የቶጎ ህዝብ የምክር ቤት እንደራሴዎቹን ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሰጥቷል። ምርጫው ዛሬ የሚደረገው፣ በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ሰበብሁለት ጊዜ ከተራዘመ በኋላ ነው።

የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ ፤ በሀገሪቱ ሊያካሂድ ያሰበውን ፤ ያስፈልጋል ብሎ ያመነበትን የብሔራዊ መግባባትና ዕርቅ ያለውን መርኀ ግብር በዛሬው ዕለት ይፋ ማድረጉን የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ፣ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

«ሒሳብ ተጭበርብሯል የሚለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃ አለገኘንም። በዕርዳታ የተሰበሰበ ገብዘብ ተጭበርብሯል የሚለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃም አላገኘንም።»

የኮርያ የዕርስ በርስ ካበቃ ዘንድሮ ስድሳ ዓመቱን ያዘ። በኮርያ ዕርስ በርስ ጦርነት ጊዜ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ በመሰለፍ ከደቡብ ኮርያዉያን ጋር የተሰለፉት ኢትዮጵያዉያን፤ የኮርያ ዘማቾች ማህበር በሚል ጥላ ስር ከተሰባሰቡ 20 ዓመት በላይ እንደሆናቸዉ ይናገራሉ።

ማዕድን፣ በተለይም የተፈጥሮ ጋዝን ለመዛቅ፣ እንደ ዘመናዊ ዘዴ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚሠራበት ብልሃት ፣ አንድ ቦታ ላይ ፣ በጥልቅ መቆፈርና ፤ «ኬሚካል» ውሃና አሸዋ ቀላቅሎ በኃይለኛ ግፊት ፣ በከርሠ ማድር የሚገኘው ዐለት እንዲፈረካከስ በማድረግ፤ ጋዙ ወይም ማዕድኑ ወደ ላዕላዩ የየብስ ክፍል እንዲዘልቅ ማብቃት ነው።

በማሊ አዲስ ፕሬዚዳንት እስኪመረጥ እስከፊታችን እሁድ ጥቂት ቀናት ናቸው የቀሩት። አሁን ጥያቄው ፣ ምርጫው በሀገሪቱ በመላ በሰሜናውያኑ ከተሞችም ይካሄድ ይሆን ወይ ? የሚለው ነው። ምርጫው ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት እንደቀሩት የኅይል እርምጃ መከሠቱ ግን ፣ ብሩኅ ተስፋ አላሳደረም ።

በዩጋንዳ ታዋቂው የተቃውሞ ወገን መሪ ኪዛ በሲግዬ ፣ ህገ ወጥ የፖለቲካ ስብስባ በአደባባይ ሊያካሂዱ ሳያቅዱ አልቀሩም በሚል ጥርጣሬ ከተያዙ ወዲህ፣ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። የዩጋንዳ የተቃውሞ ወገኖች፤ ባለፉት ሳምንታት የፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒን

የአውሮጳ ህብረት እና ደቡብ አፍሪቃ ባለፈው ሣምንት ሐሙስ፣ እአአ ሐምሌ 18፣ 2013 በፕሪቶርያ ከተማ ስድስተኛ የጋራ ጉባዔ አካሄዱ። እአአ ከ 1994 ዓም ወዲህ አጠቃላይ የንግድ ግንኙነታቸውን ማሳደግ የጀመሩት የአውሮጳ ህብረት እና

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሃገሪቱን ካቢኔ ካገዱ በኋላ ዋና ዋና የመንግሥት ተቋማት አካባቢ ጥበቃው ተጠናክሯል ። ከፕሬዝዳንቱ እርምጃ በኋላ ህዝቡ እንዲረጋጋ በራድዮ ጥሪ ተላልፏል ።

ሒዝቡባላሕ ግን ፍረጃዉን «የአሜሪካና የፅዮናዉያን ሴራ» በማለት ሲያወግዘዉ፥ የሊባኖስ መንግሥት ደግሞ ለሊባኖስ «ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ» በማለት ተቃዉሞታል።የፖለቲካ ተንታኞችም የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔን ገቢራዊነት ይጠራጠራሉ

በፌስ ቡክ የከፈተችዉን ዘመቻ «አንድ ብርድ ልብስ ለአንድ ጎዳና አዳሪ» በሚል ሥም ሰይማዋለች።ከያዘለት ለአዲስ አበባ የጎዳ አዳሪዎች አምስት ሺሕ ብርድ ልብስ ለመሰብሰብ ነዉ ዕቅዷ

በብሪታንያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወጣቶቹ ልዑል ዊልያም እና የባልተቤታቸው ልዕልት ካትሪን(ኬት)ሚድልተን ወንድ ልጅ ትናንት በለንደን የሴይንት ሜሪ ሀኪም ቤት ተወልዶዋል።

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ፤ ወደ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን በአንድ ዉይይት ላይ መገኘታቸዉ ታውቋል። በዉይይት መድረኩ የተለያዩ ምሁራንና የሲቪክ ማሕበራት ተሳታፊዎች እንደነበሩ ለመገንዘብ ተችሏል።

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ፤በዛሬው ዕለት የግብዕን ጊዜያዊ መንግሥት ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሞና ኦማርን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኅብረቱ ዋና ጽ/ቤት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተመለከተ።

ሥለ NSA የተለያዩ መፅሐፍት ያሳተመዉ ጋዜጠኛ ጀምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ፥ እርስዎ ከዱባይ ወይ ከለንደን አዲስ አበባ ላለች ፍቅረኛዎ የፍቅር ኢሜል ይመይላሉ እንበል።ስኖዳን እና ብጤዎቻቸዉ ሐዋይ፥ ሜሪላንድ ወይም የፈለጉበት ቦታ ሆነዉ-ከፍቅረኛዎ እኩል ምናልባትም ቀድመዉ ኢሜልዎን ያነባሉ።ስልኩም—

ኢትዮጵያ ዉስጥ በ1997 የተደረገዉ ምርጫ ዉጤት ደም ባፋሰሰ ግጭት ካሳረገ ወዲሕ መንግሥትን በአደባባይ ሠልፍ መቃወም ለኢትዮጵያዉያን ዝግ ሆኖ ነበር።

ባለፈዉ የካቲት ኬንያ ዉስጥ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ቃለ-መሃላ ፈፅመዉ የፕሪዝዳንትነቱን ሥልጣን ከያዙ በኋላ አዲስን ካቢኔ ሾመዋል። ኬንያታ የሾምዋቸዉ ባለስልጣናት በአብዛኞቹ ከአሁን ቀደም በኬንያ የፖለቲካ መድረክ እንብዛም ያልተሳተፉ መሆናቸም ተነግሮአል። ይህ የኬንያታ አዲስ ጅማሮ ኬንያዉያን አዲስ ተስፋን አሰንቆላቸዋል።

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጦር ሠራዊት M-23 በሚል መጠሪያ በሚታወቀው አማጺ ኅይል ላይ መልሶ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሯል። በታንክ፣ በሄሊኮፕተር ፤ አዳፍኔና ከባድ አውቶማቲክ ጠብመንጃ ፣ ወታደሮቹ ከጎማ ከተማ በስተሰሜን ፣ የአማጽያኑን ምሽግ መደብደባቸውን የዜና አውታሮች አስታውቀዋል።

በማዳመጥ መማር የተሰኘው በዶቼ ቬለ እና በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የሚቀርበው አዝናኝ እና ትምህርታዊ ተከታታይ ድራማ 6ኛ ዙር ቀረፃ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አዉሮፕላኖች የሚመጡልንን እቃዎች በወቅቱ ባለመረከባችን ተጉላላን ሲሉ አንዳንድ የአየርመንገዱ ደንበኞች አማረሩ።

የእንግሊዝና የአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ የልማት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሚሰጡት ድጋፍ በአገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ነዉ ሲል አንድ ድርጅት ከሰሰ።

ባለፈዉ ሳምንት የራድዮ ጣብያችን ባለበት ቦን ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ኮለኝ ከተማ ባሉ የተለያዩ የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት፤ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከያንያን የአገሮቻቸዉን ጥንታዊ የሙዚቃ ስልቶችን አቅርበዋል።

እሥራኤል በኃይል በያዘቻቸው የፍልስጤም ግዛቶች የሠፈራ መርኀ ግብሯን አለማጠፏ፣ የመካከለኛውን ምሥራቅ ውዝግብ በሰላም ድርድር ለመፍታት ፣ በየጊዜው የቀረቡ እቅዶችን ሁሉ መቅኖ እያሳጣ ነው ።

የኢትዮጵያ ወታደሮች ከባይደዋ መዉጣታቸዉን አሶሲየትድ ፕረስ ትናንት አመልክቷል። መንግስት መፍትሄ ይፈለጋል ቢልም ወታደሮቹ ከተጠቀሰችዉ ስልታዊት የሶማሊያ ከተማ መዉጣታቸዉም በአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪዎችና የሶማሊያ መንግስት ወታደሮች ላይ ጫና እንደሚያስከትል እየተነገረ ነዉ።

ደቡብ አፍሪቃዉያን ዛሬ የነጭ ዘረኛ አገዛዝ ታጋዩን የኔልሰን ማንዴላን 95ኛ የልደት በዓል በታላቅ ድምቀት አክብረዉ ዉለዋል። የነፃነት ታጋዩ አዛዉንት ግን ከአንድ ወር በላይ በሃኪም ቤት አልጋ ላይ ይገኛሉ። በጤናቸዉ ረገድ መሻሻሎች መኖራቸዉን ፕሬዝደንት ጄኮብ ዙማም ሆኑ ልጆቻቸዉ እየገለጹ ነዉ።

