Category: Amharic News
ፓርቲዎች ትብብሩን በመቀላቀል የተቃውሞ ጎራውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ ገዥው ፓርቲ ራሱን ለለውጥ እንዲያዘጋጅ ተጠይቋል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር : በትናንትናው ዕለት ህዳር 7/2007 ዓ.ም ሰብሰባ ጠርቶ በገዥው ፓርቲ ደህንነቶችና ፖሊስ የተበተነበት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የኢትዮጵያ ችግር ከአንድ ፓርቲ አቅም በላይ በመሆኑ በትብብሩ ምስረታ ወቅት የነበሩትንና ሌሎቹም ፓርቲዎች ትብብሩን በመቀላቀል የተቃውሞ ጎራውን እንዲያጠናክሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል፡፡
መግለጫው አክሎም አገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውንና የዜግነት ክብራቸውን ለማስመለስ በቀጣይነት ለሚደረገው ሰላማዊ ትግል ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት በጋራ ‹‹በቃን›› ብለው እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በአንጻሩ የፖሊስ ኃይልና ሌሎች አስፈጻሚ አካላት በገዥው ፓርቲ ሴራ ተጠልፈው ከሰላማዊ ዜጎች ጋር እንዳይጋጩና ህገ መንግስቱንም እንዲያከብሩ እንዲሁም ገዥው ፓርቲም ካለበት ፍርሃትና ስጋት ወጥቶ ለለውጥ ዝግጁ እንዲሆን ትብብሩ አሳስቧል፡፡
በሌላ በኩል ‹‹በህዝብ ሀብት የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውለው ገዥውን ፓርቲ ከማገልገል አልፈው በሰላማዊ ትግል የፖለቲካ ኃይሎች ላይ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ›› እንደሚነዙ ያስታወሰው ትብብሩ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ስላደረጉት አወንታዊ አስተዋጽኦ አመስግኗል፡፡ በቀጣይም ለህዝብ በመወገን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በኬንያ ስደተኞችን የማፈኑን ስራ የሚያስቀጥል የደህንነት ቡድን ናይሮቢ ገብቷል::
– በኬንያ ሰላም እያለች ራሷን የምታስተዋውቀው ገዳይ ሴት ተልእኮዋን አልተሳካላትም::
– በኬንያ የሚገኙ ስደተኞች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መረጃውን ያስተላልፉ::
Minilik Salsawi
በኬንያ የሚገኙ ስደተኞችን ለማፈን የሚረዳ የደህንነት ግብረሃይል ወደ ናይሮቢ መጓዙን ከኤምባሲው የደህንነት አታቼ ቅርብ የሆኑ ዲፕሎማቶች ያደረሱኝ መረጃ ይጠቁማል::አዲስ የተላከው ሃይል በናይሮቢ የከተመውን CID ብሎ ራሱን የሚጠራው የወያኔ የስለላ መዋቅር ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሰዎችን በማፈን ወደ ኢትዮጵያ በሰአታት ውስጥ ለመላክ የሚያስችለውን ስራዎች እንደሚሰራ ታውቋል::
የCID አባላት ታፍነው ይወሰዳሉ የተባሉትን አዋዋል ተከታትለው የጨረሱ ሲሆን እንዲሁም በቡድን የሚገናኙ ኢትዮጵያውያንን የሚገናኙበትን ጊዜ እና አከባቢ ጠብቀው ለማፈን ክትትል ላይ መሆናቸው ታውቋል:: ከኤምባሲው የደህንነት አታቼ ቢሮ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው አዳዲስ ስደተኞች አንድ ላይ ሲሆኑ ለማፈስ ዝግጅት ጨርሰዋል ስልካቸውን እንዲቀይሩ እና ከሚያውኩት ሰው ውጪ ከማንም ጋር ናይሮቢ ውስጥ እንዳይደዋወሉ ሲል እየነጠሉ እንዳይወስዷቸው ሌሎቹ ያመልጡናል ብለው ስላሰቡ ለስራው የሚሆኑ ደህንነቶች ከኢትዮጵያ ገብተዋል ብሏል:: እንዲሁም አፈናው ስደተኞቹን በተዋወቁ አዛኝ መሳይ ቆነጃጅት ቀጠሮ ይፈጸማል የሚል ተጨማሪ መረጃ ተገኝቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በናይሮቢ ስደተኞችን እያጠመደች በተመረዘ ምግብ የምትገለው እና ራሷን ሰላ እያለች የምትጠራው ቆንጆ የተሰማራችበት ተልእኮ እንዳልተሳካ ታውቋል::በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ እንደ ዲፕሎማት የተመዘገበቸው እና ለአምባሳደሩና ለደህንነት አታቼው ቅርብ እንደሆነች የምትታወቀው እንዲሁን ከCID አባላት ጋር በጋራ እንደምትሰራ የተደረሰባት ይህች ግለሰብ ከዚህ ቀደም በሚሊዮን ሹሩቤ ላይ የተጠቀመችውን ቃላቶች ልረዳህ እችላለሁ የፈለከው አደርግልሃለሁ ከማለት ጀምሮ ማግባት እና መውለድ ስለምፈልግ ከእንዳተ አይነት እውቀት ካለው ሰው ጋር …አንተን ለማኖርም ሆነ ለማዝናናት እችላለሁ ና ወደ ቤቴ ልውሰድህ …ወዘተ የሚል የማጃጃያ ዘዴ እና ውድ ግብዣዎችን በማድረግ አንድን ወጣት ለማጥመድ ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካላት እንደቀረ የኤምባሲው ምንጮች ጠቁመዋል::ግለሰቧ ቋሚ ስልክ ቁጥር የሌላት ሲሆን በምትፈለግበት ሰአት የማትገኝ ድንገት ደውላ ለግብዣ የምታመቻች ናት::እንዲሁም በደወለችው ቁጥር ተመልሶ ቢደወል ስልኩ ዝግ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል::#ምንሊክሳልሳዊ
ከኢንጂነር ኃይሉ ሻወል ተጽዕኖ ያልወጣው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ጠቅላላ ጉባኤ እና አሳፋሪው ድራማ (MUST READ)
የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት /መአሕድ/ በ1984 ዓ.ም ተመስርቶ ገዢው ፖርቲ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላና በደቡብ ክልሎች በሚኖሩ በአማራ ብሔረሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን የግፍ ጭፍጨፋና የመብት ረገጣ ለመታገል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕግ የበላይነትን እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን ዕውን ለማድረግ ሰንቆ በተነሳው አላማ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እንቅስቃሴ በማድረጉ የፖርቲው መስራችና እውቁ የሕክምና ምሁር ኘሮፌሰር አስራት ወልደየስ ደ/ብርሃን ከተማ በጠሩት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ወደ ውህኒ ወርደው በግፍ ሕይወታቸው ያለፈ ቢሆንም የፖርቲውን ተቀባይነትና እንቅ ቃሴ ገዥው ፖርቲ ኢህአዴግ የሚገደብበት አቅም አላገኘም ነበር፡፡
መአህድ ይዞት በተነሳው አገራዊ አላማ ከብሔር ድርጅትነት ራሱን በማሳደግ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ የሚለውን ስያሜ በመያዝ በ1995 ዓ.ም ሕብረ ብሔራዊነቱን አውጆ እስከ 1996 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከ1.2ሚ በላይ አባላት ያፈራና በርካታ ጽ/ቤቶችን በሀገሪቱ ክፍሎች በመክፈት ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡
መኢአድ በ1997 ዓ.ም ከሌሎች 3 /ሶስት/ ፖርቲዎች ጋር በመሆን ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ /ቅንጅት/ ፖርቲን በመመስረት ለምርጫ 97 የመኢአድ መሰረቱን ተጠቅሞ ቅንጅት ባደረገው እንቅስቄሴ ለተገኘው የፖለቲካ ተሳትፎና የምርጫ ውጤት መኢአድ የአንበሳውን ድርሻ መያዙ የትናንቱ የታሪክ እውነታ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የ97 ምርጫ ውጤትን ተከትሎ ገዥው ፖርቲ በወሰደው ኢዲሞክራሲያዊ የምርጫ ውጤት ቅልበሳ የተቆጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ “ድምጻችን ይከበር” በማለት በየአደባባዩ ለወጣው ሰላማዊ ሰልፈኛ በታጣቂ ኃይሎች የተወሰደው ያልተመጣጠነ እርምጃ ብልጭ ብሎ የነበረውን የዲሞክራሲ ጭላንጭል ወደነበረበት ጨለማ በመቀልበስ የቅንጅት አመራሮችን ወደ ወህኒ ቤት በመወርወር ካሰረና ካስፈረደ በኋላ በተለመደ ድራማው ይቅርታ እንዲጠይቁ በማድረግ ከእስር እንዲለቀቁ የተደረጉት የቅንጅት አመራሮች በእስር ቤት እያሉ በተፈጠረ አለመግባባት ከወህኒ ቤት ከወጡ በኋላም በመቀጠሉ ጉዳዩን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት አንድም ሙከራ ሳይደረግ ወደ አሜሪካና አውሮፖ በቡድን በመንቀሳቀስ ሁሉም የራሳቸውን ቡድን በማጠናከር አለመግባባቱን እንዲባባስ አድርገው በዚህ ምክንያት አብዛኛው የቅንጅት አመራር አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ የሚል ፖርቲ መስርተው ለመንቀሳቀስ የቻሉ ሲሆን ጥቂት የመአአድ አመራሮች ወደቀድሞው ፖርቲያቸው መኢአድ በመመለስ ከሰኔ 14-15 2000 ዓ.ም የፖርቲውን የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ ኢንጅነሩን ኘሬዝዳንት በማድረግ የተናጠል ጉዞውን ሲጀምሩ የፖርቲውን የውድቀት ቁልቁለት “ሀ” ብለው የጀመሩ ሲሆን ለዚህ ውሣኔና አካሄድ ዋና ምክንያታቸው ደግሞ ምንም እንኳ ቅንጅት የሚለውን ስም ለማግኘት ለሌላ አካል የተሰጠ በመሆኑና ባያገኙትም ከቀስተ ደመና ፖርቲና ከአድሊ ፖርቲ ጋር አዲስ ፖርቲ መስርተው ለመቀጠል በአዲሱ ፖርቲ ውስጥ ቦታ አናገኝም ከሚለው ስጋታቸው በተጨማሪ በመኢአድ ፖርቲ ውስጥ በተለያዩ ደረጃ ተቀምጠው የሚያገኙት ጥቅማጥቅም ይቀርብናል የሚለው ትልቁ ምክንያታቸው እንደነበር በቀላሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የመኢአድ አመራሮች በተናጠል የመስራትና የመጓዝ ልምዳቸው ከራስ ጥቅም ጋር የሚያያዝ ሲሆን ለ2002 ምርጫ ከመድረክ ጋር አብሮ ለመስራትም ሆነ የመድረኩ አባል ለመሆን አልመፈለግና የፖለቲካ ፖርቲዎችን የምርጫ ስነ ምግባር ለመፈረም ኢህአዲግ ከአጋሮቹ ጋር በመራው ውይይት ላይ የመኢአድ ተሳትፎና የፖርቲው ኘሬዝዳንት ኢንጅነር ኃይሉሻወል ከኢህአዲግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር እጅ ለእጅ መጨባበጥ የፖርቲውን ትልቁን የውድቀት ርምጃ ያበሰሩ ሲሆን በአንዳንድ ግለሰብ አስተያየትም ኢንጅነሩ ካላቸው የንግድ ተቋምና ባለሀብትነት አኪያ “ልማታዊ ባለሀብት” አስብሎ ያስጠረጠራቸው እና በምርጫውም ላይ በገጠርም ሆነ በከተማ መኢአድ ላስመዘገበው ዝቅተኛ የድምፅ ቁጥር ዋንኛ ምክንያቱ ይሄው ሀቅ መሆኑ አጠያያቂ አልነበረም፡፡
የፖርቲው ጠቅላላ የውጤት መቀነስም ሆነ ኘሬዝዳንቱ በተወዳደሩበት የምርጫ ክልል እንኳ በግላቸው ያገኙት ዝቅተኛ የድምፅ መጠን የፖርቲውን እድገት እንደ ካሮት ወደታች መሔድ ከማሳየቱም በተጨማሪ የፖርቲው ኘሬዝዳንት ግንቦት 19/2002 ዓ.ም ከፖርቲ ኘሬዝዳንትነት ለቅቄያለሁ የሚለው የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባት የዚሁ የምርጫ ውጤት ዝቅተኛነት መሆኑን ከመልቀቂያ ደብዳቤው ላይ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በኋላ ፖርቲው ያለቅደመ ሁኔታ ከአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ እንዲሁም ከብርሃን ፖርቲ ጋር ለመዋሀድ የሶስትእዮሽ ድርድር በመፍጠር በአብዛኛው ውይይት የተስማሙ ቢሆንም ከታህሳስ 16-18 ለሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ኘሬዝዳንቱ ወደ ፖርቲው በፍቃዳቸው በመመለስ ጉባኤውን አድርገን በጉባኤው እስከምናስወስን ድረስ የ3 /ሶስትዮሽ/ ድርድሩ ይቋረጥ የሚል ትዕዛዝ በመስጠታቸውና የሳቸውን ትዕዛዝ የሚቃወም አመራር ባለመኖሩ የውህደት ድርድሩ ተቋረጠ፡፡
ከታህሳስ 16-17/2003 በተደረገው የጠቅላላ ጉባኤ ላይም የፖርቲው ኘሬዝዳንት ስልጣን ይለቃሉ ተብሎ በመጠበቁ የኘሬዝዳንቱን ስልጣን የሚፈልጉ ሁለት ቡድኖች የራሳቸውን ቅስቀሳ /Lobbing/ በማጠናከራቸው ጉባኤው ጤናማ ሆኖ መቀጠል ባለመቻሉ የጉባኤው አባላት ኢንጅነር ኃይሉ ለ2/ሁለት/ ዓመት በኘሬዝዳንትነት እንዲቀጥሉ ሲያደርጋቸው እኔን በኘሬዝዳንትነት ከመረጣችሁ ተቀዳሚ ኘሬዝዳንት ሆኖ የሚያግዘኝ አቶ ያዕቆብ ልኬ በመሆኑ የእኔንም ጥቆማ አፅድቁልኝ በማለት ለጠቅላላ ጉባኤው ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጣቸውና የኢንጅነሩን ቃል በጉባኤ ተቃውሞ ማቅረብ የተለመደ ባለመሆኑ ጉባኤተኛው አፀደቀላቸው፡፡
ይሁን እንጂ በተቃራኒው የኘሬዝዳንቱ ቦታ ይፈልጉ የነበሩ ቡድኖች የአቶ ያዕቆብ ልኬ ተቀዳሚ ኘሬዝዳንት ሆኖ መመረጥ ተቃውሞ ባያቀርቡም ውስጣቸው ደስተኛ አለመሆናቸው በግልጽ ይንፀባረቅ ነበር፡፡
ታህሳስ 20/2003 ዓ.ም የስራ አስፈፃሚውን የስራ ድርሻ ኘሬዝዳንቱ በራሳቸው ፍላጎት ደልድለው ሲያበቁ ቀደም ሲል በአቶ ማሙሸት አማረ ተይዞ የነበረው የፖርቲው ዋና ፀሐፊ ለአቶ ተስፋዬ ታሪኩ መሰጠቱን ተከትሎ በእነ አቶ ማሙሸት አማረ እና በኢንጅነር ኃይሉ ሻወል መካከል የነበረው የአባትና ልጅ እንዲሁም የአካባቢዋ ገመድ ትስስር ተበጥሶ ወደለየለት አጋች ታጋች ድራማ በመሸጋገሩ የፖርቲው ሌላው ዙር የውድቀት ምዕራፍ ተከፈተ፡፡
ሐምሌ 30/2003 ዓ.ም መኢአድ በእየሩሳሌም ሆቴል በጠራው የማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የእነ አቶ ማሙሸት አማረ ቡድን ከፖርቲው እንዲባረሩ የተወሰነ ሲሆን ይህ ምክር ቤት ሌላ ታሪካዊ ውሣኔ ወሰነ፡፡ ይኸውም ከዚህ በፊት የነበረው የፖርቲው መተዳደሪያ ደንብ ለኘሬዝዳንቱ ሰፊ መብት ሰጥቶ የነበረ ሲሆን ከታህሳስ 14-15 በተጠራው የጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ደንቡን እንዲሻሻል የማዕከላዊ ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የኘሬዝዳንቱን ስልጣን በመቀነስ ለፖርቲው ማዕከላዊ ምክር ቤትና ለስራ አስፈፃሚው ቀንሶ በመሰጠቱ በኘሬዝዳንቱ እና በአብላጫው 10 /አስሩ/ ስራ አስፈፃሚ መካከል ሌላ ዙር አለመግባባት ተፈጥሮ 10 /አስር/ ስራ አስፈፃሚ በማገድ ወደ ጽ/ቤት እንዳይገቡ በመደረጉ የአባላት መከፋፈል ፖርቲውን በውድቀት ቁልቁለት እያንደረደረው በመሔዱ እና የእነ አቶ ማሙሸት አማረ ቡድንም ሆነ የእነ አቶ አሰፋ ሀብተወልድ ቡድን በየራሳቸው የያዙት አባላትና ደጋፊ ኢንጅነሩ ጽ/ቤቱን ይዘው ከቀሩት አባላት በእጅጉ የገዘፈ በመሆኑ እና የመጨረሻ እልባት ለማግኘት የጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ለምርጫ ቦርድ ከሁለቱም ቡድኖች በቀረበው ጥያቄ መሠረት ፖርቲው የጠቅላላ ጉባኤውን በመጥራት ሁሉም ቡድኖች በተገኙበት ጉባኤው የሚሰጠውን ውሣኔ እንዲያሳውቅ ቦርዱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የፖርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም የተጠራ ቢሆንም የእነ አቶ ማሙሸት አማረ ቡድንም ሆነ የእነ አቶ አሰፋ ሐብተወልድ/አብላጫው/ ስራ አስፈፃሚ በጉባኤ ተገኝቶ የታገደበትን እና የተከሰሰበትን ጉዳይ ለማስረዳት እና የመከላከል ሕገ መንግስታዊ መብቱ ሳይከበር ወደ ጉባኤው እንዳይገባ ተከልክሎ በጠቅላላ ጉባኤው እንድባረሩ ሲወሰን ጉባኤው የሁለቱም ቡድኖች ሐሳብ ለመስማት በጉባኤው ላይ እንድገኙ አለማድረጉ የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ በኘሬዝዳንቱ ጫና ስር የወደቀ ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ የሚያስፈልገው አይሆንም፡፡
በዚህ ጉባኤም የፖርቲው ኘሬዝዳንት ከኘሬዝዳንትነት ለቀው የፖርቲውን መተዳደሪያ ደንብ በማሻሻል የሌለ እና ያልተለመደ የፖርቲው የበላይ ጠበቂ የሚል አንቀጽ በመጨመር አቶ አበባው መሐሪ ኘሬዝዳንት በማድረግ ርሳቸው የበላይ ጠባቂ በመሆን ፖርቲውን ቤታቸው ሆነው ለመቆጣጠር ሪሞቱን አዘጋጁ፡፡
የዚህን ጠቅላላ ጉባኤ ውጤት እና አዲሱን የአመራር አመራረጥ ያልተቀበለው መሆኑን ቦርዱ ወዲያው ቢያሳውቅም ለአመት ያህል ይህ አመራር ፖርቲውን እያስተዳደረ ከቦርዱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች የሚፃፃፋቸው ደብዳቤዎች እና የነበሩ የስራ ግንኙነቶች ሲታዩ ፖርቲው ሕጋዊ ሆኖ ቆይቷል ያሰኛል፡፡
ቀድሞ የተጀመረው የመኢአድ እና የአንድነት የውህደት ድርድር በእነ አቶ አበባው መሀሪ ስምምነት ላይ ሲደርስ እና ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት ሲዘጋጁ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የቆየ ገመዱን ለመምዘዝ ሲቻኮል እና የሁለቱን ፖርቲዎች የውህደት ሂደት ለማደናቀፈ የተደረገውን ሴራ ሲታይ የገዢው ፖርቲ ቀጭን ትዕዛዝ የለም ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡
ይህን ተከትሎ ውህደቱን በመቃወም “መኢአድ ተሸጠ” በማለት በእነ አቶ ማሙሸት አማረ የተሰጠው መግለጫ ሲታይና የመኢአድ ከጥቅምት 28-29 የጠቅላላ ጉባኤ መጠራትና ወደ ፖርቲው ጽ/ቤት ኢንጅነር ኃይሉሻወል ሲገቡ በእነ አቶ ማሙሸት አማረ ታጅበውና ተደግፈው ወደ መድረኩ ሲወጡ ላየ ፖለቲከኛ የትናንቱ የጋዜጣ መዝለፍለፍና እስከ ፍ/ቤት የደረሰ መካሰስ በምን አይነት ሽማግሌ እርቅ እንደወረደ ግልጽ ባይሆንም ቀድሞ መኢአድ ተሸጠ ብለው በጋዜጣ መግለጫ ያወጡትን የእነ ማሙሸትን ቡድን ያስማማ የጋራ ፍላጎት አጀንዳ ሆኖ ከመታየቱም ሌላ የ3/ሶስተኛ/ እጅ ስላለመናሩስ በምን እንዳንጠራጠር ያደርጋል፡፡ የፖለቲካ መሄጃና መምጫው የማይታወቅ በመሆኑ የመኢአድን ከአንድነት ጋር መዋሀድ ከማይፈልጉት ኃይሎች ውስጥ ኢንጅነር ኃይሉና እነ ማመሸት ብሎም ኢህአዲግ በመሆናቸው ሶስቱን አካሎች ያስተሳሰራቸውን ድራማ እና ታሪክ ወደፊት እስከሚያመጣው ድረስ ለጊዜው መተው የተሻለ ይሆንና የጥቅምት 28-29 ጠቅላላ ጉባኤ ሂደትና ውጤት ላይ ማተኮርን እመርጣለሁ፡፡
ጥቅምት 28/2007 የፖርቲው ማዕከላዊ ም/ቤት ስብሰባ ስለነበር የጉባኤው አባላት /የም/ቤቱ ምዕለተ ጉባኤ በመሟላቱ ስብሰባውን ኢንጅነሩ እንዲመሩት ተደርጐ፡፡ የእነ አቶ ማሙሸት ቡድንና የእነ አቶ አሰፋ ሀብተወለድ ቡድን ታግዶ የቆየበትን አሰራር ፖርቲው በሪፖርት ከገለፀ በኋላ ም/ቤቱ እንዲወያይበትና የውሣኔ ሀሣብ በማሳለፍ በቀጣዩ ቀን 29/02/07 ለጠቅላላ ጉባኤ እንዲቀርብ በተጀመረው ውይይት መሰረት የም/ቤቱ አካሄድ ኢንጅነሩ የጠበቁት ባለመሆኑ እና እነ አቶ ማሙሸትን ለማባረር የተዘጋጀ በመምሰሉ በዚህ ሁኔታ ውይይቱን ማስቀጠሉ ለቀጣይ ቀን ለጠቅላላ ጉባኤው የሚቀርብ የውሣኔ ሀሳብ ላይ ደስተኛ ያልሆኑት ኢንጅነሩ በለመዱት ተጽኖ ፈጣሪነት ከሰዓቱ መምሸት አኳያ እንደምክናያት ተጠቅመው ይሔ አጀንዳ ለነገ ከጠቅላላ ጉባኤው ጋር ውሣኔ ይሰጥበት በማለት አካሄዱን ቀይረው በይደር አሳለፋት፡፡
አዳሩን የገባው የጠቅላላ ጉባኤ አባላት እነ ማሙሸት እንደመለሱ እንዲወሰን ቅስቀሳ /Lobbing/ ሲደረግ ያደረ ሲሆን በ29/03/07 የጠቅላላ ጉባኤው ምለዕተ ጉባኤ የተሟላ በመሆኑ የእነ አቶ ማሙሸት አጀንዳ ሲከፈት የጉባኤው አባላት 3 /ሶስት/ ሀሣቦችን አቅርቦ ነበር፡፡ እነዚህም
1. እነ አቶ ማሙሸት ከዲሲኘሊን ውጭ የተንቀሳቀሱ ስለሆነ ከፖርቲ አባልነታቸው ይባረሩ፡፡
2. ፖርቲው ካለበት ችግርና እነሱም ለፖርቲው ከሰጡት አገልግሎት አንፃር በይቅርታ ታልፈው በአባልነት ይቀጥሉ፡፡
3. ወደ አመራርነት ሳይመጡ በአባልነት ለ2 /ሁለት/ ዓመት ይቆዩ የሚሉ ሲሆን በአብዛኛው በ3ኛው ውሣኔ ላይ በመስማማት ጉባኤተኛው በጭብጨባ ያፀደቁት ሲሆን ኢንጂነሩ ጉባኤውን በለመዱት አካሄድ ውሳኔውን የሻሩት በተለመደው ተጽኖ ፈጠርነታቸውን በመድገም ወደ ፖርቲው መመላለሳቸውን ምክንያት በማድረግ የማዕከላዊ ም/ቤት አባል እንደሆኑ በማድረግ የተለመደ ጫናቸውን በጉባኤው ላይ ሲያሳርፉ አንዳንድ የጉባኤው አባላትም ሰብስበውን እየረገጡ የሄዱ ቢሆንም አብዛኛው ጉባኤትኛ ከዚህ በላይ መከራከሩና ኢንጅነሩን ማሸነፍ ያልተለመደ በመሆኑ በሳቸው ተጽኖ ስር ጉባኤው ወደቀ፡፡
ጥቅምት 30/2007 የጠቅላላ ጉባኤው አባላት የተበተነና ቀጣዩ ኘሮግራም የማዕከላዊ ም/ቤት አባላት ስብሰባ የስራ አስፈፃሚውን የስራ ምደባ ማድረግ ስለነበር ኢንጂነሩ አቶ ማሙሸት አማረን ኘሬዝዳንት አድርገው ስልጣናቸውን አውርሰዋል፡፡
እነ ማሙሸትም በአካባቢያቸው ተወላጆች ታጅበው አመራሩን ይዘው እንዲቀጥሉ ሊያስማማቸው የሚችለው አካል ማን ሲሆን ይችላል የሚለውን ጥያቄ በሂደት የምንመለሰው ቢሆንም የጉባኤው ውሳኔ በኢንጅነሩ ተሽሮ ፖርቲው በእነ ማሙሸት አማረ እጅ መግባቱ በርካታ አባላቱንና አመራሩን ከማስቆጣት አልፎ በዚህ አመራር ስር ላለመቀጠል እና ሌሎች አማራጮችን ለመውለድ የተዘጋጀውን ኃይል ስናየው የፖርቲውን የመጨረሻ የውድቀት ምዕራፍ ያስተናጋደ ታሪካዊ ሂደት ሆኖ መኢአድን እስካሁን ከገጠመው የመከፋፈልና የአባላት ድርቀት የዚህ ጉባኤ ውጤት ያመጣው ጣጣ የሶስተኛውን አካል ተሳትፎ ያጐላ በመሆኑ እስካሁን ለፖርቲው የተከፈለውን ዋጋ የሸጠ የኢንጁነር ኃይሉ አሳዛኙ ድራማ ሆኖ በታሪክ ይመዘገባል፡፡
(በጌታቸው ባያፈርስ)
በ9ኙ ፓርቲዎች ተጠርቶ የነበረው የአደባባይ ስብሰባ ፖሊስ በኃይል በትኖታል! photos

ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን እየጣረ ነው፡፡የስብሰባው አዘጋጆች አንሄድም ብለው ሜዳው ላይ ይገኛሉ፡፡
#Ethiopia #Blueparty #Election2007 #NegereEthiopia #MinilikSalsawi
9ኙ ፓርቲዎች የጠሩት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በኃይል ተበተበ
ዛሬ ህዳር 7/2007 ዓ.ም 9ኙ ፓርቲዎች በትብብር የጠሩት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በፖሊስና በደህንነት ኃይሎች ተበትኗል፡፡ ፓርቲዎቹ ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ያሳወቁ ሲሆን የፓርቲዎቹ አመራሮች ለፖሊስና ደህንነቶች ቢያሳዩም ‹‹የምናውቀው ነገር የለም፣ እኛ ታዘን ነው፡፡ ከፈለጋችሁ አለቆቻችን ሂዳችሁ አናግሩ፡፡›› በማለት ለስብሰባው የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ስብሰባው ሊደረግበት ከታሰበው ሜዳ እንዲነሱ አድርገዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮችና በስብሰባው ለመሳተፍ ወደቦታው ያቀኑ አካላት ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም ፖሊስ ግን ህዝቡን በኃይል በትኗል፡፡
ፖሊሶች የፓርቲውን አመራሮች በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ #የቤለዬሩ_ሰልፍ Morning Update
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ስብሰባው እንዳይደረግ የሚከለክሉት ፖሊሶች ለምን ትከለክላላችሁ በሚል ለሚነሳው ጥያቄ እነሱ የሚሰጡት መልስ አናውቅም፣ ታዘን ነው የሚል ነው፡፡ የፓርቲዎቹ አመራሮች ስብሰባው እውቅያ ያገኘበትን ደብዳቤ ቢያሳዩዋቸውም እኛ ስለጉዳዩ አናውቅም ነው ያሉት፡፡
ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን እየጣረ ነው፡፡ፖሊስ የአደባባይ ስብሰባ በኃይል ለማገድ እየወጣ ነው፡፡ ሞንታርቮና ጀኔሬተር የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች በኃይል አንስተዋል፡፡ የስብሰባው አዘጋጆች አንሄድም ብለው ሜዳው ላይ ይገኛሉ፡፡ ለስብሰባው የመጣው ህዝብ ሁኔታውን ለመቅረጽ እንዳይሞክር እየጠደረገ ነው፡፡ በአንጻሩ ግን ደህንነቶች ህዝቡን እየቀረጹ ይገኛሉ፡፡
ሞት ራስዋ ትደፋ እንጂ ኃይሉ አይሞትም
ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ እጁ ወርቅ ሆኖ አፉ ወለላ አንደበቱ ርቱዕ እጅጉን የሰላ አ ቋሙ ጥብቅ አንዴ እማይላላ አግዜር እያለለት የዘለዓለም ከለላ የኃይሉ ሞት ወሬ የለዉም አንዳች መላ። ሞት ራሷ እልም ብላ ትሙት ኃይሉ አይሞትም ዝም ብላችሁ አትሙት። በረከተ መርገምን እያድበለበለልኝ …
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ታሰሩ = ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ታሰሩ
#Ethiopia #Blueparty #NegereEthiopia #MinilikSalsawi
– በቅስቀሳ ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እየታሰሩ ነው
– የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ
– ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል
በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ለእሁዱ የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የታሰቱትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ፡፡
በቅስቀሳ ወቅት የነበሩት የሰማያዊ አባላትና አመራሮች መያዛቸውን ተከትሎ የእሁዱን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ለስበስባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ያሳወቁበትን ህጋዊ ደብዳቤ በመያዝ የአባላቱና አመራሩ እስራት ህገ ወጥ መሆኑን ለማስረዳትና አባላቱን ለመጠየቅ ወደ አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ የፋይንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወሮታው ዋሴ እና የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር እሁድ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ለሚያደርገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ታሰሩ፡፡የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነው አቶ ዮሴፍ ተሻገር እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆነው ሲሳይ በዳኔ መገናኛ አካባቢ ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ታስረዋል፡፡
በተመሳሳይ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሳምሶን ግዛቸው እንዲሁም የአዲስ አበባ ዞን ምክትል ሰብሳቢና ህዝብ ግንኙነት አቶ ማቲያስ መኩሪያ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት በፖሊስ ተይዘው አራዳ ፖሊስ መምሪያ ታስረዋል፡፡በሌሎች የአዲስ አበባ ክፍሎች ቅስቀሳ ላይ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች በፖሊስ ወከባ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ህዳር 7/2007 ዓ.ም ቤልየር ሜዳ ላይ የሚደረገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ የሚያስተብብረው ሲሆን በአንድ ወር የሚደረጉትን ሌሎቹን መርሃ ግብሮች 9ኙ ፓርቲዎች በየተራ እንደሚያሰተብብሩ መስማማታቸው ይታወቃል፡፡
9ኙ ፓርቲዎች በትብብር ለሚያዘጋጁትና ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያስተባብረው የህዳር 7/2007 ዓ.ም. የሚደረገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ሲቀሰቅሱ እና ታሳሪዎቹን ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በሄዱበት ወቅት የታሰሩት 6 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ፡፡
በሌላ በኩል ለነገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በአብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍሎች ስኬታማ ቅስቀሳ መደረጉን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን፤ ህዝቡ በአደባባይ ስብሰባው እንዲሳተፍ በስልክ (በመደወልም ሆነ መልዕክት በመላክ)፣ በማህበራዊ ድህረገጽና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የበኩላቸውን እንዲያደርጉ፣ ለአንድ ወሩም መርሃ ግብርም ሆነ በሌላ የትግሉ አካል ሁለገብ ድጋፍና ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ጥሪ አድርጓል፡፡
ኦሮሞነት ዘረኝነት አይደለም
ኦሮሞነት ዘረኝነት አይደለም — ግርማ ካሳ
======================
በኦሮሞዉና በአማርኛ ተናገሪው መካከል ጥላቻ እንዲሰርጽ ተብሎ አንድ የተጻፈ መርዛማ መጽሐፍ አለ። የቡርቃ ዝምታ የሚባል መጽሃፍ። የዚህ መጽሀፍ ደራሱ አቶ ተስፋዬ ገበረ አብ ይባላሉ። የሕወሃት/ኢሓአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ጊዜ የጻፉት መጽሀፍ ነው። በቅርቡ “በሞጋሳ ኦሮሞ ሆኛለሁ” ሲሉ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል። ምን ያህል የሞጋሳ ሚስጠር እንደገባቸው ግን አላውቅም።
ከአራት መቶ አመታት በፊት፣ የኦሮሞ ጦረኞች አንድ አካባቢን በሚቆጣጠሩና በሚማርኩ ጊዜ፣ አንድ የሚያደርጉት ሥርዓት ነበር። የጎሳው ሽማግሌዎች ከተማዋ ሲገቡ ከዚያ ጊዜ ጀመሮ ያቺ ክከተማ ኦሮሞ ትሆናለች። በከተማዋም የሚኖረው ህዝብ፣ በሽማግሌዎቹ ፊት ያልፋል። በዘሩ ከሌላ ወገን ቢሆንም፣ በአለቃዉ ያለፈ ሰው ሁሉ ኦሮሞ ይሆናል። ይህ ስርአት ሞጋሳ ይባላል። ኦሮሞነት ከዘር ጋር ግንኙንት እንደሌለው የሚያስተምር የኦሮሞ ባህል !
