ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ  ሁኔታ ባስመረቀበት ወቅት የህዝባዊ ሃይሉ ስልጠና በግንቦት ሰባት ስም ከሚደረጉት ስልጠናዎች የመጨረሻው መሆኑ ተመልክቷል። የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ፖሉ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ በዘገባው አመልክቷል። ‹‹አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ …

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለቤታቸውን በድንገተኛ ሞት ከማጣታቸው በፊት የፓርላማ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በራሳቸው ፍቃድ ፓርላማውን ከመልቀቃቸውም በተጨማሪ በድርጅታዊ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየተዳከመ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ ባለፈው አንድ ዓመት በፓርላማው መቀመጫቸው ላይ ታይተው የማያውቁ ሲሆን ለፓርላማው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ወይዘሮዋ  በራሳቸው ፈቃድ ከፓርላማ አባልነታቸው መሰናበታቸውን ገልጸዋል፡፡ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ማይክል ሳታ ህክምናቸውን በሚከታተሉበት እንግሊዝ ሃገር ትናንት ማክሰኞ ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። እአአ ከ2011 ዓም ጀምሮ በስልጣን የቆዩት ፕሬዝዳንት ሳታ ባለፈው ሳምንት የተከበረውን የዛምቢያ 50ኛ የነፃነት በዓል በጤና መታወክ ምክንያት መታደም አልቻሉም ነበር።

ለተንቀሳቃሽ ወይም የእጅ ስልኮች (ሴልስ፤ ሞባይልስ) መልሶ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሞላ «AKU»(አኩሙሌተር) የተለመደ መሣሪያ ነው ። የኤልክትሪክ አውቶሞቢሎች ከጸሐይ ኃይል የሚገኝ ኤልክትሪክ ጉልበት እጅግ ያስፈልጋቸዋል ፤ ዋጋው ደግሞ ተስማሚ ነው።

ተቃዋሚዉ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ በዜጎች ላይ የሚደርሰዉን መፈናቀል፤እስራት እና ግድያ መንግሥት ካላስቆሞ ፓርቲዉ ሠላማዊ ትግል በሚጠይቀዉ አማራጭ በሙሉ መንግሥትን ይታገላል።

#Ethiopia #SouthSudan #OELF #ExEthiopianArmyOfficers #MinilikSalsawi

ሰው በላው መንግስቱ ሃይለማርያም መሞት ሆነ መኖር ማንችንንም ሊያስጨንቀን ሊያሳስበን አይገባም።
Minilik Salsawi

በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔን አምባገነን መንግስት ለማስወገድ በትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡ ተቃዋሚ ሃይሎች ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ጋር መገናኘታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።ከባለስልጣናቱ ጋር የተገናኙት በኤርትራ ውስጥ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ድርጅቶች እና በአስመራ ቢሮ የሌላቸው የፖለቲካ ሰዎች እንደሆኑ ታውቋል።

በመጪው ጊዜያት ሊደረጉ ስለሚችሉ እና ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ሃይሎች ከጁባ መንግስት ተጽእኖ ስር ያልወደቀ የራሳቸው መንደርደሪያ መሬት እና ወታደራዊ ቤዝ የሚያገኙበትን ጉዳይ በተመለከተ መወያየታቸው ታውቋል። እንዲሁም አስፈላጊ የሆነ ወታደራዊ እርዳት የሚደረግበትን ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው ሲታወቅ በቀድሞ የደርግ መንግስት ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ዜግነታቸው ሃገራቸውን ለመካስ በወታደራዊ አማካሪነት ላይ የሚሰሩበትን አስመልክቶ የጁባው መንግስት ስምምነቱን ገልጿል።ምንጮቹ ከዚህ በላይ ዝርዝር ሁኔታ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