ባለፈዉ ሳምንት የራድዮ ጣብያችን ባለበት ቦን ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ኮለኝ ከተማ ባሉ የተለያዩ የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት፤ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከያንያን የአገሮቻቸዉን ጥንታዊ የሙዚቃ ስልቶችን አቅርበዋል።

ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ።

ዘንድሮ 50ኛ ዓመቱን በማሰብ ላይ የሚገኘው የነጻ ነጻ የአፍሪቃ መንግሥታት ማኅበር –የአፍሪቃ ኅብረት ፣ እንደ ኤኮኖሚውና ንግዱ ግንኙነት ፣ ከአውሮፓው ኅብረትም ሆነ ከአባል ሃገራቱ ጋር በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የሚያደርገው ትብብር ምን ይመስላል?

ውሳኔው በአዲስ አበባና በጎንደር ከተማ ተፈናቅለው ወደ እሥራኤል ለመግባት በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቤተ እስራኤላውያን ቤተሰቦችን አስጨንቋል ።

የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ፀሃፊ የፀረ ሽብሩ ህግ ይሰረዝ የሚል ድምፅ ለማሰባሰብ አዲስ አበባ ውስጥ የተንቀሳቀሱ 51 አባላቱ ያለአንዳች ምክንያት ታስረው በዋስ መለቀቃቸውን ተናግረዋል ።

ናይጀሪያ የሱዳኑን ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽርን ለዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ይዛ ባለመስጠቷ እየተወቀሰች ነዉ። ፕሬዝደንት አልበሽር በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ናይጀሪያ ላይ በተካሄደዉ የአፍሪቃ ኅብረት የHIV/AIDS ጉባኤ ላይ መገኘታቸዉን የአገሪቱ የመብት ተሟጋቾች ተቃዉመዋል።

ብሔርተኝነትን መግለፅ ለኤርትራዉያን ወጣቶች የሚመጣ ችግርን መከላከያ ጥሩ ሥልት ነዉ።ሌላ ቢሎ መዘዙ ሌላ ነዉ።አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ትንሽ ሐገር እራሷን ከተቀረዉ ዓለም ዘግታለች።ከሠላሳ ዓመት ጦርነት በሕዋላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ ነፃነትዋን በይፋ ያወጀችዉ በ1985 ነዉ።

ከዛሬ አምስት ዓመት ተኩል ወዲህ ደግሞ ጋንዲ በሲና በረሃ በግብፅ በሊቢያና በቱኒዝያ እስር ቤቶች የሚሰቃዩ ባመዛኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን እየረዳ ነው ። ጋንዲ ሲና በረሃ የታገቱ በርካታ ስደተኞችን ከአፋኞቻቸው ነፃ ለማውጣት በቅቷል ።

በኢጣልያ የሊጋ ኖርድ ፓርቲ እንደራሴ እና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሮቤርቶ ካልዴሮሊ በሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሚንስትር ዶክተር ሴሲል ኪዬንጌ ላይ አሳፋሪ አስተያየት የሰነዘሩበት አነጋገር ከተለያዩት የሀገሪቱ ፓርቲዎች እና ከሕዝቡ ብዙ ተቃውሞ ቀስቀሰ።

መጾም መራብ ሳይሆን ተፈጥሯዊ የሆነ የአኗኗር ስልት ነዉ ይላሉ የዚህ ሃሳብ አራማጆች። ዓላማቸዉ በየደረጃዉ ተዘጋጅተዉ ለገበያ በሚቀርቡት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምግቦች ምክንያት ወደአካላችን ገብቷል የሚሉት አላስፈላጊ ንጥረ ነገር እነሱ መርዝ የሚሉትን በተፈጥሯዊ ስልት ከሰዉነት ለማስወገድ ነዉ።

እስራኤል በምድሯ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂ አፍሪቃዉያንን ወደየመጡበት አስገድዳ መመለሷን የመብት ተሟጋቾች አወገዙ። ከትናንት በስተያ እስር ላይ ካቆየቻቸዉ ሁለት ሺህ ኤርትራዉያንና ሱዳናዉያን መካከል 14 ኤርትራዉያንን ወደአስመራ መላኳን አንድ የእስራኤል የመብት ተሟጋች ድርጅትና ሂዉማን ራይትስ ዎች ይፋ አድርገዋል።

የተቃዉሞ ሠልፍ መደረጉን፥ አንዳዶች ገዢዉ ፓርቲ ላለፉት ስምንት ዓመታት ይከተለዉ ከነበረዉ መርኹ የመለሳለሱ ምልክት ይሉታል።ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመጠናከራቸዉ ማሳያ ነዉ-ባዮችም አሉ። ሌሎች ደግሞ ቢያንስ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚደግፈዉ ሕዝብ ተቃዉሞዉን ለማሰማት ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት የመቁረጡ አብነት ነዉ።