የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት እና የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች መገናኘታቸው ተሰማ።

#Ethiopia #SouthSudan #OELF #ExEthiopianArmyOfficers #MinilikSalsawi

ሰው በላው መንግስቱ ሃይለማርያም መሞት ሆነ መኖር ማንችንንም ሊያስጨንቀን ሊያሳስበን አይገባም።
Minilik Salsawi

በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔን አምባገነን መንግስት ለማስወገድ በትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡ ተቃዋሚ ሃይሎች ከደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ጋር መገናኘታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።ከባለስልጣናቱ ጋር የተገናኙት በኤርትራ ውስጥ እንቅስቃሴ የማያደርጉ ድርጅቶች እና በአስመራ ቢሮ የሌላቸው የፖለቲካ ሰዎች እንደሆኑ ታውቋል።

በመጪው ጊዜያት ሊደረጉ ስለሚችሉ እና ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ሃይሎች ከጁባ መንግስት ተጽእኖ ስር ያልወደቀ የራሳቸው መንደርደሪያ መሬት እና ወታደራዊ ቤዝ የሚያገኙበትን ጉዳይ በተመለከተ መወያየታቸው ታውቋል። እንዲሁም አስፈላጊ የሆነ ወታደራዊ እርዳት የሚደረግበትን ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው ሲታወቅ በቀድሞ የደርግ መንግስት ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ዜግነታቸው ሃገራቸውን ለመካስ በወታደራዊ አማካሪነት ላይ የሚሰሩበትን አስመልክቶ የጁባው መንግስት ስምምነቱን ገልጿል።ምንጮቹ ከዚህ በላይ ዝርዝር ሁኔታ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።

መንግስቱ ሃይለማርያም የኢትዮጵያን ተቃዋሚ የትጥቅ ትግል የሚፈልጉትን አካላቶች ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ያገናኛል የሚል ፍራቻ የተከሰተ ይመስል ይህን ሰሞን ከባለፈው አመታት በተወራረሰ መልኩ በቀጥታ ግልባጭ መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ አድርገው የሻእቢያ አቧራ አጫሽ ድህረገጾች ወሬውን እያቦነኑ ይገኛሉ። በባለፈው ጊዜ እኔ ራሴው መንግስቱ ሃይለማርያም እንደሞተ ተነፋፍሼ ነበር ከዛሬዎቹ አለን ባይ ምንጮቼ ያገኘሁትን ይዤ ።

የሆኖ ሆኖ በየእስር ቤቱ ስለታሰሩብን የፖለቲካ መሪዎቻችን ጋዜጠኞቻችን እና የሃይማኖት ምሁራን መጨነቅ እና ስለመጪው ትግል ሰፋ ያለ ስራ መስራት ይገባናል ። ሻእቢያ ይህን ሰሞን በኤርትራ የተነሳበትን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በሌላው ዘንድ አትኩሮት እንዳያገኝ ከሚሰራው ስራ ጎን ለጎን የመንግስቱ ሃይለማርያምን መሞት ሊያረዳን ይፈልጋል። ወይ ሻእቢያ እና ወያኔ ለማደናበር ማን ብሏቸው።