‹‹ሰይፍህን አንሣ፣ ክተት ሠራዊት፣ ዝመት ለፍቅር፣ ሰልጥን ለምሕረት፡፡›› (አርቲስት ዘሪቱ ከበደ) ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በቆንጨራ ለተጨፈጨፉ፣ በሚያሰቅቅና በሚዘገንን ኹናቴ እሳት በቁማቸው ለተለቀቀባቸው፣ ሀብት ንብረታቸው ለተዘረፈባቸውና ለጋየባቸው፣ የጦርነትና የእልቂት አውድማ በሆነችው በአገረ የመን ለሞቱና በጭንቅ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችንና በተለይም ደግሞ በሊቢያ በአይ ኤስ የአክራሪና ጽንፈኛ ቡድን የተሠዉትን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን አስመልክቶ በጥቂቱም ቢሆን የጥበብ ባለ ሙያዎቻችን በሥራዎቻቸው […]

“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣ እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።“ አገኘሁ እንግዳ ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል። በዚህ ግፍ እንባ ያነባንም አለን። ከልባችንም ያዘንን ብዙ ነን። ቄሱ ትምህርት ሲሰጡ እነዚህ ለሃይማኖታቸው ሲሉ በወጣትነት የሞትን ጽዋ የተቀበሉ ሰማዕታት […]

ክንፉ አሰፋ

Obama Stop ISIS

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሔራዊ የኀዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም ባህርዳር ታስሯል) ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ገለፁ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመልክተው- የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና […]

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ በተባለ አካባቢ የኢህአዴግ ቡዱን የፖሊስ አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በሚፈጥሩት ግጭት እየተገደሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ፣በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ልዩ ቦታው መርሳ በተባለ አካባቢ ሚያዚያ 12 /2007 ዓ.ም አቶ መሓመድ ዓሊ የተባለ ግለሰብ ምክትል ሳጅን ከበደ አበጀ ለተባለ የፖሊስ አባል በስራው ላይ እንቅፋት ስለፈጠረበት ይዞት በነበረው ዱላ ደብድቦ እንደገደለው ከምንጮቻችን ያገኘውነው […]

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ፣ የማረሚያ ቤቱ ሹሞች ፖሊሶችን ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚፈልጓቸው ከገለጹላቸው በሁዋላ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙትን ፖሊሶች የሞባይል ስልኮች ተቀብለው ፍተሻ አድርገዋል። በፍተሻው ወቅት 18 ፖሊሶች ከኢንተርኔት የተለያዩ ፎቶዎች፣ ጽሁፎችንና ቀስቃሽ ዘፈኖችን በማውረድ በስልኮቻቸው ላይ አስቀምጠው የተገኘ ሲሆን፣ ፖሊሶቹም ወዲያዉኑ እንዲባረሩ ተደርጓል። በተለይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በጀኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፊት ለፊት  ባደረጉት ሰልፍ በሊቢያና የመን በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ጥያቄያቸውን በተወካዮች አማካኝነት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣኖች ያቀረቡ ሲሆን፣ የፖለቲካ ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአፋጣኝ ወደ ሶስተኛ አገር እንዲሸጋገሩ፣ ሌሎችም እንዲሁ አሁን ካሉበት አገር ወጥተው በሶስተኛ አገር …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚያዚያ 30 ፣ 2007 ዓም ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ አቶ አቡበክር አህመድ በተከሰሱት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት በተሰጠትእዛዝ፣ ውሳኔው ከምርጫው በፊት አይሰጥም። ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የተባሉት የደህንነት ባለስልጣን ይህንኑ አቋም በቅርቡ ተደርጎ በነበረው የኢህአዴግ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  አለም ባንክ አካባቢ የሚገኙ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ3 ሺ በላይ አባወራዎች ያለፉትን 11 ወራት በስቃይ ቢያሳልፉም ፣ እስካሁን መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። የመንግስት ባለስልጣናት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለምርጫ ቅስቀሳ መምጣታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ያሉበት ህይወት ከሞቱት በታች መሆኑን በምሬት ገልጸዋል። ቤታቸው ከፈረሰባቸው …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና የከተማዋ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ አመራሮች የመሳሪያ ፈቃድ የሚያወጡትን ነዋሪዎች፣ ለመሳሪያ ፈቃድ 260 ብር ፣ ለግዳጅ ቦንድ ግዢ 1 ሺህ ብር እንዲሁም ለቀበሌ መታወቂያ 300 ብር በማስከፈል ላይ መሆናቸውን ህዝቡን ምሬት ላይ ጥሎታል። በሱዳኗ የጠረፍ ገበያ ማዕከል በሆነችው የገላባት …

