Image
ለጥቂቶቹ መልቀቅያቸው የተሰጣቸውም ሲሆን ለአብዛኞቹ ግን ገና አልተሰጣቸውም።
Minilik Salsawi Via ፍሰሃ ደስታ

በመከላከያ ሚኒስተር ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ምንጮቼ እንደላኩልኝ የወያኔ መንግሰስት ቀኝ እጁን አጥተዋል። በዘመነ አቶ መለስ አድርግ የተባለውን ያለማወላወል የሚያደርግ : በ97 በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት የፈፀመው የኢህአዲግ ታማኙና ፈጥኖ ደራሹ የአጋአዚ ክፍለሰራዊት ከወያኔ መንግስት ጋር የነበረው ቆይታውን በፍቺ ሊፈፅመው መሆኑ ምንጮቼ ገልፀዋል።

እንደ ፍሰሃ ምንጮች ገለፃ በአጋአዚ ክ /ሰራዊት የሚገኙ ሀይሎች ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ከቤተ መንግሰት ወጥተው ወደ ሱማሊና ደቡብ ሱዳን ጸጥታ ለማስከበር በሚል እንደተሰማሩ የሚታወቅ ነው። ከሀገር ውጭ እስከሁለት ዓመት ያክል ቆይተው ሲመለሱ ሊከፈላቸው የጠበቁት: ገንዘብ በተባበሩት መንግስታት ስኬል በመሆኑ ከፍ ያለ ነበር የተሰጣቸው ግን ሀምሳ ሽህ የኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው። ለምን ብለው የጠየቁት ደግሞ የርግጫ የምንትሴ እየተባለ ተቆርጦ እንደቀረ ተገልፆላቸዋል።

ተቆርጦ ተገምዶ ሊያገኙ ከጠበቁት ሩቡን እንኩዋ አላገኙም።በዚህም ምክንያት የክፍለ ሰራዊቱ አባላት መንግስት ላይ ኩፍኛ አንዳኮረፉና በተለይ የሁለት ሀይሎች አብዛኛው አባላት መልቀቅያ እንዳስገቡ: መልቀቅያቸው እንዲቀዱ የተለያየ ተስፋ ቢሰጣቸውም: ለመዓርግ እድገት ቢታጩም ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም። ለጥቂቶቹ መልቀቅያቸው የተሰጣቸውም ሲሆን ለአብዛኞቹ ግን ገና አልተሰጣቸውም።በነገራችን ላይ የአጋአዚ ሰራዊት ከውትድርና ውጭ ሌላ ሂወት የለንም ሲሉ እንደነበር ይነገራል ታድያ አሁን ከውትድርና ሂወት ወጥተው ምን ሊሆኑ ነው? ግንቦት ሰባት ጥሪ ሊያደርግላቸው ይችላል የሚል እርግጠኛ ያልሆነ ጥርጣሬ አለኝ።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሥራ አንደ በመቶ በላይ፣ ለበርካታ አመታት እንዳደገ ይናገራል። በአገሪቷ በተለይም በአዲስ አበባ ግንባታዎች ይታያሉ። መንገዶች ይሰራሉ። ነገር ግን ግንባታዎቹ በአብዛኛው ከዉጭ በልምና በመጣ ገንዘብ የተሰሩ እንደመሆናቸው የኢትዮጵይን ምርታማነትና እድገት አመልካች አይደለም። የብር የመግዛት አቅም ከማሽቆልቆሉ የተነሳ፣ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ የሚመገበው ሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ መጥቷል።

የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ተመዝግቧል የሚሉት የኢኮኖሚ እድገት በርግጥ እድገት ነው ወይ ? ከሆነስ ስለምን ህዝቡ የእድገቱ ተካፋይ ሊሆን አልቻለም ? ለሚሉት ለመሳሰሉት ጥያቄዎች በጥናትና በመረጃ ላይ ያተኮረ መልስ ለማግኘት፣ በቃሌ የፓልቶክ ክፍል የቀረበ፣ በአንድነት ደጋፊዎች የተቀናበረና የተዘጋጀ፣ ገለጻ ያዳምጡ።

https://www.youtube.com/watch?v=rxVV-Jx … e=youtu.be

“ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”

Image
ቡርኪናፋሶን ያለገደብ ሲመሩ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ ለተጨማሪ ዓመታት ሥልጣናቸውን ለማራዘም ያደረጉት ሙከራ በመክሸፉ ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ገለጹ፤ ለአንድ ዓመት የመሸጋገሪያ መንግሥት ተመስርቶ ምርጫ እስከሚደረግ በሥልጣን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ሕዝቡና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን ይህንን የሚቀበሉበት ትከሻ እንደሌላቸውና የኮምፓዎሬ አገዛዝ አሁኑኑ መውረድ እንዳለበት በተቃውሟቸው እየገለጹ ነው፡፡ ከ27ዓመት አምባገነናዊ ሥርዓት በኋላ ቡርኪናፋሶ ወደ ሌላ አምባገነናዊ ሥርዓት ልትሄድ እንደምትች ተጠቆመ፡፡

በቀድሞው ፕሬዚዳንት ቶማስ ሳንካራ ዘመን የመንግሥት ባለሥልጣንና የሳንካራ ወዳጅ የነበሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ፤ ቶማስ ሳንካራ ባልታወቀ ሁኔታ በመፈንቅለ መንግሥት ከተገደሉ ከዛሬ 27ዓመት ጀምሮ ቡርኪናፋሶን መግዛት ጀመሩ፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱን በመምራት የተሳተፉት ኮምፓዎሬ የሳንካራን መገደል በወቅቱ “ድንገተኛ” በማለት ከመጥቀስ በስተቀር ምርመራ እንዲካሄድ አላዘዙም፤ ምስጢሩም እንዳይወጣ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ቶማስ ሳንካራን ከሥልጣን ካስወገዱ በኋላ ለሦስት ዓስርተ ዓመታት ያህል የዘለቀውን አገዛዛቸውን የጀመሩት ኮምፓዎሬ እኤአ በ1990ዎቹ በተደጋጋሚ የተመረጡት ሲሆን የአገሪቱ ሕገመንግሥት ከተሻሻለ በኋላ በሁለት ሺዎቹም ሁለት ጊዜ ተመርጠዋል፡፡

በአገዛዝ በቆዩበት ዘመን ሁሉ የአውሮጳውያንና የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሥልጣናቸው ሳይደፈር በአምባገነንነት ለመቆየት ችለዋል፡፡ አክራሪ እስላማዊነትን እዋጋለሁ በማለት የአሜሪካ ወዳጅነታቸውን ያጠናከሩት ኮምፓዎሬ በላይቤሪያና ሴራሊዮን እጅግ አስከፊ ጭፍጨፋ ያካሄዱትን እና በአሁኑ ወቅት 50ዓመት እስራት የተበየነባቸው የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ ቻርልስ ቴለር የቅርብ ወዳጅ ነበሩ፡፡ ሳንካራን ለመገልበጥና ለመግደል የቴይለር ጦር እንደተሳተፈና በምላሹ ኮምፓዎሬ ለቴይለር ወደ ሥልጣን መምጣትና ከዚያ ጋር ተያይዞ ለተፈጸመው ወንጀል ተባባሪ ናቸው በማለት ሁኔታዎችን የሚያገናኙ ወገኖች አሉ፡፡

በአገራቸው የሚነሱ ተቃውሞዎችን ስልታዊ በሆነ መንገድና በምዕራባውያን ድጋፍ ሲያከሽፉ የኖሩት ብሌዝ ኮምፓዎሬ በአካባቢው አገራት ዘንድ የሰላም ዘንባባ አቅራቢ፣ አስታራቂ፣ አስማሚ፣ ሸምጋይ፣ … ሆነው ምስላቸውን እና ማንነታቸውን ሲገነቡ ቆይተዋል፡፡ በአምባገነንነት በቆዩባቸው ዓመታት በሙስና በተለይም ከአልማዝ ሽያጭ ከሚገኘው ገንዘብ ያላቸው ተሳታፊነት ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡

በቀጣዩ የአውሮጳውያን ዓመት 2015 ሥልጣናቸው የሚያበቃው ኮምፓዎሬ “ደህና ሁኑ” ብለው ለመሄድ የተዘጋጁ አልነበሩም፡፡ በመሆኑም የአገሪቱን ሕገመንግሥት በማሻሻል እንደገና ለመመረጥ ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ፡፤ ፓርላማቸውን አሰብስበው ሕገመንግሥቱ እንዲሻሻል በማድረግ ሂደት ላይ እያሉ ሕዝቡ “በቃኝ” አለ፡፡

የ27 ዓመታት አገዛዝ የመረራቸው ዜጎች ሐሙስ ዕለት ፓርላማውን ጥሰው በመግባት ድምጽ እንዳይሰጥ ከማድረግ አልፈው በእሣት አጋዩት፡፡ ተቃውሞ በየቦታው ፈነዳ፡፡ ቡርኪናፋሶ መጋየት ጀመረች፡፡ ሁኔታው ያላማራቸው ኮምፓዎሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ፡፤ ሰሚ ግን አላገኙም፡፡ ሕዝቡ “ይህንን አገዛዝ አንፈልግም፣ በቃን” አለ፡፡ ሕዝባዊ ዓመጽ በየቦታው ተቀጣጠለ፡፡ በተለይ ዋና ከተማዋ ዖጋዱጉ የዓመጹ ዋና ማዕከል ሆነች፡፡

መንግሥት ሥራ አቆመ፣ ፓርላማውም ፈረሰ፡፡ ድህነት ያስመረራቸው ዜጎች አሁንም ተቃውሟቸውን ቀጥሉ፡፡ ኮምፓዎሬን ማየትም ሆነ መስማት በጭራሽ አይፈልጉም፡፡ ወታደሮች በየአካባቢው ሥነሥርዓት ለማስጠበቅ እየጣሩ ቢሆንም ዓመጹ ግን ቀጥሏል፡፡ ንብረት እየወደመ ነው፤ ባንኮችም ተዘርፈዋል፡፡

ዛሬ አርብ ዳግም ለመመረጥ ሲመኙ የነበሩት ኮምፓዎሬ ሥልጣን በቃኝ፤ መንግሥት ፈርሷል፤ ፓርላማውም አይሰራም፤ ከሥልጣኔ እለቃለሁ ነገር ግን በ2015 ምርጫ እስከሚካሄድ የሽግግር አስተዳደር ተመስርቶ ሁሉም ነገር መረጋጋት አለበት በማለት አስቀድሞ በተቀዳ የቴሌቪዥን መልዕክት ቢያስተላልፉም ሰቆቃ የመረራቸው፣ ኑሮ ያቃጠላቸው፣ ነጻነት የጠማቸው ዜጎች ግን አሁንም “አንሰማም” ብለው ተቃውሟቸውን በመቀጠል ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል፡፡

ሰላሳ አራት የሚሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ፕሬዚዳንቱ ያቀረቡትን ቅደመ ሁኔታ አንቀበልም ብለዋል፡፡ ለኮምፓዎሬ ምላሽ ሲሰጡም “አንድ የምንቀበለው አጭርና ግልጽ ቅድመ ሁኔታ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ብሌዝ ኮምፓዎሬ ከሥልጣን እንዲለቁ ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡

ጦሩ ሥልጣኑን የተረከበ እንደሆነ እየተጠቆመ ሲሆን አገሪቱን በበቂ ሁኔታ ለማረጋጋት እንዳልቻለ ከዋና ከተማዋ የሚመጡ ዜናዎች ይጠቁማሉ፡፡ የሕዝቡ ዓመጽም ወደ ሌሎች ከተሞች እየተዛመተ መሆኑን ከተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እየተሰማ ነው፡፡

በአንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ከአረብ ጸደይ ቀጥሎ የተጀመረ “የአፍሪካ ጸደይ” ሊሆን ይችላል በማለት ግምት የሰጡበት የቡርኪናፋሶ ሕዝባዊ አመጽ ተመልሶ በአምባገነናዊ አገዛዝ እንዳይወድቅ ስጋት አላቸው፡፡ ለዚህም ጠንካራ ተቋማት መመሥረት አስፈላጊነትን ያሰምሩበታል፡፡ በተለይ ከአምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ሕዝባዊ ሥርዓት በሚደረግ ጉዞ በቅድሚያ የሚደረጉ መሰናዶዎች ሳይከናወኑ በጭፍን አምባገነኖችን ከሥልጣን እንዲወርዱ ማድረግ በበርካታ አገራት እንደተደረገው መልኩን የቀየረ አምባገነናዊ ሥርዓት ለመመሥረት እንደሚጋብዝ ይናገራሉ፡፡ ከዚህ አንጻር የሕዝብ ንቃተ ኅሊና መዳበር፣ የእርሰበርስ ውይይት መጀመር፣ የተቋማት መመሥረት፣ … ወሳኝነት ያላቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንደሆኑ ያሰምሩበታል፡፡

*********************
“ይህ አገዛዝ በቃው! አንፈልገውም! 27 ዓመት + 1 አንቀበልም!”
ቡርኪናፋሶ ከአምባገነን ወደ አምባገነን?
http://www.goolgule.com/it-is-over-for- … rkinafaso/

Image
ስብሓት ነጋና የኤርትራ ጉዳይ
ስብሓት ነጋ በቪኦኤ የትግርኛ ፕሮግራም ላይ የሚከተለውን ብሏል (ግርድፍ ትርጉም ነው፤ ሙሉ ዝግጅቱ ሲቀርብ ወደ አማርኛ እንመልሰው ይሆናል) ፥
«የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ችግር ነው የሚለው አመለካከታችን ዳግም መፈተሽ አለበት። የአገዛዝ ችግር እንጂ የቅኝ ግዛት አልነበረም።»
ለምን አሁን???
«የኤርትራ ህዝብ ለነፃነት ከነበረው ጉጉትና ከደረሰበት ግፍ አንፃር፤ ነፃነቱን «በመረጠው መንገድ» መቀዳጀቱ ባያስቆጨንም፤ ችግሩ «የቅኝ ግዛት ችግር» ነበር የሚለው አመለካከታችን መስተካከል ያለበት ይመስለኛል።»
አሁንም በድጋሚ፤ ለምን አሁን???
የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ነበር የሚል አመለካከት የህውሓትና የሻዕቢያ ብቻ እንጂ የማንም እንዳልነበር ግልፅ ነው። (የኤርትራ ህዝብ ሳይቀር ከኢትዮጵያ ጋር በአብሮነት መቀጠል እንደሚፈልግ ቀደም ሲል በጥናት የተረጋገጠ መሆኑን በዘውዴ ረታ መፅሃፍ ላይ «የኤርትራ ጉዳይ» ያነበብኩ መሰለኝ። ) ሟች መለስ እስከ ግብአተ መሬቱ ፍፃሜ ድረስ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዢ እንደነበረች ሲያውጅ ኖሯል። ችግራቸው የአስተዳደር እንጂ የቅኝ ተገዢነት አይደለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሳደዋል፤ ወዘተ። ችግሩ የቅኝ ግዛት ነው፤ ጥያቄውም የነፃነት ጥያቄ ተብሎ፤ ያለ ህዝበ ውሳኔ መፍትሄ ተሰጥቶበታል። መፍትሄውም ጦስና ግሳንግሱን በሁለቱ ህዝብ መሃል አራግፎ፤ ኤርትራን ህዝብ አልባ ዋሻ አድርጓታል። ስንት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በነሱ ምክንያት አልቀዋል።
ይሄ የአገሪቱ ብቸኛ «ሉዓላዊ ግለሰብ»፤ ይህ አመለካከታቸው ዛሬ መታረም እንዳለበት የሚነግረን ለምን ይሆን? ምን ተንኮል አስቦ ነው??

በሽብር ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ላይ የሚገኙት እነ ሀታብሙ አያሌው ልደታ ፍ/ቤት ቀረቡ
**************************************
በማዕከላዊ እስር ቤት ከ115 ቀን እስር በኋላ ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው
****************************

<a href=”http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n.jpg”><img src=”http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2014/07/10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n.jpg” alt=”10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n” width=”252″ height=”144″ class=”alignleft size-full wp-image-15235″ /></a>
በትላናው ዕለት አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሊቀርቡ ያልቻሉት የፓርቲ አመራሮች፣ በድብቅ ትላንትናውኑ ልደታ ፍ/ቤት መቅረባቸውንና ዳኛ ባለመሟላቱ ለዛሬ ጠዋት ተቀጠረው ነበር፡፡ ዛሬ ጠዋት ከታሰሩበት ማዕከላዊ ፍርድ ቤ/ት ፖሊስ አጅቦ ቢያመጣቸውም ከቀኑ በግምት 5፡00 ሰዓት አካባቢ 4ኛ ወንጀል ችሎት ካስገቡዋቸው በኋላ፣ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ወደ መኪናቸው በመመለስ ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት እንደሚቀርቡ ለመጣው ታዳሚ ከችሎት አስተናጋጇ በመገለጹ፣ ከሰዓት በ 8፡00 ሠዓት 4ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ችሎት መግባት ይከለከል የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን ታዳሚው ችሎት እንዲገባ ተፈቀደ፡፡

በችሎቱ የቀረቡት 10 ተከሳሾች ሲሆኑ እነሱም፡-

1ኛ. ተከሳሽ የአ/አ ዩኒቨርስቲ ማስትሬት ተማሪ የሆነው ወጣት ዘላለም ወርቅአገኘሁ
2ኛ. ሃብታሙ አያሌው
3ኛ. ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ. አብርሃ ደስታ
5ኛ. የሺዋስ አሰፋ
6ኛ. ዮናታን ወልዴ
7ኛ. አብርሃም ሰለሞን
8ኛ. ሰለሞን ግርማ
9ኛ. ባህሩ ደጉ
10ኛ. ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው፡፡

በችሎቱ ላይ 3 ዳኞች የተሰየሙ ሲሆን የመሀል ዳኛው የዘገየነው ዳኞች ባለመሟላታቸው መሆኑን ከገለጹ በኋላ ተከሳሾችን ክሱ እንደደረሳቸው ጠየቁ፡፡ ተከሳሶችም ክሱ እንዳልደረሳቸው መለሱ፡፡ ክሱ የቀረበው ጥቅምት 20 ቀን2007 ዓ.ም መሆኑን ዳኛው ከገለጹ በኋላ ክሱ እንዲታደላቸው አደረጉ፡፡

ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉት ተከሳሶች አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ የሚንቀሳቀሰው ራሱን ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት አባል በመሆን ከድርጅቱ አባሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አባላት በመመልመል፣ ህጋዊ የፖቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ ሕዝቡ በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ በማድረግ፣ በደቡብ ክልል ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ መግለጫ በመስጠት፣ እንዲሁም ትህዴን ከሚባል ድርጅት ጋር በህቡዕ ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም በዋና የወንጀል ድርጊት ተካፋይ በመሆን የተከሰሱ ሲሆን ከ6ኛ እስከ 10ኛ ድረስ ያለት ተከሳሾች ክስ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ማህበራዊ ተቋማትን ለማፈራረስ የሽብር ድርጊቱን ለመፈጸም በውጭ ሀገር በተማሩት የማህበራዊ ድህረ ገጽ አጠቃቀም የተለያዩ የፌስ ቡክ አካውንቶችን በመጠቀም ለድርጊቱ መፈጸም ሲሰሩ እንደነበር የአቃቤ ህግ ክስ ያመለክታል፡፡

እንደ ቅደም ተከተሉ ክሳቸው ተነቦ ካለቀ በኋላ ዳኛው ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም ትችላላችሁ ወይስ መንግስት ያቁምላችሁ ብለው በጠየቁት መሰረት ከ8ኛው ተከሳሽ በስተቀር ሁሉም ጠበቃ እንደሚያቆሙ ገለጹ፡፡ ነገር ግን እኛ ጠበቃ ብናቆምም ከታሰርንበት ሀምሌ 1 ቀን ጀምሮ ከጠበቆቻችን ጋር መገናኘት አልቻልንም ክቡር ፍ/ቤቱ ልንገናኝ እንድንችል ትዕዛዝ ይስጥልን፣ እስካሁን ከታሰርንበት ማዕከላዊ ወደ ማረሚያ ቤት እንድንሄድ እንዲታዘዝልን በማለት አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍ/ቤቱ ጠይቋል፡፡

አቃቤ ህግ አንቀጽ ጠቅሶ በሽብር የተጠረጠረ የዋስትና መብትን አይፈቅድም ይላል በመሆኑም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ እንደረግ ጠየቀ፡፡

ዳኛውም በዋስትና ላይ ያላችሁን አስተያየት ይዛችሁ ረቡዕ ጥቅምት 26 ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት መልሳችሁን በጽሑፍ ይዛችሁ ቅረቡ ተከሳሾች በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ይደረግ በማለት ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

Image
አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል
#Ethiopia #UDJ #Blueparty #Ginbot7 #EPRDF #MinilikSalsawi

– ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል
– እነ የሽዋስን ጨምሮ 10ር ተጠርጣሪዎች በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው

Minilik Salsawi
በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡

የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡-

1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ
2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው
3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ
4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ
5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ
6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ
7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን
8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ
9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ
10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው

ለሁሉም ተከሳሾች ከዛሬ በፊት ክስ እንዳልደረሳቸውና ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በችሎቱ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው ዮናታን ወልዴ በስተቀር ሁሉም ያለ ጠበቃ የቀረቡ ሲሆን ጠበቃዎቹ ያልቀረቡበት ምክንያትም ጠበቆቹ ደምበኞቻቸው የሚቀርቡበት ቦታና ጊዜ ስላልተነገራቸው እንዲሁም ቀደም ብለው እንዳይገናኙ በመደረጋቸው መሆኑን አቶ ኃብታሙ አያሌው ችሎቱ ላይ ተናግሯል፡፡

ከሳሹ የፌደራል አቃቢ ህግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ እና የጸረ ሽብር ህግ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ሲሆን ክሶቹ በሁለት ዋና ዋና ጭብጦች ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው ጭብጥ ‹‹ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር በጋራ በመስራት›› የሚል ሲሆን ‹‹ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ የመንግስትን መሰረተ ልማት በማፈራረስ፣ ህዝብን ለአመጸ በማነሳሳት መንግስትን መለወጥ አላማው አድርጎ ከሚሰራውና ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር አባል በመሆንና በወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ›› በሚል ቀርቧል፡፡

ሁለተኛው የክስ ጭብጥ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር በመሆን›› የሚል ሲሆን በተለይም የአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹የሽብር ቡድኑ አመራር በመሆንና አባል በመመልመል›› በሚል የክስ ጭብጥ ቀርቦበታልል፡፡

ከ2-5ኛ የክስ መዝገብ የሚገኙት ማለትም ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽ፣ አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ ‹‹ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ከለላ በማድረግ ግንቦት 7 የተባለውን የሽብር ቡድን አላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ፋሲል የኔ ዓለምና ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር በስልክ በመነጋገርና በማህበራዊ ድህረ ገጸ የተለያዩ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ አብርሃ ደስታ ከግንቦት 7 በተጨማሪ ‹‹ደምኢት የተባለ ቡድን አባል ነው፡፡›› የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡

በስተመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አንደኛው ረቡዕ ጥቅምት 26/2007 ዓ.ም 3 ሰዓት ተከሳሾቹ ዋስትና ይሰጣቸው አይሰጣቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ጋር ተማክሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡ በሁለተኛነት ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቀደም ሲል ለአራት ወራት ወደቆዩበት ማዕከላዊ እስር ቤት እንዳይመለሱ ፍርድ ቤቱን ስለጠየቁ ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት (3ኛ) እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተከሳሾቹ ትናንት ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ የነበር ቢሆንም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ጠዋት ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ተወስደው የነበረ ቢሆንም እንደገና ወደማዕከላዊ ተመልሰው ከሰዓት እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡

ነገም እኛ ከሕዝብ ጥያቄ እንደማናመልጥ ልናውቅ ግድ ይለናል!!!
Minilik Salsawi
እውነትን ብንውጣት ምናለ? በሃሰት ሕዝብን እያታለልን እስከመቼ እንኖራለን ? እስከመቼ ያልሆነ እንደሆነ ያልተደረገ እንደተደረገ እስከመቼ እየተደበቀ እየተሹለከለከ። የሕዝብን የነጻነት እና የመብት ጥማትን ተገን አድርገን በማይረቡ ወንፊቶች ስር ተሸሽገን የተሸሸግን መስሎን እየታየን ለምን ? የማያዛልቅ ጸሎት …. ባለፉት አመታቶች እኮ እያየን ነው ምንም ውጤት የለም አላየንም አልሰማንም የምንልበት ደረጃ ላይ ነን ያለነው። ታዲያ ምንን እንመን ? ማን እውነትን ይዟል እንበል? በፕሮፓጋንዳ አብዮት ተወጥረን እስከመቼ?

ያሌለ ነገር እንዳለ ያልተሰራ እንደተሰራ አይ አንቺ መሬት !! አዎን ያው እውነትን እንያዝ ለህዝብ ከህዝብ በህዝብ የሆነ ስኬታማ ትግል እናድርግ በማለታችን ምናልባት ልንሰደብ ልንዋረድ ልንዘረጥጥ እንችላለን ለምን በፕሮፓጋንዳ የሞሉን እውነትን መዋጥ ስለሚከብዳቸው መግቢያ ሲጠፋ ግለሰቦች ላይ ይዘምታሉ። ግለሰቦችን ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ውጪ ይሳደባሉ ያዋርዳሉ ይወነጅላሉ። ትላንትና ምን አሉ? ዛሬ ምን አሉ? ነገ ምን ይላሉ ? በትግል ላይ ነን እያሉን መስመሩ አያዋጣም ያሉ ሰዎችንስ እንዴት አስዋጡ ? እያንዳንዱን መለስ ቀለስ እያልን በፖለቲካ እና አገራዊ ህዝባዊ ምንዛሬ ላይ ካጤነው መጭውን ጊዜ ለመወሰን አንገታችንን የሚያስደፋን ነገር አፍንጫችን ስር ይወተፋል።

በግልጽ መውጣት ሲገባን ለሌላ የተለመደ ፕሮፓጋንዳ መስመር እና ስልት ቀይረን ስንመጣ ቀን ጠብቆ ከህዝብ ጥያቄ ማምለጥ እንደማይቻል ለመናገር እንደፍራለን። አለማቀፍ ድርጅቶች እና ሚዲያዎች የእሚነግሩን ሌላ መሬት ላይ ያለው ሌላ ፕሮፓጋንዳው የሚነግረን ሌላ ታዲያ የነጻነት ጥማታችንን እንዴት እንወጣ። ያለን የመጨረሻ እድል ሕዝቡ ሆ ብሎ አደባባይ እንዲወጣ ከማድረግ ውጪ አለ አለን በሚሉት ላይ መተማመኑ እንደማያዋጣ ሊሰመርበት ይገባል እኔም እንደ ዜግነቴ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል አውቅልሃልሁ የሚል የህሰት ፕሮፓጋንዳ አንገሽግሾናል ። ነጻነት በጃችን ነውና ራሳችንን ነጻ እናውጣ ።

በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቴፒ ከተማ በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ መንግስት የከተማውን ህዝብ አርብ ጥቅምት 20፣ በትልቁ አዳራሽ በመሰብሰብ፣ በአካባቢው የሚታየውን ችግር በጋራ እንፍታ በማለት ጥሪ አቅርቧል። ለግማሽ ቀን በተካሄደው ስብሰባ ነዋሪዎችና የመንግስት ባለስልጣናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲወዛገቡ አርፍደው ሳይግባቡ መለያየታቸውን በስብሰባው የተሳተፈው ወኪላችን ገልጿል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ችግሩን የምትፈጥሩት እናንተ ሆናችሁ ሳለ እኛን መፍትሄ አምጡልን ማለታችሁ ተገቢ አይደለም በማለት በከተማዋ የሚታዩ የጸጥታና የኢኮኖሚ ችግሮችን በማንሳት ለባለስልጣኖቹ ሲያስረዱ ውለዋል።
ሀሙስ ከሰአት በሁዋላ በቴፒ መውጫ በሮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ቅኝት ማድረግ መጀመራቸውና አልፎ አልፎ የተኩስ ድምጽ መሰማቱ በከተማው ህዝብ ላይ አለመረጋጋት መፍጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቴፒ ካምፓስ ፈንጅ ተገኝቷል በሚል የተጠናከረ ፍተሻ ሲካሄድ ሰንብቷል።

የሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች ከፌደራልና ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ እንደሚያደርጉም የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በሌላ ዜና ደግሞ ለወራት በጋምቤላ በዘለቀው ግጭት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ በርካታ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት መቅረባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ። ቁጥራቸው 50 የሚጠጉ የጋምቤላ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ጋዜጣው ዘግቧል።
“ከጋምቤላ ክልል የመጡት ዜጎች በአራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ተመሳሳይ ሰዓት የሸዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ የሚቀርቡ በመሆኑ በዚህ ችሎት ለመታደም የሄደው ህዝብ ከጋምቤላ የመጡትን ዜጎች ተከትሎ በተደረገው ጥብቅ ምክንያት ከፍተኛ ፍተሻ ” መደረጉን ገልጿል፡፡
ጥቅምት 19/ 2007 ዓ.ም ወደ ማታ አካባቢ ከጋምቤላ የመጡ በርካታ ዜጎች በአውቶቡስ ተጭነው ወደ ማዕከላዊ መግባታቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
መንግስት በክልሉ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ግጭት ሲፈጥሩ ነበሩ ያላቸውን ሰዎች መያዙን አስታውቋል። የአካባቢው ግጭት የህወሃት ሰዎች ከሚያደርጉት የመሬት ቅርምት ጋር የተያያዘ መሆኑን ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች መግለጻቸውን ተናግረዋል።

በቅርቡ፣ ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት ፣ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያና የኤርትራ ሞኒተሪንግ ግሩፕ በለቀቀዉ ሪፖርት ዙሪያ አንድ መግለጫ አዉጥቷል። አንዳንድ የተወሰኑ ድህረ ገጾች የግንቦት ሰባትን መግለጫ ለጥፈው፣የተባበሩት መንግስታ ሪፖርትን ግን ሳያያይዙ ቀርተዋል። ይሄን ሰነድ በሚከተለው ሊንክ ልታገኙት ትችላላሁ፡

http://www.un.org/ga/search/view_doc.as … S/2014/727

አስገራሚ መረጃዎችን ያካተተ ሰነድ ነው። ሰነዱ አልፎ አልፎ አንዳንድ ጥቃቅን ግድፈቶች አሉት። ለምሳሌ ግንቦት ሰባትን የአማራ ድርጅት እንደሆነ የገለጹበት ሁኔታ አለ። ከዚያ ዉጭ ከሞላ ጎደል በሰነዱ የተካተተው ዝርዝር፣ የሚታመን ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ ሪፖርት ላይ በስፋትና በቅርብ ጊዜ ትንታኔ እንሰጥበታለን። ግን ለአሁን በግርድፉ አንብቤ ከሰነዱ ያገኙኋቸውን ጥቂት አንኰ ነጥቦች እንዳስቀመጥ ይፈቀድልኝ፡

1) ኦ.ኤን.ኤል፣ኤፍ ከአልሻባብ ጋር እንደሚሰራና ማእከሉን ከኤርትራ ወደ ሶማሊያ እንደወሰደና አሁን ኤርትራ ከበስተጀርባ ሆና መደገፏን እንደቀጠለች

2) ኦነግ የሚባል ነገር እንደሌለ

3) የግንቦት ሰባት ጦር ከ50 እስከ 70 እንደሆነ

4) ደሚት የሚባለው ድርጅት ትልቁና ጠንካራው እንደሆነ፣ ከሕወሃት ተቃዋሚነት አልፎ የኢሳያስ ክብር ዘበኛና ቅልብ ጦር እንደሆነና ከባባድ መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እየተወሰደ ወደ ደሚት እየተሰጠ እንደሆነ

5) ሻእቢያ ለግንቦት ሰባት ሆነ ለሌሎች ድርጅቶች የሚያደርገው እርዳታ የተባበሩት መንግስታትን ዉሳኔ የሚያፈርስ እንደሆነና ግንቦት ሰባት በተባበሩት መንግስታት ራዳር ዉስጥ እንደወደቀ

በቅርቡ ኢትዮጵያያ ሪቪው የተለያዩ ሪፖርቶች ሲያቀርብ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። የዚህ ሞኒተሪንግ ቡድን ሪፖርት በአብዛኛው ኢትዮጵያ ሪቪው ካቀረበው ጋር የሚዛመድ ነው።

በተያያዘ ዜና ደግሞ በኤርትራ ዉስጥ ከፍተኛ ተቃዉሞ በኢሳያስ አፈርቂ አገዛዝ ላይ እየተነሳ እንደሆነ ነው። ሃርነር አርቢ የሚባለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድጋፍ እያገኘ ነው። በጦር ሰራዊቱ ዉስጥ ሁሉ ዘልቆ ስለገባ ፣ ኢሳያስ ፊቷን ወደ ደሚት ለማዞር እስኪገደድ ድረስ።
በ ኤርትራ ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ እያለ የተከበሩ ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ ከአሜሪካን አገር ሳይወጡ ለምን የግፈኛው አቶ ኢሳያስ ተሟጋች እንደሆኑ አልገባኝም ? እርሳቸውስ እሺ ሌሎች የግንቦት አባላትና ደጋፊዎች፣ እንደ አበበ ገላው፣ መቼ ይሆን አንድ ግለሰብን ማምለክና መከተል አቁመው ለሕዝቡና ለትግሉ የሚጠቅም ነገር የማያደርጉት ?

የግንቢት ሰባት ንቅናቄ የተሳሳተ መንገዱን በአስቸኳይ መመርመር አለበት። ኢሳያስ ሊገነደስ ጥቂት ጊዜ የቀረው የበሰበሰ ዛፍ ነው። እስከመቼ ነው በበሰበሰ ዛፍ ላይ ተንጠልጥለው ትግሉን ብለው ወደነርሱ የመጡትን ለጋ ኢትዮጵያዉያን የሚያስበሉት ?

Image

የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልና በማጽናት ተጠናቀቀ ::

+ የፓትርያርኩ ምሬትና ብስጭት ያሳሰባቸው ብፁዓን አባቶች ሲያረጋጓቸው አመሹ::
+ አቡነ ማትያስ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡

‹‹ከሕዝብ አጋጫችኹኝ፤ ከወንድሞቼ አንድነት ለያችኹኝ፤ ከነገራችኹኝ አንዱንም የተቀበለኝ የለም›› በሚል የተመረሩት አቡነ ማትያስ ምክራቸው ያልሠመረላቸውን ሦስት አማሳኝ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡

ከትላንትናው የስብሰባ ውሎ መጠናቀቅ በኋላ ፓትርያርኩ የነበሩበት የምሬትና የብስጭት ኹኔታ ተነግሯቸው ወደማረፊያቸው የተጠሩት በሹመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ማትያስ በተጠሪነት ጉዳይ የተሟገቱለት አቋም የቤተ ክርስቲያን እንዳልኾነ፣ ለአጭር ዕድሜ የኖረው የቤተ ክርስቲያን ሕግ መለወጥ እንደሌለበት ይልቁንም የአማሳኞችንና የባዕዳንን ምክር ከመስማትና ከመቀበል ተጠብቀው ትላንት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋራ ኹነው የተከላከሉለትን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ማስከበራቸውን ቢቀጥሉ በእርሳቸውና በአባቶች መካከል ያለው ውጥረት ሊረግብና ሊተራረቅ እንደሚችል አመልክተዋቸዋል፡፡

ፓትርያርኩ በትላትናው ምሽት አማሳኞቹን በብስጭትና በምሬትም ቢኾን ከአበረሯቸውና በብፁዓን አባቶች ምክር ከተጽናኑ በኋላ በዛሬው የምልአተ ጉባኤው ውሎ ስብሰባውን በተረጋጋና በመግባባት መንፈስ ሲመሩና ‹‹እናንተ ካላችኁት አልወጣም›› እያሉ በጋራ ሲወስኑ ውለዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት(ልዕልና) በማረጋገጥ በተጠናቀቀው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ አጀንዳ፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስና ኤጲስ ቆጶስ(ጳጳስ) ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶሱ እንደኾነ ጸንቷል፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ኾኖ ሲሠራበት የቆየው ልምድ በማሻሻያው ተካትቶ እንዲደነገግ ተወስኗል፡፡ በልዩነት ነጥቦቹ ላይ በተላለፉት ውሳኔዎች መሠረት ረቂቁ ተስተካክሎ ሲቀርብ በምልአተ ጉባኤው አባላት ፊርማ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በደቡብ አፍሪቃ በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብና በምእመናን መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት መፍትሔ ለመስጠት በቀረበው የአጣሪ ልኡክ ሪፖርት ላይ የመከረው ምልአተ ጉባኤው÷ ብፁዕነታቸው ለጊዜው መንበረ ጵጵስናቸውን በናይሮቢ አድርገው በኬንያ፣ በጅቡቲና በሱዳን ተወስነው እንዲሠሩ፤ በደቡብ አፍሪቃ ደግሞ አገልግሎቱ በአድባራት አለቆችና በሰባክያነ ወንጌል ላይ ተመሥርቶ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሰሜን አሜሪካ በሚገኙት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ጉዳይ መምከር ጀምሯል፡፡

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱን የቻለ ሊቀ ጳጳስ ስለመመደብና በሀገረ ስብከቱ የተፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ በነገው ዕለት በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

ወያኔ/ህወሓት ያደራጃቸው ምሊሽያዎች በአፋር ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ

አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦

ትናንት ማክሰኞ 18/02/2007 በአፋር ክልል በሰሜናዊ ዞን በኮናባ ወረዳ በትግራይ ታጥቂ ሚሊሻዎች በኮናባ ፈራስዳገ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ጦርነት የከፈቱ ሲሆን ቦታውን በቶክስ እሩምታ ሲያምሱት ማርፈዳቸውን ከቦታው የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ለጊዜው ከአፋር ነዋሪዎች በኩል የቶክስ ምላሽ አላገኙም! ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን የተጀመረው ይህ ቶክስን ተከትሎ ከኮናባ ወረዳ ብዙ ወጣቶች ተሰብሰበው በፍጥነት ወደ ቦታው የደረሱ ሲሆን በዛን ጊዜ የኔትዎርክ አገልግሎት ወዲያው ተቋርጧል። እስካሁን ከአፋር ነዋሪዎች በኩል የተተኮሰ አንድ ጥይት የለም።

የቦታው ምንጮች አያይዘውም «ይህ ደግሞ የአፋር ወጣቶች ለሰላም ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው። ነገር ግን አስገዳጅ ነገር ከተፈጠረ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ከየቦታው ተሰብስበው ዝግጅት ላይ ናቸው።» ብለዋል። ከኮናባ አንድ ስሙን ሊናገር ያልፈለገ ወጣት እንደነገረኝ «ይሄ በህወሓት ሆን ተበሎ የሚደረግ ትንኮሳ በመሆኑ የአፋር ወጣቶች በበሰለ አስተሳሰብ ለሰላም ያላቸው ፈለጎት በትዕግስት አሳይተዋል።» ብሏል። አያይዞም «ኔትወርክ ራሱ የጠፋው ለሌሎች መረጃ እንዳይደርስና የአፋር ህዝብ እንዳይነሳ በመፍራት ነው» ሲል አክሏል። አሁንም ቦታው ውጥረት እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኮናባ ወረዳ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊን አስተያየት ለማካተት ያደረኩት ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።

ምንጭ ዘሃበሻ አማርኛ ገጽ

#Ethiopia #SouthSudan #OELF #ExEthiopianArmyOfficers #MinilikSalsawi

ሰው በላው መንግስቱ ሃይለማርያም መሞት ሆነ መኖር ማንችንንም ሊያስጨንቀን ሊያሳስበን አይገባም።
Minilik Salsawi

በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔን አምባገነን መንግስት ለማስወገድ በትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡ ተቃዋሚ ሃይሎች ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ጋር መገናኘታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።ከባለስልጣናቱ ጋር የተገናኙት በኤርትራ ውስጥ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ድርጅቶች እና በአስመራ ቢሮ የሌላቸው የፖለቲካ ሰዎች እንደሆኑ ታውቋል።

በመጪው ጊዜያት ሊደረጉ ስለሚችሉ እና ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ሃይሎች ከጁባ መንግስት ተጽእኖ ስር ያልወደቀ የራሳቸው መንደርደሪያ መሬት እና ወታደራዊ ቤዝ የሚያገኙበትን ጉዳይ በተመለከተ መወያየታቸው ታውቋል። እንዲሁም አስፈላጊ የሆነ ወታደራዊ እርዳት የሚደረግበትን ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው ሲታወቅ በቀድሞ የደርግ መንግስት ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ዜግነታቸው ሃገራቸውን ለመካስ በወታደራዊ አማካሪነት ላይ የሚሰሩበትን አስመልክቶ የጁባው መንግስት ስምምነቱን ገልጿል።ምንጮቹ ከዚህ በላይ ዝርዝር ሁኔታ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

መንግስቱ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ተቃዋሚ የትጥቅ ትግል የሚፈልጉትን አካላቶች ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ያገናኛል የሚል ፍራቻ የተከሰተ ይመስል ይህን ሰሞን ከባለፈው አመታት በተወራረሰ መልኩ በቀጥታ ግልባጭ መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ አድርገው የሻእቢያ አቧራ አጫሽ ድህረገጾች ወሬውን እያቦነኑ ይገኛሉ። በባለፈው ጊዜ እኔ ራሴው መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ ተነፋፍሼ ነበር ከዛሬዎቹ አለን ባይ ምንጮቼ ያገኘሁትን ይዤ ።

የሆኖ ሆኖ በየእስር ቤቱ ስለታሰሩብን የፖለቲካ መሪዎቻችን ጋዜጠኞቻችን እና የሃይማኖት ምሁራን መጨነቅ እና ስለመጪው ትግል ሰፋ ያለ ስራ መስራት ይገባናል ። ሻእቢያ ይህን ሰሞን በኤርትራ የተነሳበትን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በሌላው ዘንድ አትኩሮት እንዳያገኝ ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎን የመንግስቱ ሃይለማርያምን መሞት ሊያረዳን ይፈልጋል። ወይ ሻእቢያ እና ወያኔ ለማደናበር ማን ብሏቸው።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር ሆኖ የመጀመሪያው
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሕንፃ ‹‹አፍሪካ
አዳራሽ›› በሚል ስያሜ በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ
ሥላሴና በወቅቱ ሹማምንት ይፋ ከተደረገ ከ56 ዓመታት በኋላ
20ኛውን ሕንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና
የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን መረቁ፡፡ አዲስ አበባ በተመድ
ተቋማት እንቅስቃሴ፣ ከኒውዮርክና ከጄኔቫ በመቀጠል ሦስተኛዋ
ከተማ ለመሆን መብቃቷን ባን ኪ ሙን ገለጹ፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት በቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር መለስ ዜናዊ
የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው አዲሱ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን
ሕንፃ ለተመድ ልዩ ልዩ ተቋማት አገልግሎት የሚውል መሆኑን
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ
ተናግረዋል፡፡
ሕንፃውን በትናትናው ዕለት በይፋ ያስመረቁት ጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለ ማርያም እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ከ50
ዓመታት በፊት የመጀመሪያውንና የአፍሪካ አዳራሽ ተብሎ
የተሰየመውን ሕንፃ ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አገልግሎት
እንዲውል በስጦታ አበርክታለች፡፡ በ1951 ዓ.ም. የአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲመሠረት፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ
ሁኔታዎች ለአፍሪካ ኮምጫጫ ነበሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
የአፍሪካ ሕዝቦች ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት
የሚታገሉበት ጊዜ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ በውጭ የሚኖሩ
የአፍሪካ ልጆችም ለአኅጉሪቱ ነፃ መውጣት፣ ለሕዝቦች
እኩልነትና ክብር ሲታገሉ በነበረበት ወቅት ነበር የአፍሪካ
ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዕውን የሆነው፡፡
ዕድምተኛውን ፈገግ በማሰኘት ንግግራቸውን የጀመሩት የተመድ
ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ በዓለም ላይ
ደጋግመው ከጎበኟቸው ከተሞች አንደኛ ሆና እንደምትገኝ
በማስታወስ ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር
ኃይለ ማርያምን የኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር በማለት
በስህተት መጥቀሳቸው የታዳሚውን ፈገግታ ያጎረፈባቸው ባን
ኪ ሙን፣ ይቅርታ ጠይቀው የስም አጠራራቸውን በማስተካከል
ንግግራቸውን ቀጥለዋል፡፡
አዲሱ ሕንፃ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን
ሒሮሺማ ከተማ ላይ ከተጣለው የአውቶሚክ ቦምብ የተረፉ
ዛፎች መጥተው እንደተተከሉበት አስታውሰዋል፡፡ ሕንፃውን
አምስት የተባበሩት መንግሥታት መሥሪያ ቤቶች እንደሚጋሩት
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ
ተናግረዋል፡፡
ሕንፃውን የገነባው አገር በቀሉ ራማ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ባለሰባት ፎቅ የሆነውን
ዘመናዊ ሕንፃ ከኒውዮርክ በሚሰጠው ትዕዛዝና ቁጥጥር
እየታገዘ መገንባቱንና አረንጓዴ የግንባታ ይዘት ተብሎ
በሚጠቀሰው ቴክኖሎጂ መገንባቱን የኩባንያው ማኔጂንግ
ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ተድላ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡
ለሕንፃው ግንባታ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣
በ1800 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እዚያው በአፍሪካ ኢኮኖሚክ
ኮሚሽን ቅጥረ ግቢ ውስጥ የተገነባ ነው፡፡
የሕንፃው ግንባታ በሁለት ዓመታት እንዲጠናቀቅ ታስቦ ግንታው
ቢጀመርም፣ ሦስት ዓመት ፈጅቷል፡፡ ይህም ከመጀመሪያውኑ
ከርክክብ ሒደቱ ጀምሮ የተለያዪ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ
በማስገባት ሒደት፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በማግኘትና
በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደሆነ አቶ ፍሬው ተናግረዋል፡፡
ይህም ሆኖ ሕንፃው በሶላር ኢነርጂና በኃይል ቆጣቢ
ቴክኖሎጂዎች የታገዘ መሆኑን፣ ሰዎች ሕንፃው ውስጥ ሲሆኑ
የሚበሩ፣ ሰዎች በሌሉ ጊዜ ደግሞ በራሳቸው የሚጠፉ
የመብራት ይዘቶችንም አካትቷል፡፡
ራማ ኮንስትራክሽን በሐንኪን ቢራ ፋብሪካ ግንባታ፣ በወንጂ
ስኳር ማስፋፊያ፣ በአዲስ አዳማ የፍጥት መንገድ ግንባታ ላይ
የተሳተፈ ሲሆን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት በፕሬዚዳንት ሙላቱ
ተሾመ የተመረቀውንና ቦሌ አካባቢ የሚገኘውን የኦሮሚያ ልማት
ማኅበር ሕንፃን ገንብቷል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጥቅምት 18/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ አፋኙን ስርዓት በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ አቀረበ፡፡
ImageImage
‹‹የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል›› ያለው የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ ገዥው ፓርቲ ከዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መልኩ አፋኝ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ ገልጾአል፡፡

መግለጫው ለስርዓቱ አፋኝነት በምሳሌነት ካነሳቸው መካከል በአለፈው ክረምት ወራት ጀምሮ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠው የግዳጅ ስልጠና የሚገኝበት ሲሆን በስልጠናው ስነ ምግባር በጎደለው መልኩ የጥላቻ ዘመቻ በማካሄድ የሃሳብ ልዩነትን የማስተናገድ ፍላጎቱ ሙሉ ለሙሉ እንደተዳፈነ ያሳየ ነው ብሎታል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ስልጠናዎች እጅግ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆየ መሆኑንና ከጅማሬውም ተቃውሞውን በይፋ መግለጹንም መግለጫው አውስቷል፡፡
ፓርቲው በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የማሳደድ እርምጃ፣ በነጻው ፕሬስ ላይ የተፈጸመው አፈና የስርዓቱን መበስበስ እና አፋኝ አምባገነንነትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀጠል መምረጡን ግልጽ አመላካች ነው ብሏል፡፡

‹‹እጅግ የከፋውና እየተባባሰ የመጣው ከፍተኛ አደጋ ያዘለ ችግር ያለው አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ እያነሱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀይል ለመግዛት ቆርጦ መነሳቱ ነው›› ያለው መግለጫው በተለይ በኦጋዴን በርካታ ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ህይወታቸው መቀጠፉ ሳያንስ ሬሳቸው እንኳን ክብር በሌለው ሁኔታ መሬት ለመሬት እየተጓተተ ባደባባይ ሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አውስቷል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላም የህወሓት ሰዎች መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀራመታቸውን የተቃወሙ በርካታ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ሁነት ሀገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እያመራች ለመሆኑ አመላካች ነው ሲል ገልጾአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን በደል በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው ‹‹የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት መላው የሀገሪቱ ህዝብ፣ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ለሀገር ተቆርቋሪ ተቋማት እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ስር ሆናችሁ ለውጥን የምትሹ ወገኖች ሀገራችንን ወደ አደጋ እየወሰዳት ያለውን አፋኝ ስርዓት በቻላችሁት ሁሉ በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንድትሆኑ›› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር፣ ኖቬምበር 17 ቀን 1996 ነበር። በሰርቢያ (የቀድሞ ዩጎስላቪያ) ፣ የክልል ምርጫ ይደረጋል። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ SPO ፣ በቬስና ፔሲች የሚመራዉ GSS እና ሌሎች ድርጅቶች በአንድ ላይ ሆነው አብላጫ ድምጽ ያገኛሉ። ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ አምባገነን ባለስልጣናት፣ እነ ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አጭበረበሩ። ከኖቬምበር 17 1996 እስከ ፌቡሩያሪ 11 1997 ድረስ፣ «ያጄድኖ» የሚል፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች በስፋት ተደረጉ። ባለስልጣናቱ፣ የሕዝቡ ሰላማዊ ተቃዉሞ አይሎ መምጣቱን ሲያዩ አፈገፈጉ። የተቃዋሚዎች ስብስብ በክልል ምርጫዉ ያገኙትን ምርጫ፣ ተቀበሉ። ሊበራል ዴሞክራቱ ዞራን ጂንጂች የአገሪቷ መዲና የቤል ግሬድ ከንቲባ ሆኑ።

ብዙም አልቆየም፣ በተቃዋሚዎች መካከል ችግር መታየት ጀመረ። በቩክ ድራስኮቪች የሚመራዉ ፓርቲና በዞራን ጂንጂች በሚመራዉ ፓርቲ መካከል ልዩነቶች ተፈጠሩ። መካረር መጣ። የሕዝብን ጥያቄ አንግቦ በጋራ መቆም ተሳናቸው። በአደባባይ መወጋገዝ ጀመሩ። በአመቱ አገራዊ የፕሬዘዳንት ምርጫ ሲደረግ የሚሎሶቪች የሶሻሊስት ፓርቲ በቀላሉ ስልጣኑን ጨበጠ። የተለፋበት፣ የተደከመበት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከሸፈ። አምባገነኖች አሸነፉ። በሕዝብ ትግል የተገኙ ዉጤት እንደገና ተቀለበሱ። ዞራን ጂንጂችም ከናካቴዉ ከተመረጡበት የቤልግሬድ ከንቲባነት ተነሱ።

በ1998 በየክልሉ ተማሪዎች «ኦትፖር» ( በሰርቢያን ቋንቋ እምቢተኝነት) በሚል ስም ከታች ወደ ላይ የሆነ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የተከፋፈሉ የፖለቲካ ደርጅቶች በአንድ ላይ እንደገና ተሰባሰቡ። ካለፉት ስህተቶች በመማር፣ ፍጹም ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለሚቀጥለው ምርጫ መዘጋጀት ጀመሩ። ከፍተኛ ጫና እየተደረገም ዝግጅቱ ተጧጧፈ። የገዥዉ ፓርቲ ደጋፊዎችን የመሳብ ሥራ በስፋት ተሰራ። በዚህም ምክንያት በርካታ የገዢዉ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተቃዋሚዎችን መቀላቀል ጀመሩ። ኢቫን ስታምቦሊች ፣ የሚሎሶቪች አጋር የነበሩ ፖለቲከኛ ፣ ተቃዋሚዎች በመቀላቀላቸውም በሚሎሶቪሽ የደህንነት ሰራተኞች ታፍነው ተገደሉ።

ሴፕቴምበር 2000 ዓ.ም ምርጫ ተደረገ። የሚሎሶቪች ምርጫ ቦርድ፣ አሁንም የተጭበረበረ የምርጫ ዉጤት ይፋ አደረገ። ያንን አስከትሎ ኦክቶቦር 2000 ዓ.ም ፣ ትልቅ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። ምርጫ ቦርድ የምርጫዉን ዉጤት ወደ ነበረበት እንዲመልስ ተገደደ። የተቃዋሚዎች እጩ የሆኑት ኮስቶኒሳ እንዳሸነፉ ተገለጸ። የሚሎሶቪች ስልጣን ፍጻሜ ሆነ። የሰርቢያ ሕዝብ የማይቀለበስ ድል ተቀዳጀ።

ይሄንን ያለ ምክንያት አይደለም ያመጣሁት። በሰርቢያ፣ በመጀመሪያዉ ምርጫ የተከሰተው፣ በኢትዮጵያም በምርጫ ዘጠና ሰባት ከተከሰተው ብዙ የሚለይ አይደለም። ያኔ በቅንጅት ጊዜ የሕዝብ ጉልበት አያሎ የወጣበት ወቅት ነበር። ነገር ግን በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠሩ ልዩነቶች፣ በቀላሉ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ለመቆየት ቻለ። (በገዢው ፓርቲ የደረሰው ወከባ፣ ግድያ፣ እሥር፣ እንግልትን ጫና ቢኖርም፣ በዋናነት የተቃዋሚዎች ችግር ነው አገዛዙን ያቆየው ብዬ ነዉ የማምነው)

ሰርቦች ጠመንጃ አላነሱም። ሰርቦች ለዉጥ ማምጣት አይቻልም ብለው አላወጁም። ሰርቦች ተስፋ አልቆረጡም። እኛ ኢትዮጵያዉያን ግን ተስፋ ቆረጥን። ፎጣችንን መሬት ላይ ጥለን፣ አምባገነንነትን አሜን ብሎ የመቀበል አዝማሚያ አሳየን። «ተቃዋሚዎች አይረቡም። ያኔ ደግፈናቸው ጉድ አላደረጉንም እንዴ ? አርፎ መቀመጥ ይሻላል፣ ሰላማዊ ትግል አይሰራም ….» የሚሉ ጨለምተኛና የሽንፈት አባባሎችን ማሰማት ጀመርን።
የገዢዉ ፓርቲ ሰዎችም፣ ስልጣን ላይ ለመቆት የሚያስችላቸው፣ ይሄዉ የተቃዋሚዎች መከፋፈልና የሕዝቡም ተስፋ መቁረጥ ስለነበረ፣ በሚቆጣጠሯቸው ሜዲያዎች፣ ሕዝቡ በተቃዋሚዎች ላይ የበለጠ ተስፋ እንዲቆርጥ፣ ከፍተኛና ሲስቴማቲክ፣ ተቃዋሚዎች የማጥላላትን የማሳነስ ዘመቻቸዉን አፋፋሙ። ጠንካራ የሚሏቸውን የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያለ ርህራሄ አሰሩ። ብርቱካን ሚደቅሳን አሰቃይተውና ሰባብረው (ለስድስት ወራት ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር ጨለማ ቤት ዉስጥ እንዳስቀመጧት) ለስደት ዳረጓት። «እነርሱን ያየህ ተቀጣ» በሚል፣ በአንዱዋለም አራጌ፣ በእስክንደር ነጋ፣ በርዪት አለሙ፣ በዉብሸት ታዬ፣ በበቀለ ገርባ፣ በአብርሃ ደስታ፣ በሃብታሙ አያሌው፣ በዳነል ሺበሺ፣ በየሺዋስ አሰፋ፣ በተመሰገን ደሳለኝ፣ በዞን ዘጠኞች እንዲሁም በሌሎች ..ሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ፣ በተራ የዉሸት ሽብር ክስ፣ ኢፍትሃዊነትና ኢሰብአዊነት የተሞላበት ግፍ መፈጸማቸዉን ቀጠሉ። በሕዝቡ አይምሮ ዉስጥ፣ እነርሱን ማንም ሊነካቸው የማይችሉ፣ ግዙፎች (ኢንቪሲብል) እንደሆኑ ለመሳል መሞከርና፣ ሕዝቡ እርስ በርስ ተፈራርቶ እንዳይደራጅ፣ እንዳይነጋገር፣ እንዳይተማመን፣ በዘር፣ በኃይማኖት በጥቅም እንዲከፋፈል፣ ማድረጉን ተያያዙት።

ነገር ግን ኢትዮጵያዉያን መንቃት ያለብን ይመስለኛል። ከሰርቦች መማር ያለብን ይመስለኛል። አምባገነኖች ኃይለኛ የሆኑ ይመስላሉ እንጂ ሁልጊዜ ባዶ መሆናቸዉን መረዳት አለብን። ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሕዝብ ድጋፍ የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀ፣ ለሕዝብና ለዜጎች ከበሬታ የማያሳይ፣ ዜጎችን ሽብርተኞች እያለ የሚያሸብር፣ የበሰበሰ ድርጅት እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነዉ።

እንግዲህ «ትላንት ወድቀናል ብለን፣ የትናንቱ ጠባሳችንን እያየን ወደፊት ከመራመድ መቆጠብ የለብንም» እላለሁ። ከስህተቶቻችን ተምረን፣ ያለፈው ታሪካችን በአይምሯችን እየፈጠረ ካለው ጎታች ጫና ተላቀን፣ ይሄንን ዘረኛና አምባገነን ስርዓት ለመቀየር በቁርጠኝነት መነሳት የግድ ነዉ። ቁልፉ በእጃችን ነዉ። በርግጥ ለዉጥ ማምጣት እንችላለን። ጥያቄው «ፍላጎቱ አለን ወይ?» የሚል ነዉ።

እያንዳንዳች ወደ ራሳችን እንመልከት። እራሳችንን እንጠይቅ። «እስከመቼ ነዉ፣ በአገራችን እንደ ባይተዋር ፈርተን እና አንገታችንን ደፍተን የምንቀመጠው ?» ማለት እንጀመር። በየወረዳችን፣ በየአካባቢያችን፣ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶችን እንቀላቀል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ጠንካራና አገር ሰፊ የኢትዮጵያዊትነትና የሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምድ ድርጅት ነዉ። በመቀሌ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ አዳማ ፣ አሶሶ …በአገርቷ ክፍሎች ሁሉ ብትሄዱ አንድነት በዚያ አለ። አንድነትን እንቀላቀል። አንድነትን እንደግፍ። የሰማያዊ ፓርቲ ፣ መኢአድ፣ ትብብር ..ሁሉም በፊናቸው የሕዝብን ጥያቄ እያሰተጋቡ ነው። እንቀላቀላቸው። እንደግፋቸው። ልዩነቶቻቸውንም አጣበው ፣ የበለጠ ኃይልና ጉልበት ኖሯቸው ሰላማዊ፣ የኢትዮጵያዊነት የሰለጠነን የፖለቲካ ትግል ይመሩ ዘንድ፣ እንዲሰባሰቡ፣ እንዲዋሃዱ እናበረታታቸው።

ለተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪውን አቅርቧል።
ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት የተቃውሞ ሰልፉን ቀን ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀቅ መኢአድ በፋሽሽቱ ወያኔ በጋምቤላ በጉራፈርዳ እና በሱማሌ ክልል እየተካሄደ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል በጋራ ለማስቆም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሳተፍበት ተከታታይ የተቃዉሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይደረጋል፡፡ ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ።

በዉጭም በሃገር ዉስጥም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ከጎናችን በመቆም ይህን ዘረኛ ስርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በድሞክራሳዊ ስርዓት እንቀይረዉ፡፡ ያለው መኢአድ አስፈላጊዉን ዝግጅት ሁሉ አጠናቀናል፡፡ ሲል ለተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪውን አቅርቧል።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image
አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፍቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ
አቶ በላይ ፍቃዱ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጡ

Image
የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ የተሰበሰበ ሲሆን በስብሰባውም ላይ በፕሬዚዳንቱ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከውስጥና ከውጭ በተፈጠሩ አንዳንድ የማያሰሩ ችግሮች፣ ካለባቸው የሥራ ጫና እና ፓርቲው ወደፊት አንድነቱን ጠብቆ ለ2007 ምርጫ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ በማሰብ በራሳቸው ሙሉ ፍቃድ ከፕሬዚዳንትነታቸው በመልቀቅ ለብሔራዊ ም/ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አሳውቀዋል፡፡
ብሔራዊ ም/ቤቱ የኢ/ር ግዛቸው የሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ አካሄድ እጅግ ከፍተኛ በሆነ አክብሮት በመመልከትና በአገር ውስጥ በተቃውሞው ጎራ ለሚንቀሳቀሱና ለራሱ ለገዢው ፓርቲም ጭምር አስተማሪ የሆነ እርምጃ በመውሰዳቸው አክብሮትን ቸሯቸዋል፡፡
በቀጣይም የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በሚፈቅደው መሰረት በፕሬዚዳንትነት የሚመሩ እጩዎችን በማቅረብ ለማስመረጥ አምስት አባላት በአስመራጭ ኮሚቴነት ተሰይመዋል፡፡
Image
ራሳቸውን ለፕሬዚደንትነት በእጩነት ያቀረቡት
1ኛ. አቶ በላይ ፈቃዱ
2ኛ. አቶ ደረጀ ኃይሉ
3ኛ. አቶ ትዕግስቱ አወሉ ሲሆኑ እነዚህ እጩዎች ራሳቸውን ተራ በተራ ካስተዋወቁ በኋላ የብሔራዊ ም/ቤቱ አባላት
በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ለሚፈልጉት ዕጩ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም በተደረገው የድምፅ ቆጠራ አቶ በላይ ፍቃዱ ከፍተኛ ድምፅ በማማምጣት አንድነት ፓርቲን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመርጠው ቃለ መሃላ ፈፅሟል፡፡
Image
ስብሰባው እጅግ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መግባባት ተጠናቋል ሲሉ የአንድነት ፓርቲ ሴክሬታሪያት ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡

ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።

የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።

አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ? ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤ ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝቡ መብቱን እንዲያውቅና መብቱንም እንዲያስከብር ብዙ ሰርቷል-ፕሬሱ። ሙስናን አጋልጧል፣ እንደ እንባ ጠባቂም እየሆነ የህዝብን በደልም ይፋ አድርጓል። ይህን የተቀደሰ ተግባር ማከናወን እንደወንጀል፤ ጠንከር ሲል ደግሞ እንደ ሽብርተኝነት የሚቆጠርበት ሃገር ሆናለች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ።

መብትን ማወቅ እና ማሳወቅ፤ ‘ህዝብ ለጦርነት እንዲነሳ ማድረግ፤ ወይንም በስራዓቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ነው’ ተብሎ ከተተረጎመ ደግሞ ጋዜጠኛን በአሸባሪነት መፈረጁ ብዙ ሊደንቀን አይገባም።

ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት-አመታት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በቁጥር አንደኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሃገር ናት። አሁን ይህንን ደረጃዋን ለቃለች። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑን ተከትሎ ከመጡት ለውጦች አንደኛው መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የአንደኝነት ደረጃዋን ያጣችው ታዲያ ትራንስፎርሜሽኑ ይዞት በመጣው መሻሻል አይደለም። ነጻ ፕሬሱ ከሃገሪቱ እንዲጠፋ በተደረገ ሁለገብ ጦርነት እንጂ። አብዛኛው ጋዜጠኛ ተሰድዷል፣ ጥቂቶቹ ታስረዋል፣ አንዳንዶቹም አቅማቸው ተሟጦ አልቆ፤ ዝም ብለው እንዲቀመጡ ተደርገዋል። ለነጋሪ የተረፉትንም እስከዛሬዋ እለት ድረስ እያሳደዷቸው ይገኛሉ።

ከጅምሩ በፕሬሱ ላይ የተከፈተው የገዥው ፓርቲ ውግያ ቀላል አልነበረም። ፕሬሱ ግን እለት ተዕለት የሚያርፍበትን የአንባገነኖች ጡጫ ሁሉ ችሎ ብዙ ተጉዟል። እየተንገዳገደ፤ እየወደቀና እየተነሳ የህዝቡን የህሊና ንቃት እንዲሰፋ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዲዳብር ነጻው ፕሬስ ተግቶ ሰርቷል። የህትመት ዋጋ እስከ 500% እንዲጨምር ቢደረግም ፕሬሱ አልቆመም ነበር። ጋዜጠኞች እንደጥጃ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እየተሰቃዩም ስራቸውን ላለማቋረጥ መትጋታቸውን አላቆሙም። በካድሬ ዳኞች ፍርደ-ገምድል ፍትህ ሲሰጣቸው፤ ያለ አግባብ በእስርና በገንዘብ ሲቀጡም ሰራቸውን አላቋረጡም…

የአሜሪካው ፍሪደም ሃውስ በተከታታይ ባወጣቸው ዘገባዎች ኢትዮጵያን ፕሬስ (Status: NOT FREE) “ነጻ ያልሆነች” ሃገር ሲል ፈርጇል። የፕሬስ አዋጁንም ፍጹም አፋኝ ሲል ይከሳል። የፈረንሳዩ ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ፣ የኒውዮርኩ ሲ.ፒ.ጄ. እና የብራስልሱ አይ.ኤፍ.ጄ. በሽብር ክስ የተያዙ የጋዜጠኖችን ሰነድ እያከታተሉ አሳፋሪነቱን ቢገልጹም አፍ እንጂ ጆሮ ከሌለው ስርዓት ያገኙት የስድብ ምላሽ ብቻ ነው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋችም አፈናውን ይፋ ማድረጉን ተያይዘውታል። ከገዥው ፓርቲ የሚያገኙት ምላሽ “የኒዮ ሊበራል” አቀንቃኞች የሚል ስድብ እና ዛቻ ብቻ ነው።

ከምርጫ 97 ነኋላ ግን የህወሃት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን፤ ጫን ያለ ነገር ይዞ ብቅ አለ።

ሽብርተኝነት!

ከዚህ በኋላ ጋዜጠኛ በህገ-መንግስት ሳይሆን፤ ህጉን በሚጻረረው አዋጅ መዳኘት እንዳለበት ተነገረ። ስርዓቱም በባሩድ ሳይሆን ይልቁንም በብእር ጫፍ እንደሚሸበር አረጋገጠ።

ይህ የሽብርተኝነት አዋጅ ቃል በቃል የተቀዳው ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ መንግስታት ሰነድ መሆኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ድንቅ ነው። ሰውየው ግን ምን እየተናገሩ እንደሆን የሚያውቁት አይመስልም። በዚህች በሙት መንፈስ የምትመራ ሃገር ሌላም ብዙ እንግዳ ነገር እንሰማለን። የቡሽ አስተዳደር ከቶኒ ብሌየር ጋር አልቃይዳ የተባለውን አደገኛ ሽብርተኛ ለማጥፋት የነደፉት ይህ ሰነድ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን ለማጥፋት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ነው የሚነግሩን። የፈረንጆቹ ሽብርተኝነት (terrorism) ሲተረጎም፤ “በሃይማኖት ወይንም በርዕዮተአለም ጥላ ስር ተደራጅቶ አመጽን የማድረግ ተግባር” እንደሆነ ይነግረገናል።

በሽብርተኝነት ተወንጅለው በየእስር ቤቱ የተጣሉት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ የትኛውን ርዕዮተ-አለም ወይንም ሃይማኖት ተንተርሰው አመጽ እንደፈጠሩ፣ የትኛውን አውሮፕላን እንዳስጠለፉ፣ የትኛውን ህንጻ እንዳፈረሱ፣ የትኛውን ንጹህ ዜጋ እንደገደሉ አልተነገረንም።

እርግጥ ነው። የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እየተቹ ይጽፋሉ። ትችቱ ታድያ ለውጡ ላይ አይደለም። የለውጡ አቅጣጫ ላይ እንጂ። አቅጣጫው ትክክለኛ መስመር መያዝ እና አለመያዙን መተቸት “ወንጀል ነው” ሲባል ለቀረው አለም አዲስ ነገር ሊሆን ይችላል። ከዚያ የባሰም አለ። ገዢውን ፓርቲ መተቸት እና ስለ ለውጥ አስፈላጊነት መጻፍ በሽብርተኛነት ያስከሰሰ ወንጀል ሆኖ ሰማን። አስቂኙ ነገር፤ አዋጁ ለኦሳማ ቢን ላደን ሽብር በምእራባውያን ሀገሮች የረቀቀ የጸረ-ሽብር ህግ መሆኑ ነው።

ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ሲፈረጁ ነው ነጻው ፕሬስ በኢትዮጵያ አፈር የለበሰው። ይህ የመጨረሻ ጥይታቸው መሆኑ ነው። አለማቀፍ የጋዜጠኞች ተሟጋች ተቋማት ሳይቀሩ ተስፋ የቆረጡ እስኪመስል ድረድ በዘንድሮ አመታዊ ዘገባቸው የኢትዮጵያን ጉዳይ ችላ ብለውታል። እነዚህ ተቋማት በየአመቱ ስለኢትዮጵያ ፕሬስ ሁኔታ የሚያወጧቸው ዘገባዎች የሚዘገንኑ ነበሩ። ወያኔን የማይማር፣ የደነዘዘ እና የማይለወጥ ስርዓት አድረገው ስላዩት ችላ ያሉት ይመስላል። ሃያ አመት የማይሰማ፣ ያሃ አመት የማይሻሻል፣ ሃያ አመት የማይማር ስርዓት… ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ሆነባቸው።

በምርጫ 97 ሰሞን በርካታ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ቃሊቲ ተወርውረው ነበር። በጉዳዩ ላይ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዲያሬክተር ከነበሩት ዶ/ር ማርቲን ሂል ጋር ስናወራ አንድ ጥያቄ አነሱልኝ።

“ለመሆኑ ሰርካለም ፋሲል ላይ ለምን እንዲህ ጨከኑባት? ” የሚል ነበር የማርቲን ጥያቄ። እኝህ ታላቅ ሰው ይህን ጥያቄ ለምን እንዳነሱልኝ አሁን ነው የተገለጠልኝ።

የሰርካለም ፋሲልን ጉዳይ ማንሳቱ የኢትዮጵያን ፕሬስ የሰቆቃ ጉዞ በከፊልም ቢሆን ይገልጸዋል።

ሰርካለምን ከባለቤትዋ እስክንድር ነጋ ጋር አፍነው ወደ ቃሊቲ ሲወስዷት ነብሰ-ጡር ነበረች። የመውለጃዋ ቀን ሲደርስም ከእስር አልለቀቅዋትም። በምጥ ስቃይ፣ ነብስ ውጭ፤ነብስ ግቢ ሁኔታ ውስጥ ሆና እንኳን አሳሪዎችዋ ርህራሄ አላሳዩዋትም ነበር። በመጨረሻ እዚያው ቃሊቲ እስር ቤጥ ናፍቆትን ተገላገለች። በዚያ የጭንቅ ወቅት የሚይዘውን እና የሚጨብጠውን ያጣ ስርዓት ምን እያደረገ እንደነበር እንኳን በውል አየውቀውም። “የመንግስት ጠላት” የሚል ታፔላ ተለጥፎለት የሚንቀሳቀስ ጋዜጠኛ፤ ሊወድቅ ከሚንገዳገድ ስርዓት ከዚህም በላይ ሊደረግበት እንደሚችል ለማስረዳት ሞከርኩ።

ነብሰ-ጡርዋ ሰርካለም የተከሰሰችው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ እና ለማፍረስ፣ ጥላቻን የምታስፋፋ፣ ጥርጣሬን የምትነዛ… ተብላ ነበር። በ “ምህረት” ከእስር እንደተፈታች ወደ ኬንያ ተሰደደች። በኋላም ሀገር ሰላም የሆነ ሲመስላት ከስደት ተመለሰች። ይህች ወጣት እትብትዋ ወደተቀበረባት ሃገርዋ ብትመለስም እንደዜጋ የመኖር ዋስትናዋ ግን በአንባገነኖች መዳፍ ስር ሆነ። በኑሮዋ እና በትዳርዋ ዙርያ ካለፈው የባሰ ችግር መጣባት። ባለቤትዋ እስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት ተከሶ በፍርደ-ገምድል ዳኛ ለአመታት ተፈረደበት። ቤት ንብረታቸውም በግፍ ተቀማ። ከዚህ በኋላ በመኖር እና ባለመኖር የሚደረግ ምርጫ ውስጥ መግባት ግድ ሆነባት። እናም ባለቤትዋን ወህኒ ቤት ጥላ ዳግም ተሰደደች። እስዋም ሆነች በሰቆቃ የተወለደ ልጅዋ በመንገድ ከመወርወራቸው በፊት ያላቸው አማራጭ ይህ ብቻ ነበር። የሚወዷት ሃገራቸውን ጥለው ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኛ ጋዜጠኞችን ተቀላቀሉ። እንደቀልድ የሚነገር ሌላም እውነታ አለ። ከ”ሽብርተኛ” ጋር በስልክም ሆነ በአካል ያወራ፣ አብሮ የታየ፣ አብሮ ሻይ የጠጣ፣ የተነካካ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ እንደሆነ አዋጁ ይደነግጋል። ሰርካለም እና ናፍቆት በእስር ያለው እስክንድር ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ሽብርተኛ ተብለው ሊወነጀሉም ይችሉ ነበር።

በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ፍርሃት ውስጥ እንዳሉ ግልጽ ነው። በጋዜጠኛ የሚናድ ሀገ-መንግስት ይዘው ስንት አመት ሊዘልቁ እንደሚችሉ ባናውቅም፤ አሁንም ጋዜጠኞችን ሲያስሩ ይህንንኑ ዘፈን ይደጋግሙታል። 99.7 በመቶ በህዝብ የተመረጠ መንግስት መራጩን ሕዝብ ከቶውንም መፍራት አልነበረበትም። ነገሩ ስላቅ ነው። ይህ ቀልዳቸው ግን የህዝቡን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት የሚመጣ ይሁን እንጂ ጉዳዪ ሌላ ነው። አንባገነኑ ናፖሊዮን ቦናፓርት ብሎታል። ከሺ ሳንጃ አንድ ጋዜጠኛ ያስፈራል። የጭቆና እና የአፈና ስርዓት ገንብቶ ለረጅም አመት የቆየ አንባገነን በታሪክ አልታየም።

የፈቀደውን መምረጥ የሚችልን ህዝብ አዲስ ዘመንን ብቻ እንዲያነብ መምከራቸው ብቻ አይደለም በሕዝብ ላይ ያላቸው ንቀት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለበቀል የሚዘረጋ እጃቸው አድርገው ነጻውን ፕሬስ ለማጥፋት ሲጠቀሙበትም እጅግ ያንገበግባል። የህግ የበላይነትን እንዲህ እያደረጉ ናዱት።

ኢሕአዴግ የፕሬስ ነጻነትን ለህዝቡ እንዳጎናጸፈ ይመጻደቃል። ይህ ስህተት ነው። መናገር፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ፣ መጻፍ፣ … ወዘተ መብት የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጸጋ እንጂ አንድ ስርዓት የሚያጎናጽፈን ጉዳይ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀው ስርዓት እነዚሁኑ መብቶች እየጨፈለቀ እነሆ ሃያ ሶስት አመታትን ዘልቋል።

ነጻ ፕሬሱን ለምእራባውያን የዲሞክራሲ ማሳያ አድርጎ እንደተጠቀመበት እርግጥ ነው። የአለም ባንክ እና ለጋሽ ሃገሮች በኢትዮጵያ የሳንሱር አዋጅ እንደጠፋ ነው የሚነገራቸው። የእርዳታና ብድር እጃቸውን የሚዘረጉልንም ከቀድሞው የተሻለ የመጻፍና የመናገር ነጻነት አለ ብለው ስለሚያምኑ ይመስላል። ግና ይህ የሳንሱር አዋጅ በአእምሮ ሳንሱር መተካቱን የምናውቀው እኛ ብቻ ነን። ሳንሱር ቢኖር ይህ ሁሉ ጋዜጠኛ ባልታሰረ፣ ባልተንከራተተ እና ባልተሰደደ ነበር።

ምርጫ መጣ! ጋዜጠኛ ይውጣ! እንዲሉ… በቅርቡ በስድስት ነጻ ፕሬስ ህትመቶች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር በተያያዘ አስራ ሁለት ጋዜጠኞች ለስደት መብቃታቸው ተዘግቧል። በጭላንጭል የነጻነት ድባብ ይንቀሳቀሱ የነበሩት፤ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አፍሮ ታይምስ እና እንቁ ጋዜጦች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ጋዜጠኞቹም በአሸባሪነት ሽፋን ተከስሰው እስከ አስራ ስድስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበይኖባቸው የነእስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙ እጣ ይደርሳቸዋል። እነዚህ ጋዜጠኞች የነበራቸው አማራጭ የሽብር አዋጁ ሰለባ መሆን አልያም አገር ለቀው መሰደድ ነው። ተሰደዱ። የስደተኛ ጋዜጠኛውን ቁጥር ወደ 210 አሳደጉት።

ውንጀላው ግን በተያዘለት መርሃ-ግብር ቀጥሏል። ሰሞኑን “ያልተገሩ ብዕሮች” በሚል ርእስ በኢቲቪ የቀረበውን “ዘጋቢ ፊልም” ያስተውሏል? በአንድ በኩል የጋዜጠኖቹ ጉዳይ በህግ የተያዘ እንደሆነ ይነግሩናል። በሌላ በኩል ደግሞ “ልማታዊ” ተዋንያን እና የስርዓቱ አጎብዳጆችን በመገናኛ ብዙሃን አቅርበው ፍርድ እንዲሰጡ ያደርጓቸዋል። በእርግጥ በመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አንድ ተጠርጣሪን በወንጀለኝነት መፈረጅ አዲስ ነገር አይደለም። የፍትህ አካሉ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ተጠርጣሪው በኢቲቪ የፖለቲካ ፍርድ ይበየንበታል። ከዚያም እንደ “ዳኛ” ልዑል አይነት የሲቪል ሰርቪስ ምርቶች ውሳኔውን ያጸኑታል።

በዚያ የኢቲቪ ቅንብር ሃይሌ ገብረስላሴም ተዋንያን ነበር። የሚናገረውም የትዬለሌ። “ትልቁ የጦር መሳርያቸው ፕሬስ ነው።… ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል… ” ይለናል ሃይሌ ገብረስላሴ። “ዘጋቢ” ፊልሙም የእነ እስክንድር ነጋን ፎቶ፣ የእነ ተመስገን ጽሁፎች ያሳየናል። የዚህ ድራማ ሌሎቹ ተዋንያን ከሙያው ጋር የተያያዝን ነን የሚሉ አድርባዮች ናቸው። ሃይሌ ግን ምን ቤት እንደሆነ ግልጽ አይደለም። በየትኛውስ እውቀቱ ነው ፍርድ ሊሰጥ የደፈረው? “አንድ ጋዜጣ የውሃ አምራች ድርጅትን እንዲዘጋ አድርጓል።” ሲል ሃይሌ በዚያ “ዘጋቢ ፊልም” ይወነጅላል። አንድ ጋዜጠኛ እውነትን ጽፎ የንግድ ድርጅትን ወይንም የመንግስት ተቋምን ማፍረስ ወይንም በተቋማቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ከቻለ እንዲያውም ጀግና ነው የሚባለው። ጋዜጠናው የሚጽፈው ውሸት ከሆነ ደግሞ ፍርዱን ለህዝቡ ለምን አይተውለትም?

አብራሃ ደስታ ሌላው በአሸባሪነት ሽፋን የተከሰሰ ጋዜጠኛ ነው። አብርሃ አሸባሪ መሆኑ የተረጋገጠው ፍርድ ቤት ሲገባ እና ሲወጣ ነው። ሲገባ በጭብጨባ ሲወጣ በጭብጨባ ተሸኝቷል። ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ኣብርሃ ጀግና! የነፃነት ታጋይ! እንወዳሃለን፤እናከብርሃለን ሲለው እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ የት ነበሩ?

ያልተገራ አንደበታቸውን በመገናኛ ብዙሃን ሲከፍቱ የነበሩት እነዚህ ተዋንያን የሚነግሩን እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። አጠቃላይ ይዘቱ በመንግስት ላይ ምንም አይነት ትችት መቅረብ የለበትም የሚል እንድምታ አለው። የህወሃትን አንባገነናዊነት መተቸት፣ የስርዓቱ ፖሊሲዎች መንካትና በባለስልጣናቱ ላይ ጥርጣሪ እንዲኖር ማድረግ… ስርዓቱን ያፈርሰዋል ነው እያሉን ያለው። ህግ አውጭው ከህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ በሌለበት ሃገር ነጻው ፕሬስ ከዚህ ውጭ ምን ይስራ ነው የሚሉት? ፕሮፓጋንዳ?

ለፕሮፓጋንዳውማ በርካታ አማራጮሽ አሉ። አዲስ ዘመን ጋዜጣም አለልን። ለ90 ሚሊዮን ህዝብ የቀረው ጋዜጣ። አዲስ ዘመን በቁጥር ስንት ሺ እንደሚታተም ባናናውቅም በኪሎ እየተሸጠ የሸቀጥ እቃ መጠቅለያ ሆነ እንጂ። ‘የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተመረቁ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ሄዱ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ተመለሱ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ 11 እጅ እንደሚያድግ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።’ …. የሚሉ ዘገባዎችን እየያዘ ከሸቀጥ እቃ መጠቅለያነት ውጭ ለሚመጻደቁለት እድገት ምንም እንዳልፈየደ እንኳ አያውቁትም።

የመገናኛ ብዙሃን አፈናው በነጻ ፕሬሱ ላይ ብቻ አልተገደበም። በኢትዮጵያ የመረጃ መረቦችም ታፍነዋል። ከሰብ ሰሃራ አፍሪካ በኢንተርኔት ይዞታ እና አገልግሎት የመጨረሻዋ ሃገር ናት። ኢንተርኔቱን የሚቆጣጠረው መንግስታዊው ቴሌኮም ስርዓቱን የሚተቹ ድረ-ገጾችን በቻይና ቴክኖሎጂ እንዲዘጉ አድርጓል። የዜጎችን ስልክ በህገወጥ ማንገድ መጥለፍ የተለመደ ተግባር ነው። እንዲሁም ስካይፕ እና ቫይበር ያሉ የቮይስ ኦቨር ስልኮች ደግሞ ፊን ፊሸር በተባለ የኮምፒዩተር ቫይረስ አማካኝነት ይጠለፋሉ። እንዲህ እያሉ በዜጎች የግል ህይወት ሳይቀር እየገቡ ቴሌን ሙሉ በሙሉ የስለላ ተቋም እንዳደረጉት የአሜሪካው ሂዩማን ራይትስ ዋች ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያን ወደ ጨለማ ዘመን እየወሰዳት ያለው ይህ የህወሃት ስርዓት የኢንተርኔት ተጠቃሚው እንዲያሽቆለቁል እየጣረ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። በተለይ የፌስቡክ አብዮትን ለመግታት ስለሚሻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማዳከሙ ላይ ጥብቅ አቋም ይዟል። መንግስት አልባዋ ሶማልያ እንኳን፣ ስድስት የቴሌፎንና ስልክ አቅራቢ ኩባንያዎች አሏት። በዚህ ቀላል ቴክኖሎጂ እንኳን ከሶማልያ በታች ሆኖ ስለ እድገት መመጻደቃቸው ሊያፍሩበት ይገባል።

እጅግ የሚያሳዝነው ይህ ስርዓት ለፈጸመው ለዚህ ሁሉ በደል ለሽልማት መብቃቱ ነው። ልማታዊው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በአርቲስቶች ስም ለሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር የወርቅ ብዕር ነበር ያበረከተላቸው። ብዕር ትልቅ ትርጉም አለው። ብእር የሚሸለም ሰው ለፕሬስ ክብር ያለው፤ ፕሬስን የሚያከብር ሰው ነው። ሰራዊት የወርቅ ብዕር እንዲሸልም አርቲስቶች አልወከሉትም ነበር። ይህንን ሲያደርግ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እስር ቤት ውስጥ ይንገላቱ ነበር። ሰራዊት ይህንን ሲያደርግ የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ጠ/ሚኒስትሩን የፕሬስ አፈና በእጅጉ ያወግዝ ነበር። እንደ ሰራዊት ያሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ሰዎች ብዙ አይደሉም። ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ሲሉ እንዲህ አይነት ስራ እየሰሩ በሰው በቁስል ላይ እንጨት ይሰድዳሉ። ታዲያ እንደነዚህ አይነቶቹ አድርባዮችም ለፕሬሱ መጥፋት ሚናቸው ቀላል አይደለም። የማያልፍ የለም። ሁሉም ያልፋል። መንግስትም እንደ አንሶላ ተጠቅልሎ ይሄዳል። ይህ ቀን አልፎም ለትዝብት ያበቃናል።

ማን ነበር “ፕሬስ የሌለው መንግስት ከሚኖረን መንግስት የሌለው ፕሬስ ቢኖረን እንመርጣለን።” ያለው? እርግጥ ነው። ያለ ፕሬስ የሚኖር ህዝብ በጨለማ ነው የሚጓዘው። ያለ ነጻ አስተሳሰብ እና ያለ ነጻ ፕሬስ፣ እድገት ይመጣል ማለት አይታሰብም። እንዲያው የህዝብን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ መመልከት ይሆናል እንጂ።

አቶ ፈቃዱ ደሪሎ ከአባቱ ከአቶ ደሪሎ ተክለማሪያምና ከናቱ ከወ/ሮ ጥሩነሽ ደረሳ መስከረም 6 ቀን 1948 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ።

አቶ ፈቃዱ በበረራ መሐንዲስነት ከ20 ዓመታት በላይ እጅግ የላቀ የሥራ ልምድ ነበረዉ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በ1964-65 ዓ/ም የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተግባረዕድ ት/ቤት ገባ። የሙያ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በሰኔ 15 ቀን 1965 ዓ/ም ዝነኛ በነበረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀጠረ። የበረራ ፈቃድ በመያዝ በቦዪንግ 707/720 እና 727/737/767 ((Boeing 707/720 b/727/737/767) ላይ አገለገለ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉስጥ በመሥራቱ ወደ ተለያዩ የአዉሮፓ፤ ኢስያ፤ ኩባና አፍሪቃ አገሮች የመዘዋወርና የመሥራት ዕድል አገኘ። ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እድሜ ልኩን እጅግ የሚወዳቸዉን ጓደኞች አተረፈለት።

በ1985 ዓ/ም ሂትሮ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ለቦዪንግ 76 ጥገና በመመደብ በሎንዶን ከተማ እስከ 1990 ዓ/ም ድረስ ሠራ። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በርክሼር ዉስጥ ላነግሌይ በሚባል ቦታ ከኖረ በኋላ በ1989 ዓ/ም ወደ ሎንዶን ከተማ ከቤተሰቡ ጋር በመዞር በምሥራቅ አክቶን ተቀመጠ። በነዚህ ዘመናት ከርሱ ጋር ያሳለፉትን ደስታ ቤተሰቦቹና ኋደኞቹ እስካሁን ያስታዉሳሉ።

ለተለያዩ ኩባኒያዎች የሠራ ሲሆን በመጨረሻ የሠራዉ ለኤየርክራፍት ሴርቪስ ኢንተርናሺናል ግሩፕ (Aircraft Service International Group) ነበር።

አቶ ፈቃዱ ከወ/ሮ አይናለም በሻህ ጋር በኢትዮጵያ ዉስጥ የተጋባዉ በ1974 ዓ/ም ነበር። በ1985 ዓ/ም ወደ ሎንዶን ከመላኩ በፊት ኑሮዉም ሥራዉም በኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ቤተሰቦቹ መጥተዉ ተቀላቀሉት።

አቶ ፈቃዱ ተወልዶ ያደገዉ ጠንካራ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሆኑት ቤተሰቦች መሃል ነዉ፤ ይሄም ለመልካም የዕድገት ደረጃና ጠንካራ አምልኮት አድርሶታል። በየዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ በሄደ ቁጥር ቤተሰቦቹንና ኋደኞቹን ከማየቱ በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀሎት ያደርስ ነበር። ጊዜዉን በደስታ የሚያሳልፈዉ ከቤተሰቦቹ ጋር እቤት ዉስጥ በመሆን ነዉ፤ ሰፖርት ፕሮግራሞችን ይመለከታል፤ የተሌቪዥን ጥያቄዎች ይከታተላል፤ የበረራ መጻሕፍትን ያነባል፤ መኪናዉን ያጥባል፤ ይጠግናል።

መልካም ባል፤ ጥሩ አባትና ቆራጥ አያት ነበረ። ቅርቡ የሆኑት የሥራ ባልደረቦቹና ቤተሰቦቹ ዝምተኛነቱንና ተቖርቋሪነቱን ይመሰክራሉ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ አቶ ፈቃዱ በሰላም በተኛበት ቦታ በ65 ዓመቱ ማክሰኞ መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህ ዐለም በሞት ተለየ፤ ሞቱም በተፈጥሮ ምክንያት መሆኑ በአጣሪዎቹ ኮሮኔሮች ተረጋግጧል።

ቤተሰቦቹም የሚከተሉት ናቸዉ፤ ባለቤቱ ወ/ሮ ዓይናለም፤ ሁለት ልጆቹ ዮናስና እዮብ፤ የልጅ ልጆቹ፤ ረዲኤት፤ አቤልና ሲሳይ ሲሆኑ 6 ወንድሞቹና እህቱ ግርማ፤ ሙሉ፤ ታምሩ፤ ታደለ፤ ብርሃኑና አክሊሉ ናቸዉ።

ቸሩ አምላካችን ነፍሱን በመንግሥተ ሰማያት ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቹና ወገኖቹ በሙሉ ጽናቱን ይስጥልን አሜን።

በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ ።
የሽዋስ አሰፋ በርሃብ አድማው ምክንያት ሰውነቱ እንደተዳከመ ባለቤቱ ገልጻለች፡፡

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘውና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ አደረገ፡፡ የሸዋስ ማክሰኞ ጱግሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከጠበቃው ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ መገናኘት ባለመቻሉና ዘመድ አዝናድ እንዲሁም የኃይማኖት አባት እንዳይጎበኘው በመከልከሉ ነው፡፡ የሽዋስ አሰፋ በባለቤቱ ብቻ ከሳምንት አንድ ቀን እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ሲሆን የርሃብ አድማ ባደረገባቸው ቀናት ባለቤቱ ምግብ ስታስገባ ለየሸዋስ ምግቡ እንደደረሰው ተደርጎ ባዶ ሳህን ሲደርሳት ቆይቷል፡፡

ባለቤቱ የበዓል ቀን ልትጎበኘው በሄደችበት ወቅት ‹‹ወጥቷል›› ተብላ የተመለሰች ሲሆን በማግስቱ ልጆቹን ይዛ ልትጠይቅ ስትሄድም ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው!›› በሚል እንዳታገኘው በመደረጓ ለ15 ቀናት ሳትጠይቀው ቆይታለች፡፡ አቶ የሽዋስ ‹‹የርሃብ አድማውን ያደረኩት ቤተሰብና ጠበቃዬ እንዳይጠይቁኝ በመከልከላቸው ነው፡፡ ለምን እንዲጠይቁኝ አይደረግም? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብ ማንም አልመጣም፡፡ ቢመጣ እንድትጠየቅ እናደርግ ነበር፡፡›› የሚል መልስ እንደሚሰጡት ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል ጠበቃው ተማም አባ ቡልጉ የሽዋስን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንቶ የተለያየ ምክንያትና መሰናክል እየፈጠሩ ሳያገናኙት እንደቀሩ ገልጾአል፡፡ ጠበቃ ተማም ‹‹ለበርካታ ቀናት አመላልሰውኛል፡፡ ለምሳሌ አንድ ቀን ረቡዕ ጠዋት ሄድኩኝ፡፡ መብትን መለመን ጥሩ ባይሆንም እንዲያገናኙኝ ብለምናቸውም ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ ከሰዓት እንድመለስ ነግረውኝ ከሰዓት ብሄድም አሁንም ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ ለቀጣይ ረቡዕ ቀጠሩኝ፡፡ አሁንም ረቡዕ ስሄድ የተለያየ ምክንያት እየፈጠሩ ሊያገናኙኝ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ‹‹ምን ታመጣለህ አናገናኝህም!›› አሉኝ፡፡ ብዙ ጥረት ባደርግም ሊያገናኙን አልቻሉም፡፡ የሚገርመው የዳንኤልና የሃብታሙ ጠበቃ የሆኑ ሌሎች ጓደኞች አሉኝ፡፡ አንድ ሰው ከአንድ ጠበቃ በላይ ሊኖረው እንደሚችል እየታወቀና እኔም ደንበኞቼን ማግኘት እንዳልችል ከልክለውኝ እነሱን ግን ‹‹እኛ የምናውቀው ተማምን ነው›› ይሏቸዋል፡፡ እኔ ስሄድ ደግሞ ደንበኞቼን እንዳላገኝ እደረጋለሁ፡፡›› ሲሉ ሁኔታውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሽዋስ ምግብ ሲገባለት ምግቡን የሚያደርሱለት አካላት መልሰው ለሚስቱ እንዲሰጧት ይነግራቸው እንደነበር የተናገረ ሲሆን የርሃብ አድማ ላይ እንደሆነ እንዳይታወቅ ምግቡን የበላ አስመስለው እቃውን ባዶ አድርገው መመለሳቸው አሳፋሪና ቅጥ ያጣ አፋኝነት መሆኑን መግለጹ ታውቋል፡፡ የሽዋስ አሰፋ በርሃብ አድማው ምክንያት ሰውነቱ እንደተዳከመ ባለቤቱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡

ቴዲ አፍሮ በሆላንድ ባቀረበው ኮንሰርት ላይ በመድረክ ያቀነቀነው አዲስ ዘፈን

http://t.co/DuDCwQKJ2N

ቀስተ ደመናው ላይ አንበሳው ከሌለ
የኢትዮጵያ ባንዲራ ትርጉሙ የታለ፥
ምድሪቱ አረንጋዴ ‘ላዩ ሰማያዊ
ተባብሮ ከሰራ ያድጋል ኢትዮጵያዊ፥
ሣባና ሰሎሞን እናትና አባቴ
አትማልዷትም ወይ ለኢትዮጵያ እናቴ፥
ምን ይላል ምኒሊክ ካሳ ቴዎድሮስ
የአንድነቱ ጎጆ በዘር ሲታመስ፥
ምን ይላል ምኒሊክ ካሳ ቴዎድሮስ
ምን ይላል ዮሐንስ ተፈሪ ቴዎድሮስ
የተዋለደ ሰው በዘር ሲታመስ ::

– የዩንቨርስቲው ስልጠና በግሩፕ እንዲደረግ ቢሞከርም ከፍተኛ አለመግባባት በመፈጠሩ ተበትኗል።
– ሽመልስ ከማል ከለገሃር ሙልሙል ጫት ቤት ተጠርቶ አለቃ ጸጋይ ፊት በመቅረብ ማስጠንቀቂያ ተሰቶታል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ለአንድ ሳምንት ያህል ሊሰጥ የታሰበው እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን የተጀመረው የወያኔ የልማታዊ ዲሞክራሲ ስልጠና ገን ክጅምሩ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ከተለያዩ መምህራን የተሰበሰቡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ገና ስልጠናው ከመጀመሩ መምህራኑ መንግስት ያለብንን ችግር እና የሃገሪቱም ሁኔታ ማገናዘብ እና መፍታት ካልቻለ የስራ ማቆም አድማ እናደርጋለን ሲሉ በጭብጫባ የታጀበ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ይህ የግዳጅ ስልጠና በተለያዩ አደራሾች የተጀመረ ሲሆን መምህራኑ እንዳሉት የውይይቱ የመግቢያ ሰነድ ተረስቶ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና በመምህራን ሕይወት ዙሪያ ከባድ የሆነ ንትርክ ተገጥሞ ለወያኔ አሰልጣኞች ከባድ ጋሬጣ ሆነው እንደነበር መምህራኑ ክላኩት መልእክት ለማወቅ ተችሏል። የመምህራኑ ስልጠና በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን ለወያኔ የእግር እሳት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።ምንሊክ ሳልሳዊ

በዛሬው እለት ጠዋት በሽመልስ ከማል ሲመራ የነበረው እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢንዱስትሪ ካምፓስ ተማሪዎች የግዳጅ ስልጠና በጩኸት ቢበተንም ሽመልስ ከማል ደንግጦ ከስብሰባ አደራሹ በመውጣት ተደብቆ የጠፋ እና ወደ ተለመደው የጫት ሱስ ተግባሩ የሄደ መሆኑን ሁኒታውን ሲከታተሉ የነበሩ እና አብረውት በአስተባባሪነት እና በተባባሪ አሰልጣኝነት የተመደቡ ካድሬዎች ጠቁመዋል። ለአለቆቹ ሪፖርት ሳያደርግ ወደ ጫት ቤት ያቀናው ሽመልስ ከማል በአስቸኳይ የስልክ ጥሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ካለው የአለቃ ጸጋይ ቢሮ ተጠርቶ በመሄድ ከስልጠናው ጋር በተያያዝ ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሲሆን ከቢሮው ሲወጣ ፊቱ ተለዋውጦ እና ደንግጦ እንደነበር አስተባባሪዎቹ እና ተባባሪ አሰልጣኞቹ ከሰጡኝ መረጃ ለማወቅ ችያለው።

የስልጠናው አስተባባሪዎች ስልጠናውን ለመቀጠል አቶ ሽመልስ ከማልን ትተውት ወደ አ አ ዩ ኢንዱስትሪ ካምፓስ ቢደርሱም ተማሪው ከተባለበት ሰአት ሁለት ሰአታት ያህል በመዘግየት ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በየግሩፑ ቢመጣም የግሩፕ ስልጠና አስተባባሪ እና አሰልጣኝ ካድሬዎች ተማሪውን በፍጹም ሊያሳምኑት ያልቻሉ ሲሆን ተማሬው አቴንዳስ ሲደረግ የታደለውን ኖትቡክ እና ቢክ እስክርቢቶ እንዳልተጠቀመበት ታውቛል።ብዚህ ስልጠና ላይ ተዋት ተማሪው በጩኸት እና በፉጨት ስለረበሸ የውሃ እና የሻይ አቅርቦት ተከልክሏል።ምንሊክ ሳልሳዊ

የከሰአት በኋላ ስልጠና በግሩፕ የተከፋፈለ ሲሆን ይህንን ያደረጉት ተማሪው በጋራ ሆኖ ተቃውሞ እንዳያሰማ እና በግሩፑ ተቃውሞ ቢኖር እንኳን በቀላሉ መቆጣጠር እንዲቻል ተማሪው ጎን ለጎን እንዳያወራ አራርቆ በማስቀመጥ
ተማሪው እርስ በ እርስ እንዳይደጋገፍ ለማድረግ ነው። አሰልጣኞቹ ካድሬዎች ስልጠናውን በተማሪው መሰላቸት በመደናበራቸው 9 ሰአት ስልጠናውን ጀምረው ወዲያው ተማሪው ጥያቄ ካለው ብለው ጥያቄ እንዲጠይቅ ሲያደርጉ ከተጠየቁ ጥያቄዎች መካከል ስልጠናው ጥቅም የለውም?፣ አላማው ምንድነው?፣የቀድሞ ስራቶችን ክፋት ብቻ ለምን ታወራላችሁ ?፣ ራሳችሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ለምን ከኋላቀር የቀድሞ ንጉሳውያን አስተዳደር ጋር ትመዝናላችሁ፡? ከናንተ በፊት መንግስታት እንጂ የሚበድሉት በህዝብ መካከል ፍቅር እና የሃይማኖት መቻቻል ነበር ይህን አምናቹሃል አሁን የት ገባ?፤ ወደ ኋላ እየተመለስን ከምናላዝን ለምን አሁን ባሉት እና ወደፊት በሚኖሩት አስቸጋሪ ፈተናዎች እና ጉዳዮች ላይ አናተኩርም ? ወዘተ የሚሉ ጥያቂዎች ቢነሱም ምላሾቻቸው የማያረኩ የተድብሰበሱ እና የሚያደናግሩ ነበሩ ። እንዲሁም በነገው እለት በነጻ ፕሬስ በጋዜጠኞች እና በመንግስት መካከል ስላለው ሁኔታ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞ ስልጠናው በተማሪው መሰላቸት እና ጉርምርምታ 9 ሰአት ጀምሮ 10.30 ተበትኗል።

ህወሓት ብአዴንም፣ ኦህዴድም፣ ኢህአዴግም ሆኖ ሁሉም የሚጠይቀውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡
አዛዡም ናዛዡም ህወሓት ነው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ከአመታት በፊት የገዥው ፓርቲ አባል ሳይሆን በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይሰራ ነበር፡፡ 1997 ዓ.ም በኋላ ግን በዚህ አቋሙ አልቀጠለም፡፡ ‹‹አንዴ ቅንጅት ሌላ ጊዜ ደግሞ ኦነግ እያሉ ስም ሲለጥፉብኝ ‹ከዚህ ሁሉ!› ብየ ኦህዴድን ተቀላቀልኩ›› ይላል ካድሬው ለነገረ ኢትዮጵያ፡፡ ከዚህ በኋላ ባሉት ጊዜያት ደመወዝና እድገት በእጥፍ ተጨምሮለታል፡፡ የትምህርት እድል ተሰጥቶታል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ኦህዴድም ሆነ ኢህአዴግ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል በቅርብ ርቀት ተገኝቶ ተከታትሏል፡፡

ካድሬው እንደሚለው ከእነ አባዱላና መሰል ፖለቲከኞች ውጭ የኦህዴድ ካድሬዎች በፓርቲያቸው እምነት የላቸውም፣ በህወሓት በደል በእጅጉ ተማርረዋል፡፡ የ‹‹ብአዴኖችም ከእኛ የሚለይ ነገር የለውም፡፡ ተመሳሳይ ነው፡፡›› ይላል ካድሬው፡፡

በበርካታ ጉዳዮች ‹‹ፓርቲዬ›› ከሚለው ኢህአዴግ እንደሚለይ ቢገልጽም በአንድ ጉዳይ ግን ይስማማማል፡፡ ‹‹ጥያቄ የሚያቀርብ ካድሬ አንድም ኦነግ አሊያም የድሮው ቅንጅት አካል የነበረ ፓርቲ ወይንም ትምክተኛ ተብሎ ስም ይሰጠዋል፡፡ ኦነግ ወይንም ‹‹ቅንጅትነት/ትምክተኝነት›› ጥያቄ ማንሳት ከሆነ የኦህዴድ ካድሬዎች ሲገለጡ ኦነጎች ናቸው፡፡ ብአዴኖቹ ደግሞ እንደዛው ቅንጅት/ትምክተኛ ናቸው ማለት ነው››፡፡ በዚህ ጉዳይ ካድሬው የድሮው ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹ኦህዴድ ሲገለጥ ኦነግ ነው!›› በሚለው ይስማማል፡፡

ካድሬው ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጸው በተለይ የብአዴንና የኦህዴድ ካድሬዎች በህወሓት ጫና ከመቼውም በላይ ተማርረዋል፡፡ ‹‹አዛዡም ናዛዡም ህወሓት ነው፡፡ ትጠይቃለህ፡፡ ስም ይሰጥሃል፡፡›› የሚለው የኦህዴድ ካድሬ፤ የኦህዴድና የብአዴን ካድሬዎችም ሆነ ባለስልጣናት ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ እንደሌላቸው ከተሞክሮው ይመሰክራል፡፡ ‹‹ብአዴንና ኦህዴድ ይጠይቃሉ፡፡ ህወሓት ይመልሳል፡፡ የብአዴንና የኦህዴድ ባለስልጣናት ካድሬዎቹ የሚጠይቋቸውን ጥያቄዎች እንኳን በራሳቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ ህወሓት ብአዴንም፣ ኦህዴድም፣ ኢህአዴግም ሆኖ ሁሉም የሚጠይቀውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡ እንዲያው እድል ተሰጥቷቸው የሁለቱ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች ቢመልሱ እንኳ የህወሓት ተራ ካድሬም ቢሆን የሆነ ነገር ያስተካክላል፡፡ ኦህዴድና ብአዴን ብቁ አለመሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርገው ነው፡፡››

ካድሬውን ‹‹ኢህአዴግን ምን የሚያሰጋው ይመስልሃል?›› በሚል ከነገረ ኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄም የመጀመሪያው ያደረገው ፓርቲው ውስጥ ያለውን ክፍፍል ነው፡፡ ‹‹አብዛኛው የኢህአዴግ ካድሬ እንደ እኔ ፓርቲው ያደርስብኛል ካለው አደጋ ለመዳን አሊያም ለገንዘብ የተቀላቀለ ነው፡፡ አያምንበትም፡፡ ሁሉም ቀን ነው የሚጠብቀው፡፡ ወደ ህዝብ ሲቀርቡ በመካከላቸው ችግር እንደሌለ ያስመስላሉ እንጅ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች በመካከላቸው ከፍተኛ ቅራኔ አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ የኦህዴድ ካድሬዎችን አስቆጥቷል፡፡ እስካሁን ይመለስላቸው አይመለስላቸው ባላውቅም በወቅቱ እነ አባዱላ ፓስፖርታቸውን እንደተቀሙ ሰምቻለሁ፡፡ ይህ አንድ ቀን የሚፈነዳ ይመስለኛል፡፡››

ሌላው ይላል ካድሬው ‹‹ህዝብ በፓርቲው እምነት እንደሌለው ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ህዝብ ገንፍሎ የሚወጣ ይመስለኛል፡፡ በእርግጥ አሁን ህዝቡ ዝምታን መርጧል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ህዝብን ለማሳመን ወይንም ለማስተማር በሄድኩበት አጋጣሚ ከዝምታው በስተጀርባ ህዝብ ለፓርቲው ጥላቻ እንዳለው ለማየት ችያለሁ፡፡ በቅርቡ በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና የተሰጣቸው ተማሪዎች ሰነዱን አቃጥለው ስለ ነጻነት ዘምረዋል፣ ፓርቲው አብጠልጥለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲደማመር አንድ ቀን ህዝብ ገንፍሎ የሚወጣ ይመስለኛል››

የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል።

ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል።

(በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል) ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።

(በፎቶው ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል)

በመሳሪያ ኃይልና በውጭ መንግሥታት ድጋፍ የስልጣን እርካብ የተቆናነጠጠው፤ በጠባብ ብሄርተኛው በህወሓት ፍጹም የበላይነት የሚመራው፤ የኢህአዴግ መንግሥት ከተመሰረተበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ደህንነትና ነጻነት፤ የዘጠና አራት ሚሊዮን ሕዝቧ ሉአላዊዊነት፤ እውነተኛ እኩልነት፤ ማህበራዊ ጥቅም፤ መሰረታዊ ትብብር፤ ነጻነትና ዲሞክራሳዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተናግተዋል፤ ተገፈዋል። በማንኛውም የዘመናዊነት መስፈርት ቢፈረጅ፤ ኢትዮጵያን ከባሰ አደጋ፤ ሕዝቧን ከከፋ ድህነት እና የእርስ በርስ ግጭት፤ ወጣቱን ትውልድ ለሁላችንም ከሚያሳፍር ስደተኛነትና ውርደት ሊያድነው የሚችለው ተተኪ የአገዛዝ ስርአት (አማራጭ) በሕግ የበላይነት፤ በእውነተኛ የኢትዮጵይያውያን እኩልነት፤ በሕዝብ ስልጣን የተመሰረተ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ብቻ ነው። ሰፊ ለም መሬት፤ ዝናብ፤ ወንዝ፤ ተስማሚ አየር፤ ከመሬት በታች ገና የማይታወቅ ሃብት ያላት አገር ለሁሉም አስተናጋጅ ለመሆን እንደምትችል አልጠራጠርም። ፍትህ-ርትእ ከሌለ ይኼን የማይገኝ ሃብት የሚጠቀሙበት የውጭ ኢንቬስተሮችና አጋር የሆኑ የውስጥ ሃብታሞች ሆነው ይቆያሉ። ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች የሚስማሙበት አንድ አበይት ጉዳይ አለ። ይኼውም ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው የሚል። ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር ግን ሁለቱም ወገኖች ዲሞክራሳዊ አሰራርን በተግባር አላሳዩም፤ ለማሳየትም የተዘጋጁ አይመስልም። አንዱ በሌላው እያመኻኘ ሃያ ሶስት ዓመታት አልፈዋል። የሚቀጥለው ምርጫ ዘጠኝ ወሮች ቀርተውታል። ሑኔታው ከቀጠለ የሚቀጥለው ምርጫ ከአሁኑ ተወስኗል ለማለት እንችላለን፤ የገዢው ፓርቲ የበላይነት ብቻ ይሆናል። መቶ በመቶ አሸነፍኩ ቢል አንገረም። የሚወዳደረው ከራሱ ጋር ይሆናል።

ገዢው ፓርቲ መከፋፈልን ወደ ሳይንስ ለውጦታል። ተቃዋሚው ይኼን ሳይንስ አልቀበም በማለት ፋንታ እርስ በርሱ መናከሱን ቀጥሎበታል። በተደጋጋሚ የሚታየው የራእይ፤ የግብ፤ የአደረጃጀትና የአመራር ደሃነት በቀላሉ አለመፈታቱ ተቃዋሚውን ፍሬ ቢስ አድርጎታል። በአገር ውስጥ ብቻ ያለው ሳይሆን በውጭም ያለው፤ በነጻነት ለመወያየትና አብሮ ለመስራት ገዢው ፓርቲ ሊቆጣጠረው የማይችለው። ቢቀበለውም ባይቀበለውም ተቃዋሚው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆኗል ለማለት ያስችላል። የምናውቀው የሃገሪቱን አስተዳደር በቋንቋ የቀየሰው አምባገነን መንግሥት ቆይታውንና የኢኮኖሚ ጥቅሙን ለማጠናከር ህዝብን እርስ በርሱ እንዲጋጭ፤ ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው እንዲናከሱ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይኼ የመከፋፈልና ስልጣንና ሃብትን የማስተማመኛ ስልት ከታወቀ፤ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ አስበው፤ ተፈላልገው፤ ተከባብረው፤ “ተናበው”፤ በዋናው ዓላማ ላይ ተስማምተው ለመስራት የገዢው ፓርቲ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም ነበር። ችግሩ ጥበባዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ የማደራጀትና የመምራት ድክመትና ክፍተት መኖሩ ነው። ስርዓቱ የራሱን መቆያ ያጠናከረውና የሚያጠናክረው የሃገሪቱን ባጀት፤ የተፈጥሮ ሃብትና ሌላ ጥሪት ለጥቂቶች አገልጋይ የሆነ ተከታታይ የብልጭልጭ እድገት በማሳየት፤ “እኔ እስካለሁ የእድገቱ ተጠቃሚዎች ትሆናላችሁ፤ እኔ ከሌለሁ፤ ትበላላችሁ” በሚል ዘዴ ነው።

ስርዓቱ የሚሰራውን ያውቃል ማለት ነው። የሚሰራውን የማያውቀው ተቃዋሚው ሆኗል። የተበታተነው ተቃዋሚ የሚለው በኢትዮጵያ እድገት የለም አይደለም። ፍትህ የለም። የአብዛኛው ሕዝብ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ታች በመሄድ ላይ ይገኛል፤ የኑሮ ውድነት የተራውን ዜጋ የመግዛት አቅም አስጊ በሆነ ደረጃ ቀንሶበታል። የወጣቱ ትውልድ እድል ተምሮ መሰደድ ሆኗል። በዘመነ ኢህአዴግ የሃገሪቱ ለም መሬትና ወንዝ ለውጭ ኢንቬስተሮች በእርካሽ ዋጋ ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ አላሙዲ ብቻ የሚያመርተው በዓመት አንድ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለሳውዲ ገበያ ይቀርባል። እንደ ካሩቱሪ ያሉ የህንድ ኢኒቨስተሮችም የጋምቤላን ለም መሬት ተረክበው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እየተነገደባት ነው። ሳውዲዎች እየተመገቡ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይራባሉ፤ አገሪቱ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለምግብ ግዢ ታወጣለች። ህይወቱ የተናጋው አብዛኛው ሕዝብ መብቱ ሰለታፈነ፤ ድምፁን ለማሰማት ስላልቻለ መከራውን ተቀብሎ ይኖራል ወዘተ የሚሉ ናቸው።

ስለሆነም፤ ተቃዋሚው የጠራ አማራጭ ለማቅረብ ነባራዊው ሁኔታ ይፈቅድለታል። የሚጎድለው የዓላማ አንድነትና የአመራር ብልሃት ነው። እርግጥ ነው፤ የገዢው ፓርቲ አቅም ከፍተኛ ነው። መንግሥትን ከተቆጣጠረ ባጀትንም እንደፈለገው ፈሰስ ለማድረግ ይችላል።

ስንቅ ብቻውን አቅም አይሆንም
የተቃዋሚው ክፍል አቅም ጠንካራ ሊሆን የሚችለው ከሕዝብ ከሚያገኘው ድጋፍ፤ ከመተባበሩ፤ ያለውን የቁሳቁስ አቅም በጋራ ከመጠቀሙ፤ በብልሃት ከመስራቱ፤ በአንድ ድምፅ ከመነሳቱ፤ ለዓላማው ጠንክሮ፤ በውስጥ አመራር ሳይበከል መስዋት ለመክፈል ፈቃደኛ ከመሆኑ ላይ ነው። በውጭ ያለው አገር ወዳድ፤ ዲሞክራትና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃ ኃይል ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ አቅምና ፍላጎት አለው። “ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ” እያለ ሲመክር ቆይቷል። ገንዘቡን፤ እውቀቱን፤ ድጋፉን ችሯል። ወደፊትም ይችራል የሚል እምነት አለኝ። ሆኖም፤ ስንቅ አቀባይነት ያለ ድርጅትና አመራር ብቃት ኢትዮጵያን አይለውጥም። ለዚህ ነው፤ ደጋፊዎች ተስፋ እየቆረጡ “ተቃዋሚ ነኝ” ማለቱን ቀልድ አታድርጉት፤ “ጩኸቱን ወደ ተግባር ለውጡት፤ በፍርሃትና በመጠላለፍ ዓለም መኖራችሁን አቁሙ፤ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሳዊ ስርአት ያለ መስዋእትነት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። የእርስ በርስ ጦርነቱን አቁሙ። በውጭ ኃይሎች ማምለኩን አቁሙ። ድርጅት አፍርሳችሁ በድርጂት መተካቱን ተውት። አትጠላለፉ። መገናኛ ብዙሃኖችን ለእርስ በርስ ጦርነት አትጠቀሙ፤ አትወነጃጀሉ፡ የራሳችሁን የውስጥ አመራር ሳታጠናክሩ ሁሉን ነገር በገዢው ፓርቲና በሌላው ላይ አታመኻኙ፤ ተቃውሞ ብቻውን የማህበራዊ ጥቅም አይኖረውም” ወዘተ፤ ወዘተ የሚሉት።

በጀ፤ ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው?
ይኼ አጭር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ስእል በተደጋጋሚ ያሳየው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትተው ለሃገሪቱ ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ደህንነት ሲባል መተባበር፤ ቢቻል መዋሃድ አለባቸው የሚለውን ባለፉት አስር አመታት በተደጋጋሚ ሁሉን በሚመለከት ያቀርብኩትን ምክርና ጥሪ ነው። ምክር እንጅ ትእዛዝ አይደለም። ማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን ከውጭ ሆኖ ትእዛዝ ለመስጠት አይችልም። ትግሉ በአገር ቤት ካልተጠናከረ፤ አገር አቀፍና አሳታፊ ካልሆነ የፈለገው ጥረት ቢደረግ ዲሞክራሳዊ መሰረት ለመጣል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው አብሮና ተሳስቦ መኖርን ነው። ቂም በቀልነትን አይፈልግም። አንዱን አምባገነን በሌላ አምባገነን መተካት አይደፈልግም። ይኼማ ከሆነ ኢህአዴግ ምን አደረገ፤ የተካው ደርግ ምን አደረገ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴስ ምን አደረጉ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የስልጣኑ፤ የመንግሥቱ፤ የመሪዎቹ ባለቤት ለመሆን ይፈልጋል። ለዚህ ብዙ መስ ዋት ከፍሏል። ስለሆነም፤ ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች በዓላማ እንድነት በመንቀሳቀስ ታሪክ የሚጠይቀውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው። ሕዝብን ካጎለመሱ ተመጣጣኝ አቅም ይኖራቸዋል። ወሳኙ ሕዝብ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ለቅንጅትና ለህብረት የሰጠው ያልተቆጠበ ድጋፍና የከፈለው መስዋእት እንዲያንሰራራ ከተፈለገ በአገር ቤትና ከአገር ውጭ የሚገኙ የፖሌቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሞያ ስብስቦች፤ ግለሰሶብችና ሌሎች ከቡድን፤ ከፓርቲ፤ ከግል ዝናና ጥቅም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂነትና ለመላው ስብጥር ሕዝቧ ደህንነት አብረው መነሳትና አምባገነኑን መንግሥት ማንበርከክ፤ ቢያንስ ለድርድር እንዲስማማ ማድረግ ይኖርብናል። ከሁሉም በላይ የተቀነባበረ የሕዝብ አመፅ አገር አቀፍና ዘላቂነት ባለው ደረጃ ከተካሄደ ገዢው ፓርቲ ለመደራደር ይገደዳል።

ይኼን ትንተና ለማዘጋጀት የተገደድኩበት ዋና ምክንያት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የለመደውን መንገድ እየተጠቀመ፤ ከመጭው ምርጫ በፊት በሰላማዊ መንገድና በሁለገብ ትግል የሚንቀሳቀሱና ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑትን ተቃዋሚዎች ሁሉ ተባብረው እንዳይሰሩ በማሰብ በመከፋፈል ላይ ይገኛል። ይኼ አዲስ ነገር አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የመኢአድና የአንድነት ውህደት ሂደት አሳዛኝና ተስፋ በሚያስቆርጥ መልክ ስኬታማ አለመሆኑ ለገዢው ፓርቲ ቆይታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ይኼ ችግር የገዢው ፓርቲ ሳይሆን የተቃዋሚው ነው። በቅርቡ የተከሰተም ሌላ የተቃዋሚውን ክፍል ከጥያቄ ውስጥ ያስገባ አከራካሪ ጉዳይ አለ።

እንደማንኛውም አገር ወዳድ በ August 28, 2014 ሶስት በውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች በዜናና በድህረገጾች ያሰራጩትን፤ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትኩረት የሰጡትን የጋራ መግለጫ በሰከነ መንገድ ተመልክቻለሁ። መግለጫው እንዲህ ይላል። “ኢትዮጵዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋእትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳችንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል። ስለሆነም፤ ወደፊት ለመዋሃድ የተሰማማነው ድርጅቶች፤

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ነን” የሚል መግለጫ ወጥቶ ሲያነጋግር ቆይቷል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ በ September 6, 2014, በኮሎኔል አለበል የሚመራው የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ማስተባበያ አውጥቶ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም” ብሏል።

በእኔ ግምትና እምነት ምንም እንኳን የጋራ ስምምነቱ በምን አጀንዳ ላይ እንደተቀረጸ ባላውቅም፤ አሰራሩ በግልፅነት፤ በሃላፊነት፤ በዲሞክራሳዊነት፤ በዘላቂነትና ሌሎችን በሚያበረታታ መንገድ የውህደቱ ድርድር እንዲካሄድ ያለኝን ተስፋና ምኞት ለማቅረብ እፈልጋለሁ። በተመሳሳይ፤ በአንድነትና በመኢአድም በውስጥና በመካከላቸው መካከል የተከሰቱ ልዩነቶችም በውይይት፤ በግልፅነት፤ በሃቀኝነት፤ በብልሃት፤ በዲሞክራሳዊ ስልት እንዲፈቱ የታሪክ አደራ እሰነዝራለሁ። ዛሬ ለፍትህ- ርትእ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ አገርን ከአደጋ ለመከካለክ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ ኃይሎች “ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ እሴፓ፤ ፓሪስ አንድ፤ ፓሪስ ሁለት፤ ኢዲዩ፤ እዴፓ፤ ቅንጅት፤ ህብረት፤ ታንድ፤ ኦነግ፤ መድረክ፤ አሬና፤ ግንቦት 7፤ አርበኞች፤ የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች፤ አንድነት፤ ሰማያዊ፤ መኢአድ፤ አንድ ሁለትና ሶስት ወዘተ የሚሉበትና እርስ በርስ የሚወቃቀሱበት ዘመን አልፏል ለማለት የሚያስችሉ ብዙ ክስተቶች አሉ። የኼን ስል፤ ሁላችሁም ተዋሃዱ ማለቴ አይደለም፤ ብዙ ተሞክሮ አለተቻለም። ዲሞክራሳዊ ለውጥ ከተፈለገ ለመተባበርና ለመደጋገፍ ይቻላል። ይኼም ፈቃደኛነት ካለ ብቻ ነው። “አገር ትሸጥ ሲባል ስንት ታወጣለች” የሚል አዲስ ባህልና አዲስ ባለሃብት መደብ መፈጠሩን እያየን እርስ በርሳችን የምንናከስ ከሆነ ከትግሉ ዓለም መውጣት አለብን። አዲሱ ትውልድ ለራሱ ህይወት ሲል ይታገልበት ለማለት መድፈር አለብን። በምትካችን አዲስ ትውልድና አዲስ ዓመራር እየታገለ አመራሩን እንዲይዝ ቦታውን እንልቀቅለት። መሰናክል አንሁን። መቀበል ያለብን፤ እኛ ራሳችን ለመምከር ወይንም ለመመከር ስለማንፈልግ ሌሎች፤ በተለይ ፈረንጆች ለእኛ ተናጋሪ ሆነዋል። ለምሳሌ፤ ለኢትዮጵያ የሚለግሱ መንግሥታትና ድርጅቶች ደጋግመው የሚነግሩን በአንድ ላይ፤ በአንድ ድምፅ ለመናገርና አግባብ ያለው አማራጭ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማቅረብ እስካልቻላችሁ ድረስ ማንም አያዳምጣችሁም ነው። ሃቁ፤ ያለውን መንግሥት እንደግፋለን ነው የሚሉት። የተበታተነ ተቃዋሚ ውጤቱ ይኼው ነው። አንፈረድባቸው። የሚያኮራ ታሪክ እያለን የራሳችን ህብረተሰብ ለመታገድ ካልቻልን ሌሎች ያዙብናል። እያዘዙብን ነው። ከዚህ የበለጠ የጠነከረ ምክር መጠበቅ ራስን ማታለል ነው።

