እስክንድር ነጋ ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
በጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ
‹‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ከእስር ይወጣል››
‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ››
እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር። ባለፈው ሳምንት የ‹‹ባንዲራ ቀን›› በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር።