወይንም የህወሓት/ኢህአዴግ ‹‹ገንዘብ አዳይ ሆኖ ለተለዩ ፓርቲዎች ዳረጎት በሚሰፍርበት እውነታ ውስጥ ሆኖ ትብብሩ ላይ ጣት መቀሰሩን በማሳያነት አንስቷል፡፡
በመሆኑም ‹‹ትብብራችን በገዥው ፓርቲ ላይ የፈጠረውን የፍርሃት ስሜት የትብብራችን የጋራ እንቅስቃሴም ለገዥው ፓርቲ ሥጋት መፍጠሩን ለዚህም ምርጫ ቦርድ ይህን አይነቱን ህገ-ወጥ ፖለቲካዊ ድጋፍ በመገናኛ ብዙሃን በማሰራጨት ህዝቡ የሚሰጠንን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመግታት ወይንም ፈሪ ከተገኘ ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ የሚደረግ ተራ ፕሮፖጋንዳ ነው›› ብሏል፡፡
በአጠቃላይ ቦርዱ እየፈጸማቸው ያሉትን ተግባራት በህገ-መንግስቱና የምርጫ ህጉንና ሌሎች የአገሪቱ ህጎች ከተጣለበት ከባድ የዳኝነት ኃላፊነት ወጥቶ ለገዥው ፓርቲ በአጥቂነት ቦታ ተሰልፎ የሚጫወት መሆኑንና ይህም በሕገ-መንግሥት የተቀመጠውን የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሂደት ከደረሰበት ወደኋላ የሚመልስ አካሄድ ነው ሲል ገልጹዋል፡፡
በመጨረሻም ትብብሩ ህገ-መንግስቱን አክብሮ እስከተንቀሳቀሰ ድረስ በትብብር ከመስራትና የጋራ ህጋዊና ሰላማዊ ትግል ከማድረግ ለአፍታ እንደማያቆም አስታውቋል፡፡

በፖለቲካው ረገድ የስርኣቱ ገዢ ፓርቲዎች እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ ከመድረሳቸውም በላይ አመራሮቹ አድፍጠው አንዱን አንዱን እየጠበቀ በፍራቻ አለም ውስጥ እየዋተቱ ይገኛሉ::አቤት የሚባልበት እየጠፋ ነው፡፡ የውሳኔ ሰጪ ያለህ ቢባል መልስ አይገኝም፡፡ ፋይሎች የሚያያቸውና የሚያነባቸው አጥተዋል፡፡ መልካም አስተዳደር ገደል ገብቷል:: ……… የተጭበረበረ አፋኝ ፖለቲካ ያስከተለው የኢኮኖሚ መንኮታኮት የአገሪቱን የፖለቲካ አናቶች ለውጥ እንዳያመጡ በመተብተብ ቀውስ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን ከስብሰባዎች እና ከጭብጨባዎች ብዛት እየታዘብን ነው::በሌላ በኩል ሚዲያዎች ህዝብን መዋሸታቸው እና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋላቸው አገሪቷ እንድትንኮታኮት በር የከፈተ ሲሆን የዚህ መፍትሄ ስልጣን መልቀቅ………………..‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

phpBB [video]

ገዢ ቢሰባ ለመሬት አህያ ቢሰባ ላራዊት (ቢኒያም ግዛው ከኖርዌይ ኦስሎ)
Biniam Gizaw
Image
ይሄ ምርጫ መቼስ ስንቱን ያስታውሰናል?በደርግ ዘመን እናቶች ወንድ ልጃቸውን ከየጉያቸው እየተነጥቁ እና እየታፈሱ በጦርነት ሲማገዱ ወንድ ልጅ ላለመውለድ. . .
ትዝም አላለሽ ወይ የክፉ አመቱ
ላንቺና ለልጅሽ ያለቀ ስንበቱ
ማህጸኔን ዝጋ ይቅር ምን አባቱ
በእንባ እየዳከርሽ ብለሽ ያልሽበቱ።
እያሉ ፈጣሪን ወንድ ልጅ እንዳይሰጣቸው የለመኑትን ቤቱ ይቁጠራቸው። የአፈሳና የሀገራችንን አንድምታ ለመረዳት ከሰሞኑ በየከተማዎችና ጎዳናዎች ያለው የድብደባ የአፈሳና የሞት ፍርሀት ድባብ ተቀባብሎ ለቃታ የተዘጋጁ ጥይት በእያንዳንዱ ሰላማዊ ዜጋ ጆሮ ስር ተደግኖ እንደሚራመድ በቀላሉ መረዳት ይቻላል።

. . . ጭቃ ከማቡካት ጀምሮ አብሬው ያደኩት ጓደኛዬ ስሙ ጌታቸው ይባላል። እንዴት እንደምንዋደድ እንደምንተሳሰብ እና እንደምንመካከር አትጠይቁኝ። በቃ ጌቾ ምርጥ ጓደኛዬ ነው።

እናም በጊዜው ወያኔ መዲናችን አዲስ አበባ ገቡ ገቡ የሚባልበት ሰአት ኖሮ ግራ መጋባቴን ከባልንጀራዬ ላወራ በአጥር በኩል ጌቾ!ጌቾ! ብል እናቱ ወ/ሮ በለጥሻቸው ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ከበሮአቸውን ጸሀይ ላይ እያገላበጡ ግቻ ያርግህ. . . ጎይቶም አትልም! ብለው ቀልቤን ገፈፉት። ነገሩ ወዲህ ኖሮ እሳቸውም ወ/ሮ በለጥሻቸው ታጋይ ትብለጽ ተብሎ ስማቸው መተርጎሙን ያወኩት ቆይቼ ነገር ከገባኝ በኋላ ነው። ከዚያማ እነአቶ ክፍሉ (ክፍለእግዚእ) እነአዲስ (ታጋይ ሀዲሽ) ወዘተ ስናዳምጥ የጫካ ስም ብቻ ሳይሆን የከተማም ስም እንደነበራቸው ተረዳን።

ከዛ በኋላማ ምኑን ልንገራችሁ በኳስ ሜዳ ሰው የጠፋ ጊዜ በረኛ ካልሆነ ወደ ውጪ የወጣ ኳስ አቀባይ የነበረው ጊቾ በግልጥ ፎሪ የወጣውን እንደፈለገ እና ደስ እንዳሰኘው ጎል ብሎ ሲያፀድቀው ቢደብረንም መስማማት ብቻ ሆነ። አይ የቀን ክፉ! ግንቦት 20። ይኽው እስክንበታተን ድረስ ጎይቶምም እንደኛ ባሉት ላይ ተቀይሮ ሲጎለብት ታጋይ ትብለፅ ደግሞ እነማዘርን በዳቦ ተቆጣጥረው ሲጠረንፉን ከረሙ።

ጦጣ በአንድ ወቅት ለቃለ መጠይቅ ቀርባ ኖሮ ምን ትወጃለሽ? ተብላ ብትጠየቅ የዛፍ ላይ ትግል አለች አሉ። በፀዳ ሜዳ ግልፅነትና እውነት ባለበት ምርጫ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ማየት ከንቱ እየሆነ መምጣቱ በዕጅጉ ያሳዝነናል ። አንድ ጎጠኛ ብሔረሰብ ብቻ በሚመቸው ፓርላማና በየቀበሌው እንደ ጦጣ በስልጣኑ ላይ እየተንጠላጠለ 23 ዓመት መግዛቱ ስርዓቱ ምንኛ አስከፊ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘመናት ተከብራ የኖረችና ህዝቦቾም ልዩነትን ወደሆላ በመተው በጋራ ፣በመቻቻል ፣በመካባበር ሀገራቸውን አስከብረው ከዘር እና ከእምነት ይልቅ ኢትዮጵያውነትን በማስቀደም ኢትዮጵያዊነት የገነነባት ሀገር እንደነበረች ይታወቃል እነሆ ዛሬ ወያኔ የሁትሱና ቱትሲን ስርዓት ናፍቆ ገዢ ከኔ ዘር ሌላ ለአሳር እያለ ሰፊውን ህዝብ ለጦርነት ጋብዞታል። ወያኔ ፈጽሞ በኢትዮጵያዊነት የማያምን እና የኢትዮጵያ ህዝበም በአንድነትና በፍቅር እንዲኖር የማይፈልግ ጸረ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ይህንንም በመረዳት እኛ ኢትዮጵያኖች አንድነታችን ለወያኔ የራስ ምታት መሆኑን አውቅን አንድነታችንን የሚያጠናክር ስራዎች ላይ ልናተኩር ይገባል :. ዘረኛው የህህዋት መንግስት በአንድ ወቅት አርሱ አደሩ የሀገሬን ገበሬ እኔ አውቅልሀለሁ እያለ ካለበት ሀገር መሬትና ቀኤ ድረስ መጥቶ ልግዛህ እያለ መከራውን ሲያበላው . . .

ሳለቅስ ሳነባ የሰጠኽኝ ሸማ
ጉድ በል ያገሬ ልጅ እንካ መርዶ ስማ
የወንዝህ ማዕረግ በትግሬ ተቀማ

እያለ ለአያትና አባቱ በቅኔ ብሶቱን መናገሩ አፈናና ረግጣውን ቅሚያና ዘረፋውን መቋቋም ቢያቅተው መሆኑ ልብ ይሏል። የፈረንሳዩ ደራሲና ፈላስፋ ቪክቶር ሁጎ “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right.” ብሎ ማለቱ አንደ ወያኔ ላለ በአንድ ብሔር የበላይነት ተንፈናጥጦ እንደፈለኩ ልግዛህ ለሚል መንግስት ትክክለኛ አባባል ነው።

ምርጫ ፍትህና ዴሞክራሲ ምን እንደሆነ ለማይገባው መብት ማስከበሪያው ብቸኛ መንገድ ለለውጥ ፀንቶ መታገል ብቻ ነው። በአሳማ መንጋ የምርጫ ውድድር ያው አሸናፊው አሳማ እንጂ ነብር ወይ አንበሳ አይሆንም። በመሆኑም ያው አሳማ ነገም ልርገጣችሁ ማለቱ አይቀርም። በሰብዓዊ ትግል ተስፋ አይቆረጥም የሰፊው ህዝብ መብት ታላቅ ውቅያኖስ ነውና ጥቂት የአምባገነን ጠብታ ሰፊውን ባህር አያደፈርሰውምና አሁንም የሰብዓዊ መብት ትግል አሸናፊ ነው። በጥቂት ዘረኞችና በአንድ ጎሳ የበላይነት የተያዘው የወያኔ አገዛዝ የሰፊውና የታላቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በምንም መልኩ ሊገታው አይገባም ይልቁንም ”ገዢ ቢሰባ ለመሬት አህያ ቢሰባ ላራዊት” እንዲሉ በማን አለብኝነት የተንሰራፋውን ወያኔና አግዛዙ መቃብሩ ተምሶ ያለቀ መሆኑ ግልፅ ነው። እናም በሁሉም አቅጣጫ የትግላችንን ትንቅንቅ ልንቀጥል ይገባል እላለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

የምርጫ ቦርድ ቧልት ! YIDNEKACHEW KEBEDE

—————–
ከምንም በላይ ለነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል ትኩርት በመስጠት ሰማያዊ ፓርቲ ለቦርዱ ጥያቄ አቅርቧአል፡፡ ፓርቲያችን ለሚያቀርባቸው ተደጋጋሚ ጥያቂዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ምርጫ ቦርድ ሲንደፋደፍ ማየት የተለመደ ክስተት ነው፡፡
————————
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በታሕሣሥ 28/2007 ዓ.ም ባደረግው ስብሰባ፣ሰማያዊ ፓርቲ እስከ ጥር 4/2007 ዓ.ም ፣ምርጫ ቦርድን ይቅርታ በመጠየቅ የይቅርታ ደብዳቤ እንዲያስገባ ውሳኔ ማሳለፉን በ EBC የዜና እወጃው፤ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኝነት ኃላፊ ቀርበው ተናግረዋል፡፡ ፓርቲያችን በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ፣እኔ በግሌ እንዲኸ ዓይነቱ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የማይሞከር ፍፁም ድፍረት የተሞላበት የሞኝ አሞኝ ጨዋታ ምርጫ ቦርድ ባይሞክረው የተሻለ ነበር፤የሚል እምነት አለኝ !
ሰማያዊ ፓርቲ በመልመልመጥ ወይም በልመና ላይ የተመሠረት የፓለቲካ ውሳኔ እንደማያሳልፍ ዛሬ ብቻ ሣይሆን ከምስረታው ጀምሮ የሚታወቅበት የፀና አቋሙ ነው፡፡ለዚህም ፓርቲያችን ገና ከምስረታው ጅምሮ ከምርጫ ቦርድ የገጠመው ውጣ-ውረድ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ከተለመደው ከቦርዱ ጋር የመተሸሸት አካሄድ እራሱን በማራቅ በህግ እና በሞራል የበላይነቱን በማረጋገጥ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ መሠረት ሕጋዊነቱን ያረጋገጠ ፓርቲ ነው፡፡ምርጫ ቦርድ በወቅቱ የፓርቲያችን ውሳኔ በመቃዎም ደፋ ቀና ማላቱ የሚታወስ ቢሆንም ፣ ምንም ዓይነት የሕግም ሆኖ የሞራል ድጋፍ ስለሌለው የፓርቲያችን ውሳኔ በመቀበል፣ እውቅና ሰጥቻለው በማለት ሊያሳውቀን ችሎአል፡፡
ይህ ከሆነ ከ3 ዓመታ በኋላ “ሰማያዊ ፓርቲ ከምስራታው ጀምሮ በቦርዱ ተመዝግቦ እውቅና ሳይሰጠው ፣እንደተቋቋመ በማስመሰል መግለጫዎችን ሲሰጥ ቆይቷል”በማለት ቁጭት አዘል ማስጠንቀቂ ለመስጠት መቻሉን ለማመልከት ቦርዱ እንደመነሻ የተጠቀመበት አንዱ ክስ ነው፡፡ክሱ ግን ፍፁም መሠረት ቢስ ከመሆኑ ባለፈ ፣ትልቅ ተቋም ነኝ ብሎ የሚያስበው ምርጫ ቦርድ “እንደ-ነገረኛ ሰው” ቂም በመያዝ አሁን ላይ ላሰበው መጥፍ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ሲጥር መታየቱ ትዝብት ውስጥ የሚጥል አካሄድ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ምርጫ ቦርድ በተለያየ ወቅት የመወያያ ዕርስ በማዘጋጀት ለፓርቲያችን የእንወያይ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፣ፓርቲያችን ለቀረበለት ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት በቦታው ተገኝቷል፡፡ ይሁን እንጂ ከምርጫ ቦርድ ጋር በተደረገው የፓርቲዎች ውይይት፣ሕጋዊ እና መሰረታዊ ጥያቄ በመጠየቅ እንዲሁም ጠንካራ አቋም በመያዝ ከመርጫ ቦርድ ጋር አለምግባባቶች ተፈጥሯአል፡፡ ፓርቲያችን ለሚያቀርባቸው ጥያቄ እንዲሁም ገንቢ ለሆኑ አሰተያየት ቦርዱ እሱ እንደሚለው “ሆደ ሰፊነቱ”ቀርቶ በአግባቡ የፓርቲያችን አቋም የመረዳት አቅም ቢኖረው የት በተደረሰ ነበር፡፡
በተለይ ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያስገደደበት ዋና ዋና ምክንያቶች “በምርጫ አልመግባባት እና የግጭት አፈታት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጀት” ታህሳስ 3/ 2006 ዓ.ም፣ “የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ የአፈጻፀም የጊዜ ሠሌዳ” ታህሳስ 7/2007 ዓ.ም እና “የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ መንግስት ለሚያድርገው የፋይናስ ድልድል” ታህሳስ 22/2007 ዓ.ም በተካሄደው የፓርቲዎች ምክክር ላይ ሰማያዊ ፓርቲ የያዘው አቋም ነው፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ዕርስ ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶች ሰማያዊ ፓርቲ ፣ገዥው ፓርቲ በጉዳይ ፈጻሚው የምርጫ ቦርድ በኩል በተለመደው መንገድ በምርጫ ሥም ለመሥራት የተያያዘውን እኩይ ተግባር ራቁቱን የሚያስቀር፣ ምክንታዊ የመወያያ አጀንድ በማቅርብ፣ ሰማያዊ ላቀረበው ጥሪ ቦርዱ ለመቀበል ፍቃዳኛ አለመሆኑ ለማረጋገጥ ተችሎአል፡፡ከምንም በላይ ደግሞ ለነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል ትኩርት በመስጠት ለቦርዱ ጥያቄ አቅርቧአል፡፡ ፓርቲያችን ለሚያቀርባቸው ተደጋጋሚ ጥያቂዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ምርጫ ቦርድ ሲንደፋደፍ ማየት የተለመደ ክስተት ነው፡፡
ቦርዱ ከመንደፋደፍ ተግባሩ ተላቆ ወደ-እውነተኛ መንገዱ እንዲገባ የተደረገው ተደጋጋሚ ጥርተ ባለመሣካቱ፣ በሰለጠነ መንግድ ምርጫ ቦርድ የሚያዘጋጃጀቸው የውይይት መድረኮች ፓርቲያችን የተጣለበት የህዝብ አደራ ለመወጣት ስብሰባዎችን እረግጦ ውጥቷአል፡፡ይህ ደግሞ የተለመደ የተቃዎሞ መግለጫ ዘዴ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ የያዘው አቋም ተገቢ ብቻ ሣይሆን ሕጋዊም ጭምር ነው፡፡ይልቁንስ መሆን ካለበት ፓርቲያችን ለጠየቃቸው ጥያቄ እና ለሰጠው ገንቢ አሰተያየት ፈጣን ምላሽ ባለማግኘቱ ምርጫ ቦርድ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል፡፡
የምርጫ በርድ ለገዥው መንግስት የማድላት አደገኛ ሱስ መጠመዱን የሚያሳብቅ ደርጊቶች ሲፈፅም ማየት ለኢትዮጵያዊያን አዲስ ነገር አይደለም ፡፡ ይልቁንም እንዲህ አይነቱ አስመሣይ አካሄድ የሚፀየፍ ፣እውነተኛ እና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ ተቋቁሞ ኃላፊነቱን ሲወጣ ማየት የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ምኞት ነው፡፡ ሕዝብን የማስተባበር እና የመምራት ኃላፊነት ያለባቸው ፓርቲዎች ሰማያዊ ጭምር ለዚህ ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ለማለት የበለጠ ድፍርተ የሚሰጠኝ፣ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች 8 ፓርቲዎች ጋር በመተባበር በመጪው ምርጫ ሂደት ላይ እና በምርጫ ቦርድ ላይ ያለው አቋም ነው፡፡
የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ “ነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ “በሚል መርዕ በሁለት ዙር የተከፈለ ሕዝባዊ ንቅናቂ በመፍጠር በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘጠኙ የትብብር ፓርተሪዎች የመጪው ምርጫ ነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል ትኩርት በመስጠት እስከ ሕይወት መሰዋትነት በመክፈል የህዝብ የስልጣን ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ቆርጠው ተንስተዋል፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ ያልተዋጠለት ገዥው መንግስት በጉዳይ ፈፃሚው በምርጫ ቦርድ አማካኝነት የትብብሩን እንቅስቃሴ ለመግታት በመጣር ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጄ የዘጠኙ ትብብር ፓርቲዎች ተስማምተው ለማስፈፀም የተነሱለትን ዓላማ፣ በኽንዲ ዓይነቱ ተልካሻ ምክንያት ወደኋላ የሚሉበት አንዳችም ምክንት እንደማይኖራቸው ከመነሻቸው የያዙት አቋም የሚያመላክት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

Image

ብንውጠም ባንውጠውም ቢያቅለሸልሸንም ቢያስመልሰንም ፖለቲካ ውስጥ ካለ እውቀት ተዘፍቀን የምንዋልል የደረቅ ትኩሳት መርህ ተጠቂዎች እና የስሜት ፈረስ ጋላቢዎች ማወቅ ማገናዘብ ባይፈጥርብንም ካሳለፍነው ካለው የሚምጣውን እንዳቅማችን ለማንደርደር ማሰብ እንዲጠበቅብን መመከርን ባንጓጓም አንድ ነገር ግን እንድናውቅ በራሳችን የገደል ማሚቱ ውስጥ እያላተም መጎላኮስ የሚኖርብን ነገር ቢኦር እውነት ሰአቷን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች !!! የሚለውን ሃቅ ነው:: እኛ የሚለውን በእናንተ ሂሳብ አወራርዱት::

የዚህ ሰሞን የወሬ መላምቶች ወደ ተግባር በረራ ተለውጠው ብርቱዎቹ አስመራ ከትመዋል:: በደጋፊ በተባባሪ በጠርጣሪ እና በተቃዋሚ ብልቶች መካከል በየማህበራዊ ድህረገጹ እና ፓልቶክ የጡዘት ስሪቶች እየተፈተሉ ነው::ደጋፊ በኢትዮጵያ ላይ ያለው የሰቆቃ ስርአት ከስሩ ተመንግሎ እንዲወድቅ ካለው መልካም ምኞት በሃገር ወዳድነት ስሜት ሃሳቡን ሁሉ እዚያው አድርጎ ይተነገረውን ሁሉ ተቀብሎ በመፍከንከን ላይ ሲሆን ተባባሪዎች ደሞ የነአይዞን ስራቸውን በፖለቲካው ንግድ ውስጥ እያጧጧፉት ነው::ተጠራጣሪው በዋናነት ያተኮረው በሻእቢያ ላይ ያለውን እምነት በማሰላሰል አስመራ ለከተሙት ብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን ደህንነት ሲሆን በለሆሳስ ጸሎቱን በማደረስ ላይ ሲሆን ተቃዋሚ የተባሉት ያው የወያኔ አሽከሮች የዘመኑ ፖለቲካ እና የለውጥ ማእበል ያልገባቸው ድፍርስ ሆዳሞች ሲያላዝኑ ማየት ምን ያህል እውቀት አልባ እንደሆኑ ሲመዘን ያሳፍራል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና አጀንዳ ሻእቢያ ሳይሆን ወያኔ ነው::በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ እንግልት እስር ሰቆቃ ግድያ ወዘተ እየፈጸመ የሚገኘው የህዝቦች ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ነው!ይህንን ስር አት ለማውረድ በውስጥም በውጭም በስፋት ትግሉ ቀጥሎ ይገኛል:; ከበፊቱ በትሻለ ሁኔታ የተያዘው ትግል ወያኔን እያፍረከረከ በራሱ ፍርሃት እንዲሸበር አድርጎታል::ሊቀጥል የሚገባው ትግል መሆኑ እሙን ነው::በውጪው ያለው ሃይል በትጥቅ ትግል ተሰማርቻለሁ የሚሉ ቡድንኖች ከ15 አመታት በላይ በአስመራ መሽገው ይገኛሉ::እነዚህን ሃይሎች በትለያየ ጊዜ የተቀላቀሉ የጎበኙ የተገነጠሉ ወዘተ አካላት የየራሳቸውን አስተያየት በይፋ ስጥተዋል::ወያኔን ለመጣል ካላቸው ፍላጎት የመነጨ በአስመራ የመሸጉትን ታጋዮች ጎብኝተናል ያሉ ሁሉ ከበጎ ጎኑ ተነስተው ኢሳያስ አፍወርቂን እስከ ማሞገስ እና እጅ እስከመሳም ከመድረስ አልፈው ሁኔታዎችን እያጠሩ ሂደው በተመጣጠነላቸው ሰአት ላይ እውነታውን አፈንድተውታል::እውነታውን በማውጣታቸው ይህን ተከትሎ በአስመራ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከግድያ እስከ እስር እና እንግልት ደርሶባቸዋል:;ማምለጥ የቻሉም አምልጠው ኤርትራን ለቀዋል::

ጎን ለጎንም አስመራ ከትመው የሻእቢያ ስራ አያዋጣን ደባውና ሴራው ለኢትዮጵያ ነጻነት በሚደረጉ ትግሎች ላይ ከፍተኛ እንቅፋት ነው በሻእቢያ እርዳታ ነጻነት ሳይሆን ባርነት ነው የገዛነው ታጋዮቻችን በስልተና ሳይሆን በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው ቀን እየገፋን አንችልም ሻእቢያ በበቂ ሁኔታ አደራጅቶ እንድንዘምት ሊያደርገን ሳይሆን ብስማችን ገንዘብ እየሰበሰበ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እንጂ ውጤት የለውም ያሉ አስመራን ትተው ሃገር ቤት እስጥ የትጥቅ መሰእረታችንን ዘርግተናል ብለዋል::እንዲሁም ከጨካኙ ወያን ጋር በመቀላቀል የታጋይ ድርጅቶችን ምስጢር በመባከን በመሰለል ደባ የፈጸሙ ቅጥረኞችም የማይርሳ መጥፎ ተባሳ እና የትግል መጓተት አስከትለዋል::

የሰሞኑ አነጋጋሪ ጉዳይ ደሞ አንደ እውነት ካለ በፍጥነት ከዘገየ ደሞ ቀኑን እና ሰአቱን ተብቆ እንደሚያሰማን ራሳችንን አዘጋጅተን እየጠበቅን ነው::ሁኔታዎችን በጠራ መንገድ ተከታትለን አይተን እንዘግባለን ያሉ ብርቱዎቹ ኢትዮጵያውያን አስመራ ደርሰው በረቀቀ መንገድ ችሎታቸውን እና ክህሎታቸውን ተጠቅመው አንድ እውነት ይዘው እንደሚመጡ የታመነ ሲሆን ግን ግን ወዲያው እንደማይተነፍሱን የተረጋግጠ ጉዳይ ነው::ከዚህ በፊትም አስመራ የደረሱ ከታች እስከ አናቱ ኢሳያስ ድረስ ቃለመጠይቅ ያደረጉ ውነታውን ያጠሩት በሂደት ሲሆን እነዚህም ብርቱዎቹ እንደአካሄዳቸው ተመልሰው ያለውን ሁኔታ እና እውነታ በሂደት እንደሚያሳውቁን ተስፋ ሰንቀናል:: ሻእቢያ እና ልጁ ወያኔ በሃሰት ዶክመንተሪ እና በዉሸት ፕሮፓጋንዳ የታወቁ የፈጠራ ደራሲዎች ቢሆኑን ህዝቡ እውነታውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተግስት በመከታተል ትግሉ እያፋፋመ እንደሚገኝ እሙን ነው::በኤርትራ ሃገርን ከዛሬ ነገ ዘምተን ነጻ እናወጣለን ብለው ሰልጥነው በበረሃ የተቀመጡት ታጋዮች ለነሱ ሕይወት እና ደህንነታዊ ጥንቃቄ ሲባል ራሱን የቻለ የቅብብሎሽ ሂደት ቢኖርም እውንት ግን ሰአቷን ጠብቃ ነጻ ትወጣለች::ፖለቲካ የሚገባው ይገባዋል የማይገባው ጭፍን ግን አንብቦ ምራቁን ይዋጥና አርፎ ይጸልይ::

Image

=====================================
አንዳንዶች ከማይቀረው ዕጣ ፈንታቸው አይናቸውን ጨፍነው ይሸሻሉ፤
የሚሸሹበት መንገድ ግን ወደማይቀረው ዕጣ ፈንታቸው በፍጥነት ያደርሳቸዋል፡፡
=====================================

ሰሞኑን ኢህአዴግ በምርጫ ቦርድ በኩል የያዘውን ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ዘመቻው አንድነትን፣ መኢአድንና ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ 2007 ሜዳ ገፍቶ ማስወጣት ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በኢህአዴግ ጥቁር መዝገብ ላይ የሰፈሩበት ምክኒያት ደግሞ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በምርጫ 2007 ኢህአዴግ የሚያጭበረብርበትን መንገድ ዘግተው ከፍ ባለ ድርጅታዊ ጥንካሬና በቁርጠኛ አመራር የኢህአዴግን መጨረሻ ለማወጅ ስለተነሱ ነው፡፡ ኢህአዴግ የሚሸሸው በ2007 ሊገጥመው የሚችለውን የሽንፈት ዕጣ ፈንታ እንደሆነ ተግባሩ ያሳብቅበታል፡፡ ሽሽቱ የኤዲፐስ አይነት ስለሆነ ከዕጣ ፈንታው ሊያመልጥ ግን አይችልም፡፡

ኤዲፐስ፣ በግሪክ አፈታሪክ ውስጥ ያለ ገጸ-ባህሪ ነው፡፡ አባቱ የቲብዝ ንጉስ ነበር፡፡ እናትና አባቱ የልጃቸውን ዕጣ ፈንታ (አባቱን የሚገድል እናቱን የሚያገባ ልጅ እንደወለዱ) ቴረሲያስ ከሚባል አንድ ነብይ ሰምተው ስለነበር እያዘኑ እንዲሞት ይፈርዱበታል፡፡ እናም ለእረኛቸው ግደል ብለው ሰጡት፡፡ እረኛው አልጨከነም፡፡ ለሌላ አሳዳጊ ሰጠው፡፡ ኤዲፐስ ከንጉስ ቤት እንዲገደል ወጥቶ በሌላ ንጉስ ቤት አደገ፡፡ እውነተና እናትና አባቱን ሳያውቅ ጎረመሰ፡፡ ባንድ ክፉ ቀን አንድ ነቢይ የራሱን ዕጣ ፈንታ “አባትህን ትገላለህ እናትህን ታገባለህ” ሲል አረዳው፡፡ ኤዲፐስም አወጣ አወረደና አባቴን ገድዬ እናቴን ከማገባ ብሎ ሰረገላውን አሰናድቶ ፈረሱን መጭ እያለ ከሀገር ለመጥፋት በረረ፡፡ የሚሄደው ሀገር ወደ ቲብዝ ነበር፡፡ ቲብዝ ያለው ንጉስ አባቱ መሆኑን ግን አያውቅም ነበር፡፡ መስቀለኛ መንገድ ላይ ከአባቱ ጋር ተገናኘ፡፡ አሳልፈኝ አላሳልፍም በሚል የክብር ጥያቄ ጠብ ገጠሙ፡፡ ኤዲፐስ አባቱን ገደለው፡፡ ቲብዝ ያለ ንጉስ ቀረች፡፡ ኤዲፐስ የአባቱን ሚስት አግብቶ በቲብዝ ላይ ነገሰ፡፡

የኤዲፐስ ታሪክ ባጭሩ ይሄ ነው፡፡ ኤዲፐስ ከዕጣፈንታው አይኑን ጨፍኖ ሸሸ፡፡ የሸሸበት መንገድ ግን ወደማይቀረው ዕጣ ፈንታው በፍጥነት አደረሰው፡፡

ኢህአዴግም የኤዲፐስን መንገድ የመረጠ ይመስላል፡፡ በ2007 ምርጫ ከማይቀረው የሽንፈት ዕጣ ፈንታው አይኑን ጨፍኖ እየሸሸ ነው፡፡ የሚሸሽበት መንገድ ግን ወደ ማይቀረው ዕጣ ፈንታው በፍጥነት እያደረሰው እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው፡፡

አንድነት ገና ከጠዋቱ ምርጫው ላይ ያለውን አቋምና ስትራቴጂ ግልጽ አድርጓል፡፡ “ምርጫ ውስጥ እንገባለን፣ አንድነት እንዲመረጥ እንቀሰቅሳለን፣ የህዝብን አሸናፊነት ኢህአዴግ በማጭበርበር ቀለብሳለሁ ካለ ደግሞ አስጨናቂ በሆነ ህዝባዊ እምቢተኝነት የህዝብን ድምጽ ለማስከበር የተቀናጀና ቁርጠኛ አመራር እንሰጣለን፡፡” ብሏል፡፡ ይህ አቋም አሁንም ያለ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከምርጫው በፊት ማጭበርበር ውስጥ ከገባ ውድቀቱም ከምርጫው በፊት ይሆናል፡፡ ሽሽቱ እጣፈንታውን ቢያፈጥነው እንጂ ከሽንፈት አያስመልጠውም፡፡

ቺርስ! ለነገው ብሩህ ቀናችን፡፡

ስለሺ ሐጎስ

Image

Image

– አንድነት ፓርቲ በድጋሚ የምርጫ ቦርድን ደባ ለማክሸፍ ጠቅላላ ጉባዬ ጠርቷል::
– አንድነት ፓርቲን ከሰላማዊ ትግሉ ለማስወጣት የተደረገውን ደባ ተጋልጧል::
Minilik Salsawi
የወያኔው አምባገነን ጁንታ የአንድነት ፓርቲ በ2007 በሚደረገው ምርጫ ላይ እንዳይሳተፍ በሕወሓት/ኢሕአዴግ ፖለቲካዊ ውሳነ ተደርጎበት ወደ ምርጫ ቦርድ እንደተላለፈ እና ፓርቲውን ከምርጫው ለማስወጣት ደባ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቆመ:: እንደ ምንጮቹ ከሆነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ከማሰር እና ከማንገላታት ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ማሸማቀቀ እና ሰበብ ማብዛት ቢሞክርም አንድነት ፓርቲ ይህንን ሁሉ ተቋቁሞ በአሸናፊነት መገስገሱ ለገዢው ፓርቲ መደናገጥ በመፍጠሩ ፓርቲው በምርጫ እንዳይሳተፍ ውሳኔ ማስተላለፉን ተገልጿል::

የአንድነት ፓርቲ አደገኛ የሆነበት ሕወሓት/እሕአዴግ ምርጫ ቦርድን ተገን በማድረግ ከምርጫ ለማስወጣት እንዲሁም ተለጣፊ አንድነት ፓርቲ ለመመስረት በመጣር ላይ ሲሆን ዓላማው በአባላት፣ በደጋፊና በህዝቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር ታሰቦ የሚካሄድ ፖለቲካዊ ደባ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ ባስተላለፈው መግለጫ እንዳለው በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እና ዘላቂነት ያለው ደህንነት የሚያረጋግጠው እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋሞች ነፃ፣ ገለልተኛ እና በህዝብ ዘንድ አመኔታ ሲጣልባቸው ነው፡፡ ይህ ተቋም አሁን በያዘው ሁኔታ ከቀጠለ ከታሪክ ተጠያቂነት አይድንም፡፡ ገዢው ፓርቲም ጧት ማታ የሚያባንነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡

በመሆኑም አሁን ፓርቲያችንን ለመታደግ እና የቦርዱን የመጨረሻ ካርድ ለማስጣል አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተናል፡፡ ይህ ማለት የትግሉ መጨረሻ አይደለም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረሰብንን የሕግ ጥሰት ይዘን በፍርድ ቤት ክስ እንመሰርታለን፡፡ እስከ አሁን ያለውን ሂደት ስናየው የቦርዱ ፖለቲካዊ ደባ ቀጣይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም መላው አባሎቻችን፣ ደጋፊዎቻችን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምንወስዳቸው ተከታታይ ፖለቲካው ውሳኔዎች እና እርምጃዎች ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን፡፡ ብሏል አንድነት ፓርቲ::

እንደ ፓርቲው ምንጮች ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዲግ ባሰማራው ጥቂት ቡድን አማካኝነት አንድነት ፓርቲን ከሰላማዊ ትግሉ ለማስወጣት የተደረገውን ደባ አቶ ብርሃኑ ይግለጡ እና አቶ መሳይ ትኩ ያጋለጡ ሲሆን ቭዲዮው ይለቀቃል ተብሎ ይጠበqaል::

Image
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
በየትኛውም የአለም ክፍል በተለያየ አጣራርና ስያሜ ቢሰጣቸውም ምርጫን ለማስፈፀም በሕግ የሚቋቋሙ ተቋማት ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ተቋማት በአንድ ሀገር ዘላቂ ለሆነ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ለዴሞክራሲዊ ስርዓት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ በአንባገነን ስርዓት ውስጥ ላሉ ሀገሮች ደግሞ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ያላቸው ሚና ከምንም በላይ ከፍተኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ግዙፍ ተግባር እንዲያከናውን፣ የሕዝብ እና የሀገር አደራ እንዲወጣ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ የዚህ ተቋም አሰራር በተቋቋመለት ዓላማ፣ ሕግ እና አለም አቀፍ መስፈርት መሠረት ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀደሙት አሠራሮችና ውሳኔ አሰጣጦች በበርካታ ኢትዮጵያውያን እና አለም አቀፍ ታዛቢዎች በአሉታዊ ጎኑ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የ2ዐዐ7 ሀገር አቀፍ ምርጫን ‹‹የኢህአዴግ መጨረሻ›› እናደርገዋልን ብሎ ፖለቲካዊ አቋም ወስዶ እንቅስቃሴ ሲጀምር የምርጫ ቦርድን ቀደምት አሉታዊ ተግባሩን ዘንግቶ አይደለም፡፡ ይህ ተቋም መልካም ስም እንዲገነባ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን እድል ለመስጠት ነበር፡፡ በዚህ ስትራቴጂ መሠረት ቦርዱን በተግባር ፈተና ላይ ጥለነዋል፣ ማንነቱንም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለዓለም ማህበረሰብ በማጋለጥ ላይ እንገኛለን፣ ዛሬ ለሁለም የሚዲያ አካላት ያካሄድናቸውን የደብዳቤ ልውውጦች በይፋ አንሰጣለን፣ ሁሉም ዜጋ እንዲደርሰውም እናደርጋለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲን ከ2ዐዐ7 አጠቃላይ ምርጫ ገፍቶ ለማስወጣት ካልተሳካለትም በተዳከመ የአባላትና ደጋፊ ስሜት ውስጥ ገብተን እንድንጫወት የፈለገ ይመስላል፡፡ ይህ ደግሞ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ በ2ዐዐ7 ዓም ሀገራዊ ምርጫ ከጅምሩ በሁሉም ሂደቶች በንቁ ለመሳተፍ የያዘው አቋም እንዳስደነገጠው፤ ከዚያም አልፎ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠውን ስልጣን አጣለሁ በሚል መሸበሩን የሚያጋልጥ ነው፡፡ ይህን ፍርሃቱን በህዝብ ፊት በሚደረግ ትግል ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ የመረጠው ሜዳ በብሔራዊ ምርጫ ቦርደ በኩል እንዲሆን ነው፡፡ የቦርዱ ኃላፊዎች ተቋማዊ በሆነ መልክ ደብዳቤ ሲሰጣቸው፣ በደብዳቤ መልስ ከመስጠት ይልቅ በመገናኛ ብዙሃን ምላሻቸውን ቀድመው መናገር ጀምረዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው ታህሣሥ 27 ቀን 2ዐዐ7 ዓም የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዝአብሔር ከቦርዱ ስብሰባ በፊት በሚዲያ ወጥተው ውሳኔ በመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቦርዱ እንደተቋም ሳይሆን በግለሰብ ውሳኔ የሚመራ መሆኑን ነው፡፡ ለዚህም መገለጫው በታህሳስ 30/2007 የደረሰን ደብዳቤ የቦርዱን ምክትል ስብሳቢ ከሚዲያ መግለጫ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው፡፡ ከምርጫ ቦርድ ባልተናነሰ ሁኔታ በኢትዮጵያ በህግ የተቋቋሙት እና በህዝብ ሀብት የሚንቀሳቀሱት የመገናኛ ብዙሃንም በፍጥነት ተቀብለው ማስተጋባታቸው በውዥንብር ፈጠራ ላይ ተሳታፊነታቸውን ያሳያል፡፡ ዓላማው በአባላት፣ በደጋፊና በህዝቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር ታሰቦ የሚካሄድ ፖለቲካዊ ደባ ነው፡፡

በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እና ዘላቂነት ያለው ደህንነት የሚያረጋግጠው እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋሞች ነፃ፣ ገለልተኛ እና በህዝብ ዘንድ አመኔታ ሲጣልባቸው ነው፡፡ ይህ ተቋም አሁን በያዘው ሁኔታ ከቀጠለ ከታሪክ ተጠያቂነት አይድንም፡፡ ገዢው ፓርቲም ጧት ማታ የሚያባንነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ፓርቲያችንን ለመታደግ እና የቦርዱን የመጨረሻ ካርድ ለማስጣል አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተናል፡፡ ይህ ማለት የትግሉ መጨረሻ አይደለም፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረሰብንን የሕግ ጥሰት ይዘን በፍርድ ቤት ክስ እንመሰርታለን፡፡ እስከ አሁን ያለውን ሂደት ስናየው የቦርዱ ፖለቲካዊ ደባ ቀጣይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም መላው አባሎቻችን፣ ደጋፊዎቻችን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምንወስዳቸው ተከታታይ ፖለቲካው ውሳኔዎች እና እርምጃዎች ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን፡፡

ድል የሕዝብ ነው
ጥር 1 ቀን 2ዐዐ7 ዓም
አዲስ አበባ

Minilik Salsawi – ፍላጐታችንን ያከበሩ በመምሰል ፍላጐታቸውን የሚያሟሉ ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ ፀሐይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ አይደለም፡፡አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡የሌሎችን ግብና አዕምሮ ማማለልንና ማዘናጋትን የሚያውቁበት ሰዎች እንዳሉ አንርሳ! ተስፋ በመስጠት እንደዳማና እንደ ቼዝ ጠጠር (ወታደር) በፈለጉት አቅጣጫ ይገፉናል፡፡ ፍላጐታችንን ያከበሩ በመምሰል ፍላጐታቸውን የሚያሟሉ ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ ፀሐይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ አይደለም፡፡ ለነገ እበላዋለሁ የሚል ጅል ተኩላ ግን ምን ጊዜም አይጠፋም፡፡ ይህን ሁሉ የሚታዘብ ህዝብ እንዳለ የሚያውቅ ካለ የብልህም ብልህ ነው፡፡ በዚህ የተካኑ ሰዎችን በዐይነ – ቁራኛ ማየት ያባት ነው፡፡ ስሜትን ተቆጣጥሮ ደባና ሴራን ጠንቅቆ ማየትና በጠዋት መንቃት ተገቢ ነው፡፡ ድቀትና ዝቅጠት ሲያይል አሉባልታና ጥርጣሬ ይነግሳል፡፡

በእንዲህ ያለው ሰዓት አፍ – አዊ እየበረከተ፣ ልባዊና ተግባራዊ እየሳሳ ይመጣል፡፡ ይሄኔ መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ የአንድ ነገር ዋጋ በዚያ ተገልግለን በምናገኘው ጥቅም አይለካም፡፡ ይልቁንም ያንን ነገር ለማግኘት በምንከፍለው መስዋዕትነት ነው የሚለካው፡፡ አገር እንገነባለን ስንል ይህን ብሂል አለመርሳት ነው፡፡ ይሆነናል የምንለውን ሰው መርጠን ስንሾምም ይህንን አለመዘንጋት ነው፡፡ ባለሙያው እያለ ስለዚያ ሙያ የሚያወራ ሲበዛ ጠንቀቅ ማለት ያሻል፡፡

ፕሮፓጋንዳ ብቻውን ሁሉን ጉዳይ አይጨርስልንም፡፡ አስተዋይ አመራር፣ አስፈፃሚና ተጠያቂነትን ገምጋሚ እንዲኖር ያሻል፡፡ ያ ደግሞ ግልጽነትን ልማድ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡በምንም ዓይነት ግን የፖለቲካ ትግልን እንደማይተኩልን ማሰብ ተገቢ ነው! የፖለቲካ ትግል ከሁሉም በፊት መደራጀትን፣ ተደራጅቶም መስዋዕትነትን፣ በሀገር ላይ ለውጥ የማየት ልባዊ ስሜትን ይጠይቃል! በተግባር ሳይሆን አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ ተግባራዊና የሚለውን የሚተረጉም ማህበረሰብ ካልፈጠርን ሟርት ይበዛል ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image

አንድነት መኢአድና ሰማያዊ ከምርጫ ቦርድ ጋር ሲካሰሱ መድረክና ኢዴፓ ውይይት ይፈልጋሉ::
Minilik Salsawi-አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ::የሚል መግለጫ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በራዲዮ ፋና መስጠታቸውን ተከትሎ;የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ስብሰባን ረግጦ መውጣቱን አስታኮ በመጭው ምርጫ ላይ ውጥረት ማጥላቱን መረጃዎች ሲጠቁሙ በሌላ በኩል መድረክ እና ኢዴፓ የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉን በማለት ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር መደራደር(መወያየት)እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ይገኛል::

ምርጫ ቦርድ እያለ ራሱን የሚጠራው ኢሕአዴጋዊ ተቋም አንድነት እና መኢአድ በህገ- ደንባቸው መሰረት ውስጣዊ ችግራቸውን እንዲፈቱ በቦርዱ ቢነገራቸውም ችግራቸውን ሊፈቱ አልቻሉም እያለ ሲከስ መስመራቸውን ስተዋል ብሎ እንዳመጣለት በመወንጀል በምርጫ ሊሳተፉ እንደማይችሉ ቢናገሪም የፓርቲዎቹ አመራሮች ግን ምርጫ ቦርድን በመቃወም አስፈላጊ የሚባሉ ፖለቲካው እርምጃዎችን እና ውሳኔዎችን እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል::ይህ በፓርቲዎቹ እና በምርጫ ቦርድ መካከል የተነሳው እሰጥ አገባ እና ፓርቲዎችን ከፋፍሎ መወንጀል በዋናነት ህዝቡን እያነጋገረ መሆኑ ታውቋል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ በጠራው ገንዘብ የማከፋፈል ስብሰባ ላይ በሃሳብ እና በገንዘብ ክፍፍሉ ባለመስማማቱ ስብሰባዉን ረግጦ የወጣ ሲሆን ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ ይጠይቀኝ ሲል ኢሕአዴጋዊ መመጻደቅ እያደረገ ይገኛል::የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በምርጫ ቦርድ የይቅርታ ፉጨት እንደማይገርማቸው እና የተቋሙን ልፍስፍስነት እንደሚያመለክት እየተናግሩ ነው::

መድረክ እና ኢዷፓ የግዢው ፓርቲ ታማኝ ተቃዋሚ የሚባሉ ሲሆን በለዘበ ሁኔታ የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉን በማለት ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር መደራደር(መወያየት)እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ይገኛል:: ኢሕ አዴግ ምርጫውን ተገን አድርጎ የፖለቲካ ሙስና እየፈጸመ ነው የሚለው መድረክ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ጠቁሟል፡፡መድረክ ይህን ይበል እንጂ ምርጫ ቦርድ ውሳኔው የኔ መብቱም የኔ ነው በማለት አምባርቆበታል::ኢዴፓ በበኩሉ ምርጫው ላይ ቅሬታዎች አሉ ቢሊም ገፍቶ እንዳልታየበት እና በገዢው ፓርቲ አስፈላጊውን ትብብር በየክፍለ ሃገሩ እና መሃል አገር ላይ እየተደረገለት ስለሆነ ብዙም ጫና የሚፈጥር ችግር እንዳሌለ ሲናገር አንዳንድ ችግሮችን ለመፍታት ገዢውን ፓርቲ ለውይይት ሲጠይቅ ምርጫ 2007 በተመለከት መድረክ እና ኢዴፓ ምርጫ ቦርድ ጥርስ የሌለው ውሻ መሆኑን በተዘዋዋሪ እየነገሩት መሆኑን ያመለክታል:: ምርጫውን በተመለከተ ገዢውን ፓርቲ መለማመጥ ይቀላል የሚሉት መድረክ እና ኢዴፓ ከገዢው ፓርቲ ከተወያየን የምርጫ ቦርድ ጉዳይ የሞተ ነው ሲሉ ይናገራሉ::‪#‎MinilikSalsawi‬

በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
የኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ ምላሻቸዉን ለማዉጣት የእነሱ መደወልም ሆነ ትዕዛዝ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ የዝግጅት ክፍላችን አንድ ጽሑፍ የቀረበበት አካል ምላሹን በዚያዉ በተፃፈበት የህትመት ዉጤት ላይ ማስነበብ እንደሚችል በህግ የተደነገገ መሆኑን ከማወቁም በላይ የትኛዉንም አይነት ሀሳብ ለማስተናገድ ክፍት ነበርና ምላሻቸዉን በጋዜጣችን ላይ ታተመ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አልተገቱም፤ በወቅቱ የገዢዉ ፓርቲን ሀሳብ በማቀንቀን ይታወቁ የነበሩት እንደ ዳጉ ኢትዮጵያና ሰነድ ያሉ ጋዜጦች ሀሳቦቼን በሃሳብ መምታት ባለመቻላቸዉ ይሁን ባለመፈለጋቸዉ ተራ ዘለፋዎችን ያወርዱብኝ ጀመር፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የገዢዉ ፓርቲ ደህንነቶች ስልክ በመደወል፣ በዝግጅት ክፍላችን አድራሻ በስሜ ደብዳቤ በመላክና በአካልም በማግኘት ጭምር መንግስትን የሚተቹ ፅሑፎችን እንዳልፅፍ ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፡፡ “ማስፈራራት የሚቻለዉ የሚፈራ ሲኖር ነዉ” እንዲሉ ሙከራቸዉ ዋጋ አልነበረዉም፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያ ፅሑፌን ለህትመት ከማብቃቴ በፊት ልከፍለዉ ስለምችለዉ መስዋዕትነት በሚገባ አስቤበታለሁ፡፡ የሀገሬን ጉዳይ በንቃት የምከታተል ዜጋ እንደመሆኔም ከገዢዉ ፓርቲ የተለየ ሀሳብ ያቀነቀኑ ሰዎች የደረሰባቸዉን በሚገባ አዉቃለሁ፡፡ በመሆኑም ከሁለት መጥፎ ምርጫዎች አንዱን ማለትም እነሱ የደረሰባቸዉን ግፍ እንዳይደርስብኝ የሀገሬን ጉዳይ በተመለከተ ፍዝ ተመልካች መሆንን ወይም በሙያዬ የምችለዉን አስተዋፅኦ አበርክቼ የሚመጣዉን መቀበል መምረጥ ነበረብኝ፡፡ ሁለተኛዉን የተሻለ መጥፎ ምርጫ ከመረጥኩ የሰነበትኩ በመሆኑም እየበረከቱ የመጡትን ማስፈራሪያዎች ከቁብ ሳልቆጥር የጋዜጠኝነት ስራዬን መቀጠል ቻልኩ፡፡ በዚሁ መሰረት ስራ ለመያዝ፣ የደረጃ እድገት ለማግኘትም ሆነ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከደህንነት ስጋት የፀዳ ኑሮ ለመኖር የኢህአዴግ አባል ካልሆነም ደጋፊ መሆን ከጊዜ ጊዜ ግድ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳዩ፣ ገዢዉ ፓርቲ እንዳጎናፀፈን የሚገልፅልን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በተጨባጭ አለመኖሩን የሚሞግቱ፣ የኢህአዴግን እንደሀገር የማሰብ ችሎታ ወይም ፍቃደኝነት አናሳ መሆን የሚተቹና ሌሎችም መንግስት ቀናነት ቢኖረዉ ኖሮ ሊታረምበት የሚያስችሉትን በርካታ ፅሑፎች አቀረብኩ፡፡ አንድ ቀን ጧት ግን አምባገነኑ መንግስታችን ከጀመርኩት ጉዞ ገታኝ፡፡ ሰኔ10/2003 በወቅቱ እሰራባት በነበረችዉ ተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ ላይ የቀድሞዉን ጠቅላይ ሚኒስትር በተመለከተ ፅሑፍ ለህዝብ ማቅረቤን ተከትሎ ሰኔ14/2003 ዓ.ም ለእስር ተዳረግሁ፡፡
ማዕከላዊና ቃሊቲ ምንና ምን ናቸዉ?
ዉድ አንባብያን፤ ፊዘኛዉ መንግስታችን በሽብርተኝነት እንደሚጠረጥረኝ ገልፆ በእጆቼ ካቴና በማጥለቅ በቁጥጥር ስር አዋለኝ ካዋለኝ ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለቁጥር የሚያታክቱ የመብት ጥሰቶችን እየፈፀመብኝ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል እጅግ በጣም ጥቂቶቹን እነሆ!
ከህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነዉ የሚባልለት ህገመንግስት በጥበቃ ስር ያሉ ሰዎች በጠበቆቻቸዉ የመጎብኘት መብት እንዳላቸዉ ቢገልፅም እኔና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ግን ይሄ መብታችን በማዕከላዊ አለቆች ተጥሷል፡፡ ጠበቃዬን ለማግኘት የተፈቀደልኝ ምርመራዉ ከተጠናቀቀና ቃል ከሰጠሁ በኋላ ወደቃሊቲ ለመዉረድ የአስርቀናት ዕድሜ ያህል ሲቀረኝ ነበር፡፡ በቤተሰብና በጓደኞቼ ለመጎብኘት የተፈቀደልኝም ሁለት ወር ከ3 ሳምንታት ክልከላ በኋላ ነበር፡፡ ከጠበቃዬ ጋር እንዳልገናኝ ተደርጎ የሚካሄደዉ ምርመራ የፃፍኳቸዉን ፅሑፎች ለምን እንደፃፍኩ፣ ከበስተኋላዬ ሆኖ የሚገፋኝ አካል ስለመኖር አለመኖሩና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ ቢሆንም አልፎ አልፎ ደግሞ መልኩን ይቀይራል፡፡ አንዳንድ ቀን መርማሪዎቹ በማስተምርበት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄዱ ስብሰባዎች ላይ ያቀረብኳቸዉን ሀሳቦች እያነሱ ከመንግስት የደህንነት ሀይሎች የሚያመልጥ ምንም ነገር እንደሌለ በመግለፅ ቢጤ ያሰሙኝ እንደነበር ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፡፡፡ እንዲህ አይነቱ ንግግራቸዉ አሰልቺዉን ምርመራ ዘና እልበት ዘንድ የሚረዳኝ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶኛል፡፡ በአደባባይ ስብሰባዎች ላይ የተናገርኩትንና ደህንነት ሊሰልለዉ የማያስፈልገዉን ግልፅ ነገር እንደ ትልቅ የደህንነቶች የስራ ዉጤት ተደርጎ ሲገለፅ ከመስማት በላይ ምን የሚያዝናና ነገር ይገኛል? የት/ቤት ርዕሰ መምህራኖች በሙሉ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ የተደረገበት ምክንያት መንግስት እንደሚለዉ የትምህርት ፖሊሲዉን ለማስፈፀም ሳይሆን የመምህራንንና የተማሪዎችን የፖለቲካ አቋም ለማወቅና ይህንኑ ሪፖርት ለማድረግ መሆኑን የማይረዳ መምህር ይኖራል? ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ ርዕሰ መምህራኖች ሰበብ እየተፈለገላቸዉ ከቦታቸዉ እንዲነሱ ሲደረግስ ስንታዘብ አልኖርንም? “ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” አለ ያገሬ ሰዉ! ሆዴ ባዶ እንዳይቀር ሁሉን መተንፈሴን ትቼ የጀመርኩትን የማዕከላዊ ምርመራ ጉዳይ ልቀጥል፡፡
የምርመራዉ ይዘት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መልኩን እየቀየረ መጣ፡፡ በሪፖርተርነት እሰራበት የነበረዉ የኢትዮጵያ ሪቪዉ ድረገፅ አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ የሽብር ተልዕኮ እንደሰጠኝ በሀሰት እንድናገርና ተከሳሽነቴ ቀርቶ ምስክር ሆኜ እንድፈታ ለማድረግ የተለያዩ ጫናዎቸው ይደርሱብኝ ጀመር፡፡ ለአምስት ደቂቃ ያህል ጧትና ማታ ወደመፀዳጃ ቤት ለመሄድ ከሚከፍቱልኝ በስተቀር ለአስራሶስት ቀናት ያህል ብቻዬን አንድ መጥፎ ሽታ ያለዉ ክፍል ዉስጥ ተዘግቶብኝ ከረምኩ፡፡ በዚህ ወቅት ጉዳዬን የያዘዉ ዐቃቤህግ ማዕከላዊ በመምጣት እያስጠራኝ ሀሳቤን የማልለዉጥ ከሆነ እድሜ ልክ ወይም ሞት እንደሚያስፈርድብኝ ይዝትብኝ ነበር፡፡ ሀሰን ሽፋ በበኩሉ በሀሳባቸዉ የማልስማማ ከሆነ የያዘኝን የወጣት ጀብደኝነት ማስተንፈስ ለነሱ ከባድ ስራ አለመሆኑን ነግሮኛል፡፡ በኔ በኩል ደግሞ ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ንፁህ መሆኔ እንጂ ኤልያስ ላይ በሀሰት መመስከሬ ሊያስፈታኝ እንደማይገባ ስለማምን ይህንኑ በተደጋጋሚ አስታዉቄ ተከሳሽ መሆንን መረጥኩ፡፡ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ የተሻለዉን መጥፎ እየመረጡ መኖር ዕጣፋንታችን ከሆነ ቆየ አይደል?
ማዕከላዊ እያለሁ ከተፈፀሙብኝ የመብት ረገጣዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ በአንድ ፖሊስ የተሰጠኝ ጥፊና ከግድግዳ ጋር ማጋጨት በተለይ ወንድ የፖለቲካ እስረኞች ከሚፈፀምባቸዉ ለዘላቂ የአካል ጉዳት የሚዳርግ ከባድ ድብደባ አንፃር ሳስተያየዉ የማዕከላዊ መርማሪዎች እንደሚሉት “ቁንጥጫ” ተብሎ ከመግለፅ የሚያልፍ ባለመሆኑ ብዙ ልልበት አልፈልግም፡፡ በወቅቱ የነበርነዉ ሴት እስረኞች ላይ ያን ያህል የከፋ አካላዊ ድብደባ አልተፈፀመም ማለት ግን የማዕከላዊ መርማሪዎች ለሴቶች ይሳሳሉ ማለት አይደለም፡፡ ለማሳያነት እስካሁን ድረስ ማዕከላዊ በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ የተነሳ በህመም የምትሰቃየዋን የፖለቲካ እስረኛ እማዋይሽ አለሙን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አይ ማዕከላዊ! ማዕከላዊ ዘና ብለዉ የሚራመዱ ኩሩ የኢትዮጵያ ልጆች በገቡ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ በቃሬዛና በሰዎች ድጋፍ በሸክም ሲያሳልፉና የድረሱልኝ ዋይታ ሲያቀርቡ የሰማሁበት አሰቃቂ ቦታ ነዉ፡፡ ምስላቸዉ ከአይኔ ላይ፣ ጩኸታቸዉ ከጆሮዬ ተጣብቆ የሚኖረዉ እነዚህ ወገኖቼን እያሰብኩ መናደድ መቆጨት የዕለት ተዕለት የኑሮዬ አካል ሆኗል፡፡
የማዕከላዊዉን የመብት ረገጣ እዚህጋ ገታ ላድርገዉና በተለይ የፖለቲካ እስረኞችን ሰብአዊ መብት ከመጨፍለቅ አንፃር አምሳያዉ ወደ ሆነዉ የቃሊቲ እስር ቤት ልለፍ፡፡ ጳጉሜ3/2003 ዓ.ም ቃሊቲ እንደገባሁ በኋላ ላይ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ እንደሆነች በተገነዘብኩት ሀላፊ አማካኝነት ጋዜጠኝነቴ ከታሰርኩ በኋላ የቀረ በመሆኑ ግቢዉ ዉስጥ በሚኖረኝ ቆይታ አርፌ መቀመጥ እንደሚኖርብኝ ተነገረኝ፡፡ አልጋ እስከሚለቀቅ ተብሎም እኔና በአንድ መዝገብ የተከሰስነዉ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ምንም እንኳን ሁለታችንም የሳይነስ በሽታ ያለብን ቢሆንም ሽንት ቤት አጠገብ መሬት ላይ ፍራሽ አንጥፈን እንድንተኛ ተደረገ፡፡ ዉድ አንባቢያን ስለቃሊቲ ስታስቡ ወደ አዕምሮአችሁ የሚመጡት ያማሩ ግንብ ቤቶችና የተዋቡ አልጋዎች ከሆኑ ኢቲቪ እንደሸወዳችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ የፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ ፕሪዝን ፌሎሽፕ የተባለ ድርጅት እንዳሰራቸዉ የሚናገሩት እነዚህ ያማሩ ግንብ ቤቶች ሁለት ክፍሎችና መፀዳጃ ቤት ብቻ ያሏቸዉ ሲሆኑ የተቀሩት በሴቶች ዞን ዉስጥ ያሉ ክፍሎች ከሁለት ያረጁ ግንብ ቤቶች በስተቀር በቆርቆሮ የተሰሩና እስረኞች በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖሩባቸዉ ናቸዉ፡፡ የቃሊቲ ምቾት አልባነት የሚሰማዉ አካልን ብቻ አይደለም፡፡ ቃሊቲ ከአካል በከፋ ሁኔታ ለነፍስና ለመንፈስ ይጎረብጣል፡፡ እንዴት ቢሉ እንዲህ እልዎታለሁ፡፡ የቃሊቲ የሴቶች ዞን ቤተመፃሕፍት ከጥቂት ወራት ጀምሮ በመፅሐፍቱ አይነትም ሆነ ቁጥር መሻሻልን ቢያሳይም እኔ ቃሊቲ ከገባሁ ጀምሮ እስከቅርብ ጊዜያት ድረስ ግን ከመኖር በማይቆጠር ደረጃ የሚገኝ ነበር፡፡ ይህንን ክፍተት ቤተሰብና ጓደኞቼ በሚያስገቡልኝ መፀሐፍት ለመሙላት ባስብም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሚመጡልኝ መፅሐፍት የቃሊቲን ሳንሱር እንደወደቁ ተገልፆ እኔጋ ሳይደርሱ ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ መፅሐፍት ዉስጥ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የሚሳትማቸዉ የታሪክ መፅሐፍት ሳይቀር ይገኙበታል፡፡ ቃሊቲ ለመንፈስም አይመችም ያልኳችሁ በዚህ ብቻ አይደለም፡፡ በራሴ ወጪ ኢንድራ ጋኒዲ ናሽናል ኦፕን ዩኒቨርስቲ በርቀት ፖለቲካል ሳይንስ ለማጥናት ከብዙ ዉጣዉረድ በኋላ ተፈቅዶልኝ የተበዘገብኩ ቢሆንም የመማሪያ ሞጁሎቹን ለማስገባት ግን የቃሊቲ አለቆች ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ከብዙ ደጅጥናት በኋላ ሞጁሎቹ ሲገቡ ደግሞ በትምህርቱ ዙሪያ ላነባቸዉ የሚገቡኝ አጋዥ መፅሐፍት ስለፖለቲካ የሚያወሩ በመሆናቸዉ በፍጹም ሊገቡ እንደማይችሉ የመፅሐፍት ገምጋሚዎቹ አረዱኝ፡፡ ይባስ ብሎ በዚያን ወቅት ከሌላዉ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ምንም አይነት መፅሐፍት እንዳይገቡልኝ በመደረጉ ለጠቅላላ ዕዉቀት ያህል ሞጁሎቹን ማንበቤን ብቀጥልም ትምህርቱ ግን በዚህና በሌሎች ምክንያት ለማቋረጥ ተገደድኩ፡፡
በቃሊቲ የኔ ብቻ ሳይሆን ከእኔ ጋር የተቀራረቡ ወይም ደግሞ ሰላምታ ያቀረቡልኝ ሰዎች ሳይቀር መብታቸዉ ተጥሷል፡፡ ከሁለት አመታት በላይ የሚሆነዉን ጊዜ በርካታ እስረኞች በነበሩበት ክፍል ያሳለፍኩ ቢሆንም እኔን እንደሌላዉ እስረኛ ለመቅረብ የሞከሩ በሙሉ ስሜትን የሚጎዳ ወከባ፣ዘለፋና ለየት ያሉ ፍተሻዎችን አስተናግደዋል፡፡
በህክምና ጉዳይ የነበሩብኝን ችግሮች በተመለከተ ቤተሰቦቼ ደጋግመዉ የገለፁት መሠረታዊ ችግር በመሆኑ በዚህ ፅሑፍ ነካ አድርጌዉ ብቻ አልፋለሁ፡፡ ጡቴ ዉስጥ በበቀለዉ እጢ ምክንያት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል በማደርግበት ወቅት በቀጠሮዬ ቀን ወደ ሆስፒታሉ ከምወሰድባቸዉ ይልቅ የማልወሰድባቸዉ ጊዜያት ይበዙ ነበር፡፡ የግራ ጡቴ ቀዶጥገና ከተደረገለት በኋላ በወቅቱ ክትትል ታደርግልኝ የነበረችዉ ዶክተር በሶስተኛ ቀን የቁስሉ ፕላስትር መቀየር እንዳለበትና በሳምንቱ ደግሞ ክሩ መዉጣት እንዳለበት ገለፀችልኝ፡፡ አብረዉኝ የሚሄዱት አጃቢ ፖሊሶች ከዶክተሬም ጋር ስነጋገር እዛዉ ነዉና የሚቆሙት እንዲህ አይነቱን ነገር ለማድረግ የሚችል ጤናጣቢያ ማረሚያቤቱ እንዳለዉ ተናገሩ፡፡ እኔም ቀጠሮ ቢሰጠኝ እንኳ በዚህ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደሆስፒታሉ ተመልሼ መሄድ አዳጋች መሆኑን ስለማዉቅ የተባሉት ነገሮች ቃሊቲ መፈፀማቸዉን አልጠላሁትም፡፡ በመሆኑም ለህክምና ክትትል የሶስት ወራት ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ ክሩ መዉጣት ባለበት ቀን ስለጉዳዩ ለጥበቃ ክፍሉ አስታወቅኩ፡፡ እነሱም አሁን ደቡብ ሱዳን ከሚገኝዉ ጦር ጋር አብራ ከተጓዘች አንዲት የህወሐት ታጋይ የነበረች ነርስ ጋር አገናኙኝ፡፡ እሷም እዛዉ ጨርሼ መምጣት እንደነበረብኝና እዚህ ክሩን ማዉጣት እንደማይችሉ ነገረችኝ፡፡ የምታሳየኝ ጥላቻ በሷ እጅ የህክምና አገልግሎት ከማግኘት ቢቀር የሚሻል መሆኑን የሚጠቁም በመሆኑ ብዙም ልከራከራት አልፈለኩም፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ሌሎች ሀላፊዎች ወደጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲወስዱኝ ብጠይቅም “ቀጠሮ የለሽም” በሚል ሰበብ ሳይወስዱብኝ ቀሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የቀኝ ጡቴም ተመሳሳይ እጢ ያለበት በመሆኑ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ቀዶጥገና አደርግ ዘንድ የላከኝ ቢሆንም (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በእድሳት ላይ በመሆኑ)እጅግ የከፋ ህመም ካልታመምኩ በቀር ቃሊቲ ሆኜ ቀዶጥገና ማድረጉን አልፈለኩም፡፡ በመሆኑም አልፎ አልፎ የሚሰማኝን ህመም በህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች በማቃለል የቃሊቲን አስቀያሚ ቀኖች በመግፋት ላይ እገኛለሁ፡፡
ሌላዉ የቃሊቲ ቆይታዬን በተመለከተ ልጠቅሰዉ የምፈልገዉ ጉዳይ ከመንግስት አካላትና ከተለጣፊዎቻቸዉ ጋር ካለፍላጎቴ እንድንገናኝ እየተደረገ የሚፈፀምብኝ የሰብአዊ መብት ረገጣ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ያህልአንዱን ብቻ ልጥቀስ፡፡ አምና መጋቢት ወር ዉስጥ አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መምጣታቸዉን የገለፁ ሌሎች አስር ሰዎች ከአመት በፊት ወደገባሁበትና ከሌሎች ከአራት ሰዎች ጋር ብቻ ወደምኖርበት ክፍል መጡ፡፡ እኔም ኮሚሽኑ በተለይም ደግሞ አምባሳደሩ የሰብአዊ መብት አከባበርን አስመልክቶ የሚሰጧቸዉ ከእዉነት የራቁ መግለጫዎች የሚያሳዝኑኝ በመሆኑ ለመነጋገር ፍቃደኛ አለመሆኔን በማስታወቅ ከክፍሉ ወጥቼ በሩ ላይ ቆምኩ፡፡ ከሰዎች አንዱ የምኖርበትን ክፍልና አልጋዎቻችንን ፎቶ ሲያነሳ ተመለከትኩ፡፡ ገረመኝ፤ መሬት አንጥፌ ስተኛ፣በተደራራቢ አልጋ የላኛዉ ክፍል ላይ ከጡት ህመም ጋር እየታገልኩ ስተኛና በተፋፈገ ክፍል ዉስጥ ስኖር ለምን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፎቶ አላነሳም? ማረሚያ ቤቱ በጥሩ ሁኔታ እስረኞቹን የያዘ መሆኑን ማሳያ ለማድረግ እንደተፈለገ ገመትኩ፡፡ እዉነታዉ ግን ይቺ ያለሁባት በቆርቆሮ የተሰራች ክፍልና ጠባቧ ግቢ አምና መስከረም ላይ በጠያቂዎች የመጎብኘት መብቴ መጣሱን ተከትሎ በጥድፊያ የተዘጋጀች ማግለያ ቦታ መሆኗ ነዉ፡፡ ክፍሉን ብቻ ፎቶ አንስተዉ መሄዳቸዉ ያላረካቸዉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰዎች በማግስቱ አራት ሆነዉ መጡ፡፡ ሁለቱ ወደግቢዉ ዉስጥ ሲገቡ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ በሩጋ ቆሙ፡፡ ግቢዉ ዉስጥ ከገቡት አንዱ ትላንት ለምን ላናግራቸዉ እንዳልፈለኩ ጠይቆኝ በድጋሚ ከነሱ ጋር መነጋገር ያልፈለኩበትን ምክንያት እያስረዳኋቸዉ እያለ የግቢዉ በር ክፍት ስለነበር ግቢዉ በርጋ ከቆሙት አንዱ ፎቶ ሊያነሳኝ ሲሞክር ለመመልከት ቻልኩ፡፡ ምስሌን አንስቶ ቢሆንና ስለኔ አንዳች አይነት ዉሽት ሲናገሩ ብሰማ ጉዳዩን በዝምታ እነደማላልፈዉ ነገርኩትና ወደቤት ዉስጥ ገብቼ በሩን ዘጋሁት፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ከክፍሉ ወጥቼ ኢህአዴግ ማሰሩ ሳይበቃዉ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር እንዳቋቋማቸዉ በሚናገረዉ ተለጣፊ ድርጅቶቹ ሳይቀር ሰብአዊ መብቴን ለምን እንደሚጥስ ከሀላፊዎቹ አንዷን በማስጠራት ጥያቄ አቀረብኩላት እሷም ሰዎቹ ካሜራ መያዛቸዉን እንደማታዉቅ ነገረችኝ፡፡ በ2005ዓ.ም ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግኑኝነት ክፍል እኔን ለማናገር እንደመጣ የገለፀልኝ ሰዉ ኮቱ ዉስጥ ደብቆ በያዘዉ ሪከርደር ድምፄን ለመቅረፅ ሲሞክር ደርሼበት ይህንን ማድረግ የሚችለዉ የግል ፕሬስም ተገኝቶ ንግግራችንን የሚቀርፅ ከሆነ ብቻ መሆኑን ነግሬዉ ነበር፡፡ ይሄንን ያልኩበት ምክንያት የግል ፕሬሱ ባልተገኘበት ለመንግስት ሚዲያዎች ብቻ አስተያየታቸዉን የሰጡ ግለሰቦች ሀሳባቸዉ ተቆርጦና ተቀጥሎ ለማለት ያልፈለጉት ይዘት ይዞ እንደሚቀርብ አዉቅ ስለነበር ነዉ፡፡ የተናገርኩትን ሙሉዉን ነገር ቀርፀዉ ሊያወጡልኝ የሚችሉ አካላት በሌሉበት ለሰዉዬዉ አስተያየቴን መስጠት ያለፈለኩትም ይኸዉ እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር፡፡ አስገራሚዉ ነገር ይቺ የኮሚሽኑ ሰዎች ካሜራ መያዛቸዉን እንደማይታወቅ የገለፀችልኝ ሀላፊ ያኔም የሰዉየዉን የድምፅ ሪከርደር መያዝ በተመለከተ ላቀረብኩላት ጥያቄ የሰጠችኝ ተመሳሳይ መልስ ነበር፡፡
የቃሊቲ ጉድ ማብቂያ ስለሌለዉ አንድ የመጨረሻ ጉዳይ ላንሳና የፅሁፌ መነሻ ወደሆነዉ የአመክሮ ጉዳይ አልፋለሁ፡፡ ዉድ አንባቢያን በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የትኞቹንም እስረኞች አያያዝ የተመለከቱ ህጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንም ሆኑ መመሪያዎችን በጣሰ ሁኔታ ከወላጆቼ በቀር ጠበቃን ጨምሮ በሌላ በማንም ሰዉ የመጎብኘት መብቴን ከተነጠቅኩ አመት ከኣራት ወራት አልፎኛል፡፡ አዛዉንት እናትና አባቴም ከእርጅና፣ ህመምና ድካም ጋር እየታገሉ የቃሊቲን ፈታኝ መንገድ መዉጣትና መዉረዳቸዉን ቀጥለዋል፡፡
ነገረ አመክሮ
ያለፈዉ አመት ነሐሴ ስምንት ቀን ከሰአት በኋላ ወደ ጠበቃ ክፍል ሃላፊዋ ቢሮ በአንዲት ፖሊስ ተጠርቼ ተወሰድኩ፡፡ እዚያም ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋናዉ መስሪያ ቤት የይቅርታና የአመክሮ ጉዳይ ክፍል እንደመጣና ኮማንደር አስቻላዉ እንደሚባል ከነገረኝ ሰዉ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ኮማንደሩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ያቀረበልኝ የመጀመሪያዉ ጥቃቄ “ይቅርታ ለምን አልጠየቅሽም? ይቅርታ በመጠየቅ ላይ ያለሽ ሀሳብስ አልተቀየረም ወይ?” የሚል ነበር፡፡ ይቅርታ ያልጠየኩት ስላላጠፋሁና የተፀፀትኩበት ጉዳይ ስለሌለ በመሆኑና አሁንም ምንም የተቀየረ አቋም እንደሌለኝ አስረዳሁተ፡፡ “ይሄ የፍርድቤት ጉዳይ ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ እስካለሽ ድረስ ወደዚያ መመለስ አይኖርብንም” አለኝ፡፡ እኔም አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት እንዳሻዉ የሚያሽከረክረዉ ፍርድቤት በንፁሃን ላይ የጥፋተኝነት ዉሳኔና ፍርድ ማስተላለፉን አሜን ብዬ ይቅርታ የምጠይቅበት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ ገለፅኩለት፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ያህል ስለጤንነቴና በጊቢዉ ዉስጥ ስለሚያጋጥሙኝ ችግሮች በተመለከተ ጥያዎችን ስያቀርብልኝ ቆየና ወደ መጣበት ሌላዉ ዋና ጉዳይ ተመለሰ፡፡
“ቅድም ይቅርታ የማልጠይቀዉ ስላልተፀፀትኩ ነዉ ብለሻል፡፡ አመክሮ እኮ የሚሰጠዉ ለተፀፀተ ሰዉ ነዉና እንዴት ልታደርጊ ነዉ?” በማለት ስለ በአመክሮ የመፈታት አካሄድ አንዳንድ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንቦችን ጭምር በመጥቀስ ሊያብራራልኝ ሞከረ፡፡ “ታዲያ እንዲህ ከሆነ በይቅርታና በአመክሮ መሀል ምንም አይነት መሰረታዊ ልዩነት የለም ማለት ነዋ?” ለሚለዉ ጥያቄ ቀጥታ መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም ይልቁኑ ሁሉም ታራሚ 2/3ኛዉን የእስር ቅጣቱን ለመፈፀም ሁለት ወራት ገደማ ሲቀሩት እንደታረመና እንደተፀፀተ የሚገልፅ ፎርም መሙላት ስለሚኖርበት እኔም ለመፈታት ከፈለኩ ይህንኑ ማድረግ እንደሚጠበቅብኝ አስረግጦ ነገረኝ፡፡ የፃፍኩት የማምንበትንና መቼም ልቆምለት የምችለዉ እዉነት መሆኑን፣ በዚህ የተነሳ አሸባሪ መባሌ ደግሞ የበለጠ ኢህአዴግን እንድታገለዉ የሚየደርገኝ እንጂ የሚያፀፅተኝ ባለመሆኑ እንዲህ አይነቱን ከማንነቴ ጋር የሚቃረን ፎርም እንደማልሞላ አስረግጬ ነገርኩት፡፡ ኮማንደሩም ላልታረመና ለልተፀፀተ ሰዉ አመክሮ መስጠት ለእነሱም እንደሚከብዳቸዉ ከገለጸልኝ በኋላ “እኛ ፎርሙን ብንሞላልሽስ?” የሚል አስገራሚ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔ “ታርሜያለሁ” እንዳልኩ ተደርጎ ምንም አይነት ነገር ቢደረግ ሀሰት መሆኑን ከማጋለጥ ወደኋላ እንደማልል አስታወቅኩት፡፡ በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሀሳቦች ላይ እየተሸከረከርን ጥቂት ጊዜ ከፈጀን በኋላ እንዳሰብበት አሳስቦኝ ተለያየን፡፡
ይህ ከሆነ ሀሁለት ወራት በኋላ የመፈቻዬ ቀን የነበረዉ ጥቅምት 14/2007 ማለፊን ተከትሎ “የአመክሮ ፎርሙን ለምን አትሞይም?” የሚል ጥያቄ ከተለያዩ ሀላፊዎች ይቀርብልኝ ጀመረ፡፡ ከህዳ&#465

ሻእቢያ ያገታቸውን ታጋዮቻችንን ለፕሮፓጋንዳ ሊጠቀምባቸው እያስገደዳቸው ነው ሲሉ የአማራ ንቅናቄ (አዲሃን)ምንጮች ገለጹ:: ‪

Minilik Salsawi : የኤርትራ መንግስት በህገወጥ መንገድ ያገታቸውን እና የሰወራቸውን ታጋዮቻችንን በአስቸኳይ እንዲለቅ እንጠይቃለን በማለት በተደጋጋሚ መግለጫ ያወጣው የአማራ ንቅናቄ አይን ያወጣው ሻእቢያ ያገታቸውን አባሎቼን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታው በማስገደድ ሊጠቀምባቸው ነው ማለቱን የንቅናቄው የውስጥ ምንጮች ከሰሜን ጎንደር ገልጸዋል::

ሕዝቦች ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብታቸው እየተገደበ ነው የሚሉት የንቅናቄው ምንጮች ከ70 በላይ የሚሆኑ የድርጅታችን አመራሮች እና ታጋዮቻችን በኤርትራ ወህኒ ቤቶች እየተሰቃኡ ከመሆኑም በላይ እንዲሁም በሺዎች የሚቆተሩ ኢትዮጵያውያን በእስር የማቀቁ ባሉበት ሁኔታ ሻእቢያ የነጻነት አባት በመምሰል በኢትዮጵያውያን ስም የሚሰጠውን ፕሮፓጋንዳ ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ንቅናቄውን ዋቢ በማድረግ ጠቁመዋል::

– የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በተደጋጋሚ የሰጣቸውን መግለጫዎች ዚህ ሊንክ ላይ ያግኙታል::

Please wait, video is loading…

– በድምጽ እዚህ ላይ ይጫኑት :

phpBB [video]

አስመራ የታገቱት የአማራ ንቅናቄ አባላት በሻእቢያ ከባድ እንግልት እየደረሰባቸው ነው::የሚለው ንቅናቄው በዚህ ዙሪያ መግለጫ ያወጣል ተብሎ የተጠበቀ ነው::

Image

ባለፈው ሳምንት የወያኔ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ ጎንደር
አርማጭሆ ውስጥ ሶረቃ በሚባለው አካባቢው አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት
አስነስተው ቦታውን ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል ያደረጉት ጥረት ሕዝቡ ከዳር እስከዳር
በመንቀሳቀስና ውጊያ በመግጠም ያከሸፈው መሆኑ ታውቋል። በተደረገው ግጭትም ከሁለቱም
በኩል ጉዳት የደረሰ መሆኑ ከሥፍራው የሚገኙ ዜናዎች ያስረዳሉ። ሁኔታው እስካሁን ያልበረደ
ሲሆን ሕዝቡም ከዳር እስከ ዳር ተጠራርቶ መብቱን ለማስከበርና ንብረቱን ለማስጠበቅ
ባንድነት ለመታገል ወስኗል።

የወያኔ አገዛዝ ሥልጣን ላይ ለመቆየት አገሪቱን በጎሳና በቋንቋ እንዲሁም በሃይማኖት በመከፋፈል
በሕዝብና በሀገር ላይ ከፍተኛ በደል ከመፈጸሙ በተጨማሪ ለዓመታት በጎንደርና በወሎ
ክፍለሀገራት የነበሩትን ሰፊ አካባቢዎች ያለ ሕዝቡ ፈቃድና ስምምነት ቀምቶ በትእቢትና
በማናለብኝነት በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲጠቃለሉ ያደረገ መሆኑ ይታወሳል። የወያኔ እኩይ
ተግባር ሕዝቡን ከፍተኛ ብሶት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ይህ አልበቃ ብሏቸው የወያኔ ሆዳም
ባለሥልጣኖች ደኻውን ገበሬ ከእርሻ ቦታው ላይ አፈናቅለው መሬቱን ለመቀራመት የወሰዱት
እርምጃ በጽኑ የሚወገዝ ነው።

ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው የወያኔ ቡድን በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተቆናጠጠ ጀምሮ የኢትዮጵያን
አንጡራ ሀብት ዘርፎና ለቡድኑ መጠቀሚያ አድርጎ በወሰን አካባቢ ያሉ ለም መሬቶችን
ተቃዋሚዎችን ለሚቆጣጠርለትና መስል አጽፋዊ ስጦታ ለሚያደርግለት ለሱዳን አስረክቦ፤ ሰፋፊ
ለም የእርሻ ቦታዎችን ለውጭ አገር ከበርቴዎች በሊዝ ሸጦ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ትውልድ ይቅር
የማይለው ከፍተኛ በደል ፈጽሟል።

ይህን ግፍና በደል ለማስቀረትና የሕዝቡን መብትና ጥቅም ለማስከበር ከቡድኑ ጥቅም በላይ
ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደንታ የሌለውን ዘረኛና አምባገነን ቡድን በሕዝባዊ ኃይል
ከማውረድ በስተቀር ሌላ አማራጭ የሌለ በመሆኑ ዛሬም ትግላችንን በሕብረት አጠናክረን ወደፊት
እንግፋ የሚለው ጥሪ ወቅታዊ ሆኖ የሚገኝ ነው።

ሕዝባዊ ትግሉን በኀብረት እናጠናክር !!
ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ይወገዳል !!

MinilikSalsawi : በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት የአርበኞች ግንባር እና የግንቦት ሰባት ውህደት የመጀመሪያው ዙር ጉባዬ በዛሬው እለት መጀመሩን የአስመራ ምንጮች ተናግረዋል:: ጉባዬውን በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃዎች ዝርዝር እንደደረሰኝ አቀርባለሁ::

ኢሳት ሁለት ጋዜጠኞች ያለውን ሁኔታ እንዲዘግቡ ወደ ኤርትራ የላከ ሲሆን በዚህም መሰረት መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔአለም ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል::በኤርትራ ቆይታቸው የውህደቱን ጉባኤ እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ የሚቃኙ ሲሆን የሻእቢያን ባለስልጣናት ያናግራሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ለማስታወስ ያህል::

Please wait, video is loading…

Image

ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ 200 000 ዶላር የሸለመውና የኢትዮጵያ ብቸኛ የማዳበሪያ አቅራቢ የሆነው Yara ዳይሬክተር Thor Leif Enger በሙስና ክስ ፍርድ ቤት ቀረበ

መለስ ዜናዊን የሸለመው በሙስና ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ
የኖርዌይ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን Yara ላይ ክስ ሊጀምሩ ነው።
**********************************************
በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1997 (2005) ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ 200 000 ዶላር የሸለመውና ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ብቸኛ የማዳበሪያ አቅራቢ የሆነው Yara የተባለው የኖርዌይ ኩባንያ ዳይሬክተር Thor Leif Enger በኖርዌይ ታሪክ ትልቅ በተባለው የሙስና ክስ ነገ ጠዋት Oslo ፍርድ ቤት ቀረበ ።

በጣም የሚገርመው ዳይሬክተሩ የተከሰሰው በህንድ እና ሊቢያ ጉዳይ ሲሆን Yara በእነዚህ ሁለት ሃገራት ውስጥ ባልተገባ መልኩ ጨረታ አሸንፎ ማዳበሪያ የማቅረብ ኮንትራት ያገኘበት መንገድ ለሁለቱ ሃገራት ባለሥልጣኖች ዳይረክተሩ ከጨረታው በፊት 8 ሚሊዮን ዶላር በመስጠቱ መሆኑን የዛሬው የኖርዌይ የዜና አገልግሎት NRK ተዘግቧል። ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የ71 አመቱ ቱርላይፍ ኤንገን የቀረውን ህይወቱን በእስር ቤት እንደሚያሳልፍ ታውቋል።

ይህንን ቅደም ተከተል ይመልከቱ :
✦June 2005 – Ethiopian police massacred the Ethiopian oppositions on the streets of Addis Ababa.
✦July 2005 – Mr Thorleif Enger Director of Yara awarded 200 000 USD to former P.M Meles Zenawi apparently for his steps towards increasing food production and reducing poverty
✦December 2005 The Norwegian Yara wins contracts to deliver fertilizer in Ethiopia after handing out prizes to the former PM. 30% of the income went to the ruling TPLF’s companies (EFFORT)
✦January 2014 Mr Thorleif Enger the former Director of Yara appears in court indicted for corruption after for paying over $8 million USD in bribes to win fertilizer bids in India and Libya.
✦ In January 2014, Ethiopians residing in Norway (led by me) request the Norwegian National Authority for Investigation and Prosecution of Economic and Environmental Crime (ØKOKRIM) to investigate the bid that Yara won in Ethiopia December 2005. http://www.okokrim.no/artikler/in-english
ልጅ ግሩም

አርማጮ ያለው የወያኔ ጦር በአማራ ንቅናቄው ጦር አሁንም ተሰንጎ ተይዟል::

– ሻእቢያ መረጃ ያሾልካሉ ባላቸው የነጻነት ታጋዮች ላይ ማስጠንቀቂያ አወረደ::
– የውህደቱ ጉባዬ ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው:: ቅድመ ምክክሮች እየተካሄዱ ነው::
– የሕወሓት ጄኔራሎች እና የደህንነት ሃላፊዎች ጎንደር እየተመላለሱ ነው::
Minilik Salsawi

ከአስመራ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከውህደቱ ቀድመው የሚወጡ የስብሰባው መረጃዎች እና ሻእቢያን የሚመለከቱ ግፎችን በዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል የተባሉ የነጻነት ተዋጊ ኢትዮጵያውያን በግምገማ እየታመሱ መሆኑን የሻእቢያ ምንጮች ጠቁመዋል:: አመራሮቻቸውን በግንባር አስቀምጦ ለነጻነት በረሃ የገቡትን ታጋዮች ሰብስቦ በሱዳን ሲም ካርዶች እየተጠቀማቹ መረጃዎችን በኤስኤሜስ ቴክስት እና በኢንተርኔት ታቀብላላቹ የመረጃ መውጣት ፍንጮች እየታዩ ነው ሳይስፋፉ ራሳችሁን አጋልጡ እየተባሉ ሲተራመሱ መክረማቸው ታውቋል::

ስለ አስመራው ትግል ዝርዝር መረጃዎች አሉን የሚሉ የድህረገጽ ሚዲያዎች በርክተዋል በሚል ዙሪያ ከፍተኛ ግምግማ የተካሄደ ሲሆን ሁኔታው መጣራት አለበት በሚል መተራመሱ ሲቀጥል በኤርትራ የኢንተርነት አክሰስ የሚጠቀሙ እንዲታገድባቸው እና ለፕሮፓጋንዳ ሰራተኞች በክትትል እንዲፈቀድላቸው የተደረገ ሲሆን የሱዳን ሲም ካርድ የሚጠቀሙ የበረሃ ልጆች በጠቅላላ ከነስልካቸው እንዲነጠቁ እና ምንም አይነት አክሰስ እንዳይፈቀድላቸው ሻእቢያ ከባድ ማስጠንቀቂያ አውርዷል::መረጃውን የሰጡን የሻእቢያ ምንጮቻችን ከአፋኝ መንግስት ወደ ሌላ አፋኝ መንግስት በሽያጭ ይሁን በተውሶ በማይታወቅ መልኩ ዝውውር አድርገናል ሲሉ የነጻነት ታጋዮቹ ውስጥ ውስጡን ያጉረመረሙ መሆኑን ገልጸዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የውህደቱ ጉባዬ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን ቅድመ ምክክሮች መካሄዳቸውን በስብሰባው ለመሳተፍ የሄዱ ቡድኖች የገለጹ ሲሆን ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል::

በአርማጮና በአከባቢው የሚገኘው የአማራ ንቅናቄ ጦር የወያኔን ሰራዊት ሰንጎ በመያዝ እየተዋጋ መሆኑን የድርጅቱ ምንጮች ገልጸዋል::ይወያኔው መንግስት ባከባቢው የተነሳውን ጦርነት መቆጣጠር ባለመቻሉ ከኢታማጆር ሹሙ ጀምሮ የደህንነት ምክትሉ አቶ ኢሳያስ እና የጠ/ሚ የደህንነት አማካሪ አለቃ ጸጋይ ድረስ የአከባቢውን ወታደራዊ እና የደህንነት ባለስልጣናትን ጨምሮ እየተረባረቡ መሆኑን የቅርብ ምንጮች አስታውቀዋል::የአማራ ክልል የደህንነት ሃላፊዎች አቶ ተሾመ እና አቶ አያኖ መቀመጫቸውን ጎንደር በማድረግ ከፍተኛ መረጃ በመሰብሰብ ከወታደራዊ ደህንነቶች ጋር በመቀዳጀት ለፌዴራሉ መንግስት በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ::እንዲሁም ይህንን እንቅስቃሴ በበላይነት ለመምራት የመከላከያ ዘመቻ የበላይ መኮንን የሆነው ጄኔራል ገብረዝጌር መብራትኡ ከአዲስ አበባ ጎንደር በመሄድ ሂደቱን እያስተባበረ ያለ ሲሆን ወደ ሱዳን መንግስትም የደህንነት ምክትል ሹም አቶ ኢሳያስ የተባለ የሚመራው ቡድን መላኩ ታውቋል::

በትላንትናው እላት በከባድ መሳሪያዎች እና ታንኮች ታጅቦ ወደ አርማጮ የገባው የወያኔው ሰራዊት በሽምቅ ውጊያ የሰለጠነ ልዩ ጦር ሲሆን ተጨማሪ ጦር አስቸኳይ ስምሪት ..9 ..9 ..እያደረገ በአከባቢው በመዟዟር ተቃዋሚዎች ይኖሩብታል ያለውን ቦታ ሁሉ በማጽዳት ላይ ሲሆን የሃገር ቤት በወያኔ ህግ ተመዝግበው ያሉ የፖለቲካ ድርጅት አባላት የዚህ ጽዳት ዘመቻ ተጠቂ እንዳይሆኑ ሲያስፈራ ሁኔታውን በአጭር ጊዜ ሳይስፋፋ ሙሉ ሰሜን ጎንደርን እና በከፈል ደቡብ ጎንደርን ለማጽዳት ዘመቻው በደህንነቶች እና በወያኔ ጦር የተጀመረ መሆኑን ምንጮች ከአከባቢው ተናግረዋል::

Image
Eyasped Tesfaye
በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን በፖሊስ ፕሮግራም ላይ viewtopic.php?f=2&t=91626 ተቆርጦ ተቀጥሎ የተላለፈው የአንዳርጋቸው ፅጌ ድንቅ የትግል ጥሪ መልዕክት ለሊቱን ሙሉ ሲደንቀኝ ነው ያደረው፡፡ ኢቲቪ በነካካ እጇ ያልተቆራረጠውን ሙሉ ቪዲዮ ደግሞ ብትለቅልን እንዴት ሸጋ ነበር፡፡
አንዳርጋቸው ፅጌ በተቆራረጠው ቪዲዮም ውስጥ እንኳን ያስተላለፋቸው 3 መልዕክቶች ድንቅ ናቸው፡፡ ሙሉውን ንግግሩን ፅፌ እለጥፈዋለሁ፡፡ እስከዛው ግን መልዕክቶቹ እነኚህ ናቸው፡-
1ኛ፡- ለወጣቱ የተላለፈ የትግል ጥሪ፡- ወጣቱ የሴት ጓደኛውን ቀጥሮ ሸሚዙን ሲያስተካክል መዋል ሆኗል ስራው፡፡ እንዴት አድርጎ ከኢትዮጲያ እንደሚወጣ እና ደቡብ አፍሪካ ወይም አሜሪካ እንደሚገባ ብቻ ነው የሚያስበው፡፡ ወደ ፖለቲካው የሚመጣው ወጣት ቁጥር እጅግ አናሳ ነው፡፡ ተፒለፍ እና ኢህአፓ ጊዜ የነበረው ፖለቲካ በትምህርታቸው ጎበዝ የነበሩ ተማሪዎችን ሳይቀር ነበር የሚስበው፡፡ አሁን ግን የፊልም አክተር እና ዘፋኞች የሚኖሩበትን ቤት በፊልም እያየ በምኞት ብቻ የሚኖር ወይም እንዲህ አይነት ቤቶች ወዳሉበት አካባቢ ለመሰደድ የሚፈልግ ወጣት ነው ያለው፡፡ በሚል አንዳርጋቸው ወጣቱ ካረፈበት የእንቅልፍ አዚም እንዲላቀቅ እና ለትግል እና ለመደራጀት እንዲዘጋጅ ያስተላለፈው መልዕክት ነው፡፡
2ኛ፡- የተባበረ ትግል ጥሪ፡- አንዳርጋቸው ይህንን ጥሪ ያስተላለፈው ለሶስት አካላቶች ነው፡፡ አንደኛ የኦሮሞ የአማራ እና የደቡብ ኤሊቶች ልዩነታቸውን አጥብበው በህብረት እንዲሰሩ የጠየቀበት፡፡ ሁለተኛ በውጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች 5 እና 20 እየሆኑ ለየብቻቸው የሚያደርጉትንና እንደ አንዳርጋቸው አገላለፅ ‹‹ዩኒቲ ኦፍ ፐርፐዝ›› የሌለበትን ትግል እንዲተው የተናገረበት እና ሶስተኛ ደግሞ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዘጠና ፓርቲዎች 1500 ፊርማ ብቻ እያሰባሰቡ እዚህ እና እዚያ የፈሉበትን ሁናቴ የተቃወመበት ነው፡፡
3ኛ፡- ምርጫ ቀልድ መሆኑን ያጋለጠበት መልዕክት፡- መንግስት ግልፅነት ያለው አሰራር ሳይከተል ተቃዋሚዎች እንዴት ብለው ነው የምርጫ ማኒፌስቷቸውን ማዘጋጀት የሚችሉት የሚል ጥያቄ በቪዲዮው ላይ ሲጠይቅ የሚሰማው አንዳርጋቸው ፅጌ ቃል በቃል ‹‹ምርጫው ቀልድ ነው›› ሲልም ይደመጣል፡፡
ሌላው በዚህ ቪዲዮ ላይ ያስተዋልኩት ነገር ከ 6 ደቂቃ ከ 55 ሰከንድ እስከ 7ኛው ደቂቃ ከ 4 ሰከንድ ድረስ እጅግ በጣም ሳግ በተናነቀው እና በተጎዳ ድምፅ ‹‹ከዚህ በኋላ ያለው ነገር የበለጠ ቀውስ እና የበለጠ ኪሳራ በሀገሪቷ እና በህዝቧ ላይ የሚያደርስ ነገር ነው የሚል ዕምነት ነው ያለን›› የሚለው ንግግሩ ነው፡፡ ምኑ ነው የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ ያመጣል ያለው ነገር; ምናልባት ኢቲቪ ትጥቅ ትግሉ የበለጠ ኪሳራ ያመጣል እያለ ነው የሚል ምስል በተመልካች ዘንድ ለመፍጠር አሳባ ነው; ያም ቢሆን ደግሞ ትጥቅ ትግሉ የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ ያመጣል ሲል ማሰማት ነበረባት፡፡ እኔ ግን ሲመስለኝ የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ የሚያመጣ ያለው ምርጫውን እና አሁን ያለውን ስርአት ነው፡፡ ይህን ያልኩበት ምክንያትም በንግግሩ መጨረሻ ላይ የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ የሚያደርስ ነው የሚል እምነት ነው ‹‹ያለኝ›› ሳይሆን የሚለው ‹‹ያለን›› ነው የሚለው፡፡ ይህ ማለት የአንድን ቡድን አቋም እየገለፀ እንዳለ ግልፅ ነው፡፡ በቡድን ደረጃ ያውም አንዳርጋቸው ‹‹እኛ›› እያለ የሚያወራለት ቡድን ደግሞ ስለ ትጥቅ ትግሉ እንዲህ አይነት አቋም እንደሌለው ግልፅ ነው፡፡
በመጨረሻም ቪዲዮውን ደግሜ ደጋግሜ ካየሁት በኋላ የገባኝ ነገር ቢኖር አንዳርጋቸው ባገኛት ትንሽ ቀዳዳም ቢሆን መልዕክቱን ማስተላለፉን እና ምናልባትም ይህ መልዕክት በቴሌቪዥን እንዲሰራጭ ያደረጉት ሰዎች የውስጥ አርበኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው፡፡

ኢትዮ-ቻይና በቻይና -አፍሪካ አደባባይ

ኢትዮ ቻይና በቻይና አፍሪካ አደባባይ

ዛሬ ጠዋት 2፡45 ላይ ቦሌ…ከድልድይ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽየሚወስደው መንገድ መጠምዘዣ ላይ ከአስፓልቱ ጠርዞች በአንዱ ጥግ አንድ ቻይናዊ (ቻይና መሰለኝ) ከአንድ ፖሊስ ጋር ሞቅ ያለ ክርክርነገር ገጥሟል….እጁን እያወናጨፈ ያወራል…መቼም “ቻይና”ዊው አማርኛ አጥንቶ ይሆናል እንጂ በዚህ ፍጥነት የሚያወራው ነገር (ቻይንኛ/ማንዳሪንከሆነ) ፖሊሱ የሚገባው አልመሰለኝም…”ቻይና”ው የፖሊሱን ነው መሰለኝ የዱላ ቆመጥ በእጁ ይዟል…አጠገባቸው ስደርስ ቻይናው “temper is come” ሲል ሰማሁት… በእንግሊዝኛ ሊያስረዳውእየሞከረ ነው ማለት ነው….ሰይጣኑን ያመጣው ምን ይሆን ብዬ እያሰብኩ ሳለ ሴት ፖሊስ መጣችና ቻይናው በእጁ የያዘውን ቆመጥ እያየች‹‹ማነው የሰጠው;›› ስትል ሰማሁዋት …”ቻይና”ው በሆነ ብልሃት ከፖሊሱ እጅ እያሳሳቀ የወሰደው ነው የሚመስለው…ወንዱ ፖሊስ ቆመጡንተቀበለ….አንድ አስር እርምጃዎች ወደፊት ስሄድ በርከት ያሉና ሻንጣዎች የያዙ ቻይናዎች ከአካባቢው ሰው ጋር ውዝግብ የገቡ ይመስላል….ሌባ ተተናኩሎዋቸው ይሆናል አልኩ (ያው ሌቦቹ እኛ አይደለን?!) ግን በሚታዩኝ አንድ ሁለት የፌዴራል ልብስ የለበሱ ወታደሮች የታጀበአንድ ጥቁር እንደ ሌባ ተይዞ ስላላየሁ፣ እንዲሁም ከግርግሩ መሃል አንድ ቻይናዊና አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት አንገት ላንገት ሲተናነቁማየቴ ጉዳዩ ሌላ አንደሆነ ጠረጠርኩ….ይሄኔ ሌሎቹ ቻይናዎች ድብድቡ ወደእነሱ እንዳይመጣ ለመከላል ይሁን ወይ የወንድማቸው መመታትደማቸውን አፍልቶት እንጃ ብቻ አጠገባቸው የሚገኘውን ሰው ባለ በሌለ ሃይል መማታት ያዙ…አሁን ተሞኙ አልኩ…እጁን አጣጥፎ የእነሱንዱላ እንደአሻንጉሊት ወይም እንደ ጌም ገፀባህሪት የሚቀበል ሰው ያለ መስሏቸው ይሆን? (ይቺ ናት ጨዋታ አለ ጥልዬ) እዚያየተሰበሰበው ሁሉ በድንጋይም በቡጢም ቻይናዎቹ ላይ ሲረባረብ ጉዳዩ አስፈሪ መልክ ያዘ …. ሁለት ጥይቶች ወደሰማይ ተተኮሱ…አንድ “ቻይና” ፊቱ በደም ተለውሶ ከግርግሩ ውስጥ ሲወጣና “ቻይና”ዎቹ ቁጥሩ በጣም እየበዛ የመጣው ህዝብ እደማይለቃቸው ሲገባቸው (ጥይቶቹምፀቡ የዋዛ እንዳልሆነ ሲገልፁ)….ገለል ገለል አሉ…ጉዳዩ በ”ቁጥጥር” ስር ሲውልና “ቻይና”ዎቹ መሃል አስፓልት ላይ እንዲቀመጡታዘው ደምና አቧራቸውን (“ለሀገሬ የከፈልኩት ነው” ይሉ ይሆናል) እየጠራረጉ ከነሻንጣዎቻቸው ሲቀመጡ….. እኔም ወደጉዳዬ ሄድኩ….

“Made in China” የሚል ጫማ ስንገዛ አንዳንዶቻችን “መቼም እግሬን አይወስዱብኝም”ብለን ነበር…መንገድ ሲሰሩ ስናይ ያገሬ መሀንዲስ ዛሬ እዚህች ጋ…ነገ ደግሞ እዚያች ጋ እየቆፈረ የሆነች ኪሎ ሜትር ላይ አመትመተኛት አቁሞ ትንሽ መፍጠን ሲችል ቻይና ሀገሯ ትገባለች ብለን ነበር… እርግጥ ነው ከአዲስ አበባ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ወጣ ስንልየተተከሉና ግብራቸውን ለመረዳት ስንሞክር አማርኛ እያማረን ቀርቶ በተበደርነው እንግሊዝኛ እንኳ እንዳይገባን የራሳቸው ቋንቋ ብቻየተለጠፈባቸው ግዙፍ ኩባንያዎች ስናይ ፍርሃት ቢጤ የሚሰማን ጥቂቶች አይደለንም (የሀገራችንን መልክ እየቀሙን እንደሆነ ደመ ነፍሳችንእየነገረን)….(ጎበዝ፣ ቻይንኛ መማር አይከፋም…ቢያንስ ምን እያሉ እደሚያሻሽጡን ይግባን እንጂ).…
Image

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተለምዶ OCR (OldClass Rooms) በሚባለውና የኢትዮጵያና የውጪ ቋንቋዎችና ስነፅፍ እንዲሁም የፎክሎር ትምህርቶቸ በሚሰጡበት ህንፃ ውስጥ የቋንቋዎችጥናት ተቋም ቤተመፃህፍት ነበር (“ነበር” እንበል) የእነዚህ ትምህርቶችን የተመለከቱ መፃህፍት…ጥናቶችና ጆርናሎች የሚገኙበት…የህንፃው አንደኛ ፎቅ ላይ የተሰየመ….ባለፈው ሰሞን በአጋጣሚ ወደዚያ ህንፃ ሳቀና መልኩ ተቀይሮ አገኘሁት….ቤተመፃኅፍቱ ዕድሳትየተደረገለት መስሎኝ ነበር መጀመሪያ… ጠጋ ስል የተስፋፋ የቻይና ግዛት ሆኗል ….የቻይና ኢምፓየር ህንፃው ውስጥ ተገንብቷል…“ConfuciusInstitute” በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ…ግርግዳው ላይ የቻይናን ባህል የሚያስጎበኙ በፍሬም የታሸጉ ፎቶ ግራፎች ተሰቅለዋል……ቤተመፃህፍቱየለም (ነፍስ ይማር ብለናል) …. ወዳጆቼ፣ ፈቅደን ስንሰጣቸው የትድረስ እንደሆነ ካላወቅን (እናውቃለን ማለት ይከብዳል-ማወቅም የምንፈልግ አንመስልም) ንቀት ብትነግስብን በማን ይፈረዳል?
Elizabeth Mengistu

ቦሌ ወሎ ሰፈር በግድግዳ ላይ ፅሁፎች እና መፈክር በተፃፈባቸው ወረቀቶች አሽብርቃ አደረች፡፡አቡ ዳውድ ኡስማን በአዲስ አበባ በቦሌ ወሎ ሰፈር የሚገኙ የውስጥ መንገዶች በግድግዳ ላይ ፅሁፎች እና መፈክር በተፃፈባቸው ወረቀቶች አሸበርቃ ማደሯን ምንጮች አስታወቁ፡:
በቦሌ ወሎ ሰፈር ውስጥ ለውስጥ በሚያስኬዱ መንገዶች የሚገኙ ግድግዳዎች እና መንገዶች የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ የመብት ትግል የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች ተፅፎባቸው አንግተዋል፡፡
ከተፃፉት እና ከተበተኑት መፈክሮች መካከል
አሸባሪ አይደለንም፣ የታሰሩት ሙስሊሞች ይፈቱ,ኮሚቴው ይፈታ፣የሂጃብ
ገፈፋው ይቁም፣ትግሉ ይቀጥላል፣ ፍትህ ናፈቀን

የሚሉ እና በርካታ መፈክሮች በግድግዳ ላይ እና በወረቀቶች ተፅፈው መበተናቸው ታውቋል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በማጠናከር የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ድምፁን እያሰማ ይገኛል፡፡
ድል ለጭቁኑ የኢትዬጲያ ሙስሊም!!

Image
Image
Image

More Photos
https://www.facebook.com/profile.php?id … nref=story

Image
ከ26 ዓመታት በፊት የደርግ መንግሥት በትግራይ ክልል በሐውዜን ሕዝብ ላይ ያካሄደው የአውሮፕላን ድብደባ በስተጀርባ የእሥራኤል መንግሥት እጅ እንዳለበት የቀድሞ የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ስብሃት ነጋ ይፋ አደረጉ።
አቶ ስብሃት ይህን የገለፁት በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የደርግ 604 ኮር የተደመሰሰበትን የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ አስመልክቶ ሰሞኑን በሽሬ ከተማ በተሰናዳ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
አቦይ ስብሃት ሲያስረዱ፣ “የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምን ተከትሎ ታላቋ ሶቪየት ሕብረት መፈራረስ ጀመረች። ይህን ክስተት ተከትሎ ሶቪየት ሕብረት ከኢትዮጵያ እየወጣች መጣች። በእሷ እግር የተተካውም የሩሲያ ፌዴሬሽን ለደርግ አገዛዝ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጠ። ይህን ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካ ዳይናሚዝም ተከትሎ አሜሪካ መራሹ የምዕራብ ዓለም እና የእሥራኤል መንግስት ከደርግ ጋር ወዳጅ ሆኑ። የደርግ አገዛዝን መውደቅን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የጂኦ-ፖለቲካል ኃይል አሰላለፍ በመፍራት የምዕራቡ ዓለምና እሥራኤል ደርግን ወዳጅ አድርገው በእኛ የትግል እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “በወቅቱ ሕወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅሙ እየጠነከረ እየመጣ በመሆኑ አሜሪካና እሥራኤል ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል። የአዲስ አበባው መንግስት ወዳጅ ስለሆኑ እንዴት ከተጀመረው የትጥቅ ትግል ሊያድኑት እንደሚችሉ ብዙ መንገዶችን ሞክረዋል። በጊዜው ደርግን ለማትረፍ ያልሞከረ የምዕራብ ሀገር አልነበረም። ሁሉም የሚችለውን አድርጓል። አሜሪካ ለማደራደር ስትሞክር እሥራኤል ግን የተለየ ሚና ወሰደች” ሲሉ ወንጅለዋል።
“አሜሪካ አንዴ ወደ ሮማ ሌላ ጊዜ ወደ ለንደን እንድንመጣ ጠራችን። ሮማ ላይ ጂሚ ካርተር አስጠርቶን የነበረ ቢሆንም፣ የደርግ ልዑካን ቡድን እናንተ ስለኢትዮጵያ ምን ያገባችኋል አሉን። ወደ ለንደን ተጠርተን ስንሄድ ግን ሁሉን ነገር ስለጨረስን ደርግን ጥለን ነበር” ብለዋል።
እስራኤል ግን ወደ ሮማ ከመሄዳችን በፊት፣ ደርግን በጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ጀምራለች። ደርግ የታጠቀውን የክላስተር ቦምብ እ.ኤ.አ ጁን 22 ቀን 1988 ሐውዜን በገበያ ቀን ህዝቡ ላይ አዘነበው። በጥቃቱም ከ2ሺ 500 በላይ ህዝብ ማለቁን ተናግረዋል። አያይዘውም፤ “ይህ ሁሉ የህዝብ ዕልቂት በእሥራኤል አስታጣቂነት የተፈጸመ ነበር” ሲሉ አቦይ ስብሃት ለተሰብሳቢው በሃዘን ተውጠው አስረድተዋል።
የቀድሞ የደርግ መንግሥት ርዕሰ ብሔር የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም ወደ ዙምባቡዌ የሸሹት በምዕራብ ሀገሮች ድጋፍ መሆኑ ሲነገር ነበር። ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል የሞት ፍርድ ቢተላለፍባቸውም አንዳቸውም የምዕራቡ ሀገራት የዙምባቡዌ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጥ ግፊት አድርገው አያውቁም።
በ ፋኑኤል ክንፉ – www.sendeknewspaper.com

Image

የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› መረጃ እንዲሰጡት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅጽ እያከፋፈለ መሆኑ ታወቀ፡፡

ምንም እንኳ በቅጹ ላይ ዜጎች ስለ ሰማያዊ ‹‹ጥሩና መጥፎ›› አስተያየት እንዲሰጡ ቢልም መጀመሪያ ላይ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› ሲል ፓርቲው የህዝብን ሰላም እያደፈረሰ ነው ሲል ፈርጆታል፡፡

ቅጹ ከተሰጣቸው መካከልም አንድ የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪ ቅጹን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ሲል ለኢትዮ ምህዳር የላከ ሲሆን ‹‹ይህንን አስገራሚ ቅጽ እንድንሞላ በአንድ ክ/ከተማ በተገኘንበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢው ሁሉ ታደለ፡፡ ታዲያ ሁሉም ቅጹን ወስዶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እኔም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ለጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ልኬዋለሁ፡፡ አይገርምም ሕገ-መንግስት የሚፈቅደው ሰላማዊ ሰልፍ አንቀጽ በመንግስት አስፈጻሚዎች ሲጣስ›› በሚል አስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡

አርማጮ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት በውጊያ ተወጥራለች::
Image

Minilik Salsawi : በአርማጮ አከባቢ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የንቅናቄው ምንጮች ከአከባቢው አስታወቁ::የህዝቡ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ ባለበት እና ህዝቡ እና የንቅናቄው ወታደሮች በመቀናጀት ዱር ቤቴ ብለው ወደ ጫካ መግባታቸው ሲታወቅ በመተማ ሸዲ አከባቢ በትላንትናው እለት በወያኔው ጦር ላይ ጥቃት አድርሶ ወደቦታው የተመለሰው የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እጅግ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እንደማረከ ምንጮቹ ተናግረዋል::

ካለፈው አርብ ጀምሮ የተነሳው ውጊያ በአሁን ወቅት ቀጥሎ ያለ ሲሆን በዛሬው ለሊት ከፍተኛ የቶክስ እሩምታዎች እና የከባድ መሳሪያ ድምጾች በአከባቢው እየተሰሙ መሆኑ ታውቋል::በአብድራፊ አብሃጂራ ሶረቃ ግጨው ማርዘነብ ማይጸማር ሃሙስ ገበያ ዳንሻ ማይካድራ እና አከባቢው ጦርነቱ ይስፋፋባቸዋል የሚል ከፍተኛ ስጋት ስላደረ በአከባቢው የወያኔ ሰራዊቶች በብዛት መስፈራቸው ሲታወቅ አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ከባባድ መኪኖች በቦታው ደርሰዋል:: እንዲሁን ወደ ሱዳን ክልል ዘልቀው የገቡ እና ከሱዳን ወታደሮች ጋር አሰሳ የሚያደርጉ ወያኔዎችን እንዳጠቁ የአማራው ንቅናቄ ወታደሮች ተናግረዋል::

በአርማጮ እና አከባቢው የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል::

ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ ነው

• ‹‹ኢህአዴግ አይገዛንም!›› ተማሪዎቹ
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ተማሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት ጥያቄ ያነሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ስልጠና ወደሚሰጡባቸው ትምህርት ቤቶች ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም ባሻገር የድብዛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን መቃወማቸውን ተከትሎ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሰሙ የተክለሀይማኖት መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እርምጃውን በመቃወም ለድብዛ ተማሪዎች ድጋፍ መስጠታቸው ተገልጾአል፡፡

የሁለቱም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጋር በመሆን ከተማው አደባባይ ላይ በመውጣት ‹‹አህአዴግ አይገዛንም፣ ኢህአዴግ ሌባ፣…›› የመሳሰሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለጻቸውን ተከትሎም ፖሊስ ተማሪዎቹን እያፈሰ ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጥያቄ የሚጠይቁና ፖሊስ ተቃውሞውን አደራጅተዋል ብሎ የሚጠረጥራቸውን ተማሪዎች እየፈለገ እያሰረ መሆኑን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን በ17ቱም ወረዳዎች የሚገኙ ተማሪዎች ስልጠናውን ካልወሰዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስልጠናውን መቃወማቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ለውጡ ይመጣል! ጥያቄው ግን ተዘጋጅተናል ወይ? ነው፡፡
————————————————-
ስለ 1966ቱ ለውጥ ብዙ ተብሏል፡፡ በለውጡ ወቅት የነበሩትን ሰዎችም ሆነ ሌሎቹን የሚያስማማ አንድ ነገር ቢኖር የለውጡ ግብታዊነት እና ለውጡን ሊሸከም የሚችል ድርጅት በወቅቱ አለመኖሩ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ቆመን ለውጡ ገና ነው ብለን ብንዘናጋ እንደ ኃይሌ ፊዳ ልንሳሳት የምችልባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ይመስሉኛል (ሀይሌ ፊዳ ከብርሀነ መስቀል ጋር ባደረጉት ውይይት ለውጡ ገና ነው ብዙ አመታትንም ይፈልጋል ብሎ ነበረ)፡፡ ከዚያ ይልቅ ለውጡን ለመቀበል በሚያስችል ተክለ ሰውነት ላይ ለመገኘት ምን እናድርግ የሚለው ላይ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

ብዙዎች በመኢሶን እና በኢህአፓ መካከል የነበረው ልዩነት ያለፈውን ትውልድ ዋጋ እንዳስከፈለው ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንዳንዶች የሁለቱ ልዩነት የእናቸንፋለን እና የእናሸንፋለን የቃላት ጨዋታ ነበረ ሲሉ በሚያነሱት ሀሳብ ባልስማማም (ልዩነታቸው መሰረታዊ ነበር ብዬ ስለማምን) የሁለቱ ልዩነት ግን ትውልዱን ዋጋ ማስከፈሉን የማይቀበል ማንም ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡

ስለሁለቱ ልዩነት ሲነሳ ቢያንስ በሁለት ወቅቶች ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
የመጀመሪያው ከለውጡ በፊት የነበረው እና ከለውጡም በኋላ እስከተወሰነ ድረስ አብሮ የዘለቀው የሁለቱ ፓርቲዎች የመደጋገፍ ጊዜ ነው፡፡ በአልጀርስ የነበረው የኢህአድ/ኢህአፓ መስራች ቡድን ከሀይሌ ፊዳው የመኢሶን መስራች ቡድን ጋር በአንዳንድ ነጥቦች ሳይስማሙ ቢለያዩም ልዩነታቸው ሰፊ የሚባል አልነበረም፡፡ ለዚህም ማሳያው የኢህአፓ ልሳን የነበረችው የዴሞክራሲያ የመጀመሪያ ዕትሞች እና የመኢሶን ልሳን የነበረችው የሰፊው ህዝብ ድምፅ ጋዜጣ የመጀመሪያ ዕትሞች በይዘት መመሳሰል እና በሀሳብ መደጋገፍ ነው፡፡ ይህ ሂደት እነ ሀይሌ ፊዳ ከውጪ ወደ ሀገር ቤት እስኪገቡ ድረስ የቀጠለ እንደነበርም ታሪክ መዝግቦ ያስቀመጠው ሀቅ ነው፡፡

ሁለተኛው ወቅት ደግሞ ለውጡ ከመጣ በኋላና እነ ሀይሌ ፊዳ ሀገር ቤት ከገቡ በኋላ ያለው እና በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለው ልዩነት መሰረታዊ እየሆነ የሄደበት እና በጣም የተለጠጠበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በመኢሶን እና በኢህአፓ አመራሮች መካከል ግንኑነት ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም (ለአብነትም ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ከዶ/ር ሀይሌ ፊዳ ጋር፤ ነገደ ጎበዜ ከአለማየሁ ሀይሌ(ደርግ ውስጥ ሰርጎ የገባ የኢህአፓ ሰው ነው ይባል ነበር) ጋር ተገናኝተው አውርተዋል) ከረፈደ በኋላ የተደረገ ውይይት በመሆኑ ያመጣው ለውጥ አልነበረም፡፡

በእኔ እይታ ለሁለቱ ድርጅቶች አለመስማማት አቢዩ ምክንያት ከለውጡ በኋላ ኢህአፓ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት (ማስ ቤዝ) ማግኘቱ በመኢሶን በኩል ለደርግ ሂሳዊ ድጋፍ እየሰጡ መቀጠል ይሻላል ወደሚለው ሀሳብ እንዲሄዱ የገፋቸው ይመስለኛል፡፡ ከመነሻው የነበራቸውን አነስተኛ ልዩነት አጥብበው በጋራ ቢሄዱ ኖሮ አንዳቸው ተለይቶ ህዝባዊ መሰረት የሚገነባበት እና ሌላኛቸው ህዝባዊ መሰረት ለመያዝ ከወታደሩ ጋር የሚሰለፍበት ሁናቴ አይኖርም ነበር፡፡

ለማንኛውም ይህን ያነሳሁት በታሪኩ ላይ ለመነታረክ ሳይሆን ዛሬም ከታሪክ ሳንማር ያለፈውን ስሀተት እንዳንደግም ካለኝ ፍርሀት ነው፡፡
ዛሬ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ እና አንድነት በጋራ ሆነው ለሚመጣው ለውጥ ራሳቸውን ካላዘጋጁ በስተቀር ከለውጡ በኋላ ልዩነታቸውን አጥብበው ለውጡ ተፈጥሯዊ ይዘቱን ጠብቆ ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ለማስቀጠል ይችላሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ ልዩነታቸውን አሁን ላይ ማጥበብ እና በጋራ መቆም ካልቻሉ ከለውጡ በኋላ እንደ ጠላት የሚተያዩበትም እድል እጅግ በጣም የሰፋ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ በተለይም ደግሞ ለውጡን ተከትሎ ከሁለት አንዳቸው ከፍ ያለ መስዋዕትነት የከፈሉ እንደሆነ፡፡

የተቃዋሚዎች በአንድ መቆም ለለውጡ ተዘጋጅቶ ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለውጡን ለማምጣትም የተሻለው እና አጭሩ መንገድ ነውና የየፓርቲዎቹ አመራሮች(በተለይም የሰማያዊ እና የአንድነት) ዛሬ ነገ ሳይሉ ቁጭ ብለው በመነጋገር ወደ አንድ የሚመጡበትን እና በጋራ ህዝቡን የሚያታግሉበትን መንገድ እንዲፈጥሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ፡፡
Image

በደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ መረር ያለ ተቃውሞ ተነስተዋል::
በጎጃም የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቁመው እንዲወስዱ የተደረገውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ምንጮን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት የህዝቡ አስተሳሰብ፣ የግል ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ እድገት ጠንቅ ተደርገው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አቀራረብ ተቃውመውታል፡፡ በአንጻሩ ከወራት በፊት ስልጠናውን የወሰዱት መምህራንም ዳግመኛ ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርገዋል እየጠደረጉ ሲሆን ዝምታን መምረጣቸው ተገልጾአል፡፡

ተማሪዎቹ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ ከሆነ ለተቃዋሚዎችም ይፈቀድ፣ ለምን ለግጭት የሚጋብዙ ቅስቀሳ ትቀሰቅሳላችሁ፣ የኢህአዴግ ፖሊሲ ምሁራንንም ጭምር ለስደት የዳረገ ነው፣ ከቻይና እና ከኮሪያ የሚያስተሳስረን የታሪክም ሆነ የባህል መሰረት የለንም፣ ኢህአዴግ 23 አመት ያልተገበረውን ዴሞክራሲ ሊያስተምረን አይችልም›› የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት ተቃውሞዎች እየተነሱ ሲሆን በተለይም ደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ ላይ ተማሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግ ሌላ፣ ኢህአዴግ ሌባ›› የሚል ጩኸት በማሰማታቸው ሲሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ 20፣ 20 ሆነው በየክፍሉ እንዲሰለጥኑ ተደርገዋል፡፡ በተለይ በደብረማርቆስ ከተማ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹ የካድሬ ስልጠና አንሰለጥንም በማለት መረር ያለ ተቃውሞ እያሰሙ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

Image
ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: ነዋሪነት በጀርመን የሆነው እና ለአርበኞች ግንባር ትግል ታላቅ አስታውጾ እንዳበረከተ የሚነገርለት አቶ ካሳዬ መርሻ በግንባሩ አባላት አስፈላጊዉን ወጪ ተሸፍኖለት ለጉዞ ሲንደረደር በሻእቢያ መከልከሉ በውጪ የሚኖሩ የግንባሩ አባላትን ያሳሰበ ቢሆንም ሁኔታውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::

በዚህ ምክንያት በውጪ የሚኖሩ የአርበኞች ግንባር አባላት እና ደጋፊዎች የተወከለው አቶ ካሳዬ እንዳይመጣ በሻእቢያ መከልከሉን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በደብዳቤ መላካቸው ሲታወቅ በአስመራ የሚገኙ የግንባሩ አመራሮች ሁኔታውን እንዲፈቱ በደብዳቤያቸው ያሳውቁት አባላቱ በአግባቡ የተወከለው ሰው በውህደቱ ጉባዬ ላይ እንዲገኝ ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል::የወከሉት ሰው በመከልከሉ በውህደቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬም አስምረውበታል::በቂ ሃይል እና ተንካራ መዋቅር እንዳለው የሚነገርለት አርበኞች ግንባት አባላቱ በኢትዮጵያ ለሚመጣው ለውጥ ተግተው እንደሚሰሩ እና ማንም እንደማያስቆማቸው ተናግረዋል::

አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት በሃገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃገራዊ አቋም እንዳይኖራቸው ሕወሓት/ኢሕ አዴግ በሰርጎ ገብነት እየገባ እንደሚያፋልሳቸው ሁሉ በውጪ የሚኖሩ ድርጅቶችንም እንዲሁ ሻእቢያ በውስጥ ጉዳያቸው እየገባ እሱ በሚፈልገው መልኩ እንዲሽከረከሩ ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል::

ከጀርመን የተወከሉት አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ እንዳይገቡ ካልተፈለገበት አንዱ ምክንያት ከዚህ ቀደም በግንባሩ ላይ በሻእቢያ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማስቀረት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆን የግንባሩ አባላት እና ታጋዮች ይህንን በደንብ ስለሚያውቁ በውህደቱ ላይ እንዲገኝላቸው ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ሻእቢያ ግን አንድ ጊዜ ጥርስ ስለነከሰበት እንዳይመጣበት ከልክሏል::እንዲሁም በውጪ የሚኖሩ አባላት ውህደቱ ላይ ችግር ካለ እንዲወገድ ወደፊትም ችግሮች እንዳይፈጠሩ አመራሩን ለማስተካከል እና አማራጮችን መጠቀም በሚል ስልት አቶ ካሳዬ የራሱን የፖለቲካ ልምድ ተጠቅሞ ሊያስተካክል ይችላል እንዲሁም ያሉትን ችግሮች እንዲስተካከሉ በፊትለፊት ይናገራል የሚሉ ፍራቻዎች በሻእቢያ ስላሉ የተወከሉት አባል ወደ አስመራ እንዳይገቡ ከልክለዋል::

አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ ሁለት ጊዜ ካሁን ቀደም ሂዶ ካለምንም ፍርሃት ለሻእቢያ ግንባሩን በተመለከተ ያለውን ችግር እና ወደፊት መሆን የለበትን ጉዳይ ካለፍርሃት አፍረጥርጦ ስለተናገረ እንዲሁም አቶ ካሳዬ የአርማጮ ተወላጅ በመሆኑ በአከባቢው ያለውን እና በግንባሩ ታጋዮች ዙሪያ ያለውን ጉዳይ አንስቶ ካለፍርሃት ለሻእቢያ መናገሩ ለአሁኑ መከልከል ምክንያት ቢሆንም ጉዳዩን ለመፍታት አስመራ እና አውሮፓ ያሉ የግንባሩ አመራሮች እየጥሩ መሆኑን ምንጮች ከአስመራ ተናግረዋል:
******************************************************************************
የወያኔ አየር ሃይል ባልደረቦች ይዘውት የገቡትን ሄሊኮፕተር ተከትሎ አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ የአዲስ አመትን ጋዜጣዊ መግለጫ አስታከው ይናገራሉ ተብሎ በመጠበቅ ላይ ሲሆን የወያኔ ቃል አቀባዮች ሌመንግስት ታማኝ ለሆነ ጋዜጣ ሄሪኮፕተሩ ለማስመለስ ጥረት አለመደረጉን መግለጻቸው ቢታወቅም የሕወሓት ጦር ጄኔራሎች ግን ካልተመለሰ ምሳችንን አስመራ እንበላለን ሲሉ መደንፋታቸው የወያኔ ባለስልጣናቱን አለመናበብ አመልክቷል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወያኔ በውጪ ከሚኖሩ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመደራደር ማንዣበቡን ፍንጮች ጠቁመዋል:: ወያኔ በስልጣን የመቆየት እድሉ እንደተመናመነ በማወቁ ድርድር የማድረግ ፍላጎት ማሳየቱ እና በታሪክ ልንከስም ነው ያሉት ባለስልጣንን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገዢው ፓርቲ የገባበትን አጣብቂኝ ሊወጣው ባለመቻሉ ውንደለመደው በማዘናጋት ጊዜ መግዣ መፈለጉን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image
ጌታቸው ሽፈራው
ያች ስለ መገንጠል የተዶለተባት ደደቢት በዓለም ቅርስነት ትመዝገብ እየተባለ ነው አሉ፡፡ አሜሪካኖች እርስ በእርስ ተዋግተው አገር ገንብተዋል፡፡ ጣሊያንና ጀርመኖች ደም ተፋስሰው አገር አቁመዋል፡፡ ምን አልባት እነዚህ አገራት ለአገር ግንባታ (አንድነት) ደም የፈሰሰባቸው ቦታዎች በራሳቸው ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ይሰጧቸው ይሆናል፡፡ እንጅ ዩኒስኮን መዝግብልን ብለው የተጃጃሉ አይመስለኝም፡፡ ኧረ እንዲያው ቢጠይቁስ ስለ አንድነት አጀንዳ የተነሳበት ቦታ (የግድ ከሆነ) ቅርስስ ቢሆን ምን አለበት?

ደደቢት የጠባብ ‹‹ብሄርተኝነት›› እንጅ የአገር ግንባታ መነሻ አይደለችም፡፡ የዓለም ህዝብ ከህወሓት አላማ ምን ሊማርበት ነው ደደቢትን ዓለም በቅርስነት የሚሸከመው? ከዚህ በተቃራኒ ቢቻል በዓለም አቀፍ ደረጃ ካልተቻለ ደግሞ በአፍሪካ ደረጃ አድዋ የሚከበርና የሚታወስ ቦታ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ ምክንያቱም የአፍሪካ የነጻነት ትግልም የሚፈነጥቀው ከዚህ ታሪካዊ ቦታ ነውና! ግን ይህ ኢትዮጵያና አፍሪካውያን እንጅ ህወሓት እንደ ቡድን ጥቅም አያገኝበትም፡፡ ከአላማው ጋርም ፍጹም የተለያዩ ናቸው፡፡

አሊያም ህወሓት ራሱ ተዋናይ የሆነበትን የሀውዜን ጭፍጨፋ በዓለም ከተደረጉ አስከፊ ጭፍጨፋዎች መዝገብ የሚባል ነገር ካለ ቢገባ ምክንያታዊ ይሆናል፡፡ ወይንም ደግሞ ከደርግ ጋር የተደረገውና በሁለቱም ወገን በርካታ ኢትዮጵያውያንን የጨረሰው የእርስ በእርስ ጦርነትን አስከፊነት ዓለም እንዲማርበት ቢደረግ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ ቢያንስ ኢትዮጵያውያንም ሌላው ዓለምም ይማርበት ይሆናል፡፡

ደደቢት ምን ባይ ነች በዓለም ቅርስነት የምትመዘገበው? እንዲያው ፈረንጆቹን ‹‹ደደቢትን በዓለም ቅርስነት መዝግቡልን!›› ሲባሉ ምንድን ነው የሚሰማቸው? መቼስ ፈርዶብን በእነሱ ምክንያት ኢትዮጵያውያን ጅሎች ናቸው አይደለም የምንባለው? ሌላውን ነገር ለብቻቸው፤ ስድቡን ግን አብረን እንጋተዋለን፡፡ አይ አገር የመጋራት እዳው! ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር አይደለም የሚባለው?

እነዚህ ሰዎች በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ መለስ ዜናዊ የተቀመጡበት ባርጩማ፣ አልኮል የጠጡበት መለኪያ፣ የለበሱት ፒጃማ….በዚህ ከቀጠለም ሚስታቸው (አዜብ) ሳይቀሩ በዓለም ቅርስነት ይመዝገቡልን ብለው ወደ ዩኒስኮ መንከራተታቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ጋሻጃግሬም ይመዝገብ የሚል ድርጅታዊ ውሳኔ ከተላለፈ ደግሞ ለሰውዬው ቀኝ እጅ ሆነው ህዝብ ሲያስበዘብዙ የኖሩት እነ በረከት፣ አባዱላ፣ ሽፈራው ሽጉጡ….በቁማቸው የፖለቲካ ሉሲዎች መሆናቸው ነው፡፡ አይጣልኮነው!

እኔ በበኩሌ ከደደቢት ይልቅ ራሱ ህወሓት በ‹‹ቅርስነት›› ባይሆን ባንዳች አስገራሚ መዝገብ ላይ ቢሰፍር ምክንያታዊ ነው ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በዓለም ገዥ ሆኖ ገንጣይነቱን አንጠልጥሎ የሚዞር አስገራሚ ቡድን ህወሓት ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ገዥ ሆኖ ተገንጣይ ዓለም አይታ አታውቅም ነበር፡፡ አሁን ግን ጉዱ ህወሓት አለላት፡፡ በመሆኑም አንድ ቀን ትውልድ አፉን ይዞ ይስቅበት ዘንድ በአንዳች አስገራሚ መዝገብ ጎላ ብሎ ቢጻፍ ክፋት የለውም፡፡

እስከዛው ግን እነ አዜብ የስራ ሂደት ባለቤት ተቋቁሞላቸው በዓለም ቅርስነት የሚመዘገቡበት ሁኔታ እንዲመቻች አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እየጠየቅን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ያለ አንዳች ተቃውሞ! ያለ አንዳች ድምጽ ታቅቦ! በቃ የባለራዩ ሚስት አዜብ መስፍን በቅርስነት ይመዝገቡ! ከተጃጃሉና ካሰደቡን አይቀር እስከዚህ ድረስ ነው እንጅ!

Image
ወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተከሰተውን አለመተማመን ለመቆጣጠር በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀመረ::
የወያኔ ተባባሪ ባለስልጣናት በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ላይ አንሳተፍም ሲሉ አማረሩ ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
የደህንነት አባላት ለጸረ ሰላም ሃይሎች እና ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ በሃላፊው ተወንጅለዋል::

የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ ከሃገሪቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በማበር አደጋ ሊፈጥር ይችላል ሲል መፈራቱ እንዲሁም ሰራዊቱን እየከዱ የሚሄዱ መበራከታቸው አለመተማመኑን ከማስፋቱም በላይ በሕወሓት የጦር እና ደህንነት ክፍሎች ውስጥ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል ሲሉ ውስጥ አውቂዎች ይናገራሉ::ክዚህ ቀደም ተሞክሮ እንዳልተሳካ እና አሁንም ከባለፈው አካሄድ እና ግምገማ በተሻለ መልኩ በወያኔ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ አዳዲስ የሆኑ ውስጣዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ በሰራዊቱ መካከል እየተከሰተ ያለውን አለመተማመን ለመቆጣጠር የሚረዱ ግምግናዎች እና የማጣሪያ ስብሰባዎች በስፋት መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በፖሊስ ክፍሉ ውስጥ በተለይ በቡድን የሚያሴሩ ሰዎች አሉ እየተባለ ስለሚነገር የወያኔ አንድ ብሄር ሰዎችን በስፋት በመመደብ እንዲሁም ከዚህ ቀደም እንደተደረገው የቢሮ ሰራተኛውን ከደህንነት ቢሮ በሚመደቡ የሕወሓት ደህንነቶች ለመተካት የታቀደ ሲሆን ቀሪውን ከቢሮ ውጭ የሚሰራውን የፖሊስ አካል ለመቆጣጠር አዲስ ሃይል እንደሚመደብ ታውቋል።

የወያኔ ተባባሪ ባለስልጣናት በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ባለመሳተፋቸው ማማረራቸው ተሰምቷል በሃገሪቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መንግስት እንቅስቃሴ ውስጥ ከወያኔ ባለስልጣናት ውጪ ለበታች ተከታይ ባለስልጣናት ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደቆመ ሲታወቅ ማንኛውም ሃገራዊ ጉዳይ አልቆ እና በአፈጻጸም ደረጃ ላይ ሆኖ እንደማንኛውም ሰራተኛ እንደሚሰሙ ባለስልጣኖቹ በመናገር ላይ መሆናቸው ታውቋል ። በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ግምገማ የደህንነት አባላት መረጃዎችን በግል ጥቅም በመለወጥ አሳልፋቹ እየሸጣችሁ ናቸው በሚል መገምገማቸውን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።እንደ ምንጮቹ ከሆነ መረጃን ያለምንም ርሕራሔ መረጃው በአምስት ደቂቃ ውስጥ ጠላት እጅ ገብቶ ያገኘነው ነው ሲሉ አንድ የደህንነት ሹም ተናግረዋል።በዚህ ግምገማ የተከፉት የደህንነት አባላት በመንግስት ባለስልጣናቱ እየተናጡ ቢወረፉም ዝምታን መርጠዋል።

ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን ወደ እውነት ያመጡ ህጎች በኢትዮጵያ አሉ የሚለው ወያኔ ህዝቦች ግን በተግባር ተጠቃሚ ሲሆኑ አላየንም::ህጎቹ በተግባር ይዋሉ ይህንን ህጎች በመመሪያ በደብዳቤ እና በስልክ የሚቀይሩ የሚደፈጥጡ በጥቅም የሚሸጡ የሚረጋግጡ የሚለውጡ ከየወንበራቸው ተሽቀንጥረው ይጣሉ:: የቀን ተቀን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ሂደት ውስጥ እጃቸውን እያጠለቁ ፍትህን የሚያዛቡ አስተዳደራዊ በደሎችን የሚፈጽሙ ባለስልጣናት የህዝብን ማህበራዊ ህይወቶች ከማፋለሳቸውም በላይ ከቀድሞው በባሰ መልኩ ፖለቲካው እንዲጭበረበር ኢኮኖሚው እንዲደቅ ሃገር በብድር እንድትዘፈቅ ህዝብ እንዲደኽይ ከባዱን ሚና እየተጫወቱ ነው::

ለዘላቂ ልማት እንሰራለን በሚል ስርኣት ውስጥ የመሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች በጊዜያዊነት መኖር እና እንደመነገጃ መጠቀም ህዝብን አገለግላለሁ ሳይሆን አጭበረብራለሁ እንደማለት ይቆጠራል:: የወያኔ ስርኣት ባለስልጣናት በፍርሃት ተውጠው በጠበንጃ ሃይል በሚኖሩባት በዚች ኢትዮጵያችን የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አሁንም እጅግ መልስ የሚያሻቸው ጉዳዮች ናቸው::ዜጎች በሃገራቸው እንዳይኮሩ በመኖር ደህንነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ እየተደረገ ስለሆነ ይህ ደሞ ወያኔ የያዘውን ስልጣን ላለመነጠቅ የሚሰራው ፖለቲካዊ ደባ ውጤት መሆኑ እሙን ነው::

ህዝቦች ህግ እየጸደ ህግ እየተሽሞነሞነ እና እየተብለጨለጨ ቢቀመጥ ምንም የሚጠቅማቸው ነገር እንደሌለ መታወቅ ያለበት ሲሆ አንድ ህዝብ ባላረቀቀ ባልተወያየበት እና ባላጸደቀው ህግ እየተገዛ ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን ይቻላል??? መተማመን እና የዜግነት ኩራቱን በሚሰብሩ ባለስልጣናት እየተሰበረበት ያለ ህዝብ ፍትህን እና አስተዳደራዊ እንዲሁም አገልግሎቶችን በተግባል ለማየት እና ለመጨበጥ አልቻለም:: ለተበደለና ፍትሕ ላጣ ዜጋ፣ መልካም አስተዳደር አጥቶ ለሚንገላታ ዜጋ ፍትሕና መልካም አስተዳደር እንዲኖር በአንቀጽ ተደንግጓል እያልን ብናወራ ዋጋ የለውም::

ህዝብ ባለው ስርኣት ላይ እምነት የለውም:; ይህ ደግሞ ራሱ ስርኣቱ ያረጋገጠው ነገር ነው የስርኣቱ ታጣቂ ሃይሎች በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚያደርሱትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት እያዩ በሃገሪቱ ህግ የለም እኔም ነገ እደበደባለሁ እታሰራለሁ ንብረቴን እነጠቃለሁ መብቴን እነፍርጋለሁ እጠቃልሁ እገደዳለሁ እሰደዳለሁ እገደላለሁ በሚል በስርኣቱ ላይ ያላቸው እምነት የተሟጠጠ ከመሆኑም በላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሃገር የመውጣት ንብረትን እና ሃብትን የማሸሽ ተግባር ላይ በመሰማራት በዜግነት አለመተማመን እንዲፈጠር በሩን በርግዶ ከፍቷል ይህ ደሞ ህጎች በተግባር ህዝብን አለማገልገላቸው እና በባለስልጣናት የመደፍጠጣቸው ውጤት ነው::

በተግባር ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት የተነሳ ማንም የለም::ስርኣቱም በጥቅመኞች የሚመራ ህዝቡም ላላወጣው ህግ በዝምታ ደንታቢስነቱን እየገለጸ ነው; ፍትህን እና መልካም አስተዳደርን የሚጥስና የሚያደናቅፍ የስርኣቱ ባለሥልጣን፣ ዜጋም ሆነ ግለሰብ፣ በማስረጃ ሲታይና ሲረጋገጥ ዕርምጃ ለመውሰድ ሕግ ፊት ለማቅረብ ምንም አይነት የተሰራ ስራ ካለመኖሩም በላይ በባሰ መልኩ በይፋ ህጎች ሲደፈጠጡ እያየን ነው:: ባለሥልጣንም ሆነ ባለ ሀብት፣ ታዋቂም ይሁን ተራ ዜጋ፣ ከፈለገው ብሔር ብሔረሰብ ይምጣ፣ የፈለገውን ሃይማኖት የሚከተል ይሁን፣ የጾታና የዕድሜ ልዩነት ሳይኖር ተቃዋሚም ይሁን ደጋፊ ሁሉም ሕግ ፊት፣ ፍትሕ ፊት፣ መልካም አስተዳደር ፊት እኩል መሆኑን አምነን በተግባር ለማዋል ቁርጠኝነት በፍጹም የለም:: ፍትህ እና መልካም አስተዳደር እንዴት ሊረጋገጡ ይችላሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየተጓዝን ነው ጥያቄያችን ;ስለዚህ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል::የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ እትዮጵያ ውስጥ ወያኔን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ጎራ ጥያቄው የስልጣን እና የአገዛዝ ሩጫ ነው::የእኛ የዜጎች ጥያቄ ግን ፍትህ መልካም አስተዳደር የአገልግሎት አቅርቦት እና ሰላም ነው::ይህንን ለማግኘት በጃችን ያለውን ነጻነት ለመቀዳጀት ከትግሉ ያልተቀላቀላችሁ እንድትቀላቀሉ ያስፈልጋል።

ሕያው የሆነው የኢትዮጽያ ታሪክ በተገቢው መንገድ እንዳስቀመጠው የአማራው ሕብረተሰብ ለአያሌ ሺህ ዘመናት የኢትዮጽያን ሉዓላዊነት ከውጭ ተስፋፊዎች በመከላከል ሃገራችን ክብሯን እንደጠበቀች በነጻነት ደምቃ በአንድነቷ ኮርታ ከጥቁርዓለም ውስጥ ብቸኛ ልዋላዊ የግዛት አንድነት ያላት የራሷ ቋንቋና ፊደላት ባለቤት የሆነች ታላቅ ሃገር ትሆን ዘንድ የአማራው ተወላጅ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን መስፈሪያ የሌለው ዋጋ ከፍሎ ሃገሩን በነጻነት ቢያኖርም በየጊዜው አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ያባረራቸው ቅኝ ገዠ ወራሪዎችና የአድህሮት ሃይላት ሃገር በቀል የእናት ጡት ነካሽ ባንዳ ተላላኪዎችን በማደራጀትና በማስታጠቅ ታፍሮና ተከብሮ የኖረውን ሉዓላዊ ነፃነቷን ሊፈነጩበትና ነባር
አንድነቷን አላልተው ሕልውናዋን ሙሉ በሙሉ በደላሎቻቸው ቁጥጥር ስር ለማድረግና ነባር ሆኖ የቆየውን ሃገራዊ ማንንነት ለመበረዝና ለማውደም የሚያደርጉትን የተቀነባበረ ሴራ በአስተማማኝ መንገድ ለማሳካት ኢትዮጽያዊነትን አንቆ አሻፈረኝ ያለውን የአማራውን ሕዝብ ስልታዊ በሆነ መንገድ አዳክሞ ለማጥፋት ላለፉት 100 አመታት ሲደረግ የነበረው ሴራ በዘመነ ወያኔ ተሳክቶ አማራው ከስልጣንና ከወታደራዊ አመራር ሙሉ በሙሉ በማግለል ከምሁር እስከ ቀን ሰራተኛው ከነጋዴ እስከ ገበሬው ሁሉን ባደረሰ መልኩ የበቀል ሰይፍ ተመዞበት በጅምላ ኢኮኖሚያዊ ሃይሉም ተመቶ ጥገኛና ስደተኛ የማድረጉ ወያኔያዊ ስልት ተግባራዊ ከሆነበት ባለፉት 22 አመታት ውስጥ በአማራው ህዝብ ላይ የተካሄደው ጥቃት ከማንም የተሰወረ አይደለም። የህወሐት ወያኔ የጥቃት ሠይፍ ከተመዘዘበት ከደደቢት እስከ ምንሊክ ቤተ መንግስት የተቀላው የአማራው ተወላጅ አንገት ቤቱ ይቁጠረው። በጥላቻ ተወልዶ በበቀል ያደገው ይህው እኩይ የዘረኛ መንጋ ከመነሻው ይዞ የተነሳውን የጸረ አማራነት ፖሊሲ ለማሳካት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሲያካሂድ የኖረውን የዘር ማጽዳት ተግባር ስልታዊና ዝግመታዊ በሆነ መልኩ በመለወጥ በአማራው ህዝብ ላይ ፈረንጆች (Systematic Genocide) እንደሚሉት የአማራውን ሕዝብ ከሚኖርበት የተለያዩ ክልሎች በማፈናቀል ሐብትና ንብረቱን በማሳጣት ቤተሰቡን በትኖ በረሀብ እርዛት በድንቁርና በጎዳና አዳሪነት ኑሮው እንዲገፋ በማድረግ ከማንነቱ እስከ ወዲያኛው ተቆራርጦ እንዲኖር ለማድረግ በቅርቡ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳና በቤኒሻንጉል እንዲሁም ሰሞኑን በምዕራብ ሸዋ በሚኖሩ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ ድርጊት እንዲገታ በአማራነታችን ተሰባስበን ትግሉን ለማገዝ ቁርጠኛ አቋም ላይ ለመድረስ እንድንችል አብይ ምክንያት በመሆኑ ይህን ንቅናቄ ለመመስረት ሳንወድ በግድ ተገፍተን በማንነታችን ዙሪያ ለመሰባሰብ አስገድዶናል።
ይህ በአማራው ሕዝብ ላይ በተከታታይ በመፈጸም ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአንድ ቦታ መግታትና መቆም ካልቻለ አሁን በያዘው የበቀል ፍጥነት ከቀጠለ ውጤቱ አስከፊና ሊገመት ከሚችለው በላይ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፤ ስለሆነም ሕወሐት/ወያኔ የአማራውን ሕዝብ ለማጥፋት የመዘዘው የጥፋት ሰይፍ ያለ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በተዓምር ወደ አፎቱ ስለማይመለስ በዐማራው ትግዕስትና ሆደ mሰፊነት ወያኔ ያቀደው የዘር ማጥፋት ሊገታ እንደማይችል በመረዳት የአማራው ነገድ ወጣቶች በመሰባሰብ በማንነታችንና በእናት ሃገራችን ላይ የተቃጣውን አደጋ ባለን አቅም ለመከላከል ባለብን ትውልዳዊና ሃገራዊ ግዴታ በንቅናቄያችን ዙሪያ ወጣቱ በመሰባሰብ ትግሉን በማገዝ ታሪካዊ ሃለፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።
የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የትኩረት አቅጣጫው በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ፕሮግራም የሠፈረውን በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ተነጥቀው ለተፈናቀሉ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ዕርዳታ ማሰባሰብ፣ድምፅ አልባ እና ባገሩ ባይተዋር ለሆነው የዐማራ ነገድ ድምፅ መሆን የዐማራውን ሁለንተናዊ ዐቅም በመገንባት ዐማራው በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይዎት ውስጥ ተገቢ ቦታውን እንዲይዝ ለማድርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራው ድርጅት በሚያደርገው ሁሉአቀፍ እንቅስቃሴ የዐማራው ወጣት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ከመወጣት ባሻገር የዐማራውን ወጣት በዘመኑ የብዙኃን መገናኛዎች በመድረስ ትውልድና አገር አድን ሚናውን እንዲወጣ የማደራጀትና የማንቃት
ሥራዎችን መሥራት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለመላው የዐማራ ነገድ ተወላጆች የምናስተላልፈው መልዕክት፣ አባቶቻችን ያቆዩንን ነፃነት፣አንድነትና
ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው ዐማራው ተደራጅቶ በአውራ ጠላትነት ፈርጀው ፣ፈጽሞ ሊያጠፉት ከተሰለፉት ኃይሎች በአቻነት ሲቆም ብቻ ነው፡፡ ድር ሲያብር አንበሣ እንደሚያስር ሁሉ፣ የእኛም መደራጀት በማንነታችን ላይ የተከፈተውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ተግባር ፈጽሞ በማስቆም የኢትዮጵያን ትንሣዔ የሚያረጋግጥ ስለሆነ የዐማራው ወጣት ይህን ንቅናቄ በመቀላቀል ትውልዳዊ ኃላፊነታችን በክብር እንድንወጣ የድረሱልን ጥሪ በሚያሰማው የዐማራ ነገድ ስም ጥሪአችን እናቀርባለን፡፡ እኛም እንደ አባቶቻችን ታሪክ ሠሪ እንሁን!
አማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!
ሞረሽ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ ግንቦት ፳፰፤ ፪ሺ፭ ዓ/ም

ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ የጀመርነው የጋራ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

በ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሠጠ መግለጫ፤

ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን የመጀመሪያ ዙር ፕሮግራም አጠናቆ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲሸጋገር ከሁሉ በማስቀደም የአንደኛው ዙር ዕቅዳችን ተግባራት ክንዋኔ ከዓላማችን ጎን ቆማችሁ በተለያየ መንገድ ለደገፋችሁን በአገር ቤትና በውጪ አገር ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን፣ በአንጻሩ ዕቅዳችን ከዳር እንዳይደርስ ህገመንግስታዊ መብታችንን በመጨፍለቅ ጉዞኣችንን ለማደናቀፍ የተቻላችሁን ህገወጥ የቢሮክራሲ መሰናክልና ለኢትዮጵያዊ ሠላማዊ ዜጋ ቀርቶ ለጠላት የማይገባ ኃይል በመጠቀም የመብት አፈና ለፈጸማችሁ የመንግሥት አካላት ሁሉ ወደ ኅሊናችሁ እንድትመለሱ ጥሪ በማቅረብ ነው፡፡ በተጨማሪ ለሁሉም ወገን የያዝነው ትግል የአገርና የህዝብ፣ተጠቃሚውም ሁላችንም/ሁሉም ዜጎች/ና የሁላችንም የጋራ አገራችን፣ለጉዞኣችን የመረጥነው መንገድ ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣መጓጓዣችን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም በማረጋገጥ ነው፡፡

ትብብራችን የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር፣በእኛ በኩል ከፊት ቆመን ትግሉን ለመምራት ያለንን ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ለዚህም የገባነውን ቃል በማደስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ‹‹በየትም የዓለማችን ክፍል አምባገነንነት የህዝቦችን የተባበረ የዲሞክራሲ ጥያቄ በኃይል አፍኖ በጨቋኝነት የዘለቀበት ታሪክ አልተመዘገበም›› ማለታችንን በማስታወስ ነው፡፡

ይህ ዕቅድ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ እንደመሆኑ ዓላማችንም የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ሚናችንም የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው፡፡ ደጋግመን እንደገለጽነው ነጻነት በሌለበት ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው፡፡

በመሆኑም የዚህ ዙር ዓላማችንም ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የጀመርነውን እንቅስቃሴ አጠናክሮና አስፍቶ በመቀጠል ለነጻ ፣ፍትሃዊ፣ተኣማኒ፣አሳታፊ….በአጠቃላይም ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ለህዝብ ተደራሽ በመሆን በህዝብ (የተለያዩ የህዝብ ክፍሎችን፣ አደረጃጀቶችንና ዜጎችን በማካተት) የነቃ ተሳትፎ ተጽዕኖ በማሳረፍ በምርጫ ሂደቱና አተገባበሩ ላይ ያነሳናቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ ማድረግና ከዚህ ጎን ለጎን በቀጣዩ ምርጫ (2007) ተቃውሞ ጎራው በአጠቃላይ የትብብሩ አባላት በተለይ ድምጽ እንዳይሻሙ /የመራጩ ህዝብ ድምጽ እንዳይከፋፈል/ የሚያስችል ስልት በመቀየስ ከመራጩ ህዝብ ማድረስ ነው፡፡

በዚህ ላይ በመመስረት ትብብሩ በዚህ ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት አካቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት ፤በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡
4.
አስተባባሪ ኮሚቴው ተግባራቱን በጊዜ ሠለዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት አጽድቋል፡፡

እዚህ ላይ ይህን ዕቅድ ስናወጣ መንግሥት/ጠቅላይ ሚ/ሩ/ ከቅርብ ቀን በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ‹‹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግሥትን መገዳደር አይችሉም›› የሚል ኃሳብ ያዘለ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ማድመጣችንን፤ይህ መልዕክት የማደናገሪያና ማደናበሪያ ፕሮፖጋንዳ ስልትም ይሁን የተቃዋሚዎችን ዓላማና የመኖር ትርጉም የመጨፍለቅ ግልጽ መልዕክት ቢሆን እኛ የተያያዝነው ህገመንግሥታዊ መብታችንና የዜግነት ክብራችንን የማስከበር ሠላማዊና ህጋዊ ትግል በመሆኑ ማስፈራሪያውም ሆነ ማስጠንቀቂያው ህገመንግሥታዊ አይደለምና ህገወጥ ነው አይመለከተንም፤በሚል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

በመጨረሻም ለተያያዝነው ሠላማዊና ህገመንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል፡-
1ኛ/ የጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት በሠላማዊ ትግል አስገድደን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ራሱን እንዲያዘጋጅ የነቃ ተሳትፎ በማድረግና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማቅረብ ከጎናችን እንድትቆሙ፣ በተለይ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ትብብሩ ለትግሉ ተገቢውን አቅም እንዲገነባ በጀቱን ለመሸፈን ወቅታዊ የፋይናንስ ድጋፍ እንድታደርጉ፤
2ኛ/ በአገራችን የሚደረጉ ምርጫዎች ዲሞክራሲያዊ እንዲሆኑና ከማንኛውም ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ ለማስፈጸም በህገ መንግሥቱ ሥልጣኑ የተሠጣችሁ፣ ኃላፊነቱ የተጣለባችሁ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈጻሚ ባለሥልጣናት ከገዢው ፓርቲ ወገኝተኝነት እንድትላቀቁና እንደ ተቋሙ መሪና ዜጋ ራሳችሁን ከትውልድ ባለዕዳነትና ከታሪክ ተጠያቂነትና ተወቃሽነት ነጻ እንድታወጡ፤
3ኛ/ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም የመግባቢ ሰነዱና የጥናቱ ሪፖርት ባለቤቶች የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሚጠይቀውና የተያያዝነው ትግል ከፓርቲ መሪዎች የግል ፍላጎትና ከፓርቲ ጥቅም በእጅጉ የላቀ በመሆኑ ለአገርና ህዝብ ቅድሚያ በመስጠት ተቃዋሚ ጎራው ባለፉት ምርጫዎች ሁሉ በመከፋፈልና የህዝብን ድምጽ በመበታተን ሚናው ከምርጫ አጃቢነት ያላለፈ በመሆኑ ይህን ‹‹በቃ›› የማለት ወቅቱ ነገ ሳይሆን ዛሬ ስለሆነ ከ‹‹እናቴ መቀነት ጠለፈኝ›› ምክንያት ወጥታችሁ ለዚህ ዓላማ በጋራ ለመቆም ትብብሩን ያለቅድመ ሁኔታ እንዲቀላቀሉ፤
4ኛ/ገዢው ፓርቲ/መንግሥት ከተያያዘው በአፈና ‹‹ለብቻ በመሮጥ›› አሸናፊ ነኝ በሚል ሥላጣን የማስጠበቅ ኢህገመንግሥታዊ አካሄድ ታርሞ የአገርና ህዝብ ጉዳይ ከሥልጣን ማስጠበቅ በላይና የኃይል እርምጃና አፈና ሥልጣን የማራዘም እንጂ የህዝብን የለውጥ ፍላጎትም ሆነ ለውጥን የማስቀረት አቅምና ኃይል የሌለው መሆኑን ከዓለም ታሪክና ከቅርብ ጊዜ የጎረቤት አገሮች ተሞክሮ እንዲማርና ራሱን ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲያዘጋጅ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ያለመስዋዕትነት ድል የለም፤ የጋራ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ታህሳስ 17/2007 ዓ.ም! አበባ!

የፌድራል ጉዳዪች ሚኒስትር ከነሰራተኞቹ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሊሰማሩ ነው፡፡ የዶ.ር ሽፈራውን ድምጽ ይዘናል

http://goo.gl/kYqE7x
http://goo.gl/kYqE7x

በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ (ድምጽ ጥራቱ ዝቅተኛ)
http://goo.gl/AslZyM
http://goo.gl/AslZyM

Image

Image
በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፎች ይደረጋሉ :: የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ትብብሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብሩን በህዳር ወር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩ ደግሞ ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን ተገልጹዋል፡፡

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ፤ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳርና በአዳማ ደግሞ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) በመግለጫው ወቅት ተናግረዋል፡፡

‹‹የመግባቢያ ሰነዳችንና የጥናት ሪፖርታችንን እንዲሁም ከመጀመሪያው ዙር ያገኘውን ተሞክሮ በሠረት በማድረግ ይህን የሁለተኛ ዙር የሁለት ወር ዕቅድ (ከታህሳስ 16 እስከ የካቲት 15 /2007) አውጥቶ በቀዳሚነት ለዋነኛ ባለቤቶቹና ፈጻሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲያቀርብ እንደመጀመሪያው ዙር ከጎኑ እንደሚቆሙ ሙሉ እምነት በማሳደር ነው›› ያለው መግለጫው፣ በትብብሩ በኩል በአመራር ከፊት ቆመው ትግሉን ለመምራት ዝግጁነትና ቁርጠኝነት መኖሩን አስረድተዋል፡፡

‹‹የያዝነው የትግል መንገድ ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ ብቻና ብቻ፣ መጓጓዣችን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፣ መድረሻችን መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ እንዲሁም በጉዞኣችን ላይ የቱንም ያህል አረመኔያዊ የኃይል እርምጃ ይወሰድብን፣ ትግሉ የቱንም ዓይነት ዋጋና መስዋዕትነት ይጠይቅ ከጅምሩ ያለመስዋዕትነት ድል የለም ብለን ተነስተናልና ከያዝነው ዓላማ ኢንች የማናፈገፍግና ለቃላችን በጽናት የምንቆም መሆኑን ዳግም እናረጋግጣለን›› ብሏል ትብብሩ በመግለጫው፡፡

እቅዱ የመጀመሪያው ዙር ቀጣይ መሆኑን ያተተው የትብብሩ መግለጫ፣ ‹‹ዓላማችን የምርጫ ሁኔታዎች ባልተሟሉበትና የመራጩ ህዝብ ነጻነት በሌለበት ስለምርጫ መናገር አስቸጋሪ ነው፣ እነዚህ በሌሉበት አማራጭ የምርጫ ኃሳቦች በህዝብ ውስጥ ሊንሸራሸሩም ሆነ አማራጭ ኃሳባችንን ከህዝብ ማድረስ አይቻልም፣ ሚናችንም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አማራጭ ሆኖ መቅረብ ሣይሆን የህወኃት/ኢህአዴግ አጃቢነትና የሀገር ሃብት በአላስፈላጊ መንገድ የማባከን ሥራ ተባባሪነት የዘለለ አይሆንም ከሚል የመነጨ ነው›› ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡ ነጻነት በሌለበት ተጨባጭ ሁኔታ ምርጫ ቧልት ነው ሲልም አክሏል መግለጫው፡፡

ሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ዕቅዱ እንደባለፈው ተደጋጋፊ፣ ተመጋጋቢና ተከታታይ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና በሥራቸው አስራ አራት ዝርዝር ተግባራት ማካተቱም ተመልክቷል፡፡ እነዚህ በትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ጥልቅና ዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቁ ዋና ዋና ተግባራትም፡-
1. የአባላትና የትብብሩ አቅም ግንባታ፡- የትብብሩን አባላት አብሮነት ማጠናከርና የጋራ ዓላማውን የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፤
2. የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፡- የህዝብ ተደራሽነት ማስፋትና ዓላማ ማስተዋወቅ፣
3. የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ማመቻቸት፡- በአዲስ አበባና የተመረጡ ከተሞች አራት የአዳራሽ/አደባባይ የህዝብ ውይይት፤ በአዲስ አበባና በተመረጡ አስራ አምስት የክልል ከተሞች በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፤ የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡

የትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ተግባራቱን በጊዜ ሠሌዳ በማስቀመጥ ለነዚህ ተግባራት ማስፈጸሚያ የብር 1,215, 000.00 (አንድ ሚሊየን ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ) በጀት ማጽደቁንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ትብብሩ ለያዘው ሠላማዊና ህገ-መንግሥታዊ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ሌሎች ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የተቃዋሚዎች አዳዲስ የትግል ስትራቴጂ የኢሕአዴግ ስጋት ሆኗል::

– ዲያስፖራውን በድሪቶ ወሬዎች መጥለፍ ስራችን ሊሆን ይገባል::ብለዋል – በደቡብ ሱዳን አሶሳን አስታኮ እየተፈጠረ ያለ ችግር መኖሩን አንስተው ተወያይተዋል:: – በአሶሳ የኦነግ ሰራዊት ነኝ ያለ ቡድን ካለቶክስ እጁን ሰቷል ሲሉ ተደምጠዋል:: – በድርጅታችን ቢዝነሶች ላይ የሚጠሩ ባይኮቶችን የሚያደናቅፉ የተቃዋሚ ዲያስፖራዎችን ከበፊቱ በበለጠ መልኩ መተባበር እና አስፈላጊውን እርዳታ ማድረግ እንዳለባቸው ተወያይተዋል::

Minilik Salsawi
ከፍተኛ የወያኔው ቱባ ባለስልጣናት እና የደህንነት ሃላፊዎች በመጪው የአገዛዝ ሂደታቸው ላይ ተገናኝተው መወያየታቸው ከውስጥ አዋቂ ምንጮች የተገኘ ዘገባ ጠቁሟል:: በአፍሪካ ጎዳና ቦሌ መስመር ከሚገኝ ለባለስልጣናት ብቻ ክፍት ከሆነ የጎልፍ መጫወቻ ክለብ ውስጥ ተጠራርተው የተሰበሰቡት ባለስልጣናቱ የተቃዋሚዎች አዳዲስ እና ስልታዊ ስትራቴጂ እንዳሳሰባቸው እና የትግል ስልቱ ስጋት እንደሆናቸው በውይይታቸው አስቀምጠዋል::

በኤርትራ በኩል ያለውን እንቅስቃሴ መምታት ያስፈልጋል አያስፈልግም በሚለው ዙሪያ የተነጋገሩ ቢሆንም ለጊዜው እሱ ይቆይ እና በአሁን ሰአት ስጋት የሆነው የተቃዋሚዎች አዳዲስ የትግል ስልት እና የዲያስፖራው ከስልቱ ጋር መቀናጀት ስለሆነ ይህንን በፍጥነት በፕሮፓጋዳ እና በተግባር እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል::በድርጅታን ውስጥ የተሰገሰጉትን ተመሳስለው መረጃ የሚያቀብሉ እና የተቃዋሚውን እንቅስቃሴ የሚያበረታቱት የሚተረጠሩ ሁሉ ክትትል እየተደረገባቸው እንዲያዙ በሚለው የተስማሙ ሲሆን ከምርጫው በፊት እንደሁኔታው ታይቶ በሙስና እና የሃገርን ሰነድ በማባከን እንዲከሰሱ እንዲሁም አሸባሪ እየተባሉ የሚከሰሱ ሰዎች እንዲቀንሱ እና በሌላ የወንጀል ህግ አንቀጽ እንዲከሰሱ ያሉ ሲሆን አሸባሪ እያሉ መክሰስ ተቃውሞ እንዳበረከተ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ የአሸባሪነት ክስ እንዲቀርብ ተነጋግረዋል::የሃገሪት ፖሊስ በተለይ ፌዴራል ፖሊስ ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ጥቅማጥቅም እና መብቶች እንዲሰጡት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ላይ እንዳይላላ ያደርገዋል ሲሉ ተደምጠዋል::

በደቡብ ሱዳን በኩል አንዳንድ ሃይሎች እየተፈጠሩ ስለሆነ ከመበራከታቸው እና ከመጠናከራቸው በፊት በአከባቢው ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት እና ባለፉት ወራቶች በቆረጣ እና በመረጃ ስብስብ የታገዘ እርምጃ በኦነግ ታጣቂዎች ላይ እንደተወሰደ ሳይጠቅሱ አላለፉም::የኤርትራ ፓስፖርት ይዘው በኡጋንዳ በማድርግ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው በመግባት አሶሳ መስመር ላይ ስለላ ሲያካሂዱ የነበሩ ግለሰቦች የተያዙ ሲሆን ወርቁ የተባለ የኦነግ አባል የሆነ እና የዐኦ ዳውድ የቀድሞ ሹፌር ሊያመልጥ እንደቻለ ታውቋል::እጁን የሰጠው ቡድን ከኤርትራ ተደራጅቶ ይምጣ አሊያም እዛው ደቡብ ሱዳን ውስጥ ይደራጅ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን የደህንነት ሃላፊዎቹ አስረድተዋል::

ዲያስፖራው አሁንም የኢሕአዴግ የእግር እሳት እንደሆነ በሚያስታውቅ ሁኔታ ጥልቅ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ዲያስፖራው በብዛት የድህረገጽ ተጠዋሚ ስለሆነ በድሪቶ ወሬዎች መጥለፍ ዋና ስራ እንዲሁም በውጪ የሚገኙ የተቃዋሚ አባላትን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም በመደለል አስፈላጊ መረጃ ማሰባሰብ ሲሉ ውጪ አግር በሚገኙ የድርጅታችን የንግድ ስራዎች ላይ እንከን እንዳይፈጠር ባይኮት እንዳይጠራ አስታውጾ እያደረጉ እና ለሚተባበሩን የተቃዋሚ ዲያስፖራዎች አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ማድረግ አለብን ሲሉ ተደምጠዋል::በማለት የውስጥ አዋቂ ምንጮች መረጃቸውን አድርሰውኛል::

አስደንጋጭ መረጃከአስገደ ገ/ስላሴ
35 ሺ ኢትዮዽያውያን እስረኞች በኢርትራ ሳህል በረሃ ዘመኑ ያለፈው የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ::
የሻዕብያ የሽፍታ መንግስት በ1983 ዓ/ም ከደርግ ጋር በነበረ ጦርነት የተማረኩ ወጣት ወታደሮች ስቪል የመንግስት ሰራኞች በዛን ጊዜ ኢርትራ ላይ ይኖሩ የነበሩ ወጣት ዜጎች በሙያ የተካኑና ለስራው ያስፈልጉኛል ብሎ በመለየት ከ 36 ሺ በላይ በሳህል በረሃዎች በዓፍዓበት በናቅፋ በሰሜን መሰራቅ ሳህል ወስዶ በሃይልና ከባድ ስራ ያሰራቸው ነበር::
በኢትዮ ኢርትትራ ጦርነት ዋዜማ በሁሉም የኢርትራ ከተሞች የነበሩ ስቪል ሕብረተሰብና በሙያቸው ጦርነቱ ከተጀመረ እስከ ሻዕብያ የተሸነፈበት የማረካቸው ወታደሮችና ምልሻዎች ከኢርትራ ዘልቆ ወደ ትግራይ እየገባ ከ1990 እስከ 2007 ዓ/ም ለ17 ዓመት ያህል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ የጎንደር ወጣቶች አፍሶ የወሰዳቸው::
በስራ አጥነት በድህነት በመልካም አስተዳደርና ነፃነት እጦት ወደ ሱዳን ስራ ፍለጋ ብሎም ወደ ሌላ ሃገር ለመሸጋገር የኦሮሞ የአማራ የትግራይ የጋንቤላ ወዘተ ሱዳን የገቡ የሻዕብያ ልዩ ሰላዮች ወደ ሱዳን ሰርገው በመግባት ከሚሰሩበት በረሃና ከተሞች በመጥለፍና በማፈን ወደ ወገኖቻቸው ሳህል አገቡዋቸው:: እነዚህ ግፍ ይፈፀምባቸው ያሉ ዜጎች ከ1983 ዓም እስከ ዛሬ በእሱር መልክ ተይዘው በሁሉም የሻዕቢያ አካባቢዎች በከባድ ስራ ተሰማርው ይሰሩ የነበሩ እስከ 60ሺ ይገመቱ እንደነበሩ የመረጃው ምንጮች ይናገራሉ:: አሁን ግን በሳሀል በረሃዎች በተጨባጭ የሚኖሩ 36ሺ ናቸው ይባላል ከዛም ሊበልጡ ይችላሉ የቀሩ ተገድለዋል፡፡
እነዚህ ዜጎች የሚሰሩትን ስራ በሳዋ በባርካ በሰሜን ምስራቅ ሳህል በዓፍዓበት በማይሕመት በአልጌን በናቅፋ በግዝግዝያ በከረን አካባቢና በሰሜን ባህር በፍልፍል ዓራቶ የሚባሉ ቦታዎችና በሌሎች ቦታዎች በተለያዩ ከባድ ስራዎች ያሰሩዋቸው ነበሩ በሚሰሩበት ጊዜ በከባድ ጥበቃ ነው:: ለሚደርሰው ግፍ የመቃወም ምልከት ያሳዩ ወገኖች በእሰረኞች ፊት ይረሸናሉ::
ሌላ አስገራሚ ነገር ደግሞ በኢትዮዽያ ሰላማዊ ትግል አይቻልም ኢህአደግ እሱ በመጣበት መንገድ በነፍጥ ነው የሚወገድ ብለው ከሻዕብያ ጋር ተጠግተው ከህወሓት ለሻዕብያ ከሞት ለማዳን ያደረገው ሎሌነት እነዚም ከህወሓት በባሰ መንገድ ሎሌ ሆኖው የኢሳያስ ቤተ መንገሰት የሚጠብቁ ኢሳያስ ተኩሱ ሲላቸው የሚተኩሱ ደፈጣ ተዋጊዎች በመቃወም ኢትዮዽያዊ ጥያቄ ያነሱ ሻዕብያ የሚጠረጥራቸው ኢርተራውያን ወደ ሱዳን በስደት የገቡ የቻድ የናይጀርያ ዜጎች ሳይቀሩ ከ35ሺ እሰረኞች ቀላቅለው የባርያ አገዛዝ ተቋዳሽ ናቸው:: የዚህ ሁሉ ሚስጢር ያወጡ ያሉ ከእሰረኞቹ አምለጠው ወደ ዓረብ ሃገር የገቡ ሰዎች ናቸው:: እስረኞቹ ከ 10 ዓመት በፊት መላው የኢርተራ የሻዕብያ ተቋማት የእረሻና የግድበ ስራዎች እሰከ ምሸግ መስራት የሚሰሩ ነበሩ:: ማምለጥ በመጀመራቸው ግን ወደ ሳህል አካባቢ እንዲሰበሰቡ ተደረጉ::
የሚሰሩት ስራ ሻዕብያ 30 ዓመት የተቀመጠበት የቀበሮ ጉድጓድ 180 ኪሎሚትር ርዘመት ያለው ምሸግ ማደስ ለቱሪዝም ተብሎ በአፍዓበት በናቅፋ ቤቶች መስራትና ማደስ በሰሜን ምሰራቅ ሳህል የሚገኙ ትላልቅና አነስተኛ ተፋሰሶች መገደብ የእረሻ ስራ መስራት በሳህል የሚገኘው የነ ኢሳያስ የመሬት ውሰጥ ቤተመንገስተ ማደስ:: ሻዕብያ ይጠቀምባቸው የነበረ መንገዶች ማደስ ስራ ይሰማራሉ::
በዜጎቻችን የሚፈፀም ግፍ ቀን ተሊት በጥበቃ ስር ናቸው:: በቂ መገብ ህከመና የላቸውም የማምለጥ አዝማሚያ ያሳዩ ዜጎች በሆነ መንገድ ይረሸናሉ:: ሆን ተብሎ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ እርሰ በራሳቸው እንዲፈፅሙ ይደረጋል:: በቂ ልበስ የላቸውም በከባድ ስራ በህመም በርሃብ ተመጣጣኝ ምገብ ባለማግኘታቸው የወደቁ እንደልገመኞች ተቆጥረው ይረሸናሉ::
በአጠቃላይ በጨለማ የሚኖሩ ተስፋ የቆረጡ መሆናቸው ይገለጣል:: ታድያ የኢህአደግ መንገሰተና የሱ መዋቅሮች የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የደህንነት ጀነራሎች የደህንነት ባለስልጣናትና ሰላየቹ ምን እያደጉ ናቸው:: ከ35ሺ በላይ ዜጎቹ በበረሃ በአንድ ሽፈታ ስርዓት ሲሰቃዩ 23 ዓመት ሙሉ ምን እያደረጉ ናቸው:: እንደእሰራኤል ያሉ መንገሰታት እኮ ዜጎቿ በሓማስ ታጋዮች ሲጠለፉ ከባድ ጦርነት ተካሄደ ነገር ግን ኢስራኤል ወታደር ጂልዓድ ሸሊም ነፃ ለማውጣት ኋላ ግን በኢስራኤልና ከሓማስ በተደረው ስምምነት ኢስራኤል 3ሺ የፈለስጢም እስረኞች እንድትፈታና በጂልዓድ ሸሊም በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል አማካይነት የእሰረኞች ልውውጥ ተደርጎ ነው ነገሩ የተፈታው::
የኢህአደግ መሪዎች ግን በአስር ሺ የሚቆጠሩ ዜጎቹ የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ደሮ የታፈነችባቸው አይመስሉም:: በቀላሉ እንኳ በምሽግ ያለው የሻዕብያ ሰራዊት በመተራመስ በ10ሺ የሚቆጠር ወታደር ማርኮ ተደራድሮ ማስወገድ ነበረበት:: በዚሁ የሻዕብያ ሽፍታ መንግስት ግፍ የኢርትራ ህዝብም ደስተኛ አይደለም::
ሌላ ይህ የሻዕብያ የሽፍታ መንግስት የሚፈፅመው ያለ ግፍ በዓለም መንግስታት በሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ኢህአደግ ተፅኖ ለማድረግ ይችል ነበር:: ነገር ግን ምኑም አይደለም የትግራይ ክልል መሪዎች በወልቃይት ወርቅ ሲለቅሙ ከ280 በላይ ወጣቶች ታፍሰው ሳህል ሲገቡ እያወቀ ስለእነሱ ሲጠየቅ ውሸት ነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያስፋፉት ወሬ ነው አሉ::
ሌላ በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለእነዚህ ዜጎች እንደአጀንዳ ይዘው አያነሱትም:: በመጨረሻ መላው የሃገራችን ህዝብ ሙሁራኖች ተማሪዎች በውጭ የምትገኙ ዜጎች ይህ በሻዕብያ የዜጎቻችን ይፈፅመው ያለው ግፍና የህወሓትት ኢህአደግ መሪዎች ለዜጎቻቸው አለመቆርቆር ተቃውሞ በማስነሳት ተፅእኖ ሊታደርጉ ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ:: በተጨማሪም ለተባበሩ መንግስታት ለሰብአዊ መብት ተሟጓቾች በዲፕሎማሲ ፅኖ በማድረግ ስለዜጎች እንስራ ሚስጢሩም መላው ዓለም ይወቀው::