"ኢየሱስ ይሰቀል!"

 
·ዕለቱ አርብ ነው!
ኢየሱስ ይሰቀል!
ይሰቀል ኢየሱስ!
በርባን ግን ይፈታ!
2 ሺህ ዘመን
ይኸው ትጮሃለች
ዓለም አፍ አውጥታ።

በቀያፋ ምክር 
በካህናት አድማ
በጲላጦስ ስልጣን 
በግፈኞች ጡጫ
ዛሬም ይወገራል 
ጌታ ይሰቀላል።
እውነት ነው!
በድምጽ ብልጫና
በቲፎዞ መድረክ
ለምትመራ ዓለም
ሌባውን አንግሶ
ንፁሁን ከመሸጥ
ሌላ አይጠበቅም።
መጋቢት 2006 .ዓም