ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአሚባራ በአፋርና በኢሳ መካከል የተነሳውን ግጭት  ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው ገድለው ሌላ የአፋር ተወላጅን ደግሞ አቁስለዋል። በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከትናንት ጀምሮ ገዋኔና ቡድመዳ ወረዳዎች በጎርፍ መጥለቅለቃቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አሰልጥኖ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ለመደባቸው ካድሬዎች የሁለት ቀናት የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ስልጠና በመስጠት በተለይ በግንቦት ወር ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲሳካ የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለጸው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤቱ በሚኒስትሮች ምክርቤት …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በአዳማ ከተማ   ለጋዜጠኞች ባዘጋጀው ሴሚናር ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ተወክለው በስብሰባው በመገኘት ንግግር ያደረጉት አቶ ናስር ለገሰ ባቀረቡት የኢትዮጵያ ሰፖርት ታሪክ ንግግራቸው የቀደሙት መንግስታትን ስራ በማጣጣል የገዢውን መንግስት ስራ በማግዘፍ ባቀረቡት ጽሁፍ ከጋዜጠኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ የገዢው መንግስት አሁን የሚያንቀሳቅሰው ከፍተኛ በጀት ስፖርቱ እንዲጎለብት ለማድረግ …

 ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩ በጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትና በማድረግ በንጹሀን ዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞ ከህዝቦች …

የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት፣ Read more »

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የአውሮፓ ፓርላማ ጥቅምት 22 ቀን 200 7 ሥልጣን የሚረከቡትን ፣ አዲሱ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዣን ክሎድ ዩንከር ያቀረቧቸውን የኮሚሽን ሹማማንት የሥልጣን ቦታ በዛሬው ዕለት በድምጽ ማጽደቁ ተነገረ።

የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ግብረ ኃይል ሰብሳቢ የነበሩት፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው በጸና መታመማቸዉንና ዛሬ በሆስፒታል መዋላቸዉን ለማረጋገጥ ችለናል። የማእከላዊ እሥር ቤት ብዙ ቶርቸር የሚደረግበት እስር ቤት እንደሆነ ይታወቃል። አቶ ሃብታሙ አያሌው ከብሎገር አብርሃ ደሳታ፣ ዳን ኤል ሺበሺና የዚዋስ አሰፋ ጋር ሐመሌ 1 ቀን የታሰሩ ሲሆን፣ ፖሊስ «መረጃ ለማሰባሰብ ጊዜ ይሰጠኝ» በሚል አራት […]

ባለፈው እሁድ ፣ አንድ ስባሪ ኮከብ ወደ ማርስ ከዚያ በፊት ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ መጠጋቱ ፤ ለምን የሥነ ፈለክ ጠበብትን ትኩረት ሳበ? ስባሪ ከዋክብት ከየት ነው መነሻቸው? 9ኛው ፕላኔት አይደለም ተብሎ እ ጎ አ በ 2006 ከ ዝርዝር እንዲወጣ የተደረገው

በቃለ ዐዋዲው ደንብ መሠረት፣ በካህናት እና ምእመናን አንድነት በየደረጃው የተዋቀረውና የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደር ለመምራት ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ደረጃ ያካሔደውን ፴፫ኛ ሀገር አቀፍ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ቀትር ላይ የአቋም መግለጫ በማውጣትና የውሳኔ ሐሳብ በማቅረብ አጠናቅቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር …

በአሳሳቢው የኢቦላ ወረሽኝ ላይ ያተኮሩ ትምሕርታዊ ጽሁፎችን በአማርኛ አዘጋጅተው በተለያዩ የኢትዮጵያውያን ድረ ገጾችና የሕክምና መወያያ መድረኮች አማካኝነት በማሰራጨት ለንባብ ያበቁ ሃኪም ናቸው።

ዶ/ር አሸናፊ ዋቅቶላ ይባላሉ። በኢቦላና ተዛማች ርዕሶቹ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የሚቀናበረው የሃኪምዎን ይጠይቁ ተከታታይ ፕሮግራም እንግዳ አደርገናቸዋል።

የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

 

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ በ2006 በጀት ዓመት በ36 መዝገቦች በኦነግ፣ በግንቦት ሰባት፣ በኦብነግ፣ በጋህነን፣ በቤህነን እንዲሁም በአልሻባብ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን መክሰሱን በመጥቀስ የፌደራል ፖሊስ ሽብርን የመከላከል አቅሙ እንዳደገ በመግለጽ ራሱን አሞካሽቷል፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ባለፈው ዓመት 36 የሽብር መዝገቦች መካከል በ27 ቱ ላይ ምርመራ ተጠናቆ …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ወኪል እንደገለጸው በሸኮ መዠንገር ተወካዮችና በከፋ፣ ሸካ፣ ጋምቤላና ቤንች የዞን አመራሮች መካከል በሃይማኖት አባቶች አማካኝነት በቴፒ ውይይት እያደረጉ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናትን በማናገር እንደዘገበው የንግግሩ ዋና አላማ ሸሽተው በየጫካው ውስጥ የሚገኙ የመዠንገርና የሸኮ ተወላጆች አሳምኖ ወደ ቀያቸው ለመመለስ ነው። ይሁን እንጅ ለድርድር የሄዱ አንዳንድ የመዠንገር ተወላጆች …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጠኝ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቅምት 11/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ፓርቲዎቹ ነጻ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ ለመታገል መስማማታቸውን ትብብር ሰነዱ ላይ አስፍረዋል። ትብብሩን እንዲመሩ  ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከሰማያዊ ፓርቲ …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደሚለው በከተማው የታየውን የስኳር እጥረት ተከትሎ፣ አንድ ኪሎ ስኳር እስከ 30 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በተመሳሳይ መልኩ የሚታየው የዘይት እጥረት  የነዋሪውን ኑሮ አስከፊ እንዳደረገው ገልጿል። የስኳር እጥረቱ በደቡብ፣ በኦሮምያና በአማራ አካባቢዎችም በስፋት እየታየ ነው። መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት ሲገቡ ስኳር ወደ ውጭ መላክ እንችላለን በማለት …

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ በሚገኙ የሰሜን ጎንደር ጠረፋማ ወረዳዎች፣ በአዊ፣ በዋግ ህምራ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖች የሚገኙ መምህራን ወደ አጎራባች ክልሎች  በመፍለሳቸው  በትምህርቱ ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያደረሰ መሆኑን  ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡ ክፍተቱን ለመሸፈን አስረኛ ክፍል ያጠናቀቁ እና በልዩ ልዩ ሙያ የተመረቁ ተማሪዎች እንዲቀጥሩ ለአራቱ ዞኖች ደብዳቤ  ስለደረሳቸው ይህንኑም እየተፈጸሙ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ቀደም ባሉ ዓመታት የበለፀጉት ሃገራት በሽታዎች ተብለዉ ከሚፈረጁት ካንሰር አንዱ ነበር። የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተዉ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን የኗኗር ሁኔታ መለወጥን ተከትሎ በአዳጊና ደሀ ሃገራትም መስፋፋቱ ይታያል።

ተሻለ መንግሥቱ (ከአዲስ አበባ) ኢትዮጵያ እጅግ ድሃና ኋላ ቀር ከሚባሉ የዓለም ሀገሮች ተርታ የምትሰለፍ መሆንዋን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ያረዳሉ – እኛም በዘግናኙ ኑሯችን ይህንኑ መራራ እውነት እያረጋገጥነው እንገኛለን፡፡ በሰብኣዊ መብት አያያዝ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥልጣኔና በመሳሰሉ የሀገርና የሕዝብ ጤናማ ዕድገት መለኪያዎች …

ትንሹ መለስ በሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ Read more »

የመጽሐፍ ግምገማ “ያካባቢ ጉዳይ በኢትዮጵያ፣ ልብ ወለዳዊ የንባብ መጽሐፍ” ደራሲ፣ ዶ/ር ከፍያለው አባተ ገምጋሚ፣ ዶ/ር ጌታቸው መልኬ ግምገማውን  በፒ.ዲ. ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ያካባቢ ጉዳይ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ግምገማ                                                                                                                …

“ያካባቢ ጉዳይ በኢትዮጵያ፣ ልብ ወለዳዊ የንባብ መጽሐፍ” Read more »

ቃለ ጉባኤ፡- የበጀት ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ዘገባዎች ትኩረት ከሰጧቸው ዝርዝር ነጥቦች ውስጥ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ እንቅስቃሴ የሰፈረው የጉባኤተኛው ቃል (ገጽ 12) የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ፡- የማኅበራትን ታላቅ አስተዋፅኦ ስለማወቅና ችግሮቻቸውን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ስለ መፍታት የተያዘው የጋራ አቋምና የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ (ገጽ 20)

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሰሞኑን አሻሽሎ ያዘጋጀውና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት እንዲወያዩበት የተዘጋጀው  ሰነድ ለኢሳት የደረሰ ሲሆን፣ ሰነዱ የመንግስት የመረጃና የደህንነት መስሪያ ቤት ወይም ኢንሳ በኢሳት በአሜሪካ እና በጀርመን ድምጾች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ከመማጸን ጀምሮ መንግስት በሴቶች፣ በወጣቶችና በምሁራን ስም የሃይማኖት ማህበራትን እንዲቋቋሙ እገዛ እንዲደርግ፣ በሰርተፍኬትና በዲግሪ ደረጃ የሃይማኖት …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን በተመራውና ሁሉም የክልል መንግስታት የኮሚኒኬሽንና የመገናኛ ብዙሃኖች የተሳተፉበት የኢህአዴግ የምርጫ ዘመቻ ፕሮፓጋንዳ ዝግጅት ባለፈው ቅዳሜ ሲጠናቀቅ ሁሉም የክልል ሚዲያዎች ቀጣዩን ምርጫ ሊያሳምን የሚችል አቀራረብ ፣ ዜና እና ፕሮግራም እንዲየቀርቡ እንዲሁም በምርጫው የኢህአዴግ አሸናፊት ቅኝት ውስጥ ስራዎችን እንዲሰሩ ታዘዋል። ብአዴን በምርጫው ዙሪያ ለከፍተኛ አመራሩ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ የመከላከያ ሰራዊትን የሚከዱ ወታደሮችን ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ፣ በአካባቢው የሚገኙት ወታደሮች በህዝቡ ላይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰዱ ነው። የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪዎች እሁድ እለት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ለአሁኑ ሰልፍ ምክንያት የሆነው ጥቅምት 7 አንድ ወታደር መጥፋቱን ተከትሎ የአጎቱ ልጅ የሆነ የጤና ባለሙያ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት እንዲታሰር ከተደረገ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኤርትራ ድንበር አካባቢ በጥበቃ ላይ የሚገኙ ወታደሮች በመረጃ ስህተት ለ33 ዲቃዎች በባዶ ሜዳ ላይ ሲተኩሱ የዋሉ ሲሆን፣ ለጦሩ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት መከላከያን አወናብደዋል የተባሉ 5 ወታደሮች ተይዘው እንዲታሰሩ ተደርጓል። ከግንቦት ሰባት ተኩስ ተከፈተ ተብሎ ለማዕከላዊ የጦር ሃይል ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ይህን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ ተገብቶ …

ጥቅምት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ በረከት ስምኦን ” የኢሳት ዘጋቢዎችን መቆጣጠር አልተቻለም፣ በውስጣችን ያሉ ሃይሎች ጣሉን” ያሉ ሲሆን፣ ከሚኒስትሮች በስተቀር የደህንነት ሃይሎችም ሆኑ ጋዜጠኞች በፖለቲካ ስብሰባ ላይ ሞባይል ይዘው እንዳይገቡ እንደከለከሉ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። አቶ በረከት ከዚህ ቀደም እርሳቸውንና ድርጅታቸውን የተመለከቱ መረጃዎች በኢሳት ተደጋግሞ መውጣት እንዳበሳጫው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የኢህአዴግን ምክር ቤት ስብሰባዎች …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው በትልቁ የህዳሴ ግድብ ሰበብ የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ የኢትዮጵያ ፣የግብፅ እና የሱዳን ተወካዮች እና ባለሙያዎች ባለፈው ሐሙስ እና ዓርብ ካይሮ ውስጥ የሶስትዮሽ ውይይት አካሄዱ።

አክራሪው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ቦኮሃራም ያገታቸው ከ200 የሚበልጡ ልጃገረድ ተማሪዎችን ይፈታ ይሆን?የናይጄሪያ መንግሥትና ቦኮሃራም የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ከተሰማ ካለፈው ዓርብ አንስቶ ትልቅ ተስፋ ተጥሎ ነበር። ይሁንና በሳምንቱ መጨረሻ በመካሄድ ላይ ያሉት ጥቃቶች ተስፋውን የሚያመናምኑ ናቸው።

ኢቦላ-ባለፉት ሰባት ወራት አራት ሺሕ ስድስት መቶ ያሕል ሰዎች ገድሏል።ከአስር ሺሕ በላይ ለክፏል።የሰወስቱን የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ምጣኔ ሐብት አሽመድምዶታል።ዩናይትድ ስቴትስ እና ስፓኝም ቢያንስ አራት ዜጎቻቸዉ ተለክፈዋል።ዛሬ ሁሉም ዓለም ከISIS ቀጥሎ የመቅሰፍቱን ታላቅነት ያወራል።መቅሰፍቱን ለማስወገድ ግን አሁንም ሩቅ ነዉ።

ርብራብ

ኃይለ ልዑልና ዶ/ር ብርሃነ ከቀድሞው የአውስትራልያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኬቪ ሩድ ጋር

በየሀገሩ ስዞር ለሀገራቸውና ለወገናቸው ልዕልና ያለው ሥራ የሚሠሩ፣ ወግ ያለው ታሪክ ያላቸው፡፤ ከመንደርተኛነትና ወንዘኛነት ድንበር ተነጥቀው በሉላዊነት መንበር ላይ የተቀመጡ፣ ከምድጃ ሥር ወሬ ርቀው ዓለም ተኮር ነገር ውስጥ የሚዘውሩ ዜጎቻችንን ሳይ ትፍትፍ እላለሁ፡፡ እሥራኤሎች በልዩ ልዩ ሀገር ሆነው ለሀገራቸው የሠሩ ዜጎችን ታሪክ ሲጽፉ ‹የኛ ሰው በዚህ ቦታ› የሚሉት ዓይነት ርእስ ይሰጣሉ፡፡ ‹የኛ ሰው በደማስቆ› እንዲል ማሞ ውድነህ፡፡

ባለፈው ኀሙስ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓም እናንተ አቦን ስታከብሩ እኔ ደግሞ እዚህ ሜልበርን ለየት ያለ ግብዣ ደረሰኝ፡፡ የጋበዘኝ የአፍሪካና አውስትራልያ ማኅበር(African Australian Association – AAA ) ዋና ዳይሬክተሩ በሆነው ኃይለ ልዑል ገብረ ሥላሴ በኩል ነው፡፡ ኃይለ ልዑል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ካበረከተቻቸው አዳጊ የማኅበረሰብ መሪዎች አንዱ ነው፡፡ ከ ላ ቶቤ የኑቨርሲቲ በ2000 በዓለም አቀፋዊ ልማት ማስተርስ ያገኘ፣ በ2008 ከሜልበርን ዩኒቨርሲቲ በማኅበረሰባዊ ፖሊሲና አስተዳደር በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ ሰው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከ22 ዓመታት በፊት በሜልበርን እንድትተከል ከመልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን ጋር የተላከውና ዛሬ በአውስትራልያ ለምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይዋን ያስቀመጠው ኃይለ ልዑል አፍሪካ በአውስትራልያ ገንዘብ፣ ዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንድትጠቀም በአውስትራልያ የሚገኙ የአፍሪካ ዳያስጶራዎችም አህጉራቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ የተመሠረተውን የአፍሪካ አውስትራልያ ማኅበር ከመሠረቱትና ከሚመሩት ልሂቃን አንዱ ነው፡፡

በሚኖርበት በቪክቶርያ ግዛት ለአፍሪካውያን የመሪነት ኮርስ ለመስጠት የሚያስችል መርሐ ግብር እንዲቀረጽ ከዶክተር ብርሃን አሕመድ ጋር የተጋ፣ ሥራውም ውጤታማና ተቀባይነት አግኝቶ እስከ 2018 የሚዘልቅ መርሐ ግብር በቪክቶርያ መንግሥት የተያዘለት፤ እስካሁንም ከ30 የአፍሪካ ሀገሮች የመጡ 140 አዳጊ የአፍሪካ ማኅበረሰባዊ መሪዎችን በዚህ መርሐ ግብር ማስመረቅ የቻለ ፕሮጀክት ለመዘርጋት የቻለ ሰዋችን ነው፡፡

የፉት ስክሬይ ማኅበረሰብ የሥነ ጥበብ ማዕከል የቦርድ አባል፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የአውስትራልያ ማኅበረሰቦች የሚያካትተው Ethnic Communities’ Council of Victoria ሊቀ መንበር፣ የአፍሪካ የሐሳብ ማዕከል (African Think Thank) ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ማኅበረሰቡን እያገለገለ ነው፡፡ ለዚህና ለሌሎቹ አገልግሎቶቹ  የዊኒስተን ቼርቺል ፌሎው – ሽልማት(2008)፣ የዊልያምሰን ማኅበረሰብ አመራር መርሐ ግብር- ሽልማት(2009)፣ የጋራ ብልጽግና አገሮች የሚኒስትሮች አማካሪ ኮሚቴ ለአፍሪካ – ሽልማት(2012)፣ እጅግ የተዋጣለት የማኅበረሰብ መሪ – ሽልማት(2011)፣ እንዲሁም በብዝሐ ባሕል የተዋጣለት ሥራ ለሠሩ የአውስትራልያ ሰዎች የሚሰጠውን (Meritorious service in the community) ሽልማት ከቀድሞው የቪክቶርያ ገዥ(Premier) በ2004 ተቀብሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ትምህርትና ሥልጠና፡ ዕድሎችና ተግዳሮቶች

ዘንድሮ በሜልበርን ከተማ ቪክቶርያ ዩኒቨርሲቲ ኣዳራሽ የተካሄደው የአፍሪካ አውስትራልያ ማኅበር ዋና አጀንዳ በትምህርትና ሥልጠና ላይ ያተኮረ ነበር (Doing Business in Africa: Opportunities in International Education and Training)፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ከቪክቶሪያ ግዛት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከኩባንያዎችና አፍሪካ ላይ ከሚሠሩ ተቋማት የመጡ ተወካዮች ሐሳቦቻቸውን፣ ሥራዎቻቸውንና ያጋጠማቸውን ነገር አቅርበው ነበር፡፡ በተለይም ባለ ሥልጣናቱ አውስትራልያ ከአፍሪካ ጋር እስከ ዛሬ የነበራት ግንኙነት ማዕድንን የተንተራሰ እንደነበርና ከ65 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆነ የአውስትራልያ ኢንቨስትመንት በአፍሪካ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የትምህርት ግንኙነት ለአውስትራልያ 4ኛው የገቢ ምንጭ መሆኑንና ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ በየዓመቱ ለሀገሪቱ ሲያስገኝ ከ100 ሺ ሰዎች በላይ ደግሞ በሥሩ ተሠማርተው ገቢ እያገኙበት መሆኑን ነግረውናል፡፡ አውስትራልያ ትምህርት አሰጣጧን በማስተካከል፣ የተሻለ ልምድ ካላቸው ሀገሮች ደረጃዎችን በመውሰድ፣ ለተማሪዎች የሚሻሉ መንገዶችን በመዘርጋት በዓለም ከሚመረጡ የትምህርት ተቋማት ወገን የሆኑ ተቋማትን ለመመሥረት መቻሏን ነግረውናል፡፡ ‹በዓለም ላይ የትምህርት ልዕለ ኃያል ሀገር – super power in Education› ብለዋታል፡፡ የትምህርት ጥራትና ደረጃ አካዳሚያዊ ነጻነትን፣ በባለሞያ የሚመራ የትምህርት ሥርዓትንና ገለልተኛ የሆነ ገምጋሚ አካልን እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡ እኔም የሀገሬን ከፍተኛ ተቋማት እንዳስብ አድርገውኛል፡፡


 በተለይም ከትምህርት ተቋማት የመጡት ባለሞያዎችና ባለሥልጣናት በአንድ ነገር ላይ ተስማምተው ሲናገሩ ነበር፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ላይ የበጀት፣ የሰው ኃይልና የአሠራር ድጋፍ በማድረግ የአውስትራልያ መንግሥት በየጊዜው የተሻለ ሥራ ቢሠራም ሁለት ነገሮች ግን ለውጤቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች ደግሞ የሚገኙት ከተማሪዎች ነው፡፡ እነርሱም ፍላጎትና የተፎካካሪነት ስሜት(Interest and Competitiveness)፡፡ የምዕራቡ ዓለም ተማሪዎች የተሻለ ትምህርትና የትምህርት መሣሪያዎች ቢሟሉላቸውም ፍላጎትና ተፎካካሪነትታቸው ግን የእስያ ተማሪዎችን ያህል መሆን አልቻለም፡፡ በዚህም የተነሣ በአነስተኛ ወጭና ባልተሟሉ ሁኔታዎች ውስጥ የሚማሩት የእስያ ተማሪዎች የተሻለ ፍላጎትና የተሻለ ተፎካካሪነት ስለሚያሳዩ በተሻለ በጀት ከሚማሩት የምዕራቡ ተማሪዎች ይልቅ በውጤትማነት የተሻሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የተከበሩ ፊል ሀኔውድ የተባሉ የሥነ ትምህርት ባለሞያና የአውስትራልያ ዓለም ዐቀፍ የትምህርት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዳሉት ለተማሪዎች ውጤታማነት ወሳኞቹ ነገሮች ከውስጥ የሚመነጩት ሁለቱ ኃይሎች – ፍላጎትና የተፎካካሪነት ስሜት ናቸው፡፡

የአፍሪካ ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው ፍላጎትና ተፎካካሪነት የተሻለ በመሆኑ በአውስትራልያ ትምህርት ቤቶች በተመደበላቸው ትምህርት ጊዜ በመጨረስ የአፍሪካ ተማሪዎች ውጤታማ ሆነዋል፡፡ የሀገሬው ተማሪዎች የመጨረስ ዐቅም 70 ከመቶ ሲሆን የአፍሪካ ተማሪዎች ግን 94 በመቶ ነው፡፡

ይህንን ልምድ በመያዝም በስኮላርሺፕ ብቻ ከመገናኘት ይልቅ ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን ለመሥራት እየጣሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም 20 የአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ከ51 የአፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመሥረት ይህንን ሥራ ለማስፋፋት እየሠሩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በተመለከተ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች ድጋፍ ያለፈ ሪፖርት አልሰማሁም፡፡ በዚህ ረገድ ኬንያና ናይጄርያ የአንበሳውን ድርሻ መያዛቸው ነው የተነገረው፡፡

የአፍሪካ ተማሪዎች የበጀትና ትምህርት አመራር ድጋፍ ከተሰጣቸው የተሻለ ፍላጎትና ተፎካካሪነት አላቸው፡፡ በመሆኑም የአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በአውስትራልያ የትምህርት ደረጃና ጥራት የሚሰጡ መርሐ ግብሮችን በአፍሪካ ለመዘርጋት እየተሞከረ ነው፡፡ ይኼ ሁኔታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መልካም ዕድል በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚጠየቁትን ዝግጅት ከኤምባሲው በመውሰድ በጋራ ለመሥራት ቢነሡ ሀገራቸውን ለመጥቀም ይችላሉ፡፡ ተማሪዎቻችንን እንዲህ ባለ ዕድልና ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንጅ በስብሰባ ብቻ ብቁ ዜጋ ማድረግ አይቻልምና፡፡

click here for pdf


ሚሲስ ጃኩሊን ዝዋምቢላ የተባሉ በዚምባብዌ የቀድሞ የአውስትራልያ አምባሳደር እንደገለጡት የአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ገንዘብና የሰው ኃይላቸውን ይዘው፣ በአውስትራልያ ደረጃ ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት አራት መሠረታዊ ችግሮች ገጥመዋቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ብዙዎቹ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ሳይሆኑ የማስተማሪያ ዩኒቨርሲቲዎች (lecturing rather than research) መሆናቸው ከዓለም የጥናት ሥራዎች አስተዋጽዖ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 1% ብቻ እንዲያበረክቱ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኞቹ የሚያሠለጥኑት ለመንግሥት ሥራ(educating for public sector) እንጂ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚችሉ መስኮች አይደለም፡፡ ሦስተኛ ሆኖ የተነሣው የአፍሪካ ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ችግር ሊፈታ የሚችል፣ ራስ ተኮርና ራስ ፈጠር የሆነ መንገድና ደረጃ በመከተል፣ ዘላቂና ወጥ የሆነ፣ ብሔራዊ ቀለም ያለው የትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመቅረጽና በርሱም በቁርጠኛነት ከመመራት ይልቅ አውሮፓ ተኮር(Euro centric) መሆናቸው ነው፡፡ አራተኛው ብዙዎቹ ሀገሮች ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቂ በጀት ለመስጠት ባለመቻላቸው  በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለው ልዩነት የሰርተፊኬቱ ደረጃ ብቻ እንዲሆን ማድረጉ ነው፡፡ በአንድ ጥናት ላይ እንደተመለከተው ከአፍሪካ ዓመታዊ ገቢ(GDP)1% ብቻ ለከፍተኛ ትምህርት ይመደባል፡፡

