ጥንተ-ስቅለቱ በዩጋንዳ ምድር በልዩ ድምቀት እየተከበረ ነው
ጥንተ ስቅለቱ በዩጋንዳ ምድር
በልዩ ድምቀት እየተከበረ ነው።
መንበረ ፓትርያርኩን በሰሜን አሜሪካ ባደርገው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የደብሩ ማሕበረ ካህናትና ማህበረ ምዕመናን የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱን ዛሬቅዳሜ መጋቢት ሃያ ሰባት በከፍተኛ መንፈሣዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ነው።በአሁኑ ሠዓት የዕለቱ ቅዳሤ እየተከናወነ ሲሆን የዕለቱ ወንጌል ከማቴዎስ ምዕራፍ ሃያስምንት ተነቦአል።በቀጣይምበዓሉን በተመለከተ የወንጌል ማዕድ በደብሩ አስተዳዳሪቀሲስ ፀሐይ ደስታ ይቀርባል ። ታቦተ ኅጉ ይወጣል ዑደት ይደረጋል ።በመሪጌታ ይሄይስ ዓለሙ መሪነት በደብሩ ፈለገ ህይወት ሰንበት ትቤትመዘምራን ወረብ ይቀርባል።
<ሃሌ ሉያ መርሕ በፍኖት
ሞገሦሙ በፍኖት።
ዝንቱ መስቀል ለአዳም ዘአገብዖ ውስተ ገነት።>
በመጨረሻም ቃለ ምዕዳንና ፀሎተ ቡራኬ ተሠጥቶ የበዓሉ ፍፃሜ እንደሚሆን ከደብሩ ሠበካ ጉባዔ አስተዳደር ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ ጠቁሞአል።
አክሊለሠማያት ዘ መካነሠላም