አቡጊዳ – ሰማያዊ /ትብብር እና ምርጫ
“ሰማያዊ/ትብብሩ ምርጫዉን ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመሳተፍ መወሰናቸው ታወቀ” በሚል የትብብሩን ዋና ጸሐፊ አቶ ግርማ በቀለን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወቃል። አቶ ግርማ በቀለ “NO Precondition is set by members of Tibibir. We decided to be part of the election and advised all members to take their election Sign. Believe me, it is all the decision of Tibibir that is under action by its members and Blue is not an exception to present and decisions are being made in participatory process” ያሉትን በመጥቀስ ነበር የሰማያዊ/ትብብር ወደ ምርጫ የመሳተፍ ዜና ያቀረብነው።
ይሄን ትንተና ተከትሎ ፣ የሰማያዊ/ትብብር ዋና ጸሃፊ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የሰማያዊ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ማብራሪያ ሰጥተዉበታል።
ሚኒሊክ ሳልሳዊ በፌስ ቡክ ገጹ እንደዘገበው፣ አቶ ግርማ “እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው” የሚል አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ዮናታን በበኩላቸው «ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል። በምርጫው ልንሳተፍም ሆነ ላንሳተፍ ውሳኔ የምናሳልፈው እኛ ሳንሆን ሂደቱ ነው» ሲሉ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን ይናገራሉ። የአቶ የሰማያዊ ፓርቲም ሆነ ትብብር በምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ምልክት መዉሰዳቸውን በተመለከተ አቶ ዮናታን «ምርጫ ምልክት መውሰድ እጅግ ተራ እና ትንሽ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ምርጫን ለመሳተፍ ማረጋገጫ ተደርጎ ሊቀርብ አይችልም» ሲሉ ጽፈዋል።