UTC 16:00 የዓለም ዜና 16.11.2014
የዓለም ዜና
አውስትራሊያ – ብሪስባን በተካሄደው እና ኹለት ቀናት በፈጀው የቡድን-20 የመሪዎችጉባኤ ላይ ተሳታፊዎቹ መሪዎች የዓለም አቀፉን ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ መወሰድ በሚገባቸው ርምጃዎች ላይ ተስማሙ። ፑቲን ጉባኤው ሳይጠናቀቅ እስከ ሩስያ ረዥም ጉዞ ነው የሚፈጀው በሚል ምክንያት ጉባኤውን ጥለው መሄዳቸውም ይፋ ሆኗል።
በቡድን 20 አባል ሃገራት ጉባኤ የዩክሬይን ቀውስን አስመልክቶ በደረሰባቸው ብርቱ ወቀሳ የተነሳ የሩስያው ፕሬዚዳንት ጉባኤው ሳይጠናቀቅ አቋረጥው ሊወጡ እንደሚችሉ ዛቱ። በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሃገራት የሚያኪያሂዱት ጉባኤ የሚጠናቀቀው በኹለተኛ ቀኑ እሁድ ነው።
የዩጋንዳ «ናሽናል ሬዚዝተንስ ሙቭመንት» ፓርቲ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒን እአአ ለ2016 ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በዕጩነት ለማቅረብ የያዘው ዕቅድ ብርቱ ክርክር አስነስቷል።
ኤቦላ ተሐዋሲ መስፋፋትን ለመግታት የሚደረገዉ ጥረት በተጠናከረበት በዚህ ወቅት ላይቤሪያ ዉስጥ በጀርመን የሕክምና እርዳታ ድርጅት አክሽን ሜዲዮር የተገነባዉ የኤቦላ ታማሚዎች ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ሙሉ ሥራዉን ጀመረ።
ብሩክታይት ጥጋቡ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የ «ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ» ድርጅት አጋር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ናት።
በሊቢያ የሚታየዉ የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አደገኛና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ስጋት ላይ ጥሎአል። ለዘመናት ሊቢያን በደቋሽ ክንዳቸዉ የገዙት የሊቢያዉ መሪ ሞአመር ጋዳፊ ከስልጣና ከተወገዱ ከሶስት ዓመት በኋላ ዛሬ የሚታየዉ የርስ በርስ ጦርነት ሀገሪቱን ወደ መንኮታኮት እያመራት መሆኑ ተመልክቶአል።
ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ እና በክልሎች በሚሰጠው አገልግሎቱ ላይ የሚታየው ጉድለት ተጠቃሚዎችን ቅር አሰኘ። በተለይ ተገልጋዮች በሞባይል ስልክ እና በኢንተርኔት መቆራረጥ እጅግ መማረራቸውን ከመግለጽ ወደኋላ አላሉም።
በቀድሞዋ ምሥራቅ ጀርመን ይኖሩ የነበሩትና የዚያን ግዜዎቹ ኢትዮጵያዉያን የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች የሁለቱን ጀርመኖች ዉሕደት እንዴት አገኙት። የቀድሞቆቹ ተማሪዎች የዛሪዋን ጀርመንና ከዉሕደቱ በፊት የዛሬ 25 ዓመቱን የምሥራቅ ጀርመን የባህልና ኑሮ ልዩነት እንዲሁም ትስስር እንዲያጫዉቱን ጋብዘናል።
በቡርኪና ፋሶ የቀድሞው ፕሬዚደንት ብሌዝ ካምፓዎሬ በሕዝብ ኃይል የታከለበት ተቃውሞ ከሥልጣናቸው ወርደው ወደ ጎረቤት ኮት ዲቯር ሸሽተዋል። ሕዝቡ ካምፓዎሬ በህገ መንግሥቱ ላይ ማሻሻያ በማስደረግ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ያደረጉትን ጥረት በመቃወም ያካሄደው ዓመፅም አብቅቷል።
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በጎርጎሪዮሳዊው አዲስ ዓመት ለዳግም ዘመነ-ሥልጣን በመመረጥ እንደሚወዳደሩ መግለጣቸው በናይጄሪያውያን ዘንድ ከወዲሁ ቁጣ እና ደስታን የቀላቀለ ስሜት ፈጥሯል።
ከአምስት ቀናት የባሕር መናወጥ ቆይታ በኋላ ከጣሊያኗ ላምፔዱዛ ደሴት እስከ ሊቢያ ጠረፍ የባሕሩ ሞገድ ረግቷል። ካለፈው አንድ ሣምንት አንስቶ ደግሞ «ቪያኖ ዶ ካስቴሎ» የተሰኘችው የፖርቺጊዝ ባሕር ቃኚ መርከብ ከላምፔዱዛ 55 ኪሎ ሜትሮች ደቡባዊ ርቀት ላይ መቅዘፍ ጀምራለች።
በሙያ የአፈርና ቋጥኝ እንዲሁም የእሳተ- ገሞራ ተማራማሪ ነው– «ጂዎፊዚስት»፤ ጠፈርተኛ ፣ አሌክሳንደር ጌርስት! ካለፈው ዓመት ግንቦት 20 ቀን 2006 ዓ ም አንስቶ ግን፣ እስካለፈው እሁድ፣ ከምድር አናት ላይ ሆኖ ፣ ማለት 418ኪሎሜትር ከፍ ብሎ ነበረ ምርምሩን ሲያካሂድ የቆየው።
ባለፈዉ ዕሁድ በስደት በሚኖርበት ስዊድን ሐገር ያረፈዉ የኢትዮጵያዊው ባለቅኔ የኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሰሞኑን እንደሚፈጸም ወዳጆቹ አስታወቁ።ኃይሉ በኢትዮጵያ ዘመናይ ሥነ-ፅሁፍ ሥመ ጥር ከነበሩ ደራሲዎች አንዱ ነበር።
በሙያ የአፈርና ቋጥኝ እንዲሁም የእሳተ- ገሞራ ተማራማሪ ነው– «ጂዎፊዚስት»፤ ጠፈርተኛ ፣ አሌክሳንደር ጌርስት! ካለፈው ዓመት ግንቦት 20 ቀን 2006 ዓ ም አንስቶ ግን፣ እስካለፈው እሁድ፣ ከምድር አናት ላይ ሆኖ ፣ ማለት 418ኪሎሜትር ከፍ ብሎ ነበረ ምርምሩን ሲያካሂድ የቆየው።
የአውሮፓ ፍርድ ቤት ትናንት ሉክስምቡርግ ላይ ባስቻለው ችሎት የጀርመን መንግሥት ፣ ኤልሳቤት ዳኖቭ ለምትባለው ሩሜኔያዊት የስራ አጥ ድጎማ መከልከሉ አግባብነት ያለውና በሕግም የተመሠረተ ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።
በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴዖ አካባቢ የይርጋ ጨፌ ወረዳ ኑዋሪዎች የሆኑ ወደ 400 የሚጠጉ አባዎራዎች፤ ከመሬታችን የመፈናቀል ብርቱ ሥጋት አድሮብናል አሉ። አርሶ አደሮቹ፤ ለጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት ባቀረቡት የአቤቱታ ማመልከቻና ለ DW በሰጡት መግለጫ፣
ባለፉት ዓመታት ዮርዳኖስ ከአካባቢዉ ሃገራት ወደ ሃገርዋ የሚገቡትን በርካታ ስደተኞች ስትቀበል ቆይታለች። ወደ ዮርዳኖስ የሚገቡት ስደተኞች በመጀመርያ ከፍልስጤም ከዝያ ከኢራቅ ነበር አሁን ደግሞ ከሶርያ በርካታ ስደተኞች በመፍለስ ላይ ናቸዉ። ይህች በንጉሳዊ አስተዳደር የምትመራ ትንሽ ሀገር የስደተኛ ጉዳይ ከባድ ፈተና ሆኖባታል።
በግብፅ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) ምዝገባ ቀነ-ገደብ ሰኞ ኅዳር 1 ቀን፣ 2007 ዓም ተጠናቋል። የመያዶች አዲስ ሕግ መነሻ በቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ ወቅት እጅግ አፋኝ እንደነበረ የሚጠቀስለት ሕግ እንደሆነ ተነግሯል። በርካታ መያዶች የመወረስ አለያም የመዘጋት ዕጣ እንደተጋረጠባቸው በስጋት ተውጠው ገልጠዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የኅዋ ምርምር (NASA) ዋና አስተዳዳሪ ቻርልስ ቦልደን በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋ ቆይታ አደረጉ።
በቅርቡ ይፋ የሆነ ሠነድ እንዳመለከተዉ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን 382 የስኳር ሕሙማን አሉ። በዚያ ላይም 316 ሚሊዮን ሕዝብ 2ኛዉ ደረጃ (ታይፕ 2 ) ለሚባለዉ የስኳር ሕመም የመጋለጥ እድሉ ሰፊ እንደሆነ መረጃዉ ይጠቁሟል።
ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዛምቢያ ፕሬዚደንት ማይክል ሳታ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመዲናይቱ ሉሳካ ተፈፀመ። የፕሬዚደንት ሳታ ይፋ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከ50,000 የሚበልጡ የሀገሪቱ ዜጎች እና በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በአርበኞች ስቴድየም ውስጥ ነበር የተከናወነው።
የጀርመን ፌደራል መንግሥት የኤቦላ ጉዳይ ተጠሪ ቫልተር ሊንድነር የጀርመንን ተሳትፎ ሲያወድሱ ሌሎች የርዳታ ድርጅቶች የጀርመን ድጋፍ የተጓተተ ነው በማለት ይተቻሉ። በዛሬው የአውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅት የምናነሳው ርዕስ ነው ።
ኢብቲህል አብደልላጢፍ በቀድሞው የቱኒዚያ አምባገነን ገዢ በዚን አል- አብዲን ቤን አሊ የቱኒዚያ ስርዓት ስር በደል የደረሰባቸውን ሰዎች ጉዳይ ይከታተላሉ። ወይዘርዋ ቀደም ሲል በአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ፣ አሁን ደግሞ በሀገሪቱ የሀቅ አጣሪ ኮሚሽን ውስጥ ያገለግላሉ።
የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መንግሥት በፓርቲዉ አመራርና አባላት ላይ የሚሰነዝረዉን ማዋከብ ከምንጊዜዉም በላይ አጠናክሮ ቀጥሎአል ሲል ከሰሰ።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ገበያ የጥሬ ሀብት ዋጋ እጅግ አሽቆልቁሎአል። በጥሬ ሀብቱ ዋጋ መቀነስ የተጎዳዉ ደግሞ ደሃዉ የአፍሪቃ ኅብረተሰብ ነዉ።
ጎርቫቾቭን ታቸር ከለንደን ሬገን ከዋሽግተን እየተቀባበሉ ሲያንቆለጳጵሷቸዉ፤ መራሔ መንግሥት ሔልሙት ኮል የቀዳሚዎቻቸዉንም፤ የራሳቸዉንም የሕዝባቸዉንም ሕልም ምኞት እዉን ለማድረግ ሞስኮዎችን እንደ ጥሩ ወዳጅ ቀረቧቸዉ።አግባባቡ አባበሉ።
ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።
የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ፣ እንዲሁም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዚሁ ማጣሪያ ውድድር የጀመረው ዝግጅት፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ያደረጉበት የቤሩት፣ ሊባኖስ እና የኒስ፣ ፈረንሳይ አትሌቲክስ ውድድር፣ የሳምንቱ
የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ-መንግስታት ባለሥልጣን በምህጻሩ ኢጋድ እንደሚቀጣቸው በድጋሚ አስጠነቀቀ። አስፈላጊ ከሆነም ኢጋድ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ዝቷል። የደቡብ ሱዳን አማፂያን በበኩላቸው የደቡብ ሱዳን መንግስት ስምምነቱን ጥሶ ውጊያ ከፍቶብናል ሲሉ ከሰዋል።
ኢትዮጵያና ጀርመን ዘመናት የተሻገረ የሁለትዮሽ ግንኙነት በመካከላቸዉ የመሠረቱ ሃገራት መሆናቸዉ በመረጃዎች የተመዘገበ ነዉ። ሁለቱ ሃገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ዉል ከተፈራረሙም 105 ዓመታት ተቆጥረዋል።
እ ጎ አ ከነሐሴ ወር 1961 ዓ ም አንስቶ በርሊንን ከ ሁለት በመክፈል 28 ዓመታት የዘለቀው 15 ኪሎሜትር ርዝማኔ የነበረው የግንብ አጥር የፈረሰበት 25ኛ ዓመት ዛሬ በደመቀ ሥነ ሥርዓት ሲከበር ውሏል። ከበርሊን ውጭ ፤ በአጠቃላይ 155 ኪሎሜትር
ኢትዮጵያና ጀርመን ዘመናት የተሻገረ የሁለትዮሽ ግንኙነት በመካከላቸዉ የመሠረቱ ሃገራት መሆናቸዉ በመረጃዎች የተመዘገበ ነዉ። ሁለቱ ሃገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ዉል ከተፈራረሙም 105 ዓመታት ተቆጥተዋል።
ጀርመንን ለኹለት ከፍሎ የቆየው ግንብ የተገረሰሰበትና ኹለቱ ጀርመኖች ውህደት የፈጠሩበት 25ኛ ዓመት በርሊን ውስጥ እየተከበረ ነዉ። በ15 ኪሎ ሜትሮች ርዝመት ወደ 7000 የሚጠጉ ክብ አንፖሎች ብርሃን እየፈነጠቁ እንደወሰን ቆሞ የነበረዉን ግንብ ማመላከታቸዉ ለበርሊን ነዋሪዎችና ከመላው ዓለም ለተሰበሰቡ ጎብኝዎች መስህብ መሆናቸዉ ተነግሮአል።
ባለፈው መጋቢት ወር በምዕራብ አፍሪቃ ኤቦላ ከተከሰተ ወዲህ ገደማ ከ13,000 የሚበልጥ ሰው በወረርሽኙ አስተላላፊ ተሀዋሲ ሲጠቃ ፣ ከዚሁ መካከል ወደ 5,000 ሰው ሞቶዋል።
ባለፈው መጋቢት ወር በምዕራብ አፍሪቃ ኤቦላ ከተከሰተ ወዲህ ገደማ ከ13,000 የሚበልጥ ሰው በወረርሽኙ አስተላላፊ ተሀዋሲ ሲጠቃ ፣ ከዚሁ መካከል ወደ 5,000 ሰው ሞቶዋል።
ከጀርመን ዉኅደት በኋላ በምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተጀመረዉ ግንባታ ተጠናቆአል። በአዲሶቹ የጀርመን ግዛቶት በአብዛኛዉ ክፍል እጅግ ከፍተኛ ልማት ታይቶበታል። ቢሆንም ይህ ልማት ፍሬያማነቱ እስካሁን አመርቂ እንዳልሆነ ነዉ የሚገለጸዉ። ፍሬ ለማግኘት ገና ብዙ ግዜን ይጠይቃል፤ ያን ለመጠበቅ ደግሞ ግዜ የለም።
አክራሪ ሙስሊም አማፂ ቡድኖችን የሚቀላቀሉት በብዛት ወንድ ወጣቶች ሲሆኑ ፤ ከቅርብ ጊዜ አንስቶ የሴቶቹም ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ወጣቶች ለምን የሳላፊቾች ቡድንን እንደሚቀላቀሉ እና ያላቸውን ሚና በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንቃኛለን።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) የቀድሞ ዋና ጸሃፊ እና አባላት በጸጥታ ሃይሎች ተወስደው ያሉበት አለመታወቁን ፓርቲው አስታወቀ።የአቶ ተስፋዬ ታሪኩ በጸጥታ ሃይሎች ሲወሰዱ በቦታው ነበርኩ የሚሉት ባለቤታቸው ቤታቸው ሲፈተሽ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመያዛቸውን ተናግረዋል።
የታሰሩ የፖለቲካ አባላት እና ጋዜጠኞች ይፈቱ፣ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ነፃነት እንሻለን በማለት በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በቤልጄም መዲና ብራስልስ ሰልፍ ወጥተዋል።
የምሥራቅ አፍሪቃ አፍሪቃ ሃገራት ፤ የኢትዮጵያ ኬንያና ዩጋንዳ መሪዎች፤ 11 ወራት በእርስ በርስ ጦርነት ላይ የሚገኙትን የደቡብ ሱዳን ተቃናቃኝ መሪዎች ለመሸምገል ዛሬም አዲስ አበባ ውስጥ ጉባዔ አካሂደዋል።
«ባርያዉ» በሚል መጠርያዉ የሚታወቀዉ ወጣት ሰመረ ካሳ በመድረክ በሚያቀርባቸዉ አዝናኝና አስተማሪ ቀልዶቹ ተወዳጅነቱ ታዋቂነቱ እየጎላ መጥቶአል። በዕለቱ ዝግጅታችን ባርያዉን ከነቀልዱ ይዘን «ሂስ የማኅበረሰብ አረም መንቀያ መሳርያ ነዉ» ያሉንን ምሑራን ጋብዘን የሂስን ምንነት ለማየት ቀርበናል።
ከ 50 የሚበልጡ የደቡብ ሱዳን ዜጎች፤ የሰብዓዊ ተቋማትና ፤ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ጎረቤት ሃገራት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ አስቸኳይ የጦር መሳርያ ማዕቀብ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ።