ተጻፈ በ  

-የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማስተጓጐል ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተጠቁሟል በታምሩ…


ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—-
“የማይረሱ የፕሬስ ውጤቶች” በሚል ርዕስ አንድ ጽሑፍ አቅርቤ ነበረ፡፡ በዚያ ጽሑፍ በመንግሥት ሲታተሙ የነበሩትን ጋዜጦችና መጽሔቶችን ነበር የዳሰስነው፡፡ በዚህኛው ክፍል ደግሞ በግል አሳታሚዎች አማካኝነት ሲታተሙ የነበሩትን መጽሔቶች እንዳስሳለን፡፡ ታዲያ በግል የተመሰረቱት የፕሬስ ውጤቶች እጅግ በርካታ በመሆናቸው ሁሉንም ማዳረስ አንችልም፡፡ ስለዚህ ታዋቂ የሆኑትን ብቻ  እንጠቃቅስና የቀረ ነገር ካለ ወደፊት እንመለስበታለን፡፡
1.       “ኢትዮጵያን ኦብሰርቨር” እና “አዲስ ሪፖርተር” መጽሔቶች
በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዘመነ-መንግሥት በእንግሊዝኛ ይወጡ የነበሩ መጽሔቶች ናቸው፡፡ መጽሔቶቹን ሲያነቡ የነበሩ ሰዎች በይዘታቸውም ሆነ በስነ-ጽሑፋዊ ውበታቸው በጣም ያደንቋቸዋል፡፡ በመጽሔቶቹ ላይ ይጽፉ ከነበሩት ጸሐፍት መካከል አብዬ መንግሥቱ ለማ እና ዳኛቸው ወርቁ ይጠቀሳሉ፡፡
2.     “መነን” መጽሔት
1950ዎቹ መጨረሻ እስከ 1960ዎቹ መጀመሪያ ድረስ ይታተም የነበረ የአማርኛ መጽሔት ነው፡፡ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ በዓሉ ግርማ ሲሆን ስብሐት ገ/እግዚአብሄርን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ጸሐፍት ይሳተፉበት ነበር፡፡
3.     “ጸደይ” መጽሔት
የየካቲት 1966 የአብዮት ፍንዳታን ተከትሎ የተመሰረተ የግል መጽሔት ነው፡፡ መጽሔቱ በዘመኑ የሶሻሊስት ርዕዮተ-ዓለም ትንተና እና በማህበራዊና ኪነ-ጥበባዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተጨማሪም ለየት ያሉ ኩነቶችን በ“ካርቱን” ስዕል ማሳየት የጀመረው እርሱ ይመስለኛል (እርግጠኛ አይደለሁም)፡፡
 “ጸደይ” የዘመኑ መንግሥት ከሚከተለው የፖለቲካ መስመር አኳያ የተቃኘ ነው፡፡ በመሆኑም በዚያ ዘመን የነበሩ በርካታ አንባቢያን “ጸደይ”ን በአድርባይነት ይተቹታል፡፡ ሆኖም መጽሔቱ እስከ አሁን ድረስ በተወዳጅነታቸው የሚጠቀሱ ጽሑፎችንም አስተናግዷል፡፡ ለምሳሌ ጋሼ ስብሐት ስለ“አጋፋሪ እንደሻው” መጻፍ የጀመረው በዚያ መጽሔት ላይ ነው፡፡ “ዔሊን ድንጋይ ያለበስክ” የሚለው አጭር ወግም በዚሁ መጽሔት ላይ መውጣቱን አስታውሳለሁ (እኔ የዚያ ዘመን አንባቢ አይደለሁም፡፡ አሁን የምላችሁን ጽሑፍ ያነበብኩት በ1980ዎቹ ውስጥ ነው)፡፡
4.     “ጎህ መጽሔት”      
የርዕዮተ-ዓለም ይዘት ያላቸውን ጽሑፎች ነው የሚያስተናግደው፡፡ ይሁንና የፖለቲካ መስመሩ በዘመኑ ታዋቂ ከነበረውና “ኢህአፓ” ከተሰኘው ህቡእ ፓርቲ አኳያ የተቃኘ ነው፡፡ በመሆኑም “ጎህ” በህትመት ብዙ መሰንበት አልቻለም (ህትመቱ ከሶስት እትሞች በኋላ የተቋረጠ ይመስለኛል)፡፡
ታዲያ “ጎህ” በዚያች ትንሽ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ ለመሆን በቅቷል፡፡ በተለይም የጆሴፍ ስታሊን የህይወት ታሪክ በማስመልከት በጸደይ መጽሔት ላይ በወጣ ጊዜ ጎሕ መጽሔት ጽሑፉን በመቃወም ስታሊንን እየወቀሰ የሰጠው ምላሽ ከጸደይ ጋር ጦርነት ውስጥ ከትቶት ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የጸደይ መጽሔት ጸሐፊዎች ጎህን “አናርኪስት” እስከማለት ደርሰዋል፡፡
በጎህ መጽሔት ላይ ይጽፉ ከነበሩት ታዋቂ ሰዎች አንዱ የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረው ዮሐንስ ብርሃኔ ነው (ዮሐንስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የነበረ ሲሆን በመጋቢት ወር 1969 በአቃቂ ኬላ ላይ ተገድሏል)፡፡ በነገራችን ላይ ጎሕ ከደርግ መንግሥት ውድቀት በኋላ በ1984 መጨረሻ ላይ እንደገና መውጣት ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን በገበያ ውስጥ ብዙም ሊቆይ አልቻለም፡፡ ከዚያም ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ (በ1993) “ጎህ” የተሰኘ መጽሔት ተጀምሯል፡፡ ሆኖም ይህኛውም መጽሔት ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ተዘግቷል፡፡
5.     “ቢላል”
በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚዘጋጅ ሲሆን በ1966 የአብዮት ፍንዳታ ወቅት ነው መታተም የጀመረው፡፡ ነገር ግን ከሁለት እትም በላይ ሳይራመድ ጠፋ፡፡ ከአስራ አራት ዓመታት በኋላ በመስከረም ወር 1985 በዚሁ ስም አዲስ መጽሔት መዘጋጀት ጀመረ፡፡ ይሁንና የኋለኛው “ቢላል” ከድሮው ጋር ተመሳሳይ ስያሜ ከመያዙ ውጭ አሳታሚያቸው አንድ አይደለም (የ1985ቱ “ቢላል” በነጃሺ አሳታሚ አማካኝነት ነበር የሚዘጋጀው)፡፡
ከሁለቱ “ቢላል” መጽሔቶች መካከል በአንባቢያን ዘንድ ልዩ ትውስታን ጥሎ ያለፈው የ1985ቱ “ቢላል” ነው፡፡ የዚህ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ታዋቂው የኢትዮጵያ የእስልምና ሊቅ ሐጂ ሙሐመድ ወሌ ነበሩ፡፡ በ1987 በአንዋር መስጊድ ረብሻ ሲነሳ የ“ቢላል”ም ህትመት ተቋርጧል፡፡
6.     “እፎይታ”
በ1984 የፕሬስ አዋጅ ሲታወጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው የግል መጽሔት “እፎይታ” ነው፡፡ አሳታሚው “ፋና ዴሞክራሲ አሳታሚ” ይባላል፡፡ ለረጅም ጊዜ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ያገለገለው ደግሞ ተስፋዬ ገብረአብ ነው (ተስፋዬ በመጽሔቱ ላይ በአዘጋጅነት የተጠቀሰው “ዋለልኝ ብርሃነ” በሚል ስም ነበር)፡፡ ይሁንና መጽሄቱ “ነጻ ነኝ” ቢልም አብዛኛው አንባቢ የኢህአዴግ ልሳን ይለው ነበር፡፡ በእርግጥም መጽሔቱ የኢህአዴግ መስመር ተከታይ እንደነበረ ከጽሑፎቹ መረዳት ይቻላል፡፡ ተስፋዬ ገብረአብ ባሳተመው የጋዜጠኛው ማስታወሻም ይህንኑ አምኖ ነበር፡፡ የኢህአዴግ አባላት መጽሔቱን በትዕዛዝ ይገዙት የነበረ መሆኑም ሌላው አስረጂ ነው፡፡
   “እፎይታ” መታተም ሲጀምር በደርግ ዘመን በተፈጸሙ የቀይ ሽብር ወንጀሎች፣ በዓለም አቀፍ ጉዳዮችና በኪነ-ጥበባት ጉዳዮች ላይ ስለሚያተኩር  በርካታ አንባቢያን ነበሩት፡፡ በዝግጅቱም የሺጥላ ኮከብ፣ ደረጄ ደስታ፤ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር እና አረፈዓይኔ ሐጎስን የመሳሰሉ ደራሲዎችና ጋዜጠኞች ይሳተፉ ነበር፡፡ በመጽሔቱ የታተሙ በርካታ መጣጥፎችና አጫጭር ልብ-ወለዶች “እፍታ” በተሰኙት ተከታታይ መድብሎች ተሰባስበዋል፡፡
 
