UTC 16:00 የዓለም ዜና 07.04.2014
ዜና
ፓሪስ ውስጥ በተካሄደው የማራቶን ሩጫ ውድድር አሸናፊ የሆነው ቀነኒሣ በቀለ ጡንቻው ላይ ህመም ባይሰማው ኖሮ የበለጠ ፈጣን ሠዓት ሊያስመዘግብ ይችል እንደነበር ለዶቸቬለ ገለፀ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል የዋንጫ ግስጋሴውን እያሳመረ ነው። ቸልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ ዋነኞቹ የሊቨርፑል ተፎካካሪዎች ሆነዋል።
የምርጫዉ ሒደት፤ነፃነቱ፤ አፎካካሪ፤ አሳታፊነቱም፤ ያዩ እንደመሰከሩት ፤ለእልቂት ፍጅት ማዕከሊቱ ታሪካዊት ሐገር አዲስ ታሪክ ነዉ።አፊቃኒስታን።ዘንድሮ አስራ-ሰወስት ዘመን የተዋጋባትን-የዉጪ ጦር ሸኝታ የአስራ-ዘመን ታሪኳን ለሚቀይር ሌላ ታሪክም ተሞሽራለች።
የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባ ክፍል ኦፊሰር የሆኑትን አቶ ማርቆስ ብዙነህን ለማነጋገር ዛሬ ጠዋት ወደ ቢሯቸው ያቀኑት ሶስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አመራሮች በኦፊሰሩ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ማግኘቱ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የ‹‹እሪታ ቀን›› በማለት የሰየመውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ለማድረግ ለመስተዳድሩ የእውቅና ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም መስተዳድሩ በከተማው የህዳሴ ግድቡን የተመለከቱ […]
አንድነት ፓርቲ ለመጋቢት 28/2006 ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለህዝብ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል በስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የሚገኙት አክሊሉ ሰይፉና ወርቁ እንድሮ መታሰራቸውን በመቃወም የርሃብ አድማ መምታታቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱ ወጣቶች እስከ ነገ የማይለቀቁ ከሆነ ሚክሲኮ በሚገኘው ፍርድ ቤት ከፖሊስ ጣብያ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ አንድነት የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ […]
መግቢያ በዚህ ጽሁፍ ሥር ለውይይት ይሆን ዘንድ የምናነሳው ኣሳብ constitutional patriotism ወይም ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት ወይም ኣርበኝነት የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ባለፈው በተከታታይ ካቀረብኳት የ Conventional Cultural Unity ወይም በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ ጋር እንዴት እንደሚለያይና በኢትዮጵያ ሁኔታ ከሁለቱ ኣሳቦች የትኛው ተገቢና ችግር ፈቺ ሊሆን እንደሚችል ኣሳብ ለማፍራት ነው። በቅድሚያ ኣንድን ፖለቲካዊ የሆነ […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
እኛ የምናውቃት ኢትዮጲያ ከግማሽ በላይ ህዝቧ በመብራትና በውሃ እጦት የሚሰቃይባት ፣ በስልክና በኔትወርክ ችግር የሚማረርባት ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት አሳሩን የሚበላባት ፣ አብዛኛው ህዝቧ የዛሬን እንጂ የነገን ማቀድ የማይችልባት ፣ የተለያዩ ተንታኞችና አለማቀፍድርጅቶች “ችግር አለ” ብለው የሚያስጠነቅቋት ፣ ለዲሞክራሲ ፈር ቀዳጅ መሆን የሚገባው የፖለቲካ ስርዓት የሚያስፈራና ደም ደም የሚሸትባት፣ ብዙ ዜናና ትንታኔ ስለ አንዲት የመንግስት […]
ከሓላፊነታቸው ውጭ የሚንቀሳቀሱ ፕሮቴስታንትና ጉዳዩን ፖሊቲካዊ ያደረጉ የደኅንነት አባላት ነን ባዮች የኮሌጁን ሓላፊዎች በመጫን ተጠርጣሪዎቹን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠሩ ነው፤ ተጠርጣሪዎቹ በኮሌጁ አስተዳደር የተከለከለ ስብሰባ በግቢው እንዲያካሒዱ ረድተዋቸዋል፡፡ በ‹ደኅንነት አባላቱ› የሚደገፉትና ‹‹የኢሕአዴግ ተወካዮች ነን›› የሚሉት ተጠርጣሪዎቹ፣ ለሃይማኖታቸው የቆሙትን ብዙኃኑን የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በስለትና በፌሮ ብረት የታገዘ ዛቻና ማስፈራራት እያደረሱባቸው ነው፤ ደቀ መዛሙርቱና የኮሌጁ አስተዳደር ጉዳዩን ለጸጥታ …![]()
ዛሬ በአለማችን ላይ መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን …
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በትናንቱ የአፍጋኒስታን ምርጫ ምንም እንኳን እስልምና አክራሪው የታሊባን ታጣቂ ቡድን ጥቃት እንደሚዘነዝር ዝቶ የነበረ ቢሆንም፤ ለምርጫው በርካታ ሕዝብ መውጣቱን እንደሚያደንቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ገለፀ። ግድያ የታከለበት በርካታ ግጭት ቢከሰትም፤ የትናንቱን ምርጫ የተመድ ስኬታማ ሲል አድንቋል።
የዕለቱ ርዕሶች፤
ካሜሮን፤ ሶስት ታጋጆች የደረሱበት አልታወቀም
ናይጄሪያ፤ 30 የሚሆኑ ሞቱ በርካቶች ቆሰሉ
ማሌዢያ፤ የተሰወረው አይሮፕላን ፍለጋ እና ፍንጭ
አፍጋህኒስታን፤ ኦባማ ምርጫውን አወደሱ
ጀርመን፤ ወደ ሀገሪቱ ሕገ ወጥ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ክፉኛ ጨመረ
ኢትዮጵያ፤ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፓሪሱን ማራቶን አሸነፈ
የዓለም ዜና
ለትራፊክ አደጋዎች መከሰት የመንገድ አጠቃቀም ደህንነትን ከግምት አለማስገባት ዋናዉ መንስኤ እንደሆነ ይታመናል።
ከስድሳ ሺሆች በላይ የተገኘቡት የደሴዉ የአንድነት ሰልፍ – ፎቶዎችን ይመልከቱ
የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የደሴ ነዋሪዎችም “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል። የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ […]
የመሪዎቻችንን የክስ መከላከያዎች ለማሰራጨት እንረባረብ!
ኡስታዝ አቡበክር አህመድና ዳዒ ያሲን ኑሩ ያቀረቡት የክስ መከላከያ በጽሁፍና በድምጽ ተዘጋጅቶ ከታች በሚገኙት ሊንኮች ቀርቧል
1.የኡስታዝ አቡበክር አህመድ ክስ መከላከያው የፒዲኤፍ ጽሁፍ ሊንክ፡-
የኡስታዝ አቡበክር አህመድ ክስ መከላከያው የድምጽ ትረካ ሊንክ፡-
2.የዳዒ ያሲን ኑሩክስ መከላከያው የፒዲኤፍ ጽሁፍ ሊንክ፡-
የዳዒ ያሲን ኑሩ ክስ መከላከያው የድምጽ ትረካ ሊንክ፡-
መጋቢት 24 አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የቀረቡበት ልዩ ዘገባ
በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ
መጋቢት 25 ኡስታዝ በድሩ ሁሴንና
ካሚል ሸምሱ የቀረቡበት ቢቢኤን ልዩ
ዘገባ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ
የመሪዎቻችንን የክስ መከላከያዎች
ለማሰራጨት እንረባረብ!
የመሪዎቻችንን የክስ መከላከያዎች ለማሰራጨት እንረባረብ!
to be continued ………..