መንግስቱ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ተቃዋሚ የትጥቅ ትግል የሚፈልጉትን አካላቶች ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ያገናኛል የሚል ፍራቻ የተከሰተ ይመስል ይህን ሰሞን ከባለፈው አመታት በተወራረሰ መልኩ በቀጥታ ግልባጭ መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ አድርገው የሻእቢያ አቧራ አጫሽ ድህረገጾች ወሬውን እያቦነኑ ይገኛሉ። በባለፈው ጊዜ እኔ ራሴው መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ ተነፋፍሼ ነበር ከዛሬዎቹ አለን ባይ ምንጮቼ ያገኘሁትን ይዤ ።

የሆኖ ሆኖ በየእስር ቤቱ ስለታሰሩብን የፖለቲካ መሪዎቻችን ጋዜጠኞቻችን እና የሃይማኖት ምሁራን መጨነቅ እና ስለመጪው ትግል ሰፋ ያለ ስራ መስራት ይገባናል ። ሻእቢያ ይህን ሰሞን በኤርትራ የተነሳበትን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በሌላው ዘንድ አትኩሮት እንዳያገኝ ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎን የመንግስቱ ሃይለማርያምን መሞት ሊያረዳን ይፈልጋል። ወይ ሻእቢያ እና ወያኔ ለማደናበር ማን ብሏቸው።

ለቁጥጥሩ ማኅበራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሞዴላሞዴል ይጠቀማሉ ዕውቅና የመስጠት፣ ደንባቸውን የማጽደቅና የመሰረዝ ሥልጣን የቅ/ሲኖዶሱ ኾኖ ጸንቷል በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያው የማኅበራትን ጉዳይ የሚከታተለው የመምሪያ ሊቀ ጳጳሱ ነው ማኅበረ ቅዱሳን በውሳኔው ማህቀፍ ውስጥ በሚሻሻልለት መተዳደርያ ደንብ ይመራል ስብሰባው የሊቃነ ጳጳሳትን ተጠሪነት በሚወስኑና በሌሎች የማሻሻያው ልዩነቶች ላይ  ቀጥሏል

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር ሆኖ የመጀመሪያው
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሕንፃ ‹‹አፍሪካ
አዳራሽ›› በሚል ስያሜ በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ
ሥላሴና በወቅቱ ሹማምንት ይፋ ከተደረገ ከ56 ዓመታት በኋላ
20ኛውን ሕንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና
የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን መረቁ፡፡ አዲስ አበባ በተመድ
ተቋማት እንቅስቃሴ፣ ከኒውዮርክና ከጄኔቫ በመቀጠል ሦስተኛዋ
ከተማ ለመሆን መብቃቷን ባን ኪ ሙን ገለጹ፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት በቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር መለስ ዜናዊ
የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው አዲሱ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን
ሕንፃ ለተመድ ልዩ ልዩ ተቋማት አገልግሎት የሚውል መሆኑን
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ
ተናግረዋል፡፡
ሕንፃውን በትናትናው ዕለት በይፋ ያስመረቁት ጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለ ማርያም እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ከ50
ዓመታት በፊት የመጀመሪያውንና የአፍሪካ አዳራሽ ተብሎ
የተሰየመውን ሕንፃ ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አገልግሎት
እንዲውል በስጦታ አበርክታለች፡፡ በ1951 ዓ.ም. የአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲመሠረት፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ
ሁኔታዎች ለአፍሪካ ኮምጫጫ ነበሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
የአፍሪካ ሕዝቦች ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት
የሚታገሉበት ጊዜ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ በውጭ የሚኖሩ
የአፍሪካ ልጆችም ለአኅጉሪቱ ነፃ መውጣት፣ ለሕዝቦች
እኩልነትና ክብር ሲታገሉ በነበረበት ወቅት ነበር የአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዕውን የሆነው፡፡
ዕድምተኛውን ፈገግ በማሰኘት ንግግራቸውን የጀመሩት የተመድ
ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ በዓለም ላይ
ደጋግመው ከጎበኟቸው ከተሞች አንደኛ ሆና እንደምትገኝ
በማስታወስ ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር
ኃይለ ማርያምን የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር በማለት
በስህተት መጥቀሳቸው የታዳሚውን ፈገግታ ያጎረፈባቸው ባን
ኪ ሙን፣ ይቅርታ ጠይቀው የስም አጠራራቸውን በማስተካከል
ንግግራቸውን ቀጥለዋል፡፡
አዲሱ ሕንፃ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን
ሒሮሺማ ከተማ ላይ ከተጣለው የአውቶሚክ ቦምብ የተረፉ
ዛፎች መጥተው እንደተተከሉበት አስታውሰዋል፡፡ ሕንፃውን
አምስት የተባበሩት መንግሥታት መሥሪያ ቤቶች እንደሚጋሩት
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ
ተናግረዋል፡፡
ሕንፃውን የገነባው አገር በቀሉ ራማ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ባለሰባት ፎቅ የሆነውን
ዘመናዊ ሕንፃ ከኒውዮርክ በሚሰጠው ትዕዛዝና ቁጥጥር
እየታገዘ መገንባቱንና አረንጓዴ የግንባታ ይዘት ተብሎ
በሚጠቀሰው ቴክኖሎጂ መገንባቱን የኩባንያው ማኔጂንግ
ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ተድላ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡
ለሕንፃው ግንባታ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣
በ1800 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እዚያው በአፍሪካ ኢኮኖሚክ
ኮሚሽን ቅጥረ ግቢ ውስጥ የተገነባ ነው፡፡
የሕንፃው ግንባታ በሁለት ዓመታት እንዲጠናቀቅ ታስቦ ግንታው
ቢጀመርም፣ ሦስት ዓመት ፈጅቷል፡፡ ይህም ከመጀመሪያውኑ
ከርክክብ ሒደቱ ጀምሮ የተለያዪ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ
በማስገባት ሒደት፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማግኘትና
በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደሆነ አቶ ፍሬው ተናግረዋል፡፡
ይህም ሆኖ ሕንፃው በሶላር ኢነርጂና በኃይል ቆጣቢ
ቴክኖሎጂዎች የታገዘ መሆኑን፣ ሰዎች ሕንፃው ውስጥ ሲሆኑ
የሚበሩ፣ ሰዎች በሌሉ ጊዜ ደግሞ በራሳቸው የሚጠፉ
የመብራት ይዘቶችንም አካትቷል፡፡
ራማ ኮንስትራክሽን በሐንኪን ቢራ ፋብሪካ ግንባታ፣ በወንጂ
ስኳር ማስፋፊያ፣ በአዲስ አዳማ የፍጥት መንገድ ግንባታ ላይ
የተሳተፈ ሲሆን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት በፕሬዚዳንት ሙላቱ
ተሾመ የተመረቀውንና ቦሌ አካባቢ የሚገኘውን የኦሮሚያ ልማት
ማኅበር ሕንፃን ገንብቷል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጥቅምት 18/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ አፋኙን ስርዓት በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ አቀረበ፡፡
ImageImage
‹‹የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል›› ያለው የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ ገዥው ፓርቲ ከዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መልኩ አፋኝ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ ገልጾአል፡፡

መግለጫው ለስርዓቱ አፋኝነት በምሳሌነት ካነሳቸው መካከል በአለፈው ክረምት ወራት ጀምሮ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠው የግዳጅ ስልጠና የሚገኝበት ሲሆን በስልጠናው ስነ ምግባር በጎደለው መልኩ የጥላቻ ዘመቻ በማካሄድ የሃሳብ ልዩነትን የማስተናገድ ፍላጎቱ ሙሉ ለሙሉ እንደተዳፈነ ያሳየ ነው ብሎታል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ስልጠናዎች እጅግ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆየ መሆኑንና ከጅማሬውም ተቃውሞውን በይፋ መግለጹንም መግለጫው አውስቷል፡፡
ፓርቲው በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የማሳደድ እርምጃ፣ በነጻው ፕሬስ ላይ የተፈጸመው አፈና የስርዓቱን መበስበስ እና አፋኝ አምባገነንነትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀጠል መምረጡን ግልጽ አመላካች ነው ብሏል፡፡

