(በፍቃዱ ወ/ገብርኤል) የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ዘጠነኛ አመቱን የያዘ ሲሆን በአገረ አሜሪካም ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሎምበስ ኦሃዮ ይከበራል። የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለዘመናት ተጨቁነውና ተመዝብረው፤ ተንቀውና ተገልለው በሁለተኛና ሶስተኛ የዜግነት ደረጃ ይታዩ የነበሩትን ብሄር ብሄረሰቦች መብትና ነጻነት ያረጋገጠውን የፌደራል ስርአት ለመዘከርና አጽናኦት ለመስጠት ሲሆን በዚህም በአል ብሄር ብሄረሰቦች በተወካዮቻቸው አማካይነት ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትና ከሌሎች የሚተዋወቁበት፤ ልምዳቸውንና አገራዊ ጉዳዮችን የሚወያዩበት፤ የጋራ እምነታቸውንና ተስፋቸውን የሚጋሩበት የአንድነታቸው የደስታ መግለጫ መድረክ ነው። የኢትዮጵያ ፌደራል ስርአት የህዝቦችን እኩልነት ያረጋገጠና ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ለአገሪቱ አንድነት ሰላም መረጋጋትና እድገት መሰረት የጣለ አዲስ ግኝት ነው። ይህ ህያውና አዳጊ ተመንዳጊ የሆነ የአንድነት መሰረት ዛሬ ኢትዮጵያ በጽናት እንድትቆም ያስቻላት ብቻ ሳይሆን በምታደርገው ፈጣንና ሁለገብ የዕድገት ጎዳና ጉዞ ከምትራመድበት ሁለት እግሮችዋ መካከል የመጀመሪያው ነው። እንደሚታወቀው ሁለተኛው ደግሞ የምትመራበት የልማታዊ መንግስት መርሃ ግብር ነው። የብሄር ብሄረሰብች ቀን ሲታሰብና ሲዘከር የዛሬዋ ኢትዮጵያ የመንፈስና የነፍስ አባት (Founding Father) ከሆነው ከታጋዩ ከመለስ ዜናዊ ጋር ስሙ ሳይጠቅስ የማይታለፈው ዋልልኝ መኮንን ነው። የብሄር ብሄረሰቦች የመብትና የእኩልነትን ጥያቄ በአደባባይ በማስተጋባት የአደባባይ ምስጢርንቱ ተገፎ በኢትዮጵያ የፖሊቲካ መድረክ የመሃል መስመር ስፍራ (main stream politics) እንድሆን ካበቁት ስመ-ጥር የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦች ልጆች መሃል ዋለልኝ መኮንን አንዱ ነው። ዋለልኝ መኮንንን የተለየ ቦታ እንዲሰጠው የሚያደረገው የንጉሱን ስርአት ጸረ-ህዝብነትና በህዝቦች ላይ የተጫነውን ‘fake’ የ”ኢትዮጵያዊንትን” ጭንብል በዛ በጭለማ ዘመን በሰላ ብዕሩ በአደባባይ ማራቆቱ […]

የደህንነትና ፖሊሶቹን በመጣስ ህዝቡ ወደ ሰማያዊ ጽ/ቤት እያቀና ነው፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች ከሚያዋክቡትና በርካቶችን በማሳሰል ከሚታወቁት መካከል አንዱ ደህንነት ፊት ለፊት የሚያየው ነው፡፡ ከእሱ አጠገብ አራቱም ፊታቸውን አዙረው የሚሄዱት ደህንነቶች ናቸው፡፡ሰላማዊ ሰልፉ ሊጀምር ደቂቃዎች ቀርተውታል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚገኘው ህዝብ ከሌሎች ቦታዎች የሚነሱት በመጠባበቅ ላይ ናቸው
Image
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተላለፈ መልዕክት and update (Read more)

መነሻውን ሰማያዊ ጽ/ቤት የሚያደርገው እንደተጠቀ ሆነ ባለው አፈና እና ወከባ ምክንያት ሰላማዊ ሰልፉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ መነሻውን እንዲያደርግ ወስነናል፡፡ እነዚህን የሰልፍ መነሻዎች የምንገልጽ በመሆኑ ህዝቡ በንቃት እንዲከታተል እንገልጻለን! ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!
update
ሰላማዊ ሰልፉ በሚነሳበት የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በኩል ወደ መገናኛ እና 22 የሚያሳልፈው መንገድ ተዘግቷል፡፡ ከመስቀል አበባይ፣ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ በካሳንቺስ አድርጎ የሰማያዊ ፓርቲ የሚገኝበት እንደራሴ በኩል ወደ 22 እና መገናኛ የሚያስኬደው መንገድ ተዘግቷል፡፡
update
በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የ9ኙ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት አዲስ አበባ የሚገኘውን ዝግጅት እየተቀላቀሉ ነው፡፡
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተላለፈ መልዕክት!

ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚነሳው ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመስቀል አደባባይ ቅርብ የሆኑ10 ቦታዎች ላይ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጁቱ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚጀምር በየቦታው ካሉ አስተባባሪዎች መረጃ ደርሶናል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረግባቸዋል በተባሉ መሰመሮች የሚሰሩ ታክሲዎች በግዳጅ በሌሎች ቦታዎች እንዲሰማሩ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ማክሰኞ ህዳር 23/07 ዓ.ም ወደዚያች ንዳድ ወደሆነችው ዝዋይ ከተማ ስንደርስ ከረፋዱ 3፡00 ነበር፡፡ ያንን መከረኛ መንገድ እንደዋዛ አልፈን ወደ ግዞት ቤቱ ስንገባ በመመላለስ የተግባባናቸው ጠባቂዎች በፈገግታ ተቀበሉን፡፡ ሙሉ አድራሻችንን አስመዝግበን ያመጣነውን ስንቅ በማስፈተሽ ጠያቂና እስረኛ የሚገናኝበት ቦታ ላይ ስፍራችንን ያዝን፡፡ የዛሬው ቀን ግን ከሌላው ሳይለይ አይቀርም፡፡ ከተቀመጥን ደቂቃዎች ቢያልፉም ስለታሰረ ብቻም ሳይሆን አብረውት ቢያወሩ የሚናፍቁት ተመስገን አልመጣም፡፡ ከእንቅልፍ አልነቃ ይሆን? እንደምንመጣ ስለሚያውቅ ግን ይሄ ሊሆን አይችልም፡፡ ተመስገንን እንዲጠራልን የላክነው እስረኛ መልዕክቱን እንዳስተላለፈ ነግሮን አለፈ፡፡ ይህ ልጅ ታማኝ ከሚባሉት እስረኞች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ እነዚህ ታማኝ እስረኞች ከመታመናቸው የተነሳ ከጊቢውም ወደ እየወጡ እንደሚመለሱ የከተማው ነዋሪ የሹክሹክታ ወሬ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ መቼም ከተማ የሚወጡት ከዝዋይ ሀይቅ አሳ ሊያጠምዱ እንዳልሆን ግልፅ ነው፡፡ የወታደሮቹ ሀላፊ መጥቶ ገርመም አድርጎን አለፈ፡፡ እሱን ተከትሎ ሌሎች ሁለት ወታደሮች በተመሳሳይ ሁኔታ አይተውን ተመለሱ፡፡ ነገረ ስራቸው አላማረንም፡፡ ይሄን መታገስ አልቻልንም፤ ድምፃችንን ከፍ አድርገን መናገር ጀመርን፡፡ ‹ተመስገን ሳይመጣ 40 ደቂቃ አለፈው፤ ኸረ የተመስገን ያለህ› ብንልም ሰሚ ግን አልነበረም፡፡ በቦታው ከተገኘን ከ55 ደቂቃ በኋላ ታማኙ እስረኛ ተመስገን ሲጠቀምባቸውን የነበረውን እቃዎች ወረቀት ከያዙ ወታደሮች ጋር ይዞ ሲመጣ የማደርገውን ነገር እስካጣ ድረስ ድንጋጤ ወረረኝ፡፡ እንዳልናገር ምላሴ ተያያዘ፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ለማ፡፡ ከፊታችን ሊደርሱ ጥቂት የቀራቸውን ወታደሮች ‹‹ተመስገንስ? ተሜስ›› አልኳቸው፡፡ እነሱ ግድም አልሰጣቸው፡፡ የመጣሁትን ስንቅ ዕየደባበሱ ‹‹ተመስገን ትላንት አዲስ አበባ ሄዷል››፤ ‹‹የምን አዲስ አበባ ነው? መቼም ወደቤት አይሄድም?››፡፡ ወደ ቃሊቲ በለሊት መሄዱን አረዱን፡፡ አሁን ተናድድኩ፡፡ ‹‹ትላንት ከሰዓት ጠይቀነዋል፤ አንደሚሄድ እሱም አያወቅም ነበር፤ ለኛም አልንገራችሁን ሌላው ቢቀር ደውላችሁ ብትነግሩን ምን ነበረበት?›› መልስ ሳይሰጡን የራሳቸውን ወሬ ማውራት ጀመሩ፡፡ ያመጣሁት ምግብና ቡና እናታችን ዕረፍት አጥታ የሰራቸው ነው፡፡ ድካሟን ሳስበው አዘንኩላት፡፡ ምን ማድረግ ይቻላል? ምንም፡፡

ያመጣሁትን ምግብ ለክንፈሚካኤል (አበበ ቀስቶ) እንድሰጥ እንዲጠሩልኝ ብጠይቅም አልሆነም፤ ግን እናድርስላቹሁ የሚል ሀሳብ ከወታደሮቹ መጣ፡፡ አማራጭ ስለሌለን ቡናና ምግቡን ሰጥተን ተመሰገን ሲጠቀምባቸው የነበሩትን እቃዎች ይዘን ተመለስን፡፡ ተልዕኮአችን ሳይሳካ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ፡፡

ቃሊቲ ዞን 3
እንግዲህ ተመስገን ለሚወዳት ሀገሩ ሲል ከቂሊንጦ ዝዋይ፤ ከዝዋይ ደግሞ ቃሊቲ መንከራተቱን ተያይዞታል፡፡ መከራውን የሚያብሰው ደግሞ ከቃሊቲ እስር ቤት እጅግ አስከፊ ወደሆነው ቦታ መዘዋወሩ ነው፡፡ ዞን 3 ይባላል፡፡ ዞኑ ምን እንደሚመስል ዛሬ ከሰማሁት ጥቂት ላካፍላችሁ፡፡ መግቢያው ላይ ‹በከፍተኛ ጥበቃ ስር የሚገኝ› ይላል፡፡ በዞን 3 የሚገኙት እስረኞች በጠቅላላ ማለት ይቻላል በተደጋገመ ስርቆት፣ ማጭበርበርና አስገዳጅ የሌብነት ወንጀል ሲፈፅሙ ተገኝተዋል የተባሉ እስረኞች የሚታጎሩበት ዞን ነው፡፡ ታዲያ ተመስገን ይህ ቦታ እንዲገባው የተፈረደበት ስለምንድን ነው? እኛ ሳናውቅ የዘረፈው ነገር ይኖር? ህዝብ ሳይሰማ በሌብነት ንብረት አካብቶ ይሆን? ሰብዕናው ይህ እንዳልሆነ ለመመስከር ከኔ በላይ የከሳሾቹም ልብ ያውቀዋል፡፡ የዕሰረኞቹ ማደሪያ መጋዘን በቆርቆሮ የተሰራና ጠባብ ሲሆን በውስጡ ሙሉ ቃሊቲ እንኳን የማይችላቸው 300 እስረኞች ታሽገውበታል፡፡ ዛሬ ተመስገን 301ኛ በመሆን ነባሮቹን ተቀላቅሏቸዋል፡፡ የእነዚህ እስረኞች የመኝታ ሁኔታ የአንዱ ራስ ከስር ያንዱ እግር ከላይ ሲሆን በተለምዶ አስመራ ድርድር የሚባለውን መልክ ይወክላል፡፡ በርግጥ ይህ ለተሜ ትንሹ መስዋዕትነት ነው፡፡ መንፈሱን ለማድቀቅ፣ ጥንካሬውን ለማራከስ የታሰበ ቢሆንም የታመነለትን ምክኒያት ሊሸርፉት እንደማይችሉ ግን ነብሴ ትመሰክራለች፡፡ የሐዋሪያው ጴጥሮስ ተዘቅዝቆ መሰቀል ላመነበትስ አይደል! ለእነዚህ 300 እስረኞች ያለው የሻዎር አቅርቦት 1 ብቻ መሆኑ ደግሞ ሌላው ትንግርት ነው፡፡ አንድ ሰው በሳምንትም የመታጠብ እድል ላይኖረውም ይችላል፡፡ የመጋዘኑ መታፈን ለተባዮች ምቹ መኖሪያ ሆኗቸዋል፡፡ ተሜ ከከፋ ግፍ ወደ ከፋ ሰቆቃ ቢዘዋወርም ‹‹ለሀገሬ ስል ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው›› ያለውን እያደረገ እንደሆነ ስመለከት በፅናቱና በብርታቱ እደነቃለሁ፡፡

(በአማን ነጸረ) ሁለት ጽንፍ የያዙ ኃይላት ያገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ተቆጣጠረዋል–ያንድነት ኃይላት ነን ባዮችና ብሔረሰባውያን!! 2ቱም የየራሳቸው በጎ ጎን እና ለሀሳባቸው አሳማኝ ምክንያቶች እንዳላቸው እረዳለሁ፡፡ሆኖም በጎ በጎውን ላቆየውና የሚያሥከፋኝን ልናገር፡፡ያደፋፈረኝ የልሂቃኑን የብሔር መነሻ ከአመለካከታቸው ለማስተሳሰር የደፈረው የዶ/ር መረራ መጽሐፍ ነው፡፡ 1– ትናንት የተፈጸሙ በደሎችን ሽምጥጥ አድርገው ይክዳሉ ወይም ያለባብሳሉ፡፡ “እኔ አልጨቆንኩህም ሥርዓቱ ነው” ማለት አንድ ነገር ነው፡፡ነገር ግን ተጨቆንኩ ብሎ ያመነን ማኅበረሰብ–ያውም ስለጭቆናው ከአያት ቅድመ – አያቱ ብቻ ሳይሆን ከበዙ የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገሮች ሊረዳ የሚችልን ፊደል የቆጠረ ትውልድ ስለ አንተ አለመጨቆን ታሪክ እጽፍልሀለሁ ማለት ግብዝነት ነው!! “ነገሥታቱ እናንተን ብቻ ሳይሆን እኛንም ጨቁነዋል” የሚለው መከራከሪያ እኔ ራሴ ብዙ ጊዜ ብጠቀምበትም በኢ/ያ የጭቆና ትረካ አቀራረቡ ትክክል አልሆንልህ ይለኛል፡፡ምክንያቱም የአንድ ብሔር የራስ በተባለ ሰው (ብሔር) መንገላታትና ከራስ ውጭ ባለ ሰው(ብሔር) መንገላታት ያለው ትርጉም ይለያያል፡፡ለምሳሌ፡- የአጼ ቴዎድሮስ የሸዋን መሳፍንት እጅ መቁረጥ እና የአጼ ምኒልክ የኤርትራውያንን ምርኮኞች እጅና እግር መቁረጥ ታሪኩን እንደሚዳኘው ሰው የብሔር ማንነት ትርጉሙ ሊለያይ እንደሚችል መረዳት አለብን፡፡የምኒልክ ንጉሥ ተ/ሃይማኖትን እምባቦ ላይ መውጋት ራሱን እንደ ምኒልክ ልጅ ለሚቆጥረው የዛሬ ዘመን የጎጃም ልሂቅ ምንም ላይመስለው ይችላል፤ለወላይታው ልሂቅ ግን የምኒልክ ጦናን መውጋት የአባት ተግባር ሳይሆን በማንነት ላይ የተቃጣ የጎረቤት ትንኮሳ ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡የምኒልክ የደቡብ ሕዝቦችን የማስገበር ሂደት አፈጻጸሙ ታይቶ “ባልተወለደ አንጀቱ…” ቢባል አይግረመን፡፡ “እኔ ስላልተሰማኝ ለምን ይሰማችኋል??” አንበል!!በቃ!! የተሰማው የተሰማውን በተሰማው መጠን ይናገር!!ድርጊቱን እስካመንን ድረስ ቢያንስ […]

የተለያየ እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በአገር ላይ የመጣን ችግር በጋራ ሲከላከሉ ዘመናትን አስቆጥረዋል፡፡ የተቀያየሩት መንግስታት ሳይወስኗቸው፣ እምነታቸው ሳይለያያቸው በጋራ ችግሮቻቸውን ሲፈቱ ቆይተዋል፡፡ በእየ እምነቶቻችን ያሉት ጥልቅ ስነ ምግባሮች ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን ተሻግረው አብሮ ለመኖራችን ዋነኛ ሚስጥሮች ናቸው፡፡ በዚህ በኩል እምነቶቻችን ኢትዮጵያውያን ለተሳሰርንበት ድር ትልቅ ሚና እንዳላቸው መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ይህን ታሪካዊ መስተጋብር ሲያደርጉ እምነታቸውን በነጻነት ያራምዱ ነበር ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት እምነታቸውን በነጻነት እንዳይከተሉ የተለያዩ በደሎች ደርሰውባቸዋል፡፡ የእምነት ነጻነታቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ትግልም ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል፡፡
Image
ህወሓት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜም ጀምሮ እንደሚያከብር ቃል ከገባቸውና በህገ መንግስቱም ካሰፈራቸው ጉዳዮች መካከል የእምነት ነጻነት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ሆኖም ይህን መብት በየ መድረኩ ለፕሮፖጋንዳነት ከመጠቀምና የወረቀት ጌጥ ከመሆን አልፎ መሬት ላይ ሲተገበር አልታየም፡፡ ገዥው ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በህገ መንግስቱ ካስቀመጠውና በየ መድረኩ ከሚናገረው በተቃራኒ የእምነት ተቋም መሪዎችን ካድሬዎቹ በማድረግ ህዝብን ለመያዝ እየጣረ ይገኛል፡፡ ይህን የገዥው ፓርቲ አካሄድ የተቃወሙ ምዕመናን በአሸባሪነት፣ በጸረ ሰላም ኃይልነት፣ በአፍራሽነት…እና በሌሎችም ስርዓቱ በመፈረጃነት በሚጠቀምባቸው ስሞች ሲከስ፣ ሲያስርና እርምጃ ሲወስድ ኖሯል፡፡ ለአብነት ያህልም የሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ስርዓቱ ከሚፈልገው ውጭ እምነታቸውን እንዳይከተሉ እያደረገ እንደሚገኝ መጥቀስ በቂ ነው፡፡

በኢህአዴግ አገዛዝ እምነቱን በነጻነት እንዳይከተል በደል ሲደርስበት ከቆዩት መካከል የሙስሊሙ ማህበረሰብ አንዱ ነው፡፡ ኢህአዴግ በአንድ በኩል የእምነት ነጻነትን እንደሚያከብር እየተናገረ በእውኑ ግን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን መሪዎች እምነቱ ከሚፈቅደው ውጭ በቀበሌ እስከመምረጥ ደርሷል፡፡ እምነታቸው ባስቀመጠው መሰረት መሪዎቻቸውን መምረጥ እንዳለባቸው ድምጻቸውን ያሰሙ የእምነቱ ተከታዮች በስርዓቱ ከፍተኛ በደል ደርሶባቸዋል፡፡ ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው መብታቸው እንዲከበር በመጠየቃቸው ብቻ ጸረ ኢትዮጵያ፣ አሸባሪ፣ አክራሪና ሌሎች ስሞች ተለጥፎባቸዋል፡፡ በርካቶች በዘግናኝ እስር ቤቶች ታጉረዋል፣ በቅዱሱ የረመዳን እለት ሳይቀር በስርዓቱ ታጣቂዎች በጭካኔ ተደብድበዋል፤ የእስልምና እምነት ስርዓት ከሚፈቅደው ውጪ መስጊዶቻቸው ተደፍረዋል፡፡ በተለይ ባለፉት 3 አመታት መብታቸው እንዲከበር በሰላማዊ መንገድ የጠየቁት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ታሪካዊ በደል ስርዓቱ የእምነት ነፃነትን በማታለያነት ከመጠቀም ውጭ በህገ መንግስቱ ያሰፈረውን መብት እንደማያከበር፣ ከዚህም አልፎ ጸረ እምነት ስለመሆኑ ቋሚ ማሳያ ነው፡፡

ስርዓቱ የተጠናወተው እምነትን በመሳሪያነት የመጠቀም፣ የእምነት መሪዎችን ካድሬ የማድረግና ህዝብን የመሸበብ መጥፎ አባዜ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይም በግልጽ ሲንፀባረቅ ቆይቷል፡፡ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ክርስትና እምነትን ከቆዩ ስርዓቶች ጋር በማዛመድ በጠላትነት ፈርጆታል፡፡ የእምነቱ መሪዎችንም መሳሪያ ለማድረግ የሚቻለውን ያህል ደክሟል፡፡ ከዚህ አለፍ ሲል ደግሞ ኢትዮጵያውያንን በእምነታቸው ለመከፋፈልና ለማጋጨት ጥረት እንዳደረገ በርካታ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ልክ እንደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ፤ የክርስትና በተለይም የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች የስርዓቱ መጥፎ አባዜ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፡፡

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፉት 24 አመታት ኦርቶዶክስ ተከታዮችን ከሌሎች የእምነት ተከታይ ኢትዮጵያን ጋር ለማጋጨት ከመጣር ባለፈ ካድሬዎች በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዲወስኑ ትልቅ ስራ ሰርቷል፡፡ ይህ ጥረቱ በልማት ስም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እጅግ የሚከበሩ ገዳማትን እስከ ማፍረስ ደርሷል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስር የተቋቋሙና ከእሱ ካድሬያዊ መስመር ጋር ለመሄድ ያልፈቀዱ ተቋማትንና ግለሰቦችን ማጥቃቱንም ቀጥሏል፡፡ በማህበረ ቅዱሳን ላይ ሊወስድ ይችላል የሚባለው እርምጃ እንደምሳሌ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በሌሎች አማኞች ላይም ተመሳሳይ በደል እንደሚፈጸም ይታወቃል፡፡

ህወሓት/አህአዴግ የእምነት መሪዎችን ካድሬዎቹ ማድረግ የሚፈልገው የእሱ መሰረታዊ የፖለቲካ አቋም ስለ እውነት፣ ስለ አንድነት፣ ስለ ሰላም ከሚያስተምሩት የእምነት መርሆች ጋር ፍጹም ተቃራኒ በመሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በእምነታቸው መሰረት ስለ አንድንት ሲሰበኩ የኢህአዴግ የመግዢያ መሳሪያ የሆነው ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው ዋጋ አልባ እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በየ እምነቶቻቸው ስለ ሰላም ሲሰበኩ ከኢህአዴግ የጦረኝነት ባህሪ ጋር ቢጋጩ የሚገርም አይሆንም፡፡ በእየ እምነቶቻቸው ስለ እውነት የሚሰበኩት ኢትዮጵያውያን መሰረቱን በሙስና፣ በሀሰትና በፈጠራ የተመሰረተ ስርዓት የሚጠብቃቸው እርምጃ አሁን ኢህአዴግ የሚወስደውን አይነት ቢሆን ሊገርም አይችልም፡፡ በመሆኑም በኢህአዴግና በምዕመናን መካከል የሚታየው ተቃርኖ በነጻነት እምነትን የመከተልና የጸረ እምነትነት ነጭና ጥቁር ተቃርኖ ነው፡፡

እንዲህም ሆኖ ግን በርካታ ኢትዮጵያውያን በእምነታቸው ለመጽናት ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም በእስር ላይ የሚገኙት፣ እንዲሁም ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በጁምዓ እለትና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በጽናት ትግላቸውን የቀጠሉት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትልቅ አርዕያ ናቸው፡፡ ስርዓቱ በጥይትና በቆመጥ ሊገታው ያልቻለው ይህ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹም ተምሳሌት የሚሆንና ሊደነቅ የሚገባም ነው፡፡ በተመሳሳይ በየ ገዳሙና በሌሎችም ተቋማት የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ኢህአዴግ ከሌሎች ጋር ለማጋጨት ሲጥር፣ በእምነታቸው ጣልቃ ሲገባና መሪዎቻቸውን ሊመርጥ ሲሞክር በመቃወም ትግላቸውን ቀጥለዋል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ይህን ገዥው ፓርቲ በኢትዮጵያውያን ምዕመናን ላይ የሚፈጽመውን በደል እና ምዕመናኑ የእምነት ነጻነትን ለማስከበር የሚያደርጉትን ትግል ከልብ ይደግፋል፡፡ ይህን ሲያደርግ ሀይማኖት ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ ትልቅ ድር እንደሆነ፣ ትውልዱን በመልካም መንገድ ለመቅረጽ ካለው ትልቅ ሚና አንጻር እና ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያውያን የእምነት ነጻነት ሊከበርላቸው የሚገባ መሰረታዊ መብት በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም ስርዓቱ እየፈጸመው የሚገኘውን ታሪካዊ ስህተት የትኛውም ኢትዮጵያዊ ሊቃወመው የሚገባ እንደሆነ እናምናለን፡፡

ትብብሩ የአንድ ወር መርሃ ግብር አውጥቶ ሲንቀሳቀስ የመርሃ ግብሩ አንድ አካል ካደረጋቸው መካከል አማኞች በየፊናቸው ለአገራቸው እንዲጸልዩ የጠየቀበት ይገኝበታል፡፡ ይህን ስናደርግ ኢትዮጵያውያን አማኞች በአገራቸው ላይ የሚመጣን አደጋ፣ በራሳቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸምን በደል በጋራ በመከላከል ያላቸውን ተሞክሮ፣ አቅምና ታሪካዊ ግዴታም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ መርሃ ግብሩን ይፋ ካደረግንበት ጊዜ ጀምሮ ለጥሪው አመርቂ መልስ ማግኘታችን ምዕመናን ለለውጥ ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጦልናል፡፡ ወደፊትም ከገጠመን መከራ እንድንወጣ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን በእምነታቸው ላይ ከሚደርስባቸው በደል ሳይበግራቸው ከጎናችን እንደሚሆኑ ጥርጥር የለንም፡፡

ትብብሩ ህዳር 27/28 ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል የ24 ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋል፡፡ ይህ መርሃ ግብር ለኢትዮጵያውያን ምቹ ስርዓት ለመመስረት የሚያስችል የትግል ጉዞ እንደሚሆንም እናምናለን፡፡ በመሆኑም ፀረ እምነት በሆነው የገዥው ፓርቲ አካሄድ እምነታቸው እየተረገጠ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእምነት ነጻነታቸውን ለማረጋገጥ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የአዳር ሰልፉን ቅስቀሳ እንዲደግፉና በሰልፉም በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ታሪካዊ ግዴታችን በመወጣት የእምነት ነጻነታችንን እናረጋግጥ!

