የስልጤ – ቂልጦ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መቃኞ ቅዳሴ ቤት ነሐሴ 30 ይከናወናል

Silte Kilto Saint Marry ChurchSilte Kilto Tiri

  • ለክብረ በዓሉ እና ጽኑ ኦርቶዶክሳውያንን ለማጽናናት ምእመናን እንዲሳተፉ እየተጠየቀ ነው
  • ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን እና እሑድ ጳጉሜን 1 ቀን ለሚደረገው ጉዞ ምዝገባ እየተካሔደ ነው
  • በክብረ በዓሉ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የመሠረት ድንጋይ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይቀመጣል

*           *          *

  • ከሥራቸው ታግደው በፈጠራ ክሥ የታሰሩት የሰበካ ጉባኤ አባላት ቤተሰቦች ችግር ተባብሷል
  • የወረዳው ፍ/ቤት ለወሰነባቸው ከ6 – 9 ዓመት እስር ይግባኝ ለመጠየቅ ለዓርብ ቀጠሮ ተይዟል
  • ከወራቤ 40 ኪ.ሜ ርቆ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የታሰሩት አባላቱ፣ አጽናኝ ምእመናንን ይሻሉ

*          *          *

  • ተጨማሪ 3 ምእመናት ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ ተከልክለዋል፤ የሥራ ልምድም ተነፍገዋል
  • ነዋሪው፣ ለከት ባጣው የጠባብና የአክራሪ ባለሥልጣናት የማናለብኝነት ድርጊት ግራ ተጋብቷል
  • ጠባብነት እና አክራሪነት በአመራሩ የተለያዩ ደረጃዎች እንደገነገነ ለተገለጸው ጉልሕ ማሳያ ነው