የዘጠኙ ፓርቲዎች መግለጫ
በትብብር ለመሥራት የተስማሙ ዘጠኝ ፓርቲዎች በሕዳር ወር ሊያከናዉኑ ያቀዱት የሕዝብ ንቅናቄ በአዲስ አበባ መስተዳደር መስተጓጎሉን አስታወቁ።
በትብብር ለመሥራት የተስማሙ ዘጠኝ ፓርቲዎች በሕዳር ወር ሊያከናዉኑ ያቀዱት የሕዝብ ንቅናቄ በአዲስ አበባ መስተዳደር መስተጓጎሉን አስታወቁ።
የዋካንግ ጉብኝትና ዉይይት ያተኮረዉ በተለይ በደቡብ ሱዳን ጦርነትና ስደተኞች ይዞታ ላይ ነዉ
መቀመጫውን ጀርመን ያደረገው የ«አልፋ-ቤትኢትዮጵያ»ማሕበርበተለይ በኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን ያንበሊ አካባቢ ታዳሽ የሀይል ምንጭ ለአካባቢው ነዋሪዎች በማቅረብ ይንቀሳቀሳል። ይኼው ማህበር ከሁለት ሳምንታት በፊት ባዘጋጀው ስብሰባ የንጹህ ውሀ አቅርቦት እና የዕውቀት ሽግግር ቀጣዩ አላማው እንደሆነ አስታውቋል።
አልሸባብ በማንዴራ ከተማ 28 ሰዎችን ከገደለ በኋላ የኬንያ መንግስት የወሰደው የበቀል እርምጃ ለትችትና ወቀሳ አግልጦታል።የኬንያ መንግስት ችግሩን ለማስወገድ የጸጥታ ተቋማትን እንዲያጠናክርም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እያሳሰቡ ነዉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የፍርድ ሸንጎ ያልታጠቀ ጥቁር ታዳጊ ወጣትን በመግደል የተጠረጠረዉን ነጭ ፖሊስ ከመከሰስ ነፃ ማድረጉ በፈርጉሰን ሚዙሪ ግዛት የከፋ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ እንዲያገረሽ ማድረጉ ተነገረ።
አካታች ወይም integrated የማስተማር ሥልትን ኢትዮጵያ ዉስጥ የጀመረዉ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የጀርመን ቤተ-ክርስቲያን ትምሕርት ቤት ነዉ። አሁንም ቀጥሎበታል።
ሌተና ኮሎኔል ያኩባ ኢሳክ ዚዳ የወታደር የደንብ ልብሳቸውን አውልቀዋል። ትናንት በተካሄደው የቡርኪና ፋሶ የሽግግር መንግሥት የመጀመርያዉን የካቢኔ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል። ስብሰባው ከተከፈተ ከአንድ ሰዓት በኋላም ዚዳ « በርካታ ለውጦችን» ለሀገራቸው አውጀዋል።
ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍፃሜ ወዲሕ በተለያዩ ሐገራት የተለያዩ የአደባባይ ሠልፍ-አመፆች ተደርገዋል።አስር ዓመት ባልሞላ ጊዜ ሁለት መንግሥት በአደባባይ አመፅ የፈረሰባት ሐገር ግን አንድ ናት።ዩክሬን።ዛሬም ቢያንስ ምሥራቃዊ ግዛቷ ደም በሚያራጭ አመፅ እየወደመች፤ ምስራቅ ምዕራቦችን ከ25 ዓመት በኋላ ዳግም እንዳፋጠጠች ነዉ።
ሊዮኔል ሜሲ ታሪክ ሰርቷል። በታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ 37,000 ሰዎች መሳተፋቸው ተገልጧል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪዎች አቅም እየከዳቸው ይመስላል። አርሰናልና ሊቨርፑል ዳገቱ ከብዷቸው 8ኛ እና 12ኛ ደረጃ ላይ እየኳተኑ ነው። ቸልሲ ዘንድሮም ጥንካሬ አልተለየውም፤ ማንቸስተር ሲቲና ማንቸስተር ዩናይትድን በቅርብ ርቀት አስከትሎ
በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ወሲባዊ ጥቃት አሳሳቢ ነው ተባለ። በ17 ዓመቷ ታዳጊ ሐና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ድርጊቱ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።
በመጨው የካቲት ወር በናይጄሪያ በሚደረገው ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ የሚመለከታቸው ክፍሎች ሁሉ ከወዲሁ ርምጃ ካልወሰዱ እና ጥንቃቄ ካላደረጉ አመፅ ሊቀሰቀስ እና ኹከት ሊፈጠር እንደሚችል ዋና ጽሕፈት ቤቱን ብራስልስ ፣
ነጭ ዐባይ አቋርጦ የሚያልፍባት የተፈጥሮ ውበትና የደለበ የተለያየ የማዕድናት ሀብት ያላት ፤ ደቡብ ሱዳን ፣ ነጻነት አውጃ 2 ዓመት ከመንፈቅ ከተጓዘች በኋላ ፣ ፕሬዚዳንቷ ሳልቫ ኪር ፣ አምና ታኅሳስ 6 ቀን 2006 ዓ ም፤ መፈንቅለ መንግሥት
የኢራንን የአቶም መረሃ-ግብርን በተመለከተ የጋራ ነጥብ ላይ እስካሁን አልተደረሰም። የኢራንን የአቶም መረሃ- ግብር በተመለከተ ቪየና ላይ በተደረገዉ ዉይይት በቂ ዉጤት ላይ ባለመደረሱ የቴህራን መንግስት የተጨማሪ የግዜ ገደብ እንዲሰጥ ጠይቋል።
ዓለማቀፉ የአትሌትክስ ፊደሪሽኖች ማኅበር «IAAF» የዓመቱን የዓለም ኮከብ አትሌቶች ምርጫ ትናንት ምሽት ሞናኮ ላይ ባካሄደዉ ልዩ የሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ ይፋ አድርጎአል። ኢትዮጵያዊትዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በዉድድሩ ለእጩነት ቀርባ የነበረ ቢሆንም የኮከብነቱን መዕረግ ሳታገኝ ቀርታለች።
የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የጀርመን የቅርብ አጋር የሆነችዉን አፍሪቃዊት ሃገር ደቡብ አፍሪቃን ጎብኝተዋል። በደቡብ አፍሪቃ የጀርመኑ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የኤኮኖሚ አለመመረጋትና ደካማ ጎኖች አሉት በሚል ስጋት ላይ በመዉደቁ፤ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ላይ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎአል።
ሰሜን- ምስራቅ ኬንያ ውስጥ የሶማሊያው ዓማጺ ቡድን አሸባብ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ 28 ሰዎች መግደሉን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።
የሰብአዊ መብት ጉባኤ ፤ ሰመጉ ፣ ከአውሮፓ ህብረት ሲቪክ ማሕበረሰብ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያ ለሥራ ፍለጋም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሳውዲ አረቢያ እና ምስራቅ እስያ የሚሰደዱ ፤
።«ልጁ ወላጆቹን እንዲገድል ይታዘዛል።ልጁ ትዕዛዙን ሲፈፅም ወድሞቹ፤የአክስት አጎት ልጁቹ እና ሌሎች ዘመዶቹም እንዲያ ይገደዳሉ።ከዚያ በሕዋላ ገዳዩን ወላጆቹን ወይም ዘመዶቻችንን የገደለ እያሉ እረፍት ያሳጡታል።እሱም እነሱም የተሠራዉን አይረሱም
ለህጻናት ዓለማችን ከ25 ዓመት በፊት ከነበረው አሁን ይሻል ይሆን? ልክ ትናንት ከ25 ዓመት በፊት ነበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የህፃናት መብት ውል ያዘጋጀው። ባለፈው 25 ዓመታት የሆነውን አጠቃላይ ሂደት በአጭሩ በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንቃኛለን።
የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ፤ ሰመጎ ፣ ከአውሮፓ ህብረት ሲቪክ ማህበረሰብ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያ ለስራ ፍለጋም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሳውዲ አረቢያ እና ምስራቅ እስያ የሚሰደዱ ፤
