ጥያቄው የለውጥና የነጻነት ነው ። ለለውጥ እንትጋ !!! ነፃነታችን በጃችን ላይ ነው፡፤ !!!
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

አዎ የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ የግለሰቦች በስልጣን ወንበር ላይ መፈራረቅ ሳይሆን ጥያቂያችን የለውጥ ጥያቄ ነው። የፖለቲካ አስተዳደር ለውጥ የኑሮ ውድነት የሚያላቅቅ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ በጋራ ህብረተሰባዊነት ላይ የተመሰረት የማህበራዊ ፍትህ እኩልነት ለውጥ የነጻነት እና የመብት ማግኘት ጥያቄ በሃገራችን ተዘዋውረን በፈለግነው ቦታ የመስራት እና የመኖር ጥያቄ የመሳሰሉት ለውጦች በሃገራችን ላይ የሃገራችን ባለቤቶች ስንሆን የ ሚገኘው ብልጽግና እና እድገት ባለቤት መሆናችንን የሚያረጋግጥልን ለውጥ እንፈልጋለን፡፡

የጉልቻ መለዋወጥ ከሆነ እንደ ለውጥ የሚታየው በኢትዮጵያውያን የ እለት ከእለት የሕይወት ሂደት ውስጥ ድህነት እና ነጻነት ማጣት እንጂ ምንም አይነት የፈየደው ነገር አለመኖሩን ከሃይለስላሴ ጀምሮ ያየነው ነው፤ መንግስቱ ሓ/ማርያም መጣ ሄደ መለስ ዜናዊ መጣ ሄደ አሁንም ጠቅላይ ተብሎ ተሾመልን ይህም ጉልቻውን ለፖለቲካ ማጣፈጫ ሆነ እንጂ እንኳን ሊያስተዳድረን ይቅር እና የገዛ አንገቱን እንኳን ማዘዝ አልቻለም፤ ታዲአ የዜጎችን የለውጥ ጥያቄ ጉልቻ በመለዋወጥ መመለስ እንደማይቻል በይፋ እያየነው ነው፡፡

የኛ የለውጥ ጥያቄ የህዝቦችን የዜግነት መብቶች የሚያረጋግጥ እንጂ በውጭው አለም እና በሃገር ውስጥ ብሄራዊ ውርደት የሚያከናንብ አስተዳደር አይደለም፤ የኛ የለውጥ ጥያቄ በተስኪያናችንን እና መስኪዳችን እንዲሁም ታሪኮቻችንን የሚያረክስ የፖሊስ እና የጦር ሰራዊት ለውጥ ሳይሆን የነጻነት እና የመብት ጥያቂያችንን በህገመንግስት መሰረት የሚያስከብርልን አስተዳድር ነው፤ የኛ የለውጥ ጥያቄ በኑሮ ውድነት አደባይቶን በሙስና ጥቂት ሃብታም ብዙ ደሃ የሚፈጥር ዋሾ አስተዳደር አይደለም፡፤ የኛ የለውጥ ጥያቄ ህዝባዊ መሰረት ያለው ሚዲያ እንጂ በግምት የሚደሰኩር ውሸታም ሚዲያ አይደለም፡፤በአጠቃላይ የለውጥ ጥያቄያችን የባሰ እና የበሰበሰ መንግስት እንዲያስተዳድረን ሳይሆን እንደ ሃገር ባለቤትነታችን መብታችንን አስከብሮ በነጻነታችን እያኖረ ሃገራዊ ሃላፊነት እና ግዴታ እንዲሰማን የሚያደርግ መንግስት እንጂ የጉልቻ ተፈራራቂ አምባገነን ንግስና አይደለም፡፡

ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን ስንል የለውጥ ጥያቂያችንን መከለያ አድርጎ የስልጣን ጥሙን የሚያረካ የፖለቲካ ድርጅት እና የፖለቲካ ወያላ አንፈልግም፡፤ የኛን የለውጥ ጥያቄ ለፖለቲካ አጀንዳቸው ተጠቅመው ነጻነታችንን የሚያስነጥቁን የፖለቲካ ድርጅቶችን አንናፍቅም፡፤እኛ በፈረንጅ ቋንቋ የተገነባ የዲሞክራሲ ንግድ በነጻነታችን ላይ እንዲሰራፋ አንፈልግም። ኢትዮጵያውያን ነጻነታችን ያለው በፈረንጆች ሳይሆን በ እጃችን ላይ ስለሆነ እያንዳንዳችን ነጻነታችንን ለማስመለስ መረባረብ ግድ ይለናል። ጥያቂያችን የምእራብ ዲሞክራሲ ሳይሆን በነጻነት የመኖር ትያቄ ነው፡፤ ለለውጥ አሁንም እንጮሃለን። ፈረንጅ ለራሱ አጽድቆ ያራባውን ዲሞክራሲ ከነጻነት በኋላ እንደርስበታለን።

የዲሞክራሲ ትርጉም ቢገባንም ገዢዎቻችን ግን ለለበታ ስለሚጠቀሙበት በቋንቋችን ነጻነት ለውጥ እያልን እንዘምራለን፡፤ለለውጥ በጋራ በመነሳት ነጻነታችንን በትግላችን መቀናጀት ግድ ይለናል። በሃገራችን እና በነጻንትችን ላይ ባለቤቶች እንደሆንን ሃላፊነት ሊሰማን ስለሚገባ ነጻነታችንን ራሳችን ማረጋገጥ አለብን እንጂ የማንም ችሮታ እንዳልሆነ ተገንዝበን በጋራ ለለውጥ መነሳት ግዲታችን ነው። ነጻነታችን በ እጃችን ስለሆነ ዛሪውኑ ለማስመለስ እንትጋ።

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ ተሰደደ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች የራሱ “አዲስሚዲያ” ብሎግን ጨምሮ በተለያዩ ድህረ-ገፆች አዘጋጅ እና ፀሐፊ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል መሰደዱ ታወቀ፡፡ ጋዜጠኛው ቀደም ሲል የፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ፣የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢሳው መፅሔት ባልደረባና አምደኛ፤ በኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣና በቅርቡ ወደህትመት የገባው ቀዳሚ ገፅ ጋዜጣ ላይም የተለያዩ የፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ በራሱና በብዕር ስም እንደሚፅፍ ይወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተመሰረተውና በመንግስት ከፍተኛ ቁጥጥርና ጫና ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) መስራች አባል፤ በኋላም የማኀበሩ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ጋዜጠኛው ከዚህ በፊትም በመንግስት ደህንነት ኃይሎች በምሽት እገታ እንደገጠመው፣ ከስልክ ጠለፋ እስከ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስበት እንደነበር ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም፤በተለይ ከጥቅምት 2006 ዓ.ም. ከአዲሱ ጋዜጠኞች ማኀበር መመስረት ሂደት ጀምሮ እና በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. 3 ጋዜጠኞችን እና 6 የዞን 9 ብሎገሮች በመንግስት ከታሰሩ በኋላ የመንግስት ደህንነቶች ክትትል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ቀጣዩ እስር እሱ ላይም ሊፈፀም እንደሚችል በመረዳት ለቅርብ ጓደኞቹ አሳውቆ ነበር፡፡

ብስራት ባለፈው ነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አርብ ጠዋት አዲስ ባወጣው የስልክ መስመር የማዕከላዊ ስልክ ጥሪ ካስተናገደ በኋላ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጭ መሆኑን በማሳወቅ ለሰኞ እንደሚቀርብ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ባለፈው እሁድ ድንገት ሀገር ጥሎ መሰደዱ ታውቋል፡፡

በቅርቡ ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች የእስር ስም ዝርዝር ውስጥ የማኀበሩ አመራሮች መኖራቸውና በቀጣይም መንግስት በአመራሮቹ ዙሪያ መረጃ እየሰበሰበ መሆኑ ምንጮች አረጋግጠው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የማኀበሩ ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ፣ ገንዘብ ያዥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም እና መስራች አባል ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤልን ጨምሮ በ2006 ዓ.ም. ብቻ 25 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ፤3 የውጭ ዜጎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ኦሕዴድ ከኢህአዴግ ተለይቶ ራሱን የቻለ ፓርቲ እንዲሆን የሚፈልግ ቡድን ተነስቷል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በዚህ በያዝነው ነሃሴ ወር ውስጥ ብቻ የሕወሓት/ብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እና አንጋፋ ታጋዮች የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን ባገለል እና ባላሳተፈ በተከታታይ የተደረጉ ተደራራቢ ስብሰባዎች በኦሕዴድ አመራሮች ዘንድ ጥያቄን ያጫረ ሲሆን በደሕዴግ አመራርች ዘድ ደሞ የዝምታ ድባብ እንዲያጠላ በማድረጉ በኢሕአዴግ ድርጅቶች መካከል በአዲስ መልኩ የውስጥ ፍጥጫ ማየሉን የድርጅቱ መረጃዎች ጠቁመዋል።

የኦሕዴድ አመራሮች በኢሕአዴግ ውስጥ የሚደረጉ ስብሰባዎች ለምንድነው የድርጅታችንን ሰዎች የሚያገሉት የሚሉ ጥያቄዎች ስእሞኑን ለሙክታር ከድር እና ለአባዱላ ገመዳ የቀረቡ ሲሆን እስከመቼ በሕዝብ ተተፍተን በሃይል ብቻ ለመኖር እንችላለን ኦሕዴድ ከኢህአዴግ ተለይቶ ራሱን የቻለ ፓርቲ በመሆን ተሃድሶ እንዲያደርግ ካልሆነ ድርጅቱ ከአንድ አካል የበላይነት የሚላቀቅበት መፍትሄ እንዲፈለግ ሲሉ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

በዚህ ወር ወስጥ ኢሕአዴግን ለማዳን በሚል የተለያዩ ስብሰባዎች በቀድሞ አንጋፋ ታጋዮች በሆኑት እና በሲቪል እና ውታደራዊ ስልጣን ላይ ባሉት የሕወሓት እና የብአዴን አመራሮች ተከታታይ ስብሰባዎች እየተደረጉ ሲሆ የወያኔው ጁንታ ዜጎች እየሰበሰበ በማሰር እና በሕዝቡ ዘንድ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ እንድሁም ስም በማጥፋትና በተለያዩ እኩይ ተግባሮቹ በውጪም በውስጥም በደረሰበት የፖለቲካ ኪሳራ ለመጪው አመታት ሕዝቡን እንዴት አታሎ እና አጭበርብሮ መግዛት እንዳለበት እቅድ እያወጣ ሲሆን ለአዲስ አመት መጀመሪያም የኢሕአዴግ አመራሮችን ሰብስቦ መመሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ወያኔ ሲፍረከረክ አጋጣሚዎችን መጠቀም እስካሁን ያልቻሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁንም በወያኔ ላይ የደረሰውን ኪሳራ ትጠቅመው አፋጣኝ የፖለቲካ ድሎችን በማስመዝገብ የበሰበሰውን ስርአት ወደ መቃብር እንዲወርድ ያላሰለስ ትግል ማድረግ አለባቸው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራል።

‹‹ጠበቆቻቸው በእየዕለቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመጣስ በሰፊ የፖለቲካ ዘመቻ የተጠመዱ ናቸው፡፡›› ገጽ 46
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ባለፈው ሳምንት ለተማሪዎች በሚሰጠው ስልጠና ቴዲ አፍሮና ሰማያዊ አጀንዳ መሆናቸውን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስልጠናው ወደ ሙስሊሙ እንቅስቃሴና የኮሚቴው ጠበቃዎች መዞሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚሰጠው በዚህ ስልጠና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊና መንግስት የሙስሊሙ ጉዳይ እልባት እንዲሰጥ የጠየቁ አካላት በአክራሪነት ፈርጇቸዋል፡፡ ‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ፈተናዎች›› በሚለው ሰነድ የሙስሊሙ ማህረሰብ እንቅስቃሴ ደም ለማፍሳሰስ እየጣረ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡

ከዚህም ባሻገር የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቆች ከጥብቅና ይልቅ የፖለቲካ ስራ እንደሚሰሩ በሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በሰነዱ ገጽ 46 ላይ ‹‹ጠበቆቻቸው በእየ ዕለቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመጣስ በሰፊ የፖለቲካ ዘመቻ የተጠመዱ ናቸው፡፡›› ሲል ያትታል፡፡

ሰነዱ ለስርዓት ግንባታ እንቅፋት ናቸው የሚላቸው የሁለቱንም እምነት ተከታዮች ሲሆን ‹‹በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሽፋን አገራዊ አጀንዳዎችን አስቀድመው ከሚፈታተኑን ኃይሎች ባልተናነሰ ደረጃ ደግሞ በሚያገኙት የገንዘብ ጥቅማጥቅም ተደልለው አገራችን የጀመረችውን የእኩልነት ጉዞ የሚያጥላሉ፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓታችንን ጥላሸት የሚቀቡ ኃይሎች አሉ፡፡›› ሲል የሁለቱን እምነት ተከታዮች ይወቅሳል፡፡

ሰልጣኞቹ የላኩልንን የሰነዱ ክፍል እንደሚከተለው አያይዘነዋል፡፡
Image

ሰሞኑን ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም «ሸገር» ከተሰኘ በኤፍ.ኤም. 102.1 (FM 102.1) ከአዲስ አበባ መርኃግብሩን ከሚያሠራጭ የሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ «ዐማራ» የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ አለመኖሩን ልባቸውን ነፍተው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ፕሮፌሠር መሥፍን በዚህ ቃላቸው፣ በ፲፱፹፫(1983)ዓ.ም. ከሟቹ የትግሬ-ወያኔዎች መሪ መለስ ዜናዊ ጋር በቴሌቪዥን ቀርበው ስለ ዐማራው ነገድ ያለመኖር ያንጸባrmቁትን አቋም አፅንዖት በመስጠት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ዐማራ የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ ውስጥ «አለ» ወይስ «የለም» ብሎ፣ በላ! ልበልሃ! ወደሚል እጅግ የወረደ ክርክር የሚገባ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት ክርክር ውስጥ የሚገባ ሰው፣ ኃሣቡ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የማይችል የፕሮፌሠር መሥፍን ዓይነቱ ሰው ብቻ ነው። ለነገሩ በዚህ የቀን ቅዠት አቋም የሚፀና ካለ ከፕሮፌሠር መሥፍን ሌላ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ይገኛል ተብሎ አይታሰብም። የፕሮፌሠር መሥፍንም ክርክር ጭፍን ክህደት ወይም መሣት (መጃጀት) አልያም ቀቢፀ-ተስፋ የተሞላው ቁጭት ከመሆን አያልፍም። የፕሮፌሠር መሥፍን አቋም የክህደት ከሆነ፣ ወላጅ አባታቸውን ዕውቁን ሊቅ አለቃ አስረስ የኔሰውን ክደዋልና የዐማራ ነገድን ኅልውና ከመካድ የሚያግዳቸው የኅሊና ልጓም ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ከመሣት(መጃጀት) የመነጨ ከሆነ ግን አያድርስ! እንዲህ እስኪሆንስ ፈጣሪን «አታቆዬን» ከማለት ሌላ ምን ይባላል። ከቁጭት ከሆነ ነገሩ ሌላ ነው። በቁጭት የአንድን ታላቅ ሕዝብ መኖር ኅልውና ክዶ ስለዚያ ሕዝብ መከራከር እና መጮህ አይቻልም። የቁጭት ተገቢ መገለጫው «አሻፈረኝ! በቃኝ! ተነስ! ዱሩ ቤቴ በል!» በማለት እንጂ «የለህም! የሚያጠፉህ ሳትኖር ነው!» በማለት አይደለም። የሌለ፣ ኅልው ያልሆነ፣ ሊያደርገው የሚችለው ምንም ነገር የለምና!

ፕሮፌሰር መሥፍን «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» ከሚል መደምደሚያ የደረሱት፣ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ከሦሥቱ በአንዱ ወይም በሁሉም ተያያዥነት እንደሆነ ቀደም ካሉት ድርጊቶቻቸው መገንዘብ ይቻላል። የመጀመሪያው በ፲፱፹፫(1983) ዓ.ም. ከሟቹ መለስ ዜናዊ ጋር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባደረጉት ውይይት ዐማራን እና ክርስቲያንን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን በመዘንጋት፣ ወይም ሆን ብለው «ክርስቲያን እንጂ፣ ዐማራ የሚባል የለም» ብለው ተከራክረው ስለነበር ያ አቋማቸው ያልተለወጠ መሆኑን እና ዛሬም «በዚያው አቋማቸው የጸኑ ናቸው» ለመባል ከማሰብ የመነጨ፣ ከስህተት ወደ ስህተት የመጓዝ አስተሳሰብ ነው። ሁለተኛው ፕሮፌሠር መሥፍን ክህደት የመታወቂያ ባሕሪያቸው ስለሆነ ትናንት የካዱትን ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላም በክህደቱ የቀጠሉ መሆኑ የሚያመለክት ነው። ይህም ሌላው ግትርና «ያለ እኔ ዐዋቂ የለም» የሚለው የገነገነ አስተሳሰባቸው መገለጫ ነው። ሦስተኛው ከክህደት ባሕሪይ በተጨማሪ በዕድሜ መግፋት ምክንያት የመጣ፣ የኋላን ያለማዬት እና የመሣት አባዜ የገጠማቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። አራተኛው በዘመነ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በዐማራው ላይ በተከታታይ እየተፈጸመበት ያለው መገደል፣ መታሠር፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ከአገር መባረር፣ መዋረድ እና መጎሳቆል እጅግ በዝቶ የግፉ ጽዋ ሞልቶ የሚፈስበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሆኖም ዐማራው «አሻፈረኝ» ብሎ ወያኔን ግብግብ ከመግጠም ይልቅ የሚሣየውን ሆደ ሠፊነት ከኢዮብ ትዕግሥት በላይ ሆኖ ስላገኙት፥ «ዐማራ የሚባል ነገድ ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ ጥቃት እና ውርደት ሲፈጸምበት ዝም ብሎ አይመለከትም ነበር! ሌሎቹ እንደሚያደርጉት ኃይሉን አስተባብሮ ጥቃቱን ይቋቋም ነበር! ባለመኖሩ ነው ይኸ ሁሉ ጥፋት የሚፈጸምበት» ከሚል ቁጭት የደረሱበት ድምዳሜ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል።

ይህ ግን ከዐማራው ባህል፣ ዕምነት፣ አኗኗር፤ ማኅበራዊ ግንኙነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ጋር አጣምሮ ለሚያይ ሰው፣ ዐማራው በወያኔ የደረሰበትን ሁለንተናዊ ግፍ እና በደል በአርምሞ በመመልከት ላይ ያለው፣ በደሉ ሳይሰማው ቀርቶ አይደለም። እንዲያውም «የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች» እንዳይሆንበት የትግሬ-ወያኔዎችን ግፍ ለመበቀል ሲል በደልን በበደል መመለስ፣ የትልቂቱን አገሩን የኢትዮጵያን ኅልውና እንዳያፈርስ ኅሊናውን ገዝቶት፣ በሆደ ሠፊነት እና በትዕግሥት ማየቱ፥ ብልኅነቱን፣ አስተዋይነቱን፣ «አድሮ እንየው» ማለቱን፣ ውሽንፍርን እና ጥምዝምዝን አጎንብሶ ማሳለፍ ባህሉ መሆኑን፣ እንጂ፤ ጥቃትን እስከ ዝንተ ዓለሙ የሚቀበል አለመሆኑ ታሪኩ ያስረዳል። «ዐማራ ሰንበሌጥ ነው፤» የሚባለውም እኮ ለዚህ ነው። ማንም እንደሚያውቀው ሰንበሌጥ ኃይለኛ ወዠብ (ነፋስ) ሲመጣበት ለጥ ብሎ ያሳልፋል፣ ወዠቡ ሲያልፍ ይነሣል። ዐማራውም በተደጋጋሚ እና በተከታታይ ሊያጠፉት የተሰለፉትን ኃይሎች ሁሉ ተቋቁሞ እስካሁን የዘለቀው በዚህ መንገድ ነው። ጠላቶቹን የሚያሸንፋቸው በመበቀል ሣይሆን በይቅርታ እና በፍቅር መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አያስፈልግም። የኢትዮጵያዊነት ማገር፣ ዋልታ እና ጭምጭም ሆኖ ለዘመናት የዘለቀውም የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት ስሜቱ የዳበረ በመሆኑ ነው። ይህም በመሆኑ ነው የዐማራው ሥነልቦና በድል ጊዜም ሆነ በጥቃት ላይ እያለ የበላይነቱን እንደጠበቀ እንዲዘልቅ ያደረገው።

ዛሬ ወያኔን እና መሠል ቡድኖችን ያስጨነቃቸው ይኸው የዐማራው የኢትዮጵያዊነት ሥነልቦና የበላይነት አልሰበር በማለቱ ነው። እኒህን ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሌት ተቀን የሚያባንናቸው ዐማራው ኢትዮጵያዊነትን ማተቡ፣ ዕምነቱ እና የእሱነቱ መገለጫ፤ ሠንደቅ ዓላማውንም ልብሱ፣ ትራሱ እና መጌጫው አድርጎ በዓለም አደባባይ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የሚያሰማው ድምፅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያስገመገመ በመጓዙ ነው።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ይህን መግለጫ ለማውጣት የወሰነው በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን አብዛኛው ሰው የሚያምነው የሚያየውን ብቻ ሣይሆን የሚሰማውንም ጭምር በመሆኑ ነው። እንዲያውም ሰው ከሚያየው ይልቅ የሚሰማውን ይበልጥ አምኖ ይቀበላል። ስለሆነም «ፕሮፌሠር መሥፍን እኮ ዐማራ የሚባል ነገድ የለም ብለዋል» ብሎ የሚቀበለው እና የሚያምነው ሰው ቁጥር ቀላል ስለማይሆን፣ ለዚህ ዓይነቱ አድማጭ ዕውነታውን ማሣወቅ አስፈላጊ ይሆናል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ፥ ምንም እንኳን ጊዜ እየከዳቸው ያሉ ቢሆንም፣ እስትንፋሳቸው እስካለ ድረስ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሌሎች የክህደት ንግግሮችን ከመናገር ስለማይቆጠቡ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «ዐማራ የለም» ሲሉ የካዱትን ክህደት በተጨባጭ መረጃዎች በማሣዬት ለወደፊት አድማጫቸው እና አንባቢያቸው ከሃዲነታቸውን ከወዲሁ እንዲገነዘብ ለማድረግ ነው። ከዚህ አንፃር የዐማራን ነገድ ከኢትዮጵያ ምድር አልፎ በዓለም ዙሪያ ተሠራጭቶ የሚኖር መሆኑን የሚከተሉት መረጃዎች ያረጋግጣሉ። እነርሱም፦

፩ኛ አካላዊ (ነባራዊነት)፣
፪ኛ አማርኛ የተሰኘ ቋንቋ በኢትዮጵያ መኖር እና በስፋት መነገር፣ እንዲሁም
፫ኛ የጽሑፍ፣ የቃል (ድምፅ) እና የምሥል ማስረጃዎች ናቸው።

፩ኛ. አካላዊ (ነባራዊነት)
አካላዊ ወይም ነባራዊነት ስንል፥ በእጅ የሚዳሰስ፣ በዐይን የሚታይ፣ ግዙፍ፣ ራሱን «ዐማራ ነኝ» ብሎ የሚገልጽ ሰው የተሰኘ ፍጡር በኢትዮጵያ ምድር በስፋት ተሰራጭቶ የሚኖር ሕዝብ ማለታችን ነው። ይህ ሕዝብ ቀደም ሲል ክርስትና ወደ አገራችን ሲገባ ቀድሞ የተቀበለ በመሆኑ ከክርስትና ኃይማኖት ጋር አያይዞ የራሱን ማንነት የሚጠራ፤ ሌሎችም «ዐማራ» ሲሉ «ክርስቲያን የሆነ» ማለታቸው እንደሆነ አድርገው የሚገልጹት፣ በኋላም በጊዜ ሂደት ወደ አገራችን የገቡ ዕምነቶችን ሳይቃወም፣ መቻቻልን መርሑ አድርጎ የተቀበለ እና ከእርሱም ውስጥ የተወሰነው ክፍል የክርስትና ኃይማኖቱን በመተው ሌሎች ዕምነቶችን በመከተል የኖረ፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ነገዶች በቁጥር ከፍተኛውን መጠን የያዘ ማለታችን ነው።

ማንም በግልጽ ሊገነዘበው እንደሚችለው፣ ቋንቋ ከሰው በፊት አልተፈጠረም። ቋንቋ ከሰው ልጅ ኅልውና በኋላ የተከተለ የሰዎች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው። ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይዳብራል፣ ይሞታል የሚባለውም ከሰዎች መኖር ጋር በጥብቅ የተሳሰረ በመሆኑ ነው። በሌላም በኩል ቋንቋ ባህልም ነው። ከጥንት ጀምሮ የቁጥር መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሄደ እና ራሣቸውን «ዐማራ ነኝ» በሚሉ ተወላጆች የጋራ ማንነት የተገነባ ነገድ አለ። እኒህ ሰዎች አፋቸውን በአማርኛ ቋንቋ የፈቱ፣ ካለ አማርኛ ቋንቋ ሌላ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በመሠረቱም የአማርኛ ቋንቋን መግባቢያ እና መገልገያ ያደረገ ሕዝብ ሣይኖር የአማርኛ ቋንቋ ሊኖር አይችልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም ነገዶች እና ጎሣዎች አንድ ተብለው መቆጠር ሲጀምሩ በቅድሚያ በማንም ሰው አዕምሮ ውስጥ ድቅን የሚለው ዐማራ ነው። ስለዚህ በማንነቱ ከኢትዮጵያ ኅልውና ጋር በጥብቅ የተሣሰረ «ዐማራ» የሚባለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ኅልውና መካድ ኢትዮጵያን ከመካድ ተለይቶ አይታይም።

ሌላው አካላዊ ማስረጃ «ዐማራ ሳይንት» የተባለው እና በላኮመልዛ(ወሎ) ክፍለሃገር የሚገኘው የአውራጃ ስም ነው። «ዐማራ» የሚባል ነገድ ሳይኖር፣ በዐማራ ስም የሚጠራ የቦታ ስም ሊኖር አይችልም። በሌላም በኩል ከጥንት ጀምሮ በጌምድርና ስሜን(ጎንደር)፣ ጎጃም፣ ሸዋ እና ላኮመልዛ(ወሎ) የተሰኙ የኢትዮጵያ መልከዐ-ምድር አካል የሆኑ ክፍለ-ሀገሮች አሉ። የነዚህ ክፍለ-ግዛቶች አብዛኛው ነዋሪ ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ «ዐማራ የሚኖርባቸው» ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘመነ ትግሬ-ወያኔ «የዐማራ ክልል» በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ክፍል ኅልውናውን ካስቆጠረ ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሆኗል። ስለዚህ ይህን ሁሉ እንዴት መካድ ይቻላል? ለፕሮፌሠር መሥፍን የክህደት መንገዳቸው ማጠናከሪያ አድርገው የሚያቀርቡት «ስለ ዐማራ አጥንቻለሁ» የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይህ አጥንቻለሁ የሚሉት ጥናት ዕውነት ከሆነ፥ ባለፉት ዘመናት «የዐማራ ገዥ መደብ፣ ጨቋኝ የዐማራ ብሔር፣ ነፍጠኛ ዐማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔር/ብሔረሰቦች ደመኛ ጠላት፣ ወዘተርፈ» እየተባለ ሲወገዝና የመከራ ዓይነቶችን ሲቆጥር ለምን ዝም አሉ? ኢትዮጵያውያን ዐማሮች ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች፥ «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው፤ ከደቡብ፣ ከሐረርጌ፣ ከአርሲ፣ ከባሌ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቡር፣ ከሶማሌ፣ ከቤንሻንጉል-ጉምዝ እንዲሁም ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲባረሩ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «እነዚህ እኮ ዐማራ አይደሉም፣ የሌላ ነገድ አባሎች ናቸው፤» አላሉም? «እንዲያውም ዐማራ የምትሉት ሰው በምድረ-ኢትዮጵያ የለም፤» ብለው ማስተባበል እንዴት ተሣናቸው? እኒህ ሰው የሌሎችን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ኅልው መሆን ሲቀበሉ እንዴት የዐማራ ነገድን ኅልውና ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ ዳዳቸው? ማንን ለማስደሰት ይሆን?

በደርግ የአገዛዝ ዘመን ስለኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች በኢትዮጵያ የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም በተደረጉት የጥናት ውጤቶች መሠረት፣ የዐማራ ነገድ ከኢትዮጵያ ነገዶች አንጋፋው፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ተሠራጭቶ የሚኖር፣ እንዲሁም በቁጥርም ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያሉ።

ሌላው የዐማራን ነገድ ኅልውና የሚያረጋግጠው ደረቅ ማስረጃ በኢትዮጵያ የተደረጉት የሕዝብ ቆጠራ ውጤቶች ናቸው። ለምሣሌም ያህል፦ በ፲፱፻፸፮ (1976) ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ፵፪(አርባ ሁለት) ሚሊዮን ያህል እንደነበረ ይታወቃል። ከጠቅላላው የአገሪቱ ሕዝብ (42 616 876) ውስጥ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት 12 055 250 (አሥራ ሁለት ሚሊዮን ሃምሣ አምሥት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ) ነበር። ይህም ከአጠቃላይ የአሪቱ ሕዝብ 28.288 ከመቶ እንደነበረ ያሣያል። በሥርጭት ረገድም፥ በሸዋ 23.1 በመቶ፣ በአዲስ አበባ 47.86 በመቶ፣ በወሎ 79.86 በመቶ፣ በጎንደር 84.83 በመቶ፣ በጎጃም 87.58 በመቶ፣ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ነበሩ፣ በግለሰብ ደረጃም ሰዎች ማንነታቸውን «ዐማራ ነን» ብለው ማረጋገጣቸው በውል ታይቷል። ዐማራው በሌሎች የአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮችም በበቂ መጠን ተሰራጭቶ እንደሚገኝ የቆጠራው ውጤት አሣይቷል። በዚህም መሠረት በሐረርጌ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በወለጋ፣ በጋሞጎፋ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በአሰብ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንደነበረ መረጃው ያስረዳል። በዚያ የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኦሮሞን ቁጥር ከፍ፣ የዐማራን ቁጥር ግን ዝቅ ለማድረግ ሆን ተብሎ የቁጥሮች ጨዋታ የተሠራ መሆኑ ቢታወቅም፣ ዐማራው በቁጥር በአገሪቱ ከሚገኙ ነገዶች እና ጎሣዎች በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን ያረጋግጣል (ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን፣ ታኅሣሥ ፲፱፻፹፫ (1983) ዓ.ም.)።

በሁለተኛ ደረጃ በ፲፱፻፹፯(1987) ዓ.ም. በተደረገ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 53 499 248 መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ 13 834 297 ያህሉ ዐማሮች መሆናቸውን ያሣያል። በንፅፅር ሲታይ በትግሬ-ወያኔ ዘመን በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት በ፲(አሥር) ዓመታት ውስጥ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ቁጥር የጨመረው በ1,779,047 ብቻ ነው። ይህም የቆጠራው ውጤት የወያኔን ዐማራን የማጥፋት የፖለቲካ ዓላማ በጉልህ የሚያሣይ ነው። ሆኖም የዐማራ ነገድ በቁጥሩ ብቻ ሣይሆን በሥርጭትም ጭምር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በብዛት የሚገኝ መሆኑን የቆጠራው ውጤት አላስተባበለም። በመሆኑም ወያኔ «የዐማራ ክልል» ብሎ በከለለው ውስጥ ከሚኖረው 13 834 297 ሕዝብ መካከል ዐማራው 81.5 ከመቶ መሆኑን፣ በ«ትግራይ ክልል» ከሚኖረው 3 136 267 ሕዝብ መካከል የዐማራው ነገድ 2.6 ከመቶ በመያዝ በክልሉ በሕዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ታውቋል። በ«ኦሮሚያ ክልል» ከሚኖረው 18 732 525 ሕዝብ መካከል 9.1 ከመቶ የሚሆነው የዐማራ ነገድ መሆኑን እና ይህም በ«ክልሉ» ከሚኖሩት ነገዶች መካከል ከኦሮሞው ቀጥሎ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያል። አርባ አምሥት(፵፭) ነገዶች እና ጎሣዎችን ባጠቃለለው የ«ደቡብ ክልል» ዐማራው በቁጥር በስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚህ «ክልል» 10 377 028 ሕዝብ እንደሚኖር ቆጠራው አሳይቷል። ወያኔ «ሐረሪ» ብሎ የመንግሥትነት ዕውቂያ ከሰጣቸው ክልሎች አንዱ የሆነው የሕዝቡ ቁጥር 131 139 ነው። ከዚህ የ«ሐረሪ ክልል» ነዋሪ ሕዝብ መካከል 52.3 ከመቶው ኦሮሞ ሲሆን፣ 32.6 ከመቶው ዐማራ ነው። ሐረሪዎቹ 7.1 ከመቶ ብቻ ናቸው። እንግዲህ ለእነዚህ አናሣ ቁጥር ለያዙት ነው የአብዛኛውን የኦሮሞ እና የዐማራ ነገዶች ተወላጆች ዕጣ ፋንታ እንዲወስኑ ወያኔ የመንግሥትነት መብት የሰጣቸው። ይህንንም «ዲሞክራሲ ነው» እያሉን ነው። በሶማሌ ክልል 3 439 860 ሕዝብ እንደሚኖር በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. የተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ያመለክታል። ከዚህ መካከል በዚያ ክልል ዐማራው 0.69 ከመቶ በመያዝ በሦስተኛነት ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሎስ አንጅለስ በወያኔ አምባገነኖችና አጋፋሪዎቻቸው ልትጎበኝ ዝግጅቱ ከታቀደ ቆይቷል። እንዳውም የሃይለማሪያም የክብር ድግሪ መሸለሚያ ወይም መሳለቂያ ልትሆን ታጭታለች። የወያኔ ሥራ አስፈፃሚዎች እነ ወንድወሰን መስፍን፣ እነአበራ ገብሬ፣ እነፀሃይ ኃይሉና የሮዛሊንድስ ምግብ ቤት ባለቤቶች ወንድማማች ፍቅረና ሞገስ ጌቶቻቸዉን ሊቀበሉ ሽርጉዱን ተያይዘውታል። የሮዛሊንድስ …

የወያኔ ቆይታ በሎስ አንጅለስ Read more »

“..እንዲህ አይነት ጥያቂዎችን እነማን እንደሚጠይቁ እናውቃለን ደንቆሮ ዝቃጭ ..” ደብረጺሆን
“በስልጠናው ላይ ሰራተኛው ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ በሰፊው አሳይቶበታል። ” የካድሬዎች ሪፖርት
ይህን ሰሞን ለምርጫ የሚሆን ድጋፍ እና አዳዲስ አባላትን ለመመልመል የወያኔው ጁንታ የመንግስት ሰራተኞችን እና የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የመልካም ልማታዊ አስተዳደር በሚል ሽፋን ለፖለቲካ አጀንዳነት ሊጠቀምባቸው በማሰብ እያደረገ ያለው ስልጠና ከአለመግባባት አልፎ እስከ ስድብ መድረሱ ሰልጣኞችን አስቆጥቷል።

በዚሁ መሰረት የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ለስልጠና የጠራው የወያኔ ቡድን ካድሪዎቹ የሰራተኛውን ጥያቄ መመለስ ስላቃታቸው ወደ ደብረጺሆን ያስተላለፉት ሲሆን ዶክተር (በተገዛ ዲግሪ ) ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ ሲመልሱ ተስተውሏል። ሰራተኞቹ የሃይማኖት ነጻነት እና ሙስሊሞች ፣ ዞን 9 ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የዘረኝነት መስፋፋት ፣ የሃገሪቱ ታሪክ ማበላሸት እና የሃገር ዳር ድንበር ፤ የሚታሰሩ ዜጎች እና የተቃዋሚዎች ሮሮ …. ፣ ወዘተ ያቀረቧቸው ጥያቂዎች ከደብረጺሆን ጋር ካለመግባባት በስድብ እና በቁጣ የታጀቡ እንደነበሩ ታውቋል።

በወያኔ ካድሬዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ የታየበት ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና ዶክተር የሚባሉት ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በሺዎች የሚቆጠረውን ሰልጣኝ የመንግስት ሰራተኛ …..ቁጣ በተቀላቀለበት አምባገነናዊ መንፈስ ድንጋጤን ተላብሰው ….. ደንቆሮ …..ደደብ … የዘቀጠ .. በሚሉ የስድብ አጀቦች ጥያቄዎቹ የነማን እንደሆኑ እናውቃለን .. በሚል ማስፈራሪያ ሰራተኛውን ማሰልታን ሳይሆን ማስጠንቀቅ በሚል እንዲሁም ለመጪው ጊዜ እርምጃ እንደሚወሰድ መል እክት በሚያስተላልፍ መልኩ ሲዝቱ ሲሳደቡ ተስተውሏል።

ዶክተር በሚባሉት ደብረጺሆን መልስ ሰራተኛው ከፍተኛ ቁጣ ይሰማ ሲሆን ከአሁን በኋላ በሚደረጉ የስልጣና ቀኖች ላይ ምንም ጥያቄ ላለመጠየቅ እና አስተያየት ላለመስጠት ሰራተኛው አድሞ ወደ ስልጠናው እንደገባ ሲታወቅ የወያኔ ካድሬዎች የሰራተኛውን ድፍርት እና በጥያቄዎች መግነን ተከትሎ ድንጋጤ የፈጠረባቸው ቢሆንም ከጀርባ ግን ሰራተኛውን ሲያበረታቱ ተስተውሏል።
ከስልጠናው መልስ ካድሪዎች ለአለቆቻቸው የሚያቀርቡት ሪፖርት እንደሚጠቁመው የመንግስት ሰራተኛውም ይሁን የዩንቨርስቲው ተማሪ ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ መሆኑን እንደሆነ ከፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።ሚኒሊክሳልሳዊ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡

በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡

በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡ ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-

1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡

2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡

3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡

4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡

5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት… ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣ ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡

እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?

…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡

Image

በሆዳችን አንገዛም !!!!! የተማሪው የዛሪው መሪ መፈክር
“እየተቃውመ የሚሰለጥን እያጉረመረመ የሚበላ ትውልድ ……… ከሰልጣኞቹ ይልቅ አሰልጣኞቹ ጥያቄ የሚያጭር ንግግር እያደረጉ ተቃውሞውን ያባብሱታል ” ከወያኔ ካድሬዎች አንዱ በስካይፒ

ምንሊክ የዘመናዊ ኢትዮጵያ አባት ነው ።……… ኢትዮጵያዊነት በስር መሰረት ሲተላለፍ የመጣ ስለሆነ በዘረኝነት አይናድም።….. አናካሽ እና ከፋፍለህ ግዛ የሚለውን ሰነዳችሁን አቃጥሉት ።… ስልጠናው ይቁም ።….
የተትረፈረፈ ምግብ አምጥታችሁ በሆዳችን ልትገዙን ከሆነ አትሞኙ ። ምግቦች ከመትረፍረፍ የተነሳ እየተደፉ ነው ለምን ለጎዳና ተዳዳሪዎች አይሰጡም።……. ለምን ስንበላ በፖሊስ እንታጀባለን ? ………
የህዝብ ገንዘብ የገዢውን ፓርቲ ፕሮፓጋንዳ ለመርጨት ያላግባብ እየተጠቀማችሁበት ነው።፣…………..
ሕዝብን እየተሳደባችሁ እድሜያችሁ የሚረዝም እንዳይመስላችሁ …. 2007 ምርጫ ድጋፍ ለማግኘት ትባዝናላችሁ ……የሃገር ሃብት ለናንተ ፖለቲካ አጀንዳ እየዋለ እናንተ በቻይና ብድር ታራውጡናላችሁ። ………….ለሕዝብ ጥቅም የዋለ የሃገር ሃብት የለም። …የሚያሳዝነው ሕዝቡ መሮታል የሚመራው አጥቶ ነው እንጂ ….ሰበብ እየፈጠራችሁ ንጹሃንን እያሰራችሁ ተቃዋሚዎችን ወህኒ እየከተታችሁ ሌላውን እያሳደዳችሁ ምርጫ የሚኖር ይመስላቹሃል? …. ከ እናንተ ጋር የሚወዳደር ያለ ይመስላችኋል።
Image

ሰልጣኝ ተማሪዎች ስልጠናው ግጭትን የሚያስነሳ በመሆኑ እንዲቆም ጠየቁ ።ሰልጣኞቹ ፌስ ቡክ እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) VIA ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
ከነሀሴ 9 ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ተክለኃይማኖት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ መምህራን ኮሎጅና የደብረ ማረቆስ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከፋፍለው በአራት የሥልጠና ቦታዎች እንዲሁም 45 የውይይት ቡድኖች ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠናው ከፋፋይና ለትውልዱ ጎጅ በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ተማሪዎቹ በተለይም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ›› በሚል ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ያሉትን ያሉት ሰነድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች ‹‹እስር በእስር ለማናከስ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡ በመሆኑም ሰነዱ ሊቃጠል ይገባዋል፡፡ በቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስንገባ የሚያጋጨን ስለሆነ ስልጠናው በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፡፡ የኦሮሚያ ተማሪዎችን አመጽ የቀሰቀሰው በዚህ የኢህአዴግ ከፋፍለህ ግዛ ሴራ ነው፡፡ ሰነዱ እንደሚለው ኢትዮጵያ ከታናሽንት ወደ ታላቅነት ሳይሆን ከታላቅነት ወደታናሽነት ነው የወረደችው፡፡ ለዚህ ከፋፋይ ሰነድ በርካታ ወጭ ወጥቶ እርስ በእርሳችን ለማናከስ ከሚጣር በገንዘቡ በየጎዳናው የወደቁ ኢትዮጵያውያንን ከርሃብ መታደግ ይችል ነበር፡፡›› በሚል ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ገልጸውልናል፡፡

ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹አጼ ምኒልክ በጊዜያቸው መልካም ስራ ሰርተዋል፡፡ ስህተት ሰሩ እንኳ ቢባል የዘመኑ ወጣቶች ያ ስህተት ላይ ተሳታፊዎች ባለመሆናችን የእኛም ስህተት ተደርጎ ከሌሎቹ ጋር ለማናከሻነት መዋል የለበትም፡፡ በዚህ ዘመን ህወሓት፣ ብአዴንና ሌሎቹ የኢህአዴግ አባላት እንጅ ህዝብ ነፍጠኛ ሊባል አይገባም፡፡ ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፡፡›› ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ ኢህአዴግ ስኬታማ እንደሆነ በሚገልጸው የሰነዱ ክፍል ላይ ካድሬዎች በየ እምነት ተቋማት ጣልቃ እየገቡ በመሆኑ የእምነት ነጻነት እንደሌለ፣ ጋዜጠኞች እየሰደዱ መሆንንና ሚዲያዎች በመዘጋታቸው ሀሳብን በነጻነት መግለጽ እንዳልተቻለ፣ የመድብ ፓርቲ እንደሌለና የኢህአዴግ አፋኝ መሆኑን በመግለጽ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱት ስኬቶች በተግባር እንደሌሉ ተከራክረዋል፡፡

ትምህርትን በተመለከተ ሰነዱም ሆነ ኢህአዴግ በየጊዜው ያብጠለጥላቸዋል ያሏቸውን አጼ ምኒልክ ‹‹እኔ ቤት እንጀራ የለም፡፡ እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ነው ፡፡›› ብለው እንደነበር በማውሳት ከመቶ አመት በፊት ከነበረው ስርዓትም ያነሰ መሆኑን የተከራከሩ መኖራቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የትምህርት ስርዓት ከመቼውም ጊዜ በባሰ መውደቁ፣ ተማሪዎች ተመርቀው በተማሩት ዘርፍ ሳይሆን ኮብልስቶንን ጨምሮ ያልተማሩትን እንዲሰሩ መገደዳቸውንና ስራ አጥ መሆናቸውን በመግለጽ የትምህርት ስርዓቱን ውድቀት አስረድተዋል ተብሏል፡፡ በስልጠናው ወቅት ከኢህአዴግ ስኬት በስተጀርባ ዋናው ተዋናኝ ሆነው የቀረቡት አቶ መለስ ዋነኛ የመወያያ ርዕስ እንደነበሩና ተማሪዎችም ‹‹አማርኛ ተናጋሪውን አቶ መለስ አከርካሪውን መትተነዋል ብለዋል፡፡ አከርካሪውን ከተመታ አሁን ሌላ ከፋፍለህ ግዛን የሚያሰፍን ስልጠና ለምን አስፈለገ? የመለስን ራዕይ አሳካለሁ የሚለው ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፣ ህዝቡን የሚሳደቡ ባለስልጣናት ምንም አይነት እርምጃ የማይወሰድባቸው ስርዓት ለህዝብ ንቀት ስላለው ነው፣ ኢህአዴግ ራሱ ዘረኛ ነው፡፡›› በሚል ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ወጣቱ ኢህአዴግ የያዘውን የተሳሳተ መስመር ለማስያዝ የሚጥርና የማይጠቅም በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ዝምታን የመረጡ ተማሪዎችም እንደ ወጣት ማንም አውቅልሃለሁ ሳይላቸውና ሳይፈሩ ስህተቱን እንዲቃወሙ ማሳሰባቸው ታውቋል፡፡ በስልጠናው ወቅት አሰልጣኞች ተማሪዎች ፌስ ቡክ ውሸት በመሆኑ እንዳይጠቀሙ፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፌስ ቡክን በመጠቀማቸውና በፌስ ቡክ አማካኝነት በሚነሳ ብጥብጥና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መንግስት በሚወስደው እርምጃ ተጎጅ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ተማሪዎች በስልጠናው እንዳይሳተፉ ጥረት ተደርጓል ያሉት ሰልጣኞቹ ‹‹አክራሪና አሸባሪ የሚባሉ አካላት መሳሪያ እንዳትሆኑ፣ ለእነዚህ አካላት መሳሪያ በመሆናችሁ የእርምጃው ሰለባ ትሆናላችሁ፡፡ መንግስት ተጠያቂ አይሆንም፡፡›› የሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ወቅትም ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፌስ ቡከኞች፣ መንግስት በእምነታቸው እንዳይገባ ኢትዮጵያውያን በአጥፊነት መፈረጃቸውንና ተማሪዎች ከእነዚህ አካላት መራቅ እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት መተላላፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች በበኩላቸው ‹‹በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ ሚዲያውን እያፈነ ነው፣ ተቃዋሚዎችን እያሰረ ነው፣ በእምነት ጉዳይ ጣልቃ እየገባ ነው፣ የሚቀጥለውን ምርጫ ወቅት የእነዚህ ሁሉ ጭቆና ወደ አመጽ ቢያመራ ተጠያቂው ማን ነው? ለምን እንደ ሻዕቢያ በግልጽ አምባገነን መሆናችሁን አታውጁም? ህዝቦችን በየ አካባቢው እያፈናቀላችሁ ለምን ምኒልክን ትከሳላችሁ? ብሄራዊ እርቅን ለምን ትፈራላችሁ? የስልጠናው በጀት ይነገረን? ትራንስፎርሜሽኑ አልተሳካም፣ አባይ ግድብ የኢህአዴግ ፕሮጀክት ነው እና ሌሎችንም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማንሳታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በደብረማርቆስ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአሰልጣኝነት ከተመደቡት መካከል አብዛኛዎቹ የገዥው ፓርቲ የካቢኔ አባላት እንደሆኑና በተለይ ታሪክ ላይ ያተኮረው የስልጠናው አካል በብአዴን አባላት ጭምር ቅሬታ እንዳስነሳ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ነሃሴ 9 የጀመረው ስልጠና በሁለት ዙር ለ15 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ፣ የታድሶ መስመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ፣ ልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓትና ፈተናው እንዲሁም ህገ መገንስታዊ መርህና የሰላማዉ ትግል ስልት የተሰኙ አራት ጥራዞችን ያካተተ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በቀጣይ ቀናት ከሰልጣኞቹ የተላኩትን የስልጠኛ ሰነዶችና መረጃዎች እየተከታተልን ለአንባቢያን የምናደርስ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

‹‹ይድረስ ላንቺ››

ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ በዘላለም ክብረት

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣

እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi

ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት

እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን? የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም ‹ ዋስ ጠበቃዬ ነውና› ስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ “ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል” በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን! (እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን… የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው) ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን የ Russia Social Democratic Party ን ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል በ Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና)፤ በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡

እንዲህ ሆነልሽ

አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት ከ1934-1948 ድረስ ለ14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡

‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ለ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››

(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)

ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡

‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 ዓ.ም አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ ‹ሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 ዓ.ም ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይም ‹ሰው ያቅዳል ፣ እግዜር ይስቃል› እንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስ ‹የመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀል› በሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡

) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝ ‹እሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁ › ብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴ ‹ጉዳት› ባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i

ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋል› እያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ፣ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ ‹ሀገር ሰላም› ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 ዓ.ም ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡

የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር በ5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ ለ24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ ለ10 ደቂቃ ፤ ማታ ከ10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት ለ 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ ከ15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ ከ23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡

ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንት ‹አሸባሪ› ወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement ን experience ለማድረግ ‹ታድያለሁ›፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡

አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋ ‹ተፀፅቻለሁ›፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች የ84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)፡

1.

ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ

‹‹ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››

እኔ

ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም” አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችን ‹እንዳበላሸሁ › እያሰብኩና ልማታችን በወለደው የአስፋልት መንገድ ፏ ብዬ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡

2.

እመቤቴ – መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛን ‹አዎ አሲረናል› የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉ ‹አላማችሁ ምንድን ነው በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣

መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) – እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?

እኔ

መርማሪ ፖሊስ፡ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?

እኔ

መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገው ‹ከበላይ አካል› ይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤ “አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡”

ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡

3.

የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬ ‹አንቺ› እንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽ ‹አሸባሪ› ነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ ፡

መርማሪ ፖሊስ፡ ከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?

እኔ

መርማሪ ፖሊስ፡ እኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡

እኔ፡ እስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም በ አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ የማስታውሰው የለም፡፡

መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም?

እኔ፡ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ፤ ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም መቼም?!››

መርማሪ ፖሊስ፡ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡

(‹ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋል› ሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባል› ከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይ ‹ከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት ከ300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽ ‹ሰነድ› አብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ

4.

ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውም ‹ፍቅር ታጋሽ ነው› የሚለውን Paulian ወንዴነት፤ ‹ፍቅር ታጋሽ ናት› በሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይ ‹ኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡

መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነት ‹ያስረዱኝ› ነበር፡፡ “አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችን ‹በደምና በጾም› ያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉ ‹በባንዳነት› ሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜ ‹አንቺ› ትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ ከ 50 ዓመት በፊት ‹እኔና አንተ› ካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ

“ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!” ይላሉ፡፡

ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱን ‹በውበቷ ለሰከሩ› ነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎም ‹ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገር› መንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትና ‹አሸባሪ› የምንሰኝባት፣ ‹ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!

ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹ልማትን ሲተች› “እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው” በማለት ‹ልማት ብቻውን ዋጋ የለውም› ሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳት ‹ወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡

ውዴ! ያን ‹አሸባሪ› ሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡

5.

እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት በ Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘት ‹ከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትን› ባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡

በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው ከ 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡በ2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼ ‹እንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞ ‹ያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን› ሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውም ‹እስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝ› ተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ ‹ለሽብር ተግባራት› መመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?

– ‹አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)

– ‹ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ›

– ‹አሀ እናንተ ናችኋ…..›

****

– ‹አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›

– ‹ከወለጋ ዩኒቨርስቲ›

– ‹አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!….›

*****

– ‹አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)

– ‹ከአምቦ ዩኒቨርስቲ›

– ‹ሕዝቡን እርስ በርስ አጋጭታችሁ ከተማዋን በደም ያጠባችኋት እናንተ….›

– ‹አረ እኔ ከግጭቱ በፊት ነው የታሰርኩት›

– ‹በእውነት ነው የምልክ እድለኛ ነህ፡፡ የኦሮሚያን ልማት ተቃወመ ተብለህ በታሪክ አለመስፈርህ በጣም እድለኛ አድርጎሀል፡፡›

(ለመሳቅ ሁላችንም የጎልማሳውን ከክፍል መውጣት እየተጠባበቅን እኮ ነው ውዴ) – ሁሉ ቧልት የሆነበት ሀገር!

በነዚህ ሁሉ የጉድ ቀናት ለምን እንደታሰርኩ ትክክለኛውን ምክንያት የሚነግረኝ አካል ፍለጋ ሁሌም አስብ ነበር፡፡ መታሰሬ ግን አያስገርመኝም፤ አያስከፋኝም! ደስታን በሔድኩበት ሁሉ እፈልጋለሁ፤ የእድል ነገር ሆኖ ደስታም ከእኔ አይርቅም፡፡ ፍቅሬ ለረጅም ዘመናት ‹የሰው የመኖር አላማ ማወቅ ነው› የሚለውን Aristotlian (አሪስቶትሊያን) አስተምህሮ በልቤ ይዤ እኖር ነበር፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ‹የመኖር ዓላማ መደሰት ነው› የሚለው አስተምህሮ በአርስቶትሉ ‹የማወቅ ዓላማ› ደባልቄ ይሔው እየተደሰትኩልሽና እያወቅሁልሽ እገኛለሁ፡፡ ‹አንች› የደስታዬ ምንጭ፡

‘‘Thanks to you….For you exist’

Clézio

ስለክሴና ስለተስፋዬ ሌላ ደብዳቤ እፅፍልሻለሁ፡፡

P.S አሳሪዬ ሆይ ልብ ይስጥህ!

ያንችው ዘላለም

ከብዙ ፍቅር ጋር!

እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ በባለጠበንጆቹ ወያኔዎች የተነጠቅነውን መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት እንዳያብብ የሃገር መልካም ታሪክ እንዳይወራ ጠንክረው የሚሰሩት ወያኔዎችን የማሳፈር እቅዳቸውን የማደባየት ግዴታው የኛ የኢትዮጵያውያን ነው:: የዓለም፣ የአኅጉራዊና የአገራዊ ፈተናው እየከበደ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያዊነት መለኪያና የጥንካሬው ማረጋገጫ እየጨመረና እየከበደም መጥቷል፡፡ እስካሁን ድረስ ያለው ኢትዮጵያዊነታችን ጠንካራ አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሳና አነጋጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በግልጽ እንነጋገር ከተባለ ግን ኢትዮጵያዊነታችን ደካማ ነው አንልም እንጂ፣ ካለው የኢትዮጵያዊነት ስሜት በላይ እጥፍ ድርብ ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል ብለን ግን በድፍረትና በእምነት እንናገራለን፡፡

አንድነት እና ጥንካሬ በዜጎች መሃል እንዳይሰርጽ በወያኔ የሚሰራውን ደባ የማክሸፍ ሃገራዊ ግዴታ አለብን:: ኢትዮጵያዊ ሚናችንን በአግባቡ ለመወጣት እንኳ ጠንካራ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ጠንካራ ኢትየጵያዊነት ነው ሚና እንድንጫወት ዋስትና የሚሆነው፡፡

ልድገመው !!!
እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ተቀብለን የብሔራችንን ባህልና ቋንቋ እናከብራለን፤ እናሳድጋለን፤ ይህንን ማድረግ ማንንም አይጐዳም፡፡ ሁላችንን ግን ይጠቅማል፡፡ ይህን እያከናወንን ግን ከድህነት በመላቀቅ፣ በመበልፀግ፣ ሰላምና መረጋጋትን እውን በማድረግ፣ መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ ሌላ መንገድ ወይም አማራጭ የለም፡፡
https://www.facebook.com/minilik.salsawi

ሄኖክ የሺጥላ በምዕራብ አፍሪካ የተነሳውን የኢቦላ ቫይረስ ተከትሎ የተለያዩ ሃገራት ወረርሽኙ ወደታየባቸው ሀጋሮች የሚያደርጉትን ማንኛውም አይነት የአየርም ሆነ የየብስ፣ የንግድና የቱሪዝም ፣ የትምህርትና የስልጠና እና ሌሎችንም አይነት የንግድ ይሁን መሰል ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች አቁመዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ፣ አይዞዋችሁ ፣ ወደተባለው …

ኢቦላና ወያኔ (ሄኖክ የሺጥላ) Read more »

አሳቤ አበበ (ከቶሮንቶ) ሰሞኑን በአንድነትና መ.ኢ.አ.ድ መካከል ተጀምሮ ለነበረው ውህደት በወያኔ የተከሰቱ መሰናክሎች ሳያንሱ በአሜሪካ ከሚገኙ ደጋፊ ነን ከሚሉ አቶ ግርማ ካሳና አልዩ ተበጀ እንዲሁም እዚያው ኢትዮጵያ ባሉት ዶ/ር ያዕቆብ ሐይለማርያም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላይ የተወረወሩትን የማፍረሻ ድንጋይዎች ቆም …

በአንድነት ፓርቲ ላይ ደጋፊ ነን ከሚሉ የተወረወሩትን ድንጋይዎች ቆም ብሎ ማጤን ተገቢ ነው Read more »

ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር) ጸጋየ አየለ ይግዛው ይባላል። የ፴፬ ዐመት ባለትዳርና የልጆች አባት ነበር። ጎንደር ሆስፒታል ውስጥ በራዲዮሎጂስትነት ሲሰራ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባል ነህ በሚል ፖሊስ የሚያደርስበትን ወከባ ለመሸሽ ወደ ደብረማርቆስ ሄዶ በአንድ የግል ክሊኒክ ተቀጥሮ መስራት ይጀምራል። ነገር ግን የፈራው …

የጸጋየ አየለ ገዳይ አሜሪካ ይገኛል Read more »

”ለሰብአዊ መብትና ለዴሞክራሲ ጥብቅና መቆም ሽብርተኝነት ነው”፡- የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ

የሂዩማን ራይትስ ዎች የዓለም አቀፍ ዘገባ ስለ ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ የፖሊስ ሃይል፤ በጦር አባላትና በሌሎችም ተመሳሳይ አባላት፤ በደህንነት አባላት በቅጣት መልክ በተቃዋሚ ደጋፊዎችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ላይ የሚፈጸመው ስቃይና የእስረኞች የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢነትና መከራ የከፋ ከመሆኑም ባሻገር በሚስጣራዊ ማጎሪያዎች፤ በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በእስር የሚገኙት ንጹሃን ዜጎች ሁኔታ አሳሳቢነቱ በየጊዜው እየከፋ የሚሄድ መሆኑን በተደጋጋሚ በግልጽ አስቀምጧል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መለቀቅ አለባቸው፡፡ ሁኔታቸው በአ……..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ//

http://wp.me/p3p0Hd-CG

ተከብሮ ያላስከበረ፣ ሰርቶ ያላሰራ ‘ሕገ-መንግስት’

ሕዝባዊ መንግስት ማለት ሕዝቡ በቀጥታ የራሱ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት ማለታችን ነው:: ህዝቡ መሪዎቹን በነጻ የመምረጥ እና የማዉረድ መብቱ የተረጋገጠበት ማለት ነው:: ሕዝባዊ መንግስት ስንል የመግስት ስልጣን መነሻ እና መድረሻው ህዝቡ ነው ማለታችን ነው::
ህገ መንግስት ደግሞ የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ‘ህገ መንግስት’ እንደሚለው ከሆነ ‘ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገ መንግስቱ የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም።’
ሙሉውን ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ http://t.co/tM139HuDYt

በመንግስት ተቋማት ውስጥ ተቀጥሮ መስራት በፈቃደኝነት ድህነትን ለመውረስ ዝግጁ መሆን ማለት ነው፡፡ የመንግስት ተቋማቶች ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ድርቅ ተመትተዋል፡፡ ተስፋ የቆረጡ፤በሙያቸው የማይተማመኑ ወይም ሙያ አልቦዎች፣ በሠራተኛው ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ያልሆኑ የእውቀት የክህሎት፣ የዝግጅት እና የተነሳሽት ድኩማኖች መናኸሪያ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ አማራጭ አጥቶ የመንግስትን ቤት ሙጥኝ ያለ ፈጻሚ እንኳንስ አገር ሊገነባና የአፍራሽነት ሚና ነው የሚጫወተው፡፡ መንግስት በክህሎት አልቦ እና በሙያ ለምኔ ፈጻሚዎች ተከብቦ እንዴትስ ህዝብን ማገልገል ይችላል? የግሉ ዘርፍ በሰው ኃይል አደረጃጀቱ በልጦት ከተገኘ መንግስት የግሉን ዘርፍ መምራት ቀርቆ መንግስት በግሉ ዘርፍ ይመራል፡፡

http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … ost_3.html

Image

በሐሰት መንግስታዊ ማጭበርበሮች ሳንታለል በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎችን እናረጋግጥ !!!
#Ethiopia #EPRDF #UDJ #Blueparty #Ginbot7 #Medrek #MinilikSalsawi

ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉ ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል።ያለለውን እንዳለ ድሮ ተግንብቶ የታደሰውን እንደ አዲስ እንደተገነባ ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ ወዘተ በማድረግ በሁለት እና ሶስት እጥፍ በማባዛት በመቶኛ በማስላት በመደመር በማባዛት ያሌለውን ምስል በመፍጠር ሕዝቡን እያደናበሩ ይገኛሉ።

በአለም ላይ ካሉ መንግስታት በተለየ ሁኔታ ዜጎቹን እያጭበረበረ ወደ ድህነት አዘቅት እየከተተ ያለ መንግስታዊ አስተዳደር ነኝ የሚል ቢኖር ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው። የወያኔ የማይሳኩ እና የሚያደሐዩ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፖሊሲዎች መነሻቸው የተሳሳቱ ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው። ማንኛውንም ፖሊሲ ይሁን አዋጅ መመሪያ ይሁን ደንብ ወያኔ ሲያወጣ በተቆጣጠራቸው ሚዲያዎቹ እያጋነነ የሕዝብን ልብ ለመስቀል በመሞከር እደርስበታለው ያለው ግብ ምንግዜም እየተኮላሸ ተጨባጩን ሁኔታ ባለማገናዘብ እየካደ ስለሚጓዝ የሃገር ኢኮኖሚ የጨው ክምር በመሆኑ እየተናደበት ይገኛል።

ሕዝቡ ትክክለኛ አስተዳዳሪ ባለማግኘቱ ምክንያት እየተንገላታ በየቦታው ምሬት በበዛበት በአሁኑ ሰአት ተገቢውን አገልግሎት እንዳገኘ በማድረግ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ለማሳሳት እየተሞከር ሲኦን በቀረቡ መዝገቦች ላይ ውሳኔ መስጠት አቅቶት ወይም በቸልተኝነት አልወስንም ብሎ የሚኮፈስ ቢሮክራሲ ዜጎችን ሲያስለቅስ በአደባባይ እየታየ መፍትሔ እየተገኘ ነው የሚል ማደናገሪያ ሲቀርብ ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራል፡፡በፍትሕ ሥርዓቱ አካባቢም ሲታይ እየወጡ ያሉ መግለጫዎችና ሪፖርቶች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር የለውም ዓይነት ሪፖርቶች ይቀርባሉ፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲቅበዘበዝ እየታየ የማይመስል ነገር ይነገራል፡፡ በዚህ መስክ ያለው ማደናገር ራስ ያሳምማል፡፡

በኑሮ ውድነት በትራንስፖርት በውኃ በኤሌክትሪክና በስልክ አገልግሎቶች አለመሟላት እና መቆራረጥ ምክንያት ሥራውና ኑሮው አሳር እያየበት ያለው ሕዝብ የአገልግሎቱ ተደራሽነት በዚህን ያህል በመቶ አደገ ወይም ደረሰ ሲባል ቀልድ የተያዘ ይመስለዋል፡፡ ለሳምንታት ውኃ አጥቶ የሚንከራተት ሕዝብ የውኃ ተደራሽነት ከዘጠና በመቶ በላይ ሆኗል ተብሎ ሲለፈፍበት እንዴት ይቀበላል? በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ምክንያት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ማምረት እያቃተውና ሕዝቡ በጨለማ ሲሰቃይ ተደራሽነቱ ይህን ያህል ደርሷል ሲባል ማን ያምናል? በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ ማደናገሪያዎች ሞልተዋል፡፡ከመሃል አገር እና ከተለያዩ ክፍለሃገሮች ገበያዎች የተገኙ ተብለው የሚቀርቡ የእህል ዋጋዎች መጋጨት የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ጤፍ፣ በርበሬ፣ ጥራጥሬና የተለያዩ የግብርና ምርቶች ዋጋ በወያኔ መገናኛ ብዙኃኑ ሲተነተን፣ በፍፁም ገበያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያሳይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ማደናገሪያ ማንን እንደሚጠቅም አይገባንም፡፡ ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።

ስለዚህ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንዱ ለሌላው መረጃዎችን በማስተላለፍ ወያኔ እና ሚዲያዎቹ የሚጠቀሙበትን የማደናበሪያ ስልት በማጋለጥ እና ሊደናበር የሚችለውን የዋሁን ኢትዮጵያዊ በማስረዳት የዜግነት ግዲታችንን እየተወጣን በጋራ በመታገል ይህንን ውሸታም እና አጭበርባሪ አደናባሪ ስርአት ልናስወግደው እና ለመጪው ትውልድ እውነትን የተሞላች አገር የማስረከብ ሃላፊነት እንዳለብን ለማሳሰብ እወዳለሁ። በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎቻችንን እናረጋግጣለን!!1 #ምንሊክሳልሳዊ

በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲስች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።
ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ከመሃል አገር በተለያየ የጦር መምሪያ ውስጥ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት እና የአንድ ኮርስ ምሩቅ ናቸው የተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ የሕወሓት ጄኔራሎች ላይ ጥርሱን እንደነከሰ የሚነገርለት ኮሎኔል አለም የሚባለውን የተንቤን ተውላጅ ጨምሮ አስረ አንዱ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ገብተዋል የሚል መረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የሶስቱ ዱካ አለመገኘቱን እና ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ከየት ታፍነው በማን ታፍነው እንደተወሰዱ ሳይታወቅ በደብረዘይት የምድር ውስጥ እስር ቤት እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የሕወሓት ጄኔራሎችን ያመሳቸው ጉዳይ የተንቤን ተወላጆች ሌሎች የደቡብ እና የአማራ ተወላጆች ተያይዞ መጥፋት ሲሆን እንዲሁም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ እየላላ መጥቷል ሲሉ የደነፉበት የወታደራዊ ደህንነት ቁጥጥር መላላት ለነገው የስልጣን እድሜያቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳጠላበታ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩልን የመከላከያ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በሙሉ የሃገሪት እዞች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ፍተሻ እንዲካሄድ በዛሬው ስብሰባ ጥብቅ ትእዛዝ ያስተላለፉት የሕወሓት ጄኔራሎች በደቡብ እና በምእራብ ድንበሮች አከባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈተሹ በወጪ ገቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እና የየቀኑ ሪፖርት እንዲላክ እንዲሁም በመሃል አገር ያሉ የቶር መኮንኖች በየቀኑ ለቅርብ አለቃቸው ዝርዝር የአባላት እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥብቅ ትእዛዝ አውርደዋል።እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ደህንነቶች በየእዙ እንዲመደቡ አዘዋል።

በዚህ ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የወታደራዊ ደህንነት ሪፖርቶቹን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን።
#ምንሊክሳልሳዊ

ናትናኤል በርሔ ( ኖርዌይ ቲንግቮል)

ለአንድ አገር አስተዳደር መንግስት ለዜጎቹ መሰረታዊ ፍላጎቶች ከሆኑ ነገሮች አንዱ የሆነው ሰው ስራውን ሰርቶ በቂ የላፋቱን ዋጋ ማግኘት መብት ነው በተለይ በአሁኑ ሰዖት መንግስት እከተለዋለሁ ከሚለው መርህ የተገላቢጦሽ እየሆነ ዜጎች በገዛ አገራቸው በተፈጥሮዋዊ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋ የኢኮኖሚ ግሽበት ከድጡ ወደ ማጡ እየተሸጋገሩ ይገኛል።የቀድም ጠቅላይ ሚኒስተር የሽግግር መንግስቱ ሲመሩበት በነበር ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ october 1995 በተጠየቁት ጥያቄ ” የዛሬ 10 ዖመት ወይም 20 ዖመት በሗል ኢትዮጵያ በዚህ ሁኔታ ባየው ደስ ይለኛል ብለው የሚያስቡት” ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ እሳቸው ሲመልሱ የዛሬ 10 ዖመት ይሆናል ብየ ተስፋ የማደርገው እና የምመኘው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀን 3 ጊዜ ምግብ ያገኛል የሚል ነው።ከዛም ቀጥሎ ምናልባት በጣም የተሳካልን እንደሆን በአመት 2 ቅያሪ ወይም 3 ቅያሪ ልብስ ያገኛል እንዲሁም ከዛ በጣም የተሳካልን እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝብ ግፋ ቢል ከመንገድ 2 ሰዖት ርቀት በላይ ይኖራል።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህዝብ ምግብ አማርጦ ይበላል።ነገር ግን ከ19 ዖመት በፊት የተናገሩት ቃል የተስፋ ቃል ከመሆን ያለፈ እና የዘለል አልሆነም።የኑሮ ውድነቱ ይልቁንስ የታችኛው ክፍል <!–more–>ህብረተሰብ ፈተና ውስጥ እና አደጋ ውስጥ ከቶታል።በተለይ የደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ጭማሪው ይመለከተናል የተባለው የመንግስት ሰራተኞች አብዛኞቹ ይጨመርላቸዋል የተባለው ጭማሪ የኑሮውን ሁኔታ ከመቅረፍ ይልቅስ ኑሮው የባሰ የሚያደገረሽ እና ገንዘብ የመግዛት አቅም ያሳጣዋል።መንግስት ከወራት በፊት የደምዝ ጭማሪ አደርጋለሁ በማለቱ ምክንያት በአንዳንድ ምርቱን አምራች ፋብሪካዎች የምርት አቅርቦታቸው ላይ ጭማሪ አሳይተዋል።

በዚህም በተያያዘ ዜጎች፣ገበሬዎች፣ተማሪዎች፣ክሊኒኮች፣ሆስፒታሎች፣ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች የጥራት መጋደል እና በበቂ ሁኔታ ያለመቅረብ ችግሮች ያመጣል።ነጋዴ እና ቸርቻሪ ነን ባዮች ሕዝቡን ጨርቁን አስጥሎ ለመስደድ ቆርጠው የተነሱ ይመስል ከመንግስት ጋር እሽቅድምድም ይዘዋል፡፡ መንግስት ዋጋ ተምንኩ ሲል፣ እነሱ ከላይ ከላይ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ሸማቹ ግን የእነሱን ጭማሪ ያክል እድገት በየወሩ እንደማያስመዘግብ የታወቀ ነውና ግራ መጋባትን ሲጋፈጥ ይስተዋላል ይህ መተረማመስ ወራትን ተሻግሮ እንደ ከዚህ በፊቱ ድስት ጥዶ የዘይቱን ማለቅ ያየ ሮጥ ብሎ ከሱቅ ማግኘት አልቻለም፡፡ ብዙዎችም ቡና በጨው ሳይወዱ ለመጠጣት ተገደዱ፡፡ ልብሳቸውን በአመድና በእንዶድ ማጠብ እስኪከጅሉ ድረስ የሳሙና ዋጋ የማይቀመስ ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ መንግስት የቸርቻሪነትና የአከፋፋይነት መብቱን መንግስት ነክ ለሆኑ ተቋማት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ እውነት ይሄ ግና እስከምን ድረስ ያስኬዳል ?
ለመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ከመደረጉ በፊት ደሞዝ ሲጨምር አብረው ዋጋ የሚጨምሩትን ነጋዴዎች ለመቆጣጠር ተብሎ የዋጋ ተመን መደረጉ በብዙ ሚዲያዎች ተወራ፡ ፡ ደስ ብሎን ሳናበቃ የደሞዝ ጭማሪው ምን ያክል እንደሆነ ሳናውቅ የዋጋ ጭማሪን መንግስት ራሱ አንድ ብሎ ጀመረው፡፡ ማባሪያና ማቆሚያ ያጣው የየወሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያልነካካው ማን አለ?

በመጀመሪያው ወር የትራንስፖርት ወጭው አንድ መቶ ብር የነበረ ግለሰብ፣ በሁለተኛው ወር ወደ አንድ መቶ አስራ አምስት ብር፤ በሶስተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ሃያ አምስት ብር፤ በአራተኛው ወር ወደ አንድ መቶ ስልሳ ብር እያደገ ይገኛል፡ ፡ ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ ነው በየወሩ ይህንን ያክል ጭማሪ መሸከም የሚችለው; በደሞዙ ወይም በገቢው ይህን ያክል ጭማሪ መቋቋም የሚያስችል እድገት እያገኘ ያለው የትኛው ሰው ነው? ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች እጅግ እጅግ አስጨናቂ በሆኑበት በዚህ ዘመን በእግር መሄድን ምርጫ ማድረግ የብዙዎች
ግዴታ እየሆነ ነው፡፡

መንግስት ነዳጅ ወር እየጠበቀ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ የዚህን ምክንያት በተመለከተ በየጊዜው ምክንያቶች ይደረደራሉ፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የአረብ ሀገራት በአብዮታቸው ምክንያት ያቀርቡት የነበረው የነዳጅ መጠን ስለቀነሰ ወዘተ ይባላል፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ቆዳ ከመወጠር ሌላ አማራጭ የለውም ? ለመንግስት ሰዎች ስብሰባ የቅንጦት ውሃና ኩኪስ መግዣ በየጊዜው እንደ ርችት ለሚረጩት የጽህፈት መሳሪያዎች ወይም ለሌላ አልባሌ መዝናኛ የሚወጡ ወጭዎችን ቆጥቦ ነዳጅ ላይ ድጎማ ማደረግ አይቻልም እንዴ ?

የደሞዝ ጭማሪው የተደረገው ለመንግስት ሰራተኞች እንጅ ለሁሉም የሀገሪቱ ሰራተኞች አይደለም፡፡ እንደውም ይህንን ልብ ብለን ከተመለከትነው ከምሬት ብዛት ሊያስቀን የሚደርስ እውነታ እናያለን፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ኖሯቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ሁለት መምህራንን ብናነጻጽር፣ ይህንን እውነታ ማየት እንችላለን፡፡ ለነገሩ የግል መስሪያ ቤቶች ጉዳይ አሁንም ስግብግብ ነጋዴዎችን የሚመለከት ቢሆንም፣ ተቀጥረው የሚሰሩት ግን እንደዜጋም፣ እንደነጋዴም፣ እንደሰራተኛም ሊታሰብላቸው ይገባል፡፡

መንግስትም ቢሆን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቅ ከነበረው የደሞዝ ጭማሪ በታች እንደ ጨመረ ብዙዎች ይስማማሉ፡ ፡ በሰላሳና አርባ ፐርሰንት ብቻ የሚወሰን ጭማሪ ያደርጋል ብሎ ላለመገመት ታላቁ መነሻ መንግስት ቀድሞ ይሰጣቸው የነበሩ የሚያጓጉ መግለጫዎች ነበሩ፡፡የሆነው ሆኖ፣ ሀገራችን ይህን በመሰለ የወል እውነታ ውስጥ እንዳለች እየታወቀ፣ የኑሮ ውድነት ከእለት እለት ሲባባስ፣ አሁንም መፍሄ እየተባሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች ችግር ሲያባብሱ እንጅ ሲያሻሽሉ እያየን አይደለም፡፡

ሰሞኑ የተጨመረው የደምዝ ጭማሪ ውጤታማ እና አመርቂ አለመሆኑን በሰራ ላይ እናየዋለን ለምሳሌ ያክል ስኳር አቅርቦትን መንግስት አገር ውስጥ የሚያደርሳቸውን ምርት ለህብረተሰቡ በበቂ ከማዳረስ ያለፍ ገበያውን በማን አለብኝነት ተቆጣጥሮ ድሃውን ህዝብ የዕለት ጉርሱን በመንጠቅ ለረሃብ እና እርዛት ዳርጎታል።ታሪክ
እንደሚያወሳው ከሆነ በንጉሱ ዘመን የመጨረሻ ስርዓት መውደቅ ለፊውዳሉ የቀረቡና የንጉሱን ቤተሰቦች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ስልጣን ላይ መቀመጥ መሞከር ትልቁ ምክንያት በትራንስፖርት ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአገሪቱ ላይ በመደረጉ ነበር።የኢህአዴግ መንግስት ስልጣን በተረከበ ዘመን ኢኮኖሚውን በምኒተሪ እና በፊሲካሊ ፖሊሲ በነፃ የንግድ ስም ህዝቡን እያታለሉ በማደናገር የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚደረግ ስልታዊ መንገድ ነው።

በአገራችን የምትገኝበት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ምስቅልቅል፣የፖለቲካው ነፀብራቅ ነው።የዚህ ምስቅልቅል በመሆኑም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አንዱ ማሳያ ከፍተኛ የሆነ የዜጎች ስደት ነው።ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚው እና ፖለቲካው ዙሪያው ባጠኑት ጥናት ተቋማት የኢትዮጵያ ዜጎቿ ለኑሮ የማይመርጧት ሀገር እንደሆነች ተዘግቧል። 46% የሚቆጠሩ ዜጎች ከሀገራቸው ውጭ በስደት የመከራን ሕይወት ለመግፋት ተገደዋል።ዜጎች ባገራቸው ሰርቶ የመኖር ዕድሉን ማግኘት ካልቻሉበት ሀገር፣ስደት መምረጣቸው ፣የትምህርት፣የስራ ፣የቁጠባ ዕድል ለሁሉም እንዲደርስ ማድረግ ግድ የሚል በተለይ ወደ ዓረብ አገራት የሚሄዱ እህቶቻችን የሚደርስባቸው ግፍና ውርደት ፣ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው።ሁሉም አንገት የሚያስደፋ ሆኖዋል።በነዚህ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰሩበትን የደመወዝ ይከለከላሉ፣ ዜጎች በቂ ጥሪት እንዲያፈሩ ከማገዝ ጎን ለጎን ይደበደባሉ፤ ይደፈራሉ፤ በግፍ ይታሰራሉ፤ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ይገደላሉ፡፡ ይህ ዓይነት የዜጎች መብት በድርጅት፣በማህበረሰብን ጥቅም መብት ማስከበር አልቻለም።በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ሕዝቡ በመንግስት ላይ ግፊት ማድረግ አለበት።በምርጫ ሰምን የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ ማስተካከያ ህዝብን መደለል አይቻልም።ቸር እንሰንብት፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ መንግስት በመተቸታቸው በግልጽ በመጻፋቸውና በአደባባይ በመናገራቸው ከዚህም አልፎ በጥርጣሬ በተለይም በብሄረሰብ ማንነታቸው እያሳደደ የሚያፍን የሚያሰቃይና የሚገል የሽብር ተቋም ካለ ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የተቃውሞ ሃይል በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ ከወያኔ ውጪ አንዳች ሃይል የለም።

አፋኙ የወያኔ ስርአት በተለየም የህዝቡን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ የሚቀማጠሉት የህወሃት መሪዎችና ሎሌዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ በሰሙ ቁጥር እንደሚሸበሩና እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ይታወቃል። አፍነውና ዘርፈው ገለው የሚገዙት ህዝብ ግፍ በዛብኝ ብሎ በተናገረ ቁጥር የሚሸበሩት እነሱ ብቻ እንጂ ህዝቡ አይደለም።
በኢትዮጵያ ምድር ያለው አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ሺ ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማስረዳት ይቻላል። ሶስት አመት ሙሉ የሰላም እጃቸውን እየዘረጉ ከልመና ባልተለየ ሁኔታ መብታቸውን የጠየቁና ድምጻችን ይሰማ ያሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማንንም ዜጋ አላሸበሩም። የተገላቢጦሽ እነሱ አሸባሪ ተብለው የግፍ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል።

ጋዜጠኞችና ጦማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁ በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። እነሱ ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም። ከመንገድ ላይ ጎትተው እንደ እባብ ቀጥቅጠውና ፈነካክተው በማግስቱ ፍርድ ቤት ያቀረቧት ወየንሸት ሞላ የተባለች ባለ ተስፋ ወጣት የወያኔ አረመኔዎች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ጭፍጨፋ እግር ጥሏት ከማየትና ከመታዘብ ውጪ ያሸበረችው ሰው፣ ሀገር የለም። በየወህኒ ቤቱ እና አፈና ጣቢያው ታስረው የሚቀጠቀጡት የኦሮሞ ልጆች ለጥያቄያቸው መልስ ሲጠብቁ ከመጨፍጨፍ ያለፈ የፈጸሙት እብሪት የለም። በየክልሉ ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ ጥያቄ ጠየቅክ፣ ባለስልጣን ደፈርክ፣ ተሰብስበህ አየንህ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ገበሬ የሰራው ወንጀል የለም። አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሊያፈነዱ ሲሉ ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ ብሎ በአደባባይ የሚሳለቀው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ አይደለም።

የኛ መሪ አንዳርጋቸው ከልጅነት እድሜው ጀምሮ ራሱን ለህዝብ ነጻነት የሰጠ አርበኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም። በተመሳሳይ ውንብድና ከጎረቤት ሀገር ድረስ በአለም አቀፍ የወረበሎች ውንብድና መንገድ ወያኔ እያፈነ የገደላቸው አሮሞዎችና፣ ሱማሌዎች፣ አኙዋኮች፣ አማሮችና ሌሎችም ነጻነት ከመፈለግ ውጪ ያሸበሩት ህዝብና ሀገር የለም።
በኢትዮጵያ ምድር የነጻነት ድምጽና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የሚሸበረው ህወሃትና በለሟሎች ብቻ ናቸው። ይህ የነጻነት ድምጽ ደግሞ እየጎላ መሄዱ የማይቀር ነውና ወያኔ ሰፈር ሽብር ይሆናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወጣት፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ገበሬ እና በየቦታው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ! አሸባሪህ ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን አውቀህ በገዛ ሀገርህ ላይ ነጻነት በተመኘህና በጠየቅህ ጊዜ ሁሉ ለሽብር ጥቃቱ ኢላማ ያደረጉህን ወያኔ ተባብረን ከላያችን ለማውረድ ተነስ! በያለህበት እምቢ በል! ለወያኔ የሚጠቅም የመሰለህን ነገር ሁሉ አታድርግ! አትተባበር! ሸቀጣቸውን አትግዛ! ወያኔዎችን ከማህበራዊ ሂወትህ አግል! የቻልክ ሁሉ ደግሞ የነጻነት አርበኞችን ዛሬ ነገ ሳትል አሁን ተቀላቀል!!! ነጻነታችን ያለው በእጃችን ላይ መሆኑን አትዘንጋ። ግንቦት 7 ሁልጊዜም ከመቼውም ጠንክሮ ከጎንህ ነው።

የወያኔን ሽብር በተባበረ ሃይል እናቁመው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ግንቦት7

የትግራይ ስብስቡ በጂጁ ሆቴል እቅዳቸው የህወሓትና የደህንነት ሰዎች ባሉበት ኣውጥተዋል ::
ሕወሓት በትግራይ ከዚህ ቀደም በሚደረጉ ምርጫዎች ካለምንም ተወዳዳሪ በብቸኝነት ተወዳዳሪ ሲመጣ ደሞ ስም በማጥፋት እና በጉልበት በመደቆስ በብቸኝነት ምርጫዎችን እያሸነፈ ላለፉት 23 አመታት ዘልቋል። ካለፉት 6 አመታት በኋላ አረና ትግርያ ብሎ የሚጠራ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ተመስርቶ በትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን እያስፋፋ ባለበት ሰአት በመጭው ምርጫ እሸነፋለሁ ሕዝቡ በድምጹ ይጥለኛል የሚል ከባድ ስጋት ስላለበት ከአረና ፓርቲ ጋር ይመሳሰላልኛል ያለውን ተለጣፊ ፓርቲ ለመመስረን እንቅስቃሴ መጀመሩን ታውቋል።

http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … -post.html

“የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” በያዘነው ሳምንት መጀመሪያ በህግ የተፈቀደለትን ሰማኒያ ከመቶ ጊዜ አጠናቆ ተዘግቷል፡፡ ስራውን እንጂ ግዜውን አላልኩም፡፡ በቀረው 20 ከመቶ በሚሆነው ጊዜ ባለፉት አራት ዓመታት ያከናወናቸውን ዓይነት ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ ለዚህ ዋናው ምክንያት ኢህአዴግ፣ በገዢነት በማንኛውም መንገድ ሊቀጥል እንደሚችል እርግጠኛ ቢሆንም፤ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ግን መቀጠል አለመቀጠላቸውን የሚያረጋግጡበት ግልፅ የሆነ አሰራር ባለመኖሩ ስጋት ላይ እንደሚወድቁ ስለማውቅ ነው፡፡ ይህ ስጋት ካሁኑ መታየት ጀምሯል፡፡ ስለዚህ አብዛኞቹ የምክር ቤት አባላት፣ አሁን በቀጣይ ዕጣ-ፋንታቸው ላይ የሚወሰነውን የሚጠባበቁበት እና በግላቸውም ቢሆን አማራጭ የሚመለከቱበት ጊዜ ነው፡፡

እነዚሁ የምክር ቤት አባላት የአራተኛውን ዓመት ጊዜ ለማጠናቀቂያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቀረቧቸው ከደርዘን የሚበልጡ ጥያቄዎች መካከል፤ ገዢው ፓርቲ ያቀደውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ክፍተት እንዳለበት ማሳለቁ አያቋርጥም፡፡ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡትም መልስ ‹‹ያሉትን ችግሮች ተቀብሎ ቢሆንም›› በሚል ማገናኛ ቃል በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሰረት ዕድገት አስመዝግበናል የሚል ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ አንድ አንድ ነጥቦችን አንስተን እንመልከት፡፡

መንግስት፣ በዘመቻ ከሚሰራቸው የኮንስትራክሽን እና ሌሎች ግንባታዎች ጋር በተያያዘ እየተፈጠሩ ያሉ እድሎች ወደፊት ዘላቂ ሊሆኑ የሚችሉት፤ በምርቱ ዘርፍ የግል ባለሀብቱ ሲሳተፍ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ዘርፍ ግን በሚፈለገው መጠን የስራ እድል ሊፈጥር በሚችል ሁኔታ እየተስፋፋ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀብለውታል፡፡ ይህም ቢሆን የሀገራችን ኢኮኖሚ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሰረት በሁለት አሃዝ ማደጉን ግን አላቋረጠም፡፡ የምርቱ ዘርፍ የስራ እድል ቢፈጥርም ባይፈጥርም፣ ኢኮኖሚያችን ማደጉን ለነገሩ ኢትዮጵያዊያን አስማተኞች ሳንሆን አንቀርም፡፡ ስራ ቢኖረንም ባይኖረንም በልተን/ቀምሰን ማደርና ጠዋት ለስራ-ፈትነት አርፍዶ መንቃት የለመድን ይመስለኛል፡፡

መንግስት የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ፤ ስግብግብ ነጋዴዎች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደማይገባቸው በተደጋጋሚ ከመገለፁ በተጨማሪ አሁን የሚመጣ የዋጋ ጭማሪ ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንደሌለው እንድናምን እየተነገረን ነው፡፡ የኢኮኖሚክስ “ሀሁ” እንደሚነግረን ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ማለት የአቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም ሲሆን፣ የኢኮኖሚክሱ “አቦጊዳ” ደግሞ እነዚህ ሁለቱን የሚያሳልጠው የገንዘብ አቅርቦት ተመጣጣኝ አለመሆን እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ክፍተት መኖሩን አምነው፣ ይህ ክፍተት የሚዘጋው፣ የበለጠ የከፈለ ያገኛል በሚለው መርህ መሆኑን እርሱት እያሉን ነው፡፡ ይህ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ካልሆነ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩም ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክንያት ለምን ሌላ እንደሚፈልጉ ለእኔ ግልፅ አይደለም፡፡ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር መንግስት በመሰረታዊ ዕቃዎች ላይ ድጎማ በማድረግ ዋጋ እንደሚያረጋጋ የነገሩን፣ በቂ አቅርቦት በሌለበት ድጎማ ዋጋ እንደማያረጋጋ ለማወቅ የኢኮኖሚ ሊቅ መሆን አይጠይቅም፡፡ በዚህ ጊዜ የሚኖረው በኮታ ማደል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለጥቁር ገበያ እና ለከፍተኛ ዋጋ ንረት መንገድ ይከፍታል፡፡

ለማንኛውም በደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በሚፈጠር የዋጋ ንረት ሃላፊነቱን የሚወስዱት “ጥቂት ስግብግብ ነጋዴዎች” ስለሆኑ፤ እነሱን ለመታገል በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቀመጠው አቅጣጫ “ተደራጁ” የሚል ነው፡፡ በእኔ እምነት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር፣ አሁን ባለው ሁኔታ የሚያዋጣ ስላልሆነ በየመስሪያ ቤታችን የዋጋ ንረትን በጋራ ለመቆጣጠር መደራጀት ሊኖርብን ነው፡፡ ይህን ኃላፊነት ግን ለምን አሁን ያለው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት አይረከበውም? ይህ አደረጃጀት፤ አንደኛ መንግስት በትክክል መደጎሙን ይከታተላል፤ እግረ-መንገዱንም ከ“ስግብግብ ነጋዴዎች” ጋር ግብይት እንዳናካሂድ አድማ ለማድረግ ይጠቅመናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “በነፃ ገበያ” ስርዓት ዋጋ ጨመርክ ተብሎ ማሰር ስለማይቻል ነው አድማ ማድረግን ያመጣሁት እንጂ አብዮት ለመቀስቀስ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ የሚያስጠይቀው በሸማቾች ህግ ሳይሆን በፀረ-ሽብር ህግ ነው፡፡

መንግስት፣ በዕቅድ ደረጃ ስምንት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከውጭ ንግድ ለማግኘት አቅዶ ሊሳካለት አልቻለም፡፡ ለዚህም ዋና ዋና የተባሉት እና በመንግስትም እንደችግር ከተጠቀሱት ውስጥ ቡና ማልማት ከሚችለው መሬት አንፃር ከሃምሳ በመቶ በታች፣ ከምርታማነት አንፃር ገና አንድ ሶሰተኛው አካባቢ ላይ መሆናችን ነው፡፡ በዕቅድ ዘመኑ የቅባት እህሎች ለማምረት ወደ ተግባር እንደሚገቡ የታሰቡት ክልሎች ወደ ስራ ያለመግባታቸው፤ የገቡት የአማራና የትግራይ ክልልም ቢሆኑ፣ ምርታማነታቸው ከሃምሳ በመቶ በታች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከላይ እንደገለፅኩት የምርት ዘርፉ ገና ያልተጀመረ መሆኑ፣ በማዕድን ዘርፍ የወርቅ ዋጋ መቀነስ ብቻ ሳይሆን በባህላዊ አምራቾች ሊገኝ የታሰበው ያለመሳካቱ፣ እንዲሁም እጅግ ብዛት ያላቸው የንግድ ሰርዓት ማነቆዎች በመኖራቸው ምክንያት ዕቅዱ አልተሳካም፡፡ ይህን የሚያህል ሀገራዊ ዕቅድ ባልተሳካበት ሁኔታ፣ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት አንድ መድህን ግን አልጠፋም፡፡ ይኽውም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለዘመዶቻቸው የላኩት ገንዘብ ከዕቅድ በላይ ተሳክቷል፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን የሀገሪቱ አጠቃላይ እድገት በሁለት አሃዝ ከማደግ የከለከለው አንድም ምድራዊ ሀይል አልተገኝም፡፡ የውጭ ምንዛሬ ግኝታችን ከስልሣ በመቶ በታች ቢሆንም እድገታችን ግን ካቀድነው ፍንክች አላለም፡፡

የአንድ ሀገር እድገት የሚለካው ዜጎች በትምህርት በሚያገኙት ክህሎት እና ይህንንም ክህሎት እሴት ለመጨመር ሲያውሉት እንደሆነ ይታመናል፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ግብ ከትግራይ ክልል በስተቀር ያለመሳካቱ ጉዳቱን ያዩበት አቅጣጫ ምቾት ሰጥቶኛል፡፡ ልጆች ትምህርት ቤት በሚሄዱበት ወቅት ከትምህርት ገበታ ከተገለሉ ለጉልበት ብዝበዛ የሚጋለጡበት ሁኔታ እንዳለ አስረድተውናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ያለ እድሜ ጋብቻ እና ሌሎች ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚወድቁ መሆኑን ደምረን ስናየው፤ የዚህ እቅድ በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ጉልህ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በትምህርት ዘርፍ ወደ ስልሳ ሁለት ከመቶ ለማድረስ የታቀደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋን ያልተሳካ መሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢታመንም፤ በእድገታችን ላይ አንድም ነጥብ ለመቀነስ ግን በቂ አይደለም፡፡

መንግስት፣ በገጠር ከተሞች እና ማዕከላት ለማስፋፋት አቅዶት የነበረው የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም፤ በባለሞያ ዕጥረት እና አንዳንድ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ባለመቻሉ እንደታሰበው ሊሄድ እንዳልቻለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምነዋል፡፡ መቼም የመብራት አስፈላጊነት ጨለማን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን መብራት በሚገባላቸው አካባቢዎች የሚፈጥረውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ታሳቢ በማድረግ ጭምር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አንዳንድ ሰዎች መብራት በሌለባቸው አካባቢዎች የወሊድ ምጣኔም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ያስረዳሉ፡፡ በእኛ ሀገር ግን ይህ እቅድ በታሰበው መጠን ባይሳካም፣ አጠቃላይ እድገታችን ላይ ምንም ጫና የለውም፡፡ ለዚህም ይመስላል በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሁለት አሃዝ ያደግነው፡፡

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አራተኛ ዓመት ማገባደጃ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ አንድ የቱሪዝም ምክር ቤት ተመስርቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በክልሎችም፣ በክልል መስተዳድሮች የሚመራ የቱሪዝም ምክር ቤት እንዲያቋቁሙ ከስምምነት ተደርሷል ብለውናል፡፡ በቱሪዝም ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሀብት ለመጠቀም አቅጣጫ የሚያሳይ የተባለለት ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትራችን ገለፃ መሰረት ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሴክትር ያላትን አቅም የሚያህል አንድም የአፍሪካ ሀገር የለውም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ልንጠቀም እንዳልቻልን ይስማማሉ፡፡ ይህን ባናደርግም ግን እድገታችንን ከሁለት አሃዝ ማን ሊያወርደው ይችላል? የሀገር እድገት በእምቅ ሀብት ሳይሆን በተግባር ላይ በዋለ ምርት የሚለካ ቢሆንም፣ ‹‹ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ›› የሚሉት ሹሞች ግን ‹‹አድገናል›› እያሉን ነው፡፡

የምክር ቤት አባላት ካቀረቡት ጥያቄ አንዱ ‹‹የኦዲት ሪፖርትን መሰረት ያደረገ ተጠያቂነት ለምን አይኖርም?›› የሚል ነበር፡፡ ክቡርነታቸው መልስ ሲሰጡ ዋናው ነገር ሪፖርት አቅራቢ መስሪያ ቤቶች ያለውን እውነት ማሳየታቸው ነው ብለውናል፡፡ ሌላው በሂደት የሚደረስበት ነው ማለታቸው ነው፡፡ ችግሮቹን ለመሸፈን የሚደረግ ጥረት ቢኖር አሳሳቢ ይሆን ነበር፡፡ ይህ አቅጣጫ መቼም የመንግስትን ሀብትና ንብረት ተገቢ ባልሆነ መስመር ለሚጠቀሙ ሰዎች፣ ጥሩ አረንጓዴ መብራት ይመስለኛል፡፡ ዘራፊዎቹ ዘረፋ ይቀጥላሉ፤ ሀብት ይባክናል፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የሀገሪቱን እድገት ከሁለት አሃዝ የሚያወርድ አይሆንም፡፡

በመጨረሻም በግሌ ያነሳሁት የግል ባንኮች ተሳትፎ በሚኖርበት ሁኔታ የማኑፋክቸሪንግን ዘርፍ ለማስፋፋት መንግስት ማበረታቻ ማድረግ ይኖርበታል የሚል ነበር፡፡ ለዚህ ጥያቄ የተሰጠው መልስ ለግል ባንክ የምንሰጠው ገንዘብ የለም የሚል ነው፡፡ የግል ባንኮች ገንዘብ መሰብሰብ ያለባቸው ከደንበኞች ቁጠባ ነው የሚል ሃረግም አክለውበታል፡፡ በግሌ ያቀረብኩት ሃሳብ፤ መንግስት ለግል ባንኮች ገንዘብ ይስጥ ሳይሆን፤ መንግስት ከግል ባንኮች የሚወስደውን ሃያ ሰባት በመቶ ያቁምና እራሳቸው ብድሩን ለግል ሴክተር ይስጡ ነው፡፡ መቼም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ባይጠፋቸውም፣ አጠቃላይ አድማጩን ህዝብ ለማሳሳት በሚመስል መልኩ ጥያቄውን ወደሌላ አቅጣጫ መርተውታል፡፡ አሁንም የግል ተሳትፎ እንዲጎለብት የግል ባንኮች ተሳትፎ መኖር አለበት ብንልም አይሆንም ብለዋል፡፡ የግል ሴክተሩ ለኢኮኖሚው ሞተር ነው እያሉ ሞተሩ የሚነሳበትን ባትሪ በመንቀል እንዳይሰራ እያደረጉት ነው፡፡ የግል ሴክተሩ ቢሳተፍ ባይሳተፍ በሁለት አሃዝ ማደጋችን ግን ይቀጥላል፡፡
አንድ ጥያቄ አለኝ! መንግስት የዚች ሀገር እድገት ሊቀንስ የሚችለው ምን ምን ሁኔታዎች ሳይሳኩ እንደሆነ ሊገልፅልን ቢችል እኛንም ከመደናገር ያድነናል ብዬ አምናለሁ፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ውስጥ ይህ እቅድ እንዲሳካ ታሳቢ ተብለው የተቀመጡት ነገሮች በአብዛኛው በታሰበው መሰረት አልነበሩም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን እድገቱ በታሰበው መሰረት ቀጥሏል …… የጉድ

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ድብደባ እና ህግ አስከባሪው ፖሊስ ሚና

ድብደባ ከድሮም ባህላችን የነበረ ባል ሚስቱን መደብደብ፣ አባት ልጁን መግረፍ፣አስተማሪ ተማሪውን መጠፍጠፍ፣ለኛ ኢትዮጵያውያን የታዘዘልን ባህላዊ ህክምናዎች ኣንዱ ይማስለኛል፣ በሀሳብ እና ንግግር ችግርን ክመፍታት ይልቅ ጉልበት አለኝ የሚለው አካል በሀይል አስገድዶ የራስን ፍላጎት መጫን በመሀበረሰባችን ውስጥ ያለ እውነታ ነው። እናስ መንግስት የማህበረሰቡ ውጤት ነውና ክድሮም ጀምሮ በተለያዩ ገዢዎቻችን ስንጠፈጠፍ ኖረናል አሁንም አለም ስለ ሰብአዊ መብቶች የተሻለ ግንዛቤ አለባት በምንልበት ወቅትም እኛና ድብደባ ላንፋታ የተጋባን ይመስል የድብደባ ሌጋሲያችንን እያስቀጠልን ነው። በቅርቡም ባሎች ሚስቶቻቸውን በመደብደብ የሶስተኛ ማእረግነት አግኝተናል እንዲሁም፣ በቅርቡ በመንግስት በኩልም በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን እና ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በጅምላ በፌድራል ፖሊስ ለመደብደብ ታቅዶ ታልሞ የሰለጠኑ በሚመስል ሁኔታ ብዙ ሺህ ሰዎች ፅሎት ሊያደርጉ በሄዱበት እንዲሁም ነጋዴዎች እና ገበያተኞች እንደ አንበጣ ወረሽኝ በድንገት ተወረው ተደብድበዋል።
Image

አድማ መበተን ወይስ ድብደባ

እንደ ፈረደብን ሌላ ሀገር ምሳሌ ላርግና ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲኖሩት ሰልፍ መውጣት የተለመደ ነው። ነገሩ ከፍቶም ችግር ከተፈጠረ አድማ በታኝ ፖሊሶች መተው ሰልፉን መበተን እንዲሁም ከተቃውሞ አድራጊዎቹ ወገን እንደ ድንጋይ እና ሀይል መጠቀም ከተጀመረም በተለያዩ መንገዶች መበተን አዲስ አይደለም። ነገር ግን ባለፈው አርብ በአንዋር መስጊድ እና መርካቶ አካባቢ የታየው ሁኔታ ግርም የሚል ነው።

ምክንያት፡~
1 ድብደባው የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፉ ሳይደረግ በፊት እየተሰገደ ነበር።
2 የተቃውሞ ስልፈኞቹ መሀል በገቡ ደህነነቶች እና ምልምል ካድሬዎች ሰልፉ ሰላማዊ እንዳይሆን አስቀድመው ህዝቡ መሀል ድንጋይ በመወርወር እንዲረበሽ አስደርገዋል።
3 በሌላ ሀገር እንደምናየው ህዝቡ እንኩዋን ከፖሊስ ሀይል ጋር ሊጋጭ ይቅርና አንድ ፖሊስ በያዘው ዱላ ብቻ እስክ ሀምሳ ሰዎችን የሚሆኑ እያሩዋሩዋጠ ሲዥልጥ ነበር።ህዝቡም እራሱን ለመከላከል ያደረገው በአለም የምንተወቅበትን እሩጫ ብቻ ነበር።
4 እናም የፖሊስ ተልእኮ አድማ መበተን ሳይሆን መግረፍ ይመስል ነበር።
5 መርካቶ አካባቢ ደጅ ላይ በልብስ ስፌት የሚተዳደሩ ወጣቶች ስራቸውን እየሰሩ ባሉበት ሰአት ከየት እንደመጣ እንኩዋን ያላዩት የፖሊስ መንጋ መቶ አናት አናታቸውን ሲፈልጣቸው ማሽናቸውን ጥለው እግሬ አውጪኝ ሲሉ ባለሱቆች ሱቃችሁን አልዘጋችሁም ተብለው እንግልት እና ድብደባ ተደርጎባቸዋል።

ፖሊስ መታሁ ስትል የሰማሁዋት አንዲት ልጅ ብቻ ነች ምክንያትዋን ስታስረዳም” መስጊድ ውስጥ ታግተን እንዳለ አንዱ ፖሊስ መጣና ከአጠገቤ የቆሙትን አሮጊት በያዘው ዱላ ወገባቸውን ሲላቸው አላስቻለኝም ለምን እኔን አይመታም እንዴት እኝህን ሴትዮ አልኩና ጫማዮን አውልቄ አናቱን ብየው ወደ ህዝቡ ውስጥ ስገባ ቆይ በሁዋላ ላግኝሽ እያለኝ ተሰወርኩበት። ” በተረፈ አንድ ተጎድቶ የተኛ የፖሊስ ምስል እዚሁ ፌስቡክ ላይ የተለቀቀ አይቻለሁ እሱንም በግርግሩ መሀል መኪና የገጨው መሆኑን ተረድቻለሁ።

ከአንዋሩ ድብደባ በሁዋላ መስጊድ ውስጥ የታገቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ ታግተው ወደ ተለያዩ ቦታዎች በትልልቅ መኪኖች እንደ ሰርዲን ታጭቀው ተወስደዋል።

በየማቆያ ጣቢያዎቹ የነበረው ሁኔታም የተለያየ ነበር በጉለሌ አካባቢ የታሰሩት ሰዎች በተለያዩ ኮማንደሮች ልማታዊ የምክር አገልግሎት ተሰጥቶዋቸው የተወሰደባቸው ሞባየሎቻቸው ተመልሶላቸው ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ተለቀዋል።

ወደ ኮልፌ ያለው የፌድራል ፖሊስ ማሰልጠኛ የተወሰዱት ግን ያዩት አበሳ አሳዛኝና ዘግናኝም ነበር የሴቶችን መከናነቢያ ማቃጠል ለሊቱን ሙሉ የሰልጣኝ ፌድራል ፖሊሶች ድብደባ እንዲሁም ሞባየሎቻቸውን ቅሚያም ነውር አልነበረም። ሞባየል ሲነ’ጥቁ ቆምንለት ከሚሉት የህግ ማስከበር አላማ በተፃራሪ እንደቆሙ የሚያገናዝብ ህሊናም አልነበራቸውም። እንዲሁም ድብደባው ይደረግ የነበረው ቀጥታ አናት አናት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ደግሞ ሰዎቹ ጭንቅላት እና ከበሮን መለየት ይችላሉ ወይ ያስብላል።

አንዱ ሽማግሌ ሲያጫውቱኝ እኔ ስብሰባ ይሁን ምን የማውቀው ታሪክም አልነበረም በቃ ከባንክ የሰው አርባ ሺ ብር ቼክ አውጥቼ በዛው ልሰግድ አንዋር ሄድኩ የገጠመኝ ግን ድብደባና ዝርፊያ ነበር። በግርግሩ መሀል ስሮጥ ብሩ ተበተነ ካጠገቤ የደረሱትም ፖሊሶች “የአሸባሪ ብር ፥የአሸባሪ ብር “እያሉ ብሩን ወደ ኪሳቸው መዶል ጀመሩ እኔንም አንዴ አናቴን ሲሉኝ ነብሴን ለማዳን ፈረጠጥኩ።እንዲሁም ልጆቻቸው የታሰረባቸው ቤተሰቦችን አንዳንድ ፖሊሶች ልጆቻችሁን እንድናስለቅቅላችሁ እያሉ እስከ ሁለት ሺ ብር መጠየቅም ተጀምሮ ነበር።

እናም ህግ አስከብራለሁ የሚለው ፖሊስ እና መንግስት አሸባሪ ሆነው ህዝቡ ደግሞ ሲሸበር ዋሉ ለማጠቃለያም የዛሬ አመት እንዲሁ በኢድ ሰላት ላይ ድብደባ ተደርጎ ነበር፣ እናም አንድ ገጠመኝ አጫውቼያችሁ ልሰናበት ልጁ ፖሊሶች እንደ ለመዱት አናት አናቱን በዛ ዱላቸው ሲያራውጡት የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ሆኖበት “ወላሂ እኔ ክርስትያን ነኝ” አላቸው።