ዜና ብሥራት – ቋሚ ሲኖዶስ: ጥናታዊ ሪፖርቱን በማጽደቅ አማሳኞች በሕግ እንዲጠየቁ ይኹንታውን ሰጠ!
- ሪፖርቱ ሲነበብ እየተነሡ እና ራሳቸውን እየያዙ እግዚኦ… የሚሉ ብፁዓን አባቶች ነበሩ
- ኃይሌ ኣብርሃ፤ በ3 አድባራት ምዝበራው ቀንደኛው የሙስና ቀለበት በመኾን አስደምሟል
- አማሳኞች፣ ቋሚ ሲኖዶሱ በአንድ ልብ እንዳይወስን ባማሰኑት ገንዘባቸው ተረባርበው ነበር
* * *
- በማስረጃና በማጣራት የተረጋገጠው የሙሰኞች ጥፋት ዝርዝር በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ይዘጋጃል
- ጥናታዊ ሪፖርቱን ተቀብለናል፤ የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ቃለ ጉባኤ እና ውሳኔዎችም አጽድቀናል
- የጥናቱን የመፍትሔ ሐሳቦች በመቀበል የመሬትና የንብረት አስተዳደር ሕግ በማዕከል ይወጣል
ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ
