የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ዛሬ ያወያያል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ
- በፀረ ሙስና፣ በመልካም አስተዳደርና በዕቅበተ እምነት ንቅናቄውየአማሳኞች የሕግ ተጠያቂነት እንዲኹም በእስር እና በወከባ የሚያደርሱት እንግልት ዋነኛ ትኩረት እንደሚኾን ተጠቁሟል
- ዋና ሥራ አስኪያጁ÷ በአለቆች፣ በካህናትና በሰባክያነ ወንጌል ላይ እንዳደረጉት ኹሉችግሮችን ውጫዊ በሚያደርግ ኦሬንቴሽን የውይይቱን ትኩረት ለማስቀየስ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም
- ‹‹የተሾምኩት በመንግሥት ትእዛዝ ነው›› የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያነሡባቸውን ሠራተኞች በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ
* * *
- ‹‹…የሔዱትን[በቀደሙት ውይይቶች የተሳተፉትን አለቆች፣ ካህናት እና ሰባክያን] ጠይቁ፤ ሰሞኑን ሚኒስትሩ አቅፈውኝ ትከሻዬን እየመቱኝ፣ በርታ፤ እኔ ከጎንህ ነኝ፤ ያለምንም ስጋት መንጥራቸው ብለው መመሪያ ሰጥተውኛል … ስም እየጠሩ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እስካለ ድረስ እጨርሳችኋለኹ ብለዋል፡፡ መንግሥት እርሳቸው እንደሚሉት የእርሳቸው ብቻ አይደለም፡፡ እኛ መንግሥት ከዜጎቹ ጋር ነው ያለው ነው የምንለው፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ይድረስልን፡፡››
/በጥቅመኝነት እና በጎጠኝነት ትስስር ላይ በተመሠረተው የዋና ሥራ አስኪያጁ የዝውውር አሠራር የተማረሩ ሠራተኞች አቤቱታ/
