ካህናቱ እና ምእመናኑ ሀገረ ስብከቱን በሰልፍ ለመጠየቅ እየመከሩ ነው የአለቃው ጣልቃ ገብነት ሙዳየ ምጽዋቱ በወቅቱ እንዳይቆጠር አድርጓል “ሀገረ ስብከቱ ለቤተ ክርስቲያናችን ችግር ግድ እንደሌለው አሳይቶናል” /ምእመናኑ/ (ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅጽ 03 ቁጥር 121፤ ቅዳሜ መስከረም 22 ቀን 2008 ዓ.ም.) በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አባላትና ምእመናን፤ ከአስተዳደርና ከአሠራር ጋር በተያያዙ …

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ጥንታውያን እኅት አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። የኹለቱ ግንኙነት ሃይማኖታዊ እና ተፈጥሯዊ ነው። ሃይማኖታዊ ትስስሩ ከኹለት ሺሕ ዓመት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረ ነው። በተፈጥሮ ያለው ግንኙነት ደግሞ የዓባይ ወንዝ መፍሰስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ያለ ነው። ይኸው የሁለቱ እኅት አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ …

  click here for pdf
ክፍል አንድ

በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ምእመናን ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙባቸው ከእግዚአብሔር ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡(2ኛ ነገሥት 5፤ ዮሐ. 5፣ዮሐ. 9)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ውስጥ በልዩ ልዩ ገድላተ ቅዱሳን ላይ እንደምናነበው በጠበል ሕዝቡን ሲፈውስ ኖሯል፡፡ ሕዝብ ፈውስ የሚያገኝባቸው እንደ ሰሊሆምና እንደ ቤተ ሳይዳ የታወቁ የቃል ኪዳን ቦታዎችም ነበሩ፡፡
አሁን በያዝነው ዘመን አያሌ ‹አጥማቂ> የሚባሉ ሰዎች ተነሥተዋል፡፡ ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፣ መቁጠሪያ ይሸጣሉ፣ ቅባት ይቀባሉ፣ አዳራሽ ከፍተው ወይም ሕዝብ በሜዳ ሰብስበው እንፈውሳለን ይላሉ፤ ሰይጣን ተናገረ የሚባለውን በካሴት ቀድተው ይሸጣሉ፡፡ ከዚህ ቀጥዬ በማቀርባቸው አሥር ምክንያቶች እነዚህን ሐሳውያን መቀበል የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡

1.      በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት፣ ክህነታዊ ሕይወት፣ የጸሎት ሕይወት ወይም ሌላ አንዳች ተጋድሎ ሳይኖረው ማጥመቅ ብቻ ሥራው የነበረ ክርስቲያን የለም፡፡ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች የሌላው መንፈሳዊ ሕይወታቸው ውጤት ወይም ነጸብራቅ ነበር እንጂ ሥራቸው እየዞሩ ማጥመቅ አልነበረም፡፡ የሐዋርያት ሥራን ብናነብ ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ሲሠማሩ በአንድ በኩል አሕዛብን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት በሌላ በኩል የአንደበት ትምህርታቸውን በእጃቸው ተአምር ለማጽናት  ተአምራትን ያደርጉ ነበር እንጂ በአንድ ከተማ ውስጥ ሲያጠመቁ ውለው ያደሩበት፣ ወይም ከወንጌል አገልግሎት ተለይተው አጥማቂ ብቻ የሆኑበት፣ ወይም ደግሞ በዚህ ቦታ ፈውስ እንሰጣለንና ተሰብሰቡ ብለው ያስነገሩበት አንድም ማስረጃ የለም፡፡ በገድለ ቅዱሳንም ቅዱሳን ጸጋ እግዚአብሔር ሲያድርባቸው፣ ሥጋቸውንና ሰይጣንን ድል ሲነሡ፣ በክርስትናቸው ሲበስሉ ተአምራት ይከተሏቸዋል እንጂ እንዲሁ ማጥመቅና መፈወስ ብቻ ሕይወቱ የነበረ ቅዱስ የለም፡፡ ሰው ያለ ተጋድሎ እንዴት ጸጋ ያገኛል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ከተራ ሰዎች የተለየ መንፈሳዊ ሕይወት የሌላቸው ሁሉ እየተነሡ አጥማቂ ሊሆኑ የቻሉበት አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡
2.     በገድለ ቅዱሳን ውስጥ ቅዱሳን በገዳማዊ ሕይወት፣ በሰማዕትነት፣ በክህነታዊ አገልግሎት ሲሠማሩ እግዚአብሔር ምእመናንን ለመጥቀም ወይም ክብረ ቅዱሳንን ለመግለጥ በእነርሱ ላይ ተአምራትን ያደርጋል፡፡ እነርሱ ግን ይህ ክብር እንዳይገለጥባቸው ሲሸሹ፣ እኔ አላደረግኩም ሲሉ ወይም ስለራሳቸው ደካማነት ሲነገሩ እናያለን እንጂ ‹ኑ እንፈውሳችኋላን› ብለው ዐዋጅ ሲናገሩ አይተንም፣ አንብበንም አናውቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ወጥተው ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ  ገዳም የሄዱበት ዋናው ምክንያት በገዳሙ እያሉ በፈወሱት አንድ በሽተኛ ምክንያት ስማቸው ከፍ በማለቱ፣ ብዙ ሰዎችም በመሰብሰባቸው የተነሣ ነው፡፡ ታላቁ አባት መቃርዮስ ገዳሙን ትቶ ወደ አንዲት መንደር መጥቶ የኖረው በገዳሙ ክብሩ በመገለጡና ተአምራቱ በመታየታቸው ከከንቱ ውዳሴ ለማምለጥ ነበር፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው አካባቢውን ትቶ የጠፋው ተአምር አድራጊነቱ በመታወቁ ምክንያት ነበር፡፡ አሁን ግን ከዚህ በተቃራኒው ሰዎች እናጠምቃለን፣እንፈውሳለን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩበት፣ ካሴት የሚሸጡበት፣ ፖስተር የሚሰቅሉበት ዘመን ነው፡፡
3.      ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ማን እንደሆነ፣ ድንግል ማርያም ማን እንደሆነች፣ ቅዱሳን መላእክት ማን እንደሆኑ ሌሎቹም ቅዱሳን ማን እንደሆኑ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰዎች ሰጥታ አታውቅም፡፡ ቅዱሳንን ከፈጣሪ አስበልጣ አታወቅም፡፡ የቅዱሳን መገኛና መሠረት በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑን ታምናለች፣ታስተምርማለች፡፡ ለእግዚአብሔር የማይቻል ለቅዱሳን ይቻላል፣ በእግዚአብሔር የማይሠራ በቅዱሳን ይሠራል ብላ አታምንም፣ አታስተምርም፡፡ በዘመኑ አጥማቂዎች ዘንድ የምናየው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ በክርስቶስ ስም የማይወጣው ሰይጣን የቅዱስ ሚካኤልን ስም ሲጠሩበት ይወጣል፡፡ በክርስቶስ ስም የሚያሾፍ ሰይጣን የድንግል ማርያምን ስም ሲጠሩበት ተቃጠልኩ ይላል፡፡  ይኼ ፈጽሞ ክህደት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንም ትምህርት አይደለም፡፡ ‹‹በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ›› ብላ ያስተማረች ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹በክርስቶስ ስም አንወጣም፣ በማርያም ስም ግን እንወጣለን›› እያለ አጋንንት ወጣ የሚል ትምህርት ማስፋፋት ክህደት ነው፡፡
4.     መቁጠሪያ በቤተ ክርስቲያናችን ለጸሎት መቀስቀሻና ማስታኮቻ የሚውል ነው፡፡ ምእመናን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ፣ በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ፣ ኪርኤ አላይሶን የተባሉትን የምሕላ ጸሎቶች በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተመደበላቸውን ቁጥር ሳይስቱ እንዲጸልዩ የተሠራ ሥርዓት ነው፡፡ በጸሎት ጊዜ ዝንጋኤ እንዳይገጥማቸው ኅሊናቸውን ለመሰብሰብም ይረዳል፡፡ አንድ ቅዱስ ለብዙ ዘመን የጸለየበት መቁጠሪያ፣ የተደገፈበት መቋሚያ፣ የቆመበት ምድር፣ የለበሰው ልብስ፣ የተጠቀመበት መጽሐፍ ተአምራት ቢያደርግ አይገርምም፡፡ ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸውም ለልብሳቸው፣ የልብሳቸው ለጥላቸው ተርፎ አይተን እናውቃለንና(የሐዋ. 5፣12-17፤ 19፣ 11-12)ከዚህ ውጭ ግን የሚሸጥ መቁጠሪያ ሰይጣን የሚያስወጣበት፣ ሰው ራሱን በመቁጠሪያ ስለደበደበ ከዲያብሎስ እሥራት የሚፈታበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሰይጣን በጾምና በጸሎት እንጂ በመቁጠሪያ ድብደባ አይለቅም(ማቴ.17፣21)፡፡ ያ መቁጠሪያ ተአምር የሚሠራ ቢሆን እንኳን አንድ ቅዱስ የተጋደለበት፣ ከዚያ ቅዱስም በረከት ያተረፈ መሆን አለበት፡፡ ልክ የቅዱስ ጳውሎስ የጨርቁ እራፊ ይፈውስ እንደነበረው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም የትኛውም አባት መቁጠሪያ ሲያድልና በመቁጠሪያ ሰይጣን ታወጣላችሁ ብሎ ሲያስተምር አልታየም፡፡
5.      ጌታችን በሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አስተምሯል፡፡ በጌንሳሬጥ ምድር አምስት ሺ(ማቴ 1413-21)፣ በገሊላ ባሕር አጠገብ አራት ሺ(ማቴ 15፣32-39)፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይቶ ይኼድ ነበር እንጂ ሰይጣን አድሮበት በአንድ ጊዜ የጅምላ ጩኸት ሲጮህ ታይቶ አይታወቅም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ግን እየቀረቡ ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ አግኝተዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢሆን መድኃኒት ያደረገብሽ፣ ድግምት ያስደገመብህ፣ መተት ያስመተተብህ እገሌ ነው የሚል ሰይጣን አልተሰማም፡፡ ዛሬ ግን በአንድ ቦታ ለጥምቀት የሚሰበሰቡ ሰዎች አብዛኞቹ ይጮኻሉ፡፡ ሁሉም በሰይጣን ተይዘዋል ይባላሉ፣ ሁሉም ድግምት፣ መተት፣ መድኃኒት፣ ጥንቆላ እንደተደረገባቸው ይነገራቸዋል፡፡ ሰይጣንን አምነው ከባሎቻቸው፣ ከሚስቶቻቸው፣ ከእኅት ወንድሞቻቸው፣ ከጎረቤቶቻች፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ይጣላሉ፡፡ ከባቴ አበሳነትን ፈጽሞ የረሳ፣ ከፍቅር ይልቅ ጠላትነትን ለማስፈን የመጣ፣ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነው ከመፋቀር ይልቅ ሰይጣንን አምነው እንዲጣሉ የሚያደርግ የሰይጣን አሠራር ነው፡፡ ለመሆኑ ይህንን ሁሉ ሕዝብ ሰይጣን ሲቆጣጠረው ክርስቶስ የለምን? የተጠመቅነው የልጅነት ጥምቀት፣ የቆረብነውስ ቁርባን አይሠራምን? ገና ወደ ክርስትና ያልመጡ የገሊላ ክርስቲያኖች እንኳን በጩኸት አልተደበላለቁም እንኳን እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ የተባልነው፡፡ ይህ አሠራር የክርስቶስን ነገረ ድኅነት የሚፃረርና ከማዳን ሥራውም የወጣ ነው፡፡ ከክርስቶስ ክብርና ኃይል ይልቅ የሰይጣንን ኃይል ለማሳየት የሚሠራም ነው፡፡  
6.     ለመሆኑ ስመ እግዚአብሔርን የሚጠራ ሁሉ ትክክለኛ ነውን? አንዳንድ ምእመናን እንዲህ ይላሉ ‹እግዚአብሔርን ይጠራሉ፣ እመቤታችንንም ያከብራሉ››፡፡ ልክ ነው ሰይጣን ለአመሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል ይባላል፡፡ ሰይጣን ምንም እንኳ የሐሰት አባቷ ቢሆንም (ዮሐ. 8፣44) ሙሉ ውሸት ግን አይናገርም፡፡ በከፊል እንጂ፡፡ ሔዋንን ‹ንግሥተ ሰማይ ወምድር› ሲላት ከፍሎ ነው የዋሻት፡፡ ንግሥተ ምድር ናት፤ ንግሥተ ሰማይ ግን አልነበረቺም፡፡ በወንጌል ውስጥ አጋንንት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ያውቃሉ፡፡ ሰይጣን ጌታን ሲፈትነው ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሶ ነው(ማቴ 4)፤ ጌታችን በጌርጌሴኖን ያገኛቸው አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ‹የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ› ብለው ነበር የተናገሩት፡፡ ንግግራቸው ልክ ነው፡፡ እነርሱ ግን አጋንንት ናቸው፡፡ ጌታም አስወጣቸው እንጂ ማን ድግምት እንዳደረገባቸው አላናዘዛቸውም፡፡ በሌላ ቦታም በምኩራብ ሲያስተምር አንድ ሰይጣን ያደረበትን ሰው አመጡለት፡፡ ሰይጣኑም ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ‹ ብሎ ነበር የጠራው፡፡ ጌታ ግን ‹ዝም ብለህ ወጣ› አለው እንጂ መድኃኒት ማን እንዳደረገ ተናገር አላለውም(ማር. 1፣21-28)፡፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ ስላለውም ሰይጣንነቱን አልቀየረውም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስተምር ፊልጵስዩስ የተባለ ከተማ ደረሰ፡፡ በዚያም አንዲት በርኩስ መንፈስ የተያዘች ሴት እየተከተለቺው ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው›› አለች፡፡ ሴትዮዋ የተናገረቺው ምንም ስሕተት የለውም፡፡ እነ ቅዱስ ጳውሎስ የመዳንን መንገድ ያስተምራሉ፡፡ የልዑል አምላክ ባሪያዎችም ናቸው፡፡ ይህ ትክክል ስለሆነ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ዝም አላለም፡፡ መንፈሱን አስወጣው እንጂ(የሐዋ.16፣16-18)፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚነግሩን አንድ ሰው ስመ እግዚአብሔርን ወይም ስመ ቅዱሳንን ስለጠራ ብቻ ትክክል መሆኑን እንደማያሳይ ነው፡፡ እርስ በርሱ የማይጣረስ ርቱዕ የሆነ እምነትም ያስፈልገዋል፡፡ ርቱዕ የሆነ ሕይወትም ያሻዋል፡፡ በክርስትና አንድ ሰው መንገዱ ትክክል ሳይሆን ውጤቱ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ያለ ትክክለኛ እምነት፣ ያለ ትክክለኛም መንፈሳዊ ሕይወት ትክክለኛ ተአምራት ሊኖረው አይችልም፡፡ በሲኦል በኩል ወደ ገነት ሊገባ አይችልምና፡፡  
7.     ተአምራት ማድረግ ብቻውን የቅድስና ማሳያ አይደለም፡፡ ተአምራት ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት ሲመነጩ እንጂ፡፡ ተአምር ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት የመጣ ሲሆን ‹ስም በመንግሥተ ሰማያት በመጻፉ እንጂ በድንቅ ነገር ማንም ደስ አይለውም››(ሉቃ. 10፣ 17-20)፡፡ ተአምራትን ሲከተሉ መኖርም የአሕዛብነት ምልክት እንጂ የክርስትና ምልክት አይደለም(ማቴ. 12፣ 39)፡፡ የክርስትና ዋና መሠረቱ ክርስቲያናዊ ትምህርት፣ ክርስቲያናዊ እምነትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ናቸው፡፡ አንዳንዶች በማርቆስ ወንጌል መጨረሻ ላይ(ማር 16) ‹‹ያመኑት እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል›› የሚለውን ይጠቅሳሉ፡፡ እዚህ ላይ ያመኑት የተባሉት ‹የበቁት› ማለት ነው፡፡ ያማ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም ተአምር ስናደርግ መኖራችን ነበር፡፡ አምነናልና፡፡ ደግሞም ያመኑት የሚለው ለሁላችንም ይሠራል ካልን እስኪ መርዝ ጠጥተን ምንም ሳንሆን ፣እባብም ጨብጠን ስንተርፍ እንየው፡፡ ይህ ሁሉ ግን በእመነት ለበሰሉ የሚቻል ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራም በሐዋርያት እጅ ያመኑት ሁሉ ተአምር ሲሠሩ አናይም፡፡ በሐዋርያት ሥራ ድንቅ ሲሠሩ የምናያቸው ክርስቲያኖችም በጸሎት የተጉ፣ በሐዋርያነት አገልግሎት ሰማዕትነት የከፈሉ፣ በገድል የተቀጠቀጡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ ሕይወቱ በተአምራት ከመገለጡ በፊት በሱባኤ የተወሰነ ነበረ(የሐዋ. 13፣ 1-3) የዛሬ አጥማቂዎች ግን ማጥመቅ ፕሮፌሽናቸው እንጂ የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መገለጫ አይደለም፡፡ እንዲህ ባለው ገዳም በገድል የኖሩ፣ እንዲህ ያለ መሥዋዕትነት ለክርስትና የከፈሉ ወይም ለምእመናን አርአያ የሚሆን እንዲህ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የነበራቸው ናቸው ተብሎ የማይመሰከርላቸው ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ ናቸው፡፡
8.     የሰይጣን ምትሐትም አለ፡፡ የሙሴ ጸጋና ሕይወት ድል እንዲሆኑ ባያደርጋቸው ኖሮ የፈርዖን ጠንቋዮች ብዙ አስደናቂ ነገር ሠርተው ነበር(ዘጸ. 7፣8- 13)፡፡ በዘመነ ሳዖል የነበረቺው ሟርተኛም የሙታንን መንፈሶች ትጠራ ነበር(1ኛ ነገሥት. 28፣ 8-24)፡፡ አይሁድም አጋንንትን ያወጡ ነበር(የሐዋ. 19፣13)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የሐሳዊ መሲሕን አመጣጥ ሲያስተምረን ‹‹የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች፣ በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመጽም ማታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው›› ይላል (1ኛ ተሰ. 2፣9)፡፡ ይህም  ከመንፈሳዊ ብቃት የማይመጣ ተአምር፣ ድንቅና ምልክት ምንጩ ከሰይጣን እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡ ዛሬ በእነዚህ ይህንን ያህል የምንታለል ከሆነ ነገ ሐሳዊ መሲሕ ከዚህ የሚበልጡ አስደናቂ ተአምራትን ሲያደርግ ጨልጠን ገርኝተን መከተላችን የማይቀር ነው፡፡ ‹‹የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ›› ተብሏልና፡፡
9.      ምሥጢረ ቀንዲል መሠረቱን መጽሐፍ ቅዱስ ያደረገ(ያዕቆብ. 5፣13) ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የሚፈጸመው በካህናት ሲሆን የራሱ የሆነ የጸሎትና የመቀባት ሥርዓት አለው፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ምሥጢረ ቀንዲልን ማንበብ ይጠቅማል፡፡ አሁን የምናየው ግን በጀሪካል ቅባት ይዞ ማከፋፈል፣ ምእመናን ከአጥማቂዎች ‹ቅብዐ ቅዱስ› ወስደው እንዲጠጡና እንዲቀቡ ማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያልነበረ፣ በምሥጢረ ቀንዲል ያልተፈቀደና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ የሌለ ነው፡፡ አንዳንድ አጥማቂዎችም ‹‹ከኢየሩሳሌም የመጣ ነው›› ይላሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የሚመጣ የተለየ ቅባት የለም፡፡ አንድን ቅባት ቅዱስ የሚያደርገው ጸሎቱና ሥርዓቱ አንጂ የተሠራበት ከተማ አይደለም፡፡ ኢየሩሳሌም ውስጥ ግሪክ ኦርቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች፣ የይሖዋ ምስክሮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ሌሎችም አሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የመጣ ማለት ከየት የመጣ ነው? ምእመናን ለኢየሩሳሌም በጎ ኅሊና ስላላቸው ‹‹ከኢየሩሳሌም ተባርኮ የመጣ ›› ይባላል፡፡ ማን ባረከው? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡፡
10.    ከአክባሪው ይልቅ ከባሪው፣ከሰጭው ይልቅ ተቀባዩ፣ከጌታው ይልቅ አገልጋዩ የሚከብርበት ሥራ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው እግዚአብሔርን ማክበር፣ አሕዛብም እግዚአብሔርን እንዲያውቁ ማድረግ፣ ከመንገድ ጠራጊውም ይልቅ መንገዱን እንዲያገኙት ማስቻል ነው፡፡ አሁን የምናያቸው ‹አጥማቂዎች› እና ‹ተአምራት› አድራጊዎች ግን ራሳቸውን የሚያከብሩ፣ እግዚአብሔርን የሚሸፍኑ፣ ሕዝቡ ቅዳሴና ትምህርት እየተወ እነርሱን በየሜዳው እንዲከተል የሚደርጉ፣ ሕዝቡ ንስሐ መግባት፣ ሥጋወ ደሙ ከመቀበል ይልቅ የእነርሱ አድናቂና ካዳሚ እንዲሆን የሚስቡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ስለ ራሱ ሲናገር ‹እኔ ዝቅ ዝቅ ልል፣ እርሱም ከፍ ከፍ ሊል ይገባል›. ነበር ያለው (ዮሐ. 3፣29)፡፡ ለእነ ቅዱስ ጳውሎስም በልስጥራ እግሩ የሰለለውን ሰው በፈወሰው ጊዜ ሕዝቡ ተደንቆ  እንደ አምላክ ሊሠዉላቸው ወድደው ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ‹እንደ እናንተ ሰዎች ነን›. እያለ ለምኖ አስተዋቸው፡፡ ሕዝቡንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መለሳቸው፤ የእግዚአብሔርም ስም እንዲከብር አደረገ(የሐዋ 14፣8-18)፡፡
በእነዚህና ቤሎችም ምክንያቶች በዘመናችን የተነሡትን ‹አጥማቂ ነን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩትን፣ መቁጠሪያና ቅብዐ ቅዱስ የሚያከፋፍሉትን፣ በየሜዳው ሕዝብ ሰብስበው ምትሐት የሚሠሩትን ሰዎች መቀበል አለብን ብዬ አላምንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የጸጋው ግምጃ ቤት ናት፡፡ በጸሎት የሚተጉ፣በእምነት ሕይወት ያሉ ክርስቲያኖች በየምሕረት አደባባዮች ምሕረትን ያገኛሉ፡፡ በቤተ ሳይዳ መልአኩ ውኃውን ይባርከው እንደነበር ሁሉ የጠበል ቦታዎችን ራሱ እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ባርኳቸዋል፡፡ የተለየ አጥማቂ አያስፈልገቸውም፡፡ የክህነት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው እንጂ፡፡ ደግሞም ሁሉም ሕመም መዳን የለበትም፡፡ ደዌ ዘእሴት(ለበጎ የሚሰጥ ሕመም) አለ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የብዙዎችን ሰይጣን እያስወጣ እርሱን ግን የሚጎስመው ሰይጣን ነበረው፡፡ ጌታን ሲለምንም ‹‹ተወው›› ነው የተባለው(2ኛቆሮ. 12፣ 7)፡፡ የዛሬ አጥማቂ ነን ባዮች ግን ሁሉም ሕመም ይድናል ይላሉ፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ ያልተቻለ ተቻላቸውን? ከሐዋርያት አንዱ የነገረው ያዕቆብ እግረ በሽተኛ ነበር(ዜና ሐዋርያት፣ በእንተ ያዕቆብ ሐዋርያ)፤ እርሱ ግን ብዙዎችን ይፈውስ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ምሕረት አገኘን የምንለውም ስንፈወስ ብቻ መሆን የለበትም፤ የምንታገሥበት ዐቅም ስናገኝም ጭምር እንጂ፡፡ ልመናችንም ለፈውስ ብቻ ሳይሆን ለመታገሥ ዐቅም እንዲሰጠን መሆንም አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ለመፈውስ የሚችል ቢሆንም ሁሉንም ግን አይፈውስም፡፡ ለበረከት፣ ለተግሣጽ፣ ከከንቱ ውዳሴና ከትዕቢት ለመከላከል የሚፈቅደው ደዌም አለ፡፡ ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ይህ ተሰጥቶት ነበር(ዘፍ. 32፣31)፡፡ ክርስትና በመንፈሳዊ ሕይወት በመኖር፣ በንስሐ መንገድ በመመላለስ፣ በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በመሳተፍ እንጂ በድንቅና በተአምራት የሚኖር አይደለም፡፡
አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ‹‹ገንዘብ ይሰበስባሉ፣ ገቢ ያስገኛሉ›› ብለው እነዚህን ሐሳውያን እንደሚደግፉ ይታወቃል፡፡ ምእመናንም ‹‹ታድያ አቡነ እገሌ ለምን ፈቀዱ›› ይላሉ፡፡ እኛ ግን መሠረት ማድረግ ያለብን የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ታሪከ ቤተ ክርስቲያንን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ማንም ከዚህ የወጣ ቢኖር ትምህርቱን ለመቀበል አንገደድም፡፡ ታላቅነት በእምነት እንጂ በሥልጣን አይገኝምና፡፡ ታላቁ አባት ዲዮስቆሮስ በ451 ዓም የኬልቄዶን ጉባኤ የልዮንን የሁለት ባሕርይ ትምህርት አልቀበል ሲል የሮም ባለ ሥልጣናት ‹‹እርሱኮ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የተቀመጠ የሮም ፖፕ ነውና አለቃህ ነው›› ባሉት ጊዜ ‹‹ሰይጣንም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበረ›› ብሎ ነው የመለሰላቸው፡፡
ሳንድያጎ፣ ካሊፎርንያ

፻፲፰ኛው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ወዳጃዊ ጥሪ መሠረት ባለፈው ፳፻፯ ዓ.ም.፣ ከጥር ፩ – ፯ ቀን ድረስ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ …


click here for pdf

አሁን ባለንበት ዘመን ያለን የኢትዮጵያ ትውልድ የሀገራችንን ታሪክ፣ የሕዝቦች የእርስ በርስ ግንኙነትና የመሪዎቻችንን ሁኔታ ስንነጋገርና ስንጽፍ በአብዛኛው አሉታዊውን ነገር ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ፣ ጥላቻ እንዲበቅል፣ ቂም እድሜ እንዲያገኝ፣ ልዩነት እንዲሰፋ፣ ጠብም ሥር እንዲሰድ በማድረግ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ይታያል፡፡ ርግጥ ነው በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ የመስተጋብር ችግሮች ሁሉ በኛም ሀገር ተፈጥረዋል፡፡ በኛ ሀገር የተፈጠሩትም በሌሎች ይገኛሉ፡፡ በዓለም ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ የኩራትም የውርደትም፣ የፍቅርም የጠብም፣ የሰላምም የጦርነትም፣ የእኩልነትም የጭቆናም፣ የመረዳዳትም የመጠፋፋትም፣ የሥልጣኔም የስይጣኔም ታሪኮች አሉ፡፡ እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖሩ የተለያየ ዘውግ፣ ቋንቋ፣ እምነትና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ቀርተው በተመሳሳይ ቋንቋ፣ ባሕልና የኑሮ ደረጃ የሚገኝ የአንዲት ሀገር አንድ ወጥ ሕዝብ እንኳን በውስጡ ጽጌረዳም እሾህም አለው፡፡ 