ፕሮፌሰር ዴቪድ ሞሪሰን የተባሉ የሞርዶክ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ምክትል ቻንስለር አውስትራልያ በሚከተሉት ጉዳዮች በአፍሪካ ትኩረት እንደሰጠች ገልጠዋል (በአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር ለምታስቡ ተማሪዎች ወይም በጋራ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለመሥራት ለምትፈልጉ ተቋማት)፡፡ በአርብቶ አድር ልማት፣ በእርሻና ማዕድን፣ ለእናቶችና ሕጻናት ደኅንነት የዐቅም ግንባታ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ከአውስትራልያ ተቋማት ጋር አብረው ከሚሠሩ ወይም ከሚያጠኑ ጋር ለመቀናጀት መርሐ ግብር አላቸው፡፡ ‹‹ትልቁ ችግር›› አሉ ፕሮፌሰሩ ‹‹የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ምርምር ላይ ትኩረት ስለማይሰጡ የጥናት ባሕላቸው ዝቅተኛ ነው(underdeveloped research culture)፡፡ በዚህም ምክንያት የአውስትራልያ ተቋማት እንዲደረግ የሚፈልጉት ጥናትና የአጥኝው ዐቅም አለመጣጣም ይከሰታል፡፡ እኒህ የጥናት ባለሞያ ደጋግመው እንደገለጡት ‹የአንዲት ሀገር የመፍጠር ዐቅም በሳይንስ መሠረቷ የተጽዕኖ ዐቅም ይወሰናል(the country’s ability to innovate is influenced by the size of its science base)፡፡››

በአሁኑ ጊዜ 4.5 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በየሀገሩ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ ተማሪዎች በፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካና ሳዑዲ ዐረቢያ ነው የሚማሩት፡፡ በአውስትራልያ ከሚማሩ ዓለም ዐቀፍ ተማሪዎች መካከል ቻይናውያን 27.4፣ ሕንዶች 10.4፣ ቬትናማውያን 5.1 በመቶውን ይዘዋል፡፡ በአውስትራልያ ትምህርት ቤቶች ለመማር ከሚያመለክቱት መካከል አፍሪካውያን ከ1 – 15 ከሚገኙ ዋና አመልካች ሀገሮች ውስጥ የሉበትም፡፡ ለዚህ ዋና ምክንያቱ ቪዛ ለማግኘት ያለው ጣጣ፣ በቂ የመኖሪያ ወጭ ሽፋን አለመኖር(10 በመቶዎቹ ብቻ በተማሪዎች መኖሪያ ይኖራሉ)፣ አውስትራልያ እስያ ላይ በማተኮሯ፣ በአፍሪካ የሚገኙ ትምህርት ኤጀንሲዎች ስለ አውስትራልያ ትምህርት ዕድሎች በቂ ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑ፣ ቻይና ለአፍሪካ የተሻለ ስኮላርሺፕ በመስጠቷ መሆኑ ተገልጧል፡፡ በአውስትራልያ ለመማር የሚያስቡ ይኼንን ገጸ ድር ቢያዩት ተመክረዋል –

   www.studyinaustralia.gov.au

ከ2012 ጀምሮ ከ8000 በላይ የአፍሪካ ተማሪዎች በአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም 1500ዎቹ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ 40ዎቹ የዶክትሬት ዲግሪ እየሠሩ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የአውስትራልያ የትምህርት ተቋማት 14000 አፍሪካውያን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው፡፡ የአውስትራልያ መንግሥትም በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 5000 የማስትሬትና የአጫጭር ኮርሶች ዕድል ለአፍሪካውያን ማዘጋጀቱ ተገልጧል፡፡ ለአጫጭር ኮርሶች ይህንን ድረ ገጽ በማየት መጠቀሙ መልካም ነው –

www.australiaawardsafrica.org

ለቢዝነስ ጉዳዮች ደግሞ ወደዚህ ይዙሩ

www.dfat.gov.au

በጉባኤው ከነበሩት አቅራቢዎች ለአፍሪካውያን ስኮላርሺፕ ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ የተነሣው ለትምህርት የሚመጡ ተማሪዎች ወደ ሀገራቸው ያለመመለሳቸው ችግር ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም የስኮላርሺፕ ዕድላቸው የተንጠለጠለባቸው ሀገሮች አሉ፡፡ አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች በኮሪደር ወሬ ኢትዮጵያ ከእነዚህ አንዷ መሆኗን ነግረውኛል፡፡

ነፍሱን ይማረውና ጋዳፊ በአንድ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ ‹የአደጉትን ሀገሮች የአየር መበከል፣ የጦርነትና የፖለቲካ ችግር እንደምንካፈለው ሁሉ የእነርሱን ሀብትና ዕድገትም መካፈል አለብን‹ ብሎ ነበር፡፡ ናይጄርያውያንና ኬንያውያን ከአፍሪካ፤ ሕንድ፣ ቻይናና ቬትናም ከእስያ የአውስትራልያን የትምህርት ስጦታና ዕድል በሚገባ እንደሚጠቀበሙት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትምህርት ተቋማትና በአውስትራልያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስጶራ ተጋግዘን ዕድሉን ብንጠቀምበትና ለሀገራችን ሰው ብናፈራበት መልካም ይመስለኛል፡፡ በተለይም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና መካከለኛ ተቋማት ከአውስትራልያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለመሥራት የተዘጋጀውን መርሐ ግብር ተሻምቶ በመጠቀም በትንንሹ ዳቦ ከምንራኮት ትልቁን እንጀራ እንቁረስ፡፡ ወደ 310 ሚሊዮን ዶላር ለስኮላርሺፕ መንግሥት መመደቡን አብሥረዋል በጉባኤው ላይ፡፡ መልካም ዕድል፡፡

ሜልበርን፣ አውስትራልያ

“ማር እንኳን 23 አመትት ቢላስ ይመራል ። 23 አመት እንደ ኢሕአዴግ ላለ ፓርቲ እጅግ በጣም ረጅም አመት ነው” “ሕዝቡ ለዉጥ ይፈልጋል። በዚህ ላይ ምንም አነት ጥርጣሬ የለም፡፡በመላው ኢትዮጵያ ሲኬድ ይሄን አይነትት ስሜት አለ” “ትልቁ ነገር አማራጭ ሆኖ ሕብረተ ሰቡ ተስፋ ሊይደርገው የሚችል ፓርቲ ሆኖ መዉጣት የውወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ይመስልኛል” “አንድነት የሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች ቤትና ፓርቲ እንዲሆን […]

የበርካታ የአገዛዙ ባለስልጣናት የግል ቢዝነሶችና ፎቆች በፍጥነትና በጥራት እየተጠናቀቁ ባለብት በአሁኑ ወቅት፣ በ2002 ዓ.ም ለሕዝብ ይፋ ከሆነውና ላለፉት በርካታ አመታት በኢቲቪ ሲነገርለት ከቆየው፣ የአምስት አመቱ የእድገትና የትራስፎርሜሽን እቅዶ ዉስጥ በዋናነት ከሚጠቀሱት ሁለቱ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ፣ በአምስት ኮሪደሮች የታቀደው የባቡር ግንባታ መሆኑ ይታወቃል። ከታቀደው የ2300 ኪሎሜተር የባቡር መስምር ፣ ከመቶ ኪሎሜትር በላይ እንዳልተሰራ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የቀድሞ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው በፍቃዳቸው ሃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው ፣ በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ፣ አቶ በላይ ፍቃዱን አዲሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሆኑ መምረጡ ይታወቃል። አቶ በላይ፣ ዛሬ እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 20006 ዓ.ም ፣ አብረዋቸው የሚሰሩ 12 የሥራ አስፈጻሚ አባላትን መርጠው በብሄራውዊ ምክር ቤቱ አጸድቀውዋል። ከተመረጡት 12 የሥራ አስፈጻሚ አባላት ፣ 6 ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ሊቀመንበር የነበሩ ጊዜ፣ የሥራ […]