ሀብታሙ አያሌው ስለ “መለስ ራዕይ” ምን ብሎ ነበር?
በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
‹‹መለስ በህይወት ቢኖር ራሱ የሚቃወማቸው ይመስለኛል››
‹‹አቶ ኃይለማርያም፣ የራሱን አመለካከት አሳድራለሁ ያለ ቀን፤ ወደ እነአንዱአለም ጎራ ይቀላቀላል፤ መለስ ቢኖርም ባይኖርም!!!››
አቶ ሀብታሙ አያሌው /የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ/
አሁን በእስር ላይ ማዕከላዊ ሆኖ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእግር ህመም እየተሰቃየ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከመታሰሩ 10 ቀናት ቀደም ብሎ ለ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ጋዜጣ እኔ እና ባልደረባዬ አናንያ ሶሪ በ‹‹መለስ ራዕይ›› ዙሪያ ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገንለት ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱም በጋዜጣው ላይ ተስተናግዷል፡፡ ቃለ-ምልልሱን ማንበብ ላልቻላችሁ ወገኖቼ ታነቡት ዘንድ የተወሰነውን እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡-