የሰው መሳቂያ ሆናቹ አገራችንን የሰው መሳለቂያ አደረጋችሁ::የደህንነት ባለስልጣናቱ ተደብቀው ያዩ ነበር:: ምንሊክ ሳልሳዊ

ምንሊክ ሳልሳዊ :- እናት ሃገሬ በናንተ ስም መጠራቷ ለኔ ይሁን ሃገሩን ለሚወድ ሁሉ ትልቅ እፍረት ነው:: ስለ ዲፕሎማሲ እና እንግዳ አቀባበል መማር ያስፈልጋል እንዳይባል አሊያም ትምህርት ቤት እንዳይከፈት ይህ ጉዳይ የተለመደ የፕሮቶኮል ጉዳይ እና በየሚዲያው የሚታይ ነገር ነው:: እንኳን ባለስልጣን አይደለም ማንም ሚዲያ የሚከታተል ዜጋ ከአለባበስ ጀምሮ እስከ ስንብት ያለው ፕሮቶኮል ጠንቅቆ ያቃል::የወያኔ ባለስልታንት ጉዳይ ግን ግራ ያጋባል ሳይሆን ያሳፍራል::የሰው መሳቂያ ሆነው ሃገራችንን የሰው መሳለቂያ አደረጉብን::የኢትይኦፕያውያን የፖለቲካ ፕሮቶኮል በአለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ስፍራ የሚያሰጠው እና ለአፍሪካ ሃገሮች ሳይቀር ያስተማርነው ጉዳይ ነው::
Ethiopia .
የወያኔ ባለስልጣናት እንደበሶ በሁሉም ነገር ስለሚበጠበጡ የሚያደርጉትን አያውቁም:: የሚሰሩትን አያውቁም ልነሱ የኦባማ መምጣት እንደ ድል ቆጥረውት ከሆነ ፖለቲካ አያውቁም::ስለማያውቁም ነው እንደ አሽቃባኝ አሰፍስፈው ኦባማን ለመክበብ ተጎንብሰው ሲንደፋደፉ ነበር::ጉዳዩ የሚመለከተው ግርማ ብሩ እንኳን ቀና እንዲሉ ሲነግራቸው እና ሲነካካቸው ታይቷል::የኦባማ ጠባቂዎች ፎት አንሺ እንዲሁም የፕሮቶኮል ሃላፊዋ ሳትቀር የተለያየ አክሽኖችን በማሳየት ስነ ስርአቱን ለማስተካከል ሞክረዋል::ተምታቶባቸው ተደበላልቆባቸው ታይተዋል::የወያኔ የደህንነት ባለልስጣናት የነወዲ አድሃኖም እና ሬድዋን ጉንበሳን በቅርብ ርቀት ሆነው ይመለከቱ እንደነበር ታይቷል::ሕወሓት ሆዳም ባለስልጣኖቿን መሳቂያ አደረገቻቸው::ሕወሓት ሓገሬን መሳለቂያ አደረገች::የቀድሞ መንግስታት የነበራቸውን የፕሮቶኮል ስራ ሂደት ወያኔ 10% እንኳን የለውም:: ከአፍሪካ ሃገራት የፕሮቶኮል እንግዳ አቀባባል ሂደት እንኳን መማር አልቻሉም::የሩቁን ትተን እንኳል ትላንትና ኬንያ ባለስልጣኖች ኦባማን እንዴት እንደተቀበሉት መኮረጅ አለመቻላቸው የወያኔዎችን የውስጥ ጉዳይ አደባባይ ላይ አውጥቶታል::ውወያኔ በደንብ በስብሷል::
Kenya