‹‹እጅግ የከፋውና እየተባባሰ የመጣው ከፍተኛ አደጋ ያዘለ ችግር ያለው አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ እያነሱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀይል ለመግዛት ቆርጦ መነሳቱ ነው›› ያለው መግለጫው በተለይ በኦጋዴን በርካታ ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ህይወታቸው መቀጠፉ ሳያንስ ሬሳቸው እንኳን ክብር በሌለው ሁኔታ መሬት ለመሬት እየተጓተተ ባደባባይ ሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አውስቷል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላም የህወሓት ሰዎች መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀራመታቸውን የተቃወሙ በርካታ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ሁነት ሀገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እያመራች ለመሆኑ አመላካች ነው ሲል ገልጾአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን በደል በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው ‹‹የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት መላው የሀገሪቱ ህዝብ፣ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ለሀገር ተቆርቋሪ ተቋማት እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ስር ሆናችሁ ለውጥን የምትሹ ወገኖች ሀገራችንን ወደ አደጋ እየወሰዳት ያለውን አፋኝ ስርዓት በቻላችሁት ሁሉ በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንድትሆኑ›› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ   ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው “ምርጫ” ምን ያህል ያውቃሉ?  ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ካለው የገዥው አካል የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ በመገናኘት እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር…”በዚህ ዓመት ጠቅላይ ሚስትር [ኃይለማርያም ደሳለኝ] እና …

ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለኢትዮጵያ ምርጫ ምን ያህል “ያውቃሉ”? Read more »

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2011 እስካሁን ያለውን ሁኔታ አጥንቶ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ፣ ከ5 ሺ ያላነሱ ኦሮሞች በእስር ላይ ይገኛሉ። ጥናቱን ያጠኑት የአምነስቲ የኢትዮጵያ ክፍል ሃላፊ ክሌር ቤስተን መንግስት አገሪቱን ለአለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን፣ ለአለማቀፍ የሰብአዊ  መብት ድርጅቶች እንዲሁም ለአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ክፍት ቢያደርግ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊሶች ሰኞ እለት አሸባሪዎች በከተማዋ ገብተዋል በማለት በቦሌ አካባቢ ፍትሻ ባደረጉ ምሽት መንግስት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳውን ጥያቄ እንዲመልስ የሚጠይቁ መፍክሮች  በቦሌ ወሎ ሰፈርና በደንበል አካባቢዎች ተጽፈው አደረዋል።  መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም፣ ድምጻችን ይሰማ፣ በመንግስታዊ ጥቁር ሽብር ተስፋ አንቆርጥም የሚሉ መፈክሮች በየመንገዱ ተለጥፈው ታይተዋል። ተመሳሳይ መልእክት የያዙ …

ጥቅምት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ የሚገኙት የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጂም ዮንግ ኪም በምእራብ አፍሪካ የሚታየውን የኢቦላ ወረርሽን ለመዋጋት ቢያንስ 5 ሺ ዶክተሮች የሚያስፈልጉ በመሆኑ ፣ ዶክተሮች ና የጤና ባለሙያዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃዳቸውን እንዲገልጹ ተማጽነዋል። ” በአሁኑ ሰአት ይህን ሁሉ ቁጥር ያለው የህክምና ዶክተር ከየት እንደምናገኝ ሳስብ እጨነቃለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ …

የስዊድን ጋዜጠኞች ማኅበርና የተለያዩ ለፕረስ ነጻነት የሚቆረቆሩ ወገኖች በትናንቱ ዕለት ፣ ኤርትራ ውስጥ ባለፉት 13 ዓመታት በአሥራት ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅን አስበውት ዋሉ ። በትውልድ ኤርትራዊ በዜግነት ስዊድናዊ የሆነው ዳዊት ጉዳይ

