በቫንኩቨር የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ተካሄደ
“የታረዱትንና በጥይት የተደበደቡት ኢትዮጵያዊያን ሰማእታት ናቸው ‘ነፍስ ይማር’ ወይንም RIP ሊባልለት የሚገባው በቁሙ ለሞተው አይሲስ ነው።” ዲያቆን መምህር አድማሱ ዘባን
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. April 25, 2015)፦ ራሱን የእስላም መንግስት በማለት የሚጠራው እና ዘግናኝ ግድያዎችን በንጹሃን ዜጎች ላይ በመፈጸም ላይ በሚገኘው ቡድን እጅ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዊያኖችና በሳውዝ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖች ላይ የሚፍጸመውን ሰብአዊነት የጎደለው አስከፊ ድርጊት በመቃዎም በቫንኩቨር (ካናዳ) ታላቅ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሄደ።