ኢትዮጵያውያን በአንድነት እንዲነሱ ጥሪ ቀረበ
ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ ሜይ 2፣ 2015 ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶና ታዋቂው ጸሃፊ እና ፖለቲካ ተንታኝ አቶ የሱፍ ያሲን፣ አገራችን ከገባችበት ችግር መላቀቅ የምትችለው በአንድነት በመነሳት መሆኑን ተናግረዋል። አቶ የሱፍ ገዢው ፓርቲ ባመጣው የፌደራል ስርአት ሳንጣላ ተራርቀናል …