የሚገርመው ነገር ኢትዮጵያን ከዓለም የተለየች የሚያደርጋት ምን እንደሆነ አለመታወቁ ነው፡፡ ኢትዮጵያኮ ሲኦልም አልነበረችም መንግሥተ ሰማያትም አልነበረችም፡፡ ሀገር ነበረች፣ አሁንም ሀገር ነች፡፡ ሀገር የሚገጥማት ፈተና ሁሉ ገጥሟታል፤ ሀገር የሚኖራት ጸጋ ሁሉ ታድሏታል፡፡ በአንዳንድ የታሪክ ምእራፏ ለመንግሥተ ሰማያት ጠጋ፣ በሌላው ምእራፏ ደግሞ ለሲኦል ጠጋ ብላ ይሆናል እንጂ፣ ፈጽማ ሲኦልና መንግሥተ ሰማያት ሆና አታውቅም፡፡ እኛ ልጆቿ ግን ወደ መንግሥተ ሰማያት ጠጋ ማለት ብቻ ሳይሆን ምድራዊት መንግሥተ ሰማያት ብትሆንልን እንወዳለን፤ ለዚያም እንሠራለን፡፡ ወደዚያ በተጠጋችበት ታሪክም እንኮራለን፤ ወደ ሲኦል ለመውረድ አዘንብላ የነበረችበትንም ዘመን ስናስብ በልብ ስብራት እንመታለን፡፡
የታሪክ ሂደት ያመጣቸውን የትናንት ነገሮች ዛሬ አንቀይራቸውም፡፡ ሆነዋልና፡፡ ነገር ግን እንማርባቸዋለን፤ ከትናንት ወስደንም ለዛሬ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ የዛሬ ማንነታችን መገንቢያም እናደርጋቸዋለን፡፡ በተቃራኒውም ያለፉትን ዘመናት ጠባሳዎች እየነካካን ቂምን ማመርቀዝ፣ ጥላቻን ማጎንቆል፣ ልዩነትን ማስፋት፣ ፍቅርንም ማደብዘዝ እንችላለን፡፡ ሁለቱም በእኛ ምርጫ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ምርጫው ለእህሉ ወይስ ለአረሙ ትለፋለታለህ? የሚለው ነው፡፡ 
ታሪካቸውን ለዕድገታቸውና ለሰላማዊ መስተጋብራቸው የተጠቀሙት ግን ከአረሙ ይልቅ ለእህሉ ጊዜና ጉልበታቸውን ያፈሰሱት ናቸው፡፡ ገበሬ ዓመት በሙሉ የሚለፋው አረም ለማብቀል አይደለም፡፡ አረም ለመብቀል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ ጉልጓሎ፣ አያስፈልገውም፡፡ ወንፈልና ደቦ አይሰበስብም፡፡ ጉልበትና ጊዜውን አያባክንም፣ ወዝና ላቡን አያንጠፈጥፍም፡፡ ለአረም አንድ ነገር በቂ ነው፡፡ ስንፍና ብቻ፡፡ ገበሬ ከሰነፈ ምንም ሳይደክም አረም እርሻውን ከዳር ዳር ይወርስለታል፡፡ በሬ ሳይጠምድ፣ እርሻ ሳይውል፣ ሌሊት ሳይነሣ፣ ማታ ሳይገባ፣ ዝናብ ሳይመታው፣ ፀሐይ ሳይከካው፣ ብርድ ሳይገርፈው፣ ወላፈን ሳይጠብሰው አረም እንዲሁ ይበቅልለታል፡፡ ገበሬ ለአረም አይለፋም፡፡
የገበሬን ጥበብ፣ የገበሬን ድካም፣ የገበሬን ጉልበት፣ የገበሬን ማዳበሪያ፣ የገበሬን ትዕግሥት፣ የገበሬን ሐሞት፣ የገበሬን ልምድ፣ የገበሬን  ጊዜ፣ የሚፈልገው እህሉ ነው፡፡ ወንፈልና ደቦ የሚሰበስበው ለእህሉ ሲል ነው፡፡ በሬ የሚጠምደው፣ ሞፈር የሚቆርጠው፣ ቀንበር የሚነድለው፣ ጎተራ የሚያዘጋጀው፣ አውድማ የሚለቅልቀው ለእህሉ ሲል ነው፡፡ አረም በስንፍና የሚበቅለውን ያህል እህል የሚበቅለው በጉብዝና ነው፡፡ እህል ያለ ገበሬው ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ጉልበትና መሣሪያ ከምድር አይወለድም፡፡ አረም ግን አዋላጅ አይፈልግም፡፡ አረም በራ ተወልዶ በራሱ ያድጋል፡፡   
በታሪክ መስክ ላይ የተሠማራ ትውልድም ጊዜውን ማጥፋት፣ ጉልበቱን መሠዋት፣ ጥበቡን ማፍሰስ፣ ዕውቀቱን መከስከስ፣ ያለበት ለአረሙ አይደለም፡፡ ጥላቻው፣ ቂም በቀሉ፣ መቆራቆሱ፣ መናከሱ፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ይኼ የትውልድ አረም ነው፡፡ በስንፍና ብቻ ሊበቅል የሚችል፡፡ በታሪካችን ውስጥ በቅሎ የነበረው እህል ፍቅራችን ነበረ፣ አንድነታችን ነበረ፣ መዋለዳችን ነበረ፤ መዋሐዳችን ነበረ፤ ሥልጣኔያችን ነበረ፤ ጀግንነታችን ነበረ፤ ነጻነታችን ነበረ፡፡ ትኩረታችንን እህሉ ላይ ካደረግነው አረሙን እንቋቋመዋለን፡፡ መቋቋምም ብቻ ሳይሆን እናጠፋዋለን፡፡ አረሙን ማጥፋት ያለብን አረም ስላልነበረ አይደለም፣ አረምን ለመሸፋፈን ሲባልም አይደለም፡፡ አረም ስለማይጠቅመን ነው፡፡ በሀገራችን እንክርዳድ የተሰኘው አረም ሳይለቀም ቀርቶ ከስንዴ ጋር ገብቶ ጠላ የሆነ እንደሆነ ያሳብዳል፡፡ ለዚህም ነው፡-
እንክርዳድ እንክርዳድ የተንከረደደ
ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ
የተባለው፡፡
አሁን አሁን በሀገራችን ጉልበት እየጨረስን ያለነው አረሙን ለማብቀል ይመስላል፡፡ አንዲት ጽጌረዳን ከማብቀልና ፈንድታ አበባዋ ሠፈሩን እንዲያውድ ከማድረግ ይልቅ አንድ ማሳ ሙሉ አረም ማብቀል በጣም ቀላል ነው፡፡ አረሙ ስንፍናን ብቻ ይጠይቃልና፡፤ ጽጌረዳዋን ለማብቀል ግን ከመሬቱ፣ ከሰማዩ፣ ከአየሩ፣ ከአራዊቱ፣ ከአላፊ አግዳሚው ጋር መጋደልን ይጠይቃል፡፡  
በታሪካችን ውስጥ የነበረውን እህል ዘሩን አምጥተን መዝራት፣ ዘርተን መከባከብ፣ ተከባክበንም ማሳደግ ይገባን ነበረ፡፡ ጥበባችንን፣ ዕውቀታችን፣ ገንዘባችንንና ጉልበታችንን ለእርሱ ማፍሰስ ይገባን ነበረ፡፡ አሁን ግን ድርሰቶቻችንን፣ ሚዲያዎቻችንን፣ ሐውልቶቻችንን፣ ትርክቶቻችንን፣ ዲስኩሮቻችንን፣ ንግግሮቻችንን፣ የፖለቲካ ፕሮግራሞቻችንን የምናባክነው አረሙን ለማብቀል ሆኗል፡፡ አረምኮ ይህንን ሁሉ አይፈልግም ነበር፡፡ አረምን ለማብቀል ሥርዓተ ትምህርት መቅረጽ፣ ዩኒቨርሲቲ መገንባት፣ የፖለቲካ ፓርቲ ማደራጀት፣ ሚዲያ መዘርጋት፣ ብዕርና ወረቀት ማባከን፣ ምስትርናና ዱክትርና መድረስ አያስፈልግም ነበረ፡፡ አረም እንዲሁ ይበቅላልኮ፡፡
የፖለቲከኞቻችን ብስለት፣ የምሁሮቻችን ብቃት፣ የትውልዱ ምጥቀት፣ የተቋሞቻችን ሥልጠት፣ የሐሳቦቻችን ጥልቀት፣ የሚዲያዎቻችን ፍጽመት፣ የሥልጣኔያችን ርቀት፣ የጥበበኞቻችን ልህቀት የሚታወቀው ባበቀልነው እህል እንጂ ባበቀልነው አረም ብዛት አይደለም፡፡ ለአረምማ እነዚህ ሁሉ አያስፈልጉትም፡፡ እነዚህ ያስፈለጉት ሲቻል አረሙን ቀድሞ ለመከላከል፣ ካልሆነም የበቀለውን አርሞ እህሉን አህል ለማድረግ ነበር፡፡ ለማስተማር እንጂ ለማደንቆር ምን ትምህርት ቤት ይሻል? ለማዳን እንጂ ለማሳመም ምን ሆስፒታል ያስከፍታል? ለፍትሕ እንጂ ለወንጀል ምን ዳኝነት ያስፈልጋል? ለመግባባት እንጂ ላለመግባባት ምን ቋንቋ ያስፈልጋል? ለልዕልና እንጂ ለውርደት ምን ኪነ ጥበብ ያሻል? ለዓለም ዓቀፋዊ እሴቶች እንጂ ለጎጠኝነት ምን ጥበብ መፍሰስ ያሻዋል? ለማጥገብ እንጂ ለማስራብ ምን ፖሊሲ ያስፈልጋል? ለሥልጣኔ እንጂ ለስይጣኔ ምን ፓርቲ ማቋቋም ያስፈልጋል? ለጽድቅ እንጂ ለኃጢአት ምን የእምነት ተቋም ያሻል?
የኛ ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት አረም ላይ እየፈሰሰ ነው፡፡ የገበሬ ጉብዝና በአረም ብዛት እንደማይለካው ሁሉ የትውልድ ጉብዝናም በአረም አይለካም፡፡ ‹እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ› እንዲሉ እንኳንና የእኛ ጥበብና ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ተጨምሮበት አረም በራሱም ሀገር ያጠፋል፡፡
እንዲህ እርሻው ሁሉ አረም እስኪወርሰው
የለም ወይ የለም ወይ የለም ወይ ባር ሰው
ተብሎ የለ፡፡
አረም አያዋለዱ ሀገርን ለማሠልጠን መመኘት፣ ተኩላን እያረቡ የበግ ሥጋን እንደመመኘት ያለ ነው፡፡
በገበሬዎቻችን ታሪክ ውስጥ በ16ኛው መክዘ በሀገራችን ተከስቶ በነበረው የሃይማኖት ጦርነት ጊዜ ከ20 ዓመታት በላይ ገበሬው ተረጋግቶ በእርሻ ላይ ስላልነበር አገሩን አረም ወርሶት ነበር ይባላል፡፡ በዚያ ጊዜ ከሀገራችን ገጽ የጠፉ የእህል ዓይነቶች አሉ፡፡ ለዘር ተብሎ የተቀመጠው ወይ በቀጠና ምክንያት ተበልቶ፣ አለያም ቤቱ ሲቃጠል ተቃጥሎ፣ ካልሆነም የተቀበረበት ቦታ በዘመን ብዛት ጠፍቶ ሳይተኩ የቀሩ የእህል ዘሮች አሉ፡፡ የካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔርን ኅብረ ብዕር ያነበበ ሰው ከሚያያቸው የእህል ዘሮች መካከል ብዙዎቹ ስማቸውን ትተው ጠፍተው የቀሩት እንዲህ ባሉ ዘመናት ነው ይባላል፡፡ አረሙ ግን አልጠፋም፡፡ እንዲያውም ተመችቶት ነበር፡፡
በታሪካችንም ውስጥ እየጠፉና እየመነመኑ የመጡ በጎ እሴቶች፣ ባሕሎች፣ ልማዶችና ወጎች አሉ፡፡ አገር ችግር ላይ ስትወድቅ እህሉን የሚያመርተው ሲያጣ፣ ዘሩ ይጠፋል፡፡ ያንን ዕድልም አረሙ ይጠቀምበታል፡፡ ምድሩም እህል ተዘርቶበት የማያውቅ ይመስላል፡፡  
አሁን ለዚህ ትውልድ ጥያቄው አንድ ነው፤ ለአረሙ እንድከም ወይስ ለእህሉ? እህሉን በማምረት ብርታትህን ታሳያለህ ወይስ አረሙን በማብቀል ስንፍናህን? የኢትዮጵያ መልክ የሚቀየረው ለዚህ ጥያቄ በምንሰጠው መልስ ነው፡፡

በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አካባቢ በወያኔ የሚተላለፈው “የሀገር ፍቅር” በመባል የሚጠራው የማደናቆሪያና የማዘናጊያ ሬዲዮ ዝግጅት አቅራቢ የሆነው ንጉሴ ወልደማርያም ከአሳዳሪው ከወያኔ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአባ መላኩ ፊታውራሪነት በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ በተከፈተው ዘመቻ ላይ እሱም ተሳታፊነቱን በዛሬው ዕለት አዉጇል። …

“ዘመቻ አባ መላኩ” ከወያኔው ተላላኪ ከንጉሴ ወልደማርያም እርዳታ ጠየቀ Read more »

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም       ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 “ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የእራሱን ጥላ የሚፈራው ለምንድን ነው?“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችት ላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊዎች የወያኔው አመራሮች በግንቦት ስለሚካሄደው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ …

ኢትዮጵያ የተሻሉ አማራጮችን አጥታ ነውን ? Read more »

አሜሪካ ከመጣች 20 አመት አለፋት። ታዋቂ ድምፃዊ ናት። ከአመታት በፊት ተወልዳ ካደገችበት ጐንደር ይኖሩ የነበሩ ወላጅ እናቷን ወደዚህ ታስመጣለች። ምስኪን እናት አገሩ አልተመቻቸውም። ድምፃዊቷ በከፈተችው (ዝጉብኝ) መሸታ ቤት ዋልጌ ሃበሾች የሚያሳዩዋቸው ድርጊቶች እንባ ያስፈስሣቸው ያዘ። ሙዚቃው ሲረብሻቸው ይነጋል። ድምፃዊቷ ልጃቸው …

የፀፀት ደወል Read more »

(ሪፖርተር፤ ነአምን አሸናፊ፤ መስከረም ፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ ለመታደም እና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቤተ ክርስቲያኒቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመኾን አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ አራት ቀናት …



አንድ ጆሮና ጊዜ የገጠሙለት ሰው ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው የተማረው ትምህርት የለውም፡፡ ሁለት ችሎታ ግን ነበረው፡፡ ሲባል የሰማው እውነትም ይሁን ስሕተት ልቅም አድርጎ ይይዝና ሌላ ቦታ ሄዶ የተማረው ያህል ያንደቀድቀዋል፡፡ ሁለተኛው ችሎታው ደግሞ አፈ ጮሌ ስለሆነ ነገር በምላሱ ይቆላል፡፡ ያንንም ይኼንንም እያቆላመጠ ከተማሩትና ከተመራመሩት በላይ ከብሮና ታፍሮ ይኖራል፡፡ አንድ ቀን የማያውቀውን ቀለም ሲያዜም የሰሙት ሊቅ አፍረው አቀረቀሩ፡፡ እርሱ ግን ከዕውቀት የደነገለ ነበርና አልገባውም፡፡ በኋላ ቀረብ ብሎ ‹ደኅና ነዎት የኔታ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹ደኅና ነህ›› ብለው ዝም አሉት፡፡ እርሱም ያላወቁት ስለመሰለው ‹አላወቁኝም መሰል መሪጌታ እኮ ነኝ› አላቸው፡፡ሊቁም ‹ዐዉቄሃለሁ› አሉት፡፡ እንዳቀረቀሩ፡፡ ‹ታድያ ምነው ካወቁኝ ከነ ማዕረጌ ሳይጠሩኝ ቀሩሳ› አላቸው፡፡ ‹አንተን አከብራለሁ ብዬ ሞያውን እንዳልሰድበው ፈርቼ ነው›› አሉት ይባላል፡፡
 
እኔም ‹እርቲስቶቻችን› የሚለው ቃል በትእምርተ ጥቅስ ያደረግኩት ሊቁ የፈሩትን ፈርቼ ነው፡፡ እንዳልተውባቸው ደግሞ ምን ብዬ እንደምጠራቸው ግራ ገብቶኝ፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማውን መርሐ ግብር በዕለቱ ለማየት ስላልቻልኩ ቪዲዮውን ነው የተመለከትኩት፡፡ ሊነግሩን የፈለጉት ስለ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ፣ ስለ ሀገራችን ዕድገት፣ ስላለፈው ስኬታችን ቢሆንም እንኳን የቀረበው ዝግጅት ግን አደገች የምትባለውን ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ጥበብ ዞር ብላ ያላየቺው፣ ከንግግር ከፍ፣ ከፉከራ ዝቅ ያለ፤ ከፕሮፓጋንዳ ወረድ፣ ከዲስኩር ራቅ፣ ከድንፋታ ጠጋ ያለ ወለፈንዲ ሆኖ ነው የታየኝ፡፡ 
 
በሀገራችንኮ የልቅሶ ሥነ ሥርዓት እንኳን ወግ አለው፤ ጥበብ አለው፤ ትርዒት አለው፤ ፍሰት አለው፤ ድባብ አለው፤ ፈጠራ አለው፤ ርቀት አለው፣ ምጥቀት አለው፤ ደረጃ አለው፡፡ ይኼኮ ወግ የለው፣ ጥበብ የለው፣ ትርዒት የለው፣ ፍሰት የለው፣ ፈጠራ የለው፣ ደረጃ የለው፡፡ ድፍረት ብቻ፡፡ መሪዎቻችን ግን ለምንድን ነው የጥበብ አማካሪ የማይኖራቸው? ለምንድን ነው ጥበብን ከሚሰድቡ ሰዎች ጋር አብረው የሚቆሙት? ለምን ‹አርቲስቶቹን› እናከብራለን ብለው ሞያውን ይሰድቡታል? ይህቺ ሀገርኮ ሰማየ ሰማያት ደርሰው የመጡ፣ ድንጋዩን አቅልጠው ጥበብ የሚያፈልቁ፣ አራት ጸሐፊ አስቀምጠው አንድ አንድ ምዕራፍ እየነገሩ መጽሐፍ የሚያስጽፉ፤ መሰንቆ እንደ ሰው፣ ክራር እንደ ወፍ፣ በገና እንደ መልአክ የሚያናግሩ፤ ስንትና ስንት ጠቢባን ነበሩባት፡፡ ከሐይቅ ዳር የሸንበቆ ውዝዋዜ ተነሥተው ኅሊና የሚመስጥ አቋቋም የቀመሩ፣ እያዜሙ ሲሄዱ እንኳን ገበሬውን በሬዎቹን የሚያስደምሙ ጠቢባን ነበሩባት፡፡ እንዴት በጥበብ ሀገር በኢትዮጵያ ጠቢብ ነኝ የሚል ሰው ‹ከዕውቀት ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ› በድፍረት ይኖራል? ይኼኮ ሀገርን መድፈር ነው?  
አገሪቱ አድግበታልሁ፣ እመነደግበታለሁ፣ እለወጥበታለሁ፣ አሰላለፌን አስተካክልበታለሁ ብላ የደከመችበት የአምስት ዓመት ዕቅድ እንዴት በስሕተትና በድፍረት በተሞላ መድረክ እንዲታወጅ ይፈቀዳል? ይህንን ዕቅድ ባስታወስን ቁጥር ያንን ትልቅ ስሕተት እንድናስታውስ ለምን ተፈረደብን? ጥበብ ሳይሆን ድፍረት ትዝ እንዲለን ለምን ተገደድን? 
 
ጥበብ ምንም ዓይነት ይዘት ይኑረው የጥበብን ደረጃ ማሟላት ግን አለበት፡፡ ልማታዊም ሆነ አብዮታዊ፣ ዲሞክራሲያዊም ሆነ አምባገነናዊ፣ ይዘቱ ይለያይ እንጂ የጥበብ ደረጃው ግን አንድ ነው፡፡ ጥበብም የሚያሰኘው የጥበቡ ደረጃ እንጂ የያዘው ይዘት አይደለም፡፡ እንዴት ምግብ ቤቶቻችን ለምግብ አሠራርና አቀራረብ የሚጨነቁትን ያህል ለሀገራዊ መድረክ የሚጨነቅ ይጥፋ? እንዴት የበያይነቱ ምግብ ያህል ጥበብ በሀገራዊ መድረክ ላይ እንጣ?
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹ሀገራችን የራስዋ የሆነ ልዩ የዘመን አቆጣጠር አላት› ብለው ነገሩን፡፡ እውነት ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሀገር ባህል ልብስ ለብሰው በነገሩን የሀገራችን ልዩ የዘመን ቆጠራ እንስማማለን፡፡ ‹አርቲስቶቹ›› ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሳስተዋል፤ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የላትም›› አሉን፡፡ ‹‹አዲስ ዘመንም የሚብተው እንደ አውሮፓውያን በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የዘመን አቆጣጠራችን የተለየ ነው ያሉት ተሳስተው ነው›› አሉን፡፡ ኧረ እባክዎን ይጠይቁልን? ለምን ‹‹አርቲስቶቹ›› ጠቅላይ ሚኒስትሩን መቃወም ከፈለጉ የፖለቲካ ድርጅት መሥርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ተቃዋሚ ፓርቲ አያቋቁሙም? ደግሞስ ለሌሎች ያልተፈቀደ እንዴት ለእነርሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቀጥታ የዓመት በዓል ሥርጭት እንዲቃወሙ ተፈቀደላቸው? እንደ አሜሪካ የምርጫ ክርክር በቀጥታ ሥርጭት ተቃዋሚና መንግሥት በአንድ መድረክ የሚቀርቡ ከሆነማ እውነትም ሀገሬ ተለውጣለች?
 
የዛሬ ዓምስት ዓመት እንዲሁ ያለ ስሕተት ‹አርቲስቶቹ› ሲሠሩ ዐውቀው በድፍረት ሳይሆን ሳያውቁ በስሕተት ነው ተብሎ ታለፈ፡፡ ዘንድሮ እንዳይደገምም ብዙዎች በሚችሉት ሁሉ አስቀድመው አሳሰቡ፡፡ ሰሚም መስሚያም ጠፋና ስሕተቱ በባሰ ሁኔታ ተደገመ፡፡ ሰውና ሰይጣን የተለያዩትኮ ከስሕተት በመታረምና ባለመታረም ነው፡፡ ወደ ሥልጣኔው መሄድ ሲገባን ወደ ስ…   
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ አሁን ማንን እንመን? እርስዎን እንመን ወይስ ‹አርቲስቶቻችንን››?
  

ማስረጃዎች ለሕጋዊ ጥያቄ በሚያመቹበት ኹኔታ በአፋጣኝ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ታዟል በጥምር እና በተናጠል ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በስም ዝርዝር ይለያሉ የቤት እና የመኪና ሽልማት የተሰጣቸው አለቆች እና የስጦታው ምክንያት ተብራርቶ ይቀርባል   *          *          * የመሬት፣ የሕንጻ እና የልማት ይዞታዎች የኪራይ ውላቸው ለአንድ ዓመት ብቻ ይኾናል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ለመዋዋል እንዲቻል የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በቋሚ …

“እንደ ረዳት ጳጳስ ነኝ” የሚሉት ሥራ አስኪያጁ፣ ሕጋዊ ህልውናዋን ለአደጋ አጋልጠውታል ምደባቸው፣ ከመንግሥት ሕግ እና ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ጥያቄ ተነሥቶበታል ለስምንት ዓመታት የሒሳብ ሪፖርት ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል አልቀረበም በመላው ደቡብ አፍሪቃ ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት አትራፊ ባልኾኑ ሕዝባዊ ድርጅቶች ዐዋጅ(NPO) ሕግ መሠረት እ.አ.አ በ26/01/1999 ሕጋዊ ፈቃድ አግኝታ፣ በቁጥር 006-083 …

የታደለ አገልጋይ የበላዩን ከስሕተት ይጠብቃል፡፡ ‹አማካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ› እንዲሉ፡፡ አክዓብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት(871-852 ቅልክ) የነበረ ንጉሥ ነው፡፡ የሚስቱን የኤልዛቤልን ቃል ሰምቶ ነቢያተ እሥራኤልን ሊያጠፋ ተነሣ፡፡ ብዙዎች በሰይፉ ጠፉ፣ ብዙዎችም አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ በአክአብ ቤተ መንግሥት ውስጥ ግን አብድዩ የተባለ ልብ ያለው ባለሟል ነበር፡፡ ንጉሡን ከጥፋቱ ማዳን ቢያቅተው በንጉሡ ስሕተት ባለመስማማቱ 100 ነቢያትን በሁለት ዋሻ ውስጥ ደብቆ የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየመገበ ከአክዓብ ጥፋት አድኗቸው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ነቢያት የእሥራኤል የዕውቀትና የእምነት መሪዎች ናቸው፡፡ የእሥራኤል ባህል፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ዕውቀት የሚተላለፈው በነቢያት ትውፊት ነበርና፡፡ ነቢያቱን ማጥፋትም ሀገሪቱን ያለ ታሪክ፣ ዕውቀት፣ ባህል፣ ሥርዓትና ቅርስ ማስቀረት ነበር፡፡ ለዚህ ነው አብድዩ የንጉሡን ዐዋጅ ማስቀየር ቢያቅተው ነቢያቱን ደብቆ እየመገበ ሀገሪቱን ከከባድ ጥፋት የታደጋት፡፡ 

