Category: Amharic News
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሰኔ 16/2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ ድል ተቀዳጀ !
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሰኔ 16/2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ ድል ተቀዳጀ!
አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የይስሙላውን ምርጫ በመጪው ዓመት እንደተለመደው ግልጽና ፍትሃዊ ባልሆነ መልኩ ለማከናወን ሲል ገና ከአሁኑ ለለውጥ የተነሳሱ ዜጎችን በማሰርና በማሳደድ ብሎም ደብዛቸውን እያጠፋ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊትየወገን ደራሽ ጥቃቱን በጎጠኛው ቡድን ታጣቂዎች ላይ መውሰዱን ቀጥሏል።
በሰኔ 16/2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ በስርዓቱ የሚሊሻ ታጣቂ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ አስራ ስምንት(18) ገድሎ ሁለት(2) ማርኳል የምርኮኞቹ ስም1ኛ- ቻለው ሲሳይ 2ኛ- ተጫነ ንጉሱ ሲሆኑ ሠራዊቱ ለሁለቱም ምርኮኞች ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታና ስለ ድርጅቱ አላማና ግብ በማስተማር ለቋቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰኔ 18/2006 ዓ/ም ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝበ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ከወያኔው የልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር በወልቃይት አወርቂ በተባለ ቦታ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ለአራት ሰዓት ያህል ባካሄደው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሰላሳ ስድስት(36) ገድሎ አርባ ስምንት(48) በማቁሰልና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸውና ትጥቃቸው ጋር ማርኳል።
ውጊያው በተካሄደበት አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችና በ2007 ዓ/ም ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የምርጫ ድራማ ሳቢያ ከፍተኛ እንግልትና ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙ ወገኖች የተሰማቸውን ደስታ ከመግለጻቸውም ባሻገር የወያኔን ቡድን በጥይት አረር ለመፋለም ግንባሩን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
source — http://www.arbegnochginbar.org/index.ph … &Itemid=50
ምስራቅ እዝ የመከላከያ መኮንኖች መካከል ውስጣዊ ውጥረት መስፈኑ ተገለጸ
ከምኒልክ ሳልሳዊ
በወያኔ መኮንኖች እና በኢትዮጵያ የመከላከያ ስራዊት መኮንኖች መካከል በፖለቲካ እና በጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ዙሪያ ውስጥ ውስጡን እየተካረረ የመጣው አተካራ ከባድ ውጥረት መፍጠሩን በእዙ የሚገኙ መኮንኖች የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ሕገመንግስታዊ ጥያቀዎችንእና ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚተይቁ መክንኖች ከየክምፑ ተለቅመው ወደ ሰሜን እዝ እና ወደ ሶማሊያ ከሄደው ጦር ጋር እንዲቀላቀሉ ከተደረገ በኋላ ውጥረቱ እየሰፋ መምጣቱ ታውቋል።
ከዚህ ቀደም የተነሱ ሕገመንግስታዊ ጥያቄዎችን የሕወሓት ከፍተኛ መኮንኖች የጥያቄው ባለመብቶችን ወደ ሌላ አከባቢ በመቀየር የቀሩትንም በጥቅም ለመያዝ ቢሞክሩም ያላዋጣቸው ሲሆን ክመሃል ሃገር ሰልጥነው የተመደቡትም ወታደራዊ ደህንነቶች የአንድ ብሄር አባላት ስለሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱ የበታች መኮንኖች በጥርጣሬ ስለሚመለከቷቸው የተላኩበትን ግዳጅ በብቃት መፈጸም ባለመቻላቸው ምንም አይነት ውጤት አለማምታታቸው ችግሩ ዳግም እንዲያገርሽ ሆኗል።
በወታደራዊ ደህንነቶች አማካኝነት እንቆጣጠረዋለን ብለው የምስራቅ እዝ ከፍተኛ የሕወሓት መኮንኖች ያሰቡት ጉዳይ ዳግም ውጥረት መፍጠሩ በድንበሩ አከባቢ ስጋት ስለፈጠረ ወደ አከባቢው አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አንድ ሻለቃ ጦር እንዲመደብላቸው ጠይቀዋል።
የምስራቅ እዝ ምኮንኖች አብዛኛው ስራቸው የኮንትሮባድ ተግባራትን መፈጸም መዝረፍ እና ሴቶችን መድፈር መሆኑ ይታወቃል። የሕወሓት መኮንኖች ሌላውን አስፈላጊውን ሕግ የሚፈቅደውን ጥቅማ ጥቅም በመከልከል ከፍተኛ በድል እያደረሱ ሲሆን በሶማሊያ ክልል ውስጥ በዘረጉት ከፍተኛ የቢዝነስ ስራ ውስጥ ማንም ሌላ ሰው እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችል ሲሆን እነሱ በሚሰሩ ቢዝነስ ውስጥ የሚገባ ንብረቱ እንደሚወረስ ታውቋል፡፤ የሞባይል ቀፎዎችን እና የኢሌክትሮኒስ ዕቃዎችን በሕገወጥ መንገድ ጭነው ካለፍተሻ ወደ መሃል ህገር በማምጣት በይርጋ ሃይሌ ሕንጻ ካሉ ወኪሎቻቸው ጋር በመተባበር በመላው ሃገሪቱ እንደሚያከፋፍሉ ታውቋል።
የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!
ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።
ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።
የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።
ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።
ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።
ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።
ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።
የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
አብዛኛው ህዝብ ለመንግስት ጥላቻ አለው” ሲል አንድ ከኢህአዴግ የወጣ ሰነድ አመለከተ
በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል።
የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣ እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።
በስልጠናው የብአዴን ታሪክ አብሮ መቅረቡንና ሰልጣኞችም የብአዴንን ታሪክ በማወቃቸው መርካታቸውን ሰነዱ አክሎ ይዘረዝራል።
“ግልጽነት ያልተያዘባቸውና በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተከታታይ ውይይትና ስራ የሚጠይቁ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ድረስ ብአዴንን የማይቀበሉ እና ከ97 ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ድምጾች አሉ፣ ነገር ግን የመንግስትን የሃይል እርምጃ ተከትሎ በፍራቻ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሎአል።” ሲል አስቀምጧል።
“በውይይቱ ወቅት የታዩ የአመለካከት ችግሮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በርካታ ችግሮች ተዘርዝረው ቀርበዋል። ” በ1989 ዓም የነበረው የመሬት ክፍፍል ለቢሮክራቶች ለምን 4 ቃዳ መሬት ተሰጠ? በአማራ ክልል ብቻ የአርሶ አደር መሳሪያ ለምን ተነጠቀ? ልማቱ ወደ ትግራይ ይሄዳል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አስመራንና አሰብን መያዝ ነበረብን” የሚሉት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰልጣኞች መቅረቡን ያወሳል።
ሰነዱ በስልጠናው የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችንም ይዘረዝራል። ሰልጣኙ እርስ በርስ በመተጋገዝ፣ በመማማር ተሞክሮውን በማካፈልና በመተራረም የነበረው ሁኔታ በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ለመንግስት ህዝቡ በአብዛኛው ጥላቻ ማሳየቱ” የሚል ሰፍሮአል።
የብአዴን አመራርና አባላት ” በአብዛኛው ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ የለም ” ብለው እንደሚያምኑ፣ “ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ደንታ እንደማይሰጣቸው”፣ እንዲሁም “መንግስትን በትክክል ዋጋ ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ” በሰነዱ ማብቂያ ላይ ተገልጿል።
ሰነዱን ለኢሳት የላኩትን የኢህአዴግን ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ በህዝብ ስም ለማመስገን እንወዳለን።
ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና
UK ban on drug khat = የእንግሊዝ መንግስት ጫት ወደ ሃገሩ እንዳይገባ አገደ።
A ban comes into force in the UK on Tuesday on the drug, khat, that is traditionally used by Ethiopian, Kenyan, Somali and Yemeni communities.
The British government says outlawing khat brings the UK into line with other European countries where it is a controlled substance.
However in Kenya’s khat-growing region, there is concern about the economic impact of the ban.
The BBC’s Anne Soy reports.
Read more http://betinews.com/?p=1354

እኛ ላይ የምትጮኸው ጠብ-መንጃ ስለሌለን ነው?!! ነገረ-ኢትዮጵያ
በነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ የተስተናደ
ይስጥልኝ!! እንደምን ሰነበቱልኝ፡፡ ዛሬ ከካሳንቺስ ስድስት ኪሎ በቤተ-መንግስቱ አጥር ስር እያለፍን እናወራለን፡፡ እንቀጥል፡፡ ከካዛንቺስ ስድስት ኪሎ ለመሄድ የታክሲ ሰለፍ ይዣለሁ፡፡ እንደ በረሃ ዘንዶ የተጥመለመለው ሰልፍ የቤተ-መንግስቱን አጥር ታኮ ፊት በር ሊደርስ የጥቂት ምስኪን ተሰላፊዎችን ከኋላ መሆን ብቻ ይጠባበቃል፡፡ ትንሽ ክብዶ(ማካበድ) ስንጨምርበት ደግሞ ከኋላ በተሰለፈውና በቤተ-መንግስቱ ጠባቂ መካከል ያለው ርቀት አንድ መትረየስ አያሥጠምድም፡፡ አንድ ሰዓት ላይ የማልቀርበት ብርቱ ቀጠሮ 6 ኪሎ አካባቢ ይጠብቀኛል፡፡ ሳላረፍድ ለመድረስ 11 ሰዓት ካዛንቺስ ታክሲ መያዣ ደርሸ የመሰለፍ ግዴታየን መወጣት ይኖርብኛል፤ ወይም ይህን ሰልፍ ትቸ የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ በቤተ መንግስት አጥር ስር አንገቴን ደፍቸ ማለፍ ይጠበቅብኛል፡፡በዚህ ቤተ-መንግስት ለሚያልፍ ሰው አንገቱን ደፍቶ ማለፍ ግድ ይለዋል፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻለን አስገድደው አንገት የሚያስደፉ ስልጡን ጠባቂዎች እንደ ግሪሳ ወፍ ወረውታል ቤተ-መንግስቱን፡፡ የሆነ ነገር ፈልገው ወይም የሚያሳክክ ነገር ቢገጥምዎት እንኳን ቀና ማለት ውጉዝ ነው፡፡ ይህን ካደረጉ ደግሞ ቁጭ በል ተነስ፤ቁም ሂድ የሚል ግልምጫ ሊከተልዎት ይችላል፡፡ አለፍ ካለና ጥበቃዎቹ እጅና እግራቸውን ማፍታታት ካስፈለጋቸው ደግሞ ጡጫ ነገርም ሊቀምሱ ይችላሉ፡፡ ለምን ብሎ ጥያቄ የለም፡፡ ምክንያቱም ይህ ቤተ-መንግስት ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሽር ማለት የሚችል መንግስት እንጅ እንደ እኔ አይነት አመዳም ድሃ አይደለምና፡፡ እድለ ጠማማ ከሆንክ ደግሞ አንዱ የአፍሪካ ነፍሰ ገዳይ አምባገነን መሪ ከቦሌ አየር ማረፊያ እየመጣ ስለሆነ ጀርባህን ሰጥተህ ቁም ልትባል ትችላለህ፡፡ በደርግ ጊዜ ነው አሉ እንዲህ እንዳሁኑ ሊቀመንበሩ ሲያልፉ ፊትህን አዙረህ ቁም ይባል ነበር፡፡ ይህ ድርጊታቸው ስልችት ያላቸው ሴትዮ ‹‹ሰውየውን የሚጠብቁት ከአይን ነው ወይስ ከጥይት›› አሉ ይባላል፡፡ ስለዚህ ይህን አካባቢ ፈጥን ብሎ በታክሲ ላፍ ማለት ይበጃል፡፡
በዚህ ደዲቃዎችን ሳይሆን ሰዓታትን በሚጠይቀው ሰልፍ ላይ የተደረደሩት ምስኪን የሀገሬ ዜጎች ሰማያዊ ታክሲ ላይ ትኩረት አድርገው አይናቸውን ላይ ታች ያቅበዘብዛሉ፡፡ በዚህ ሰልፍ ላይ የሌለ የሰው አይነት የለም፡፡ ከወፍራም እስከ የኔ ቢጤ ሲንብሮ፡ከሰማይ ቅርቡ ሞጋጋ እስከ እንቅፋት የመሰለ ድንክ፡ከምሁራን እስከ መሰረተ-ትምህርት ምሩቅ ብቻ ሁሉንም ሊያስማማ ከሚችለው መመዘኛ ከድህነት ውጭ ሰልፉ የሰው ማህበራዊ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ ታክሲዎች የመስቀል ወፍ በሚሆኑበት አጋጣሚ እንደ እኔ አይነት ቀጫጫዎች ተወዳጅነታቸው ይጨምራል፡፡ ቀጫጫዎችን በአንድ ወንበር እስከ ሶስትና አራት ሰው ለመጫን ስለሚመች፡፡ በመሆኑም እርስዎ ታክሲ ይሳፈራሉ እርስዎን ሌላ ሰው ተሳፍሮዎት ይጓዛሉ፡፡ ለምን ብሎ ጥያቄ የለም ምክንያቱም ይህ ጽሀዩ መንግስታችን ያመጣው ልማት ውጤት ነውና፡፡ በፈረንጅ ሀገር ወፍራም ሰዎች ተጨማሪ ክፍያ ይጠየቃሉ ሲባል ብሰማ መንግስቴን አጥብቄ አመሰገንኩት፡፡ እንዴት ብለው ከጠየቁኝ፤እንዲህ እመልሳለሁ፡፡ ሀገሬ ፍትሀዊነት የሰፈነባት በመሆኗ ወፍራሙም ቀጫጫውም እኩል የታክሲ ታሪፍ ስለሚከፍል፡፡ ደግሞ ኢቲቪ እንዳይማኝ፡፡ ኢቲቪ ከሰማ ግን እንዲህ ነው የሚዘግበው፡፡ ሀገራችን በታክሲ ታሪፍ ፍትሃዊነት በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት፤ አክሎም የታክሲ ሰልፈኛው ፈዛዛነት ለጎረቤት ሀገራት ምርጥ ተሞክሮ ሊቀመር የሚችል ነው ሲሉ አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል!! ማለቱ አይቀርም ኢቲቪ ነፍሴ፤ ነፍሱ ይጥፋና፡፡ ጎበዝ በስንቱ አንደኛ ሆንን ተብሎ ይዘለቃል፡፡ ሌሎቹ ሀገራ ስራ አቆሙ እንዴ?!! በአንድ ወቅት አቶ መለስ ስለ ፍትሀዊ የገቢ ክፍፍል ሲናገሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ቀጥላ ሁለተኛ ናት ሲሉ ሙድ ይዘው ነበር፡፡ ከደረጃ ጋር በተያያዘ የሆነ ወቅት ላይ ሚስተር ኦባማ የአለም መሪዎችን ሰብስበው ተወያዩ ሲባል የሰማ ካድሬ መሪዎቹ በጉብዝናቸው ነው የተመረጡት ሲል አወራለት፡፡ ጓደኛየ ካድሬውን እንዲህ ጠየቀው ‹‹የመረጣው መስፈርት አንድ ከላይ አንድ ከታች ነው እንዴ››ብሎ ነበር፡፡ በታችኛው መመዘኛ የገባው ማን እንደሆነ መቸም ገምታችኋል፡፡ የእኔ ነገር የተነሳውበትን ነገር ስቸ ወዴት ተሰነቀርኩ፡፡ ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና ስለ ታክሲ ሰልፌ ላውራ፤ ሰልፍ ሰልፍ ሰልፍ………….ኡፍፍፍፍፍፍ……….
ለምንና እስከ መቸ እንዲህ እንደምንሰለፍ ባይገባኝም፡የወገኔ ድካም ግን እጅጉን ያመኛል፡፡ ተሰላፊው የሰውነቱን ክብደት መሸከም አቅቶት እግሩ የዛለው ወገቡን ይዞ፤የባሰበት እየተቀመጠ፤የቀናው ደግሞ ከጎኑ የተሰለፈችን ኮረዳ እያሽኮረመመ ሰማያዊ ታክሲ ይጠባበቃል፡፡ ኮረዳ አሽኮርማሚው እንኳ ታክሲው ባይመጣም ግድ አይሰጠውም፡፡ በስንት ደቂቃ ልዩነት ብቅ የምትለው ታክሲ ከአስራ አምስት ሰው በላይ ጭና ላፍ ትላለች፡፡ ቀሪዎቹ ሰዎች ሰማያዊ ታክሲ መጠበቃችን እንደቀጠለ ነው፡፡ ፍቅረኛው ‹‹ሰማያዊ ልብስ ለብሸ እመጣለው ያለችው ጎረምሳ በታክሲ ይደነብራል›› እንደሚባው ሰማያዊ ነገር ባየን ቁጥር እናንጋጥጣለን፡፡ እንዲህ ወደ ታክሲው ያንጋጠጥነውን ያክል ወደ ቤተ-መንግስቱ ብናጋጥጥ መና ይወርድልን ነበር አልላችሁም መቸም፡፡ ታዲያ ቤተ-መንግስት ምን የሚወርድ ነገር አለ እንዳላችሁ ገብቶኛል፡፡ ‹‹ሆድ ይፍጀው›› አለ ሰውየው ብየ አልፈዋለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እኮ ስለ ቤተ-መንግስቱ የማይሆን ነገር ማሰብ አሸባሪነት ነው፡፡ ቀድማ የሄደችው ታክሲ የምትመለሰው ሾፌሩና ረዳቱ መቶ ግራም ገለምሶ ካኘኩ በኋላ ነው፡፡ ከስንት ሰዓት በኋላ እንደምንም እየተንፋቀቅን በሀይለ ስላሴ ጊዜ የተገዛች ከርካሳ ታክሲ ላይ ተጭነናል፡፡ መኪናዋ በጣም ከማርጀቷ የተነሳ ግጭት ቢደርስባት ቲታነስ ሊገድለዎት ይችላል፡፡ የብሄራዊ ሙዚየም ድክመት ነው እንጅ ታክሲዋ መገኛዋ እዛ ነበር፡፡ ለማንኛውም ጠጋ በል ከሚል የወያላ ንዝንዝ ለመዳን ስል ጋቢና መሳፈር እወዳለሁ፡፡ በእዛውም ቶሎ ለመድረስ ጋቢና መቀመጥ መፍትሄ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በታክሲ ፈልፍ ያባከንኩትን ጊዜ ያካክስልኛል ብል በአለም የመጀመሪያው ውሸታም አልሆንም፡፡
ሰው እንደ ቲማቲም ግጥግጥ ብሎ ተጭኗል…….ተሳፋሪዎች ጥቅጥቅ ብለው እንደገቡ ሴታ ሴት መሳዩ ሾፌር ገብቶ የመኪናውን ሞተር ቆሰቆሰው፡፡ ሞተሩ ተረክ ብሎ ተነሳ፡፡ በመቀጠል የተወዳጇ አስቴር አወቀ ተስረቅራቂ ድምጽ ከእስፒከሩ ወደ ጆሯችን ፈሰሰ፡፡ ‹‹ወይ ኑሮ ወይ ኑሮ›› ትላለች አስቱ የዛን ዘመን ኑሮ ዳገት ለመተረክ፡፡ የተዘፈነበትን ዘመን ሳይሆን ዛሬን የሚሰብከው የአስቴር ዘፈን ኑሮ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለማስረዳ ያጣጥራል፡፡ ዘፈኑ በዚህ ዘመን ተዘፍኖ ቢሆን ምን ሊባል ኑሯል፡፡ ይህ ዘፈን ሲዘፈን የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ በአሁኑ የአንድ ምግብ ዋጋ ጋር እኩል ነበር፡፡ አስቱ አሁን ሪሚክስ አድርጋ ብትዘፍነው እንደ ብሄራዊ መዝሙር ሁሉም ሰው ተቀባብሎ ይጫወተው ነበር፡፡በዚህ በሀል አንዱ ተሰፋሪ በኑሮ ይማረር በምን እሱ ያውቃል፤ከሙዚቃው ድምጽ በላይ 11.2% ጮክ ብሎ ሙዚቃውን ቀንሰው ሲል ደነፋ፡፡ እንደ ተንቤን ኮረዳ ሹርባ የተሰራው ሴታሴት ሾፌር ድንገት ወንዳወንድ ሆኖ አልቀንሰውም ሲል መለሰለት፡፡ ቀጠል አድርጎም ተሳፋሪው ላይ የትችት ማዕበል አወረደበት፡፡‹‹ታክሲ ውስጥ ብቻ ነው መብትህ ትዝ የሚልህ?››ከሁለት ሰዓት በላይ ተሰልፈህ ስትቆይ ለምን ብለህ አልጠየቅክም? ወይስ አሁን ነው ሰው መሆንህ የገባህ? በሚሉ ሞጋች ጥያቄዎች ያፋጥጠው ጀመር፡፡ ሁሉም ተሳፋሪ በሾፌሩ መልስ በመገረም ጸጥ አለ፡፡ አሁንም ሾፌሩ መናገሩን ቀጥሎ ‹‹እኛ ላይ የምትጮኸው ጠብ-መንጃ ስለሌለን ነው›› ሲለው የኮረኮሩኝ ያክል አሳቀኝ፡፡ ሌላው ተሳፋሪም አብሮ ሳቀ፡፡ ሰውየውም ሂሱን ውጦ ዝም አለ፡፡ ‹‹ጠብ መንጃ ስለሌለን›› ድንቅ አባባል፡፡ ተናጋሪው ሰውየ ድንገት የተቃዋሚዎች ስብሰባ እንደታደመ ካድሬ ቅስሙ ተሰብሮ ጸጥ አለ፡፡ ወደ ውስጤ አሰብኩ የሹፌሩ ነገር ትክክል ነበር፡፡ ከሁለት ሰዓታት በላይ ታግሶ መሰለፍ የቻለ ሰው እንዴት የሙዚቃ ድምጽ በዛ ብሎ ለመቃወም ወኔ አገኘ፡፡ ያውም ለስለስ ብሎ የተከፈተን ሙዚቃ ካቀነስክ በሚል ጥያቄ፡፡ በነገራችን ላይ ከመጠን በላይ የሚለቀቁ ሙዚቃዎች አግባብ ናቸው የሚል መከራከሪያ የለኝም፡፡
ታክሲዋን ቀና ብየ አየኋት፡ጥቅሶች ተንጠልጥለዋ፡፡ ዙሪያ ገባዋ በአብዮተኛ ጥቅሶች ተሞልታለች ያች ከርካሳ ታክሲ፡፡ ትኩረቴን የሳበችኝ ግን ‹‹መብትህን ከታክሲ ስትወርድም ጠይቅ!!›› የምትለዋ ነች፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሾፌሩን አደነቅኩት፡፡ ሳትፈራ ጠይቅ ነው ያለው ሾፌሩ፡፡ የጥበብ መጀመሪያው መጠየቅ ነው!! እንዲል የእኔ ፍልስፍና የመጨረሻው ምዕራፍ፡፡ ትክክል መስሎ ያልተሰማንን ነገር መጠየቅ፤ያላመንበትን ላለማድረግ እንቢ ማለትን መለማመድ ይጠበቅብናል፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንባል ትልቁ ችግራችን ክፉ ቀንን ታግሎ ከማሸነፍ ይልቅ ችግሩን መለማመድ ይቀለናል፡፡ ልመደው ሆዴ የዘወት እንጉርጎሯችን ነው፡፡ ‹‹ክፉ ቀንን እና ቅዝምዝምን ጎንበስ ብሎ ማሳለፍ ነው›› ስንል እንተርታለን፡፡ ‹‹ቀን ሲያልፍ ተናገር ወንዝ ሲጎድል ተሻገር›› እንላለን፡፡ በአባቶቻችን ተረት የምንኖር በተረት እንኳን እራሳችንን ያልቻልን ምስኪኖች፡፡ ‹‹ቻለው ሆዴ ልመደው በዘዴ››ን በአደባባይ የምዘፍን………
የተንዘላዘለውን ሰልፍ ለማስቀረት ከምንዘይደው ይልቅ የምንለምድበትን ዘዴ እንፈጥራለን፡፡ ኑሮ ማለት ሰልፍ እስኪመስለን ድረስ ለዳቦ እንሰለፋለን፡ለታክሲ ሰልፍ፡ሲያስለቅሰን ለኖረ ሰው የሀዘን ሰልፍ፡ለሰልፋችን መንስኤ የሆነን አምባገነን ለመቅበር ሰልፍ፡በአጠቃላይ ኑኗችን ሰልፍ የሆንን ድንጉጦች….!! በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ከእድገት በህብረት ዘመቻው ሰልፍ ቀጥሎ ረጅሙ ሰልፍ የታክሲ ሰልፍ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህ ሁሉ ሰልፋችን መንስዔ የሆነውን መንግስት እንፈረዋለን፡፡ ከፍርሀታችን የተነሳም መንግስትን ለማማረር እንኳ በራችን በደንብ መዘጋቱን እርግጠኛ የምንሆን ስንቶቻቻን ነን?፡፡ እንዚህን ሰልፎች አንድ ቀን አንዱ ወፈፌ መፎክር ያስያዛቸው እለት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡ ‹‹መንግስት ባቡሩ ሲያልቅ ችግሩ ይቀረፋል እስከዚያው ድረስ ባቡሩን መስላችሁ ተሰለፉ›› እያለ ጥሩምባውን ይነፋል፡፡ ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይበላ ኖሮ እከክ ይበጣጥሰው ነበር እንዳሉት አይነት ነው፡፡እኔ የምጠቀመው የስድስት ኪሎ ታክሲ ስለሆነ ችግሬ አይቀረፍምና ዝም አልልም፡፡ ወይም እንደተባለው ተስፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለነገሩ ዝም ባንልስ ምን እናመጣለን፡፡ እኛ ጠብ-ምጃ የለን ማን ይፈራናል፡፡ ከታክሲው በሰላም ወርጃለው፤የቀጠርኩት ወዳጀም ከፊት ለፊቴ ይታየኛል፡፡ የሾፌሩ ድምጽ ግን አሁንም ይከተለኛል፡፡ ‹‹እኛ ጠብ-መንጃ ስለሌለን ነው የምትጮኸው››?!! ትልቅ አባባል!!
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!!
የዚህን ሰሞን የመቀሌን ባለስልጣናት ያደፈረሰ ጉዳይ ተከስቷል። ሰላዮች እንደ አሸን ፈልተዋል። የህወሓቶች የውስጥ ቅራኔ ዳግም እንዳያገረሽ ያሰጋል።
አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ በተከታታይ እየተካሂዱ ያሉ ስብሰባዎች ውጥረቱ ያመለክታሉ። እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችንን የሚከታተሉ እና የሚያጨልሙን ሰላዮች ተመድበውብናል ሲል መቀሌ ያለው የሕወሓት አንጃ አኩርፏል። ከመሃል አገር የፌዴራል መንግስቱን በመቆጣጠር እያሾረው ያለው የሕወሓት አመራሮች ቡድን መቀሌ በሚገነው አንጃ ላይ ሰላዮችን አሰማርቷል ሲሉ በትግራይ ክልል ያሉ የሕወሓት ባለስልጣናት እየከሰሱ ነው፡፤ ይህንን ተከትሎ የተነሳው ኩርፊያ እና አለመግባባት ሕወሓቶችን ዳግም ወደ ቀድሞው ሽኩቻ እና ቅራኔ ውስጥ እንዳይከታቸው ያሰጋል ሲሉ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል።
በግንቦት ሃያ በአል ምክንያት ወደ አውስትራሊያ ተጉዘው የነበሩት አለቃ ፀጋይ በርኸ እና ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ብምካከላቸው በተነሳ አለምግባባት በተለያየ በረራ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን አለቃ ጸጋይ አብረውን በተጓዙ ጭፍሮቹ ያሰልለናል ሲሉ የቡድኑ አባላት ሲናገሩ ተደምጧል። አለቃ ጸጋይ ሰክረው የሰው ሚስት ሊያሽኮርምሙ ሲዳዳቸው በቡጢ መዘረራችው ይታወቃል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የሕወሓት የደህንነት ባለስልጣናት በከፍተኛ የዘረፋ እና የማገት ስራ ላይ መሰማራታቸው ተጋለጠ።
በቅርቡ የታጠቁ ግለሰቦች ከዶላር ጋር በተያያዘ በመሃል አዲስ አበባ በጠራራ ጸሃይ ሁለት ሚሊዮን ብር በመዝረፍ መሰወራቸውን ተከትሎ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዘረፋውን የፈጸሙት ግለሰቦች በአቶ ጌታቸው እና በአቶ ኢሳያስ የሚመራው የደህንነት የማፊያ ቡድን አባላት መሆናቸው ታውቋል። እስካሁን በምርመራ ላይ ተብሎ ሌሎችን በመያዝ ካለወንጀላቸው ያሰረው ፖሊስ ከሳሾች የተባሉትን በመክሰስ እንዲሁም ከሳሾች ዘራፊ ግለሰቦቹ እነዚህ አይደሉም ቢሎም ፖሊስ ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም።
በመከላከያ ሰራዊት የሕወሓት መኮንኖች ስር የሰደደው የሙስና እና የዘረፋ አድራጎት በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥም ከሹሙ ከአቶ ጌታቸው እና ከባለስልጣኖቻቸው ጀምሮ እስከ ገራፊዎች ድረስ መንሰራፋቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ የደህንነት ባለስልጣኖቹ የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት በከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ ባማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::
ከዚህ ቀደም በሙስና የተከሰሱ የስርኣቱ ባለስልጣናትን ተገን በማደርግ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::
ኢትዮጵያውያን በሕወሓቱ የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::
#ምንሊክሳልሳዊ
ዜጎችን ሊታደጉ የማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ሊወገዱ ይገባል።

ዜጎችን መታደግ የማይችሉ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ የመቀላቀል ግዴታ አለባቸው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ጨቋኝ መንግስታት የሆኑ ከጥንት እስከ ዛሬ የተንሰራፉ በህዝብ ላይ የሚያደርጉት ጭቆና እና በደል ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ በሰው ልጆች የትውልድ ሂደት ላይ መፍጠሩ እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖቶች ሚና ግን እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ዜጎች በግፍ በጨቋኝ መንግስቶች ሲታረዱ በመባረክ የመንግስታቱን እድሜ አስረዝመዋል አሁንም እያስረዘሙ ነው። የመንግስት እና የሃይማኖት ቁርኝት የሚፈለገው ስልጣንን አደላድሎ ለመያዝ እና ህዝብን ረግጦ ለመግዛት ካለ ምኞት እንጅ ለዜጎች ከመቆርቆር የመነጨ አይደለም። የሃይማኖት አባቶች በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ ተገዝተው አሊያም አድርባይ ሆነው በመስራት ላይ ያሉ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች እጅግ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በዜጎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎች ድብደባዎች እስሮች እና መንገላታቶችን እንደ አንድ መንፈሳዊ የሃይማኖት መሪ እንደ ሰብአዊ ተፈጥሮ አሊያም መጽሃፋቸው እንደሚያዛቸው ለዚጎች ሲደራደሩ ሲከራከሩ ሲዋያዩ ሲሆንም አንተም ተው አንተም ተው ሲሉ አልታዩም ከዚህ በከፋ መልኩ በልማታዊ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ፉጨት ስር ተደብቀው በለው በሚል አብዮታዊ ዜማ ዜጎችን እያስፈጁ ይገኛሉ።
አንድ የሃይማኖት አባት የታመመ ሲጠይቅ፤ የሞተ ሲቀብር ፤የተቸገር ሲረዳ ፤የታሰረ ዞሮ በመጎብኘት ሲያጽናና እንጂ ሲፖተልክ አሊያም ሲወሸክት ማየት ያማል። በሃገራችን ምእመናንን እንምራለን የሚሉ ሕዝብን መንፈስ እንመግባለን የሚሉ የለሊት ወፍ የሆኑ የክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት መሪዎች ዜጎችን መታደግ የማይችሉ ከሆነ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ መቀላቀል ግዴታ አለባቸው። ይህ ጉዳይ የብዙሃኑ የዜጎች ጉዳይ ስለሆነ ክርስቲያን እስላም የሚባልበት ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳይ ነው።

በሃገሪቱ ዜጎች በአለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በነጻነት በመጻፋቸው የእኩልነት እና የነጻነት ጥይቄ በማንሳታቸው ብቻ አሸባሪ ተብለው እስር ቤት በታጎሩባት ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስኪ ላስጠናው ላጥናው ያለ የሃይማኖት መሪም ይሁን የሃይማኖት ሃራጥቃ የለም። እንዲሁም በታሰሩ ሰዎች እና በአሳሪዎች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ለወደፊቱ ስህተቶች ካሉ እንዳይደገሙ ነገሮችን ለማግባባት እና ለማቻቻል የፈቀደ አንድም የሃይማኖት መሪ የለም። ይብስኑ የሃይማኖት መሪዎቹ በየስብሰባው እና በየጭብጨባው ዜጎች የመንግስታዊ ሽብር ዱላ ሰለባ እንዲሆኑ እያበረታቱ ይገኛሉ ።
የዜጎች ሁኔታ ያሳሰባቸው የሃይማኖት መሪዎች በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት እንዲሁም በጥቅም በማሰር እንዳይንቀሳቀሱ አሊያም በተዘዋዋሪ ባልሰሩት ወንጀል ለማጥመድ ሴራ በመጎንጎን እያስፈራሩ የህዝቦችን የሰብ አዊ መብት ጥያቄዎች እንዳያነሱ በማስደንገጥ እንዲሁም በጥቅማ ጥቅም እና በገንዘብ በመደለል አባትነታቸውን ለስጋዊ ባለስልጣናት እንዲሸጡ እና የፖለቲካ ምንዝር እንዲፍጽሙ እየተደረገ ሲገኝ ይህንን የምንዝር ጌጥ ከመለማመዳቸው የመጣ የሃይማኖት አባቶች ከጨቋኞች ብሰው በሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እንዲፈስም ከባዱን ሚና እየተቻውቱ ይገኛሉ ።
የሃይማኖት አባቶች ሰጥ ለጥ ብለው ስለልማት ብቻ እንዲሰብኩ የእስላሙንም ሆነ የክርስቲያኑን ጥያቄዎች በተገኙበት እንድያስተጋቡ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው አባቶች መካከል አቡነ ማትያስ አቡነ ሉቃስ እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው እንዲሁም የወያኔ መንግስት በቅርቡ ለሾማቸው የእስልምና ምክር ቢት ሼሆችን ከፍተኛ የሆነ ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። እኔ ስጨፈጭፍ እናንተ አጨብጭቡ የሚለው አሸባሪው የወያኒ መንግስት ሃይማኖቶችን በራሱ አይዲኦሎጂ በመቀጽ ቀሚሳቸውን ያንዥረገጉ ሰላዮችን እና የሃይማኖት ነቅእዞችን በመመደብ ዜጎችን በተመለከተ የሚደርሱ በደሎች እና ገፈፋዎች ጠያቂ እንዳያገኙ አስታራቂ እንዳይሹ አድርጓል። ፓትርያርኩ ተንገላተው ከተለቀቁ በኋላ በማህበራዊ ድህረገጾች ላይ ብዕራቸው ለምን ታቀበ? ከፋሲካ ክብረ በአል በኋላ በትዊተር ላይ እንዳልተገኙ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከማንኛውም አንደፋዳፊ ንግግር በመቆጠብ በተረጋጋ መልኩ አንገታቸውን እንዲሰብሩ እና በቅርባቸው ለተመደቡላቸው የመንግስት ደህንነቶች /አማካሪዎች ተገዢ እንዲሆኑ ተደርጓል።
ዜጎቹን የማይታደግ የሃይማኖት መሪ ቆቡን አውልቆ ከፖለቲካው ጎላ ልኢቀላቀል አሊያም ገለልተኛ ሰው ሆኖ እንዲቀመጥ ለመምከር እንፈልጋለን ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሃይምኖቶች ለመንግስታዊ ሽብር ተገዢ እና ታዛዥ እንዲሁም የሽብር ሰባኪ ሆነው ዜጎችን በአደባባይ እያስግደሉ ዜጎች ከሞቱ በኋላ በሃይማኖታቸው ስር አት እና ደንብ እንዳይቀበሩ ተጽእኖ በማድረግ ለምድራዊው የጨቋኝ ምደብ ተባባሪ እና አስተባባሪ በመሆን ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ። ስለዚህ በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የማይቆረቁራቸው የሃይማኖት አባቶች ሊወገዱ ይገባል።
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … st_18.html
ማሳሰቢያ ፦ በዛሬው እለት በኦርቶዶክስ በእስልምና በካቶሊክ እና ከመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን የተዘዋወረው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ቡድን ያሰባሰበውን ጉድ የያዘ መረጃ በቅርቡ በይፋ እናወጣዋለን ይጠብቁን።
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ተፈናቃዮቹ የክስ መዝገብ ዛሬ ተሰማ።
“ሰዎቹ ለፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ መጠቀሚያ እየሆኑ ነው::” የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
ባለፈው ዓመት ለዓመታት ከኖሩበትና ሀብት ንብረት ካፈሩበት መኖሪያቸው እንደተፈናቀሉ በመግለጽ ይህን ተግባር ፈጽመዋል፣ አስፈጽመዋል ባሏቸው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ቡለል ወረዳ ላይ ተፈናቃዮቹ በተወካዮቻቸው በኩል ክስ መስርተዋል፡፡
በዚህ መሰረት ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ 8ኛ ፍትሃ ብሄር ምድብ በዋለው ችሎት የክስ መዝገቡ ተሰምቷል፡፡ ተፈናቃዮቹ በጠበቃቸው በዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም አማካኝነት እየተመሩ ክሱን እንዲያስኬዱላቸው ቄስ መስፍን አስፋውንና አቶ አቻምየለው ደሴን ወክለው አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል፡፡
ከሳሾቹ ከ15-20 ዓመታት ከኖሩበት ስፍራ ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ መደረጋቸውንና ይህም ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው አስረድተዋል፡፡ ክሱ የቀረበባቸው የፌደራል ጉዳዮችና የቡለል ወረዳም መልስ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሳሾቹ ይኖሩበት በነበረው ቦታ ቤት ንብረት አላፈሩም፤ ሰዎቹ ለፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ መጠቀሚያ እየሆኑ ነው ሲል ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
የቡለል ወረዳ በበኩሉ ከሳሾቹ በወንጀል የሚፈለጉ እንደሆኑ ጠቅሷል፡፡ ችሎቹ ግራ ቀኙን አዳምጦ ሶስቱም አካላት ለክርክር ቀጠሮ ሰኔ 30 ድጋሜ ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ወስኗል፡፡
ይህን የፍርድ ሂደት ለማስጀመር ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ባካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የዜጎችን ከአመታት ከኖሩበት ቀየ መፈናቀል በማውገዝ ጉዳዩን ወደ ህግ ለማቅረብ ቃል በገባው መሰረት የተፈናቃዮችን ሁኔታ ቦታው ድረስ በመሄድና በመከታተል ለአሁኑ የህግ ሂደት እንዲደርስ ማስቻሉን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ አሁንም ፓርቲው አጠቃላይ የፍረድ ሂደቱን በቅርበት እንደሚከታተል አቶ ዮናታን ጨምረው አስረድተዋል፡፡
የአገራችን የፖለቲካ ሰማይ ያረገዘው ጥላቻ፣ጽንፈኝነትና ቂም በቀል መጽዳት አለበት።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
እርስ በርስ መካሰስ፣ መጠላላት፣ መበላላት፣ የሌላውን ታሪክ ማጉደፍ፣ የሌሎችን ሰብዓዊ ክብር መንካትና ማዋረድ እንደ ጀብዱና አሸናፊነት በሚቆጠርበት፣ ጥላቻ፣ ጽንፈኝነትና መለያየት የአገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞቻችን ልዩ መለያ ሆኖአል፡፡
ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ያሻግራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ተማሪ፣ ገበሬ፣ ወታደር፣ ምሑር፣ወዘተ በነቂስ ሆ ብሎ የተሳተፈበት አብዮት በአገራችን ላይ ጥሎት ያለፈው ጠባሳ እጅግ ከባድና መራር ነበር፡፡ እስከ አሁንም ድረስ በዚያን ዘመን ትውልድ አባላት ለውጥ አራማጆች ላይ የፈጠረው የልዩነት ገደል፣ ጥላቻና መራርነት ሳይናድ እዚህ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡
የትናንት ትውልድ አባል የሆኑት አብዛኛው የዛሬዎቹ ፖለቲከኞቻችን የብዙ ወገኖቻቸውን ክቡር ሕይወት የቀጠፈውንና አገሪቷን ወደ አሰቃቂ እልቂትና ፍጅት የመራውን ፖለቲካዊ ቀውስ አስመልክቶ ይቅር ለመባባልና እርቅ ለማውረድ ከወሬ ባለፈ ተግባራዊ የሆነ እንቅስቃሴ ለማድረግ አልደፈሩም፡፡ ዛሬም ቢሆን ትናንት በአገራችን ላይ ለተከሰተው ሰብዓዊ እልቂት፣ ኢኮኖሚያዊ ውድመትና ማኅበራዊ ምስቅልቅል አንዱ አንዱን ተጠያቂ የማድረግ አባዜ ነው ጎልቶ የሚታየው፡፡
የፍቅርን፣ የሰላምንና የዕርቅን ባንዲራ ከፍ አድርጎ በማውለብለብ የኢትዮጵያችንን የዘመናት ፖለቲካዊ ስብራቷንና እያመረቀዘ ያስቸገራትን የቂም በቀልና የጥላቻ ቁስሏ ይሽር ዘንድ የፍቅርንና የይቅርታን ዘይት የሚያፈስላት እንደ ማንዴላ ያለ ብሔራዊ የፍቅር ጀግና ለማግኘት ገና አልታደለችም፡፡ እናም ያልሻረ ቁስሏን፣ ያልተፈወሰ ሕመሟንና ያልተጠገነ ስብሯቷን ይዛ በማንከስ እናት ኢትዮጵያ በእኛም ዘመን ወንድም ወንድሙን ትናንት በተፈጸመ ታሪክ ለበቀልና ለሞት የሚፈላለጉባት ምድር ሆና ዘልቃለች፡፡
በጥላቻ፣ በቂም በቀለኝነትና በጽንፈኝነት እግረ ሙቅ ውስጥ ለወደቀው የአገራችን ፖለቲካ መፍትሔው ከልብ የሆነና ከፍቅር የመነጨ ብሔራዊ እርቅ፣ መግባባትና በግልጽ መነጋገር እንደሆነ በግሌ በእጅጉ አምናለሁ፡፡ ይህን ጹሑፍ ለመጻፍ የተነሳሁበት ዋነኛው ምክንያትም በገዢው ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚ ፖለቲከኞቻችን መካከል ተቀራርቦ በመግባባት መነጋገር ይቻል ዘንድ፣የአንድ አገር ልጆች በሐሳብ ልዩነትና ፖለቲካዊ አመለካከት ምክንያት በጠላትነት የምንፈራረጅበት የጨለማው ታሪክ ዘመናችን ያበቃ ዘንድ በመመኘት ነው፡፡
አሁንም ድረስ የአገራችን ፖለቲካ በጥላቻና በጽንፈኝት ሥር ወድቆ የሚማቅቅ መሆኑን ከበቂ በላይ የሆኑ ማሰረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዕርቅና በፍቅር መንገድ ሊነሱ ቀና ቀና ያሉትንም ባለ ራዕዮች ከጠላቶቻቸው ቀድመው ወዳጆቻቸው ነን የሚሉት ራዕያቸውን አምክነው፣ ተስፋቸውን አድብዝዘው ከትግሉ መድረክ ገፍተዋቸዋል፡፡ እናም ዛሬም ድረስ የአገራችን የፖለቲካ ሰማይ ካረገዘው ከጥላቻ፣ ከጽንፈኝነትና ከቂም በቀል የጸዳ ለማድረግ ገና ከፊታችን እልህ አስጨራሽ የሆነ ረጅም ጉዞ የሚቀረን ይመስለኛል፡፡
ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- የመንግስት ሹመኞችና ባለሟሎቹ የሙስናን በሽታውን ወደ ሕዝብ ነዝተውታል፡፡ ነጋዴው ማህበረሰብ እንደወትሮው ወጭ ገቢውን የሚያሰላው ከቀጥተኛ ወጭው ጋር ያተያያዘውን ግዢና ግብር ብቻ አይደለም፡፡ የቀን ጅብ ለሆኑ ሙሰኞች የሚሰጠውን ኮሚሽንና ውጣ ወረዱን ጭምር ነው። ………… ሕዝቡ የኑሮ ውድነት ከበደኝ! የእቃ ዋጋ ንረት አስመረረኝ! ግፍ በዛብኝ! ሸምቶ መቃመስ አቃኝ የሚል ምሬት ሲያሰማ.. ሹመኞች አፍ ለማስያዝንና ለማሸማቀቅ ይሽቀዳደማሉ፡፡ “በገበያ ስርዓት ነው የምንመራው የሚችል ይገዛል፡፡ ያልቻለ አይገዛም” ይባላል፡፡ ገፋ ሲልም “አጭበርባሪ ነጋዴ ስናሳድድ አንገኝም!” የሚል ማበረታቻ አከል መልስ ለሕዝቡ ይሰጣል፡፡
የተረጋጋ የነበረውን የግብይይት ስርዓት ያለበቂ መነሻና ጥናት የዋጋ ጣራ በማወጅ፣ ውቅያኖሱን ደብድቦ አሳውን የሚረብሽ ፖሊሲ ይዘረጋል፡፡ አለመረጋጋቱን ታኮ ነጋዴው እጥረትን፣ የጥራት ችግርን፣ ቅሸባን፣ ሚዛን ማጓደልን አይነተኛ የስራውና የትርፉ መሰረት ያደርገዋል፡፡ ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … -post.html
በአራት ቡድኖች ተከፍሎ በከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ስራ መጀመሩን መረጃዎች ጠቁመዋል
መጪው ጊዜ ለወያኔ ጨለማ ሆኖቦታል። መላ ሃገሪቱን በስለላ መረብ አጥሮታል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የሃገሪቱ ግማሽ በጀት ላፓርላማቸው ሳያሳውቁ ለደህንነት እና ለስለላ ተግባር መድበዋል።
በአራት ቡድኖች ተከፍሎ በከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ስራ መጀመሩን መረጃዎች ጠቁመዋል ፤ ኢሕአዴግ ውስጥ በተነሳው የብሩህ ተስፋ ክሽፈት የመጣ በባለስልጣናቱ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት አመራሮችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። ባለፉት 23 አመታት በህዝብ እና በሃገር ላይ የተደረገው ከፍተኛ የሆነ በደል እና ዘረፋ በሕዝቡ ዘንድ ጥርስ እንዳስነከሰባቸው እና መጪው ጊዜ ይጨልምብናል ብለው ከፍተኛ ስጋት ስላደረባቸው በአራት ቡድኖች የተከፋፈለ በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ እና በመላው ሃገሪቱ የተበተነ የድህንነት እና የስለላ ሃይል ማሰማራታቸው ታውቋል።
በአራት ቡድኖች ተከፍሎ በከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ስራ የጀመረው በየአከባቢው ከመንደር እና ቀበሌ ጀምሮ እስከ ከተሞች የገጠር ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በወያኔ ላይ ደባ ይሰራሉ ይፈጸማሉ ይመከራሉ የተባሉ እያንዳንዱን የዜጎች እንቅስቃሴዎች ሪፖርቶችን በትጋት በመሰብሰብ ወደ መሃል አገር በመላክ መታፈን ያለባቸው መገደል ያለባቸው ደብዛቸው መጥፋት ያለባቸውን ሰዎች በተመለከተ ከበላይ በሚተላለፍለት ትእዛዝ መሰረት መፈጸም ዋናው ስራው ነው። ይህ የደህንነት እና የስለላ መዋቅር ከመሃል ሃገር ተነስቶ እስከ ኬንያ ዩጋንዳ የኤርትራ ደጋማ አከባቢዎች ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ጅቡቲ እና ሰሜን ሱማሊያን ያጠቃልላል።
ወያኔ የሚጠራው መጪው ምርጫ ሕዝቡ በ1997 እንዳደረገው አሁንም እንዲሁ ቂሙን በካርድ ይገልጽብናል በማለት የሚሰጋው ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የሃይል እርምጃ በመጠቀም ለማክሸፍ የሚያስችለው በየትኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሊሆን እንደሚችል ስለላውን ተያይዞታል፡፤
አራቱ የደህንንት እና የስለላ ቡድኖችን የሚመሩት ከፍተኛ የሕወሓት አመራሮች የደህንነት ሹሞቹ ጌታቸው እና ኢሳያስ በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለውን እና በጎረቤት አገሮች ያለውን በደብረጺሆን ገብረሚካኤል የሚመራው ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ በብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን የሚመራው ቡድን በምእራብ ኢትዮጵያ እንዲሁም ባለፈው አውስትራሊያ ውስጥ በቡጢ የተዘረሩት አለቃ ጸጋዪ የሰሜኑን ክፍል እና የኤርትራ ደጋማ አከባቢዎችን የደህንነት እና የስለላ መዋቅር ለመምራት ከፍተኛ ገንዘብ ለስልጣን ማቆያቸው በመመደብ የገቡበትን ውጥረት ለማኮላሸት እየሰሩ መሆኑን ታውቋል።
በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች የካድሬዎች እንቢተኝነት የውጪ ሃይሎች ጫና የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ ማጣፊያው አጥሮት የሃገሪቱን ግማሽ በጀት የሚሆነውን ለደህንነት እና ለስለላ ተግብር በማዋል ከፍተኛ የሆነ አደጋ በሃገር ላይ አውጆ ሕዝብን እያሸበረ ይገኛል።
UTC 16:00 የዓለም ዜና 100514
የዓለም ዜና
UTC 16:00 የዓለም ዜና 230414
የዓለም ዜና
UTC 16:00 የዓለም ዜና 180414
የዕለቱ ዜና
UTC 16:00 የዓለም ዜና 160414
የዕለቱ ዜና
15.04.2014 ዜና 16:00 UTC
የዓለም ዜና
UTC 16:00 የዓለም ዜና 130414
የዕለቱ ዜና
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የሰጡት የክስ መከላከያ ( በድምጽ ) AUDIO
የመሪዎቻችንን የክስ መከላከያዎች ለማሰራጨት እንረባረብ!
ኡስታዝ አቡበክር አህመድና ዳዒ ያሲን ኑሩ ያቀረቡት የክስ መከላከያ በጽሁፍና በድምጽ ተዘጋጅቶ ከታች በሚገኙት ሊንኮች ቀርቧል
1.የኡስታዝ አቡበክር አህመድ ክስ መከላከያው የፒዲኤፍ ጽሁፍ ሊንክ፡-
የኡስታዝ አቡበክር አህመድ ክስ መከላከያው የድምጽ ትረካ ሊንክ፡-
2.የዳዒ ያሲን ኑሩክስ መከላከያው የፒዲኤፍ ጽሁፍ ሊንክ፡-
የዳዒ ያሲን ኑሩ ክስ መከላከያው የድምጽ ትረካ ሊንክ፡-
መጋቢት 24 አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የቀረቡበት ልዩ ዘገባ
በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ
መጋቢት 25 ኡስታዝ በድሩ ሁሴንና
ካሚል ሸምሱ የቀረቡበት ቢቢኤን ልዩ
ዘገባ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ
የመሪዎቻችንን የክስ መከላከያዎች
ለማሰራጨት እንረባረብ!
የመሪዎቻችንን የክስ መከላከያዎች ለማሰራጨት እንረባረብ!
to be continued ………..

ምን ይደረጋል? እናት አገር ትኑር!
ጌታቸው ሽፈራው እንደጻፈው ፤- የመመረቂያ ጽሁፌን ለመጨረስ ደፋ ቀና እያልኩ ባለሁበት ወቅት ነው አንድ የማላውቀው ስልክ የተደወለልኝ፡፡ ይህ ስልክ አባል ባለመሆኔ ስራ እንደማላገኝ ተስፋ ወደመቁረጥ በተቃረብኩበት ወቅት ለስራ እንደምፈለግ አበሰረኝ፡፡ ስልኩ ከኢመድኤ (INSA) መሆኑ ተነግሮኛል፡፡
ይህን መስሪያ ቤት ስም ፈጽሞ ሰምቼው አላውቅም፡፡ ለጓደኞቼ ሳወራቸው ከእኔ በፊት አብዛኛዎቹ ተደውሎላቸው እንደነበር አጫወቱኝ፡፡ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደኢህዴን ልጆች እርስ በእርሳቸው እንደተጠቋቆሙም ወሬ ደረሰኝ፡፡ በስተመጨረሻ እኔም መጠራቴ ነው፡፡ ሌላኛው ግራ የሚያጋባው ወሬ ግን መስሪያ ቤቱ የስለላ ተቋም እንደሆነ መስማቴ ነው፡፡ ሁለት ሆድ ሆንኩ፡፡ የኋላ ኋላ አይቶ መውጣቱ እንደሚሻል ወሰንኩ፡፡ አንድ በጣም የሚቀርበኝ ጓደኛዬ ስለተቋሙ ካጫወተኝ በኋላ እንዲቀጥሩኝ አባል መሆኔን (ሸውጄ) እንድነግራቸው አግባባኝ፡፡ አልፈለኩም፡፡
ለጥያቄ የተቀጠርንበት ቀን ደረሰ፡፡ ለፈተና ቀረብን፡፡ ጥያቄዎቹ ከጠበቅናቸው በላይ ናቸው፡፡ ከጠበቁት በላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፡፡ ከዚህ መርህ ያፈነግጣሉ የተባሉ ጓደኞቻችን ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ ፈተናውን አልፈን ለስልጠና በገባንበት ወቅት ደግሞ ሌላ ተስፋ ሰጭ ጉዳይ ተከሰተ፡፡ በነጻነት መከራከር ቻልን፡፡ በአንድ ትምህርት ዘርፍ (ፖለቲካል ሳይንስ) ለቅጥር ያለፍነው 12 ወጣቶች ሌሎቹን እንድናስተባብር በየ ውይይት ክበቡ ተሰባጠርን፡፡ ኢንሳን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውን የሚርቁትን ይቀይራሉ ተብለንም ‹‹12ቱ ሐዋሪያት›› የሚል ስም ወጣልን፡፡ በኋላ አንዷ የውጭ አገር እድል አግኝታ ስትወጣ ‹‹ይሁዳዋ!›› ብለን ተሳልቀንባታል፡፡ ይሁዳ ያወቀው ይህኔ ነው፡፡ ነገር ሳይበላሽና ሳይቆስሉ ቦታ መያዝን የመሰለ ነገር የለም፡፡
ስልጠናውን ጨርሰን ለአንድ አመት ያህል በነጻነት ሰራን፡፡ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ይህ አቋም ስራ ላይ ማንጸባረቅ አይፈቀድም ተባልን፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ነገር ነበር፡፡ አሁን አሁን ሳስበው ግን ለኢንሳዎች ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ማለት ኢዴፓ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም አንዱ ‹‹አለቃ›› ስለጉዳዩ ተናግሮ ሳይጨርስ ‹‹ይህን ስል ግን የኢዴፓን አቋም እዚህ (ስራ) ላይ ማንጸባረቅ ይቻላል ማለት አይደለም፡፡›› ሲል አስታውላለሁ፡፡
ብቻ ያ ጊዜ ለመስሪያ ቤቱ መልካም አመለካከት የነበረን ጊዜ ነው፡፡ ጅራትና ምንድን ነበር ወደኋላ የሚመጣው? በእርግጥ ከዚህ በፊት ኢንሳ ጠለፋና ሌሎቹንም ነገሮች እንደሚሰራ መስማት ጀመረናል፡፡ ስለ ጉዳዩ እርግጠኛ ባንሆንም የት ነው የምትሰራው ተብሎ ‹‹ኢንሳ!›› ለማለት የሚያኮራ አልነበረም፡፡ ብዙዎቹ ጓደኞቻችን ‹‹ሰላይ!›› እንመስላቸው ነበር፡፡ የእኛ አገር ችግር ይህ ነው፡፡ ስለላን ገዥዎች አበላሸተውታል፡፡ ህዝቡም ሆነ ሰላይን መልሶ መሰለል የሚባል ነገር አያውቅም፡፡ ዝም ብሎ መራቅ፡፡ ዝም ብሎ ማማት ብቻ ነው፡፡
አሁን ጅራትና ጉድ ጭራሹን እየፈጠጡ መጡ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አትችሉም ተባለ፡፡ መጀመሪያ የነበረን ተስፋ ሁሉ እንደገና ተስፋ አጣ፡፡ ይህ በሆነበት ወቅት ነው፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንደ አንዳች ክፉ ነገር የሚጠሉትና የሚጠየፉት አቶ መለስ ሰንደቅ አላማውን ከላይ ወደታች ገለበጡት፡፡
እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ‹‹ሰውዬው ለምን ሰንደቅ አላማውን ገለበጡት?›› የሚል ጥያቄ አነሳሁ፡፡ ከቀናት በኋላ ይህን ሰንደቅ አላማው ላይ የጻፍኩትን ትንሽዬ ነገር ተከትሎ 12 አስቂኝ ከስሶች ቀረቡብኝ፡፡ አብዛኛዎቹ ህገ መንግስቱን ካለመቀበል፣ የፖለቲካ ቡድኖች (እነማን እንደሆኑ እነሱው ይወቁት) አባል ሆነሃል እና ጽንፈኝነት ጋር የተለነቀጡ ናቸው፡፡ በዝርዝር የአሰብ ወደብን የኢትጵያ ነው ብለሃል፣ ኢትዮጵያ የውጭ ብድር አለባት ብለሃል፣ የጋዳፊን ፎቶ ግራፍ አጋርተሃል (ሸር አደርገሃል)፣ ከጉራፈርዳ ስለተባረሩት አርሶ አደሮች ጽፈሃል፣ ኢህአዴግን ግንባራም ብለሃል……የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በእነዚህ ክሶች መሰረትም ለ2 ወራት ያህል ከስራ ታገድኩ፡፡ በዚህ ወቅትም ለክሶቼ መልስ እንድሰጥ ታዝዣለሁ፡፡ እናም ክሱ እንዲነሳልኝ የክሶቹን ፍሬ ቢስነት ጠቅሼ ተከራከርኩ፡፡ አይ እኔ ሞኙ! ህግ በሌለበት፡፡ በዚህ ክርክር የዲስሊን ኮሚቴ አባል ናቸው የተባሉ የህወሓት አባላት ልክ እንደ ከሳሽ ‹‹እንዴት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ታንቋሽሻለህ›› የሚል ክስ አቅርበው ተከራክረውኛል፡፡ የብአዴን አባላት ደግሞ እነሱን ተከትለው አስተጋብተዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ‹‹በከፍተኛ ወንጀል›› ተባረርኩ፡፡ በዚህ ወቅት አንድ የብአዴን ካድሬ ያለኝ መቼም ሊረሳኝ አይችልም፡፡ የቅርብ አለቃዬ ስለነበር ስለ ነበረኝ ስነምግባር፣ ስለ ስራ አፈጻጸም፣ ክስ የተባሉት የማያስከስሱኝ መሆኑን ገልጬ መባረሬ አግባብ አለመሆኑን አሳወቁት፡፡ እሱም ‹‹ዋናው ታማኝ መሆን ነው፡፡›› ብሎኝ አረፈው፡፡ ኢህአዴግ ብትሆን አትባረርም ነበር ለማለት ነው፡፡ የሚገርመው ይህ ካድሬ ፌስ ቡክ ላይ እራሱን ፈላስፋ አድርጎ ስለነጻነትና ፍትህ ሲዛላብድ የሚውል መሆኑ ነው፡፡
ከተባረርኩ ከሳምንት በኋላ መሰናዘሪያን ተቀላቀልኩ፡፡ ከወራት በኋላ (ጥቅምት 20) ደግሞ አቶ መለስ የማይወዱት ሰንደቅ አላማ በዓል ተከበረ ተባለ፡፡ በእውኑ ግን ተከብረው የዋሉት ሟቹ ሰውዬ ናቸው፡፡ ጥቅምት 21 መሰናዘሪያ በፊት ገጽ አንድ ጽሁፍ (የእኔው ነው) ይዛ ወጣች፡፡ መለስ የገለበጡትን ሰንደቅ አላማ አንግባ ‹‹እውን ኢህአዴግ ሰንደቅ አላማውን ያከብረዋልን?›› የሚል ነው፡፡ መሰናዘሪያ በሳምንቱ አልተመለሰችም፡፡ አታሚው ኢህአዴጎችን ሰንደቅ አላማው ላይ የተጻፈው ጽሁፍ ስላስቆጣቸው እንዳያትም እንደነገሩት አስታወቀን፡፡ በቃ ዳግም ተባረርኩ ማለት ነው፡፡ አሁን ሌላ ስራ መፈለግ ይጠበቅብኛል፡፡ የኢንሳን ልምድ ሳሳይ ደግሞ በርካቶች ይበረግጋሉ፡፡ በግል ሚዲያው ብጽፍም በቋሚነት ለማሰራት አቅም አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ከገዥው ፓርቲም በላይ ለሚዲያውም ሆነ ለሰራተኛው በዝባዥና ገዳዮች ሆነው አግቻቸዋለሁ፡፡
እንዲህ እንዲህ ስል ለሁለት አመት ያህል ቋሚ ስራ መፈለግ ነበረብኝ፡፡ አራት አመት ያህል ደግሞ ከቤተሰብ ጋር ተቆራርጫለሁ፡፡ 18 አመት ያህል አስተምራኝ፣ ስራ ይዠያለሁ ያልኳትን እናቴን እንዴት ተባርሬያለሁ ልበላት? በፖለቲካ አቋሜ ተባረርኩ ብላት ደግሞ ከዚህ ሁሉ የባሰ ይሆናል፡፡ እናም ዝም ብዬ ስራ ፍለጋ መኳተኑን ያዝኩት፡፡ መነኩሴዋን እናቴን አይኗን ሳላያት አራት አመት ሞላ፡፡ ዛሬ ነገ እሄዳለሁ ስል ቀኑ ነጎደ፡፡ ከዛሬ ነገ አግይቼ አይኗን አያታለሁ ያልኳት እናቴም እንደሳሳኋት፣ እሷም እንደሳሳች ለወዲያው ላንገናኝ ተለያየን፡፡ እናቴ አለፈች፡፡ ያለ አግባብ የተፈናቀልኩበትን ስራ ልይዝ፣ ከያዥኩ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ‹‹ልረጋጋ!›› ላይ ታች ስል ለረዥም ጊዜ የተለየኋት እናቴ አመለጠችኝ፡፡
በእርግጥ እናቴ ወርቅን በባሌስትራ ከሚቀይሩት ወገን አይደለችም፡፡ መሬት አልሸጠችም፡፡ ህዝብን በጠባብ ማንነት አልከፋፈለችም፡፡ አገር አላስገነጠለችም፡፡ ሰንደቁን አላዋረደችም፣ አልዘቀዘቀችም፡፡ የህዝብ መብት አላፈነችም፡፡ የህዝብ ገንዘብ ወደ ውጭ አላሸሸችም፡፡ ንጹሃንን አልገደለችም፣ አላሰረችም፡፡ አላፈናቀለችም፡፡ እናቴ ንጹህ ነች፡፡ የእሷ ነፍስ የገነት ነፍስ ነች፡፡ ሌሎች ግን የሞት ሞታቸውን ሞተዋል፡፡ ትውልድም አጥንታቸውን እንደረገመ ይኖራል፡፡
እኔም እላለሁ፡፡ ሞት ማለት የሞት ሞት ሲሆን ነው፡፡ ይህን እናቴ አልሞተችውም፡፡ ምስኪኗ ወላጅ እናቴ የክብር ሞቷን ስትሞት አሁን ለእኔ የቀረኝ አንዲት እናት ብቻ ናት፡፡ እናት አገር ኢትዮጵያ! አገር ብትኖር ወላጅ እናቴ ተቀብራበታለች፡፡ እኔም አልቅሸበታለሁ፡፡ አዎ! ወላጅ እናት ባትሞት እጅጉን መልካም ነበር፡፡ ከሞተች ግን ምን ይደረጋል? ብቻ እናት አገር አትሙት!
