UTC 16:00 የዓለም ዜና 07.12.2014
የዓለም ዜና
የፕሬዚዳንት ሙጋቤ ባለቤት የዚምባቡዌ ቀጣይ የሀገር አስተዳዳሪ ለመሆን ራሳቸውን እጩ እስከመሆን አበቁ። ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤን የገዢው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ሀራሬ ውስጥ ባካሄደው ስብሰባ የ49 ዓመቷን ወ/ሮ ከሴቶች ክፍል ተጠሪ አድርጎ ሰይሟል። ወይዘሮ ግሬስ አንዱን ቀን የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሚሹም አመላክተዋል።
የፕሬዚዳንት ሙጋቤ ባለቤት የዚምባቡዌ ቀጣይ የሀገር አስተዳዳሪ ለመሆን ራሳቸውን እጩ እስከመሆን አበቁ። ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤን የገዢው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ሀራሬ ውስጥ ባካሄደው ስብሰባ የ49 ዓመቷን ወ/ሮ ከሴቶች ክፍል ተጠሪ አድርጎ ሰይሟል። ወይዘሮ ግሬስ አንዱን ቀን የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሚሹም አመላክተዋል።
በይፋ ለሦስት ጊዜያት እንደተገረሰሰ ቢነገርም፥ ዛሬም ቢሆን በሞሪታንያ የባርነት ስርዓት ጭቆና አልተወገደም። የዕድሜያቸውን እኩሌታ በባርነት ቀንበር ሲማቅቁ የነበሩ አንድ ሞሪታኒያዊ ትውስታቸውን ያካፍላሉ። በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ የሰፈረው የፈረንሣይ ጦር ሠላም ማስፈን ተስኖታል እየተባለ ነው።
በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ «አዲስ ሾፒንግ ፌስቲቫል» የተባለ ፌስቲቫል አዲስ አበባ ውስጥ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ስለ ፌስቲቫሉ ምንነት እና ይዘት በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንቃኛለን።
የደቡብ አፍሪቃዉ የነፃነት ታጋይና የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ኔልሰን ማንዴላ ልክ በዛሬዋ ቀን የዛሬ ዓመት ነበር ላይመለሱ ይህችን ዓለም የተሰናበቷት። በአንደኛ የሙት ዓመታቸዉ ዛሪ ታድያ የሀገሪቱ ነዋሪ ከዳር እስከ ዳር በቩቩዜላ ጡሩምባ፤ የፖሊስ እና የቀይ መስቀል ጡሩምባን በማስጮኽ ለስድስት ደቂቃ አስተጋብቶላቸዋል፤ አስቦአቸዋልም።
10ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪቃ መገናኛ ብዙኀን ጉባዔ፣ ትናንት ጧት አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሮ ማምሻውን ተደምድሟል ።ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች የተውጣጡ ጋዜጠኞች በተሳተፉበት ጉባዔ የመነጋገሪያ አጀንዳው ኢቦላነበረ። አፍሪቃውያን ጋዜጠኞች
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በአፅህሮቱ (IOM) ታንዛንያ ዉስጥ ታስረዉ የነበሩ 253 የኢትዮጵያ ስደተኞችን ባለፈዉ ሳምንት ወደ ሃገራቸዉ መልሶአል። ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ ከታንዛንያ እስር ቤት ተለቀዉ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት ስደተኞች መካከል 39 ኙ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ናቸዉ።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በአፅህሮቱ (IOM) ታንዛንያ ዉስጥ ታስረዉ የነበሩ 253 የኢትዮጵያ ስደተኞችን ባለፈዉ ሳምንት ወደ ሃገራቸዉ መልሶአል። ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ ከታንዛንያ እስር ቤት ተለቀዉ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱት ስደተኞች መካከል 39 ኙ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ናቸዉ።
ራሳቸዉን ቤተ- እሥራኤላዉያን እያሉ የሚጠሩ የኢትዮጳያ አይሁዶች ባለፈዉ ሰሞን በየዓመቱ የሚያከብሩትን የሥግድ በዓል እያሩሳሌም ላይ በከፍተኛ ድምቀት አክብረዋል። የሥግድ በዓል በቤተ እሥራኤላዉያን ዘንድ እንዴት እና ለምን ይከበራል? በለቱ ዝግጅታችን ቤተ-እሥራኤላዉያን ስለሚያከብሩት የሥግድ በዓል ምንነት እንመለከታለን።
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (አይ ሲ ሲ )በኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላይ የቀረበው ክስ በአንድ ሳምንት ውስጥ እንዲጠናቀቅ አለያም ክሱ እንዲሰረዝ ወሰነ ።የፕሬዝዳንቱን ጉዳይ የያዙት አቃቤ ህጎች መረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸዉ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ዉድቅ አድርጎቷል።
በጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን ፤ ከጀርመን መራኂተ መንግሥት ወ/ሮ አንጌላ ሜርክልና ሌሎችም ባለሥልጣናት ጋር በጋራና በአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው ተገልጿል። የሁለቱ ሃገራት ባለሥልጣናት ሕንጻ ውስጥ
የ NATO አባል ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ፣ ትናንት ባራሰልስ ውስጥ፤ ባደረጉት ስብሰባ፤ የመከላከያው ጉድኝት ኃይል በሚደራጅበትና በሚመደብበት ሁኔታ የተስማሙ ሲሆን፤ ከመጪው ወር 2015 አዲሱ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት መግቢያ አንስቶ ጊዜያዊ ፈጥኖ ደራሽ
ላቲን አሜሪካዊቷ ሀገር ፔሩ ፣ ከትናንት በስቲያ አንስቶ ለ 12 ቀናት የዓለምን የአየር ንብረት ጉባዔ ስታስተናግድ ትሰነብታለች። የ 195 አገሮች ተወካዮች ናቸው በዚህ ዐቢይ ጉባዔ የሚመክሩት። ለተፈጥሮ አካባቢ ፤ ለየብስ ባህርና ከባቢ አየር
በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የዘንድሮው ዓመት የሙስና ሠንዘረዥ መሰረት ዴንማርክ እንደ አምናው ከሙስና ነፃ ከሚባሉት ሀገራት ተርታ በቀደምትነት ስትሰለፍ ሶማልያ ደግሞ በሙስና ከተዘፈቁት ሀገራት ከመጨረሻ 1ኛ ሆናለች። ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራትስ?
«ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል» በመባል የሚታወቀው፣ በዓለም ዙሪያ ለነባር ህዝቦች ኅልውና የሚታገለው ድርጅት የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስለኦሞ ሸለቆ ጉዳይ እንዲያነሱ አሳሰበ። ድርጅቱ በኦሞ ሸለቆ «የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተከሰተ ነው፤ ጀርመንም ሆነች ሌሎች የአውሮጳ ሃገራት የመብት ጥሰቱን አይተው እንዳላዩ ሆነዋል» ብሏል።
በጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም የሚመራዉ ቡድን የጀርመንኗን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ የተለያዩ የጀርመን ባለሥልጣናትንና ባለሐብቶችን ለማነጋገር ቀጠሮ አለዉ።ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፤ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የሠብአዊ መብት ተሟጋቾች ባንፃሩ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ተቃዉሞ ሠልፍ ለማድረግ አቅደዋል።
በቱርክ የሶስት ቀናት ጉብኝትን ያደረጉት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ በጉብኝታቸዉ ማጠቃለያ በተደረገዉ የመሰናበቻ ዝግጅት ከኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በርተለሜዎስ ጋር የሐዋርያዉን ቅዱስ አንድርያስ ዕለተ ሞት በልዩ መንፈሳዊ ሥነ-ስርዓት አስበዋል።
በሶስት የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የተዛመተዉ ኢቦላ 6000 ገደማ ሰው ገልዋል። ወደ 16 ሺህ ህዝብ ደሞ በተውሓሲው ተለክፎአል። የኢቦላ ወረርሺኝ ያደረሰዉ ቀዉስ ከቁጥጥር ዉጭ የሚወጣበት ደረጃ መድረሱ እየተነገረ ነዉ። የኤቦላ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገዉ ጥረትና ትብብር ጀርመን የምታደርገዉ ርዳታ ሳይዘገይ እየተነገረ ነዉ።
የአዲስ አበባ መስተዳድር ዕዉቅና መንፈጉን ሕገ-ወጥ ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲዎቹ በዕቅዳቸዉ እንዲሚቀጥሉበት አስታዉቀዋል።
የሶማልያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የአሸባብ ታጣቂዎች ኬንያ ዉስጥ ሰላሳ ስድስት ድንጋይ አዉጪዎችን ገደሉ። ታጣቂዎቹ በሰሜናዊ ምስራቅ ኬንያ ማንዴራ ከተማ አጠገብ ዛሬ ሲነጋጋ በከፈቱት ጥቃት የገደሏቸዉ አብዛኞቹ ሰዎች የቀን ሰራተኞችን ነበሩ።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን አንድነት ፓትሪያርክ በርጦሎሜዎስ ቀዳማዊ ፣ ክርስቲያኖች ከመካከለኛው ምሥራቅ እንዲጠፉ የመላው ዓለም ፍላጎት አይደለም አሉ።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ ፈጣን ግስጋሴው ገታ ብሏል፥ የአምናው ባለዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ እግር በእግር መከተሉን አላቋረጠም። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ኃያሉ ባየር ሙንሽን እንደልማዱ ሊጋው ከመጠናቀቁ ቀደም ብሎ ዋንጫውን ለመጨበጥ ተቃርቧል፤ የቀድሞው ብርቱ ተፎካካሪ ቦሩስያ ዶርትሙንድ አቅም አንሶት በወራጅ ቃጣናው ጠርዝ ላይ እያጣጣረ ነው።
ኢትዮጵያም -በአብዮትና ፀረ-አብዮት ግብግብ ትናወጥ ነበር።የሶማሊያ ጦርም ገሚስ ኢትዮጵያን ለመያዝ ምሥራቅና ደቡባዊ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ።የአብዮቱ ትርምስ፤ የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት፤ የዩናይትድ ስቴት መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም መያዝ፤ ለቤገን ዕቅድና ቃላቸዉን ገቢር ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ነበር።
የገዳዩን የኤቦላ ተሐዋሲ የመዛመት ዜናን ተከትሎ ሰናይ ዜናን መሰማቱ ያልተለመደ ነበር። በቅርቡ ግን ተሐዋሲዉን ለመከላከል ያስችል ይሆናል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የክትባት መድሃኒት፤ ሰዎች ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጭ ዉጤትን አስገኝቶአል። ። በሌላ በኩል ክትባቱ አሉታዊ ገፆች እንዳሉትም ነዉ የተነገረዉ።
የጀርመን ዓለም አቀፉ የትብብር ድርጅት በምህፃሩ GiZ በአዲስ አበባ 11 000 የቁጠባ ቤቶች ያሉት 700 የቁጠባ ህንፃዎች ሰርቶ ጨርሶ ማስረከቡን ይፋ አድርጓል።
ምንም እንኳን በግብፅ በኩል አድርገው በህገ ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር፣ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ቢቀንስም፣ አሁን ድረስ በእስራኤል 48 000 የአፍሪቃ ስደተኞች እንደሚገኙ ይታመናል።
በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን ወሲባዊ ጥቃት አሳሳቢ ነው ተባለ። በ17 ዓመቷ ታዳጊ ሐና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባት ህይወቷ ካለፈ በኋላ ድርጊቱ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል።
የግብፅ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከተመሰረተባቸው ክስ በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም በመዲናይቱ ካይሮ ደም አፋሳሽ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።ሙባረክን በነፃ ያሰናበተውን የግብፅ ፍርድ ቤት ለመቃወም ታህሪር አደባባይ በወጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጸረ-ሙባረክ ሠልፈኞች እና ፖሊሶች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
የግብፅ ከፍተኛው ፍርድ ቤት፥ የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ከተከሰሱበት የግድያ እና የሙስና ወንጀሎች በነፃ ማሰናበቱ ተገለጠ።
ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሠፈሩ እና ከአሁን ቀደም የዜግነት ጥያቄያቸዉ አጠራጣሪ በመሆኑ ወደ ሀገራቸዉ መመለስ ፈቃድ ያላገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ አንጎላዉያን ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ የሚችል ስምምነት መፈረሙ ተገለፀ።
በእስራኤል የአይሁዳውያን ምኩራብ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ እየሩሳሌም የግጭት ስጋት ውስጥ ተዘፍቃለች። የዶይቼ ቬሌ ወኪል የሆነችው ታኒያ ክራመር በዘገባዋ ለአንዳንዶች አሁን በከተማዋ የሚታየው ስጋት ሁለተኛውን ህዝባዊ አመጽ ወይም ኢንቲፋዳ ያስታውሳል ትላለች።እሸቴ በቀለ ዘገባውን እንዲህ አሰናድቶታል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓመት አንዴ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል። የዘንድሮው ማለትም 14ኛው የሩጫ ውድድር እንዴት አለፈ? አረንጓዴ እና ቀይ ቲሸርት ለብሰው ባለፈው እሁድ በሺ የሚቆጠሩ ፣ በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገነኙ ኢትዮጵያውያን ፣ አዲስ አበባ የሚኖሩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና
በአፍሪቃ እና በእስያ የሚገኙ የአሸባሪ ቡድኖች በተደጋጋሚ እስላማዊ መንግሥት ብሎ ራሱን የሚጠራዉን አሸባሪ መንግሥት ሲቀላቀሉ ተስተዉሎአል። ፅንፈኛዉ ቡድን «እስላማዊ መንግሥት» ከፅንፈኛዉ አልቃይዳ ቡድን ይልቅ የአሸባሪነት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉ ነዉ የተመለከተዉ።
ናሚቢያን ላለፉት 24 ዓመታት የመራት የደቡብ ምዕራብ አፍሪቃ ሕዝባዊ ድርጅት በእንግሊዘኛ ምኅጻሩ SWAPO በዘንድሮው የናሚቢያ የምክር ቤት እና የፕሬዚዳንት ምርጫ የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ እንደሆነ ተገምቷል። ሆኖም በአንዳንድ የፓርቲው አባላት ዘንድ ይኽ መነቃቃት ደብዛዛ መሆኑ ተጠቅሷል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች አራት ሐገራት ግን ኮሚቴዉ ዉሳኔ ከመስጠቱ በፊት እራሳቸዉን ከዉድድሩ አግልለዋል።
በ 70 ዎቹ ዓመታት በፖፕ ሙዚቃ ጥበቡ፣ በዓለም የሙዚቃ መድረክ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈዉና የስልምና ሐይማኖትን በመቀበሉ የሚታወቀዉ ምዕራባዊዉ ዝነኛ ሙዚቀኛ በጀርመን የሙዚቃ መድረክ ዳግም ብቅ ሊል መሆኑ ከተገለፀ በኋላ የብዙሃን መገናኛን ቀልብ ስቦ ይገኛል።
ፈርግሰን-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ያልታጠቀ ጥቁር ወጣትን የገደለዉ ነጭ ፖሊስ እንዳይከሰስ የከተማይቱ ፍርድ ሸንጎ መወሰኑ የቀሰቀሰዉ ሕዝባዊ ቁጣና ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ። ጀርመንም ቢሆን ፖሊሶች በቆዳ ቀለም ከፍተኛ የዘር መድሎ ያደርጋሉ በሚል በተደጋጋሚ ይወቀሳሉ።
ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መግቢያ ላይ ማይክል ብራውን የተባለው አንዳች የመከላከያ መሣሪያ ያልያዘ የ 18 ዓመት ወጣት ፣ዳረን ዊልሰን የተሰኘው ነጭ ፖሊስ በተደጋጋሚ ጥይት ተኩሶ መግደሉ ብዙ የተባለለት ጉዳይ ነው።
አውሮጳ ለዜጎቿ ዋስትና ልትሰጥ ብሎም ዕድል ልታመቻች ይገባል፥ ለእዚያም አዲስ አንቀሳቃሽ ኃይል ያሻታል ሲሉ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ በአውሮጳ ምክር ቤት ተናግረዋል። የፍራንሲስን ንግግር የምክር ቤቱ አባላት ያጤኑት ይኾን?
ምግብ ማግኘት ፍጹም መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ነው፤ መብቱን የሚገነዘብለት ፣ መብቱን የሚያከብርለት –ኖረም -አልኖረ! የገንዘብ አቅም ላለው ደግሞ፣ በኢንተርኔት አገልግሎት መሥመር መጠቀምም መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ነው። ይህ አገልግሎት ፍጹም
በሊቢያ የባህር ዳርቻ ከተማ ዴርና በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ራሱን « እስላማዊ መንግሥት» አይሲስ ብሎ የሚጠራውን የሙስሊም አክራሪ ቡድን መቀላቀላቸው ተሰምቷል። ተንታኞች ቡድኑ ሊቢያ ውስጥም ተዋጊዎችን ሊመለምል ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።