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከምሁራንና ከዲሞክራሲ አቀንቃኞች ጋር በጋራ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ተጋባዥ እንግዶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወረቀቶችን ያቀርባሉ። ምሁራኑ ኢትዮጵያ የገጠሙዋትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በማንሳት ተጨባጭ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል። በውይይቱ ላይ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ምሁራን፣ የዲሞክራሲ አቀንቃኞችና የውጭ አገር ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዳንኤል ክብረት
ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓም
ባሕርዳር
ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም ምሥረታ ማብሠሪያ ቀን የቀረበ የማሳሰቢያ ሐሳብ
ዩአን ሊ የተሰኘ ጃፓናዊ Breaking the message, በተሰኘው የ2006 ዓም መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል፡፡ በኢንዶኔዥያ ገጠሮች ውስጥ በሠራባቸው 7 ዓመታት የታዘበው ትልቁ የሕዝብ ግንኙነት ችግር ለሕዝቡ መልእክት ለማስተላለፍ የሚመጡት ባለሞያዎች መልእክታቸው ተሟልቶ ወደ ሕዝቡ ለመድረስ አለመቻሉ ነው፡፡ ለዚህ ችግር መፈጠር ምክንያት ናቸው ያላቸው ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው መልእክቱ ለሕዝቡ በሚመጥን መልኩ ተዘጋጅቶ አለመቅረቡ ነው፡፡ የሚተላለፈው መልእክት የአስተላላፊውን ማንነት፣ የዕውቀት ደረጃ፣ የፖለቲካ ጠገግ፣ የተማረውን የትምህርት ዓይነትና የአስተሳሰቡን መጠን የሚያሳይ እንጂ ለመልእክት ተቀባዩ ታስቦ በደረጃውና በመጠኑ የቀረበ አይደለም፡፡
‹‹ምንም እንኳን ሥጋ ሥጋ ቢሆንም ለሕጻንና ለዐዋቂ ግን በእኩል መጠንና ዓይነት አይቀርብም፡፡ ሕጻኑ ጥርሱና የምግብ ማዋሐጃ አካሉ ስላልጠነከረ በቀላሉ ሊፈጨው በሚችለው መጠን ሥጋው ደቅቆ መቅረብ አለበት፡፡ ለዐዋቂው ግን ሥጋው ጠንክሮና በቅመማ ቅመም ዳብሮ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሥጋ ግን ሥጋ ነው›› ይላል ዩአን ሊ፡፡ መልእክት ሲቀርብም ከአቅራቢው በላይ የሚቀርብለትን ወገን ዐቅምና ችሎታ፣ ደረጃና ፍላጎት የመጠነ መሆን አለበት፡፡ ምንም የመልእክቱ ይዘት ባይቀየርም፡፡ 

ሌላው ለመልእክቱ መሰበር ምክንያት ነው ብሎ የታዘበው ነገር ምሁራኑና ሌሎችም ሕዝቡ በማይገባው ቋንቋ መናገራቸው ነው፡፡ አቅራቢዎቹ ለምዶባቸው ወይም እነርሱ የተማሩት በእንግሊዝኛ በመሆኑ ያለበለዚያም (እንደ እኛ ሀገር የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው በእንግሊዝ አናግሪያቸው የሚለው ዘፈን እነርሱም ጋር አለ መሰል) እንግሊዝኛ መቀላቀል የዕውቀትና የደረጃ ማሳያ አድርገውት፣ እንግሊዝኛውን ከኢንዶኔዥያ ቋንቋ ጋር (በነገራችን ላይ ኢንዶኔዥያ 700 ሀገራዊ ቋንቋ የሚነገርባት ሀገር ናት፤ ብዙዉ ሰው ‹ባሐሳ ኢንዶኔዥያ› የተሰኘውን ብሔራዊ ቋንቋ ይናገረዋል፡፡) እየቀላቀሉ በሚያስፈልገውም በማያስፈልገውም ስለሚጠቀሙ መልእክቱ እየተሰበረ እንዲደርስ አድርገውታል፡፡
‹‹በቴሌቭዥን ኳስ ስንከታተል›› ይላል ዩአን ሊ ‹‹የኳሱን ፍሰት ሳይቋረጥ መከታተል እንፈልጋለን፡፡ የቴሌቭዥን ጣቢያው  ይኼንን ትቶ በየመካከሉ ሙዚቃ እየጋበዘ ኳሱን ቢያስተላልፍልን የኳስ ጨዋታው ሙሉ ሥዕል አይኖረንም፡፡ ምናልባትም በመካከል ጎል ገብቶ፣ ተጨዋች በቀይ ወጥቶ፣ ግጭት ተፈጥሮ፣ ተጨዋች ተቀይሮ፣ አስደናቂ ወይም አሳዛኝ ክስተት ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህን ነገሮች አሳልፈን የምናየው ጨዋታ ግርታን ይፈጥራል እንጂ ደስታን አያመነጭም፡፡ በየመካከሉ ሕዝቡ የማይረዳውን ቋንቋ እየደባለቁ መልእክት ለማስተላለፍ መጣርም እንደዚሁ ነው፡፡ ድምፁን ለማስተላለፍ እንጂ መልእክቱን ለማስተላለፍ አይረዳም›› ይላል፡፡
እንዲያውም በአንድ በሰሜናዊ ኢንዶኔዥያ ክፍል ጥናት ሲያደርግ አንድ አዛውንት የነገሩትን እንደ ምሳሌ አስቀምጦታል፡፡ በዚያ መንደር ውስጥ አንድ የሕክምና ባለሞያ መጥቶ ለመንደሯ ሰዎች ስለ ኢንፍሉዌንዛ ገለጻ ያደርጋል፡፡ በገለጻው መካከል የአካባቢውን ቋንቋ ሱንዳኒዝንና እንግሊዝኛን እየደባለቀ ይናገር ነበር፡፡ መንደርተኞቹ ተቸገሩ፡፡ አንድ ሰውም ተነሡና ‹ልጄ፣ ወይ በእንግሊዝኛ ንገረንና ከመካከላችን ዕውቀቱ ያላቸው ይተርጉሙልን፤ ያለበለዚያ ደግሞ በአካባቢያችንን ቋንቋ በሱንዳኒዝ ንገረንና ያለ ችግር እንስማው›› ብለው አስተያየት ሰጡት፡፡ ከባለሞያው ይልቅ መንደርተኞቹ እንደሚቆራረጥ ስልክ መልእክቱ እየተሰበረ እንደደረሳቸው ገብቷቸዋል፡፡
አሁን አሁን በሀገራችን እየገጠመን ያለውም ልክ ዩአን ሊ በኢንዶኔዥያ የገጠመውን ዓይነት ነው፡፡ አማርኛን የሚናገር ሰው የጠፋ እስኪመስል ድረስ በአማርኛ መልእክት መለዋወጥ ከባድ እየሆነ ነው፡፡ የመልእክት ልውውጦቻችን በስሕተቶች የ&#4720

  ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡ … የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በዚህ ሣምንት እያወጣቸው ባሉ ተከታታይ የፕሬስ መግለጫዎች በዓለም ዙሪያ […]

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ  አደጋ ተከትሎ ለተቃውሞ የወጡ ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበው እንዲታሰሩ በተደረገ ማግስት፣ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በምሽት በማፈን ወደ እስር ቤት እያጋዙ ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች …

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ ባሃድያ ዞን በሶሮ ወረዳ በጊምቢቾ ከተማ የፊዚክስ መምህር የነበረው ጌታቸው አብራሃም ፣  በወረዳው አስተዳደር  ግቢ ውስጥ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል። የመድረክ አባል የነበረው መምህር ጌታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። የተቃዋሚ አባል በመሆኑ ብቻ የ3 ወር ደሞዙን እንዳያገኝ የተከለከለው መምህር፣ አቤቱታውን …

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢችል ቀሬ እና ብርሃኑ ታየ የተባሉ ወጣቶች መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የደረሱበት አልታወቀም። ወጣቶቹ በምን ምክንያት ታፍነው እንደተወሰዱም ሆነ  ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ በህይወት ይኑሩ አይኑሩ  እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ለወጣቶቹ መሰደድ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች ይነሳሉ አልጄዚራ በድረ-ገጹ ባወጣው ፅሁፍ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ለኢትዮጵያውያኑ መሰደድ በዋነኛነት የሚነሱ ምክንያቶችን ዘርዝሯል ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በኢኮኖሚ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገሮች መካከልም ስሟ የሚጠራ ቢሆንም ዜጎቿ ግን መሰደድን አላቆሙም በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ በሚመርጡት ህገወጥ ስደት ብዙዎች እየሞቱ ይገኛሉ በከተሞች አካባቢ አጥጋቢ የስራ እድል አለመኖሩ, በአብዛኛው የሚሰሩ ስራዎች የዜጎችን […]

ከዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች
ጊዜው በጣም ይነጉዳል፡፡ ሀላፊነት የማይሰማው ስርዓት የገዛ ዜጎቹን ዕድሜ በእሳት ይማግዳል፡፡ ሚያዚያ 17/08/2006 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንድንውል የተደረግነው ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ሶስት ጋዜጠኞች ይሔው ከታሰርን ድፍን አንድ የእስር አመት ቆጠርን፡፡ መለስ ብለን ስናየው አጭር በሚመስለው ዓመት ውስጥ የሆነውንና የታዘብነውን ጠቅለል አድርገን ለማካፈል እንሞክራለን፡፡ይህ የእኛ ገጠመኝ እና ትዝብት፣ የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ የሚከብደው መንግስት እስካለን ድረስ የነበረ እና የሚኖር ስለሆነ የሁሉም ‹የኅሊና እስረኛ › ገጠመኝ እና ትዝብት ሊሆን እንደሚችል አስታውሱልን፡፡
‹እንዳይችሉት የለም . . .›
ከያለንበት ቦታ በዘመቻ መልክ ተይዘን የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (በተለምዶ ‹ማዕከላዊ›) በገባንበት ቅፅበት ነበር ሥርዓቱ እንዴት እንደሚሰራ ከውስጡ መመልከት የጀመርነው፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ስርዓቱ ውጪ ሆነን ከምናውቀው የባሰ እንጂ የተሻለ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ለምርመራው የተያዝነውን ‹‹ተጠርጣሪዎች ›› የሚያቆዩባቸው ክፍሎች መሰረታዊ የሆነውን ሰብዓዊነትን ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገቡ እና ሕግ የማያውቃቸው ይመስላሉ፡፡ ተዘግተው በሚውሉና በሚያድሩ ክፍሎች ውስጥ ተበታትነን ታጉረን በቀን ሁለቴ (ለአስር ደቂቃዎች) መፀዳጃ ቤት እንድንሄድ(ተፈጥሮን በቀጠሮ እንድንቆጣጠር ) እንገደድ ነበር፡፡ ‹የፀሃይ ብርሃንም› በቀን አንዴ ለአስር ደቂቃ እንቃመስ ነበር፡፡ይህምየሚሆነው የእኛን ‹መብት› ለማክበር ታስቦ ሳይሆን በአሳሪዎቻችን ‹በጎ ፈቃድ› ነው፡፡ ክፍሎቻችን ውስጥ ሆነን የሰማናቸውና ያየናቸው በታሳሪዎች (inmates) የሚወሩት እና በገዛ አይናችን የምንታዘባቸው የሰቆቃ ታሪኮች ብቻ ናቸው፤ ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ‹‹እመን››በሚል የማይቀጣ የለም፡፡ ማዕከላዊ ውስጥ እረፍት ብርቅ ነው፤ የካቴና ድምፅ በተቅጨለጨለ ቁጥር ‹‹ማነው ባለተራ›› የሚል ጭንቀት ሁሉንም ሰው ሰቅዞ ይይዛል፡፡ የትኛው ተረኛ ወደ ‹ምርመራ› ክፍል ተወስዶ ይደበደብ ይሆን? የሁሉም እስረኛ ጥያቄ ነው፡፡
ሁላችንም ለጥያቄ ‹ምርመራ› ክፍሎች ውስጥ በተመላለስንባቸው ጊዜያት ሰብአዊ ክብራችንን እንድንዘነጋ እንገደድ ነበር፡፡ ፀያፍ  ስድቦችን የመርማሪዎቻችን አፍ መፍቻ የሆኑ ይመስል ከንፈራቸው ላይ ተንጠልጥለዋል፡፡ጥፊ፣ ካልቾና ስፖርታዊ ቅጣቶች የእለት ቀለቦቻችን ነበሩ፡፡ ሴቶች ሊደረግልን የሚገባ ጥበቃ ቀርቶ ሴትነታችንን መቀጣጫ የሚያደርግ አበሻቃጭ (abusive) ‹ምርመራ› ተደርጎብናል፡፡ ‹የምርመራ› ስዓቱ ገደብ የለውም ጠዋት፣ ከሰዓት፣ ማታ እና ሌሊት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ከእንቅልፍ ተቀስቅሶ ወደ ‹ምርመራ› ክፍል መወሰድ እና የደንቡን ተደብድቦ መምጣት የተለመደ ነው፡፡ ለነገሩ ማዕከላዊ የቆየ ሰው የሚታሰርባቸው ክፍሎች የተፈጥሮ ብርሃን የማያስገቡ እና ለ24 ሰዓታት በቂ የሆነ የኤሌክትሪክ ብርሃን የማያገኙ በመሆናቸው መምሸት እና መንጋቱን እንኳን ለማወቅ በፖሊስ መነገርን ይጠይቃል፡፡ የመጀመሪያዎቹን ሶስት የእስር ወራት በዚህ ሁኔታ አሳለፍን፡፡
‹የመርማሪዎችን› አካሄድ በመመልከት በጋራ የተረዳነው አንድ ነገር ቢኖር የተጠረጠርንበት ተጨባጭ ወንጀል ወይም ማስረጃ ያልነበረ መሆኑን ነው፡፡ ሆኖም መጀመሪያ ‹በተጠረጠርንበት› ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በአመፅ እና በዛቻ ለማፍረስ እና ማኅበረሰብ ሚዲያን ለአመጽ ለመጠቀም የመሞከር ወንጀል ወይም ኃላ በተከሰስንበት የሽብርተኝነት ድርጊትን ለመፈፀም የማሴር፣ የማነሳሳት፣ የማቀድ፣ የመዘጋጀትና የመሞከርን ወንጀል ከእኛው አፍ (በሃሰትም ቢሆን) በጉልበት ለመስማት ‹የመርማሪዎቹ› ቁርጠኝነት ወደር ያልነበረው መሆኑን ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ ቤታችን፣ ቢሮአችን፣ ኮምፒውተሮቻችን ፣ስልኮቻችንና ቃላችን ሁሉ ተፈትሾ የተገኘው ማስረጃ እንኳንስ ክስ ሊያቋቁም ቀርቶ የተገላቢጦሽ የእኛን ንፅህና የሚመሰክሩ ሆኑ፡፡ ይሁን እንጂ ሕግ የማይገዛው አሳሪያችን ከ15 ዓመት እስከ ሞት ሊያስቀጣ የሚችል ክስ አቀረበልን፡፡ጉዳዬን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ደሞ በምርመራው ወቅት አንድም ቀን የሽብር ተግባር እና አላማቸውን በማስፈጸም የተከሰስንባቸው ድርጅቶች አንዳቸውም አለመጠቀሳቸው ነው ፡፡
ክሱን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ የቀጠሮ ማረፊያ ቤት (ወንዶች ወደ ቂሊንጦ ሴቶች ወደ ቃሊቲ) ተላክን፡፡ ማረፊያ ቤቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የሚንስትሮች ምክር ቤት ያወጡላቸው መተዳደሪያ አዋጅና ደንብ ያላቸው ሲሆን፤ ነግር ግን የሚገዛቸው ያልተፃፈ ሌላ ደንብ ነው፡፡ በተለይ ሴቶችን የሚያሳድረው የቃሊቲው የአዲስ አበባ የሴቶች የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ገና ለገና ‹በሽብርተኝነት ወንጀል የተጠረጠርን› በመሆናችን ብቻ አግላይ አያያዝ በማድረግ የቀደመ ልምዱን ተግብሮብናል፡፡ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች / ታራሚዎች በተለየ ሁኔታ የጠያቂዎቻችንን ስም ዝርዝር እንድንፅፍ በማስገደድ መብታችንን ሲገድብብን፣ የምንጠየቅበትን ሰዓትም በአዘቦት ቀን ከአስር ደቂቃ እና ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከ30 ደቂቃ እንዳይበልጥ አድርጓል፡፡ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ብናቀርብም የማረፊያ ቤቱ አስተዳደር ‹ችግር የለም› በማለት እውነታውን በግልጽ ሲክድ ፍርድ ቤቱም ተባብሮት አጽንቶታል ፡፡ ፍትህን የሕግ የበላይነት ከፖሊስ እጅ እንዳጣነው ሁሉ በአያያዝ ረገድ ከማረፊያ ቤቱም ደጃፍ ልናገኘው አልቻልንም፡፡