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

የፍርድ ቤት ሙሉና የተጣራ ዘገባ በቂሊንጦ ልሳን

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የፋክት መፅሄት ዓምደኛ እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ለኮሚቴዎቻችን አስደናቂና አስደማሚ ምስክርነታቸውን ሰጡ።
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
★የቂሊንጦ ልሳን
(የኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች ድምፅ)

⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄

ህዳር 25/2007 ዕለተ ሃሙስ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው ጉዳያቸውን CMC ከዲቦራ ት/ቤት አጠገብ በሚገኝው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እየተከታተሉ የሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችንና ወንድሞቻችን በዛሬው እለት እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አቅርበው አስደናቂ የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን እንደሰጠ ተገለፀ።

እንደሚታወሰው ትላንት ህዳር 24/2007 ዕለተ ረቡዕ በዋለው ችሎት የቲሞች አባት የሆኑትና በነኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ 12ተኛ ተከሳሽ የሆኑት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ለ9ኛ ተከሳሽ ለሆኑት ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ሲሆን በተለይም በጭብጡ ላይ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት የደረሰባቸውን የህግ ጥሰትና ኢ-ሰብዓዊ ድብደባና እንግልቶችን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። በማያያዝም ቃሉን በሃይል እንደሰጠና አካላዊ ድብደባው አሁን ድረስ ምልክቱ እንደሚታይ ገልፀዋል።

በፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮ መሰረትም መሪዎቻችንና የሰላም አምባሳደሮቻችን በችሎት የቀረቡ ሲሆን ለተከታታይ ጊዜያት ዳኞች እንዲቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጡም በማረሚያ ቤቱ ያረባ ምክንያት የተነሳ ያልቀረበው፥ ህዳር 17/2007 ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ እንዲቀርብ በታዘዘው መሰረት ትላንት አመሻሹ ላይ ከታሰረበት ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ወደቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የመጣው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የፋክት መፅሄት ዓምደኛ እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አስደናቂና አስደማሚ የመከላከያ ምስክርነቱን ለኮሚቴዎቻቻንና ለወንድሞቻችን ሰጥቷል።

እንደሚታወቀው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የፋክት መፅሄት ዓምደኛ እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 9ኛ ወንጀል ችሎት፣ ጥቅምት17 ቀን 2007 በህገ መንግስቱ የተፈቀደውን የመፃፍና የመናገር መብት በመጣስ የፌደራሉ አቃቤ ህግ ካቀረባቸው 3ት ክሶች ውስጥ የወንጀል ህግ 257(ሀ)ን በመተላለፍ የተመለከተውን “በፍትህ ጋዜጣ ላይ አመፅ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በራሱና በሌሎች አመንጭነት እንዲታተሙ ማድረግ” በሚለው በአንዱ ክስ ብቻ የ3ት አመት ፅኑ እስራት እንደፈረደበት ይታወቃል።

ዛሬ ህዳር 25/2007 ዕለተ ሃሙስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ታጅቦ በፍርድ ቤት ቀርቦ የመከላከያ ምስክርነቱን የሰጠ ሲሆን ያስረዳውም ጥር 11/2004 በታላቁ አወሊያ መስጂድ ቅጥር ጊቢ እንደተገኝ በመግለፅ ሶስቱን ጥያቄዎች ህዝቡ እንደጠየቀ፣ ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ ና ህዝባዊ እንደነበር፣ የጥያቄው መነሻ ህዝበ ሙስሊሙ እንደሆነ፣ ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ለህዝቡ ጥያቆዎቻችሁን አቅርቡ ብሎ በመድረኩ ተናግሮ ህዝቡም በወረቀት እየፃፈ እንደሰጠ፣ በአጠቀላይ ምርጫው ፍትሃዊ እንደነበረና ኮሚቴዎቹም በህዝብ እንደተመረጡ አስረድቷል።

በመቀጠልም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥር 11/2004 ላይ ጥር 18/2004 እንገናኝ ብለው ቀጠሮ በሰጡት መሰረት በአወሊያ እንደነበር በመግለፅ በውቅቱም ከህዝቡ የመጡትን ጥያቄዎች ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጠቢያ እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳደረሱ በመድረክ መግለፃቸውን አስረድቷል። የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄዎችና የኮሚቴውን ሂደትም በሚያዘጋጀው ጋዜጣ ላይ እንዳወጣውምገልፆዓል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሃምሌ 9/2004 የህግ አዋቂውን ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን፣ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን፣ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋን፣ የታሪክ ሙሁሩን ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ቃለ መጠይቅ ማድረጉን በመግለፅ በቃላ መጠይቁ ላይም በዋናነት የሚያጠነጥነው ጥያቄዎቻቸው እንዳልተመለሱና ጥያቄውም እስኪመለስ ድረስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደሚቀጥሉ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

ተመስገን ደሳለኝ አያይዞም የመንግስት ባለስልጣን የሆኑት አ/ቶ ሪድዋን ሁሴን በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ በመቅረብ “ኮሚቴው አላማው ኢስላማዊ መንግስት ማቋቋም ነው” ብለው መግለጫ ሲሰጡ ማየቱንና ኡስታዝ አቡበክርን ስለሁኔታው ጠይቆት በጭራሽ አላማቸው እንዳልሆነ መግለፁን አስረድቷል፤ ተመስገን ጨምሮም በወርሃ መስከረም የተካሄደው የመጅሊስ ምርጫ መንግስት በቀበሌ ይሁን ያለው ” መንግስት ለ23 ዓመታት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በቀበሌ ምርጫ እያካሄደ ጨፍልቋል፥ አሁንም ለመጨፍለቅ ነው፥ ከጨፍላቂዎቹ አንዱ ደግሞ አ/ቶ ሪደዋን ሁሴን ናቸው” ብሎ አስደማሚ ንግግር አርግቷል።�

በቀጣይም ኡስታዝ ያሲን ኑሩ በነአቡበክር አህመድ መዝገብ ለተካተቱት ለኡስታዝ ሙራድ ሽኩር የመሰከሩ ሲሆን በተለይም ማዕከላዊ እስር ቤት በተለምዶ ሳይቤሪያ ተብሎ በሚጠራው ክፍል ውስጥ አብረው እንደነበሩ በመግለፅ የተፈፀመበትን የመብት ጥሰትና ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ አጋልጠዋል።

ኡስታዝ ሙራድ ሽኩር ኮሚቴው ኢስላማዊ መንግስት ሊያቋቁም አቅዷል፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ ከአልቃዒዳ ጋር ግንኙነት አላቸው…ወዘተ እያሉ እየደበደቡና መስክር እያሉት እንደነበር ኡስታ ያሲን ገልፆዓል።

በማያያዝም ለኡስታዝ ሙራድ ሽኩር “ያሲን ጋር አብረን አንድ ክፍል ውስጥ ለምን እንዳረግንህ ታውቃለህ? አይተከዋል አይደል እንዴት ጨርቅ እንዳረግነው? ከእሱ እንድትማር ነው አንድ ክፍል ላይ ያስገባንህ” ይሉት እንደነበር ለፍርድ ቤቱ ገልፆዓል።

እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የመከላከያ ምስክርነታቸውን ከሰጡ በሁዋላ በፌደራሉ አቃቤ ህግ የቀረበላቸውን መስቀለኛ ጥያቄዎች በአስደናቂ ሁኔታ መልሰው ችሎቱ ተጠናቋል።
Image
የፍርድ ሂደቱ ነገም ይቀጥላል።

ፍትህ ለኮሚቴዎቻችን!
ፍትህ ፍትህን ለተነፈጉ!
ሰላምና መረጋጋት ለኢትዮጲያ ህዝብ!

የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የዕውቀት…መስዋዕትነት ተከፍሎባቸው የሚሰሩ ዘገባዎችን ሼር እና ኮፒ በማድረግ እንዲሁም በየሰሌዳን፣ በየጉረፑ፣ በየፔጁ በመለጠፍ መረጃውን ለሰፊው ማህበረሰባችን በማሰራጨት ኢስላማዊ ግዴታዎን ይወጡ!!!! ይጠቀማሉ!!! ኢንሻ አላህ

ህዳር 27 እና 28 2007 ዓ.ም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የሚያደርጉት የአዳር (24 ሰዓት) ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃ ላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን ሰው በሰውና ቲሸርት በመልበስ ቅስቀሳ ሲደረግ እንደቆየና በተለይ ዛሬ ህዳር 24/ 2007 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ በአዲስ ከተማ፣ ጉለሌ፣ አራዳ፣ የካ፣ ንፋስ ስልክ፣ ኮልፌና ሌሎች የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማዎች ወረቀት በመበተን የተሳካ ቅስቀሳ መደረጉን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ለአዳር ሰልፉ ሲቀሰቅሱ ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ሜሮን አለማየሁ፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ባህረን እሸቱ፣ ማቲያስ መኩሪያ እንዲሁም ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲቀሰቅስ የነበረው ሲሳይ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ተግልጾአል፡፡

ከአሁን ቀደም ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ ሲያደርጉ በርካታ የፓርቲው አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ያስታወሱት አቶ ዮናታን ‹‹ይህ የገዥው ፓርቲ የተለመደ እርምጃ ነው፡፡ በቀጣይነትም ሌሎች አባላትንና አመራሮች መታሰራቸው አይቀረም፡፡ ትግሉ መስዋዕትነት የሚያስከፍል እንደመሆኑ በእስሩ ሳንገታ ትግሉን እንቀጥላለን፡፡›› ሲሉ እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ የዛሬው ቅስቀሳ 12 ሰዓት ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ነገ ጠዋት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Image

Image

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለንግዱ ማህበረሰብ ጥሪ ቀረበ ::

ጥሪው እንደሚከተለው ነው::
የንግድ ማህበረሰብ ለአንድ አገር ምሰሶ ነው፡፡ በዴሞክራሲ በበለጸጉ አገራት የንግዱ ማህበረሰብ ለራሱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ያለውን ፈርጣማ የኢኮኖሚያዊ አቅምና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ የሚፈጥርለትን የተሻለ ንቃተ ህሊና በመጠቀም ለጭቁኖች መከታ ሲሆን ታይቷል፡፡ ለዚህም ነው የንግዱ ማህበረሰብ ዴሞክራሲን በመገንባት ትልቅ ሚና እንዳለው የሚነገርለት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ባለው ሁኔታ የንግዱ ማህበረሰብ በነጻነት ሰርቶ የሚበለጽግበት፣ ወገኑንና አገሩን በተለያየ መንገድ የሚያግዝበት መንገድ በመዘጋቱ የሚገባውን ያህል አስተዋጽኦ አበርክቷል ለማለት ይከብዳል፡፡

ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት ጊዜ ነጻ ገበያን እንደሚከተል በመግለጹ የንግዱ ማህበረሰብ በነጻ ገበያ መርህ ተወዳድሮ ራሱንም አገሩንም ይጠቅማል የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም ይህ ተስፋ እውን ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ይልቁንም ገዥው ፓርቲ የራሱን የኢኮኖሚ ኢምፓየር በመመስረት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ስርዓት አበላሽቶታል፡፡ በራሳቸው ነግደው የሚያድሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ግልጽነት በጎደለው መንገድ የአገሪቱን አንጡራ ሀብት እየተጠቀሙ ከሚገኙት የገዥው ፓርቲ ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር መወዳደር አቅቷቸው የከሰሩት በርካቶች ናቸው፡፡ በተለያየ መንገድ አሁንም ድረስ የቀጠሉትም ቢሆን ከገዥው ፓርቲ ተቋማት ጋር መወዳደር ተስኗቸው ለራሳቸውም ሆነ ለአገራቸው ማበርከት የነበረባቸውን አስተዋጽኦ እንዳያበረክቱ ተደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ለገዥው ፓርቲ ባለማደራቸው ምክንያት አግባብ ያልሆነ ቀረጥና ሌሎች ጫናዎች እየተጣሉባቸው አንድም ከገበያ ወጥተዋል፡፡ አሊያም የሚገባቸውን ጥቅም ማግኘትና አገራቸውን መጥቀስ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ለገዥው ፓርቲ መዋጮ እንዲከፍሉ ከመጠየቃቸውም በላይ ስርዓቱ ባነገሰው ሙስና ምክንያት እጅ ተወርች ተይዘው ራሳቸውን፣ ህዝባቸውንና ለአገራችን ዴሞክራሲ ግንባታ ያበረክቱትን የነበረው አስተዋጽኦም ተገድቧል፡፡
በሌላ በኩል በገበያው ላይ የሚቆየው ለስርዓቱ ያደረ ብቻ በመሆኑ በርካቶች ለአገር ከመስራት ይልቅ ለገዥው ፓርቲ ማደር መርጠዋል፡፡ በዚህም አንድ የንግድ ማህበረሰብ ለአገሩ ያበረክት የነበረውን አስተዋጽኦ ረስተው የተሳሳተ መንገድ ይዘዋል ብለን እናምናለን፡፡ ራሳቸውን ለገዥው ፓርቲ አሳልፈው በመስጠታቸውም ታሪካዊ ግዴታቸውን ሳይወጡ ቀርተዋል፡፡ ይህን ስንል ግን ከገዥው ፓርቲ ተጠግተው ከሚያገኙት ጥቅም ይልቅ ከህዝብ ጋር ቆመውና ግዴታቸውን እየተወጡ መስዋዕትነት የሚከፍሉ የሉም ማለት አይደለም፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት የንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቅበትን ያህል እየሰራ እንዳልሆነ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

የንግዱ ማህበረሰብ ስርዓቱ በራሱም ሆነ በአገሩ ላይ የሚፈጽመውን ህገወጥነት በየግሉ ከመቃወምም ባሻገር ትግሉን በማገዙ ወደፊት ለራሱም ሆነ ለአገሩ የሚያሰራ ስርዓት መፍጠር ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ በመሆኑም ስርዓቱ በራሱና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን በደል በመቃወም ላይ የሚገኙትን ተቃዋሚዎች ትግል በሞራል፣ በገንዘብና በሌሎችም ድጋፎች በማገዝና ትግሉን በመቀላቀል ለንግዱ ማህበረሰብና ለኢትዮጵያ የሚያዋጣትን ስርዓት እንድንመሰርት ጥሪ እናደርጋለን፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለንግዱ ማህበረሰብና በአጠቃላይም ለኢትዮጵያ የሚመች ስርዓት ለመፍጠር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህም መካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋል፡፡ ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን መብታቸው ተከብሮ የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ጮራ የሚፈነጥቅ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በመሆኑም የራሱንም መብት በማስከበርና የአገሩን ዴሞክራሲ በመገንባት ታሪካዊ ሚና ያለው የንግዱ ማህበረሰብ ትግላችን በመቀላቀል፣ በገንዘብና በሞራል በመደገፍ የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

ታሪካዊ ግዴታችን በመወጣት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንገንባ!

የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደተለመደው በጸረ ሰላም እና በጸረ ሕዝብነት በጥብቅ ይፈረጃሉ::
Minilik Salsawi

የወያኔው ጁንታ ስልጣኑን እንዳያጣ እየተፈረካከሰ ባለበት በዚህ ወቅት መጪው ምርጫ ከመድረሱ በፊት አስፈላጊውን ከለላ ለማግኘት ለመከላከያ ለፖሊስ እና ለደህንነት ክፍሉ ምርጫውን ተገን በማድረግ እና በማሳበብ የስልጠና ሰነድ ይዞ በየክፍሉ ካድሬዎችን በማሰራጨት የፓርቲውን አስተሳሰብ ለመጫን ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል::

ስልጠናው ዋናው ነጥብ በመጭው ምርጫ ህዝባዊ አመጾች የነጻነት እና ይመብት ጥያቄዎች እንዳይይፈነዱ ስጋት ያለብት ወያኔ በሰራዊቱ እና ደህንነቱ ላይ ያለውን ጥርጣሬ ለመቅረፍ እና ለማሳመን ያዘጋጀው ሰነድ እንዲሁን በግሩፕ እየለየ ጠላቱን ለመልቀም ያመቸው ዘንድ ያዘጋጀው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::

ምንጮቹ የስልጠናውን ሰነድ ጠቅሰው እንደተናገሩት በዋናነት በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ የተዘጋጀ ሲሆን እንደተለመደው በጸረ ሰላም እና በጸረ ህዝብነት ይፈረጃሉ::ድርጅቶቹ ለሃገር አደጋ እንደሆኑ እና ሰራዊቱን ሊበትኑ የተዘጋጁ እንደሆነ ታውቋል:: ምንጮቹ አክለው እንደተናገሩ በሃገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ሰራዊቱን ና የደህንነት ክፍሉን በመረጃ በዝርዝር ማስተማር አለባቸው:: ያሉ ሲሆን የሚያጉረመርሙ የሰራዊቱ እና ደህንነቱ ክፍሎች የለውጡ አካል እንዲሆኑ ከፖለቲካ ድርጅቶቹ ትልቅ ስራ ይጠበቃል ብለዋል::ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሰኝ አቀርባለሁ::

በምርጫ አለመሳተፍ መብት ነው !በኢትዮጵያ ያለው ጭላንጭል የፖለቲካ ምኅዳር ሲታይ፣ይህ ውሳኔ የሕግ፣የፖለቲካ እና የሞራል ድጋፍ አለው፡፡ሆኖም ግን በምርጫ ያለመሳተፍ መብት በራሱ-የራሱ የሆነ ተግዳሮቶች አሉትና፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትርፍ-ኪሳራ ሥሌት የግላቸው ነው የሚሆነው፡፡
Yidnekachew Kebede
ይህ ጹሑፍ በምርጫ አለመሳተፍ መብት መሆኑን ከህግ አንፃር ለማየት እንጂ፣ የሚጪው አገረ አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ “ኢሕአዴግ ለመርጫ አልተዘጋጀም !” እና “የ24 ሰዓት ተቃውሞ በአዲስ አበባ !” በሚል ዕርሶች ከዚህ በፌት በፃፍኳቸው ፁሑፍ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ፣ ገዥው መንግስት ለነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ እራሱን አዘጋጅቶ፣ ውጤታማ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል የግል እምነቴን ገልጫለው፡፡
ወደተነሳሁበት ዕርስ ስገባ፡- ማንኛውም ሰው በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንዲሳተፉ አይገደድም፣ባለመሳተፉ ግን ተቃውሞን የመግለፅ እና ደግፋ የመስጠት መብት ይነፈጋል ማለት አይደለም ፡፡ይህም በመሆኑ የትኛውም የዲሞክራሲ ሥርዓት የተሟላ ተሳትፎ በህብረተሰብ ካልተደረገበት ውጤታማነቱ ደካማ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡የዲሞክራሲ ሥርዓት ማሳያ መስታዎት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት መንቀሳቀስ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ያለምንም ፍርሃት በፈለገው ወይም በፈለገችው ፓርቲ ውስጥ አባል የመሆን ዕድልና አማራጭ ማግኘት የግለሰብ መብት ነው፡፡ግለሰቦች በፈለጉት የፖለቲካ ፓርቲ የመደራጀት እና የመሳተፍ ነፃነት ሲኖራቸው ለዲሞክራሲ መሠረት ይሆናል፡፡
ይህ አይነቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት በአገራችን ምን ያኸል ተፈፃሚ ነው ? ተብሎ ቢጠየቅ ምላሹን ለማወቅ ብዙም አድካሚ አይደለም፡፡ውጤቱ አሉታዊ ነው፡፡እርግጥ ነው በሕገ መንግስት አንቀፅ 31 ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓለማ በህግ “የመደራጀት” መብት እንዳለው በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ይሄን መነሻ በማድረግ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የተቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡የእነዚህ ፓርቲዎች መብት እና ግዴታ እንዲሁም ሊከተሏቸው የሚገባ መርህዎች፣ በሕገ መንግስቱ፣በፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጁች እዲሁም በመተዳደሪያ ደንብቻው ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ተቋቁመው እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአገራችን ቁጥራቸው በርካታ ቢሆንም፣ ቢሚፈለገው ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ግን በቁጥር አነስተኛ ፓርቲዎች ሲሆን፣ የተቀሩት የምርጫ መጣ ወይም የመግለጫ አሯሯጮች pacemaker መሆናቸው በግልፅ የሚታወቅ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋንኛ ዓላማ በመርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ የፓለቲካ ሥልጣን በመያዝ የቆሙለት ዓላማ በስልጣን ዘመን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡
ምርጫ በዲሞክራሳዊ አካሄድ ለሚወከል መንግስት የጥንካሬ መለኪያ ነው፡፡ይህን ለማለት የሚያስችለው ተመራጮች መብታቸው እና ግዴታቸውን ሙሉ በሙሉ ከመራጩ ሕዝብ ስለሚያገኙት ነው፡፡እንዲ አይነቱ በሕዝብ ተሳትፎ ሥልጣን የሚቀየርበት ዋናው መንገድ ነፃና ሚዛናዊ የሆነ ምርጫ ሲደረግ ብቻ ነው፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በኢሕአዲግ/ በህወሐት መንግሰት የ24 ዓመት የስልጣን ዘመን በተደረጉ ምርጫዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለመሆን አልቻለም፡፡ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በዋነኛነት የሥርዓቱ አስከፊ ድርጊት ቢሆንም፣ በተጨማሪ ጠንካራ የሆኑ በመላው ኢትዮጵያ የሕዝብ ድጋፍ ያለው የተቃዋሚ ፓርቲ አለመኖሩም ጭምር ነው፡፡ እርግጥ ነው በ1997 ዓ.ም በቅንጅት የታየው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መነቃቃት፣ በአገራችን የዲሞክራሲ በዓል አንድ እርምጃ ወደፊት ከነበረበት ያንቀሳቀሰው ቢሆንም፣ በገዥው ሥርዓት ቀጥተኛ ተፅኖ፣ እንዲሁም በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ በታየው ድክመት እና የስልጣን ሽኩቻ የለውጥ እንቅስቃሴውን ገትቶታል፡፡
አሁን ላይ በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከበፊቱ “በቆምክበት እርገጥ” አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተላቀው ምን ያህል “ወደፊት” እየሄዱ ነው የሚለውን ምላሽ ይህን ጹሑፍ ለሚያነቡ እና ለጉዳዩ ቅርብ ነኝ ለሚሉ ወገኖች የምተወው ሃሳብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአገር ውስጥ የሚንቀሣቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ6 ወር በኋላ አገር አቀፍ ምርጫ ይጠብቃቸዋል፡፡ፓርቲዎች የምርጫ ፓርቲ ቢሆኑም ፣በምርጫ አለመሳተፍ መብታቸው በሕግ የተጠበቀ መሆኑን አውቀው ግራ ቀኛቸውን ቢመለከቱ፣ዝም ብሎ ገዥውን ፓርቲ በምርጫ ከማጀብ ይላቀቃሉ፤አሊያም በእኩል ተሳትፎ ወደ ምርጫው የሚገቡበትን መንገድ ተገዳድረው ማመቻቸት ይቻላል፡፡
የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ቁ .573/2000 አንቀፅ 39 ቁ.2 ሐ.“ የፖለቲካ ፓርቲ ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን የጠቅላላ ወይም የአካባቢ ምርጫ ወድድርን ሳይሳተፍ የቀረ እንደሆነ ” ምርጫ ቦርድ በአዋጁ መሠረት ውሳኔ በማስተላለፍ ከመዝገብ ሊሰርዝ ይችላል፡፡የሚል የህግ ድንጋጌ አለ፣ይህን ድንጋጌ ከተነሳንበት ዓላማ ጋር በማገናኘት ምክንያት እና ውጤቱን መመልከት ተገቢ ነው፡፡
በመሠረቱ የፓርቲ ነፃነት በእንዲ መልኩ መገደብ አጠቃላይ የአዋጁ ችግር ዋንኛ ማሳያ ነው፡፡የትኛውም ፓርቲ በምርጫ የመሳተፍ ወይም ያለመሳተፍ መብት ካለጊዜ ገደብ ለራሱ ለፓርቲ የሚተው ስራ እንጂ ፣በህግ ገደብ የተጣለበት መሆን የለበትም፡፡ይህን ለማለት የሚያስደፍረው የግል እንዲሁም የጋራ መብት የሚጋፋ በመሆኑ ነው፡፡ለዚህም ማሳያ የመምረጥ እና ያለመምረጥ መብት የተጠበቀ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ በመጪው ምርጫ አልመርጥም ፣አልመረጥም ይህ በህግ ክልከላ ተደርጎብኝ ሳይሆን የእኔ መብት በመሆኑ ነው፡፡ልክ እንደኔ የግል መብት ያላቸው ሰዎች ተሰባበስበን የጋራ መብታችን ለማቋቋም በምንቀሳቀስበት ወቅት በግሌ ማድረግ የምችለውን በጋራ እንደማጣት ይቆጠራል፡፡ከዚህ አንፃር ይህ ድንጋጌ በእኔ እይታ ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሃቅ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሚተዳደሩት በዚህ አዋጅ ነው፡፡በመሆኑም አዋጆን መሠረት በማድገረግ በምርጫ አለመሳተፍ ገደብ ቢኖረውም ለፓርቲዎች የተሰጠ መብት አለ፡፡ ማንኛው ፓርቲ ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን ሳይሳተፍ የቀረ እንደሆነ ይሰረዛል፡-ይህ ማላት፣በ2002 አገር አቀፍ ምርጫ በማንኛውም ምክንያት በምርጫ ያልተሳተፈ “ሀ” የተባለ ፓርቲ በ2007 የማይሳተፍ ከሆነ ይሰረዛል ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይሄ “ሀ” የተባለው ፓርቲ በ1997 ምርጫ አልተሳተፈም ብንል ፣በ2002 ተሳትፏል ካልን በ2007 ምርጫ አለመሳተፍ የ”ሀ”ፓርቲ መብት ነው፡፡ይህም በማድረጉ ከምርጫ ቦርድ ምን አይነት ጥያቄ ለዚህ ፓርቲ አይቀርብም፡፡በዚህ መሠረት ፓርቲዎች ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን በምርጫ ካተሳተፉ የመሰረዝ እጣቸው በእጃቸው ነው፡፡ሆኖም ግን የምርጫ ዘሙኑ ተከታታይነት ሳይኖረው በምርጫ አለመሳተፍ በአዋጁ መሠረት የሚያስከትለው ውጤት አይኖረውም፡፡
ይህ ከላይ የቀረበው ማሣያ፣ ለአገር አቀፍ እንዲሁም ለአካባቢ ምርጫ የሚያገለግል ነው፡፡በአሁን ወቅት ሁለቱ ምርጫዎች በተመሳሳይ የምርጫ ዘምን ባለመካሄዳቸው እረሳቸውን ችለው የሚቆጠሩ የምርጫ ዘመን ነው፡፡በኢትዮጵያ አሁን ባለው የምርጫ ስርዓት ፣የአንድ የምርጫ ዘመን አምስት ዓመት ነው፡፡ስለዚህም በአገር አቀፍ እና በአካባቢ የምርጫ ዘመን የ2 ዓመት ልዩነት አለ ማለት ነው፡፡በመሆኑም በዘንድሮ የአገር አቀፍ ምርጫ ዘመን ከባለፈው ሁለት ዓመት ከተካሄደው የአካባቢ ምርጫ ዘመን ፈፅሞ የሚገኛኝ አይደለም፡፡
በሕገ መንግሥት አንቀፅ 38 ቁ.1 ሐ.“ በማናቸውም ደረጃ በሚካሄዱ ምርጫ፣የመምረጥ እና የመመረጥ ፣ምርጫው ሁሉ አቀፍ፣በእኩልነት ላይ የተመሰረት እና መራጩ ፈቃዱን በነጻነት የሚገልፅበት ዋስትና የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡”በማለት የህጎች ሁሉ የበላይ ሕግ በሆነው ሕገ መንግሰት በግልፅ ተቀምጧል፡፡
ሆኖም በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ሕገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ምርጫ ስለመካሄዱ አጠራጣሪለው የሚል ፓርቲ፣እንዲሁም ምርጫው ከመካሄዱ በፌት በምርጫው ሄደት ላይ ቅደመ ሁኔታ እስካልሟላለት ድረስ የታሰበው ምርጫ ነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አይደለም በማለት ከበቂ ምክንያቶች ጋር በማዛመድ ከላይ በተገለፀው የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ መሰረት፣ በምርጫ ያለመሳተፍ መብት በሕግ ድጋፍ ያላው መብት ነው፡፡
ይህ መብት ከሕገ መንግሰቱ እና ከላይ በተገለፀው አዋጅ የመነጨ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ ያሉ ማናቸውም አሰራሮች፣ልማዳች እንዲሁም መመሪያ ይህን መብት የሚጋፉ መሆን እንደሌለባቸው የታወቀ ነው፡፡እናም ፓርቲዎች ሁሌም የፖለቲካ ምኅዳሩ ተዘግቷል፣ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ አልቻልንም፣መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከለከልን……..ወዘተ እያሉ ከሚናገሩ፣ምኅዳሩ እንዲሰፋ ከገዥው ፓርቲ ጋር በመነጋገር ማስተካከል ካልተቻለ፣በጊዜ ከምርጫው ታቅበው ገዥው ፓርቲ እራሱ ደግሶ እራሱ ለብቻው ይስተናገድበት ዘንድ በመተው እውነታውን ለህዝብና ለዓለም ቁልጭ አድርጎ ማሳየት ነው፡፡እስከ መቼ በምርጫ መጭበርበር !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

መስታወት ራሱን አያይም ! ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳና
ሜሮን ጌትነት ፤
አበበ ተካ ፤

ይህን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ በሁሉም ዌብ- ሳይቶች ላይ ማለት ይቻላል ፣ የወጣ አንድ የአድናቆት ፅሁፍ ነው ። ጽሁፉ አንዲት ገጣሚትን ለማድነቅ የተፃፈ ነው ። የፅሁፉ ርእስ “ሐገሬ ፤ ሕዝቤ ፤ ክብሬ ” የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛ እንዲህ ተተርጉሟል ፤ “My Country, My People, My Honor” :: ይህ የአድናቆት ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ፤ ሚሮን ጌትነት በምትባል ኢትዮጵያዊት ዘመናዊ የፊልም ተዋናይ ችሎታና
በግጥሙ ታክኮ ለሃገሯ ያላት ልዩ ፍቅር ላይ ነው ።
ፅሁፉ ገና ሲጀምር ነው “The poet-artist with an “unconquerable soul?” በማለት ተዋናዩዋን ማንቆለጳጰስ የሚጀምረው ። ፀሃፊዋና አድናቂዋ ደግሞ በእንግሊዝኛ መፃፍ የሚቀናቸው አል ማርያም ናቸው ። እናም አል ማርያም ናቸው ከላይ እንደጠቀስኩት በሁሉም ዌብ ሳይቶች ላይ አድናቆታቸውን የናኙት ። የግል አድናቆታቸውን ትክክል ነው አይደለም የሚል ክርክር ወስጥ አልገባም ። ከዚህ በፊትም ይህቺው ሜሮን ጌትነት የተባለች ተዋናይ የተሳተፈችበትን “ድፍረት” የሚል ፊልምን ክሊፕ አይቼ በጣም ተደነቅኩባት ብለው አሞካሽተዋት ነበር ። ካለፈው ሙገሳቸው ላይ እንዲህ ሲሉ በመጨረሻ ባወጡት ፅሁፍ ላይም ቀንጭበው አስቀምጠዋል ፡፤

“… The beautiful young actress Meron Getnet sat stunned and speechless. She is visibly shocked and confused. She looked around in total disbelief trying to get someone to tell her what she has just heard is not true… In her seat, Meron clasps her palms in the traditional praying position as if to implore God’s intervention to save her and her country from such cruel public humiliation. An unidentified interviewer asks her how she feels. (How does one really feel when one’s heart is yanked out before the entire world!?) Meron is visibly brokenhearted. But she puts on a calm and brave face. She is struggling to hide her outrage and fury. She is fighting tears; but she does not breakdown though she is manifestly broken-hearted…”

እንዲህ ይተረጎማል ።

“…..ውቢቱ ወጣት ተዋናይ ሜሮን ጌትነት ፍዝዝ ብላ በዝምታ ተቀምጣለች ፤ እንደሚታየው ደንግጣለች ግራ ተጋብታለችም ። የሰማችውን ነገር ማመን ስላቃታት ዙሪያዋን እየቃኘች እውነት አይደለም የሚላት ሰው ፈለገች…… እንደተቀመጠች ሜሮን የእጆቿን መዳፎች በተለመደው የፀሎት አይነት ገጥማ፤ እግዚአብሄር እሷንና አገሯን ከህዝባዊ ውርደት እንዲያድናቸው ጣልቃ ገብነቱን እንዲያሳያት ተመኘች ። ያልታወቀ ቃለ መጠይቅ አድራጊ ምን እንደሚሰማት ጠየቃት ። (አንድ ሰው በመላው አለም ፊት ልቡ ቡጥርቅ ብሎ ሲወጣ ምን ሊሰማው ይችላል ? ) ሜሮን ልቧ እንደተሰበረ ይታያል ። ሆኖም ግን መረጋጋትና ጀግንነት ይታይባታል ። ብስጭትና ንዴቷን ለመደበቅ ትታገላለች። እንቧዋ ይተናነቃታል ፤ ግን እንባዋ አልወረደም ይሁንና ልቧ የተሰበረ መሆኑ በግልፅ ይታይባታል…….”
የትርጉሙ መጨረሻ ።

አል ማርያም ይህን ከላይ የሰጡትን ሙገሳ ያደረጉት የፊልሙን ቅንጫቢ ብቻ አይተው ነው። ሙሉውን ገና አላዩትም ከፅሁፍዎ እንደተረዳሁት ። እንዴት ነው በቅንጫቢው ብቻ ይህን ያህል ሙገሳ ያፈሰሱላት ። በፊልሙ ውስጥስ ከሷ ሌላ ተዋናዮች አልነበሩም ፤ የነሱስ ሚና ምን ነበር ? ብየ ልጠይቅ እገደዳለሁ ፤ መቼም አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብ ። እንደተመልካችና እንደ ውበቷ አድናቂ ቀደምብየ እንዳልኩት የተዋናይዋ የግል አድናቂዋ ከሆኑ የግል አመለካከትዎ ነውና ነውር የለበትም ። ፍቅር እንደ አፍቃሪው አይን ነው እንደሚባለው ፤ አድናቂም እንደዚያው ነው ። አድናቂና አፍቃሪ አለምንና ህይወትን እንደሚያይበት መነፅርም ይለያያል ።
“ድፍረት” የሚለውን ፊልም ወያኔ/ኢሕዲጎች እንዳይታይ ከለከሉ ። ይህ ዘረኛ አገዛዝ ይህን አደረገ ያን አደረገ ሲሉ የተቹት ግን አልገባኝም ። ፊልሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊታይ ከነበረበት ቦታ በፖሊሶች መከልከሉ እሙን ነው ። የፊልሙ ዳይሬክተር ዘረሰናይ መሃሪ እንደተናገረው በፍርድ ቤት ፊልሙ ክስ አለበት ተብለን ነው እንዳይታይ የተደረገው ሲል በጊዜው ለገባው ታዳሚ ገልጿል ። ዘረሰናይን ለሚያውቀው ደሞ ከማንም በላይ ለወያኔው ስርአት የተሻለ ቀረቤታ አለው ። እኔ እዚህ ላይ አል ማርያም ወያኒያዊውን አገዛዝ አይተቹ አይንቀፉ የሚል ፍላጎት የለኝም ።
“ድፍረት” ፊልም ግን በታገደ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲታይ ተፈቅዶ እየተየ ነው ። የፊልሙ ይዘትም ከወያኔ ስርአት ጋር ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ ተቃርኖ የለውም ። ወያኔ ለምን ሲል ያግደዋል ? የጠለፋ ጋብቻ ከወያኔያዊው ስርአት በፊትም ነበረ ፤ አሁንም አልፎ አልፎ ይኖራል ብዬ እገምታለሁ ። ይህው ሰሞኑን የሰማነው በታዳጊዋ በሃና ላላንጎ ላይ የተፈፀመ የደቦ አስገድዶ ድፍረት አንዱ ማሳያ ነው ። “ድፍረት” የሚለው ፊልም በራሱ እንዲያውም አገራችን ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ረገድ በጎ አስተወኦ አለው ብዬ አላምንም ። ይህ ራሱን የቻለ ሌላ ርእስ ስለሆነ በሌላ ጊዜ ልመለስበት እችላለሁ ።

አሁን ተመልሰን ወደ ተዋናይቷ ሜሮን ጌትነት እንምጣ ። የተዋናይነት ብቃቷንም ሆነ ገጣሚነቷ ላይ ዛሬ ልተች አልፈልግም ፤ የራሴ አስተያየት ቢኖረኝም ። አል ማርያም ሆይ የሚያደንቋትን የሜሮንን ግጥም እንደገና ያዳምጡና ወደራስዎ እንዲመለከቱ በዚህ አጋጣሚ ጋብዤዎታለሁ ።
“….መቼም የአሳ ዝላይ መልሶ ከውሃው ነው እመጣለሁ ዞሬ ፣ ስሜን ቀያይሬ ፣
ያኔ ይቀበለኛል ፤ ፍቅር ያጠግበኛል ህዝቤ ፤ አገሬ ፤ ክብሬ ፤”.. ….. ይላል አንዱ የገጣሚዋ ስንኝ ። አቶ አለማየሁ ገ/ማርያም የሚለው ስምዎን አል ማርያም ካሉት ጋር አይገጥም ይሆን ይህ ስንኝ ።
በተረፈ ሜሮን ጌትነት በወያኔው ቴሌቪዥን ላይ የወያኒው የልማት ፕሮግራም ውድድር አዘጋጅነቷንና አቅራቢነቷን ነው እኛ የምናውቀው ። “The poet-artist with an “unconquerable soul”? የሚለው ሙገሳዎ አለቦታው የገባ ነው ብየ እከራከርዎታለሁ ፤ የሜሮን ጌትነት ነፍሷ በወያኔ/ኢሓዲጎችconquer ከተደረገ ከረመ። እንዲያውም ሰሞኑን አሶሳ ወስጥ እየተደረገ ባለው የወያኔ ብሄር ብሄረሰቦች በአል ላይ ይመልከቷት፤ የህገ/መንግስቱ አወዳሽና ቀዳሽ አስተዋዋቂ ናት ። ይህ ከልክ ያለፈ ሙገሳዎ፤ ይህን እያወቁ ከሆነ እታዘብዎታለሁ ፤ ካላወቁ ደግሞ ይቅርታ አደርጋለሁ ። ወይም የፅሁፍዎ አቢይ አላማ ሜሮን ጌትነትን የማስተዋወቅ የPR ስራ ከሆነ ደግሞ ከጋራ አገራችን ፍቅርና ደህንነትና ጋር አይለውሱብኝ ። ኢትዮጵያንና ሚሮንን አንድ ላይ ሳይለውሱ ኢትዮጵያን ለቀቅ አድርገው ሜሮንን ጠበቅ ያድርጉ ። እዚህ ላይ እንዲታውቅልኝ የምፈልገው ነገር አለ ። ሜሮን ከወያኔ/ኢሕአዲግ ጋር ሰራች አልሰራች የራሷ ምርጫ ነው ፤ ስሪ ወይም አትስሪ ብዬ ልጫናት መብቱም ሆነ አቅሙ የለኝም ። አል ማርያም ሆይ ፤ እኔ የምመክረዎ ፤ መስታወት ራሱን አያይምና ዘውር ብለው እንደገና ያሞገሱላትን ግጥም “….ህዝቤ ፤ አገሬ ፤ ክብሬ …” የሚለውን ከራስዎ ጋር አያይዘው እንዲመለከቱ ነው ። ለዛሬው በሜሮን ጌትነት ላይ በዚሁ አበቃለሁ ። አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁት ደግሞ በግጥሙም ሆነ በተዋናይነት ብቃቷ ላይ እመለስበታለሁ ። ከዚያው ከሜሮን ጌትነት የግጥም ንባብ ላይ ለወደፊቱ ፅሁፌ ታግዘኝ ዘንድ አንድ ስንኝ ጥዬ ልለፍ ።

“……እድሜህን ቀርጥፈህ ብትሆን ባለ ዲግሪ ፣ ማስትሬት ዶክትሬት ብትደክም ብትለፋ ፤
እውነቱን ልንገርህ በሃገሬ ሂሳብ ፤ ከውጪ የመጣ የሶስት ወር ኮርስ ነው ሚዛን የሚደፋ ፡…….”

…………………………………………………….

ውድ አንባቢዬ ሆይ እንግዲህ ይህን አጋጣሚ አግኝቻለሁና አንዳንድ ተዋንያንና ድምፃውያን ላይ በየዌብ-ሳይቱ ተለጥፈው ካገኘኋቸው ዜናዎችና እኒም ከታዘብኳቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ላጋራችሁ ።
ከጥቂት ወራት በፊት ነው አበበ ተካ የሚባል ነዋሪነቱን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ ድምፃዊ ላይ “አበበ ተካ ለሴት ሲል አገሩን የከዳ ” በሚል ርእስ አንድ ዜና በተወሰኑ ዌብ-ሳይቶች ላይ ተሰራጭቶ ያየሁት ። ይህ አበበ ተካ የሚባል ድምፃዊ የምን አገር ዜጋ አግብቶ ነው ሙዚቃ ያስተወችው ? የሚል ጥርጣሬ ነው በውስጤ ያደረው ። ምክንያቱም በአበበ ተካና በአገሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ፤( በአድናቂዎቹና በሱ መካከል እንዳለ ግንኙነት አድርጌ በመገመት) አበበ ተካም ሆነ ባለቤቱ ትዳራቸውን የሚወዱ ባልና ሚስት አድርጌ ገምቼም ነበር ። ለሚወዳት ባለቤቱ ሲል አንድ ያለችውን ሙያ ትቶ በፍቅር ተሰብስቦ የሚኖር ግለሰብ አድርጌ ገምቼውም ነበር ። ህይ ዜና በወጣ በጥቂት ወራት ውስጥ አበበ ተካን ባለቤቱ አስገድዶ ደፈረኝ ብላ ከሰሰችው የሚል ሌላ ዜና ደግሞ በነዚሁ ዌብ-ሳይቶች ላይ ብቅ አለ ። ምንድነው ነገሩ ! ያቺ ስሙ የጠፋላት ሚስቱ ነች ወይስ ስለሌላ አበበ ተካነው የምሰማው እያልኩ ሳስብ ፡ የአስገድዶ ደፈረኝ ክስ ተነስቶለት ልጆቹን የማየት እድል እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቀ ተባለ ። ከፍርድ ቤት ሲወጣ ፤ በዩ-ቲዩብ ላይ አጥር ያለች ቃለ መጠይቅ ቢጤ ሰጥቶ ስለነበር ያችኑ ሳዳምጥ አበበ ከባለቤቱ ጋር የነበረው አለመግባባት ስር የሰደደ እንደነበር በግልፅ ይታይ ነበር ፤ የወራት ሳይሆን አመታት የተቆጠሩበት አለመግባባትም ነበር ። ስለዚህ ከወራት በፊት አገሩን የከዳ ሲል የተጻፈው ዜና ከንቱና ባዶ ፈጠራ ሆኖ አገኘሁት ። እንግዲህ ጉዳዩ የቤተስብ ቢሆንም አንዴ አደባባይ ወጥቷል ፤ በዚህ ላይ አበበ ተካ Public Figure ታዋቂ ግለ-ሰብ ስለሆነ ነው እንጂ ብዙ አበሻ እሱን ከገጠመው በባሰ ሁኔታ ትዳሩ ተፈቷል ፤ መፋታት አዲስ አይደለም ለማለት ነው ። ይህንና ግን ባለቤቱ እንዲህ አደረገችው እንዲህ በደለችው እየተባለ ነው ወሬው የሚናፈሰው ።ስለዚህ የአንድ ወገን የአበበ ተካን ብሶት ብቻ ከመስማት የባለቤቱን ብሶትም መጠየቅ ተገቢ ነው። አለዚያ ለፍርድ አይመችም ።

……………………………………..

ሌላው ትዝብቴ ደግሞ ቀልዶ-አደሩን ክበበው ገዳን ይመለከታል ። ክበበው ገዳ ከኢትዮጵያ ቀልዶ-አደሮች ውስጥ ቁንጮ ነው ብየ ብናገር ማጋነን አይሆንም ። የቀልድ ስራዎቹ ላይ እንደማንኛው ሰው ችግሮች ሊታዩበት ይችላሉ ።
ተመልካችም በቀልደኛው ንግግር እየሳቀ ሲሰደብ እንኳን መሰደቡ አይገባውም ። ወይም እየገባው ያው የአበሻ ባህሪይ ሆኖበት ዝም ብሎ ያልፈዋል ። የአበሻ ባህሪይ ያልኩት አንድ የምናደንቀው ሰው ላይ ዛሬ የምናየውን ስህተት በይሉኝታ ፤ ወይም ይቅርታ እንድናደርግ ሳንጠየቅ በይቅርታ ፤ እናሳልፈውና ነገ በላያችን ላይ ሲጨፍርብን ፀጉራችንን መነጨት መጀመራችንን ነው ።
ዛሬ በሰለጠነው ዘመን ማንኛውም ሙያ በትምህርት ሲደገፍ ጥቀሜታ አለው ። ሁሉም የቁም ቀልዶ-አደር Stand-Up Comedian በአሜሪካም ቢሆን እንኳ ፤ የመድረክ ላይ ትምህርት አለው ማለት አይደለም ፤ ሆኖም ግን በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎች ያማክሩታል ፤ ቀልዶቹን ይመርጡለታል ፡ቃላቱን ይቀርፁለተል ፤ መድረኩን ይመሩለታል ፤ ሰአቱን ያቅቡለታል ። በኛ ሃገር ግን ከፈረንጆቹ በተለይ ከአሜሪካ ሁሉንም ነገር እየኮረጅን መሟላት ከሚገባቸው ሁነታዎች አንዱን እንኳ ሳናሟላ የምንገባበት ሙያ ላይ ብዙ ስህተቶች ሲፈጠሩ እንመለከታለን ። ከነዚህ ሙያዎች ውስጥ የቁም-ቀልድ Stand-up comedy ሙያ አንዱ ነው ።

ሌላ ሌላውን እንተወውና ከአስኮራጃችን አሜሪካን ሃገር አንድ የቁም ቀልዶ-አደር ፤ ቢያንስ ፕሮግራሙን የሚመራለት ዳይሬክተር ብሎም አማካሪ ይፈልጋል ። እንደፈለገና አፉ እንዳመጣለት ያሻውን አይዘላብድም ። በተለይ ለተመልካቹ ያለው ክብር ከፍተኛ ነው ። ምክንያቱም ኑሮው የተመሰረተው እንጀራው የሚጋገረው በተመልካቹ ላይ ነውና ። ኒውዮርክ ሾው ላይ የነበረውን ተመልካቹን አትላንታ ሄዶ አይቀልድበትም ። በሌሎቹ የአውሮፓ አገሮችም እንደዚሁ ነው ።
ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳ የታዳሚውን የልብ ትርታ ማዳመጥና አድናቂዎቹ መኖሪያቸው ኢትዮጵያም ይሁን አሜሪካ ፤ ካናዳም ይሁን ቻይና ማክበር ይገባዋል ። እንደ አለቅላቂ ሴት አንዱ አገር ሲሄድ ቀደም ብሎ የሄደበትን ከተማ ማንቋሸሽ ወይም መዝለፍ አይገባውም ። ይህን እንድል ያነሳሳኝ ክበበው ገዳ ከተወሰኑ አመታት በፊት ወደ ኮሎምበስ ኦሃዮ ብቅ ብሎ ነበር ። ከተመልካቹ መሃል ቀልዱ ያላስደሰተው አንድ ግለ-ሰብ ጋርም መጣላቱን ሰምቻለሁ ። ከዚያ ወደዋሽንግቶን ዲሲ ሲመለስ መድረክ ላይ ወጥቶ “ ኢትዮጵያ እያለሁ አገሬ መራቧን እሰማ ነበር ። አሁን ግን ኦሃዮ ደርሼ ከመጣሁ በኋላ አገሬ ለምን እንደተራበች ገባኝ ፤ ለካ ገበሬው ሁሉ ተሰብስቦ ኦሃዮ ገብቶ ነው ሲል ቀለደ ።” ዋሺንግቶን ዲሲም ኦሃዮ በብዛት የወልቃይት ፀገዴ ተወላጆች እንደሚኖሩበት በማውቅ ለቀልዶ-አደሩ ክበበው ገዳ ሳቀለት አስካካለት ።
የአንተን የቀልዶ-አደሩን ሆድ ለመሙላት ውልቃይት ፀገዴ ማረስ ነበረበት ? ቀልዶ-አደሩ ወንድሜ አገራችን ረሃብተኛ መባሏን ከሰማህና ገበሬው ሁሉ ኦሃዮ መመጣቱን ከተገነዘብክ ለምን ራስህ ገብተህ አታርስም ነበር ። በዚህ አጋጣሚ አገር የምትለማው በአርሶ አደሮች እንጂ በቀልዶ አደሮች እንዳልሆነ ልገልፅልህ እወዳለሁ ። ታዲያ ይህን አባባልህን ሳትወቀስበት በዋሽንግተን ተስቆልህ አለፍክ ።
ውድ አንባቢዬ ፤ አሁን በቅርቡ ደግሞ ይባስ ብሎ አውሮፓ አንድ የፋሽን ትርኢት ላይ እንደሟሟያ ሆኖ ቀርቦ ነበር ክበበው ገዳ ። የአዲስ አበባ ጆክ ነው ብሎ አንድ ቀልድ አወራ ። “ጎስቋላዎቹና ማዲያታሞቹ ሴቶች ሁሉ አሜሪካና ካናዳ ነው ያሉት” ሲል ቀለደ ። ጆኩ እንደጆክ ተወርቶ በዚያ ቢያበቃ መልካም ነበር ። “ለነገሩ እውነት ነው እኔ ዘወር ዘውር ብየ አይቻለሁ” ማንከሽከሻ ብቻ ናቸው ሲል አሾፈ ። ይህን አባባሉን ለመመልከት የሚቀጥለውን ሊንክ ይመልከቱhttps://www.youtube.com/watch?v=t0-qU60ik3E ።ወይም ክበበው ገዳ ብለው ጉግል ያድርጉና “ ቆንጆዋን እንካ ግን አትንካ ” የሚለውን ርዕስ ይጫኑ ።
ቀደም ብየ እንዳልኩት እንደ አለቅላቂ የመንደር ሴት የኦሃዮን ዲሲ የአሜሪካና ካናዳን አውሮፓ እየወሰደ ያለቀልቃል ። ቀልዶ አደሩ ወንድሜ ክበበው! እነዚህ ማንከሽከሻ ፤ ጎስቋላ፤ ያልካቸው የአሜሪካና የካናዳ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ሚስቶቻችንና እናቶቻችን ናቸው ። አዎ ማዲያታም ሊሆኑን ይችላሉ ሊጎሳቆሉም ይችላሉ ። አንተ ኢትዮጵያ ወስጥ ያውም አዲስ አበባ ብቻ እንደምታውቃቸው ፤ ምሽት-አደር ሴቶች ላይቆነጁ ይችላሉ ። ሰርተው ጥረው ግረው በላባቸው በወዛቸው የሚያድሩ ናቸውና ። በዚህ በፈጣኑ አለም ውስጥ ልጆች አሳድገው አስተምረው ትዳራቸውን ጠብቀው ከዚያም አልፈው ኢትዮጵያ ወስጥ ቤተ-ሰብና ዘመድ ረድተው የሚኖሩ ሴቶች ናቸው ፤ ቢጎሳቆሉ ይነሳቸው ፤ ማዲያት ቢወጣባቸው ይብዛባቸው ።
የአንተ የአዲስ አበባ ቆነጃጅት ሴቶች ለፀጉራቸው ሶስት ሰአት ፤ ለጥፍራቸው ሁለት ሰአት ለቅንድባቸው ሌላ ሁለት ሰአት ለማጥፋት በቂ ጊዜ ያላቸው ናቸው ፤ ምነው አይቆነጁ ። ስለዚህ ስትቀልድም የምትናገረውን እወቅ ። በአንድ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ስትቀልድም እዚያው እፊታቸው ላይ ቀልድ ። አንዱን ካንዱ አታምታታ ። አንድ እውነታ ግን ልንገርህ ። ኦሃዮም ካናዳም ሆነ አሜሪካ አንተ መጣህባቸው እንጂ እነሱ አንተን ብለው አልመጡብህም ። ኦሃዮም ካናዳም አሜሪካም ያላንተ ኖረዋል መኖርም ይችላሉ ። አስር አመት ቀልደህ ከአዲስ አበባ ቆነጃጅት ሴቶች የማታገኘውን ገንዘብም በአንድ ትርኢት የምታገኘው ከነዚህ ማንከሽከሻዎች ፤ ማዲያታሞችና ባሎቻቸው ነው ። ዘወር ዘወር ብየ አለምን አይቻለሁ ብለሀናልና እግርህ ተፍታቶ ክንፍ አውጥተህ ዘወር ዘወር ያልከው ከነዚሁ ከማዲታሞቹ በተገኘ ገንዘብ እንደሆነ ልትረዳው ይገባል ። ይህ እውነት አይደለም እንዴ ወንድሜ? መቼም ቀልደኛ ነህና ፤ አይደለም ከአባቴ በወረስኩት ገንዘብ ነው ብለህ እንዳታስቀኝ ።

ውድ አንባቢየ ለዛሬው በዚሁ ላብቃ !

ከአንበሳው ይብራ

እ.ኤ.አ ዲሴምበር 2 2014

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ ዕለታዊ መግለጫ

ዝግጅታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል! እርስዎም ይዘጋጁ!
‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል የአንድ ወር መርሃ ግብር ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ስርዓቱ መርሃግብሮቻችን በማጨናገፍ ለነጻነት የምናደርገውን የትግል ጉዞ ለማደናቀፍ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል፡፡ ሆኖም የነጻነት ትግሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል መሆኑን የተረዳው ትብብሩ ለገዥው ፓርቲ አፈና ሳይንበረከክ ስራውን ቀጥሏል፡፡ በተለይ ከመርሃ ግብሮቻችን መካከል ስርዓቱን ያስፈራውን የ24 ሰዓት የአደር ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅታችን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡ ለዚህ የአዳር ሰልፍ የትብብሩ አባል ፓርቲዎች ሰው በሰው በመቀስቀስ፣ ወረቀት በመበተን እንዲሁም በየ ፓርቲዎቻችን ስም የታተሙ ቲሸርቶችን በመልበስ ህዝቡን እያነቃቃን እንገኛለን፡፡ ሰልፉ እስከሚደረግበት ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም ድረስም ዝግጅታችን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ይህን መርሃ ግብር ስንነድፍ ለነጻነት የሚከፈለው መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተንና የቀድሞ አባቶቻችን ካሳዩት ቆራጥነት ተምረን ነው፡፡ በዚህ ለቀጣይ የትግል ጉዞአችን ጭላንጭል ለምናይበት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በውጭም ሆነ አገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት ለምናደርገው ጉዞ የጀመርነውን የሰው በሰው ቅስቀሳ በመደገፍ፣ በገንዘብ፣ በሞራልና በሌሎች ለመርሃ ግብሩና ለአጠቃላይ ትግሉ ይጠቅማል ባሉት መንገድ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ መርሃ ግብሩ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በሞራልና በተለያየ መንገድ መልዕክቶቻችን ለህዝብ እንዲደርሱ ድጋፍ ያደረጋችሁልን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ልባዊ ምስጋናችን ማቅረብ እንፈልጋለን፡፡ አሁንም ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ በመቀጠል ታሪካዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡

በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በኩል ለሰላማዊ ሰልፉ የሚያስፈልገው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ህዝቡ በዝግጅቱ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በመስቀል አደባባይ በሚኖረን ቆይታ የሚያስልጉት ቁሳቁሶች በተለይም ደረቅ ምግብና ውሃ ከአሁኑ እንዲያዘጋጅ ማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚደረገው የ24 (አዳር) ሰልፍ ኢትዮጵያውያን ላይ የተጫነውን የፍርሃት ድባብ በመስበር ለነጻነት የምናደርገው ወሳኝ ጉዞ ጅማሬ በመሆኑ በሁሉም የማህረሰብ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ራሳቸውንና አገራቸውን ነጻ ለማውጣት የትግሉ አካል እንዲሆኑ ጥሪያችን እያቀርባለን፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

ህዳር 23/2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎቹ ዋና ኢንስፔክተር ጐይቶም አረጋዊ ኪዳነ ማርያም፣ ረዳት ኢንስፔክተር አንተነህ አስናቀ ተፈራና ኮንስታብል ዘሪሁን ሲሳይ ሲሆኑ፣ ሁሉም በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን የክስ ቻርጁ ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ለሕግ ተቃራኒ በሆነ መንገድ በማስገደድና ከሕግ ውጪ የግል ተበዳይ ናቸው የተባሉትን አቶ አህመድ ኑርን ይይዟቸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከሶማሌ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመምጣት፣ ተበዳዩን የያዟቸው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጐተራ አካባቢ መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ የግል ተበዳይ ናቸው የተባሉት አቶ አህመድን ከነበሩበት ተሽከርካሪ ላይ ጐትተው በማውረድ፣ በሽጉጥ በማስፈራራት፣ በቦክስ ፊታቸውንና የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን በመምታት ራሳቸውን ሲስቱ፣ ተጠርጣሪዎቹ በያዙት ተሽከርካሪ ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ መድኃኔዓለም አካባቢ እንደወሰዷቸውም ተገልጿል፡፡

ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በሚገኘውና ‹‹የሶማሌ ክልል ዳያስፖራ ቢሮ›› በመባል በሚታወቀው ጊቢ በሚገኝ ሰርቪስ ቤት ውስጥ በማስገባት፣ ለሦስት ሰዓታት እንዳቆዩአቸውም ክሱ ያብራራል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከሦስት ሰዓታት በኋላ የሰሌዳ ቁጥሩ 0071 በሆነ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ፒክአፕ ተሽከርካሪ ጭነው፣ ወደ ጅግጅጋ ያመራሉ፡፡ አዋሽ፣ ልዩ ቦታው አዋሽ ድልድይ ኬላ ላይ የሚጠብቁ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አባላት በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸውና ሰውን ከሕግ ውጪ ይዞ ማስቀመጥ ወንጀል መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና የጠየቁ ቢሆንም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ኅዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ውድቅ አድርጐ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከራከሩ ብይን ሰጥቷል፡፡
Source: Reporter Amharic

ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!

ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!

የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተጓዝንበትን መንገድ ለጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤትና ለባለ ድርሻ አካላት ስናሳውቅ የነበረ በመሆኑ ያጋጠሙንን ችግሮች በመደጋገም ማሰልቸት አንሻም፡፡

ስለሆነም የዛሬው መግለጫችን በቀጣይ ለቀሩን ተግባራት የደረስንበትን ድምዳሜና ያወጣነው ዕቅድ በሚመለከት ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በእስከዛሬው እንቅስቃሴያችን ይዘን የተነሳነው ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሚለው መርህ ትክክልና ወቅታዊ፣ ያነሳናቸው ጥያቄዎችም አግባብ መሆናቸውን ያረጋገጥንበትና ገዢው ፓርቲ መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማለት ፍጻሜዬ ነው በሚል ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜትና ሥጋት ለተቃውሞ ጎራው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በሩን ለመዝጋት የተዘጋጀ መሆኑን አገር ለ23 ዓመታት በላይ ካስተዳደረ መንግስታዊ ሥርዓት የማይጠበቅ መረን የለቀቀ የውንብድና ተግባራት ያረጋገጥንበት ነው፡፡ በመሆኑም ጥያቄዎቻችንን በህገ መንግስቱና በአገሪቱ ህጎች መሠረት ለመመለስ ቀርቶ ለመስማትና ለማንበብ ፍቃደኝነቱና የኃላፊነት ስሜቱ እየተሟጠጠ በመሆኑ የአፈናና ማስፈራራት መንገድን ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፡፡ ይህ በመሆኑም የራሱን መንግሥታዊ መዋቅር አሰራር ሥርዓት እንኳ በአደባባይ ለመቀበል እምቢተኛ መሆኑን በአደባባይ አረጋግጧል፡፡ ባለሥልጣናቱ በግንባር ያቀረብነውን ደብዳቤ ካለመቀበል አልፈው በመንግሥታዊው ፖስታ ቤት የተላከ ደብዳቤ ያለመቀበላቸው የሚያመለክተው ይህንና የደረስንበትን የመልካም አስተዳደር አዘቅት ነው፡፡

በተቃራኒው አበረታችና መልካም ዜናም አለ፡፡ ይህም ይህን የአፈናና ማስፈራትት አካሄድ አንቀበልም ያሉ ለነጻነታቸውና ክብራቸው፣የራሳቸው ብቻ ሣይሆን የመንግሥት መዋቅሮችና ባለሥልጣናትም ነጻነት መረጋገጥ አለበት ብለው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት የተዘጋጁ በትብብሩ የታቀፉ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላት መኖራቸውና በትግሉ ለመቀጠል መወሰናቸው ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ትብብሩ ለመጀመሪያ ዙር ዕቅዱ ማጠቃለያ የህዳር 27/28 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ አመራሩ በግንባር ቢያቀርቡም አሻፈረኝ አንቀበልም ያሉት አሰራርና ባለሥልጣናት ከፖስታ ቤት እንዲቀበሉ ተደርጓል፡፡ለዚሁ ደብዳቤ መስተዳድሩ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ (ቁጥር 3/1983) ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል በዛሬው ቀን (22/03/07) መልስ አድርሶናል፡፡ በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ በመሆኑም ለተግባራዊነቱ ዝግጅቱን በሙሉ አቅም ጀምሯል፤ ለዚህም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከአገር ውስጥና ከውጪ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፤ አበረታተውናል፡፡ ይህም የያዝነው የትብብር የጋራ ዓላማችን ተቀባይነት፤ የኅብረትና አንድነትን ዋጋ አመላካች፣ ለማይቀረው ሠላማዊ ትግላችን ሥንቅ ነውና በታላቅ አክብሮት ተቀብለነዋል፡፡

ስለሆነም ይህ መግለጫ ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28 ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ነጻነታችንና ክብራችን ለማስመለስ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ፣ ያለመስዋዕትነት ድል የለምና!!
Image

በአለፈው ዓመት በ­22.11. 2013 የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ፣ በእስራኤል ለሚገኘው የወያኔ ሚዲያ ለ­“IETV” ያመጣው የክስ መዘዝ፣ቀጥሎ ለውሳኔ መቀጠሩ የክሊክ ሃበሻ ዘገባ አመልክቷል::የዛሬ ዓመት ኖቨምበር 22 ቀን 2013 ነበር፤ ቴል አቪቭ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ኢትዮ­ይሁዳያንና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ፣ ሞተና የሴቶች መደፈር፣ ሰቃይና ሰቆቃ የወያኔ/ኅውሃት ገዥውና እምባገነኑ መንግሥት ችላ ብሎታል ብሎ በመቆርቆርና በመበሳጨት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ነው። http://www.clickhabesh.com/?p=105083

Image
ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል አብዛኛዎቹ በልጅነት እድሜ የመጡና ከዚህ የተወለዱ ወጣት የኢተዮጵያ ይሁዳውያን የተሳትፉበት ከመሆኑም ባሻገር፤በዚህ መልኩ በኢምባሲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት ወጣት ኢትዮ ይሁዳውያንን አልገብግቦ እንደዚህ ዓይነት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በእሥራኤል ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀምሪያ ነበር ቢባል ማገነን አይሆንም። ምክንያቱም ቴል አቪቭ የሚገኘው አምባሳደር ኽላዊ ዮሴፍ የወጣት ኢትዮ ይሁዳውያን በሰልፉ መሳተፋቸው አስደንግጦት፣ እዚሁ እሥራኤል በሚገኘው የአማረኛ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቀርቦ ከተናገረው፣ በእሥራኤል መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሚተዳደረ የአማረኛው ሬዲዮ ጣቢያ የተናገርውን አዳምጡ የሬዲዮውን ቃለ ምልልስ አዳምጡና ንባቡን ቀጥሉ፦

ልብ በሉ፦ በዲሞክራሲና በነጻው ሚዲያ ሃገረ እሥራኤል ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ “የአንድን ወገን ብቻ አቅርቦ” በተደጋጋሚ ማለትም አምባሳደሩንና ደጋፊዎቹን ቃለመጠይቅ ሲያደርግ፣ ቴሌቪዥኑም ሆን ሬዲዮው ከሙያው ህግ ውጭ በመሆን አንድም ቀን የተቃዋሚውን ወገን በጋራም ሆነ በተናጠል ቃለ መጠይቅ አካሂዶ አያውቅም። ህዝቡ በነጻውሚዲያ ሃገር የሁለቱንም ሃሳብ ሳያዳምጥ አንድ ወገን ብቻ ይዞ እንዲጓዝ መደረጉ ያበሳጫቸው ከዚህ ህዝብ አብራክ የወጡ በተናጠል ትግል የጋራ ትግል በማለት ተደራጅተው፣ “መሬት ­

ኢትዮ ­እሥራኤል የሰብዓዊና ነጻነት ድምጽ ምክር ቤት” ብለው ያቋቋሙት የመጅመሪያ ትግላቸው ማተኰር ያለበት በዲሞክራሲና በነጻ ሚዲያ ሃገር የህዝብ ድምጽ የታፈነውን መብተማስጠበቅ መሆኑን እጠቁማለሁ። ይህ የአምባሳደሩ መግለጫ አንዳንድ የዋህ አዛውንቶችን የኢትዮጵያን ህዝብ እያስራበ በሚያስመጣው “ጤፍ” በማታለል ለማሳመን መሞከሩ ነበር። ምክንያቱም የሚያስበው እሥራኤል የሚገኘው ኢትዮ ቤተ እሥራኤላውያን እኛ እንዳዘዝነው ነው ብሎ ያስብ ስለነበር ሳያስበው የደረሰበት የውርደት ካባ የተከናነበበት በመሆኑ ለማስተባበል መሞከሩ ነበር።ስለጤፍ ከአንድ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ተመልከቱ፦ይህን ያህል ለመንደርደሪያ ካልኩ ዘንዳ፣ ወደ ዋናው ሃሳብ ልንደርደር።

ምንም እንኳ ዓርብ ቀን ድምጻውያን እንድሚሉት “….ዓርብ ዓርብ ይሸበራል እየሩሳሌም!” ያለ ምክንያት አይደለም። ዓርብ ህዝበ እሥራኤላውያን ለ 26 ስዓታት ሰንበትን የሚቀበሉበት ቀን ስለሆነ፤ ሁሉም ነገር ከመዘጋጋቱ በፊት ማልደው በመገዛዛት ሲያበስሉና ቤታቸውን ሁሉ ሲያጸዱ ከዋሉ በኋላ ሁሉም ቤተሰብ ሰውነቱን ታጥቦ ጽዓዳ በመልበስ ወደ ጸሎት ቤት ሄደው ሲመለሱ፣ ሰንበት ከመግባቱ በፊት ያበሳስሥሰሉትን፣ መላው ቤተሰብ በአንድ የጠረጴ ዙሪያ በመቀመጥ እየበሉና ወይናቸውን እየተጡ አምላካቸውን የሚያመሰግኑብት ቀን ሲሆን፤ የህዝብ ማመላለሻዎች፤ ሱቆች፤ መ/ቤቶች፤ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛውም በሙሉ ዓርብ ከስዓት በኋላ ከቀኑ 14፡00 ማለት 02፡00ስዓት (በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከቀኑ 08፡00 መሆኑ ነው) ይዘጋል።

ሆኖም ግን በዚህ ቀን የቤተሰብ ኃላፊነት ያላቸው ሌሎች በእድሜ ትንሽ ከፍ ያሉ ቢኖሩም፤ አንዲት ወጣት ቤተ እሥራኤል ከገጠሪቱ ኢትዮጵያወደ እሥራኤል በ­8 ዓመት ዕድሜዋ፤ ኅውሃት አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ ከሁለት ቀን በፊት “ዘመቻ ሰሎሞን” (Operation Solomon) በተባለውየመጣች፤ አሁን የ 31 ዓመት ወጣት፤ በፌስ ቡክ ያተላለፈውን በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን መከራና ሥቃይ ችግርና ስቆቃ ተመልክታ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው!” ብላ፤ ልጆቿን ዛሬ የ­7 እና የ­የ­5 ዓመት ዕድሜ፡(ባለፈው ዓመት የ­6 እና የ­4 ዓመት) ከወላጆቿ አስጠግታ፤ ከምትኖርበት ከተማከተወሰኑ ጓደኞቿ ጋር በባቡር ተሳፍራ በስዓቱ ከተባለው ቦታ ቴል አቪቭ በመድረስ ከሌሎች ከሰላማዊ ሰልፈኛው ጋር በመሆን፤ በሳዑዲ ዓረብያ ጭካኔ የተጐዱትንና የሞቱትን ኢትዮጵያኖች ፎቶ በማንገብ፤ የኢትዮጵያው መንግሥት ለዜጐቹ ግድ ሳይሰጠው ዝም ማለቱ በጣም ስለአንገበገባት፣ የዲሞክራሲ መብቷን በመጠቀም በጉዳት ላይ ላሉት ወገኖቿ ስትጮህላቸውና ድምጿን ስታሰማ ዋለች፡፡

ታዲያ ከሰላማዊ ሰልፉ አንድ ሳምንት በኋላ (በሳምንቱ ዓርብ) “IETV” በተባለው ቴሌቪዥን ይህችን ወጣት ያልተናገረችወን በኤዲቲንግ የተቀነባበረ ፕሮግራም ቀረበ። (የኢዲቲንግ ዕውቀቱ ወይም ሙያው ያለው አቆራረጡንና አቀጣጠሉን ይረዳል)ይህን ፓርት/ክፍል ተመልከቱ፤ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ “ሰባት” (7 ጊዜ)ይህ ቃል በፕሮግራሙ ተደጋግሟል። ለምን? ተደጋገመ የሚለውን የፍርዱ ሁኔታ ሲያበቃ ከህግ ጠበቃዋና ከወጣቷ ጋር ፈቃደኛ ከሆኑ በቃለ መጠየቅ ከአንደበታቸው እንሰማለን የሚል እምነት አለኝ። እንደ ባለመያ እስኪ የራሴን አስተያየት ጠቆም አድርጌ ልለፍ፤

1ኛ) እንደዚህ ዓይነት ነገር ልጅቱ ከተናገረች፣ መሆን ያለበት ሙሉ ንግግሯን ከነመልኳ ማቅረብግዴታ ነው፤ ከዚያ በኋላ ቋንቋ ልማይረዱ ትክክለኛ ትርጉሙን ማቅረብ የሙያ ግዴታ ነው፣

2ኛ) በጋዜጠኛ ህግናደንብ መሰረት “Sling” ወይም “የመንገድ ቋንቋ” ብሎ ነገር የለም። ለህዝብ መቅረብ ያለበት “እውነተኛና ሃቅ ብቻ እና ሃቁ ብቻ ነው”፤ ምክንያቱምሚዲያ የአንድ ሃገር ህዝብ ጠበቃ ማለት ነው፣ወደ ታሪኩ ልመልሳቸሁ፣ ይህን የተላለፈ ፕሮግራም ያዩ ዘመድ አዝማድና ቤተሰቦቿ ”እንዴት ፋሲል ይገደል ትያለሽ?” “ለምን ልጆችሽን ዝም ብለሽ አታሳድጊም?” እያሉ
ሲያዋክቧት በመደናገጥ በጣም ተረብሻ ወዲያውኑ የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊ የነበሩትን ስታማክር፤ በመጀመሪያ እንድትረጋጋ ከመከሯት በኋላ፡
ፕሮግራሙን በኢንተርኔት በማየት በፍጹም ቃላት የተለቃቀመበት የተቀጣጠለ ስለሆነ፤ ቴሌቪዥኑንና አቅራቢውን “በስም ማጥፋት” የሚያስወነጅል እንደሆነ ገለጹላት። ይህች የ­31 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባትና ልጆችዋን ብቻዋን እንደምታሳድግ ስታማክር፤ የተወሰኑ ከተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ የተሳተፉ በመመካከር ወደ­5 የሚሆኑ ገንዘብ በማዋጣት ከፍለውላት“ፒኒ ጌልዓድ” የተባለ የሀግ ጠበቃ እንድትይዝ ሆነ።

በተላለፈው ፕሮግራም ላይ እንዳያችሁት፦የሀግ ጠበቃዋ በህጉ መሰረት ክሱን ጀመረ፣ “IETV” ወዲያውኑ ከኢንተርኔትና ከፌስ ቡክ ላይ ሙሉ ፕሮግራሙን አወረደው፤ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራሞችን እያወረደ የሚያስቀምጥ የተጠናከረ የወጣቶች ቡድን ቀድሞ ቀድቶ አስቀምጦታል።ክሱ ተጀመረ ብያለሁ፤ እናስ ማለታችሁ አይቀርም፤ እናማ የቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ የከሳሽና ተከሳሽን የህግ ጠበቆችን ቃል ከሰማ በኋላ፤ እንደ እሥራኤል ህግና ደንብ መሰረት የሚቻል ከሆነ ሁለቱ የከሳሽ የህግ ጠበቃና የተከሳሽ የሀግ ጠበቃ በጋራ ተስማምተው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ ለሆነ የሀግ ጠበቃ ሁኔታውን በመካከላቸው ሁና ከህግ አንጻር እንድታሸማግል “Court Mediators” ዘንድ ተላኩ። እዚያ መስማማት ባለመቻላቸውም በአለፈው ኦጐስት/ነሃሴ 2014 ወረዳው ፍ/ቤት ቀርብው ነበር።

ታዲያማ የተከሳሽ ጠበቃ ለዳኛው በ”ይፋ” ከሳሾችና ተከሳሾች በተገኙበት(በ”ይፋ” የሚለው ይሰመርበት) በመከራከሪያነት የተጠቀመው (የ“IETV” የህግ ጠበቃ በሂብሪው የተናገረውን ቃል በሂብሪውና በእንግሊዝኛ ላስቀምጠው) በሂብሩ የተጠቀመው ቃል “להבהיר” (Apologize) ከማለቱም በተጨማሪ፤ ከሳሿ ፈቃደኛ ከሆነች በዚያው ቃለ መጠይቅ ልናደርግላት እንችላለን ሲል የመከላከያ መልሱን አቅርቧል። የወጣቷ የህግ ጠበቃ ግን በወጣቷ ማህበራዊ ህይዎትም ሆነ የሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ መረበሽና አለመረጋጋትን ስላስከተለባት፤ ሆን ተብሎ በወጣቷ ላይ የተክናወነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለተካሄደ፤ ለድርጊቱ “IETV” ይቅርታ ከመጠየቅም ባሻገር የሥነ ልቦና ጉዳት ካሳና የህግ ጠበቃዋን ወጭ ሊከፍል ይገባዋል ሲል መልስ ሰጥቷል።

ዳኛውም ወጣቷን ተከሳሾቹ በሚሉት ትስማማ አትስማማ እንደሆን ተጠይቃ፤ በ­“IETV” ምን ዓይነት ቃለ ምልልስ እንደማትሰጥና፣ ይህ ቴሌዥን በህይወቴ ላይ ከፍተኛ የሆነ መጥፎ አሻራ ያጣለባት መሆኑንና፤ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ከተለያዩ ክፍሎች የደረሳት መሆኑንም ለፍ/ቤቱ አስረድታለች። ፍ/ቤቱም ለ­19.01.2015 ቀጥሯል። ችሎቱ ክፍት ስለሆነ ማንም ሰው የዲሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ መገኘት ይችላል። ቦታው ቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፤ “ቫይጽማን ጎዳና 1 ­ ቴል አቪቭ“ ትክክለኛውን ስዓትና ቀን ቀኑ ሲቃረብ እናሳውቃለን። ለወገን ደራሽ ወገን ነው ብላ ድምጿን ለማሰማት ወጥታ ሥነ ልቦናዊ ድቀት ለደረሰባት ወጣት እህታችን፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ያለበት ሃገር ያለሽ በመሆንሽ ሁላችንም መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን!!
ሐና መከተ – ጋዜጠኛ እሥራኤል

የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሊያደርገው ላቀደው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግለት፣ ህዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ መጠየቁ የሚታወስ ቢሆንም አስተዳደሩ በቁጥር አ.አ/ከፅ/10/30.4/55 ህዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም በፃፈው የመልስ ደብዳቤ ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና አለመስጠቱን አስታውቋል፡፡

ትብብሩ ለሰልፉ የመረጠው ቦታ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ አስተዳደሩ በበኩሉ የ24 ሰዓቱን ሰልፍ ላለማወቁ ምክንያት ነው ያለውን ሲያስቀምጥ፣ ‹‹የተጠየቀው ቦታ በልማት ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅና ትላልቅ የመንግስት ተቋማት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያሉበት ስለሆን ጥያቄውን ተቀብለን ለማስተናገድ የምንቸገር መሆኑን እየገለጽን፣ የአደባባይ ስብሰባውም ሆነ ሰላማዊ ሰልፉ እውቅና ያልተሰጠው መሆኑን እናስታውቃለን›› በማለት አስፍሯል፡፡

የትብብሩን ሰልፍ እያስተባበሩ ያሉት ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ለአስተዳደሩ በጻፉት ደብዳቤ እንደጠቀሱት ደግሞ፣ የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1983 አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 2 “የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 1 የተመለከቱትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው በሌላ ጊዜ ወይም በሌላ ሥፍራ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት ካለው ምክንያቱን በመግለፅ ይህንኑ ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሁፍ ለአዘጋጁ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም የከተማው ወይም የአውራጃው አስተዳደር ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባው ምን ጊዜም ወይም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ማለት አይችልም” በማለት አስተዳደሩ እውቅና የመንፈግ ስልጣን እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
Image
በመሆኑም፡-
‹‹1ኛ. እውቅና እንዲሰጥ የተጠየቀ ማንኛውም አካል ከላይ የተደነገገውን በማገናዘብ ለሌላ ጊዜና በሌላ ቦታ እንዲደረግ ሃሳብ ከማቅረብ ውጭ ሰላማዊ ሰልፉ ምን ጊዜም ወይም በየትኛውም ቦታ ሊካሄድ አይችልም ለማለት ለመስሪያ ቤታችሁ ስልጣን ያልተሰጠ በመሆኑ፤
2ኛ. ሰላማዊ ሰልፉና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የሚከናወኑት በመሰረታዊነት ለትላልቅ የመንግስትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ በመሆኑ በእነዚህ አካባቢ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረግ በአዋጁ ያልተከለከለ በመሆኑ፤

ለጥያቄያችን የተሰጠን መልስ ከምክንያታዊነትና ህጋዊነት ውጭ ሰልፉ እንዳይካሄድ ለመከልከል ስለሆነ እንዲህ ዓይነቱን ኢ-ህጋዊ የሆነ ውሳኔና አሰራር ፈፅሞ የማንቀበል በመሆኑ አስቀድመን ባሳወቅነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉን በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ የምናካሂድ መሆኑን እያሳወቅን በጽ/ቤታችሁ በኩል አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን በድጋሚ እናስታውቃለን›› ብሏል ትብብሩ ዛሬ ለአስተዳደሩ በጻፈው ደብዳቤ፡፡

1- ሁለቱም በፈጣሪ አያምኑም ( የራሴ የሚሉት እምነት የላቸውም)
2- የጦር አዛዦቻቸው::ሂትለር በራሱ ግዜ ሮሚዮን ማርሻል አድርጎታል –መለስ ሳሞራን < ጀነራል> አድርጎታል
3-ሂትለር ሁለት ልጅ ነበረው::መለስም ሁለት ልጆች አሉት
4-ሁለቱም በጅምላ ህዝቦችን ጨርሰዋል (የዘር ማጥፋት ፈጽመዋል)
5-ሁለቱም insomnia ይሰቃዩ ነበር :; ( የመተኛት ችግር ከተኙም ቶሎ አለመንቃት)
6-ሁለቱም የሶሻሊዝም issue ነበራቸው:;ለዚህም ማሌሊትን ልብ ይልዋል
7- በዘር እና በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፓርቲ በመፍጠርም ይታወቃሉ ::
8-ሂትለር ታላቅዋን ጀርመን ለመመስረት እቅድ የነበረው ሲሆን መለስ ደግሞ ታላቅዋን ትግራይን ..
9-E -ዲሞክራሲ ናቸው
10-ራሳቸውን በራሳቸው የፓርቲ እና የአገር መሪ አድርገው ሾመዋል Dagem Ahunem

Image

Eyasped Tesfaye…….(የግል ዕይታ)
‹‹……ሪቮሉሽን የአዳራሽ ዙሪያ አመፅ አይደለም፤ የሰፊው ህዝብ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሰፊው ህዝብ ካልተሳተፈበት፣ ካልደገፈው፣ አይሆንም፤ አይፀናምም፡፡ የጥቂቶች አመፅ በሌሎች ጥቂቶች አመፅ ይገለበጣል፡፡ መሰረታዊ ለውጥ፣ በሰፊው ህዝብና በጨቋኝ መደቦች መካከል የሚካሄደው የትግል ፍሬ ነው፡፡….››ዴሞክራሲያ ቅፅ1 ቁ15
የኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ1993 ያሳተመው አማርኛ መዝገበ ቃላት አብዮት የሚለውን ቃል ‹‹በአንድ ነገር ክስተት ወይም ሂደት ውስጥ ያሉ ቅራኔዎች ተካረው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የሚፈጠር መሰረታዊ ለውጥ፤ አዲስ ከፍተኛና የተሻለ ነገር፤ ክስተትና ሂደት ወይም አስተሳሰብና እውቀት የሚከሰትበት፡፡›› የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል፡፡
አብዮት በተለያየ የታሪክ ወቅት እንዲሁም በተለያየ ቦታ ተከስቷል፣ እየተከሰተ ነው፤ ወደፊትም ይከሰታል፡፡ ከፈረንሳይ አብዮት እስከ ሩሲያው አቢዮት፤ ከላቲን አሜሪካ ሀገሮች እስከ ሩቅ ምስራቅ እስያ ብሎም እስከ አረቡ አብዮት፤ የአብዮት ንፋስ ያልነፈሰበት የአለማችን ክፍል የለም፡፡ በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ አብዮቶች እንደወቅቱ እና እንደቦታው የራሳቸው የሆኑ መለያዎች ያሏቸው ይሁን እንጂ ሁሉም የሚጋሯቸው የወል የሆኑ ባህርያትም አሏቸው፡፡ ይኸውም ሁሉም አብዮቶች በጭቆና ማህፀን ውስጥ ተፀንሰው መወለዳቸው ነው፡፡
አብዮቶች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ አሊያም ኢኮኖሚያዊ መነሾ ምክንያቶች ሊኖሯቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ ታሪካዊውን የፈረንሳይ አብዮት ያየን እንደሆነ ሶስቱም መነሾ ምክንያቶች እንደነበሩት እንረዳለን፡፡ የፈረንሳይ ህዝብ በፈላጭ ቆራጭ ንጉሳዊ አስተዳደር ስር ሆኖ መብቶቹን መገፈፉ የአብዮቱ ፖለቲካዊ መነሾ ሲሆን፤ በፈረንሳይ ህዝብ መካከል የነበረው የመደብ ልዩነት በተለይም አብዛኛው የፈረንሳይ የህብረተሰብ ክፍል በድህነት የሚማቅቅበት እና መብቱን የተነፈገበት ሶተኛው መደብ ውስጥ መካተቱ የአብዮቱ ማህበራዊ መነሾ ሆኗል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በወቅቱ ፈረንሳይ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ መገኘቷ እና በዜጎች ላይም ያለው የግብር ጫና ከፍተኛ መሆኑ የአብዮቱ ኢኮኖሚያዊ መነሾ ሆኗል፡፡
አብዮቶች አብዛኛውን ጊዜ በገዢው መደብ በኩል ሳይጠበቅ የሚከሰት ክስተት ነው፡፡ ለዚህም ነው የሩቁ የፈረንሳይ አብዮትም ሆነ የቅርብ ግዜው የአረቡ አለም አብዮት አለምን ያስደነቀው፡፡ አንዳንድ አብዮቶችን ትልልቅ የስለላ ተቋማት(ሲ.አይ.ኤ፤ ኬጂቢ) ሳይቀር ያልጠበቁት ክስተት እንደነበር ታሪክ ያስገነዝበናል(መሀመድ ሬዛን ያስወገደውን የኢራኑን አብዮት ልብ ይሏል)፡፡ ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ቲሙር ኩራን የተሰኘው ፀሀፊ ‹‹sparks and praire fires: a theory of unanticipated political revolution›› በተሰኘው ፅሁፉ ላይ በአለማችን ላይ የተከሰቱትን ሶስት ዋና ዋና አብዮቶችን እንደምሳሌ በማንሳት ህዝብ የተቃውሞው ወገን እስኪጠናከር ድረስ በገዢው ወገን ላይ ያለውን ጥላቻ በውስጡ ደብቆ መያዙ አብዛኛውን ግዜ ገዚዎችን እንዲዘናጉ እንደሚያደርጋቸው ገልፆ አብዮቱ አንድ ግዜ ከፈነዳ በኋላ ለማስቆም አስቸጋሪ የሚያደርገውም በህዝብ ዘንድ ስር የሰደደ እና የቆየ ጥላች እና ቅራኔ መኖሩ እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ለአብዮት መነሳት ምክንያቱ ከላይ የዘረዘርናቸው ቅራኔዎች(ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ) ቢሆኑም ከእነዚህ ሁሉ ቀድሞ የሚመጣው ግን የህብረተሰቡ የንቃተ ህሊና(enlightenment) ጉዳይ ነው፡፡ በላቲን አሜሪካ የተካሄዱት አብዮቶች ላይ ጥናት ያካሄዱት እንደ ዴቪድ ክሎስ ያሉ ምሁራኖች ለአብዮቱ መነሳት ዋና ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የህብረተሰቡ ንቃተ ህሊና መዳበሩን እና በሌሎች ሀገራት የተካሄዱትን አብዮቶች ከራሱ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማስተያየት እና ማገናዘብ መቻሉ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
በሀገራችን በኢትዮጲያም ተከስቶ የነበረውን የ66ቱን አብዮት ያየን እንደሆነ በአለም ዙሪያ የነበረው ሁኔታ በወቅቱ የነበሩትን ወጣቶች ላይ ተፅእኖ ማሳደር መቻሉ እና የወጣቱ ንቃተ ህሊና የዳበረ መሆኑ ከነበረው ጭቆና ባሻገር ለአብዮቱ መነሳት አበይት ምክንያት ነበር፡፡
እነዚህን ከላይ የዘረዘርናቸውን የአብዮት መነሾዎች ይዘን የሀገራችን ነባራዊ ሁናቴ ካጤንን በኢኮኖሚው በፖለቲካውም ሆነ በማህበራዊው ዘርፍ ያለው ከፍተኛ የሆነ ምስቅልቅል እና ብሶት ለአብዮቱ መነሳት በቂ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን መረጃ የማግኘት መብቱን የተነፈገው ሰፊው የህብረተሰብ ክፍል መብቱን በማስከበር ዙሪያ ላይ ያለው የንቃተ ህሊና መዳበር በጥያቄ ውስጥ ያለ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡
የቡርኪና ፋሶው የአብዮት ንፋስ በፍጥነት ወደ ቶጎ እና ጋቦን ተዛምቶ አምባገነን መንግስታትን ሲያንቀጠቅጥ ይህንን ጀብዱ የሰማው የኢትዮጲያ ህዝብ ምን ያህል ነው; ሰምቶስ ወስጡን የኮረኮረው እና መንፈሳዊ ቅናት ያደረበት ስንቱ ነው; የሚለው ጉዳይ ያሳስበኛል፡፡
በእኛ ሀገር አብዮት እንዲነሳ ካስፈለገ አብዮቱ መሪ ያሻዋል፡፡ በቡርኪና ፋሶም ሆነ አሁን በቶጎ እና በጋቦን የተነሳው ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እየመሩት ያሉት፡፡ በእኛም ሀገር ባለው ተጨባጭ ሁናቴ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተባባሪነት ውጪ በአሁኑ ሰዓት በራሱ የሚፈነዳ አብዮት ይኖራል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን ተቃዋሚዎች
1ኛ፡- ለህዝብ ወቅታዊ መረጃዎችን በማቀበል እና በመተንተን የህዝብን ንቃተ ህሊና የሚያሳድጉበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ፡- በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በማሳደግ የሚሞትላቸው ድርጅቶች መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
Image

Image

ሠማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት መድረክ በመፍጠር ሰላማዊ ሰልፍ ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ/ም ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀው የሐገሪቱ ህዝብ በቦታው በመገኘት ድምፁን እንዲያሠማ ባሳወቁት መሠረት የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እና የማህበሩ አባላት በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ከሌላው የሐገራችን ህዝብ ጋር በመሆን ድምፃችንን እንደምናሠማ እየገለፅን ለሠላማዊ ሠልፉ መሣካት የበኩላችንን ደርሻም ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ በዚህ በጨለማ ዘመን ኃላፊነት ወስደው ይህንን ታላቅ ሠለማዊ ሠልፍ ላዘጋጁት የሠለማዊ ሠልፉ አዘጋጆች ምስጋናችንን በማቅረብ ነው፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያን እያስተዳደሩ ሳይሆን እየገዙ ያሉት ብዙሀኑ ባለስልጣናት ከትምህርት አለም እርቀው ወደ ትግል የገቡ እና አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና የተሻለ ንቃተ ህሊና ያለው ሰው እንዳይፈጠር ትግል ላይ ናቸው በተለይ ለመምህራንና ባጠቃላይ ለትምህርት ስርአቱ ያላቸው ጥላቻ ላቅ ያለ ነው ይህንን እንኳን ስላልተማሩ ነው ብለን እንዳናልፈው የስርአቱ አመራሮች እና አጃቢዎች አለማወቃቸውንም ሊደብቁ ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ሟቹ መለስ ዜናዊ በህይወት ያለው ተፈራ ዋልዋ መምህራኑን ለማሰደብ አፋቸውን ከፍተው ባዶነታቸውን በነጻ ሲያስኮሞኩሙን ኖረዋል፡
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መምህር እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጥርስ ውስጥ ከገቡት መካከል ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ገዢው የወያኔ ቡድን ጠንካራውን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በማፍረስ ተለጣፊ ማህበር ከማቋቋም አልፎ ታላላቅ የማህበራችንን አመራሮች ከአሰፋ ማሩ ጀምሮ በመግደል በተለያዩ ጊዜያት ከኢትዮጵያዊው መምህር ሊነሱ የሚችሉ ተቃውሞችን ለማፈን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል በ2004 እንኳን የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳው የመምህራን ጥያቄ መብታችን ይከበር ያሉ የማህበራችንን አባላት ከስራ ማባረር ጀምሮ ለእስር መዳረጉ የሚታወስ ሲሆን ይህም ሳያንስ በወቅቱ ከአንድ የሐገር መሪ ነኝ ከሚል ግለሠብ የማይጠበቅ ንግግር ከቀድሞው የሐገራችን አምባገነን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በሐገራችን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስማታችን ይታወሳል ይህ በወያኔ አመራች ዘንድ ያለውን ከፍተኛ ንቀት እና ፍርሐት የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ውስጣዊ ፍርሀት የተነሳ በርካታ መስራት የሚችሉ እና ሀገሪቱን ሊቀይሩ ምሁራንን እንዲሰደዱ በማድረግ ያልተሰደዱትን ደግሞ በማሰር እና በማንገላታት የመምህርነትን ሙያን እንደማሰሪያ ብሎም አነስተኛ ደመወዝ በመክፈል የመምህራኑ አእምሮ በማጀት ወሬ እንዲጨናነቅ ማድረጉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
ከሰሞኑም ይህንን ውስጣዊ ፍራቻውን ለካድሬዎቹ በመመሪያ መልክ በመስጠት በየት/ቤቱ የሚገኙ የገዢው ፓርቲ አባላት ያልሆኑ መምህራንን ስማቸውን ከተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በማያያዝ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ሲያቀርብባቸው ሰንብቷል በተለይ የግንቦት ሰባት እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቹህ በማለት በየእለቱ ዛቻ የሚደርስባቸው መምህራን ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው በተለይ ከሰሞኑ የአባይ መዋጮ እንደአዲስ ለማስከፈል የሚደረገውን ጥረት ተከትሎ በተነሳው የመምህራን ጥያቄ በመምህራን ላይ የሚደርሰው መከራ እና ግፍ መጠኑ ጨምሯል፡፡
ስለሆነም የዚህ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን ቢያሳውቅም እልባት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የትምህርት ሚኒስቴሩም ለጉዳዩ እልባት ከመስጠት ይልቅ የአባዬን ወደእምዬ እንዲሉ በኮሚቴው አባላት ላይ ወቀሳ እና ማስፈራሪያ አቅርቧል ይኸውም ወትሮውም በትምህርት ሚኒስቴር ላይ አመኔታ ያልነበረውን ኮሚቴ ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ከሚታገሉ ሌሎች የሙያ ማህበራት እና ፓርቲዎች ጎን እንዲሠለፍ አድርጎታል በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ኮሚቴ አባላት በሰልፉ ላይ እንደምንገኝ ቃል እየገባን ሌላው የሀገራችን መምህርም ከጎናችን በመሆን በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ይገኝ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የኢትዮጵያ መምህራን ድምጽ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
ህዳር 21/2007
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ኢሕአዴግ አምባገነን መንግስት ነው::የአምባገነን መሰረቱ ደግሞ ፍርሃት ነው:: የህሊና እስረኛ የሆነው አንዷለም አራጌን ንግግር ያድምጡት::‪

Please wait, video is loading…

ይህ ፅሑፍ አብርሐ ደስታ በህወሀት ማፍያዎች ተይዞ እስር ቤት ከመግባቱ በፊት የፃፈው ነው፡፡ ስለትግራይ ህዝብ የተለያዩ ሠዎች የተለያዩ ፅሁፎችን ይፅፋሉ እንደዚህ እንደአብርሐ ደስታ ግን እስካሁን ሳነበው የሚመስጠኝ የለም
መልካም ንባብ

የትግራይ ህዝብ ከኢሕአዴግ መንግስት ምን ተጠቅሟል? የትግራይ ህዝብና መንግስት ምን አይነት ግንኙነት አላቸው? እነዚህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ አብርሃ በላይ ከመቀሌ አጥጋቢ መልስ ሰጥቷል:: አብርሃ እንደመነሻ ያደረገው ከአንድ የትግራይ ተወላጅ የቀረበለትን ጥያቄ ነው:: ጥያቄውም ይህ ነው:: “ኢህኣዴግን ትቃወማለህ፣ ግን ህዝብን ለለውጥ ኣነሳስተህ ከህወሓት የባሱ ፅንፈኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ስልጣን ቢይዙስ ??? ስትቃወም ስለዉጤቱም ማሰብ ኣለብህ። በምትፅፋቸውን ነገሮች ለአዳንድ የትግራይ ጠላቶች መጋበርያ እየሆንክ ነው።”

መልስ
ሁሉም ዜጋ (የገዢው ፓርቲ ደጋፊም ተቃዋሚም) መጠየቅ ያለበት (የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ባህሪያዊ ሂደት መሆኑ ተገንዝቦ) በኢህኣዴግ እጅ ያለው ስልጣን (በለውጡ ሂደት) ‘ለማን ይሰጥ’ የሚለውን ነው። ሁለት ስልጣን ለመቀበል ያሰፈሰፉ ሃይሎች ኣሉ፤ (1) የኢትዮዽያ ህዝብና (2) ስልጣን በሃይል ለመያዝ የጓጉ የፖለቲካ ቡድኖች።
ኣንድ
እኔ ታድያ ‘ስልጣን ለኢትዮዽያ ህዝብ መሰጠት ኣለበት’ ከሚሉ ሰዎች ጎራ ነኝ (የምቃወምም ለዚህ ነው)። ምክንያቱም ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ዲሞክራሲን ማስፈን ነው። በዲሞክራሲያዊ መንግስት ህጋዊ ተቃዋሚዎች ይበረታታሉ፣ ኣማራጭ ፖሊሲያቸው ለህዝብ እንዲያቀርቡ ነፃ ሚድያ ይኖራል። ህዝቦች በነፃነት የፈለጉትን ፓርቲ ይመርጣሉ፤ ድምፃቸውም በገለልተኛ የምርጫ ቦርድና የፍትሕ ኣካላት መኖር ይከበራል። የህዝብ ድምፅ ከተከበረ ሲቪላዊ መንግስት የማቋቋም ዕድል ይኖራል። በዚ መንገድ በሃይል ስልጣን ለመያዝ የሚቋምጡ ሃይሎች ቦታ ኣያገኙም። ዓፈናው ከቀጠለ ግን ….
ዲሞክራሲ ማስፈን የብዙ ችግሮች መፍትሔ ይሆናል። የ’ኣፍርሶ መገንባት’ ስትራተጂ ዕዳ ይቀንሳል። ደም ማፋሰስ ያስወግዳል። ኧረ ሲንቱን …… ህወሓት/ኢህኣዴግ ኣሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ማድረግ የሚችለው ትልቁ ኣስተዋፅኦ ዲሞክራሲን በማስፈን ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ነው። የትግራይ ህዝብ ትግልም ለውጥ ኣመጣ እንላለን።
በኢትዮዽያ ታሪክ (እስከ ኣሁን ድረስ) ስልጣን የተያዘው በህዝብ ፍላጎትና ምርጫ ሳይሆን በጠመንጃ ኣፈሙዝ ነው። ፓርቲዎች ተጠናክረው ስልጣን መያዝ ከቻሉ ለመጀመርያ ግዜ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር ተግባራዊ ያደርጋሉ (የኢትዮዽያ የፖለቲካ ታሪክ ይቀይራሉ) ። ሰለማዊ ሽግግር ተደረገ ማለት ደግሞ ስልጣን ወደ ህዝብ ወረደ ማለት ነው። ህዝብ የስልጣን ባለቤት ከሆነ የመንግስት ኣካላት የሰው ጌቶች ሳይሆኑ የሰው ኣገልጋዮች ሆኑ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የህዝቦች ነፃነት ተከበረ ማለት ነው፤ ቀጥሎም እኩልነት፣ ኣንድነት፣ መከባበር ይኖራሉ። እኛም ተዋደድን። ስለዚ ፓርቲዎች ሊከበሩ ይገባል።
ህወሓቶች የስልጣን ዕድሜ ማራዘም መፍትሔ እንዳልሆነ መገንዘብ ኣለባቸው። የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ድጋፍ ማሰባሰብ ዘለቄታ ያለው የህዝብ ደህንነት ዋስትና ሊሆን ኣይችልም። የህዝብ ዋስትና ዲሞክራሲያዊ (ጠንካራ፣ ነፃና ገለልተኛ) ተቋማት ናቸው። መሪዎች ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ፤ ሲሄዱና ሲመጡ እንደ ድልድይ ሁኖው በማገልገል ለህዝብ ደህንነት ዋስትና (ወይ ጋሻ) የሚሆኑ እነዚህ የፍትሕ ተቋማት ናቸው።
ሁለት
ህወሓት /ኢህኣዴግ የያዘውን ስልጣን በፍቃደኝነት (በምርጫ) ለህዝብ ካላስረከበ በሃይል እስኪወርድ ድረስ በስልጣን ይቆያል ማለት ነው። ይህንን የሚያሳየን ህወሓት ስልጣኑን ለሌላ ታጣቂ (ተዋጊ) ሃይል እንጂ ለህዝብ ለመስጠት ፍላጎት የለዉም ማለት ነው።
ሌላ የታጠቀ ሃይል ስልጣን ከያዘ ሌላ ህወሓት /ኢህኣዴግ መጣ ማለት ይሆናል። ምክንያቱም ስልጣን በሃይል ለመያዝ ሰው መግደልን ጨምሮ ሌሎች የተወሰኑ ወንጀሎች ይሰራሉ፣ ግድያ ይኖራል። (ሃይል ስንጠቀም ወንጀሎችም ይኖራሉ ኣለበለዚያ ግን ለውጡ የመጣው በሃይል ሳይሆን በሰለማዊ መንገድ ነው ማለት ነው)። እነዚህ የተወሰኑ ወንጀሎች ለመሸፈን ሲባል ሌሎች ተጨማሪ ወንጀሎች ይፈፀማሉ። እነዚህ ወንጀሎች እንዳይጋለጡ ለማድረግ (ጉዳቸውን እንዳይወጣ) ስልጣን የያዘውን የፖለቲካ ቡድን የራሱ ዳኞች፣ ወታደራዊ መኮነኖች፣ የደህንነት ሃላፊዎች ወዘተ ይኖሩታል።
ከተሸናፊው የፖለቲካ ድርጅት ‘ደህንነታዊ ስጋት’ በመስጋትም የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በጠላትነት ይፈርጃል። እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎችም ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ሌላ የኣደረጃጀት ኣማራጭና የፖለቲካ ስልት ያፈላልጋሉ። የሃገር ኣንድነትም ኣደጋ ላይ ይወድቃል።
ስልጣን ላይ የወጣ ሃይል ድክመቱን ለመሸፈን ሲል የሚጠራጠራቸውን ህዝቦች ለመቆጣጠር (የመገንጠል ጥያቄን በሃይል ለመመለስ) እንዲችል ኣሻንጉሊት ድርጅቶችን ያቋቁማል። ይህንን ሁኔታ ሌላ ኢህኣዴግ ያደርገዋል። እኛ ደግሞ “ኣዲስ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ …” እንዘፍናለን።
ሦስት
በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት ህዝቦችን የመጨቆን ዕድሉ ይቀንሳል። ምክንያቱም ፖለቲከኞቹ ከወንጀል ነፃ የመሆን ዕድል ኣላቸው። (ከወንጀል ነፃ ካልሆኑ ኣይመረጡማ) ወይም ከስልጣናቸው ለማውረድ ቀላል ይሆናል። እነሱም ከስልጣን መውረድን የሞትን ያህል ኣይፈሩም (በህዝብ የተመረጡ ናቸዋ)። ስልጣን ላለመልቀቅ ኣያንገራግሩም (ህዝቡ ሰልፍ ይወጣላ)። መሪዎቹ ሰልፍ ለወጣ ህዝብ እንዲገድሉ ወታደሮቻቸውን ኣያዙም። ምክንያቱም በፖለቲከኞችና ወታደሮች መሃከል (ህገ መንግስታዊ ከሆነ በቀር) ልዩ ግንኙት ወይ ትስስር ኣይኖራቸውም።
በህዝብ የተመረጡ መሪዎች ተጠያቂነታቸው ለመረጣቸው ህዝብ ይሆናል (የስልጣን ምንጫቸው ህዝብ ነውና)። ስልጣን የያዙት በሃይል ከሆነ ግን ተጠያቂነታቸው ለጠመንጃቸው ነው። የህዝብ ጉዳይ ኣያሳስባቸውም። ስለ ካድሬዎቻቸው እንጂ ስለ ህዝቡ ችግር ላይጨነቁ ይችላሉ።
ኣራት
ኢህኣዴግን መቃወም ለምን???
(1) ገዢው ፓርቲ ስልጣን ወደ ህዝብ እንዲመልስ ለማገዝ ያስችላል። ኢህኣዴግ የህዝብን ድምፅ ኣላከበረም፣ ህዝብ እየገዛ እንጂ እያስተዳደረ ኣይደለም ያለው። ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንፈልጋለን። የሁሉም ህዝቦች ደህንነትና ልማት የሚረጋገጠው ዲሞክራሲያዊ ነፃነት ሲፈቀድ ነውና።
(2) ኢህኣዴግ ችግሮቹን እንዲያርም ለማድረግ ነው። የመናገር መብት ያፍናል፤ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም ሌሎች ህዝቦች ይጨቁናል፤ ለራሱ ጥቅም ሲባል ኣሻንጉሊት ድርጅቶች በማቋቋም የሚገዙትን ህዝብ የማይወክሉ መሪዎች በኣስገዳጅነት እንዲገዙ ያደርጋል። እነዚህ ህዝቦች ራሳቸው ይወክሉናል ብለው በመረጡዋቸው ድርጅቶች መተዳደር ኣለባቸው። ህዝቦች በሚወክሉዋቸው መሪዎች ሲተዳደሩ የትግራይ ህዝብ ቢጠቀም ‘ጂ ኣይጎዳም።
(3) ለውጥ ፈልገን ነው። ለውጥ የመፈለግ ኣባዜ የተፈጥሮ ጥሪ ነው። እያንዳንዱን ትውልድ የራሱ /ለራሱ የሆነ ለውጥ የማምጣት ወይም የማድረግ የግል የቤት ስራ ኣለው። የኣባቶቻችን ታሪክ ለኛ (የኛ) ሊሆን ኣይችልም። ስለዚ ለውጥ መፈለግ በራሱ ስሕተት ኣይደለም። ለለውጥ መነሳት የህይወት ግዴታችን ነው።
ኣምስት
የትግራይ ስጋት የሚመነጨው ከነዚህ ዲያስፖራ ፖለቲከኞች ከሚያራምዱት ኣስተሳሰብ እንደሆነ ተነግሮኛል። እነዚህ የ ‘ትግራይ ጠላቶች’ እንደሆኑ ተደርገው የሚታሰቡ ሃይሎች መነሻቸው ምንድነው ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።
እነዚህ ሰዎች በኢህኣዴግ መንግስት በጠላትነት ተፈርጀው ‘ኣሸባሪ’ ተሰይመው ከሃገራቸው የተባረሩ ናቸው። ከሃገራቸው ከተባረሩ ታድያ እንዴት ለህወሓት ጥሩ ኣመለካከት ሊኖራቸው ይችላል? በህወሓት ዘመነ መንግስት ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ካልተፈቀደላቸው ሃገራቸውን ለመግባት ህወሓትን በሃይል ማስወገድ ግድ ሊላቸው ነው። ስለዚ ጥረታችው ኣይደንቀኝም።
ጥያቄው እነዚህ ሰዎች ለምን የትግራይን ህዝብ target ያረጋሉ የሚል ነው። መልሱ ግን ቀላል ነው። (1) ህወሓት ራሱ … ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ኣንድ እንደሆኑ ኣድርጎ ይሰብካል (ድጋፍ ለመሰብሰብ)።
(2) የዲያስፖራው የፖለቲካ ስትራተጂ ተደርጎ ይወሰዳል። የትግራይን ህዝብ target ሲያደርጉ የትግራይን ህዝብ ፈርቶ ህወሓትን ከመደገፍ ይቆጠባል ከሚል ኣስተሳሰብና ከትግራይ ህዝብ ውጭ ያለው ኢትዮዼያዊ ‘በኣንድነት በመቆም’ ህወሓትን ከስልጣን ለማውረድ እንዲነሳ ታስቦ ነው።
(3) ተሳዳቢዎቹ ዲያስፖራ ኣራት ዓይነት ናቸው።
(ሀ) የፖለቲካ ብቃት የሚያንሳቸው (ህዝብና ገዢው ፓርቲ መለያየት ያቃታቸው ወይም መለያየት ያልፈለጉ)። እነዚህ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ህወሓትን ያግዛሉ። የትግራይን ህዝብ ሲሳደቡ , የትግራይ ተወላጆችም ሳይፈልጉ ከህወሓት ጎን እንዲሰለፉ ይገደዳሉ። ግን ስጋት ሊሆኑ ኣይችሉም ስልጣን ኣይዙምና (በሃይል ካልሆነ በቀር)፤ የፖለቲካ ዕውቀት ፤ስለሚያንሳቸው ።
(ለ) ወደ ሃገራቸው እንዳይገቡ የተከለከሉ (በሰለማዊ መንገድ እንዲታገሉ በህወሓት ያልተፈቀደላቸው)። እዚ ላይ ስጋት ፈጣሪው ህወሓት ራሱ ነው።
(ሐ) በሻቢያ ተልከው ኢትዮዽያን ለመበጥበጥ ተከፍሎቸው የሚሰሩ (ኣብዛኞቹ ኤርትራውያን ናቸው)። ኢትዮዽያውያን ካልተባበርናቸው የትም ኣይደርሱም።
(መ) ከህወሓቶች ጋ ግንኙነት ያላቸው …. ይህንን ስትራተጂ ‘ዲያስፖራ ፖለቲከኞች ጥላቻ የሚሰብኩ ናቸው’ ተብለው እንዲፈረጁና የትግራይ ህዝብ እነሱን ፈርቶ ና ሰግቶ ከህወሓት ጎን እንዲሰለፍ ለማድረግ የታለመ ነው።
ስለዚህ ጥላቻን የሚሰብኩ ኣንዳንድ ፖለቲከኞች ሃገራቸውን እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ህዝባቸውን ለለውጥ እንዲያነሳሱ ቢደረግ የትግራይ ህዝብ የሚያዋሩዱበት ምክንያት ባልኖራቸው ነበር። ስለዚ የትግራይ ስጋት ሆን ተብሎ በህወሓት የተቀናበረ ነው።
ስድስት
ስጋቱ ቢኖርስ??? መፍትሔው በህወሓት እጅ ነው። ሥጋቱን ለመቀነስ ራሳችን የሌሎች ህዝቦች ስጋት ፈጣሪ መሆን የለብንም። እንደ ኣሰራርም :
(1) ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም ሌሎች ህዝቦች መጨቆን እንዲሁም ስጋት መፍጠር የለበትም። (ካልጨቆነ ስጋቱ ኣይኖርም)። ከዚህ ኣልፎም የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮዽያ ህዝቦች በሰላም መኖር የሚፈልግ እንጂ የህወሓት የጥላቻ ፖለቲካ እንደማይደግፍ በግልፅ መናገር ኣለበት። ይህ ካልሆነ ደግሞ መፍትሔው መደራጀት እንጂ ስልጣን የሙጥኝ ይዞ ህዝቦችን መጨቆን ኣይደለም።
(2) ህወሓት ዲሞክራሲን ማስፈን ሲገባው የታጠቁ ሃይሎችን ወደ ስልጣን መጋበዝ የለበትም። ህወሓት ህጋዊና ሰላማዊ የተቃውሞ ድርጅቶችን ሲያዳክምና ሲያፈርስ ስልታቸውን ቀይሮው የሃይል መንገድ ተከትለው ከስልጣን እንዲያወርዱት እየጋበዛቸው ነው። ይህ ኣካሄድ ደግሞ ህወሓት በሌሎች ህዝቦች እንዳደረገው ሁሉ ኣሻንጉሊት ድርጅት መስርተው የትግራይን ህዝብ ለመጨቆን ያስችላቸዋል።
ሰባት
“ለአዳንድ የትግራይ ጠላቶች መጋበርያ እየሆንክ ነው” የሚል ነገር ኣለ። የትግራይ ጠላት ማነው? እንደኔ እምነት: የትግራይ ህዝብ ጠላት ጭቆና ነው። ጠላቶቹ ጨቋኞቹ ናቸው። ድሮ ደርግ ነበር ጨቋኝ፣ ኣሁን ደግሞ ህወሓት። ስለዚህ የትግራይ ጠላቶች ጨቋኝ ገዢዎቹ እንጂ ሌሎች ብሄሮች ወይ ሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ኣይደሉም።
ተጋሩ (የትግራይ ተወላጆች) የራሳቸው የፖለቲካ ኣቋም ይዘው ገዢውን መደብ ሲቃወሙ ‘ከጠላቶቻችን ኣብረዋል’ ወይ ‘ለጠላቶቻችን ያጋሉጥናል’ በሚል ሴራ በመንግስት ደጋፊዎች ይወቀሳሉ፣ ይገለላሉ። ግን እንዲህ ከተነቀፉኮ የትግራይ ተወላጆች የመቃወም መብት የላቸውም ማለት ነው። (ወይም እንዲቃወሙ ኣይፈቀድላቸውም ማለት ነው?)
በዚህ መልኩ (ተጋሩ የመቃወም መብታቸውን ከተገደበ) ‘ከትግራይ ወጥቼ ለትግራይ እቆማለሁ’ የሚል የህወሓት ድርጅት ፀረ ተጋሩ እየሆነ ነው ማለት ነው። ህወሓት ለትግራይ ቢቆም ኑሮ እኛ ተጋሩ የፈለግነውን የፖለቲካ ኣመለካከት እንድነራመድ ለምን ኣይፈቅድልንም? ደርግ ኣፈነን። ህወሓትም እንዲህ ካፈነን፣ ህወሓት ከደርግ (ለትግራይ ህዝብ) በምን ይሻላል? በምንስ ይለያል???
ህወሓት የመናገር መብታችን ካላከበረ፣ ሁሉም የትግራይ ሰው በእኩል ዓይን ካልታየ፣ በተግባሩና በስራ ኣፈፃፀሙ መመዘን ሲገባው በጎጠኝነት በስራው ግልፅ የሆነ ኣድልዎ ከተፈፀመበት፡ ከዚህ በላይ የህዝብ ጠላትነት ከየት ሊመጣ ነው? የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም ሌላ ህዝብ በነፃነት ሓሳቡ የመግለፅ መብት ኣለው፤ ሊከበርለትም ይገባል።
ህይወቱ ሙሉ ከጭቆና ነፃ ለመውጣት ሲታገል የኖረ ህዝብ የእኩልነት መብቱ ሲነፈግ እኛ ዝም ብለን ሳንቃወም ማየት ነበረብን? ብዙ መስዋእት የተከፈለበት የ17 ዓመት የትጥቅ ትግል በተወሰኑ ሰዎች ተጠልፎ ለግል ስልጣንና ጥቅም ሲውል እኛ ዝም ብለን ተመልካች እንድንሆን ነው የሚጠበቀው? ወይስ የራሳችን ሚና መጫወት ይኖርብናል!?
ስምንት
የኢህኣዴግ መንግስትን የተቃወመ ሰው ወይ የፖለቲካ ድርጅት የትግራይ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ኣድርገው በማቅረብ የትግራይን ህዝብ ለማጭበርበር የሚሞክሩ የመንግስት ኣካላት እንዳሉም ይታወቃል። ግን ህወሓትን መጥላት የትግራይ ህዝብን መጥላት ኣያሰኝም። ህወሓትን መቃወም የትግራይ ህዝብን መቃወም ማለት ኣይደለም። ምክንያቶች
(1) ህወሓት (ገዢው መደብ)ና የትግራይ ህዝብ (ተገዢው ህዝብ) አንድ አይደሉም፤ ሊሆኑም ኣይችሉም። ፓርቲና ህዝብ አንድ ተደርጎ የሚወሰደው ለፕሮፓጋንዳ (የህዝብ ግንኙነት) ሥራ ነው። የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በፊት ነበር፤ ከህወሓት በኋላም ይኖራል።
(2) ተቃዋሚን በጠላትነት ማየት የፖለቲካዊ ኣስተሳሰብ ችግር ውጤት ነው። መቃወም ተፎካካሪ (ኣማራጭ ሃይል) መሆን እንጂ ጠላትነት ኣይደለም። ዴሞክራሲ ኣሰፍናለሁ የሚል መንግስት ተቃዋሚዎችን በጠላትነት መፈረጅ ተገቢ ኣይደለም።
(3) ሰዎች ወይ ድርጅቶች ህወሓትን (እንደገዢ ፓርቲ) የመቃወም ተፈጥሮኣዊ መብት ኣላቸው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ከፈለገ (በፍላጎቱ ) ይምረጠውና ትግራይን ያስተዳድር (መብቱ ነው)። ህወሓት ላልመረጠው ህዝብ ኣሻንጉሊቶችን በመፈብረክ ሌሎች ህዝቦችን በእጃዙር የመግዛት መብት ግን የለውም።
ህወሓት ለኢትዮዽያ ህዝቦች መሪዎች የመምረጥ መብት ማን ሰጠው? ራሳቸው እንዲመርጡ ለምን ኣይፈቀድላቸውም? ስለዚ ህወሓትን ለመቃወም በቂ ምክንያት ኣላቸው። ይህን ሁኔታ በመቃወማቸው ‘የትግራይ ህዝብ ጠላቶች’ ሊያሰኛቸው ኣይችልም። የኢትዮዽያ ህዝቦች የራሳቸውን ተወካዮች በነፃነት የመምረጥ ሙሉ መብት ኣላቸውና።
(4) ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የቆመ ድርጅት ከሆነ ለምን እንድንደራጅ ኣይፈቅድልንም? መደራጀትኮ ሃይል ይፈጥራል። ለምንድነው ተደራጅተን ሃይል እንዳንፈጥር የሚያደርገን? ከዚህ በላይ ጠላትነት ኣለ እንዴ? ስለዚ ‘የትግራይ ህዝብ ጠላት ህወሓት ነው’ ማለት እችላለሁ።
(5) የትግራይ ህዝብ (ባይሳካም) አንድ ኣስተሳሰብ እንዲኖረው ጥረት ማድረግ ትውልድን መግደል ነው። ብዙ ሰዎች አንድ ዓይነት ኣስተሳሰብ እንዲይዙ ለማድረግ የብዙዎቹ ኣስተሳሰብ መግደል ግድ ይላል። ኣስተሳሰብ ታፈነ፣ ተገደለ ማለት ደግሞ ትውልድን ተገደለ ማለት ነው። ምክንያቱም የለውጥ ምንጭ ኣስተሳሰብ ነው።
(6) ደሞ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት አገዛዝ ነፃ መውጣት ኣይፈልግም ያለ ማነው? በትግራይ ሁሉም ቢሮዎች (ከላይ እስከ ታች) በተወሰኑ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ቁጥጥር ስር ነው። ማነው ትግራይ የነሱ ብቻ ናት ያለው? ትግራይኮ የሁላችን ናት? ወይስ የነሱ ባሮች (Slaves) ሁነን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል?
ማንም ሰው የመደገፍም የመቃወምም ተፈጥሮኣዊ መብት ኣለው። የመቃወም መብት የህወሓት የግል ስጦታ ኣይደለም። ህወሓት ሲፈልግ የሚሰጠን ሲፈልግ ደግሞ የሚከለክለን የግል ሃብቱ መሆን የለበትም።
ዘጠኝ
የስርዓቱ ተጠቃሚዎች (በቤተሰባዊ ሙስና) ገዢውን ፓርቲ በሚቃወሙ ግለሰዎች ላይ ስም የማጥፋት ዘመቻ ከማካሄድ ኣይቦዝኑም። “የስርዓቱ ተጠቃሚዎች” ያልኩበት ምክንያት፡ ሕገ ወጥና ተቀባይነት የሌለው መንገድ በፈጠረው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥገኝነታቸው በራስ የመተማመን ስሜታቸው ካላሽመደመደው በቀር ሃሳባቸውን በነፃነት በሚፅፉ ሰዎች ስም የማጥፋት ዘመቻ ማድረግ ኣስፈላጊነቱ ኣይታየኝም ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው።
ህወሓቶች ለሚቃወማቸው ሰው ኣንድም ያስራሉ (ያዋክባሉ) ኣልያም ስም በማጥፋት ተግባር ይሰማራሉ። ለምን ስም ያጠፋሉ???
(1) በሙስና የበሰበሰ ስርዓት ተቃውሞ የሞትን ያህል ይፈራል። ምክንያቱም የግለ ሰዎች የተቃውሞ ፅሑፎች ድጋፍ ሊያሳጡት ይችላሉ። ድጋፍ ካጣ ስልጣን ሊለቅ ይችላል፤ ስልጣን ከለቀቀ የሰራውን ጥፋት ይጋለጣል።
(2) ጥቅሙ እንዲጎድልበት ኣይፈልግም (የእህል-ውሃ ጉዳይ ነው)። (“ኣብ ፃሕልና ኢድኩም ኣይትሕወሱ፤ ንሕና ክንበልዕ ንስኹም ጠጠው ኢልኩም ረኣዩ” ዝዓይነቱ።) ኣጥንት የያዘ ውሻ …… ይሆናል።
ህወሓት ተቃውሞ ሲያይልበት (ሁሉም ነገር ለብቻው ጠቅልሎ በመያዙ) ” እኔ ብቻ ኣይደለሁም የበላሁት፡ የትግራይ ህዝብም ኣብሮኝ በልቷል፤ ስለዚ እኔ ብቻ ተጠያቂ ኣልሁን፣ ከትግራይ ህዝብ ኣትነጥሉኝ” የሚል መልእክት ያለው ተግባር እያከናወነ ይገኛል።
የትግራይ ህዝብ ባልዋለበት (‘የማዩ የሰማዩ’) ሊያስወነጅለው እየሞከረ ነው (‘ጅብ ይበለሃል’ ከሚል ማስፈራርያ በተጨማሪ መሆኑ ነው)።
እኔ ግን እላለሁ፡ የህወሓት ሰዎች ባጠፉት ጥፋት የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ ሊሆን ኣይገባም። እውነታውን መካድ የችግሩ መፍትሔ ኣይሆንም።
አስር
ሓሳብ በመግለፅ ብቻ ኣንድን ብሄር ወይ ፓርቲ ከስልጣን ለማውረድ ወይ ለማውጣት ኣይቻልም ። ሓሳባችን በነፃነት በመግለፃችን ከህወሓት ‘የባሱ’ ሃይሎች ስልጣን እንድይዙ ኣያስችልም ። እነዚህ ‘የትግራይ ጠላቶች ’ እየተባሉ የሚፈረጁ ግለሰዎች ተሳክቶላቸው ስልጣን ብይዙ እንኳ የራሳችውን ህዝብ ነው የሚያስተዳድሩ። ትግራይን የሚያስተዳዱርበት መንገድ የለም (እነሱም ትግራይን የማስተዳደር ስራ ‘ለኛ ይሰጠን’ ኣላሉም)። በህወሓት የሚሰጠን “እኔ ከሌለሁ ጅብ ይበላችኋል” ዓይነቱ ማስፈራርያ ግን ለትግራይ ህዝብ ያለው ንቀት የሚያሳይ ነው። ትግራይ የህወሓት ባለስልጣናት ብቻ ወልዳ የቀረች መኻን ኣይደለችም።
It is so!!!
ኣብርሃ ደስታ
Image

Image

– ክፍተኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚል ተከፍለው እየተሰለሉ ስልካቸው እየተጠለፈ መሆኑ ታውቋል::
– የሕወሓት ስጋት ውስጥ ውስጡን ክሻእቢያ ጋር ግንኙነቱን እንዲያጠናክር አድርጎታል::
– የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስኝ የለውጥ ወቅት ላይ መሆኑን አውቆ አደባባይ በመውጣትወያኔን ሊያስወግድ ይገባል::
Minilik Salsawi
ከፊታችን አደጋ አለ በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገቡት እና በመፍትሄፍለጋ ስብሰባዎች የተወጠሩት የሕወሃት ሰዎች ክከፍተኛ ባለስልጣናት ጀምሮ እንከ በታች ሹሞች ድረስ በብአዴንና በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ክፍተኛ የማስፈራራት እና የማዋከብ ሽብር እየፈጸሙ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ባለስልጣን ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::

በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የሚገኙ የብአዴን እና የኦሕዴድ አባላት በግል እንዳይገናኙ እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ጋር እንዳይገናኙ ከፍተኛ የሆነ ክትትል እየተደረገባቸው ሲሆን በባለስልጣናት ደረጃ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚያጠና የደህንነት ቡድን የተመደበባቸው ሲሆን ስልኮቻቸውም እየተጠለፉ መሆኑን እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል::

የብአዴንና የኦሕዴድ ሰዎችን ከፍተኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚል ተከፍለው በሕወሓት እየተሰለሉ ስልካቸው እየተጠለፈ ሲሆን እንደ በግ የሚታዘዝላቸው የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ውስጥ ዘልቀው እንዳይገቡ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆኑ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት መቀራረብ እና አብሮ መዋል የሕወሓት ሰዎችን ማሳሰቡን እና የደህንነት ክትትል እያደረጉባቸው እንደነበረና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደመቀ መኮንን እና ከሙክታር ከድር ጀምሮ እስከ በታች የፌዴራል ባለስልጣኖች ላይ ከፍተኛ ስለላ እየተካሄደ ምንጮች መረጃ ሰተው እንደነበር ሲታወቅ ይህ በአሁኑ ወቅት በእጥፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል::

ሁኔታዎች መልካም አይደሉም ከፊታችን አደጋ ተደቅኗል::ለውጥ ያስፈልጋል::የሚሉ የተቆጡ ድምጾች በስፋት በኢሕኣዴግ አባላት እየተሰሙ ያለበት አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ሕወሓት በግል እና በጋራ ባለስልጣናቱ ላይ ከፍተኛ ማስፈራራት እና ዛቻ እያደረገባቸው መሆኑን የተናገሩት ምንጮቹ ኢሕአዴግን ለመናድ ብትሞክሩ ሃገሪቷ ትበታተናለች::እንደ ሱማሊያ መንግስት አልባ ሆና እንደ ሩዋንዳ ትበጠበጣለች እያሉ ከማስፈራራትም አልፎ በግል የተነከራችሁበት ሙስና አደባባይ እናወጣዋለን:: እኛን ማንም ሊጠይቀን አይችልም ቁልፉ እኛ ጋር ነው የሚሉ በኣደገኛ መርዞች የተሞሉ ማስፈራሪያዎች መሰንዘር ክጀመሩ እንደቆዩ ተገልጿል::

የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ሶማሌ እና ሩዋንዳ ማስብ ጅልነት ነው::የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ እንጂ ፍጅት ስለማይፈልግ ኢሕ አዴግ ሲፈርስ ሕወሓት እንደሚያስበው ሳይሆን ትልቅ ሰላም በሃገሪቱ ላይ ይሰፍናል ያሉት ምንጩ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት የየቀን ሪፖርት እና ግንኙነት በተመለከተ ማን ከማን ጋር እንደዋለ ማን እነማን ቤት እንደሄደ በመከታተል እየቀረበ ሲሆን የሃገሪቱን የደህንነት ቢሮ በጋራ የሚመሩት ጸጋዬ:ጌታቸውና ደብረጺሆን በየቀኑ ለትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶች በአጫጭር ስብሰባዎች መመሪያ እያወረዱ ከመሆኑም በላይ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እየደጋገሙ እንደሚናገሩ ምንጮቹ አክለዋል::

በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ወሳኝ የትግል ወቅት ላይ መሆኑን በማወቅ የበሰበሰውን የወያኔ አምባገነን ስርአት ለመጣል በጋራ አደባባይ በመውጣት የሚያካሂደውን አብዮት የመከላከያ ሰራዊት የፖሊሱ እና የብአዴን እንዲሁም የኦሕዴድ ፓርቲ ለውጡን እንደሚደግፉት የህዝቡን መነሳሳት እየጠበቁ መሆኑን እና ሕወሓት ከመስጋቱ የመጣ ከሻእቢያ ጋር በውስጥ ግንኙነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም ለተመረጡ የኤርትራ ስደተኞች የደህንነት ትምህርት የተሰጠ እንደሚገኝ እኚሁ ባለስልጣን መረጃ አድርሰውኛል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ህዳር 27 እና 28 ሰማያዊ ፓርቲ ከትብብሩ ጋር በመሆን ለነፃነት አደባባይ እንወጣለን፤ የማስተባበሩ ዝግጅት ቀጥሏል – በትግላችን ሰብዓዊ መብቶቻችንን እናስመልሳለን! ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር! ህዳር 20 2007

Image

Image

Image

Image

Image

Image

Image

‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››
Image
ይህን ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ዛሬ (ህዳር 19/2007 ዓ.ም) እኩለ ቀን ላይ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰሞኑን እያካሄዱት ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስመልከት እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን እና ሌሎችንም ሊጠይቁ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡

በጠዋት ቂሊንጦ የሚገኙ ወዳጆቼን ጠይቄ አብረውኝ ከነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ነበር ወደ ቃሊቲ ያመራሁት፡፡ ቃሊቲ የተገኘው ሰው ሁሉ መጠየቅ የሚፈልገውን ሰው እና ሙሉ አድራሻውን እያስመዘገበ ሳለ በመሐል እኔም እስክንድርን መጠየቅ እንደምፈልግ ነግሬ ተመዘገብኩ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን ስማችሁ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ አሁን መግባት አትችሉም መባሉን መዝጋቢ ፖሊሱ አረዳን፡፡ እኔ እና ትንሽ ሰዎች መግባት ስንችል አብዛኛው ሰው ግን መግባት እንደማይችል ተነገረን፡፡

በዚህ ሁኔታ እስክንድር ጋር ደርሰን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል ሰሞኑን ፓርቲያቸው እስረኞችን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ ለእስክንድር ያብራራለት ጀመር፡፡ እስክንድር በተለመደ ጥሞናው ሲያዳምጠው ቆይቶ፣ በግሉ የተሰማውን እና መሆን ቢችል ያለውን ነጥብ ተናገረ፡፡ በመሐል ወጣቱ የአንድነት አባል ወደ እስክንድር ጠጋ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን ሲነግረው ድንገት አንድ የፖሊስ አዛዥ ጨዋታቸውን እንዲያቆሙና እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እንዲገባ፣ ወጣቱ የአንድነት አባል ደግሞ ወደ ውጪ እንዲወጣ በትዕዛዝ ማጣደፍ ያዘ፡፡

ይህኔ እስክንድር ለስለስ ባለ አነጋገር ምንም እንዳላጠፋን በመግለጽ ፖሊሱ መረጋጋት እንዳለበት አስረዳ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ግን ጭራሽ ብሶበት ወጣቱ በቶሎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹ፖለቲካ ማውራት አቁሙ› የሚል ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ እስክንድር ድንገት በኃይለ ቃል ተናገረ፡፡ ‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው!›› አለ እስክንድር በስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

በግሌ እስክንድር እንዲረጋጋ፣ ሁኔታው ግን ያልተገባ እንደሆነ ገለጽኩ፡፡ ፖሊሱ ግን ሊረጋጋ አልቻለም፡፡ እስክንድርን ይዞት ሄደ፡፡ ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› ሲል እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እየገባ ተናገረ፡፡ የፖሊስ አዛዡም ከእስክንድር ጋር የነበረንን ቆይታ ሰዓቱ ሳይደርስ ገታው፡፡ የእስክንድር ያገባኛል ባይነት አስደመመኝ፡፡ እስር ቤት ሆኖም፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እስክንድር ስለ ሀገሩ እንደሚያገባው በስሜት ተናገረ፡፡ መብቱን መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ አስረገጠ፡፡

ስለ ያገባኛል ባይነት ሳስብ በጠዋት ቂሊንጦ ያገኘኋቸውን የዞን 9 ጦማሪዎች አስታወስኩ፡፡ ‹ስለሚያገባን እንጦምራለን!› ይላሉ ወጣቶቹ ጦማሪያን፡፡ ከአብርሃ ደስታ ጋር አብረው ያገኘኋቸው እነ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ አወጉኝ፡፡ ‹‹ህወሓት አንድ ወይም ሁለት ነባር የህወሓት ባለስልጣናትን በሽብር ከከሰሰ ስርዓቱ እንዳበቃለት እቆጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሽብር ማታለያ መሆኑ ይቀራል›› አለኝ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ አብርሃ ደስታ ቀበል አድርጎ ‹‹እናት አልጋነሽ በሽብር ስትከሰስ በጣም ብዙ ሰው ተቃውሞ ነበር›› አለ፡፡ አጥናፍ በበኩሉ ‹‹ቄስና ሸህ ሽብርተኛ እየተባለ አይደለም እንዴ›› በማለት ጠየቀ፡፡

አብርሃ ደስታ አንድ ነገር በኃይል እንደሚቆጨው ተናገረ፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹ብዙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሳላደርግ መታሰሬ ይቆጨኛል!›› አለ፡፡ በፍቃዱ በበኩሉ፣ ‹‹እኔም የገባኝ ነገር ያለውን የሰላማዊና ህጋዊ የመስሪያ ልክ አለመስራታችን ነው፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዲህ ለሚያስሩን ስንት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳ ሳናደርግ በትንሽ ነገር በርግገው እዚህ ሲያስገቡን ይቆጨኛል›› በማለት ሀሳቡን ቀጠለ፡፡ ‹‹በእርግጥ አንድ ሰው አሁን መጠንቀቅ ያለበት የሚሰራው ስራ ህጋዊ መሆን አለመሆኑን እንጂ፣ ይህን ካደረኩማ ያስሩኛል የሚለውን መሆን የለበትም፡፡ እነሱ ከፈለጉ ያስሩሃል፤ ስለዚህ መብትህን ተጠቅመህ መታሰሩ ይሻላል እንዲሁ ምንም ሳይሰሩ ከመግባት›› ሲል አብርሃ ሀሳቡን አካፈለ፡፡

ቂሊንጦ ከእነ በፍቃዱ ጋር ስንጨዋወት ስለእስክንድር ነጋ ትሁትነት፣ አስተዋይነት፣ ሰላማዊነት እያነሱ ሰላምታ እንዳደርስላቸው ጠየቁኝ፡፡ እኔም እስክንድር ነጋን ሳውቀው በትሁትነቱ፣ በአስተዋይነቱና በሰላማዊነቱ ነው፡፡ ዛሬ በነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተበሳጭቶ ነበር የተመለከትኩት፡፡ ያ ፈገግታው ከፊቱ ብን ብሎ ጠፍቶ ‹‹ያገባኛል!›› ሲልበት የነበረውን ስሜት ግር አለኝ፡፡ ካልነኩት የማይነካ ሰው ሲነኩት ትንታግ ነው፡፡ እስክንድር እዛ ስሜት ውስጥ የገባው ተገድዶ ነበር፡፡ ሊጠይቁት የመጡትን ሰዎች አብዛኞቹን አላስገባም ማለታቸው ሳያንስ ከገቡትም መካከል የምታወራውን እኔ ልምረጥልህ በሚል ግብዝነት አባርረዋል፡፡ እስክንድር ይህን አይቶ ዝም ማለት አልቻለም፡፡ ስለሆነም እንዲህ አለ፤

‹‹…እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው! ስለሀገሬ ያገባኛል!››

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳሩ ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ አስገባ
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ.ም ለሚደረገው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ህዳር 18/2007 ዓ.ም ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የእውቅና ደብዳቤ አስገባ፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የገባው ደብዳቤ በሰማያዊ፣ መኢዴፓ እና ኢብአፓ ተፈርሞ የገባ ሲሆን የእውቅና ደብዳቤውንም ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር አስገብተዋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ በሄዱበት ወቅት የአቶ ማርቆስ ተወካይ ለሆኑት አቶ ፈለቀ አበበ ደብዳቤውን ለመስጠት ጥረት ቢያደርጉም ተወካዩ ‹‹የከንቲባ ጉዳዮች ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የለም፡፡ እሱ ካልመራበት መቀበል አንችልም›› በሚል ደብዳቤውን አልቀበልም እንዳሏቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹ ወደ አቶ አሰግድ ቢሮ ቢያቀኑም እንዳላገኙዋቸው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሆኖም የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤ መስጠት እንጂ ደብዳቤ ማስመራት የሰራተኞቹ እንጂ የእነሱ ስራ እንዳልሆነ በመግለጽ ደብዳቤውን ዛሬ ህዳር 18/2007 ዓ.ም ታመዋል የተባሉት የአቶ ማርቆስ ተወካይ የሆኑት አቶ ፈለቀ ቢሮ በአራት ምስክሮች ፊት አስቀምጠው መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡ አመራሮቹ የእውቅና ደብዳቤውን አቶ ፈለቀ ቢሮ አስቀምጠው ከመውጣታቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በፈጣን መልዕክት (ኢ ኤም ኤስ) በሪኮመንዴ ቁጥር eg157416502et መላካቸውን ገልጸዋል፡፡

የአዳር ሰላማዊ ሰልፉ ህዳር 27 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተጀምሮ ህዳር 28 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ቦታውም መስቀል አደባባይ ላይ እንደሚሆን መወሰኑ ታውቋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች የእውቅና ደብዳቤውን ለማስገባት በሄዱበት ወቅት በቦታው የትብብሩ አመራሮች የሚያውቋቸው ደህንነቶች ባለ ጉዳይ በመምሰል ይመላለሱ እንደነበርና ፖሊሶችም ይከታተሉ እንደነበር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Image

የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል። ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል። (በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል)

ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።

በሰሜን ጎንደር የሕወሓት አማሳኞች ሰርገው የበመግባት ወጣቱን እያጋደሉ መሆኑ ተሰማ::

-ከከተማው ለስራ የሄዱ ወጣቶች ንብረታቸውን እና ገንዘባቸውን ሳይሰበስቡ አከባቢውን ለቀዋል
በኢትዮ ሱዳን ድንበር ላይ ለስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን መንደር እየለዩ በመቧደን በከፍተኛ ጭፍጭፍ ውስጥ እንደሚገኙ ከአከባቢው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::

ከሱዳን ጋር በተያያዘው እና የታች አርማጮ መሬት ከሆነው ሰቲቱ ሁመራ ማይካድራ ሉግዲ አብዲራፍ አብድራሃጀር መተማ ሸዲ የተወሰነውን ጠገዴ ያሉት የጎንደር መሬቶች ላይ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተማሩ የሕወሓት አባላት የሆኑት የጊዜው ባለሃብቶች በቀተሯቸው እና ከአማራው ክልል ጎንደር ጎጃም እና ወሎ የመጡ ወጣት ገበሬዎችን እርሲ በራስ በመንደር እና በጎጥ በመከፋፈል እንዲተራረዱ እንዲጨራረሱ የሰሩበትን ገንዘብ ሳይሰበስቡ አከባቢውን በፍርሃት ለቀው እንዲሄዱ እያደረጉ መሆኑን መረጃዎቹ የሰሞኑን ከፍተኛ ግጭት አስመልክተው ጠቁመዋል::

በሉግዲ አከባቢ በዚህ ሰሞን ብቻ በጎንደር እና በጎጃም በወሎ እና በሸዋ በሚል የተቧደኑ ሰዎች በሕወሓት ኢንቨስተሮች ነገር አስፋፊነት ከፍተኛ ግጭት በመከሰቱ በርካታ ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ንብረታቸውን እና ገንዘባቸውን ሳይሰበስቡ ድንገት ግጭቱን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሄዱ መሆናቸው ታውቋል::

የሕወሓት አማሳኞች እና ሰላዮች በወጣቶቹ መካከል ሰርገው በመግባት እሪስ በ እርስ ጎጥና መንደር እንዲለይ አድርገው በማቧደን እርስ በ እርስ ሕዝቡ እንዲተራረድ አድርገዋል ሲሉ ምንጮቹ በላኩት መረጃ ተናግረዋል::በዚህ ሳምንት ብቻ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሬሳዎች ወደ ሉግዲ ከተማ የተጓጓዙ ሲሆን ይህ የሕወሓት ሰላዮች/አማሳኞች የሚቀሰቅሱት የሰርጎ ገብነት ዝሴራ እስከ ማይካድራ ድረስ ተስፋፍቶ ከፍተኛ የደም መፋሰስ እና የዘር መጠፋፋት እየተደረገ መሆኑን አክለው ገልጸዋል::

መረጃ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ጠቃሚ ነው ብሎ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ የተሟላ መረጃ የሰውን ልጅ ሙሉ ያደርገዋል፡፡ መረጃን አጣሞ ማቅረብ ደግሞ የሰውን ልጅ ውሳኔ ለማጣመም ካልሆነ በስተቀር ግቡ ምን ሊሆን እንደሚችል አይገባኝም፡፡ በሰሞኑ ሰው በላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጥርሱም በጥፍሩም ዘመቻ የጀመረው እኔ ላይ ነው፡፡ ዓላማው ግልፅ ነው፡፡ በነፃነት የማሰብ መብቴን ለድርድር እንዳቀርብ ነው፡፡ ለነፃነቴ ያለኝን ዋጋ የማያውቁ ሰዎችን ይህንን ለማድረግ ቢሞክር ካላቸው የመረጃ እጥረት ወይም ማወቅ ባለመፈለጋቸው ነው፡፡ አንዳንድ ቅን ሰዎች ሰህተት እንደሰራው አድርገው ይቅርታ እንድጠይቅ፤ ይቅርም እንድባል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ በቅን ልቦና ላደረጋችሁት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ነገር ግን በሰጠሁት አስተያየት ያልተስማማ ሰው በሃሰብ ልዮነት መለያየት እያለ ይቅርታ ጠይቄ፤ ይቅርታም ተደርጎልኝ ወደ እነሱ ሃሳብ እንድገበ መፈለጉ ምን ዓይነት ከፍተኛ ችግር ያለበት አስተሳሰብ እንደሆነ የተረዱት አይመሰለኝም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም አስገራሚ የሚሆነው የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ደጋፊ፣ ለግለሰብ ነፃነት እንቆማለን የሚሉ ወገኖች መሆናቸው ነው፡፡ ለሃሳብ ነፃነት የማይቆም እንዴት አድርጎ ለመድበላ ፓርቲ ስርዓት ግንባታና የግለሰብ ነፃነት እንደሚያከብር አይገባኝም፡፡
Image
ጫጫታ ወደ ፈጠረው አጃንዳ ስገባ፡፡ አንድነት ፓርቲ የምርጫ ግብረ ሀይል ማቋቋሙን ለህዝብ በይፋ ለማሳወቅ እና በቀጣይ ሳምንት ስለሚያደርገው የህሊና እስረኞች ስለሚታሰብበት ፕሮግራም መግለጫ በሰጠንበት ወቅት በፍፁም ጠቃሚ ያልሆነ የተቃዋሚ ጎራውን በተለይ በሀገር ውስጥ ለምንገኝ ሰዎች የማይጠቅም (በኢቲቪ ቢቀርብ የማይገርም) ጥያቄ ቀረበ፡፡ ጥያቄው በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ አንድነት አባል የነበሩ ታሳሪ ስም ጠርቶ በአንድነት አቋም እኝህ ሰው የህሊና እስረኛ ናቸው ብላችሁ ታምናላችሁ ወይ? የሚል ነበር፡፡ የሰጠሁት መልስ የማንንም ታሳሪ ስም ማንሳት ሳያስፈልግ የአንድነት ፓርቲ አባል ሆኖ የሌላ ፓርቲ አባል መሆን ትክክል እንዳልሆነ፣ ከአንድነት ጋር በትግል ስትራቴጂ ከማይመሳሰሉት ጋር ብቻ ሳይሆን በትግል ከሚመሳሰሉትም ጋር ቢሆን የተሻለ ወደሚለው መጠቃለል እንጂ ሁለት ቦታ መሆን ትክክል እንዳልሆነ አስረድቻለሁ፡፡ በማስከተልም “በፀረ ሽብር” ህግ መንግሰት እየከሰሰ የሚያስራቸው ሰዎች አንዳንዶቹ በወንጀል ህግ ሊያስጠይቅ የሚችል ሰህተት አልሰሩም የሚል ድምዳሜ እንደሌለኝ አሰረግጬ ተናግሬያለሁ፡፡ ለምሳሌ በፈንጂ ስው የገደለ ሰው በወንጀለኛ ህግ መጠየቅ እና መቀጣት አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ እምቴ አሁን ፅኑ ነው፡፡ የ “ፀረ ሽብር” የሚባለውን ህግ በይፋ አሸባሪ ህግ ነው፡፡ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች አሸባሪ እየተባሉ የሚታሰሩ ያሉት የአራት ኪሎን ወንበር ስለሚያሸብሩ ነው የሚል አቋሜን ከብዙዎቹ ተችዎቼ በላይ እና ከማንም በማያንስ መልኩ ሃሳቤን በነፃነት አራምጃለሁ፡፡ ይህን ሳራምድ ማንንም ለማስደስት ሳይሆን አምኜበት ነው፡፡ አንድነት የ “ፀረ ሽብር” የሚባለው ህግ እንዲሰረዝ የተገበረውን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” ዘመቻ በቁርጠኝነት ከመሩት አንዱ ስሆን፤ በተለይ በደሴ ከተማ የተደረገውን የሚሊዮኖች ድምፅ ዘመቻ በቦታው ተገኝቼ የመራሁት እኔ ነኝ፡፡ ይህን ሁሉ የምዘበዝበው በዚህ ህግ ላይ ያለኝን ግልፅ አቋም በድጋሚ ለማረጋገጥ ነው፡፡

በእኔ በኩል የአቋም ለውጥ ሳይኖር እሳት ጭረው ቤንዝን እያርከፈከፉ ያሉት ግለሰቦችና ቡድኖች ለምን ተፈጠሩ? የሚለው ነው፡፡ በእኔ እምነት የአንድነት በምርጫው የመሳተፍ ውሳኔ በትግል ስልታቸው ላይ የሚፈጥረው ጫና ስለሚያስጨንቃቸው ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ምርጫ መሳተፍ ትክክል አይደለም ብሎ መሟገት ሲያቅታቸው የፈጠሯት ስልት ነች፡፡ አንድነት ምርጫ መሳተፍ ሲወስን በምንም መመዘኛ የመወዳደሪያው ሜዳ ምቹ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሶ አይደለም፡፡ የፖለተካ ምዕዳሩ ጠበበ ብቻ ሳይሆን ዝግ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሶዋል፡፡ ልዩነቱ ማስከፈቻ መንገዱ ምን ይሁን የሚለው ነው፡፡ በህዝብ ድምፅ የተዘጋው የፖለተኪ በር ይከፈታል ነው አንድነት ያለው፡፡ በዚህ ውሳኔ የማይስማማ ሊኖር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በዚህ ደረጃ ወርዶ ግን በጥርስና በጥፍር ለመናከስና ለመቧጨር መሞከር ግን ያስተዛዝባል፡፡

የግል ሰሜቴን ለመግለፅ እሰከ ዛሬ ድረስ ለሚቀርብልኝ ሙገሳና የማጀገኛ ቃለቶችን ተመርኩዥ ልቤ አላበጠም፡፡ አንድ ቀን ያለአግባብ ከፍ አድርገው ከሰቀሉ ቦታ ላይ አውርዶ የሚከሰክስ ማህበረሰብ አባል መሆኔን አውቃለሁ፡፡ ያለ አግባብ በእራሳቸው ስሜት ሊወስዱኝ የፈለጉት ከፍታ ላይ ስለአልሄድኩኝ አሁን ሊያወርዱኝ አይችሉም፡፡ እደግመዋለሁ ለነፃነቴ የምሰጠውን ዋጋ የማያውቁ ሰዎች ምንም ሊሞክሩ ቢችሉም ነፃነቴን ለኢህአዴግ አሳልፌ አልሰጥም ስል በተቃዋሚ ጎራ ለተሰለፈ አሳልፌ እሰጣለሁ ማለት አይደለም፡፡ ለነፃነቴ የመደብኩት ዋጋ ነብሴን ነው፡፡ ስም፣ ዝና፣ ክብር፣ ገንዘብ፣ ወዘተ እንዳይመስላችሁ!!!!! ነብሴን ነው፡፡

አቶ ይድነቃቸው የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ናቸው። አንድነት ፓርቲ ላይ ያነጣጠረ ሁለት ጽሁፎችን በቅርቡ ለቀዋል። እንደ አንድነት ደጋፊ አንድነት ላይ ትችት መቅረቡን አልቃወምም። ሆኖም ትንሽ የመረጃ ክፍተት ሳይኖርባቸው እንደማይቀር በመገመት እንደሚከተለው ምላሽ ስጥቻለሁ፡

ወንድም ይድነቃቸው፡

“እኔም ሆንክ ሌሎቻችን በሰጠነው ትችት እና አስተያየት አንድነት ፓርቲ ጉዳዩን ለማጥረት በዛሬው ዕለት “አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!” በማለት ያዋጣው መግለጨ የሚበረታታ እና የሚደነቅ ነው፡፡” ብለ በጻፉት ላይ አስተያየት እንድሰጥ ይፍቀዱልኝ።

ይመስለኛል አንድነት በጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ላይ ያልጠራ ነገር እንደነበረዉና አሁን በመገልጫው እንዳጠራው የሚገልጽ እድምታ ያለው ሐሳብ መሰለኝ ያስቀመጡት። አስተያየቶችን በነጻነት ለመጻፍና ለመናገር መብትዎትን እየተለማመዱ መሆንዎትን አደንቃለሁ፨ ማንም የተቃዋሚ ድርጅት ሆነ የተቃዋሚ መሪዎች ሁልጊዜ ቻሌንጅ ሊደረጉ ይገባል። ቻሌንጂን የሚፈሩ አምባገነን ባህርሪ ያላቸው ብቻ ናቸው ።
ሌላው “ አቶ ግርማ ሰይፉ “……ሁሉ ጊዜ ከመንግስት ጋር “እንትን” የምንለው በኢትዮጵያ ሰላም እና ፀጥታ፣ ችግር ይፈጥራሉ ብሎ የሚባል ነገር ካለ እኛም የበለጠ ያጋባንል….” ያሉትን ጠቅሰዉ “ይቺ ናት ጨዋታ” ብለዉም ጽፈዋሃል።

ይመስለኛል የሕግ ባለሞያ ሳይሆኑ አይቀሩም። የናንተ የሰማያዎችን አቋምን አላውቅም። አንድነት ግን ጠንካራ ጽረ-ሽብርተኛ አቋም ያለው ድርጀት ነው። እንደ አልካይዳ፣ አልሻባብ የመሳሰሉ ድርጅቶች ለመዋጋት የሚደረገዉን አለም አቀፍ ጥረት ይደጋፍፋል። በተለይም አል ሻባብ የአካባቢያችን ትልቅ ጠንቅና ካንሰር እንደሆነም ያምናል። እንደ አይሳስ፣ ቦኮ ሃራም ያሉትን ይቃወማል። ይህን አቋም መያዝ ከህወሃት/ኢሕአዴግ ጋር መመሳሰል አይደለም።

ስለዚህ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት በአገራችን ሰላምን ለማናጋት የሚሞክሩ ኃይላት ካሉ የአገር ሰላምና ጸጥታ አንድነትን ያገባዋል። ወንድሜ እኔ እስከሚገባኝ የአንድነት አላማና ራእይ ኢትዮጵያን ማዳን ነው። የእንግሊዘኛ አባባልን ልጠቅምና “ Andinet ( UDJ) is not against anyone ; but is FOR Ethiopia”.

ጸረ-ሽብርተኝነትን ሽብርተኛ የሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት ህጉ የተለይያዩ ነገሮች ናቸው። አንድነትን የምትተቸው ለምን ሽብርተኝነት ላይ ጠንካራ አቋም ያዘ ብለህ ከሆነ ንገረን ? ይሄን ትላለህ ብዬ አላስብም። አንተም እንደ አይሰስ ያሉ ሽብርተኞችን አጥብቀህ የምትቃወም እና የምትኮንን መሆንህን ስለማወቅ።

አንድነትን የሚተቹት የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉን ይደግፋል ብለው ከሆነ ደግሞ መረጃ ያቅርብልን። እኛም ትችትዎትን እንድነጋራ። ግን የሚያቀርቡት መረጃ አይኖርም ለምን የአንድነት ፓርቲ በስራው አቋሙን ያስመሰከረ ነውና። የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ አደራጅቶ በይፋ በአደባባይ የጸረ-ሽብርተኝነት ህግን ተቃዉሞ ሲንቀሳቀስ ለማየት የሚከተሉትን ፎቶውፖች መመለክቱ ብቻ ይበቃል፡ መቃወም፣ መተቸት መብት ነው። ግን ተቻለ መጠን አገናዝበን መረጃ ይዘን ብናደርገውው ደግሞ የበለጠ ጥሩም ይሆናል።

ከዚህ በታች ያሉት ፎቶዎች ፣ አሁን ለሕሊና እስረኞች ተቆርቋሪ ነን የሚሉቱ ጡሩምባ ከመንፋታቸው በፊት፣ አሁን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የሚቃወሙ ፊታወራሪዎች ከመነሳታቸው በፊት፣ የአንድነት ፓርቲና አንድነቶች ናቸው ለሕሊና እስረኞች አጋርነት በማሳየት፣ እስረኞች እንዲታሰሩበት ምክንያት የሆነው የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ፣ በሶሻል ሜዲያዉና ከመገልጫም ባለፈ፣ ህዝብ ጋር በመዉረድ፣ ህዝብን በማስተባበር ሲጮሑ የነበሩት። ከአንድ አመት በፊት በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ዉጭ ባሉ ከተሞች በተደረጉ ሰልፎች የነበረዉን በጥቂቱ ይመልከቱ። “የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ሕግ መንግስቱን የጣሰ ነው” ወዘተረፈ የሚሉ መፈክሮችን ያንብቡ። ሐቁ እንግዱህ ይሄ ነው።

ወንድም ይድነቃቸው በርግጥ የጸረ-ሽብተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ፣ ለዉጥ እንዲመጣ. የሕሊና እስረኞች እንዲፈቱ ፍላጎት ካሉ እድነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሶሻል ሜዲያ ያለፈ ህዝብን የማደራጀት ሥራ እርስዎና ድርጅትዎ ለመስራት ሞከሩ። የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ባባህር ዳር፣ በአዳማ፣ በመቀሌ በመሳሰሉ ጽ/ቤቶችን በአዲስ መልክ አጠናክሮ በየከልሉ ህዝቡ ወርዶ እያደራጀ ነው። በአዲስ አበባ በ23ቱም ወረዳዎች በአሥሩም ክፍለ ከተማው መዋቅሩን ዘርግቶ ወደ ህዝብ እየወረደ ነው። እናንተ እዚያ ላይ በርቱ።

አቶ ግርማ ሰይፉ በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛ የተቃዋሚዎች ተወካይ ናቸው። በፓርላማ ዉስጥ ሆነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ልብ ትረታ የሳቡ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎች በመጠየቅ፣ በተስጣቸው ጥቂት ደቂቃዎች የአገዛዙ ባለስልጣናትን ደም ግፊት በየጊዜው እንዲጨመር የሚያደርጉ አንጋፋ ሰው ናቸው። በዚህ አጋጣሚ ለተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን፣ በፓርላማ የሕዝብ ብቸኛ ድምጽ በመሆን ለሚያበረክቱት አስተዋጾ ያለኝን ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ። ለእኝህ ወዳጄ ትልቅ አክብሮት እንዳለኝ እገልጻለሁ።

የሕሊና እስረኞችን በተመለከተ ይፋ በሆንው የሚሊዮኖች ድምጽ ለሕሊና እስረኞች የበየነ መረድ ዘመቻን በተመለከተ፣ በአንድነት ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ጊዜ አቶ ግርማ ሰይፉ አንድ ጥያቄ ይጠየቃሉ። የአንድነት ፓርቲ አባል የነበሩና ከነጀነራል መላኩ ተፈራ ጋር፣ ከአምስት አመታት በፊት ስለታሰሩ፣ አቶ መላኩ ስለሚባሉ እሰረኛ የተመለከተ ነው። “አቶ መላኩ የአንድነት አባል ነበሩ። የሕሊና እስረኛ ተደርግው ነው ወይ የሚታዩት ?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። አቶ መላኩ እነ አንዱዋለም አራጌ፣ እስክንደር ነጋ፣ ናትናኤል መኮንን ከመታሰራቸው ሁለት አመታት በፊት የታሰሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ተገደው ይሁን አምነዉበት፣ በኢቲቪ ቀርበው፣ ከግንቦት ሰባት ጋር እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ስንት እስረኛ እያለ፣ የእኝህ ሰው ስም በተናጥል ተጠቅሶ ጥያቄ መቅረቡ በራሱ አጠያያቂ ነው። ሆን ተብሎ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በሚሰጡት መልስ ችግር ዉስጥ እንዲገቡ፣ ታስቦ እንደሆነ መገመት አያቅትም።

አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የታሰረ ሁሉ የሕሊና እስረኛ እንዳልሆነ ገልጸው፣ አንድ ሰው ጥፋት አጥፍቻለሁ ብሎ ካመነ (ወዶም ሆኖ ተገዶ) ፣ አላጠፋም ብለው መከራከር እንደማይችሉ ገልጸዋል። ሰላምን በማስጠበቅ አንጻር፣ አንድነት ከኢሕአዴግ የበለጠ እንጂ ያላነሰ የጸረ-ሽብርተኝነት አቋም እንዳለውም አቶ ግርማ ሰይፉ አስረድተዋል።

ሆኖም የአቶ ግርማ ሰይፉ መልስ በመለጠጥና በማጦዝ ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ዘመቻ አቶ ግርማ ሰይፉ ላይ እና ፓርቲያቸው አንድነት ላይ ተከፍቷል። የዚህ ዘመቻ አዝማች ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለው ደግሞ “የሕዝብ አይን እና ጆሮ ነኝ” የሚለው በሻእቢያ የሚደገፈው ኢሳት ነው።
አቶ ግርማ ሰይፉ አንድነት በሽብርተኝነት ላይ ከኢሕአዴግ የበለጠ እንጂ ያነሰ አቋም እንደሌለው በግልጽ አስቅምጠዋል። ጸረ-ሽብርተኝነት እና ሽብርተኛ የሆነው የጸረ-ሽብርተኘንት ሕጉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። የአንድነት ፓርቲ በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ላይ ያለው አቋም ግልጽ ነው። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎ እንቅስቃሴዎችን ባደረገ ጊዜ ዋና አጀንዳ አድርጎ አንግቦት የነበረው የጸረ-ሽብርተኝኘት ሕጉ እንዲሰረዝ በማድረጉ ላይ ነበር። በወቅቱ የአንድነት ፓርቲን ወክለው፣ ከነሽመለስ ከማል ጋር በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ዙሪያ ክርክር ያደረጉት፣ አቶ ሃብታሙ አያሌውም፣ በይፋ ሕጉ እንደማያስፈልግም መግለጻቸው ይታወሳል። በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ ግርማ ሰይፉ ራሳቸው፣ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር በጸረ- ሽብርተኝነት ሕግ ስም መንግስት ህዝቡን እያሸበረ እንደሆነም አስረድተዋል። እንደዉም “ሽብርተኞች” እየተባለ ዜጎችን የማሰሩ ጎጂ ተግባራትን “መንግስታዊ ዉንብድና” ብለው ነው ያቀረቡት። እንደዉም ያለማገናን እንደ አንድነት ፓርቲ ይሄ ዜጎችን እያሸበረ ያለውን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ የታገለ ድርጅት የለም።

ታዲያ ሁኔታው ይሄ ሆኖ እያለ፣ ቅንጣቢ በመያዝ፣ ብዙ ዋጋ በአገር ቤት እየተከፈሉ ያሉ ወገኖች ላይ፣ አሁን ኢሳት እንዳደረገው፣ አክብሮት በጎድለው መልኩ ጠጠር መወርወር የሚያስተዛዝብ ነው። በተለይም ኢሳት አላማው ምን እንደሆነ እንድንገነዘብ እያደረገን ነው። ትግላቸው ጸረ-ወያኔ ነው ቢሉንም ሌሎች ላይም ሳያነጣጥሩ እንዳልቀረም እያየን ነው።

ኢሳቶች በአቶ ግርማ ሰይፉ ላይ ያቀረቡት ከዚህ በፊትም አቶ ሃብታሙ አያሌውም ላይ አቅርበዉት ነበር። “ከአድማጮች የመጡልን ነው” በማለት አቶ ሃብታሙን ወያኔ ነው እስከማለት የተደረሰበትም ሁኔታ እንደነበረም ሁላችንም የምናስታወሰው ነው።

እንደኔ አስተያየት፣ አቶ ግርማ ሰይፉ የተናገሩት ነገር ምንም ስህተት አለው ብዬ አላስብም። ስህትት ሰሩ ቢባልም ደግሞ ብዙ ልንደነቅም አይገባም። ከፖለቲካ መሪዎቻችን ስህተቶች ሲሰሩ፣ ስህተቶችን አርመው፣ ከወደቁበት ተነስተው ጉዞ እንዲጀመሩ መደግፍና ማንሳት እንጂ ማብጠልጠል ነውር ነው። እንዲህ ስል አቶ ግርማም ሆነ ሌላ የፖለቲካ መሪ ተጠያቂ መሆን የለባቸዉም ማለቴ አይደለም። (በቅርቡ የአንድነት መሪ በነበሩት ኢንጂነር ግዛቸው ላይ እና የሰማያዊ መሪ አቶ ይላቃል ላይ ትችቶች እኔም አቅርቤ ነበር) ሆኖም ስንተችና ስንቃወም መረጃ ይዘን መሆን አለበት። ዉይይቶች ከተደረጉ፣ እዉነትን ይዞ፣ ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶ፣ በአክብሮት መሆን አለበት። ኢሳት ለነ ዶር ብርሃኑ ነጋ ሰዓታት በየጊዜው ዓድማጮች እስኪሰለቻቸው ድረስ እንደሚሰጥ፣ ለአንድነቶች ወይም ለአንድነት ድጋፍ ድርጅት መሪዎች በቂ ጊዜ ቢሰጥ፣ ምናልባት ሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ በሚገባ ሊኖረው ይችል ነበር። ኢሳቶች ግን ያንን አላደረጉም።

ሌላው የአንድነት ፓርቲ የአንድ ግለሰብ ፓርቲ እንዳልሆነም መታወቅ አለበት። አቶ ግርማ ሰይፉ አንድ የፓርቲው አንጋፋ ጠንካራ አመራር ናቸው። ሆኖም አንድነት ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ብዙ አባላትና ደጋፊዎች ያሉት ድርጅት ነው። በቅርቡ በመቀሌ፣ በአዳማ፣ በባህር ዳር፣ በአዋሳ ጽ/ቤቶቹን በአዲስ መልክ ከፍቶ ትልቅ ድርጅታዊ ሥራ እየሰራ ነው። በመጪው ምርጫ እሳተፋለሁ ብሎ በይፋ አዉጆ የምርጫ ዘመቻውን ጀምሯል። ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጋዜጣውን አላትምም በማለቱ፣ የራሱ ማተሚያ ማሽን ገዝቶ፣ በር ሲዘጋ ሌላ በር አስከፍቶ፣ መልእክቶቹን ለሕዝብ እያቀረበ ነው።

ታዲያ ኢሳቶች የአንድነት ፓርቲ እንደ ፓርቲ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ያልዘገቡ፣ አንድ የአንድነት አባል ተሳሳተ ብለው በብዙ ሺህ ዶላር የሚያወጣ የአየር ጊዜ ማጥፋት ምን ይባላል ?

ኢሳቶች አቶ ግርማ ሰይፉ ተናገሩት ካሉት በዘለለም አንድነት ለምርጫ እሳተፋለህ ማለቱን እየተቸ በይፋ እየተናገሩ ነው። ኢሳቶችም ሆነ ሌሎች አንድነት ለምርጫ እሳተፋለሁ ማለቱ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸው ላይ ችግር የለኝም። የተሻለ አማራጭ ኖሯቸው፣ በአንድነት ፓርቲ ላይ ተቃዉሞ ቢያሰሙ ለምን ሊባሉ አይገባም። ለምን ሲቃወሙ ሌላ አማራጭ በማቅረባቸው። ነገር ግን ምንም አማራጭ ሳይኖራቸው፣ እነርሱም በባዶ ዉስጥ ሆነው፣ በፈታኝ ሁኔታ ዉስጥ ደፋ ቀና የሚሉት፣ እኔ አቶ ግርማ ሰይፉና አንድነቶች ላይ ጠጠር መወርወር ትንሽ አስቸጋሪ ነው። በዚህ ረገድ ቆም ብለው እንዲያስቡ እመክራለሁ።

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እምነት ያላችሁ፣ ህዝቡ ከተደራጀና ከተባበረ ለዉጥ ያመጣል የምትሉ፣ የጥላቻና የስሜት፣ የግትርነት ፖለቲካን ሳይሆን የበሰለ፣ የስለጠነ ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ያቀፈን ፖለቲካን የምትደገፉ፣ በሁሉም አካባቢዎች ህዝቡ ለፍትህና ለነጻነት ለማንቀሳቀስ ደፋ ቀና እያለ ያለውን ፣ ከሕዝቡ ጋር ያለውን አንድነትን ተቀላቀሉ፣ ደግፉ።

የአንድነት ፓርቲ አንጻራዊ ጥንካሬ ቢኖረውም ብዙ ድክመቶች አሉት። ድክመትን፣ አክብሮት ባለበት መልኩ እየጠቆምን፣ የአመራር አባላቱም ሲሳሳቱ እየገሰጽን፣ ካልሰሙም ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ግፊት እያደረግን፣ ፓርቲው አቅሙን እንዲያጎለበት ማድረግ ነው የሚጠበቅብን። እነ ከበደ ካሳና ኢቲቪ ትንሽ ነገር ባገኙ ቁጥር በአንድነት ልስይ ይጮሃሉ። እነ ሲሳይ አጌናና ኢሳቶች ደግሞ ኢዚያ ትንሽ ነገር ይዘው ብዙ የአየር ሰዓት ፈጅተው፣ አንድነትን በማጥላላት ይፈርጃሉ።

የአንድነት አመራር አባላት ከየአቅጣጫው ቀሥት እንደተመዘዘባቸውም ተርድተው ለነዚህ ቡድኖች ብዙ ቀዳዳ ላለመስጠት እንዲጠነቀቁ አጥብቄ እየመከርኩ፣ “ሥራችሁ ላይ በርቱ” እላቸዋልለሁ: የሚያወራው ፣ የሚተቸው መተቸቱን ዕና ማወራቱን አያቆምምና ለወሬ ቦታ አትስጡ እላለሁ።

በአገር ዉስጥና ከአገር ውጭ ያለን፣ በሚሊዮኖች የምንቆጠር ለዉጥ ፈላጊ ወገኖች፣ በግላችን የድርሻችንን ለመወጣት እንሞክር። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሆን። እኔ አምነት አለኝ እያንዳንዳችን ከተነሳን ለዉጥ ማምጣት እንችላለን። አንርሳ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ እንደ ዜጋ የድርሻቸዉን በአገር ቤት እየከፈሉ ነው። እኛም የድርሻችንን ለመከፈል እንዘጋጅ።

አቶ ግርማ አገዛዙ አፍንጫ ሥር ሆነው በፓርላማ እያደረጉት ያለው ለማወቅ ይችን ያዳምጡ፡

https://www.youtube.com/watch?v=9HffknkPwYw

ናትናኤል በርሔ (ኖርዌይ)

የኢትዮጵያ መንግስት(EPRDF) በ1988፣1992፣1997 እና 2002 ዓም አገር አቀፍ የምርጫ እንቅስቃሴ አድርጎዋል።
ሁላችንም እንደምናውቀው ላለፉት 24 ዓም በሞኖፖል ያስተዳደረ መንግስት ሲሆን በዚሁ አገዛዝ ዘመን በዘር፣በጎሳ፣በሃማኖት የመከፋፈል እያስተዳድረ ሲሆን በ 2002 ዓም ላይ በተደረገው የምርጫ ዘመን በፓርላማ በነበረው 547 የምርጫ ወንበር ውስጥ 545(99.6%) በብቸኝነት ያሸነፈ መንግስት ነው። በሚመጣው ዘመን 2007 ዓም እነሱ እንደሚሉን ከሆነ የምርጫውም ውጤት 11% ያሳድጉት እና 547 መቀመጫውን ይወስዱት ይሆን ? አሁን እንኳን ስለምርጫ ለመናገር ሳይሆን በአገራችን ውስጥ እየተፈፀመ ስላለው ዜጎች ከቀያቸው (መኖሪያ ) አካባቢ ሳይፈልጉ መፈናቀል፣ መሰወር ፣ የሰራ ዋስትና ማጣት ፣ሰብዓዊ ክብራቸውን ማዋረድ፣ያለበቂ ማስረጃ ማሰር፣ እና ሌሎችንም ምክንያቶች እየተጠቀመ የሚያደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና እየተስፋፋ በመሔድ ላይ ይገኛል። አንዳንድ ግዜ መንግስት በማን አለብኝ ያሰራቸውን ሰዎች ፍርድ በቤት ለማቅረብ መረጃዎችን አይኖራቸውም ስለዚህ ያለው አማራጭ እስረኞቹ እንዲናዘዙ ማድረግ ብቻ ነው።ለምሳሌ በኢትዮጵያ ወንጀል መቅጫ ህግ አንቀፅ 27 መሰረት አንድ ተከሳሽ ወንጀሉን ሰርቻለሁ ብሎ የእምነት ቃሉን እስከሰጠ ድረስ መረጃ ባይቀርብበትም እንኳን ተጠያቂ ይሆናል።

በ1997 እስር ቤት ውስጥ በድብደባ ህይወታቸው ካለፉ ግለሰቦች መሃከል ፣

1.ገድሉ አየለ ሁሉአንተ

2.ፀጋዮ አየለ ይግዛው
3.እርጋት(አርጋት) ጎበና ማሩ

የተባሉ ግለሰብ በደረሳባቸው ከፍተኛ ድብደባና ህክምና በመነፈጋቸው ህይወታቸው አልፎዋል።እንዲሁም ውቢት ሌንጋሞ የተባለች ነፍሰጡር ሴትም ክፉኛ በመደብደቧ ጽንሷ አጨናግፈውታል።

በቅርቡ በ2006 ዓም ዘመን ብቻ

1.ተስፋሁን ጨመዳ

2.ኒሞና ጥላሁን

3.ኑረዲን ሀሰን

4.አህመድ ነጃሺ
ቁጥራቸው በውል ያልታውቁ ዜጎች ለነፃነት በሚያደርጉት ትግል ዛሬም አሁንም እየሞቱ ይገኛል።

“ጠመንጃን ተገን አድርጎ በህዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓትና አራማጆቹ፤የህዝብን ሰላማዊ ኑሮ ለማተራመስ አማራጭ አድርገው እየተጠቀሙበት ያለው ስልት “ጠንካራ ናቸው

የሚሉዋቸውን” ተቃዋሚዎች ወደ ዘብጥያ መወርወር ሆኗል”
የኢሕአግ መሰረታዊ ዓላማም ወታደራዊ ሃይሉን መከታ አድርጎ በሕዝብ ጫንቃ ላይ በጉልበት የተጫነውን የወያኔ አገዛዝ በተባበረና በሁለገብ የትግል ስልት ለሕዝብ ወሳኝነት እንዲበረከክ ማድረግና ከአንድነትና ከዴሞክራሲ አንፃር ሀገሪቱ የተደራጀ ሃይል በማጣቷ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ትግሉ ያለው መራራነት ግልፅ ቢሆንም አማራጭ ለዚህም መፍትሔው በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ገዥውን መንግስት ከስልጣን ማወረድ ነው።ህዝቦችን በዘር፥ በብሄር፥ በቋንቋ፥ በሀይማኖት፥ በቀለም፥ ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት፥፥ እርስ በእርስ እንዳይስማሙ፥ አብረው እንዳይኖሩ፥ አንድንት እንዳይፈጥሩ፥ በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ፥ የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ፥ ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ።

“ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት፥በመልካም አስተዳደር፥በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ፥፥ ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፥ ነፃ ጋዜጦች፥ የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ (ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ) ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ በተጨማሪም በከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ ከሀገር ውጨ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፉዋቸውን ጋዜጦች፥ የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ማፈንና ከነዚህም ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን ግለሰቦች ኮተት የሆነ የውሸት ክሶች በመደርደር በአሸባሪነት እየከሰሰ ህዝቡ መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም አድርጎዋል” የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ነፃነት “በእርግጥ ሀሳብን በነፃነት መግለጽ አሸባሪነት ከሆነ፤”አሸባሪዎች”ተባሉትን ጋዜጠኞች ብዕር አንስተን ጥቁር ሽብር ያፋፈመውን ወያኔ ኢህአዴግን በሽብር ማንቀጥቀጣችን በእርግጠኝነት የሚቀጥል ይሆናል” ሲሉ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበርና በስደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። Article 19 ማንኛውም ሰው ነፃ ፕሬስ በነፃነት የማንሸራሸር መብት አለው ብለው ያምናሉ።በ አፍሪካ ካሉት ጨቋኝ አፋኝ ይሉት አገራት ግን ይህን የመሰለ መብት ለመተግበርም ሆነ ለመፈፀም ፈቃደኝነት ካለመታየቱም በተጨማሪ “በሽብርተኝነት ስም” እየፈፀባቸው ያለውን ግፍና በደል አገርን ጥሎ ለመሠደድ ያበቃቸውል።

በአሁኑ ጊዜ በትንሹ ከ250 በላይ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች በስደት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ይህን ያህል ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች ከአገር በማሰደድ ኢትዮጵያ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር እንደሆነች፤ ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ) በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በ2014 እአአ አሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ እስቴት ዘገባ ከሆነ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ላይ ያላትን አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም እያስቆለቆለ እና እየባሰበት በመወረድ ላይ ይገኛል።በዘገባም ላይ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ጉዳዮችን ፌደራል ፖሊስና የፀጥታ ቡድን አባላት በተናጠል፣ በቡድን በማድረግ ግለሰቦችን ከተፈጥሮ ውጭ ህገወጥ ግርፋት፣እስራት፣መግደል ይፈፀማሉ።ያለ በቂ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስራት መዳረግ የግለሰቦችን እና የቡድን መብት መጣስ፣ጋዜጠኞች፣ብሎገሮች እንዲሁም የመጽሔት አታሚዎችን እና ባለንብረቶችን ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ መብቶችን መንፈግ።የመሰብሰብ መብት በተቃዋሚ ፖርቲዎች ላይ የስልጣን ጉልበት በሀይል በመጠቀም በፀጥታ ሀይሎች እና በፌዴራል ፖሊስ ተፅእኖ በመፍጠር በመበጥበጥ ሊገኙ ይችላሉ በሚባሉ ነገሮች ላይ አፍራሽ ሃሳቦችን በመፍጠር የመንግስት ሠላዮች አብሮ በማስገባት ብጥብጥ ሁከት መፍጠር ስራየ ብሎ ተያይዞታል።እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሁለተኛ አለም የሚኖሩ ህዝቦች ጨቋኝ መንግስት ዜጋዎቹን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር (human traffiking ) የመጀመርያ መጨረሻው ነው።

ፀረ ሽብር ህግ በመንግስት ህግ ሆኖ በወጣበት ቅርብ አመታት ጊዜያት ብዙዎችን ለእስራት፣ግድያ እንዲሁም በውል በቁጥር ለማይታወቅ ዜጋ ለስደት ዳርጎታል።እንደ ሰብዓዊ መብት ተማጋች (human Right Watch) እምነት ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ consisted to express their right to freedom of expression ይህም ማለት ህጉ ምን ያህል አፋኝ እንደሆነ ለመጥቀስ ይክል በትንሹ March 2011-December 2011 ብቻ በዚሁ ወራቶች 108 የፖለቲካ አባላት አመራር እንዲሁም 6 ጋዜጠኞችን ለእስራት የዳረገ አፋኝነቱን ያመለክታል።አንድ የአንጎላ ጋዜጠኛ እንዳለው ከሆነ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ በመግለፃቸው ምክንያት በገፍ ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ ህብረቱ ዝምታን መምረጡ እጅግ አሳፋሪ ነው ሲል ተናግሮዋል። አያይዞም አንጎላዊ ጋዜጠኛው ራፋየል ሲነገር ጋዜጠኞች በእስርና በእንግልት እየተሰቃዩ ባለበት ሁኔታ የህብረቱ አዲስ አበባ መቀመጥ አስመሳይነት ነው ብሎ አክሎዋል 53 አገሮችን የሚወክለው የአፍሪካ ህብረት ለሰብአዊ መብትና ለግልጽነት ቀርጠኛ መሆኑን ይግለፅ።አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ለሚንገላቱ ለሞያ አጋሮቻቸው መቆርቆር አለባቸው።ይህ ሁሉ በደል እየተፈፀመ ባለበት ሁኔታ ህብረቱ ምንም ማድረግ ካልቻለ የ አፍሪካዊያን ባለቤት ሁኔታ ህብረቱ ምንም ማድረግ ካልቻለ የ አፍሪካዊያን ጋዜጠኞች የህብረቱ መቀመጫ በሰብአዊ መብት አያያዝ መልካም ስም እና ዲሞክራሲ መብቶችን ወደ ሚከበርበት አገሮች መዘዋወር እንዳለበት ዘመቻ መጀመር አለባቸው ብሎዋል።

የ ፖለቲካ ነፃነት ስንል በፖለቲካ ለህብረተሰብ ይበጃሉ ይጠቅማሉ እንዲሁም ለአገሪቱ ካለችበት ብሔራዊ ጥቅም የተሻለ የተለወጠ የእድገት ለውጥ ለማምጣት የሚከናወንበት መድረክ ማለት ነው።በእኛ አገር ግን ይህን የመሰለ ፖለቲካን በነፃነት ለማራመድ ካልታደሉት አገሮች ተርታ ትመደባለች።የፖለቲካ አባል ወይም ደጋፊ መሆን ማለት የተገላቢጦሽ በገዢው መንግስት መፈረጅ ነው።ለዚህም ምሳሌ አስረጂነት የአንድነት ዲሞክራሲና ፍትህ ፣የሰማያዊ ፖርቲ፣የግንቦት 7 አመራርና ሌሎችም አባላት ላይ እየተደረገ ያለው ነገር ለዚህ ሁሉ አስረጂ ነው።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች የመብት ገፈፋ የድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ ከ357 እስር ቤቶች በላይ ይገኛል ከዚህ ውስጥ ዴዴሳ፣ጦላይ፣ታጠቅ፣ብር ሸለቆ፣ዝዋይ፣ብላቴ፣ሰንቀሌና በሌሎችም ማረምያ ቤቶች 37,000 በላይ ሰዎች የፖለቲካ እስረኞች ሆነው በየእስር ቤቶ እየተሰቃዩ ይገኛል።

የሲቪክ ማህበራት ግንኙነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ዘመን ቁርኝነት ከነበራቸው መሰል ማህበራት አንዱ ነው።እነዚህ ማህበራት የበጉ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጄንሲ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ 2009 እኤአ ከወጣው አዋጅ ማህበራትን የሚሰጡትን አገልግሎት በማፈንና ከአገልግሎት ውጭ ከማድረጉም በላይ የብዝሀን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት አሳጥቷል።ከዚህም አፋኝ አዋጅ የሲቪክ ተቋሞችን ሊገኝ የሚችሉን የአለም አቀፍ መብቶችን፣የሰብአዊ መብት፣የሴቶች መብት፣የህፃናት መብት፣በህገመንግስታዊ ስም የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት ለማስታረቅ ከመርዳታቸውም በላይ የሰውን መብት ለማስከበር ይረዳሉም ይጠቅማሉ።ያለመታደል ሆኖ የሲቪክ ተቋም የዚሁ አካል ተተቂም ለመሆን ቻለ።

ከቀያቸው በልማት ስም ማፈናቀል የተለመደ ሆን ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ነው።አንድን አካባቢ በልማት ስም ሲፈናቀሉ ዘርን(ብሔር) መከታ ያደረገ ነው። መሰረተ ልማት የሚፈለግን አካባቢ በመጀመሪያ ለህብረተሰቡ ፍላጎት መሟላት የሚገባቸው መሰረታዊ ስራዎችን መስራት ተገቢ ነው።ከክልሉ የሚነሱ የጤና፣የትምህርት ቤት፣የውሀ መጠጥ፣በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ መሆን አለበት።ማፈናቀል ማለት የህብረተሰቡን የማህበራዊ ኑሮ በማናጋት ህዝብን ወዳልተፈለገ ስደት፣ለጎዳና መዳረግ ነው።ለዚህ ሁሉ ማሳያ ይሆን በአለም አቀፍ ያለን ደረጃ እንመልከት።

-2009-2012 Global Competives index Ethiopia 118 ከ 133

-2009 Global Peace index Ethiopia 128 ከ144

-2011Corruption Perceptions index Ethiopia 120 ከ 182

-2012Human Developemet index Ethiopia 173ከ187

-2014 Global Slavery Index Ethiopia 71 ከ 167

-2014ReporterWitthoutBoarder Index Ethiopia 143 ከ 180

*ሰብአዊ መብቶቻን ለመመለስ የግድ ልማታዊ መሆን አየጠበቅብንም መብታችን ይመለስ።

*ሰብአዊ መብቶችን በመጣስ በማንኛውም መልኩ የስልጣን ጥምን ማራዘም አይቻልም።

ቸር እንሰንብት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
አስተያየትለመስጠት:- [email protected]

የአማራ ንቅናቄ ሻእቢያ አመራሮቼን አግቶ ሰውሮብኛል ሲል በድጋሚ ከሰሰ(ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ)
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎AmaraForce‬ ‪#‎Ginbot7‬ ‪#‎EPPF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
ኤርትራ ውስጥ ተቀምጦ በትጥቅ ትግል ነጻነት ይገኛል ብሎ ስለማያስብ ወሳኝ ሃይሉን ከኤርትራ ያስወጣው አማራ ንቅናቄከማንም አስመራ ከመሸገ ድርጅት ጋር ውህደትም ሆነ ትብብር አለመፍጠሩን እና ከሻእቢያ ቁጥር ውጪ ካልወጣን በስተቀር ውህደትም ይሁን አስመራ ተቀምጦ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት አይታሰብም ሲል ተደምጧል::
የኤርትራ መንግስት በህገወጥ ሁኔታ ያገታቸውን እና የስወራቸውን ታጋዮቻችንን በአስቸኳይ እንዲለቅ ሲል የአማራ ንቅናቄ ጠየቀ:: የአማራ ንቅናቄ የሚከተሉት በሻእቢያ አመራሮቹ ታፍነው ተወስደዋል ሲል በድጋሚ አስታወቀ::በዚህም መሰረት:
1ኛ – ታጋይ ዳዊት ተሰማ የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ
2ኛ – ታጋይ መላኩ ውብነህ (ሳሚ) የድርጅቱ የትምህርት እና ስልጠና ሃላፊ
3ኛ – ታጋይ ጌትነት አድማሱ (ጃናሞራ) የሻምበል አዛዥ
4ኛ – ታጋይ አስማማው ሙሃባው የሎጀስቲክ እና አቅርቦት ሃላፊ
5ኛ – ታጋይ መሳይ ጥላሁን (ዳሞት) የሻምበል አዛዥ
Image

Image

ከአስገደ ገ/ስላሴ
Image
የህወሓት መሪዎች ከ40 ዓመት በፊት ጀምረው ለህወሓት መሪዎች የሚቃወም ወይም ደግሞ ከነሱ የበለጠ ሃሳብ የሚያመነጭ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ በውስጣቸው ሳይቀር ካለ ለሚፈልጉትን ዓላማቸው ያሰጋናል የሚሉትን ሁሉ በጠላትነት ደረጃ በማስቀመጥ ያላቸው ልዩነት በክብ ጠረቤዛ በውይይት በመፍታት ፈንታ በኢትዮዽያ የነበሩ የደርግ ተቃዋሚዎች ኋላም ለህወሓት መሪዎች ለተቃዋሚ ኃይሎች ጦርነት በማወጅ ከሁሉም ጋር በጦርነት ፈቱት::

በጦርነት ከጠፉ ፓርቲዎች ለመጥቀስ ለትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት TELF ጋድሎ ሓርነት ትግራይ ጠረናፊት ኮሚቴ የኢትዮዽያ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት (ኢዲህ) ለኢህአፓ ለዓፋር ነፃ አውጪ ግንባር (ጉጉመ) ለኦነግ ለአብነግ በደቡብ ለነበሩ ፓርቲዎች ለቅንጂትና ለሌሎች አጠፉ::

ይህ የማጽዳት ስትራተጂ በመቀጠል ለህወሓት ኢህአደግ የሙጡኝ ብሎ በስልጣን ለዘልዓለም ለመኖር እንቅፋት ሊፈጥሩልኝ ናቸው ብሎ የሚገምታቸው የመድረክ አባል ፓርቲ የነበሩ እነ አንዳለም አራጌና ሌሎችም በቅርብ ደግሞ የአንድነት የሰማያዊ ፓርቲ የሚኢአድ የኦሮሞ ፓርቲዎች የዓረና ፓርቲ አሸባሪ ናቸው በማለት ለ2007 ዓ/ም ሃገራዊ ምርጫ ሾልከው ገብተው በፓርላማ መድረክ ሊገቡ ይችላሉ ብሎ የሚገምታቸው ጦርነት ባያውጅም ከጦርነት የባሰ ሽብርተኝነትን በመፍጠር በመላው የሃገራችን ክልሎች የሚገኙ የሰላም ታጋይ ወጣት ሙሁራኖች ጋዜጠኞች የማሕበራዊ ድህረ ገፆች ፀሐፊዎች በቃሊቲና በቅሊንቶ ወህኒ ቤቶችና በማእከላዊ የደህንነት ምርመራ አጉሮዋቸው እያሰቃያቸው ይገኛሉ:: ይህ ተግባር ከ 4 ወር በፊት በአንድነት በሰማያዊ በዓረና ፓርቲዎች ወጣት የሙሁራን አመራር ታስረዋል ተገርፈዋል ተመሳሳይ እርምጃ ወጣት ሙሁራኖች ቅስማቸው እንዲሰበር ለማድረግ ነው:: እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚያሳየው የህወሓት መሪዎች ለ40 ዓመታት ይዘውት የመጡ የሥራ ልምድ ስልጣንህ እድሜ እንዲኖረው እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚባለው አስቀድመህ ማፅዳት ከሚል ፀረዲሞክራሲ ስትራተጂ የመነጨ ፖሊሲ ነው:: እንደዚህ ዓይነት አሰራር የህወሓት መሪዎች መለያ ባህረያቸው ነው::

ኢህአደግ በዚሁ በ40 ዓሙቱ ይከተለው ያለው አሰራርም ለመጪው የ2007 ዓ/ም ምርጫ ተወዳዳሪ ሆኖው ለማሸነፍ ወይም ደግሞ ብዙ ተቃዋሚ አባላት ወደ ፓርላማ ሊገቡ ይችላሉ ብሎ ታሳቢ በማድረግ የህዝብ ነባራዊ ሁኔታ ስልአሰጋው ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው የሚሉዋቸው የነ አንድነት ሰማያዊ ፓርቲ መኢአድ መድረክ የወጣት አመራርና ጠንካራ አባላት ያሉዋቸው ናቸው::

ስለዚህ እነዚህ ፓርቲዎች ጠንካረዎች በመሆናቸው አስቀድመን ማፅዳት አለብን አሉ:: ለዚሁ እርምጃ መውሰድ ሽፋን ይሆናቸው ዘንድ ወንጀል እየለጠፉ ደረቅ ወንጀል ፈፅመዋል፣ ሕገ መንግስት ጥሰዋል፣ አሸባሪዎች ናቸው በማለት የኢትዮዽያ ወህኒ ቤቶች በወጣት ፖለቲከኞች ተመልተዋል::

የህወሓት መሪዎችና አጋሮቻቸው በሰላም ታጋዮች ላይ እየወሰዱ ያሉ እርምጃ የህዝብ ፍላጎት በፋሺስታዊ እርምጃ በመግደል በማሰር በመግረፍ እንደማይቀለበስ ደርግ የሃገራችን ሃብትና የሰው ኃይል ወደ ጦርነትና ጭፍጨፋ አሰማርቶ የአፍሪካ ጎብለል እየተባለለት በህዝቦች የተባበረ ክንድ እንደተንኮታኮተ የቅርብ ጊዜ ትዝታ እያላቸው ተመሳሳይ የደርግን ፋሺስታዊ ተግባር ተከትለው ሁለተኛ ስህተት መፈፀማቸው አሳዛኝ ክስተት ነው::

እነዚህ ሰዎች 40 ዓመት ሙሉ በዲሞክራሲ ኃይሎች ያደረሱትን ፀረዲሞክራሲ የማፅዳት ዘመቻ ቢታቀቡ ለራሳቸውና ለህዝባችን ይበጃል::

Image
አንድነት የፀረ ሽብር አዋጁ ተቀብሎትም አያውቅም፤ አይቀበለውም!
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት በፀረ ሽብሩ አዋጅ ላይ የተለየ አቋም እንደያዘ ተደርጎ እየቀረበ ያለው አሉታዊ ቅስቀሳ መሰረት የሌለው መሆኑን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፀረ ሽብሩ አዋጅ እንዲሰረዝ በተለያዩ
የሀገሪቱ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ከማድረግ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ
እንዳደረገ የሚታወቅ ነው፤ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት እንቅስቃሴም አንዱ አካል
የፀረ ሽብር አዋጁ ይሰረዝ የሚል ነው።

ለዚህም አባላቱንና በርካታ የተለያዩየህብረተስብ ክፍሎች ፊርማ አሰባስቧል። አንድነት ከመጀመሪያው ጀምሮ “ፀረሽብር አዋጁ እራሱ አሸባሪ ህግ ነው” ብሎ አቋም ተንቀሳቅሷል፤
በዚህም ሂደት በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትና አመራሮች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
አሁንም ቢሆን ፓርቲያችን አንድነት በሀገራችን አምባገነናዊ ስርዓት እስኪወገድ
ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፍል ዝግጁ የሆኑ አባለት ያሰለፈ ፓርቲ
ነው፡፡

በመሆኑም፤ ይህ አዋጅ በገዥው ቡድን እየተጠቀሰ ወደ ወህኒ ቤት እየተወረወሩ
ያሉት ዜጐች የህሊና እስረኞች ናቸው ብለን እናምናለን። በዚህ ምክንያትም ነው
እነርሱን የሚያስታውስ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች” የሚል የአንድ
ሳምንት ዘመቻ አውጀን እየተንቀሳቅስን ነው ያለነው።

በአንዳንድ ወገኖች አንድነት በፀረ ሽብሩ አዋጅ ላይ የተለየ አቋም እንደያዘ ተደርጎ
እየቀረበ ያለው አሉታዊ ቅስቀሳ መሰረት የሌለው መሆኑና ፓርቲ በፀረ-ሽብር
አዋጁ ላይ ያለው አቋም አሁንም ያልቀየረ መሆኑን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን።
አንድነት አሁንም ቢሆን በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ
መፈታት እንዳለባቸው ያምናል፤ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱና ዴሞክራሲያዊ የሆነ
የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አንድነት ፓርቲ
ህዳር 13 ቀን 2007 ዓ.ም.

ተቃዋሚዎች – ግብታዊነት እና የሆያሆዬ ፖለቲካ መቆም ያለበት ጉዳይ ‪#‎Ethiopia‬
ከመጠላለፍ ከወሬና ሃሜት ከሴራና ደባ ይልቅ እስትራቴጂ ያለው የፖለቲካ መስመር መከትል ወሳኝ ነው::
‪#‎UDJ‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎AEUP‬ ‪#‎Medrek‬ ‪#‎Freedomforfairelection‬ ‪#‎Election2007‬
ሃገሪቷ ህገ መንግስት አላት ቢደሰኮርም በስርኣት አልበኞች እየተጣሰ ህግ በህግ እየተሻረ እና ባለስልጣናት እየሸረሸሩት አማራጭ የፖለቲካ አመለካከቶች እና አስተሳሰቦች እንዳይንሸራሸሩ እና እንዳይወዳደሩ በማድረግ በህግ የተረጋገጠውን የብዙሃን የፓርቲ ስርኣት እንዳይሰፍን እንቅፋት ቢሆኑም ይህ ደሞ ከስርአቱ አምባገነንነት ጎን ለጎን የተቃዋሚዎች ድክመት ታይቶ የሚወሰድ እርምጃ ነው:: ደህንነቱ ሰራዊቱና ሚዲያው ምርጫ ቦርዱ ህዝባዊ ባልሆኑበት የአንድ ፓርቲ ወገንተኛ እና አገልጋይ በሆኑባት ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ አለ የሚል እምነት በፍጹም የለኝም:: ስለወያኔ ምርጫ እና በምርጫው ስለመሳተፍ የፓርቲዎቹ መብት ቢሆንም ሕዝቡ እምቢኝ ብሎ አደባባይ እንዲወጣ ለማድረግ በጋራ እንዲሰሩ ይህንን ለመናገር እወዳለሁ:: Minilik Salsawi

ብቁ እና ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ አለመገኘቱ -የአገር ጉዳይ የአንድ ሰሞን ሆሆይታ እና ትኩሳት ተከትሎ ማውራቱ በፖለቲካ ሴራ እና ጠልፎ መጣል አባዝ የተሞሉ -ፖለቲካ የትርፍ ሰአት ስራ- መሆኑ ያልበሰሉ ስሜታዊ እና የፖለቲካ ስልታዊ እውቀት ያሌላቸው በፓርቲዎች ዙሪያ መሰባሰባቸው – በሚገባ የተደራጀ፣ አቅሙን እያጎለበተና ለሕዝቡ የተሻለ አማራጭ የሚያቀርብ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አለመኖር የፓርቲዎቹ አባላት እና ካድሬዎች አንድ ስትራቴጂ ሳይኖራቸው በነፈሰበት እየነፈሱ በጥቂት ድላሮች እየተሽከረከሩ አቧራ ከማጨስ ውጪ አንድ ባልፈየዱበት ሕዝባዊ እምቢተኝነትን ለመፍጠር በሚደረገው ሩጫ ውስጥ ሆን ተብሎ በሚፈጠረው መንቀራፈፍ የወያኔን እድሜ ማስረዘማቸው በጎሳ ፖለቲካ የሚናጠው የዲያስፖራው ዶላሮች የሚፈጥሩት ግብታዊ ተጽእኖዎች በኢትዮጵያ የሚፈለገውን ለውጥ አለማምጣቱ የታወቀ ጉዳይ ነው::ሰበብ የማያጡት ተቃዋሚዎች ይህንን ማድረግ ያልቻልነው ወያኔ እንዳንጠናከር እያዳከመን እያንገላታን እያሰረን ነው ቢሉም ይህንን አሰራር የወያኔው ጁንታ እንዲቀይር መስዋትነት ለመክፈል ምንም ያደረጉት ነገር የለም::

በእርግጥ የወያኔው ጁንታ በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረግ ድርጅቶቹ እንዲቀጭጩ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሚናውን እየተጫወተ ነው:: ሆኖም ግን ተቃዋሚዎች ከታጋይነት ይልቅ ባለፈ ታሪክ የመኮፈስ- እርስ በእርስ የመወቃቀስ- ያለፉትን ስርኣቶች የመናፈቅ-ህዝብን በታሪክ ስም ለመደለል መሞከር-ከመስዋትነት ይልቅ ለጥቅም መገዛት-መረጃ መሸጥ -ለስልጣን መጓጓት የመሳሰሉት ድክመቶች ያሉባቸው ሲሆን ስሜታዊ እና ያልበሰሉን ሰብስቦ ቲፎዞ በማድረግ መንጠራራትም ያልቀረፉት ችግራቸው ነው::የወያኔ ተጽእኖ እና ጫና እዳለ ድርሻው ሳይካድ መጀመሪያ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል::በውስጣቸው የሚታየውን ችግር ቢያድበሰብሱትም በአደባባይ እያየነው ያለ ጉዳይ ነው፡፡

አንድ ፓርቲ ከተለመደው ስልት ወጥቶ በአዲስ ስትራቴጂ ራሱን ሲገነባ ከፓርቲው ውጪ ያሉ ስለ ፓርቲው ምንም አይነት እውቀቱ እና ግንዛቤው የሌላቸው አባል ያልሆኑ የጠልፎ መጣል ኋላቀር ፖለቲካ ተጠቅመው ፖለቲካው አዲስ ባህል እንዳይኖረው ለመጠላለፍ እና ለማልፈስፈስ ትራካቸው ላይ ከመሮጥ አልፈው ከሴራ ፖለቲካ፣ ከሀሜት፣ ከወሬ አውጥተን መሬት በረገጠ፤ በእስትራቴጂ የሚመራ እውነተኛና ዘላቂ ፖለቲካዊ ምህዳር እንፈጥራለን ያሉት ፓርቲዎች ለማክሸፍ እየተራውጡ ነው። የአንድ ወቅት ሆያሆዬ በየጊዜው በህዝቡ ላይ የፈጠረው አጉል ተስፋ ህዝቡ የፈጠረው ተስፋ መቁረጥ በዓይናችን እያየን ነው፤ ይህ ሁሉ የመጣው ፖለቲካው በስልትና በእስትራቴጂ ሳይሆን በግብታዊነት የሚመሩ ፖለቲከኞች በመብዛታቸው ነው።

ተቃዋሚዎች ራሳቸው ቆራጦች፣ ጠንካሮች፣ ቅኖችና ለመስዋዕትነት ዝግጁዎች ቢሆኑ ኖሮ ከዚህ በላይ የተጠናከሩ ይሆኑ ነበር፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከባድ እና ሊቃለል እንኳን ያልቻለ የመንግስት ጫና ….ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውስጣቸው በተሰገሰጉ የወያኔ ሰላዮች የታጠሩ ናቸው::ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአንድነት ችግር ….ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአደረጃጀት ችግር …ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአመለካከት ችግር …ተቃዋሚ ፓርቲዎች የውስጥ የዲሞክራሲ ችግር…..ተቃዋሚ ፓርቲዎች የደጋፊና የአባል ብዛት ችግር ….ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፋይናንስ አቅም ችግር … ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖለቲካ መስመር፣ የስትራቴጂና የታክቲክ ችግር አለባቸው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ችግሮችን የሚፈቱበት መንገድ ራሱ ችግር አለበት፡፡

ተቃዋሚዎች ከዚህ በላይ ለተተቀሱት ነገሮች አትኩሮት መስተት እና ማስተካከል አለባቸው ስሜታዊነት እና የሆያሆዬ ፖለቲካ መቆም ያለበት ጉዳይ ነው::በውስጣቸው ያለውን አንድነት ማጠናከር እና የስርኣቱን ተላላኪዎች ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል:: የአደረጃጀት መዋቅራቸውን ማስተካከል በበሰሉ እና ወደፊትን ግብ በሚያደርጉ ጠንካራ እና ብቁ ፖለቲከኞች መታጠር አለባቸው:: አመለካከታቸውን ካረጀ እና ከታሪክ ምርኩዝነት አውጥተው በሰለጠነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ራሳቸውን ማስተሳሰር እና አማራጭ ሃሳቦችን በማሸራሸር ጠንካራ ብሄራዊነት መፍጠርና ለላሸቀው የዲያስፖራው ፖለቲካ ፊት አለመስጠት ስለ ፖለቲካ እውቀት ያሌላቸው ሰዎች በደመነፍስ ፖለቲከኛ እየሆኑ መምጣት የፖለቲካ ስትራቴጂ እና ታክቲክ እንዳይኖር አድርጓል:: ስለዚህ እነዚህ ጉዳዮች በጥራት እና በአጽንኦት አትኩሮት ከተሰጠባቸው ትግሉ ሊያብብ ይችላል:: ከዚህ ውጪ አሁን ባሉበት ሁኔታ ተቃዋሚዎች ከቀጠሉ የወያኔን እድሜ ከማስረም ዉጪ ምንም ፋይዳ የለውም::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image

የበይነ መረብ ዘመቻው ኢህአዴግን አሳስቦታል::
‪#Ethiopia‬ ‪#UDJ‬ ‪#EPRDF‬ ‪#MillionsVoicesforPrisonersofconscience‬

ምንጮች በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል በዛሬው እለት ማስጠንቀቂያዊ ትዕዛዝ መተላለፉን ገልፀዋል፡፡
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

አንድነት ፓርቲ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያካሂድ ይፋ ያደረገው የበይነ መረብ ዘመቻ ግቡን እንዳይመታ በቅርቡ አሰልጥኖ ባሰማራቸው የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ብሄርን፤እምነትን እና የአንዱ ፓርቲ ደጋፊና የሌላው ፓርቲ ነቃፊ በመሆን አጀንዳዎን በማንሳት የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎችን ትኩረት ለመሳብና የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ወደ ጋራ አጀንዳ እንዳይሰባሰቡ ሳምንቱን ሙሉ በንቃትና በጥንቃቄ መስራት እንዳለባቸው በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል በዛሬው እለት ማስጠንቀቂያዊ ትዕዛዝ መተላለፉን ማስጠንቀቂያው የደረሳቸው ተሳታፊ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል ፡፡

እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፃ ምን አልባትም ዘመቻው ትኩረት እየሳበ የሚሄድ ከሆነ በቴሌ አማካኝነት የኔት ወርክ መስተጓጎል እና ማቋረጥ ለመፍጠርም መታሰቡን አያይዘው ገልፀዋል፡፡አንድነት ፓርቲ የበይነ መረብ ዘመቻ በቀጣይ ሳምንት እንደሚያደርግ በትላንትናው እለት ለመገናኛ ብዙሀን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
Image

አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት የአካባቢውን መሬት ለኢንቨስተሮች መስጠቱን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ ነው።ኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል::
Image

ከታሰሩት መካከል አርሶ አደር ኪጣጣ ረጋሳ፣ ተማሪ ቶሎሳ ተሾመ፣ ድሬ ማሾ፣ ታሪኩ ቡልሾ፣ ያለው ባንቲ፣ ቢንያሳ ኢባ፣ ተስፋይ ቢይነሳ እና ነጋዴ መግስቱ ሞሲሳ ይገኙበታል።
እንዲሁም ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የጅምላ እስራቶች እየተከናወነ ነው። ብዙዎቹ በህጋዊ መንገድ የሚታገለው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላት በመሆናቸው ብቻ መታሰራቸውን የሚገልጸው ሊጉ፣ በጅማ የድርጅቱ አመራሮች የሆኑት አቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድ፣ አቶ ሙሃመድ አሚን ካልፋና አቶ ነቢብ ጀማል ታስረው 2 አመት ከስድስት ወር እንደተፈረደባቸው ጠቅሷል።

ተፈጸመ ስለተባለው እስራት ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ተጠሪ አቶ በቀለ ነገአ ሰዎቹ በሃሰት እንደተፈረደባቸው አረጋግጠዋል። መሳሪያ የሌላቸውን ህገወጥ መሳሪያ ደብቃችሁዋል በሚል በሃሰት ተመስክሮባቸው መታሰራቸውን አቶ በቀለ አስረድተዋል

ከታሳሪዎች መካከል የአቶ አጀብ ሼክ ሙሃመድባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ለኢሳት እንደገለጹት ደግሞ ባለቤታቸው በሀሰት ተመስክሮባቸው ከታሰሩ ጀምሮ እርሳቸውም በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ከቤት ለመውጣት መቸገራቸውን ገልዋል። ወደ ጎረቤት ሄደው እሳት እንዳይጭሩ ከመከልከላቸውም ሌላ፣ ቤታቸው በደንጋይ የደበደባል። የባለቤታቸው ወንድም ተመሳሳይ ችግር ስላጋጠመው ስራውን ትቶ ወደ ከተማ መምጣቱንም ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን እስር ቤቶች በኦሮሞ ተወላጆች መሞላቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ አለም የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።
Minilik Salsawi Via ESAT

በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቄራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና አካባቢ አንዲት የአሥረኛ ክፍል ተማሪ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ከተወሰደች በኋላ በደረሰባት አስገድዶ መደፈር ጉዳት ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሟቿ ተማሪ ሃና ላላንጎ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. አየር ጤና በተለምዶ ሳሚ ካፌ በሚባለው አካባቢ በአንድ ሚኒባስ ውስጥ ተሳፍራ ወደ ጦር ኃይሎች እየመጣች እንደነበር ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤተሰቦቿ በመጓዝ ላይ የነበረችው ሟች ተማሪ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘች በኋላ መድረሷን ተናግራ ‹‹ወራጅ አለ›› ስትል፣ በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አራት ወንዶችና ሾፌሩ ስለት በማውጣት አስፈራርተው እንዳገቷትም ተጠቁሟል፡፡

ሟች እንዳትናገር በማድረግ በሰዋራ ቦታ በታክሲው ውስጥ እንድታመሽ ከተደረገች በኋላ፣ ከተጠርጣሪዎቹ አንደኛው ቤት ወስደው ለአምስት እየተፈራረቁ እንደደፈሯት ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ በራሱ ቤት ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲደፍራት እንደከረመም ምንጮቹ አክለዋል፡፡

ሁለተኛ ተጠርጣሪ ነው የተባለው ግለሰብ ለአምስት ቀናት በተደጋጋሚ ሲደፍራት ከከረመ በኋላ፣ ከቤት አውጥቶ ጭር ባለ ቦታ ጥሏት መገኘቷንም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

ሟች ከፍተኛ የሆነ የማሕፀንና የፊንጢጣ ጉዳት አጋጥሟት ስለነበር በተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና ያደረገች ቢሆንም፣ በደረሰባት ከባድ ጉዳት በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በመታከም ላይ እያለች ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ሟች በመሀል በአንደኛው ተጠርጣሪ ስልክ ወደ ቅርብ ጓደኛዋ በመደወል ስልኩን በመዝጋቷ ጓደኛዋ የደወለችበትን ስልክ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች፡፡

የሟች ቤተሰቦች የሞባይሉን ቁጥር ለፖሊስ አሳልፈው በመስጠታቸው ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ የክትትል ሥራ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርበው በወንጀል መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 35 መሠረት የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውንም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

Reporter
Image

የሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፡፡
Minilik Salsawi

በሀገራችን “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የተባለው ተረት ዕድሜው እጅግ ረጅም ነው፡፡ የሥርዓቶቻችንን ያህል አርጅቷል፡፡ በተግባር ሲተረጐም ግን ገና ዛሬ የተወለደ ነው የሚመስለው፡፡ በየቢሮው፣ በየማህበሩ፣ በየፓርቲው የምናየው ሀቅ ነው፡፡ “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ”፣ “እከክልኝ ልከክልህም” አብሮ ሲተረት የኖረ ነው፡፡ ማናቸውም ዕቅድና ስትራቴጂ ህዝብ ኑሮ ላይ ያነጣጠረ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ማለት የእርስ በርስ ሙግትና የአዕምሮ አክሮባት ከመሥራት ይልቅ፤ የህዝቡስ ሁኔታ እንዴት ነው? ማለት ዋና ጉዳይ ነው፣ ማለት ነው፡፡

ሕዝቡ የኑሮ ውድነት ከበደኝ! የእቃ ዋጋ ንረት አስመረረኝ! ግፍ በዛብኝ! ሸምቶ መቃመስ አቃኝ የሚል ምሬት ሲያሰማ.. ሹመኞች አፍ ለማስያዝንና ለማሸማቀቅ ይሽቀዳደማሉ፡፡ የህዝብን የኑሮ ደረጃ ዝቅ ብሎ ወርዶ የሚያይ መሪ፣ አለቃ፣ ኃላፊ ማግኘት መታደል ነው፡፡ ያስቀናል፡፡ የዋጋ መናርና የታክስ ማሻቀብ አንድን ማህበረሰብ የጦርነትን ያህል ያጠፋዋል፡፡ ለዚህ ነው መሪዎች ሁሉ የህዝባቸውን ኑሮ በቅርብ ያስተውሉ የሚባለው፡፡ ህዝብ የሀገር ሙቀት መለኪያ ነው፡፡ ህዝብ የሚከፍለው ግብር ከሚያገኘው አገልግሎት ጋር ካልተመጣጠነ የቀዘቀዘች አገር ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነት እና በገሃድ የሚታየው ህዝብ ደሞዙ ከሚኖረው ኑሮ ጋር ስለማይመጣጠን ኖረ አይባልም፡፡ ህዝብ ከዕለት ዕለት ህይወት እየከበደው በመሄዱ ከሳቁ ምሬቱ፣ ከደስታው ሐዘኑ እየበረታ ሥርዓቱን፣ አገዛዙን፣ ገዢዎቹን፣ አስተዳዳሪዎቹን እጅግ ጠልቷቸዋል፡፡ ሀገሩም የእሱ አትመስለውም፡፡ ህዝብ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ለማግኘት ነግ-ሠርክ መሰለፉ ፤ አልፎ ተርፎም ከናካቴው ዕጥረት የሚከሰትበት ሁኔታ፣ ብሶቱ ወሰን የለውም በብሶት ተሞልቷል፡፡ ህዝብ በመኖሪያ ቤት ችግር እየተሰቃየ ሲሆን መሰረታዊ የኑሮ አስፈላጊ ነገር ጎሎበታል ፡፡

ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ ይህንን የሚገልፅበት መንገድ እንዳያገኝና በፍርሃት ተሸማቆ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ “አዲስ ያይጥ – ወጥመድ በሰራህ ቁጥር” አዲስ አይጥ የምትወለድ ከሆነ፣ ወይ ወጥመዷ ላይ ወይ አጥማጁ ላይ ችግር አለ ማለት ነው” ይባላል፡፡ በሙስና የተሞላ ልማት ዘርዛራ ወንፊት ነው፡፡ ዕብቁንም፤ እንክርዳዱንም፤ እያሳለፈ፤ እያዩ እህል አለን እንደሚሉት አይነት የዋህነት ይሆናል፡፡ የዚህ ሁሉ መጨረሻው ድህነት ነው፡፡ ድህነት ሲመጣ ቃላት ይበዛል። ስብሰባ፣ ንግግር፣ የማይተገበር ቃል – መግባት እንደህይወት ይወሰዳል፡፡ እንደኑሮ ይለመዳል፡፡ይህ በወያኔዎች በተግባር እያየነው ያለው ሃቅ ነው::

ሃገራችን እና ወገናችን በጨለማ ውስጥ እየዳከረ ባለበት በዚህ የወያኔ አገዛዝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በመረባረብ የዜግነት ግዴታውን አውቆ ለህዝቦች መብት እና ነጻነት መታገል አለበን። ሃገሪቷ በዚህ አደጋ ውስጥ ባለችበት ሰአት ላይ ህዝብ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ለኑሮ ውድነት ለሞት ለስደት እየተዳረገ ኢትዮጵያዊነት እየተዋረደ ከመሆኑም ባሻገር ሃገሪቷን ወደ ፍርስራሽነት ለመቀየር የሚሮጡ ጥቂት ሆዳሞች ባሉበት ልንቀብራቸው ይገባል።