በዛሬው ሰድስተኛ ዙር የምርጫ ተብዬ ክርክር ጉዳዩ በመሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጎምቱ ያላቸውን ሹሞቹን ለክርክር ይዞ የቀረበበት ቢሆንም ለእኔ ግን ትኩረቴን የሳበው የተከራከሩበት ርዕስ ሳይሆን ተከራካሪዎቹ ሰዎች እና ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ማለት የፈለኩት የመሰረተ ልማት በሚል ርዕስ ክርክር ስመለከት የተገነዘብኩት ጉዳይ ቢኖር ኢህአዴግ ክርክር እያደረገ ያለው የዛሬ አስር ዓመት ለሚዲያ ክርክር ድመቅት ይሰጥ ከነበረው […]

ኤዶም ካሳዬ
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት እና የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት አባላት መርማሪ ደስታ በዋናነት

ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – በተያዝኩባቸው ቀናት በሙሉ በተለይ ሚያዝያ 18 ,20, 21, 22, 23
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ቢሮ ላይ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት

-መርማሪዬ ደስታ በተደጋጋሚ በጥፊ ይመታኝ ነበረ ሲሆነ ከዚህ ቤት የፈለግነውን ልናደርግሽ እንችላለን በአካል አትወጪም እያለ አስፈራርቶኛል

-የዞን 9 አባል አይደለሁም በማለቴ ፌቴን አዙሬ ከባድ የአካል አንቅስቃሴ የሰራሁ ሲሆን በተጨማሪም አላማቸውን ተናገሪ ሲለኝ የተለየ አላማ እንዳላቸው አላውቅም በማለቴ ሳታውቂ አንዴት አብረሻቸው ትውያለሽ ሸርሙጣ ብሎ በተደጋጋሚ ሰድቦኛል፡። ሌሎቹ መርማሪዎች አብረው ተቀምጠው በስድቦቹ ይስቁ ነበር

-ሌላኛው ተከሳሽ አጥናፍ መደብደቡን ፍርድ ቤት በመናገሩ አንቺ ትሞክሪውና ዋጋሽን ታገኛለሽ እኛ ፍርድ ቤት አያዘንም የግለሰብ መብትም አያሳስበንም ብሎኛል

-ጥጋቡ የሚባለው መርማሪ ምርመራ መሃል ደንገት በሩን ከፍቶ ገብቶ በጥፊ መቶኝ ይወጣ ነበር ( ስለምናወራው ጉዳይም ሆነ ስለምርመራው ሳይሰማ) እምቢ ካለችህ ልብሷን አስወለወቀህ ግረፋት ብሎ እኔን የተለመደውን ስድብ ሰድቦኝ ሄዷል

-በምርመራ ወቅት የዞን አባል ነኝ ብለሽ እመኚ ተብዬ ልብሴን አውልቄ ሙሉ እርቃኔን አንድመረመር ተገድጃለሁ ፡። በጥፊ እመታ የነበረ ሲሆን በዚህ ቀን ምርመራው ምሽት ላይ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰአት ቆይቷል

-በተለምዶው ከምመረመርበት ቢሮ ውጩ አንደኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ለምርመራ ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ እና የተለያዬ ለመናገር የሚከብዱ ስፓርታዊ አንቅስቃሴዎችን እንድሰራ ተገድጃለሁ፡፡ እንዲህ ከምትዋረጂ አመጽ ልናስነሳ ነበር ብለሽ ለምን አታምኚም እያለ ይመታኝ ነበር ፡፡ በጥፊው ተደጋጋሚነት የተነሳ ታምሜ ክሊኒክ ተመላልሻለሁ::

-በጋዜጠኝነት ሞያየ የተሳተፍኩበትን ስልጠናዎች ስናገር አንቺ ለምን ተመረጥሽ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ለምን አይሄዱም አንቺ ለፈረንጅ ስለምትሰልዬ ነው ብሎኛል፡፡ በተጨማሪም ዞን9 ላይ የሚወጡት ጽሁፎች አንድ ገጠር ያለ ሰው ቢያነበው ለአመጽ የሚያነሳሳው ልማቱን የሚያጣጥል ነው ብሎ በተደጋጋሚ በጥፊና በካልቾ ተመትቻለሁ፡፡

-በተጨማሪም በተፈቺ እስረኛ ወደውጪ መልእክት ልከሻል በሚል ሰበብ ሌሊት ተጠርጬ በዱላ ሲዛትብኝ አርፍዷል

-በእስሩ ወቅት ከማህሌት ፋንታሁን ጋር ለብቻችን ከሰው አንዳንገናኝ ተደርገን ቆይተናል፡፡

*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው

ላለፉት አራት ዓመታት ለንባብ ሲበቃ የቆየው የ“ቆንጆ” መፅሄት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሳ አገር ጥሎ ተሰደደ፡፡ ጋዜጠኛው በተለያዩ ጊዜያት የመንግስት ደህንነቶች ቢሮው ድረስ በመሄድ ዛቻና ማስፈራራት ስላደረሱበትና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ በመሆኑ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ መገደዱን እንደነገራቸው ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ የደህንነት ኃይሎች በየጊዜው ወደ ቢሮው እየሄዱ “ክስና እስር ይጠብቅሃል” እያሉ ያስፈራሩት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ፕሬሱን የሚወነጅል […]

ዘላለም ክብረት
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት እና የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት አባላት መርማሪ ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( ስሙ በትክክል የማላውቀው) በተለይ መርማሪ ምን ላድርግልህ መርማሪ ጽጌ መርማሪ አብዱልመጂድ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – በተያዝኩባቸው ቀናት በሙሉ በተለይ ሚያዝያ 17፣ ሚያዝያ 22 ሚያዝያ 25 እና ግንቦት 9
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ቢሮ ላይ
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– በታሰርኩነት ወቅት ህጋዊ የእስር እና የብርበራ ትእዛዝ አልነበረም፡፡ ህጋዊ ያልሆነ ፍተሻ ከ12 ሰአት በኋላ አታድርጉ ብልም የሚሰማኝ አላገኘሁም ፡። ፍተሻው በከፍተኛ ማስፈራሪያ የታጀበ ነበር፡፡ ፓሊስ ጣብያ እሄዳለሁ ብለህ እንዳታስብ ራስህን ለምትሄድበት ቦታ አዘጋጅ እያሉ ከፍተኛ ስነልቦና ጫና አድርሰውብኛል
– በመጀመሪያው ቀን ፍርድ ቤት ስንቀርብ ትምህርቴን አጠናቅቄ ላስረክበው ያዘጋጀሁትን የመመረቂያ ጽሁፍ ፓሊስ መያዙን እና ኮፒ አድርጌ እንዳስረክብ ይፈቀድልኝ ብዬ ስጠይቅ ፍርድ ቤቱም መብቱ ነው ብሎ ትእዛዝ ቢሰጥም ፓሊስ ትእዛዙን ተግባራዊ አንዲያደርግ ብጠይቅ የማዕላዊ ወንጀል ምርመራ ሃላፊ ኢንስፔክተር “ፍርድ ቤት እኛን አያዘንም“ ” የት ያለህ መሰለህ” ዳኛዋ ታስረክብልህ” አንዲሁም “አንዲህ አይነት ጥያቄ ካነሳህ እርምጃ ይወሰድብሃል” የሚሉ ንግግሮችን ተናገረውኝ አንጓጠውኛል በዚህም ምክንያት መመረቂያ ጽሁፌን ማስረከቤ ተሰናክሏል፡፡
– በምርመራ ወቅት በዙ አጻያፌ ስድቦችን እየተሰደብኩ የምመረመር ሲሆን ከነሱም መካከል “የነጭ ተላላኪ የነጭ አምላኪ አገር ሻጭ ከሃዲ “ የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
– የዞን 9 አላማ ተናገር ካልሆነ ያሉንን የምርመራ መንገዶች ተጠቅመን እንድታወጣ እናደርጋለን የሚለው ማስፈራሪያ በተደጋጋሚ በምርመራ ወቅት የደረሰብኝ ነው
– የሰጠሁት ቃል ላይ እኔ ያላልኩትን ጨምረው በፍርሃት ጥፋተኛ ነኝ ብዬ አንድፈርም ከመገደዴም በላይ የበላይ አካል ተቀባይ አንዲሆን በሚል እየቀያየሩ በተደጋጋሚ አስፈርመውኛል፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው

በሶማሊያ የሽብር ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቀው አልሸባብ ደመኛና አረመኔውን አይሲስን ሊቀላለቀል መሆኑ ተሰማ፡፡አገራችንን በተጨማሪ የሽብር ስጋት ውስጥ እነደሚጥላት ተገምቷል፡፡ የሶማሊያን ስፊ ግዛት የሚቆጣጠረው አልሸባብ የማእከላዊ ስልጣኑን ካጣ ወዲህ በደረሰበት ወታደራዊ ኪሳራ የአለም አቀፍ አሸባሪው አልቃይዳ ክንፍ በመሆን እያካሄደ ባለው የደፈጣ ውጊያ ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ርቋት በንጹሃን ደም የታጠበች መንግስት አልባ ጦር ሜዳ ከሆነች ከሁለት ዓስርት አመታት […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው # ስንታየሁ_ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታቀቀ ቦታ ተወስዶዋል። ‪ስንታየሁ_ቸኮል‬ ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል […]

ተስፋለም ወልደየስ

ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) መርማሪ የህይስ መርማሪ ጽጌ መርማሪ ታደሰ ( ስሙን እርግጠኛ ያልሆንኩት) 

ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት ማእከላዊ ምርመራ በቆየሁበት ጊዜ ሁሉ 
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ

ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
-በውል በማላስታውሳቸው ቀናት እስከእኩለ ሌሊት ድረስ የቆየ ምርመራ ተደርጎብኛል
-ለ75 ቀናት በተለምዶው ሳይቤሪያ የሚባለው ቦታ በቀን 15 ደቂቃ ብቻ የጸሃይ ብርሃን ለማየት ተፈቅዶልኝ ከዚያ ውጪ ያለውን ጊዜ 24 ሰአት አንድ በር ተዘግቶብኝ ቆይቻለሁ፡፡
-አራት በአራት በሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ ቁጥራቸው አስር ከሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ጤናዬን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ
-በእስር በቆየሁባቸው ቀናት በቀዝቃዛው ሳይቤርያ ውስጥ በማሳለፌ በከፍተኛ ቅዝቃዜው የተነሳ ለጤና ጉዳት እና ለበሽታ ተዳርጌያለሁ
-ከፍተኛ እና ከአቅሜ በላይ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ያደረኩ ሲሆን በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ እመታ ነበር
-በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት ደረሰብኝ ሲሆን በስተመጨረሻም ያላልኩትን አለ ተብዬ ፣ የማላምንበት እና ያልፈጸምኩትን ጥፋተኛ ነኝ ብለህ ፈርም በመባሌ ለመፈረም ተገድጃለሁ

*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው 

ናትናኤል ፈለቀ 

ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ ሳጅን ምን ላድርግልህ ፣ ም/ሳጅን አብተው 

ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 22 ( ከምሽቱ 2 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 23 ከጠዋቱ 4 ሰአት፣ ግንቦት 6( ከምሽቱ 3 ሰአት ገደማ)፣ ሚያዝያ 24 ከጠዋቱ 4 ሰአት እና ከሚያዝያ 22 እስከ ግንቦት 6/2006 ድረስ ባሉት ቀናት ከእሁድ በስተቀር 

የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 30፣ 32 በ1981 አም በተሰራው ህንጻ ላይ 2ተኛ ፎቅ በስተግራ ጥግ በኩል ያለ ቢሮ

ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– በምርመራ ወቅት ዛቻ እና ማስፈራሪያ የደረሰብኝ ሲሆን በተጠራሁባቸው ቢሮ ውስጥ ሁሉ በጥፌ ተደብድቤያለሁ ፡፡ በጥፌ መመታት የተለመደ ነበር ፡። በተደጋጋሚ ክፍተኛ ስፓርት የሰራሁ ሲሆን በቀን 10 ደቂቃ ብቻ የፀሃይ ብርሃን እያየሁ በጠባብ ክፍል ውስጥ ያለምንም ተፈጥሮ ብርሃንና መጸዳጃ ለ 76 ቀናት ቆይቻለሁ፡፡

– ጫማዬን አውልቄ በባዶ እግሬ አንድቆም ከተደረኩ በኋላ እግሮቼ ጣቶች ላይ መርማሪዎቹ በጫማቸው በሃይል በመርገጥ እግሬ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰውብኛል፡፡ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስም እጄ እንደታሰረ አናቴ ላይ አድርጌ እንድመረመር ተገድጄ ነበር፡፡

– የምሽት ምርመራዎች ወቅት በአብዛኛው ጊዜ እጄን ወደላይ አድርጌ እንድመረመር እገደድ ነበር ፡። ምርመራው ቀኑን ሙሉ የሚቆይ ሲሆን ምሽት እስከ ሌሊቱ ስድስተ ሰአት ድረስ ስፓርት በመስራት እና ፌቴን በማዞር እንድመረመር እገደድ ነበር፡፡

– ሰብአዊነቴን የሚነኩ ስድቦች ልክስክስ ፣ ውሻ መሳሰሉትን ስድብ በምርመራ ወቅት እሰደብ የነበረ ሲሆን አካለ ጎዶሎ ሆነህ ነው ከዚህ ቤት የምትወጣው ፣ ለግለሰብ መብት አንጨነቅም አንተን አንደፈለግን እነድናደርግ አሰራራችን ይፈቅድልናል የሚሉ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያዎች ነበሩብኝ ፡፡

*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው

አቤል ዋበላ 
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ
– ምን ላድረግልህ 
– ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( የሽፋን ስም )
– ደስታ ወይም ሃሰን ( የሽፋን ስም)
– ዬሃንስ
– ፈይሳ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 18(ከሰአት ከ8-10) ፣ ግንቦት 11 ( ከምሽቱ 2 ሰአት- ሌሊቱ 6 ሰአት) እና ሰኔ 26 ( ከምሽቱ 4 ሰአት -ሌሊቱ 7 ሰአት) እና በማእከላዊ ምርመራ በልዬ ሁኔታ በቆየሁባቸው 76 ቀናት
የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 5.፣ 32፣30 ፣ የስብሰባው አዳራሽ እና ከዋናው ህንጻ ተነቅሎ በሚገኝ ህንጻ ውስጥ በሚገኝ ጨለማ ክፍል
ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– የተያዝኩበት ማግስት አቶ ምን ላድርግልህ የተባለ የምርመራ ክፍሉ አባል ብሄሬን ጠይቆኝ ኢትዬጲያዊ መሆኔን እና በተለያዬ ብሄሮች ስር ራሴን አንደማልገልጽ እና በጥቅል ኢትዬጲያዊ መባል አንደምመርጥ ነገርኩት ተነስቶ ድብደባ ጀመረ ፡፡ በጥፌና በእርግጫ በተደጋጋሚ መታኝ፡፡ ሌላው መርማሪ ንግግራችንን ያልሰማ ከውጪ መጥቶ ያለምንም ጥያቄ ድብዳባውን ተቀላቀለ ፡፡ ከዱላው በተጨማሪ በጣም አጸያፌ ስድቦችን ሰደቡኝ፡፡ ብሄርህን የካድክ በብሄርህ የምታፍር ይሉኝም ነበር፡፡
– ከሚያዝያ 19-ሰኔ 26 2006 ባሉት ቀናት ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ አያድንህም በማለት አጸያፌ ቃላት በመሰንዘር ሰውነቴ ሊቋቋመው የማይችለው የአካል እንቅስቃሴ እንዳደርግ ተገድጃለሁ ፡፡
– በተለይ ግንቦት 11 ላይ የዞን9 አላማ ጠይቀውኝ ስናገር እውነቱን አውጣ በሚል በተደጋጋሚ ድብደባ የደረሰብኝ ሲሆን ደስታ እና ሃሰን የተባሉ ሽፋን ስሞች የሚጠቀመው መርማሪ በተደጋጋሚ ባደረሰብኝ ጥፌ ድብዳባ ጆሮዬ ተጎድቶ በህመም ላይ እገኛለሁ፡፡
– ቤቴ የተገኘው ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ያሉትን ቃላት ነጣጥለው የሰጠሁት ቃል ውስጥ ያስገቡትን፣ ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ያለው ሙሉው ነው አንጂ ተነጣጥሎ ቃሌ ውስጥ ተካቶ አልፈርምም በማለቴ አቶ ፈይሳ፣ አቶ ዬሃንስ ( ስማቸው የሽፋን አንደሆነ የምጠረጥረው) ታደሰ( ጥጋቡ በሚልም ይጠራል) ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውብኛል፡፡
– ድብደባውም ጨለማ ክፍል ውስጥ በማስገባት አፌ ውስጥ ካልሲ በመወተፍ እግሮቼን ከላይ፣ ውስጥ እግሬን እና ከውስጥ ባቴን ታፋዬን እንዲሁም ጀርባዬን በእንጨትና በኮምፒውተር ገመድ ገርፈውኛል ፡፡
– የምርመራ ክፍሉ ወለል ላይ በደረቴ አንዲሁም በጀርባዬ እያገላበጡ በማስተኛት መላ ሰውነቴን ረግጠው ተራምደውብኛል፡። አፌን ሳይቀር ረግጠውታል፡። ይህንን በሚያደርጉበት ሰአት ሞራል የሚነካ ስድብ ይሳደቡ ነበር፡፡ ሁሉም የአካል ሆነ የስነልቦና ጥቃት ሲደርስብኝ እጄ በካቴና ታስሮ ሲሆን በቀን 15 ደቂቃ በላይ የጸሃይ ብርሃን የማላይበት ቀዝቃዛ ክፍል ውስጥ ለ76 ቀናት ቆይቻለሁ፡፡
*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው

የታረዱትንና በጥይት የተደበደቡት ኢትዮጵያዊያን ሰማእታት ናቸው ‘ነፍስ ይማር’ ወይንም RIP ሊባልለት የሚገባው በቁሙ ለሞተው አይሲስ ነው።” ዲያቆን መምህር አድማሱ ዘባን
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 25, 2015)፦ ራሱን የእስላም መንግስት በማለት የሚጠራው እና ዘግናኝ ግድያዎችን በንጹሃን ዜጎች ላይ በመፈጸም ላይ በሚገኘው ቡድን እጅ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያኖችና በሳውዝ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖች ላይ የሚፍጸመውን ሰብአዊነት የጎደለው አስከፊ ድርጊት በመቃዎም በቫንኩቨር (ካናዳ) ታላቅ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሄደ።vancouver-vigil-01.JPG

ሙሉውን አስነብበኝ …

ISIL የሚባለው ሰይጣናዊ ቡድን በምድረ ሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ያስቆጣኝ በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ምክንያቴ በጥይት የተረሸነውና በስለት የታረደው ኢትዮጵያዊ ወንድሜ መሆኑ ነው፡፡ አዎን!! “ዘወትር በድህነት ከምንገላታ ወደ ውጪ ሄጄ ዕድሌን ብሞክር ይሻላል” በሚል የሃሳብ ምጥ ተነሳስቶ በምድረ …

“አይሲስ” ስለሚባለው ሰይጣናዊ ቡድን አስተያየት ከአፈንዲ ሙተቂ Read more »

በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት ተቃወሙ
Ethiopians protested in Meelbourne. በሜልበርን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ኢሰብዓዊ ጥቃት በመቃወም ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. (April 24, 2015) የሜልበርን ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ እና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን በሕብረት ባስተባበሩት የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የነበረው ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ቁጣውን በመረረና እልህና ቁጭት በተንጸባረቀበት መልክ ሲገልጽ አርፍዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የዲ.ሲ. የደብረኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ውስጥ በተደረገ ጸሎተ ፍትሐት ላይ የተላለፈ የሀዘን መልዕክት። ሙሉውን መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የሀዘን መልዕክት

* ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በህክምና ስህተት ለ9 ዓመታት ለከፋ አደጋ መዳረጉ ተረጋግጧል ! * የሳውዲ ጤና ጥበቃ ልዩ አጣሪ ኮሚቴ የሰጠው ውሳኔ ግን አሳዝኖናል * የብላቴናው ቀሪ ህይዎቱም ውስብስብ ሆኗል * አሰልችውን የዘጠኝ አመታት ፍትህ ፍለጋ ግን አልሰመረም * ” ከሬሳ የማይተናነስ በድን አድርገው አኮላሽተው ውስጅ ይሉኛል ፣ እንዴት ይህን ውሳኔ ልቀበል ? ፍትህ እሻለሁ! እርዱኝ! […]

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ የሚቃወሙ ሰልፎች፣ የሻማ ማብራት ስነስርአቶችና ጸሎቶች በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያና በአውስትራሊያ ተካሂዷል። በለንደን ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓም በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሱትን በደሎች አጥብቀው ኮንነዋል። ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስፍራው ተገኝቶ እንዳለው …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት የልማት ድርጅት ፣ ኢፈርት ንብረት የሆነው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ላለፉት ሶስት አመተት  ያለተቀናቃኝ በከፍተኛ ዋጋ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ሲያቀርብ ከቆየ በሁዋላ ፣ ስራውን አቋርጧል። የአባይ ግድብ ግንባታ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይፋ ከተደረገ በኃላ በባለስልጣናት መካከል ውዝግብ መነሳቱ ታውቋል። ጉባ የሚገኘው  የስሚንቶ ማምረቻ …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፒተር ስዋይዘር የተባሉ ጸሃፊ በቅርቡ በሚያሳትሙት መጽሃፍ ላይ ሼክ አላሙዲን ለክሊንተን ፋውንዴሽን 20 ሚሊዮን ዶላር እኤአ በ2006 መስጠታቸውን አጋልጠዋል። የሼክ አላሙዲን ድርጅት ለክሊንተን ፋውንዴሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ እርዳታው የተሰጠው በኢትዮጵያ መንግስት ስም ሲሆን፣ የቡሽ አስተዳደር የውጭ ፖሊስ በክሊንተን አስተዳደር ጊዜም  እንዲቀጥል ያስስባል። በባለቤታቸው ስም ገንዘብ የተቀበሉት ሂላሪ …

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጎንደር ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ቀናው ክንዴ የተባሉ የከተማው ነዋሪ  ሚያዚያ 6/2007 ዓም ከጧቱ ሁለት ሰአት ላይ የብአዴን ኢህአዴግን የምርጫ ምልክት ቀደዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ግለሰቡ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው ብቻ የሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው ቢናገሩም የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በማግስቱ ሚያዚያ 7/2007 ዓም …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ወደ ሊብያ የተሰደዱት ኢትዮጵያውያንና ሌሎች እስላማዊ መንግስት ነኝ በሚለው ጽንፈኛ ቡድን አስቃቂ በሆነ መንገድ መገድላቸውን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀዘን ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪቃውያን ስደተኞች ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በየመንና በሊብያ እንዲሁም በሌሎች አገሮች ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት ለአስከፊ ሁኔታ እየተዳረጉ ነው።

ለስደቱ ምክንያት የሆነውንና መፍትሄ ሊሆን ይችላል የሚሉትን እንዲያብራሩልን ዶክተር መሐሪ ታደለንና ፕሮፌሰር መረረ ጉዲናን ጋብዘናል።  ዶክተር መሐሪ በአፍሪቃ ህብረት የፍልሰት መርሀ-ግብር ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃ ሰላምና ጸጥታ ተቋምን ይመራሉ። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ የአመራር አባል…

ሰማያዊ ፓርቲ በየመን፣ ደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እየተከታተለ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል በማውገዝና መንግስትም መፍትሄ እንዲሰጥ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያስቆም አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ ፓርቲያችን የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ […]

ባለፈው ታህሳስ 2007 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ሀይማኖታዊ በዓላትን የሚያከብሩበት (በተለይ ጥምቅትና መስቀል በዓላትን) ስፍራ መስቀል አደባባይ በከፊል እና የተለያዩ የህዝብ ተቋማት ‹‹ለመንገድ ልማት›› በሚል ሊፈርሱ ይችላሉ መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ህዝብ ለተቃውሞ ወጥቶ ዜጎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ እነዚህ ህዝብ የሞተላቸው ተቋማትና የሐይማኖት ቦታ ከሰሞኑ መፍረሳቸው እርግጥ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ […]

“መንግስት በሊቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ሰፋፊ ሰራዎችን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ቴድሮስ በቤንጋዚ ያሉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ መንግሰት በኩል፣ ትሪፖሊ ያሉትን ደግሞ ከሱዳን መንግሰት ጋር በመተባበር ከሊቢያ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።” የሚል በዶር ቴድሮስ አዳኖም ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አነበብኩ። የዝግጅቱን ዝርዝር ባላውቅም ዝግጅቶች እየተደረጉ ሊሆኑ እንደሚሉ […]

