የአምባገነኖች የስልጣን ጥም አባዜ
ዛሬ በአለማችን ላይ መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዶ ናት :: በአሁኑ ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን ያወጣ የሰበሃዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ እየፈጸመ እንዳለ ይታወቃል ይህም የወያኔ የዜጎችን የሰብሃዊ መብት መርገጥ እና ሕዝብና እያስፈራሩ ረግጦ መግዛት ከምንም ነገረ የመነጨ ሳይሆን ሕዝቡ ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች ያዋጣናል ብለው የመረጡት መንገድ ሲሆን ዜጎችን መረበሽ፣ መዝረፍ፣ ማሰር እና መግደልን ተያይዘውት ይገኛሉ::
ዜጎችን ማሰቃየት፣ ማሰር እና መግደል የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫና መታወቂያ ሲሆን አንባ ገነን መንግስታቶች በሰለም እና በመረጋጋት ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት የበላይ ሆነው የተሾሙለት ሕዝብ ሰበሃዊ መብት በመርገጥ ግፍና በደል እንደሚፈጽሙባቸው በገሀድ የታወቀ ሲሆን እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች ለምንድ ነው ግን ሕዝባቸውን የሚያሰቃዩት፣ የሚያስሩት እና የሚገደሉት ብለን ማሰባችን እና መጠየቃችን አይቀርም በየትኛውም አለም እንደምናየው አንባ ገነኖች ያለምንም ተቀናቃኝ በስልጣን ዙፋናቸው ላይ ለመቀመጥ ከመሻት የተነሳ ዜጎቻቸውን ያሰቃያሉ፣ ያስራሉ፣ይገድላሉ
በተለይም እኛ ኢትዮጵያኖች በሀገራችን መንግስት በየጊዜው በግፍ ስለሚያሰቃዩት፣ ስለሚታሰሩት እና ስለሚገደሉት ወገኖቻችን ሁል ጊዜ እንዳለቀስን እና እንደጮህን እንገኛለን::
ምክንያቱም ወያኔ /ኢህአዲግ ወደ ስልጣን ከመጣበትና የኢትዮጵያንም ሕዝብ በሀይል መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከሁለት አስርት ከአመታት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል ማጋነን አይሁንብኝም::ይኼው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ሁልጊዜ እንደፈራ ሕዝቡንም እንዳስፈራራ ሁል ጊዜ እንደተረበሸ ሕዝቡንም እንደረበሸ የሚኖር ሲሆን ይህም የወያኔ ባህሪና መገለጫዎች ናቸው:: ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መገዛት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ወያኔ ያሰረው እና የገደለው ሀገሩንም ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገው ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሲሆን የዜጎችንም ሰላም በመረበሽ እና በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይቀመጡ በማድረግ ላይ ይገኛል::
ከዚህ በታች የአንባ ገነኖችን ማንነት መገለጫ የሆኑትን ነገሩች በአጭሩ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት ለመዳሰስ እሞክራለው
1) አምባገነኖች ያለ ሕዝብ ፍላጎት ለብዙ አመታት በስልጣን ላይ የመቆየት ማንነት ይታይባቸዋል (የስልጣን ሱሠኞች) ናቸው ::
በግብጽ በቱኒዚያ በየመን እና በሌሎችም ሀገሮች እንዳየነው አንባገነኖች ለብዙ አመታት ስልጣንን በማውረስ እና በመረካከብ ሕዝብን በመጨፍለቅ ሲገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ለምሳሌ በግብጽ ጀማል ሙባረክ የሚቀጥለው የግብጽ መሪነትን ከአባቱ ለመውረስ እና ለመረከብ በመዘጋጀት እያለ ነበር ድነገት ባልጠበቁት ሰአት የቱኒዚያው ሱናሜ የተነሳው እና ያለሙትን አላማ ሳይተገብሩ በአንባ ገነኖች መገዛት በሰለቸው ሕዝብ ቁጣ እንደ ሰም ቀልጠው የቀሩት:: እነዚህን ሀገሮች እንደ ምሳሌ አነሳው እንጂ እንደነ ምሮኮ እና ኮንጎ የመሳሰሉ አብዛኞች