ፀረ ኤቦላ ትግሉን የማስተባበሩ ጥረት

በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሲየራ ልዮን የብዙ ሺዎችን ሕይወት እያጠፋ ያለውን የኤቦላ ወረርሽኝ ለማጥፋት ከያቅጣጫው ጥረቱ ተጠናክሮዋል። በዚሁ መሠረትም፣ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች ባለፈው ዓርብ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን የፀረ ኤቦላ ትግል ግብረ ኃይል አስተባባሪ በጠራው ስብሰባ ላይ በመገኘት