ስለአመጋገብዎ ምን ያህል ይጠነቀቃሉ?

የዓለም የጤና ቀን በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ሚያዝያ ሰባት ቀን ይታሰባል። የዓለም የጤና ድርጅት የዘንድሮዉን የዓለም የጤና ቀን ያሰበዉ «የሚመገቡት ምግብ ምን ያህል ለጤና ተስማሚ ነዉ» በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርቶ ነዉ።