መኢአድ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሊያደርግ ነው።
ለተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪውን አቅርቧል።
ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት የተቃውሞ ሰልፉን ቀን ይፋ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀቅ መኢአድ በፋሽሽቱ ወያኔ በጋምቤላ በጉራፈርዳ እና በሱማሌ ክልል እየተካሄደ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል በጋራ ለማስቆም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሳተፍበት ተከታታይ የተቃዉሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይደረጋል፡፡ ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ።
በዉጭም በሃገር ዉስጥም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ከጎናችን በመቆም ይህን ዘረኛ ስርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በድሞክራሳዊ ስርዓት እንቀይረዉ፡፡ ያለው መኢአድ አስፈላጊዉን ዝግጅት ሁሉ አጠናቀናል፡፡ ሲል ለተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ እንዲዘጋጅ ጥሪውን አቅርቧል።#ምንሊክሳልሳዊ