ይህንን ሥራውን ማንም እንዲያውቅለትም፣ እንዲያውቅበት አላደረገም፡፡ ዓላማው ዕውቅና ጥቅም ማግኘት ሳይሆን ሀገር ማትረፍ ነውና፡፡ የንጉሡን የጥፋት ዐዋጅ ማስቀረት አልችልም ብሎ ዝም አላለም፤ ነገር ግን በዐቅሙ የሚችለውን በማድረጉ በእውነትም እሥራኤል የዕውቀት፣ የታሪክና የባህል ጥፋት እንዳይገጥማት አደረገ፡፡ ያን ክፉ ዘመንም አሻገራት፡፡  
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የበላዮቻቸውን ጥፋት ከማስቀጠል ይልቅ በራሳቸው ዐቅም የሚችሉትን መልካምነት የፈጸሙትን ብቻ ሳይሆን፣ ‹ትእዛዝ ከበላይ እግር ወደ ላይ› ከማለት አልፈው አለቆቻቸውን ከጥፋት የታደጉ የበታች አገልጋዮችንም ታሪክ እናገኛለን፡፡ የሶርያው ንጉሥ የቤን ሐዳድ 2ኛ የጦር አዛዥ ንዕማን ወደ ሰማርያ መጥቶ ነቢዩ ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ ከለምጽ ሕመሙ ይድን ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ እንዲጠመቅ መክሮት ነበር፡፡ ንዕማን በዚህ ደስተኛ አልሆነም፡፡ ተቆጥቶም ወደ ሀገሩ ሊጓዝ ተነሣ፡፡ አንደኛው ባለሟሉ ግን ለጦር አዛዥ የሚገባ ምክርን መከረው ‹‹ጌታዬ ምን ቸገረህ፣ ውረድና ተጠመቅ፤ ከተፈወስክ እሰዬው፤ ክልሆነ ግን ከሰማርያ ጋር የምንዋጋበት ምክንያት እናገኛለን››፡፡ የጦር አዛዡ ንዕማን በዚህ የወታደሩ ሐሳብ ተስማማ፡፡ ዮርዳኖስ ወርዶም ተጠመቀ፡፡ ዳነም፡፡ አገልጋዩም አዛዡን ከጥፋት አዳነው፡፡ ንዕማንም ሊፈጽመው በነበረው ስሕተት ተጸጸተ፡፡
 
በታሪክ ውስጥ ግን እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር የበላዮቻቸውን ስሕተት የማይደግሙ ወይም አለቆቻቸውን ከስሕተት የሚታደጉ የበታቾች ብቻ አይደሉም የነበሩት፡፡ ያሉትም፡፡ አለቆቻቸው ያላሰቡትን ጥፋት በመሥራት አለቆቻቸውን ያስደሰቱ መስሏቸው ሀገር ያጠፉም አሉ፡፡ ‹ከለማበት የተጋባበት› እንዲሉ፡፡ ‹ጌታዬ እንዲህ ባደርግለት ይደሰታል› ብለው በማሰብ ከልክ እያለፉ፣ የሌለ እየጻፉ፣ ያልታዘዘ እየፈጸሙ ግፍ ሲሠሩ የኖሩ፡፡ ያዘው ሲባሉ ጣለው፤ እሠረው ሲባሉ ግደለው፤ አምጣው ሲባሉ ስቀለው፤ ተቀበለው ሲባሉ ቀማው የተባሉ እየመሰላቸው ሕግ ሲያልፉ፣ ገደብ ሲጥሱ የኖሩ አሽከሮችም ነበሩ፡፡ አሉም፡፡   
 
በሀገራችን ከነነዌ ጾም በኋላ የሚመጣው ኀሙስ ‹የዕብድ ኀሙስ› ይባላል፡፡ ቀኑ አለቆቻቸውን ለማስደሰት ሲሉ በግፍ ላይ ግፍ፣ በክፋት ላይ ክፋት፣ በመከራ ላይ መከራ፣ በቅጣት ላይ ቅጣት፣ በእንግልት ላይ እንግልት በሕዝብ ላይ ለሚጨምሩ አሽከሮች መታሰቢያ ነው፡፡ እንደ አብድዩና የንዕማን ወታደር ‹እስኪ ነገሩን እንየው› ከማለት ይልቅ ጭካኔ፣ ግፍ፣ ቅጣትና በደል አለቆቻችንን ይበልጥ ያስደስትልናል ብለው ለሚያስቡ አሽከሮች መታሰቢያ፡፡
 
በሸዋው ንጉሥ አስፋ ወሰን ዘመን ንጉሡ ለዘመቻ እየተጓዙ በደብረ ብርሃን አልፈው አንጎለላ ደረሱ፡፡ ይህን ጊዜ ጎሜ ጎሹ የተባለ አሽከር አስፋ ወሰንን በምን ላስደስታቸው ይልና በራሱ ጊዜ ዐዋጅ ያውጃል (‹መቼም ንጉሡ ሥራ በዝቶባቸው ረስተውት ነው እንጂ ይህን ሳያውጁ አይቀሩም‹ ብሎም ይሆናል)፡፡ ‹‹በዚህ ሀገር ያለውን ሰው ሁሉ አንድ ሳታስተርፍ በለው ብለውሃል› የሚል ዐዋጅ፡፡ ሠራዊቱም የንጉሥ ዐዋጅ መሰለውና አእምሮው ትቶ ጉልበቱን በማሠራት ፈረሱን እየጋለበ ከበሬሳ እስከ አያብር፣ ካንድ ዐርብ እስከ መገዘዝ የነበረውን ሀገር ሁሉ በነነዌ ፋሲካ ዕለት ኀሙስ ዘምቶበት ዋለ፡፡ ሕዝብ አለቀ፣ ተሰደደ፣ በሀገርም ላይ መከራ ወረደ፡፡ ንጉሡም የሆነውን ሲሰሙ አዝነው ጎሜ ጎሹን ‹‹ማን አዞህ ዐወጅክ?› ቢሉት ‹‹ጌታዬ መቼም የዘመትነው ለዚህ ነው ብዬ ነው›› አለ ይባላል፡፡ ቃላዊ መረጃዎች እንደሚነግሩን አስፋ ወሰን ጎሜ ጎሹን ቀጥተውና አሥረው ከዘመቻ ወደ አንኮበር ላኩት፡፡
ሕዝቡም ‹‹ወይ ጎሜ ጎሹ ወይ ጎሜ ጎሹ
በድፍን ሀገር ዕዳ ነስናሹ› ብሎ ገጠመበት፡፡ ቀኑም ‹የዕብድ ኀሙስ ተባለ›› ይላሉ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ በጻፉት የዳግማዊ ምኒሊክ ታሪክ ላይ፡፡
 
የቻለ እንደ ንዕማን ወታደር አለቃውን ከስሕተት ይታደጋል፣ ከጥፋት ያድናል፤ ያልቻለም እንደ አብድዩ የበላዩን ስሕተት ማረም ቢያቅተው እርሱን ስሕተቱ ይዞት እንዳይጠፋ ራሱን ከስሕተቱ ያድናል፣ ከጥፋቱም ይጠብቃል፡፡ ለሌሎችም የመዳኛ ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ ጎሜ ጎሹ ‹አለቃየ ይህን ባጠፋለት ደስ ይለዋል› ብሎ የሚያስብ አሽከር ግን ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳል›፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ትንሽ ቀዳዳ ካገኙ አስፍተው ስለሚጓዙባት አለቆቻችን ምንም አይሉንም ብለው ያስባሉ፤ እንዲያውም አብልጠው በማሰባቸው እንደሚሸለሙ ያምናሉ፡፡ ጎሜ ጎሹዎች የአለቆቻቸውን በር በመዝጋት፣ እንደ አለቆቻቸው ሆነው በመወሰን፣ ቁጣውን ወደ ጥፊ፣ ጥፊውን ወደ ግርፊያ፣ ግርፊያውን ወደ ግድያ በማሳደግ የተሻለ አፈጻጸም ለማሳየት ይተጋሉ፡፡ 
 
አብድዩና የንዕማን ወታደር የበዙላት ሀገር ዶፍ ዝናብን በጣራ፣ ካፊያን በጥላ እንደሚከለል ሰው፣ ከላይ የሚመጣውን ጥመት አቃንተው፣ የሚወርደውን ጥፋት አርመው፣ ቁጣውን በትዕግሥት፣ መዓቱን በምሕረት ስለሚለውጡት ድፍን ሀገር ዕዳ ሳይሆን ፋታ ያገኛል፡፡ ጎሜ ጎሹዎች ሲበዙ ግን በበሆር ላይ ቆረቆር፣ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፣ በዕዝል ላይ እንጥልጥል፣ በራቁት ላይ ብርድ፣ በጥማት ላይ ንቃቃት ይሆናል፡፡ ሕዝቡ እንዳለው ጎሜ ጎሹዎች ‹በድፍን ሀገር ዕዳ ይነሰንሳሉ›፡፡ እነርሱ ለዕለቱ የሚያገኙትን ሹመት ሽልማት፣ ጉርሻና ድርሻ እንጂ አለፍ ዘለቅ አድርገው የችግሩን ውጤት አያስቡትምና ጎሜ ጎሹዎች የሚያመጡትን ዕዳ ሀገር ስትከፍለው ትኖራለች፡፡    
 
በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያችን ጎሜ ጎሹዎች ሳይሆን አብድዩዎችና የንዕማን ወታደሮች የሚበዙባት ሀገር ትሁን፡፡

ተሸራርፈው እና ተገልብጠው ጎልተው እንዳይወጡ መደረጋቸውን ዳይሬክቶሬቱ ገምግሟል “የመልካም አስተዳደር ድምፃችን አልተሰማም፤ ውክልናችንም አንሷል” (ሰንበት ት/ቤቶች) ምክክሩ፣ በሀገረ ስብከቱ የሰባቱ ክፍላተ ከተማ እና በሌሎችም አህጉረ ስብከት ይቀጥላል (ሰንደቅ፤ ፲፩ኛ ዓመት ፭፻፳፪፤ ረቡዕ፣ ጳጉሜን ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 170 አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ ካህናት፣ የሰንበት …

የቡድኖች ማጠቃለያዎች፣ ውይይቱን የማያንጸባርቁ እና የጋራ አቋሞችን የማይወክሉ ነበሩ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በሚኒስቴሩ ከተሰጣቸው ትርጉም እና ማብራሪያ ውጭ ውለዋል ለመልካም አስተዳደር የተሰጠው መድረክ በቀማኞች የስመ አሸባሪ ዝባዝንኬዎች ተጠልፏል የሰንበት ት/ቤቶች እና መንፈሳውያን ማኅበራት በአክራሪነት እና በጽንፈኛነት ተፈርጅዋል *            *            * ጥሪው በአማሳኞቹ በመጠለፉ ከ169 አጥቢያዎች 20 የሰንበት ት/ቤት አባላት ብቻ …

ሪፖርቱ ሲነበብ እየተነሡ እና ራሳቸውን እየያዙ እግዚኦ… የሚሉ ብፁዓን አባቶች ነበሩ ኃይሌ ኣብርሃ፤ በ3 አድባራት ምዝበራው ቀንደኛው የሙስና ቀለበት በመኾን አስደምሟል አማሳኞች፣ ቋሚ ሲኖዶሱ በአንድ ልብ እንዳይወስን ባማሰኑት ገንዘባቸው ተረባርበው ነበር *           *           * በማስረጃና በማጣራት የተረጋገጠው የሙሰኞች ጥፋት ዝርዝር በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ይዘጋጃል ጥናታዊ ሪፖርቱን ተቀብለናል፤ የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ቃለ ጉባኤ …

የዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ውይይቱን በቡድናዊ አካሔድ የመቆጣጠር ሙከራ ተነቅቶበታል አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል መሸፈን እንደማይችሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋቸዋል “ስለ መልካም አስተዳደር ከሚደረሰው መግባባት በመነሣት መንግሥት ርምጃ ይወስዳል” ከአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከማኅበረ ካህናት፣ ከሰባክያነ ወንጌል፣ ከሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች እና የሀገረ ስብከቱ አንድነት አመራሮች ጋር በተናጠል ሲወያይ የቆየው፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ ውይይት ያካሒዳል፡፡ የመርሐ ግብሩን አስተባባሪዎች …

ለክብረ በዓሉ እና ጽኑ ኦርቶዶክሳውያንን ለማጽናናት ምእመናን እንዲሳተፉ እየተጠየቀ ነው ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን እና እሑድ ጳጉሜን 1 ቀን ለሚደረገው ጉዞ ምዝገባ እየተካሔደ ነው በክብረ በዓሉ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የመሠረት ድንጋይ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይቀመጣል *           *          * ከሥራቸው ታግደው በፈጠራ ክሥ የታሰሩት የሰበካ ጉባኤ አባላት ቤተሰቦች ችግር ተባብሷል የወረዳው ፍ/ቤት ለወሰነባቸው ከ6 – 9 …

የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር: “ባልተጣራ ሒሳብ እንዴት ሕንፃ ይሠራል?” የግንባታ ጥናቱ ከክፍያ ነፃ እንደተሠራ ቢነገርም የብር 250,000 ክፍያ እያነጋገረ ነው ሕግን መጣስ፣ ያለዕቅድ እና ያለጥናት ከፍተኛ ገንዘብ ማባከን የአስተዳደሩ መገለጫ ነው በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የተካሔደው የምዝበራ እና ብክነት ምርመራ ውጤቱ አልታወቀም ነገ ዕብነ መሠረቱን የሚያስቀምጡት ፓትርያርኩ ኹኔታውን እንዲያጤኑት ተጠይቋል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ …

አማሳኝ ሓላፊዎች፤ በካህናት እና ሠራተኞች ስም የሚያቀርቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ከብፁዕ ዋ/ሥራ አስኪያጁ ጀምሮ ብፁዓን አባቶች ለማስፈራራትና ለመደለል እየተሞከረ ነው “እጁ የተገኘበትን ኹሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ አሳልፋ ትሰጣለች፤ ይኼ የመጨረሻ አቋሜ ነው”                                    /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/  *       …

የቀድሞው የብሥራተ ገብርኤል፣ የመካኒሳ ሚካኤል እና የገርጂ ጊዮርጊስ አለቆች ተጠቅሰዋል ከግለሰቦች ጋር የሕገ ወጥ ጥቅም ተጋሪ በመኾን አድባራቱን ለዕዳ የዳረጉ አለቆች ይገኙበታል የመኪና እና የኮንዶሚኒየም ቤት ቁልፍ ሽልማት በፓትርያርኩ ሳይፈቀድ እንዳይሰጥ ተወስኗል ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ጥንተ ክብሯ የሚመልስ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ይደረጋል ተብሏል በጥናታዊ ሪፖርቱ፣ ‹‹አስገራሚ እና ለምዝበራ የተመቸ›› በተባለ አሠራር፣ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል …

አርአያ ተስፋማሪያም [ፎቶ: ሰሎሞንና ልመንህ] የዛሬ አመት አንድ አርቲስት እዚህ ዲሲ መጥቶ ሲያወራ « ከሌሊቱ 10 ሰዓት ቀረፃ አብረውኝ ያመሹትን ለማድረስ በሾላ መንገድ እያሽከረከርኩ ስጓዝ አካባቢው ጭር ብሎ ነበር። ሃይለኛ ዝናብ ይጥላል። በርቀት ዶፍ እየወረደበት በእግሩ የሚጓዝ ሰው ተመለከትኩ። ስንቀርብ …

ጐዳና የተገፉ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን Read more »

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ከሢመተ ፕትርክናቸው በኋላ የመጀመሪያ በኾነው የግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው÷ ፀረ ሙስና ሥርዐት ከተደነገገ ሙስና ይጠፋል፤ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ታገኛለች፤ በማለት አስቸኳይ ርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ነበር፡፡ ርምጃው ካህናትንና ምእመናንን በማስተባባር የሚፈጸም፣ ቆራጥነትን የሚጠይቅ እና በይዘቱም ሥር ነቀል መኾን እንደሚገባው አመልክተው ነበር፡፡ ፓትርያርኩ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ ተግባራዊ እንዲኾኑ …

‹‹የሕግ አማካሪ የማግኘት፣ የማማከር እና የመከላከል መብታቸው ተጣቧል፡፡›› /የወረዳው ምእመናን/ ‹‹መታሰር በክርስትና ያለ ነው፤ ክልሉ ጣልቃ እንዲገባ ጥሩ አቅጣጫ ተይዟል፡፡›› /የሐዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/ (ኢትዮ-ምኅዳር፤ቅጽ 03 ቁጥር 116፤ ቅዳሜ ነሐሴ 2 ቀን 2007 ዓ.ም.) በኦርቶዶክሳዊ ክርስትናቸው ለሚደርስባቸው በደል መፍትሔ በመሻት የድረሱልን ጥሪ ያሰሙት በምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የስልጤ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ […]

ከሕጋዊ አሠራር ውጭ በውስጥ ስምምነትና ድርድር እንዲከራዩ በመደረጉ፣ በመሐል ከተማ ከብር 500 – 3500 እየከፈሉ በቤተ ክርስቲያን ሀብት ሚሊየነር የኾኑ በርካታ ግለሰቦች አሉ በአዲስ አበባ የመሬት ገበያ በማይታሰብ ኹኔታ፣ ዝቅተኛው 0.37 ሳንቲም ከፍተኛው ብር 70 በካሬ ሜትር መከራየቱ አማሳኞቹ እና ግለሰብ ነጋዴዎቹ እንዲበለጽጉባት ዕድል ሰጥቷል *                *     …

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልእክት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትገኙ፣ የእግዚአብሔር እና የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች ምእመናን እና ምእመናት፣ እንኳን ለ፳፻፯ ዓ.ም. የቅድስት ድንግል ማርያም መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችኹ፡፡ …

አስተዳዳሪው ለጥያቄዎቻቸው በሳምንት ውስጥ ምላሽ ካልሰጡ ችግሩ እንደሚባባስ አሳስበዋል ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ጥያቄ በማንሣቱ በአለቃው ተበትኗል፤ ምክትል ሊቀ መንበሩንም አግደዋል የክፍለ ከተማው ፖሊስ አስተዳደሩን ከሰበካ ጉባኤውና ከምእመናኑ ጋር እንደሚያወያይ ተጠቁሟል (ሰንደቅ፤ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፲፯፤ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) በመንፈሳዊ እና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች ነን ያሉ የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን …

በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና በሚኒስቴሩ ሓላፊዎች ውይይት፡- በሓላፊዎች የሀብት ምዝገባ የተጠያቂነት ሥርዐት ለመዘርጋት እገዛ እንዲደረግ ተጠይቋል የሰንበት ት/ቤቶች በስልት እና በሰላማዊነት ተጋድሏቸውን እንዲያጠናክሩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል መንግሥትም በሙስና ወንጀሎች ተዋረዳዊ መዋቅሩን ጠብቆ ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል *        *        * የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች፡-  የመልካም አስተዳደር ዕጦት ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም መደፍረስ ዋናው መንሥኤ ነው ቅዱስ …

በኹለት ዓመት ውስጥ ለደብሩ ከብር 18 ሚልዮን በላይ ተቀማጭ አስመዝግቤአለኹ የተነሣሁት ሕገ ወጥ ክፍያዎችን በመቃወሜ እና ምዝበራዎችን ለመሸፋፈን ሲባል ነው ሕገ ወጥ አሠራር ቢረጋገጥም ውሳኔ አያገኝም፤ በአጥፊዎችም ላይ ርምጃ አይወሰድም የሰነዶቹ ደኅንነት ታይቶ ቢሮዬ ይታሸግልኝ፤ መንግሥት ኦዲተሮችን መድቦ ያጣራልኝ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስለሚፈጸሙ አደገኛ አሠራሮች ቀርቤ በቃል እንዳስረዳ ይመቻችልኝ *         *         * …

  በፀረ ሙስና፣ በመልካም አስተዳደርና በዕቅበተ እምነት ንቅናቄውየአማሳኞች የሕግ ተጠያቂነት እንዲኹም በእስር እና በወከባ የሚያደርሱት እንግልት ዋነኛ ትኩረት እንደሚኾን ተጠቁሟል ዋና ሥራ አስኪያጁ÷ በአለቆች፣ በካህናትና በሰባክያነ ወንጌል ላይ እንዳደረጉት ኹሉችግሮችን ውጫዊ በሚያደርግ ኦሬንቴሽን የውይይቱን ትኩረት ለማስቀየስ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም ‹‹የተሾምኩት በመንግሥት ትእዛዝ ነው›› የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያነሡባቸውን ሠራተኞች …

ልደት እና ትምህርት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ሊቀ ጳጳስ ከአባታቸው ከመምህር ሀብተ ማርያም ደስታ ተክሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ በስሙ ቸርነት ታኅሣሥ 19 ቀን 1925 ዓ.ም. በድሮው አጠራር ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እየተባለ ይጠራ በነበረው እንሳሮ ወረዳ በአኹኑ አጠራር በሰላሌ አውራጃ በውጫሌ ወረዳ ልዩ ስሙ በርጋፈት ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተወለዱ፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ በታላቁ …

የሰበካ ጉባኤው እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው 6 አባላት የሐሰት ወሬ ማሰራጨት በሚል ተከሠዋል ከ11-14 ቀናት እስር በኋላ በዋስ ቢወጡም ሊቀ መንበሩ የማርያም ወርቅ ተሻገር እንደታሰረ ነው ‹‹ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ›› በቤተ ክህነት እና በመንግሥት አካላት ‹‹ጥረት እየተደረገ ነው›› የሰላም ጉባኤ በማካሔድ የቤተ ክርስቲያኑን ቅዳሴ ቤት ለማክበር መዘጋጀቱን ሀ/ስብከቱ አስታውቋል *          *          * በ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ››ው፣ የጥንቱ የቅዱስ …

በእገሌ ቦታ በጀትና መደብ በሚል ተገቢ ያልኾነ ጥቅም ይሰጣል፤ ተገቢ የኾነ ጥቅም ይነፈጋል የሒሳብ ሹሞች ያለወቅቱ ዝውውር አጥፊዎችን በመከላከል ተጠያቂነትን እንዳያዳፍን ተሰግቷል በግንኙነቱ መስተጓጎል ጠቅ/ቤተ ክህነቱ ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች አቤቱታ ምላሽ አይሰጥም ‹‹አቤቱታችንን የት እና ለማን እንደምናሰማ ግራ ተጋብተናል››/የአጥቢያ ሠራተኞች/ (ኢትዮ-ምኅዳር፤ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]

የአስተዳደር ሓላፊዎቹ÷ የተዛቡ መረጃዎችንና ያልተጨበጡ ወሬዎችን እየነዙ በተለይ በሒሳብ አሠራር፤ በቆጠራ አካሔድ፤ በኦዲት ክንውን፤ በንብረት አያያዝ እና በግዢ ሥርዐት ዙሪያ ሰበካው በተለያዩ ጊዜያት ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና መመሪያዎች እንዳይተገበሩ አድርገዋል፡፡ በፓትርያርኩ እና በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሰጣቸው ተስፋ ከተግባር የራቀባቸው የሰበካ ጉባኤው አባላት፣ ከሚመለከታቸው የፍትሕ እና የጸጥታ አካላት ጋር እየመከሩበት ነው፡፡ ‹‹ምእመኑን ጃኬት ለባሽ አይመራንም …

በ7 ወራት ውስጥ ከብር 1.5 ሚልዮን በላይ የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ተመዝብሯል የፓትርያርኩ የኦዲት ክንውን ትእዛዝ “ከቃለ ዐዋዲው ውጭ ነው” በሚል ተጓትቷል “ታማኝ እና ብቁ የኾነ የሰው ኃይል ምደባ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል” (ሰበካ ጉባኤው) (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፭ ቁጥር ፰፻፯፤ ቅዳሜ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መቀመጫ የኾነችው የቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሰበካ …

ለደብሩ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና ለየሰንበት ት/ቤቱ ታላቅ ድል፤ በየአጥቢያው ለተጋጋለው የፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ ታላቅ የምሥራች፤ የንቅናቄውን ኃይሎች በነፍስ ግድያ ዛቻዎች ጭምር ለማዳከም ለሚሯሯጡት አማሳኞች ከባድ ድንጋጤ እና መርዶ ኾኗል !!! በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ባለፈው ሳምንት ዓርብ ረፋድ ባሳለፈው የቅጣት ውሳኔ፣ የደብሩ ዋና ሒሳብ ሹም ዲያቆን ተስፋዬ …

ትላንት እሑድ ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ ደብሩ፣ በአለቃው ‹‹የመንግሥት ያለኽ›› ጩኸት እና በምእመናን ‹‹ኃይል የእግዚአብሔር ነው፤ አንፈራም፤ አንሰጋም›› መዝሙር እና ተቃውሞ ውሏል *           *           * የቤተ ክርስቲያንን ነገር አደራ ብለው መባረኪያ መስቀላቸውን የሰጡ እንደ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እና ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ያሉ …

‹‹ደቀ መዛሙርቱ ከየአህጉረ ስብከቱ ተመርጠው ሲላኩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መኾናቸው እና የሃይማኖታቸው ጥንካሬ ታይቶ እንዲመለመሉ አህጉረ ስብከት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡›› ‹‹ወደ ኮሌጅ የሚገቡ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀታቸው እና መንፈሳዊ ሕይወታቸው እየታየ ወደ ኮሌጁ ገብተው እንዲማሩ እና እንዲያስተምሩ  ይደረግ፡፡›› /የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የጥቅምት ፳፻፬ ዓ.ም. ውሳኔ/ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛየትምህርት ተቋማት እና …

ማኅበረ ቅዱሳንን በመወንጀል ‹‹ወጣቶቹን ሰብስባችሁ እሰሩልን›› ያሉ አስተዳዳሪዎች የፖሊስ እና የደኅንነት አካላትን በተባባሪነት ወቀሱ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን እንደተቋም መወንጀል አትችሉም፤ ፖሊስ የእናንተ ብቻ አይደለም፤ መጀመሪያ ራሳችኹን ፈትሹ›› /ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም/ የቅድመ ውይይት ምክክሩና ውይይቱ፣ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን ማኅበረ ካህናትን፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮችን ሊያካትት ይገባል፡፡ (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፭ ቁጥር ፰፻፭፤ …

ወደ ሚኒስቴሩ ካመሩት 25 አለቆች 20 ያኽሎቹ በዋና ሥራ አስኪያጁ በተደረገባቸው ጫና ያለፍላጎታቸው እንዲሔዱ መገደዳቸውን እየተናገሩ ነው በየሰንበት ት/ቤቶቹ የዕቅበተ እምነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ መነሣሣት ማኅበረ ቅዱሳንን ወንጅለዋል፤ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ልብሱን ለውጦ የመጣበት ነው›› /ኃይሌ ኣብርሃ/ ‹‹እንዴት አድርገን መከላከል እንዳለብን አሠልጥኑን እንጂ ስለ ሰላም መወያየት ምን ያደርግልናል?›› /የደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ/ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን …

Originally posted on ሐራ ዘተዋሕዶ:
በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔና በፓትርያርኩ ቡራኬ ያጠኑትን በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች ብለዋቸዋል የሰ/ት/ቤቶችን፣ ከኮብልስቶን ሥራ ይልቅ ከአፋችን ሙዳይ ምጽዋት የሚነጥቁ በሚል ዘልፈዋል በሒሳብ አያያዝ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ያተኮረ ሥልጠና ተጀምሯል አለቆችን፣ ጸሐፊዎችንና ሒሳብ ሹሞችን ጨምሮ የሀ/ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎች ይሳተፋሉ ያለበቂ ዝግጅት የተጀመረው ሥልጠና ከወሬ ያላለፈ በሚል በተሳታፊዎች ክፉኛ ተተችቷል ለሥልጠናው ድጋፍ ከንግድ…

በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔና በፓትርያርኩ ቡራኬ ያጠኑትን በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች ብለዋቸዋል የሰ/ት/ቤቶችን፣ ከኮብልስቶን ሥራ ይልቅ ከአፋችን ሙዳይ ምጽዋት የሚነጥቁ በሚል ዘልፈዋል በሒሳብ አያያዝ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ያተኮረ ሥልጠና ተጀምሯል አለቆችን፣ ጸሐፊዎችንና ሒሳብ ሹሞችን ጨምሮ የሀ/ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎች ይሳተፋሉ ያለበቂ ዝግጅት የተጀመረው ሥልጠና ከወሬ ያላለፈ በሚል በተሳታፊዎች ክፉኛ ተተችቷል ለሥልጠናው ድጋፍ ከንግድ ባንክ የተገኘው ብር …

(ሰንደቅ፤ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፲፤ ረቡዕ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ት/ቤቶች ሙስና እና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደር እና ፍትሕ እንዲሰፍን፣ አስተምህሮ እና ሥርዐት እንዲጠበቅ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ውሳኔ እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ አስታወቀ፡፡ የሰንበት ት/ቤቶቹ፣ በአማሳኝ የአስተዳደር ሓላፊዎች እና በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ …

ቋሚ ሲኖዶሱ የሀ/ስብከቱን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር በማነጋገር ትእዛዝ ሰጥቷል መዋቅሩ ችግሮችን በየደረጃው የሚፈታበት ፍትሐዊነት እና ተአማኒነት መፈተሽ ይኖርበታል ከቤተ ክህነቱ በላይ የሚያሾሙና የሚያሽሩ አማሳኝ አለቆች እንዳሉ መግባባት ላይ ተደርሷል በፓትርያርኩ ዙሪያ ያሉትን ጨምሮ በፀረ ሙስና እየተመረመሩ በሕግ እንዲዳኙ ተጠይቋል *          *          * ዋ/ሥ/አስኪያጅ የማነ÷ ‹‹በፀረ ሙስና አብሬ እሠራለኹ፤ በፀረ ተሐድሶ …

በሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተጠራ ጉባኤ፣ የአንድ ወር እንቅስቃሴውን ገምግሟል ንቅናቄውን ከመሪ ዕቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ጋር አስተሳስሮ የሚመራ ራሱን የቻለ አካል ተቋቁሟል ከማኅበረ ካህናት እና ምእመናን፣ የማኅበረሰብ ተቋማት እና የፀረ ሙስና አካላት ጋር ይሠራል ዓላማውን ከቤተሰብ እስከ ኅብረተሰብ በማስተዋወቅ በስፋት ማነሣሣትና ማንቀሳቀስ ተግባሩ ነው የዕቅበተ እምነት የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ንቅናቄው በገዳማውያን አበው ጸሎት ይታገዛል *        …

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን: በልማት ስም ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግሉ በማካበት በሚታወቀው የቀድሞው አለቃ ኃይሌ ኣብርሃ፥ በግንባታ እንዲኹም የባለቤትነት እና የተጠቃሚነት መብቱን አሳልፈው በሚሰጡ የኪራይ ውሎች ከመመዝበሩም በላይ የሚልዮኖች የባንክ ባለዕዳ አድርጎት ያለተጠያቂነት ለመሰል ዘረፋ ወደ ሌላ ደብር ተዘዋውሯል፡፡ በእግሩ የተተኩት ግብታዊው እና ዐምባገነኑ መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ […]

በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል፤ በሌለ ልማት! ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት …

  የቁጥጥር እና የፋይናንስ ሓላፊዎች የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ዝቅተኛ ነው ከአጥቢያዎች የሚዘረፈው የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቢሯቸው ድረስ ይመጣላቸዋል የቤተሰብ ጉባኤ በሚመስለው የቁጥጥር ክፍሉ ስብሰባ የዘረፋ ስልቶች ይቀመራሉ ትኩረቱን ወደ ከፍተኛ ግዥዎችና ፕሮጀክቶች ለማዞር እስከ መምከር ተደርሷል እነኃይሌ ኣብርሃ እንዳሉት፣ ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል!›› /ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች/ ‹‹ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች›› …

የታሸገው የሰሚት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት ሳያውል ሳያድር መከፈት፤ የታሰሩት አባላት እና ምእመናን መፈታት በተሰላፊዎቹ ሰንበት ት/ቤቶች እና በዋና ሥራ አስኪያጁ መካከል ወሳኝ ልዩነት የፈጠረ ጉዳይ ኾኗል፤ ‹‹በአንድ ደብዳቤ እንዳዘጋኸው በአንድ ደብዳቤ ዛሬውኑ አስከፍት!›› የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ውስጥ ለውስጥ በቤተ ክርስቲያን እና በአገልግሎቷ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ እንዳለ በማመን በትጋት እና በጽናት እንዲሠራበት በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ …