የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እና ኤልያስ ተጫነ: በሥልጠና ስም፣ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያዎችን ባጠኑ ባለሞያዎችና በየሰንበት ት/ቤቶች ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ እያካሔዱ ነው

Originally posted on ሐራ ዘተዋሕዶ:

  • በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔና በፓትርያርኩ ቡራኬ ያጠኑትን በማያገባቸው የገቡ ደንቆሮዎች ብለዋቸዋል
  • የሰ/ት/ቤቶችን፣ ከኮብልስቶን ሥራ ይልቅ ከአፋችን ሙዳይ ምጽዋት የሚነጥቁበሚል ዘልፈዋል
  • በሒሳብ አያያዝ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ያተኮረ ሥልጠና ተጀምሯል
  • አለቆችን፣ ጸሐፊዎችንና ሒሳብ ሹሞችን ጨምሮ የሀ/ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎች ይሳተፋሉ
  • ያለበቂ ዝግጅት የተጀመረው ሥልጠና ከወሬ ያላለፈበሚል በተሳታፊዎች ክፉኛ ተተችቷል
  • ለሥልጠናው ድጋፍ ከንግድ ባንክ የተገኘው ብር መቶ ኀምሳ ሺሕ መመዝበሩን ያመለክታል

Lique Maemeran Yemane ZeMenfes Kidusዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፡-

ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም. ውሳኔው፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እስከ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረስ እንዲሠራበት ይኹንታ እና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበት የመዋቅር የአደረጃጀት እና የአሠራር ጥናት ወደ ታች ወርዶ በማኅበረ ካህናት፣ በማኅበረ ምእመናን እና በየሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች በውይይት ዳብሮ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

የመዋቅር የአደረጃጀት እና የአሠራር ጥናቱ፣ ከ96 በመቶ በላይ የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችን ድጋፍ ባረጋገጠበት የኹለት ቀናት ውይይት፣ የዛሬው የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሳተፉት በመጀመሪያው ግማሽ ቀን ብቻ እንደነበር በወቅቱ የተያዘው የመከታተያ ቅጹ ያስረዳል፡፡

View original 414 more words