የሊማዉ የአየር ንብረት ጉባኤ ፍፃሜና ዉጤቱ
የሊማዉ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ የበለፀጉትና ደሀ ሃገራት ለአየር ንብረት ለዉጥ ሊደረግ ይገባል የሚሏቸዉ አጣዳፊ ጉዳዮች በመለያየታቸዉ ምክንያት ብዙም ዉጤት ያመጣል የሚል ተስፋ ሳያሳድር ነበር የተጀመረዉ።
የሊማዉ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ የበለፀጉትና ደሀ ሃገራት ለአየር ንብረት ለዉጥ ሊደረግ ይገባል የሚሏቸዉ አጣዳፊ ጉዳዮች በመለያየታቸዉ ምክንያት ብዙም ዉጤት ያመጣል የሚል ተስፋ ሳያሳድር ነበር የተጀመረዉ።
በምዕራብ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት ማለትም በሴራሊዮን በጊኒና ላይቤርያ የኤቦላ ወረርሽኝ ስርጭት አሁንም አልተገታም። ናይጀርያዊዉ የተዋሐሲ ጉዳዮች ጥናት ባለሞያ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በምዕራብ አፍሪቃ የኤቦላ ተዋሐሲ ጨርሶ አለመጥፋት ዋና ምክንያት የአፍሪቃዉያኑ ዉሳኔ ሰጭዎች የአሠራር ጉዳይ ነዉ፤
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን በሚደግፉ የመንግሥት ወታደሮችና በቀድሞዉ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ደጋፊ ኃይላት መካከል የተጀመረዉ ጦርነት አንድ ዓመት አስቆጠረ።
ዘጠኝ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ሳምንት የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ የፓርቲው አባላት መታሰራቸው ከፖለቲካ ጥላቻ የመነጨ ነው ሲሉ የፓርቲዎቹ ትብብር ሊቀ መንበር ኢንጅንየር ይልቃል ጌትነት ገለጹ።
በደቡብ ጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አቅራቢያ ለስደተኞች በተሰናዱ መጠለያዎች ላይ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ፤ ቃጠሎውም ሆን ተብሎ እንደደረሰ የሚጠቁሙ የፅንፈኞች ምልክቶች በመገኘታቸው ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ ከተሞች ዘረኝነትን የሚቃወሙ እና የሚደግፉ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሲየራ ልዮን የብዙ ሺዎችን ሕይወት እያጠፋ ያለውን የኤቦላ ወረርሽኝ ለማጥፋት ከያቅጣጫው ጥረቱ ተጠናክሮዋል። በዚሁ መሠረትም፣ በርካታ ሀገራት እና ድርጅቶች ባለፈው ዓርብ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን የፀረ ኤቦላ ትግል ግብረ ኃይል አስተባባሪ በጠራው ስብሰባ ላይ በመገኘት
ሀሳን አሊ ለበርካታ አመታት የአሸባብ አባል ሆነው ሰርተዋል። መፃፍ እና ማንበብ በመቻላቸውም በተለያዩ የቡድኑ ዘርፎች ተሰማርተው ነበር። ሀሳን አሊ የአሸባብ ቡድንን እንዴት እንደተቀላቀሉ እና በምን ምክንያት ቡድኑን እንደከዱ፤ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።
በምዕራብ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት ማለትም በሴራሊዮን በጊኒና ላይቤርያ የኤቦላ ወረርሽኝ ስርጭት አሁንም አልተገታም። ናይጀርያዊዉ የተዋሐሲ ጉዳዮች ጥናት ባለሞያ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በምዕራብ አፍሪቃ የኤቦላ ተዋሐሲ ጨርሶ አለመጥፋት ዋና ምክንያት የአፍሪቃዉያኑ ዉሳኔ ሰጭዎች የአሠራር ጉዳይ ነዉ፤
ሁለቱ፤ በአንዱ-ዓለም አቀፍ አስተሳሰብ አንድ የሆኑበት ሰበብ ምክንያት አንድም አጋጣሚ-አለያም «ትንኝም ለሆዷ፤ ዝሆንም ለሆዱ —-» እንዳለዉ ኢትዮጵያዊዉ ባለቅኔ ካልሆነ በስተጠቀር ብዙም ትንታኔ የለዉም።
በኦስትሬሊያ የሲድኒ ከተማ አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ዛሬ ንጋት ላይ በርካታ ሰዎችን ያገተበትን አንድ ቡና ቤት የከተማይቱ ፖሊስ ከጥቂት ጊዜ በፊት ማጥቃቱ እና በዚሁ ጊዜም ሁለት ሰዎች፣ መገደላቸውን፣ እንዲሁም ፣ ሶስት በጠና መቁሰላቸው ተገለጸ። ከተገደሉት መካከል አንዱ አጋቹ ነው።
ከ 12 ተኛዉ እስከ 20ኛዉ ክፍለ ዘመን በብራና ላይ የተፃፉ የኢትዮጵያ የክርስትናና የእስልምና ጥንታዊ የእጅ ጽሑፎች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን በንጽጽር ያቀረበና የታሪክ ምሁራን የተሳተፉበት ዐውድ ጥናት
በቤልጅግ ፤ ሶስት ሚሊዮን ገደማ አባላት ያሏቸው ሶስት ትላላቅ የሠራተኞች ማሕበራት በጠሩት የ 24 ሰዓት የሥራ ማቆም አድማ መሠረት፤ መዲናይቱን ብራሰልስን ጨምሮ አገሪቱ በመላ የሥራ እንቅሥቃሤዋ ተገትቶ ውሏል።
ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በተከታታይ መሣሪያ ያልያዙ ጥቁሮች በነጭ ፖሊሶች መገደላቸዉ ያስነሳዉ ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ።
ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት «አይ ሲ ሲ» በሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ኧል በሽር ላይ የጣለዉን የጦር ወንጀልነት ክስ ለተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን አስታዉቋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሥር ዓመት አንድ ቢልዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ በ6,6% በሆነ ወለድ ለዓለም አቀፉ ገበያ እንደምታቀርብ ሰሞኑን ይፋ አድርጋለች። የዚሁ ውሳኔዋ ትርጓሜ፣ ጥቅሙን እና ተፅዕኖውን በተመለከተ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂደናል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሠልፍ ዛሬ ከግንፍሌ አካባቢ ተነስቶ 22 አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 8 ሜዳ ላይ መጠናቀቁ ተገለጠ።
ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ ICC ዳርፉር ላይ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ከፍቶት የነበረውን ክስ ማቋረጡን አስታወቀ።
በምሥራቅ አፍሪቃዊትዋ ሀገር በርዋንዳ የፕሬስ ሕግጋትች ነጻ ሆነዉ ቢቀመጡም፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኞች በነጻነት መሥራትና መፃፍ እንዳልቻሉ ለጋዜጠኞች የሚሟገቱ ድርጅቶች ዘግበዋል።
በምዕራቡ ሀገራት የግድግዳ ጡፍ ወይም ግራፊቲ እንደ ተመልካቹ እና ማህበረሰቡ አተረጓጎም ይለያያል። አንዳንዶች ግራፊቲን ከውንብድና ጋር ሲያገናኙ ሌሎች ስሜት የሚገለፅበት አንድ መንገድ እንደሆነ ይናገራሉ። ሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የተወሰኑ ወጣቶች የግድግዳ ጡፍን እንደ አንድ የስዕል ጥበብ ነድፈው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።
ጠበቃ ተማም የተከሰሱት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚባለዉ የመንግሥት መገናኛ ዘዴ ሥለተከሳሾች ያቀረበዉን ዘገባና የፀረ-ሽብር ሕጉን በመተቸታቸዉ ነዉ
ናይጀሪያ በመጪዉ በምታካሂደዉ የምርጫ ፉክክር ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩት እጩዎች ማንነት ታወቀ። ዋናዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የእድገት ኃይሎች ምክር ቤት በምርህፃሩ APC በጡረታ ላይ የሚገኙትን የቀድሞዉ ወታደራዊ መሪ ሜጀር ጀነራል ሙሀማዱ ቡሀሪን እጩ ፕሬዝደንት አድርጎ አቅርቧል።
የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት FAO በያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2014 ከፍተኛ የሰብል ምርት መገኘቱን አመለከተ። እንደFAO ዘንድሮ ከ2,5 ቢሊዮን ቶን በላይ የሰብል ምርት በመመረቱ በዓለም የምርት ታሪክ አዲስ ሪከርድ ተመዝግቧል።
ከአፍሪቃና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ በጀልባ ፤ ባህር አቋርጠው አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በየጊዜው በመናር ላይ ነው። ቁጥራቸው የሚያመዝነው የአፍሪቃ ስደተኞች መሆናቸውም ይነገራል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን
በሰሜን ማሊ ፤ ሰሐራ ምፍረ በዳ ጫፍ ላይ የምትገኘው ጥንታዊቷ ገናና የንግድ ማዕከል ቲምቡክቱ፣ እ ጎ አ በ 2012 ፣ ከአክራሪ ሙስሊሞች እጅ ከወደቀች ወዲህ የከተማይቱ የንግድ እንቅሥቃሴ ከቶውንም ማንሠራራት እንዳልቻለ ነው የሚነገረው።
በዓለማችን የተለያዩ ቦታዎች የእርስ በርስ ግጭት፣ ጦርነት፣ ያለመረጋጋት እና ወረርሽኝ ሰፍኗል። እንዲያም ሆኖ ግን ሊሰናበት ጥቂት ቀናት በቀሩት የጎርጎሪዮሳዊው 2014 ዓም ውስጥ የዓለም ምጣኔ ሀብት ሦስት በመቶ እንዳደገ ተነግሯል። የምጣኔ ሀብቱ ጭንቀት ይልቁንስ ወደ ዩሮ ዞን የንግድ ቃጣና መሸጋገሩ እንደማይቀር ተገልጧል።
«መጽሐፈ ፈላስፋ ጠቢባን» በአጼ ዘረያቆብ ዘመነ መንግሥት ከ 1510 እስከ 1520 ባለዉ ጊዜ ከአረብኛ ወደ ግዕዝ ደብረሊባኖስ ዉስጥ እንተተረጎመ ስለ መጽሐፈ ፈላስፋ የሚያጠኑት ምሁራን ይገልፃሉ።
በሰሜን ምሥራቅ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ውስጥ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ማሕበረሰቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ እደጣለዉና መፍትሄ አልባ እንዳደረገዉ ተገልፆአል። የሲቪሉ ማሕበረሰብ ድርጅቶች አማፅያን የሚያደረሱት ጥቃት ለመከላከል የዓለም አቀፉን ርዳታ ጠይቀዋል።
ዛሬ የኖቤል መሥራች አልፍረድ ኖቤል የሞተበት ዕለት መታሰቢያ ሲሆን የሚታሰበውም ለዓለም ሰላም ጉልሕ አስተዋጽዎ ለሚያደርግ ለሚያደርጉ የኖቤል የሰላም ሽልማት በመሰጠት ነው። የሚሰጠውም በኖርዌይ መዲና በኦስሎ ሲሆን ፤በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ፤ ውጤታማ ለሆኑ ድግሞ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ነው ሽልማቱ የሚሰጠው።
በሰሜን ምሥራቅ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ውስጥ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ማሕበረሰቡን ከፍተኛ ስጋት ላይ እደጣለዉና መፍትሄ አልባ እንዳደረገዉ ተገልፆአል። የሲቪሉ ማሕበረሰብ ድርጅቶች አማፅያን የሚያደረሱት ጥቃት ለመከላከል የዓለም አቀፉን ርዳታ ጠይቀዋል።
የአሜሪካው የስለላ ተቋም «CIA» በሽብርተኝነት ተጠርጣሪ እስረኞችን በምርመራ ወቅት በከፍተኛ ሁናቴ ማሰቃየቱን የሚያጋልጠው ሠነድ በስተመጨረሻ ይፋ ሆኗል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቿ ሎውራ ፒተር ሠነዱን፦ «ለበርካታ አሜሪካውያን እጅግ አስደንጋጭ ነው» በማለት ገልፀዋል።
በተለይ አዲስ አበባ ከተማ በሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችና የሴቶች ጥቃት ፖሊሶችና የሕግ ተርጓሚዎች ተገቢዉን ድጋፍ እንደማያደርጉ ይባስ ብለዉም ወንጀሉን የሚያባብሱ ተግባራት እንደሚፈጽሙ ተገለጸ።
ከአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ፣ ሞሮኮ፣ ለኃይል ምንጭ ፣ ከነዳጅት ዘይት ይልቅ ለፀሐይ ሙቀትና ብርሃን የላቀ ግምት የሰጠችበት እንቅሥቃሤ በአወንታዊነት ሲጠቀስ፣ ዩጋንዳ ለተፈጥሮ ተስማሚ ነው ያለችውን በኤሌክትሪክ የሚሽከረከር አውቶሞቢል መሥራት ብቻ
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ቅዳሜ በአል-ማካ የወደብ ከተማ አካባቢ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ መስመጧን እና 70 ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን የየመን አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገፁ አስታውቆ ነበር። ይህ መረጃ እስካሁን አልተረጋገጠም
የዛሬ አምስት ዓመት ኮፐንሃገን የተካሄደዉ የአየር ንብረት ለዉጥ ጉባኤ ብዙ ተብሎለትና ብዙ ተጠብቆበት ካለ ዉጤት መጠናቀቁ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ብቻ ሳይሆን ተስፋም ያስቆረጠ መስሎ ነበር።
ድርጅቱ ቀደም ሲል ሆስፒታሉን አዲስ አበባ ዉስጥ ለመገንባት ጥያቄ ቢያቀርብም የከተማይቱ መስተዳድር ለሆስፒታሉ ማስገንቢያ የሚሆን መሬት ባለመፍቀዱ ትግራይ ዉስጥ ለማስገንባት ወስኗል።
ፈረንሳይ በሚኖሩ አይሁዶች በሚታየው ዘረኝነት እና በሚፈፀምባቸው ጥቃት አንፃር በርካታ ሰዎች ባለፈው እሁድ በፓሪስ አቅራቢያ በምትገኘው ክሬቴይ ሰልፍ ወጥተዋል።አይሁዶች ሀብታሞች ናቸው የሚል የቆየ አነጋገር እንዳለ ይሰማል። ይኸው አነጋገርም ዛሬም ድረስ ብዙ ጠላት አፍርቶባቸዋል።
ትናንት በተጀመረዉ ሥብሰባ ላይ የአፍሪቃ መንግሥታት ፍርድ ቤቱ ከዓለም አቀፍነቱ ይልቅ አፍሪቃዉያንን ለመክሰስና ለመቅጣት ያለመ ነዉ በማለት ወቅሰዉታል። ፍርድ ቤቱ ከተመሠረተ ጀምሮ የከሰሳቸዉ ወይም የቀጣቸዉ በሙሉ አፍሪቃዉያን ፖለቲከኞች ናቸዉ።
የዘጠና አመቱ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የዛኑ ፒ.ኤፍ. መሪ ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል። የፕሬዝዳንቱ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤም በፓርቲው የሴቶች ክንፍ መሪ በመሆን ወደ ፖለቲካው መቀላቀላቸው ይፋ ሆኗል።
አሳካሪ-እና ግልፅ ያልሆነ ፖለቲካ።ለአዲስ አበባ በርግጥ እንግዳ አይደለም።ጥንት እንደ ቅዳሜዉ ነበረች።የዛሬ አርባ አመት የጥንት ሥርዓቷ መለወጡ በታወጀ፤ ያለምንም ደም የኢትዮጵያ እንከን እንዲወድም በተዘመረባት ማግስትም በደም ኩሬ ተነከረች።በ1983 ያቺ ጉደኛ ከተማ የሠላም፤ ዲሞክራሲን ጉዞ መጀመሯ ተነግሮባት ሳያበቃ በሌላ ደም ጨቀየች።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ ቅዳሜ ዕለት የመጀመሪያውን ሽንፈት ቀምሷል። በጆሴ ሞሪንሆ የሚመራው ቸልሲን ጉድ ያደረገው በ7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኒውካስል ዩናይትድ ነው። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ባየር ሙይንሽን እየመራ ነው፤ ዶርትሙንድ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ተደጋጋሚ ሽንፈት ለምን?
ዘጠነኛዉ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንና እና ሕገ መንግሥቱ የፀደቀበት 20ኛ ዓመት ዛሬ በቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ ላይ መከበሩ ተገለፀ።
የዩኤስ አሜሪካ ፖሊስ ያልታጠቀ ጥቁሮች ላይ ያደረሰዉን ግድያ ተከትሎ በዩኤስ አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች የጀመረዉ ተቃዉሞ በሳምንቱ መጨረሻ በበርካታ ከተሞች እጅግ ጎልቶ መታየቱ ተነግሮአል።
በበርካታ አጫጭር እና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በትወና ተሳትፏል። በተለይ በቅርቡ በቴሌቪዥን በተላለፈው የ«ሰው ለሰው» ተከታታይ ድራማ እና አሁን በመታየት ባለው «ሞጋቾቹ» ድራማ ይታወቃል። መንፈሣዊ ዜማዎቹም በኢንተርኔት እና በሲዲ ተሰራጭተዋል።