ፍ/ቤቱ ‹እንደተጠርጣሪ› ለማረፊያ ቤቶቹ ያስረከበን በአደራ አቆዩልኝ ብሎ ቢሆንም፣ ማረሚያ ቤቱና የመብት ረገጣው ዋነኛ ተዋናዮች የሚመለከቱንግን ግን በጦር ሜዳ እንደማረኩት ግዳያቸው ነው ፡፡ እኛም በዚህና መሰል ለደህንነታችን ምንም አይነት ዋስትና በማይሰጥ አያያዝይህንን የመአት ዓመት ችለን አንድ ዓመት አስቆጥረናል፡፡
ምን ያሟግተናል?
በግልፅ የአሳሪያችንን መልካም ፈቃድ በወገንተኝነትና በታማኝነት በሚያገለግሉ ግለሰቦች የሚመሩትን የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ‹የወንጀል ምርመራ ቡድን› እና በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ‹ገለልተኝነት› ተሸማቀን ስናበቃ የተጋፈጥነው አንበሳውን  የፍትህ ስርዓታችንን ነው፡፡
ወንጀልን ሊያቋቁም የሚችል ምንም አይነት ማስረጃ በሌለበት በወንጀል መጠርጠራችንና መከሰሳችን ከሁሉም ቀዳሚው በደል እንደሆነ ይሰማናል፡፡ ነገር ግን ስለፍትህ አውርተናል ጠይቀናል ተከራክረናልና የኖርንበትን ታላቅ አላማ እኛው ፈልገን የፍትህ በርን እያንኳኳን እንገኛለን፡፡ ‹‹ለምን ተጠረጠርን?›› ‹‹ለምንስ ተከሰስን?›› ብለን ፍትህን ከመሻት ራሳችንን ሳናቅብ የቀረበብን ክስ እንደ ክስ ሊቆም የማይችል እንደሆነ ሕጋዊና ሙያዊ መቃወሚያ አቅርበን ፍርድ ቤቱም ‹ተቀብዬዋለሁ ግን አልተቀበልኩትም› በማለት ልንረዳው ያልቻልነውን ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ከእስራችንም በፊት የምንታወቅበትን የአገሪትዋን ህግ በመጠቀም መብቶቻችንን የመጠየቅን ሂደት አጠናክረን የምንገፋበት ተቋማቱ ገለልተኛ ናቸው ብለን ስለምናምን ሳይሆን ከተቋማቱ ጀርባ ላለው ፍትሕ እና ህግ የበላይነት ያለንን ቁርጠኛነት ለማሳየትም ጭምር ነው፡፡
ከሳሻችን አለኝ የሚለውን ‹ማስረጃ› በከፊል ከእኛ ከተከሳሾች ደብቆ እንኳን የተባለውን ‹ማስረጃ› ለማድመጥ የአንድ አመት ጊዜ መጠበቅ ነበረብን፡፡ የዘገየ ፍትሕ እንደተነፈገ ይቆጠራል መባሉን ከሳሻችን እንደሚያውቅ ብናውቅም እኛ ግን የዘገየውን ‹ፍትሕ› እንኳን ለመጠየቅ የሚያስችልትዕግስት አላጣንም፡፡
አሁንም ፍትሕ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዓይነተኛ መለያ ቀለም ነው ብለን እናምናለን፡፡ ፍትሕ ይኖር ዘንድ ገለልተኛ ተቋማት መኖራቸው ደግሞ የግድ ነው፡፡ ተቋማት ለተቋቋሙበት ዓላማ ከመኖር ይልቅ ታማኝነታቸውን ለስርዓቱ ሹማምንት ማድረግ ሲጀምሩ ፍትሕ አስቸጋሪ ፈተና ውስጥ ይገባል፡፡ ፍትሕ እኛ በታሰርንባት ኢትዮጵያ ይሕ ፈተና እንደገጠማት ይሰማናል፡፡ እንግዲህ የኛ ተስፋና ጥበቃም ከዚህ እውነት የሚመነጭ ነው፡፡
ወንጀላችንን ፈልገን ማግኘት አልቻልንም በህግ ፊት ንጹህ ነን ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ይሕ ንፅሕናችን መቼና እንዴት እንደምንፈታ አይነግረንም፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጠኞች ነን፡- እውነት ከኛ ጋር መሆኗን፡፡
በተስፋ የሚያቆመን . . .
እኛን ከአገራችን ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም የዴሞክራሲ ቤተሰብ ጋር ያስተሳስረናል ብለን የምናምነው ዕሴት ሐሳብን በነፃ የመግለፅ ነፃነት ላይ ያለን ፅኑ እምነት ነው፡፡ ሰዎች ሀሳባቸውን ያለምንም ጣልቃ ገብነትና ፍርሃት መግለፅና መደማመጥ ሲችሉ አገራችንን ጨምሮ በዓለማችን ያሉ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን መቅረፍ የሚችሉ ሀሳቦችና መነሳሳቶች መፍጠር ይችላሉ የሚል እምነት ከመታሰራችንበፊትም ይሁን በኋላ በውስጣችን አለ፡፡ የታሰርነውም ይህንን ተፈጥሮአዊ ነፃነታችንን ለመጠቀም ሙከራ ማድረግ ስንጀምር ነው፡፡ በየትኛውም አምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ እውነትን ለጉልበተኞች መናገር ዋጋ ያስከፍላል፡፡ እኛም ሐሳባችንን በነፃነት ስለመግለፅ እየከፈልን ያለነው ዋጋ የማይከብደን የነገይቱ ኢትዮጵያ ከዛሬይቱ ኢትዮጵያ የተሻለች ትሆናለች የሚል ተስፋ በማድረጋችን ነው፡፡
የሚያበረታን . . .
የመታሰራችንዜና ከተሰማ ጀምሮ ብቻችንን አልታሰርንም፡፡ ብዙዎች አኛን ከከለለን አጥር ውጪ አብራችሁን ታስራችኋል፡፡ ስለዚህ የእስርቤት ጌጥ የሆኑት የመረሳትና ተስፋ የማጣት ስጋቶች እንዳይጎበኙን ያደረገንና በብርታት ያቆመን የእናንተው በእሳት የተፈተነ አብሮነት ነውና ሁላችሁም ምስጋና ይገባችኋል፡፡
እምነታችን እዳ ሆኖባችሁ ከታሰርንበት ደቂቃ አንስቶ የመንፈስም፣ የአካልም ዕረፍት ሳያሻችሁ እየደከማችሁ ላላችሁ ቤተሰቦቻችን፣ በፈተናችን ሰዓት ሕመማችንን አብራችሁ ለታመማችሁ ወዳጆቻችን (friends indeed)፣ ከታሰርንበት ጊዜ ጀምሮ ንፅህናቸንን ተረድታችሁ ጉዳያችንንእንደ ጉዳያችሁ እየተከታተላችሁ ላላችሁ እና የመንፈስ ድጋፋችሁ ላልተለየን አገር በቀል እና አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን፣ ሰብአዊነትናየዴሞክራሲ ተቆርቋሪዎች ስለድካማችሁ ምስጋናችን የበዛ ነው፡፡ የማረፊያ ቤት ቆይታችን አዲስ አይነት የህይወት ልምድ የምናገኝበትናየምንማርበት ይሆን ዘንድ አብራችሁን በማረፊያ ቤት የነበራችሁ/ያላችሁ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን እናንተም ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ እንዲሁም ይህን በሕግ አግባብ ያልተመሰረተ ክስ በሕግ አግባብ እንዲቋጭ ያላሰለሰ ጥረት እያረጋችሁ ያላችሁት ጠበቆቻችንና ሌሎቻችሁም. . . ምስጋናችን ከልባችን የፈለቀ ነው፡፡ ሁላችሁም የምንበረታው በእናንተ ነውና እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡

#Ethiopia  #FreeZone9Bloggers  #FreeEdom  #FreeTesfalem  #FreeAsemamaw 

የአንድነት ፓርቲ አባል እና የሚሊየኖች ድምፅ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ ትላንትና ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዶ ለእስር መዳረጉን ወላጅ እናቱ አስታወቁ፡፡ እስማኤል፣ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ቤቱ በመምጣት ‹‹ቃል ሰጥተህ ትመለሰላህ›› በማለት ከቤቱ ወደ አራዳ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱት በኋላ ‹‹ቃሉን ሰጥቶም ቢሆን መለቀቅም እንደማይችል አስታውቀውት ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ […]

የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች፣ ካድሬዎችና ፖሊሶች ሰማያዊ ፓርቲ አዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይቀሰቅስ እንደከለከሉ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሲቀሰቅስ ቆይቶ ወደ አዋሳ ያቀናውን የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዋሳ ሲደርስ እንዳይቀሰቅስ እንደተከለከለ የገለጹት አቶ ስለሽ ደህንነቶች የመኪናውን ባለቤት በማስፈራራት በእጅ አዙር ቅስቀሳችንን […]

ጋሻው መርሻ . ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ […]

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ስጋት የወለደው ስብሰባ ሲያካሂዱ መሰንበታቸውን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣እንደምንጮቻችን መረጃ።- የብ.አ.ዴ.ን. /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዝያ 6 እና 7 2007 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ የአካባቢያችን ደህንንትና ሰላም ምን ይመስላል? የዚህ ክልል አለመረጋጋት ምክንያቱ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎችም ጉዳዮች ሲከራከሩ መቆየታቸውን የገለፀው መረጃው። በተለይ የትጥቅ ትግል የሚያካሂደው የአርበኞች ግንቦት […]

‹‹የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግሥት›› (Islamic State in Iraq and Syria) የሚል መጠሪያ ለራሱ የሰጠው ታጣቂ ቡድን፣ ጸጥታቸው የደፈረሰ አገሮችን የወታደራዊ ኃይሉ እንዲኹም እስከ ኹለት ቢልዮን ዶላር የሚገመተው የገንዘብ እና የንብረት ሀብቱ ማጠናከርያ በማድረግ ወደ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ‹‹የጥንቱን ገናና የእስልምና ሥርዐት›› በ፳፩ኛው ምእት ዳግም ለማስፈን የአምስት ዓመታት ግብ ያስቀመጠው ቡድኑ÷ መካከለኛው …

በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ነዋሪዎች ወይዘሮ ዌንዲ ሸርማን የተባሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስቴር በቅርቡ ኢትዮጵያው ውስጥ ያደረጉትን ጉብኝት ባጠናቀቁበት ጊዜ አገራችን ውስጥ በተጨባጭ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በተጣረሰ ሁኔታ የተናገሩን እንዲያብራሩ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጠይቀዋል። በተለየም በአሁኑ …

ሰበር ዜና፣ የኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ Read more »

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)

አብዛኞቻችን ፈሳሽ ነገሮች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ሻይ እና የመሳሰሉትን መጠጣት ለሰዉነታችን የሚያስፈልገዉን ዉሃ እንደሚተካ እናስባለን፡፡ እዉነታው ግን እነዚህ ፈሳሾች ስኳር እና ጨው በውስጣቸው ስለሚይዙ በሰውነታችን ተመጠው በዉሃ እርዳታ ከእንሽርሽሪት ይወገዳሉ፡፡ በየቀኑ 8 ያህል ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ለጤና ተስማሚ ነው የአፍና ጉሮሮ ድርቀት እንዳይከሰት ከማድረጋቸው በላይ የተለያዩ በሽታዎችና ህመሞችን…

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመላው አገሪቱ በሚታየው የሕዝብ ቁጣ ስጋት ላይ የወደቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት፣ በምርጫ ቦርድ አማካይነት ግንቦት 16 ቀን ሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሠላም ስለሚጠናቀቅበት ለመምከር የአንድ ቀን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ በተቃዋሚዎች ሁልጊዜም ቅሬታ የሚቀርብበት …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም  ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል። በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማምረቻ ወይንም በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ መንግስት በያዘው የአምስት ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት መከናወን ካለባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል ከሲሚንቶ በስተቀር አለመሳካቱን አንድ ሰነድ አመልክቷል፡፡ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ እንዳመለከተው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የአምስት ኣመት እድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀቶችና ከነባር ፋብሪካዎች …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ …

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ጥናት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2030 ወይም ከ15 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 820 ዶላር ይደርሳል። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በ2030 ኢትዮጵያ ፣ የመካከለኛ ገቢ ዝቅተኛ መነሻ ከሆነው 1 ሺ ዶላር ለመድረስ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

Image

Minilik Salsawi የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ም/ ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሰብሳቢ የነበረው በአሁን ጊዜ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆን የወያኔን ስርዓት እየታገለ የነበረው ስንታየሁ ቸኮል ከመኖሪያ ቤቱ በር ገንጥለው በገቡ ፖሊሶችና የደህንነት ኋይሎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስዶዋል።

ስንታየሁ ቸኮል ለረጅም ዘመን በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔን ስርዓት ለመጣል በሚደረገው ትግል ላይ ትግል እራሱን ሰጥቶ ይታገል የነበረ ጠንካራና ለትግሉም በምንም የማይደለል ታማኝ ወጣት ታጋይ ነው።

Image

ከስምንት ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሙሉ ክፍያ ፈጽመዋል

የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅፈር ይፋ ከተደረጉት አራት ፕሮግራሞች አንዱ በሆነው 40/60 ከተመዘገቡ 165 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ውስጥ ሰባት ሺሕ ያህሉ ውላቸውን ሲያቋርጡ፣ 8,329 ተመዝጋቢዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ክፍያ ፈጽመው ቤታቸውን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው…

“እያንዳንዳችን ወደልቦናችን መመለስ አለብን“ የክርስትና ተወካይ

“ቀዳዳውን አብረን እንድፈን“ የእስልምና ተወካይ

“በሰሃራ በረሃ አካላታቸው ለተበለተ ወገኖቻችን ዝም ማለት የለብንም“ የኤርትራ ተወካይ

Ethiopians and Eritrians protested in Sweden. በስዊድን ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በጋራ ኀዘናቸውን ተወጡ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 27, 2015)፡- ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት (16፡00) ጀምሮ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ከ2000 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሰርገልስ አደባባይ በመሰብሰብ በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ አሰቃቂ ግድያ የተፈጸመባቸውን ወገኖቻቸውን በማሰብ ኀዘናቸውን እና ተቃውሟቸውን በጋራ ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አጥናፍ ብርሃኔ 
ስቃይና መብት ጥሰት ያደረሱብኝ ሰዎቸ ስም ዝርዝር ( ሁሉም የፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት) በተለይ
– ሳጅን ምንላድርግልህ
-ታደሰ ወይም ጥጋቡ ( የሽፋን ስም )
– ኢንስፔክተር አሰፋ
– ም/ሳጅን መኮንን
– ኢንስፔክተር ገብሩ
ዋና ዋና የማሰቃየት ተግባር የተፈጸመበት ቀንና ሰአት – ሚያዝያ 17 እስከ ሃምሌ 11 /2006 አም

የማሰቃየት ተግባራት የተፈጸመበት ቦታ – የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ህንጻ በተለይ ቢሮ ቁጥር 5.፣ 32

ዋና ዋና ማሰቃየት ተግባራት
– ታደሰ የተባለው መርማሪ ፓሊስ ያለምንም ምክንያት ምርመራ ክፍል ውስጥ እያነቀኝ በተደጋጋሚ “እውነቱን የማትናገር ከሆነ ሽባ ነው የምናደርግህ ፣ እኛ ለግለሰብ መብት አንጨነቅም” በማለት በጥፊ ሲደበድበኝ ነበር

– ሳጅን ምን ላድርግልህ የተባለ መርማሪ “ጦማር ምን ማለት አንደሆነ ተናገር” ሲለኝ ጦማር ማለት መጻፍ ነው ብለውም ፡።፡።”ምህጻረ ቃል ነው እያንዳንዷ ምጻረ ቃል ምን ማለት አንደሆነች ካልተናገርክ አንላቀቅም” በማለት ከግርግዳ ጋር እያጋጨ ደብድቦኛል፣ ከግርግዳ ማጋጨት ብቻም ሳይሆን ረጅም ሰአት ከአቅሜ በላይ የሆነ የአካል አንቅስቃሴ እየሰራሁ የተመረመርኩ ሲሆን ምራቁን እየተፋብኝ አጸያፊ ስድብ ሲሰድበኝ ነበር፡፡

– ግንቦት ወር ላይ ሳጅን ምን ላድርግልህ የተባለው መርማሪ “ ኢህአዴግን ለምንድነው ተችታችሁ የምትጽፉት ?” “ከአገር ውጪ የምትሄዱት የመንግሰትን ስም ለማጥፋት ነው አንጂ የአባይ ግድብ ቦንድ ለመግዛት አይደለም” በማለት እጄን ወደላይ አድርጌ አንድመረመር አንዲሁም ጆሮዬን እየጎተተ በጥፌ ሲደበድበኝ ውሏል፡፡ ከዚህ ቤት ደንቁረህ ነው የምትወጣው በማለትም ያስፈራራኝ ነበር፡፡ እየተፋብኝ አጸያፊ ስድብ እየተሰደብኩ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል፡፡

– በሰኔ ወር ኢንስፔክተር አሰፋ የሚባለው መርማሪ ሌሊት 6 ሰአት አካባቢ ጠርቶኝ አላማችሁን ካልተናገርክ ጭለማ ቤት ነው የምትገባው በማለት ከማስፈራራቱም በላይ ሌሎች እስረኞች ሲደበደቡ እና ሲጮሁ ሲያለቅሱ በማሰማት እነደነሱ አንዳትሆን በማለት ዛቻ ተፈጽሞብኛል።

– ሰኔ ወር ላይ ኢንስፔክተር ገብሩ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ በመግባት ወረቀት ጽፈሃል የሚል በውል በማላውቀው ምክንያት ከሌሎች እስረኞች ለይቶ በተኛሁበት በተደጋጋሚ ከባድ የእርግጫ ደብደባ ፈጽሞብኛል። ሲደበድበኝም ህዝብ ልታጫርስ ነው እያለ ነበር፣ አስካሁንም የዛን ቀኑን ድብደባ ምክንያት ነው ያሉትን ነገር አላውቀውም፡፡

– በማእከላዊ ቆይታዬ 4በ4 በሆነች ክፍል ውስጥ በቀን ሁለቴ ብቻ ለ15 ደቂቃ ወደውጪ በመውጣት ከአስር ሰው ጋር ተቆልፎብኝ ታሬያለሁ ፡፡ የመጸዳዳት እድልም ቀኑን ሙሉ አልነበረኝም ፡፡ በየቀኑ ከባድ የአካል አንቅስቃሴ መስራት የምርመራው አካል ነበር፡፡

– በሃምሌ ወር ከምሽቱ 2.30 አካባቢ ሳጅን ምንላድርግልህ ፣ ም/ሳጅን መኮንን እና ሌላ የማላውቀው መርማሪ በመሆን ጭንቅላቴን በሃይል ከግንብ ጋር በማጋጨት እና የኮምፒውተር ኬብል በማሳየት አንደምገረፍ በመንገር ሳጅን ምንላድርግልህ የተባለው መርማሪ ፓሊስ የጻፈው የእምነት ቃል ላይ በግዳጅ አንድፈርም ተገድጃለሁ፡፡

*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው 

አቢይ አፈወርቅ
Sydney candlelight vigil. በሊቢያ በደቡብ አፍሪካና የመን ለተገደሉ ወገኖቻችን በሲድኒ የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተከናወነ

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ያስቆጣቸው የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን እሁድ ኤፕሪል 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ የሻማ ማብራት ስርአት አካሂደዋል። በዚህ በኒው ሳውዝ ዌልስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አስተናባሪነት በተዘጋጀው ሥነሥርዓት ላይ ቁጥራቸው ከ350 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …