የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የልደታ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሎ ለ32ኛ ጊዜ ለሓምሌ 22 ተቀጠረ::

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የልደታ ካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሎ ለ32ኛ ጊዜ ለሓምሌ 22 ተቀጠረ::

Minilik Salsawi በዛሬው እለት ከእስር ባልተፈቱ አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን በቦታው የጦማርያኑ ቤተሰቦች እና ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች በካንጋሮው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል::እንዲሁም በቅርቡ የተፈቱት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን ርእዮት አለሙን ጨምሮ በፍርድ ቤቱ ታድመዋል::ያልተፈቱት አራቱ ብሎገሮች በፍቃዱ;ናትናኤል:አጥናፍ እና አቤል ከእስር ቤት ሲነሱ በፍርድ ሂደቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ ጥቁር ካኒተራ ቢለብሱም ወደ ፍርድ ቤቱ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በሃይል እንዲቀይሩ እንደተደረገ ተሰምቷል::የካንጋሮው ችሎት በመሙላቱ እጅግ በርካታ ሰዎች ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቀምጠው የችሎቱን ውሳኔ ሲከታተሉ ነበር::

በዛሬውም ችሎት የዳኞች ማርፈድ የተለምደ ነው::አቃቢ ሕጎች በቦታው አልደረሱም:: የችሎት አስተባባሪዋ አቃቤ ህጎች ተደውሎላቸዋል ይመጣሉ::በማለት ስትናገር ተደምጧል::ፋይሉ በፍርድ ቤቱ ጠረጴዛ ላይ ቀርቦ ዳኞቹ በማርፈዳቸው የሚያየው አጥቶ ነበር::አቃቢ ሕጎች ከፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ተደውሎላቸው በቦታው ደርሰው ከካንጋሮው ፍርድ ቤት ተዋህደዋል::ዳኞች በቦታቸው ተሰይመው የምስክሮች ቃል በፅሁፍ አልተገለበጠም በሚል ሰበብ ለሰላሳ ሁለተኛ ጊዜ ለሃምሌ 22 ሲቀጠር ጦማሪ አጥናፍ ” ዛሬ ከታሰርን 450 ኛ ቀናችን ነው በቀጠሮዎች መራዘም ምክንያት ቤተሰቦቻችን እና ወዳጆቻችን እየተንገላቱ ስለሆነ ፍርድቤቱ ይሄንን ከግምት ያስገባልን። ” ሲል ለፍርድ ቤቱ ተናግርዋል::«ለ450 ቀን ያህል በእስር ቆይተናል። በመሆኑም አጭር ቀጠሮ በመስጠት ለብይን ልንቀጠር ይገባል» አጥናፍ ብርሃኔ ሲል «አጠር ያለ የ10 ቀን ቀጠሮ እንስጣችሁ» በማለት ዳኛው መልሶለታል::