ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በጎንደርና ደሴ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ፤«የሚሊዮኖች ድምፅ ለነጻነት »በሚል መሪ ቃል ለ 3 ወራት ያወጣውን የህዝብ ንቅናቄ እቅድ ትናንት በጎንደርና ደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲከናወን በማድረግ ጀመረ። ከትናንቱ ሰልፍ በፊት ፣ ህዝብ ለሰልፍ እንዲወጣ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ፤«የሚሊዮኖች ድምፅ ለነጻነት »በሚል መሪ ቃል ለ 3 ወራት ያወጣውን የህዝብ ንቅናቄ እቅድ ትናንት በጎንደርና ደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲከናወን በማድረግ ጀመረ። ከትናንቱ ሰልፍ በፊት ፣ ህዝብ ለሰልፍ እንዲወጣ
አንድ ቢሊዮን ገደማ ህዝብ ባለው ክፍለ ዓለም 54 አባል ሃገራትን ያቀፈውና ዘንድሮ 50 ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በየጊዜው በሚከሠቱ የአህጉሩ ችግሮች መፈተኑ አልቀረም ። የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ወይዘሮ እንኮሳዛና ድላማኒ
በማዕከላይ አፍሪቃዊቱ ሬፓብሊክ ያማፅያን ቡድኖች የተሰባሰቡበት የየሰሌካ ህብረት የቀድሞውን ፕሬዚደንት ፍራንስዋ ቦዚዜን በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ሥልጣን ከያዘ ወዲህ ሀገሪቱ አሳሳቢ ሰብዓዊ ቀውስ ገጥሞዋታል።
በሶማሊያ የግል መገናኛ ብዙኀኗ ቁጥርከቀድሞው እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው ። የጋዜጠኞች ቁጥርም አድጓል ። በተለይ የመዲናይቱ የመቅዲሾ ነዋሪዎች የሚያዳምጡ የሚያዩዋቸው የቴሌቪዥንና የራድዮ ጣቢያዎች የሚያነቧቸው ጋዜጦችም በዝተዋል ። የሶማሊያ መገናኛ ብዙኀን ስርጭቶች አሁን ውጭ ላሉ ሶማሊያውያንም እየደረሱ ነው ።
በአዲስ አበባ አነዋር መስጊድ ለተወሰኑ ጊዜያት ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊሞች ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሏል ። በወልድያም ተመሳሳይ ሠላማዊ ተቃውሞ ተካሂዷል ።
ትናንት በታሰበው የኢትዮጵያ የችግኝ ተከላ ቀን ሱናርማ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ያስተባበረው የዛፍ ተከላ ከደብረብርሃን ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ ተካሂዷል ።
የዓለም ዜና
የአፍሪቃን የተፈጥሮና የሰዉ ሐይል ሐብትን ለማልማት ደግሞ የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት እንደሚያምኑት አፍሪቃ እራሷን ከርዳታ ተቀባይነት ወደ ንግድ ተሻራኪነት፥ ወደ ወረት መስሕብነት ቀስ በቀስ እየቀየረች ነዉ። በተለይ በወረት ፍሰት እና ወጣቶችን በማሰልጠኑ መስክ ጀርመን እንድትሳተፍ ዙማ ጋብዘዋል።
ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በዚሁ በቦን አቅራቢያ በምትገኘው የኮሎኝ ከተማ ሰመርጃም የተሰኘዉ የሬጌ የሙዚቃ ድግስ ተካሂዷል። በዚሁ ድግስ በሺዎች የሚቆጠሩ ከተለያየ ሀገር የመጡ ታዳሚዎችና የሙዚቃ ባንዶች ተገኝተዋል።
«ማንኛዉም ፖለቲካዊ ለዉጥ ቢደረግ ተጠያቂ እንሆናለን ብለዉ ያስባሉ።ለዚሕም ነዉ የሕዝብ ጥያቄን የሚያነሳ፥ የሕዝብን ጉዳይ የሚናገርን የሚያፍኑት።እኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሠረት ጥሪ እያቀረብን ነዉ።አሁን የምናየዉ ግን የዲሞክራሲ ምሕዳሩ በጣም እየጠበበ ነዉ።»
በአገራችን የኪነ-ጥበብ መድረክ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ እና በአሁኑ ወቅት በበሽታ በእድሜ አቅም አንስዋቸዉ ተረስተዉ የሚገኙ ታዋቂ ሰዎችን ለመርዳት በጀርመን አገር የተቋቋመዉ ማዕከል የዛሬ 10 ቀን ግድም ከኢትዮጵያ 6 ታዋቂ የመድረክ ሰዎችን ጋብዞ በተለያዩ የአዉሮጳ አገራት የመጡ ከያንያን በተገኙበት ባህላዊ የመድረክ ዝግጅትን አካሂድዋል።
ቢንላደን እንዳይያዙ በመጠበቅ ከለላ አድርገዋል ሲል በስም የጠቀሰው ባለሥልጣን ባይኖርም ከአሁኑም ሆነ ከቀድሞ ባለሥልጣናት ድጋፍ ያደረገላቸው እንደማይጠፋ ጠቅሷል ። ምዕራባውያን ተንታኞች ግን የፓኪስታን የደህንነት ባለስልጣናት ቢንላደን የኖሩበት የነበረውን ቤት ለይተው ማወቅ ያለመቻላቸው ምክንያት ቸልተኝነት ነው የሚለውን አይቀበሉም ።
የብሪታንያ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ አመሸ። ሃዉስ ኦፍ ኮመን በመባል የሚታወቀዉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ማምሻዉን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና ያለፉት 22ዓመት እንዲሁም ወደፊት እያንዣበበ የመጣ ያለዉን ችግር የዳሰሰ ጉባኤ ተካሂዷል።
ጀርመን በቢራ ዓይነት የታወቀ ሀገር ነው ፤ በብዛትም ይጠጣል፤ በዓመት በነፍስ ወከፍ ሲሰላ እያንዳንዱ ሰው 112,5 ሊትር ያህል ቢራ ይጠጣል ማለት ነው። ትኩሱ መጠጥ ቡና ደግሞ ፣ አሁንም ከዚያ ልቆ ፣ የአንደኝነቱን ሥፍራ እንደያዘ ነው ።
ዴቼቬለ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትርጉም ያለው ተፅእኖ የሌለውን የፕሬዝዳንትነት ሥልጣን ከመመኘት ይልቅ ተሰሚነቱን ተጠቅሞ ፋይዳ ያለው አስተዋፅኦ ቢያደርግ ይሻላል ብለዋል ።
የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች የታሠሩትም ፊርማ ለማሰባሰብ፥ ሠልፍና ስብሰባዉን ለማደራጀት ሲንቀሳቀሱ ነዉ።ከሰኔ ሃያ-ሁለት እስከ ሰላሳ በነበረዉ አንድ ሳምንት ብቻ ዘጠኝ የፓርቲዉ አባላት በፀጥታ አስከባሪዎች ታስረዋል።አብዛኞቹ የታሠሩት ሰሜን ጎንደር ነዉ።አንዱ ታስረዉ ተለቀዋል።አስራ-አንደኛዉ ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል።
በግብፅ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በህዝቡ መካከል ልዩነቱ መስፋቱና ፍጥጫውም ማየሉ የግብፅን የፖለቲካ ሂደት ይብሱን እንዳያሰናክለው ሃገሪቱንም ወደ ፖለቲካ ትርምስ እንዳይከታት የሚያሰጋ ነው ሲል የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ።
የዓለም ዜና
ዶቼቬለ ያነጋገረው አንድ ሙስሊም በፆሙ ወራትም ቢሆን ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ለመንግሥት ያቀረባቸው 3 ጥያቄዎች እንዲመለሱ በተጨማሪ የታሰሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም እንዲፈቱ መጠየቁን እንደማያቋርጥ አስታውቋል ።
በዩ ኤስ አሜሪካና በአውሮፓ ሕብረት መካከል የሚካሄደው ትራንስ አትላንቲክ የንግድና መዋዕለ ነዋይ ሽርክና ውል ድርድር ባለፈው ሰኞ ዋሺንግተን ላይ ተጀምሯል።
የግብፅ የአስቸኳይ ሁኔታ አገልግሎት ኀላፊ ሙሐመድ ሱልጣን እንዳስታወቁት ቁጥራቸው ከ51 የማያንስ ሰዎች ሲገደሉ፤ 435 ቆስለዋል። የአዉሮጳ ኅብረት ድርጊቱን አዉግዟል።
በዛሬዉ ዕለት አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ ተመልክቷል።
በዓለማችን የሕፃናትን ህይወት ስለሚቀጥፉ በሽታዎች ሲወሳ ብዙዎች ቶሎ የሚያስቧቸዉ HIV AIDS አለያም የወባ በሽታዎችን ነዉ። አንዳንድ ጥናቶች የተዘነጉት ችግሮች ይሏቸዋል ተቅማጥና የሳንባ ምችን፤ እነዚህ ሁለት በሽታዎች የሚያደርሱት ጉዳት አሁንም ባለመገታቱ የህጻናትን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያሻ እየተጠቀሰ ነዉ።
ከ12 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የቀድሞዋ የዩጎዝላቪያ ግዛት ክሮኤሽያ 28 ተኛዋ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን በቃታለች ። የአውሮፓ ህብረት እንዳለው ክሮኤሽያ ማሻሻያዎች እንድታደርግ የተሰጧትን የቤት ሥራዎች አሟልታለች ።
አሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል የምትፈልገዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖዉደን በ 21 ሀገራት ተገን ጠይቆ፤ ከበርካታ አዉሮጳ ሃገራት ይሁንታን ካጣ ወዲህ፤
በሜሪላንድ እና በዋሽንግተን ዲሲ ላላፈዉ አንድ ሳምንት ሲካሄዱ የቆዩት፤ የስፖርት የባህል ፊስቲቫሎች፤
ዶሃ ፤ ቀታር ላይ አንድ ብሎ የጀመረው በ 14 የተለያዩ የዓለማችን ከተሞች የሚካሄደዉ የዳይመንድ ሊግ አትሌቲክስ ዘጠነኛዉ ዉድድር ባለተራ ፓሪስ ውስጥ የዓለማችን ታዋቂ ሯጮች፤
በብሪታንያ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ፣ ለአቅመ ዓዳም አልያም ለዓቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህጻናት ከፍተኛ ጾታዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸዉ ተገለጠ።
ሐይማኖተኛ በመሆናቸዉ እንዳድ የግብፅ መገናኛ ዘዴዎች በወታደራዊዉ ምክር ቤት የሙስሊም ወንድማማቾች ተወካይ በማለት እስከ መዉቀስ ደርሰዉም ነበር።ሰዉዬዉ ግን እንዲያ አልነበሩም። ብሪታንያም አሜሪካም የተማሩ በመሆናቸዉ ለግብፅ ጦር በየዓመቱ ከአንድ ነጥብ ሰወስት ቢሊዮን ዶላር በላይ በምታንቆረቁረዉ በአሜሪካ ዘንድ ተወዳጅ ናቸዉ
የዕለቱ ዜና
ለስደቱ እየተባባሰ መሄድ፣ በሃገራቱ የተለያዩ መንስኤዎች መኖራቸው ቢታወቅም በጥቅሉ ግን ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ችግሮች በዋነኛ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ዜጎቻቸው ለስደት የሚዳረጉባቸው እነዚህ ሃገራት ደግሞ በርካታ የየጎረቤት ሃገራት ስደተኞችን ተቀብለውም ያስተናግዳሉ።
በዓለም ዙሪያ እጅግ የታወቁትና የተከበሩት የደቡብ አፍሪቃ ፀረ አፓርታይድ ስመ ጥር ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ፣ ሀኪም ቤት ውስጥ ፣ በሞት-ሽረት ላይ እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን፤ የተወለዱባት መንደር፣ ኩኑ፣ ኑዋሪዎች፣ በእርሳቸው ዝና ሳቢያ የኤኮኖሚ
የአፍሪቃ ኅብረት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባትን ግብጽን ከአባልነት አገደ። ግብፅ ውስጥ፤ «የቁጣ ፣ የተቃውሞ ቀን ነው»ሲሉ የሙስሊም ወንድማማች ፓርቲ አባላት ባቀረቡት ጥሪ፣ ተከታዮቻቸው አደባባይ በመውጣት እንደተነገራቸው ፈጽመዋል።
ግብፅ ውስጥ፤ በሀገሪቱ በመላ ዛሬ ፣ «የቁጣ ፣ የተቃውሞ ቀን ነው»ሲሉ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር አባላት ባቀረቡት ጥሪ መሠረት ፣ ተከታዮቻቸው አደባባይ በመውጣት እንደተነገራቸው ፈጽመዋል። በቅርቡ የተከሠተውን ለውጥ የሚደግፉት ወገኖች በፊናቸው
በቤንቺ ማጂ ዞን የሚዛን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የመብት ጥያቄ በማንሣታቸው ለእሥር መዳረጋቸውን የታሣሪዎቹ ተማሪዎች ቤተሰቦች ገለጡ።
በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት በዕረፍት ላይ ይገኛሉ። ለመሆኑ የዕረፍት ጊዜያቸውን እንዴት ለማሳለፍ አስበዋል?
የዓለም ዜና
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 39 ኛው መደበኛው ስብሰባ የፌደራል መንግሥት ለ 2006 ዓም ያቀረበውን የ 154,9 ቢልዮን ብር በጀትን አፀደቀ።
በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ በምዕራባዊትዋ አፍሪቃ አገር በማሊ ሚታየዉን ዉጥረት ለማርገብ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ኒኑስማ «MINUSMA»የተሰኘዉ የተመድ አረጋጊ ቡድን 12,600 ወታደሮቹን እንዳሰለፈ ተነግሮአል።
በግብጽ ለመጀመሪያ ጊዜ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝደንት ሞሐመድ ሞርሲ በጦር ኃይሉ ከስልጣናቸዉ ከተነሱ ወዲህ የአገሪቱ የፖለቲካ አቅጣጫ ወዴትነት እስካሁን አለየለትም።
በያመቱ ፣ እ ጎ አ ከ 1901 ዓ ም አንስቶ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀውን የኖቤል ሽልማት ለማግኘት የማይመኝ የሳይንስ ተማራማሪ ይኖራል ብሎ መገመት ያስቸግር ይሆናል። ተሳክቶላቸው በየጊዜው ከፍኛውን ሽልማት የሚያገኙትና በሙያው አንቱ የሚሰኙት ሊቃውንት
የቀድሞይቱ ዩጎዝላቪያ ሬፑብሊክ ክሮኤሺያ ባለፈው ሰኞ 28ኛዋ የአውሮፓ ሕብረት ዓባል አገር ለመሆን በቅታለች። ሕብረቱ ክሮኤሺያን የተቀበለው በጋራ ምንዛሪው በኤውሮና በርከት ባሉ ዓባል መንግሥታት የበጀት ቀውስ ተወጥሮ በሚገኝበት ወቅት ነው።
ሙርሲ በቴሌቪዥን ሲነጋሩ ደጋፊ-ተቃዋሚዎቻቸዉ እዚያዉ ካይሮ ዉስጥ ይገዳደሉ ነበር።ጄኔራል ሲሲ የቆረጡት ገደበ-ሠዓትም አብቅቷል።እና ታንክ መትረየስ አስጠምደዉ ካይሮ ቤተ-መንግሥት ቢገቡስ? ምርጫዬ አሉ ሙርሲ «ሞት»
የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ትናንት በሴኔጋል፣ በደቡብ አፍሪቃ እና በታንዛንያ ያካሄዱትን የአንድ ሣምንት ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ። ኦባማ በጉብኝታቸው ወቅት በአህጉሩ ያለውን ግዙፍ የኤኮኖሚ ዕድል በማመልከት፣ ሀገራቸው በዚሁ ዘርፍ ከአፍሪቃ ጋ ግንኙነትዋን እንደምታስፋፋ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያናብራዚል ግንኙነታቸዉን እንደሚያስፋፉ እና እንደሚያጠናክሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የበረራ መስመር ወደሪዮደጄኒሮ እና ሳኦፖሎ በዘረጋበት ወቅት አሳወቁ።
ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የወጣት ስራ አጥነት ላይ የመከሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ችግሩን ለመፍታት የሚውል 6 ቢሊዮን ዮሮ ለመመደብ ተስማ…
ዉጪ አገር ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኖረዋል። ወደአገራቸዉ ሲመለሱ ያደጉበት አካባቢ ተጎሳቁሎ፤ ደኑ ተራቁቶ ቢያገኙት ልባቸዉ ተነካ። መንፈሳቸዉ ተነ…