በክንውን ላይ፤ ከረፋዱ 4፡50፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

አስተዳደሩ፣ በሕገ ወጥ ኪራይ የደብሩን ጥቅም ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ይታወቃል ጽ/ቤቱን አስበይደው በማሸግ የተቆጣጠሩት ምእመናኑ የተመሩት በሰንበት ት/ቤቱ አባላት ነው *      *      * በመ/ፓ ቅ/ቅ ማርያም፣ የሒሳብ ፈራሚነቱን ለቄሰ ገበዙ ለማሳለፍ የተደረገው ጥረት ከሽፏል ሒሳብ ሹሙ ‹‹ጉረሮዬን ዘግተኽ አትኖርም›› እያለ በምእመኑ ተወካይ ላይ ሲዝት ሰንብቷል *      *      * በደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ያለደንቡ የታሰበው የሰ/ት/ቤት …

‹‹ጉዳዩን በፌስቡክ እያጋጋላችኹ ነው›› የተባሉ 16 የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ፣ ያለው ፈርሶ በአዲስ ምዝገባ በሚቋቋመው ሰንበት ት/ቤት ዕድሜአቸው ከ30 በላይ የኾኑ ይባረራሉ ‹‹አዲስ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ያዘዝኹት እኔ ነኝ፤ ዑራኤል ጸሐፊ ኾኜ 700 ሰንበት ተማሪ በትጥቅ ድጋፍ አስበትኛለኹ››/ሥ/አስኪ. ሊ/ማእ. የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ/ በአዲስ አበባ […]

፳፩ የምርመራ ቀናት የጠየቀባቸው የወረዳው ፖሊስ የ፲ ቀን ጊዜ ተፈቅዶለታል በድረሱልኝ ጥሪው÷ ከሥራቸው የታገዱ፣ ከደረጃ ዝቅ የተደረጉ እና የታሰሩ አሉ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችና ምእመናኑ ከወረዳው አስተዳደር ጋር እየተነጋገሩበት ነው በተቃጠለው የቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው መቃኞ ሰኔ ፳፩ ይመረቃል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 15 ቁጥር 803፤ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.) በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት …

አስተዳደሩን፣ የገንዘብ እና ንብረት እንቅስቃሴውን የመቆጣጠር ሕጋዊ ሓላፊነታቸው ተገድቧል በዕቅድ ባልተያዙ ከፍተኛ ግዥዎች እና የወጪ ሰበቦች ምዝበራ ሊፈጸም እንደሚችል ተጠቁሟል በቅ/ሲኖዶስ የተመደቡትን ረዳት ያጣው ሀ/ስብከቱ ከ50 ሚልዮን በላይ ተቀማጩ ለአደጋ ተጋልጧል *        *        * የሠራተኞች ደመወዝ እና አይቀሬ የኾኑትን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንዳይወጡ ፈቃደኛ ያልኾንኩበት እና ሥራዎች እንዲጓተቱ ያደረግኹበት ወቅት እስከ ዛሬ ድረስ የለም፡፡ …

ፓትርያርኩ የሀገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎችን ባለማነጋገራቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል ከገቢያቸው በላይ ሀብት ያከማቹ ሓላፊዎችን በሕግ ለመጠየቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው (ሰንደቅ፤ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፰፤ ረቡዕ ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) ሙስና እና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ፣ ሃይማኖት እንዲጠበቅ በተደጋጋሚ ያቀረብነው አቤቱታ መፍትሔ አላገኘም ያሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች፣ …

በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከሚሹት የዘመናችን የውስጥ ችግሮች እና የውጭ ተግዳሮቶች ውስጥ ሙስና እና ኑፋቄ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ አንዱ የሌላው መተላለፊያ፣ መንሥኤ እና ውጤት እየኾኑ ለቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ለውጥ የተደረጉ ጥረቶችን ሲያመክኑ፤ የመዋቅር እና የአደረጃጀት አቅሟን ሲያዳክሙ ቆይተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ …

ፓትርያርኩ ጠቅላላ ጉባኤው በላካቸው ብፁዓን አባቶች እና ተሳታፊዎች ላይ በራቸውን ዘጉ የፓትርያርኩን ዳተኝነት በማጋለጥ ፍትሕን የሚጠይቁ የዐደባባይ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሔዳሉ በአማሳኞች እና በተሐድሶ መናፍቃን ላይ የሚደረገው ተጋድሎ በየአጥቢያዎቹ ይቀጣጠላል ማስረጃ የተገኘባቸውን አማሳኞች በአገሪቱ ሕግ ለመጠየቅ የባለሞያዎች ቡድን ተቋቁሟል *       *       * ፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ባለ18 ነጥቦች …

የንቅናቄው መነሻ የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ እና የፓትርያርኩ አባታዊ መመሪያ ነው ከ25 በላይ አማሳኝ የአድባራት አለቆች እና ጸሐፊዎች ላይ በቂ ማስረጃዎች ተሰብስበዋል የተሐድሶ አራማጅ ሰባክያንን የሚጋብዙ አለቆችና የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች ተለይተዋል የደብረ ናዝሬት ቅ/ዮሴፍ፣ የመካነ ሰማዕት ቅ/ቂርቆስ እና ጃቲ ኪዳነ ምሕረት ተጠቅሰዋል የሀ/ስብከቱ ሥ/አስኪያጅ የሰንበት ት/ቤቶቹን አመራሮች ‹‹እኔ ራሴ አሳስራችኋለኹ›› አሏቸው ‹‹እንቅስቃሴው ይቀጥላል፤ የመላው የአ/አ ሰንበት …

ታሪካዊው የቅዱስ እንጦንስ ጽሌ በአርተፊሻል ተቀይረዋል ከተባሉት አንዱ ነው የስእለት እና የስጦታ ወርቆች እና የብር ጌጣጌጦች በየመሸታ ቤቱ እየተሸጡ ነው የውጭ ኦዲት እንዲካሔድ በፓትርያርኩ የተሰጠው መመሪያ ተግባራዊ አልተደረገም በየመሸታው አስነዋሪ ሥራ የሚያዘወትሩ ካህናት ለምእመናን መራቅ ምክንያት ኾነዋል የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ለችግሩ መባባስ ተጠያቂ ተደርገዋል (ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅጽ 03 ቁጥር 107፤ ቅዳሜ ግንቦት 22 …

ዓመታዊ ጉባኤው የሚካሔድበት ወቅት ‹‹የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን›› በሚል ተሠይሟል በአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ ላይ አቋም እንደሚይዝ ይጠበቃል ዋና ሓላፊው፣ ‹‹የአ/አበባዎችን ጥያቄ እንዳትቀበሉ›› በሚል ያደረጉት እንቅስቃሴ ተነቅቶበታል የሀ/ስብከቱ ሥ/አስኪያጅ ለአንድነቱ ልኡካን የውክልና ደብዳቤ ባለመጻፍ በዓላማ ተባብረዋቸዋል በዓለ ጰራቅሊጦስን ተንተርሶ በየዓመቱ የሚካሔደው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ …

የወቅቱ ሰበካ ጉባኤ የኹለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመገንባት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል የቦታ፣ የሕንፃ እና የልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ተቋማት ኪራይ ማጣራት በመገባደድ ላይ ነው የሊ/ን የማነ፣ የዋና ጸሐፊነትም የሥ/አስኪያጅነትም ሥልጣን የተጠያቂነት ዕንቅፋት ፈጥሯል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት እና አድባራት÷ የመሬት እና የሕንፃ ኪራይ፣ የመካነ መቃብር አጠቃቀም እና የመኪና ሽልማት ጉዳዮችን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ ከጠቅላይ …

ርምጃው የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ አመራሩ እንዲቀየር የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ ያደረገ ነው ለጥያቄአቸው ምላሽ ባለማግኘታቸው በፓትርያርኩ ላይ ቅሬታቸውን በመዝሙር ገልጸው ነበር ከ200 በላይ አባላት የሚማሩበት አዳራሽና የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ቁልፎች ተሰብሮ ታሽግዋል የደብሩ ስምንት አመራሮች ከመሳለም በቀር ወደ ደብሩ ገብተው እንዳይሰበሰቡ ተከልክለዋል *       *       * በካህናትና በምእመናን አንድነት መመራት ባለበት ደብር የአለቃው ዓምባገነንነት ሰፍኖበታል ሰበካ ጉባኤ …

የሰንበት ት/ቤቶቹን አንድነት ለማገድ እና አመራሩን ለመበተን መታቀዱን ተቃውመዋል በአጥቢያዎች የተቀናጀ ፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ እንቅስቃሴ እንደሚካሔድ ተጠቁሟል ‹‹የቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እንጂ የበዓላት ማድመቂያ ብቻ ቄጤማ አይደለንም››/ወጣቶቹ/ (ሰንደቅ፤ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፮፤ ግንቦት ፲፪ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) በምዝበራ ላይ የተሰማሩ አማሳኝ የገዳማት እና የአድባራት ሓላፊዎች የሀብት ምንጭ እንዲመረመር፣ ማስረጃ በቀረበባቸው የተሐድሶ መናፍቃን፣ በሕገ ወጥ […]

ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁ ከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻ ይደረግባቸዋል፤ የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤት …

ያለሊቀ ጳጳሱ ዕውቅናና ፈቃድ በአምስት ሓላፊዎች ላይ እግድ እና ዝውውር ተፈጽሟል አካሔዱ በሊቀ ጳጳሱ ሕገ ወጥ ነው በሚል ታግዷል፤ የሊቀ ጳጳሱ እግድ በፓትርያርኩ ተሽሯል የተጠናከረው የሰንበት ት/ቤቶች ፀረ ኑፋቄ እና ፀረ ሙስና መነሣሣት በመንሥኤነት ተጠቅሷል ‹‹ያለአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ እና ያለጥናት የአንድ አካባቢ ሰዎችን በመምረጥ የተፈጸመ ነው፡፡›› /ዋና ሓላፊዎቹ/ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በፓትርያርኩ ብቸኛ ምርጫ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት ጀምሮ ለአራት ቀናት ያካሔደውን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ኹለተኛ ዓመታዊ ቀኖናዊ ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ባወጣው ባለዐሥራ አንድ ነጥቦች መግለጫው÷ በሊቢያ ራሱን እስላማዊ መንግሥት(ዳኢሽ) እያለ የሚጠራው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን ስለ ክርስቲያንነታቸው በግፍ እና በአሠቃቂ አኳኋን የገደላቸውን ኢትዮጵያውያን እና ግብጻውያን ኦርቶዶክሳውያን የሰማዕትነት ሥያሜ …

የኤጲስ ቆጶሳትን ሢመት ጨምሮ በርካታ አጀንዳዎች ለጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ተላልፈዋል የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራሮችን ለማሳሰር በአማሳኞች አጋሮች ተሞክሮ ነበር በሰንበት ት/ቤቶቹ ጥያቄ የተቆጡት ፓትርያርኩ፣ ረዳት ሊቀ ጳጳሱን በቀስቃሽነት ከሠዋል ከስድስት ያልበለጡ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ትላንት የተጀመረው የ፳፻፯ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማጠናቀቁ ተገለጸ፤ በነገው ዕለት ጠዋት መግለጫ […]

ዝርዝር መግለጫው በይፋ የሚወጣው በቀጣዩ የጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ነው በስደት ያሉ የሚመለሱበትና በኑሯቸው የሚቋቋሙበት ጠንካራ ውሳኔ ተወስኗል ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጋራ የሚሠራ ኮሚቴ ይቋቋማል

 የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደባቸው፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ የባሕር ዳር ከተማ የአዊ እና መተከል ዞኖች ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ ፱ ቀን በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን …

በሊቀ ጳጳስ ሥር የማትመራ ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ለማለት ያስቸግራል እንደቀደሙ ጠንክረን በማስተማር ወደ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጉያ ማሰባሰብ ይገባናል ቀኖናን በመጠበቅ ተልእኳቸውን በአንድነት እንዲያጠናክሩ ኹኔታው ሊመቻችላቸው ይገባል ይህን ጊዜያዊ ስሕተት ለማስተካከል በሚደረገው ጥረት ምእመናን ተባባሪ መኾን ይጠበቅባቸዋል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤውን፣ ዛሬ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፯ …

ዛሬ፣ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተካሔደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት ወቅት ከመላው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት እና አድባራት የተውጣጡ ከኹለት ሺሕ ያላነሱ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች÷በአድራሻ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያቀረቡት እና በግልባጭ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ በሀገረ ስብከቱ ለፓትርያርኩ ረዳት …

በሺሕዎች የሚቆጠሩ ከ160 በላይ ገዳማት እና አድባራት ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የመክፈቻ ጸሎቱ በሚከናወንበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተሰበሰቡ ነው  

(ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ፤ መድሎተ ጽድቅ፤ ሚያዝያ ፳፻፯ ዓ.ም.) መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ በእግዚአብሔር ቸርነት የተሰጠን መዳን በመስቀል ላይ የተፈጸመ መኾኑን እንደሚነግረን ኹሉ ያን መዳን ገንዘብ ለማድረግ እያንዳንዱ ሰው ከማመን ጀምሮ በተቻለው መጠን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሠርቶ ባሳየንና ባስተማረን መጓዝና መጋደል ያለበት መኾኑን ያስተምረናል እንጂ በክርስቶስ ድነናል እንጂ ንጽሕናን ለመጠበቅ መጋደል፣ እንዲኹም ሰውነትን በገድል ማስጨነቅ አያስፈልግም …

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የጥናት እና ምርምር ማእከል÷ ‹‹ሰማዕትነት ለክርስትና›› በሚል ርእስ ነገ፣ ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 – 11፡00 ሰዓት በማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት አዳራሽ ጥናታዊ ውይይት ያካሒዳል፡፡ የጥናታዊ ውይይት መርሐ ግብሩ፣ በየኹለት ወሩ (በዓመት ስድስት ጊዜ) በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ የሚዘጋጀው የነገረ ቤተ …

በረከታቸው ይደረብንና የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (1932 – 1982 ዓ.ም.) ሚያዝያ 23 ቀን 1982 ዓ.ም. በሻሸመኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከሰጡት ትምህርት ጀግና በጦር ሜዳ ይወለዳል፤ በክፉ ቀን ከብዙ ፈሪዎች ከብዙም ጀግኖች መካከል ቅ/ጊዮርጊስ ተገኘ የተወደዳችኹ ምእመናን፤ በዚኽች በበዓለ ኀምሳ ውስጥ፣ ዛሬ ተጨማሪ በዓል የምናከብረው የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን …

‹‹የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግሥት›› (Islamic State in Iraq and Syria) የሚል መጠሪያ ለራሱ የሰጠው ታጣቂ ቡድን፣ ጸጥታቸው የደፈረሰ አገሮችን የወታደራዊ ኃይሉ እንዲኹም እስከ ኹለት ቢልዮን ዶላር የሚገመተው የገንዘብ እና የንብረት ሀብቱ ማጠናከርያ በማድረግ ወደ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ ‹‹የጥንቱን ገናና የእስልምና ሥርዐት›› በ፳፩ኛው ምእት ዳግም ለማስፈን የአምስት ዓመታት ግብ ያስቀመጠው ቡድኑ÷ መካከለኛው …

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን ‹‹ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ = የአባቶቻችን ሃይማኖት የቀናች ናት›› ራሱን እስላማዊ መንግሥት (አይ ኤስ አይ ኤስ) እያለ የሚጠራው የጨካኝ አረመኔዎች ስብስብ፣ በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ላይ ያካሔደው ዘግናኝ ግድያ ሳይበቃው ይህን እኩይ ድርጊቱን በልዩ ልዩ ምክንያት ከአገር ተሰድደው በሊቢያ በነበሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን …

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ ‹‹ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን? ልጆቻችን የምንኮራባቸው መጻሕፍቶቻችን፣ የምንማርባቸው ዩኒቨርስቲዎቻችን ናቸው፤ አስተምረውናል፤ አኩርተውናል፤ አስከብረውናል›› (ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) የልጆቻን የኃይለ ሚካኤል(ኢያሱ ይኵኖ አምላክ) እና የኃይለ ኢየሱስን(ባልቻ በለጠ) ነፍስ ይማርልን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የሐዘን ዳርቻ ያድርግልን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የቤተሰቡን …

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ‹‹እስመ በእንቲኣሁ ይቀትሉነ ኲሎ አሚረ፡፡ ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ = ስለ አንተ ቀኑን ኹሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን::›› (መዝ.43÷22) *       *       * ራሱን እስላማዊ መንግሥት (IS) እያለ በሚጠራው ዓለም አቀፋዊው አሸባሪ ድርጅት በይፋ በኢንተርኔት ባሰራጨው የቪዲዮ መረጃ፣ በኹለት የተለያዩ ቦታዎች በአሠቃቂ ኹኔታ የገደላቸው ወንድሞቻችን የተገኘባቸው አበሳ ወይም ወንጀል ክርስቲያን ኹነው …

በነገው የአ/አበባ ነዋሪዎች የመስቀል ዐደባባይ ሰልፍ ቤተ ክርስቲያን መልእክቷን ታስላልፋለች ራሱን አይ ኤስ እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን፣ በንጹሐን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ በፈጸመው ግፍ ለገደላቸው ወገኖቻችን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ወንጌል ለማድረግ ለነገ ከጠዋቱ 2፡30 – 4፡30 የወጣው መርሐ ግብር ለኀሙስ ጠዋት፣ ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. […]

ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ በግፍ የተሠው ክርስቲያኖች፣ ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን መኾናቸውን አረጋገጠ፤ ‹‹የልጆቻችን ሰማዕትነት በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ዋጋ ስላላቸው በዚኽ ከሐዘናችኹ እንድትጽናኑ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡›› ነገ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንት፣ ካህናት የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እንዲኹም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው …

በሊቢያ፣ በየመን እና በሌሎችም ክርስቲያኖች ለጥቃት በተጋለጡባቸውና የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ በሚገኙባቸው አገሮች ከተጨማሪ ጉዳት ለመታደግ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል በአዲስ አበባ እና በአህጉረ ስብከት የሰማዕታት ቤተ ሰዎችን እያፈላለጉ የማጽናናት እና የመደገፍ መርሐ ግብር ይካሔዳል ከሊቢያው የግፍ ተግባር ጋራ በተያያዘ ባሉ ኹኔታዎች ላይ በየዕለቱ እየተሰበሰበ በመምከር መልእክት ለማስተላለፍ የወሰነው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም መግለጫ ይሰጣል

በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡

ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?

ዜጎቹ በሕገ ወጥ መንገድም ይሂዱ በሕጋዊ፣ ድንበር ጥሰውም ይሂዱ በአውሮፕላን ተሳፍረው፤ መጀመሪያ ሰዎች፣ ቀጥሎም የዚህች ሀገር ዜጎች ናቸውና ኀዘን ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ክብር አንዱ በሞቱ ጊዜ የክብር ልቅሶና ኀዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአካባቢያቸው ላለመራቅ፣ ከራቁም ለመመለስ ከሚሰጧቸው ምክንያቶች አንዱ ‹በክብር ዐርፎ በክብር መቀበርን፣ የክብር የኀዘን ሥነ ሥርዓትን ማግኘትን› ነው፡፡
ካገሬ እንዳወጣህ አገሬ መልሰኝ
በሹም የታዘዘ አፈር አታልብሰኝ፤
እንኳን የሚቀብረው የሚያዝንለት አጣ
ምን ወግ ማረግ ያያል ካገሩ የወጣ፤
የሚሉት ለዚህ ነበረ፡፡

የመንግሥት አካላት ለምን ይኼንን ለመዘንጋት እንደፈለጉ አልገባኝም፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቃጠሎና ግድያ ሲመጣ የሀገራችን ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ብቅ ብለው ‹‹በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ነገር ከልብ እናዝናለን፣ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጋር ተነጋግረን አስፈላጊውን እናደርጋለን፤ ተመሳሳይ ችግር ለወደፊቱ እንዳይከሰትም አንሠራለን› ዓይነት ሰውነት ያለበት መግለጫ ጠብቄ ነበር፡፡ የለም፡፡ ሲሆን በሀገራችን የልቅሶ ሥነ ሥርዓት መሠረት፡፡ አሁን ደግሞ ዓለም ያወቀው አሸባሪ ‹አይ ሲስ› ኢትዮጵያውያኑን በክርስትና እምነታቸው ብቻ ሲሠዋቸው የተሰጠው መግለጫ ስሜት የሌለበት፣ ማዘን መደሰታቸውን የማይገልጥ፣ እንኳን ሰው እንስሳ የሞተብን የማያስመስል ሆነ፡፡ ከማጣራቱም ከምኑም በፊትኮ ስሜቱ ይቀድማል፡፡፡ አዝናችኋል ወይ? ስትሰሙና ስታዩ ምን ተሰማችሁ? የአሜሪካ መንግሥት እንደዚያ ዓይነት መግለጫ ሲያወጣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ያንን ነው ወይ መስማት ያለብን? ለመሆኑ መሪዎቻችን ኀዘናቸውን የሚገልጡት ምን ስንሆን ነው? ለምንድን ነው ሁሉም ነገር ፖለቲካ የሚሆነው?

ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?
መንፈሳዊ መሪዎችስ የት ናቸው? አንዳንዶቹ ውጭ ሀገር መሆናቸው እየተሰማ ነው፡፡ ሲሆን ይህንን ሲሰሙ አቋርጦ መምጣት፤ ካልሆነም ባሉበት ሆኖ አባታዊ ኀዘንን መግለጥና በእምነቱ የሚገባውን ማድረግ ይገባ ነበር፡፡ ሲኖዶሱስ ምን እየሠራ ነው? አልሰማም ይሆን? ዛሬ ጠዋት ቢያንስ በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት መደረግ አልነበረበትም? ባፈው ካይሮ ሄዳችሁ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው ያያችሁት? በጎቹ እረኛ የላቸውም ማለት ነው? አባቶች የሚያዝኑት ምን ሲገጥማቸው ነው? እረኛው የሚያለቅሰው ስንት በጎች ሲታረዱ ነው?

ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሩን በዝምታ የምታልፈው ከሆነ እኛ እንደ ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ቀኖና እነዚህን በክርስትናቸው ምክንያት የተሠው ክርስቲያኖች ‹ሰማዕታተ ሊቢያ› ልንላቸው ይገባል፡፡ የሰማዕትነታቸውንም በዓል ማክበር አለብን፡፡ በስንክሳሩ ማስገባት ባንችል ታሪካቸው በኅዳጉ ማስፈር አለብን፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ በሚገባ የተማሩም ይሁኑ ያልተማሩ፣ ከመካከላቸው የማያምኑም እንኳን ቢኖሩ የተገደሉበት ምክንያት ክርስትና ነውና ሰማዕታት ናቸው፡፡ ያውም ‹ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት›፡፡ በስንክሳሩ እንደምናነበው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የክርስቲያኖች መንደርና ቤተ ክርስቲያን እየተወረረ ክርስቲያኖቹ ሲሠው ገና ያልተጠመቁት፣ ነገሩ ያልገባቸው፣ ክርስትናን ለመቀበል ያልወሰኑት ሁሉ አብረው ተሠውተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን የተሠውበት ምክንያት ክርስትና በመሆኑ ሁሉንም ሰማዕታት ብላቸዋለች፡፡ የእነዚህም ክብር እንዲሁ ነው፡፡

እነርሱ በሰማይ ዋጋ አላቸው፡፡ አክሊለ ሰማዕታትንም ተቀብለዋል፡፡ እኛ ግን ሰማዕታቱን ባለማክበራችን ክብር ይጎድልብናል፡፡ ‹በረከታቸው ይደርብን› እንጂ ‹ነፍስ ይማር› አንልም፡፡

‹‹የሥነ ምግብ ጥናቱ የትኛውንም ሃይማኖት በተለየ የሚመለከት አይደለም›› /አስተባባሪው/  ‹‹ሥጋወደሙን ከምግብ መቁጠር ሃይማኖታዊ ነጻነትንና ሥርዓትን የሚፃረር ነው›› /ምእመናን/ (አዲስ አድማስ፤ ቅዳሜ፤ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) ከውልደታቸው እስከ ስድስት ወራት ዕድሜአቸው ድረስ ያሉ የአገሪቱ ሕፃናት፣ ከእናቶቻቸው ጡት ወተት ውጭ ተጨማሪ ነገር ስለመውሰዳቸው የዳሰሳ ጥናት ለማካሔድ በሚል ለመረጃ ሰብሳቢዎች የተሰጠው ሥልጠና፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሕፃናት …

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የጥናት እና ምርምር ክፍል የወሩን ኹለተኛ ጥናታዊ ውይይት መጋቢት ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በኮሌጁ አዳራሽ አካሔዷል፡፡ ከግማሽ ምእት በላይ የምሥረታ ዘመን ባስቆጠረው መንፈሳዊ ኮሌጅ ከዐሥር ዓመት በፊት የተጀመረው የውይይት መድረኩ፣ እንዳስፈላጊነቱ የሚጋበዙ የአገር ውስጥ እና የውጭ ምሁራንና ሊቃውንት ጥናታቸውን ሲያቀርቡበት ቆይተዋል፡፡ ከስድስት ዓመት ወዲኽ ደግሞ መርሐ ግብሩ ራሱን የቻለ አስተባባሪ ተመድቦለት …

እኛ ዘንድ ቀኖና እና ሥርዐት ሲጣስ ‘No’ ማለት የለም፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማስፈጸም ከኹሉም የሥራ ሓላፊዎች የሚጠበቅ ኾኖ ሳለ በዝምታ ማየት ነው፡፡ ምእመናን ናቸው ሃይማኖታችን እያሉ የበለጠ መቆርቆር እያሳዩ ያሉት፡፡ መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ በየጊዜው በሚፈጠረው ውዝግብ የተነሣ÷ የቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖናዊ ሥርዐት ይጣሳል፤ የእርስ በርስ ግጭት ይስፋፋል፤ ሙስናና ዝርፊያ …

መመሪያቸው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶሱ ስብሰባ ያቀረበውን ስጋት አጣጥለውታል በአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ምርጫ እና ሥያሜ የፓትርያርኩን የአካሔድ ስሕተት ከማረም አንጻር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ እና መመሪያ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል በሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ሥያሜ አለመግባባቱ አጋጣሚ፣ ፓትርያርኩ፡- ረዳት ሊቀ ጳጳስ መርጦ ከማቅረብ …

ፓትርያርኩ ‹‹አልመራኹትም›› በሚል ያፈኑት የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና የዋና ሥራ አስኪያጁ ጥያቄ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አቅራቢነት ቋሚ ሲኖዶሱ ዛሬ ይወያይበታል ረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ ፓትርያርኩ መመሪያቸውን ከቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ሕግና ከሀ/ስብከቱ ዘለቄታዊ ሰላም አንጻር መዝነው የእርምት ማስተካከያ እንዲያደርጉ በድጋሚ አሳስበዋቸዋል የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት በወረራ መልክ በመቆጣጠር ስለ ሥዩማን ሥራ አስኪያጆቹ ምደባ ያብራሩት እነዘካርያስ ሓዲስ፡- …

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡- ‹‹የአ/አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት ነው›› የሚለውን ድንጋጌ ተገን አድርገዋል የወቅቱ ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዲዛወሩ አዝዘዋል የሀ/ስብከቱ ብልሹ አሠራር የቀጠለው ‹ሥዩማኖቹ› በወቅቱ ሥራ ባለመጀመራቸው ነው ብለዋል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ፡- ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስም ለፓትርያርኩም የኾኑት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ አልተስማሙበትም የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ድርሻ ከሌሎች …

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ፓትርያርኩ ከሕግ አግባብ ውጭ ለሾሟቸው ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የምደባ ደብዳቤ እንደማይጽፉ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ አስታውቀዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አስተያየታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ አዝዟቸዋል፡፡ አሠራሩ፣ ምርጫው እና መመሪያው ተቀባይነት የሚኖረው ሥራ አስኪያጆቹ ‹‹በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ተመርጠው ቀርበው ከጠቅላይ …

መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተመድበዋል ብፁዕ ጠቅ/ሥራ አስኪያጁ ውሳኔውን በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ በሹመት መመሪያ ታዝዘዋል ሊቀ ማ/ን የማነ ሥራን በመበደል፣ አእመረ አሸብር በሃይማኖታቸው ርቱዕነት ነቀፌታ አለባቸው የፓትርያርኩ አካሔድ በረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው ቋሚ ሲኖዶስ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚነጋገርበት ይጠበቃል *      *     * ተተኪው ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ በወቅቱ በዋና ጸሐፊነት …

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሬት፣ የሕንጻ እና የልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ተቋማት አጠቃቀምና የኪራይ ተመን ጉዳዮችን በመፈተሽ የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም የሚያስከብር ፖሊሲ ለማውጣት የሚያስችል ዝርዝር የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ በፓትርያርኩ በተሰጠው መመሪያ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተቋቋመው ኮሚቴ በወርኃ ታኅሣሥ መባቻ የጀመረውን ጥናት እንደቀጠለ ነው፡፡ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ እና ከሀገረ …

ፓትርያርኩ እና የመስተዳድሩ ፕሬዝዳንት በጉዳዩ ላይ መወያየታቸው ተጠቁሟል ‹‹የኢሬቻ ቱሉ በዓል በክልል ደረጃ የት አካባቢ መከበር እንዳለበት ገና አልተወሰነም፡፡››                                                      (የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ምክር ቤት) የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ‹‹ኹለተኛው ዙር የኢሬቻ በዓል በዝቋላ ተራራና በአካባቢው ይከበራል›› በሚል በሬዲዮና ቴሌቪዥን ለአስተላለፈው መግለጫ እርምት እንዲያደርግ በክልላዊ መንግሥቱ ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር ከድር …

ለአፈጻጸሙ የወረዳው እና የዞኑ አስተዳደር ባለሥልጣናት ሓላፊነት ወስደዋል ከመጋቢት ፭ ክብረ በዓል በፊት ማስተባበያው እንዲተላለፍ ከስምምነት ተደርሷል ከኹሉም አካላት የተውጣጣ የሽማግሌዎች ኮሚቴ የችግሩን ቆስቋሾች ያጣራል በክብረ በዓሉ ቀን የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል * * * ‹‹ለእኛ ዐዲስ ነገር ነው፤ እዚኽ ቦታ ኢሬቻ የለም፤ በአራት ወይም በስምንት ዓመት አንዴ ዝናም እምቢ እንዳይለን ገዳሙን አስፈቅደን ከምንፈጽመው …

የሄሊኮፕተር እገዛ አልያም የውኃ ቦቴ መኪኖች ድጋፍ እየተጠየቀ ነው በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም፣ ትላንት ጠዋት የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎ አሞራ ገደል በሚባለው አቅጣጫ መዛመቱ ተገለጸ፡፡ በሰሜን በኩል ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው የገዳሙ መውጫ ትላንት ጠዋት 2፡00 የተቀሰቀሰው ቃጠሎ፣ በአዱላላ ወረዳ ሠራተኞችና በነዋሪው ሕዝብ ርብርብ ማምሻውን መጥፋቱ ከተገለጸ በኋላ …

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱን የገዳሙ መነኰሳት እየተናገሩ ነው፡፡ ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው፡፡ ይህ አቅጣጫ፣ የገዳሙ ሞፈር ቤት የሚገኝበት መውጫ መንገድ ሲኾን በአኹኑ ሰዓት በበርካታ ቦታዎች ጭስ እንደሚታይ በመነኰሳቱ ተገልጧል፡፡ የቃጠሎው መንሥኤ በውል …

በጨረታ የተሰጠ የ61 ሚ. ሕንፃ በዲዛይን ክለሳ ስም ያለጨረታ ብር 175 ሚ. ተደርጓል ሢሦ ለማይሞላ ሥራ የተፈጸመው ከብር 25 ሚ. በላይ ክፍያ እንዲመረመር ተጠይቋል ሊቀ ጳጳሱ ያልፈቀዱት የብር 40 ሚልዮን የኪራይ ውል ከንግድ ባንክ ጋራ ተፈጽሟል ከባንኩ የተለቀቀው ብር 14 ሚ. ያህል ገንዘብ በሕገ ወጥ ክፍያ እንዳይባክን ተሰግቷል ያለውድድር በተሠራ ፕላን ከብር 12 ሚ. በላይ …