“እፎይታ” ከ1987 በኋላ ድሮ በነበረበት ይዘት መቀጠል አልቻለም፡፡ በመሆኑም የአንባቢዎቹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀንሷል፡፡ ቢሆንም በመንግሥታዊዎቹ “አዲስ ዘመን” እና “ኢቴቪ” የማይዘገቡ ወቅታዊ ጉዳዮችን በብቸኝነት እንዲያስተናግድ ስለሚደረግ እስከወዲያኛው ድረስ በአንባቢ እጦት ድርቅ አልተመታም፡፡
7.     “ሩሕ”
“ዩሬካ” በሚባል አሳታሚ ድርጅት አማካኝነት በሚያዚያ 1984 ነው መታተም የጀመረው፡፡ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ጋሽ ጳውሎስ ኞኞ ነው፡፡ ሆኖም ጳውሎስ ከጥቂት እትሞች በኋላ (በ1984 ክረምት ወራት) ሞቷል፡፡
በመጽሔቱ ላይ ከሚጽፉ ብርዕተኞች መካከል “ሱልጣን ኢንሻ አላህ” የተባለው ጸሐፊ ይጠቀሳል፡፡ ይህ መጽሔት በ1985 ከተቋረጠ በኋላ በ1993 እንደገና አንሰራርቷል፡፡ ነገር ግን በዚህኛውም ጊዜ ብዙ ሳይጓዝ ተቋርጧል፡፡ “ሩሕ” መጽሔት በደንብ የሚታወሰው የሼኽ ሑሴን ጂብሪልን ትንቢታዊ ግጥሞች ለመጀመሪያ ከአንባቢያን ጋር በስፋት ያስተዋወቀ በመሆኑ ነው፡፡
8.     “ጦቢያ”
በታዋቂው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ አማካኝነት በ1984 የተጀመረ ነው፡፡ “ጦቢያ”ን ለየት የሚያደርገው በሚያዚያ 1984 ከተጀመሩት የነጻ ፕሬስ ውጤቶች መካከል ሳይቋረጥ እስከ መስከረም 1998 ድረስ ለመጓዝ የቻለ ብቸኛ መጽሔት መሆኑ ነው፡፡ በመጽሔቱ ላይ ይጽፉ ከነበሩት ብዕርተኞች መካከል ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ፣ ስንሻው ተገኘ እና ሐሰን ዑመር አብደላ በጣም ይታወሳሉ፡፡
በጦቢያ መጽሔት ከወጡት ጽሑፎች መካከልም ዶ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ዙሪያ የጻፏቸው ተከታታይ ጽሑፎችና በ1953ቱ የታህሳስ ግርግር ዙሪያ የተጠናቀረው ታሪካዊ ዘገባ ይጠቀሳሉ፡፡ በ1987 አጋማሽ ላይ በጄኔቭ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከነበሩት ጓድ ካሳ ከበደ ጋር የተደረገው ቃለ-መጠይቅም የመጽሔቱን ተፈላጊነት በእጅጉ አንሮት ነበር፡፡ 
9.     “ሳሌም”
በኢትዮጵያ ታሪክ ከተከሰቱ የምንጊዜም ተወዳጅ መጽሔቶች አንዱ ነው፡፡ “ሳሌም” በአቀራረቡ ሚዛናዊ በመሆኑ በርካታ ደንበኞች ነበሩት፡፡ እንዲሁም ለግል መጽሔቶች ባልተለመደ ሁኔታ የትኛውንም አካል አነጋግሮ ዘገባ ይሰራ ነበር፡፡ የመንግሥት ባለስልጣናት ለሳሌም መረጃና ቃለ-መጠይቅ ይሰጡ ነበር፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም እንደዚያው!!
ሳሌም መጽሔት በአንባቢያን ዘንድ በጣም የሚታወሰው በሁለት ነገሮች ነው፡፡ አንደኛው በወሩ ውስጥ አነጋጋሪ በሆነ ጉዳይ ዙሪያ የግራና የቀኝ ምንጮችን እያነጋገረ የሚያቀርበው “አቢይ ርዕስ” ነው፡፡ የዚህ ዘገባ አጻጻፍ ከብዙ ዓመታት በኋላ “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ይዞት ከመጣው “ፊቸር ጽሑፍ አጻጻፍ” ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ልዩነቱ ሳሌም መጽሔት ከዋናው ዘገባ አጠገብ ፎቶግራፎችንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደረጉ አጫጭር ቃለ-ምልልሶችን የሚያክል መሆኑ ነው፡፡
  በሌላ በኩል ሳሌም መጽሔት ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎችን፣ ምሁራንንና አርቲስቶችን እየጋበዘ በሚሰራቸው ልዩ ቃለ-መጠይቆችም ይታወሳል፡፡ ሳሌም ካስተናገዳቸው ቃለ-መጠይቆች መካከል የኦነግ ም/ሊቀመንበር ከነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ከቀድሞው የደህንነት ሚኒስትር ኮ/ል ተስፋዬ ወልደሥላሤ፣ ከቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሤ ወግደረስ፣ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከነበሩት ኮ/ል ደበላ ዲንሳና ዶ/ር ዓለሙ አበበ እንዲሁም ከአርቲስት ሙሉቀን መለሠ ጋር የተደረጉት ይጠቀሳሉ፡፡ “ሳሌም” በ1986 መጨረሻ ላይ ለጊዜው ባላወቅኩት ምክንያት ተዘግቷል፡፡ በመጽሔቱ ላይ በዘጋቢነት ይሰሩ ከነበሩት መካከል የአሁኑ አርቲስት ሰይፉ ፋንታሁን ይጠቀሳል፡፡
10.    “አሌፍ”
1985/86 ከሳሌም ቀጥሎ ሰፊ ተነባቢነት የነበረው መጽሔት ነው፡፡ በአቀራረቡም ከሳሌም ጋር የመመሳሰል ነገር ይታይበት ነበር፡፡ በተለይ የመጽሔቱ “ዐቢይ ርዕስ” አጠር ከማለቱ በስተቀር ከሳሌም የ“ፊቸር ዘገባ” ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በአሌፍ የሚታየው የተለየ ነገር ቢኖር ከዋናው ዘገባ አጠገብ ከርዕሱ ጋር የሚሄዱ አነጋጋሪ ጽሑፎችን የሚያክል መሆኑ ነው፡፡
የአሌፍ መጽሔት ባለቤት አቶ ብርሃነ መዋ ነበሩ፡፡ ዋና አዘጋጁ ደግሞ አሁን የቪ.ኦ.ኤ ዘጋቢ ሆኖ የሚሰራው መለስካቸው አመሀ ነው፡፡ በዘጋቢነት (ሪፓርተርነት) ይሰሩ ከነበሩት መካከልም አሁን የሸገር ኤፍ.ኤም ታዋቂ ሰው የሆነችው ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ትጠቀሳለች፡፡
ይህ መጽሄት ስለኢህአፓ ጉዳይ እየደጋገመ ይጽፍ ነበር፡፡ በ1986 ለመዘጋት የበቃው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
11.     “ሪፖርተር” መጽሔት
የአማረ አረጋዊ ኩባኒያ በሆነው ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሴንተር የሚዘጋጅ ወርሃዊ መጽሔት ነበረ፡፡ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ እሸቴ አሰፋ  ሲሆን ከመጽሔቱ ከፍተኛ አዘጋጆች መካከል ኋላ ላይ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መስፍን ነጋሽ ይጠቀሳል፡፡
 ሪፖርተር በመጽሔትነቱ ከሪፖርተር ጋዜጣ በጣም ይለያል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ብዙ ገጽ ቢኖረውም አብዛኛው ክፍል በማስታወቂያ የተያዘ ነው፡፡ የንባብ ጥማት ላለው ሰው ብዙም አርኪ የሚባል አይደለም፡፡ ሪፖርተር መጽሔት ግን በመረጃና በምርምር የተደገፉ አነጋጋሪ፣ አከራካሪ እና አወያይ ጽሑፎችን ይዞ ይወጣ ስለነበረ በተለይም በምሁሩ ክፍል ከፍተኛ ተነባቢነት ነበረው፡፡ በሪፖርተር መጽሔት ከወጡ ጽሑፎች መካከል ኤርትራ “ናቅፋ” የተባለውን ገንዘብ በስራ ላይ ባዋለችበት ወቅት የተጠናቀረው ዘገባ፣ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፈነዳበት ጊዜ የተጠናቀረ ዘገባ፣ እነ ተወልደ ወልደማሪያም ከህወሐት ተገንጥለው በወጡበት ወቅት “ቦናፓርቲዝም” በሚል ርዕስ የወጣው አነጋጋሪ ዘገባ፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከኦህዴድ በወጡበት ጊዜ የተጠናቀረው ቃለ-ምልልስ፣ በጋምቤላው ግጭት ዙሪያ የተጠናቀረው ሪፖርታዥ በከፍተኛ ደረጃ ተነበዋል፡፡ በመጽሔቱ ላይ መጣጥፎችን ከሚያቀርቡ ብዕርተኞች መካከል የኢህዴን/ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረው መዝሙር ፈንቴ ይጠቀሳል፡፡
ሪፖርተር እስከ 1997 መግቢያ ድረስ በህትመት ላይ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ መጽሔቱ መቼ እንደተቋረጠና በምን ምክንያት እንደተቋረጠ ግን ትክክለኛ መረጃ የለኝም፡፡
12.     “ኢትኦጵ”
በሰኔ ወር 1991 የተጀመረ የግል መጽሔት ነው፡፡ መጽሔቱ በተለይ በመረጃ ስፋትና ጠለቅ ባለ ትንታኔው ይታወሳል፡፡ ታሪክ-ነክ ጉዳዮችንም እየቆሰቆሰ ብዙ አንባቢያንን በማፍራቱም ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በብርቱ የተቋሰሉ ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎች ይጽፉበት ስለነበረ ከፍተኛ ተፈላጊነት ነበረው፡፡ ለምሳሌ እነ አቶ እያሱ አለማየሁ፣ አቶ አሰፋ ጫቦ፣ አቶ አብርሃም ያየህ፣ አቶ ጌታቸው ጋረደው የመሳሰሉት የፖለቲካ ሰዎች በርካታ ጽሑፎቻቸውን አቅርበውበታል፡፡ የገጣሚ ሀይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) እና የህወሐት ቁልፍ ሰው የነበረው የብስራት አማረ (ከኮሎምበስ-ኦሃዮ) ተከታታይ ጽሑፎችም ተስተናግደውበታል፡፡
በሌላ በኩል “ኢትኦጵ” መጽሔት በህትመት ኢንዱስትሪው የሚታወስበት አንድ ታሪክ አለው፡፡ ይህም ታዋቂና ዝነኞች ብቻ የመጽሔት እንግዳ የሚደረጉበትን ልማድ በመስበር በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ለሚገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች ቃለ-መጠይቅ የማድረግ ልማድን ማስተዋወቁ ነው፡፡ እነዚህ ቃለ-መጠይቆች “መንገድ” በተሰኘው አምድ ይስተናገዱ ነበር (እኔ ኢትኦጵን ማንበብ የምጀምረው “መንገድ” ከተሰኘው ዓምድ ነበረ)፡፡ “ኢትኦጵ” ከምርጫ 1997 ግርግር ጋር በተያያዘ በመስከረም ወር 1998 ተዘግቷል፡፡
13.    “አዲስ ጉዳይ”
ይህ መጽሔት በ1998 ገደማ ሲጀመር “ሮዝ” የሚል ስም ነው የነበረው፡፡ በ2003 ደግሞ “አዲስ ጉዳይ” የሚለውን ስያሜ ያዘ፡፡መጽሔቱ በጅምሩ ላይ በኪነ-ጥበብና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኩር ነበር፡፡ “አዲስ ጉዳይ” በሚል ስም መዘጋጀት ከጀመረ በኋላ ግን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያው ጉዳዮችን ጨምሮ ሁሉንም ዘርፎች የሚዳስስ ሆኗል፡፡ በመጽሄቱ ላይ ስም ያላቸው ምሁራንና ታዋቂ ወጣት ጸሐፍት የሚሳተፉ ከመሆናቸው የተነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ አንባቢያንን ለማፍራት በቅቷል፡፡ “አዲስ ጉዳይ” የሚታወስበት ሌላኛው ነገር ደግሞ መጽሔቶች በወር ብቻ የሚዘጋጁበትን የረጅም ጊዜ ልማድ ሰብሮ የአስራ አምስት ቀን እና ሳምንታዊ ህትመትን ማስተዋወቁ ነው፡፡
*****
ከላይ ከጠቀስኳቸው መጽሔቶች በተጨማሪ መስታወት፣ ማለዳ፣ አእምሮ፣ አቢሲኒያ፣ ሉሲ፣ ገዳ፣ የአፍሪካ ቀንድ፣ ህብር፣ ለዛ፣ ምኒልክ፣ ልሳነ-ህዝብ፣ ኮከብ፣ ማሕሌት፣ ዜጋ፣ ወዘተ… የተባሉ መጽሔቶችም በሀገራችን ይታተሙ ነበር፡፡ አሁን ግን አንዳቸውም የሉም፡፡ በህትመት ላይ ካሉት መጽሔቶች መካከል ዘላቂ በሆነ መልኩ የሚቀጥሉት የትኞቹ ናቸው?… ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ እድሜና ጤና ይስጠንና!!
—-
ነሐሴ 11/2006
አፈንዲ ሙተቂ
—-
Afendi Muteki is a researcher and author of the ethnography and history with special focus on the peoples of East Ethiopia. You may follow him on his blog and his facebook page by clicking the following links

Image
የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች (Amara Force) እኛ በውህደቱ የለንበትም ብሏል::
Minilik Salsawi ምንሊክ ሳልሳዊ – ከአስመራ ከተማ የሚገኙ ምንጮቼ በስልክ እንዳስታወኩኝ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የሆኑት አቶ ነእመን ዘለቀ:የአቶ አንዳርጋቸው ወንድም አቶ ብዙአየሁ ጽጌ አቶ አበበ ቦጋለ እና ሌሎች የኢሳት ሪፖርተሮችን አስከትለው አስመራ የገቡ ሲሆን የአርበኞች ግንባር አመራሮች ወደ አስመራ የሚልኩትን ሰው መርጠው ባለመጨረሳቸው እንደዘገዩ ሲጠቆም እስከ እሁድ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ቢሞከርም ሆተሎች ጥብቅ የጸጥታ ክትትል ስለሚደረግባቸው መረጃዎች ለጊዜው እንዲዘገዩ ተደርጓል::

በአስመራ የተለያየ ሆተል ማረፊያ የተዘጋጀላቸው የግንቦት ሰባት አመራሮች የአርበኞች ግንባር አመራሮች እንደገቡ በመጭው አዲስ አመር ጥር መጀመሪያ የውህደት መስራች ጉባያቸውን በማድረግ የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር ይመሰርታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ውህደቱን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደምህት እና ሻእቢያ ሰራዊቶች ሊያጅቡት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ሲሉ ምንጮቹ ከአስመራ ገልጸዋል::

እንደ ደምሕት እና ኦነግ እንዲሁም የጋምቤላ ቤንሻንጉል እና አፋር ነጻ አውጪዎች በውህደቱ እንዳይሳተፉ ተደርጓል ያሉት የአስመራ ምንጮች ሻእቢያ የጎሳ ድርጅቶችን ለአላማው ስለሚተቀምባቸው ከአንድነት ሃይሎች ጋር እንዲዋሃዱ አይፈሊግም ሲሉ ተናግረዋል::(በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ምንጮቹ አሁን እንዳይጻፍ ጠይቀዋል::)

የአይሮፕላን ወጪያቸውን ሸፍነው አስነራ የደረሱት ነጻ አውጪዎች በሻእቢያ አስመራ ከተማ ውስጥ ሙሉ ወጪያቸው ሲሸፈን የመብራት አገልግሎት እንዳይቋረጥባቸው ጄኔራተር በመትከል እና እንዲሁም የደህንነት እና የጸጥታ ጥበቃ በማድረግ ላይ እንደሆነ ምንጮቹ ሲናገሩ በግንባር ያገኟቸው የግንቦት ሰባት ሰዎች ለጊዜው ዝርዝር ምረጃ ሊሰጡ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጸዋል::

በውህደቱ ዙሪያ በአርማጮ በረሃ ያሉትን የአማራ ፎርስ ሰራዊት አመራሮችን አነጋግሬቸው እንደመለሱልኝ ከሆነ ክታሰሩ አባሎቶቻችን ውጪ በአስመራ ያለንን ሃይል ያስወጣን እና ከሻእቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ዘግተናል ሲሉ የገለጹ ሲሆን ካሁን በፊት ባወጡት መግለጫ ከአስመራ መንግስት ጋር ሆኖ ዪትዮጵያን ህዝብ ነጻነት ማሰብ ስህተት መፍጠር ነው ሲሉ ገልጸው ነበር::በአስመራ በኩል የተዘጋጁትን ነጻ አውጪዎች የተሳካ ቀሪ ዘመን እየተመኘው ቀሪ ዝርዝር ዘገባ ይዤ ለመመለስ ቃል እገባለሁ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ዛሬ ጠዋት የተሰየመው 19ኛ ወንጀል ችሎት ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ቀድመው ቢገኙም ለሰአታት ያህል ችሎቱ ሳይጀመር ቆይቷል፡፡ የተወሰኑ ወዳጆች እና የቤተሰብ አባላት ችሎቱን ለመታደም እድል ያገኙ ሲሆን የተለመደው የቦታ ጥበትን ተከትሎ ብዙዎች ውጪ ቆመው ሲጠብቁ አንደነበርም ተስተውሏል፡፡ 

ባልተለመደ ሁኔታ ዘግይተው የተሰየሙት ዳኞች የጠበቆች የተሻሻለው ክስ ላይ ያላቸውን አስተያት ማቅረባቸውን ሰምተዋል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ የጽሁፍ አስተያየታቸውን ማቅረባቸውን ነገር ግን አቃቤ ህግ ክሱን አለማሻሻሉን በቃል ክርክር ለማቅረብ ቢሞክሩም ፍርድ ቤቱ የቃል ክርክር አስፈላጊ አንዳልሆነ እና መሻሻል አለመሻሻሉን አይቶ አንደሚወስን በማሳወቅ የጠበቆችን የቃል ክርክር ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት ጠበቃ አምሃ የጽሁፍ ምልልሱ የፍርድ ሂደቱን እያጓተተው በመሆኑ በቃል ማስረዳትን አንደአማራጭ ለመጠቀም ፈልገው አንዳልተሳካ ገልጸዋል፡፡ 

ከሰአታት ጥበቃ በኋላ የተሰየመው የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የፍርድ ሂደቱን ለታህሳስ 27 በመቅጠር ተጠናቋል፡። በእለቱ የጦማሪ ዘላለም ክብረት የልደት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ብዙዎች ወዳጆቹ የመልካም ልደት ምኞታቸውን ገልጸውለታል፡። ጦማርያኑ ሲገቡ በጀርባ በር በኩል አንዲገቡ በመደረጋቸው ከሚጠብቃቸው ቤተሰብ እና ወዳጅ ጋር በደምብ ሰላምታ ለመለዋወጥ ባይችሉም በጠንካራ መንፈስ ጥንካሬ እና ፈገግታ ታይተዋል፡፡ 

የጠበቆቹ የተሻሻለው ክስ ፡፡#Ethiopia #FreeZonebloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 

The bloggers and journalists outside at lideta court  
Edom Kassaye (journalist) and Mahilet Fantahun (bloggers) today outside court    
Birthday man, Zelalem Kibret with Zone9bloggers and Journalists

 

From Kilinto prison, Addis Ababa Ethiopia 
O! The mighty reminiscence! Of all the thoughts nothing is more haunting than reminiscence. When I read, walk; sleep — in all of my daily routines I recall yesterday. Yesterday as if it is painted by one of the renaissance realist painters. Those yesterdays are here facing me virtually, if Raphael and Titan meets for a team work and puts those yester times in a big canvas.
How you doing comrades? You might be confused by my word choice of comrade. I got you Yes, our (me and you) formal relationship was a ‘Master’ pupil, ‘teacher – Student’, ‘Boss – Subordinate ‘ relationship. I am not comfortable with such hierarchical dichotomy. Rather, we were friends. I think we are still friends but, from afar and I hope our friendship will blossom by tomorrow. Hence, our bond of relationship is the rationale behind my choice, comrade (with all its political connotations) instead of something else.
Comrades, since my departure from the scene that is common for both of us, I know some of you are done with your formal schooling and I know that some of you are still counting your orders in the main dish, please consider my humble wishes.  For those who are done with your time in school, I wish a good time of preparation for the sequel. For those who are still struggling in school, have a wonderful fight.
The ‘departed’
Friends, if you remember we used to have a term of relationship, which put us in a promise to get together in the classroom. Regrettably, I am the one who fails to fulfill my promise but, forgivably. I say, forgivably. Because it is not I rather tyranny that should take the blame. Dictatorship is the hurdle that set us apart. It is the state which is the sinner. I fail to keep my words of promise because of a force majeure called despotism.
A short summery of what happens to me may give you the excuses to forgive me for my incompliance with terms of our promise.
Hundreds of days back out of the blue I was arrested for a suspicion of felony, that eventually turned to be a crime of preparation and conspiracy to commit an act of terrorism. However, the charge was not a simple matter as I mentioned. Rather, I passed through a prolonged medieval-like ordeal or as ‘they’ called it ‘interrogation’. Finally I end up in a remand center which have thousands of ‘detainees -of – conscience’. Even if it is laughable but, the crime that I am accused of is neither bail able nor an easy thing to face. Since I face capital punishment if I fall in the ‘convicted’ basket. So, comrades ain’t my failure to fulfill our promise forgivable?
Addendum: let me know you something extra about the situation that I live, if it helps me to get your piety of forgiveness;
Since my departure from the chalk and talk I never saw the sunset. Because I am a detainee who should be roll-called before the sunset.
My privacy has gone with the wind of April, since I am a detainee who lives with hundred plus detainees in one cell.
Fellow friends, you have no idea about how a day in prison is vicious. The viciousness of the day is like dancing the same, with the same rhythm and in the same dance floor, day-in-day-out. I am a detainee who is dancing this ‘Sisyphusic’ dance in a minute base. Save my trail to dilute the viciousness of the day by the virtuous souls.
The depression that resulted from counting the plight of my love, my friends and my families is so immense. Because I am a detainee who have nothing to do for them. Again save my trial to console myself with a thought of how I am lucky to be expired to this prison environment and its population.
Comrades, the types of book that I have to read, the utensils that I have to use, even my hair-style and shoe-type must be ‘proper’, which fulfils the remand center’s regulation. Because I am a detainee.
Thus, comrades, in consideration of such ill facts of my life and how my life is digressed from its normal course, how could an inmate who lives in such a situation which limitation is a rule fulfills his promise of coming to the class room? How could a man who is in chain live to his terms of promise? I hope I got your forgiveness.
The Puzzled
The Roman jurist and philosopher, Cicero upon his Critic of the state says:
“The Republic is oppressed with arms and enfeebled by slavish fear. So it has no Power to innovate the free spirit”.
It seems present day Ethiopia is the incarnation of the republic that Cicero is critical of voices muzzled. Thinkers exiled and dissenters incarcerated. This is the situation that bewildered me. What is wrong with us comrades? Why the Free spirit is chained and cuffed? Why oppression exist in a continuum? Why fear reign, democracy manacled and the gun is the domineering player of the entire player? Why today looks like a Siamese twin of yesterday?…
Comrades, my list of whys about our nations illness is bottomless. I hope yours too. However, I feel that the answer/s for our quests is/are not bottomless; even it can be a single one. And the very question is what could be that panacea?
Out of those numerous thought wonderings, sometimes I stopped somewhere and start to feel that the problem of our nation lies on the ‘Clash of Generations’! I know it seems naive to think so. But, it is not something we have to ignore. My wandering result a question of is our country suffer because of the ‘Clash of Generations’ for ideas, for principles or for power?
Scott Fitzgerald in his ‘This Side Of Paradise’ puts the mission of ‘his’ generation eloquently as ‘our generation had grown up to find all gods deal, all wars fought and all faiths in mankind’ Yes every generation, perished or breathing have its own generational mission.
Ethiopia can’t be an anomaly in this regard. Each Ethiopian generation had its own generational mission some proved trans-generational and some other proved futile and abortive.
Upon the 1991 regime change in Ethiopia one of the prominent Ethiopia economists, Eshetu Chole puts the chance and hope of his generation as;
“History was giving us another chance to redeem two opportunities in less than a generation is a privilege seldom granted to a people; squandering both of them is a crime that will not be forgiven by posterity”
(Quoted in Tefera Degefe’s ‘minutes of an Ethiopian century’)
Poor Eshetu! We in the posterity are witnessing the second chance squandered flatly. But comrades, can’t we forgive the squanderers of the second chance in a generation? I hope we can. For a reason that we in the posterity should have something in excel than those who doomed the chance friends, might -have-been must leave its place for a by-gone is by-gone state of mind. I hope you are in my side.
A generation which misuse and abuse those two golden chances (As Eshetu mentioned) are still in the throne. And hunting the ‘Free spirit’ to death. Thus, we are not able to live our dreams and the spirit of our generation. But, by saying this I am not fool to dichotomize the problem in a ‘we’ and ‘then’ spectrum. Rather there are many ‘wes’ in them and the vice-verse.
When my generational clash thesis paled and blurred my puzzle reinvent itself and again forced me to ask if the problem is not a generational disparity, where its lies? Generation passed and Generation come but, those common denominators; turbines and trembling, the sound of the midnight knock, arbitrary arrest and summary execution, the feeling of the muzzle in the back, the sword in the nape, the cuff in the hand and that weird sound of ‘hands-in-the-air’ remains to live with us.
Comrades in those good-old class session side talks, we talk about a lot of things. But, I don’t remember about raising this grand issue of why we as a nation condemned to live in a state of terror? If we already talked about it take this note as a reminder, If not please think over it for the sake of our comradeship.
(By the way, when I am writing this, I am not about whether ‘they’ initiate a new criminal change against me for a ‘crime’ of inciting students to think. Because the state that we are living is a state that proclaims right as wrong, righteousness as wrong doing and the gun-bearer as the peace-lover.)
Sisters and brothers, to sum-up I am saying that our good nation is in a swamp of problems. To give answer for those problems first we have to identify the problems in a solvable manner. But my puzzle lies here, what are those problems? I mean the extent of the complexities makes the problem headless and tailless. Spotting the head and the tail of our problem is a mission that our generation shouldered. If we are done with that my state of bewilderment will be resolved.
The hopefull
Here the remand center of our cells have high windows that I developed a habit of staring to the darkness in the night time. Six months after my incarceration something beautiful happened via those windows. A full snow-white moon glares in those windows. Yes Jelaluddin  Rumi was right when he said ‘The moon won’t use the door, only the window’. A sight of the moon after a long wait was something new for me comrades. Because I am a prisoner. But that is what I called ‘Hope’, to wait and to see the moon. A lone awaited dream fulfilled.
Comrades, we are living in a state which employed a policy of ‘blood and iron’ in a form of ‘arrest and pardon’. In such a state freedom is omnipresent and dissent costs a lot of price, hope is the only shelter to hide.
After examining many failed human life projects, the sixth century Greek poet Theogins Megara concludes as ‘Hope is the only good god remains among mankind’, By now, I can’t say Megara was wrong.
I used to despise hope as a weapon of the weaklings. Even I was dare enough to say ‘is audacious about hope. Rather hope is overrated.’ I remember my feeling after reading Alber Camus’s double edged blow to hope and hopelessness as ‘Humans must learn to live beyond hope and hopelessness’ on his ‘the myth of Sisyphus’ which I endorsed.
Now I realize that it was one of my regrettable stances. Now I am re-reading Sisyphus’s story in a different state of mind I mean even Sisyphus, a poor creature who was condemned to do the something, forever, was hopeful for change in his life.
I know my present state of living is temporal. Thus, while Sisyphus who is condemned eternally was hopeful, why not me?
Friends, one of the ‘joy’ of prison is the plenty of time that you have to think, thanks to my detention, I got the time to audit the last ten thousand day that I live in flesh and blood. (By the way, funnily I was arrested in the week that I was celebrating the tenth thousand day of my life, if I am not mistaken). And my auditing should that there is nothing hopeless about the future.
In the state that I stand by now, even if I understand the situation of hopelessness. Rather again and after Patrick Henery’s brave state of questioning as. ‘If life so dear, or peace so sweet as to be purchased at the price of chains and slavery?’ is echoing in my ears, as if I were one of the attendants when Henery speaks.
Comrades, I am nostalgic of everything, the sessions, what we talk, even the greeting. My hope is that we will meet again. Upon my farewell Theognis  Megara is here again saying ‘As long as many lives and sees the light of the sun, let him … count on hope.’ Yes, as long as our comradery exist, let us count on hope.
O! Tyranny what a loser are you!? Whatever you are doing, for us there is hope and reminiscence!

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች በባህርዳር በተሰባሰቡበት ወቅት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፣ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋም የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ መሆኑን ለማስረዳት ነው። ዶ/ር ሽፈራው ከአፋር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ” መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል? ለምንስ በአገራችን የሌለ ችግር ያመጣብናል?” በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ሰዎች እንደገለጹት በአፋርና በኢሳ መካካል ያለውን የቆየ የድንበር ውዝግብ ተከትሎ መንግስት የተወሰኑ ቦታዎች ወደ አፋር ክልል እንዲካተቱ መወሰኑን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ 7 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ሲገደሉ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ሰዎችም ተይዘው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አሁንም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስትን …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንግድ ሚኒስቴር የዋጋ ቅናሹን ካደረገ በሃላ ማደያዎች አዲሱ ታሪፍ አያወዋጣንም በሚል መናገራቸውን ተከትሎ የአቅርቦት እጥረት የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴሩ የተወሰኑ ማደያዎችን በማሸግና በማስፈራራት ነገሩን ለማርገብ ቢሞክርም ችግሩ ሳይቀረፍ  8ኛ ቀኑን ይዞአል፡፡ በቦሌ፣ በካዛንቺስ፣ በንፋስስልክ በሌሎችም የከተማዋ አካባቢዎች በየማደያው ረጃጅም ሰልፎች የሚታዩ ሲሆን የችግሩ ትክክለኛ መንስኤ ምን እንደሆነ እንዳላወቁያ ያነጋገርናቸው …

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደሰገበው በታሊባን የተፈጸመ ነው በተባለው በሲህ ጥቃት ከሞቱት መካከል በርካታዎቹ ህጻናት ናቸው። ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ አምስት ወይም ስድስት የሚሆኑ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ መግባታቸውን የትናገሩት ባለስልጣናቱ፤ ወዲያውኑ አካባቢው በደህንነቶች እንዲከበብ መደረጉን ተከትሎ የተኩስና የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን ተናግረዋል። ወደ 500 ከሚጠጉ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በርካቶቹ ማምለጣቸውን …

በጁባ ጭፍጨፋ የተፈጸመበት አንደኛ ዓመት ያሉትን በጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወሱት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች ፕሬዚደንት ሳልቫኪር ማያርዲት የኑዌር ተወላዶችን ለይተዉ አጥቅተዋል ሲሉ ወንጅለዋል።

(አሥራት አብርሃም – የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ‹‹የአንድነት እስትራቴጂ ከሁሉም ይለያል!›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ ገጹ ያተመው) በምርጫው እንደሚሳተፉ እርግጠኛ ሳይሆኑ የምርጫ ምልክት ከወሰዱ ፓርቲዎችና በሂደቱ በደመነፍስ ከገቡ ፓርቲዎች አንድነት በእርግጠኝነት የተሻለ አቅጣጫ ያስቀመጠ ፓርቲ ነው። የፖለቲካውን ምህዳር ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር በማስፋት በምርጫው ላይ በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ወስኗልና። አንድነት በባዶ መሬት ህዝቡን ሳያደራጁ ህዝባዊ አመፅ ከሚጠሩትም በእጅጉ የተሻለ እቅድ ያለው ፓርቲ ነው! አሥር ሰው ይዞ ፓርቲ መመስረት ይቻል ይሆናል አሥር ሰው ይዞ ስርዓት መቀየር ግን የሚታሰብም፤ የሚቻልም አይደለም። ስለዚህ እስኪ በመጀመሪያ ህዝቡ ከጫፍ እስከጫፍ ይደራጅ፤ እስኪ በምርጫው ሂደት በንቃት እንዲሳተፍ እናድርገው፤ ከዚያ ባግባቡ የተደራጀ ህዝብ ምን ማድረግ እንደሚችል ለማየት ቀላል ነው የሚሆነው። መምረጥ የሚችል ዜጋ ሁሉ በትክክል የህዝብ ታዛቢዎች ይምረጥ፤ የምርጫ ካርድ በነቂስ ወጥቶ ይያዝ፤ እንደገናም በነቂስ ወጥቶ ይምረጥ ይህን ሁሉ ሂደት ከታለፈ በኋላ ምርጫው የሚዘረፍ ከሆነ ያኔ ይህ የተደራጀ ህዝብ ህዝባዊ እምቢተኝነት ለማካሄድ በቂ የሆነ ምክንያት ይኖረዋል። የአንድነት እቅድ ይሄ ነው፤ ሌላ እቅድ አለኝ የሚል ካለ መብቱ ነው፤ አንድነት በእኔ እቅድ አጨብጫቢ ሆኖ ይሰለፍ ማለት ግን ተገቢ አይደለም፤ ተቀባይነትም የለውም። አንድነት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ መዋቅር ያለው፣ ስለአባላቱና ስለህዝቡ ሀላፊነት የሚሰማው ፓርቲ ንው። ከዚህም ባሻገር የነገው መንግስት መሆን የሚያስችለው ቁመናና ስብስብ ያለው ፓርቲ ነው። በዚህ ምክንያት በእርሱ ክብደት ድልድዩን አንቀጠቀጥነው ለማለት ለሚመኙ ሁሉ የሚመች ፓርቲ አይሆንም፤ ከሆያሆዬ ፖለቲካ ነጥሮ ከወጣም ቆይቷል። […]

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የሊማዉ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ የበለፀጉትና ደሀ ሃገራት ለአየር ንብረት ለዉጥ ሊደረግ ይገባል የሚሏቸዉ አጣዳፊ ጉዳዮች በመለያየታቸዉ ምክንያት ብዙም ዉጤት ያመጣል የሚል ተስፋ ሳያሳድር ነበር የተጀመረዉ።

በምዕራብ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት ማለትም በሴራሊዮን በጊኒና ላይቤርያ የኤቦላ ወረርሽኝ ስርጭት አሁንም አልተገታም። ናይጀርያዊዉ የተዋሐሲ ጉዳዮች ጥናት ባለሞያ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በምዕራብ አፍሪቃ የኤቦላ ተዋሐሲ ጨርሶ አለመጥፋት ዋና ምክንያት የአፍሪቃዉያኑ ዉሳኔ ሰጭዎች የአሠራር ጉዳይ ነዉ፤

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን በሚደግፉ የመንግሥት ወታደሮችና በቀድሞዉ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ደጋፊ ኃይላት መካከል የተጀመረዉ ጦርነት አንድ ዓመት አስቆጠረ።

ዘጠኝ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ሳምንት የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ የፓርቲው አባላት መታሰራቸው ከፖለቲካ ጥላቻ የመነጨ ነው ሲሉ የፓርቲዎቹ ትብብር ሊቀ መንበር ኢንጅንየር ይልቃል ጌትነት ገለጹ።

በደቡብ ጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አቅራቢያ ለስደተኞች በተሰናዱ መጠለያዎች ላይ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ፤ ቃጠሎውም ሆን ተብሎ እንደደረሰ የሚጠቁሙ የፅንፈኞች ምልክቶች በመገኘታቸው ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ ከተሞች ዘረኝነትን የሚቃወሙ እና የሚደግፉ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሲየራ ልዮን የብዙ ሺዎችን ሕይወት እያጠፋ ያለውን የኤቦላ ወረርሽኝ ለማጥፋት ከያቅጣጫው ጥረቱ ተጠናክሮዋል። በዚሁ መሠረትም፣ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች ባለፈው ዓርብ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን የፀረ ኤቦላ ትግል ግብረ ኃይል አስተባባሪ በጠራው ስብሰባ ላይ በመገኘት

ሀሳን አሊ ለበርካታ አመታት የአሸባብ አባል ሆነው ሰርተዋል። መፃፍ እና ማንበብ በመቻላቸውም በተለያዩ የቡድኑ ዘርፎች ተሰማርተው ነበር። ሀሳን አሊ የአሸባብ ቡድንን እንዴት እንደተቀላቀሉ እና በምን ምክንያት ቡድኑን እንደከዱ፤ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።

በምዕራብ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት ማለትም በሴራሊዮን በጊኒና ላይቤርያ የኤቦላ ወረርሽኝ ስርጭት አሁንም አልተገታም። ናይጀርያዊዉ የተዋሐሲ ጉዳዮች ጥናት ባለሞያ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በምዕራብ አፍሪቃ የኤቦላ ተዋሐሲ ጨርሶ አለመጥፋት ዋና ምክንያት የአፍሪቃዉያኑ ዉሳኔ ሰጭዎች የአሠራር ጉዳይ ነዉ፤

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ባለው ዘመቻ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ አለ። ፓርቲው በአሁኑ ጊዜ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች መዋቅሩን መዘርጋቱናን በየትኛውም ደረጃ የምክር ቤት እጩዎችን ለማቅረብ እንደሚችል ገልጿል።

“ሰማያዊ/ትብብሩ ምርጫዉን ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመሳተፍ መወሰናቸው ታወቀ” በሚል የትብብሩን ዋና ጸሐፊ አቶ ግርማ በቀለን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወቃል። አቶ ግርማ በቀለ “NO Precondition is set by members of Tibibir. We decided to be part of the election and advised all members to take their election Sign. Believe me, it is all the decision of Tibibir […]

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አንድነት ፓርቲ ከአሁን በፊት ቀደም ብሎ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል ሰፊ የሆነ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ የሚታወቅ ነው። በመቀጠል ደግሞ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነትና የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች የሚሉ ዘመቻዎች በተከታታይ አካሄዷል። የዚህ ዘመቻ የመጨረሻው ምዕራፍ የሆነው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃና ፍትሀዊ ምርጫ በዚሁ እጅግ የተሳካ ጉባኤ ባካሄድንበት ማግስት የሚካሄድ በመሆኑ ፓርቲያችን ባሁኑ […]

Image
Eyasped Tesfaye
ይህን ሁለት ቀን በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ በትብብሩ እና በፓርቲዬ ላይ እየተናፈሰ ያለውን አቧራ ማጥራት ግዴታ ስለሆነብኝ የሚከተለውን ፅፊያለሁ፡፡ ልቦና ያለው ልብ ይበል፡፡
ሰማያዊ እና ትብብሩ የምርጫ ምልክት ወስደዋል እንዲሁም ደግሞ የትብብሩ ዋና ፀሀፊ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫው እንደሚሳተፉ በፌስቡክ ገፃቸው መግለጫ ሰጥተዋል በሚል ከተለያዩ አቅጣጫዋች የተለያዩ ድንጋዮች እየተወረወሩ ነው፡፡ የዚህ ነገር መነሾ ለእኔ ሁለት ምክንያት ያለው ይመስለኛል፡፡
1ኛ፡- ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድነት ፓርቲ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫው እሳተፋለሁ ማለቱን ተንተርሶ በሶሻል ሚዲያው ላይ አንድነት ፓርቲን የሚያጥላሉ ፅሁፎች በርክተው ነበር፡፡ አሁን እንደገባኝ ከሆነ ወንድሜ አስራት አብርሀምን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች አንድነት ላይ ዘመቻውን የከፈቱት ሰማያዊዎች ናቸው የሚል ግንዛቤ ወስደው የነበረ ሲሆን የአሁኑ ፅሁፋቸው የመልስ ምት እንደሚሉት አይነት መሆኑ ነው፡፡ በወቅቱ ግን ወዳጄ ዮናታን ተስፋዬ(የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ) በፌስቡክ ገፁ ላይ ከዚህ በታች በፎቶ ያያዝኩትን ፅሁፍ ፅፎ ነበር፡፡ ሰሚ አላገኘም እንጂ፡፡
2ኛ፡- የሰሞኑን አቧራ ያስነሱት ሰዎች ምርጫውን ያለምንም ቅድመሁናቴ እንሳተፋለን ብሎ መግለጫ በመስጠት እና ‹ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ› ብሎ ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን በመታገል መካከል ያለውን ልዩነት በቅጡ ያልተገነዘቡ ናቸው፡፡
ማብራሪያ፡-
ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ስምንት ፓርቲዎች በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል እንቅስቃሴ እያደረጉ እናዳለ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ የዚህን እንቅስቃሴ ስያሜ እንኳን በቅጡ ብናየው ሁለት ነገሮችን እንገነዘባለን፡፡ የመጀመሪያው ነገር ነፃነት ሳይኖር ምርጫ ሊኖር አይችልም ስለዚህም ነፃነት የምርጫ ቅድመሁናቴ ነው የሚል ሀሳብ የያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በነፃነት የሚደረግ ምርጫ እንዲኖር ትግል እንደሚደረግ አመላካች ነው፡፡
ከፊታችን የሚደረገው የ2007ቱ ምርጫ ነፃና ፍትሀዊ እንዲሆን ታግዬ ነፃ ሲሆን እሳተፋለሁ ማለት እና ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫ እሳተፋለሁ ብሎ መግለጫ መስጠት ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ ለነገሩ የዛሬው ጫጫታ ከጀርባው ሌላ ተንኮል እንዳለው አንዱ ማሳያ የትብብሩ ፀሀፊ የሆኑት አቶ ግርማ ከዛሬ 10 ቀን በፊት ከግርማ ካሳ ጋር በኮመንት ሲከራከሩ ኮመንት ያደረጉትን ነገር አዲስ መግለጫ እንደሰጡ በማስመሰል ‹‹ሰማያዊ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫው እንደሚሳተፍ ገለፀ›› ብሎ ዜና መስራቱ በራሱ የጤነኝነት አይመስልም፡፡ ምናልባትም ሰማያዊም ሆነ ትብብሩ ነፃነት ከሌለ ምርጫ የለም በሚል በያዙት ጠንኳራ አቋም ምክንያት ያገኙትን ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ለማሳጣት የታለመም ይመስላል፡፡
ሰማያዊ የምርጫ ምልክት ወሰደ ማለትስ በምርጫው ውስጥ ያለምንም ቅድመሁናቴ በምርጫው እሳተፋለሁ ብሎ መግለጫ ሰጠ ወይም ወሰነ ማለት የሚሆነው እንዴት ነው??? ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ 2007ትን ከወዲሁ ቦይኮት ማድረጉን ቢገልፅ እና ከሂደቱም ራሱን ቢያገል፤ በአንፃሩም ሰማያዊ እና ትብብሩ ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ በሚል እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ውጤት ቢያመጣና ምርጫው ነፃ ቢሆን ማን በጠረገው መንገድ ማን ሊሄድ ነው??? ይህ የነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚለው ትግል እኮ ቢያፈራ ፍሬውን ለመሰብሰብ በሂደቱ ውስጥ መቆየት ግድ ነው፡፡
አንድነት ያለምንም ቅድመሁናቴ በምርጫው እሳተፋለሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱን አልቃወምም፡፡ አባላቶቼን ከወዲሁ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳኛል ብሎ ይሆናልና፡፡ ልክ እንደዚሁም ሁሉ ሌላውም የእኛን አቋም እንዲያከብርልን እሻለሁ፡፡ ሰማያዊ እና ትብብሩ ምርጫ የሚኖረው ነፃነት ሲኖር ነውና ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ ብለው እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ አዲስ ነገር የለም! አይኖርምም!!!

Image

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

አንድ የሌላ ፓርቲ ደጋፊ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርጫው ውስጥ ስለመግባትና አለመግባት ላይ ባነሳው ክርክር የግል አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ይህ የግል አስተያየትም ትብብሩም ሆነ አባል ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ሳያነሱ ወደ ምርጫው እንደሚገቡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል፡፡

አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የምርጫ ፓርቲ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምርጫ ፓርቲ ሆኖ እንደ ስልት በምርጫ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ የሚችለው በምርጫው ሂደት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ፓርቲ ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በምርጫ ነውና ምርጫ እገባለሁ ብሎ ሊያውጅ አይችልም፡፡ የምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ከምርጫው ራሱን አገለለ ማለት አይደለም፡፡ እኛ በምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከአሁኑ ራሳችን ከምርጫ ያገለልን የሚመስላቸው አካላት አሉ፡፡ ግን እኛ ራሳችን አላገለልንም፡፡ ከአሁኑ ምርጫ እንሳተፋለን ብሎ ማወጅም አላስፈለገንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡

ስለሆነም ምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄዎችን አንስተን ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ ስለሆነም በምርጫው ሂደት ላይ አለን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሂደቱ ላይ አለን ማለት ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ምርጫውን እንሳተፋለን ማለት አይደለም፡፡ በምርጫው ሂደት ሲሳተፍ ቆይቶ ሂደቶቹ ፍትሓዊ ባለመሆናቸው፣ የተነሱት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በሂደቱ ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው ራሱን ከምርጫው ያገለለ ፓርቲ አውቃለሁ፡፡

ከአሁኑ ምርጫው ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከምርጫው ራሳችን አግልለናል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ፍትሓዊ ካልሆነ አጃቢ መሆን አንፈልግም፡፡ ለዛም ነው ሂደቱን ለማስተካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል እየታገልን ያለነው፡፡ በትግላችን መሰረት ሂደቱን እናስተካክለዋለን ብለን እናስባለን፡፡

ፓርቲያችን አንድነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ በሠላማዊ ትግል ትንቅንቅ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ግንባር ቀደሙ ነው!

በትግሉ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ በመክፈል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ልዕልና እየተጋ ያለው ፓርቲያችን በየጊዜው በሚገጥሙት መሠናክሎች ከመዳከም ይልቅ እየጠነከረ፤ ውስጣዊ ዴሞክራሲው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበተ የመጣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄ በአስተማማኝ መንገድ ለመመለስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቁርጠኛ አባላትን ያፈራ በመሆኑ ኩራታችን ከፍ ያለ ነው፡፡

አንድነት በ2ዐዐ7 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ አሸናፊ ኃይል ሆኖ ለመውጣት መሠረተ ሠፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ ሠፊ እንቅስቃሴያችን ምክንያትም ገዢው ፓርቲ በአባላትና አመራሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የእስር፣ የማሳደድና የማጥፋት ሥራ እየሰራ ቢሆንም ፓርቲያችን ይህንን ሁሉ ጫና በመቋቋም አሁንም በሠላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ በቁርጠኝነት ቆሟል፡፡

ለዚህ ቁርጠኝነታችንና ፓርቲያችን ስላለው መሠረተ ሠፊ አደረጃጀት ከዚህ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በላይ ምስክር የለም፡፡ በአንድ ሳምንት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ጉባኤ ለማድረግ ችለናል፡፡ ይሄ ፓርቲያችን የደረሰበትን እድገት የሚጠቁም ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ፓርቲዎችም አርአያ ለመሆን የሚበቃ ነው፡፡

እኛ የእዚህ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አባላትም በዛሬው እለት ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባም የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፈናል፡፡

1. የፓርቲው ብ/ም/ቤት የቀድሞው የፓርቲው ፕሬዚደንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ብ/ም/ቤቱ ባለው የጠቅላላ ጉባኤ ውክልና መሠረት ያካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተገቢና ሕገ-ደንባዊ መሆኑን አረጋግጦ አቶ በላይ ፍቃዱን እስከሚቀጥለው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው ፕሬዚደንት እንዲሆኑ በከፍተኛ ድምጽ ወስነናል፡፡

2. በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ ከብ/ም/ቦርድ የሚፈለጉ ማብራሪያዎችን እና ሃሳቦች ተከትሎ ጠቅላላ ጉባኤው የተወሰኑ ማሻሽያዎች አድርጓል፡፡

3. መድረክን በተመለተ በፓርቲያችን ላይ የጣለውን ሁለተኛ እገዳ ተከትሎ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ በወሰነው መሠረት ብ/ም/ቤቱ ከመድረክ እንዲወጣ የወሰነውን ውሳኔ ተገቢ ሆኖ ስላገኘው በከፍተኛ ድጋፍ አፀድቋል፡፡

4. ገዢው ፓርቲ ህገ መንግሥቱን በመጣስ በእየእስር ቤቱ ያጎራቸውን የዴሞክራሲ አርበኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጉባኤው አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

5. የዜጎችን በነፃ የመደራጀት ነፃ አመለካከታቸውን በአምባገነንነት በማፈን ያሰራቸውን የነፃነት አርበኞች ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች፣ የቤተ እምነት መሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን መንግሥት በሩን ለብሔራዊ ውይይት ክፍት እንዲያደርግ ጉባኤው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

6. የተቀማነውን ነፃነታችንን በድምፃችን ለማስከበር ‹2ዐዐ7 ለለውጥ› የሚል የህዝባዊ ንቅናቄ ዘመቻ አንድነት በዛሬው እለት ጠቅላላ ጉባኤው አውጇል፡፡ ስለዚህ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው በንቃት በመሳተፍ በምርጫ ካርዱ ነፃነቱን እንዲያስከብር አንድነት ፓርቲ ጥሪውን ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ነፃነታችንን እናስከብር!

የአንድነት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሣሥ 3/2ዐዐ7 ዓ.ም
አዲስ አበባ

* ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል
* በምርጫው ልንሳተፍም ሆነ ላንሳተፍ ውሳኔ የምናሳልፈው እኛ ሳንሆን ሂደቱ ነው
ትንሽ ስለ አንዳንድ ጉዳዮች ማብራሪያ አቀርባለሁ ዮናታን ተስፋዬ ረጋሣ

ኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ምርጫ ስላለመግባቱ እንጂ ምርጫ ስለመግባቱ ዜና ሲሆን በጣም ግራ ያጋባል፡፡ ምርጫን መሳተፍ አንዱ የትግል አካል የሆነውን ያህል አለመሳተፍ የራሱ የሆነ ፋይዳ አለው፡፡ ያን የሚወስነው ግን ሂደቱ እንጂ ፓርቲዎቹም ይሁኑ ምርጫ ቦርዱ አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር በሂደቱ ውስጥ አንድ ፓርቲ ወይም ፓርቲዎች አንሳተፍም ሊሉ ይችላሉ (ህጋዊነትም አለው)፡፡ ምክንያታቸውንም በዝርዝር አስቀምጠው መግለጫም ይሁን ሌላ ሌላ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ያም ዜና ከመሆን ባለፈ ባጠቃላይ የህዝቡንም የዓለም አቀፍ ማሕበረሰቡንም ትኩረት ያገኛል፡፡
ከዚህ ውጪ ግን አንዱ ያለ ቅድመ ሁኔታ ምርጫ እሳተፋለሁ ስላለ እና ሌላው ደግሞ ሂደቱ እንዲወስን እድል ስለሰጠ ምርጫ ተሳታፊና ምርጫውን የማይሳተፍ ብሎ ማቅረቡ በራሱ አንድም ስህተት ነው ሲልም ከንቱ ራስ ማዋደጃ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡ ይህ ግልፅ ነገር እንዲገባው ያልፈለገ እና ህመም የሆነበት ማስታገሻ ወስዶ ቢያርፍ መልካም ነው፡፡
ጓደኞቼም ሆነ እኔ ኢሳትና ቪኦኤን ጨምሮ በብዙ መገናኛ ብዙኃን እና በዲፕሎማቶች በኩል በተደጋጋሚ በምርጫው ጉዳይ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ የያዘውን አቋም በተጠየቅንበት ወቅት የሰጠነው የማያሻማ መልስ ከላይ ያሰፈርኩትን ነው (ሚዲያዎቹ ላይ ፈልጎ መስማት ይቻላል)፡፡ ‹‹ምርጫ ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ አሁን የመወሰኛ ጊዜ አይደለም፤ ሂደቱ እንጂ እኛ(ተቃዋሚም ይሁን ኢህአዴግ) አሁን ልንወስነው የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡›› ይህ በግልፅ የሚያሳየው ነገር ሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ እንደምንሆን ሲሆን ለመጨረሻው ውሳኔ ግን በወቅቱ የሚፈጠረው ሁናቴ እንደሚወስን ነው!
እንደ አንድ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኮሚቴና ጊዜውን መሰረት ባደረገ 70 ሰው ያቀፈ የምርጫ ግብረሃይል አቋቁመን፣ የዓመቱ እቅዳችንም በምርጫ ላይ ሆኖና በትብብሩም የጀመርነው ዘመቻ ‹‹ነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› እያለ ለምርጫ የማንዘጋጅ አስመስሎ ማቅረቡ ምንአልባት ከተሳሳተ ግንዛቤ አልያም ከተንኮል ያለፈ ሊሆን እንደማይችል ግልፅ ነው፡፡ የምርጫ ምልክትን መውሰድም የሂደቱ አካል እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ አይደለም፡፡ ከዚህ ተነስቶም በእርግጠኛነት ምርጫ ይሳተፋሉ ብሎ መደምደም ተገቢ ነው ብዬ አላምንም! ባጠቃላይ ግን ለምርጫው ያስቀመጥናቸውን ቅድመ ሁኔዎች በሂደቱ የማይመለሱ ከሆነ ያኔ ውሳኔው ከነምክንያቱ ይፋ ይሆናል ማለት ነው፡፡
በግልፅ ቋንቋ ምርጫውን ለመሳተፋችንም ሆነ ላለመሳተፋችን አጠቃላይ ሂደቱ፣ በሂደቱ ውስጥም ያነሳናቸው ጥያቄዎችና ያስቀመጥናቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንጂ ማናችንም ወሳኝ ልንሆን አንችልም! የምርጫ ምልክትም ስንወስድ መነሻችን ይኸው እውነታ እና ነባራዊ ሁኔታ ብቻ ነው! ይህ የኛ መንገድ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ያለ ቅድመ ሁኔታ ባለው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ምርጫ እሳተፋለሁ ብለው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ምንም ይሁን ምንም፣ ሂደቱ ይመርም አይመርም ምርጫውን ለመሳተፍ ወስነው ወደ ስራ የገቡትን ውሳኔያቸውን አከብራለሁ፡፡
የመረጥነውን መንገድ መደገፍም መንቀፍም ያባት ነው፤ እየጠመዘዙ ሌላ መልክ እንዲይዝ ማድረግ ግን ራስን ከማስገመት ያለፈ ጥቅም ያለው መስሎ አይሰማኝም፡፡
(ይህ ርዕስ ከዚህ በላይ መወያያ ባይሆን ምኞቴ ነው!)
ሊንኩን በመጫን ለምርጫ ቦርድ የስገባውን ደብዳቤ እና ያስቀመጥናቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ይመልከቱ፡-
https://www.facebook.com/semayawiethio/ … =3&theater

የግንቦት ሰባት ከፍተኛ ኣመራሮች ኣስመራ ገቡ ሲሉ የድርጅቱ ካድሬዎች ተናግረዋል

በዚህ ሰሞን የሚወጡ ዘገባዎች አንደሚያመለክቱት የተከበሩ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አና የግንቦት ሰባት ሚዲያ ኢሳት ሃላፊ አና የግንቦት ሰባት ምክትል የሆነው ኣቶ ነእመን ዘለቀ ያሉበት ቡድን ኣስመራ ገብተዋል ሲሉ የድርጅቱ ካድሬዎች ውስጥ ውስጡን የሚያናፍሱት መረጃ ጠቁፙል፥፥

ዶክተር ብርሃኑ ኣስመራ በተደጋጋሚ በኢሳያስ ኣወርቂ ተጠርቶ አንዳልሄደ የሚናገሩት ኣስተያየት ሰጪዎች በሃሰት አና በተስፋ ህዝቡን ለመደለል የሚደረግ ፕሮፓጋንዳ ነው፥፥ተደብቆ መህዐድ ምን ኣስፈለገ ከሄዱ በህWላስ ለምን ይፋ ኣይደረግን ማበረታቻ ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል፥፥አንዲህ ኣይነት የውስጥ ሹክሹክታ ድርጅቱን ለፖለቲካ ኪሳራ አንዳይዳርገው ሲፈራ ከኣሁን ቀደም በኣንዳርጋቸው የመጣውን የፖለቲካ ቁስል ሳያክም ወሬ ማናፈስ አንደማያዋጣ ኣስተያየት ሰጪዎች ኣስረግጠው ተናግረዋል፥፥

Image
በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ለሽርሽር የሄዱት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች 12 ስዊድናውያን የተኩስ እሩምታ ወረደባቸው
ኢሳት ራድዮ ታህሳስ 6/2007 ዓም እንደዘገበው በግድያ ሙከራው ላይ የስዊድን የመገናኛ ብዙሃን በብዛት እየዘገቡበት መሆኑን ያብራራል።እንደ ዘገባው በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ለሽርሽር የሄዱት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች 12 ስዊድናውያን የነበሩ መሆኑን እና የተኩስ እሩምታ እንደወረደባቸው ይገልፃል።አቶ ሞላ ይግዛው በስዊድን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፎረም ምክትል ሊቀመንበር በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል –

”አስራ ሁለት የስዊድን ዜጎች አምባሳደሩን ጨምሮ ይላልእዛ ላይ አራት ሰዎች የጫነው መኪና ላይ ስዊድናውያንን ለመግደል ያለመ እና ያነጣጠረ ተኩስ ነው የተከፈተው።ከእዚህ ጋር በጥያየዘ ባለፈው ጊዜ H&M የተሰኘው ድርጅትን ያጋለጠ አንድ ጋዜጠኛ በእዛ አካባቢ ወይም ደቡብ ኢትዮያ የሚደረገውን ግፍ ለዓለም ማጋለጡ እና በዓለም የሌለ ዲክታተር መባሉ ይታወቃል።ከእዛ በፊት አንድ ቀን የስዊድን የጦር ፍርድቤት ያቀረብነውን የወንጀል ክስ ተቀብሎ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቆ ነበር።በመሆኑም ይህንን ያደረገው ወያኔ ነው ሌላ ሊሆን አይችልም” ብለዋል።

ኢሳት ራድዮ በመጨረሻ ላይ እንደገለፀው ጉዳዩን የስዊድን ጋዜጦች፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ሌሎች የመገናኝ ብዙሃን ሽፋን ቢሰጡትም ኢህአዲግ ም ሆነ የሚቆጣጠራቸው ራድዮ እና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም ያሉት ነገር እንደሌለ ይገልፃል።

Image
በቅርቡ የአንድ ወር መርሃ ግብር አዉጥቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲና የዘጠኝ ድርጅቶች ስብስብ፣ ፓርቲዎች ትብብር፣ ያለ ቅድሜ ሁኔታ በመጪው የ2007 ምርጫ እንደሚሳተፍ አሳወቀ። ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን የምገልጹ አንዳንድ ዘገባዎች በተለይም በዳያስፖራ አካባቢ የሚሰሙ እንደሆነ ቢታወቅም፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ አቶ ግርማ በቀለ በፌስ ቡክ በግልጽ በሰጡት አስተያየት፣ ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ አለማስቀመጡን ገልጸዋል።

“NO Precondition is set by members of Tibibir. We decided to be part of the election and advised all members to take their election Sign. Believe me, it is all the decision of Tibibir that is under action by its members and Blue is not an exception to present and decisions are being made in participatory process.” ሲሉ የትብብሩ አባል ድርጅቶች ለምርጫ የሚያስፈልገውን የምርጫ ምልክት በአስቸኳይ ለመዉሰድ መስማማታቸውንም አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል።

በዚሁም መሰረት፣ የሰማያዊ ፓርቲንም ጨምሮ ሌሎች የትብብሩ አባል ድርጅቶች የምርጫ ምልክት ከሌሎች ድርጅቶች ቀድመው እንደወሰዱም የሚገልጹ መረጃዎች እየደረሱን ነው። ምርጫ ቦርድ ከአንድ ሳምንት በኋላ የድርጅቶቹን ምልክት ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ የሰማያዊን ጨመሮ የሌሎች ድርጅቶች የምርጫ ምልክትም ምን እንደሆነ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ የትብብሩን ዉሳኔ አስፈላጊና ጠቃሚ ዉሳኔ ሲሉት፣ ሰማያዊ/ትብብሩ ወደ ምርጫ ያለ አንዳች ቅድሜ ሁኔታ ለመሳተፍ በመወሰኑም፣ በምርጫው ረገድ ከአንድነት ፓርቲ ተመሳሳይ አቋም እንደያዘ በግልጽ ያመላከት እንደሆነም አስረድተዋል።

“ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ ለመግባት ሰማያዊ/ትብብር ከወሰኑ፣ ለምርጫው መዘጋጀት አለባቸው። ድርጅታዊ ሥራ ላይ ማተኮሩ የድግ ነው። ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸው ከነ አንድነት ጋር በምርጫው ረገድ መተባበር ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ እኙ ተንታኝ ትብብሩ ወደ ምርጫ ከገባ ዘንዳ የምርጫ ዘመቻውን አብሮ ከሌሎች ጋር ለማቀናጀት እንዲዘጋጅም ጠይቀዋል።

በተያይዘ ዜና የአንድነት ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች በማስመረጥ ዙሪያ በተቻለ መጠን ገለልተኛ የሆኑ የሕዝብ ታዛቢዎች እንዲመረጡ ለማድረግ በየዞኖቹና በየወረዳዎች ስምሪት እንደጀመረም ለማወቅ ችለናል።

አቡጊዳ


ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሲጠቀሱ በቅድሚያ የሚታወሱት በላስታ አውራጃ፣ በ“ሮሃ” (ላሊበላ) ከተማ አጠገብ ከአንድ-ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩት አስራ አንድ ቤተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ የአስራ አንዱ ቤተ ክርስቲያናት ስም እንደሚከተለው ነው፡፡
1.      ቤተ መድኃኒ-ዓለም
2.     ቤተ ማርያም
3.     ቤተ ደናግል
4.     ቤተ መስቀል
5.     ቤተ ሚካኤል
6.     ቤተ ጎለጎታ
7.     ቤተ አማኑኤል
8.     ቤተ ገብርኤል
9.     ቤተ አባ ሊባኖስ
10.    ቤተ መርቆሬዎስ
11.     ቤተ ጊዮርጊስ
እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙት በሦሥት የተለያዩ ስፍራዎች ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ስድስቱ በአንድ ስፍራ፣ ተከታዮቹ አራቱም በሌላ ስፍራ ላይ ነው የተሰሩት፡፡ ቤተ ጊዮርጊስ ግን ከሁሉም ተነጥሎ ለብቻው ቆሟል፡፡ ከአብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ ትልቁ “ቤተ መድኃኒ-ዓለም” ሲሆን በኪነ-ህንጻውና በዲዛይኑ በዓለም ዙሪያ የተደነቀው ግን በመስቀል ቅርጽ የተሰራው “ቤተ ጊዮርጊስ” ነው፡፡
እነዚህን ቤተ ክርስቲያናት ያሳነጸው ከ1181-1221 የነገሠው የዛግዌው ንጉሥ ገብረ መስቀል ሲሆን ይህ ንጉሥ በታሪክ ምዕራፎች በደንብ የሚታወቀው “ላሊበላ” በሚል ስም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ለንጉሥ ላሊበላ የቅድስና ማዕረግ መስጠቷ ይታወቃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በበኩሉ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን በዓለም ቅርስነት መዝገቦአቸዋል፡፡
       *****
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ደንብና ትውፊት መሰረት አንድ ቤተ-ክርስቲያን የሚታነጸው ሦሥት ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጎ ነው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል “መቅደስ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ታቦት (ጽላት) በዚህ ክፍል ውስጥ ነው የሚቀመጠው፡፡ በመቅደሱ ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅድላቸውም ካህናት ብቻ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ክፍል “ቅድስት” ይባላል፡፡ የ“ስጋ ወደሙ” ስርዓት የሚፈጸመው በዚህኛው ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ሶስተኛው ክፍል “ቅኔ ማህሌት” ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ በአንድ ወገን ደብተሮች ይዘምራሉ፡፡ በሌላ ወገን ቀሳውስት ሰዓታት ይቆማሉ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የሚመጡት ምእመናንም ስርዓተ ቅዳሴውንና ልዩ ልዩ ስብከቶችን የሚከታተሉት በዚህ ክፍል ውስጥ ነው፡፡
       *****
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክህነት ስር የሚተዳደሩት አብያተ-ክርስቲያናት በሶስት ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም ገዳም፣ ደብር እና “ገጠር” (አጥቢያ) በመባል ይታወቃሉ፡፡ “ገዳም” የሚባለው መነኮሳት ከዓለማዊ ኑሮ ተገልገለው የምንኩስና ህይወት የሚኖሩበት ቤተ-ክርስቲያን ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ገዳም የቆረቆሩት በ5ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ሶሪያዊው “አቡነ-አረጋዊ” ሲሆኑ በርሳቸው የተቆረቆረውም በትግራይ የሚገኘው የ“ደብረ ዳሞ” ገዳም ነው፡፡ ሌሎች ታዋቂ ገዳማት ደግሞ “ደብረ-ሊባኖስ” (በሰሜን ሸዋ፣ ሰላሌ አውራጃ ውስጥ የሚገኝ፣ በአስራ ሦሥተኛው ክፍለ ዘመን በኖሩት “አቡነ ተክለ-ሃይማኖት” የተመሰረተ)፣ “ደብረ ቢዘን” (በደቡብ ኤርትራ፣ ሰራዬ አውራጃ ውስጥ የሚገኝ፣ በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን በኖሩት “አባ ኤዎስጣቴዎስ” የተመሰረተ)፣ “ደብረ ወገግ” ወይንም የ“አሰቦት ገዳም” (በሀረርጌ ክፍለ ሀገር፣ በአሰቦት ተራራ ላይ የሚገኝ፤ “አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ” በተባሉት ታዋቂ መነኩሴና የብዙ መጻሕፍት ደራሲ እንደተመሰረተ የሚታመን) እና የ“ዋልድባ ገዳም” (በትግራይና ጎንደር ወሰን ላይ የሚገኝ፤ “አባ ሳሙኤል” በተባሉ መነኩሴ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የተመሰረተ) የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የገዳም አስተዳዳሪ ከመነኮሳቱ መካከል በዕድሜው፣ በስነ-ምግባሩ፣ በዕውቀቱ እና በገድሉ ተመርጦ “አባት” በሚል ማዕረግ ይሾማል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት “ደብር” ይባላሉ፡፡ እነዚህኛዎቹ በርከት ያለ ህዝብ በሚኖርበት ስፍራ የተሰሩ እና ሁለገብ የቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጡ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ ቆየት ባለው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትውፊት መሰረት ደብሮች የሚሰሩት በኮረብታ ላይ ነው፡፡ ደብሮቹ የሚጠሩትም በክርስትና ታሪክ ቅዱስ መሆናቸው በተመሰከረላቸው ቀደምት የሃይማኖት አባቶች፣ በሰማእታትና በመላዕክት ስም ነው፡፡
   የደብር አስተዳዳሪ “አለቃ” ይባላል፡፡ ሆኖም እንደ አስፈላጊነቱ “ንቡረ እድ”፣ “ሊቀ-ስልጣናት”፣ “መልአከ ጸሐይ”፣ “መልአከ ገነት” ወዘተ… በመሳሰሉ ማዕረጎችም ሊጠራ ይችላል፡፡ አንዳንድ ደብሮች በየዓመቱ የሚከናወኑ ታላላቅ የንግሥ በዓላትን በማስተናገድ ይታወቃሉ፡፡ በዚህ ረገድ ጎላ ብለው የሚጠቀሱት የአክሱም ጽዮን ማሪያም ቤተ-ክርስቲያን፣ የግሸን ማሪያም ቤተ-ክርስቲያን እና የቁልቢ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን ናቸው፡፡
“ገጠር” የሚባሉት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚሰሩ ቤተ-ክርስቲያናት ናቸው፡፡ እነዚህ ቤተ-ክርስቲያናት መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡት  ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው፡፡ የገጠር ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ “መሪ ጌታ”፣ “ጎበዝ” እና “አለቃ” በሚሉ ማዕረጎች ይጠራል፡፡
       *****
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስርዓት መሰረት ዘጠኝ ዐቢይ በዓላት፣ ዘጠኝ ንዑሳን በዓላትና ሰባት አጽዋማት አሉ፡፡ ዐቢይ በዓላት የሚባሉት “ልደት” (ገና)፣ “ጥምቀት”፣ “ደብረ ታቦር”፣ “ሆሳዕና”፣ “ስቅለት”፣ “ትንሳኤ”፣ “ዕርገት” እና “ጰራቅሊጦስ” ናቸው፡፡ ንዑሳን በዓላት የሚባሉት ደግሞ “መስቀል”፣ “ስብከት”፣ “ብርሃን”፣ “ኖላዊ”፣ “ግዝረት”፣ “ልደተ ስምዖን”፣ “ቃና ዘገሊላ”፣ “ደብረ ዘይት” እና “ሁለተኛው መስቀል” (መጋቢት አስር ቀን የሚውል) ናቸው፡፡
ሰባቱ አጽዋማት “ዐቢይ ጾም” (ሁዳዴ)፣ “ጾመ ሐዋሪያት”፣ “ጾመ ፍልሰታ”፣ “ጾመ -ነቢያት”፣ “ገሃድ”፣ “ጾመ ነነዌ” እና የ“ረቡዕ እና ዐርብ” ጾም ናቸው፡፡ የእምነቱ ተከታዮች ከቻሉ ሁሉንም አጽዋማት ይጾማሉ፡፡ ካልቻሉ ግን “ዐቢይ ጾም”ን፣ “ጾመ-ፍልሰታ”ን እና ረቡዕና ዐርብን የመጾም ግዴታ አለባቸው፡፡
       *****
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 5/2007
በገለምሶ ከተማ ተጻፈ፡፡
ምንጮች
1.      ሉሌ መልአኩ፡ “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ”፡ ትንሳኤ ብርሃን አሳታሚ ድርጅት፤ 1986
2.     ተክለ-ጻዲቅ መኩሪያ፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ከአጼ ልብነ-ድንግል እስከ አጼ ቴዎድሮስ፣ 1936
3.     Encyclopaedia Ethiopica: University of Hamburg: 2004: Volume 1-5
4.      የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ድረ-ገጽ (www.ethiopianorthodox.org )

በቅርቡ የአንድ ወር መርሃ ግብር አዉጥቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲና የዘጠኝ ድርጅቶች ስብስብ፣ ትብብር፣ ያለ ቅድሜ ሁኔታ በመጪው የ2007 ምርጫ እንደሚሳተፍ አሳወቀ። ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን የምገልጹ አንዳንድ ዘገባዎች በተለይም በዳያስፖራ አካባቢ የሚሰሙ እንደሆነ ቢታወቅም፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ አቶ ግርማ በቀለ በፌስ ቡክ በግልጽ በሰጡት አስተያየት፣ ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ አለማስቀመጡን ገልጸዋል። “NO Precondition […]

ኢቦላን ለመዋጋት ወደ ምዕራብ አፍሪካ ይጓዛሉ ለተባሉት ከ200 በላይ ሐኪሞችና ሌሎችም ባለሙያዎች አሁን በአዲስ አበባ ሂልተን አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያን የኢቦላ ምላሽ የሚያስተባብረ ው የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቤል የሻነህ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ሽኝቱ የተዘጋጀው ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዘማቾች ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ ባለሙያዎች ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚጓዙት የአፍሪካ ኅብረት ፀረ-ኢቦላ ምላሽ አካል ሆነው እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እስከአሁን የኢቦላ ተጠርጣሪም ሆነ የወረርሽኙ ምልክት ኢትዮጵያ ውስጥ አለመታየቱ በአይሮፕላን ጣቢያዎች ላይ እየተካሄደ ያለው ፍተሻና ክትትልም እንደቀጠለ መሆኑን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት – አይሲሲ አቃቤ ሕግ ዳርፉር ውስጥ የሚያካሄዱትን ምርመራ ለጊዜውም ቢሆን እንደሚያቋርጡ ከገለፁ በኋላ የሃገሪቱ “ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ንፁህ ሰው ስለመሆናቸው ማረገገጫ ነው” ሲሉ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አሕመድ ቢላል አስታውቀዋል፡፡

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አልበሽርን “የሰላም ሰው” ብለዋቸዋል ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ፡፡

ዳርፉር ላይ ሲያካሂዱ የቆዩትን ምርመራ እንደሚያቆሙ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፋቱ ቤንሱዳ ያሳወቁት “ለጊዜውም ቢሆን” በሚል ቢሆንም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ግን ይህ የቤንሱዳ ውሣኔ ከኦማር ሁሴን አል በሽር የሚገኝ “አንዳች ጥፋት ላለመኖሩ ማረጋገጫ ነው” ሲሉ የድል ብሥራት ከማውጣት አልቦዘኑም፡፡

አቃቤ ሕጓ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈው ሣምንት ሲናገሩ…

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ ትላንት በአዲስ አባባ ባካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው ምርጫ ነጻና ፍትሀዊ እንዲሆን ጠየቀ።

የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጣኞችና የሙስሊሙ ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል። የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ፤

 

(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ) የተቃዋሚዉ ጎራን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት አብይት ፖለቲካዊ ክስተቶችን አስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ትግል ሲኮላሽ የመድረክ ደግሞ ቀዝቀዝ ያለ በሚመስል መልኩ ተስተናግዷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በተስተጓጎለ በሳምንቱ የመድርኮቹ መሳካቱ ምን ሊያመላክት ይችላል የሚለውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የመድርኩን ሰልፍ ከራሱ ከመድርክ፣ ከመንግስትና ከህዝብ አንፃር ሊኖረው የሚችለውን እንድምታ አጠር ባለ መልኩ ለማየት እንሞክራለን፡፡ ሀ) ከመድረክ አንፃር መድርክ ከሌሎችና ፓርቲዎችና ከራሱም ያለፈ የትግል ልምድ የተማረው ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ፓርቲው ቀድሞ ከነበረበት ጽንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ በተወሰነ መልኩ ለዘብ እያለ መምጣት የሚያሳዩ ሁሄታዎችን መታዘብ ይቻላል፡፡ መድረክ ከሌጋሲው የተማረው ጉዳይ ቀድም ሲል በነበው ፅንፍ ይዞ የመታገል አቅጣጫ የመንግስትን የቁጥጥር ጫና እንዲሚያጠብቀው ሳይማር እንዳልቀረ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ባልተለመደ መልኩ ሌሎች ተቃዋሚዎች ክፉኛ የሚጥሉትንና መንግስት እየተጠቀመበት ያለውን ባንዲራ በሰልፍ ውስጥ መጠቀሙ በተወሰነ መልኩ ከአክራሪነት ለዘብ ያለ አቋም እያሳየ ለመምጣቱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ፓርቲው ወዶም ይሁን ተገዶ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢህአዴግ ጋር መመሳሰል ባይችል እንኳን መንግስት ከሚፈልገው የአቋም መለሳለስ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል የሚጠቁሙ ፍንጮች እንዳሉ መውሰድ ይቻለላል፡፡ በሌላ መልኩ መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን ዉጤት ተከትሎ መንግስት የሚሰጋባቸውን ችግሮች እንዳይከሰቱ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ለማድርግ ከመንግስት ጋር ስምምንት ላይ ሳይደርስ እንዳልቀረ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ፡፡ በአቋም እየተለሳለሰ መምጣቱና ለሰልፉ ኃላፊነቱን ከመንግሰት ጋር መጋራቱ ሰልፉን ስኬታማ ለማድረግ ሳይግዘው እንዳልቀረ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በ2002 ምርጫ ከኢህአዴግ ጋር […]