ጌታቸው ሽፈራው እንደጻፈው ፤- የመመረቂያ ጽሁፌን ለመጨረስ ደፋ ቀና እያልኩ ባለሁበት ወቅት ነው አንድ የማላውቀው ስልክ የተደወለልኝ፡፡ ይህ ስልክ አባል ባለመሆኔ ስራ እንደማላገኝ ተስፋ ወደመቁረጥ በተቃረብኩበት ወቅት ለስራ እንደምፈለግ አበሰረኝ፡፡ ስልኩ ከኢመድኤ (INSA) መሆኑ ተነግሮኛል፡፡
ይህን መስሪያ ቤት ስም ፈጽሞ ሰምቼው አላውቅም፡፡ ለጓደኞቼ ሳወራቸው ከእኔ በፊት አብዛኛዎቹ ተደውሎላቸው እንደነበር አጫወቱኝ፡፡ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደኢህዴን ልጆች እርስ በእርሳቸው እንደተጠቋቆሙም ወሬ ደረሰኝ፡፡ በስተመጨረሻ እኔም መጠራቴ ነው፡፡ ሌላኛው ግራ የሚያጋባው ወሬ ግን መስሪያ ቤቱ የስለላ ተቋም እንደሆነ መስማቴ ነው፡፡ ሁለት ሆድ ሆንኩ፡፡ የኋላ ኋላ አይቶ መውጣቱ እንደሚሻል ወሰንኩ፡፡ አንድ በጣም የሚቀርበኝ ጓደኛዬ ስለተቋሙ ካጫወተኝ በኋላ እንዲቀጥሩኝ አባል መሆኔን (ሸውጄ) እንድነግራቸው አግባባኝ፡፡ አልፈለኩም፡፡
ለጥያቄ የተቀጠርንበት ቀን ደረሰ፡፡ ለፈተና ቀረብን፡፡ ጥያቄዎቹ ከጠበቅናቸው በላይ ናቸው፡፡ ከጠበቁት በላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፡፡ ከዚህ መርህ ያፈነግጣሉ የተባሉ ጓደኞቻችን ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ ፈተናውን አልፈን ለስልጠና በገባንበት ወቅት ደግሞ ሌላ ተስፋ ሰጭ ጉዳይ ተከሰተ፡፡ በነጻነት መከራከር ቻልን፡፡ በአንድ ትምህርት ዘርፍ (ፖለቲካል ሳይንስ) ለቅጥር ያለፍነው 12 ወጣቶች ሌሎቹን እንድናስተባብር በየ ውይይት ክበቡ ተሰባጠርን፡፡ ኢንሳን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውን የሚርቁትን ይቀይራሉ ተብለንም ‹‹12ቱ ሐዋሪያት›› የሚል ስም ወጣልን፡፡ በኋላ አንዷ የውጭ አገር እድል አግኝታ ስትወጣ ‹‹ይሁዳዋ!›› ብለን ተሳልቀንባታል፡፡ ይሁዳ ያወቀው ይህኔ ነው፡፡ ነገር ሳይበላሽና ሳይቆስሉ ቦታ መያዝን የመሰለ ነገር የለም፡፡
ስልጠናውን ጨርሰን ለአንድ አመት ያህል በነጻነት ሰራን፡፡ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ይህ አቋም ስራ ላይ ማንጸባረቅ አይፈቀድም ተባልን፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ነገር ነበር፡፡ አሁን አሁን ሳስበው ግን ለኢንሳዎች ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ማለት ኢዴፓ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም አንዱ ‹‹አለቃ›› ስለጉዳዩ ተናግሮ ሳይጨርስ ‹‹ይህን ስል ግን የኢዴፓን አቋም እዚህ (ስራ) ላይ ማንጸባረቅ ይቻላል ማለት አይደለም፡፡›› ሲል አስታውላለሁ፡፡
ብቻ ያ ጊዜ ለመስሪያ ቤቱ መልካም አመለካከት የነበረን ጊዜ ነው፡፡ ጅራትና ምንድን ነበር ወደኋላ የሚመጣው? በእርግጥ ከዚህ በፊት ኢንሳ ጠለፋና ሌሎቹንም ነገሮች እንደሚሰራ መስማት ጀመረናል፡፡ ስለ ጉዳዩ እርግጠኛ ባንሆንም የት ነው የምትሰራው ተብሎ ‹‹ኢንሳ!›› ለማለት የሚያኮራ አልነበረም፡፡ ብዙዎቹ ጓደኞቻችን ‹‹ሰላይ!›› እንመስላቸው ነበር፡፡ የእኛ አገር ችግር ይህ ነው፡፡ ስለላን ገዥዎች አበላሸተውታል፡፡ ህዝቡም ሆነ ሰላይን መልሶ መሰለል የሚባል ነገር አያውቅም፡፡ ዝም ብሎ መራቅ፡፡ ዝም ብሎ ማማት ብቻ ነው፡፡
አሁን ጅራትና ጉድ ጭራሹን እየፈጠጡ መጡ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አትችሉም ተባለ፡፡ መጀመሪያ የነበረን ተስፋ ሁሉ እንደገና ተስፋ አጣ፡፡ ይህ በሆነበት ወቅት ነው፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንደ አንዳች ክፉ ነገር የሚጠሉትና የሚጠየፉት አቶ መለስ ሰንደቅ አላማውን ከላይ ወደታች ገለበጡት፡፡
እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ‹‹ሰውዬው ለምን ሰንደቅ አላማውን ገለበጡት?›› የሚል ጥያቄ አነሳሁ፡፡ ከቀናት በኋላ ይህን ሰንደቅ አላማው ላይ የጻፍኩትን ትንሽዬ ነገር ተከትሎ 12 አስቂኝ ከስሶች ቀረቡብኝ፡፡ አብዛኛዎቹ ህገ መንግስቱን ካለመቀበል፣ የፖለቲካ ቡድኖች (እነማን እንደሆኑ እነሱው ይወቁት) አባል ሆነሃል እና ጽንፈኝነት ጋር የተለነቀጡ ናቸው፡፡ በዝርዝር የአሰብ ወደብን የኢትጵያ ነው ብለሃል፣ ኢትዮጵያ የውጭ ብድር አለባት ብለሃል፣ የጋዳፊን ፎቶ ግራፍ አጋርተሃል (ሸር አደርገሃል)፣ ከጉራፈርዳ ስለተባረሩት አርሶ አደሮች ጽፈሃል፣ ኢህአዴግን ግንባራም ብለሃል……የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በእነዚህ ክሶች መሰረትም ለ2 ወራት ያህል ከስራ ታገድኩ፡፡ በዚህ ወቅትም ለክሶቼ መልስ እንድሰጥ ታዝዣለሁ፡፡ እናም ክሱ እንዲነሳልኝ የክሶቹን ፍሬ ቢስነት ጠቅሼ ተከራከርኩ፡፡ አይ እኔ ሞኙ! ህግ በሌለበት፡፡ በዚህ ክርክር የዲስሊን ኮሚቴ አባል ናቸው የተባሉ የህወሓት አባላት ልክ እንደ ከሳሽ ‹‹እንዴት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ታንቋሽሻለህ›› የሚል ክስ አቅርበው ተከራክረውኛል፡፡ የብአዴን አባላት ደግሞ እነሱን ተከትለው አስተጋብተዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ‹‹በከፍተኛ ወንጀል›› ተባረርኩ፡፡ በዚህ ወቅት አንድ የብአዴን ካድሬ ያለኝ መቼም ሊረሳኝ አይችልም፡፡ የቅርብ አለቃዬ ስለነበር ስለ ነበረኝ ስነምግባር፣ ስለ ስራ አፈጻጸም፣ ክስ የተባሉት የማያስከስሱኝ መሆኑን ገልጬ መባረሬ አግባብ አለመሆኑን አሳወቁት፡፡ እሱም ‹‹ዋናው ታማኝ መሆን ነው፡፡›› ብሎኝ አረፈው፡፡ ኢህአዴግ ብትሆን አትባረርም ነበር ለማለት ነው፡፡ የሚገርመው ይህ ካድሬ ፌስ ቡክ ላይ እራሱን ፈላስፋ አድርጎ ስለነጻነትና ፍትህ ሲዛላብድ የሚውል መሆኑ ነው፡፡