ለማጠቃለ፤ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች እንዲያስቡበት የምመኘውና አደራ የምለው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እድሜውን ለማራዘም ለሚያደርገው ያልተቆጠበ ሴራና ሰለባ ምርኮኛ መሆን የለባችሁም/የለብነም የሚል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውና የሚመኘው የእርስ በርስ መጠላለፍና ለስልጣን መሻማትን አይደለም፤ አብሮና ተባብሮ አምባገነኑን ስርዓት በዲሞክራሳዊ ስርዓት መተካትና ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው የእድገት በርና መሰረት እንዲከፈትለት ነው። ስለሆነም፤ የተቃዋሚዎች ሙሉ እምነት በኢትዮጵያ ሕዝብ አቅም ላይ ይሁን አላለሁ።

ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ ከ10 ዓመት በላይ የኖረ፣ የራሱን የተደላደለ ኑሮ ይመራ የነበረ፣ ነገር ግን በነ አንዳርጋቸውና ብርሃኑ እንደሌሎች ጓደኞቹ ለአመራር ስልጠና በኤርትራ በኩል ወደ አውሮፓ ትላካላችሁ በሚልና ሌላም ሌላም የእውሸት ክምር ተታሎ ወደ ኤርትራ የሄደ፤ ልክ ኤርትራ እንደገቡ የውሸቱን ክምር ለማወቅ ጊዜ አልወሰደበትም። ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በመሆን ከብርሃኑ ነጋ ጋር ባደረገው የስካይፕ ውይይት ብርሃኑ እራሱን ነጻ ለማድረግ እኔ የማውቀው ነገር የለም፤ አንዳርጋቸው ብቻ ነው የሚያውቀው በሚለው አነጋገሩ ድርጅቱ ባለቤት የሌለውና የደረሰበትንም የውድቀት ደረጃ ተረድቶ ለእስር ከመዳረጉ በፊት አስቀድሞ አካሄዳቸውን ማየት የቻለና ሁኔታዎችን አመቻችቶ የወጣ ወጣት ነው። የህዝባዊ ሃይል ተብየውም የምልመላ ክፍል ሃላፊ የነበረ ሲሆን በአባላት ለህዝባዊ ሐይሉ ምክትል አዛዥነትም ተመርጦ ነበር። ቴዎድሮስ ከኤርትራ እንደወጣ ባለፈው አመት “በኛ ይብቃ” በሚል ርእስ ህዝብን ያስደመመ ጽሁፍ በመጻፍ እኩይ ምግባራቸውን ያጋለጠ ፋና ወጊ ወንድማችን ነው። ቴዎድሮስን ተደብቆ ከሚኖርበት አግኝተን አነጋግረነዋል ውይይቱን ተከታተሉ፤

loading … [audio]

Or click here: http://www.ginbot7d.org/audio/TewdrosMinilik.mp3

]በአሉ ግርማና አስፋው ዳምጤ

[email protected]

ባለፉት ወራት የአገር ቤቶቹንም ሆነ ውጪ ያሉትን የሚዲያ አውታሮች በተለያየ መልክ ያነጋገረው የበአሉ ግርማ አሟሟት ላለፉት 30 አመታት ሲያነታርክ ቆይቶአል ። እስከደርግ መጨረሻ ድረስ በድብቅ ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ በግልፅ አነታርኳል ። ይህም የሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው ። አንደኛው ምክንያት በአሉ ግርማ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ስነ-ፅሁፍ አቻ የማይገኝለት ደራሲ በመሆኑና በብዙ አንባቢዎቹ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ ያለው መሆኑ ሲሆን ፣ ሁለተኛው ደግሞ ፍትህንና እውነትን ፈላጊ ተስፋ የማይቆርጥ ቤተሰብ ስላለው ነው ። በተለይ ደግሞ ባለቤቱ ወ/ሮ አልማዝ አበራ ። ለፍትህ እታገላለሁ የሚል ወገን ሁሉ ለበአሉ ግርማ ቤተሰብ ፍትህ ማግኘት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ ። ይህን ያልኩበት ምክንያት በውጪም ሆነ በአገርቤት “በቃ በአሉ ግርማን ደርግ ገድሎታል ሁላችንም የምናውቀው ነውና እንተወው ፦ የሚሉ ወገኖች ስላሉ ፤ በተለይ የእያንዳንዱ ግለሰብ የግል ነጻነት ተከብሮ በሚኖርበት አውሮጳና አሜሪካ እየተኖረ ይህን የመሰለ ድፍን ያለ ድምዳሜ ላይ መድረስ በስደት ከየምንኖርበት አገር የፍትህ ስርአት የተማርነው እንደሌለና ሆዳችንን ከመሙላት በቀር ምንም ትርፍ እንዳላመጣን ማሳያ ይሆናልና ነው ።

ይህን ካልኩ በኋላ ለዛሬ አብይ ነው ብዬ ወደተነሳሁበት ጉዳይ ልምጣ ።

አቶ አስፋው ዳምጤ “በበአሉ ግርማ ጉዳይ ላይ ከህሊና እዳ ነፃ ነኝ” በሚል ርዕስ ስለ በአሉ ግርማ መሰወር ጉዳይ የሰጡትን ቃለ- መጠይቅ ፍቱን ከምትባል መፅሄት ላይ ተወስዶ በአንድ ዌብ ሳይት ላይ ተለጥፎ አግኝቼ አነበብኩትና ከቃለ መጠይቁ የተረዳሁትን ለአንባቢ ለማሳወቅ ፈልጌ ነው ።
አቶ አስፋው ፤ በመጀመሪያ በራስዎ ስም መልስ ለመስጠት በመሞከርዎ ላድንቅዎ እፈልጋለሁ ።የሰጡት መልስ አሳማኝም ይሁን አይሁን ዋናው ለቀረበብዎት ጥያቄ በቃለ-መጠይቅ መልክ መልስ ለመስጠት ሞክረዋል ። ያስመሰግንዎታል ። ከቃለ መጠይቅ ይልቅ በራስዎ ፅሁፍ የነበረውን ሁኔታ ቢገልፁልን ኖሮ ደግሞ ተመራጭ ይሆን ነበር ። አዲስ አበባ ተወልደው ስላደጉም ይሆናል በወዳጅ በዘመድ አፅፈው በጎን ለማለፍ አለመፈለግዎ ፤ ትልቅ ነገር ነው ።(በጋዜጠኛው አቀራረብ ላይ ጥያቄ ቢኖረኝም)።
ያነጋገርዎ ጋዜጠኛ እንደነገረን የመጀመሪያ ዲግሪዎን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛውን ደግሞ ከካምብሪጅ አግኝተዋል ። ከዚያም ለረጂም ዘመናት በገንዘብ ሚኒስቴር ሰርተዋል ። ከዚህ በመነሳት ትምህርትዎ የጋዜጠኝነት ወይም የስነ-ፅሁፍ እንዳልሆነና economics ሊሆን እንደሚችል ጠርጥሬአለሁ ። ተሳስቼ እንደሆን ለመታረም ዝግጁ ነኝ ። ከዚያም በመፅሃፍ ድርጅትና በኩራዝ አሳታሚ ሰርተዋል ።
ይህን ካልኩ በኋላ በቀጥታ ወደርስዎ ቃለ-ምልልስ ልምጣ ።
የደራሲ በዓሉ ግርማ ባለቤት፣ ወ/ሮ አልማዝ አበራ፣
‹‹…የካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ም. ቀን ላይ አስፋው ዳምጤ እቤት ስልክ ደወለ :: በዓሉ ቤት አልነበረምና፣ ስልኩን አንሥቼ ያነጋገርኩት እኔ ነበርኩ :: የእግዜር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፣ ‹… በዓሉ እንደመጣ እዚያ እቀጠሯችን ቦታ ባስቸኳይ እንድትመጣ ብሎሃል በዪልኝ …› ብሎ ስልኩን ዘጋ ::››
አቶ አስፋው ፡ የዚህ አጭር መልሱ “ሃሰት” ነው ። ብለዋል ።
አበራ ለማ ከበአሉ ባለቤት ከወይዘሮ አልማዝ አገኘሁት ብሎ ካቀረበው ፅሁፍ ላይ ለእርስዎ ቃለ መጠይቅ መንደርደሪያ ሃሳብ ሆኖ የቀረበው ከፊሉ ብቻ ነው ። የአበራ ለማ ሙሉውን ምእራፍ ስናነብ ነው ፈታ ያለ ግንዛቤ የሚኖረን ። እንዲህ ይነበባል ፤ እጠቅሳለሁ፦
“….የካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ም. ቀን ላይ አስፋው ዳምጤ እቤት ስልክ ደወለ፡፡ በዓሉ ቤት አልነበረምና ስልኩን አነስቼ ያነጋገርኩት እኔ ነበርኩ፡፡ የእግዜር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ’… በዓሉ እንደመጣ እዚያ እቀጠሯችን ቦታ ባስቸኳይ እንድትመጣ ብሎሃል በዪልኝ…’ ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡ በዓሉ ወደ አሥራ አንድ ሰዓት ገደማ ወደ ቤት ሲመጣ መልእክቱን ነገርኩት፡፡ ወዲያው ሻወር ወስዶ ወጣና ለመሄድ ሲጣደፍ፣ ’እደጅ ውለህ መምጣትህ ነውና እባክህ ትንሽ እህል ብጤ ቀምሰህ ውጣ’ ብለው፤ ’አልችልም… ብርቱ ቀጠሮ አለንና ወደዚያው መፍጥን አለብኝ’ ብሎኝ ፈጥኖ ከቤት ወጣ::” የጥቅሱ መጨረሻ ።
መርምሮ ለሚያነብ ሰው የነገሩ ጭብጥ ያለው ወ/ሮ አልማዝ ከጠየቁትና አበራ ለማ ካቀረበው ከላይኛው ጥቅስ ጋር የተያያዘ ነው ። ወ/ሮ አልማዝ በስልክ መልእክት ከአቶ አስፋው ተቀብዬ ለባለቤቴ ነገርኩትና በመልእክቱ መሰረት ወደ ጓደኛው ወደ አቶ አስፋው ሄደ ነው የሚሉት ።
አቶ አስፋው የሚሉት ደግሞ የለም ስልክ አልደወልኩም ፤ ቀጠሮም አላደረኩም ፤ ሆኖም ግን ያለቀጠሮ በዚያች የመጨረሻዋ ምሽት በአሉን አግኝቼዋለሁ ነው ። እዚህ ላይ አንድ መሰረታዊ ጥያቄ ይነሳል ። ይኸውም ወይዘሮ አልማዝ ከአቶ አስፋው ጋር ጠብም ወዳጅነትም ቅርርብም የላቸውም አቶ አስፋው ዳምጤ እንደነገሩን ። ይህ ከሆነ ደግሞ ለምን ወይዘሮ አልማዝ እስካሁን ድረስ የምታውቀው ነገር አለና ንገረኝ ብለው አቶ አስፋውን ያስጨንቃሉ ፤ ለምን ሌሎቹን የበአሉ ጓደኞች አንደ አቶ አስፋው ሁሉ ጠይቀው አያውቁም ? ሌላው ደግሞ በመጨረሻዋ በአሉ በተሰወረባት ምሽት ፤ በአሉ ወደቤቱ ስላልተመለሰ ለወይዘሮ አልማዝ ከአስፋው ጋር አመሸሁ ብሎ አልነገራቸው ፤ ከእርስዎ ጋር ማምሸቱንስ ወ/ሮ አልማዝ እንዴት አወቁና ነው ወደቤትዎ የደወሉት ፤ ቀድመው ወደቤት ደውለው በወይዘሮ አልማዝ በኩል ለበአሉ ቀጠሮ ካልሰጡ ? አቶ አስፋው ወ/ሮ አልማዝ ወደቤቴ አልደወለችም ብለው ቢያስተባብሉም ጠዋት ላይ ወደስራዎ ደውለው እንደተነጋገሩ ደግሞ አልካዱም ። ወይዘሮ አልማዝ ባለቤቴ በአሉ ግርማ ማታ አልገባምና የምታውቀውን ንገረኝ ብለው ሲጠዩቅዎ “ አይቼዋለሁ ግን” ብየ የምለው ጠፋኝና ፤ የምለው ጠፋኝና ነው ያሉት ! ለምን የሚሉት ጠፋዎት ? አሁን የሚነግሩንን መገናኛችሁ አጠገብ ቆመን አንድ አንድ ብለን ተለያየን ብለው ለምን አልነገሯቸውም ለወ/ሮ አልማዝ ። ይህን ብለዋቸው እስቲ ደግሞ ከሌሎች ሰዎች ላጣራ ብለው ቢሆን ኖሮ የተናገሩት እውነት ይመስል ነበር ። አንድ ሰው የሚለው የሚጠፋው አንድ የሚያውቀው ነገር ሲኖርና ለዚያ መልስ ሳይዘጋጅ ድንገት ጥያቄ ሲቀርብበት ነው ። ወዲያው የሚያስገድደው ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ የመዘጋጃ ጊዜ ለመግዛት ዘዴ ይቀይሳል ። አቶ አስፋው ለርስዎ ጊዜ መግዣ አድርገው የተጠቀሙበት “ አሁን አንድ ትልቅ ባለስልጣን ዘንድ ስለምሄድ እሱን ጠይቄ እነግርሻለሁ ብለው ዛሬ በህይወት የሌሉትን ሰው ለማ ጉተማን ምስክርነት መጥራት ነው ። እስቲ ቆም ብለው ያስቡት ለራስዎም አልገረመዎትም ?
ሌላው ወ/ አልማዝ የተናገሩትን ለማስተባበል ማስረጃ አድርገው የተጠቀሙበት የሬይደልፍ ኬ ሞልቬርን Reidulf K. Molvaerን ብላክ ላዮንስ Black Lions የተባለው መፅሃፍ ላይ ደራሲው በአሉ ግርማ በጠፋባት በዚያች ምሽት ያቀረበውን ትንተና ነው ። በአጭሩ መፅሃፉ ላይ እርስዎ በአሉን መጥተው ከቤቱ ወሰዱት አይነት አቀራረብ ስለሆነ አንዴ ስልክ ደውሎ ቀጠሮ ሰጠው ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከቤቱ መጥቶ ወሰደው ተብሏልና አንዱን ይምረጡ ነው አባባልዎ ። መፅሃፉ ላይ እኮ ወ/ሮ አልማዝ እንደነገሩኝ ብሎ አልፃፈም ሞልቬር ፤ ስለዚህ ሞልቬር ይህን ነጥብ ከየትም ሊያገኘው ይችላል ። ሞልቤር ስህተት ፈፅሞ ከሆነ እንኳን ወ/ሮ አልማዝን ምርጪ አትምረጪ ሊያሰኛቸው አይችልም ። መፅሃፉ ላይ ለወጣው ፅሁፍ ተጠያቂ መሆን ያለበት ሞልቬር ብቻ ነው ። ታዲያ እኮ ሞልቬር እዚያው ገፅ ላይና እዛው ፓራግራፍ ላይ የጠቀሳቸው ነጥቦች ነበሩ ፤ እርስዎ ሳያዩአቸው አልፈዋል ወይም ሆን ብለው ዘለዋቸዋል ። ሞልቬር እንዲህ ይላል እዚያ ላይ ፤ እርስዎ አቶ አስፋው በአሉ ከተሰወረባት ከመጨረሻዋ ቀን አስራ አምስት ቀን በፊት ነው በአሉን ያየሁት ብለው ለሌሎች ሰዎች ተናግረዋል ብሏል ። ይህም ወ/ሮ አልማዝ ከተናገሩትና ከሚሉት ጋር ባለመግጠሙ ሰዎች ደንቆቸዋል ሲል ፅፏል ፤ ይህን ነጥብ ይያዙ ። ቀጥሎም እንዲህ ይላል ሞልቬር (ስም ባይጠቅስም) ምንልባትም ይህ ጓደኛው ፤ ላደረገው አብዮታዊ አስተዋፅኦ መንግስታዊ ለሆነው ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት በዚያኑ ሰሞን ስልጣን ተሰጠው ፤ ብሏል ። ሞልቬር ብላክ ላዮንስ በሚለው መጽሃፉ ላይ ያስቀመጠው እንዲህ ይነበባል ገፅ 348 ፦ To other people he ( the friend ) said that he had not seen Be’alu for two weeks before he disappeared, and they were surprised to hear another story from Be’alu’s wife . Soon after the friend got ( perhaps as areward for his contribution to the revolutinary cause ) a high position with Kurraz , the government publishers.
እዚህ ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ። አበራ ለማ የሰዎች ስም አጠፋ የርስዎን የአቶ አስፋው ዳምጤን ጨምሮ እየተባለ ሲጠቀስ በየመጣጥፉ ላይ አንብቤ ነበር ። የእርስዎም ብሶት አበራ ለማ ስሜን አጥፍቷል ነው ። ከዛሬ 17 አመታት በፊት በ1997 እ.አ.ኤ ሞልቬር ይህንኑ ፅፎት የለም እንዴ ያውም ዘላለማዊ ሆኖ በሚቀር መፅሃፍ ላይ ! ምነው አበራ ለማ እንዚህን መረጃዎች ሰብስቦ ሲፅፍ ድንቅ ሆነ ?
አቶ አስፋው ሌላው ያሳዘነኝን ሳልገልፅልዎ ማለፍ አልፈልግም ። ጋዜጠኛው ከአበራ ለማ ጋር ቅራኔ ነበራችሁ ? ብሎ ይጠይቅዎታል ። መሆን የነበረበት ከቮልቴር ጋር ቅራኔ ነበራችሁ ? ነው ። እርስዎም ሲመልሱ “ እኔ ከእርሱ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቻለሁ ብየ አስቤ አላውቅም ብለው ነበር ። ይህ የጨዋ መልስ በቂ ነበር ። በተረፈ ከዚያ አልፎ ከዛሬ 37 አመታት በፊት የተደረገን ስነፅሁፋዊ ክርክር ቂም በቀል አድርጎ ለማቅረብ መሞከርና በዚያ አስታኮ ስሙ ያልተጠቀሰ አስተማሪው እንዲህ ብሎ አለው ብሎ በማለት ሰውን በሾርኒ ለመስደብ መሞከር ትንሽነትን የሚያስይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ። በስነፅሁፍ ቅስሙ ቢሰበር ኖሮማ አበራ ለማ አሁን ይህን የመሰለ ኢንቬስቲጌቲቭ ስራ ባላቀረበልን ነበር ። በነገራችን ላይ አበራ ለማን ከፅሁፉ በስተቀር ጥቁር ይሁን ቀይ ሰልካካ ይሁን ኩርፋድ አላቀውም ። አስተያየቴ በሙሉ በአሉ ግርማን አስመልክቶ ከፃፈው ጋር የየያያዘ ነው ። በርግጥ ሌሎች የግጥም ስራዎቹንም አውቃለሁ ቅስሙ አልተሰበረም ህያው ነው ለማለት ነው ። እውነቱን ለመናገር እርስዎን ቃለ-መጠይቅ ካደረገልዎ ጋዜጠኛ ነው የድርሰት ስራዎች እንዳሉዎትም የሰማሁት ። ልጅ ሆኜ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ነው መፅሕፍትን የማንበብ ልምድ የተጥናወተኝ ። ካነበብኳቸው ውስጥ አንዱ ርዕሱ “ከልታማዋ እህቴ” ይላል አሁን የዚህን መፅሃፍ ደራሲ ማን እንደ ደራሲ ቆጥሮ ያስታውሰዋል !
ወደ ወ/ሮ አልማዝ አበራ ልመለስ ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ የወ/ሮ አልማዝ ጥያቄ አቶ አስፋው ባለቤቴን በአሉን ገድለዋል ፤ ወይም በግድያው ላይ እጃቸው አለበት አይደለም ። በኦሮማይ ምክንያት ህይወቱ እንዳለፈም ያውቃሉ ። የሳቸው ጥያቄ ግን አንድና አንድ ብቻ ነው ። የሟች ባለቤቴን የሞት መንገድ ፍለጋ ላይ ነኝ መዳረሻውን ላለፉት 30 አመታት እየፈለኩ ነው ። የዚያች መንገድ መግቢያ ቁልፍ አቶ አስፋው እርስዎ እጅ ላይ ይገኛልና ለፍትህ ብሎም ለህሊናዎ ሲሉ ይጠቁሙኝ ነው ። አቶ አስፋው ወ/ ሮ አልማዝ ልብ ውስጥ እንደማንኛውም ሰው ሊመላለስ የሚችለውን ስሜት ሊረዱት ይገባል ። የውድ ባለቤታቸውን ደብዛ እየፈለጉ ያሉ ናቸውና ። ቀያፋ ላዘዛቸው ሮማውያን ወታደሮች ጲላጦስ እየሱስን በግላጭ ጉንጩን ስሞ አሳልፎ ሰጥቶታል ብለው ቢያስቡስ ወ/ሮ አልማዝ ላይ ይፈረዳል ?
አቶ አስፋው ሌላው ያሳዘነኝን ሳልገልፅልዎ ማለፍ አልፈልግም ። ወ/ሮ አልማዝ ላይ ለምን ጠየቀችኝ ከሚል ቅሬታ ተሰምቶዎታል ስለዚህም አቂመውባቸዋል ። ወ/ሮ አልማዝ ጋር በስራ ምክንያት የሚያገናኛችሁና በዚህ ተቀይማኛለች በማለት ሊያቀርቡት የሚችሉት ምክንያት ሊኖር አልቻለም ። እና የሞተውን ባላቸውን በአሉን ሌላ ውሽማ ነበረችው በማለት የሴትነት ብቃታቸውን ለማዋርድ ሞከሩ ። ባልሻረ ቁስላቸው ላይ ጨው ነሰነሱበት ። ምን አይነት ጭካኔ ነው ! አዝናለሁ እንዲህ በማለቴ ፤ እንዲያውም ወራዳነት ነው ። የገባበትና አፅሙ እንኳ የት እንደወደቀ ያልታወቀ ሙት ወዳጁን አጽም ፤ ሰው እንዴት ይግጣል ። ቤተሰቡን ለማስቀየምስ ለምን ይቸኩላል ። ከራስዎ ጥያቄና መልስ ልነሳና ይህን ራስዎ የፈጠሩት መሆኑን ደግሞ ላስረዳዎ አቶ አስፋው ።
ጠያቂው ጋዜጠኛ ቀድሞ የተዘጋጀበት በሚመስል መልኩ ከመሬት ተነስቶ አንድ ጥያቄ ያቀርብልዎታል ። በአሉ እርስዎጋ ከመድረሱ በፊት ይት ቆየ ብለው ነው የገመቱት ? ይልዎታል ። ከዚያ አስቀድመው እርስዎ ካላዘጋጁት በቀር የበአሉን መቆያ ቦታ ሐሳብ ከዬተ አመጣው ? የቃለ- መጠይቁን ቁራሽ እነሆ
ፍቱን ፦ በአሉ እርሶ ጋ ከመድረሱ በፊት የት ቆየ ብለው ነበር የገመቱት ?
አቶ አስፋው፦ጥቂት ቀደምብሎ እዚያው አካባቢ ወዳጅ እንደነበረው ተገንዝቤ ነበር ።
ፍቱን፦ የማን ቤት ነው?
አቶ አስፋው ፦ እሱን አልውቅም ።
ፍቱን፦ወንድ ሴት?
አቶ አስፋው ሴት ።
ፍቱን፦ በዚያች እለት ምሽት እዚያ ቆይቶ ከተመለሰ በኋላ ነበር ከእርሶ ጋር የተገናኛችሁት ?
አቶ አስፋው፦ እንደዚያ ነበር አመጣጡን ሳይ የገመትኩት ።
ወዳጅ እንደነበረው ተገንዝቤ ነበር ። ተገንዝቤ ነበር የሚለውን ቃል መጠቀም የሚቻለው ለትምርት ለእውቀት ሲሆን ነው ። ውሽማ ነበረችው ለማለት ግንዛቤ አያሻውም አውቅ ነበር ነው የሚባለው ፤ ፈጠራዎን ግዝፈት ለመስጠት ግዙፍ ቃል ተጠቀሙ ። ይህ የሚያሳየው ደግሞ ራስዎም የተናገሩትን እንዳላመኑበት ነው ። እዚያው ላይ ዝቅ እንበልና የማን ቤት ነው ? ሲል ይጠይቃል ጋዜጠኛው ። አቶ አስፋው እሱን አላውቅም ሲሉ ይመልሳሉ ። ወንድ ሴት ይልዎታል ጋዜጠኛው ። የእርስዎ መልስ ደግሞ ሴት ይላል ። የማን ቤት መሆኑን ከላይ ሲጠቅሱ አልውቅም ካሉ በኋላ ፤እንዴት የሴት ቤት መሆኑን አወቁ ? እርስዎ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ደግሞ ውሽማውጋ ቆይቶ ነው የመጣው ? ሲልዎ ጋዜጠኛው ፣ እንደዚያ ነበር አመጣጡን ሳይ የገመትኩት ይላሉ እርስዎ ። ለካ ግምት ነው የተረጋገጠ ማስረጃ የለዎትም ! ታዲያ በስድስት አረፍተ ነገሮች ወስጥ ሶስት የተለያዩ የተምታቱ ነገሮችን ማቅረብ ወ/ሮ አልማዝን ለመስደብ የተፈጠረ ቅጥፈት መሆኑን አያሳይም ?
አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ ፤
1)በአሉ ግርማ ከወደአንዲት ሴት ቤት መምጣቱን ገመትኩ አሉ፡
2) ኮማንደር ለማ ጉተማን ምስክርነት ጠሩ ፤በህይወት የሌለ ሰው ፡
3)ስሙን ያልጠቀሱትን የአበራ ለማን መምህር ፤ እንዲህ ብሎ አለው አሉ ፡
4)ወ/ሮ አልማዝ መስሪያ ቤትዎ ደውለው ሲያነጋግሩዎ የሚሉት ጠፋብዎ ፡
5)አበራ ለማ በግጥሙ ምክንያት አደረገ ላሉት ክርክር ምስክር አድርገው አሁንም ያቀረቡት በህይወት የሌለውን ስብሃት ገ/እግዚአብሄርን ነው ።
ከተደረገልዎ ቃለ-መጠይቅ ላይ ከሰጧቸው መልሶች የቱን ተቀብለን የቱን እንተው ፤ የትኛው እውነት የትኛው ሃሰት እንደሆነስ በምን እናረጋግጥ ?
እስቲ እኔም እንደርስዎ ልገምት speculate ላድርግ በአሉ ግርማ ከሌላ ሴት ቤት መጣ ብየ ገመትኩ እንዳሉት ማለት ነው ። ከዚያ በፊት በደህናው ጊዜ በአሉ ከደሞዙ ሌላ በድርሰት ስራዎቹ የሚያገኘው ጠቀም ያለ ገንዘብ ነበረው ። እርስዎም ተቸግረው ከበአሉ ገንዘብ ተበድረው ነበር ። ያን ገንዘብ ሊከፍሉት አልቻሉም ወይም አልፈለጉም ። በመጨረሻዋ እለት ላለፉት 6 ወራት ስራ ስላልነበረው የተበደረውን ገንዘብ ሊከፍለኝ ነው ብሎ ይሆን እንዴ ለወይዘሮ አልማዝ በሰጧቸው ቀጠሮ አማካይነት ከቀጠሮው ስፍራ የደረሰው ። በቃለ- መጠይቅዎም ላይ እኔና እሱን ብቻ የምትመለከት የግል ጉዳይ ነበረችን ብለዋል ከገንዘብ ብድር ጋር የተያያዘች ትሆን ? በአሉን ሰዋራ ስፍራ ድረስ በመውሰድ ለደርግ ሰዎች ማስረከብ እርስዎን ከገንዘብ እዳ ነጻ ሲያደርግዎ ፤ ደርግ ተረጋጋሁ ባለበት በዚያ ዘመን በኦሮማይ እርቃኑን ያስቀረውን የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣኑን በአሉን ያለግርግር እርስዎ ከወሰዱበት ስፍራ በቀላሉ ማፈን ችሏል ማለት ይሆን ?
አቶ አስፋው ፤ አንድ ነገር እንዲያስቡ እፈልጋለሁ ። ላለፉት 30 አመታት የውድ ባለቤቴን መውደቂያ እፈልጋለሁ ብላ ያለድካም የምትተጋ አንድ ወይዘሮ በቤቷ ውስጥ ምን ያህል ፍቅር እንዳለ ማሳያ ናት ። ለባለቤቷም ሆነ ለራሷ የፍቅር ተምሳሌት ናት ። እንዲህ አይነት ሴት ደግሞ ለማይነጥፍ የቤት ውስጥ ፍቅር ምንጭ ናት ። እንደማናቸውም ድንቅ ደራስያን ሁሉ በአሉ ግርማም ከቤቱ ያገኘው የነበረው ፍቅር ለድርሰት ስራዎቹ ሁሉ ፅኑ መሰረት ሆኖት ለኛም ለአንባቢዎቹና ለአድናቂዎቹ የድርሰቶቹ ትሩፋት ደርሰውናል ።
ለዛሬው በዚሁ ላብቃ ።

ከአንበሳው ይብራ !


በሶፍት ኮፒ ተሰርቶ በኢንተርኔት የተሰራጨውን መጽሐፍ አሁን አንብቤ ጨረስኩት (ነሐሴ 27፡ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ማለቴ ነው)፡፡ መጽሐፉ በስውር አልደረሰኝም፡፡ እዚሁ ፌስቡክ ላይ Book for All ከሚባለው ግሩፕ ነው ያገኘሁት፡፡ እርግጥ የደረሰኝ ኮፒ ለህትመት የተዘጋጀው ሳይሆን የመጽሐፉ የመጀመሪያ ረቂቅ ይመስለኛል፡፡

ያም ሆነ ይህ መፅሐፉን አነበብኩት፡፡ ሆኖም በመጽሐፉ ያነበብኩት ነገር ብዙም አላስደነቀኝም፡፡ የቀድሞው ም/ሚኒስትር ስናየው፣ ስንሰማውና በግሉ ፕሬስ ስናነበው የነበረውን ነው መልሰው የጻፉት፡፡ ያ ማለት ግን ዋሽተውናል ማለት አይደለም፡፡ አቶ ኤርሚያስ ለጊዜው ያልተናገሯቸው በርካታ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ብረዳም አሁን የጻፉት ነገር በኢህአዴግ አባላት ሲነገረን ከነበረው በምንም መልኩ የሚለይ አይደለም፡፡ አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋ የኢህአዴግ መሪዎች በልዩ ልዩ የግምገማ መድረኮች ሲያወጧቸው የነበሩት ሪፖርቶች ከዚህ ቢብሱ እንጂ ከዚህ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ ለአብነትም አቶ መለስ “ቦናፓርቲስታዊ የመበስበስ አደጋዎች” እና “ድርጅታችን ከእንጥሏና ከጭንቅላቷ መግማት ጀምራለች” በሚሉ ርዕሶች የጻፏቸውን ሪፖርቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡

የአቶ ኤርሚያስ መጽሐፍ መልዕክቱ ለኢህአዴግ ተቃዋሚዎች አልመሰለኝም፡፡ ከዚህ ይልቅ አቶ ኤርሚያስ ለኢህአዴግና ለአባላቱ ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉበት የተቆርቋሪነት ድርሳን ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ አቶ ኤርሚያስ በጥቅሉ “ድርጅቱ የተመሰረተበትን ዓላማ እየሳተ በስህተት ላይ ስህተት እየጨመረ ሄዷል፤ ለወደፊቱ በዚሁ መንገድ ከቀጠለ የህልውናው ነገር አጠያያቂ ይሆናል፤ ሀገሪቷም አደጋ ላይ ተወድቃለች፤ ስለዚህ አመራሩና አባላቱ የድርጅቱን ህልውና ማስቀጠል ከፈለጉ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃዎችን በጊዜ መውሰድ አለባቸው” የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፉት፡፡

ይህ የአቶ ኤርሚያስ ስጋት በአቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ ጊዜያት ተንጸባርቋል፡፡ አቶ መለስ “የቆሰለው ጅብ ታሪክ”ን እያነሱ “ኢህአዴግ ራሱን እያረመና እያስተካከለ ካልሄደ እንደቆሰለው ጅብ ራሱን በልቶ ይጨርሳል” በማለት ጽፈዋል፡፡ በሌላ ጊዜም “የኢህአዴግ ዋነኛ ጠላቱ ተቃዋሚው ሳይሆን ኢህአዴግ ራሱ ነው፤ ኢህአዴግ ራሱን ካልጠበቀ ህልውናው ለአደጋ ይጋለጣል” በማለት በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ሰውየውንና መጽሐፉን ከማጥላላት ይልቅ የአቶ ኤርሚያስን ምክር በአዎንታዊነት ተመልክተው ለተግባራዊነቱ ሊንቀሳቀሱ ይገባል እላለሁ፡፡

—–

በአንጻሩ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ “እነኝህ በስልጣን ማማ ላይ ከቆዩ በኋላ ወደ ውጪ እየኮበለሉ የኢህአዴግን እኩይነት የሚያወጉን ባለስልጣናት ራሳቸው ምን ያህል ንጹህ ናቸው?” የሚል፡፡ እንዲህ የምለው ከኢህአዴግ አፈንግጠው ወደ ወጪ ከሚጠፉት ባለስልጣናት መካከል የብዙዎቹ ግለ-ታሪክ የተበላሸ መሆኑን ስለማውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የኦህዴድና የኢህአዴግ ፖሊት ቢሮ አባልና የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ሃላፊ የነበሩት አቶ ዮናታን ዲቢሳን እንውሰድ፡፡ እኝህ ግለሰብ በየካቲት 1993 ከተሰደዱ በኋላ ኢህአዴግ የሰራቸው ወንጀሎች በማለት ብዙ ነገር ለፍልፈዋል፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ስልጣን ላይ ከነበሩት የኦህዴድ (ኦፒዲኦ) መሪዎች መካከል የርሳቸውን ያህል በወንጀል የተነከረ ግለሰብ ያለ አይመስለኝም፡፡ በታችኛው እርከን (ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ) የነበሩት የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር አካላት ተጠሪነታቸው ለርሳቸው ነበር፡፡ በመሆኑም በኦሮሚያ ክልል የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን በቅርበት ይቆጣጠሩ ነበር፡፡ በዚህ ስልጣናቸው ተጠቅመው የከወኗቸው ብዙ ጉዶች አሉ፡፡

እኝህ ግለሰብ በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች በኦነግ ደጋፊነት ተከስሰው እንዲታሰሩ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲሰደዱና ደብዛቸው እንዲጠፋ የተደረገበትን ኦፕሬሽን ካቀናበሩትና ካስፈጸሙት አንዱ ናቸው፡፡ የኦሮሚያ መሬቶችን አላግባብ እየቆረሱ ለጎረቤት ክልሎች ሰጥተው ካበቁ በኋላ በሌሎች ክልሎች የተከለሉ ኦሮሞዎች “ወደ ኦሮሚያ ክልል መጠቃለል እንፈልጋለን” የሚል ጥያቄ ሲያነሱ አይቀጡ ቅጣት እንዲቀጡ አድርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በተካሄዱ የመግደል፣ የማስደንበርና የማፈናቀል ዘመቻዎችም አውራ ተሳታፊ እንደነበሩ በሰፊው ይታወቃል (ወደ ውጪ ከኮበለሉ በኋላ በወለጋ ክፍለ ሀገር ከሆሮ ገድሩ አውራጃ ለተናፈቀሉ የአማራ ተወላጆች ተቆርቋሪ ሆነው የአዞ እምባ ማንባታቸው በጣም አስደምሞኛል)፡፡

አቶ ዮናታን በተለይም ለሃያ ዓመታት የግጭት ቀጣና በሆነው የአዋሽ-ቦርዶዴ-ሚኤሶ-አፍደም መስመር ላይ (የባቡር ሐዲድን ተክትሎ ባሉት ከተሞች) በኦሮሞና በሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች መካከል በየሶስት ወሩ ለሚቀጣጠለው ግጭት ኢ-ፍትሐዊ ሽፋን በመስጠት ግጭቱ እንዳይረግብ ከሚያደርጉ ግለሰቦች ዋነኛው ነበሩ፡፡ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ የዞንና የወረዳ ስራ አስፈጻሚዎችን አስረዋል፤ ከስራ አባረዋል፡፡ በግጭቱ የምንጊዜም ተጠቂ የሆኑት የአሰቦትና የሚኤሶ አርብቶ አደሮች ራሳቸውን የሚከላከሉባቸውን የጦር መሳሪያዎች በመንጠቅ ከሩቅ አካባቢ በሚመጡ ቆለኛ የከብት ዘራፊዎች በተደጋጋሚ እንዲገደሉና እንዲዘረፉ አድርገዋል፡፡ በዚህ ጥቃት የተንገበገቡት የሀረርጌ ሽማግሌዎች ለአቤቱታ ወደ ጨፌ ኦሮሚያና የፌዴራል መንግሥት ሲሄዱ ሰድበው በማዋረድ መልሰዋቸዋል፡፡
እኝህ ነውረኛና ወንጀለኛ ግለሰብ ናቸው እንግዲህ ወደ ውጭ ሄደው የኢህአዴግን አውሬነት የሚያረዱን፡፡ በልዩ ልዩ ሚዲያዎች ቀርቦ ሲጠየቅ “ለኦሮሞ ህዝብ ስለተቆረቆርኩና ኢሕአዴጎች በነጻነት ስላላሰሩኝ ሀገር ጥዬ ወጣሁ” ብሎናል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ የሚለው ኦነግ “የኦነግ ደጋፊዎች ናችሁ” በሚል ስም የኦሮሞ ወጣቶችን ቁምስቅላቸውን ሲያሳይ የነበረውን ነውረኛ ግለሰብ በሁለት እጆቹ መቀበሉ!! አይ ፖለቲካ!! ውቢቷ እመቤት!!

አቶ ዮናታን ከሀገር የጠፉት በወቅቱ ኦሮሚያን በስውር ይመራ ከነበረው ሰለሞን ተስፋይ (ጢሞ) ጋር በመጣላታቸው ነው እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ በመቆርቆራቸው አይደለም፡፡ ከሰለሞን ጋር በጥቅም ተጋጩ፤ ከርሱ የሚሰጣቸውንም ትእዛዝ አልቀበልም እያሉ ማስቸገር ጀመሩ፡፡ በመሆኑም “ቆይ! የሚል ዛቻ ደረሳቸው፡፡ በዚህም ቀን ከሌሊት እንቅልፍ አጡ፡፡ በመሀሉ እርሳቸውን የሚወዱ ሰዎች ለአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ አውሮጳ ላኳቸው፡፡ ዮናታንም በዚያው ኮበለሉ፡፡ ታሪካቸው ይኸው ነው፡፡ (በነገራችን ላይ በመጋቢት 1993 ህወሐት ለሁለት ሲከፈል አቶ ሰለሞን ተስፋይ ከነ ስዬ አብረሃ ጋር ከድርጅቱ ተባረዋል፤ አቶ ዮናታን የሰለሞንን ዛቻ ችሎ ለአንድ ወር ቢቆይ ኖሮ ከሀገር ባልኮበለለም ነበር)፡፡

—–

የመጽሐፉ ፀሐፊ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ወንጀለኛ እንዳልሆኑ አምናለሁ፡፡ እኔም ወንጀለኛ ናቸው ከሚል አይደለም ይህንን የጻፍኩት፡፡ ነገር ግን ወደ ውጭ የኮበለሉት ባለስልጣናት ጠቅላላ ታሪካቸው መጠናት አለበት ባይ ነኝ፡፡ ሰውዬው እንደ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፖለቲካ ተሳትፎው ውጪ በግል የሰራው ወንጀል ከሌለ እሰየው! አሰላለፉን መቀየር ይችላል፡፡ ሰውየው እንደ ዮናታን ዲቢሳ በደም የጨቀየ ዶሴ በእጁ ላይ እያለ የኢህአዴግን እኩይነት የሚዘበዝብልን ከሆነ ግን በጭራሽ አንቀበለውም፡፡ ወንጀለኛ ምንጊዜም ቢሆን ወንጀለኛ ነው፡፡ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ወንጀለኛነትን አይፍቀውም፡፡ አንድ ሺህ አንድ ነጥብ!!!

ይህን የአንዱአለም አራጌን በራሱ አገላለጽ ከጠባቧ የቃሊቲ እስር ቤት የተጻፈ ግሩም መጽሐፍ ሳነብ የተሰማኝን ስሜት ባጭሩ ለመግለጽ እንጂ ሥነ ጽሑፋዊ ደንብ የተከተለ ሂስ ወይም የመጽሐፍ ግምገማ ለመስጠት አለመነሳቴን መግለጽ እፈልጋለሁ – መሆኑን እንዴት ከረማችሁ?

ከሁሉ በፊት ግን ከሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል ቂላቂሉ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሠራውን አስቂኝ ድራማ ስመለከት እያዘንኩ የታዘብኩትን በዓለም ወደር የማይገኝለት ምርጥ የምርመራ ውጤት በሚመለከት ትንሽ ልበል፡፡

የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን በውነቱ አልመለከትም፤ አለመመልከቴ ስህተት መሆኑ ቢገባኝም ጤንነቴን አጥብቄ ስለምፈልገው ይሁነኝ ብዬና ቁም ነገር አገኝበታለሁ ብዬ ኢቲቪን አላየውም – ብዙዎች እኔን መሰሎች ስላሉ “የዐዋጁን በጆሮ” እንዳትሉኝ እንጂ፡፡ የሆኖ ሆኖ በቀደምለታ ከሰዎች ጋር የሆነ ቦታ ቁጭ ብዬ ቁርስ ቢጤ ስንቀምስ በፖሊስ ፕሮግራም የተከታተልኩት በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ድንቅ የሆነ የወያኔ የወንጀል ምርመራ ቴክኒክና ውጤት ያጫረብኝን ልዩ ስሜት በዚህ አጋጣሚ ሳላነሳው መቅረት አልፈለግሁም፡፡ ከእውነት ሰው መሆኔን ጠላሁ፡፡

“መርማሪው” ወያኔ አይታይም፤ ይህን የለመድነው ነው፡፡ ወያኔዎች ራሳቸውን እንደወንጀለኛ አድርገው ስለሚቆጥሩና ከአልቃኢዳ ጋር የሚያመሳስሏቸውን ድርጊቶች የሚፈጽሙ መሆናቸውን ሕዝቡ የተረዳው መሆኑን ስለለተገነዘቡ ይመስለኛል የመንግሥትን ሥልጣንና ኃይልም የጨበጡ “ምሁራኑ መርማሪዎች” በግልጽ በሚዲያ መታየትን የሚወዱ አይመስሉም ፤ እነዚህ ጭራቅ ገራፊዎችና ሀዘን አምላኪዎች (ሳዲስቶች) በራሳቸውም በመንግሥታቸውም የሚተማመኑ እንዳልሆኑና በሆዳቸውና በዘረኝነት ቁርኝታቸው ብቻ ተለክፈው በስሜት ፈረስ የዕውር ድምብር ግልቢያ ዜጎችን የሚያሰቃዩ ናቸው – ቀናቸው ሲደርስ ምን እንደሚውጣቸው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ አሣር አለባቸው – የቁናው ሥፍር እየተንደረበበ ይጠብቃቸዋል – እዚህ ወይም እዚያ፡፡ ከሞራል ዕሤቶቻችንና ከምርመራ ህግ በወጣ ሁኔታ አቡበከር የሚባለውን የሙስሊም ተቃውሞ አመራር አባል እጆቹን በእጀሙቅ አስረው የሚያካሂዱትን “ምርመራ” በአደባባይ በቲቪ ለዓለም ሕዝብ ሲያሳዩም “መርማሪው ሊቅ” መታየትን አልወደደም – አስጠሊታ ሣቁ ግን ከአንጀቱ ጥርስ ሳይሆን ከማተብ የለሽ አንገቱ ይሰማ ነበር፡፡ ስለዚህ የአንዲ ልዩነት እጆቹ አለመታሰራቸው እንጂ ሂደቱ ልክ እንደአቡቦከር ነው፡፡ ይህ የምርመራ ሂደትና ውጤቱ የሀገራችን የለየለት ውርደትና የወያኔን ማንአለብኝነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ወያኔዎች ከግዑዝ ድንጋይ የማይሻሉ የመጨረሻ ደደቦች መሆናቸውን ምናልባትም ለሚሊዮንኛ ጊዜ የገለጡበት ማፈሪያ ድርጊት ነው፡፡ የሚታዘነው በተመርማሪዎቹ ሳይሆን በመርማሪ ተብዬዎቹ ነው፡፡ ከመነሻው የዘረኝነት ልክፍት ያሽመደመደውና ከዘር ማዕቀፍ ውጭ የማያስብ ደንቆሮ ማይምና ሳዲስት እንዴት አንድን የተማረን ሰው ይመረምራል? እንዲያው ትንሽም ቢሆን የተማረ ዘረኛ ወያኔ ጠፍቶ ነው ወይ? ይህ ዓይነቱ የአደባባይ ግፍ ሄዶ ሄዶ የሚያስከትለውን መዘዝ እንዴት አጡት? ድንቁርና ይህን ያህል በጀብደኝት ያሳውራል?

ወደአስቂኙ ድራማ ልለፍ፡፡ አንዳርጋቸው በ“ነፃ ኅሊናው” የሰጠውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በደናቁር የወያኔ ወንበዴዎች እሳቤ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ይህን ይመስላል፤ “የግንቦት ሰባት ኅልውና ከእንግዲህ ግፋ ቢል ለሁለት ወራት ቢዘልቅ ነው፤ ወዲያም አለ ወዲህ ዕድሜው ከሁለት ወር አይበልጥም፡፡ የአውሮፓና አሜሪካ ምቾቱን ትቶ እንደኔ በረሃ ወርዶ የሚያታግል ቆራጥ ሰው አይኖረውም፡፡…” የግንቦት ሰባት ቀሪ ዕድሜ ሁለት ቀንም ይሁን ሁለት ወር እሱ ሌላ ጉዳይና ወደፊትም የሚታይ ሆኖ ይህን የተናገረው ግን አንዳርጋቸው ጽጌ መሆኑን ልብ ይሏል – አንዲን በሚዲያም ቢሆን ባላውቀው ኖሮ ከአሁን በፊት “የተናገረውን”ና ገና ወደፊት “እንደሚናገረው በጉጉት” የሚጠበቀውን ሁሉ በበኩሌ ሳላንገራግር በሙሉ ልቤ አምኜ በተቀበልኩና ከወያኔ የሸፈተውን ልቤን ወደወያኔ በመለስኩ ነበር – ይህ ሁሉ ድካማቸው ታያ የማንን ቀልብ ለመሳብ ? በመሠረቱ እስካሁን ወያኔ የነበረ በአንዳርጋቸው ንግግር ምክንያት የወያኔነት ደረጃው አይጨምርም – በተቃራኒውም እስካሁን ወያኔ ያልነበረ በዚሁ የአንዲ ንግግር ምክንያት ንዴቱና ቁጭቱ ይጨምርና ወደድርጊት ይገባ እንደሆነ እንጂ ከተቃዋሚነቱ የሚያፈገፍግ አይመስለኝም፤ እናም የወያኔዎች የጅልነት ምጥቀት ያሳዝነኛል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንና ዓለምን በጠቅላላው እስከዚህን ያህል መናቃቸው ምን ያህል ወራዳዎች – እደግመዋለሁ ምዕመናን – ምን ያህል ወራዳዎች መሆናቸውን ከማሳየት በስተቀር የአንዲ ስቃይና የሙሌት ኑዛዜ የሚጨምርላቸው አንዳችም አወንታዊ ነገር የለም – ይህን ነባራዊ እውነት ለመናገር ደግሞ የክር ወይም የሃቂቃ ጉዳይ እንጂ የግንቦት ሰባት አባልም ሆነ ደጋፊ መሆንን አይጠይቅም፡፡ የወያኔዎችን ውስጠ ምሥጢርና የግፍ ታሪክ በየመድረኮች ሲዘከዘክ ሚሊዮኖችን በዕንባ ሲያራጭና በትካዜ ባህር ሲያሰምጥ የምናውቀው አንዳርጋቸው ጽጌ በምትሃታዊ ፍጥነት ወደማፊያው መንግሥት ተገልብጦ ተናገረው የተባለውን እንዲያ ሲናገር ይታያችሁ፡፡ የምናውቀው አንዳርጋቸው የምናውቅለትን ጽኑ ፀረ-ወያኔ አቋሙን በሻጥርና በብዙ ገንዘብ ክፍያ በየመኖች ተይዞ በወያኔዎች እጅ በገባ በሁለት ሣምንታት ጊዜ ውስጥ ሲለውጥ በዐይነ ኅሊናችሁ ይታያችሁ፡፡

ግሩም የምርመራ ውጤት! ዓለምን የሚያስደምም ሣይንሳዊ የወንጀል ምርመራ ግኝት! በዚህ በአንዳርጋቸው ቃልና የመከራ ኑዛዜ ማፈር ያለበት ቀደም ሲል ለመጠቆም እንደሞከርኩት ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ከወያኔ ውጭ ማንንም ሊያሳፍር አይችልም፡፡ እንዲያውም እኔ ብሆን ኖሮ “ግንቦት ሰባት የሚባል ድርጅት ከነአካቴው በሕይወት አለ እንዴ? አሁን እናንተ ስትሉ ሰማሁ፡፡ ማን ተናገር እንዳለኝ አላውቅም ዝም ብዬ ነበር እኮ በኢሳት ያንን ሁሉ ንግግር የምዘባርቀው፡፡ ደግሞ ብርሃኑን ብሎ ግንቦት ሰባት! ከመነሻው ግንቦት ሰባት ብሎ ነገር ሲኖር አይደለም ወርቆቼ! …” ብዬ አስደስታቸው ነበር እንጂ የሌለን ምሥጢር ለመደበቅ በመሞከር ሰውነቴን ለስቃይ አልዳርግም – ሊያውም በዚያ ኑዛዜየም ስቃዩን ቢቀንሱልኝ አይደል? ግን አይቀንሱልኝም – ስለዚህ ብናገርም ባልናገርም ለውጥ የለውም፤ ጠባችን በደም የሚጠራ እንጂ በውሃ ታጥቦ የሚጸዳ አይደለምና፡፡

እንደውነቱ ታዲያ አንዳርጋቸው ሊሰጠው የሚችለው የማይታወቅ የተከደነ አዲስ ምሥጢር ሊኖር ይችላል? ሁሉም ነገር እኮ ግልጽ ነው፤ ወያኔ የሚባል ሀገር አጥፊና ፀረ-ሕዝብ የሆነ የማፊያዎች ቡድን አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ውስጥ መሽጎ አለ – እሱን ለማስወገድ ደግሞ ዜጎች በተበታተነ ሁኔታም ቢሆን በየፊናቸው ጥረታቸውን እያደረጉ ነው፤ ምሥጢር ከተባለ ይህ ነው ምሥጢሩ፡፡ አንዳርጋቸው የትግል መስመሩ ስላበሳጫቸውና እየሠራ ያለው ነገር ለኅልውናቸው አስጊ ሆኖ ክፉኛ የሚያሳስባቸው በመሆኑ እርግጥ ነው እሱን ከመድረክ ገለል እንዲል ማድረግ ቢፈልጉ ያንን መቀበል ይቻላል – ሰይጣናዊ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሄዱበት ርቀት ብዙ የሕግና የሞራል ችግር ማስነሳቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ከዚያ ውጪ ምሥጢር አውጣ ብሎ የዓለማችን ቤት ባፈራው የማሰቃያ ዘዴ ሁሉ ሰውን ማሰቃየት፣ በዚያም ሂደት ራስን ለትዝብትና ለስላቅ የሚያጋልጥ ነውረኛ የምርመራ ሂደት ማካሄድና ተመርማሪዎች የማያምኑበትን ነገር እንዲናገሩ ማድረግ በእግረ መንገድም “በሰላም አንገዛም፣ አንገብርምም ያሉንንና ሕዝብን የሚያሳምጹብንን ቀንደኛ ጠላቶቻችንን ‹እንዲህ አሸናናቸው!›፣ የወንዶች ወንዶች መሆናችንን ብልታቸውን እየቆረጥን አሳየናቸው…” በማለት ስብዕናን ለማዋረድ መሞከር ወደራስ የሚዞር አሉታዊ ውጤትን መጋበዝ መሆኑን መረዳት ይገባቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ወያኔ ልብሱም ጉርሱም ቅሌትና ውርደት በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚሰማው አንድም የሀፍረትም ሆነ የይሉኝታ ስሜት የለም፡፡ ጃዝ ብለው የለቀቁት 13 እና 33 ቁጥሮችም እየሳቁበትና እየተዝናኑበትም ቢሆን ወያኔ ለሚሠራው ግፍና በደል ሁሉ ቡራኬያቸውን አይነፍጉትም፡፡ እነሱስ ቢሆን በጭፍሮቻቸው አማካይነት በጓንታናሞና ኢራቅ ውስጥ አስከሬኖች ላይ እስከመሽናት በሚዘልቅ ኢሰብአዊነት ስንትና ስንት ግፍ ይፈጸሙ የለም? ልጅ ከአባት ቢማርና የጭካኔ ደረጃውን አዘምኖ ምሥኪን ኢትዮጵያውያንን ምድራዊ ገሃነም ውስጥ ቢዘፍቃቸው ዋኖቹ ሀዘን አምላኪዎች ይደሰታሉ እንጂ ከከንፈር ሽንገላ ባለፈ ሕዝቡን ሊታደጉት አይፈልጉም – ይህንንም አሳምረን እናውቃለን፡፡ ጭምብሉን ፖለቲካዊ የተለሳለሰ የሚመስል አካሄድም አንዘነጋም – አገም ጠቀሙን፡፡

በነገራችን ላይ 13 እና 11 ወይም 33 ደግሞ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ለሚያምንበት ሁሉም የትልቁ ቁጥር የአውሬው መገለጫ የ666 ቅንስናሾች ናቸው፡፡ አሥራ አንዶች በ110 የለበጣ ቀመር ቢያላግጡም እውነቱ ቀፎ የመለዋወጥ – የትሮይን ፈረስ ቅርጽ የማሻሻል ጉዳይ እንጂ ሲሙ ያው ነው – አሥራ አንድ፡፡ ለነገሩ ዝናር ባንገቴም ይሁን 11 ወይም ዜሮም ይሁን አንድ ሽንትር ዋናው ነገር ተግባር ነው፡፡ ሌላው ትርፍና ጨዋታን ለማሳመር ያህል በአጃቢነት የገባ ነው፡፡ እናም በሀገራችን ሁኔታ የሰውዬው ማንነት ምንም ይሁን ምን በስቃይና በግድያ የሚያምን ሁሉ እናት ክፍሉና ጥንተ አመጣጡ ከአውሬው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ክፉና ደግ መንፈሶች ኅብረት የላቸውም፡፡ ሩህሩህ መሐሪና አረመኔ/ጨካኝ ገዳይ አንድነት የላቸውም፡፡ መጽሐፉም ጣፋጭ ፍሬ በዛፍ ላይ ሳለ ይታወቃል እንደሚል ማን የማን ወገን መሆኑ በተለይ በዘመናችን በግልጽ ይታወቃል፡፡ ማን ነው የበሽታ ሕዋሳትን በቤተ ሙከራ እየፈለሰፈና እያራባ ለዓለም በተለይም ለኋላቀር ሀገሮች እንደ ዕርዳታ ስንዴ የሚያከፋፍል? ማን ነው የዓለማችንን የአየር ንብረት እያዛባና ዕድሜዋን በብርሃን ፍጥነት እያሳጠረ የሚገኘው? የዓለምን ጠቅላይ ገዢነት በትረ መንግሥት በጉልበት የተቆጣጠረውና “ለኔ ካልሰገዳችሁ ሀብትና ሥልጣን አይኖራችሁም” ብሎ ሁሉን እያስደገደገ የሚገኘውና በትዕምርተ ኅቡኣታዊ ባለአንድ ዐይን ፒራሚዳዊ ቅርጽ ወይም በፔንታጋራማቲን የኮከብ ቅርጽ የሚታወቀው ምሥጢራዊ ኃይል ማን ነው? ማን ነው አሁንም ሆነ ከአሁን በፊት መካከለኛውን ምሥራቅ እያተራመሰ ያለው? መፍለቂያው የሆነችን የአንዲት ትንሽዬ ሀገር ኅልውናና የበላይነት ለማስጠበቅ ሲል ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቱ የዓለምን የመንግሥታት ኅብረት እንደአሽከር ሰጥ ለምበጥ አድርጎ የሚገዛ ማን ነው? አይኤም ኤፍ፣ ዩኤን፣ ወርልድባንክ፣ ኔቶ፣ ሲአርኤፍ፣ … የማን አድቃቂ ክንዶች ናቸው? ለመሆኑ የዚህ ሞገደኛ የወቅቱ የዓለማችን ገዢ ዋና መሥሪያ ቤትና ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ የት የት ናቸው? ጽዮንና ሀማስ የማን ልዑካን ናቸው? የግጭቶች መንስኤና የምክንያታዊነት ሚዛኑ ለማንም ያጋድል ዋናው የሁለቱም ተልእኮ ግና ለአውሬው ግብር የሚሆን ብዙ የደም ባህር ማቆር መሆኑን መዘንጋት የዓለም ነገር አያገባኝም ብሎ እንደመመነን ይቆጠራል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል – ማን ነው የጦር ኃይሎችን በሁለት ጎራ እየከፈለ በተፃራሪነት በማሰለፍ የሚሊዮኖችን ደም በከንቱ እያፋሰሰ ያለው? ኢራንና አሜሪካ በርግጥም ባላንጣዎች ይሆኑ እንዴ? በፍጹም፡፡ ጠላቶች መስለው ትያትር በመከወን ለአንድ ዓላማ ስኬት የሚተጉ የአንድ ገዢ አንድ አምሳል አንድ አካል ናቸው፡፡ ማን ነው በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከአፍ እስከገደፋቸው በንጹሃን ተሣፋሪዎች ጢም ብለው የሞሉ የሲቪል አውሮፕላኖችን(የማሌዥያን) ባልታወቀ ዕፀ መሠውርና በሚሳኤይል ድራሻቸውን ያጠፋው? ምን ዓይነት ወያኔያዊ ጨካኝ አንጀት ያለው ፍጡር ይሆን ይህን ያደረገ? ለምን ዓላማ? ቫቲካንንና መለስተኛ አውሮፕላን የምታህል የነጭ እርግብ ምስል ለማስመሰል ያህል በሰላም ምልክትነት በዋና የፓትርያርክ ጸ/ቤቱ በር ላይ ያቆመውን የኛኑ ኦርቶዶክስ ሳይቀር ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተቆጣጥሮ ሁሉንም ሃይማኖት አለኝ ባይ በአውሬው ትዕዛዝ ሥር ያደረገው ማን ነው? ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ቅዱስ ሊባል የሚችል ቦታና ሰው አለ ወይ? ፖፕ ጆን ፖል አንደኛ፣ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ፣ ‹አቡነ› ጳውሎስ የኛ… ሌሎችም የማን ወኪል ነበሩ? ፍየሎች በበጎች ጋጣ ውስጥ መሽገዋል፡፡ በጎች እያለቁ ነው፡፡ አውሬው ሆሊውድና ቦሊውድን ብቻ ሳይን ገዳማትንና ካቴድራሎችንም ከተቆጣጠረ ምዕተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ጭካኔን በሚያስተምሩ ፊልሞች፣ በልቅና ባልተገሩ ኢ-ሞራላዊም በሆኑ ፖርኖግራፊዎች በተለይ የዓለምን ወጣት ትውልድ ጡጦ ከመጣሉ በእንጭጩ ለማምከን ይህችን ዓለም ማንና ከየትስ ሆኖ እየገዛት እንዳለ መች አጣነው? የዚያ ‹ታላቅ› የጨለማ ንጉሥ የእጅ ሥራዎች የሆኑ ወያኔዎችም ባቅማቸው ቅድስቲቱን ሀገር ድራሽዋን ቢያጠፏት ከድጋፍ በስተቀር ማን ከልካይ አላቸው? በጎችስ ቢጮኹ አለጊዜው ማን ይደርስላቸዋል? ግን ግን አይዞን፤ የፍየሎችና የበጎች የመጨረሻ ዕድል ተለይቶ የሚታወቅበት የፍርድ ቀን በፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ብሎም ቢሆን ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ድል በምኞት ሊገኝ እንደማይችል ልብ ማለት ይገባናል፡፡ ብቻ ይህን መሰሉን ነገር በሆድ ይፍጀው ለሌላ ቀን በይደር ማቆየቱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለነገሩ እኛን ምን አገባን? ሁሉም ከልኩ አይዘል፡፡

ከሰው ተውሼ እያነበብኩት ነበር – “ያልተሄደበት መንገድ”ን፡፡ በቅርብ ካነበብኳቸው በሀገር ችግር ዙሪያ ከሚያጠነጥኑ የቅርብ ጊዜ መጻሕፍት ውስጥ በኔ ዕይታና ለኔ ፍጆታ ይሄኛውን ወደር አላገኘሁለትም፡፡ አንዱአለም አራጌ ዋለ የተዋጣለት መጽሐፍ በመጻፉ – ሊያውም በዚህ አፍላ የጎልማሳነት ዕድሜውና በመከራ ውስጥ ሆኖ – ባለበት አድናቆቴ ይድረሰው፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ የሚባለው በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ነው፡፡ ሚሊዮኖች ፈርተንና ለሥጋችን አድረን በየሽርንቁላው ተወትፈን በፍርሀት ቆፈን ስንርድ ሊያውም በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ይህን የመሰለ አብሪ መጽሐፍ ካለበቂ ማጣቀሻና ዋቢ መጻሕፍት በአዩኝ አላዩኝ ሰቀቀን ሌሊት ሌሊት እየተደበቁ መጻፍ ልዩ ጀግንነትና ተሰጥዖም ነው፡፡ አንዱአለምና መሰል የብዕርና የፖለቲካ ታጋዮች ለነፃይቱ ኢትዮጵያ በሕይወት እንዲደርሱ እግዚአብሔር ይታደገን፤ ይታደጋቸው፡፡ ቤተሰባቸውንም ይባርክ፡፡ ለእኛም ለባከንነውና ለራሳችን ጥቅምና ፍላጎት ስንል በ‹እስኪያልፍ ያለፋል› ተረት ራሳችንን እያታለልን የወያኔ ባርያ ሆነን ለጠፋነው ዜጎችም ፈጣሪ ረድኤቱንና ወኔውን ይስጠን፡፡ እንደዚህ ያሉ ዜጎች ባይኖሩን ኖሮ ሕይወት በጠቅላላው ለይቶላት ጨለማ በሆነች ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር እግዜር የተመሰገነ ይሁን፡፡ እርሱን መሰል ሌሎች ጸሐፊዎችንና ታሳሪዎችንም ጭምር እግዜር ይባርክልን፡፡ ለቤታቸውም ያብቃልን፡፡ የሚሳነው ነገር የሌለው የኢትዮጵያ አምላክ የመከራ ደብዳቤያችንን የሚቀድድና ሃራ የሚያወጣን አንዳች ኃይል ይዘዝልን፡፡ አሜን፡፡

ይህ መጽሐፍ የዋቢ መጻሕፍትን ገጽ ጨምሮ በጠቅላላው 320 ገጾች አሉት፡፡ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ሥር የተካተቱ 18 ርዕሶችንም ይዟል፡፡ ጠቅጠቅ ብሎ የተጻፈ በመሆኑ እንደሌሎች በርካታ መሰል መጻሕፍት በቀላሉ አይገፋም፡፡ የሆኖ ሆኖ በተለይ እስከማገባደጃው ድረስ ስሜትን ቆንጥጦ በመያዝ መነበብ የሚያስችለው ሥነ ጽሑፋዊ ውበትና ይዘታዊ ግርማ ሞገስ አለው፡፡ እናም አንብቡት፡፡ በነገራችን ላይ ይህን መጽሐፍ እያነበብኩ ወደ ገጽ 100 አካባቢ ስደርስ የተዋስኩትን እንደምመልስ ገባኝና ወዲያውኑ ከተማ ወጥቼ ገዛሁት፡፡ ተውሼ ያነበብኩትን ወይም እያነበብኩት ያለሁትን መጽሐፍ ስገዛ ይህ የመጀመሪያ ጊዜየ ነው፡፡ አንጡራ ሀብቴና የመጻሕፍት መደርደሪያየ አንዱ ፈርጥ እንዲሆን ተመኘሁ፡፡ ተመኝቼም አልቀረሁ፡፡ ለልጆቼ ውርስ ይሆናል፡፡ እናንተም አሁኑኑ ግዙና ንብረታችሁ አድርጉት፡፡ መጽሐፉ “ኩሎ አመክሩ ወዘሰናየ አጸንዑ” እንዲል፡፡

አመስጋኝ አማሳኝ እንዳልባል በዚህ መጽሐፍ የታዘብኳቸውን አንዳንድ ግድፈቶችም በዚሁ አጋጣሚ ብጠቁም ደስ ይለኛል፡፡ ጥቂት የማይባሉ የአርትዖት ችግሮች አሉበት፡፡ አሉታዊ መሆን ያለበት በአወንታዊ ወይም የዚህ ተቃራኒ ሆኖ የሚጻፍበት አጋጣሚ አልፎ አልፎ ይስተዋላል፡፡ አማርኛ ላይ ብዙውን ጊዜ የምታስቸግር ነገር አለች – ለምሳሌ “እኔን እንደሚያገባኝ እንዴት ረሳኸው?” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ “ሚ”ን “ማ” ብናደርጋት ትርጉሙ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል፡፡ “ጽንፍ” ለማለት “ቅንፍ” ብንል አንዳንዶችን ግር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የአርትዖት ሥራ ሽንፍላ እንደማጠብ ነው፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች በብዙ አዳዲስ ዐይኖች ሊተባበሩበት የሚገባው አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ የማይጠራበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚህ አኳያ ይህን ቆንጆና ለታሪክ የሚቀመጥ መጽሐፍ ዐዋቂ ሰው እንደገና “ኤዲት” ቢያደርገው የበለጠ ማለፊያ ይሆናል፡፡ የግሌ አስተያየት ነው፡፡ (አንድ ወዳጄ የነገረኝ አንድ አርትዖታዊ ስህተት በጭንቅላቴ ብልጭ እያለ ‹እዚህ ላይ ካልጻፍከኝ ሞቼ እገኛለሁ!› ብሎ አስቸገረኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ የብድር ኮሚቴ ስብሰባ ይጠራል፡፡ ለተሰብሳቢዎችም “ከብድር ኮሚቴ…. ለጠቅላላ አባላት” የሚል ጽሑፍ ተበትኗል፡፡ ሁሉን ያስፈገገው ግን ጸሐፊዋ “ከብድር ኮሚቴ” ከሚለው ሐረግ ውስጥ የአንዱን ቃል የመጨረሻ ፊደል ሳትጽፈው መቅረቷና እስከዚያን የስብሰባ ጊዜ ድረስ ማንም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ስህተቱን ልብ አለማለቱ ነበር፡፡ ያቺ “ነገረኛ” ጸሐፊ የትኛዋን ሆሄ እንደዘነጋቻት እኔም አሁን ዘነጋኋት፡፡ )

ከሆሄያት ግድፈትና ሞክሼ ፊደላትን በነባሩ ሰዋስዋዊ ልማድ ከመጠቀም አኳያ ከሚታዩ አንዳንድ ጥቃቅን “ስህተቶች” በተጓዳኝ ጥቂት የመረጃ መዛባትና የዘይቤና ፈሊጥ አጠቃቀም እጅግ አነስተኛ ችግር ሳይኖር እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ለምሳሌ “ኢሕአፓ” የሚለው ምሕጻረ ቃል ሲፈታ እኔ የማውቀው “የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ” በሚል ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ግን “የኢትዮጵያ ሕዝብ አደራጅ ፓርቲ” በሚል ከአንዴም ሁለቴ ገደማ ቀርቧል፡፡ ፈሊጥን በተመለከተ “ለያዥ ለገራዥ” ለማለት “ለያዥ ለገናዥ” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የሃሳብ ድግግሞሽ በስፋት ይታይበታል፡፡ በዚያም ምክንያት አንድ አንባቢ በጀመረበት የስሜት ሞቅታ መጨረስ ባይችል ችግሩ ከዚህ የሃሳቦች መደጋገም የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ የመጽሐፉ አጻጻፍና ለኅትመት መብቃት በብዙ ችግር የታጠረ በመሆኑ የአሁኑ ይዘቱ ራሱ ከሚጠበቀው በላይና በአንጻራዊ ሁኔታ ከሌሎች በርካታ መሰል ጸሑፎች(እኔ ካነበብኳቸው) በጣም የተሻለ መሆኑን በበኩሌ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥረቱ ደራሲውን በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው ጓዶች፡፡ እነኚህንና መሰል ሌሎች እንከኖችን አስተካክሎ በቀጣይ ኅትመት ለንባብ የሚያበቃው ወገን ከተገኘ መልካም ነው፡፡ ደግሞም የማይቻል አይመስለኝም፡፡

አንዱአለምን በዚህ መጽሐፉ ደርቤ እንዳነበብኩት የፕሮፌሰር መስፍን ደቀ መዝሙር ይመስለኛል፡፡ ይህን የምለው ፕሮፌሰሩ አንድ ወቅት እነብርሃኑ ነጋ “ሁለገብ ዘዴን በመጠቀም ወያኔን እንታገላለን” ባሉ ወቅት ክፉኛ ይተቿቸውና “እኛ ወደዚህ ‹የማይረባና ውዳቂ› የአስተሳሰብ ደረጃ አንወርድም” ማለታቸውን በማስታወስና አንዱአለምም በዚያው ቅኝት አሁንም ድረስ በዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንዝ ቀርቶ የደረቀ ምንጭ በማያሻግር የሰላማዊ ትግል ሥልት ወያኔን እንጥላለን ብሎ የሚያምን በመሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዱአለም አሁን ባለበት ሁኔታ በኃይል ወይም በጦር መሣሪያ ወያኔን እንታገል ብሎ ቢጽፍ የሚደርስበትን ተጨማሪ መከራና ፍዳ ስለምንገነዘብ ይህን አቋም ያርምድ ብለን በሰው ቁስል እንጨት አንሰድም፡፡ ይሁንና ቢያንስ ዝም ማለት ሲገባ ወያኔ የፈጠረው የኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ችግር የሚፈታው ወያኔን በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ነው የሚል እምነት በጭፍን ማራመዱን አልወደድኩለትም፡፡ (በነገራችን ላይ ኤርምያስ ለገሰ ቅድም በኢሳት አንድ ውይይት ላይ ሲናገር እንደሰማሁት የአንዳርጋቸውን በወያኔዎች መያዝ ኔልሰን ማንዴላ በኢዲያሚን ዳዳ እንደተያዘ ያህል እቆጥረዋለሁ ማለቱን እኔም በጣም እደግፋለሁ፡፡) ሰው ከሰው ጋር ቢታገል አሸናፊውና ተሸናፊው ይለያል፡፡ ከአውሬ ጋር ግን እንዴት መታገል ይቻላል? ውሾች በ“አስተሳሰብ” ከሚበልጡት ወያኔ ጋር እንዴት ስለሰላም መወያየት እንደሚቻል አንዱአለም ቢያስረዳኝ ደስ ባለኝ፤ ውሾ ሲሸናነፉ በሚያሳዩት ተፈጥሯዊ ምልክት ይግባቡና ጦርነቱን ያቆማሉ፤ ከዚያም በመካከላቸው ሰላም ይሰፍናል፡፡ ሁኔታዎችም ወደጥንቱ (statusquo ante) ይመለሱና ማኅበረከልባዊ ሕይወት ትቀጥላለች (“ከልብ” ውሻ ማለት ነው – “ል” ጠብቃ አትነበብም)፡፡ ወያኔ ግን ያሸነፈውን ሁሉ በሕይወት ያለውን ብቻም አይደለም የሞተውን ሳይቀር እስከ&#4