እናቴ ሆይ! አምባገነኖቹ ፊቴ ላይ የደቀኑብኝን አቀበት ለመውጣት ስጥር አንቺ አምልጠሽኛል፡፡ አሁን ብችል እናት አገርን ለማዳን ከሌሎቹ ጋር ሆኜ ጠጠር ለመጣል፣ ጥረቴ ለዚህ ባይበቃ እንኳ የራሴን መብት ለማስከበር፣ ይህንን ደግሞ ባልችል ሆድ አደር ላለመሆን አቀበቱ ላይ ነኝ፡፡ ሞት አይቀርምና አንድ ቀን እንደምሞት አውቀዋለሁ፡፡ የሞት ሞት መሞት ግን አልፈልግም፡፡ ደግሞም ከአንቺ ጋር ያለያየኝን አቀበቱን ወጥቼ ሜዳው ሳልደርስ ባልከተልሽ ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ አንቺም እንደማትቀየሚኝ አውቃለሁ፡፡ እስከዚያው ግን አምላክ ነፍስሽን በገነት ያኑራት!
ብኣዴን እና ኦሕዴድ ምን እየሰሩ ነው? የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው::
የሕወሓት የበላይነት እስከመቼ ?? … መሸዋወድ እስከየት?
ምንሊክ ሳልሳዊ :- የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 22 ድፍን አመታትን አስቆተረ::
በ22 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሆዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱት የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::
የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::
በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው::ምንሊክ ሳልሳዊ
UDJ Demonstration in Dessie – UPDATE ደሴ በህዝቦቿ አንድነት ደምቃለች ። PHOTOS
አዲስ አበባ የሚገኘው የአንድነት ቢሮ በከፍተኛ ሁኔታ በፖሊስ እና በደህንነት ሃይሎች ተከቧል። የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ነው።

ደሴ በህዝቦቿ አንድነት ደምቃለች ። #Ethiopia #Dessie #UDJ #EPRDF #Demonstration
#MillionsVoicesforlandownership
በደሴው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከአስር ሺ በላይ የሚሆን ህዝብ ፍርሃትን ሰብሮ የደሴ ጎዳናዎች ላይ ወጥቷል።
ህዝቡ አሁንም ወደ ሰላማዊ ሰርፉ በመጉረፍ እየተቀላቀለ ነው። መብቱን እና ነጻነትን በማወቅ ጥያቀዎቹን ለማሰማት የአንድነት ፓርቲ ጥሪን ተከትሎ አደባባይ የወጣው ህዝብ በመፈክር እና በዝማሬ ብሶቱን እያሰማ ነው።
“ኢህአዴግ እንዴት ቢንቀን ነው በ30 ብር አበል ነፃነታችንን ለመንጠቅ የሚሞክረው?”
ለሰልፍ ተሳታፊ የቀረበ ጥያቄ
ፖሊስ መንገድ በመዝጋት እየሞከረነው ሆኖም ሰልፈኛው ግን ጥሶ በማለፍ ላይ ነው፡፡
ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ
– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ
የአዲሱ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ተርሚናል የዲዛይን ስራ ተጠናቀቀ
airport new design.jpgአዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ከሁለት ወራት በኋላ ግንባታው የሚጀመረው አዲሱ የኤርፖርት ተርሚናል የዲዛይን ስራ ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት እንዳለው በ225 ሚሊዮን ዶላር የሚገነባው ተርሚናል 22 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል ነው።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ለተርሚናሉ ግንባታ የሚውለው ገንዘብ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ በብድር የተገኘ ነው።
የብድር ስምምነቱ በትላንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ ሲሆን የተርሚናሉ የዲዛይን ስራ ሲ.ፒ.ጂ በተሰኘ የሲንጋፖር ኩባንያ ተዘጋጅቶ ዛሬ ለድርጅቱ ቀርቧል።
ግዙፍና ዘመናዊ ነው የተባለለት የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል የእንግዳ ሳሎን፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽና ኢንተርኔት ካፌን በውስጡ አካቷል።
በኤርፖርቱ በስተምስራቅ በኩል የሚያርፈው ይህ ዘመናዊ ተርሚናል ከሁለት ወራት በኋላ በቻይናው ሲ.ሲ.ሲ.ሲ ኩባንያ የግንባታ ስራው ይጀመራል።
አቶ ወንድም ድርጅቱ ከዚሁ ፕሮጀክት ጋር የሚያያዝ የአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳ የማስፋፊያ ስራም አማከናወኑንና ይህም ቀድሞ 19 አውሮፕላኖችን ብቻ ይይዝ የነበረው የማረፊያ ሜዳ 45 ግዙፍ አውሮፕላኖችን እንዲያስተናግድ አስችሎታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጥንተ-ስቅለቱ በዩጋንዳ ምድር በልዩ ድምቀት እየተከበረ ነው
ጥንተ ስቅለቱ በዩጋንዳ ምድር
በልዩ ድምቀት እየተከበረ ነው።
መንበረ ፓትርያርኩን በሰሜን አሜሪካ ባደርገው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመራው የካምፓላ መካነሠላም መድሐንያለም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የደብሩ ማሕበረ ካህናትና ማህበረ ምዕመናን የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱን ዛሬቅዳሜ መጋቢት ሃያ ሰባት በከፍተኛ መንፈሣዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ነው።በአሁኑ ሠዓት የዕለቱ ቅዳሤ እየተከናወነ ሲሆን የዕለቱ ወንጌል ከማቴዎስ ምዕራፍ ሃያስምንት ተነቦአል።በቀጣይምበዓሉን በተመለከተ የወንጌል ማዕድ በደብሩ አስተዳዳሪቀሲስ ፀሐይ ደስታ ይቀርባል ። ታቦተ ኅጉ ይወጣል ዑደት ይደረጋል ።በመሪጌታ ይሄይስ ዓለሙ መሪነት በደብሩ ፈለገ ህይወት ሰንበት ትቤትመዘምራን ወረብ ይቀርባል።
<ሃሌ ሉያ መርሕ በፍኖት
ሞገሦሙ በፍኖት።
ዝንቱ መስቀል ለአዳም ዘአገብዖ ውስተ ገነት።>
በመጨረሻም ቃለ ምዕዳንና ፀሎተ ቡራኬ ተሠጥቶ የበዓሉ ፍፃሜ እንደሚሆን ከደብሩ ሠበካ ጉባዔ አስተዳደር ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ ጠቁሞአል።
አክሊለሠማያት ዘ መካነሠላም
ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ ጄኔቭ የመጣው የኢህአዴግ ልኡካን
ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራውይህ ቡድን ከሜይ 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካመቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህንአበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግንጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንምአሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውልየለም ብለዋል።በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስበመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱመብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎችእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያንለመረዳት ችለናል።ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውንቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱየገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህንአበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳትፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆችእንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።