ዓለም አቀፉ አጥኚ ተቋም ICG እንደሚለዉ ልዩነቱን ለማስወገድ መሠረታዊዉ ነገር የሁለቱ ፖለቲካዊ ራዕይ ነዉ።አርቆ ማስተዋሉ ካለ ዉክልና ወይም ሥልጣን መጋራት፥በጋራ ጉዳዮች በጋራ መወሰን አካባቢዉን ማልማት፥የሕዝቡን ኑሮ ማሻሻሉም አይገድም።

የኮት ዲ ቯር የፍትሕ ሚንስቴር በእስር ከሚገኙት የቀድሞው የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሎውሮ ባግቦ ደጋፊዎች መካከል የቅርብ ረዳቶቻቸው ናቸው የሚባሉትን 14 ሰሞኑን በጊዜያዊ ሁኔታ ፈታ። ግለሰቦቹ የተፈቱበት ርምጃ በሀገሪቱ ለተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሂደት ዓቢይ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ቢገምቱም፣ የባግቦ ደጋፊዎች በቂ እንዳልሆነ አስታውቀዋል።

ረሃብን ለመቅረፍ በሽታን ለመከላከል፣ መሠረተ ልማትን በሰፊው ለመዘርጋት ፣ በአጠቃላይ ኑሮን ለማሻሻል፤ ዕውቀት ወሳኝ ነው። ዕውቀት የሚስፋፋው ፤ የሚዳብረው ፣ በመመራመርና ከሌሎች ጋር የሐሳብ ልውጥ በማድረግ ነው። ይህን በማከናወን ቀዳሚውን ቦታ

ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በተለያዩ አካባቢዎች፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ፤ አካኺደው እንደነበረ የሚታወስ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ሻሻመኔ አካባቢ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ፤

የMDC ሥሌት መረጃዎቹ ሕጋዊ መሠረት ካገኙ የዉጪ ሐይላት በተለይም የአፍሪቃ ሕብረት እና የደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማሕበረሰብ (SADC) በፕሬዝዳት ሙጋቤ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ይጠቅማሉ ነዉ።ከተሳካ አዲስ ምርጫ።

ጀርመን ውስጥ በተለይ በምሥራቅ ጀርመን ዘረኝነት ከቀድሞው እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን አንድ ጥናት አስታውቋል ። የጀርመን መንግሥት ምስራቅ ጀርመን ውስጥ በሚገኙ ፌደራል ግዛቶች ዘረኝነትን ለመከላከል ተግባራዊ ያደረገው መርህም ለውጥ አለማምጣቱ በጥናቱ ተገልጿል ።

የወጣቶቹ ማሕበር በጠራዉ ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የሕክምና ባለሙያዎችና የሐይማኖት መሪዎችም ግብረ-ሰዶማይነትን ያስፋፋሉ ባላቸዉ ተቋማት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዲደረግ ጠይቀዋል

በደቡብ ሶማልያ የምትገኘው የኪስማዮ ከተማ አስተዳደር ለሶማልያ ማዕከላዊዉ መንግሥት እንዲሰጥ ሀሳብ ቀረበ። ይህንን ሀሳብ ያቀረቡት በሳምንቱ መጨረሻ በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ የአንድ ቀን ምክክር ያካሄዱት ያካባቢ ሀገራት መሪዎች ናቸው። ይህ የቀረበው ሀሳብ በተግባር ሊተረጎም መቻል አለመቻሉ የሚመለከታቸውን ወገኖች ብዙ እያነጋገረ ነው።

ስለጤና ጉዳይ የሚቀርቡ መረጃዎችን ምን ያህል ህዝብ እንደሚያገኛቸዉ፤ ወይም ለምን ያህል ህዝብ እንደሚደርሱ መገመት ይቸግራል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች ለጤና ይዞታቸዉ ትኩረት መስጠትን ችላ ሊሉ አይገባም።

ኮፈሌ አርሲ ዉስጥ በሳምንቱ ማብቂያ የፀጥታ አስከባሪዎች በተሰባሰቡ የከተማይቱ ኗሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች መግደል እና ማቁሰላቸዉን የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል።

አል ቃይዳየሽብርጥቃትሊጥልዕቅድ መያዙ ታውቋል ከተባለ ወዲህ ዩኤስ አሜሪካ ከትናንት ጀምራ በብዙ የሙሥሊም ሀገራት የሚገኙ ኤምባሲዎችዋን መዝጋቷ ተሰምቶዋል።

በሁለት ሺሕ ስምንቱ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ግን አዲሱ ፖለቲከኛ አሮጌዉን መሪ አሸነፉ።ሰዉዬዉ ተንገዳገዱ ግን አልወደቁም።እንዳይወድቁ መጀመሪያ፥-በፀጥታ አስከባሪዎችና በቻንግራይ ደጋፊዎች መካካል በተደረገዉ ግጭት ከሁለት መቶ ባላይ ሰዉ መገደል፥ ቻንጋራይ ሳይቀሩ በመቶ የሚቆጠሩ መደብደብ፥ መቁሰል፥ መታሰር፥ ብዙ ሺሕ መሰደድ ግድ ነበረበት።

በቱኒዝያ በእሥላማዊው መንግሥት እና በተቃዋሚዎች መካከል ውዝግቡ እየተባባሰ ሄዶዋል። የተቃውሞ ወገን ፖለቲከኛ መሀመድ ብራሂሚ እና በሣምንቱ መጨረሻም ሌላ የተቃዋሚ ቡድን ፖለቲከኛ ከተገደሉ ወዲህ ገዢው የኤናሀዳ ፓርቲ ከሀገሩ እና ከዓለም ዙሪያ ግፊት ተጠናክሮበታል። የተቃዋሚ ወገኖች አክራሪዎቹ ሙሥሊሞች እያጠናከሩት በመጣው የኃይል ተግባር

በቱኒዝያ የተቃውሞ ወገን ፖለቲከኛ መሀመድ ብራሂሚ ከተገደሉ ወዲህ ገዢው የኤናሀዳ ፓርቲ ከሀገሩ እና ከዓለም ዙሪያ ግፊት ተጠናክሮበታል። የተቃዋሚ ወገኖች አክራሪዎቹ ሙሥሊሞች እያጠናከሩት በመጣው የኃይል ተግባር አንፃር መንግሥት ቁርጠኛ ርምጃ አልወሰደም በሚል አብዝተው ወቅሰውታል።

27 ተፎካካሪዎችን ያወዳደረው የማሊው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ባንድ ዙር እልባት ሊደረግለት ባለመቻሉ ነሐሴ 5 ቀን 2005 ዓ ም ፤ በ 2 ኛ ዙር ውድድር እንደሚደመደም ተነገረ። ያኔ የሚቀርቡት 2 ተወዳሪዎች ብቻ ሲሆኑ እነርሱም ፤ የቀድሞው ጠ/ሚንስትር

የዩናይትድ እስቴትስ ብሔራዊ የስለላ ድርጅት አባል የነበረውና ፤ ከ2 ወራት ገደማ በፊት ከድቶ፤ ምሥጢሮችን በማጋለጥ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነጋገሪያ አጀንዳ ያስከፈተው ኤድዋርድ ስነውደን ፤ ትናንት ሩሲያ ውስጥ ለአንድ ዓመት ጊዜያዊ ተገን ማግኘቱ ፤

በአፍሪቃ በህፃናት ላይ የሚካሄድ ወሲባዊ ንግድ እንዲገታ ህብረተሰቡና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቁ ። በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ እንደተገለፀው በአፍሪቃ በሚሊዮች የሚቆጠሩ ወጣቶችና ህፃናት የወሲብ ንግድ ሰለባ ናቸው ።

ፖሊስ ከዚሁ መስጊድ ፣ ሶላት ከመጀመሩ በፊት አንድ ምዕመን ከሶላቱ በኋላ ደግሞ ወደ 15 የሚሆኑ ምዕመናን ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ማሰሩን ፣ በአካባቢው እስከነበረበት ጊዜ ድረስ መመልከቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግሯል ።

የግብፅ ጦር የሰየመዉ ጊዚያ መንግሥት ግን ጥሪ ማሳሰቢያዉን የተቀበለዉ አይመስልም።የጊዚያዊ መንግሥቱ ካቢኔ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም በሁለት አደባባዮች የከተመዉን ሕዝብ «ለሐገሪቱ ፀጥታ አስጊ» እና «አሸባሪ» በማለት ወንጅሎታል።ፖሊስ ሕዝቡን ከሁለቱም አደባባዮች እንዲያባርርም አዟል።

ኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ወደሰላማዊ የድርድር መድረክ ለማቅረብ 250 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል በነጻ ለመስጠት አስባለች መባሉንየሚጠቁም ዜና በድረገጾች እየተነበበ ነዉ።

የዛኑ ፒኤፍ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምርጫውን አሸንፈናል ፣ ተቀናቃኛችን የዲሞክራሲያዊ ለውጦች ንቅናቄ MDC አልቋለታል ተቀብሯል እያሉ ነው ። ስማቸውን ያልጠቀሱ አንድ ነፃ የዚምባብዌ የምርጫ ታዛቢም የድምፅ ቆጠራ የመጀመሪያው ውጤት ለቻንጋራይ ታላቅ ውድቀት እንደሚመስል ለሮይተርስ አታውቀዋል ።

የረመዳን የጾም ወር ተጋምሶ ፍችዉ የኢድ አልፈጥር በዓል እየተቃረበ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በቀን ወደ 18 ሰዓት ያህል ይጾማሉ። በዕለቱ ዝግጅታችን በቦን ከተማ አቅራብያ በምትገኘዉ በብሩል ከተማ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ቤተሰብ ቤት ጎራ ብለን የእፈጠር ምሽትን አብረን አሰልፈን ልናካፍላችሁ ይዘናል፤

የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዛሬው ምርጫ የሚሸነፉ ከሆነ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። አያሌ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ሙጋቤ፣ ተፎካካሪአቸውን ጠ/ሚንስትር ሞርጋን ቻንጊራይን ለማሸነፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚተማመኑም ገልጸዋል። በሃራሬ

«ጨው ሲበዛ ያቅራል ፤ በርበሬ ሲበዛ ይመራል» ይባላል፣

ለሰውና እንስሳ ጠቀሚ ከሆኑ ማዕድናት መካከል አንዱ ጨው ነው፤ የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት(WHO) እንደሚመክረው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ መጠኑ ፣ከ 5 ግራም የማይበልጥ ጨው መመገብ

ማሕበሩ በተለይ ብሪታንያ፥ ፈረንሳይና ዳች (ወይም ኔዘርላንድን) ካሳ እንዲከፍሉ በሕግ ሊሞግታቸዉ ተዘጋጅቷል።ጠበቆች፥ አንዳድ ሙሑራንና የመብት ተሟጋቾችም የማሕበሩን አቋም እንደሚጋሩ እየተናገሩ ነዉ

እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1701 ፈረንሳዊዉ የቅኝ ገዢ ጦር መኮንን አንቶኒዮ ደ ላ ሞንቴ ካዲላክ የቆረቆራት ከተማ ከሰሜን አሜሪካ ትላልቅ ከተሞች አንዷ ለመሆን ብዙ ጊዜ አልወሰደባትም።ዲትሮዮት።

በማሊዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ የሚሳካላቸዉ ይመስላል። የእሁዱ ምርጫ መነሻ ዉጤት የሚያመለክተዉም ይህንን ነዉ። የሆነ ሆኖ ኬይታ በምርጫዉ ያገኙት የድምጽ መጠን ገና አልተረጋገጠም። የዶቼ ቬለዋ ካትሪን ጌንዝለር እንደዘገበችዉ ግን የማሊ የፖለቲካ ተቃዋሚ ወገን በዚህ አልተደሰተም።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከሀገር እንዳይወጡ በቅርስ ጥበቃ ረገድ መስሪያ ቤታቸዉ ከሌሎች ድርጅቶችና የመንግስት ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ አቶ ፋንታ በየነ ለዶቼ ቬለ ገለጹ።

በግጥም ምሽት የኪነጥበብ አድናቂዎችን ሲያዝናኑ ወራት አስቆጥረዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ የካንሰር ታማሚ ህፃናትን መደገፍ ብቻ ሳይሆን ኅብረተሰቡ ስለበሽታዉ ያለዉን ግንዛቤ ለማስፋት እየጣሩ ነዉ።

በአሁኑ ጊዜ በስዊዘርላንድ የስደተኞች አቀባበል መርህ ከቀድሞው እየጠበቀ መምጣትና ፣ ሌሎችም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተፅእኖዎች በበስዊዘርላንድ የተገን ጠያቂዎችን ህይወት አስቸጋሪ አድርጎታል እንደ አቶ ምስጢረ ።

ባለፈው ቅዳሜ፤ የሰቆጣና አካባቢዋ ኑዋሪዎች ከላሊበላ -ሰቆጣ እንደሚሠራ ቃል የተገባልን አስፋልት መንገድ ተግባራዊ ይሁን በማለት አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር በማሊ፣ እንደተፈራው ሳይሆን የትናንቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰላም ነው የተከናወነው። የዶቸ ቬለ ባልደረባ ፣ ካትሪን ጌንትስለር፣ ከማሊ የላከችው ዘገባ እንደሚጠቁመው፣ከ 27 ቱ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል፤

የኢትዮጵያን አብያተ ክርስቲያን ንዋዬ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሶችን በሥርዓት ለመጠበቅ ባለመቻሉ፣ የሚያስጠብቅም ባለመኖሩ ፣ ባለፉት አያሌ ዓመታት እጅግ በዛ ያሉ ንዋዬ ቅድሳትና የተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ ቅርሶች ወደ ውጭ እየተጋዙ ገበያ ላይ መዋላቸው እንግዳ ነገር አልሆነም።

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ፤ ትልቅ ሥም ያላቸውን ፤ ገጣሚ ፣ ደራሲና ደራሴ ተውኔት ፤ የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅንን የህይወት ታሪክ፣ በሚዳስስ መጽሐፍ ላይ ፤ ሜሪላንድ ፣ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ውይይት ተካሄደ።

የአዉቶማቲክ ጠመንጃ ተኩስ ይሰማናል።ተቃዋሚ ሠልፈኞቹ (እኛ እንዳንመታ) ዙሪያችንን ከበዉ ሠብአዊ ጋሻ ሠሩ።ጥይቶችና የሲ ኤስ ጋሶች ይተኮሱብናል።አየሩ በጢስ ታፍኗል።ሰዎች ያስታዉካሉ።የመስክ ሆስፒታሎቹ ወለል ደም ተንጣሎባቸዋል።—“

በአዉሮጳ ኢትዮጵያዉያን የስፖርትና የባህል ፊዴሪሽን የዘንድሮዉን ዝግጅቱን በስዊዘርላንድ ጄኔቭ አጠገብ በምትገኘዉ ኒዮ ከተማ በደማቅ ዝግጅት አካሂድዋል።

የተባበሩ መንግስታት ድርጅት የጸጥታዉ ምክር ቤት ከሃያ ዓመታት በላይ ያስቆጠረዉን ሶማሊያ ላይ የተጣለዉ የመሳሪያ ማዕቀብ እንዲላላ ወስኗል። የጸጥታዉ ምክር ቤት የመቅዲሹ መንግስት ራሱን ከጽንፈኛዉ አሸባብ ለመከላከል እንዲችል አቅሙ እንዲጠናከር በሚል ዉሳኔዉን ማሳለፉን አመልክቷል።

በአዉሮጳ ኢትዮጵያዉያን የስፖርትና የባህል ፊዴሪሽን የዘንድሮዉን ዝግጅቱን በስዊዘርላንድ ጄኔቭ አጠገብ በምትገኘዉ ኒዮ ከተማ በደማቅ ዝግጅት አካሂድዋል።

የተቃዉሞ ሠልፉና የሥብሰባዉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት ዩናይትድ ስቴትስ፥ ካናዳ፥ አዉስትሬሊያ በተለያዩ የአዉሮጳና የመካካለኛዉ ምሥራቅ ከተሞች አደባባይ የወጣዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የኢትዮጵያ መንግሥት ሐማኖታዊ ነፃነትን እና ሠብአዊ መብትን እንዲያከብር፥ ጠይቋል