የዓመቱ ዐቢይ ስኬት – በሕግ ተጠያቂ ስለሚኾኑ አማሳኞች ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለአጥኚ ኮሚቴው አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ!

  • ማስረጃዎች ለሕጋዊ ጥያቄ በሚያመቹበት ኹኔታ በአፋጣኝ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ታዟል
  • በጥምር እና በተናጠል ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በስም ዝርዝር ይለያሉ
  • የቤት እና የመኪና ሽልማት የተሰጣቸው አለቆች እና የስጦታው ምክንያት ተብራርቶ ይቀርባል

 

*          *          *

  • የመሬት፣ የሕንጻ እና የልማት ይዞታዎች የኪራይ ውላቸው ለአንድ ዓመት ብቻ ይኾናል
  • ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ለመዋዋል እንዲቻል የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቋል
  • የቤትና የመኪና ሽልማት ለፓትርያርኩ ቀርቦ በቋሚ ሲኖዶስ ሳይጸድቅ እንዳይፈጸም ተወስኗል

*         *           *

  • ጥናቱ ከመቶ በላይ የገዳማትና የአድባራት የመሬትና የሕንጻ አጠቃቀም ችግሮች ላይ ይቀጥላል
  • አማሳኞች÷ ከስም ማጥፋት፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ያለፈ አካላዊ ጥቃት ለመፈጸም እያቀዱ ነው

    Quwami Synod decision