ሰበር ዜና – ‹‹አቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩ የማኅበራትን ተጠሪነትና የገንዘብ እንቅስቃሴ በሚመለከተው የሕጉ ረቂቅ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ተፋጠው ዋሉ
ፓትርያርኩ የማኅበራት ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ኾኖ በማእከል ካልተመራ በሚል ከማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋራ የሚቃረን ግትር አቋም ይዘው ውለዋል፡፡ አቋማቸው ተቀባይነት ካላገኘ ስብሰባውን ለመምራት እንደሚቸገሩ በመግለጽ ምልአተ ጉባኤን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽኑ አቋም ሳቢያ አልተሳካላቸውም፡፡ ጉዳዩ ‹‹ከአዲስ አበባ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ የሠራኹበትና የደከምኩበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› …![]()