ሞጋሳ የሚያሠባስብ ነው። አንድ የሚያደርግ ነው። በመሆኑም ኦሮሞነት አንድነት ነው። ኦሮሞነት ሌላውን እንደ እራስ አድርጎ ማቀፍ ነው። ኦሮሞነት ሌላውን ማሳነሳ፣ ሌላውን ማባረር፣ ሌላውን መጥላት አይደለም።
እርግጥ ነው አንዳንድ አክራሪ የኦሮሞ ብሄረተኞች፣ በኦሮሞነት ስም ሌሎችን የመጥላት ፖለቲካ ያራምዳሉ። ከሌሎች የመለየት፣ ሌሎችን የማግለል፣ የመከፋፈል፣ የጥላቻ ፖለቲካ ያራግባሉ። የኦሮሞ ባህል ግን ፣ የሞጋሳ ባህል ግን ፣ አንድ የሚያደርግ ባህል ነው። እነርሱ ከሚናገሩትና ከሚረጩት መርዝ ጋር ግንኙነት የለውም።
ሌላው በአማርኛም ሳይቀር የምንጠቀማት ቃል አለች። ጉዲፈቻ። ጉዲፈቻ ማለት የሌላውን ሰው ልጅ እንደ ራስ አድርጎ ማሳደግ ማለት ነው። ጉዲፋቻ የሚለውን ቃል በአማራኛ መጠቀማችን በራሱ የሚያሳየው፣ የሌላውን ልጅ እንደራስ አድርጎ የማቀፍ ባህል፣ በኦሮሞው ማህበረሰብ ዉስጥ ምንም ያህል ስር የሰደደ ባህል እንደሆነ ነው። የኦሮሞው ማህበረሰብ፣ ትግሬ ይሁኑ አማራ፣ ጉራጌ ይሁኑ ከፊቾ ፣ ከሌላ ዘር የሆኑትን እንደራሱ አድርጉ የሚያሳድግ ማህበረስብ ነው። ከሌላው ጋር የተዛመደ፣ የተዋለደ፣ የዘረኝነት ነገር የሌለበት ማሀብረሰብ ነው።
ላለፉት 23 አመታት ግን በሽታ ገባ። የኦሮሞ ማህበረሰብን ከሌላው ለማጣላት ብዙ ተሞከረ። የባለስልጣናቱ ካድሬዎች ሆን ብለው በኦሮሞው እና ኦሮሞ ባልሆነው ማህብረሰብ መካከል ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ቀን እና ሌሊት መስራት ጀመሩ።
ለአማርኛው ተናጋሪዎች “ ኦሮሞዎቹ ዘረኞች ናቸው። አማርኛን ይጠላሉ። ይጨርሷቹሃል። ያርዱዋቹኋል” የሚል እድምታ ያለው መልእክት በጎን ያስተላልፋሉ። ለኦሮሞ ደግሞ ” እነርሱ ነፍጠኞች ናቸው። በቋንቋህ እንዳትናገር ሊያደርጉህ ነው። ሊያጠፉህ ነው። የድሮው የአማራ የበላይነትን ሊያመጡብህ ነው። አሃዳዊ ስርዓት ሊጭኑብህ ነው” ይሉታል። አማርኛ ተናጋሪዎች በአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ላይ ፣ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ደግሞ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ጥርጥሬ እንዲያድርባቸውና እና እንዳይግባቡ እያደርጓቸው ነው። ኦሮሞዎች አማርኛ እንዳይማሩ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች ደግሞ አማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ተደርጎ፣ የአንድ አገር ልጆች ሆነን እንዳንግባባ ተደርገናል። መነጋገር ስላልቻልን፣ አንዳንች ስለአንዳንች የሚነጉን የአገዛዙ ካድሬውዎችና ዉጭ ያሉ አንዳንድ አክራሪዎች ናቸው። ነገሮችን እየጠመዘዙ ስለሚነግሩንም እርስ በርስ እየታመስን ነው።
መንቃት ይኖርብናል። እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በኛ ላይ የሽረቡትን ወጥመድ ማፈራረስ አለብን። የኦሮሞ ባህል፣ የኦህደድ ካድሬዎች ወይንም ዉጭ ያሉ አንዳንድ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ግን በጥላቻ የተሞሉ አክራሪዎች እንደሚነግሩን አይደለም። ኦሮሞነት ዘረኝነት አይደለም። ኦሮሞነት አንድነት ነው። ኦሮሞነት ሌሎች እንደ ራሱ አድርጎ መቆጠር ነው። ኦሮሞነት የሚለያይ ሳይሆን የሚያሰባስብ ነው። የኦሮሞነት ፖለቲካ የጉዲፈቻና የሞጋሳ ፖለቲካ ነው።
የኦሮሞ ማህበረሰብ ከምንም በላይ ፣ በበሃሉ የሚመቸውና የሚቀበለው የአንድነትን እና የፍቅርን ፖለቲክ ነው። “እገሌ ከዚህ ዘር ስለሆነ፣ ወይንም ይሄ ቋንቋ ስለሚናገር ከአገራችን ይዉጣ። ይሄ ምድር የኦሮሞ ብቻ ነው ….ወዘተረፈ” የሚባለው አክራሪዎችና ካድሬዎች የሚረጩት እንጂ, ከሕዝቡ የሚመጣ አይደለም። የኦሮሞ ማህበረሰብ በባህሉ ሌላውን የሚቀበል፣ እንደራሱ አድርጎ የሚያኖርና የሚያሳድግ ነው። ለዚህም ነው ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንድነት ፓርቲ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነቱ እየጨመረ የመጣው።
አፋን ኦሮሞ የማናውቅ ካለን፣ እንማር። አማርኛ የማናውቅ ካለን፣ አማርኛ እንማር፡ ብዙ ቋንቋ ማውቅ በረክት ነው። ሌላ ቋንቋ መማር አያሳንሰንም። እንደ ወንድማማቾች፣ ለመግባባት፣ ለመነጋገር፣ አብረን አገራችንን ለማሳደግ ቋንቋ አለማወቃችን እንቃፋት ሊሆንብን አይገባም።
የወያኔው መንግስት ፖሊስ ጣቢያዎችን ለማስገንባት ስፖንሰር እየጠየቀ ነው::

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፖሊስ ጣቢያዎችን እንዲሰሩ ተጠየቁ Minilik Salsawi
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በየ አካባቢያቸው ለሚሰሩት አዳዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በየ አካባቢው የሚገኙት የፖሊስ ጣቢያዎች ነዋሪዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ በየ ቤታቸው ደብዳቤና የገንዘብ መክፈያ ቅጽ እየሰጡ ሲሆን ነዋሪዎቹ ገንዘብ እንዲከፍሉ የተጠየቁበትን ቅጽ ሳይሞሉ መመለስ አይችሉም ተብሏል፡፡
ደብዳቤው ላይ ባለው የፖሊስ ጣቢያው ስልክ ቁጥር ደውለን ያነጋገርናቸውና ስማቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ ያልሆኑ አንድ የፖሊስ አባል ‹‹ህዝቡን ለምን ፖሊስ ጣቢያ እንዲሰራ ታስገድዳላችሁ?›› በሚል ላነሳነላቸው ጥያቄ ‹‹ህዝቡኮ ራሱ ነው ሴት ልጆቻችን በሰላም መግባት አልቻሉም እያለ ያለው፡፡ ፖሊስ የህዝብ እስከሆነ ድረስ ህዝብ ፖሊስ ጣቢያ ቢያሰራ ምን ችግር አለው? ህዝቡ አልከፍልም ካለ ሊቀር ይችላል፡፡ እናንተ ግን ይህን እንደጥያቄ የምታነሱት ስብሰባው ላይ ስላልነበራችሁ ነው፡፡›› ብለውናል፡፡
ከወራት በፊት ‹‹ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ›› በሚል አደረጃጀት ህዝቡ በየቤቱና ከጎረቤት ጋር 1ለ5 በመደራጀት ከፖሊስ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው የሚያዝ ህግ መውጣቱና ነዋሪዎቹንም ማደራጀት መጀመሩን ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወቃል፡፡
አዲሱ የመኢአድ አመራር ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ግንኙነት እንደሚያስቀጥል አስታወቀ • የፓርቲውን ማህተም ተሰርቄያለሁ ብሏል
ዛሬ ህዳር 4/2007 ዓ.ም በፓርቲው ዋና ጽፈት ቤት መግለጫ የሰጠው የመኢአድ አዲሱ አመራር ከመኢአድ ጋር ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸውና ከሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ከአሁን ቀደም አብሮ ለመስራት የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚያስቀጥል አስታውቋል፡፡
በ2003 ዓ.ም ከታህሳስ 15-17 ድረስ አይቤክ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ በፓርቲው አመራሮች መካከል ችግር እንደነበር የገለጸው አዲሱ አመራር ከዛ በኋላ አቶ አበባው መሃሪ ፕሬዝደንት የሆኑበት አካሄድ ትክክል እንዳልነበር፤ለአራት አመት ያህል በሁለቱ ቡድን መካከል የነበረው አለመግባባት በእርቅ እንደተቋጨና አቶ አበባው ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደለቀቁ የጻፉትን ደብዳቤ ዋቢ አድርጎ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ያለ ምንም ገደብ ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መምጣት ይችላሉ ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በአንጻሩ አዲሱ አመራር በህገ ወጥ መንገድ ነው ወደ ስልጣን የመጣው በሚል ቅር የተሰኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ዛሬ ከሰዓት መግለጫ እንደሚሰጡ ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት አቶ አበባው መሃሪ ጋር በተደጋጋሚ ብንደውልም የእጅ ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው ሀሳባቸውን ማጠቃለል አልቻልንም፡፡
በሌላ በኩል አዲስ አመራር ማህተሙ አዲሱ አመራር ከመምጣቱ በፊት ፓርቲው ውስጥ በነበሩትና በአዲሱ አመራር ጋር ባልተስማሙ አካላት እንደተሰረቀ አስታውቋል፡፡ ‹‹ማህተሙ ከዚህ ቤት በነበሩ ሰዎች ተሰርቋል፡፡ ይህን ጉዳይ በወቅቱ ለፖሊስ አመልክተናል፡፡ በፓርቲው ማህተም እኛ የማናምንበትና ህገ ወጥ ነገር ቢሰራበት ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው፡፡›› ሲሉ አዲሱ የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ ገልጸዋል፡፡
የደኢህዴን ጉባዔ አስመልክቶ የሶዶ ከተማ ጎዳና ተዳዳሪዎች በግዳጅ ገለሜ እስር ቤት እንዲገቡ ተደረገ:: – ለአስነዋሪ ተግባር ሽፋን የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን የሳምንት ቀለብ ልታቀርብ ነው::
– ለአስነዋሪ ተግባር ሽፋን የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን የሳምንት ቀለብ ልታቀርብ ነው::
– ለጉባዔ ተብሎ የጠፉት አገልግሎቶች ለጊዜው እንዲስተካከሉ መደረጉ በህዝቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል
Minilik Salsawi
ከህዳር 6/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 10/2007 ዓ.ም በሶዶ ከተማ የሚደረገውን የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ አስመልክቶ ሶዶ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች በግዳጅ ወደ ካምፕ እንዲገቡ መደረጋቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሴት፣ አዛውንትና ህጻናት ጎዳና ተዳዳሪዎች ሶዶ ውስጥ አራዳ ክፍለ ከተማ ተብሎ በሚጠራውና አዲስ እየተሰራ በሚገኘው ገለሜ የተባለ እስር ቤት ውስጥ በግዳጅ እንዲገቡ መደረጉን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ካምፕ ውስጥ የገቡትን የጎዳና ተዳዳሪዎችም የቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን ለሳምንት ቀለብ እንደሚያቀርብላቸውና ጉባዔው ካለቀ በኋላ ወደነበሩበት እንደሚመለሱም ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፡፡
‹‹ለጉባኤው ሲባል ዜጎችን በግዳጅ ወደ ካምፕ ማስገባቱ ደኢህዴን በከተማዋ ልማት እንደተመዘገበና ህዝቡን ከድህነት እንዳላቀቀ ለማስመሰል ያደረገው አስነዋሪ ተግባር ነው›› ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ የወላይታ ዞን የአደረጃጀት ኃላፊ አቶ ታደመ ፈቃዱ ‹‹እስካሁን ሶዶ ከተማ ውስጥ መብራት ስለማይኖር በርካቶች ተዘርፈዋል፡፡ የተገደሉም አሉ፡፡ የከተማዋ ውበትም እምብዛም የተጠበቀ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ከተማዋን ለማጽዳት እየተሯሯጡ ነው፡፡ መብራት ባልነበረበት ከተማ መንገዱ ሁሉ ባውዛ ሆኗል›› ሲሉ ስለሁኔታው አስረድተዋል፡፡
ለደኢህአዴን ጉባዔ ተብሎ የከተማዋ ውበት እንዲጠበቅና የጠፉት አገልግሎቶች ለጊዜው እንዲስተካከሉ መደረጉም በህዝቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል ተብሏል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪም ‹‹ህዝቡ በአገልግሎቶች መጥፋት ተማሯል፡፡ የከተማው ውበት ለሚኒስትሮቹ እንጅ ለእኛ አይደለም፡፡ እንዲህ ከሆነ ደኢህዴን በየ15 ቀኑ ጉባዔ ቢያደርግ ጥሩ ነበር›› ሲሉ ስለሁኔታው ገልጸውልናል፡፡
ለጉባዔው ሲባልም በጸጥታ ስም በተቃዋሚዎች ላይ ክትትል እየተጠናከረ ይገኛል ያሉት አቶ ታደመ ‹‹ከተማዋ በፖሊስ ተጥለቅልቃለች፡፡ ፖሊሶች በየ 10 ሜትሩ ቆመው ነው የሚታዩት፡፡›› ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት ለሁለት ተሰነጠቀ የሚባለው የመኢአድ አመራር በሁለት ወገን መግለጫ ሰቷል::
– የሁለቱንም አንጃዎች ዜና ዝርዝር ይመልከቱት :: – ድጋሚ እርቅ ያስፈልጋቸዋል; Minilik Salsawi
– ምርጫ በመጣ ቁጥር ስህተትን በመደጋገም የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ማደናቀፍ ማብቃት አለበት::
– በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለው የፖለቲካ አሻጥር (ሳቦታጅ) ግልጽ መሆን አለበት::
– አዲሱ የመኢአድ አመራር ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ግንኙነት እንደሚያስቀጥል አስታወቀ
– አዲሱ የመኢአድ አመራር የፓርቲውን ማህተም ተሰርቄያለሁ ብሏል
በዚህም መሰረት በአቶ አበባው መሃሪ የሚመራው መኢአድ ስልጣኑን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በኢሓዴግ ጥርስ ውስጥ በመግባቱ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ከመነፈጉም በላይ ከአንድነት ጋር ሊያደርገው የነበረው ውህደት በምርጫ ቦርድ እንቅፋትነት ተንጠልጥሎ የቀረ ከመሆኑም በላይ የምርጫው ውህደት በሚፈጸምበት እለት አሁን መኢአድን በአመራርነት ላይ ነኝ የሚሉት አቶ ማሙሸት የኢትዮጵያን ቴሌቭዥንን እና የደህንነት ሃይሎችን አስከትለው በመምጣት አከባቢው ላይ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ይታእሳል::
ይህንን ተከትሎ አቶ ሃይሉ ሻውል በተገኙበት እርቅ ተፈጸመ ቢባልም ውጥረቱ ሰፍቷል የሚሉ የድርጅቱ አባላት እየተናገሩ ነው በዛሬው እለት ነገረ ኢትዮጵያ ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው ዜና መሰረት እና በአቶ አበባው የሚመራው የመኢአድ ጓድ የሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ሰፍሯል::
ዛሬ ህዳር 4/2007 ዓ.ም በፓርቲው ዋና ጽፈት ቤት መግለጫ የሰጠው የመኢአድ አዲሱ አመራር ከመኢአድ ጋር ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸውና ከሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ከአሁን ቀደም አብሮ ለመስራት የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚያስቀጥል አስታውቋል፡፡
በ2003 ዓ.ም ከታህሳስ 15-17 ድረስ አይቤክ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ በፓርቲው አመራሮች መካከል ችግር እንደነበር የገለጸው አዲሱ አመራር ከዛ በኋላ አቶ አበባው መሃሪ ፕሬዝደንት የሆኑበት አካሄድ ትክክል እንዳልነበር፤ለአራት አመት ያህል በሁለቱ ቡድን መካከል የነበረው አለመግባባት በእርቅ እንደተቋጨና አቶ አበባው ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደለቀቁ የጻፉትን ደብዳቤ ዋቢ አድርጎ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ያለ ምንም ገደብ ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መምጣት ይችላሉ ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በአንጻሩ አዲሱ አመራር በህገ ወጥ መንገድ ነው ወደ ስልጣን የመጣው በሚል ቅር የተሰኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ዛሬ ከሰዓት መግለጫ እንደሚሰጡ ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት አቶ አበባው መሃሪ ጋር በተደጋጋሚ ብንደውልም የእጅ ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው ሀሳባቸውን ማጠቃለል አልቻልንም፡፡
በሌላ በኩል አዲስ አመራር ማህተሙ አዲሱ አመራር ከመምጣቱ በፊት ፓርቲው ውስጥ በነበሩትና በአዲሱ አመራር ጋር ባልተስማሙ አካላት እንደተሰረቀ አስታውቋል፡፡ ‹‹ማህተሙ ከዚህ ቤት በነበሩ ሰዎች ተሰርቋል፡፡ ይህን ጉዳይ በወቅቱ ለፖሊስ አመልክተናል፡፡ በፓርቲው ማህተም እኛ የማናምንበትና ህገ ወጥ ነገር ቢሰራበት ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው፡፡›› ሲሉ አዲሱ የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በታች የመኢአድ ፕረዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ከስራ አስፈጻሚዎቹ ከአቶ ካሳሁን እና ከአቶ ሲራክ ጋር የሰጡትን መግለጫ በጥሞና ያንብቡ::


ስልጣኔን የለቀኩት በአንዳንድ ብልጣብልጦች እና የሴራና አድማ አካሄድ በሚችሉ ሰዎች ፓርቲው ስለተጠለፈ ነው::(ሙሉ ደብዳቤውን ከታች ያንብቡ)
“ስልጣኔን የለቀኩት በአንዳንድ ብልጣብልጦች እና የሴራና አድማ አካሄድ በሚችሉ ሰዎች ፓርቲው ስለተጠለፈ ነው::’ – አቶ አበባው መሓሪ የመኢአድ ፕሬዚዳንት
“ፓርቲው ወደፊት ለመራመድ የማይችልበት ወደፊትም የማይሻሻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል::”አቶ አበባው
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመኢአድ ፕረዚዳንት የነበሩት አቶ አበባው መሓሪ ስልጣናቸውን ሊለቁ የቻሉት በገጠማቸው አስገዳጅ የድርጅታዊ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል እንደ አቶ አበባው ደብዳቤ በአብዛኛው የመኢአድ አባላት ከፍተኛ የድምጽ ድጋፍ ከተመረጥኩበት የፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ ድርጅቱ ወደፊት እንዳይራመድ የሚያደርጉ እና ከዚህ በፊት ተሳስረውና ተቆላልፈው በመጡ የውስጥ ችግሮች ለሃገራቸው መስራት አለመቻላቸውን በመጥቀስ ፓርቲው ወደፊት የማይራመድበት አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን ለጠቅላላው ጉባዬ ገልጸዋል::
የመኢአድ የውስጥ ችግር በመጪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ላይ ውሃ የቸለሰ ነው ያሉት አቶ አበባው ኢትዮጵያውያን አቤት የሚልላቸው አካል እየጎደለ መሄዱን ጠቁመው በመኢአድ ውስጥ ያለው ችግር ከአቅም በላይ የሆነ ስለሆነ ፍርዱን እና መዝገቡን ለታሪክ በመተው ስልጣናቸውን እንደለቀቁት ከአቅም በላይም እንደሆነ አስረድተዋል::
ከአቅም በላይ ያሉትን ጉዳይ ሲገልጹ … ለየኢትዮጵያውያን ምሁራን ከትግሉ መሸሽ ምክንያቱ የትግሉ መስመር በአንዳንድ ብልጣ ብልጦች እና የሴራ እና የአድማ አካሄድን በሚችሉ ግለሰቦች ስለሚተለፍ መሆኑን መኢአድ ውስጥ ከተከሰተው ችግር እንደተገነዘቡ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል::
የአቶ አበባው መሃሪ ፊርማ የሰፈረበትን ሙሉ ደብዳቤውን ከታች ያንብቡት :
የህወሓት ሦስቱ ጉልቾች ስሪትና ተግባራቸው፡፡ ከላገሬ ኢትዮጵያ
የጉልቾቹ ስም ብአዴን፣ኦህዴድ፣ደህዴን ሲባሉ የተሰሩትም ዴሞክራሴ ከተባለ ዘረመል(ሴል) ሆኖ ይህ ሴል ያለማችን ገራሚው የጉልቾች ሴል ተብሎ እንዲመዘገብ እራሱን ነፃ አውጭ ብሎ የሰየመው ህወሓት ባለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አድርጉዋል፡፡
ይህ ሴል በውስጡ ሂዎት የሌለው አርቴፊሻል የህወሓት የላባራቶሪ መመራመሪያ ሲሆን እስካሁንም ወደር ያልተገኘለት ሂዎት አልባ ተንቀሳቃሽ ቁስ ግን የዎያኔ መጠቀሚያ ሆኖ ያገለግላል፡፡
አስገራሚው ነገር ህወሓት የሚባለው በድን የዴሞክራሴ ሴል ሰራሽ አካል የዴሞክራሴ ፅንሰ ሀሳብ የሌለው እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ብሎ የሰየመ ሆኖ አላማውም የትግራይን ህዝብ እና ህዝብ ብቻ ነፃ ለማውጣት የተቋቋመ ጠባብና ዘረኛ የፖለቲካ አጀንዳ ያነገበ መሆኑ ነው፡፡
ሌላው ገራሚ የሚያደርገው ነገር እራሱን ህወሓትን ጨምሮ ሌሎች ኦህዴድ፣ደህዴን በድን የዲሞክራሴ ሴል ውስጣቸው እንዳለ ተደርገው የተሰሩት ቁሶች ህዝብ የሚል ሌላ የሚያምታታ ማጭበርበሪያ ታቤላ የተለጠፈባቸው ሲሆን ብአዴን የሚለው ጉልቻ ግን ከህዝብ ይልቅ ብሄር የሚል መታወቂያ ተሰጥቶታል ምክንያቱም ይህ ስም ለህወሓት የፖለቲካ መሳሪያ በቀጥታ ላገልግሎት እንዲጠቅም ተፈልጎ ነው፡፡
እዚህ ጋር መጤን የሚገባው ነገር ብሄር በሚለው ስም ብሄርብሄረሰቦች የሚለውን ሌላ የፖለቲካ ትርፋ ለማምጣትና የሰደቅ አላማውን የቀድሞ ልዕልናውን ለማሳጣትና የምሐለኛውን ሴጣናዊ ምናምንቴ በብሄር ብሄረሰብ ስም ለመለጠፍ ተፈልጎ የተሰራ አገር የማፍረስ ደባ ነው፡፡
አሁን ህወሓት በዚህ መልኩ ጉልቻዎቹን ከሰራ በሗላ ሁሉንም አንድ ለማድረግ የተጠቀመበት ዘዴ ጉልቾቹ ከተሰሩበት በድን የዴሞክራሴ ሴል በቀጥታ ሴሉን በመውሰድ ኢህአዴግ ብሎ በመሰየም ዋና ህዝብን ለማወናበድ ወደሚጠቀምበት አዛኝ ቅቤ አንጉዋች እንደሚባለዉ የጭቃ እሾኩን በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ተከለ፡፡
አሁን የሚቀረዉ ቁጭ ብሎ በነዚህ ከንቱ ያትራፊነት የሴራ መረብ በመጠቀም ምሁር ነን የሚሉትን ሁሉ በማታለልና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይፈቀዳል፣መናገር ይቻላል፣መፅፍ ይቻላል እናም ሌሎች ኘሮፖጋንዳዎችን በመናገርና ህገመንግስት እያለው በሚጠራው ምናምንቴው ለይ የፃፈዉን በማየት ህብረተሰቡ እውነት መስሎት ተሸወደ ምሁሩም ተግባራዊ ለማድረግ ሞከረ ግን እንደማይቻል ሲያውቅ የታሰረውም ታስሮ ሞት የተፈረደበትም ተገደለና ጥቂት የማይባለው ወገኔ ሲሰደድ አብዛኛው ህብረተሰብ በሲቃይ መዓበል ውስጥ መፍተሄ አልባ የፅር ድምፅ እያሰማ በሐገሩ ባይተዋርና የበይ ተመልካች ሆኖ ተቀምጡዋል፡፡
ሶስቱ ጉልቾች የህወሓት የጀራ መጋገሪያ ምጣድ ለማስቀመጭያነት በቀጥታ የዋሉ ሲሆን አንዳንድ ግዜም ወጥ ለመስሪያ የሚጠቅም ድስት መጣጃዎች ሆነው እናያቸዋለን እዚህ ጋር ግን ሌላ ማስተዋል የሚጠበቅባችሁ ነገር የጉልቻዎቹ ትክክለኛ በድንነት የምትለዩት ምንም እሳት ቢነድባቸው ሚሊዮን እንጀራ ቢጋገርባቸው ቅንጣት የማይሰማቸው ስሜት አልባ እቃዎች መሆናቸዉ ነው፡፡
የሰወስቱ ጉልቾች አባላቶችና ደጋፊዎች ሆይ እባካችሁ ፈጣሪ ነፍስ ከዘራባችሁ ይህንን አንብቡትና የህወሓትን ስውር አደንዳ ከስር መሰረቱ ለመገርሰስ ሞክሩ ቢያንስ ለልጅ ልጆቻችሁ ታሪክ ነውና ንቁ፡፡ይሄንን ለማድረግም አይመሽባችሁም እስኪ ግማሾቻችሁ እንኩዋን በቃን ብላችሁ የዚህ አይነቱን የርግማን እንጀራ ከመብላት ተቆጠቡ ምክንያቱም አሁን የምትበሉት የህዝብ ስጋ ሲሆን የምጠጡትም የወገናችሁ እንባና ደም ነዉና ትውልድ ይዳን ትላንት የገደላችሁትና ያስገደላችሁት የግፍ ፅዋ ይብቃ እላችሗለሁ፡፡
ከላገሬ ኢትዮጵያ
03/03/2007
ሰማያዊ ትልቅ የፖለቲካ ክስረት አጋጠመው። በርካታ አባላቱም የአመራሩን ግትርነት መጠየቅ ጀመሩ። በአንድ አመት ዉስጥ የሰማያዉ ድጋፍ ወደ ታች አሽቆለቆለ።
ትንሽ የግል አስተያየት በሰማያዊ ላይ
==================== Girma Kassa
ኃዳር ሰባት ቀን በቤልሄር ሜዳ ሰማያዊ ፓርቲ ብዙም ስማቸው ከማይታወቅ ድርጅቶች ጋር በመሆን የአደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል። የአደባባይ ስብሰባ ማለት ብዙ ከሰልፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።
የሰማያዊ ፓርቲ ሰኔ ወር 2005 ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰልፍ በማድረግ ታሪክ የሰራ ድርጅት ነው። ወደ ሰባ ሺህ የሚሆን ሕዝብ በሰልፉ ተገኝቶ ነበር። ሰማያዊ ባደረገው ሥራ አንድነቶች ከእንቅልፋቸው ነቅተው የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል ተስፋ ሰጪና አገር እቀፍ እንቅሳሴም ለማድረግ ችለዋል። ለዚህ የሰማያዊ ፓርቲ ትልቅ ምስጋና ይገባዋል።
ትንሽ ድጋፍ ሲያገኙና በየቦታው ስማቸው ሲጠራ፣ የሰማያዊ መሪዎች ሌሎች ድርጅቶችን ማሳነስ ጀመሩ። ሊቀመንበሩ ይልቃል «ምን የሚረባ ድርጅት አለ ብለህ ነው?” ብሎ እንደተናገው። በዚህ ምክንያት ከብዙ ድርጅቶች ጋር ሰማያዊ መጋጨት ጀመረ።
የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 5 2006 በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ ጠየቀ። ገዢው ፓርቲ እውቅና አልሰጥም አለ። ሚያዚያ 12 ተጠየቀ። ያኔም አልተቻለም ወደ ሚያዚያ 26 ሰልፉ ዞር። በዚህ መሃል ሰማያዊዎች በመሃል ገብተው፣ ሚያዚያ 12 ሰልፍ ለማድረግ ጠየቁ። ለአንድነት ተከልክሎ ለነርሱ እውቅና ተሰጣቸው (ያው አገዛዙ ማጋጨት ይወድ የለም) አብዛኞቻችን የሰማያዊ ድርጊት አልተመቸንም። ባይሆን ሰልፉ ከአንድነት ጋር ለምን አይደረግም ብለን ተሟገትን። በይልቃል የሚመራው የሰማያዊ አመራር ግን የአብራችሁ ቁም ጥሪያችንን አጣጣለው። ግትር ሆኑ።
በሰልፉ ቀን፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለሰማያዊች መልእክቱን አስተላለፈ። ከዘጠኝ ወራት በፊት ወደ ሰባት ሺህ የወጣ ሕዝብ፣ ሰማያዊዎች ግማሽ ሚሊዮን ጠብቀው፣ ከአራት መቶ የማይበልጥ ህዝብ ብቻ ተገኘ። ሰማያዊ ትልቅ የፖለቲካ ክስረት አጋጠመው። በርካታ አባላቱም የአመራሩን ግትርነት መጠየቅ ጀመሩ። በአንድ አመት ዉስጥ የሰማያዉ ድጋፍ ወደ ታች አሽቆለቆለ።
በህዳር ሰባቱ ሕዝባዊ ሰብሰብ ወይም ሰልፍ፣ ከዚህ በፊት ግማሽ ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ ይገኛል ብለው የነበሩት ሰማያዊዎች፣ «ወደ ሶስት ሺህ ይገኛል» አሉ። ሶስት ሺህ ሰው ብቻ የሚጠበቁ ከሆነ ለምን በአንድ አዳራሽ ስብሰባዉን እንደማያደርጉት አልገባኝም። ይመስለኛል በወረቀት ሶስት ሺህ ይበሉ እንጂ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ይገኛል የሚል ግምት ዉስጥ ዉስጡን ሊኖራቸው ይችላል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባዉን አዘጋጀሁ፣ የሚለው ከሌሎች ስምንት ድርጅቶች ጋር ነው። ከነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ መኢአድን ስታስወጡት የሚቀሩት ሰባት ናቸው። (ለምን መኢአድ በአሁኑ ወቅት በዉስጥ ችግሮቹ የተጠመደ ስለሆነ)። ሰባቱ ድርጅቶች የኦሞ ህዝቦች፣ የከንባታ ሕዝቦች የመሳሰሉ፣ ጥቂት ግለሰቦችን ያካተቱ፣ የማይታወቁ ድርጅቶች ናቸው። እነዚህን ድርጅቶችን አሰባሰቦ ሰማያዊ ትልቅ ትብብር እንደተፈጠረ ለማስመሰል ተሞከረ እንጂ፣ በዋናነት ይሄንን ስብስበ የሚያንቀሳቅሰው የሰማያዊ ፓርቲ ነው።
ይህን ስጽፍ ከላይ ባየሁት ነው። ዉስጣዊ ድርጅታዊ ሥራ ተሰርቶ፣ በቂ ዝግጅት ተደርጎ ሊሆን ይችላል። በርግጥ ያኔ ብዙ ሳይታወቁ የመጀመሪያዉን ሰልፍ ባደረጉ ጊዜ የተገኘውን ያህል ወደ ሰባ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ከተገኘ፣ በርግጥ ትልቅ ነገር ነው። ለአገዛዙም ጠንካራ መልእክት ለማስተላለፍ ይቻላል።
ሆኖም አንድ ነገር በግልጽ መታወቅ አለበት። ሰልፍ መጥራትና በሰልፉ ዉጤት ማስመዝገብ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን። ብዙ ተጠብቆ የመጣው ሰው ቁጥር ካነሰ የፖለቲክ ክስረትም ሊሆን ይችላል። ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ በፊት ሰባ ሺህ ሕዝብ ሰብስቦ፣ እንደገና በመቶ የሚቆጠር ሰው ብቻ ከመጣለት፣ ፓርቲው መንገዱን እና ስትራቴጂዉን መቀየር ይኖርበታል እላለሁ። ደርጅቱ እንደዚህ ወደ ታች እንዲያሽቆለቁል ያደረጉ ግትር የአመራር አባላቱን ተጠያቂ ማድረግና መቀየር ያስፈልጋል። እየተደረገ ያለው፣ ብዙዎችን ትልቅ ዋጋ የሚከፍሉበት አገርን ነጻ የማውጣት ትግል እንጂ የግለሰቦችን ወይንም ትናንሽ አማባገነኖችን ተክለ ሰዉነት መገንባት አይደለም።
ለማንኛውም ከእሁድ በኋላ ፣ የድርጅቱን ጥንካሬና የአስቀድሞ ዝግጅት አይተን በስፋት ትንተናዎች እናቀርባለን። የፌስ ቡክ ዘመቻው ግሩም እንደሆነ ታዝቢያለሁ። በሜዳ በየወረዳዉና በየቀበሌውስ ? የምናየው ይሆናል …
ቤተ ክርስቲያን እንዳይፈርስ የተቃወሙት ዜጎች የት እንደደረሱ አልታወቀም ተባለ
• ‹‹ይህ ሁሉ የሆነው የእምነቱን ተከታዮች በመናቅ ነው››
ትናንት ህዳር 3/2007 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ የማሪያም ቤተ ክርስቲያን እንዳይፈርስ በመቃወማቸው የታፈኑት ዜጎች የት እንደደረሱ አልታወቀም ሲሉ በወቅቱ ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎችና የእምነቱ ተከታዮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
በወቅቱ 600 ያህል ዜጎች ተገኝተው ቤተ ክርስቲያኗ እንዳትፈርስ ሲቃወሙ እንደተመለከቱ የገለጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የቤተ ክርስቲያኗን መፍረስ የተቃወሙትን ጨምሮ ሌሎች በአካባቢው የተገኙ ዜጎችም በፖሊስ መታፈሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ‹‹ህዝቡ በሰንደቅ አላማ አምላክ አታፍርሱብን እያለ ቢለምንም እነሱ ግን ጥይት ወደላይ በመተኩስ ህዝቡን ከማሸበራቸውም በላይ ያገኙትን እየደበደቡ በ9 የድንጋይ መጫኛ መኪና አስገድደው በመጫን ወዳልታወቀ ቦታ ውስደዋቸዋል፡፡ አድማ በታኝ ፖሊስ ቄስ፣ አዛውንት፣ ህጻንና ሴት ሳይል ያገኘውም አፍሶ ወስዷል፡፡ የኮብል ስቶን ጠራቢዎች ሳይቀሩ በአካባቢው በመገኘታቸው ታፍሰው ታስረዋል፡፡ አሁን የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ ከተሰራች ከሁለት አመት በላይ እንደሆነ የገለጹት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ ከተሰራችበት ጊዜ ጀምሮ እንድትፈርስ ጥያቄ እንደቀረበ ተገልጾልን አያውውም፡፡ አሁን ነው ደርሰው ያፈረሱት፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን አገልጋዮች ጨምሮ በጣም ብዙ ሰው በዱላ ተደብድቧል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የእምነቱን ተከታዮች በመናቅ ነው፡፡›› ሲሉ ቅሬታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎችና አማኞች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ 9 ሰዓት ቤተ ክርስትያኗ እንዳትፈርስ እንደተቃወሙ፣ አድማ በታኝ ፖሊስ በአካባቢው ያገኘውን ሰው ካፈሰ በኋላ ቤተ ክርስቲያኗን በማፍረስ ቆርቆሮውን በመኪና ጭኖ እንደሄደ የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በመተማ ጭልጋ እና አርማጭሆ የህዝብ አመጽ በርትቷል::ተጨማሪ ወታደሮችን የጫኑ ኦራሎች ወደ አከባቢው እያመሩ ነው::
በመተማ ገንዳ ውሃ በአርማጮህ እንዲሁም በጭልጋ ከህዝብ አመጽን ተከትሎ ከፍተኛ ተኩስ እየተሰማ መሆኑን የአከባቢው ምንጮች ጠቁመዋል::በተልይ በመተማ ገንዳ ውሃ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ስትሆን ኦራሎች ወታደሮችን በማመላለስ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ በአከባቢእ የሚገኙ የአማራ ንቅናቄ አባላት ተናግረዋል::የህዝቡ አመጽ ከፖሊሶች እና የአከባቢው ሚሊሻ በላይ በመሆኑ ተጨማሪ ወታደሮችን የጫኑ ኦራሎች ወደየከተሞቹ እያመሩ መሆኑን ታውቋል::የነጻነት ሃይሎች ነን የሚሉ ይህንን የህዝብ እንቅስቃሴ በመጠቀም ትግሉን ማስፋፋት እንደሚችሉ ተጠቁሟል::
ከባለፈው ወራት ጀምሮ መተማ ከተማ ሳሉግ በመባል የሚታወቁት የበረሃ ሰራተኞች መካከል በተነሳው አለመግባባት የሰው ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ ግጭቱ በመባባሱ እስካሁን ከ10 በላይ ሰወች መገደላችውና በርካቶችም መቁሰላቸው የታወቀ ሲሆን፣ ችግሩን በማባባስም የወያኔ እጅ እንዳለበት ተረጋግጧል። ይህን የመሰለ ግጭት ከዚህ ቀደምም በተለይ በጎንደር፣ጎጃምና ወሎ ተወላጆች መካከል የሚደጋገም ሲሆን ወያኔ ነገሩን ሲያባብስ ቆይቶ ለአሁኑ ከባድ አደጋ አድርሶታል።
በአሁኑ ጊዜ ግጭቱ ሰፋ ባለ መልኩ እየቀጠለ ያለ እና በተለይም በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳወች መዛመቱና ከጎንደር የሚያገናኙ መንገዶችም መዛጋታቸው ታውቁኣል። ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላትም ሂደቱን በቅርብ እንድትከታተሉና ወጣቶቹ የእርስበርስ መጠፋፋቱን አቁመው ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ተሰላፊ እንዲሆኑ ለሚደረገው ጥረት መስራት ያስፈልጋል።
ከሳምንታት በፊት በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ታጣቂዎች እና በፌዴራል ፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት አራት የፌዴራል ፖሊሶች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ተከስቶ የነበረው ግጭት ከፖለቲአክ አጀንዳና ከህዝባዊ ጥያቄ ውጪ የነበረ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል::
ጊዜው የሕዝባዊ እምቢተኝነት ነው!!!
በአሁኑ ወቅት በአገራችን በከተሞችና በገጠሮች እየታዩ ያሉ ምልክቶችን በጥንቃቄ የመረመረ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን መታዘቡ አይቀርም።
በአንድ በኩል፣ ወያኔ የተወገደባት፣ ፍትህ የሰፈነባትና የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየት ተስፋችን እየለመለመ ነው። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረጂም ዓመታት በሕዝብ ላይ ሰፍኖ የነበረው የፍርሀት ደመና እየገለጠ በመሆኑ ተዘግተው የቆዩ አንደበቶች መናገርና “ይኸ ሁሉ ግፍ ለምን?” ብለው መጠየቅ ጀምረዋል። ይህንን መነቃቃት በአስተሳሰብም፣ በተግባርም፣ በኪነጥበብም እያየነው ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ለውጥ በአገራችን ሊመጣ እንደሚችል ከማመን አልፎ ራሳቸውን በለውጥ አምጭ ኃይልነት መመልከት ጀምረዋል። በርካታ ወጣቶች ወያኔን በትጥቅ ለመገዳደር የወሰኑ ወገኖቻችንን እየተቀላቀሉ በዚህም ምክንያት ጉልበታቸውን እያፈረጠሙ ነው። የለውጡ እርሾ ከሲቪሉ አልፎ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በኢሕአዴግ ድርጅቶች ውስጥም እየተብሰለሰለ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፣ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚጠቀምበት ኃይል መሆኑ እያበቃ በአንፃሩ የትግሉ አጋር የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እየታዩ ነው። በሁሉም የሠራዊቱ ክፍሎች ጉምጉምታው ወደ ጩኸት እየተቀየረ በመሆኑ ሠራዊቱ በአለቆቹ ላይ የሚነሳበት ጊዜ እሩቅ አይደለም። በተለያዩ ምክንያቶች ህወሓትን ወይም ህወሓት የፈጠራቸውን ድርጅቶች የተጠጉ በአጠቃላይ ኢሕአዴግ በሚባለው ስብስብ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንም “ለመሆኑ ማንን ነው እያገለገልን ያለነው?” ብለው በመጠየቅ ላይ ናቸው። በዚህም ምክንያት ወያኔ ውስጡ እየተረበሸ ነው። ከኢትዮጵያም ውጭ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ያለው ቁጣና ዝግጁነት ከወትሮው እጅግ የላቀ ነው። በአጭሩ፣ በሁሉም አቅጣጫ፣ ደረጃ በደረጃ የሕዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።
በአንፃሩ ደግሞ፣ የጨለማ ንጉሥ የሆነው ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ወደ ፍርሀት ቆፈን ለመመለስ እስሩን ከመቸውም በላይ ያጧጧፈበት ጊዜ ነው። በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር በሶማሊ … በመላው ኢትዮጵያ ብሩህ ራዕይ የሰነቁ ወጣቶችና አዛውንት ታድነው እየታሰሩ ናቸው። የወያኔ እስር ቤቶች በአርቆ አስተዋይ ዜጎቻችን ተሞልተዋል። ወትሮም ከፍተኛ የነበረው ስደት ብሶበታል፤ ለእውነት በጽናት የቆሙ ጋዜጠኞች ወይ ታስረው፣ አልያም ተሰደው አልቀዋል። የወያኔ የግዴታ ስልጠና አገሩን እያመሰው ነው። የኢትዮጵያዊያን ኑሮ በእጦቶች የታጀበ ሆኗል። የነፃነት እጦት፣ የፍትህ እጦት፣ የመብራት እጦት፣ የስኳር እጦት፣ የዘይት እጦት፣ የታክሲ እጦት፣ የመኖሪያ ቤት እጦት፣ እጦት፣ …. እጦት።
እነዚህ ሁለት ተፃራሪ እውነታዎች ሁለት ተፃራሪ ኃይሎች ለወሳኝ ፍልሚያ ፊት ለፊት መፋጠጣቸዉን በግልጽ ያሳያሉ። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃነትና ባርነት፣ ፍትህና ጭቆና፣ ደስታና ሀዘን፣ ተስፋና ተስፋ መቁረጥ፣ ብልጽግናና ድህነት፣ እውቀትና ድንቁርና፣ ብርሃንና ጨለማ፣ ለወሳኝ ግጥሚያ ተፋጠዋል። ይህ ፍጥጫ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታን በመወሰን ረገድ አቢይ ሚና የሚኖረው ወሳኙ ግጥሚያ – ሕዝባዊ እምቢተኝነት – መጀመሩን አብሳሪ ነው። የነፃነት፣ የፍትህ፣ የተስፋ፣ የብልጽግና፣ የእውቀትና የብርሃን ወገኖች ነን የምንል ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይህንን ፍልሚያ በድል መወጣት ግዴታችን ነው።
ወያኔ ታጋዮችን ቢያስር ትግሉን አያስርም። በእጦት ኑሮዓችን በማመሰቃቀል በድህነት ሊያንበረክከን ቢሻም፣ በፍጹም አንበረከክለትም። በተዘረፈ የድሆች ድካም ህንፃዎችን ቢገነቡም የራስ ባልሆነ ጌጥ አንኮራም። የወያኔ የሆነ የኛ አይደለም፤ የእነሱ መክበር የኛ መክበር አይደለም። ወያኔ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ገዢና ተገዢ፤ በዳይና ተበዳይ፣ ገፊና ተገፊ ናቸው።
ተበዳይና ተገፊ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረኞች፣ ሙሰኞችና ከፋፋዮች የህወሓት ባለሥልጣኖቻቸውና ሎሌዎቻቸው ላይ ይነሳሉ። የተጀመረው ሕዝባዊ እምቢተኝነት አመቺ በሆኑ መንገዶች ሁሉ ይጧጧፋል።
የወያኔ ትዕዛዛትን መሻር፤ በሥራ ላይ መለገም፤ ግብር አለመክፈል፤ አድማ መምታት፤ የወያኔ ካድሬዎችን ማግለልና ማዋረድ፤ የነፃነት ኃይሎችን መደገፍ፤ የፓሊስና የጦር ሠራዊት አባላትን ማቅረብ እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እነሱም የትግሉ አካል እንዲሆኑ ማበረታታት፤ ህሊና ያላቸው የኢሕአዴግ አባላት የሕዝቡን ትግል እንዲያግዙ ማበረታታት … – እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ በርካታ የትግል ስልቶች ከአሁን ጀምሮ በተከታታይ በሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል። የወያኔን የጭቆና ምሽግ ከውስጥ መሸርሸር፤ ከውጭ መደርመስ ይኖርበታል። የመሸርሸርና የመደርመስ ሥራዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ ማድረግ ይገባል። ጊዜው የእምቢተኝነት ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ንቅናቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጠገቡ ባሉት መሪዎቹ አስተባባሪነት በአንድነት እንዲነሳ ጥሪ ያቀርባል፤ በመላው ዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው ሁለገብ ትግል በጽናት እንዲደግፉ ያሳስባል። ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው፤ እንወጣዋለንም!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
አቃቢ ህግ በጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ የመሰረተውን ክስ እንዲያሻሽል ታዘዘ •ክሱ ተሻሽሎ መቅረቡን ለማየት ለህዳር 24 ቀጠሮ ተሰጥቷል

የፌደራል አቃቢ ህግ በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በጦማርያኑና በጋዜጠኞቹ ላይ የመሰረተውን የሽብር ክስ እንዲያሻሽል የልደታ ከፍተኛ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ህዳር 3/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀደም ብሎ የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን በመስጠት በንባብ አሰምቷል፡፡ በዚህ መሰረትም ፍርድ ቤቱ በክስ መቃወሚያው ላይ የቀረቡትን ዝርዝር ነጥቦች መርምሮ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ አቃቢ ህግ ክሱን እንዲያሻሽል ትዕዛዝ ሲሰጥ፣ በሁለተኛነት ቀርቦ የነበረው የክስ ይዘት በአንደኛው የክስ ይዘት ላይ መጠቃለል ስለሚችል ሁለተኛውን የክስ ይዘት ፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አድርጎታል፡፡
በክስ ዝርዝሩ ላይ ተከሳሾቹ ‹‹ለአመጽ ማነሳሳትና መምራት›› የሚያስችል ስልጠና ወስደዋል በሚል በተጠቀሰው ላይ ስልጠናው መቼ፣ በማን እና በምን ጉዳዮች ላይ ተሰጠ የሚለው ግልጽ ስላልሆነ አቃቢ ህግ ክሱን እንዲያሻሽል ተጠይቋል፡፡
በተጨማሪም ተከሳሾቹ አመጽ ለመምራት የስራ ክፍፍል አድርገዋል በሚል የተጠቀሰባቸው የክሱ ይዘት ‹‹ምን አይነት የስራ ክፍፍል፣ ማን ምን እንዲሰራ ክፍፍሉ ተደረገ›› የሚለውን ስለማያመለክት ይህንንም መሻሻል እንዳለበት ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
በተጨማሪም በክሱ ዝርዝር ላይ ‹‹ቡድን›› እና ‹‹ድርጅት›› በሚል (ግንቦት 7፣ ኦነግ ወይስ ሌላ የሚለውን ስለማይገልጽ) በደፈናው የቀረቡት ነጥቦች ላይ በዝርዝር መቀመጥ ስላለባቸው አቃቢ ህግ ማሻሻያ እንዲያደርግ ታዝዟል፡፡
በሌላ በኩል የተከሳሽ ጠበቆች ‹‹በኢሳት ሬድዮና ቴሌቪዥን መረጃ በመስጠት›› በሚል ተከሳሾች ላይ የቀረበው የክስ ይዘት ሆን ተብሎ ወደ ሌላ አካል (ግንቦት 7) ጋር ለማገናኘት ነው በሚል ያቀረቡትን መቃወሚያ፣ ‹‹በኢሳትና በግንቦት 7 መካከል ያለው ግንኙነት ወደፊት በማስረጃ የሚታይ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ መቃወሚያውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ከተከሳሽ ጠበቆች መካከል የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን ከችሎቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ጠበቆች ላይ የቀረበውን የክስ መቃወሚያ ጊዜ ወስዶ መርምሮ ውሳኔ እንዳሳለፈ ጠቅሰዋል፡፡ ይሻሻላሉ የተባሉት የክሱ ይዘቶች ላይ ጥያቄ የተነሳላቸው አቶ አምሃ የውሳኔው ዝርዝር በጽሑፍ ገና እንዳልደረሳቸው ጠቅሰው፣ ‹‹አቃቢ ህግ በታዘዘው መሰረት ክሱን የማያሻሽል ከሆነ ይሻሻላሉ የተባሉት የክሱ ይዘቶች ውድቅ የሚሆኑበት አሰራር አለ›› ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ክሱ ተሻሽሎ መቅረብ አለመቅረቡን ለማየት ለህዳር 24/2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ሰበር ዜና – አዲስ አበባ በግድግዳ ላይ መፈክሮች ተጥለቅልቃ አደረች:ደፍሮ መፈክሮቹን የሚያነሳ አልተገኘም: Photos And Video

ኢወጋን – በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የቅስቀሳ መልእከቶችን ለህዝብ እይታ አብቅቷል።
የአትዮጵያ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ኢወጋን)አባላት በአዲስ አበባ ዋና ዋና የህዝብ መገናኛ ቦታዎች እና የአውቶብስ መጠበቂያ የገበያ ቦታዎች ላይ የወያኔን ስርአት የሚያወግዙ እና ስርአቱን ለማውረድ ህዝቡ በጋራ እንዲነሳ የሚያደርጉ ጥሪዎችን ያነገኡ መፈክሮችን በመለጠፍ እንዲሁም ለፖሊስ እና ጦር ሰራዊቱ የሚገባውን የአንድነት እና የህዝብህን አድን ጥሪ በማስተላለፍ የተሳካ ስራ መስራታቸውን ከአዲስ አበባ ኢወጋን የደረሰን መረጃ ያመለክታል::በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የቅስቀሳ መልእከቶችን ለህዝብ እይታ አብቅቷል።
መላው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከኢወጋን ጎን እንዲሰለፍ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል።
በቭድዮ የተደገፈ ዝርዝር ዜናውን በኢትዮጱያ ወጣቶች ድምጽ በኩል ይፋ እናደርጋለን።
ያለ መስዋዕትነት ድል የለም !!! – የኢትዮጵያ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ኢወጋን)አዲስ አበባ

የ24 ሰዓት ተቃውሞ በአዲስ አበባ ! Yidnekachew Kebede
ደካማ የመንግስት አስተዳደር ለመለወጥ ምርጫ ያስፈልጋል፡፡ይሁን እንጂ ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም፣ በምርጫ ሥም ጫፍ ላይ የደረሰው ሠላማዊ የነጻነት ትግል ጥያቄ መዳፈን የለበትም፡፡
======================
“ብልህነት የተሞላበት ታላቅ የትግል መርህ ማድረግና መስፋፋት፣ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ፣ጠንካራ ሥራና ሥነ-ሥርዓታዊ አበራታች ትግል ለድል የመብቃቱ ዕድል የሰፋ ነው፡፡” ይህ ፁሑፍ የተወሰደው ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ከሚለው ከ ጄን ሻርፕ መፃሐፍ ነው፡፡ በዙህ አጋጣሚ ይህ መፃፍ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፣በተለይ በአገር ውስጥ ለሚንቀሳቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ለሚያደርጉት አመፅ አልብ ትግል ብዙ አመላካች መረጃዎችን የሚሰጥ ነው፡፡ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብና የመንግስትን የፖሊሲ ውሳኔዎች እና አሰራሮች የመቃወም መብታቸው የተጠበቀ ነው፣በሰላማዊ ሰልፍ፣በተቃውሞ የፊርማ ሰነድ ፣ለመንግስት ጥሪ ባለመተባበር፣በሥራ ማቆም አድማና በመሳሰሉት ዘዴዎች ተቃውሞ መግለፅ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የዲሞክራሲ መብት ነው፡፡ በዓለም አቀፍ የተባበሩት መግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባሄ ባፀደቀው መግለጫ ኢትዮጵያም በፈረመችው ስለ መሰብሰብ እና መደራጀት መብቶች የሚከተሉትን ብሏል ‹‹ የዜጎች የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ተግባራዊ ሂደት ገደብ በማይጣልበት ሁኔታ መከበር ሲኖርበት ነገር ግን ገደብ ቢደረግ እንኳን ገደቡ የዓለም ዓቀፍ ህግና ሰብአዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ እና የእነዚህን መብቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ እዉን የሚያደርግ መሆን አለበት፤በተለይም ዜጎች የፖለቲካ እና የአይማኖት ለማስከበር የሚያደርጓቸው ተቃውሞዎች መደገፍ አለባቸው፡፡ ››የሚል ሲሆን ፡፡የኢፌዴሪ ህገ መንስት አንቀፅ 30 ንዑስ አንቀፅ 1 ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዞ በሰላም የመሰብሰብ ፣ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ ነፃነት እና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ በማለት በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ይህ መብት ምን ያህል በአገራችን ተፈፃሚ ነው ብሎ መጠየቅ እና ምላሹን ማወቅ ብዙ እርቀት መሄድን የማይጠይቅ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት እና ቦታ በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲ የተደረጉ አመፅ አልባ የአደባባይ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ምን ያህል ፈተኛ እንደነበሩ ለአብዛኞቻችን ግልፅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሂደቶ የገዥው መንግስት ፍላጎት ከማስጠበቅ አንፃር እንጂ በየትኛውም ሕግ ድጋፍ ሣይኖረው አብዛኛው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውጤት አልባ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ይህ ማለት ግን የተደረጉ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ውጤት አልነበራቸውም ማለት አይደለም፡፡ መንግሰት የሕግ ድጋፍ ሣይኖረው በራሱ ፍላጎትና ፍራቻ ብቻ የህዝቡን ቅሬታዎች ሁሉ ጫና በመፍጠር አፍኖን እንገኛለን፡፡ እንዲህ አይነቱን ሕገ-ወጥ መንግስታዊ ሥራ፣ አልቀበለም ማለት የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግዴታም ነው፡፡ይህን ደግሞ የማሳውቅ እና የማንቃት ኃላፊነት ስለ-አገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ የሚመለከተው ሲሆን ፣በተለይ ፓርቲዎች የቀን-በቀን ሥራቸው መሆን አለበት፡፡ይሄንን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የተረዱ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም ትብብር የመሰረቱት ዘጠኝ ፓርቲዎች “ ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የሕዝባዊ ትግል ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር እንቅስቃሴ ይፋ አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ የተቃወሞ እንቅስቃሴ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር የተጠራ አመፅ አልባ የ24 ሰዓት የአዳር የአደባባይ የተቃውሞ ትይንት በታሪክ የመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡እንዲህ አይነቱ የሞራል የበላይነት እና ጥልቀት ያለው ሃሳብን የሚጠይቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጥሪ ላስተላለፉት ፓርቲዎች በሙሉ አድናቆትን በሙሉ ልብ የሚያሰጥ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሌሎች እውነተኛ የተቃዋሚ የፓርቲዎች በትብብሩ ያልታቀፉ፣ በተለይም በሂደቱ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ተሳትፋው በተለያየ ምክንያት የስምምነቱን ሰነድ ያልፈረሙ፣ የተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከጋራ ትግሉ ብትቀላቀሉ ውጤቱ የበለጠ ያማረ ይሆናል፡፡በመሆኑም ከሕግ አግባብ ውጪ በማን-አልብኝ እና ትምክተኝነት የተነጠቅነው “የአደባባይ ተቃውሞ” የምናስመልስበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡ ይዚህ ጽሑፍ አቅራቢ፣ ከዚህ ቀደም “ኢህአዴግ ለምርጫ አልተዘጋጅም” በሚል ርዕስ፡፡ “ኢሕአዴግ በጭራሽ እራሱን ነፃ ለሆነ የምርጫ ውድድር እያዘጋጀ አይደለም !የፖለቲካ ሊቃውንት እንደሚያስገነዝቡት እና ዓለም አቀፍ ነባሪዊ ሁኔታ የሚያመላክተው ለምርጫ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ ፤በእኩል ደረጃ ባይወንም እንኳን በአንፃራዊነት የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ነፃነት እና እኩል ተሣትፎ ሊኖር ይገባል፣ፓርቲዎችን ሊያወዳደሩ የሚችል ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ምርጫ ቦርድ እና ጉዳዩን ሙያዊ ስነምግባር መሠረት በማድረግ ለህዝብ መረጃ የሚያደርስ ነፃ ሚዲያ ያስፈልጋል፡፡እነዚህ መሰል ዋንኛ መስፈርቶች ባልተሟሉበት በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ግንቦት ወር ነፃ ምርጫ ማካሄድ የሚታሰብ አይደለም፡፡” ሲል ግንዛቤውን አቅርቧል፡፡ ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ፣ የተዘጋውን በር ለማስከፈት ይቻል ዘንድ በ9 ፓርቲዎች ትብበር ትግሉን የ ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል የፕሮግራም መርህ የመጀመሪያውን ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ የአንድ ወር ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡ በዕቅዳቸው መሠረት ዝግጅቱ የፕሮግራሙ የአፈጻጸም ስልት ፣የጊዜ ሰሌዳ፣ የቦታ ሽፋን፣የፋይናንስ ምንጭ፣ ዓላማዎች፣ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮችና መንግስታዊና የህዝብ ክፍሎች፣ዋና ዋና ተግባራት ፣በተጨማሪም በታሳቢነት በአፈጻጸም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች/ደንቃራዎችና ሥጋቶች እንዲሁም ለፕሮግራሙን ስኬት አጋዥ ሁኔታዎች እንዲካተቱ አድርገዋል፡፡ይህ ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው የፓርቲዎቹ ጥንቃቄ የታከለበት ዕቅድ መንደፋቸው የሚያመላክት ነው ፡፡ዘጠኙ የትብብር ፓርቲዎች በህዳር ወር የሚያተኩሩባቸው የተቃወሞ ተግባራትን እንደሚከተለው ይፋ አድረገዋል፡- 1.በየቤተ እምነቱ ጸሎት ፕሮግራም እንዲደረግ ጥሪ ማድረግና አባላት እንደየእምነታቸው ተሳትፎ ማድረግ፤ 2. በምርጫ ዙሪያ የፓናል ውይይቶችን ማድረግ፤ 3. የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ፤ 4. ለመንግሥታዊ ተቋማት ደብዳቤ ማስገባት፤ 5. የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት፤ 6. የህዝብ ተሳትፎ ማበረታታትና ድጋፍ ማሰባሰብ፤ ናቸው፡፡ የነዚህ እንቅስቃሴዎች ማጠቃለያ ሕዳር 27 ተጀምሮ ሕዳር 28 የሚያበቃ የ24 ሰዓት የአዳር “የአደባባይ ተቃወሞ” ነው፡፡ በዚህ ፁሑፍ መግቢያ ላይ እንደተገለፀው “ብልህነት የተሞላበት ታላቅ የትግል መርህ ማድረግና መስፋፋት፣ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ፣ጠንካራ ሥራና ሥነ-ሥርዓታዊ አበራታች ትግል ለድል የመብቃቱ ዕድል የሰፋ ነው፡፡” እንደተባለው ሁሉ በዘጠኙ የተቃወሚ ፓርቲዎች የተጠራው የሕዳር ወር የተቃውሞ እንቅስቃሴ በስልት የተሞላ ስለሆነ ሂደቱ እና ውጤቱ ታሪካዊ እንደሚሆን ተስፋ የሚጣልበት ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ እንዲህ አይነት ገፍቶ የመጣ ሕዝባዊ ጥያቂ ዕድል በመስጠት ፣ለሚጠየቁ ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ይህ ደግሞ መንግሰት ደግ ስለሆነ የሚያደርገው ሣይሆን ግዴታውም ጭምር ስለሆነ ነው፡፡ሆኖም ግን ከዚህ በተቃራኒ በጦር መሣሪያ ኃይልና በደህንነት አቅም በመመካት የሕዝብን ጥያቄ ለማፈን በተለመደው መልኩ መሄድ ከባድ ቀውሶች እንዲፈጠሩ መመኘት ነው፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ አይነቱ አሉታዊ ነገር መንግስት እንዲፈጠር ቢፈለግ እንኳን፣ ሕዝብ ከፓርቲዎቹ በሚሰጠው መመሪያ ሥነ-ሥርዓታዊና ደፋር እርምጃ ፣ብልህነት የተሞላበት አካሄድ በመከትል ፤አደባባይ ይዞ የወጣውን ጥያቄ ምላሽ አሰጥቶ፣ ሁሉም ነገር በሠላም እንደሚያበቃ የለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህም መሠረት የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል›› ከሚለው አልፎ ‹‹ ተዘግቷል›› ወደሚል ድምዳሜ መሸጋገራቸውን በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጠዋል፡፡እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳችሁንም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ለሕዝብ አሳውቀዋል፤ሕዝቡ ደግሞ ወትሮም ቢሆን በአገራችን እየተካሄዱ ባሉ ምርጫዎች ሙሉ በሙሉ እምነት የለውም፡፡ይህ ደግሞ “ሰኔ እና ሰኞ” እንደሚባለው ነው፡፡ አሁን ላይ የእምነት ነጻነት ጠያቂዎች፣ጋዜጠኞች፣ጦማሪያን፣የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና አባላት፣ ከገዢው ፓርቲ የተለየ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች በአፋኝ ህጎች፣ በፈጠራ ወንጀል ተከሰው አንድም በወህኒ ወይም በስደት ይገኛሉ፡፡በአገራችን የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት የለም፣የኑሮ ውድነት የአብዛኛ ኢትዮጵያዊ ትከሻ ያጎበጠ ነው፣ዜጎች በአገራችን ኢትዮጵያ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመንቀሳቀስ እና ንብረት የማፍራት እንዲሁም የመኖር መብት እየተነፈገ ነው፣ሥራ-አጥነት፣ስደት ፣በአገር ላይ ተስፋ መቁረጥ እና ሌሎች መሰል ችግሮች በመንግሰት አስተዳደር ድክመቶች አማካኝነት የተከሰቱ ናቸው፡፡ ስለዚህም እንዲ አይነቱ ደካማ የመንግስት አስተዳደር ለመለወጥ ምርጫ ያስፈልጋል፡፡ይሁን እንጂ ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም፣ በምርጫ ሥም ጫፍ ላይ የደረሰው ሠላማዊ የነጻነት ትግል ጥያቄ መዳፈን የለበትም፡፡ በመጨረሻም ለዚህ ጽሑፍ ማጠቃለይ እንዲሆን ሙሉ በሙሉ ከዘጠኙ የፓርቲዎች ትብብር ከሰጡት ጋዜጣዊ መግላጭ ሃሳብ በመዋስ ነው፣የዚህም ፁሑፍ አቅራቢ ከዚህ የተለይ እምነት የለውምና፡፡ “ ገዢው ፓርቲ በጉዳይ ፈጻሚው የምርጫ ቦርድ በኩል በተለመደው መንገድ በምርጫ ሥም ለመሥራት የተያያዘውን ቧልት ራቁቱን በማስቀረት ለ ነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል በሠላማዊ ትግል አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማሳረፍ በእኛ በኩል አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈልና እስከ መጨረሻው በጽናት መቆም ” በማለት ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል ፡፡ይበል !!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
አምሳሉ ገኪዳንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ታሰሩ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የብር 20,000(የሃያ ሺህ ብር) ዋስ ተጠይቆበት ወደ ማረፍያ ክፍል መግባቱ ታወቀ፡፡
ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበበት ክስ የፕሬስ ህጉን በሚፃረር መልኩ ለአራት ቀናት በማዕከላዊ ታስሮ የተለቀቀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ክሱ እንደ አዲስ እንዲቀሰቀስበት ከተደረገ በኋላ ዛሬ በተለምዶ ገዳም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሁለተኛ የወንጀል ችሎት ከእንቁ መፅሔት አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን ጋር እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡
ችሎቱ በሰጠው ትዕዛዝም ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና የእንቁ አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን እያንዳንዳቸው የብር 20,000(የሃያ ሺህ ብር) ዋስ እንዲያቀርቡ እስከዛውም ወደ ማረፊያ እንዲሄዱ አዟል፡፡ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን በአሁኑ ሰዓት ችሎት መድኃኔዓለም አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 8 ጣቢያ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ የጥበብ ዝግባ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) (እ. ኤ. አ. 1935 – 2014) አረፈ !!!- Hailu Gebre Yohannes (Gemoraw-P.N.) Died !!!
( …. መርዝን በመርዝነት ስለመርዝ መመረዝ :
የመርዙን ለመርዙ በመርዙ ማስመረዝ …. )
(መርዝ ……. ::) #Ethiopia #EPRP #EthiopiaTeachers #MinilikSalsawi
iframe
የታላቁ ገጣሚ እና ባለቅኔ ሃይሉ ገብረዮሃንስ (ገሞራው) አጭር የሕይወት ታሪክ http://www.debteraw.com/gemoraw/ = ድምጽ ላጣው ሕብረተሰብ ድምጽ ሆኖ በማስተጋባቱ በሶስት መንግስታት ስቃይ ያየ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሃይሉ ገሞራው – ቨድዮውን ይመልከቱት

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ።
ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የምትፈጽመውን ጥሰት ካላቆመች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ከአዲስ አበባ መቀየር አለበት ተባለ። በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ አንጎላዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች መፍታት አለበት ብሏል።
ራፋኤል ማርኩዌዝ ደ ሞራይዝ አንጎላዊ ጋዜጠኛ ነው። በሙያው በሃገሩ አንጎላ በርካታ ክስ እና እስር እንደገጠመው ይነገራል። ባለፈው ወር በደቡብ አፍሪካ ዊትስ በተካሄደው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥሰት በመፈጸም ከአፍሪካ ህብረት ህልም በተቃራኒ ቆማለች በማለት ተችቷል። ”የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በቀዳሚነት የመላ አፍሪካውያንን ህልም ይወክላል። የሰው ልጅ ክብር እና የሰብዓዊ መብት ክብር ደግሞ የሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ህልም ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት በመጣስ በተቃራኒው መንገድ እየተጓዘች ነው። ይህ ደግሞ የአፍሪካውያንን ህልም አይወክልም። የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች በመፍታት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትን እንዲያከብር እና ዜጎች እና ጋዜጠኞች ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በተግባር እንዲያውሉ እንዲፈቅድ የአፍሪካ ህብረት ጫና ማድረግ ይኖርበታል። ”
ራፋኤል በጉባኤው የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን እስር እና ክስ እንዲሁም የቀድሞው ፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን የሶስት አመት ብያኔ በማሳያነት አንስቷል። አፍሪካውያን ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቸልታ አልፈዋል ሲልም ተችቷል። ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ማክበር ካልቻለች የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ መነሳት ይኖርበታል ብሎ ያምናል።
”የተወሰኑ ጋዜጠኞችን አውቃለሁ። በ2005 ተኩስ ሲጀመር እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በአዲስ አበባ ነበርኩ። አሁን በሃገሪቱ ስላለው ሁኔታ በቂ ግንዛቤ አለኝ። ከኢትዮጵያውያን ምሁራን እና አሁን ባለው መንግስት የተለያየ ጫና የደረሰባቸውን ሰዎች አገኛለሁ። የአፍሪካ ህብረትን ለመወከል በመጀመሪያ ሰብዓዊ መብትን የሚያከብር ሃገር እንፈልጋለን። ኢትዮጵያ ይህንን ማድረግ ካልቻለች እንደ አፍሪካዊነታችን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫውን ዜጎች ራሳቸውን የመግለጽ እና ሰብዓዊ መብት ወደ ተከበረበት ሃገር እንዲዛወር መጠየቅ ይኖርብናል። ምክንያቱም ግለሰቦች የሚከበሩባት መንግስታት የህዝብ አገልጋይ እንጂ ከህግ በላይ ያልሆኑባት አጋርነት የጠነከረባት አፍሪካን እንሻለን። ኢትዮጵያ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ይህን እያደረገች አይደለም። ””
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት ብቻ በኢትዮጵያ ስድስት የህትመት ውጤቶች ሲዘጉ ከ ሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች መሰደዳቸውን ይፋ አድርጓል። በምህጻሩ ሲፒጄ ተብሎ በሚጠራው የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋም መሰረት ደግሞ ቢያንስ 17 ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ በእስር ላይ ይገኛሉ። ራፋኤል ማርኩዌዝ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ አፍሪካውያን ሊተባበሩ ይገባል ሲል ይናገራል።
”አፍሪካውያን በሙሉ በተለይም ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በትብብር ከሰራን የኢትዮጵያ መንግስት ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንችላለን። አላማችን ኢትዮጵያን ማግለል አይደለም። አላማችን ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንድታከብር ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትንም እንድትፈታ ነው።”
ኤፈርት – የሙስና መርከብ – አገርን ለማጥፋት የተቋቋመ ተቋም

“ኤፈርት-መር ካፒታሊዝም” ብዙዎችን እያደኸየ ጥቂት የወያኔ ጎጠኞ ገዢዎችን ግን በሃብት
እያንበሻበሸ በመገስገስ ላይ ነው። ለመሆኑ ኤፈርት ምንድነው? የማነው?
ኤፈርት /በትግርኛው ምህፃር “ትእምት” ወያኔ በረሃ እያለ ባንኮችን፣ የመንግሥት መኪናዎችን እና የግለሰቦችን ንብረት
በመዝረፍ ያቋቋመው ህገ-ወጥ የዘራፊዎች ድርጅት ነው፡፡ ወያኔ የሚኒሊክ ቤተመንግስትን ከተቆጣጠረ ወዲህም
ኤፈርት ራሱን በአስራ ሶስት ግዙፍ ኩባንያዎች አደራጅቶ በሁሉም አቅጣጫ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመቦጥቦጥ የወያኔ
ሹማምንትን ኪስ እንዲያደልብ አደራ የተጣለበት ተቋም ነው።
በዚህም መሠረት መሶበ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ አዲስ የመድሃኒት
ማምረቻ፣ ኢዛና የማዕድን ልማት፣ ጉና የንግድ ድርጅት፣ ሕይወት የግብርና ሜካናይዜሽን፣ ሳባ እብነ በረድ ማምረቻ፣
ሼባ የቆርቆሮ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ አልሜዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ ኤክስፕረስ የትራንዚት አገልግሎት፣
ኢትዮጵያን እንወቅ አስጎብኚ ድርጅት እና ትራንስ ኢትዮጵያ የጭነት ማመላለሻ አገልግሎት የተሰኙ ግዛዙፍ
ኩባንያዎችን አቋቁሞ እንደ ተባይ ድሆች ኢትዮጵያንን የሚመጥ “ካፒታሊዝም” ኢትዮጵያ ውስጥ ለማንሰራፋት
ተንቀሳቀሰ። ከጥቂት ዓመታት ሥራ በኋላ የቁጥጥር አድማሱን በማስፋት ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ፋብሪካ፣ ማይጨው
ፓርቲክል ቦርድ ፋብሪካ፣ ዲማ የማር ማጣሪያ፣ አላጌ ደንና የደን ውጤቶች፣ ናሽናል ጂኦ-ቴክስታይል እና አበርደሌ
የእንስሳት ማድለቢያና ኢክስፖርት ድርጅት የተባሉ ስድስት ኩባንያዎች የያዘው ደጀና ኢንዳውመንት ተጨመረለት።
ይህ በአደባባይ የሚታወቀው ኤፈርት ነው። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በቅርበት የሚከታተሉ እንደሚያውቁት ሁሉ ኤፈርት
በኮንትሮባንድ ንግድ ጭምር የገባ “ወንበዴ ድርጅት” ነው። ኤፈርት ያሻውን ያህል ተበድሮ ያለመክፈል ልዩ ፈቃድ
ያለው ቅምጥል ድርጅት ነው፡፡ እስካሁን ከሶስት ቢሊዮን በላይ የባንክ እዳ እንደተሰረዘለት ይወራል፡፡ የህወሓት
ማዕከላዊ ኮሚቴ በተሰበሰ ቁጥር ከማይቀሩ አጀንዳች አንዱ ትዕምት (ኤፈርት) ነው። ለኤፈርት የቦርድ አባላትንም ሥራ
አስኪያጆችንም የሚሾምለት ህወሓት ነው። የአገሪቱ የፓርቲዎች ህግ ፓርቲዎች እንዳይነግዱ ይከለክላል። ህጉ ሕወሓት
ላይ አይሠራም። እርግጥ ኤፈርት ዘራፊ እንጂ ነጋዴ ስላልሆነ አዋጁ አይመለከተውም።
የኤፈርት ኢትዮጵያን የመዝረፍ ሕልም ትልቅ ነው። “በግል” ባንኮችም የአንበሳ ድርሻ አክሲዮን በመያዝ የፋይናንስ
ሴክተሩን ሊቆጣጠረው ደርሷል። በአገሪቱ ያሉ ያሉ ዋና ዋና የቢዝነስ ኮንትራቶችን የሚወስደው ኤፈርት ነው። ለሕዳሴ
ግድብ ግንባታም ዋና እቃ አቅራቢ ነው። የአገሪቱን 40 በመቶ የፒቪሲ (ፕላስቲክ ነክ ምርቶች) ገበያ ለመቆጣጠር
የሚያስችለውን ማምረቻ እየገነባ ነው። ኤፈርት የድሀውን ገንዘብ እየሰበሰ ለወያኔ ጄኔራሎችና ሹማምንት የሚያድል
አገርን ለማጥፋት የተቋቋመ ተቋም ነው። “የሙስና መርከብ” የኤፈርት የቤት ስሙ የሆነው ያለምክንያት አይደለም።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ከባድ አደጋ ውስጥ ነው:: ሲሉ አባላቱ ገለጹ
– “መኢአድን ለማዳን እንረባረብ::” የጠቅላላ ጉባዬ አባላቱ
– ከድርጅቱ የተባረሩ የወያኔ ቅጥረኞች በእርቅ ስም ወደ ድርጅቱ ተመልሰዋል::(አባላት)
– ጠቅላላ ጉባዬው የተካሄደው ፍጹም አምባገነንነት በሞላበት ሁኔታ ነው::
Minilik Salsawi
በኢትዮጵያ በአንጋፈነቱ የሚታወቀው እና በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተመሰረተው መአሕድን የተካው በኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ሲመራ ቆይቶ አቶ አበባው መሃሪ የተረከቡት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ (መኢአድ)ከባድ የመፈረካከስ አደጋ ከፊቱ ተደቅኗል ሲሉ የድርጅቱ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ በላኩት መረጃ ገልጸዋል::
መኢአድ ከአንድነት ፓርቲ ጋር የሚያደርገውን ውህደት ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ከድርጅቱ የተባረሩትን እነ አቶ ማሙሸት እና ኮሎኔል ታምሩን አደራጅቶ ውህደቱን በመበጥበጥ በመኢአድ ቢሮ ውስጥ ከዚህ ቀደም በተደረገ ስብሰባ ላይ ደህንነቶችን እና ፖሊሶችን አስከትሎ በመምጣት ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥ አንስተው የነበረ ቢሆንም ሳይሳካላቸው ቀርቷል::
ውህደቱ የጉሮሮ ላይ አጥንት የሆነበት የወያኔው መንግስት ምርጫ ቦርድን ተገን በማድረግ መኢአድን በማጉላላት ውህደቱ እንዳይፈጸም ከፍተኛ ደባ ከቅጥረኞቹ ከነማሙሸት ጋር በመሆን ሲፈጽም ቆይቶ በስተመጨረሻ ኢንጂነር ሃይሉን በማስገደድ የተባረሩ አባላትን አቶ አበባው መልሶ እንዲያስገባ ካላስገባ ስልጣኑን እንዲለቅ በሚል ጫና የበላይ ጠባቂነታቸውን ተገን በማድረግ የወያኔ ስራ አስፈጻሚዎች ወደ ድርጅቱ ሰርገው በመግባት ድርጅቱ አደጋ ውስጥ መሆኑን የድርጅቱ አባላት በምሬት ተናግረዋል::
ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ከዚህ ቀደም ከወያኔ ጋር ከድርጅቱ እውቅና ውጪ በራሳቸው ፍቃድ ከሟቹ መለስ ዜናዊ ጋር የምርጫ ደንብ የሚል ስምምነት ተፈራርመው ድርጅቱ እንዲዳከም እና ለወያኔዎች በሩን እንዲከፍት ያደረጉ ሰው ቢሆንም ቀደም ብለው ለትግሉ የከፈሉት አስታውጾ ታይቶ የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ እና አማካሪ ቢደረጉም በድርጅቱ ማህተም የተባረሩ ቅጥረኞች ወደ ድርጅቱ እንዲመለሱ አድርገዋል ሲሉ አባሎቹ ተናግረዋል::ኢ/ር ሀይሉ ሻውል በፍጹም አምባገነንነት ጉባኤተኛውን አፍነው እርሳቸው በሚፈልጉት መልኩ በእርቅ ጭምብል አንዱን አስወጥተው አንዱን አስገቡ፡፡ ሲሉ የጠቅላላ ጉባዬ አባላቱ ተናግረዋል::
ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘዉን መኢአድን የተመለከተ የአቶ ሸንቁጥ አየለን ጽሁፍ ያንብቡት ::
viewtopic.php?f=2&t=89291
አቶ ማሙሸት አማረ :- አዲሱ የመኢአድ ፕሬዝዳንት ተስፋና ተግዳሮት
የአቶ ሸንቁጥ አየለን ጽሁፍ ያንብቡት ::
መግቢያ –
——-
“የቱ ይቀድማል?:- በዲክራሲያዊ መርህ ላይ የቆመ ሀገር ወይስ ዲሞክራሲን ሊሸከም የሚችል ባህል ላይ የቆመ ማህበረሰብ ?” በሚለዉ ጽሁፌ የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን የዉይይትና የክርክር ባህል አለመዳበርን በማስመልከት የተወሰኑ ፓርቲዎችን እያነሳሁ ወቅሼአቸዉ ነበር:: ፓርቲዎች ዉስጥ በግለሰብ ወይም በቡድን ደረጃ የሀሳብ ክፍፍል ሲነሳ ፓርቲዎች በሀሳብ የመሸናነፍ ባህል እንዳላዳበሩ ምሳሌ አድርጌ ካቀረብኩት ፓርቲ አንዱ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ነበር:: እንዲህም ስል ፓርቲዉን በሀሳብ ሸንቆጥ አድርጌዉ ነበር:-
“መኢአድ ዉስጥ ችግር ከተፈጠረ አራት አመታት አለፉ:: በርካታ የእርቅ ጥረቶች እንደተደረጉ የኢትዮጵያ ሰዉ አስተዉሏል :: በልዬ ልዩ ሚዲያዎችም ላይ ተደምጧል:: ሆኖም በሃሳብ የተለያዩት ሰዎች አንድም ቀን ቁጭ ብለዉ ተደማምጠዉ በሀሳብ ተፋጭተዉ እና ልዩነታቸዉን አቻችለዉ መፍትሄ ላይ ሲደርሱ አልታዬም:: አንዱ ሌላዉን ይወነጅላል:: አንዱ አንዱን ሰርጎ ገብ ነዉ : ባንዳ ነዉ ሲል ስሙን ያጠፋል:: ደግሞ አንዱ እሱ ብቸኛ የድርጅቱ ተጠሪ ይሆንና ሌላዉን ለማግለል ዳዉላ ሙሉ ከዚያም ዘሎ ከቶንም ስፍር የበለጠ ሀሰትና ዉሸት ይደረድራል:: እናም መደማመጥና መነጋገር ብሎም በሀሳብ መፋጨትና ወደ መቻቻል መድረስ ቦታም አላገኙም:: አስቂኙ ነገር ታዲያ መኢአድ ዉስጥ ተከፋፍለዉ ያሉ ብድኖች ሳያፍሩ ስለ ብሄራዊ እርቅ ጉዳይ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነገር መሆኑ ነዉ:: እራሱን ከራሱ ጋር በሀሳብ ተከራክሮና ተወያይቶ ለማስታረቅ ያልቻለ ቡድን ስለብሄራዊ እርቅ ሲያወራ መስማት እጅግ አስቂኝ ነገር ነዉ::”
ይሄን ወቀሳ ያወረድኩበት በመኢአድ ላይ ብቻ አይደለም ነበር:: ሌሎችም የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎችንም አጣቅሸ ነበር:: ሆኖም ዛሬ ትኩረቴን መኢአድ ላይ አድርጌአለሁ:: ምክንያቱም ዛሬ መኢአድ ማንም ኢትዮጵያዊ ያላሰበዉን እና ያልጠበቀዉ የዲሞክራሲ ማማ ላይ ተፈንጥሮ ወጥቶ ተገኝቷልና::
ለራሱ ሀሳብና ህሊና ብቻ ተገዥ የሆነዉ ደፋሩ : እዉቁና ወጣቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባንድ ወቅት የመኢአድ ሰዎች እርስ በርስ ንክሻ እና አለመግባባት ብቻ ሳይሆን በፕሮፌሰር አስራት የሙት አመት ላይ እንኳን ሲጣሉ ቢያስተዉል ” ዛሬ የፕሮፌሰር አስራት ሙት አመት ብቻ ሳይሆን የመኢአድም ሙት አመት ነዉ” ሲል መጻፉን አስታዉሳለሁ::
እኔም ሆንኩ ተመስገን ደሳለኝ በመኢአድ ላይ ትችቶችን ያወረድንበት ወደን ሳይሆን በሚጠበቅበት ስፍርና ቁመት ልክ ሆኖ አልገኝ ስላለን ነበር:: መኢአድ ከ2003 ዓም እስከ አሁኑ ጥቅምት 30/ 2007 ዓም ድረስ ለአራት አመታታ ያሳለፈዉ ዉጣ ዉረድ እና አባላቱም በአምስት ቡድን ተከፋፍለዉ ያደረጉት ሽኩቻ ጉድ የሚያስብል ብቻ ሳይሆን ወይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚያሰኝ ነበር:: አንድ ፓርቲ አምስት ቡድን ተከፋፍሎ መልሶ ሊድን የሚችለዉ እንዴት ነዉ?
የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ወደ ዲሞክራሲ የከፍታ ጉዞ ?
========================================
ለአራት አመታት በአምስት ቡድኖች ተከፋፍለዉ የማያቋርጥ አሉባልታ: ስድብ ወቀሳና ክስ ላይ ተጠምደዉ የነበሩ ሀይሎችን ወደ አንድ ማምጣትና በዉይይት ችግራቸዉን ፈትተዉ እርቅ ወርዶ አንድ የፖለቲካ ሀይል ሆነዉ እንዲቀጥሉ ማድረግ ይቻላል? ለአራት አመታት ያስተዋልነዉ ነገር አይቻልም የሚል ፍጹም አስተማማኝ ድምዳሜ ላይ መድረስ ነበር:: ለዚህም ነዉ ከንግዲህ የመኢአድ ነገር አከተመለት የተባለዉ ነበር::
የሆኖ ሆኖ በጠንካራ ሽማግሌዎች እረዳትነት እያንዳንዱን አምስት የተለያዬ ቡድን በማነጋገር : በተለያዬ ወቅት አመራር በመሆን የተመረጡትን ሀይሎች ሁሉ በማካተት እንዲሁም አንድንም ወገንን ያላገለለ : ከገጠር እስከ ከተማ ያለዉን አመራር በማካተት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ አስገራሚ ዉጤት ላይ የደረሰ ፓርቲ ሆኖ ወጥቷል:: ዉጤቱን አስገራሚ ያደረገዉም የጠቅላላ ጉባዔዉ ሂደት እጅግ ጠንካራ: በበርካታ ሙግቶች : ክርክሮች : ፊት ለፊት በሚነሱ የተፋጠጥ አካሄዶች እዲሁም አንድም እዉነት ሳይቀር እዚችዉ እህዝብ ፊት ትፋት የሚል አካሄድ የታጀበ መሆኑ ነበር::
እያንዳንዱ ቅሬታ አለኝ የሚል ቡድን ከስድስት መቶ ተሰብሳቢ በላይ ባለበት እዉነት ስትሞግተዉ ወይ ያቀረቅራል ወይም እዉነትን ተርትሮ ለተሰብሳቢዉ ያስረዳል;: ተሰብሳቢዉ ያደምጣል: አፋጣጭ ጥያቄን ይጠይቃል ብሎም ደግሞ ብይንን ይበይናል:: መሸወድ አይቻልም:: ብዙሃን እዉነትን እሰዉ ፊት ላይ ያነባታል: ብዙሃን እዉነትን ከሰዉ ኪስ ዉስጥ በርብሮ ያወጣታል:: አሉባልታ ተናግሮ ማምለጥ አይቻልም:: ፊት ለፊት ላሉባልታዉ መልስ የሚሰጥ ወገን አለና:: ከሁሉም በላይ ደግሞ አይኑን እና ጆሮዉን አንቅቶ የሚያስተዉል ከስድስት መቶ በላይ ህዝብ አለና:: የትም መደበቅ አይቻልም:: የዲሞክራሲ ዉበቱ ህዝብ ፊት እራቁትን ስለሚያስቆም ነዉ::
እናም እያንዳንዱ ቡድን ከጥቅምት 28 እስከ ጥቅምት 30/2007 ዓም በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ግን ደግሞ የዲሞክራሲ የከፍታ ማማ ላይ የረገጠ ሊባል በሚችል የጠቅላላ ጉባዔ ሂደት ዉስጥ ያለዉ አማራጭ ወደ አንድ መምጣትና በጋራ ለዲሞክራሲ መታገል መሆኑን በደንብ የተማረበት: እያንዳንዱንም ለሌላው ወገን ያስተማረበት ወቅት ሆኖ አልፏል:: ለሶስት ቀናት በዘለቀዉ የስብሰባ ሂደት ዉስጥ እስከ ለሊቱ ስድስት ሰዓት ድረስ በማምሸት የተደረገዉ የዲሞክራሲ ከፍታ ላይ የደረሰ የሀሳብ ፍጭት: ክርክር: እና ዉይይት እጅግ ገንቢና ለወደፊት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ጥሩ ልምድ ጥሎ ያለፈ አስተምህሮት ይመስላል:: እዚህች ጋ በተለያዩ ፓርቲዎች ስር የታቀፉ ፖለቲከኞቻችን ፈገግ ሲሉ ይታዩኛል:: እኛማ የዲሞክራሲዋን ቁልፍ ጨብጠናታል ሲሉ ፈገግ ማለታቸዉ አንዱ የዲሞክራሲ ድቀት መገለጫ መሆኑን እናጣቅስና እንለፈዉ::
ሀይሉ ሻዉል ከ28-30/3007 ዓም ባሉት መጨረሻ የፖለቲካ ቀኖቻቸዉ ዉስጥ የሰጡት አመራርም ብዙዎቹን አስገርሟል:: “ከንግዲህ እኔ ከማንም ጋር ጸብ የለኝም:: እያንዳንዳችሁም እርስ በርሳችሁ መታረቅና በመሃከላችሁ ያለዉን ጸብ ንዳችሁ አብራችሁ መስራት አለባችሁ::” ይሄን አቋማቸዉን የተፈታተኑ አንዳንድ ወገኖች ቢኖሩም የብዙሃኑም ተሰብሳቢ ዋና ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ሂደትን ማዬት እንጅ ብጥብጥ ስላልነበረ ነገሮች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቅ ችለዋል:: በዉነቱ ሂደቱ እጅግ አስጨናቂ እንደነበረ ከ20 በላይ ተሰብሳቢዎችን አንድ ባንድ ቃለ መጠይቅ በማድረግ ተረድቻለሁ:: ብዙዎች እንዳሉትም በመጀመሪያ አካባቢ ሂደቱ ከመክበዱ የተነሳ አንድ አጀንዳ ላይ አንድ ቀን የመዋል አካሄድ እንደነበርም አብራርተዉልኛል::
አቶ ማሙሸት አማረ :- አዲሱ የመኢአድ ፕሬዝዳንት ተስፋና ተግዳሮት
=================================================
ማሙሸት አማረ የመኢአድ አዲስ ፕሬዝዳንት ሆኖ በከፍተኛ ድምጽ ተመርጧል:: ማሙሸት አማረ ገና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት የአንደኛ አመት ተማሪ ሆኖ ዩኒቨርስቲ እንደ ገባ ወገን ሀገርህ አይደለም ተብሎ ካባቶቹ ሀገር ሲባረርና ገደል ሲገፈተር የምን ትምህርት ነዉ ሲል ከፕሮፈሴር አስራት ጋር የፖለቲካ የትግል አዉድማ በወጣት እድሜዉ የተቀላቀለ ሰዉ ነዉ:: አቶ ማሙሸት በፖለቲካ ሂወት ዉስጥ እየተመላለሰም በርካታ የትምህርት ዘርፎችን በማጥናት እራሱን ለአመራር ብቁ ያደረገ ሰዉ ነዉ :: በማርኬቲን ዲፕሎማ: በሊደርሽፕ/አመራር/ ዲፕሎማ እንዲሁም በማኔጅመንት ዲግሪዉን አጠናቋል:: በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በፖለቲካ ሳይንስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን የቀጠለ ብርቱ የሰላማዊ ትግል መሪ ነዉ::
ለአስራ ሁለት አመታት የታሰረ ሰዉ ቢሆንም በኢትዮጵያ ፖለቲካ የማይማረር : በዲሞክራሲ ሂደት የሚያምን እና የሚያምንበትን ሀሳብ ፊት ለፊት የሚያራምድ ፖለቲከኛ ነዉ:: በቅርበት የሚያቁትም እንደሚገልጹት ለሚያምንበት ነገር ብቻ የሚኖር ሰዉ ሲሉ ይገልጹታል::
ማሙሸት በሀሳብ ልዩነት ያምናል:: በክርክር ያምናል:: ሰዉ አክባሪ እንደሆነ የሚነገርለት ማሙሸት ተናግሮ የማሳመን አቅሙን አብረዉት የሰሩ ሁሉ ይመሰክሩለታል:: ከ28-30/2007 ዓም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባዔ ላይም ይሄንኑ ተናግሮ የማሳመን ችሎታዉን እንዳስመሰከረ ብዙዎች ተስማምተዉለታል:: ሆኖም ማሙሸት አንድ ነገር አይሆንለትም:: ይሄዉም እዉሸትና መስሎ ማደር:: ይሄ ነገር ለፖለቲካ ሂወቱ ዋናዉ ተግዳሮትም አዎንታዊ ገጽታም ሆኖ ከፊቱ የተደነቀረ ይመስላል::
ለአራት አመታት ከማሙሸት አማረ ጋር በሀሳብ ተለያይተዉ የከረሙትና በማሙሸት ላይ ክፉኛ ቂም ይዘዉ የነበሩት ኢ/ር ሀይሉ ሻዉል ከማሙሸት ጋር ሲታረቁ ማሙሸት ለአቶ ሀይሉ በሽማግሌዎች ፊት ያቀረበላቸዉ አንዱ ጥያቄ “ለመሆኑ እኔ እርስዎን ሰድቤዎታለሁ?” የሚል ጥያቄ ነበር:: ሀይሉም ” እረ በፍጹም” ሲሉ መለሱ:: ማሙሸትም በማስከተል ” ታዲያ ሚዲያዉ ሁሉ ማሙሸት አማረ አቶ ሀይሉን ሰደባቸዉ እያለ ሲያናፍስ እርስዎ ዝምታን የመረጡት ለምን ነበር?” ሲል ጠየቀ:: ሀይሉም መለሱ “እኔ ለያንዳንዱ ሚዲያ ያሉባልታ ወሬ ምላሽ ልሰጥ የምችልበት እድሜ ላይ አይደለሁም” ሲሉ መለሱ::
“እኔና አንተ የተጣላንዉ አንተ ለእኔ አልታዘዝም ስላልክ ብቻ ነዉ” ሲሉ አስከትለዉ ሀይሉ ተናገሩ:: ማሙሸትም ለአቶ ሀይሉ ሲመልስ ” እኔ ለእርስዎም ሆነ ለማንም ህገወጥ በሆነ መንገድ የምታዘዝ ሰዉ አይደለሁም:: ከእርስዎም የተጣላንዉ እርስዎ የድርጅቱን ህገ ደንብ ጥሰዉ ያለስልጣንዎት የማይገቡ ዉሳኔዎችን ስለወሰኑ ነዉ::አሁንም ሆነ ወደፊት የድርጅትን ህገ ደንብ የሚጥስ መሪ አምባገነን መሪ ነዉ:: የተጣላንዉም እርስዎ ህግ ስለጣሱ ነዉ:: አሁን ያለዉን አምባ ገነን ስርዓት እየታገልን በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉስጥ ደግሞ የፓርቲ አምባ ገነንነትን አናበረታታም:: ማንኛዉንም አይነት አንባገነንነትን እንታገለዋለን እንጅ:: ” ሲል ቁርጥ ያለ መልስ መለሰ::
ማሙሸት በማስከተል እንዲህ አለ “አባቴ ገና ዩኒቨርስቲ አንደኛ አመት ተማሪ እያለሁ ጠርቶ “ወገን እያለቀ ዝም የምትሉት ምንድን ነዉ? ከፕሮፌሰር አስራት ጋር ተነስታችሁ ታገሉ:: ለእዉነት ሙት” ሲል ለእዉነት ብቻ እንድኖር መመሪያ ሰጥቶኛል:: እዉነትን ማንም ከጣሳት ከዚያ ሀይል ጋር በሀሳብ ሙግት መግጠሜ አይቀርም:: ከርስዎም ጋር የሆነዉ ይሄዉ ነዉ::” ሲል አስገራሚዉን ያባቱን ታሪክ ተናገረ:: ግን በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት አባቶች አሉ እንዴ የሚያስብል ነገር ነዉ::
እናም ሀይሉ ሻዉል ጠቅላላ ጉባዔዉ በተደረገበት ቀን አንድ አስገራሚ ነገር ተናገሩ ” እናንተ ይሄን ማሙሸትን አታቁትም:: እሱ የሚለዉ እዉነት ብቻ ትዉጣ ነዉ:: እንደ ፖለቲከኛ የሚያድበሰብሰዉ ነገር የለም:: የሚፈልገዉ እዉነቷን ብቻ ነዉ:: በአንደበቱ ሁለት ወይም አንድ ነገር አይናገርም:: አንድ ነገር ብቻ ይናገራል:: እሱም እዉነት ብቻ::”
የጠቅላላ ጉባዔዉ ተሰብሳቢ በአቶ ሀይሉ ንግግር እየተገረመ እያለ ድርጅቱን ለተወሰነ ጊዜ በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ አበባዉ ደግሞ (ከማሙሸት ጋር ጸብ የነበሩ ናቸዉ) ብድግ ብለዉ ” አቶ ማሙሸት ድርጅትን በመክዳት ወይም በገንዘብ ወይም በሌላ በምንም መጥፎ ባህሪ አይታማም :: የሱ ችግር ሀይለኝነት ብቻ ነዉ:: ተጋፋጭ ነዉ:: እልህኛ ነዉ” ሲሉ ስለ ማሙሸት አማረ ያላቸዉን አመለካከት አካፈሉ::
እንግዲህ እነዚህና ከሌሎችም በርካታ ምንጮች የሰበሰብኋቸዉ መረጃዎችን ስተነትናቸዉ ማሙሸት አማረ አሁን በተረከበዉ የፕሬዝዳንትነት ሀላፊነት ቦታ ላይ የሚያሳካቸዉ በርካታ አዎንታዊ ጉዳዮች እንደሚኖሩ መገመት ይቻላል:: እንዲሁም የሚገጥሙት ተግዳሮቶች ቀላል የሚሆኑ አይመስለኝም::
እነዚህ አሉታዊና አዎንታዊ ፈተናዎች ከኢትዮጵያ ባህላዊ ጽንፍ ዉስጥ መንጭተዉ የሚዎጡ ጭብጦች ናቸዉ:: በኢትዮጵያ እዉነት ወዳዱ ሰዉ ፍጹም እዉነት ወዳድ ነዉ:: ሸፍጠኛዉ ደግሞ ጽንፈኛ ሸፍጠኛ ነዉ:: ፕሮፌሰር ሰባስኪ የተባለ የጣሊያን ፕሮፌሰር የኢትዮጵያ ታሪክ በፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት በሚለዉ መጽሀፉ (እምሻዉ አለማዬሁ ወደ አማርኛ ተርጉሞታል ) አንድ አስገራሚ መረጃን አካፍሎናል:: ጣሊያኖች ስለ ሀበሻ ስነ ልቦና ጥናት አደረጉ:: በርግጥ ጥናቱ ወታደራዊ ጥናት ስለነበረ ያተኮረዉ የሀበሻን ሰዉ ስነልቦና ከወታደራዊ ጭብጥ አንጽር የመተንተን ስራ ላይ ነበር::
እናም የጥናቱ ዉጤት አስገራሚ ነበር:: አጭር የጥናቱ ድምዳሜም ሀበሻ ጀግና ከሆነ ፍጹም ጀግና ነዉ:: ከአፍሪካ ምድር የጀርመንን ጦር ጠራርገህ ለማስወጣት ከፈለግህ ጀግኖቹን የሀብሻ ወታደሮችን መልምል:: ሆኖም ደግሞ አበሻ ፈሪ ከሆነም ፍጹም ፈሪና አድር ባይ ነዉ:: ስለዚህ ምልመላችን ለመለዬት ከባድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል የሚል ነበር::
ልክ እንደ ጣሊያኖቹ ጥናት ሁሉ ኢትዮጵያ ባህል ዉስጥ እዉነተኛ ሰዎች ሁለት አይነት ጽንፈ ላይ የተንጠለጠለ ቦታ አላቸዉ:: አንድኛዉ ማማቸዉ የጀግናና የተወዳጅነት ማማ ሲሆን ሁለተኛዉ ማማ ደግሞ የተጠላ ማማ ነዉ:: ገትጋታ ተብለዉ የመጠላታቸዉ እድልም የዚያኑ ያህል ሰፊ ነዉ::
ለዚህ እንግዲህ ብቸኛዉ መፍትሄ ሁል አቀፍ የሆነ የጋራ አመራር እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም የተለያዩ ሀሳቦች የሚያንጸባርቁ ቡድኖችን ማበረታታት ወሳኝ ነዉ:: ማሙሸት አማረ ትልቁ የቤት ስራዉ የሚሆነዉም ይሄዉ ነዉ:: እርግጥ ነዉ ባዋቀረዉ ካቤኔ ዉስጥ አካታች ስራን እንደሰራ ብዙዎች መስክረዉለታል:: በተለያዩ ጎራ ተከፋፍለዉ የነበሩትን ልዩ ልዩ አመራሮች ሁሉ ጥሩ አድርጎ በካቢኔዉ ዉስጥ ማካተቱም ለወደፊት ሰፊ የሀሳብ ምንጭ ያለዉ አመራርን በድርጅቱ ዉስጥ እንዲፈጠር ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዳሰበ እንዲሁም ሁሉም አካላት በትክክል እንዲታቀፉ መፈለጉን አመላካች ነዉ:: የሆነ ሆኖ ግን ወደፊትም ሰፊ መሰረት ላይ የቆመ ሰፊ ማህበረሰብን የሚያካትት የአመራር ሀይል የመመስረት ጠንካራ ጥረት የሚጠበቅበት ይመስለኛል::
ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በትብብር የመስራት እና የላቀ ሀገራዊ የዲሞክራሲ እሴት ላይ መስራት ሌላዉ ትልቁ የቤት ስራዉ የሚሆን ጉዳይ ይሆናል:: በተለይም የኢትዮጵያ ሰዉ እፊት ጀምሮ ፓርቲዎች ወይ ተባበሩ አለዚያ ተሰባበሩ የሚለዉ አቋሙ ወደፊት እየጠነከረ እንደሚመጣ ይጠበቃል:: እናም መኢአድ ለዚህ የህዝብ የልብ ትርታ የሚሰጠዉ ምላሽ የማሙሸት አማረ ያመራር ብቃትን ከሚፈትኑ ጥቂት ጉዳዮች ዉስጥ አንዱ የሚሆን ይመስላል::
ሌሎች ፓርቲዎች ከመኢአድ ተሞክሮ ምን ሊቀስሙ ይገባል?
==============================
መኢአድ ለአራት አመታት በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍሎ የዳከረዉን መዳከር ከቶ እንዳይደገም ደግሞም እንዳይታሰብ ብለዉ ሌሎች ፓርቲዎች ተሞክሮ ሊሆናቸዉ የሚችል አስተምህሮት መርምረዉ ማዉጣት ያለባቸዉ ይመስለኛል:: እኛ ሀገር የፖለቲካ ትንታኔ ማድረግ: ከአንድ ሂደት ምን ተማርን ብሎ መወያዬት : ሀሳብ ለሀሳስብ ለመለዋወጥ መነሳሰት ፈጽሞ ባህላችን አይደለም:: በተለያዩ ፓርቲዎች ጥላ ስር ታቅፈዉ ያሉ ሀይሎች በተለይም አሁን በተለያዩ ብድኖች ተከፋፍለዉ ያሉ ሀይሎች ቁጭ ብለዉ ትንታኔ መስሪያ ግዜአቸዉ ይመስለኛል::
ህጋዊ መፈንቅለ ስልጣን ተደረገ ብሎ አንዱ ወገን ሲጮ አንድኛዉ ወገን አትንጫጫ ብሎ አፍ ለማሲያዝ ከመሄድ የመኢአድ ተሞክሮ ምን ይመስላል ብሎ መጠዬቅና መወያዬት ብልህነት ይመስለኛል:: ጠንካራ ዉይይትና ክርክር ሁሉንም የሀሳብ ልዩነቶች ባይፈታቸዉም ዲሞክራሲያዊ ከፍታ ላይ መዉጣት ግን ያስችላል:: ዲሞክራሲ ከፍታ ላይ የወጣ ሀይል ደግሞ ሀሳቦችን ዲሞክራሲያዊ በሆነ አካሄድ ወደ ጋራ ስምምነት ያመጣቸዋል:: ከመኢአድ መማር የሚቻለዉ ይሄን ነዉ::
በዚህ አጋጣሚ እግዚአብሄር በሰጠን ጥቂት የጽሁፍ ጸጋ ሀሳባችንን የምናካፍል ሁሉ በኢትዮጵያ ያለዉ የፖለቲካ ባህላዊ እሴት ያብብ ዘንድ እያንዳንዱ ወገን ወደ ዲሞክራሲ ከፍታ ይራመድ ዘንድ የምንጽፈዉ ጽሁፍ : የምንሰነዝረዉ ሀሳብ ዋጋ ያገኝ ዘንድ ለሚመለከተዉ ሁሉ እናሳስባን:: ሆኖም ማንንም አንማጸንም::
በአዲስ አበባ እና አስመራ ያሉት የወንበዴ መንግስቶች እየተፍረከረኩ ነው::

-በሰሞኑ የሰራዊቱ ግምገማ የወያኔው መከላከያ ሰራዊቱ እንደ ደርግ ሰራዊት ሊበተን ይችላል ተባለ::
-በአዲስ አበባ የለውጥ ሃይሎች በመተባበር የሕዝባዊ እንቢተኝነት ጥሪዎችን ለማድረግ ዝግጅት ላይ ናቸው::
-በአስመራ አርብ ቀን ሰው አልባ ተቃውሞ ከቤት ባለመውጣት ሓርነት አርቢ የተሰኘ ንቅናቄ ተጀምሯል::
Minilik Salsawi
ላለፉት 23 አመታት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሕዝቦች ላይ ከፍተኛ የቀውስ ማእበል ያስከተሉት ሕዝቦቻቸን ለስደት እና ለእስር እንዲሁም ለሞት የዳረጉት የገደሉት የሻእቢያ እና ወያኔ መንግስታት እስከዛሬ ድረስ ተደጋግፈው እዚህ የደረሱ ቢሆንም ከአሁን በኋላ ያላቸው ሃይል እየተሟጠጠ ህዝባዊ እምቢተኝነት እና አመጽ እየተፈጠረባቸው በውስጣቸውም እየተቦጠቦጡ በመፍረክረክ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል::
የሻእቢያ እና ወያኔ ባለስልጣናት በመጭው ጊዜ ማድረግ የሚገባቸውን ጉዳይ እየተገናኙ እንደሚወያዩ እና በመደጋገፍ ቀሪውን ጊዜያት በስልጣን ለመቀጠል የሚያደርጉት ሙከራ የለውጥ ሃይሎች ህዝቡን በማስተማር እያከሸፉባቸው መሆኑ ተሰምቷል::በዚህም መሰረት በአስመራ ሐርነተ አርቢ ወይንም የአርብ ነጻነት የተባለ የለውጥ ንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን ከኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ንቅናቄው ትልቅ ዉጤት አምጥቶ በአስመራ ከተማ ኢሳያስን የሚቃወም ወረቀት በብዛት ሲበተን የደህንነት አባላትና ፖሊሶችም ወረቀቶችን ሳይሰበስቡ ጥሪው ሕዝቡ ዘንድ እንዲደርስ መተባበራቸው ታውቋል። እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትንንሽ ፓርቲዎችን በትብብር በማቀፍ እንዲሁም በተናጠል በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች ታላላቅ ሰልፎችን እና ተቃውሞዎችን በማድረግ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲፈጠር ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ የለውጥ ግብረሃይልም ከባዱን ሚና በመጫወት ትግሉ እንዲፋፋም አስታውጾ እያበረከተ ነው::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህን ሰሞን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተደረገ ባለ ግምገማ ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ የአሸባሪ ሃይሎችን መቆጣጠር ካልቻለ እጣው እንደ ደርግ ሰራዊት መበተን ነው ሲሉ የግምገማው መሪዎች መናገራቸው ታውቋል:: በምድር ጦር መምሪያ ስር ባሉ የሰራዊት ክፍሎች በተደረገ ግምገማ በሁሉም አደራሾች ይህ አይነት የመበታተን አደጋ እንዳለ በይፋ ተገልጿል::የአሸባሪ ሃይሎች የተባሉት በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የዲያስፖራ ጽንፈኞች እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን የዲያስፖራ ጽንፈኞች በሃገር ቤት የሚገኙሃይሎችን በመርዳት አመጽ ሊቀሰቅሱ ሕገመንግስቱን ሊያፈርሱ ምናምን የሚል ዛቻ እና ሃይል የተቀላቀለበት መመሪያ ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የብሄራቸው ስም እየተጠራ እና እየተለየ ሲተቹ እና ሲገመገሙ እንደነበር ታውቋል::
የመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤው ተጠናቀቀ – እነ አቶ አባበውና በርካቶች ለቀው ወጡ
ነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም መኢአድ እና አንድነት ዉህደት ይፈጽማሉ ተብሎ ተጠብቆ እንደነበረና የሕወሃት ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ አመራር እውቅና አልሰጥም በሚል ዉህደቱን ማጨናገፉ ይታወቃል። ከሁለት አመታት በላይ በአቶ አበባው መሐሪ ከሚመራው መኢአድ ጋር ደብዳቤዎች ሲጻጻፍ የነበረው ምርጫ ቦርድ ፣ አንድም ጊዜ በአመራሩ ላይ ጥያቄ አንስቶ ሳያውቅ፣ ዉህደት ሊደረግ ሲል፣ ሸንካላ ምክንያት በመፍጠር ሆን ብሎ ዉህደቱን ማጨናገፉ፣ ምርጫ ቦርዱ በሕወሃት አመራር ታዞ ያደረገዉ እና ምንም አይነት ገለልተኝነት እንደሌለው ያሳየበት እንደሆነ ብዙዎች ያናግራሉ።
የምርጫ ቦርድን ሕገ ወጥ ጥይቄ ለማሟላት መኢአድ ቅዳሜ ጥቅምት 29 እና እሁድ ጥቅምት 30 ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባኤው ባለመስማማት እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ችለናል።
አርብ ጥቅምት 28 ቀን፣ የመኢአድ ላእላይ ምክር ቤት ተሰብስቦ የመኢአድ አመራር የነበሩና በተለያዩ ችግር የተገለሉ ፣ አቶ ማሙሸት አማረን ያካተተ ፣ 14 ሰዎችን ጉዳይ፣ ጠቅላላ ጉባኤው በነገታው ዉሳኔ እንዲያሳልፍ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን፣ ምንም እንኳን ከአንድንት ጋር ሊደረግ የነበረዉን ዉህደቱ ምርጫ ቦርድ ቢያጨናግፈውም፣ የምርጫ ዘመቻውን ከአንድነት ጋር በተቀናጀ መልኩ ለማድረግ በጠቅላላ ጉባኤው ዉሳኔ ለማስወሰን ታስቦም እንደነበረ ለማወቅ ችለናል።
ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው በአቶ ሃይሉ ሻዉል መሪነት የተከፈተ ሲሆን፣ ከ335 በላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዉም ነበር። እነ አቶ ማሙሸት በርካታ ሰዎች በስብሰባው እንዲገኙ ማድረጋቸዉንም ለማረጋገጥ ችለናል።
በስብሰባው ወቅት በአቶ ኃይሉ ሻዉልና በአቶ አበባው መሐሪ መካከል ጠንካራ ልዩነቶችና አለመስማማቶች የነበሩ ሲሆን ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ እንዳልተጠናቀቀም ለማውቅ ችለናል። አቶ አበባው፣ ከሁለቱ በስተቀር የሥራ አስፈጻሚ አባላት በሙሉ ለደህንነታቸው ፈርተናል በሚል ስብሰባዉ ጥለው እንደወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከስብሰባው ከወጡት መካከል የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ተስፋሁን አለምነህም ይገኙበታል።
ስብሰባው እሁድ ጥቅምት 30 በቀሩት በአብዛኛው እነ አቶ ማሙሸት የሰበሰቧቸው ተወካዮች ባሉበት አቶ ማሙሸት አማረን የመኢአድ ፕሬዘዳንት አድርገው መርጠዋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ቅዳሜ ጥቅምት 29 ቀን የተደረገ እለት የምርጫ ቦርድ ተወካይ እንዳልነበረም የደረሰን ዘገባ ሲያመለክት፣ የምርጫ ቦርድ ተወካይ በሌለበት፣ አብዛኛው የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች አልተገኙም በተባለበት የተደረገ ምርጫ ምን ያህል ሕጋዊ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ የሆነ ነገር እንደሌለ ከመኢአድ አባላት የሚደርሱ ዘገባዎች ይገልጻሉ።
ከአራት አመታት በላይ ያልታዩት ኢንጂነር ኃይሉ ሻዉል፣ በዚህ መልኩ ስብሰባው በሰላም እንዲጠናቀቅ አለማድረጋቸው እንዳልተደሰቱ የሚገልጹት አንድ ያነጋገርናቸው የመኢአድ አባል ለመኢአድ አሁን ያለበት ደረጃ በዋናነት ተጠያቂው አቶ ኃይሉ ሻወል እንደሆኑ ይናገራሉ።
በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ሊደረግ ታስቦ የነበረ አብሮ የመስራት ዉሳኔ በነበረው አለመስማምምት አልመሳካቱ ጥሩ እንዳልነበረ የተናገሩት እኝሁ የመኢ፤አድ አባል፣ “አብዛኛው የመኢአድ አባል ከአንድነቶች ጋር እየታሰረ፣ እየተደበደበ፣ እየተገደለ ነው። በተግባር የመኢአድ እና የአንድነት አባላት አንድ ናቸው” ሲሉ በአመራሮች ዘንድ አለመስማማቶች ቢፈጠሩም በሜዳ በየዞኑና በየወረዳው ያለው የመኢአድ ታግይ እንኳን እርስ በርሱ እንደ አንድነቶ ካሉ ሌሎች የትግል አጋሮቹ ጋር አንድ ሆነ እየሰራ እንደሆነም ይገልጻሉ።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ከበርካታ ተወካዮች ጋር ስብሰባዉን ለቀው የወጡት አንድ የመኢአድ ከፍተኛ አመራርር አባል፣ በማንም ድርጅት አለመስማማቶች እንደሚፈጠሩ ገልጸው፣ ብሶት ለመናገር ወደ ኢቲቪ እንደማይሮጡ ገልጸዋል።
በአቶ አማረ ማሙሽት የሚመራው መኢአድ ጽ/ቤቱን ተቆጣጥሮ አዲስ ካቢኔም እንዳዋቀረ ለማወቅ ችለናል። በዚሁ መሰረት አዲስ ካቢኔ የሚከተሉት አባላትን አካቷል፡
1: አቶ ማሙሸት አማረ (ፕሬዝዳንት)
2: ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ (ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት)
3: አቶ እንድርያስ ኤሮ (ምክትል ፕሬዝዳንት)
4: አቶ ተስፋየ መላኩ (ዋና ፅሃፊ)
5: አቶ ሰማሀኝ አብርሃም (የድርጂት ጉዳይ)
6: ኮኔሌር ትርሶት ጉልላት(የህዝብ ግንኙነት)
ገ: ወ/ሮ አለማየሁ ሞገድ (የሴቶች ጉዳይ)
8: አቶ አብርሀም ጌጡ (የውጭ ጉዳይ)
9: አቶ ሀብተማርያም ያንተ(ፋይናንስና አስተዳድር)
10: አቶ ታጠቅ አሰፋ (የወጣቶች ጉዳይ)
11:አቶ ሀይለየሱስ ሚናስ (የምርጫ ጉዳይ)
13:አቶ ተስፋሁን አለምነህ (ትምህርትና ስልጠና አላፊ)
14 : መ/አ አየለ አለ(የህግና ዲስፕሊን አላፊ)
15: አቶ ወርቁ ከበደ (የምሃል ቀጠና ሃላፊ)
16: አቶ አዳነ ጥላሁን(የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
17: አቶ ብሩ ደሲሳ( የምራብ ቀጠና ሃላፊ)
18: አቶ ገለቱ ደጀርሳ (የደቡብ ቀጠና ሃላፊ)
19: አቶ ተፈራ መንግስቴ (የምስራቅ ቀጠና ሃላፊ)\
ኤርትራና ስደት ተወራራሽ ቃላት

Eritrean refugees in North Ethiopia
በአውሮፓና በአሜሪካ፣ በአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ፣ በሩቅ ምስራቅና በአውስትራልያ ሳይቀር እያደር
ኤርትራና ስደት ተወራራሽ ቃላት (synonymous) እየሆኑ መጥተዋል። እገሌ/ እገሊት እኮ ኤርትራዊ
ነው/ነች ሲባል ስደተኛ ነው/ነች እንዴ? – ብሎ መጠየቅ የተለመደ አነጋገር ሆኗል። እዚህ አገር ስደተኞች
በዝተዋል ሲባል ሱማሌና ኤርትራውያን በዝተዋል የሚል – ድምዳሜ ላይ ይደረሳል። ኢትዮጵያውኖችም
በዝተዋል ሊባል ትንሽ ቀርቷል።
በቅርብ ዘመናት የነበሩት የኢትዮጵያ ነገስታት ከአውሮጵውያኖች ዘመናዊ መሳርያና ጥቅማጥቅሞችን
ይፈልጉ ነበርና ከባህረ ነጋሹ መሬት (ቦገስ፣ሠሃጢን) ቆንጠር እያደረጉ ለባእዳኑ ኃይላት እንደ መወዳጃነት
ይሰጡ ነበር። የስዊዝ ቦይ ሲከፈት ታድያ የቀይ ባህር ቀጠናነቱ እየጎላ በመሄዱ የአውሮጳ ቅኝ ገዝዎችን
ቀልብ እየሳበ መጣ። በመሆኑም እንግሊዝ ግብጽን – ነጭ አባይን ራሷ መቆጣጠር ፈልጋ ለጥቁር አባይ
ቃፊር በመፈለጓ ይህንኑ ኃላፊነት ኢጣልያ ላይ ወረወረች። ኢጣልያ ይህንኑ ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ
ስትቅበዘበዝ የአድዋው ጦርነት ተከስቶ የውርደት ሸማ ተከናነበች። ይሁንና ግን በወቅቱ በነበረው
አስቸጋሪ ነባራዊ ሁኔታ ኢጣልያ ከመረብ ወድያ ያለውን የኢትዮጵያ መሬት በቁጥጥሯ ሥር አደረገች።
በመሆኑም ባህረ ነጋሽን – ኤርትራ የሚል መጠርያ ሰጥተዋት ከእናት ሀገርዋ ነጠሏት።
ኤርትራውያን ከስድሣ ዓመታት በላይ በእጣልያ አገዛዝ በነበሩበት ወቅት የኢጣልያን ስልጣኔ እጅግ
ቀስመዋል። በእጃቸው ከመብላት ይልቅ ሹካና ማንኪያን መጠቀምን ለምደዋል። የቤት ቁሳቁሶችን
አጠቃቀምና በንጽህና አያያዝን ያውቁበታል። አለባበሳቸው ይማርካል። አነጋገራቸውና ዘበናይነታቸው ደስ
ያሰኛል። ጓደኝነታቸው በወረት አይደለም፣ በችግርም ይሁን በደስታ ጊዜ ከወደዱት አይለዩም።
ኤርትራውያን በክልልላቸው ጉዳይ ላይ ድብቅ ቢሆኑም እንኳን በተለያዩ ቁምነገሮች ላይ ለወዳጆቻቸው
ግልጽ ናቸው። ብዙውን ጊዜ ከሸጋዋ ኤርትራዊ ቆንጆ ጋር የተፈጸመ ትዳር እንደ አበባ የፈካ ነው።
ከትዳር አክባሪዋ ኤርትራዊ ጋር የሚመሰረት ጋብቻ ጽናትን ይወልዳል።
ኤርትራውያን ወንድምና እህቶቻችን “ኤርትራን” እንደማትታየዋ “ሠማያዊዋ ሀገራቸው” ሲያመልኳት
ሌሎቹን የአለም አሕጉራት ደግሞ እንደ “ምድራዊ ሀገራቸው” ይቆጥራሉ። ብዙዎች ኤርትራን በሩቅ ሆነው
እንደ መካና መዲና ያከብሯታል፣ ይጨፍሩላታል፣ የጀግኖች ሀገር እያሉ ያወድሷታል እንጂ ጎጇቸውን
ከእሷ ዘንድ መቀለሱን አይመርጡም። በእድሚአቸው የገፉት እንኳን ሳይቀሩ ሀገራቸውን ትተው በውጭ
ሀገር መኖር አይከብዳቸውም። መሰደዱ አላንገሸገሻቸውም። ይህን አስመልክቶ አቶ መለስ
“ኤርትራውያን እግር እንጂ ሀገር የላቸው” – አሉ እየተባለ ይቀለዳል።
ኤርትራውያን አስመራን ንጹሂቷ ትንሿ ሮማ ይሏታል። ሥዕሏ እንደ መላዓከ ሚካኤል ሥዕል ከቢታቸው
ግድግዳ ተለጥፋለች። ነግደው ያተረፉባትን – ተምረው የከበሩባትን አዲስ አበባ ግን ቆሻሻ ይበዛባታል ሲሉ
ያንቋሽሿታል። አፋቤትን፣ ምጽዋን፣ ከረንን፣ ደቀመሀሪን ያንቆላጵሷቸዋል – ረብጣ ነዋይ የዛቁባቸውን
ድሬዳዋን፣ ናዝሬትን፣ አዋሳንና ጅማን አያስታውሷቸውም።
የኤርትራና ስደት መወደጃጀት እክልላቸው መኖር ካለመፈለግ ምክንያት የመነጨ ይመስላል። ስደት
ይቀናቸዋል – ያሳምራቸዋልም። ስለ መሪያቸው አቶ ኢሳይያስ አንዳች ክፉ ነገር ለመናገር የማይፈልጉት
እነዚሁ ኤርትራውያን ይልቁንም በሳቸው ፈላጭ ቆራጭ ባላባታዊ አገዛዝ ምክንያት የመሰደዱ በር ዳግም
ክፍት ስለሆነላቸው በውስጣቸው ያከብሯቸዋል። አቶ ኢሳያስም ቢሆን በበረኸኝነት እልሃቸው ፈረንጆቹን
መናቃቸውና ፊት መንሳታቸው በሌላ በኩል ለኤርትራውያኑ የምዕራቡ ሀገር የመግቢያ ቪዛ መገኛ ስልት
ሆነ።
የኤርትራ የነጻነት ትግል – “ሕዝቡን ነጻ የማውጣት ትግል” – ወይንስ – “መሬቱን ነጻ አውጥቶ ለአቶ
ኢሳይያስ መሸለም”? – የሚለው ጥያቄ አዲስ የማህበራዊ ሳይንስ ንድፈ ሃሳብን ፈንጥቋል። ብዙ ሰዎች
ምትክ የሌላት ሕይወታቸውን ሰውተውላቸው፣ በመድፍና በታንክ እየተታኮሱላቸው የትልቅ ጋሻ መሬት
ብቸኛ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ – ባለርስቱ ፕሬሲደንት ኢሳያስ በጣት ከሚቆጠሩት የዓለም ሰዎች
አንዱ ናቸው። ግናስ ሕዝቡ አካባቢውን እንደ ኒውክለር ራድየሽን ብክለት እየፈራ የሚፈረጥጠው ለምን
ይሆን? ይህም ጥያቄ አዲስ የማህበራዊ ሳይንስ ምርምርን መፈንጠቁ አልቀረም።
በቅርቡ ሃያ አንድ ዓመት የነጻነታቸውን በዓል ያከበሩት ኤርትራውያን ታሪክ በቅጡ የመዘገበው የግማሽ
ምዕት ዓመት የጦርነትና የስደት ታሪክ አላቸው። ከሃያ አንድ ዓመት በፊት የተጎናጸፉት ነጻነት በየሀገሩ
በስደት የወጡትን ዜጎች ሊመልስ አልቻለም። ይህ ከናቅፋ የተተኮሰው የፋኖ መራዒው የነጻነት ጥይት –
“የመንፈሱን ነጻነት” – ማምጣት አልቻለም። ይልቁንም ከነጻነቱ ማግስት ጀምሮ የሚሰደደውን ሕዝብ
ብዛት ባለፈው ሰላሳ ዓመት ከተሰደደው በመብለጥ ኤርትራውያን ከሶማሌያ ቀጥሎ ምዕራቡን ዓለም
ኢትዮጵያን ጨምሮ እንዲያጨናንቁ አድርጓል። ከባለእርስቱ አቶ ኢሳይያስ ጋር የውስኪ ብርጭቆ
የሚያነሱት የግል አውሮፕላን ነጂዎቻቸው ሳይቀሩ በቅርቡ አውሮፕላኑን ሰርቀው ወደ ሳውዲ
መኮብላላቸው ራሱ አቶ ኢሳይያስ ወዳጅ አልባ መሆናቸውን ያስመሰክራል።
ኤርትራውያኖችን የስደቱ ሰለባ ያደረገው የብሔር ብሔረሰቦችን ጥያቄ አስመልክቶ ንድፈሀሳባዊ ግንዛቤን
ለማግኘት የማርክስንና ኤንግልስን ሥራዎች በጥሞናና ስነምግባራዊ በሆነ መንገድ መረዳትን ይጠይቃል።
በተጨማሪም የራሽያ የጥቅምቱ አብዮት ክስተትንና ተያይዞ የመጣውን የብሔር ጥያቄ ጽንሶችን በጽሞና
መመርመርም ከውዥንብር ያድናል። በእርግጥ የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄ አቀንቃኞች ማርክስና ኤንግልስክ
ብቻ ሳይሆኑ ቦልሸቪኮች፣ ሮዛ ሉክሰምበርግና ካርል ካውትስኪም ተጠቃሾች ናቸው።
ማርክስ እ/ኤ/አ በ 1848 ዓ/ም ወደ ተሻለ ማህበራዊ ብልጽግና ደረጃ የሚያሸጋግሩት የምርት ኃይሎች
እድገት (productive forces) ወሳኝ እንደሆኑ አትቶ ይኸው ሂደት በተለያዩ የብሔር ጥያቄዎች ላይ
እንኳን ቢሆን ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ ገልጿል። በመሆኑም በሰራተኛው መደብ (working class) ትግል
ውስጥ የብሔር ጥያቄ የሞተ ነው ሲል ማርክስ ጨምሮ አብራርቷል። የሰራተኛው ትግል መደቦችንና
(classes) ብሔሮችን (nationalities) ስለሚያጠፋ የብሔሮች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ቦታ
አያገኝም ብሎ ነበር። የማርክስ ዋነኛ መፈክር የዓለም ሠራተኞች ሁሉ ተባበሩ ነበር። (workers of all
countries unite)
ማርክስና ኤንግልስክ ከ እ/ኤ/አ 1850 በፊት ስለ ብሔር ጥያቄ በቂ ንድፈሃሳቦችን ያልቀረጹ ቢሆንም ቅሉ
እ/ኤ/አ – በ 1863 በተከሰተው የፖላንድ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ብሔራዊ ጥያቄ ላይ
አስተሳሰባቸውን በመለወጥ አየርላንድ ከእንግሊዝ ተገንጥላ ራሷን ማስተዳደር ትችላለች የሚል ጠበቅ
ያላለ፣ ብዥታዊ መደምደምያ ላይ ሊደርሱ ቻሉ። ሌኒንም በተመሳሳይ በሠራተኛው መደብ ልዕልና ላይ
በማተኮር የአርመንያኑ ሶሻል ደሞክራሲ የመገንጠልን ጥያቄ በሠራተኛው መደብ ነጻ መውጣት ይፈታል
ቢልም ቅሉ ሀሳቡን በመለወጥ የተጨቆነ ብሒረ እስከ መገንጠል ሊያደርስ የሚችል መብት አለው ሲል
ድንብርብር ያለ ጽሁፍ ሞነጫጭሯል። በሌላ በኩል ደግሞ ስታሊን – ሌኒንን መሠረት በማድረግ አንድ
ሕዝብ ተመሳሳይ ቋንቋ ከተናገር፣ ባንድ አካባቢ ሳይነጣጠሉ የሚኖሩ ከሆኑ፣ አካባቢአቸው ድንበር
ሊበጅለት የሚችል ከሆነ፣ ሕዝቡ በቂ የምጣኔ ኃብት ክምችት ካለው፣ ተመሳሳይ ስነልቦናዊ አመለካከት
እንዲሁም ተመሳሳይ ባህላዊ ትስስር ካለው ብሔር ሊባል የሚያስችለውን መስፈርት ስለሚያሟላ
የመገንጠል ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል የሚል መደምደምያ ሰጠ። ሆኖም ግን ስታሊን ከነዚህ ስድስቱ
መስፈሮቶች አንድ እንኳን ለተጓደለ ብሔር ስለማይባል መገንጠል እንደማይቻል አስጠንቅቋል።
ይህ ከላይ የተመለከትነው የፈረንጆቹ አኳኋን፣ ፖለቲካ፣ ፍልስፍና፣ ርዕዮተ ዓለም፣ ብዥታ፣ አመለካከትና
ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ዘልቆ በመግባት –
“የብሔረሰቦች ስታሊናዊ ራስን በራስ ማስተዳደር እስከመገንጠል” – በሚል አጉል ሀሳብ ተቀሽሮ ቀረበ።
ሻዕቢያ ከዚህ ንድፈሃሳብ በመነሳት – “አረብ ነኝ” – የሚለውን ጀብሃ ካስወገደ በኋዋላ በመገንጠሉ ጥያቄ
ጸንቶ ሲያበቃ ኦነግን በራሱ አምሳያ በመፍጠር መከረኛይቱን ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ጦርነት አናውጦ
ሲያበቃ ተገነጠለ።
ሻዕቢያ አስቀድሞም ቢሆን ኤርትራን ለመገንጠል ያመቸው ዘንድ በንጉሡ ዘመን የተሰነዘሩትን
የኢትዮጵያን ጭቁን ሕዝብ ጥያቄዎች በራሳቸው ስውር ዓላማ ሥር ሸሽገው ላይ ላዩን ኢትዮጵያዊ
ተቆርቋሪዎች መስለው በደጋፊዎቻቸው በመታገዝ በጥንቃቄ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። ከቀዝቃዛው ጦርነት
ማክተም በኋላ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም ሃሳቦች በሚካኤል ጎርባቾቭ ፔሪስትሮይካና ግላስኖስት ተሀድሶ
አዲስ መልክ ቢይዝም ቅሉ ሻዕቢያ፣ ሕወሀትና ኦነግ በመገንጠሉ ርዕዮት ላይ ጽናታቸውን አሳዩ።
ሻዕቢያ በገሀድ፣ ሕወሀት በዘዴ ኦነግ በተቀጽላነት። እንዴት?
የኃይለሥላሴ ንጉሳዊ መንግስት በድንገት መገርሰሱ “ለማርኪሲዝም ሌኒኒዝም” ርዕዮተ ዓለም መስፋፋት
ጥርጊያ መንገድ እንዳዘጋጀ ሁሉ፣ የደርግ በራሱ የውስጡ ቅራኔ ምክንያት መፈረካከሱ ደግሞ
ለብሔረሰቦቹ “የራስን በራስ መወሰን እስከመገንጠል” ዓላማ ተግባራዊነት እጅግ ምቹ ሆነ። ድንገት
ሳይታሰብ የሚኒልክ ቤተ መንግስቱን የተቆጣጠሩት በሕወሀቱ ውስጥ የነበሩት ታጋዮች – “የታላቋ ትግራይ”
– ምስረታን መርሀ ግብር ለጊዜው ወደ ጎን ቢተዉም ቅሉ በወቅቱ ለተከሰተው ድንገተኛና አስቸጋሪ ነባራዊ
ሁኔታ ተጋለጡ። ኢሕአዲጎቹ አባቱ ሻዕቢያን ተከትሎ ኦሮምያን ለማስገንጠል ያሰፈሰፈውን ኦነግ
ለማዘናጋት እንዲሁም አዲስ አበባ ድረስ አብሯቸው የመጣውን የጦር አጋራቸውን ሻዕቢያ ላለማስቀየም
መላ በመዘየድ የብሔረሰቦች ራስን በራስ ማስተዳደር እስከመገንጠል የሚለውን የማርክሲዝም ሌኒኒዝም
ጽንሰሃሳብ አንቀጽ 39 በህገመንግስቱ ውስጥ ለማካተት ተገደዱ። ቀስ በቀስ ግን ኢሕአዲግ የኦነግን
ሠራዊት ከቦ ከማረከና መሪዎቹን ከምክር ቤቱ ሲያስወግድ ” አንቀጽ 39″ ለይስሙላ የተቀመጠች አንቀጽ
መሆኗ ገሀድ ወጣ። የሕወሃቶቹ ትግራይዋዎቹ፣ ከተወሰኑ ዓመታት ቆይታ በኋላ፣ ኤርትራውያን ቀድሞ
ያካበቱት ሃብት ንብረታቸው ተቀምቶ ባዷቸውን እንዲባረሩ ሲያደርጉ መገንጠል ፋይዳ ቢስ የእልኸኞች
ፖለቲካ መሆኑን በማሳየት ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊት ማርክስና ኤንግልስን ውዥንብር ውስጥ ከቶ
የነበረውን የብሄረሰቦች እስከመገንጠል ጥያቄን ውጤት አልባነትን በተግባር በማሳየት ለሲሪላንካ ታሚል
ተገንጣዮች አዲስ ትምሕርት አስገኙ። ኢሕአዲግ በሌላ በኩል ደግሞ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ
ግንባርን (ኦብነግ) በመፋለም ላይ ሲገኝ የመገንጠሉ ጥያቄ ከስታሊን ጋር አብሮ ለመቀበሩ ገለጻ ለማድረግ
ናይሮቢ ውስጥ ስብሰባ ጠርተዋቸዋል።
በመሆኑም ከስታሊናዊው – “የብሔር ራስን በራስ ማስተዳደር እስከመንገንጠል” – ጽንስ የተወለደችዋ
ኤርትራ ውርዴ ስትሆን አንቀጽ 39 የእንግዴው ልጅ ነው። በዚህም በዚያም ሰበብ ግን ገናናዋና ጥንታዊዋ
ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሀገር እንድትሆን ክፉ ደባ ተሸረበባት።
የመገንጠሉ ሰለባ የሆነው የኤርትራ ሀገር ሕዝብ እንደ ግለሰብ እጅግ መልካሞች ናቸው። ከሚወዷት
እናት ሀገራቸው የነጠላቸው ዘመናዊው የፈረንጆቹ ፖለቲካ ነው። ይኸው የትዕቢትና የማናህሎኝነት
ማኦኢስት ፖለቲካዊ አስተሳሰብ በተማሪዎች ንቅናቄ ዘመን ከነበሩት ተማሪዎችና የዛሬው መሪዎች
አዕምሮ ውስጥ ፈጽሞ እስካልተነቀለ ድረስ ሕዝቡ በራሱ ፈቃድ መኖር አይችልም። ፖለቲካ በማስተዋል
ካልታገዘ መከራን ይወልዳል። ፖለቲካ በጥበብ፣ በትዕግስት፣ በሥነምግባርና በጨዋነት ካልተመራ ሕዝብን
ያሸብራል። ከንቱ እልህና ጀብደኝነት ደሀውን ያሰቃያል። በምስኪኑ ሕዝብ ስቃይ የሚደሰቱ ደግሞ የኋላ
ኋላ የመከራውን ጽዋ ይጨልጡታል። የእቴጌ ጣይቱ ፍርሀት እውን ሆኖ ኢትዮጵያ ራሷ ዘመናዊ
ትምህርት ያስጨበጠቻቸው ልጆችዋ ተረከዛቸውን አነሱባት። በእርግጥ እግዚአብሔር ታሪክ ሠሪ ነው።
ኢትዮጵያን እየጠበቀ ዘመን ከዘመን አሻግሯታል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ፈጽሞ አይተዋትም።
የሻዕቢያው ባለሥልጣናትና በርከት ያሉ ኤርትራውያን ደጋፊዎቻቸው ኤርትራ ከእናት ሀገርዋ ኢትዮጵያ
መሬት ጋር ዳግም እንድትዋሀድ አይፈልጉም። ኤርትራን የጀግንነት ምሳሌአቸው፣ የስልጣኔ ምንጫቸውና
የቀይ ባህር በራቸው አድርገው ይቆጥሯታል። ማንም እንዲነካባቸው አይፈልጉም። የሕወሀቶቹ
ኤርትራውያኖቹም ቢሆን ባለርስቱ ፕሬዚደንት ኢሳይያስን ማስቀየም አይፈልጉም። ከዚህ ቀደም ሥልጣን
ላይ በነበሩት የሕወሀቱ ትግራዋዮች የተፈጸመውን ኤርትራን የኢትዮጵያ ኤኮኖምያዊ ድጋፍ ያሳጣውን
ርምጃ ለመካስ በሚቻለው ይሞክራሉ። ላንዳንዶቹ ንግዳቸውንና ቤታቸውን እየመለሱላቸው ነው።
አንዳንዶቹም የተጀጋጀውን ቅጽ እየሞሉ ኢትዮጵያው ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ፈቅደውላቸዋል።
“ጠርጥር ከገንፎም አይጠፋ ስንጥር” – ያሉ ደግሞ ነገ ምን እንደሚፈጠር ስለማይታወቅ መጠንቀቁ
ይበጃል በሚል አርፈው እተሰደዱበት ሀገር ሆነው አድፍጠዋል።
የሻዕቢያውም ሆነ የሕወሀቱ ቀን የሰጣቸው ኤርትራውያኖች በክፉም በደጉም ጊዜ አብረውት የኖሩትን
የየዋሁን ኢትዮጵያ ሕዝብ ስነልቦናዊ አመለካከት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ማናከሱን፣ ማከፋፈሉንና
ማጠላለፉን እንደ በቀል ዱላ ይጠቀሙበታል። የግፍ ሥራዎችንም የሥልጣን ዘመናቸው ማራዘምያ
ምትሀት አድርገው ሊጠቀሙበት ይሞክራሉ። “የቤት ሥራ” – የሚሏቸውን እነዚህኑ የርኩስ መንፈስ
ሕዋሳት በየፖለቲካ ማህበሮች፣ ትምህርት ቤቶች፤ ሕዝባዊ ስብስቦችና በየመዝናኛ ቦታዎቹ ሳይቀር እንደ
አንደ አንደ መተት እያሰሩ የዋሁን ኢትዮጵያዊ ያደነዝዛሉ። ታድያ ይህን እያወቁ አንዳንድ ተቃዋሚዎች
ከሻዕቢያ ጋር የመሞዳሞዳቸው ጥፋት – “የፖለቲካ ቂልነት” ወይም “የፖለቲካ ንዝህላልነት” – ተብሎ ብቻ
ሊታለፍ የሚችል አይደለም። ማን ይሙት ማን ሻዕቢያ የወያኔን መውደቅ ይሻል? ወያኔም ቢሆን ልብን
በፕሮፖጋንዳ እያደረቀ እግዚአብሄር በቃ እስከሚለው ቀን ድረስ ያሾፋል እንጂ ከኤርትራ ጫፍ እንኳንስ
ጦር ሣር እንደማይመዘዝ ያውቃል።
እግዚአብሄር በቃ ሲል ኤርትራውያን ወንድምና እህቶቻችን በበጎና በንጹህ ፍላጎት ወደ እናት ሀገራቸው
ጉያ ይመጣሉ። ተንኮል – ተንኮልን መውለዱን ያቆማል። መሠሪነት፣ ሸርና ደባ ወደ ጥልቁ ይወረወራሉ።
ጊዜው ይቅረብም ይራቅም እግዚአብሔር ይህንንም መስራት አይሳነውም።
ኢትዮጵያ ስትበደል እግዚአብሔር ዝም አይልም። ሰላምና ብልጽግና – ፍቅርና አንድነት ለመላው ሕዝብ
ይሁን።
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች። አሜን
ከሀበሻ አበበ (ኖርዌ)
ጄ/ል አበባው ታደሰና ፍጥጫው
ከአርአያ ተስፋማሪያም ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል። ከመከላከያ የጦር አዛዥነታቸው በጄ/ል ሳሞራ የኑስ እንዲነሱ የተደረጉት ጄ/ል አበባው ከአገር እንዳይወጡ የተደረገበት ምክንያት ግልፅ እንዳልሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ …
አቶ በረከት ስምኦን የስልጣን መልቀቂያቸው ለጊዜው ይቆይ በሚል ውድቅ ተደርጓል::

-በውሳኔው የማይስማማ ከሆነ በሱና በቤተሰቡ በወዳጆቹ ስም የተመዘገበው ሃብት እንዲጣራ ተብሏል::
-ሳያገግሙ ስብሰባ እንዲመራ እና ሚዲያ ላይ እንዲቀርብ ታዟል::
Minilik Salsawi
የብአዲን/ኢሕአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ያቀረቡት የስልጣን መልቀቂያ ለጊዜው በሚል ውድቅ መደረጉን ሆኖም በቅርቡ መልስ ይሰጥበታል ሲሉ የሕወሓት ባለስልጣናት መመለሳቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
አብዛኛውን ጊዜ ራሳቸውን ከቤት በማስቀመጥ እና በማዝናናት ያሳልፋሉ የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን በልባቸው ላይ በተገጠመላቸው አርቴፊሻል መሳሪያ በጤንነታቸው ላይ ከባድ እክል እንደፈጠረባቸው እና ከወራት በፊት ሳኡድ አረቢያ ታክመው ቢመጡም ሊሻላቸው እንዳልቻለ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በድጋሚ ቢሄዱም ሆስፒታሉ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ሲታወቅ ከሕክምና መልስ ወደ ቢሯቸው የገቡት በጣት የሚቆጠር ቀናት እንደሆነ ታውቋል::
ይህን ሰሞን ስብሰባ መምራት አለብህ በሚዲያ መታየት አለብህ የሚል ግዳጅ ከሕወሓት ባለስልጣናት ወርዶላቸው የተደናበሩት አቶ በረከት ማገገም እንኳን ሳይችሉ በስራ መደራረብ እንዲሞቱ እየተደረገ ነው ሲሉ ከቤተሰባቸው አንዱ የሆኑት ሲናገሩ ተሰምቷል::አቶ በረከት በከፍተኛ ህመም ውስጥ እንዳሉ ሲታወቅ የሕወሓት ባለስልጣኖች የአዜብን ቡድን እንደመቱት ወዲያው በረከትንም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ አሽቀንጥረው ካሳንቺስ አዲስ ቢሮ እንደሰጡት ሲታወቅ መገፋቱ እያንገበገበው በሽታውን እንዳባባሰበት ታውቋል::
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች በቅርቡ በጋምቤላ ተከስቶ በነበረው ግጭት የሞቱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰመጉ ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
በሪፖርቱ እንደቀረበው 27 የአማራ፣ 27 የመዠንገር፣ 2 የከፋና 4 የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል። እንዲሁም 16 የአማራና 6 የመዠንገር ተወላጆች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው፣ 36 የአማራ ተወላጆች ተፈናቅለዋል። 4 የአማራ ተወላጆችም የደረሱበት አለመታወቁ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ከተገደሉት ሰዎች መካከል የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የመዠንገር ተወላጅ የሆኑት ዳኛ ፀጋዬ ጌታሁን ሲገኙበት፣ መካሻ መንግስቱ የተባሉ ሰው ደግሞ እስከነባለቤታቸው ተገድለዋል።
ሰመጉ በግጭቱ መነሻ ዙሪያ የተናገረው ነገር ባይኖርም፣ በተለያዩ አካባቢዎች የብሄረሰቦች ግችት እየተስፋፋ ቢመጣም መንግስት ይህን አሳሳቢ ጉዳይ በዘላቂነት ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት ከችግሩ ክብደትና እየደረሰ ካለው ጉዳት አንጻር ሲታይ ጨርሶ የሚመጣጠን አይደለም ብሎአል። መንግስት ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት ለነገ የማይባል አንገብጋቢ ጉዳይ ነው የሚለው ሰመጉ፣ በመዠንገር ዞን ለተፈጠረው ሰብአዊ እልቂትና መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችንና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግልሰቦችንና ቡድኖችን አጣርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
ሰመጉ ባወጣው መግለጫ ላይ መንግስት የሰጠው አስተያየት የለም። መኢአድ የተገደሉ ዜጎችን ቁጥር ከ540 በላይ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።



ለተቃዋሚዎች…….ለድክመታችን ሁሉ ኢህአዴግ ተጠያቂ አይሆንም!!! ጋሻው መርሻ
በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ታሪክ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በህገ መንግስት እውቅና ያገኘውና በይፋ ፓርቲ መመስረት የተቻለው በኢህአዴግ ዘመን ነው፡፡ ይህ መቸም እንደ ጅምር ሊያስመሰግን የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ምንም እንኳ ኢህአዲግ ለነፍሱ ብሎ ባያደርገውም፡፡ ሁኔታዎች አስገድደውት ያደረገው እንደሆነ ቢታወቅም በይፋ መደራጀት መቻልን እንደ ትልቅ ለውጥ ነው የምወስደው፡፡
ቁም ነገሩ ግን ኢህአዲግ የፈቀደልንን ህገ መንግስታዊ (ከጫካ ስለሆነ የመጣው ያለመፍቀድ እድልም ነበረው) የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ተጠቅመን ለውጥ ለማምጣት ተንቀሳቅሰናል ወይ? የሚለው ነው፡፡ ለእኔ መልሱ አይደለም የሚል ይሆናል፡፡ ከአዛውንቱ ዶክተር አስራት ወልደዬስ በቀር አንድም እንኳ ህዝብ አስተባብሮ መሬት ያረፈ ትግል ያደረገ እና ኢህአዲግን የተገዳደረ ፓርቲ ፈጽሞ የለም፡፡ ከጠብ-መንጃ ጋር ፊት ለፊት በባዶ እጅ የተጋፈጡት ቆፍጣናው ምሁር አስራት ውልደዬስ እድሜያቸውና ክብራቸውን በማይመጥን ሁኔታ ለእስር ተዳርገው ለሞት ቢበቁም ከእርሳቸው በኋላ ለምልክት እንኳ የተንቀሳቀሰ የፓርቲ መሪም ሆነ ፓርቲ አላየሁም፡፡
ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው አንድም እንኳ የፓርቲ መሪ ለእስርም ሆነ ለሞት ሲዳረግ ታይቶ አለመታቁ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በመንፈስ አንዳች ጉዳት ደርሶባቸው አለማወቁ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የግድ ለምን አልታሰሩም ወይም አልሞቱም የሚል መንቻካ ሀሳብ ለማንሳት ሳይሆን ከኢህአዲግ አምባገነንነት አንጻር ምንም አይነት እርምጃ ያለመውሰዱ የመሪዎቹን ልክ ያሳያል ለማለት ነው፡፡ ሁሉንም የግፍ ገፈት የሚጨልጡት አባላትና ዜጋው ነው፡፡ ቆፍጣናዋን እንስት ብርቱካን ሚዴቅሳን ግን መርሳት ከቶ አይቻልም፡፡
በኢህአዲግ ክፍተት ወይም እንዝላልነት በአጋጣሚ የተገኘው የ1997 ዓ.ም ተሞክሮም ቢሆን በፖለቲከኞች ልፋት ያልመጣ መሆኑ ለክርክር የሚቀርብ አይደለም፡፡ የመለስ ዜናዊ ‹‹እንከን አልባ ምርጫ እንደርጋለን›› ፉከራን ተከትሎ ገርበብ ያውን በር ነጻነት የተጠማው ህዝብ በርግዶት ከመግባቱ በቀር ይህን አስተዋጽኦ አደርጌያለው የሚል ካለ ለክርክር ፈቃደኛ ነኝ፡፡
ምን ይሻል???
እስካሁን የነበረውን ‹‹የእናቴ ቀሚስ ጠለፈኝ›› ማስተባበያ ወደ ጎን ብለን ህዝቡ ድረስ በመውረድ ማደራጀት፤ የነጻነትን ጣዕም እንዲያውቅ ማንቃት፤ ዲሞክራሲን በተግባር ማለማመድ፤ ህዝቡ የሥነ ልቦና ለውጥ እንዲያመጣ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለውድቀታችን ሁሉ ኢህአዲግን መክሰስ ግን እንደ ቋንጣ የደረቀና አዋጭ ቢዝነስ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ለፖለቲካችን መበላሸት ኢህአዲግ ሰፊ መዳፍ የለውም የሚል የሞኝ አስተሳሰብ የለኝም፡፡ የእኔ መከራከሪያ የኢህአዲግ ባህሪ የታወቀ ስለሆነ እርሱን ወደ ጎን ትተን እና እረስተን ህዝቡ ጋር መድረስና ህዝባችን ማንቃት የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም የነቃ ህዝብ ለጭቆና ስለማይች፡፡ በተቃራኒው ያልሰለጠነና ያልነቃ ህዝብ ‹‹ቢጭኑት አህያ ቢጋቡት ፈረስ›› ከመሆን አያልፍምና፡፡
‹‹መንግስት የቆመጠው ቆማጣ አይባልም›› ብሎ የሚተርትን ህዝብ መንግስት መቁመጥ መብቱ አለመሆኑን ማስረዳት ይኖርብናል፡፡ በተቃራኒው ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን የበላይነት አንጽሮ መንገርና ሀሳብ ማስታጠቅ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሀገራችን ፖለቲከኞች ኢህአዲግን ከመክሰስ እና ሰሞነኛ ነገር ከማራገብ ያለፈ ስር ነቀል ለውጥ የምንፈልግ አይመስለኝም፡፡
‹‹ኢህአዲግ ገዳይ ነው፤ ኢህአዲግ ያስራል ፤ ያፈናቅላል፤ ያሰድዳል፤ የመንግስትን በጀት ለድርጅት ይጠቀማል፤ ይዋሻል…..ብላ ብላ ከሚል ማላዘን ያለፈ ተጨባጭ አማራጭ የለንም፡፡ አለን የምንለው እንኳ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ አይደለም ሀገርን ያክል ትልቅ ነገር ይቅርና መንደር ለመምራት የሚያስችል አቅም ያለው ፓርቲ ማግኘት ጨረቃ ላይ እንደመውጣት ያለ ከባድ ነው፡፡
‹‹የኢህአዲግ የትምህርት ፖሊሲ የተሳሳተ ነው›› የሚል ተቃዋሚ አማራጭ የማቅረብ ግዴታ አይኖርበትም፡፡ እውነታ ግን ባ ተቃውሞ ብቻ ነው፡፡ የእያንዳንዱን ፓርቲ ገመና ቀርባችሁ ስታዩት ከበርሜል ጩኸት አይለይም፡፡ ባዶ ‹‹የእንዲህ ሆነብን›› ጩኸት!! ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት ለውጥ ማምጣት ይቻለል?? በነገራችን ላይ ‹‹ኢዴፓ›› መስተካከል ያለበት እንዳለ ሆኖ ማንም ፓርቲ ሊስተካከለው የማይችል ዝርዝር የትንታኔ ሰነድ ባለቤት ነው፡፡
መፍትሄው
መፍትሄው እራሳቸውን በሸንበቆ አጥር ከልለው በጸጉር ስንጠቃ አባዜ የተበታተኑ ፓርቲዎችን ወደ አንድ ጎራ እንዲፈሱ በማድረግ ግዙፍ የሆነ እና አማራጮችን ማቅረብ የሚችል የተቃውሞ ጎራ መፍጠር ብቻ ነው፡፡ ደግሞም ይህን ለማድረግ የሚያግድ አንዳች እንኳ ምክንያት የለም፡፡ ምን አልባት እንደ ዘመነ መሳፍንት ሁሉ በዬ መንደሩ አለቃ ሆነው የከረሙት የፓርቲ አመራሮች ይህ እንዳይሆን አይታገሉም ማለት አይደለም፡፡
ነገር ግን ኢህአዲግን ከመታገላችን በፊት እነዚህን ‹‹የመንደር አውራዎች›› ልክ ማስገባት ለነገ የማይባል ስራ መሆን ይኖርበታል፡፡ መነጋገሪያችን መሆን ያለበትም ፍትህ የተጠማውን ህዝባችን መታደግ የሚችል ፋና ወጊ ፓርቲ እንዴት መመስረት ይቻላል የሚል መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ ለዛሬ እንጅ ለነገ መባል አይገባውም፡፡
በተባበረ ክንድ ወደ ነጻነት የምንጓዝበት ቀን ሩቅ አይሆንም!!
…………….እናቸንፋለን……!!!
በግንቦት ሰባትነት የተወነጀሉት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ተከሳሾች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው ::
አቶ ሀብታሙ አያሌው ግራ እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት ችሎቱን ተቀምጦ ለመከታተል መገደዱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ተከሳሾች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው ::
7 ሙስሊም ወንድሞች እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ በሽብር ወንጀልም ተሳትፈዋል›› የተባሉ ተከሰዋል ::
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት አራቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ አስሩ ተከሳሾች ዛሬ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የዋስትና ጉዳያቸውን ለማየት ለህዳር 2/2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ሀብታሙ አያሌው፣ የሽዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሺን ጨምሮ አስሩ ተከሳሾች ላይ የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ከቀናት በፊት መመስረቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የዋስትና ጉዳያቸውን አይቶ ብይን ይሰጣል ቢባልም የተከሳሽ ጠበቆች አጭር የጊዜ ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ለህዳር 2/2007 በአምስት ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከ1-5ኛ እና የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ የተከሳሾች የዋስትና ጉዳይ ከመታየቱ በፊት በተከሳሾች ላይ የቀረበው ማስረጃ የገጽ ብዛት ተጠቅሶ ለጠበቃዎቹ እንዲደርሳቸውና የአቃቢ ህጎቹ ስም እንዲጠቀስ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ጠበቃው የዋስትና ጉዳዩን በተመለከተ በቃል ጥያቄውን ማድረስ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ነገር ግን ጊዜ ተሰጥቷቸው በጽሑፍ ለዳኞቹም ለአቃቤ ህጎቹም ማቅረብ እንደሚችሉ ለችሎቱ በጠየቁት መሰረት ለቀጣይ ቀጠሮ በጽሑፍ አዘጋጅተው እንዲቀርቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አቃቤ ህግ በበኩሉ ያለውን የሰነድ ማስረጃ ከክሱ ጋር አያይዞ ማቅረቡን በመግለጽ የሰው ማስረጃዎችም እንዳሉት አስረድቷል፡፡
አቶ ሀብታሙ አያሌው ግራ እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት ችሎቱን ተቀምጦ ለመከታተል መገደዱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ሀብታሙ አያሌው 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ሌሎች ተከሳሾች ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ፣ 5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ፣ 6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ፣ 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን፣ 8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ፣ 9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ፣ እና 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ 7 ሙስሊም ወንድሞች እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ በሽብር ወንጀልም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳትፈዋል በሚል አቃቤ ህግ ዛሬ ክስ እንደመሰረተባቸው ታውቋል፡፡
ተከሳሾቹም፡-
1ኛ. ተከሳሽ ጃፋር መሀመድ
2ኛ. መሀመድ ኑሩ
3ኛ. መሐመድ ሰሊም
4ኛ. ኑረዲን ጀማል
5ኛ. መሀመድ አባብያ
6ኛ. አኑዋር ጃኒ
7ኛ. ጀማል አብዱ ናቸው፡፡
= በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርት =
ኢሕአዴግ ለመርጫ አልተዘጋጀም ! ይድነቃቸው ከበደ
ኢሕአዴግ በጭራሽ እራሱን ነፃ ለሆነ የምርጫ ውድድር እያዘጋጀ አይደለም !የፖለቲካ ሊቃውንት እንደሚያስገነዝቡት እና ዓለም አቀፍ ነባሪዊ ሁኔታ የሚያመላክተው ለምርጫ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ ፤በእኩል ደረጃ ባይወንም እንኳን በአንፃራዊነት የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ነፃነት እና እኩል ተሣትፎ ሊኖር ይገባል፣ፓርቲዎችን ሊያወዳደሩ የሚችል ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ምርጫ ቦርድ እና ጉዳዩን ሙያዊ ስነምግባር መሠረት በማድረግ ለህዝብ መረጃ የሚያደርስ ነፃ ሚዲያ ያስፈልጋል፡፡እነዚህ መሰል ዋንኛ መስፈርቶች ባልተሟሉበት በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ግንቦት ወር ነፃ ምርጫ ማካሄድ የሚታሰብ አይደለም፡፡
እንደ መግቢያ፡- በመዝገበ ቃላት አተረጓጎም መሠረት “ዲሞክራሲ ማላት በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ማለት ሲሆን የመጨረሻውም ሥልጣን በሕዝብ ቁጥጥር ስር ያለ፣በቀጥታ በራሳቸው ወይም እነርሱ በወከሉት ወገን ብቻ በሥራ የሚተረጐምና በነፃ ምርጫ ስርዓት የተመረኮዘ ነው” ይላል፡፡ በአብርሃም ሊንከን አባባል “ዲሞክራሲ ከሕዝብ የወጣ ፣በሕዝብ የተመረጠና ለሕዝብ የሚያገልግል መንግስት ነው፡፡”በማለት የሰጠው ትርጓሜ በአብዛኛው ተቀባይነት ያገኝ ሃሳብ ነው፡ሦስቱ መሠረታዊ የመንግስት ምሶሶዎች ተብለው የሚታወቁት ማለትም ሕግ አውጪ፣ሕግ አስፈጻሚ እና ሕግ ተርጓሚ በሁለት መንገድ ሥራቸውን ያከናውናሉ፡፡እነኚኽም አካሄዶች ቀጥተኛ እና የተወካይ ዲሞክራሲ ተብለው ተለይተው ይታወቃሉ ፡፡
ቀጥተኛ ዲሞክራሲ ዜጎች የሚመርጧቸው ምንም ዓይነት ተወካይ አይኖራቸውም፡፡ይህ ማላት ግን አስተዳዳሪ ወይም መሪ የላቸውም ማለት አይደለም፡፡በማናቸውም ጉዳዮች ውሳኔ የሚወስነው በቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎ ነው፡፡ለየትኛውም የህዝበ ውሳኔ ጉዳዮች ፣ዜጎች በጋራ ተሰባስበው በመመክር በአንድ ዓይነት ስምምነት፣ ውይም በድምፅ ብልጫ ውሳኔ የሚያስተላልፉበት ስርዓት ነው፡፡የዲሞክራሲ እናት በመባል የምትታውቀው አቴንስ ከ4 ሺህ እስከ 7ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ስብሰባ በማካሄድ ነበር ቀጥተኛ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ተግባራዊ ታደርግ የነበረችው፡፡ይሁን እንጂ ከሕብረተሰብ ብዛት እና ከውስብስብነቱ አኳያ ለቀጥተኛ ዲሞክራሲ ተግባራዊነት የሚሰጠው ጥቅም ውስን በመሆኑ ብዙም ሳይጓዝ እንዲቀር ተደርጓል፡፡በአሁን ወቅት በዓለማችን በአብዛኛው ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የዲሞክራሲ ዓይነት የተወካዮች ዲሞክራሲ ነው፡፡እንዲህ ዓይነቱ ዲሞክራሲ ዜጎች የፖለቲካ ውሳኔዎችን የሚወስንላቸው ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ነው፡፡ተመራጮችሁም በበኩላቸው የመረጣቸውን ሕዝብ ወክለው ውስብስብ መንግስታዊ ሥራዎችን እውቀታቸውን፣ጊዜያቸውን እና ጎልበታቸውን ሰውተው ግልጋሎት ይሰጣሉ፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ፡- ከቀጥተኛ ዲሞክራሲ ይልቅ የተወካዮች ዲሞክራሲ ውጤቱ አጥጋቢ ባይሆንም፣ ተግባራዊ ለማድረግ ሙከራዎች ከዚህ ቀደም ተደርጓአል፡፡በተለይ በቀዳማዊ ንጉሳችን ኃይለ ስላሴ የተወካዮች ዲሞክራሲ ወደ አገራችን በማስገባት የዲሞክራሲ በዓላችን እንዲዳብር የተደረገው ጥረት እና ውጤት በታሪክ በአውንታዊ ጎን ተፅፎ የሚኖር ነው፡፡ይሁን እንጂ የተወካዮቹ አመራረጥ እና የሥራ ሂደታቸው ሲለካ ውጤቱ ምን እንደነበር ለታሪክ አዋቂዎች ቢተዉ የተሻለ ይሆናል፡፡ከዚህ ባለፈ በደርግ የተካሄደው የብሔራዊ ሸንጎ እና የኢሕአዴግ የ4 ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ለዜጎች ከሰጠው ፋይዳ ይልቅ የአምባገነን ሥርዓት ለማስቀጠል የሰጠው ጥቅም የበዛ ነው፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም ወዲህ፣ ገዥው መንግሰት የምርጫን መቃረብ ተከትሎ መንገዶችን ይሰራል፣ የጋራ መኖራይ ቤት ገንብቶ በዱቢ እና በረጅም ወራት ክፍያ ለተጠቃሚዎች ያስተላልፋል፣ለመንግሰት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ያደርጋል፣በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በመጠቀም የምረጡኝ ዘመቻ ይጀምራል፣አብዮታዊ ዲሞክራሲ ስልጠናና ጥምቀትን ያካሂዳል፣ዘላቂነት የሌላቸው ጊዚያዊ የሥራ እድሎችን በመፍጠር የሥራ አጦችን ካርድ ይነጥቃል፤ይህ ሣይሆን ሲቀር ኢ-ፍህታዊ ጥቅማ-ጥቅምን በመስጠት ደጋፊን ያበዛል፡፡ በተጨማሪም መቼም የማይፈፀሙ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በየቦታው የመሠረት ድንጋይ በመጣል ዳንኪራ ያስጨፍራል፣ከዚህም በላይ የሆነበትን ደግሞ ቃል ይገባል ፡፡እነዚህና መሰል የሆኑ ሁሉ ነገሮችን ማከናወኑ ለምርጫ ካርድ እንጂ ለዘለቂታዊ ልማት አይደልም፡፡የምርጫ ወቅት ሲቃረብ መንግስት ደፋ ቀና ደፈ ቀና የሚለበት ሥራ ሁሉ ለይስሙላ እንጂ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ እንደሌለው ላለፉት አራት ዙር በተደረጉ ምርጫዎች ለማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ በይበልጥ ደግሞ የፊታችን ግንቦት ወር ይካሄዳል የሚባለው ምርጭ በገዥው መንግሰት ቀጥተኛ ተፅኖ ስር በወደቀው ምርጫ ቦርድ እና ፣በመንግስት በኩል መንገስት ስል ኢሕአዴግ ወይም ወያኔ ለማለት እንደተፈለገ ግንዛቤ ይወሰድልኝ፡፡ምክንያቱ ደግሞ ገዥው ፓርቲ እና መንግስት ባልተለያዩበት ሥርዓት ውስጥ በመሆናችን ነው፡፡ስለሀኖም በእነዚህ ሁለት ሃይሎች ተፎካካሪ ወይንም አማራጭ በሆኑ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ይህ-ቀረሽ የማይባል ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ችግሩ ደግሞ ቀጥተኛ በሆነ መንግድ የሚፈፀም ስለመሆኑ ከዚህ በታች በመጠኑ ለማመላከት ይሞከራል፡፡
የገዥው መንገስት ቀጥተኛ ጫና በፓርቲዎች፡-
በዓለም አቀፍ የተባበሩት መግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባሄ ባፀደቀው መግለጫ ኢትዮጵያም በፈረመችው ስለ መሰብሰብ እና መደራጀት መብቶች በሚከተሉው መልኩ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ “ የዜጎች የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ተግባራዊ ሂደት ገደብ በማይጣልበት ሁኔታ መከበር ሲኖርበት ነገር ግን ገደብ ቢደረግ እንኳን ገደቡ የዓለም ዓቀፍ ህግና ሰብዓዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ እና የእነዚህን መብቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ እዉን የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡በተለይም ዜጎች የፖለቲካ እና የአይማኖት ለማስከበር የሚያደርጓቸው ተቃውሞዎች መደገፍ አለባቸው፡፡”የሚል ነው ፡፡
ይህ እጅግ በጣም ጠንካራ የሆነ ዜጎች በፖለቲካ የመደራጀት መብታቸውን የሚያስከበር ዓለም አቀፍ ሕግ ነው፡፡አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገመንገስት ይህን ህግ በመቀበል አካቶ ይገኛል፡፡እርግጥ ነው ህገመንግስቱ በራሱ ማሻሻይን የሚፈልጉ በርካታ አንቀፆች አሉት፡፡በዚህ አጋጣሚ ሰማያዊ ፓርቲ ዜጎችን በጋራ አግባብቶ በዘላቂነት ሊያገለግል የሚችል እና ለሕገመንግሰት መሠረት ወይም ምሶሶ የሚሆን “የዜጎች ቃል-ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ”የተሰኘ ሠነድ በማዘጋጀት ለህዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ለዚህም መልካም ጅማሮ ለሰማያዊ ፓርቲ አድናቆት ሊቸረው ይገባል፡፡ወደጉዳያችን ስንመለስ በዓለም አቀፍ እዲሁም በኢትዮጵያ ሕግ የፖለቲካን ዓላማ ለማስፈፀም ሕግን መሠረት ያደረገ አደረጃጀት የተፈቀደ ነው፡፡ይሁን እንጂ ይህን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት ኖራቸው በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቃወሚ ፓርቲዎች፤ ሰብዓዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች ይከበሩ፣የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ፣ህዛባዊ መንግሰት ይመስረት በማለታቸው እና ለተግባራዊነቱ በመንቀሳቀሳቸው ብቻ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ለሞት፣ለእስራት፣ለስደት እና ለእንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡
ይህም በመሆኑ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶቺ ታስረዋል፣የመንግሰት ታጣቂ ሃይሎች በግልፅ እና በስውር በፓርቲ አባላት ወከባና እንግልት እየፈፀሙ ይገኛሉ፣ጠንካራ የሚባሉ የተቃዋሚ ሃይሎች የቀን-ተቀን ሥራቸውን የሚያከናውኑበት ቢሮ መከራየት እንዳይችሉ አከራዩች በቀበሌ ካድሬዎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ከብዙ ልፋት እና እንግልት በኋላ በሚያገኙት ቢሮ የፓርቲ አባላቶች ወደ ቢሮ ሲገብ እና ሲወጡ እየጠበቁ የመንግሰት ደንነቶች ወከባ ከፍ ሲልም ትንኮስ እየፈፀሙ ይገኛሉ፣ ፓርቲዎች ዋንኛ የተቋቋሙለትን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ከደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን በነፃነት አደባባይ ወጥተው ቅስቀሳ እንዲሁም ተቃውሞ ማድረግ የሞት ሽረት ትግል ነው፡፡በተለይ ደግሞ አዲስ ተመዝጋቢ አባላት የአባልነታው የእጩ ቀናት መቁጠር ከመጀመራቸው በፊት በመንግሰት ታጣቂ እና በካድሬዎች የሚደርስባቸው ማስፈራሪያ እና ዛቻ ልጉድ ነው፡፡ከምንም በላይ ደግሞ የአባላትን ወራዊ መዋጮ እና ድጋፍ የፓርቲዎች የፋይናስ አቅም አይነተኛ መንግድ ነው፡፡ሆኖም ግን ይህ ገንዘብ በራሱ በቂ አይደለም፡፡ይህም በመሆኑ የፓርቲ አባላት ሣይሆኑ ደግፍ መስጠት ለሚፈልግ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ በልብ ሙሉነት ገንዘባቸውን እንዳይለግሱ ጫና ይደረግባቸዋል፡፡የጉዳዩ አሳሳቢነት ምን ያኸል እነደሆነ ለማሳያ አነድ ምሣሌ መጥቀስ ይቻልል፤አቶ የሺዋስ አሰፋ፣አቶ አብታሙ አያሌው፣አቶ ደንኤል ሽበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ በማእከላዊ እስር ቤት በዋንኛነት የሚደረግባቸው ምርመራ “የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድነው ? ማነው በቋሚነት ድጋፍ የሚያደርግላችሁ ?ገንዘቡ የት ነው የሚቀመጠው” የሚሉት ዘወትር የተለያየ የምርመራ ዘዴዎች በመጠቀም የሚጠየቁት ጥያቄ ነው፡፡ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ከላይ የተገለፁት የፓርቲ አባለት የተያዙት “በሽብር ወንጀል በመጠርጠር ነው”በማለት ገዥው መንግስት ገልፆአል ሆኖም በምርመራ ወቅት ግን የሚጠየቁት የፓርቲ ገንዘብ ወጪና ገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆን ብቻ ነጋዴው ከንግዱ፣ተማሪው ከት/ት፣ሰራተኛው ከስራው፣ገበሬው ከእርሻው፣አርብቶ አደሩ ከከብቶችሁ እየተፈናቀለ ይገኛል፡፡
ስለዚህም ተፈካካሪን የተቃወሚ ፓርቲን በእንዲህ መልኩ እያዳከመ እና አንዳንዶችን በጭራሽ ከወደቁበት እንዳይነሱ እያደረገ ይገኛል፡፡በእንዲህ መልኩ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር ኢሕአዴግ ተፎካካሪ በመሆን ለመርጫ እራሱን እያዘጋጀ ነው እንዴት ሊባል ይቻላል ?
የገዥው መንገስት ቀጥተኛ ጫና በምርጫ ቦርድ ፡-
በየደረጃው ትክክለኛ ምርጫ እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 102 ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሹመታቸው ከመንግስት መልካም ፍቃድ የመነጨ ሲሆን አሰራራቸውም ለገዥው መንግስ በእጅጉ በጣም ያደላ ነው፡፡ስለዚህም ምርጫ ቦርድ ህገመንግስቱን መሠረት አድርጎ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ለማለት ከበድ ድፍረትን የሚጠይቅ ነው፡፡የስከዛሬውም የምርጫ ቦርድ የሥራ አንቅስቃሴ ለገዥው መንግስት ያለው ታማኝነት እና አገልጋይነት በድብቅ ሣይሆን በአደባባይ “እዩልኝ፣ስሙልኝ” እያለ በራሱ ላይ መስክሮ የእኛን መስክርነት ከሰጠን አመታት ተቆጠሩ፡፡ከወረዳ የምርጫ አስፈፃሚ ጀምሮ እስከላይ ያለው የምርጫ ቦርድ ሃላፊ፣ በገዥው መንግሰት ቀጥተኛ ተፅእኖ ስር መሆናቸው ግልፅ እና አሻሚ ያልሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ላይ ከዘህ በላይ ማሣያዎችን ለማመላከት መሄድ ዉሃ ቅዳ ዉሃ መልስ ይሆናል ነገሩ፡፡
በመሆኑም ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በአገራችን የለም፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሣለ ከተፈካካሪ የተቃወሚ ፓርቲዎች ጋር ኢሕአዴግ ለመርጫ እራሱን እያዘጋጀ ነው ማለት እንዴት ይቻላል ?
የገዥው መንገስት ቀጥተኛ ጫና በነፃ በጋዜጠኛ ላይ ፡-
ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ አሳብን ለመግለፅ ይቅርና ከገዥው መንግስት ፍላጎት እና አሳብ ውጪ ማሰብ በራሱ ለእስራት እና ለእንግልት ይዳርጋል፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለማችን መጥፎ ሪከረድ አስመዝግባለች፡፡በአሁን ወቅት ከ17 የማያንሱ ጋዜጠኞች በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡21 የሚሆኑ ጋዜጠኖች በስደት መከራን እየተቀበሉ ነው፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ተጠራርጎ ቃሊቲ የሚገባበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡በውጪ አገር የሚገኙ የተለያዩ ሚዲያዎችም ቢሆኑ፣በአገር ውስጥ ተደማጭ እና ተነባቢ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ አፈና እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
ስለዚህም ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ተፈካካሪ ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻ ቅስቀሳ የሚያደርጉት በይትኛው ነፃ ጋዜጣ እና መፅሔት ነው ? ህሊናውን እና ሙያውን ብቻ መሠረት አድርጎ የሚሰራ ጋዜጠኛ ምን ያህል አለ ? እርግጥ ይህ ፁሑፍ የቀረበበት ሚዲያ ጋዜጣ በቀጣይ የሌሎች ጋዜጣ እና ጋዜጠኞች እጣ ፈንታ እንደማይደረሰው በምንም እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡በምንም!!
እናም ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ጋዜጠኛ እና የእትመት ውጤት ሣይኖር መርጫ እንዴት ይታሰባል፡፡አገራችን በጋዜጠኛ ድርቅ እንድትመታ ገዥው መንግሰት ሆነ ብሎ ያደረገው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ይህ በሆነበት ሁኔታ ኢሕአዴግ ለመርጫ እራሱን እያዘጋጀ ነው ማለት በራስ ላይ እንደመተኮስ ይቆጠራል ፡፡
ከላይ በመጠኑ የዚህ ፁሑፍ አቅራቢ ለመዳሰስ የሞከራቸው እና ሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ኢሕአዴግ በጭራሽ እራሱን ነፃ ለሆነ የምርጫ ውድድር እያዘጋጀ አይደለም !የፖለቲካ ሊቃውንት እንደሚያስገነዝቡት እና ዓለም አቀፍ ነባሪዊ ሁኔታ የሚያመላክተው ለምርጫ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ ፤በእኩል ደረጃ ባይወንም እንኳን በአንፃራዊነት የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ነፃነት እና እኩል ተሣትፎ ሊኖር ይገባል፣ፓርቲዎችን ሊያወዳደሩ የሚችል ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ምርጫ ቦርድ እና ጉዳዩን ሙያዊ ስነምግባር መሠረት በማድረግ ለህዝብ መረጃ የሚያደርስ ነፃ ሚዲያ ያስፈልጋል፡፡እነዚህ መሰል ዋንኛ መስፈርቶች ባልተሟሉበት በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ግንቦት ወር ነፃ ምርጫ ማካሄድ የሚታሰብ አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
በሰሜን ጎንደር በተጠራ የስራ ማቆም አድማ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ:: በአድማው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጎንደር ፦ የህዝቦችን መብቶች የማይወክሉ የወያኔ ሰንደቅ አላማዎች ከሚውለበለቡበት ወረዱ ::
#Ethiopia #Gonder #Kimant #ESAT #MinilikSalsawi #Freedom
– በሰሜን ጎንደር ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ:: ESAT
– በሰሜን ጎንደር ዞን 130 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አልተገኙም።
– በአድማው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም መጨረሻ መልስ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።
እስካሁን ከ130 ሺ ያላናሱ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የቀሩ ሲሆን፣ ሌሎች ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያ ቤቶችም በአድማው ይቀጥላሉተብሎ ይጠበቃል። በተዘጉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚውለበለቡ ሰንደቃላማዎች እንዲወርዱ ተደርጓል። ሰንደቃላማዎች እንዲወርዱ የተደረገበት ምክንያት የህዝቦችን መብቶች የሚወክሉ አይደሉም በሚል ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ጎንደር የዞን ሰብሰቢ አቶ አግባው ሰጠኝ በገዢው ፓርቲ ሀይሎች ታፈነ

ትናንትና ምሽት አካባቢ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ የተወሰደው የዞኑ አስተባባሪ እስከአሁን ሰዓት ድረስ ያለበትን ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ትናንት ማምሻውን በሲቪል እና መሳሪያ በታጠቁ የገዢው ፓርቲ ሀይሎች ቤቱ ተበርብሮ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ መወሰዱን በዞኑ ያሉ የፓርቲው አካላት አረጋግጠዋል፡፡
ከሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ዞን አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ በተጨማሪም ወደ ስድስት(6) የሚደርሱ የአንድነት እና መኢአድ ፓርቲ አባላትም ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍነው መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል በጎንደር ባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነ የዞኑ ተጠሪዎች አመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል ከሥልጣናቸው ተነሱ
ለአቶ ዛይድ መነሳት ምክንያት የሆነው ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላይ ባይተነተንም፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔውን እንዳሳለፈ ደብዳቤው አትቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለትራንስፖርት ሚኒስቴር ሪፖርት ያቀርባል፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየው የመንገድ ባለሥልጣን ቦርድም ሰብሳቢ ናቸው፡፡ ሰሞኑን አቶ …
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል ከሥልጣናቸው ተነሱ Read more »
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የመጀመሪያ ዙር ህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ የ24 ሰዓት (የአዳር) የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል( VIDEO )
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር – ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡
‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ›› እንዳዘጋጀ ያሳወቀው ትብብሩ የትግሉ ዓላማ ፍትሃዊ ምርጫ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጾአል፡፡
‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል›› ያለው መግለጫው በመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ፕሮግራሙ 6 ዋና ዋና ተግባራትን ለመፈጸም ዝርዝር እቅዶችን አውጥቶ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በህዳር ወር የሚያከናውናቸው ተግባራትም፡-
1. በቤተ እምነት ጸሎት እንዲደረግና ጥሪ ማቅረብና አማኞች እንደየ እምነታቸው ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ
2. የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ
3. የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት (ሰላማዊ ሰልፍ)
4. ለመንግስት ተቋማት ደብዳቤ ማስገባት
5. በምርጫ ዙሪያ የፓናል ውይይቶችን ማድረግና
6. የህዝብን ተሳትፎ ማበረታታትና ድጋፍ ማሰባሰብ እንደሆኑ በመግለጫው አሳውቋል፡፡
ከእቅዶቹ መካከልም በሶስት ተከታታይ እሁዶች በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች 3 የአደባባይ ስብሰባዎች እንደሚኖሩ፣ በመጨረሻው መርሃ ግብርም ህዳር 27ና 28 በፕሮግራሙ ማጠቃለያነት የ24 ሰዓት (የውሎና የአዳር) የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡
በገዥው ፓርቲና በምርጫ ቦርድ ጥምረት ይፈጸማል ያለውን ህገ ወጥ ተግባር በመታገል ለሰላማዊ ትግሉ አወንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት እስከመጨረሻው በፅናት ለመቆም መዘጋጀቱን የገለጸው ትብብሩ በአገር ቤትና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ በትብብሩ ሂደት ቆይተው እስካሁን ያልፈረሙና ሌሎች ፓርቲዎች እና የዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡ 



ጦማርያነና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ።ችሎቱና 2 ዳኞች ተቀይረዋል።ለህዳር 3 ቀጠሮ ተሰቷል። የዋስትና ጉዳይ ለነገ ተቀጥሯል።
የበፍቃዱ ሃይሉ ወንድም በፎቶ ማንሳት ሙከራ ተይዟል።የዋስትና ጉዳይ ለነገ ተቀጥሯል።
Minilik Salsawi
193 ቀናት ካለምንም ማስረጃ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስት ጋዜጠኞች በዛሬው እለት በልደታ ፍርድ ቤት ተገኝተዋል ። ነጭ በመልበስ ሰላማዊነታቸውን ያሳዩት ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ በልደታ ፍርድ ቤት ሲደርሱ ፎቶግራፍ ለማንሳት ሞክሯል የተባለ የጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ወንድም በወያኔ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውሏል።
ፍርድ ቤቱ ለህዳር 3 2007 ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ማህሌት እና ኤዶም ያቀረቡትን የማረሚያ ቤቱ የሚደርስባቸውን በደል በተመለከተ ሃላፊዎቹ ቀርበው እንዲያስረዱ ት እዛዝ ሰቷል።ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለ10ኛ ጊዜ ችሎት የቀረቡት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሶስቱ ጋዜጠኞች ለሳምንት (ህዳር 3/2007 ዓ.ም) ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በጦማርያንና በጋዜጠኞቹ ቀደም ሲል የቀረበውን የክስ ማሻሻያ አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፣ ምርመራው አላለቀም በሚል ምክንያት አጭር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዛሬው ችሎት ላይ ከተሰየሙት ዳኞች መካከል ሁለቱ አዲሶች በመሆናቸው ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃ አምሃ መኮንን ገልጸዋል፡፡ ዳኞች ብቻ ሳይሆን ችሎት ክፍሉም በመቀየሩ ክፍሉ ጠባብ ነው በሚል፣ የተከሳሽ ቤተሰቦችና ጋዜጠኞች ችሎት መግባት አለመቻላቸውም ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በነገው ዕለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተከሳሾች ዋስትና ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን አቶ አምሃ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በተከሳሾች በኩል ደግሞ፣ ሁለቱ ሴት ተከሳሾች (ኤዶም ካሳዬ እና ማህሌት ፋንታሁን) በቃሊቲ ማረሚያ ላይ ያነሱትን የመብት ጥሰት አቤቱታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በቀጣይ ቀጠሮ ድጋሚ ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ሁለቱ ተከሳሾች በቀን ለ10 ደቂቃ ብቻ ስማቸው ቀድሞ በተመዘገቡ ሰዎች ብቻ እየተጎበኙ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
በአዲስ አበባ የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ይደረጋል የሚል ፍራቻ ተከስቷል።
– የወያኔ ልማታዊ ዲሞክራሲ የህዝብን መጉላላት እንደጨመረ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አማረሩ።
– አዳማ ናዝሬት ውጥረቱ የነገሰ ሲሆን ሕዝባዊ ተቃውሞ ይፈነዳል ተብሎ ተፈርቷል።
– ሕዝቡ ለታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ በመተባበር ለህግ የበላይነት እና ልእልና እንዲነሳ ተጠይቋል ።
– በአዳማ ናዝሬት የባጃጅ ባለቤቶች ሊያደርጉት የነበረው የስራ ማቆም አድማ አስተላለፉት። – የታክሲ ባለንብረቶች ከትላንትና ጀምረው ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።
Minilik Salsawi
በወያኔው መንግስት አዲሱ የልማት ስታራቴጂ በሚል በታክሲዎች እና በሕብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰ እንደሆን ነዋሪዎች በመግለጽ ላይ መሆናቸው ታወቀ ። ከትላንትና ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ በከተማው ትራፊኮች እየተካሄዱ ያሉ ድርጊቶች በከፍተኛ ሁኔታ ህዝብን ወደ ተቃውሞ የታክሲ ባለንብረቶችንም ወደ ስራ ማቆም አድማ የሚመራ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ልንጠራ እንችላለን ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የታክሲዎች ባለንብረቶች ማህበር አባል የገለጹ ሲሆን የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ከበፊትም የታሰበበትና በሂደት የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶበት እንደሚካሄድ ሲገልጹ ሕዝቡም ለዚሁ ያለውን ትብብር እንዲገልጽ በማለት ሲናገሩ ሕዝቡ ለታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ በመተባበር ለህግ የበላይነት እና ልእልና እንዲነሳ ጠይቀዋል ።
የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ መታየት አለበት በሚለው ሃሳብ የሚስማሙ ሹፌሮች እንዳሉት ከዚህ ቀደም በተለያዩ የከተማዋ ቦታዎች የነበሩት የታክሲ መጫኛዎች እንዲቀሩ የተደረጉ ሲሆን ወደተለያዩ ቦታዎች በመበታተናቸው የህዝቡ እንግልት ከመጨመሩም በላይ ሹፌሮችም ይህንን ተከትሎ በመንገድ ላይ እንዳይጭኑ ከጫኑ ከባድ ቅጣት እየተጣለባቸው ስለሆነ ከልማታዊው የትራፊክ ህግ ጋር ተስማምተው ሊሄዱ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። የታክሲ ባለንብረቶችም ይሁኑ ሹፌሮች እና ረዳቶቻቸው በልማታዊው የትራፊክ እኩይ ህግ የተበሳጩ ሲሆን ቁጣቸውን በመግለጽ ወደ ስራ ማቆም አድማ ጥሪ ለማድርግ እያመሩ መሆኑን ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዳማ ከትላንትና ጀምሮ ከፍተኛ ውጥረት እንደተከሰተ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሕዝባዊ ተቃውሞ ይፈነዳል በሚል በነገሰው ውጥረት የባጃጅ ባለንብረቶች ባጃጆቻቸው ወደ ከተማው እንዳይወጡ ይዘዋቸው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ውጥረት እንዳሌለ እና ስራwቸን እንዲጀምሩ ሲያስገዲዳቸው ውሏል።
ስራቸውን እንዲጀምሩ ቢያስገድዳቸውም የባጃጅ ሹፌሮች ስራ ለማቆም ያስነሱት ተቃውሞ በፖሊስ የከሸ መሆኑንም ተያይዞ የመጣው ዜና ይገልጻል። ሹፌሮቹ በመንግስት ትራፊኮች ከፍተኛ የአስተዳደር በደል እና ዘረፋ ይፈጸምብናል በማለት ሲናገሩ የነበረ ሲሆን ከትላንት ጀምረው አዳማን ፖሊሶች በአጥለቅልቀዋታል ሲሉ ምንጮቹ ገልጸዋል።በአዳማ ናዝሬት ከሁለት አመት በፊት በተደረገ የስራ ማቆም አድማ ባጃጆች እና ሹፌሮቻቸው በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰምተው እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው ሲሉ ምንጮቹ አስታውስዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና በቅርብ ቀናቶች ውስጥ ህዝቡ በንቃት እንዲከታተል እና በአዳማ ናዝሪት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉ የስራ ማቆም ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የባጃጅ ሹፌሮች በላኩት ቃላቸው ገልጸዋል።
በወያኔ ባለስልጣናት እና በቅርብ ሰዎቻቸው ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ እየታየ ነው። የሃገሪቱን ጉዳይ በተመለከተ ለበታች “ተከታይ ” ባለስልጣናት መረጃ መስጠት ቆሟል።
– የመከላከያ እና ፖሊስ ሰራዊቱ ላይ አለመተማመኑ እየጨመረ መጥቷል።
– የደህንነት አባላቱ መረጃን በግል ጥቅም በመለወጥ እየሰሩ ነው የሚል ግምገማ ቀርቦባቸው ተንጠዋል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
– የሃገሪቱን ጉዳይ በተመለከተ ለበታች “ተከታይ ” ባለስልጣናት መረጃ መስጠት ቆሟል።
– የሕወሓት ታጣቂዎች ከምቾት ኑሮ ተነስተው ለመሸሽ እንጂ ታጥቀው ደም ለመፋሰስ ዝግጁ አይደሉም ።
በኢትዮጵያ ውስጥ መጭው ጊዜ በህዝቡ ዝምታ ተከትሎ በስርአቱ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ይከተላል የሚል መረጃ መሰማት ከጀመረ ጀምሮ በወያኔ ባለስልጣናት እና በቅርብ ሰዎቻቸው ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መኖሩን ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።የአስመራ ተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ሪሞት ኮንትሮል ወያኔ እጅ ነው ስለዚህ የትጥቅ ትግል ወያኔን አያስፈራውም ያሉት ምንጮች የሃገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ወያኔ ልሙጥ የሚላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አጋር ዲያስፖራዎች በለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ህዝቡን በማንቃት ረገድ እያደረጉት ያለው ርብርብ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው እንዳስደነገጣቸው ሲታወቅ በድንጋጤ የመጣ ለኢሕአዴግ አንዳንድ ወቅታዊ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ያሉ ባለስልጣናት ከሃገር እንዳይወጡ እና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ፓስፖርታቸውን ከመነጠቅ ጀምሮ በአይነቁራኛ እንደሚጠበቁ ታውቋል። የሕወሓት ታጣቂዎች ከምቾት ኑሮ ተነስተው ለመሸሽ እንጂ ታጥቀው ደም ለመፋሰስ ዝግጁ እንዳልሆኑ ከምንጮቹ ተሰምቷል።
በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ አዳዲስ የሆኑ ውስጣዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ በሰራዊቱ መካከል እየተከሰተ ያለውን አለመተማመን ለመቆጣተር የሚረዱ ስብሰባዎች በስፋት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በፖሊስ ሰራዊቱም ውስጥ በተለይ በቡድን የሚያሴሩ ሰዎች አሉ እየተባለ ስለሚነገር የወያኔ አንድ ብሄር ሰዎችን በስፋት በመመደብ እንዲሁም ከዚህ ቀደም እንደተሰረገው የቢሮ ሰራተኛውን ከደህንነት ቢሮ በሚመደቡ የሕወሓት ደህንነቶች ለመተካት የታቀደ ሲሆን ቀሪውን ከቢሮ ውጭ የሚሰራውን የፖሊስ አካል ለመቆጣጠር አዲስ ሃይል እንደሚመደብ ታውቋል።የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ ከሃገሪቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በማበር አደጋ ሊፈጥር ይችላል ሲል መፈራቱ እንዲሁም ሰራዊቱን እየከዱ የሚሄዱ መበራከታቸው አለመተማመኑን ከማስፋቱም በላይ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መንግስት አቀፍ እንቅስቃሴ በተመለከተ ከሕወሓት ባለስልጣናት ውጪ ለበታች ተከታይ ባለስልጣናት ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደቆመ ሲታወቅ ማንኛውም ሃገራዊ ጉዳይ አልቆ እና በአፈጻጸም ደረጃ ላይ ሆኖ እንደማንኛውም ሰራተኛ እንደሚሰሙ ባለስልጣኖቹ በመናገር ላይ መሆናቸው ታውቋል ። በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ግምገማ የደህንነት አባላት መረጃዎችን በግል ጥቅም በመለወጥ አሳልፋቹ እየሸጣችሁ ናቸው በሚል መገምገማቸውን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።እንደ ምንጮቹ ከሆነ መረጃን ያለምንም ርሕራሔ መረጃው በአምስት ደኢቃ ውስጥ ጠላት እጅ ገብቶ ያገኘነው ነው ሲሉ የአዲስ አበባው ደህንነት ሹም አቶ ጸጋዬ ተናግረዋል።በዚህ ግምገማ የተከፉት የደህንነት አባላት በመንግስት ባለስልጣናቱ እየተናጡ ቢወረፉም ዝምታን መርጠዋል።#ምንሊክሳልሳዊ
መፍትሄ ያጣው ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠው የፍትህ አካላቱ ፖለቲካዊ ንቅዘት
ፍትህ ! ፍትህ ! ፍትህ ! በሰላማዊ ጥያቄ ፍትህን ለማረጋገጥ ባለመቻሉ በህዝባዊ እምቢተኝነት ይረጋገጣል!!!
Minilik Salsawi
እኛ ኢትዮጵያዊያንን በላያችን ላይ እየነቀዙ ያሉትን ነቀዝ አምባገነኖች ለማስወገድና ፍትህ ዲሞክራሲ ነጻነት እና ሰላም ለመቀናጀት ካደቀቀን የኑሮ አለንጋ ለመላቀቅ በጋራ አደባባይ በመውጣት ስርአቱን የምንገረስስበት ወሳኝ ጊዜ ላይ መሆናችንን አውቀን የተነፈግነውን ፍትህ በሃቀኝነት ማረጋገጥ አለብን።
የበሃገራችን የተንሰራፋው የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት የፍትህ ስርአቱ እንዲቀበር እና በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲሞት በማድረግ ህዝቦች በፍትህ አካላት ላይያላቸው እምነት ተስፋ እንዲያጣ አድርጓል::የፍትህ አካላት ለሃገሪቱ ዜጎች ማገልገል ሲገባቸው ለጥቂት ባለስልጣናት እና ለጥቅማ ጥቅም በመገዛት ህጎች እንዲፋለሱ በማድረግ ላይ ይገኛሉ :;ሊሻሻል እና ሊለወጥ በማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰው ይህ የፍትህ አካላቱ ንቅዘት አለኝታነቱን እና ታማኝነቱን በማጉደል ከፍተኛውን ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል::
በጥቅም የነቀዙት የፍትህ አካላቱ በሙስና ላይ እርምጃ እንዲወስዱ መቀመጣቸውን ዘንግተው በፓርቲ ካድሬነት ብቻ የሰለጠኑ እና ታማኝነታቸው ለአንድ አካል እና ተጠሪነታቸውም ለገዢው በመሆኑ ህዝብ ትክክለኛ ፍትህ እንዳያገኝ በማድረግ ላይ ሲገኙ ይህንንም ላላቸው የፓርቲ ቀረቤታ በማናለብኝነት በሙስና ተዘፍቀው ፍትህ በማጓደል ህገመንግስቱን እና ተከታይ ህጎችን እያጣመሙ በመተርጎም የዜጎች መንፈስ እንዲበላች እና በፍትህ ሂደት ላይ እምነት እንዳይጣል እያደረጉ ይገኛል:: የፖለቲካ ታማኝነታቸውን መከታ በማድረግ ከፍትህ ማጓደል በተጨማሪ በጉቦ ቅሌት ላይ ተሰማርተው የሙስና ሰለባ የሆኑት የፍትህ አካላቱ በሚያገኙት ጥቅማጥቅም መዝገቦችን በመዝጋት እና ሰነዶችን በማጥፋት በተዘዋዋሪ ፍትህ ፈላጊዎችን በህገወጥ መንገድ በሃይል በማስደንገጥ በአጭሩ ሊፈቱ የሚችሉ እና ውስኔ የሚገባቸውን ጉዳዮች ቀጠሮ በማስረዘም እና የፍርድ ውሳኔዎችን በማዛባት ፍትህ ከቁጥጥር ውጪ ወቶ ህገወጥነት እንዲስፋፋ አድርገዋል::
በዳኝነት ወንበር ላይ መቀመጥ የፖለቲካ ደላልነት የሚመስላቸው የእሕኣዴግ ካድረዎች ካለምንም በቂ የህግ እውቀት በፖለቲካ ፓርቲ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፕሮግራም ተገርተው የገረፍ ገረፍ ህግን ሰልጥነው በህግ ባለመብሰል ካለ አቅማቸው ወንበሩን ስለያዙት ከፍተኛ የፍትህ መበላቸት በመስፋፋቱ ህዝቦች ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ችግር እያደረሱ ነው:: እነዚህ በህግ እውቀት የአቅም ማነስ የተጠለፉ የፖለቲካ አገልጋዮች ተቆጣጣሪ አካል ሳይሆን ፍርድ እንዲያዛቡ ያስቀመጣቸው አካል የስልታን እድሜው እንዲረዝም ምንም አይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዜጎችን እያስለቀሱ ይገኛሉ::
ለፍትህ አረም የሆኑት የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት እጅግ በወረደ መልኩ ከአንድ ህዝብ አስተዳድራለሁ ከሚል አካል በማይጠበቅ አካሄድ በፍትህ ስርኣቱ ላይ ጣልቃ በመግባት ሕግ አውጪው፣ ሕግ አስፈጻሚውና ሕግ ተርጓሚው ነፃ ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ እንዳይሰሩ በየፍርድ ቤቱ ዳኞች ላይ በስልክ እና በተለያዩ ዘደዎች ትእዛዝ በማስተላለፍ አደገኛ ሽብር እየፈጸሙ ይገኛሉ::የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን እና ጫና በመሸሽ ሽብር ስጋት እና ፍርሃት ስለተፈጠረባቸው ቁጥራቸው ብዙ የሆነ እና በቂ የህግ እውቀት ያላቸው ዳኞች ተሰደዋል-ከስራ ተባረዋል-በገዛፍቃዳቸው ስራ ለቀዋል-ታስረዋል..::
ይህ ማስፈራራት እና ሽብር በፍትህ አካላት ላይ የሚፈጠረው በባለስልታናት ብቻ ሳይሆን ባለስልጣናቱን መከታ ባደረጉ ሰዎችም ጭምር ነው::ባለስልጣናቱ በየፍርድ ቤቱ ዳኛ አድርገው የመደቧቸውን ካድሬዎቻቸውን በማዘዝ በህሊና እና በፖለቲካ እስረኞች ላይ ካለምንም ማስረጃ እንዲፈረድ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መዝገብ እንዲዘጋ ሰነድ እንዲበላሽ እንዲቃጠል በማድረግ ጫና እየፈጠሩ የፍትህ ስርኣቱ እንዲነቅዝ አድርገውታል:: ይህንን የነቀዘ ስር አት እና የፍትህ ሂደት ለመገርሰስ በጋር ተያይዘን አደባባይ በመውጣት ሕዝባዊ ሃይላችንን ተጠቅመን ድላችንን ማረጋገጥ አለብን።#ምንሊክሳልሳዊ
ወያኔ በገጠመው የውጭ ምንዛሬ ችግር የብርን ዋጋ ዲቫሉዊት ሊያደርግ ነው።
የወያኔ መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል
• ‹‹የወያኔ መንግስት የብርን ዋጋ በቅርቡ ‹ዲቫሊዌት› ሊያደርግ ይችላል››
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ነገረ ኢትዮጵያ
ነገረ ኢትዮጵያ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጥኚ እጥረቱ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ከ20 ቀናት በፊት እያንዳንዱ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የውጭ ምንዛሬ ይሸጥ እንደነበር የተናገሩት ምንጮች፣ ከ20 ቀን ወዲህ ግን በሁሉም የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማንኛውም አይነት የውጭ ምንዛሬ እንዳይሸጥ በደብዳቤ (cercular ዞሯል) ተከልክሏል፡፡
በመሆኑም አሁን ላይ ዜጎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቸገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹በተለየ ሁኔታ የሚሸጥላቸው ሰዎች ከጉዞ ወኪላቸውና ከበላይ አካል ይዘውት በሚመጡት ደብዳቤ መሰረት ብቻ ነው ምንዛሬ ሊያገኙ የሚችሉት፡፡ ከዚህ ውጭ ግን እንደበፊቱ ማንም የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይችልም›› ሲል አንድ የንግድ ባንክ ሰራተኛ ገልጹዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ የተከሰተው በዶላር ምንዛሬ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የውጭ ምንዛሬዎች ላይ መሆኑንም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ አሁን ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በጥቁር ገበያ እስከ 22 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል ከብሄራዊ ባንክ አካባቢ የደረሱት የነገረ ኢትዮጵያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መንግስት ቀደም ሲል በIMF የቀረበለትን የ‹ዲቫሊዌሽን› ጥያቄ መቀበሉ እንደማይቀር ታውቋል፡፡ ‹‹አሁን ያለው ሁኔታ እንደሚያሳየን መንግስት የብርን ዋጋ በቅርቡ ‹ዴቫሉዌት› ማድረጉ አይቀሬ መሆኑን ነው፡፡ አንዳንድ ‹አርቲፊሻል› የውጭ ምንዛሬ እጥረቶች ቢኖሩም ዋናው የችግሩ መነሻ ግን የ‹ዴቫሊዌሽኑ› ጉዳይ ነው›› ሲሉ የብሄራዊ ባንክ የኢኮኖሚ አጥኚው ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡
ሰሞኑን መንግስት ለወራት ተከልክሎ የነበረው የአረብ ሀገራት የስራ ጉዞ እንደገና እንዲጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ይህም ወደ አረብ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎች ተጨማሪ ምንዛሬ እንዲያስገኙ ከማሰብ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