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የእስራት፣ የስቃይ፣ የግድያ እና የግፍ ተግባር ይፈፅማል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገዉ ሪፖርት ገለፀ። ድርጅቱ ይፋ ባደረገዉ ሪፖርት በሽዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች የእስር የስቃይና የግድያ ሰለባ ሆነዋል።

የሶርያዉ ደም አፋሳሽ የርስ በርስ ጦርነት አራት ዓመት ሆነዉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶርያዉያን ጦርነቱን በመሸሽ ሀገር ቀያቸዉ ጥለዉ ተሰደዋል። ፖለቲከኞችና የርዳታ ድርጅቶች የዓለም ዓቀፍን ድጋፍ እየጠየቁ ነዉ። ዛሬ የ 40 ሀገራት መንግሥታትና ዓለማቀፍ ድርጅቶች የሶርያን ስደተኞች በተመለከተ ጉባኤ አድርገዋል።

የአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ሰላም እና ፀጥታን ለማጠናከር እንዲሰሩ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን እና የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ጂም፣ እንዲሁም፣ በኢትዮጵያ የአውሮጳ ህብረት ተጠሪ ማርኮ ካማሮ ጠየቁ።

ከጥቂት ወራት በፊት ሰንዓ የመን ውስጥ ተይዘው ለኢትዮጵያ ተላልፈው የተሰጡት የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በተመለከተ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካምረን ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከጥቂት ጊዜ በፊት ደብዳቤ እንደላኩ ተገልጾዋል።

ያደረውን የሕገ ቤተ ክርስቲያን አጀንዳ በፈቃዳቸው ትተው ሌላ ርእሰ ጉዳይ አንሥተዋል የተቃወሟቸውን አባቶች በአሳፋሪ ንግግሮች በመዝለፍ ለማሸማቀቅ ሙከራ አድርገዋል የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አጀንዳ ቀጣይነት በድምፅ ሊወሰንበት እንደሚችል ተመልክቷል እንደ ሕጉ ስብሰባውን በአግባቡ ካልመሩ ምልአተ ጉባኤው ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ይቀጥላል *                *               * ‹‹ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ …

ባሳለፍናቸው አመታቶች የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገር አቀፍ በብሄር አቀፍ እና ቤተሰብ አቀፍነት ተመስርተው ከስመዋል። ሲንደባለሉ ለአሁኑም ወቅታዊ ጡዘት የደረሱም እያዛጉ እና እያፋሸኩ በፖለቲካ አንጎበር እየተናጡ በገሺው አምባገነን ፓርቲ እየተደቆሱ ላለመሞት በወንዳታነት እየተፈራገጡ ይገኛል። የተቃዋሚ ሃይሎች እና የለውጥ ፈላጊ ሃይሎች አንድነት የሚያስፈልግበት ወቅታዊ እና ወሳኝ ትግል ላይ መድረሳችን ለሕዝብ ያለንን አክብሮት ለማሳየት እና ግባችንን በመምታት ለህዝባዊ […]

በአቤ ቶኪቻው

ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ከተከሰሰባቸው ክሶች በአንደኛው ሶስት አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት።

በሌሎቹ ክሶች ምን እንደሚፈረድበት ቀጥሎ የምናየው ቢሆንም ተሜ እና ሌሎች ወንጀለኛ ያልሆኑ ሰዎችን… (ይሄን ግዜ አንዳድ አብዝተው የዋህ የሆኑ ሰዎች እና አብዝተው የኢህአዴግ ዝምድናን የተጋመዱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ያላቸውን ሰዎች ከወንጀል ነጻ ናቸው ማለት ተገቢ ነውን… እያሉ ሊሞግቱን ጣታቸውን ሲያሞጠሙጡ ይታየኛል…

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነቢዩ ሲራክ

ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ”… አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው!” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ፣ ተናደድኩ … በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነቢዩ ሲራክ

ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ” … አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው! ” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው ፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ ፣ ተናደድኩ …በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በዓለማየሁ ገላጋይ 

የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል… ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመን ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራል ይናቃል…
… ወይም ….

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። ሃብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ወደ መጸዳጃ ቤት እንድዳይሄድ በመከልከሉ በፌስትታል ይጠቀም እንደነበረ፣ ለሶስት ሳምንታትም ቁጥር ስምንት በምትባል የጨለማ ቤት ዉስጥ ለብቻው እንዲቀመጥ መደረጉንም አረጋግጠናል። “ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ከሆነ ትወጣለህ። አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተው” […]

ፓትርያርኩ የማኅበራት ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ኾኖ በማእከል ካልተመራ በሚል ከማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋራ የሚቃረን ግትር አቋም ይዘው ውለዋል፡፡ አቋማቸው ተቀባይነት ካላገኘ ስብሰባውን ለመምራት እንደሚቸገሩ በመግለጽ ምልአተ ጉባኤን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽኑ አቋም ሳቢያ አልተሳካላቸውም፡፡ ጉዳዩ ‹‹ከአዲስ አበባ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ የሠራኹበትና የደከምኩበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመስተዳድሩ ኃላፊዎች በፖለቲካ ስልጠና እና በግምገማ መወጠራቸው ውሳኔ በወቅቱና በአግባቡ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ነዋሪዎች አገልግሎት ለማግኘት ተቸግረዋል። በእያንዳንዱ የሴክተር መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙጥ ኃላፊዎች የሉም ያለው ዘጋቢያችን፣ ውሳኔዎችን የሚሰጥ በመጥፋቱ የውጪም ሆነ የውስጥ አግልገሎት ቆሟል። ኦህዴድ በአዲስ አበባ ያሉትን ከፍተኛ የአመራር አካላት ወደ አዳማ በመጥራት ለ14 ቀናት …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋምቤላና በደቡብ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በሚኖሩ በመዠንገርና በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ ቁጥራቸው 50 የሚጠጋ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያና የአካባቢው ሚሊሺያዎች ከተገደሉ በሁዋላ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሰራዊት አሁንም በአካባቢው እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። ወኪላችን እንደሚለው ጦርነት ይነሳል በሚል ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ከፍተኛ ስጋት የነበረ ሲሆን፣ …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ ግዙፍ ባልሆነ ማሰናዳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት ወንጀል ተከሶ ሲከራከር ከቆየ በሁዋላ፣ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 9ኛ ወንጀል ችሎት በ3 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። ጋዜጣውን ሲያሳትም የነበረው ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት ደግሞ በ10 ሺ …

ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ አባላት አሸባሪዎች ገብተዋል በማለት የሚያደርጉት ተደጋጋሚ ፍተሻ እንዳስመረራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የተጠናከረ ፍተሻ ሰኞ እለት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት በቦሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች፣ አሸባሪዎች ገብተዋልና አጋልጡ በሚል መኪኖች ሲፈተሹ መዋላቸውን፣ መንገደኞች እየቆሙ መፈተሻቸውን እንዲሁም የቤት ለቤት አሰሳ መደረጉን ለሰአታት ታግተው የቆዩ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኩባ ዓለም አቀፍ ቀውስ ሲያጋጥም እንዴት ባፋጣኝ ለርዳታ መረባረብ እንደሚቻል ፣ ወረት የማካበት ሥርዓት ያለውን ምዕራቡን ዓለም በማስተማር ላይ ናት። ከመስከረም ወር ማለቂያ ገደማ አንስቶ እስካሁን ከ 250 በላይ የህክምና ዶክተሮችንና ነርሶችን ወደ ምዕራብ አፍሪቃ ልካለች።

የአውሮጳ ህብረት፣ የዓለም ባንክ እና ሌሎች ያካባባ የልማት ባንኮች ለአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ስምንት ቢልዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ቃል ገቡ። ይህ ዜና ይፋ የሆነው የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ከዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ጂም ዮንግ ኪም ጋር ዛሬ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ ነው።