እንደ የዓለም የጤና ድርጅት አንድ ዘገባ ከሆነ፣ በምድራችን አደገኛ ጨረሮችን የሚከላከለው የኦ ዞን ንጣፍ ሳስቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሀገራቸው ቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት በዩናትድ ስቴትስ የሚገኙ 5 ሚሊዬን የሚጠጉ ህገ ወጥ ስደተኞች፣
የሰዉ ልጅ በሚያደርገዉ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ዉስጥ ጥበብ እንዳለ ባለሞያዎች ይናገራሉ። የሰዉ ልጅ ይህን እንቅስቃሴዉን በማስመሰል በትያትር መልክ ለራሱ ተዉኖ ያቀርበዋል፤ እንደ መስታወትም ገሃዱን ዓለም ራሱን ያይበታል፤ በትያትር። ትያትር እንደሚታሰበዉ ለሳቅ ለጫወታ ለመዝናኛ የሚቀርብ ሳይሆን፤ ትያትር «የሃገር የህዝብ ፍልስፍና ፤
የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ጉድ ላክ ጆናታን ሦስት ያገሪቱ ግዛቶችን ከቦኮ ሃራም ለመጠበቅ ያቀረቡት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማስተዳደር ሃሳብ እክል ገጥሞታል። በቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን ጥቃት በደረሰባቸው የሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ግዛቶች እ.ኤ.አ. ግንቦት
ሕዝብ መምረጥ የሚችለዉ አማራጮች ሲቀርቡለት ነዉ።ፓርቲዉ «የሕሊና እስረኞች» ያላቸዉ ፖለቲከኞች፤የሐይማኖት መሪዎች እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ እንደሚከፍትም መሪዎቹ አስታዉቀዋል
የአውሮጳ ዳኞች እስር ቤት የሚወረወሩ ተገን ጠያቂዎች ቁጥር አነስተኛ እንዲሆን ያደረጉት ጥረት በስተመጨረሻ ውጤት አስመዝግቧል። ሆኖም ለስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች የሚቆረቆረው፥ ኢየሱሳውያን በመባል የሚታወቀው የካቶሊክ ጽ/ቤት ይኽ በቅርቡ መቀየሩ አይቀርም ሲል ስጋቱን ገልጧል። ያን ሊቀይር የሚችል ሕግ በጀርመን ሚንስትሮች እየተመከረበት ነው።
የእስራኤል መንግሥት የገዳዮችን፤የወላጆቻቸዉንና የዘመዶቻቸዉን መኖሪያ ቤቶች እያስፈረሰ ነዉ። የአንዲት ከተማ ከንቲባ ደግሞ አረብ እስራኤላዉያን በግንባታ ሥራ-እንዳይሰማሩ አግደዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ባለፈው ወር ብቻ ከ5000 በላይ ኤርትራውያን ድንበር ተሻግረው በኢትዮጵያ ጥገኝነት መጠየቃቸውን አስታወቀ።በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ቁጥር
በሱማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሳን ሼይክ ሞሐሙድ እና በጠቅላይ ሚንስትር አብዲዋይል ሼይክ አኽመድ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ መባባሱ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡትን የሚንስትሮች ምክር ቤት መዋቅር ፕሬዚዳንቱ እንዳልተቀበሉት ተገልጿል።
መብረቅ የሚፈጥር ደመና ከሩቅ ሲታይ ፣ የተፈጥሮ ትርዒት በመሆኑ ዐይንን ሊስብ ይችላል። ከቅርብ ከሆነ ግን፣ ፍርሃትና ጭንቀት ነው የሚያስከትለው፤ የመብረቁ ብልጭታ አደጋ ሊያስከትል የሚችልበት ሁኔታ በመኖሩ! የምድር
በኤቦላ ተሐዋሲ ወደተጠቁት ሶስት የአፍሪቃ ሃገራት ተጉዞ የነበረዉ የአዉሮጳ ኮሚሽን ልዑክ የጉብኝቱን ዉጤትና አስተያየት ለኅብረቱ ልዩልዩ ተቋሞች አቀረበ።
የአውሮጳ ህብረት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በምሥራቅ ዩክሬይን ዓማፅያን አንፃር አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማሙ። የህብረቱ ዲፕሎማቲክ ክፍል በዚህ በተያዘው የህዳር ወር መጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት አንድ የዩክሬይንን ዓማፅያን ዒላማ ያደረገ አዲስ ዝርዝር እንዲያቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ጠይቀዋል።
ኩፍኝን ከዓለም ፈፅሞ ለማጥፋት የሚደረገዉ ጥረት መሻሻል አለማሳየቱን የዓለም የጤና ድርጅት ባለፈዉ ሳምንት ይፋ አድርጓል። በምክንያትነት ከተጠቀሱት የበሽታዉ ከሰዉ ወደሰዉ ፈጥኖ የመተላለፍ ባህሪ አንዱ ሲሆን የክትባት አለመዳረስም ሌላዉ ጉዳይ ነዉ።
ከመስከረም ወር አጋማሽ አንስቶ በቻይናዋራስ-ገዝግዛትሆንግኮንግ የተጀመረው የተቃዉሞ ሠልፍ እና አድማ አልተጠናቀቀም። አሁንም ሰልፈኞቹ የፋይናንስ ቦታዎችን ይዘው ይገኛሉ። ይሁንና ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የሆንግ ኮንግ ፖሊስ የተወሰኑ ቦታዎችን ከሰልፈኞች አስለቅቋል።
በየእሩሳሌም ሙክራብ ላይ የደረሰ ጥቃትእየሩሳሌም ውስጥ የተነሳው ብጥብጥ ይበልጥ ከሯል። ዛሬ ዳግም አዲስ ጥቃት ከተማዋን አናግቷል። ይህም በአይሁዳውያን ቤተ ፀሎት ላይ ነው። በዚህም ጥቃት 6 ሰዎች ሰዎች ተገድለዋል። ሁለት ጥቃት አድራሾች እና አራት ሲቪሎች።
ከሁለቱ ሐገራት የተዉጣጡ ከሁለት መቶ የሚበልጡ የሁለቱ ሐገራት የንግድ ድርጅቶችና የኩባንያ ባለቤቶች ተካፍለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪቃ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታውን እጅግ የጠበበ ዕድል ይዞ ረቡዕ ያከናውናል። ቡድኑ በአዲስ የውጭ ሀገር አሠልጣኝ መመራት ከጀመረ ወዲህ ለማሸነፍ የቻለው አንድ ጨዋታ ብቻ ነው። ምክንያቱ ምንድን ነው? ጂብራልታርን 4 ለ0 ያሸነፈው የጀርመን ቡድን አሠልጣኝ በውጤቱ አልተደሰቱም።
አንዱ ቡድን በ15ለ 1 ተፃራሪ ሐይላት የተወጠረ፤ በ4መሐል ሰፋሪዎች የተትመከመከ መሆኑን መስካሪ ነዉ።ለዘንድሮዉ ጉባኤ የመነጋገሪያ ርዕስ፤ የአቋም መግለጫምከቡድኑ ይፋዊ አላማ ጋር የሚጣጠም ነዉ።ምጣኔ ሐብት።
በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በኢትዮጵያ ሶስት የኢቦላ ተጠርጣሪ ህሙማን ተገኙ የሚል ደብዳቤ እየተሰራጨ ነው። የክልሉ ጤና ቢሮ ደብዳቤውን እንደማያውቀው የኢቦላ በሽታም በክልሉ አለመኖሩን አስታውቋል።
ከጀርመን ወደ 450 ጀርመናዉያን ሳላፊስቶች ወደ ሶርያ መጓዛቸዉ ተመልክቶአል። ከነዚህ መካከል ደግሞ 10 በመቶዉ የሚሆኑት ራድዮ ጣብያችን ከሚገኝበት ከቦን ከተማ መምጣታቸዉ ነዉ የተነገረዉ። የቀድሞዋ የምዕራብ ጀርመን መዲና ቦን ለምን የፅንፈኞች ማዕከል ለመሆን በቃች?
ከየካቲት 1966 ጀምሮ አንዳዶች የሚድኸዉ መፈንቅለ መንግሥት፤ ሌሎች አዝጋሚዉ አብዮት፤ ሌሎች ደግሞ ግብታዊዉ ለዉጥ የሚሉት አብዮት የወደፊት ሒደት በግልፅ የታየበት፤ደርግ «ያለ ምንም ደም» ከሚለዉ መሪ መፈክሩ በታቃሮኑ መቆሙ የተረጋገጠበት፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞም በደም «በጨቀየ» ጎዳና መደናበር የጀመረበት ወቅት ነዉ።