ከተባረርኩ ከሳምንት በኋላ መሰናዘሪያን ተቀላቀልኩ፡፡ ከወራት በኋላ (ጥቅምት 20) ደግሞ አቶ መለስ የማይወዱት ሰንደቅ አላማ በዓል ተከበረ ተባለ፡፡ በእውኑ ግን ተከብረው የዋሉት ሟቹ ሰውዬ ናቸው፡፡ ጥቅምት 21 መሰናዘሪያ በፊት ገጽ አንድ ጽሁፍ (የእኔው ነው) ይዛ ወጣች፡፡ መለስ የገለበጡትን ሰንደቅ አላማ አንግባ ‹‹እውን ኢህአዴግ ሰንደቅ አላማውን ያከብረዋልን?›› የሚል ነው፡፡ መሰናዘሪያ በሳምንቱ አልተመለሰችም፡፡ አታሚው ኢህአዴጎችን ሰንደቅ አላማው ላይ የተጻፈው ጽሁፍ ስላስቆጣቸው እንዳያትም እንደነገሩት አስታወቀን፡፡ በቃ ዳግም ተባረርኩ ማለት ነው፡፡ አሁን ሌላ ስራ መፈለግ ይጠበቅብኛል፡፡ የኢንሳን ልምድ ሳሳይ ደግሞ በርካቶች ይበረግጋሉ፡፡ በግል ሚዲያው ብጽፍም በቋሚነት ለማሰራት አቅም አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ከገዥው ፓርቲም በላይ ለሚዲያውም ሆነ ለሰራተኛው በዝባዥና ገዳዮች ሆነው አግቻቸዋለሁ፡፡
እንዲህ እንዲህ ስል ለሁለት አመት ያህል ቋሚ ስራ መፈለግ ነበረብኝ፡፡ አራት አመት ያህል ደግሞ ከቤተሰብ ጋር ተቆራርጫለሁ፡፡ 18 አመት ያህል አስተምራኝ፣ ስራ ይዠያለሁ ያልኳትን እናቴን እንዴት ተባርሬያለሁ ልበላት? በፖለቲካ አቋሜ ተባረርኩ ብላት ደግሞ ከዚህ ሁሉ የባሰ ይሆናል፡፡ እናም ዝም ብዬ ስራ ፍለጋ መኳተኑን ያዝኩት፡፡ መነኩሴዋን እናቴን አይኗን ሳላያት አራት አመት ሞላ፡፡ ዛሬ ነገ እሄዳለሁ ስል ቀኑ ነጎደ፡፡ ከዛሬ ነገ አግይቼ አይኗን አያታለሁ ያልኳት እናቴም እንደሳሳኋት፣ እሷም እንደሳሳች ለወዲያው ላንገናኝ ተለያየን፡፡ እናቴ አለፈች፡፡ ያለ አግባብ የተፈናቀልኩበትን ስራ ልይዝ፣ ከያዥኩ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ‹‹ልረጋጋ!›› ላይ ታች ስል ለረዥም ጊዜ የተለየኋት እናቴ አመለጠችኝ፡፡
በእርግጥ እናቴ ወርቅን በባሌስትራ ከሚቀይሩት ወገን አይደለችም፡፡ መሬት አልሸጠችም፡፡ ህዝብን በጠባብ ማንነት አልከፋፈለችም፡፡ አገር አላስገነጠለችም፡፡ ሰንደቁን አላዋረደችም፣ አልዘቀዘቀችም፡፡ የህዝብ መብት አላፈነችም፡፡ የህዝብ ገንዘብ ወደ ውጭ አላሸሸችም፡፡ ንጹሃንን አልገደለችም፣ አላሰረችም፡፡ አላፈናቀለችም፡፡ እናቴ ንጹህ ነች፡፡ የእሷ ነፍስ የገነት ነፍስ ነች፡፡ ሌሎች ግን የሞት ሞታቸውን ሞተዋል፡፡ ትውልድም አጥንታቸውን እንደረገመ ይኖራል፡፡
እኔም እላለሁ፡፡ ሞት ማለት የሞት ሞት ሲሆን ነው፡፡ ይህን እናቴ አልሞተችውም፡፡ ምስኪኗ ወላጅ እናቴ የክብር ሞቷን ስትሞት አሁን ለእኔ የቀረኝ አንዲት እናት ብቻ ናት፡፡ እናት አገር ኢትዮጵያ! አገር ብትኖር ወላጅ እናቴ ተቀብራበታለች፡፡ እኔም አልቅሸበታለሁ፡፡ አዎ! ወላጅ እናት ባትሞት እጅጉን መልካም ነበር፡፡ ከሞተች ግን ምን ይደረጋል? ብቻ እናት አገር አትሙት!
እናቴ ሆይ! አምባገነኖቹ ፊቴ ላይ የደቀኑብኝን አቀበት ለመውጣት ስጥር አንቺ አምልጠሽኛል፡፡ አሁን ብችል እናት አገርን ለማዳን ከሌሎቹ ጋር ሆኜ ጠጠር ለመጣል፣ ጥረቴ ለዚህ ባይበቃ እንኳ የራሴን መብት ለማስከበር፣ ይህንን ደግሞ ባልችል ሆድ አደር ላለመሆን አቀበቱ ላይ ነኝ፡፡ ሞት አይቀርምና አንድ ቀን እንደምሞት አውቀዋለሁ፡፡ የሞት ሞት መሞት ግን አልፈልግም፡፡ ደግሞም ከአንቺ ጋር ያለያየኝን አቀበቱን ወጥቼ ሜዳው ሳልደርስ ባልከተልሽ ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ አንቺም እንደማትቀየሚኝ አውቃለሁ፡፡ እስከዚያው ግን አምላክ ነፍስሽን በገነት ያኑራት!
የሕወሓት የበላይነት እስከመቼ ?? … መሸዋወድ እስከየት?
ምንሊክ ሳልሳዊ :- የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 22 ድፍን አመታትን አስቆተረ::
በ22 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሆዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱት የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::
የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::
በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ
አዲስ አበባ የሚገኘው የአንድነት ቢሮ በከፍተኛ ሁኔታ በፖሊስ እና በደህንነት ሃይሎች ተከቧል። የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ነው።

ደሴ በህዝቦቿ አንድነት ደምቃለች ። #Ethiopia #Dessie #UDJ #EPRDF #Demonstration
#MillionsVoicesforlandownership
በደሴው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከአስር ሺ በላይ የሚሆን ህዝብ ፍርሃትን ሰብሮ የደሴ ጎዳናዎች ላይ ወጥቷል።
ህዝቡ አሁንም ወደ ሰላማዊ ሰርፉ በመጉረፍ እየተቀላቀለ ነው። መብቱን እና ነጻነትን በማወቅ ጥያቀዎቹን ለማሰማት የአንድነት ፓርቲ ጥሪን ተከትሎ አደባባይ የወጣው ህዝብ በመፈክር እና በዝማሬ ብሶቱን እያሰማ ነው።
“ኢህአዴግ እንዴት ቢንቀን ነው በ30 ብር አበል ነፃነታችንን ለመንጠቅ የሚሞክረው?”
ለሰልፍ ተሳታፊ የቀረበ ጥያቄ
ፖሊስ መንገድ በመዝጋት እየሞከረነው ሆኖም ሰልፈኛው ግን ጥሶ በማለፍ ላይ ነው፡፡
ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ
– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ
airport new design.jpgአዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ከሁለት ወራት በኋላ ግንባታው የሚጀመረው አዲሱ የኤርፖርት ተርሚናል የዲዛይን ስራ ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት እንዳለው በ225 ሚሊዮን ዶላር የሚገነባው ተርሚናል 22 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል ነው።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ለተርሚናሉ ግንባታ የሚውለው ገንዘብ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ በብድር የተገኘ ነው።
የብድር ስምምነቱ በትላንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ ሲሆን የተርሚናሉ የዲዛይን ስራ ሲ.ፒ.ጂ በተሰኘ የሲንጋፖር ኩባንያ ተዘጋጅቶ ዛሬ ለድርጅቱ ቀርቧል።
ግዙፍና ዘመናዊ ነው የተባለለት የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል የእንግዳ ሳሎን፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽና ኢንተርኔት ካፌን በውስጡ አካቷል።
በኤርፖርቱ በስተምስራቅ በኩል የሚያርፈው ይህ ዘመናዊ ተርሚናል ከሁለት ወራት በኋላ በቻይናው ሲ.ሲ.ሲ.ሲ ኩባንያ የግንባታ ስራው ይጀመራል።
አቶ ወንድም ድርጅቱ ከዚሁ ፕሮጀክት ጋር የሚያያዝ የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ የማስፋፊያ ስራም አማከናወኑንና ይህም ቀድሞ 19 አውሮፕላኖችን ብቻ ይይዝ የነበረው የማረፊያ ሜዳ 45 ግዙፍ አውሮፕላኖችን እንዲያስተናግድ አስችሎታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር!
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ
ግፍ ከበዛበት ወህኒ የአክብሮት ስላምታየ ይድረሳችሁ!
እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍታ ያህል እድሉን አግኝቸ ወህኒ የመውረዴን እውነታ ላስረዳችሁ ግድ አለኝ ። ዛሬ አስረግጨ የምነግራችሁ ወህኒ የመውረዴ ምክንያት ሚስጥር ግምሽ እድሜየን ህግና ስርአቷን አክበሬ የኖርኩባትን የሳውዲት አረቢያን ህግ ተላልፊ አይደለም ! የስደተኛው ጉዳይ ያገባኛል በሚል የማቀርበው መረጃ ቅበላየ የማይመቻቸው ፣ ያመማቸው ከተሴረውና እየተሴረ ካለው እገታ ጀርባ ስለመኖራቸው አልጠራጠርም ። … ዛሬ በዚህ ዙሪያ ብዙ አልልም!
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ወጣት የርዋንዳ ዜጎች በሀገራቸው እአአ 1994 ዓም በተካሄደው የጎሣ ጭፍጨፋ የሞቱትን ለማሰብ 2014 ዓም ከገባ ወዲህ አንድ ማስታወሻ ችቦ በመላይቱ ሀገር ይዘው በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ። እአአ የፊታችን ሰኞ፣ ሚያዝያ ሰባት፣ 2014 ዓም ችቦው መዲናይቱ ኪጋሊ ይገባል። በዚሁ ዕለት የጎሣው ጭፍጨፋ የተጀመረበት 20ኛ ዓመት ይታሰባል።
ዛሬ በአለማችን ላይ መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዶ ናት :: በአሁኑ ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን […]
ነገ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅድቀሳእ በደመቀ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጸ። አቶ ሃብታሙ አያሌዉ ከስፋራዉ ይሄን አስተላልፈዋል ፡ ===================== “እረ ደሴ ደሴ ገራዶ ረጋዶ…….. አለቀልሽ ልቤ አንድነትን ወዶ” ይህንን የማጀቢያ ዘፈን እያሰማ ህዝቡ ከጎናችን ተሰለፈ …… ደሴ በአንድነት አባላትና ደጋፊዎች እንደደመቀች፤ ትንቅንቁም እንደቀጠለ …..ለዚህ ሰዓት ደርሰናል…ነጻነት ከፍርሃት አይገኝም!!! ድል የህዝብ ነው!! […]
አፍጋኒስታን ውስጥ ዛሬ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ነዉ። ፕሬዚዳንት ሃሚድ ካርዛይን የሚተካ ለመምረጥ ወደ 12 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ለምርጫ መጠራቱ ተመልክቷል።
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረቦች ክስተቱን በፎቶግራፍ አንስተዋል —————– የአንድነት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተውን የቅስቀሳ ቡድን ተግባር ለማደናቀፍ ፖሊሶችና ደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች በስውር ቪዲዮ በመቅረፅ እና ስለሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የሚስተጋቡ መፈክሮችን ለማስቆም ሙከራ አድርገዋል፡፡ በተለይም የከተማዋ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ቅስቀሳው በተደረገባቸው ስፍራዎች በመገኘት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማስፈራራትና ከቅስቀሳ ቡድኑ አባል ላይ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ለመንጠቅ ሲሞከር […]
ጥንተ ስቅለቱ በዩጋንዳ ምድር
በልዩ ድምቀት እየተከበረ ነው።
መንበረ ፓትርያርኩን በሰሜን አሜሪካ ባደርገው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የደብሩ ማሕበረ ካህናትና ማህበረ ምዕመናን የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱን ዛሬቅዳሜ መጋቢት ሃያ ሰባት በከፍተኛ መንፈሣዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ነው።በአሁኑ ሠዓት የዕለቱ ቅዳሤ እየተከናወነ ሲሆን የዕለቱ ወንጌል ከማቴዎስ ምዕራፍ ሃያስምንት ተነቦአል።በቀጣይምበዓሉን በተመለከተ የወንጌል ማዕድ በደብሩ አስተዳዳሪቀሲስ ፀሐይ ደስታ ይቀርባል ። ታቦተ ኅጉ ይወጣል ዑደት ይደረጋል ።በመሪጌታ ይሄይስ ዓለሙ መሪነት በደብሩ ፈለገ ህይወት ሰንበት ትቤትመዘምራን ወረብ ይቀርባል።
<ሃሌ ሉያ መርሕ በፍኖት
ሞገሦሙ በፍኖት።
ዝንቱ መስቀል ለአዳም ዘአገብዖ ውስተ ገነት።>
በመጨረሻም ቃለ ምዕዳንና ፀሎተ ቡራኬ ተሠጥቶ የበዓሉ ፍፃሜ እንደሚሆን ከደብሩ ሠበካ ጉባዔ አስተዳደር ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ ጠቁሞአል።
አክሊለሠማያት ዘ መካነሠላም
ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራውይህ ቡድን ከሜይ 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካመቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህንአበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግንጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንምአሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውልየለም ብለዋል።በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስበመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱመብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎችእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያንለመረዳት ችለናል።ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውንቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱየገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህንአበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳትፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆችእንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
(ወልደ አረጋዊለደጀሰላም እንደጻፉት መጋቢት 27/2006 ዓ.ም፤ April 5/2014)፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ነቢይ የማይቀረውን የኢየሩሳሌምን ጥፋትና በከላውዴዎን ንጉስ እጅ፣ ለከለዳውያን ሠራዊትና፣ ለባቢሎን ሕዝብ ተላልፋ መሰጠቷን እግዚአብሔር ራሱ በተረዳ ነገር በገለጠለት ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ልብሱን ቀዶ፣ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ከባሮክ ጋር እያለቀሱ ተቀመጡ፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ እግዚአብሔርንም ሁለት ታላቅ ነገሮች ለመነው። ጉዳዮቹም፦
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
አንድ ሰው ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ እንዲማር ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለበት ግልፅ ነው።የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ከነዚህ ተማሪዎች አንዱ ነው።
የጀርመን ፌደራል ጦር እጎአ ከ2010 አንስቶ የሶማሊያ ወታደሮችን በማሠልጠን ይሳተፋል። እስካሁን ሥልጠናው የሚሰጠው ዩጋንዳ ነበር። የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ከአሁን በኋላ የጀርመን ወታደሮች ስልጠናውን ሶማሊያ ውስጥ መስጠት ይጀምራሉ።
በአፍጋኒስታን የምርጫ ዋዜማ ለመዘገብ ወደዚያ አምርተው ከነበሩ ጋዜጠኞች መካከል አንዲት ጀርመናዊት የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ በዛሬው ዕለት መገደሏ ተነገረ። ካናዳዊቷ ባልደረባዋ ቆስላለች። አፍጋኒስታን ዛሬም ፀጥታዋ መረጋጋትን አይጠቁምም።ታሊባኖች ፣ 6 ዓመታ
ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ለ2 ቀናት የተካሄደው 4ተኛው የሁለቱ ክፍለ ዓለማት መሪዎች ጉባኤ ሲጠናቀቅ መሪዎቹ የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታትም ፅኑ አቋም እንደያዙ አስታውቀዋል ።
የአንድነት ፓርቲ «ህግን እያከበርን የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን» በሚል ርእስ ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ይፋ ባደረገው መግለጫ «የአዲስ አበባ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በመጋቢት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በቁጥር አ.አ ከስ/1ዐ/3ዐ.4/236 በላከልን ደብዳቤ ሠላማዊ ሠልፉን ለማድረግ በጠየቅንበት ቀን ተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስላሉ ተለዋጭ ቀን እንድናቀርብ ጠይቆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ለመጋቢት 28 ቀን […]
የአዲስ አበባ አስተዳደር መጋቢት 26 ቀን ለአንድነት ፓርቲ በላከው ደብዳቤ ፣ አንድነት መጋቢት 28 ቀን ሊያደርግ ያሰበዉ ሰላማዊ ሰልፍ ፣ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ጠየቀ። ሰልፉ በታሰበበት ቀን ሌሎች ዝግጅቶች እንዳሉ የገለጸዉ የአስተዳደሩ ደብዳቤ «ተጨማሪ መስመርና ቦታ በመጥቀስ (ሰልፉን) የምታካሂዱበትን ሌላ ቀን ጭምር እንድታሳዉቁን እንገልጻለን» ሲል አስተዳደር ሕግና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ ሰጧል። በመጋቢት 28 ቀን […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የሚሊዮኖች ድምጽ የደሴ ከተማ ቅስቀሳ ፎቶዎች !