አማሳኞች ባለመገሠጻቸው ‹‹እነ እገሌ ምን ተደረጉ? እኛስ ምን እንኾናለን?›› በሚል በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ላይ እየዘበቱና ሀገረ ስብከቱን ለማወክ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በሃይማኖት ሕጸጽ ስለሚጠረጠሩ ሰባክያንና ሥርዐት አልባ ዘማርያን የሚቀርቡ ማስረጃዎች ውሳኔ ሳያገኙ ምደባና ስምሪት መሰጠቱ ሰንበት ት/ቤቶችን እያዳከመ ነው፡፡ በአማሳኝ አለቆችና በሙዳይ ምጽዋት ገልባጮች ግርግር የውኃ ሽታ የኾነው የሀ/ስብከቱ ተቋማዊ ለውጥ ጥናት ለሰንበት ት/ቤቶች በሚያመች አኳኋን …

Minilik Salsawi : ሕዝቡ እየተፈረካከሰ የሚገኘውን ወያኔን በጋራ ታግሎ በማስወገድ ነጻነቱን ማረጋገጥ አለበት::ኢትዮጵያውያን ጨለማን ተገን በማድረግ በታጠቁ በሕወሓት የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ሙስና እና ዘረፋ የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጹ::

የደህንነት ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው በከፍተኛ ደረጃ በዘረፋ ላይ መሰማራታቸው ታውቋል:እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ ባለስልጣኖቹ እና ጭፍሮቻቸው የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት ከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ በየዋህነት ፍትህ ያገኘ መስሎት ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ በማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::

በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን እንዲሁም ተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::ሕዝቡን በማስተባበር እና በመቀስቀስ የተጫነበትን የአምባገነኖች ብትር በጋራ በመታገል አምባገነኖችን እና ጭፍሮቻቸውን ከስልጣን በማስወገድ ነጻነቱን ማረጋገጥ ያለበት ወስኝ ወቅት ላይ መሆኑን ለመናገር እወዳለሁ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ በሙስሊሞች ላይ መከፈቱ ተገለፀ
ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን በአዲስ አበባ ለማሰር ታቅዷል፡፡
የቢላል ሬዲዬ ጋዜጠኛ የነበረው ካሊድ ሙሃመድ በደህንነት ሀያሎች ታፍኖ ተወስዷል።
ህውሃት መራሹ ወያኔ አሁንም ንፁሃን ሙስሊሞችን ከየአካባቢው ማደነኑን ቀጥሏል። በዛሬው እለት በብርጭቆ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ይኖር የነበረው ወንድማችን የሆነው እና የቢላል ሬዲዬ ጋዜጠኛ የነበረው ፣ ከአመት በፊት በረመዳን ወር መግቢያ ላይ በ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ ካሊድ ሙሃመድ በዛሬው እለት የፈጅር ሰላቱን ሰግዶ ወደ ቤቱ በሚመለስበት ወቅት በደህንነት ሀያሎች ታፍኖ እየተደበደበ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል። ከቤቱ ውስጥም ላፕቶፖችን ጨምሮ በርካታ የሚገለገልባቸውን ንብረቶች እንደተወሰደበት ለማወቅ ተችሏል።

ወንድማችን ካሊድ በአሁኑ ወቅት የ2 ወር ልጅ ያለው ሲሆን በዛሬው እለት የደህነነት ሀይሎች በአራስ ባለቤቱ ላይም ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙ ለማወቅ ተችሏል።
በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ በሙስሊሞች ላይ መከፈቱ ተገለፀ

ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን በአዲስ አበባ ለማሰር ታቅዷል፡፡

ፍትህ ራዲዬ /ዕለተ ረቡዕ የካቲት11/2007- በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ መከፈቱን የፍትህ ራዲዬ የውስጥ ምንጮች አስታወቁ፡፡

ዘመቻው የተጀመረው በቀጣይ ሃገራዊ ምርጫ ላይ በህዝበ ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩብናል በሚል የሚሰጓቸውን ሰዎች በማሰር እንደሆነ ታውቋል፡፡

በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የነበሩ ፖለቲካ ፓርቲዎችን እርስ በእርስ እንዲከፋፈሉ በማድረግ የማዳከም ስራ የሰራው መንግስት ፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአሁኑ ወቅት ለኢህአዴግ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ብቻ በመንጠላጠል በመሆኑ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የመጨረሻ የማዳከም ዘመቻ ሊከፈትበት እንደሚገባ በማመናቸው አዲስ ዘመቻ በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ላይ በሚኖሩ በሙስሊሞች ዘመቻው መጀመሩን የፍትህ ራዲዬ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የአሰሳ እና ስምሪት ተግባር እየተካሄደ ሲሆን በአዲስ አበባም በርካታ ሙስሊሞች የማሰሩ ዘመቻ ተጠናክሮ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በሙስሊሙ ትግል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ተብሎ የሚታሰቡ ሰዎችን በሙሉ ወደ እስር ቤት ለማስገባት የተወሰነ ሲሆን ይህንንም ዘመቻ በጅማ እና በአዲስ አበባ እየተተገበረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ይህ ዘመቻ የሚመራው በከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልኩ በተዋቀረ ና በተደራጀ ሁኔታ የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ በመከታተል ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ተብሎ የሚታሰቡ ሰዎችን ወደ እስር ቤት የማጎር ዘመቻ እየተካሄደ እንደሚገኝ የፍትህ ራዲዬ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ሃገር አቀፍ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ቁጥራቸው ከ 800 እስከ 1000 የሚደርሱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ሰዎችን ለማሰር እቅድ የተያዘ ሲሆን ምርጫውን ለማደናቀፍ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አብዬት ለመቀስቀስ ሲንቀሳቀሱ ነበር በማለት ለመወንጀል መታቀዱን ምንጮች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በዛሬው ዕለት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ከያሉበት እየታደኑ እየታሰሩ እንደሚገኙ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የራዲዬ ቢላል ጋዜጠኛ የነበረው ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቀ በርካታ ሙስሊሞች ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች እየታፈኑ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሙስሊሞቹ በተያዙበት አካባቢ በወደሚገኙ የፖሊሰ ጣብያዎች እየታጎሩ ሲሆን የመኖሪያ ቤታቸውም በፖሊሶች እና በደህንነቶች እየተፈተሸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡በመኖሩያ ቤታቸው የሚገኙ የተለያዩ ላፕቶፕ እና የግል ንብረቶቻቸው በደህንነት ሃሎች በፍተሸው ወቅት ለምርመራ በሚል መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

Image

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡

በተያያዘ ዜና የመሀል ዳኛው የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ ይቀየሩልን ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት ከችሎቱ ያገለሉ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር በፍርድ ቤት ጉዳዩን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

Image

በምስሉ የሚታዩት የቢራ ማስታወቂያዎችን የያዙ የመጠጥ ግሮሰሪዎች፣ የውበት ሳሎን፣ ባርና ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለምንና የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል አብያተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም፣ ቅጥርና ገረገራ ይዘው የሚታዩ የንግድ ማዕከላት ናቸው፡፡ የቦታውን ዋጋ ባገናዘበ አኳኋን በሕጋዊ መንገድ ከአለመከራየታቸውም በላይ በተከራይ አከራይ ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም የተላለፉት እኒኽ የንግድ ማዕከላት፣ በቤተ ክርስቲያን መሳለሚያና መዳረሻ …

ImageImage
አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል።
ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። ቀደምት ተብላ እንደመጠራቷም ሀገሪቷ ከ100 አመታት በፊት በቱርክ ግዛት ስር ሆና ደማስቆን እና የቤሩትን የወደብ ከተሞች የሚያካልል ሀዲድ ተዘርግቶ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠቃሚም ሆናለች። ከዚያም በመነሳት ነጻነቷን አውጃ ራስዋን ማስተዳደር ስትጀምር የዛሬ 60 አመት በፊት 1956 እ.ኤ.አ ሞደርን ሲኤፍኤስ ፓሴንጀር ትሬን በማለት አዲስ መዋቅር አበጅታ እስከ 2012 ተገልግላበታለች።አሁን ያ ያላት መልካም ገጽታ እና ታሪኳ እንዲሁም ከሁሉ በፊት ባብር ነጂ መሆናዋ ከመሰባበር አላዳናትም።

የሶርያ ፕሬዘዳንት ባሻር አል አሳድ በአንባገነንነት ምድሪቷን መግዛት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ከ2011 ዓ.ም ወዲህ አሁን ድረስ መልኩን ቀያይሮ እና የተለያየ ስም ይዞ ታልቅ እልቂት ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ220,000 ንጹሀን ዜጎች በላይ ለህልፈተ ሞት ያበቃ ሲሆን 11 ሺህ 420 ህጻናት መገደላቸው እና ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የሆነ ዜጋ ሀገሩን ጥሎ በየጎረቤቱ ጥገኛ እና ስደተኛ ሲሆን የፍትህ የዲሞክራሲ ረሀብ እና ናፍቆት እንጂ መንገድ፣ ፎቅ፣ ባቡርና ሀዲድማ ነበራቸው። ዴሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ እና ስርዓት ምድሪቷን እስካልተቆጣጠራት ድረስ ሁሉም ነገር ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው።

ስለ ኢትዮጵያ ደግሞ እናንሳ ። በ1895 ዓ.ም አንድ በደረት ላይ የሚንጠለጠል የምድር ባቡር ማሳሰቢያ ባጅ ነበር። በአንዱ ገጽ የአጼ ምኒልክ ምስል በሌላው ደግም 1895 የምድር ባብር ማሳሰቢያ የሚል ተቀርጻበታል። የዛሬ 112 ዓመት በፊት መሆኑ ነው።በአጼ ምኒልክ ውሳኔ የመሰረት ድንጋዩ ተቀምጦ የስዊዝ ተውላጅ በሆኑት ኢንጅነር አልፍሬድ ኢልግ እገዛ መሰረት የሀዲድ መሰመር ግንባታው እኤአ በ1893ተጀምረ። ከ24 ዓመት በኃላ ስራው ተጠናቅቆ በ1917ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ባብር ተነዳ። ይህም የዛሬ 98 ዓመት መሆኑ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያ ምን ያህል ቀደምት የስልጣኔ ከፍታ እንዳላት ያስረዳል።በአፍሪካ ካሉት ቀደምት የባቡር ተጠቃሚዎች መሀል 1ኛ)ግብጽ በ1856 ዓ.ም 2ኛ) ደቡብ አፍሪካ በ1897 ዓ.ም 3ኛ) ሱዳን በ1898ዓ.ም 4ኛ)ኬንያ በ1901ዓ.ም 5ኛ)ታንጋኒካ በ1905 ዓ.ም 6ኛ) ሴራሊዮን 1909ዓ.ም 7ኛ) ናይጄርያ 1912 ዓ.ም 8ኛ) ኢትዮጵያ በ1917 ዓ.ም በሀገራቸው ላይ ባቡርን ለህዝብ ጥቅም ካዋሉት የመጀመራዎቹ ተርታ ትሰለፋለች።

የዛሬው ዘመን ላይ ደርሰን ባቡር እና ሀዲዱ ብርቅ ሆኖ ባብር! ባብር !ባቡር እየተባለ ጡርንበኞች ሲጮሁ መስማት ምን ያህል ከፍትህ እና ከሰላም ይልቅ ግኡዝ ነገር አእምሮአቸውን እንደጨመደደው ልብ ይሏል። በምድሪቷ ላይ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት የተከሰከሰው የአባቶች አጥንት ለባቡር ለፎቅ እና ለመንገድ አልነበረም። ይልቁንም ለፍትህ ለሉዐላዊነት ለነጻነት እና ለአንድነት ነበር። አሁንም ያ አጥንት ትውልዱን ይወቅሳል። ባቡርማ ብርቅ አይደለም! ኢትዮጵያም ነበራት። ሶርያም ኢራቅም ነድታለች ዳሩ የህዝብ ረሀብ ነጻነት ሆነ እንጂ። ሶርያ ያላት ህንጻ፣መንገዷ፣ባብሯ እና ሀዲዷ ከመበታተን ከመሰባበር አላዳናትም።የሀገር ሀብት ዲሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ የሆነ እንደሆን ብቻ ሀገር ይለማል። ሀብት እና ንብረታችን ነጻነት እና አንድነታችን ነው። የድል ክንዳችን መያያዛችን እና መቀባበላችን ብቻ ነው።

በወያኔ አለንጋ ደንዛዛ እንዲሆን የተመተተብት ትውልድ አፍዝ አደንግዙን ረግጦ ስለኢትዮጵያው ሊነቃ የሚገባበት ዘመን አሁን ነው። ባቡሩና ሀዲዱ መጥፎ ነው ለማለት አይደለም ስላስፈለገም ነው ከ98 ዓመት በፊት የተገነባው። ድሮስ ወያኔ የራሱን ሆድ ሲያጭቅ ድሆች ከፍርፋሪው ባቡር እና ሀዲድ እንደቡችላ ቢወረውርላቸው ምን ይከፋል። ይህ እኮ የወያኔ ካዝና ውድቅዳቂ እና ፍርፋሪ ነው።ፍርፋሪ ደግሞ ሆድ አይሞላም እንዲያውም ቢያስርብ እንጂ።ይህ ማታለያ ወያኔ ሀፍረቱ እንዳይታይበት የለበሰው ብጣቂና ቅዱስ የመሰለበት ማስመሰያው ነው። ተኩላ በበግ ለምድ እንዲከለል ሰይጣንም አውሬነቱን ለመደበቅ ራሱን እንዲከልል ወያኔም ነፍሰ ገዳይነቱን ለመደበቅ አዛኝ መስሎ የማይበስል ቅቤ ያነጉታል። ለኢትዮጵያ እድገት እና ልማት ለሀገሪቷ ፍቅር ያለው መሪ ህዝብን ነጻ ከማድረግ እና የእኩልነት መንፈስ በምድሪቷ ላይ እንዲሰፍን ከመትጋት ይጀምራል ። ነጻነት የሌለው ህዝብ ፎቅ ላይ ቢወጣ በባቡር ቢሳፈር ዳሩ እስረኞቹ ተሳፍረው እየሔዱ ነው ቢባል እንጂ ሌላ የማታለያ መጠርያ ቢሰጠው በመጫኛ መጣል ይሆናል። እንዶሮዋ።

ዳሩ በግኡዛን ቁሳቁስ ብናምር ብንቆጠቆጥ ማን እርሱን ይጠላል። ግን እርሱ ሐብት አይደለም። አንድ ቀን ይከዳል። ምድሪቷ ድንገት ቢያስነጥሳት አሊያም ብትንጠራራ ከበላይዋ በብድር ገንዘብ ያንጋጠጠው ፎቅም በሉት ባቡር አሊያም ሌላ ግኡዝ የፍርስራሽ ቁልል ሁኖ ለመዛቅ ዕዳ ይሆናል። ስለዚህ ስለብልጽግና ስናወራ ስለ ገንዝብ ካወራን ስተናል ማለት ነው። ገንዘብ ኖሮህ ነጻነት ከሌለህ ፎቅ ገንብተህ በየደቂቃው የወያኔ አባት በጣረ ሞት መንፈስ እየመጣ ካስጨነቀህ ከዚህ በላይ ምስኪንነት የለም። ኢትዮጵያ በለጸገች አሊያም ብሩህ ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሎ ወያኔ ራሱን በራሱ ቢያንቆለጳጵስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የማባበያ እና የማታለያ ባዶ ዲስኩር ፊቱን ሊመልስ እና ሊነቃ ግድ ነው።

የሀገር ሀብት ፍትህ፣አንድነት፣እኩልነት፣ እና ለአንዲት ሀገር በአንድ ክንድ ለሀገር ሉአላዊነት የቆመ አንድ ህዝብ እንጂ ብሩም ወርቁም ነጻ ባልወጣ ሀገር አያምርም! አያደምቅም! የውሸት ነው። በአዲስ አባባ ላይ ብቻ የታየው ብልጭልጭታ ህጻኑ እንዳያለቅስ የተሰጠው ማታለያ ይመስላል። ኢትዮጵያ አዲስ አባባ ብቻ አይደለችም ።

ከቤት እንሰሳት ጋር የውሀ ጥሙን ለመቁረጥ ወደወንዝ የሚርደው ህዝብ፣ ዛፍ ስር በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ወጉ እንዳይቀር ሀ ሁ ሂ . . . እያለ ፊደል የሚቆጥረው፣ ለቀዶ ጥገና የ2 አመት ቀጠሮ የሚጠብቁ ታማሚዎች፣በየክፍለሀገራቱ ከልጅነት እስከእውቀት በበጋም በክረምትም መጠለያ ሳይኖራቸው በየጥጋጥጉ ቆሼ ተራ እየተመገቡ ያደጉት ሌላም ቢተረክ ጌዜ የማየበቃው ቁርቁዝና ከሁም በላይ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ እውነቱን እንዳይናገር የታፈነ እና የተለጎመ የታሰረ አንደበት የተጠራቀመባት ምድር ናት ኢትዮጵያ የሚትባለው። ይህች ናት በወያኔ የተቀረጸችው ኢትዮጵያ። ስለዚህም ነው አሁን የመንቃት ጊዜ እንደሆነ የምንናገረው። ኢትዮጵያውያንን እንደ ህጻን በብልጭልጭ ነገር የማታለል የወያኔ ዘመን ያክትም። ሀብታችን ባቡርና ፎቅ ሳይሆን አንድነት እና እኩልነታችን ነው። በመጀመሪያ ነጻነት!!!

እናቸንፋለን !!!
Biniam Gizaw (Norway)

አንድነቶች በምርጫ ጨዋታዉ ግጥሚያዉ ሳይጀመር አሸንፈናቸዋል፤በሰላማዊ ትግሉም የመጨሻዉን ሽንፈት ይጎነጫሉ!!
Image
ምርጫ 2007 ለለዉጥ ብለን ተነሳን፡፡በሙሉ ልብና ዝግጅት ለህዝቡ አማረጭ ለመሆን ለምርጫ የሚየስፈልገዉን ግብኣት ይዘን ተሰለፍን፡፡አጥቂዎችን ከተከላካዮች ለይተን ደጀኖችን ከኃላ አሰልፈን በትምህርት ዝግጅትና በአባላት ጥራት እንዲሁም በሃሳብ የበላይነት ከኢህአዴግ የሚበልለጡ እጩዎችን አዘጋጀን፡፡ከሃቀኛ ፓርቲዎች ጋር ላለመወዳደር በሰጥቶ መቀበል መርህ ለመዳረደርና ለህዝቡ ብቁ ተመራጭ ይዞ ለመቅረብ ተደራዳሪ ኮሚቲም አቋቋምን፡፡ህወሓት ሃሳብ የለዉም፡፡ቢኖረዉም ያረጀ ነዉ፡፡ለዚህ ትዉልድ አይመጥንም፡፡የሚጮኸዉን ያህል ቀርቶ ከኣባለቱ ሩብ ያህል እንኳን አድማጭ የለዉም፡፡እኛ ብዙ ተምረናል፡፡ከወደቁትና ዛሬም በጽናት ከሚታገሉቱ ቡድኖችና ግለሰቦች ትምህርት ቀስመናል፡፡ከአሮጌዉ ህወሓትም ይሁን ከወጣቱ ሰማያዊ ፓርቲ የምንቀስመዉን ቀስመናል፤ለመማር ዝግ አይደለንም፡፡ለዉህደትና ለትብብርም እንዲሁ፡፡እደሉም ስላልነበራቸዉ እነሱ የብሄረሰብን ጥያቄ ከነስታሊን መጽሃፍት የቃረሙት ሲሆን እኛ በተግባር አብርን ኖረን የምናዉቀዉ፤በብሄረሰብ መሰረት ከተደራጁ ሃይሎች ጋር ግንባር ፈጥረን ችግረቸዉን ተረድተን የህዝብን ጥያቄ በተግባር ለመመለስ የቆረጥን በህዝብና በሃገር ሉኣለዊነት የማንደራደር የዘመኑ አስተሳሰብ ዉጤት ነን፡፡በመሳሪያና በገንዘብ ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት ኮርተን፤ ዳኛዉን ሳይሆን ህዝቡን ተማምነን ለምርጫ ጨዋታዉ ዝግጁ ሆነን ነበር፡፡
ሽንፈቱ ከወዲሁ የገባዉ ህወሓት መጋረጃ ዉስጥ ሆኖ ጨዋታዉን ከወዲሁ አበላሸዉ፤አንድነት ፓርቲን ቢያሸዉ ቢደፈጥጠዉ ጎማ ሆነበት፡፡አልፈርጥለት ሲል የመጨረሻዉን አደረገ፡፡በጠራራ ጸሃይ ከህግ በላይ በጉልበት ዋናዉን ቢሮ ወረረዉ፡፡ምን እንደወሰዱ ምንስ እንዳስገቡብን አናቅም፡፡እርጉዝ ሴት በዱላ መትተዉ የወርቅ ሃብል የወሰዱ፤ጽ/ቤት ገብተዉ ምን እንደሚያደርጉ መገመት ይቻላል፡፡ያለ ህግዊና በእማኝ ፊት ርክክብ እንደልማዳቸዉ የህዝብ ሃብት ነጥቀዋል፡፡በሂደቱም ግለሰቦችና የህወሓትን ተግባር ለመፈጸም የተቋቋሙ ተቋማት ጥቁር ታሪካቸዉን ሲያኖሩ በእስር እየማቀቁ ያሉቱ የለዉጥ ሃይሎችና በዚህ ሂደት የለዉጥ ሃይሉን ከሚመራዉ ጋር የቆሙ የእንድነት አባላትና ደጋፊዎች ታሪካቸዉን በወርቅ ቀለም ጽፈዉ አኑረዋል፡፡እንዲሆም ድርጊቱን በማዉገዝ ከጎናችን የቆማችሁ ሁሉ በነጻነት ትግሉ የክብር ቦታ አላችሁ፡፡
አንድነቶች በበምርጫ ጨዋታዉ ግጥሚያዉ ሳይጀመር አሸንፈናቸዋል፤በሰላማዊ ትግሉም የመጨሻዉን ሽንፈት ይጎነጫሉ፡፡ ዛሬም የነጻ አዉጪን ስም የተሸከመዉ ህወሓት የሚያስበዉ እንደራሱ ነዉ፡፡የፓርቲ ስም፤አርማና ማህተም በዚህ ትዉልድ ቦታ እንደሌላቸዉ አልተረዳዉም፡፡የትዉልዱ ጥያቄ በእኩልነት ላይ መሰረትዋን ያኖረች ጠንካራ ሃገር እንጂ እወክለዋለሁ የሚለዉን ህዝብ እንኳን በበለጠ የሚያፍን የፓርቲ ስም አይነት አይደለም፡፡የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራምና የኛ ራእይና በኛና በህዝብ ልብ እንዲሁም በሌሎች ፓርቲዎች ዉስጥ እንደሚገኝ አልገባቸዉምና ፓርቲን ሲነጥቁ ሰላማዊ ትግሉን የገደሉ፤እኛንም የበተኑ መስሎአችዋል፡፡የለዉጥና የአንድነት ሃይል ይበልጥ ይጠናከራል እንጂ አይበተንም፡፡እርግጥ ነዉ የመድበለ ፓርቲ ስርኣትን አደጋ ላይ ጥለዉታል፡፡ህዝባዊ ሰላማዊ ትግሉ ላይ ግን ጉልበትና ተጨማሪ እድል ጨምረዉለታል፡፡ የአንድነትና የለዉጥ ሃይሎች ዛሬም ይበልጥ ቁርኝነታችንን በማጠንከር ለሰላማዊ ትግሉ መጎልበት ያለንን አቅም ልናበረክት ይገባል፡፡ሁላችንም እድሉን እንጠቀምበት፤የጠበቡ ቤቶችንም ለሁሉም እንዲሆኑ ባፋጣኝ እናስፋቸዉ !
ይህ ተዉልድ የቃል እዳ አለበት፤እነአንዷለምም እነ አሞራዉም የሚሉቱና እያሉ ያሉቱ ይህን ነዉ፤ ፍትህና ነጻነት በኢትዮጵያችን በትግላችን ይሰፍናሉ!!

በአህጉረ ስብከት እና በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም በተደረገው የአራት ዓመታት መተባበር ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት በጥምቀተ ክርስትና የተጨመሩት ምእመናን ቁጥር ከ፴ ሺሕ በላይ ደርሷል፡፡ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በወንጌላዊው ቅዱስ ፊልጶስ የተጠመቀበትን የፊልጶስ ምንጭ (ቤት ሶሮን) በማቅናት የቤተ ፊልጶስ ገዳም (ቤተ ክርስቲያንና የመነኰሳት መኖርያ) የመመሥረት ውጥን ሳይፈጸም ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ የፊልጶስ ምንጭን ይዞታ በማስከበር ጥንተ ክርስትናችን …

‹‹የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ››
መግቢያ መውጫ አሳጥቶ፤ የወንድ በር እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በማን አለብኝነትና በትምክህት ስነልቦና ተወጥሮ በአፈና ጅራፉ ሲገርፈን ፀጥ ብለን የምናይበት የፈሪ ልብ፤ መጠን ያለፈውን የጭቆና ቀንበር የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም፡፡
አዎን ኢህአዴግ የደም መስዋዕትነት የከፈልኩበትን ስልጣን በቀላሉ አለቅም በሚል የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርግ ሁሉ እኛም ጓዶቻችን የታሰሩበትን ትግል እና ፓርቲ ወደጎን ትተን የትም አንሄድም፡፡ አንዱአለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሀ ደስታ፣ አግባው ሰጠኝ እና ሌሎቹም የታገሉለትን አላማ ከግብ ሳናደርስ ወደኋላ ማለት የለም፡፡
ትግሉ ሰላማዊ እና ሰላማዊ ብቻ እንዲሆን ከአንድ ወገን ብቻ (ከተቃዋሚዎች በኩል) እየተደረገ ያለውን ጥረት ኢህአዴግ እንደፈሪነት እየቆጠረው በትዕቢት ተወጥሮ ያስራል ይገላል፡፡ ነገም ኢህአዴግ ከዚህ የተለየ ነገር አያደርግም፡፡
ፓርቲያችን አንድነትን ለጀሌዎችህ ስትሰጣቸው እጃችንን አጣጥፈን ዝም ብለን አናይህም በሚል ነገ የአንድነት አባላቶች እና ደጋፊዎች ሰልፍ ሲወጡ ወያኔ እንደለመደው ያስራል፡፡
ዛሬ በልሳኑ ኢቲቪ/ኢቢሲ ደግሞ ሰማያዊ ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን እሰራለሁ አመፅንም እጠራለሁ ብሏል ሲል በሬ ጥጃ ወለደ ዲስኩሩን ደስኩሯል፡፡
አንድነትን ለእነ ትዕግስቱ አወሉ ሰጥቼ እውነተኛ አመራሮቹንም አስሬ አፈርሰዋለሁ፤ ሰማያዊን ደግሞ አመፅ ሊጠራ ነው በሚል ፓርቲውን አግዳለሁ አመራሮቹንም አስራለሁ በሚል ስሌት እየሰራ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልፅ ሆኗል፡፡
እንግዲያው ፓርቲዎችን ከዘጋ፣ ህጋዊ አመራሮችንም ካሰረ እና ሰላማዊውን መንገድ ከዘጋው የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን ይቀይራል፡፡
ጓዶቹ የታሰሩለትን ፓርቲ፣ አላማ እንዲሁም ትግል ወደጎን ትቶ የሚሄድ የለምና አሁን ትግሉ ሞትን ፊት ለፊት የመጋፈጥ እና ነፃነትን የመሻት ነው፡፡ ‹‹የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ›› እንዲል ጋዜጠኛው ነቢዩ፡፡

አንለያይም ሞትም ቢመጣ!!!
‪#‎እናቸንፋለን‬ Eyasped tesfaye

ቃጠሎው ለአትክልት ልማት ከተደረገ ምንጣሮ ጋራ የተያያዘ መኾኑ ተጠቁሟል በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ደን ውስጥ ዛሬ፣ ጥር ፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡30 ላይ የተቀሰቀሰው እሳት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ፡፡ ቃጠሎው በቁጥጥር ሥር የዋለው ከቤተ ክርስቲያኑ በግምት ከመቶ ሜትር ባነሰ ርቀት ላይ በደረሰበት ኹኔታ ነው ብለዋል – እሳቱን በማጥፋት የተራዱ የዐይን እማኞች፡፡ …

ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በ1901 ዓ.ም. በፀለምት /ሰሜን ጎንደር/ ተወልደው ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ትምህርት ቤት ገብተው ንባብና ዳዊት እንዲኹም ፀዋትወ ዜማ አጠናቅቀው ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ማዕርገ ዲቁናና ማዕርገ ቅስና ተቀብለዋል፡፡ በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ገብተው ለዘጠኝ ዓመታት ያኽል (ከ1933 – 1942 ዓ.ም.) ሥርዓተ ገዳሙን ከአጠኑና በግብዝና ከአገለገሉ በኋላ …

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግብጽ የአምስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ነገ፣ ጥር ፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ማምሻውን ወደዚያው እንደሚያመሩ ተገለጸ፡፡ የመንበረ ተክለ ሃይማኖት ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ግብጽን የሚጎበኙት፣ ከመንበረ ማርቆስ ፻፲፰ኛ ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ በተደጋጋሚ ሲቀርብ በነበረ ግብዣ እንደኾነ ተገልጧል፡፡ ፓትርያርኩ ከጥር ፪ – ፮ ቀን በግብጽ በሚኖራቸው …

መሬት በካሬ በሺሕዎች ዋጋ እያወጣ የቤተ ክርስቲያን በ1.50/2.00 ተከራይቷል ሀብትና ጥቅሟን የሚያስጠብቅ የኪራይ ተመን ፖሊሲ ጥናት ተጀምሯል የጥቂት አድባራት ሓላፊዎች እንቅስቃሴ ጥናቱን እንዳያኮላሸው ተሰግቷል የአለቆች የመኪና ሽልማት የአማሳኞች ከለላና ለብልሹነት በር የሚከፍት ነው *       *       * የኪራይ ውሎችንና ሌሎች ሰነዶችን በመደበቅ በአግባቡ ያለማቅረብ፣ የጥናቱን ዓላማ በማጣመም ተቃውሞ ለማነሣሣት መሞከር፣ የልኡካንን ስም ማጥፋትና ሥራውን ማጥላላት ከቀንደኛ …

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ተዋሕዶ በተወለደ ጊዜ በቃል ርስትነት ሰው እግዚአብሔር ኾነ፤ በሥጋ ርስትነት አካላዊ ቃል ሰው ኾነ፤ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ይህን ተዋሕዶ የተመለከቱ የሰማይ ሠራዊትም አካለ ሰብእን በተዋሕዶተ ቃል ለአምላካዊ ክብር ላበቃ ለእርሱ ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን፤ ሰላምም በምድር ይኹን፤ በጎ ፈቃዱም ለሰው ይኹን›› ብለው በደስታ ዘመሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን …

ከምንም በላይ ግን ያኔ ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው !
—————————- YIDNEKACHEW KEBEDE ——————————————
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተ አሁን ሦስተኛ ዓመቱ ነው፣የአገራችን አሉታዊ እና አዎንታዊ ፖሊቲካ ድርጊቶችና ክስተቶችን በመመርመር የመፍትሔ አካል ለመሆን በአገር ወዳድ ኢትየጵያዊያን ታህሳስ 22/2004 ዓ.ም በይፋ ተመሰረተ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሰላማዊ ትግል በማድረግ ፣የዜጎች የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ አባላቱ እና ደጋፊዎችሁ እያሣየነው ያለው ቁርጠኝነት እና ታማኝነት ለፓርቲያችን ጥንካሪ ዋንኛ መሠረት ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ከምስረታው ጀምሮ ያስመዘገባቸው አኩሪ ድሎች፣ በአገራችን እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ቁጥራቸው ከበዛ ፓርቲዎች ተርታ፣ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠሩ አንዱ ለመሆነ ችሎአል፡፡ፓርቲያችን ከተመሠተር እና ወደ እንቅስቃሴ ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ፣በኢትዮጵያዊያን ካለው ተቀባይነት እና በገዥው መንግስት ላይ እያሣደረ ያለው አስጨናቂ ተፅኖ በመመልከት አንዳንድ ታዛቢዎች ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? በማለት ይጠይቃሉ፣ መልሱ ግን አጭር ነው፡፡ እሱም ጠንከራ ጓዳዊ ትስስር ፣ጥልቅ የሆነ የአገር ፍቅር ስሜት፣ለዓላማ መሞት፣ በእውቀት እና በእውነት ላይ የተመሰረት ሰላማዊ ትግል ተግባሪዊ ማድረግ ፣ለፓርቲያችን ውጤት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡
ይህ ማለት ግን ፓርቲያችን ሊደርስበት ካሰበው ደረጃ እጅግ በጣም ትንሽ መሆኑ ሁላችንም የምንረዳው ሃቅ ነው፡፡ የሁላችንም የጋራ ዓላማ፣ ህዝብ የአገሩና የሥልጣን ባለቤትነቱ እንዲረጋገጥ ማድረገግ ነው ! ይህን ለማሳካት አሁን ላይ ፓርቲያችን ያስመዘገበው ድል የዋናው ትግላችን ውጤት ማሣያ መለኪያ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ከትግሉ ጅምሮ አንስቶ የጠልፎ መጣል የተለመደው አዙሪት ፓለቲካ፣ ፓርቲያችን ፈተና ውስጥ የከተተው ቢሆንም በአመራሩ ጠንካራ ውሳኔ ከገጠመው ፈተና በብቃት ለመወጣት የተቻለው ሲሆን፣ወደፊትም እንዲኸ ዓይነቱ ክስተት እንዴት መወጣት እንዳለበት ት/ት ያገኘበትም መልካም አጋጣሚ ጭምር ነው፡፡
ፓርቲያችን ከሌሎች በአገር ውስጥ ከሚንቀሣቀሱ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በመተባበር መጪው አገር አቀፍ ምርጫ 2007፣ ፍታሓዊ እና ዲሞክራሳዊ እንዲሆን ጠንክሮ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣በ2005 ዓ.ም ሊካሄድ ታስቦ የነበረ የአካባቢ ምርጫ፣ ገዥው መንግስት በቻውን ተወዳድሮ ብቻውን ያሸነፈበት የይስሙላ ምርጫ መሆኑን የ33 ፓርቲዎች ጠንካራ ትብብር ያስገኘው ውጤት ነው ! የዚህም ውጤት ባለቤት ከሆኑ ፓርቲዎች ውስጥ ሰማያዊ ከዋናዎቹ አንዱ ነው፡፡አሁንም ወደፊትም ለአገር እና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ፓርቲያችን በጥናት ላይ የተደገፈ ከእውነተኛ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር የሚያደርጋቸው ማናቸውም ዓይነት ግንኙነት በፓርቲያችን ደንብ መሠረት ገደብ የተጣለበት አይደለም፡፡
ገዥው መንግስት የፓርቲያችንን ጥንካሪ በአግባቡ በመረዳት፣በምናደርጋቸው ሰላማዊ ትግል ምክንያት በመፍጠር በተደጋጋሚ ከሚወስዳቸው የእስራት እና ደብዳባ እርምጃ ባለፈ ፓርቲያችንን ለማፍረስ በግልፅ እና በስውር እየተነቀሣቀሰ ይገኛል፡፡ከዚህም በላይ የፓርቲያችን ሰላማዊ ተጋይ አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአ/አ፣ አቶ በፍቃዱ አበበ ከአርባምንጭ እና አቶ አግባው ሰጠኝ ከሰሜን ጎንደር በሽብርተኝነት ከሱ እያሰቃያቸው ይገኛሉ፡፡ይሁን እንጂ የጀመረነው ሰላማዊ ትግል ከዚህም በላይ ዋጋ እንደሚያስከፍል ቀድመን የተረዳነው ስለሆነ ወደፊት እንጂ ወደ-ኋላ ማለት በእኛ ዘንድ ነውር መሆኑ ጠንቅቀን እናውቃለን !
ፓርቲያችን ባሣለፈው ሦስት ዓመታ ውስጥ የገጠመው ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ማንኛወም ጠንካራ ፓርቲ ሊገጥመው ከሚችለው የተለይ ነገር አይደለም ፡፡ሆኖም ግን ያጋጠሙት ችግሮች ለመፍታት የተሄደበት መንግድ ማንኛውም ፓርቲ እና የፓርቲ አባላት ከሚሄዱበት በአንፃራዊ እጅግ በጣም የተሻለ ነበር ፡፡አሁንም ወደፊትም ችግሮች መኖራቸው የማይቀር መሆኑ ታሣቢ በማድረግ፣ የፓርቲው አባል የሆን ጥልቅና ዝርዝር ውይይት በግልፅ በማካሄድ ክፍተቶቻችን እንደምንሞላ ተስፋ አድርጋለው፡፡
ከምንም በላይ ግን ያኔ ገና ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው !ለዚህም በመብቃታችን መስራች አባላት ለሆን እንኳን ደስ አለን፣አላችሁ! ለማለት እወዳለው፡፡
የጀመራችሁት አገር የማዳን ትግል የእናተ የመስራቾች ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው !በማለት ከፓርቲው ምስረታ ጀምሮ እስካሁን ሰማያዊን በመቀላቀል በአመራርነት እና በአባልነት በማገልገል ፣አኩሪ የትግል መሰዋትነት እየከፈላችሁ ለምትገኙ ለገዥው ለወያኔ መንግስት የእግር እሳት ለሆናችሁ የእኔ ትውልድ ጓዶች እንኳን አደረሳችሁ !
ፓርቲያችን አሁን ላይ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በአሳብ እና በገንዘብ እየረዳችሁ ለምትገኙ በአገር ውስጥ እና በውጪ የምትገኙ ድጋፍ ሰጪዎቻችን ፣ድካማችሁ ፍሬ እያፈረ በመሆኑ የሚሰማችሁ ደስታ ለተጫማሪ ድጋፍ እንደሚነሳሳችሁ ተስፋዬ የበዛ ነው !ከምንም በላይ ግን ሁሌም ለማይለይን የሃሳብ እና የገንዘብ ድጋፋችሁ አገራዊ ግዴታችሁ ቢሆንም፣ በቀናነት እና በአገር ወዳድነት ለምታደርጉት ድጋፍ ምስጋና ተገቢ ነው፡፡ምስጋናውን ከአክብሮት ጋር እንድትቀበሉ በመጠየቅ ፣ለዚህ በመብቃታችን እንኳን አደረስን በማላት የ3ኛ ዓመት የእንኳን አደረስን የግል መልእክቴን በዚህ አጠቃልላለው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
Image

‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ ከወንድሞቻቸው ጋራ ብዙ ትግል ያደረጉ አለኝታ ሊቅ ነበሩ፤ እርሳቸውን ማጣታችን ትልቅ ጉዳት ነው፤ ሐዘኑ የልጆቻቸውም አይደለም፤ ሐዘንተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ እግዚአብሔር ለዚኽች እናት ቤተ ክርስቲያን እርሳቸውን የመሰለ ይተካልን ከማለት በቀር ምንም ማድረግ አንችልም፡፡›› ከዘመናችን የቤተ …

ከትምህርት ቤትና ከመጻሕፍት ያገኙት ዕውቀት አራት ዓይና ያደረጋቸው ሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ በተጠያቂነት ደረጃ የሚገኙና አገልግሎታቸውም ሙሉ ነበር፡- ቀዳሽና መዘምር፤ ጋዜጠኛና ሰባኬ ወንጌል፤ ጸሐፊና ተርጓሚ፤ አስተዳዳሪና መምህር፤ የአውራጃ አብያተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፤ ኤርትራን ጨምሮ የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስምንት መምሪያዎች ምክትልና ዋና ሓላፊ፡፡ ሊቁ በሓላፊነት በተመደቡባቸው ቦታዎች …

ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንና አገራችን ኢትዮጵያን በክህነት፣ በሊቅነት፣ በመምህርነት፣ በአስተዳደር እና በጸሐፊነት ሞያቸው በብቃትና በትጋት ሲያገለግሉ የኖሩት ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ዐረፉ፡፡ የሊቁ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል ሞተ ዕረፍት የተሰማው÷ ዛሬ፣ እሑድ ታኅሣሥ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ቀበና መካነ ሕይወት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ …

በአስመራ የመሸጉ ተቃዋሚዎች እና የሻእቢያ ግፍ
Image

አንደኛ – በሻእቢያና በወያኔ ልዩነት የለም ፤ ጠባቸው በራሡ ሻቢያ ወያኔን አንስቶ በሌላ ትግሬ መተካት ይፈልጋል እንጅ ከወንድሞቹ “ትግራዋይ” ጋር ምንም ፀብ የለውም ደምህት የሚባለው የትግሬ ድርጅት ባጭር ጊዜ የት እንደደረሰ ማየት ይቻላል፤ ወያኔም እንደዛው ምንሊክ ነው ከወንድሞቻችን የለየን እያሉ እየነገሩን ነ።

ሁለተኛ ፦ ከደምሕት በአራት አመት ቀደም ብሎ የነበረው አርበኞች ግንባር አመራሮቹ ታስረዋል እንደውም ኮለኔል ታደሰን ሻብያ ገድሏቸዋል ።በርካታ የአርበኞች ግንባር አባላት ታስረዋል ትግሉን ጥለው ተሰደዋል:: በቅርቡ የአማራ ንቅናቄ የሚባሉት በኤርትራ ያለው ትግል የውሸት ነው በሻእቢያ ቤት ሆኖ ነጻነት የለም መውጣት አለብን ብለው ስላሉ አምስት አባሎቼን ሻቢያ አፈነብኝ ሲል ተሰምቷል፤ ልብ በሉ እንኳን መደራጅት በቃን ብለው ከኤርትራ መውጣት አልቻሉም ።

ሶስትኛ :- ግንቦት ሰባቶች ግልጽ የሆነ አድር ባይነት እያሣዩን ነው ፤ እነሱ የሚሉት እዛ የታሰሩት ከኢሳያስ ጋር ችግር ስላለባቸው ነው ይሉናል ። የምን ችግር ብለን አማራ ፎርስ የሚባሉትን ስንጠይቅ ሻእቢያ እንደህጻን ልጅ “ሁን” የሚልህን ከመሆን ውጭ እንዲህ አደርጋለሁ ማለት ፈጽሞ አይታለምም ይሉናል ። እውነት ነውም ። ግንቦቴዎች ግን ይህን ተቀብለው እየሰሩ ነው ። ልብ አድርጉ ኤልያስ ክፍሌ አስመራ የኢትዮጵያን ሪቪው ቅርንጫፍ ሊከፍት ከሻብያ ጋር ተስማምቶ ነበር ፤ የኮለኔል ታደሰን መታፈን እንደሚቃወም ስለጻፈ ብቻ ከሻእብያ ጋር ተጣልቷል ፤ ኢሳት ኤርትራ ውስጥ ስለሚደርሰው ሰቆቃ ሲዘግብ ሰምታችሁ ታቃላችሁ ? አይችልም ። አንዱ የሚረዳው ሻእቢያ እንደሆነ የዶክተር ብርሀኑን ድምጻቸውን ሰምተናል (የሚረዳው ሲባል ለድርጅቶች የሚገባው ገንዘብ መጀመሪያ ሻእብያ ላይ ነው ፣ ያኑ ገንዘብ ነው የሚስጣቸው እሱ የፈቀደውን እና እንዴት ነው ኢሳትስ አለቃየ ሻእብያ ይሄን በደል ሰራ ብሎ የሚናገረው ?)

ልብ ያለው ልብ ይበል ሻእብያ ወያኔ ቢጠላ ኢትዮጵያን ወደደ ማለት አይደለም ። ወያኔም እንደዛው ። ሻእብያ ትናንት ኢትዮጵያን የመቶ አመት የቤት ስራ ስጠሓት ብሎናል ። መቸም ቢሆን ኢትዮጵያን አይወድም ። አትልፉ ። ለምን አርበኞችና ግንቦት ሰባት አልታጠቁም ደምሒት ባጭር ጊዜ ካሥር ሺ በላይ ሰራዊት አለው ። ሁለቱ 500 የሚሆን ታጣዊ አላቸውን ? ይሄ ሆን ተብሎ በሳይካተሪስቶች የኢትዬጵያን ህዝብ ለዛላለሙ ልቡን ለመሥበር የተቀየሰ መንገድ ነው ። እንዴት እንደሚሆን ወደፊት የምናየው ነው ።

ባሁኑ ስዐት ሻእቢያ ሀገር ያለው ነገር ፡ ወያኔ ኦሕዴድና ብአዴን ብሎ እንዳስቀመጣቸው ያሉ በደምሕት ስር ቅጥረኛ ሆነው ሊገቡ ያሰፈሰፉ ናቸው ። እነሱ የሚሉት ወያኔ ይውደቅ እንጅ ነው ፤ እውነታው ወታደራዊ መንግስት ሆኖ ነው የሚመጣው ከዚያ ቡሃላ ትግራይና ኤርትሬ “ፒስ” በሚል ቅኝ ግዛት ውስጥ ለዘላለሙ ትወድቃለህ ።

ግንቦቴዎችን ለመቃወም ምንም አልፈራም ምክኒያቱም አሥመራ የሚያሥገርፉት ኢትዮጵያውያንን ነው በተለይ አማራውን ፤ ድርጅቱ ለይሥሙላ ያማራ ነው ተብሏል ። ግንቦት ሰባት NAIVE ነው ፤ ዋለልኝ ከግንቦት ሰባት በጣም በጣም ላማራዎች ይሻላቸዋል ብየ እላላሁ ።ግንቦት ሰባት ከማንም ድርጅት ሲነጋገር ተሰምቶ አይታወቅም ከ FIRST OROMOዎች ጋር ብቻ እንጅ ። ከሌሎች ጋር መነጋገር የማይችሉበት ምክኒያት መሰረት ሥለሌላቸው ብቻቸውን በሜድያ ህዝብ አታለው መያዝ ስለሚፈልጉ ብቻ ነው ።ግንቦቴዎች የትም እንደማይደርሱ እስረግጬ ስነግራችሁ ህብረትሰቡን ግን ላንዴና ለመጨርሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊ የሚባል ድርጅትን እርግፍ አድርጎ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደርገዋል ።የሻእብያን ግንቦቴዎች ማሸነፍ የምንችለው ሜድያ ሲኖረንና አስመራ የሚሰራውን ግፍ ማጋለጥ ስንችል ብቻ ነው ።

በአድባራት አለቆች ላይ የተላለፈው ውሳኔ ‹‹ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው›› /ፓትርያርኩ/ ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕገጋት አሏት፤ ማእከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል፤›› /ሲኖዶስ/ ልዩ እና አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ስለ መጥራት ምክክር መደረጉ ተጠቁሟል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፸፱፤ ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹በቤተ ክርስቲያን አባቶች እና …

Image
ከሠሞኑ ወደግብፅ የሚያቀና ህወሀታዊ የልዑካን ቡድን ሲቋቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊጠብቀው በማይችለው መልኩ የልኡካን ቡድኑ ውስጥ የአንድ ሠው ስም ተሠማ “ግርማ ሠይፉ” የሚል በርካቶች ተገረሙ ወይ አንቺ ሐገር ሲሉም አዘኑ፡፡ ከዚህ ቀደም ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ ተብለው በተቀመጡባቸው ያለፉት 4 ዓመታት ለሐገራችን ፖለቲካ ያንን ያህል ለውጥ ባያመጡም፤ የህሊና እስረኞቹ ይፈቱ ዘንድ አሁንም ያንን ያህል ጠንከር ያለ ስረ ባይሠሩም አቶ ግርማ ሠይፉን ሌሎች አካላት ሲተቿቸው ግርማ ሠይፉን ደግፈው ከሚቆሙ አካላት መካከል አንዱ እኔ ነበርኩኝ ብዬ አስባለው፤ አስባለው ያልኩት ስለግርማ ሠይፉ ከኔ በላይም የሚያስብ ሌላ ህወሀት የተሠኘ የሠዎች ስብስብ መኖሩን ስላልተረዳሁና በቅርቡ እየታዩ ያሉትን የግርማን መንሸራተቶች ባለመመልከቴ ነበር፡፡

በሐገራችን ፖለቲካ ማየት ከማንፈልጋቸው ነገሮች የከዳተኝነት ፖለቲካ አንዱ እና ዋነኛው ነው፤ ይህ ህዝብ ለፍቶ ከሚያገኘው የወር ገቢው ላይ ግብር ተወስዶበት ፓርላማ ለሚገኙ የህዝብ ተወካዮች በአበል እና በደመወዝ መልክ ይሠጣል ህዝቡ ይህንን የሚያደርገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተሠኘው የሚገኙ አባላት መብቴን የሚያስከብር ህግ ያወጡልኛል፤ ስለእኔ መብት ስለቆሙ የታሠሩ የህሊና እስረኞችን የበላይ አካል እንደመሆኑ ያስፈታልኛል ብሎ አለመሆኑ እሙን ነው ምክንያቱም በህወሀት ፓርላማ ውሳኔ ችግሬ ይፈታልኛል ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ እርሱ የህወሀት አባል መሆን አለበት ሆኖም ተባራሪ ሆነው ፓርላማ ውስጥ የሚታዩ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የህዝብ ችግር ያሏቸውን ጉዳዮች ነቅሰው አውጥተው ለፓርላማው ሲያቀርቡ እንመለከት ነበር እነዚህ ሠዎችም ሲከዱ ተመልክተናል እውን ግርማ ሠይፉ ካዳ? ግርማ ሠይፉ ካዳ ወይስ አሁንም ለህዝቡ እንደቆመ ነው የሚሉትን ጉዳዮች ከማንሳታችን በፊት ከግርማ ሠይፉ ጋር የልዑካን ቡድኑ አባላት ውስጥ የሚገኙ አባላት እነማን ናቸው የሚሉትን መመልከት ተገቢ ይመስለኛል፡፡

የህዝብ ልዑካን ቡድን ሲቋቋም መታሠብ ካለበት መካከል አንደኛው እና ዋናው ነገር የልዑካን ቡድኑ አባላት በህዝብ የታመኑ፣ በመልካም ስነምግባራቸው አርዓያ የሆኑ እና ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል ወደግብፅ ባቀናው የልዑካን ቡድን ውስጥ የተካተቱት ግን በየትኛውም መለኪያ የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ ከመሆን ውጪ የህዝብ አመኔታ ያላቸው ግለሠቦች አይደሉም፡፡ ከልዑካን ቡድኑ ውስጥ መካከል አንዱ ሠራዊት ፍቅሬ የተሠኘው ግለሠብ ነው፡፡ ይህ ግለሠብ ልክ እንደሌሎቹ የህወሀት አባላት እና አመራሮች ከወታደር ቤት ወጥቶ ሚሊየነር የሆነ ግለሠብ ነው፡፡ ሠራዊት ፍቅሬ የህዝብ ተወካይ መሆን የማይችልባቸውን ምክንያች ለማንሳት ያህል ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በአንድ ተማሪ ላይ በማን አለብኝነት የፈፀመውን የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ሠራዊት ፍቅሬ አስገድዶ ሊደፍረኝ ሲል አመለጥኩኝ ያለችውን ግለሠብ አዲስ አድማስ የተሠኘው ሐገር ቤት የሚታተም ጋዜጣ አነጋግሯት እንደነበረና ከጥቂት ቀናት በኋላ በሠራዊት ፍቅሬ የመድፈር ሙከራ የተደረገባት ተማሪ ሁኔታ ተደባብሶ ቀረ ወጣቷ አሁን የት እንዳለች እንኳን አይታወቅም አዲስ አድማስም ከህወሀት ሠዎች ሊደርስበት የሚችለውን ዛቻ በማሠብ ተወው ይህንን ድርጊት የፈፀመው ሰራዊት ፍቅሬ ነው አንዱ የዚህ ልዑክ አባል፡፡