ሀገሮች ስልጣንን በሀይል ወይም በውርስ በማውረስ እና በመረካከብ ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ህውቅና ለዘመናት በማን አለብኝነት ስልጣንን በግላቻው በመቆጣጠር የሕዝቦችን ሰብሃዊ መብት ሲጨፈልቁ የሚኖሩ ሀገሮችን መጥቀስ ይቻላል::አንባ ገነኖች እነሱን ከሚመስላቸው ውጭ ለሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅትም ሆነ ሀገርን ለመምራት አቅምም ሆነ ብቃቱ ላላቸው ሰዎች በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣንን ለመልቀቅ ፍቃደኞች ሲሆኑ አይታዩም::
ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ይህንኑ ነው የምናየው በአሁኑ ሰአት ሀገራችንን ኢትዮጵያን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ መንግስት ስልጣንን በዘር ሲወራረሱ እንደነበሩ እንደ አንዳንድ አረብ እና አፍሪካ ሀገራት አንባ ገነን መሪዎች በዘር አይወራረሱ እንጂ ከሕዝብ ፍቃድ እና ፍላጎት ውጭ ለዘመናት የስልጣን ወንበሩን በማን አለብኝነት በሀይል ተቆጣጥሮ የዜጎችን ሰብሃዊ መብት እየረገጠ ያለ መንግስት መሆኑ ይታወቃል::አሁን ባለው አካሄድ እና አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣኖች አንዳንድ ጊዜ አፋቸው እያመለጣቸው እንደሚናገሩት እነዚህ የስልጣን ሱሠኞች የሆኑት የወያኔ ባለስልጣኖች በፈቃዳቸው ስልጣንን ይለቃሉ ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም ድንገት ግን የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ የሚባል የአንባ ገነን የማፊያ ቡድን ዳግመኛ እንዳያንሰራራ በግብጽ ፣ በቱኒዚያ እና በሌሎችም ሀገሮች እንደ ሆነው ሁሉ የአንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት ስርአት ወደ መቃብር ያስገበዋል የሚል ከፍተኛ የሆነ እምነት አለኝ::
የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች ለአስርት ዓመታት በአምባገነን አገዛዝ ተገዝተዋል። እኛ ደግሞ ለአስርት ዓመታት አምባገነን ብቻ ሳይሆን ዘረኛም ጭምር በሆነ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጠወ አገዛዝ እየተገዛን ነው። እኛ እየደረሰብን ያለውን ዓይነት አዋራጅ ዘረኝነት እነሱ ላይ አልደረሰባቸውም። አምባነንነት እነሱን አስመርሮ በገዚዎቻቸው ላይ በአንድነት እንዲነሱ አድርጓቸዋል። እኛ ዘንድ ደግሞ አምባገነንነትና ዘረኝነት ተዳብለውብናልና ከእነሱ በላይ አምርረን በህብረት የስልጣን ሡስ በተጠናወጣቸው አንባገነኖች ላይ እንነሳለን።
2)አምባገነኖች በራስ የመተማመን (self confidence)ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።
አምባገነኑ የወያኔ መንግስት በራሱ የማይተማመንና በስጋት ውስጥ የሚኖር መንግስት እንደሆነ በቅርቡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች የወያኔን መንግስት አሳፋሪ ድርጊት በመኮነን ያወጣው ሪፖርት አመላካች ነው::እንደ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሪፖርት ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገር አዘጋጀሁት ባለውና ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንዳለ እና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም አገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማንኛውም መንገድ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያኖች በወያኔ መንግስት እንደሚሰለሉ እና እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በተለይ ደግሞ ከውጭ አገር የተደወለ ከሆነ ያለ ግለሰቦቹ ፈቃድ ወይም ዕውቅና ተጠልፎ እንደሚቀዳ ሒዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርት ላይ ይፋ አድርጎል ለዚህም የስለላ ተግባሩን ለመፈጸመ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘ፣ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አድርጓል::
የወያኔ መንግስት በራስ መተማመን የጎደለው እና በፍርሃት የተሞላ መግስት መሆኑን በአደባባይ ያስመሰከረ አንባ ገነን መንግስት ነው ::መሪዎቹ በጭራሽ በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው መተማመኛቸው ጠብመንጃ፤በጦሩ ጉያ ተሸጉጠው ሃገርና ሕዝብን ለእልቂት ለረሃብ ለመከራ የሚያበቁበትን ቆመውም ተቀምጠው ተኝተውም ማውጠንጠን ነው፡፡ ይህንንም ስል እንዴው ዝም ብዬ ከመሬት ተነስቼ እንዳለ ይታወቅልኝ:: እኔ እስከማቀው ድረስ የወያኔ መንግስት ስልጣኑን ሀ ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከ22 አመት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል የተሳሳትኩኝ አይመስለኝም:: ከዚህ ስጋታቸውም የተነሳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍነው ይዘውታል::
ዜጓች ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የሚደርስባቸው ጭቆናና የሰበሃዊ መብት ጥሰት በነጻነት መቃወም አልቻሉም :: አንባ ገነኑ ወያኔ ይኼን ያክል ዘመን በስልጣን ላይ ሲቆይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ ስንቶችን ሲገርፍ፣ ሲያስር ፣ ሲያሰቃይ እና ሲገድል እንደኖረ በአደባባይ የተገለጠ ሀቅ ነው::ሕዝብም ስለመብቱ እና ነጻነቱ የጠየቀ ከሆነ ይታሰራል ፣ይገረፋል ይገደላል::
ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል። ዛሬ የኛዎቹ እነ እስክንድር ነጋ ፣ርዕዮት አለሙ እና ሌሎችም ወጣት ወገኖቻችን በሽበርተኝነት ስም ተወንጅለው በአንባ ገነኖች እስር ቤት ውስጥ ተጥለው እየተሰቃዩ ያሉት የወያኔ መንግስት እንደሚለው ሽብርተኛ ሳይሆኑ የነጻነት እና የፍትህ ታጋይ ጀግኖች እንደሆኑ በድፍረት መናገር እችላለው::
የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች በያገራቸው ፍትህ በመጓደሉ ተማረዋል። እኛ አገር ደግሞ ፍትህ ራስዋ ተዋርዳለች። ፍርድ ቤቶች ማጥቂያዎች ሆነዋል። አገራችን እስር ቤት ሆናለች። አብዮት ከቀሰቀሱት ጎረቤቶቻችን በባሰ እኛ ተበድለናልና ከእነሱ በባሰ አምርረን ልንነሳና አንባ ገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ልንቀብራቸው ያስፈልጋል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣና ላይ ያለው አምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስናና በሌብነት ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ ቢፈለግ አይገኝም ብል ማጋነን አይመስለኝም:: በአሁኑ ሰአት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አበባን ነዋሪ ጨምሮ ሕዝቡ በከፍተኛ የኖሮ ችግር ውስጥ እንዳለ ይታወቃል:: ካለውም ታላቅ የኑሮ ውድነትና፣ የስራ ማጣትና ያለው ብልሹ የመንግስት ፖለቲካዊ አስተዳደር ተደምሮበት ሕዝቡ ሀገሮን ጥሎ ወደ ተለያየ ሀገር እየተሰደደ በተለይም ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች እህቶቻችን ሀገራቸውን ጥለው ሲወጡ በየድንበሩ እየሙቱና ወደ ተለያየ ሀረብ ሀገራትም ሄደው ለተለያየ መከራ ስቃይ እና ችግር ሲደርስባቸው እና ዜጓቻችን ሲገደሉ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ነገር ግን እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የወያኔ አንባ ገነን መሪዎች ሙሰኞች ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ከኢትዮጵያ ህዝብ በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በማካበት ላይ እንደሚገኙ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአገሪቱ ገንዘብ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል ።
በወር ስድስት ሺህ ብር ደሞዝተኛ እንደነበሩ በባለቤታቸው የተነገረላቸው አንባ ገነን የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከጥቂት ዓመታት በፊት የትንሳኤ ሬድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የዘረፉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖችን፥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የዘረፉትን ሀብት መጠንና ገንዘቡን ያስቀመጡበትን አገር ጭምር ይፋ አድርጎ እንደነበር አስታውሳለው። ይሄ ሬድዮ ጣቢያ አቶ መለስ ዜናዊ በማሌዥያ በባንክ ፬፪ (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንዳስቀመጡ ገልጾ ነበር።ይታያችው እንግዲህ በተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ በሆኑ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ሰውየው ስለ ሀገራቸውና ስለ ሕዝባቸው ፍቅር የነበራቸው፣ ባለራእይ መሪ እንደነበሩ ሲወደሱ እና ሲዘመርላቸው መስማት የሰለቸን ጉዳይ ነው:: እውነታው ግን የሚያሳየው ሌላ ነው ተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ እንደሚሉት ሳይሆን አንባ ገነኖች አንድም ቀን የሀገር እና የሕዝባቸው ፍቅር ኖሯቸው አያውቅም እኝው አንባ ገነን የቀድሞ መሪ ሕዝባቸውን ሲያዋርዱና ሲያንቋሽሹ ለሀገራቸውም ቅንጣት ያከል ፍቅር እንደሌላቸው የሚያሳይ ስራ ይሰሩ የነበሩ እና ጀግኖች አባቶቻችን የታወደቁለትን ባንዲራ እንኳን ሳይቀር ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬ የነበሩት አንዴ ሲዘቀዝቁት አንዴ ጨርቅ ነው ሲሉት እንደነበር እናስታውሳለን::
ሙስና የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫ ሲሆን የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት የነበሩት አንባ ገነን ሹሞች በሙስና ያካበቱት ሃብት በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚገመትና ሕዝቡንም ለአመጽ ያነሳሳው ይኸው የአምባ ገነኖች ከልክ ያለፈ ሙሰኝነትና ሌብነት እንደሆነ ይታወቃል። የእኛ የመጨረሻይቱ ድሃ አገር አንባ ገነን የወያኔ ሹሞችም በሙስና ያካበቱት ሃብት እንደዚያው ነው። እርግጥ ነው በከተሞቻችን ህንፃዎች በርክተዋል ሆኖም ግን የሙሰኞቹ እንጂ የለፍቶ አዳሪዎቹ አይደሉም። ስለዚህ በአሁኑ ሰአት እያደጉት ያሉት አንባ ገነኖች እና ሙሰኞች እንጂ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዳይደለች መታወቅ አለበት የሀገሬ ምስኪንና ደሃ ሕዝብማ በየቦታው በረሃብ እያለቀ ነው የሚገኘው:: በሃብት መበላለጥ የተቆጩት እና በሙስና መብዛት በአንባ ገነንና በስልጣን ሱሰኞች መሪዎቻቸው የተናደዱ የአህጉራችን የሰሜን አፍሪቃ ዜጎች በገዢዎቻቸው ላይ ተነስተዋል እኛ ደግሞ ከእነሱ በላይ ተጎድተናልና ከእነሱ በላይ አምርረን ልንነሳ ሙሰኛውን፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር የሌለው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ልንፋለመው ይገባል እያልኩኝ ጹሁፊን ላጠቃላል ፈጣሪ ቸረ ወሬ ያሰማን ።