የ24 አመታት ሂደቶች .. ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው እንዳይኖሩ የሆነበት…ለአንድ ወገን ያደላ እና በፓርቲ አባልነት ላይ የተመሰረተ አድልኦ የተንሰራፋበት … ጥቂት የፖለቲካ ቱጃሮች ብዙሃን ደሆች የፈሉባት … አምባገነንነት የነገሰባት ….ሃገራችን ኢትዮጵያ ልጆቿን አቅፋ እንዳታኖር የተደረገበት እና ወደ ስደት የተበተኑበት … ይህንን ሁሉ ተሸክመን ከትከሻችን ለማውረድ የምንታገልበት ወቅት … ከትግሉ ፍሬዎች አንዱ ሰማያዊ ፓርቲ ነው::ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊነቱን […]

በስደት በሊቢያ ሳሉ ሚያዝያ ፲፩ ቀን ፪ሺ፯ ዓ.ም በሰማዕትነት ስላረፉት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሕጋዊው ቅዱስ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ። መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።ከሕጋዊው ቅዱስ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ …

ከሕጋዊው ቅዱስ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የተሰጠ መግለጫ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት […]

The post አደጋ ላይ ነን!! appeared first on ሳተናው .

በጣም አስደንጋጭ ዜና ነው። ነገሩ እውነት ከሆነ በጣም ያስፈራል። ከሰሞኑ ሲያስጨንቀኝና አእምሮየን ረፍት ሲነሳው የነበረ ስጋት። የ ISIS ወደ የመን መግባት። በጦርነት የፈራረሱ አገራትን እንደ ምሽግ ተጠቅሞ ሰይጣናዊ የሽብር እንቅስቃሴውን እየፈጸመ የሚገኘው የ ISIS ቡድን ዛሬ የመን ሰንአ መግባቱን አወጇል። አውሬዎቹ ISIS ሶች ዛሬ በለቀቁት የ 9 ደቂቃ ቪዲዮ የሁቲ አማጽያንን አንገት ልንቆርጥ የመን ገብተናል […]

The post በጣም አስደንጋጭ ዜና .. ይህንን አስቸኳይ መልዕክት ሼር በማድረግ በየመን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንዲደርስ እናድርግ!! appeared first on ሳተናው .

ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት […]

ይህ ሳምንት ለመላው ኢትዪጲያውያን የሃዘን ወክት ነው በወንድሞቻችንላይ በደረሰው የጭካኔ ድርጊትና  አዘናቸውንና ቁጣቸውን ለመግለፅ በወጡ ወገኖቻችንላይ የወያኔ መንግስት ባደረሰው ድብደባና በርካታ ሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ለህስር በመዳረጋቸው አፍረናል ይህ የግፍ የወያኔ ቡድን ከአይ ኤስ አይ ኤስ ባልተናነሰ እያደማን እያረደንና እየገደለን ይገኛል  እስከመቼ  ስለዚህ ይበቃል ልንለው ይገባል በግፍ ለታረዱት ወገኖቻችን አዘናችንን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን አይ ኤስ አይ ኤስ በሊቢያ ተጨማሪ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዳዊት ሰለሞን ኢትዮጵያዊያኑ በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የገቡት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያሻግሯቸው ተስፋ በሰጧቸው ደላሎች አማካኝነት እንዲያርፉባት በተደረገች ክፍል ውስጥ ተደራርበው እንደተኙ ነው፡፡ አየሩ በታፈነ ክፍል ውስጥ ታጭቀው የተያዙት ወጣቶች የሚበዙት ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስተው ሞያሌን አቋርጠው ናይሮቢ የደረሱ ነበሩ፡፡ቤተሰቦቻቸው የነበረቻቸውን መሬትና ከብቶቻቸውን ሸጠው፤የገሚሶቹ ተበድረው ጥቂት የማይሰኙት ደግሞ በአዲስ አበባ ጭምር ለዓመታት በጫማ ጠራጊነት ተሰማርተው ያጠራቀሟትን […]

እማማ ኢትዮጵያ የሐዘን ማቅ ለብሳ በዋይታና በልቅሶ ተጨንቃ ልጆቿን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማች ትገኛለች!! አንገታችንን የሚያስደፋና በሐፍረት የሚያሸማቅቅ፣ ጆሮን ጭው የሚደርግ፣ የወላድ እናቶችን አንጀት የሚያላውስና በእንባ ጎርፍ እንዲታጠቡ የሚያደርግ ሌላ የሞት፣ ሌላ የውርደት፣ ማብቂያ የሌለው የሚመስል መሪር የሆነ የመርዶ፣ ሰቅጣጭና ክፉ ዜና ለእናት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ምድር፣ ከሊቢያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሀገረ የመን ተሰምቷል፡፡ ስለሆነም በቦስተን እና አካባቢዋ […]

የዋሽንግተን ዲሲ ደብረሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሊቢያ ውስጥ በሰማዕትነት ያለፉትን 28 ኢትዮጵያዊያን አስመልክታ ያወጣችው መግለጫ። ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ፳፰ ሰማዕታት የመሪር ኃዘን መግለጫ

በ  

     የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ከዘመናዊ ህክምና ይልቅ ባህላዊ ሕክምናን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ አዕምሮ ጤና ማኅበር…

አረመኔው ወገኖቻችንን አረደ!! አፈንዲ ሙተቂ “ኢትዮጵያም እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች” የሚለውን ታዋቂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ በብዙ ስፍራዎች ተለጥፎ አየዋለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የመንፈሳዊ መጽሔቶች የሽፋን ዘገባ ርዕስ ሆኖ ያጋጥመኛል፡፡ አንድ ሁለት ጊዜም የመጻሕፍት ርዕስ ሆኖ ያየሁት ይመስለኛል፡፡ እኔ ሙስሊም ነኝ፤ ነገር …

አረመኔው ወገኖቻችንን አረደ Read more »

Ermias Legesseሰሞኑን በኢትዬጲያውያን ላይ የመከራ ዶፍ እየዘነበ ነው። ይህ የድቅድቅ ጨለማ ናዳ ባስከተለው አደጋ የተፈጠረው ቁጭትና መብከንከን ከቃላት በላይ ሆኗል። በኢትዬጲያውያን ዘንድ ከዚህ ውጭ የመተከዣ አጀንዳ ያለ አይመስልም። እንባ እንደ ጐርፍ እየወረደ ነው። የእናቶቻችን ደረት በእሳት የተለበለበ እስኪመስል ድረስ እየተደለቀ ነው። ወጣቶቻችን ከአረመኔዎች ጋር ግብግብ እየገጠሙ ነው። በመንገድ፣ በትራንስፓርት፣ በምግብ ቤት፣ በስራና በተለያየ አጋጣሚ የምናገኛቸው የባእድ አገር ሰዎች ሳይቀር የሀዘናችን ተካፋዬች መሆናቸውን እየነገሩን ነው። ነግረውን ብቻ አያቆሙም ። አያይዘው ፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም     ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በአሁኑ ጊዜ ቱርክ እየተባለች በምትጠራው ሀገር ከ100 ዓመታት በፊት በዛሬው ሳምንት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 24/1915 በአርሜኒያ ዜጎች ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ፍጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ያ የዘር ፍጅት የኦቶማን ግዛት/Ottoman Empire ዋና …

በአርመኞች ላይ የተደረገው የዘር ማጥፋት ዕልቂትን እናስታውስ፣ Read more »

መሰረታዊ ምንጭና መፍትሔው ፓለቲካዊ ነው’!! ሰሞኑን በኢትዬጲያውያን ላይ የመከራ ዶፍ እየዘነበ ነው። ይህ የድቅድቅ ጨለማ ናዳ ባስከተለው አደጋ የተፈጠረው ቁጭትና መብከንከን ከቃላት በላይ ሆኗል። በኢትዬጲያውያን ዘንድ ከዚህ ውጭ የመተከዣ አጀንዳ ያለ አይመስልም። እንባ እንደ ጐርፍ እየወረደ ነው። የእናቶቻችን ደረት በእሳት የተለበለበ እስኪመስል ድረስ እየተደለቀ ነው። ወጣቶቻችን ከአረመኔዎች ጋር ግብግብ እየገጠሙ ነው። በመንገድ፣ በትራንስፓርት፣ በምግብ ቤት፣ […]