ሌላኛው የልዑካኑ ቡድን አባል ቴዎድሮስ አድሐኖም ወይም እንደሱ አጠራር ቴድሮስ አድሐኖም ነው፡፡ ይህ ግለሠብ አምና በዚህ ሠዓት ሣውዲ አረቢያ ይገኙ ለነበሩ ሠዎች ሞት እና እንግልት ተጠያቂ ሊሆን የሚችል ሠው ነው፡፡ ቴዎድሮስ አድሐኖም የውጪ ጉዳይ ሚኒስተሩነቱን እና የህወሀት አባልነቱን ተጠቅሞ ለሳውዲአረቢያ የንጉሳውያን ቤተሠቦች በላከው ደብዳቤ ኢትዮጵያውያኑ ከሳውዲ ኢሠብዓዊ ድርጊት ተፈፅሞባቸው እንዲወጡ ማድረጉ ይታወሳል ይህ ግለሠብ ስለእውነት እና ስለህዝብ የቆመ ቢሆን ኖሮ የሳውዲ ንጉሶችን አሳምኖ የኢትዮጵያውያን መውጫ ቀን በማስረዘም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከእልቂት እና ከግፍ ያድን ነበር ሆኖም ዛሬ ይህ ግለሠብ የሠራቸው ወንጀሎች ተደብቀውለት ዛሬ የህዝብ ልዑካን ተብሎ ተሠይሞ ይገኛል፡፡ ግርማ ሠይፉም ከእነዚህ ሠዎች መካከል ይገኛል የህዝብ ልዑካን ቡድን ተብሎ፡፡ ከሠራዊት ፍቅሬ እና ከቴዎድሮስ አድሐኖም ጋር አብሮ መስራትን የመሠለ ምን ከዳተኝነት ይኖር ይሆን?

ግርማ ሠይፉ የልዑካን ቡድኑ ውስጥ መካተቱን ሳይነግረን ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ “ይህ የአሁኑ ሠንደቅ ዓላማ ለእኔ ከበፊቶቹ ይሻለኛል፤ ሁሉም የታሠሩት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ንፁህ ናቸው ብዬ አላምንም” ምናምን የሚሉ በህዝብ ላይ የተቀለዱ መጥፎ ንግግሮችን በኢንተርቪው እና በብሎጉ ላይ አሰምቶናል በተጨማሪም አምና አንድነት ጠርቶት በነበረው ሠላማዊ ሰልፍ ላይ ሠልፈኛው ሲግናል አካባቢ ሲደርስ ሲግናል ለአንድ ጎሳ አባላት ብቻ የተሠሩትን ህንፃዎች ተመልክቶ ዝም ብሎ ማለፍ ያልቻለው ሠልፈኛ ሌባ ሙሰኛ እያለ ሲጮህ ዝም በሉ እያለ ሠልፈኛውን ከሀብታሙ አያሌው ለመነጠል ሲሞክር እንኳን በግርማ ላይ ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር አሁን ግን ከኢትዮጵያ የምንም ጊዜ ጠላቶች ጋር አበረ፡፡ የልዑካን ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሠዎች እኮ በበደኖ እና በአርባጉ የአማራውን ጎሳ የጨፈጨፉ፤ በአምቦ ንፁሐን የኦሮሞ ተማሪዎችን የገደሉ፤ ፤ በጋምቤላ ንፁሀንን ያስፈጁ፤ ፕ/ር አስራትን እና አሠፋ ማሩን የመሳሰሉ ድንቅ የሐገራንን ምሁራን ያስገደሉ፤ እስክንድርን፤ ርዕዮትን፤ በቀለ ገርባን፤ ኤርባና ሌሊሳን፤ የሺዋስ አሠፋን፤ አብርሐ ደስታን፤ ዳንኤል ሺበሺን፤ አበበ ቀስቶን፤ ናትናኤልን፤ ሐብታሙን፤ እና ሌሎችንም ያሠሩ፤ ከጥቂት ቀናት በፊት እንኳን የሠማያዊ ፓርቲን እና የትብብሩ አባላትን ቶርች ያደረጉ፤ በትላንትናው እለት ባህርዳር ላይ ህዝብን ያስፈጁ ሠዎች ጥርቅም ውስጥ ግርማ ዘው ብሎ የገባው፡፡

ግርማ ቆም ብሎ አስቦ ህዝቡን ይቅርታ ብሎ ጠይቆ እራሱን ከፖለቲካ ከማግለል ውጪ ሌላ አማራጭ ይኖረዋል ብዬ አላስብም ፓርቲው አንድነትም ቢሆን እንደግርማ ሠይፉ ያሉ አባላትን ይዞ መቀጠሉ ለፓርቲው አደጋ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝቡን ይቅርታ ሊጠይቅ እና ግርማ ሠይፉን ሊቀጣው ይገባል ይህ ካልሆነ ግን ለወትሮውም በሐገራችን ፖለቲካ ተስፋ ለቆረጠው ህዝባችን ጭራሹኑ ፊቱን እንዲያዞር የሚያደርግ ታሪክ ሲወቅሠው የሚኖር ተግባር ከዛም አልፎ ሌሎች እየለፉ ያሉ ፓርቲዎች ላይ ህዝቡ እምነት እንዳይኖረው የሚያደርግ አስወቃሽ ስራ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ከግርማ እና ከፓርቲው መልስ ያስፈልጋል
#ሁኔአቢሲኒያ

የግንቦት ሰባት ከፍተኛ ኣመራሮች ኣስመራ ገቡ ሲሉ የድርጅቱ ካድሬዎች ተናግረዋል

በዚህ ሰሞን የሚወጡ ዘገባዎች አንደሚያመለክቱት የተከበሩ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አና የግንቦት ሰባት ሚዲያ ኢሳት ሃላፊ አና የግንቦት ሰባት ምክትል የሆነው ኣቶ ነእመን ዘለቀ ያሉበት ቡድን ኣስመራ ገብተዋል ሲሉ የድርጅቱ ካድሬዎች ውስጥ ውስጡን የሚያናፍሱት መረጃ ጠቁፙል፥፥

ዶክተር ብርሃኑ ኣስመራ በተደጋጋሚ በኢሳያስ ኣወርቂ ተጠርቶ አንዳልሄደ የሚናገሩት ኣስተያየት ሰጪዎች በሃሰት አና በተስፋ ህዝቡን ለመደለል የሚደረግ ፕሮፓጋንዳ ነው፥፥ተደብቆ መህዐድ ምን ኣስፈለገ ከሄዱ በህWላስ ለምን ይፋ ኣይደረግን ማበረታቻ ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል፥፥አንዲህ ኣይነት የውስጥ ሹክሹክታ ድርጅቱን ለፖለቲካ ኪሳራ አንዳይዳርገው ሲፈራ ከኣሁን ቀደም በኣንዳርጋቸው የመጣውን የፖለቲካ ቁስል ሳያክም ወሬ ማናፈስ አንደማያዋጣ ኣስተያየት ሰጪዎች ኣስረግጠው ተናግረዋል፥፥

Image
በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ለሽርሽር የሄዱት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች 12 ስዊድናውያን የተኩስ እሩምታ ወረደባቸው
ኢሳት ራድዮ ታህሳስ 6/2007 ዓም እንደዘገበው በግድያ ሙከራው ላይ የስዊድን የመገናኛ ብዙሃን በብዛት እየዘገቡበት መሆኑን ያብራራል።እንደ ዘገባው በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ለሽርሽር የሄዱት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች 12 ስዊድናውያን የነበሩ መሆኑን እና የተኩስ እሩምታ እንደወረደባቸው ይገልፃል።አቶ ሞላ ይግዛው በስዊድን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፎረም ምክትል ሊቀመንበር በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል –

”አስራ ሁለት የስዊድን ዜጎች አምባሳደሩን ጨምሮ ይላልእዛ ላይ አራት ሰዎች የጫነው መኪና ላይ ስዊድናውያንን ለመግደል ያለመ እና ያነጣጠረ ተኩስ ነው የተከፈተው።ከእዚህ ጋር በጥያየዘ ባለፈው ጊዜ H&M የተሰኘው ድርጅትን ያጋለጠ አንድ ጋዜጠኛ በእዛ አካባቢ ወይም ደቡብ ኢትዮያ የሚደረገውን ግፍ ለዓለም ማጋለጡ እና በዓለም የሌለ ዲክታተር መባሉ ይታወቃል።ከእዛ በፊት አንድ ቀን የስዊድን የጦር ፍርድቤት ያቀረብነውን የወንጀል ክስ ተቀብሎ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቆ ነበር።በመሆኑም ይህንን ያደረገው ወያኔ ነው ሌላ ሊሆን አይችልም” ብለዋል።

ኢሳት ራድዮ በመጨረሻ ላይ እንደገለፀው ጉዳዩን የስዊድን ጋዜጦች፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ሌሎች የመገናኝ ብዙሃን ሽፋን ቢሰጡትም ኢህአዲግ ም ሆነ የሚቆጣጠራቸው ራድዮ እና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም ያሉት ነገር እንደሌለ ይገልፃል።

Image
አዜብ መስፍን ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ የፓርቲው ሊቀመንበርና የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለመረከብ አቅደው እንደነበረ ታማኝ ምንጮች አጋለጡ። የደህንነት ዋና ሹም የነበረው ወ.ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከፊት በማስቀደም ወ/ሮ አዜብ የሞከሩትና በፓርቲው አንዳንድ አመራሮች “መፈንቅለ ድርጅት ሙከራ” ሲሉ ፈረጀውታል።

ከምንጮቹ የተገኘው ዝርዝር መረጃ ተከታዩን ይመስላል። አቶ መለስ ዜናዊ መሞታቸውን ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ሁለት አይነት ቡድኖች ብቅ አሉ። ወ/ሮ አዜብ የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን የጠ/ሚ/ር ስልጣኑን ለመረከብ ካልሆነም ምክትል ጠ/ሚ/ርነትን ለመቆናጠጥ ከፍተኛ ፍላጐት አሳደሩ። ከአዜብ ጐን የቆሙት በረከት ስሞኦን “የመለስን ራዕይ የማስፈፅመው እኔ ነኝ” ሲሉ ለካድሬዎቻቸው ቀሰቀሱ።

በአንፃሩ እነስብሃት ነጋ ከጀርባ የሚመሩትና ፀጋይ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ አርከበና ደብረፂዮን ያሉበት ቡድን በተቃራኒው ቆሞ በውስጥ አድፍጦ የፖለቲካ መስመሩን እያስተካከለ ነው። አዜብ ከጐናቸው ያሰለፏቸው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴ፣ ገ/ዋህድን እንዲሁም ሚሊየነሩ ነጋ ገ/እግዚያብሄር መቀሌ ድረስ ኔትዎርክ ዘረጉ። አዜብን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጐ ለማስመረጥ አዜብ የመደቡት በ10ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በአቶ ነጋ በኩል ወጪ እየተደረገ በነወ/ስላሴ አማካይነት ለበርካታ ካድሬዎች ይታደል ጀመር። አዜብ ያንን ሁሉ ገንዘብ ያለምንም ጠያቂ ፈሰስ ማድረጋቸውና ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነበር። ለካድሬዎች በነፍስ ወከፍ ከ3 እስከ 8 ሚሊዮን ብር ተከፋፈለ።

ካድሬው ድምፅ ለአዜብ በመስጠት የሕወሐት ሊ/መንበር ማድረግ እንዲሁም ወ/ስላሴን በፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት ለማስመረጥ በተጨማሪ ጌታቸው አሰፋን እንዳይመረጥ ማድረግ የሚሉ መመሪያዎች ገንዘቡን ለሚቀበሉ ካድሬዎች ጥብቅ መመሪያ ከነወ/ስላሴ ተላለፈ። ካድሬው እነወ/ስላሴ የሰጡትን ገንዘብ በመቀበል ትእዛዙን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ነገራቸው። ጉዳዩን ሰምተው እንዳልሰሙ የሆኑት እነጌታቸው አሰፋ በጐን ካድሬውን እያስጠሩ « የሚሰጧችሁን ገንዘብ ተቀበሉ። የሚሏችሁን እሺ በሉ። በጉባኤው ላይ ግን ከእኛ ጐን ትቆማላችሁ» ሲሉ በማስጠንቀቂያ መልክ ነገሩ። ካድሬው ከነጌታቸው ጐን እንደሚቆም ቃል ገባላቸው። እነወ/ስላሴ፣ አባይ ወልዱ፣ ገ/ዋህድ..እንዲሁም በባለሃብት ሽፋን የአዜብን ተልእኮ ለማስፈፀም ሲሯሯጡ የከረሙት ነጋ ገ/እግዚያብሄር ጉባኤው ሳምንት እየቀረው በመቀሌ “ቡቡ ሂልስና አክሱም” በመሳሰሉ ሆቴሎች ካድሬውን በግብዣ ሲያንበሸብሹ ሰነበቱ።

የጉባኤው እለት ደረሰ። ለሕወሐት ሊቀመንበርነት እጩዎች ሲጠቆሙ ወ/ስላሴ እጅ በማውጣት “አዜብ መስፍን” ሲል ጠቆመ። ተሰብሳቢው ድጋፍና ተቃውሞ ሲጠየቅ 12 ጣቶች (ድምፆች) ብቻ ሲደግፉ የተቀረው አዜብን በመቃወም ውድቅ አደረገው። አባይ ወልዱ፣ ወ/ስላሴ፣ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ ትርፉ፣ በየነ፣ ገ/ዋህድ…ለአዜብ ድጋፍ ከሰጡ 13 ድምፆች ይጠቀሳሉ። አዜብ « የመለስ ራዕይ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለማስቀጠል..» አልጨረሱም የመድረኩ መሪ ጣልቃ ገብተው « ስነ ስርዓት ..አሁን የእጩዎች ምርጫ እያካሄድን ነው» ሲል አርከበ ቀበል አድርግው « የመለስ ራዕይ የሚባል የለም። የፓርቲው ራዕይ ነው ያለው» ሲሉ አዜብ በግልምጫ እያዩ ተናገሩ። ካድሬው እንደካዳቸው ያወቁት አዜብ ንዴት በገፅታቸው ላይ ይነበብ ነበር። ብሽቀት የገባው ወ/ስላሴ እቅዳቸውን ጌታቸው እንዳኮላሸው የተረዳ ይመስላል። እጁን በማውጣት « ጌታቸው አሰፋ ለማ/ኮሚቴ አባልነት አይመጥንም። ሰካራም ነው፣ ሴሰኛ (ሴት በማማገጥ) ነው። ውሎና አዳሩ ሸራተን ነው። እንዳውም አቶ መለስ ዜናዊ በጌታቸው ዙሪያ ማጣራት እንዲካሄድ ያስጀመረው ምርመራ ነበር። ውሳኔ ሊሰጥበት ጫፍ ሲደርስ እንዳጋጣሚ ሞት ቀደመው። ስለዚህ ጌታቸው ለፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባልነት አይመጥንም» በማለት በእልህ ስሜት ይናገራል።

አስመላሽ ወ/ስላሴ (በቅፅል ስማቸው አባይ ነብሶ- በፓርላማ ከመለስ ዘናዊ ኋላ አዘውትረው የሚቀመጡና ጥቁር መነፅር የሚያጠልቁ አይነስውር) እጃቸውን በማንሳት በዚህ ዙሪያ መናገር እንደሚፈልጉ ይጠይቃሉ። ሲፈቀድላቸው እንዲህ አሉ፥ « አሁን ወ/ስላሴ እንዳለው በጌታቸው ዙሪያ ማጣራት ስናካሂድ ከነበርነው ሶስት ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ። እንድናጣራ ያዘዘን መለስ ነው። የቀረበልን ጥቆማ “ጌታቸው ቪላ ቤት ገንብቷል፣ ሙስና ውስጥ ገብቷል” የሚሉ ነበሩ። ረጅም ጊዜ ስናጣራ ቆየን። ነገር ግን የተባለውን ቤትም ሆነ በሙስና ያፈራው አንዳች ነገር ልናገኝ አልቻልንም። ከዚያ በጌታቸው ላይ ጥቆማውን ያቀረበው ወይም ያመጣው ማነው?.ብለን ስንጠይቅ ወ/ስላሴ መሆኑን አወቅን።

በወ/ስላሴ ዙሪያ ለምን ማጣራት አናካሂድም ብለን ጀመርን። በስሙ፣ በወንድምና እህቱ እንዲሁም በቤተሰቡና በሌሎች ግለሰቦች በሙስና መበልፀጉን አረጋገጥን» በማለት የሙስናውን ማስረጃ በዝርዝር አባይ ነብሶ ለጉባኤው አቀረቡ። ለማ/ኰሚቴ የተጠቆመው ወ/ስላሴ 2 ድምፅ ብቻ በማግኘቱና ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ ኩም አለ። ጉባኤው በነጌታቸው አሰፋ ድል አድራጊነት ተጠናቀቀ። የሙስናዋን ፋይል የያዙት ጌታቸው አሰፋ በቅድሚያ ያደረጉት ወ/ስላሴን ከስልጣን ማባረር ነበር። ከዛም እነገ/ዋህድን ጨምሮ ለአዜብ ገንዘብ ሲረጩ የነበሩትን እነነጋ ገ/እግዚያብሄርን በሙስናው ፋይል እስር ቤት መክተት የሚለውን እቅድ ተግባራዊ አደረጉ። የደህንነቱን ቢሮ እንዳሻው ይፈነጭበት የነበረውና የአቶ መለስና አዜብ ቀኝ በመሆን አገሪቱን በአፈና መዋቅር ሲያሰቃያት የከረመው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በበርካታ የደህንነት አባላት ጥርስ የተነከሰበት ጭምር ነበር። ይህን የሚያውቁት ጌታቸው አሰፋ በደህንነቶች ለተከታታይ ቀናት ወ/ስላሴ እንዲደበደብ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

Image

የጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን አስረድተዋል።

በብአዴን በኩል የአቶ በረከት ስሞን ከስልጣን መገፋት በደጋፊዎችቻቸውና አመራሩ በኩል ቅሬታ መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቹ በረከት ስሞን የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም አማካሪ ተብለው ቢሾሙም ነገር ግን በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ እንዳልተሰጣቸውና የተሰጣቸው ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ቢሮ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው በዚህ ቢሮ ኩማ ደመቅሳ እንደሚገኙና በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት አዲስ ቢሮ ተገንብቶ ይሰጣችኋል የተባለው ተግባራዊ እንዳልሆነ አያይዘው አስረድተዋል።

በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ የተሰጣቸውና ከአቶ ሃ/ማርያም እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ያልተለዩት አርከበ እቁባይ፣ አባይ ፀሐዬና ፀጋይ በርሄ ሲጠቀሱ በም/ጠ/ሚ/ር ቦታ ደብረፂዮን መኖራቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ለሕወሐት አመራሮች ሌላው ራስ ምታት የሆነባቸው የኦህዴድ ፓርቲ ከሕወሐት እኩል መገዳደር እያሳየ መምጣቱ ነው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኦህዴድ የተለያዩ የስልጣን ጥያቄዎች በማንሳት ድፍረት እያሳየ መጥቷል ብለዋል።

ሕወሐት የጠ/ሚ/ርነት ስልጣኑን መቆጣጠር የፈለገበት አንዱ ምክንያት ይህ መሆኑን ምንጮቹ አልሸሸጉም። በኦህዴድ በኩል የጠ/ሚ/ር ስልጣን ለኦሮሞ ይገባል በሚል ከዚህ ቀደም የነበረው የሕወሀት ስልጣንን አንሰራፍቶ የመያዝ አካሄድ መገታት አለበት የሚል አቋም እንደተያዘ ያስረዱት ምንጮቹ በተለይ የህወሀት አመራር የኦህዴድ አካሄድ እንዳልተዋጠለትና ከዚህ ቀደም ማን ጠ/ሚ/ር ስልጣን ይያዝ የሚለው የህወሀት ምክክር በእንጥልጥል ቆይቶ በቅርቡ ግን ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ስልጣኑን መያዝ አለበት የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ምንጮቹ አስገንዝበዋል። የደብረፂዮን ወደ ጠ/ሚ/ር ስልጣን የማምጣት እቅድ በተመለከተ አርከበ እቁባይ ተቃውሞ አሰምተው መከራከራቸውንና በመጨረሻ ግን ኦህዴድና ብአዴን ለመጨፍለቅ ሲባል አርከበ መቀበላቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። የህወሀት አመራሮች ከስምምነት የደረሱበትን ጉዳይ ከቀጣዩ ምርጫ በኋላ ጠ/ሚ/ር አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝን ከብቃት ማነስ ጋር በማያያዝ ከስልጣን ለማውረድና በምትካቸው የጠ/ሚ/ርነቱን ቦታ ለደብረፂዮን ለመስጠት መወሰናቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።

በእገዳው ቤተ ክርስቲያን ሕግን እንደጣሰች ቅ/ሲኖዶሱም አላዋቂ እንደኾነ ተደርጎ ተዘልፏል አማሳኞቹ ሐቅ ተናጋሪዎች ቅ/ሲኖዶሱ ደግሞ ጊዜ ያለፈበትን አፈና አንጋሽ ተደርጎ ተገልጧል የአማሳኞቹ ውንጀላ ከባድ ጥፋት ሳይኾን እንደ ‹‹ዳኅፀ ልሳንና የአፍ ወለምታ›› ተቆጥሯል የአማሳኞቹ ጉባኤ ሕግን የጣሰ ሳይኾን በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት እንደተሰበሰበ ተጠቅሷል የውሳኔውን አፈጻጸም የሚያግደው ደብዳቤ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ግልባጭ ተደርጓል ብፁዕ ዋ/ጸሐፊውና ብፁዕ ጠቅ/ሥራ …

1- ሁለቱም በፈጣሪ አያምኑም ( የራሴ የሚሉት እምነት የላቸውም)
2- የጦር አዛዦቻቸው::ሂትለር በራሱ ግዜ ሮሚዮን ማርሻል አድርጎታል –መለስ ሳሞራን < ጀነራል> አድርጎታል
3-ሂትለር ሁለት ልጅ ነበረው::መለስም ሁለት ልጆች አሉት
4-ሁለቱም በጅምላ ህዝቦችን ጨርሰዋል (የዘር ማጥፋት ፈጽመዋል)
5-ሁለቱም insomnia ይሰቃዩ ነበር :; ( የመተኛት ችግር ከተኙም ቶሎ አለመንቃት)
6-ሁለቱም የሶሻሊዝም issue ነበራቸው:;ለዚህም ማሌሊትን ልብ ይልዋል
7- በዘር እና በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፓርቲ በመፍጠርም ይታወቃሉ ::
8-ሂትለር ታላቅዋን ጀርመን ለመመስረት እቅድ የነበረው ሲሆን መለስ ደግሞ ታላቅዋን ትግራይን ..
9-E -ዲሞክራሲ ናቸው
10-ራሳቸውን በራሳቸው የፓርቲ እና የአገር መሪ አድርገው ሾመዋል Dagem Ahunem

Image

የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል። ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል። (በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል)

ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።

‹‹የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት የአገር ነው፤ ቤተ ክርስቲያንን ልናስቀድም ይገባል›› ፓትርያርኩ   ‹‹ገንዘብን አሸንፉት፤ መቃብርን አትርሱት›› /ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ/ ‹‹ሕዋሳት ድርሻ አላቸው፤ ሕዋሳቱ ካልታዘዙ ግን ችግር ይፈጠራል›› /አቡነ ቀሌምንጦስ/ ‹‹ሀገረ ስብከቱን የሚያመሰቃቅለው አሉባልታና ሐሰት መወገዝ አለበት›› /ዋ/ሥራ አስኪያጁ/ ‹‹ያልምዶት እንጂ እንኳን ደስ ያለዎት አንልዎትም›› /አስተያየት ሰጭ የደብር አለቃ/ ‹‹ንግግር ከማብዛት ይልቅ ወደፊት በየሥራችን ብንመዘን›› /ሌላው የደብር አለቃ/ …

ከ1300 በላይ አዲስ አማንያን በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተጠመቁ በዓመቱ 17‚000 አዲስ አማኞችን ለማፍራት በመርሐ ግብር የተያዘው ዕቅድ አካል ነው ከተጠማቂዎቹ፣ ከባዕድ አምልኮ የተመለሱ አርብቶ አደሮች እንደሚገኙበት ተመልክቷል *              *              * በዲዛይን ሥራው የማኅበረ ቅዱሳን ሞያዊ አስተዋፅኦ ከተገለጸበት አዲሱ የጂንካ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት (ምረቃ) ጋራ ጥምቀተ ክርስትና የተፈጸመላቸውና …

የጉልቾቹ ስም ብአዴን፣ኦህዴድ፣ደህዴን ሲባሉ የተሰሩትም ዴሞክራሴ ከተባለ ዘረመል(ሴል) ሆኖ ይህ ሴል ያለማችን ገራሚው የጉልቾች ሴል ተብሎ እንዲመዘገብ እራሱን ነፃ አውጭ ብሎ የሰየመው ህወሓት ባለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አድርጉዋል፡፡

ይህ ሴል በውስጡ ሂዎት የሌለው አርቴፊሻል የህወሓት የላባራቶሪ መመራመሪያ ሲሆን እስካሁንም ወደር ያልተገኘለት ሂዎት አልባ ተንቀሳቃሽ ቁስ ግን የዎያኔ መጠቀሚያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

አስገራሚው ነገር ህወሓት የሚባለው በድን የዴሞክራሴ ሴል ሰራሽ አካል የዴሞክራሴ ፅንሰ ሀሳብ የሌለው እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ብሎ የሰየመ ሆኖ አላማውም የትግራይን ህዝብ እና ህዝብ ብቻ ነፃ ለማውጣት የተቋቋመ ጠባብና ዘረኛ የፖለቲካ አጀንዳ ያነገበ መሆኑ ነው፡፡

ሌላው ገራሚ የሚያደርገው ነገር እራሱን ህወሓትን ጨምሮ ሌሎች ኦህዴድ፣ደህዴን በድን የዲሞክራሴ ሴል ውስጣቸው እንዳለ ተደርገው የተሰሩት ቁሶች ህዝብ የሚል ሌላ የሚያምታታ ማጭበርበሪያ ታቤላ የተለጠፈባቸው ሲሆን ብአዴን የሚለው ጉልቻ ግን ከህዝብ ይልቅ ብሄር የሚል መታወቂያ ተሰጥቶታል ምክንያቱም ይህ ስም ለህወሓት የፖለቲካ መሳሪያ በቀጥታ ላገልግሎት እንዲጠቅም ተፈልጎ ነው፡፡
እዚህ ጋር መጤን የሚገባው ነገር ብሄር በሚለው ስም ብሄርብሄረሰቦች የሚለውን ሌላ የፖለቲካ ትርፋ ለማምጣትና የሰደቅ አላማውን የቀድሞ ልዕልናውን ለማሳጣትና የምሐለኛውን ሴጣናዊ ምናምንቴ በብሄር ብሄረሰብ ስም ለመለጠፍ ተፈልጎ የተሰራ አገር የማፍረስ ደባ ነው፡፡

አሁን ህወሓት በዚህ መልኩ ጉልቻዎቹን ከሰራ በሗላ ሁሉንም አንድ ለማድረግ የተጠቀመበት ዘዴ ጉልቾቹ ከተሰሩበት በድን የዴሞክራሴ ሴል በቀጥታ ሴሉን በመውሰድ ኢህአዴግ ብሎ በመሰየም ዋና ህዝብን ለማወናበድ ወደሚጠቀምበት አዛኝ ቅቤ አንጉዋች እንደሚባለዉ የጭቃ እሾኩን በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ተከለ፡፡

አሁን የሚቀረዉ ቁጭ ብሎ በነዚህ ከንቱ ያትራፊነት የሴራ መረብ በመጠቀም ምሁር ነን የሚሉትን ሁሉ በማታለልና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይፈቀዳል፣መናገር ይቻላል፣መፅፍ ይቻላል እናም ሌሎች ኘሮፖጋንዳዎችን በመናገርና ህገመንግስት እያለው በሚጠራው ምናምንቴው ለይ የፃፈዉን በማየት ህብረተሰቡ እውነት መስሎት ተሸወደ ምሁሩም ተግባራዊ ለማድረግ ሞከረ ግን እንደማይቻል ሲያውቅ የታሰረውም ታስሮ ሞት የተፈረደበትም ተገደለና ጥቂት የማይባለው ወገኔ ሲሰደድ አብዛኛው ህብረተሰብ በሲቃይ መዓበል ውስጥ መፍተሄ አልባ የፅር ድምፅ እያሰማ በሐገሩ ባይተዋርና የበይ ተመልካች ሆኖ ተቀምጡዋል፡፡

ሶስቱ ጉልቾች የህወሓት የጀራ መጋገሪያ ምጣድ ለማስቀመጭያነት በቀጥታ የዋሉ ሲሆን አንዳንድ ግዜም ወጥ ለመስሪያ የሚጠቅም ድስት መጣጃዎች ሆነው እናያቸዋለን እዚህ ጋር ግን ሌላ ማስተዋል የሚጠበቅባችሁ ነገር የጉልቻዎቹ ትክክለኛ በድንነት የምትለዩት ምንም እሳት ቢነድባቸው ሚሊዮን እንጀራ ቢጋገርባቸው ቅንጣት የማይሰማቸው ስሜት አልባ እቃዎች መሆናቸዉ ነው፡፡

የሰወስቱ ጉልቾች አባላቶችና ደጋፊዎች ሆይ እባካችሁ ፈጣሪ ነፍስ ከዘራባችሁ ይህንን አንብቡትና የህወሓትን ስውር አደንዳ ከስር መሰረቱ ለመገርሰስ ሞክሩ ቢያንስ ለልጅ ልጆቻችሁ ታሪክ ነውና ንቁ፡፡ይሄንን ለማድረግም አይመሽባችሁም እስኪ ግማሾቻችሁ እንኩዋን በቃን ብላችሁ የዚህ አይነቱን የርግማን እንጀራ ከመብላት ተቆጠቡ ምክንያቱም አሁን የምትበሉት የህዝብ ስጋ ሲሆን የምጠጡትም የወገናችሁ እንባና ደም ነዉና ትውልድ ይዳን ትላንት የገደላችሁትና ያስገደላችሁት የግፍ ፅዋ ይብቃ እላችሗለሁ፡፡

ከላገሬ ኢትዮጵያ
03/03/2007
Image

ትንሽ የግል አስተያየት በሰማያዊ ላይ
==================== Girma Kassa
ኃዳር ሰባት ቀን በቤልሄር ሜዳ ሰማያዊ ፓርቲ ብዙም ስማቸው ከማይታወቅ ድርጅቶች ጋር በመሆን የአደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል። የአደባባይ ስብሰባ ማለት ብዙ ከሰልፍ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።
የሰማያዊ ፓርቲ ሰኔ ወር 2005 ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰልፍ በማድረግ ታሪክ የሰራ ድርጅት ነው። ወደ ሰባ ሺህ የሚሆን ሕዝብ በሰልፉ ተገኝቶ ነበር። ሰማያዊ ባደረገው ሥራ አንድነቶች ከእንቅልፋቸው ነቅተው የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል ተስፋ ሰጪና አገር እቀፍ እንቅሳሴም ለማድረግ ችለዋል። ለዚህ የሰማያዊ ፓርቲ ትልቅ ምስጋና ይገባዋል።

ትንሽ ድጋፍ ሲያገኙና በየቦታው ስማቸው ሲጠራ፣ የሰማያዊ መሪዎች ሌሎች ድርጅቶችን ማሳነስ ጀመሩ። ሊቀመንበሩ ይልቃል «ምን የሚረባ ድርጅት አለ ብለህ ነው?” ብሎ እንደተናገው። በዚህ ምክንያት ከብዙ ድርጅቶች ጋር ሰማያዊ መጋጨት ጀመረ።

የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 5 2006 በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ ጠየቀ። ገዢው ፓርቲ እውቅና አልሰጥም አለ። ሚያዚያ 12 ተጠየቀ። ያኔም አልተቻለም ወደ ሚያዚያ 26 ሰልፉ ዞር። በዚህ መሃል ሰማያዊዎች በመሃል ገብተው፣ ሚያዚያ 12 ሰልፍ ለማድረግ ጠየቁ። ለአንድነት ተከልክሎ ለነርሱ እውቅና ተሰጣቸው (ያው አገዛዙ ማጋጨት ይወድ የለም) አብዛኞቻችን የሰማያዊ ድርጊት አልተመቸንም። ባይሆን ሰልፉ ከአንድነት ጋር ለምን አይደረግም ብለን ተሟገትን። በይልቃል የሚመራው የሰማያዊ አመራር ግን የአብራችሁ ቁም ጥሪያችንን አጣጣለው። ግትር ሆኑ።

በሰልፉ ቀን፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለሰማያዊች መልእክቱን አስተላለፈ። ከዘጠኝ ወራት በፊት ወደ ሰባት ሺህ የወጣ ሕዝብ፣ ሰማያዊዎች ግማሽ ሚሊዮን ጠብቀው፣ ከአራት መቶ የማይበልጥ ህዝብ ብቻ ተገኘ። ሰማያዊ ትልቅ የፖለቲካ ክስረት አጋጠመው። በርካታ አባላቱም የአመራሩን ግትርነት መጠየቅ ጀመሩ። በአንድ አመት ዉስጥ የሰማያዉ ድጋፍ ወደ ታች አሽቆለቆለ።

በህዳር ሰባቱ ሕዝባዊ ሰብሰብ ወይም ሰልፍ፣ ከዚህ በፊት ግማሽ ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ ይገኛል ብለው የነበሩት ሰማያዊዎች፣ «ወደ ሶስት ሺህ ይገኛል» አሉ። ሶስት ሺህ ሰው ብቻ የሚጠበቁ ከሆነ ለምን በአንድ አዳራሽ ስብሰባዉን እንደማያደርጉት አልገባኝም። ይመስለኛል በወረቀት ሶስት ሺህ ይበሉ እንጂ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ይገኛል የሚል ግምት ዉስጥ ዉስጡን ሊኖራቸው ይችላል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ስብሰባዉን አዘጋጀሁ፣ የሚለው ከሌሎች ስምንት ድርጅቶች ጋር ነው። ከነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ መኢአድን ስታስወጡት የሚቀሩት ሰባት ናቸው። (ለምን መኢአድ በአሁኑ ወቅት በዉስጥ ችግሮቹ የተጠመደ ስለሆነ)። ሰባቱ ድርጅቶች የኦሞ ህዝቦች፣ የከንባታ ሕዝቦች የመሳሰሉ፣ ጥቂት ግለሰቦችን ያካተቱ፣ የማይታወቁ ድርጅቶች ናቸው። እነዚህን ድርጅቶችን አሰባሰቦ ሰማያዊ ትልቅ ትብብር እንደተፈጠረ ለማስመሰል ተሞከረ እንጂ፣ በዋናነት ይሄንን ስብስበ የሚያንቀሳቅሰው የሰማያዊ ፓርቲ ነው።
ይህን ስጽፍ ከላይ ባየሁት ነው። ዉስጣዊ ድርጅታዊ ሥራ ተሰርቶ፣ በቂ ዝግጅት ተደርጎ ሊሆን ይችላል። በርግጥ ያኔ ብዙ ሳይታወቁ የመጀመሪያዉን ሰልፍ ባደረጉ ጊዜ የተገኘውን ያህል ወደ ሰባ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ከተገኘ፣ በርግጥ ትልቅ ነገር ነው። ለአገዛዙም ጠንካራ መልእክት ለማስተላለፍ ይቻላል።

ሆኖም አንድ ነገር በግልጽ መታወቅ አለበት። ሰልፍ መጥራትና በሰልፉ ዉጤት ማስመዝገብ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን። ብዙ ተጠብቆ የመጣው ሰው ቁጥር ካነሰ የፖለቲክ ክስረትም ሊሆን ይችላል። ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ በፊት ሰባ ሺህ ሕዝብ ሰብስቦ፣ እንደገና በመቶ የሚቆጠር ሰው ብቻ ከመጣለት፣ ፓርቲው መንገዱን እና ስትራቴጂዉን መቀየር ይኖርበታል እላለሁ። ደርጅቱ እንደዚህ ወደ ታች እንዲያሽቆለቁል ያደረጉ ግትር የአመራር አባላቱን ተጠያቂ ማድረግና መቀየር ያስፈልጋል። እየተደረገ ያለው፣ ብዙዎችን ትልቅ ዋጋ የሚከፍሉበት አገርን ነጻ የማውጣት ትግል እንጂ የግለሰቦችን ወይንም ትናንሽ አማባገነኖችን ተክለ ሰዉነት መገንባት አይደለም።

ለማንኛውም ከእሁድ በኋላ ፣ የድርጅቱን ጥንካሬና የአስቀድሞ ዝግጅት አይተን በስፋት ትንተናዎች እናቀርባለን። የፌስ ቡክ ዘመቻው ግሩም እንደሆነ ታዝቢያለሁ። በሜዳ በየወረዳዉና በየቀበሌውስ ? የምናየው ይሆናል …

አባቶቻችን በቤተ ክርስቲያን ላይ ግለሰባዊ ዓምባገነንነትን አልፈቀዱም የቤተ ክርስቲያን አሠራርና አመራር ማኅበራዊና ጉባኤያዊ ነው፡፡ ግለሰባዊ አመራር÷ ክሕደትንና ኑፋቄን ለማስገባት፣ ለሌሎች አካላት ቁጥጥር እና ዘመን የፈቀደለት ኹሉ ልቡ የወደደውን በቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲጭን ያመቻል፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ መኪና መሪውን የያዘ መኪናውን ወደ ፈለገው ሊወስደው የሚችልባት ቦታ ብትኾን ኖሮ ዘመነ ሱስንዮስን መሻገር ባልቻለች ነበር፡፡ *             *             * …

Image
“ኤፈርት-መር ካፒታሊዝም” ብዙዎችን እያደኸየ ጥቂት የወያኔ ጎጠኞ ገዢዎችን ግን በሃብት
እያንበሻበሸ በመገስገስ ላይ ነው። ለመሆኑ ኤፈርት ምንድነው? የማነው?
ኤፈርት /በትግርኛው ምህፃር “ትእምት” ወያኔ በረሃ እያለ ባንኮችን፣ የመንግሥት መኪናዎችን እና የግለሰቦችን ንብረት
በመዝረፍ ያቋቋመው ህገ-ወጥ የዘራፊዎች ድርጅት ነው፡፡ ወያኔ የሚኒሊክ ቤተመንግስትን ከተቆጣጠረ ወዲህም
ኤፈርት ራሱን በአስራ ሶስት ግዙፍ ኩባንያዎች አደራጅቶ በሁሉም አቅጣጫ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመቦጥቦጥ የወያኔ
ሹማምንትን ኪስ እንዲያደልብ አደራ የተጣለበት ተቋም ነው።
በዚህም መሠረት መሶበ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ አዲስ የመድሃኒት
ማምረቻ፣ ኢዛና የማዕድን ልማት፣ ጉና የንግድ ድርጅት፣ ሕይወት የግብርና ሜካናይዜሽን፣ ሳባ እብነ በረድ ማምረቻ፣
ሼባ የቆርቆሮ ፋብሪካ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ አልሜዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ ኤክስፕረስ የትራንዚት አገልግሎት፣
ኢትዮጵያን እንወቅ አስጎብኚ ድርጅት እና ትራንስ ኢትዮጵያ የጭነት ማመላለሻ አገልግሎት የተሰኙ ግዛዙፍ
ኩባንያዎችን አቋቁሞ እንደ ተባይ ድሆች ኢትዮጵያንን የሚመጥ “ካፒታሊዝም” ኢትዮጵያ ውስጥ ለማንሰራፋት
ተንቀሳቀሰ። ከጥቂት ዓመታት ሥራ በኋላ የቁጥጥር አድማሱን በማስፋት ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ፋብሪካ፣ ማይጨው
ፓርቲክል ቦርድ ፋብሪካ፣ ዲማ የማር ማጣሪያ፣ አላጌ ደንና የደን ውጤቶች፣ ናሽናል ጂኦ-ቴክስታይል እና አበርደሌ
የእንስሳት ማድለቢያና ኢክስፖርት ድርጅት የተባሉ ስድስት ኩባንያዎች የያዘው ደጀና ኢንዳውመንት ተጨመረለት።
ይህ በአደባባይ የሚታወቀው ኤፈርት ነው። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በቅርበት የሚከታተሉ እንደሚያውቁት ሁሉ ኤፈርት
በኮንትሮባንድ ንግድ ጭምር የገባ “ወንበዴ ድርጅት” ነው። ኤፈርት ያሻውን ያህል ተበድሮ ያለመክፈል ልዩ ፈቃድ
ያለው ቅምጥል ድርጅት ነው፡፡ እስካሁን ከሶስት ቢሊዮን በላይ የባንክ እዳ እንደተሰረዘለት ይወራል፡፡ የህወሓት
ማዕከላዊ ኮሚቴ በተሰበሰ ቁጥር ከማይቀሩ አጀንዳች አንዱ ትዕምት (ኤፈርት) ነው። ለኤፈርት የቦርድ አባላትንም ሥራ
አስኪያጆችንም የሚሾምለት ህወሓት ነው። የአገሪቱ የፓርቲዎች ህግ ፓርቲዎች እንዳይነግዱ ይከለክላል። ህጉ ሕወሓት
ላይ አይሠራም። እርግጥ ኤፈርት ዘራፊ እንጂ ነጋዴ ስላልሆነ አዋጁ አይመለከተውም።
የኤፈርት ኢትዮጵያን የመዝረፍ ሕልም ትልቅ ነው። “በግል” ባንኮችም የአንበሳ ድርሻ አክሲዮን በመያዝ የፋይናንስ
ሴክተሩን ሊቆጣጠረው ደርሷል። በአገሪቱ ያሉ ያሉ ዋና ዋና የቢዝነስ ኮንትራቶችን የሚወስደው ኤፈርት ነው። ለሕዳሴ
ግድብ ግንባታም ዋና እቃ አቅራቢ ነው። የአገሪቱን 40 በመቶ የፒቪሲ (ፕላስቲክ ነክ ምርቶች) ገበያ ለመቆጣጠር
የሚያስችለውን ማምረቻ እየገነባ ነው። ኤፈርት የድሀውን ገንዘብ እየሰበሰ ለወያኔ ጄኔራሎችና ሹማምንት የሚያድል
አገርን ለማጥፋት የተቋቋመ ተቋም ነው። “የሙስና መርከብ” የኤፈርት የቤት ስሙ የሆነው ያለምክንያት አይደለም።

ውጥረት በተመላበት ኹኔታ ተጀምሮ ተጋግሎ የሰነበተውና በመጨረሻም ወደ መግባባትና አንድነት የመጣው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ÷ ለኹለት ሱባዔ ያኽል ሲያካሒድ የቆየውን የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ነገ፣ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቀትር በፊት ያጠናቅቃል፡፡ በስብሰባው ማጠናቀቂያ÷ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰንበቻውን ስለተነጋገረባቸው ጉዳዮች፣ ስላሳለፋቸው ውሳኔዎችና ስለወሰዳቸው አቋሞች የምልአተ ጉባኤው ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በንባብ የሚያሰሙት ጋዜጣዊ መግለጫ …

በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ የተሐድሶ መናፍቃን (አላውያን) ድርጅቶችና ግለሰቦች አስተዳደራዊ ችግርንና ጎሳዊ ርእዮታዊ ጥላቻን ሰበብ በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን ከሕዝቡ ነጥሎ ለማዳከም በኅቡእ እና በገሃድ የሚያራምዱትን የክሕደት ትምህርት ማጋለጥ ጠንካራ የጋራ መግባባትና አቋም ተይዞበታል፡፡ በምልመላና ቅበላ ክፍተት ሳቢያ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን የትምህርት ተቋማት ሰርገው ገብተው እንጀራዋን እየበሉ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ድርጅቶች እንደሚሠሩ የተጠረጠሩ ተቋማቱንና ብዙኃን ደቀ መዛሙርቱን …

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው በተመለከተው የሊቃነ ጳጳሳት ዝውውርና ምደባ አጀንዳ፣ የሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጉዳይ በመመልከት ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጥቷል፡፡ በዚኽም መሠረት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል÷ የድሬዳዋ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ መድቧቸዋል፡፡ …

የመተዳደርያ ደንቡን ማሻሻያ ረቂቅ ለግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ ማኅበሩ በጊዜአዊነት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ለመምሪያው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪ ኾኖ አገልግሎቱን በመፈጸም ይቆያል፡፡ ጠቅላይ ቤቴ ክህነቱ ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት መከተሉ ማኅበሩ ከፋይናንስ ሥርዐቱ ጋራ የሚጣጣሙ የሒሳብ ሰነዶችን ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡ የኤጲስ ቆጶሳት …

ውሳኔው በዋናነት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስንና መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃን ይመለከታል በቀጣይ ክትትልና ቁጥጥር በተቀጡበት ድርጊታቸው ከተገኙ ክህነታቸው እንዲያዝ ተወስኗል ፓትርያርኩ ‹‹አጀንዳው መያዙን አላውቅም›› በሚል ውይይት እንዳይካሔድ ተቃውመው ነበር *          *         * ‹‹እምነት አለው ለማለት ይከብዳል፤ የሙስና አባትና የሰላም ጠንቅ ነው፤›› የተባሉት ንቡረ እድ ኤልያስ የነበሩትም ያሉትም ፓትርያርኮች ችግር ዋነኛ መንሥኤ እንደኾኑ ተሠምሮበታል በብፁዕ አቡነ …

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ዐሥረኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ መደበ፡፡ ብፁዕነታቸው፣ ትላንት በተጠናቀቀው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ፣ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ኾኖ በተደነገገው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ በምልአተ ጉባኤው የተመደቡት …

‹‹ከሕዝብ አጋጫችኹኝ፤ ከወንድሞቼ አንድነት ለያችኹኝ፤ ከነገራችኹኝ አንዱንም የተቀበለኝ የለም›› በሚል የተመረሩት አቡነ ማትያስ ምክራቸው ያልሠመረላቸውን ሦስት አማሳኝ አማካሪዎችን በከፍተኛ ድምፅ ‹‹ውጡልኝ›› በማለት ከፊታቸው አበረሯቸው፡፡ ከትላንትናው የስብሰባ ውሎ መጠናቀቅ በኋላ ፓትርያርኩ የነበሩበት የምሬትና የብስጭት ኹኔታ ተነግሯቸው ወደማረፊያቸው የተጠሩት በሹመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ማትያስ በተጠሪነት ጉዳይ የተሟገቱለት አቋም የቤተ ክርስቲያን እንዳልኾነ፣ ለአጭር ዕድሜ የኖረው የቤተ …

አቡነ ማትያስ÷ የሊቃነ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ተጠሪነት ለፓትርያርኩ በማድረግ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት በፓትርያርኩ የበላይነት ለመተካት ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መሟገታቸውን አጠናክረው ውለዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ያላትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በፓትርያርኩ ዐምባገነናዊ አመራር ሰጪነት በመርገጥ በስም እንጂ በግብር የሥልጣን ልዕልና የሌለው ሲኖዶስ ለመፍጠር እየተጣጣሩ ነው፡፡ …

ለቁጥጥሩ ማኅበራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሞዴላሞዴል ይጠቀማሉ ዕውቅና የመስጠት፣ ደንባቸውን የማጽደቅና የመሰረዝ ሥልጣን የቅ/ሲኖዶሱ ኾኖ ጸንቷል በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያው የማኅበራትን ጉዳይ የሚከታተለው የመምሪያ ሊቀ ጳጳሱ ነው ማኅበረ ቅዱሳን በውሳኔው ማህቀፍ ውስጥ በሚሻሻልለት መተዳደርያ ደንብ ይመራል ስብሰባው የሊቃነ ጳጳሳትን ተጠሪነት በሚወስኑና በሌሎች የማሻሻያው ልዩነቶች ላይ  ቀጥሏል

ያደረውን የሕገ ቤተ ክርስቲያን አጀንዳ በፈቃዳቸው ትተው ሌላ ርእሰ ጉዳይ አንሥተዋል የተቃወሟቸውን አባቶች በአሳፋሪ ንግግሮች በመዝለፍ ለማሸማቀቅ ሙከራ አድርገዋል የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አጀንዳ ቀጣይነት በድምፅ ሊወሰንበት እንደሚችል ተመልክቷል እንደ ሕጉ ስብሰባውን በአግባቡ ካልመሩ ምልአተ ጉባኤው ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ይቀጥላል *                *               * ‹‹ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ …

ፓትርያርኩ የማኅበራት ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ኾኖ በማእከል ካልተመራ በሚል ከማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋራ የሚቃረን ግትር አቋም ይዘው ውለዋል፡፡ አቋማቸው ተቀባይነት ካላገኘ ስብሰባውን ለመምራት እንደሚቸገሩ በመግለጽ ምልአተ ጉባኤን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽኑ አቋም ሳቢያ አልተሳካላቸውም፡፡ ጉዳዩ ‹‹ከአዲስ አበባ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ የሠራኹበትና የደከምኩበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› …

ምልአተ ጉባኤው በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የጋራ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ላይ መክሮ አጽድቋል፤ በሥራ ላይ እንዲውልም መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ከአጠቃላይ ጉባኤው አጀንዳ ውጭ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ለማስወሰን ታቅዶ በፓትርያርኩ ግፊትና በአማሳኞች ውትወታ የተከፈተው መድረክ÷ ስብሰባው ‹‹ባለቤት የለውም ወይ?›› ያሰኘና የአጠቃላይ ጉባኤው ክብረ ሞገስ በርእሰ መንበሩ አመራርና የቀጥተኛ ተሳትፎ መብት በሌላቸው አማሳኞች ሥርዐት አልባነት የተጣሰበት …

ልማቱ የሀብት ምንጭን በማስፋት አቅምን የመገንባት የድርጅቱ ስትራተጅያዊ ዕቅድ አካል ነው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እስከ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ያለው ይዞታችን ይለማል 13 ሕንፃዎች፣ ባለ4 ኮከብ የእንግዳ ማረፊያ፣ የስብሰባ አዳራሽና ሙዝየም ሥራዎችን ያካትታል የግንባታ 3ቢልዮን ብር ወጪ 85% በኩባንያው፣ 15% በአስተዳደርና ልማት ድርጅቱ ይሸፈናል የከተማውን የቤት እጥረት ከማቃለልና የአካባቢውን ገጽታ ከመቀየር አገራዊ ጠቀሜታው ባሻገር …